ETHIO-MEREJA® @ethio_mereja Channel on Telegram

ETHIO-MEREJA®

@ethio_mereja


Addisababa, Ethiopia🇪🇹

News & Media Company®
.

USA : Washington

.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot

ETHIO-MEREJA® (English)

Are you looking for the latest news and updates from Addis Ababa, Ethiopia? Look no further than ETHIO-MEREJA®! This Telegram channel is your go-to source for news and media content related to Ethiopia, with a focus on the capital city of Addis Ababa. Stay informed about current events, cultural happenings, and more with updates from this reliable source. Based in the USA, specifically Washington, ETHIO-MEREJA® covers a wide range of topics to keep you informed and engaged. Looking to advertise your business or services? ETHIO-MEREJA® offers advertising opportunities to reach a wide audience. For inquiries about ads or any other information, visit https://telega.io/c/ethio_mereja. Stay connected and up to date with the latest news from Ethiopia by joining ETHIO-MEREJA® today! 🇪🇹

ETHIO-MEREJA®

23 Nov, 19:43


ማንቺስተር ሲቲ በሜዳው በቶተንሃም 4 ለ 0 ተሸነፈ!

በ12ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምሽት 2፡30 ላይ በተደረገ ጨዋታ ማንቺስተር ሲቲ በሜዳውና በደጋፊው ፊት በቶተንሃም ሆትስፐር 4 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

በጨዋታው የቶተንሃም ሆትስፐርን የማሸነፊያ ግቦች ጀምስ ማዲሰን በ 13ኛው እና በ20ኛው ደቂቃ፣ ፔድሮ ፖሮው በ52ኛው ደቂቃ እንዲሁም ቤናን ጆንሰን በ94ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡

ማንቺስተር ሲቲ ይህን ጨዋታ መሸነፉን ተከትሎ በሁሉም ውድድር 5ኛ ተከታታይ ሽንፈቱ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ

ETHIO-MEREJA®

23 Nov, 19:36


🌺Spa Gel Socks

🔰ለእግር ልስላሴ
🔰ለሚሰነጣጠቅ እግር
🔰ድርቀትን የሚያለሰልስ
🔰የሚታጠብ

በቀን ከ20-30 ደቂቃ ብንጠቀመው የእግራችንን ልስላሴ ሙሉ በሙሉ መመለስ ይቻላል


⭕️ዋጋና ተጨማሪ እቃዎችን👇 ለማየት ሊንኩን ይጫኑ!
   🌞 https://t.me/AddisEka1 Join us!
   🌞 https://t.me/AddisEka1 Join us!

አድራሻ፣ መገናኛ ሲሳይ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ 1-010ቁ

ETHIO-MEREJA®

23 Nov, 17:58


“ለማንችስተር ዩናይትድ ትክክለኛው ሰው ነኝ ብየ አስባለሁ”- ሩብን አሞሪም

አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ሩብን አሞሪም ለመጀመርያ ጊዜ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “በኦልድ ትራፎርድ የሚጠብቀኝን ፈተና ብገነዘብም ክለቡን ማሻሻል እና መለወጥ እንደሚቻል አምናለሁ” ብሏል፡፡

በተጨማሪም "ከቡድኑ አስተዳደር ጋር አንድ አይነት ሀሳብ ያለን ይመስለኛል ፤ይህ ደግሞ የቡድኑን አቅም ለመጨመር የሚረዳ ነው” ሲል ተናግሯል፡፡ብዙዎች በተጫዎቹ እምነት እንደሌላቸው ያነሳው አሞሪም በተጨዋቾቹ አቅም እንደሚተማመን እና አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እንደሚፈልግ ለዚህ ደግሞ ትክክለኛው ሰው መሆኑን አስታውቋል። ከአራት አመታት የስፖርቲንግ ሊዝበን ቆይታ በኋላ ዩናይትድን የተቀላቀለው ፖርቹጋላዊ ማንችስተር ዩናይትድን ለዋንጫ ክብር ለማብቃት ጠንክሮ እንደሚሰራም ገልጿል፡፡
 
“ሊጉ በርካታ ጠንካራ ክለቦች የሚሳተፉበት ቢሆንም ጨዋታዎችን ማሸነፍ እንዳለብን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ሊግ ከባድ ስለሆነ ብዙ ጊዜ እንፈልጋለን። በዚህ ሂደት ውስጥም ወደ ዋንጫ አሸናፊነት የምንቀርብ ይሆናል” ነው ያለው፡፡

3-4-3 ወይም 3-4-2-1 በማጥቃት እና በኳስ ቁጥጥር ላይ ላይ የተመሰረተ ጨዋታ የሚከተለው አሞሪም ወጣቶችን በማብቃት እና አቅማቸውን በማጎልበት ልዩ ችሎታ እንዳለው ይነገርለታል፡፡ከ2021 ጀምሮ ስፖርቲንግ ሊዝበንን ተረክቦ ማሰልጠን የጀመረ ሲሆን ቡድኑ አምስት ዋንጫዎችን ሲያነሳ በአማካይ 71.7 በመቶ ወይም ከአስር ጨዋታዎች 7 ጨዋታዎችን የማሸነፍ ምጣኔ ያለው ቡድን መገንባትም ችሏል፡፡

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ

ETHIO-MEREJA®

23 Nov, 16:02


🎁ከአፍሮ ስፖርት ትልልቅ ሽልማቶች ያሉት ቻሌንጅ ይዘንላችሁ መጥተናል!🎁

ለመሳተፍ 2 ቀላል ነገሮችን ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ!

1. በዚህ ቻሌንጅ ለመሳተፍ በመጀመርያ በአፍሮ ስፖርት ወብሲተ ረጂስተር አድርገው ደፖዚት ማድረግ እንዲሁም

2. የአፍሮስፖርት ማህበራዊ ገፆችን ማለትም Facebook , Instagram, Telegram እና Tiktok ገጾች መከተል

ቻሌንጁ ለ 1 ሳምንት ብቻ ስለሚቆይ እንዳያመልጣችሁ!

💸🏆🥇ይሳተፉ ያሸንፉ!💸🏆🥇

Website
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok

ETHIO-MEREJA®

23 Nov, 14:44


#Update

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ ወረዳ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ታውቋል።

አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው።

የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሥራ ሒደት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ዘውዴ በአደጋው እስካሁን የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል ብለዋል።

በተጨማሪም በ40 ሰዎች ላይ ከባድ እና 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ዛሬ ጠዋት 2:30 ላይ በተከሰተው አደጋ የተጎዱ ሰዎች በሰንዳፋ ሆስፒታል ሕክምና እተከታተሉ እንደሚገኙም አመልክተዋል ሲል ፋና መረጃውን አጋርቶ ተመልክተናል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ

ETHIO-MEREJA®

23 Nov, 10:54


አሳዛኝ አደጋ🕯🕯

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተጋጭቶ የበርካቶ ህይወት ማለፉ ተሰምቷል

በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ ደረሰ አደጋው አለልቱ አቅራቢያ ጮሌ ጸበል ጋር የተከሰተ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን በስፍራው ያሉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን እንዲሁም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት መንገዱ ለረጅም ሰዓት መዘጋቱ የተነገረ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደሆስፒታል የማድረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ከአሐዱ ሬዲዮ ዘገባ ሰምተናል።(አሀዱራዲዮ)

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ

ETHIO-MEREJA®

23 Nov, 08:46


የጥንቃቄ መልእክት!

ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለማሰማራት ለየትኛውም አካል ውክልና አልተሰጠም - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል ውክልና አለመስጠቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለሥራ ዜጎችን እንልካለን በማለት የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጿል።

ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ከሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ዜጎች የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ለማግኘት (lmis.gov.et) የተሰኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ጠቁሟል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ

ETHIO-MEREJA®

23 Nov, 08:03


የኢለን መስኩ ኒውራሊንክ በካናዳ አካል ጉዳተኞች ላይ ቺፕ ለመቅበር ፈቃድ ማግኘቱ ተሰማ!

የአሜሪካዊው ቢሊየነር ኢለን መስክ ንብረት የሆነው የባዮ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ኒውራሊንክ ባለፈው ጥር ወር የመጀመሪያውን ችፕስ በሰው አእምሮ ውስጥ መቅበሩ ይታወሳል፡፡

የመስክ ባዮቴክ ኩባንያ የ30 አመት እድሜ ባለው ግለሰብ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ችፕ የገጠመው ባለፈው ጥር ወር ላይ ነበር።ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው ባለፈው ነሀሴ ወር ሁለተኛውን ሙኩራ አሌክስ በሚል ስም ለሚጠራ አካል ጉዳተኛ አዕምሮ ውስጥ መግጠሙን እና ግለሰቡም ለውጥ በማሳየት ላይ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

ኩባንያው በሌላኛዋ የሰሜን አሜሪካ ሀገር ካናዳ አካል ጉዳተኞች ላይ እንዲሞከር ፈቃድ እንዳገኘ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው ከሆነ የካናዳ ጤና ዩንቨርሲቲዎች ማህበር የኒውራሊንኩን ቺፕ የመንቀሳቀስ ችግር ላጋጠማቸው ዜጎች መግጠም የሚያስችለውን ቀዶ ጥገና ህክምና ለማድረግ ዝግጁ ናቸው፡፡

የሳንቲም መጠን ያላትን ቺፕ የሰው ልጅን እንቅስቃሴ ፍላጎት ከሚያዘው የአእምሮ ክፍል ላይ በቀዶ ጥገና እንድትቀመጥ የሚደረግ ነው።ይህቺ ቺፕ የአእምሮን እንቅስቃሴ በመመዝገብና የእንቅስቃሴ ፍላጎትን ወደሚተረጉም ማቀላጠፊያ መተግበሪያ ወይም አፕ ለማስተላለፍ ጥቅም ላይ ትውላለች።

ባሳለፍነው ነሀሴ በቀዶ ጥገና አማካኝነት ቺፕ የተገጠመለት እና በጀርባው ላይ በደረሰበት ጉዳት የእጅ እና እግር መገጣጠሚያ አጥንቶቹን ማንቀሳቀስ አይችልም የተባለው አሌክስ ይህች የኒውራሊንክ ችፕስ ከተገጠመችለት በኋላ በኮምፒውተር ጌም መጫወት ጀምሯል ተብሏል፡፡እንደ ዘገባው ከሆነ ግለሰቡ በተገጠመለት ቺፕ አማካኝነት አልታዘዝ ሲሉ የነበሩት የተወሰኑት ነርቮቹ መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡(አልአይን)

ETHIO-MEREJA®

22 Nov, 18:56


ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተኮሰችው “ኦሬሽኒክ” የተሰኘው ሚሳኤል በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን በ20 ደቂቃ ውስጥ መምታት የሚችል ነው ተባለ

በሰዓት ከ12 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛል የተባለው ይህ አዲስ ሚሳኤል ለመምታት አስቸጋሪ እንደሆነም ተገልጿል ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተኮሰችው “ኦሬሽኒክ” የተሰኘው ሚሳኤል በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን በ20 ደቂቃ ውስጥ መምታት የሚችል ነው ተብሏል።፡

አሜሪካ እና ሌሎች የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎችን መስጠታቸውን ተከትሎ ኪቭ ሞስኮን ከሰሞኑ አጥቅታለች፡፡ ይህን ተከትሎ ሩሲያ “ኦሬሽኒክ” በተሰኘ አዲስ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ዩክሬንን መታለች፡፡

እንደ ሩሲያ መከላከያ መግለጫ ከሆነ ወደ ዩክሬን የተተኮሰው “ኦሬሽኒክ” ሚሳኤል በዲንፒሮ የሚገኘውን የሚሳኤል ማምረቻ እና የጦር መሳሪያ መጋዝንን አጥቅቷል፡፡ የአሜሪካ ጦር በዚህ ሚሳኤል ዙሪያ እንደገለጸው ሚሳኤሉ አዲስ እና አህጉር አቋራጭ፣ የኑክሌር አረር መሸከም የሚችል ነው ብሏል፡፡

ሩሲያ ሚሳኤሉን የተኮሰችው ለሙከራ ጭምር እንደሆነ ያሳወቀው የአሜሪካ ጦር ሚሳኤሉ በቀጣይ የመሻሻል አቅም እንዳለው እና ሞስኮ ይህንን ሚሳኤል በብዛት ሊኖራት እንደሚችልም ገልጿል ሩሲያ ወደ ዩክሬን አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል መተኮሷ የተነገረው የብሪታንያ ጦር በበኩሉ የሩሲያ አዲሱ ሚሳኤል አውሮፓን ኢላማ ለማድረግ ተብሎ የተሰራ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ከደቡባዊ ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተተኮሰው ይህ ሚሳኤል ብሪታንያ ለመድረስ 19 ደቂቃ፣ ጀርመን ለመድረስ 14 እንዲሁም ፖላንድ ለመድረስ 8 ደቂቃዎች በቂ መሆናቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በ40 ደቂቃዎች ውስጥ በአሜሪካ ያሉ ኢላማዎችን መምታት እንደሚችልም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

   T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ

ETHIO-MEREJA®

22 Nov, 16:01


በየቀኑ በርካታ አሸናፊዎችን በሚያስተናግደው የአቪዬተር ጨዋታችን እየተዝናኑ ያሸንፉ!

በአፍሮ ስፖርት ጌሞች ለማሸነፍ ወደ👉 https://bit.ly/3M9qBIw ይሂዱ። 

የ አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
Website

ETHIO-MEREJA®

22 Nov, 14:40


ፑቲን “የዩክሬን ጦርነት ዓለም አቀፋዊ እየሆነ ነው” አሉ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላደሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዩክሬን ጋር የገጠመችው ጦርነት ዓለም አቀፋዊ እየሆነ መምጣቱን አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ቭላደሚር ፑቲን በትናንት ምሽቱ ንግግራቸው፤ አሜሪካ እና ብሪታኒያ ዩክሬን የረጅም ርቀት መሳሪያዎቻቸውን ተጠቅማ ሩሲያን እንድታጠቃ መፍቀዳቸውን ተከትሎ ጦርነቱ ወደ አለም አቀፍ ግጭት እየተሸጋገረ መምጣቱን ተናግረዋል።

ፑቲን በንግግራቸው የአሜሪካ እና የብሪታኒያ ሚሳዔሎች ሩሲያን ለማጥቃት ጥቅም ላይ መዋላቸውን ተከትሎ ሞስኮ አዲስ የመካከለኛ ርቀት ሃይፐርሶኒክ ባለስቲክ ሚሳኤል በዩክሬን ወታደራዊ ተቋም ላይ በመተኮስ የአጸፈ ምላሽ ሰጥታለች ብለዋል።

“ተጨማሪ የአጸፋ እርምዎችም ይከተላሉ” ሲሉ ያስጠነቀቁት ፑቲን፤ ሩሲያ ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ እንደምትሰጥም አስታውቀዋል።ፕሬዝዳንት ፑቲን አክለውም፤ “አሜሪካ በፈረንጆቹ 2019 የተፈረመውን የሚሳዔል ስምምነት በመጣስ ትልቅ ስህተት ሰርታለች” ሲሉም ተናግረዋል።“አሜሪካ የዓለም ሀገራትን ወደ ዓለም አቀፍ ግጭት እየገፋች ነው” ሲሉም ፕሬዝዳንት ፑቲን በንግግራቸው አሳስበዋል።

ዩክሬን ሩሲያን ለማጥቃት የአሜሪካ እና የብሪታኒያ የረጅም ርቀት ሚሳዔሎችን መጠቀሟን ያረጋገጡት ፑቲን፤ የጦር መሳሪያዎቹ በጦር ሜዳ ያለውን ጨዋታ አይቀይሩም፤ ሩሲያ ወታደሮች አሁንም ወደፊት እየገፉ ነው ብለዋል። ፑቲን በንግግራቸው “አሁን ላይ ዩክሬን መሳሪያዎቻቸውን ተጠቅማ በሩሲያ ተቋማት ላይ ጥቃት እንድትፈጽም የፈቀዱ ምእራባውያን ሀገራት ወታራዊ ተቋማት ላይ መሳሪያዎቻችንን ተጠቅመን እርምጃ የመውሰድ መብት እንዳለን እያጤንን ነው” ብለዋል።

     T.me/ethio_mereja
             ኢትዮ-መረጃ

ETHIO-MEREJA®

22 Nov, 11:34


መንግሥት ካርድ የተሰኘዉን የሰብአዊ መብት ድርጅትን ጨምሮ ሌላ አንድ ተቋምን ከስራቸዉ አገደ

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን ዋዜማ አረጋግጣለች። ከታገዱት ድርጅቶች መካከልም “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል” (በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃሉ “CARD” እና “ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” (AHRE) ይገኙበታል።

ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አስታውቋቸዋል። 

ዋዜማ የተመለከተችው ደብዳቤ ለእገዳው የሰጠው ምክንያት “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ማረጋገጥ ተችሏል” የሚል ነው። ዋዜማ የደረሳት መረጃ የታገዱት ድርጅቶች ቁጥር ከሁለት እንደሚበልጥ ቢጠቁምም፣ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻልንም።

ይህ እርምጃ መንግሥት በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በሚሠሩ ድርጅቶች ላይ ሲያደረግ የቆየው ጫና የመጨረሻ ከፍታ ነው ሲሉ ስለጉዳዩ በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። የእግድ እርምጃው በድርጅቶቹ መሪዎች አካባቢ የተጠበቀ እንዳልነበር ለመረዳት ችለናል።

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን መያዶችን የማገድ ስልጣን ቢኖረውም “የአሁኑ እርምጃ በሕጉ የተዘረዘረውን ቅደም ተከተልና ቅድመ ሁኔታ የሚጥስ ነው” ብለዋል ሌላ የሕግ ባለሞያ። ድርጅቶቹ እግዱን በሕግ የመቃወም መብት ይኖራቸዋል። ለባለሥልጣኑ ቅርብ የሆኑ የዋዜማ ምንጮች እገዳው የተላለፈበት ሂደት ለእርሱም ግልጽ እንዳልሆነ ተናግረዋል።(Via-ዋዜማ)

      T.me/ethio_mereja

ETHIO-MEREJA®

22 Nov, 11:33


የጀርመንኛ ቋንቋ ሥልጠና በመራህያን
💡 እንያንዳንዱ ደረጀ በ2ወር ያልቃል
German:
ለ Goethe certificate exam እናዘጋጃቹሃለን

ለመመዝገብ
☎️ 0989747878

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀለዋሉ : @merahyan

ETHIO-MEREJA®

22 Nov, 11:02


🔥 ለአጭር ጊዜ የሚቆይ 30% ቅናሸ ለ10 እድለኞች ብቻ
👉በካሬ 78,000 ጀምሮ
👉50% የባንክ ብድር የተመቻቸለት
👉በ8% ቅድመ ክፍያ
📌ቦታ- ለቡ መብራት ሀይል
📌ለኢንቨስትመንት ቢሉ ለመኖሪያ ምቹ
👉ከሰቲዲዬ እሰከ ባለ 4 መኝታ የተለያዩ የቤት አማራጮች ያሉት

ስቲዲዮ -  56.5 - 57.3 ካሬ
ባለ 1መኝታ  - 69 - 90 ካሬ
ባለ 2 መኘታ -   99 - 150 ካሬ
ባለ  3 መኝታ  - 133 - 181 ካሬ
ባለ 4 መኝታ  - 177.1 - 190 ካሬ
የንግድ ሱቆች - 23 - 175 ካሬ

👉ለበለጠ መረጃ እና ለሳይት ጉብኝት ቀጠሮ ለመያዝ
የሪል እስቴት የሽያጭ አማካሪ
📱 +251911866350
📱 +251923801518