ካሊድ አቅሉ @kalidakelu Channel on Telegram

ካሊድ አቅሉ

@kalidakelu


"ከባባድ ጥያቄዎች በቀላል መልሶች ይረታሉ"
ሀሳብ ለማስፈንጠር.... @kalu30

ካሊድ አቅሉ (Amharic)

ካሊድ አቅሉ የሚለው አማርኛ የቴሌግራም አርቲስት ነው። ሞተረሊስት በመነሻ ያገኘው ከዚህ..."ከባባድ ጥያቄዎች በቀላል መልሶች ይረታሉ" ብለው የሚከናወኑ ጠቃሚ ተናጋሪዎችን ለማንበብ ሲሳተፉ ሀሳብ ለማስፈንጠር፣ ስለቤተሰብዎ በመክፈት ይስጡ። በዚህ አለም ማዕከላዊ መጣጥፋት የሌላ ሰዎችን የማስተዋል የፊልም ወርቅና ምድር ለመጠቀምና ለሌሎች የምግብ ዝግጅቶች እንዲጠቀሙ መረጃ እንዲሆኑ፣ ከባባድ ፕሮፋይል ማለትም ለተከሰተው ዓምዲን ሲህከሞች ወደ ዋልታ ሊገኝ ይችላሉ። በዚህ መንገድ በሚከተለው ሳምን ስልክ ቁጥር @kalu30 ለመላክ በሚፈልጉ ቀላል ሀሳብን እና ዜናውን መረጃ ተለዋዋጭ።

ካሊድ አቅሉ

14 Feb, 18:06


የመክሊቱን ገፅ
( ካሊድ አቅሉ)

ሲሄድ ያየነዉን ያለፈን በመንገድ
ጥላን እያደመቅን አብረን
አንሰደድ ፣
መልክ አለን ሚገለጥ ሚዛኑን
ጠብቆ
ዉበት አይገኝም መሙላት
መንደር ደርቆ
ዳና አለዉ ሁሉም ሰዉ በእግሩ
የተለካ
ሲራመድ ሚደምቅ ሲረግጠዉ
ሚፈካ !
ሁሉም የራስ ላንባ በትንፍሽ
ለኩሶ
መኖሩን ያገኛል ልብ በራፍ ደርሶ
ክንፍ ያለዉ ሁሉ እንደማይበረዉ
ሰከን እንበል የመክሊቱን ገፅ
እንመርምረዉ !

ካሊድ አቅሉ

12 Feb, 18:51


ቡናዋ ላይ ስኳር ትጨምራለች ። እኔም ተመስጭ ቆጥራለዉ አንድ ማንኪያ ሁለት ማንኪያ ሶስት ማንኪያ አራት ማንኪያ እስከ ስድስት ቀጠለች ። ምን ቢሆን ነዉ “ይሄን ያህል ስኳር ምትጠጣዉ ሬት ነዉ እንዴ” እላለዉ በዉስጤ ወይንም ህይወት ውስጥ የመረራት ብዙ ነገር አለ ግን እኮ መጣፈጥም ሲበዛ ይመር የለ “ ሳታማሲይዉ ጠጪዉ “ አልኳት አንድ አፌን ደንግጥ ብላ “ለምን?” ስትል “ ማለቴ እንዳይመርሽ ስኳር ስላበዛሽበት ማለቴ ነዉ”አልኳትና መሬት መሬት አየዉ ። “እእእሺ “አለች ግራ ስትጋባ ይበልጥ ታምራለች ገረፍ አርጋ አየቺኝ ጠይም ሴት ለማማር ቁጥብ መሆን ይበቃታል ደግሞ ለስለስ አርጎ ሚገባ ዉበት አወጣጡ እንዳገባብ አይደለም ልብ ላይ ይቀራል ።

ምሽቴን በስዋ ገፅ ስለጀመርኩ እድለኝነት ተሰማኝ ከካፌው ለስለስ ያለ ሙዚቃ በስሱ ወዳለንበት ይመጣል ሙሉቀን መለሰ ነዉ ፦

“አይኔማ ወዳጄ ያላንቺ አላይ አለ
ጥርሴማ ወዳጄ ያላንቺ አልስቅ
አለ
ሆዴ ነዉ ጠላቴ እህል በልቶ
ያደረ”

የኔ ጠላት ምን ነበር?ምን አልባት እግሬ ያለችበት አምጥቶ ታምር ያሸከመኝ ወይንስ ባለዉለታዪ ጥያቄዉ ለአፈታት ጊዜ ይፈልጋል ግን ልጅትዋ ከማማር በላይ ታምራለች !

(ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

11 Feb, 18:57


‘ በህይወታችን ጉዞ ስንት የመዝጊያ በር ተገጥሞ ይጠብቀን ይሆን ? መዝጊያነቱንስ እናዉቅ ይሆን እያንዳንዱ መዝጊያ መድረሻ እየመሰለን የስንቶቻችን ልጅነት እንደ እናቶቻችን ፍላጎት ሳይሆን ባክኖ ቀርቶ ይሆን ? ‘

አለማወቅ
( ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ)

ካሊድ አቅሉ

08 Feb, 19:58


‘You character define nature beauty🥰

( @Kalidakelu)

ካሊድ አቅሉ

06 Feb, 18:36


“ ቁስሎች በቁስል ይጠፋሉ እንዴ ቂም በቂም ይጠፋል እንዴ ያነሰን ፍቅር ነዉ ። እኔም ያነሰኝ ፍቅር ነበር ጥቂት ሰዉ መሆን ነዉ ያነሰን ወንዝ አይደለም ። ለተከፋይ የምናረግፈዉ አንድ የእንባ ጠብታ ነዉ እሱም ዉድ አይደለም ሁሉ በየሀይማኖቱ ይመርቃል ብዙ የተማርኩ ባልሆንም አይቻለዉ ። ቁጭ ብዪ ቂጤ እስኪያብጥ ሰዉ ሲያሴር ሲተበትብ ሲያፈቅር አይቻለዉ ሰምቻለዉ ። በብዛት ካሉ ጥሩ መስመሮች ለምን እግሮቻችን ሞላጫላጫዉን ጎዳና እንደሚመርጡ አላዉቅም የአይምሮ ብስለት ነዉ እንዳልል ናና ከረሜላ ለልጆቻችን እንኳን አልሰራንም።”


ግራጫ ቃጭሎች
(አዳም ረታ)

ካሊድ አቅሉ

02 Feb, 11:55


Sunday

ፕሌቶ ፦ የበደሉህን ትጠላለህን ?


ሶቅራጥስ ፦ በጭራሽ ! ጥላቻ በራሴ
ላይ የምጥለዉ ቅጣቴ ነዉ ።

ካሊድ አቅሉ

31 Jan, 18:33


ብዙ ግዜ ንግግር ቦታ ‘መሆን’ ያዳግታል እስኪ አስተውሉ “ሽንት መሽናት ክልክል ነዉ ! “ በሚል ትልቅ ፅሁፍ ያለበት ቦታ ነዉ የሽንት ሽታዉ አላሳልፍ ሚላቹ ።


( ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

30 Jan, 18:24


“ፈጣሪ አብዝቶ ይወደኛል “

“እንዴት አወቅክ ?”

“የጠየቅኩትን ሁሉ አይሰጠኝም ! “

(ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

26 Jan, 18:45


“ ስሩ ከተስማማዉ ቅርንጫፉ ከማማር ዉጪ ምርጫ አይኖረዉም ። “

“ምክንያት ?”

“ እናት ዉበትዋን ምትገልፀዉ ልጆችዋ መልክ ላይ ስለሆነ ! “

(ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

24 Jan, 18:19


ባይራ ዲጂታል መጽሔት


ልዩ ዕትም



በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ

ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ካሊድ አቅሉ

24 Jan, 08:19


ጁመአ

‘ በዓለም ላይ ያለኝ አንድ ወዳጅ ,,, ልብስ ሰፊ ብቻ ነዉ

ምነዉ ቢባል ~ በዛሬዉ እንጂ በትናንት አይለካኝም !

Credit : Hal Bey

ካሊድ አቅሉ

19 Jan, 12:40


‘ ሀብታም ሲታመም ደሃዉ እየተመላለሰ ስለ ጤንነቱ ይጠይቀዋል ይሻለዉ ዘንድም መልካም ምኞቱን ይገልፅለታል , ደሃዉ ሲታመም ደግሞ እስኪሻለዉ ይጠብቅና ሀብታሙ ጋር ሄዶ አሞት እንደነበር እየተናነሰ ይነግረዋል ።
( መራር ሐቅ …. ኧረ እየተጠያየቅን )
Chinwa achebe

Credit : seido jimma SH

ካሊድ አቅሉ

16 Jan, 18:04


መሳቅ ይቻላል ?
( ካሊድ አቅሉ)

መሳቅ ይቻላል ? ብዪ ልጠይቅ
ግዛቱ የእሷ ነዉ ብርሃን የሆነዉ
ስትፍለቀለቅ ፣
አንቺ በራድ ሴት
አንቺ ውብ ጠይም
ስርሽ ከርሜ ቀኔን ሳስታምም ፣
አገኘዉ መኖር
ቀለለኝ ምድር

ምን መታደል ነዉ ?
በሳቅ ቅላፄ በድን ማስነሳት
እንዴትስ ቻልሽዉ ?
በትንፉሽ መስመር መሳል
ንቅሳት !

እራስን መርሳት
“የት ነዉ ያለሁት “
ዋና ጥያቄ
ሆኖ ይመጣል ኮቴ ሳጠና
አንቺን ናፍቄ ፣
በአል ማስጌጫ የሳሎኑ ፈርጥ
ብኩን ህይወቴ ተራማጅን ሰዉ
ስታበላልጥ ፣

ልብሽ ነዉ ልኬት
እሷን ምትመስል ሚባለዉ
ሁሉ ፀሐይ ጨረቃ
ሌላዉን ተይው መሽቶ ለመንጋት
መኖርሽ በቃ !
ሰለቸዉ አትበይ
አዎ አብዝቻለዉ
አንዱን ጥያቄ
መሳቅ ይቻላል ? ምድር በገባዉ
ስርሽ ፈንድቄ ።

ካሊድ አቅሉ

13 Jan, 18:29


ስንት አይነት ችኩል ሰዉ አለ!
መሮጥ መንደርደሩን በቀር
መድረሻዉን ያልታደለ ፤
( ጋሽ ነብይ መኮንን)

“ የግልብጥ እሩጫ”
ከስውር ስፌት 2 ላይ የተወሰደ ።

ካሊድ አቅሉ

06 Jan, 18:08


“ አንዳንድ አዋቂ ነን ባዮች ምን እንደሚያዉቁ ባላዉቅም ግን የሰዉ መዝናኛ ማረፍያ እያበላሹ አሪፍ ነን በስለናል ለማለት ሲሞክሩና ሲሆንላቸዉ አይቻለዉ። “


ግራጫ ቃጭሎች
( አዳም ረታ)

ካሊድ አቅሉ

02 Jan, 17:59


“ ላንተማ ሁሉን ነገሬን ሰጣለዉ “ ስትለዉ ወንድየዉ ቀበል አርጎ “ኩላሊትሽንም ቢሆን ? “ ሲላት ምን ብትል ጥሩ ነዉ “እሱንማ ወንድ ነዉ ሚሰጠዉ”😁

ካሊድ አቅሉ

29 Dec, 18:15


ቀድመህ ምትማረክ
(ካሊድ አቅሉ)

አንተማ
ከጅቦች መንጋጋ ፤ ደርሰህ ያተረፍከኝ
ሺዎች ሲገፉኝ ፤ ብቻህን ያቀፍከኝ

የመንገዴ ቀዳሽ ፤ የመብሰል ተምሳሌት
እቺ ብኩን አለም፤ ስትመረኝ እንደ እሬት
አንተን ነው ማስበው ፅልመቱን ለመግፈፍ
ድምፅህ ይበቃኛል ሕይወቴን ለማትረፍ!

ሲያመኝ የምትከሳ ቀኔን ለማሳመር
ቀንህን ያከሰምክ
አንተ እኮ ነህ አባ መኖር ሊሰዋኝ ሲል
ቀድመህ ምትማረክ !
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ካሊድ አቅሉ

27 Dec, 18:36


ያልጠገበ ሁሉ “የተራበ” አይደለም !


(ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

26 Dec, 18:37


ታድለዋል አትበይ
(ካሊድ አቅሉ)


“አንተንማ ያገኘች የታደለች ናት”
ምናምን እያልሽ በቃል
አትሸንግዪ
እስኪ አንዴ መተሽ ካንቺ ቡሃላ
ያሉትን አንዴ ቆመሽ እዪ ፣


ትዝታ መልሶኝ የያዝኩትን ሁሉ
በስምሽ ስጠራ
ፍቅር ሲለግሱኝ ማጣጣም
ተስኖኝ በትናንት ስበራ

መች ታደሉ እነሱ !
ቃርዳ ቀርቶላቸዉ የክት የተቀሙ
ታድለዋል አትበይ እኔን ያዩበትን
ቀን እየረገሙ ።

ካሊድ አቅሉ

21 Dec, 18:25


ስሙኝማ የሰሞኑን ብርድ እንዴት ይዞዋችዋል? በየቤታችን ሆነን እንደዚህ ያረገን በየጎዳናዉ ላይ ላሉ እህት ወንድሞቻችን አስበን እናውቃለን ? ቁም ሳጥን ያጣበበ ፊሽን አለፈበት ብለን በየቦታዉ የጣልነዉ ጨርቅ የስንቱን ገላ ከብርድ ይከላከላል በምስሉ ላይ በተመለከቱት አድራሻ ወይንም በዚህ ቴሌግራም 0984802544 አድራሻ አውረን ያሉበት መጥተን እንወስዳለን ።

ካሊድ አቅሉ

20 Dec, 18:56


ስሙኝማ የሰሞኑን ብርድ እንዴት ይዞዋችዋል? በየቤታችን ሆነን እንደዚህ ያረገን በየጎዳናዉ ላይ ላሉ እህት ወንድሞቻችን አስበን እናውቃለን ? ቁም ሳጥን ያጣበበ ፊሽን አለፈበት ብለን በየቦታዉ የጣልነዉ ጨርቅ የስንቱን ገላ ከብርድ ይከላከላል በምስሉ ላይ በተመለከቱት አድራሻ ወይንም በዚህ ቴሌግራም 0984802544 አድራሻ አውረን ያሉበት መጥተን እንወስዳለን ።

ካሊድ አቅሉ

18 Dec, 18:58


እኛ ሀገር እኮ “ሙስናን በጋራ እንከላከል!” የሚል የቲቪ ማስታወቂያ ለመስራት ተዋናዮች በዘመድ ነዉ ሚመረጡት😂😂😂 እናሳዝናለን ብዙ ነገር ከምንጩ ነዉ ሚደርቅብን

ካሊድ አቅሉ

17 Dec, 17:34


አደገኛ አጥር
( ናትናኤል ግርማቸዉ)
****

የእሾህ አክሊል አጥራቸዉ
ቅልብ ዉሾች ከግቢያቸዉ
ይህም ደሞ ሳያንሳቸዉ
ዘብ አቆሙ ከበራቸዉ
ግና …
እንኳን ጌቶች ሊዘረፉ
ሌቦች ሀብትን ተጠየፉ።

ካሊድ አቅሉ

14 Dec, 18:56


Live stream finished (1 hour)

ካሊድ አቅሉ

14 Dec, 17:44


ጀምረናል ገባ ገባ በሉ

ካሊድ አቅሉ

14 Dec, 17:43


Live stream started

ካሊድ አቅሉ

14 Dec, 17:40


Live stream started

ካሊድ አቅሉ

13 Dec, 18:22


የሀሳብ ምሽት ፕሮግራማችን ነገ ይመለሳል ! ነገ 2:30 ላይ በሰርግ ባህላችን ላይ ዉይይት እናደርጋለን በሰአታችን ተገኝተን አለን ምንለዉን ሀሳብ እናሻግር ።

ካሊድ አቅሉ

10 Dec, 17:45


ሁለት መስመር ግብህ
(ካሊድ አቅሉ)

በመሰንበት አትመዝነው የህይወትን
ጥዑም ለዛ
ለጭረቱ መጨነቅ ነው ሙሉ ስዕሉን
የሚገዛ

ከተፃፉት በላይ አሻራ ለመክተብ
ማጤን እኮ ያሻል የሰሩትን ማንበብ

በገፆች ብዛት አይለካም ገድል
ሁለት መስመር ግብህ ልትሆን ትችላለች
ጥራዙን የምትጥል !!

ካሊድ አቅሉ

06 Dec, 13:38


ባይራ ዲጂታል መጽሔት


ቅጽ 1 ቁጥር 10



በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ

ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ካሊድ አቅሉ

02 Dec, 19:12


“ሰዉን ፈራሁ!” ብሎ ጮኸ።

ተድባብ - ገጽ 204
በሕይወት ተፈራ

እወነትም ከባለሁለት እግር በላይ አስጊ ምድር ብትታሰስ የሚገኝ አይመስለኝም።

ካሊድ አቅሉ

27 Nov, 18:09


በህይወት ተሰላችቶ
ሰዉ ቢሰብር ቀልቡን
ልብ ተስፈኛ ነው
ተንበርክኮ ያሳያል
የመሮጥ አቅሙን !


(ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

21 Nov, 18:06


ስቀሺልኝ ልብሽ በራፍ ስኮላተፍ
ልክ አይደለሽ ፍፁማዊት ጎንሽ
ሆኜ እንዴት ልረፍ ?

ወጀብ ናት ምታንቀሳቅስ
አሳስቃ ልብ ላይ ምትፈስ
እንዴት ብዪ ልሸንግላት
እንዴት ብዪ ላወዳድራት
ከጎደለ የምድር ሰዉ
መሬቱማ ትንፋሽ አልባ
የእሷን መኖር ስቀንሰዉ !


(ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

19 Nov, 15:50


የመንገዴ መንገድ ❤️❤️❤️
መልካም እድል ወንድም አለም
ይነበብ !!!

ካሊድ አቅሉ

17 Nov, 14:40


Sun day

. . . Slow down !

ካሊድ አቅሉ

16 Nov, 19:00


አንዳንድ ሰው በበጋ ሙቀት ተታሎ የሸለማቹን ጃኬት ክረምት ሲመጣ ባለፎ ያረከውን ጃኬቴን ስጠኝ ይላችዋል ! ከልብ ያልመነጨ ደግነት ወቅቶች አብዝተዉ ይፈትኑታል ።

(ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

14 Nov, 19:14


ተይ ድንጋይ አይቅናሽ ወራጅ
ላይ መወርወር
ገፅሽ ይበላሻል መልክሽን ላየዉ
ነዉ ወንዝ ፊት ምገተር !


(ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

12 Nov, 18:34


እስቴቨን ሀዉኪንግ ( የፊዚክስ ሊቅ) ለልጆቹ የእድሜዉ መጨረሻዉ ላይ እነዚህን ምክሮች አስተላልፍዋል ፦

1) ወደ ታች ወደ እግራቹ ሳይሆን ወደ ላይ ወደ ከዋክብት ማየት አትርሱ ።

2) በምንም ምክንያት ከስራ አትቦዝኑ ስራ ትርጉምና ምክንያት ይሰጣቹሃል ፣ ህይወት ያለ ስራ ባዶ ናት ።


3) ለመወደድ እድል ያላችሁ ከሆናች ብዙ ጊዜ ማይገኝ መሆኑን አስታውሳቹ አክብራቹ ያዙት ።

ካሊድ አቅሉ

08 Nov, 05:17


Jumea

“ባለህ ተደስተህ ልትኖር ባለመቻልህ ልታፍር ይገባሃል !”

‘ ዴል ካርኔጌ ‘

‘ You should be ashamed of not being able to live happily with what you have !

ካሊድ አቅሉ

02 Nov, 18:55


ክፉ መሀል ያረከሰኝ
( ካሊድ አቅሉ)

ሳል ስጀምር ማቃሰቴ ሲደራረብ
በእርቃኔ ነዉ አንቺን ላለብስ
ምረባረብ ።

ገላ ከብዶኝ ስጋ ባዳዉ የሩቅ
ዘመድ
አወዳደቅ ላቀና ነው ቦታ ይዥ
ምንገዳገድ ፤

የተሳልኩት ፈሩን ባይዝ
አልከፋም በለገሰኝ
መድሃኒቴን ሊያሳይ ነው
ክፋ መሀል ያረከሰኝ !

ካሊድ አቅሉ

01 Nov, 06:59


JUMEA

አዛዉንቶችን አክብሩ , ዘመናቸዉ ባልሆነ ዘመን ውስጥ እየኖሩ ነዉና
ሸ. ተብሪዝ


Respect the elders, for they are living in a time that is not their own
Shams Tabriz

Credit : seido jimma

ካሊድ አቅሉ

29 Oct, 18:32


“ አንዳንዴ ክፉ ዕጣችን የራሳችን ፍርሃት ይመስለኛል።”

ኩርፊያ የሸፈነዉ ፈገግታ
( ከስዩም ወልዴ ራምሴ)

ፎቶ ምንጭ ፡ Adiss Book Club

ካሊድ አቅሉ

25 Oct, 03:53


JUMEA
(ደስታ ልክ እንደ መልካም ሽቶ ነዉ ለሌሎች ሲያርከፈክፉት ለራስም ይተርፋል)

ገንዘብ እንደ ፍቅር ነዉ ንፉጉን ሰዉ ቀስ እያለ አሰቃይቶ ይገለዋል ከሌሎች ጋር ተካፍሎ የሚበላዉን ደግ ሰዉ ብሩህ ሕይወትን ያጎናፅፈዋል , ለአቅመ ደካሞች ባካፈላችሁ ቁጥር የድሆች ደስታ ወደናንተ ሲነፍስ ታዩታላችሁና ከማካፈል አትዘንጉ , ደስታ ልክ እንደ መልካም ሽቶ ነዉ ለሌሎች ሲያርከፈክፋት ለራስም ይተርፋልና ,
ምድር ላይ ምነዉ በኖረኝና ተካፍዬ በበላሁ ብለዉ በቁጭት የሚንገበገቡ ብዙ ፍጡሮች አሉ , አንተስ ታካፍል ዘንድ ዕድሉን የሰጠህ . . . .

K.JIBRAN
Credit : Seido Jima SH

ካሊድ አቅሉ

23 Oct, 19:30


በምን ብፀድቅ ነዉ?
( ካሊድ አቅሉ)


የሳምሺኝ ቦታ ላይ ይሄዉ
ሳልታጠብ ዘመናት ነጎዱ
እንዲያዉ ባይገርምሽ ሰዉነት
ቀለሜ በኑሮ ተጎዱ ፣

ፊቴ ጭምደድ ለስለስ
ሰዉነቴም ፍርስ

ሁሉም በየግብሩ ለእርጅና
ተሰዋ ቦታውን ለቀቀ
የሳምሺኝ ጉንጭ ግን እርጅና
ሲመጣ ይባሱን ደመቀ

ቦታዉን ዳብሼ ሁሌ ምገዋለዉ
በእስተርጅና እድሜዪ
በምን ብፀድቅ ነዉ ገነት የገባሁት ፃድቃንን ቀድሜ

ካሊድ አቅሉ

22 Oct, 18:07


“ ዕድለኞች ሁሉ ተመሳሳይ ናቸዉ፣ ዕድለቢሶች ግን በየግላቸዉ የተለያዩ ናቸዉ። “


( አና ከረኒና)

ካሊድ አቅሉ

19 Oct, 19:21


Live stream finished (1 hour)

ካሊድ አቅሉ

19 Oct, 17:48


https://t.me/KALIDakelu?livestream=c1fd90f9ece0a11ae0

ካሊድ አቅሉ

19 Oct, 17:43


ጀምረናል ገባ ገባ በሉ

ካሊድ አቅሉ

19 Oct, 17:43


Live stream started

ካሊድ አቅሉ

19 Oct, 07:02


ለእናንተ አመቺ እንዲሆን በማሰብ “የሀሳብ ምሽት” ፕሮግራማችን ወደ ቅዳሜ ተመልስዋል ዛሬ ከ 2:30 እስከ 3፡30 ስለ ‘መተማመን’ እናወጋለን በሰአቱ በመገኘት ሀሳቦቻቹን አሻግሩ ።

ካሊድ አቅሉ

13 Oct, 19:35


Live stream finished (1 hour)

ካሊድ አቅሉ

13 Oct, 18:17


https://t.me/KALIDakelu?livestream=d7e06f2ad92f1f60b8

ካሊድ አቅሉ

13 Oct, 18:17


Live stream started

ካሊድ አቅሉ

13 Oct, 18:17


Live stream finished (41 seconds)

ካሊድ አቅሉ

13 Oct, 18:16


Live stream started

ካሊድ አቅሉ

13 Oct, 18:16


ጀምረናል ገባ ገባ በሉ

ካሊድ አቅሉ

11 Oct, 18:54


በዚህ ሳምንት እሁድ ምሽት ከ 2፡30 እስከ 4:00 በሚኖረን “የሀሳብ ምሽት“ ፕሮግራም ስለ ቡድን አስተሳሰብ ( Group thinking) እንወያያለን ለሁሉም ክፍት በሆነዉ መድረክ በቀጥታ ስርጭት ሀሳባቹን ማስተላለፍ ትችላላቹ ከልዩ እንግዳ ጋር እንጠብቃቹሃለን ።

ማስታወሻ ፡ ( አናርፍድ!)

ካሊድ አቅሉ

11 Oct, 14:14


እነሆ!

ባይራ ዲጂታል መጽሔት

ባይራ ቅጽ 1 ቁጥር 9

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ

ኢ-ሜይል- [email protected]


ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ካሊድ አቅሉ

09 Oct, 18:46


እኩል ነሽ ይሉሻል አንቺን አሳንሰው
ከመቻልሽ ፀጋ ፆታሽን ቀንሰው
አታውቅም ይላሉ አለማወቃቸው ከፊት እየታየ
የመቻልን አቅም የመድረስን ነጥብ በድፍን እያየ ፤

ሄዋን ልክ እንደ አዳም ጉድለት የታደለች
በምክክር ውጤት እኩል እጅ አንስታ ቅጠል
                                                  የበጠሰች ።

ታድያ በየት በኩል በምንስ አፈታት
አለች ለመባል መተንፈስ ሚበቃት !


( ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

08 Oct, 18:39


እያንዳንዱ ልማድ በግዜ ዑደት ላይ ብዙ ውጤቶችን የሚያመጣ ነው። እንዳለመታደል ሆኖ ደግሞ እነዚህ ውጤቶች በትክክለኛው ጥምረት አናገኛቸውም። መጥፎ ልማዶች ወዲያውኑ የሚመጣው ውጤታቸው ደስ የሚል ሲሆን የመጨረሻውና ዋናው ውጤታቸው ግን መጥፎ ነው። የጥሩ ልማዶች ነገር ደግሞ በተቃራኒው ነው። ጥሩ ልማዶችን ስታደርግ ወዲያው የሚመጣው ውጤት ደስ አይልም ፤ ጣፋጩና አስደሳቹ ፤ እውነተኛው ውጤታቸው የሚመጣው ደግሞ ዘግይቶ ነው።

የፈረንሳያዊው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ፍሬድሪክ ባስቲያት ይህንን ነገር እንዲህ ብሎ አብራርቶታል። " ሁልግዜ ቶሎ የሚመጡ ውጤቶች ደስ የሚሉ ከሆኑ ፣ ዘግይተው የሚመጡት ውጤቶች መጥፎ ይሆናሉ። በተቃራኒውም እንደዚያው ነው። ብዙውን ጊዜ ደግሞ የአንድ ልማድ የመጀመሪያው ፍሬ ጣፋጭ ከሆነ ከዚያ ቡሃላ ዘግይተው የሚመጡት ፍሬዎች መራር ይሆናሉ።"

በሌላ አባባል የጥሩ ልማዶችህ ዋጋ ዛሬ ላይ ናቸው። የመጥፎ ልማዶችህ ዋጋ ግን ወደፊትህ ላይ ናቸው።
________

Atomic Habits ( የልማድ ሐይል )
በጀምስ ክሊር
ትርጉም : ድረስ ጋሻነህ

ካሊድ አቅሉ

06 Oct, 20:17


Live stream finished (2 hours)

ካሊድ አቅሉ

06 Oct, 18:34


https://t.me/KALIDakelu?livestream=61e7b8f70608fa964f

ካሊድ አቅሉ

06 Oct, 18:16


ገባ ገባ በሉ ጀምረናል

ካሊድ አቅሉ

06 Oct, 18:13


Live stream started

ካሊድ አቅሉ

06 Oct, 18:12


ካሊድ አቅሉ pinned «በምርጫቹ መሰረት “ ደግነት እስከ ምን ድረስ” በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነገ ምሽት 3 ሰአት በቀጥታ ስርጭት ወይይት እናረጋለን ክፍት መድረክ ስለሆነ ሁላችሁም መሳተፍ ትችላላችሁ። በተጨማሪም ካነሳነዉ ርዕሰ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ ግጥም እና ወጎችን በቀጥታ ማቅረብ ትችላላችሁ ።»

ካሊድ አቅሉ

05 Oct, 18:28


በምርጫቹ መሰረት “ ደግነት እስከ ምን ድረስ” በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነገ ምሽት 3 ሰአት በቀጥታ ስርጭት ወይይት እናረጋለን ክፍት መድረክ ስለሆነ ሁላችሁም መሳተፍ ትችላላችሁ። በተጨማሪም ካነሳነዉ ርዕሰ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ ግጥም እና ወጎችን በቀጥታ ማቅረብ ትችላላችሁ ።

ካሊድ አቅሉ

04 Oct, 18:52


ላጎርሳት እጄን አስጠጋዉ “ብላ ለራስህ በእጄ በላለዉ!“ አለችኝ በሚገፉ ድምፅ የድምፅዋ ቅላፄ ውስጥ ሶስት ነገሮችን ሰማዉ
1. ሌላ ለምጃዉ
2. መቼ ነዉ ምላቀቅህ
3. ይሄ ምኑ ሞኘ አፍቃሪ ነዉ። የሚሉ ትቢት የጋረዳቸዉ የሞኝ ድምዳሜዎች።

አላጎረስከኝም ብላ ምታኮርፍ ልጅ ሳጎርሳት መበሳጨት መጀመርዋ አስደነቀኝ ። ለካስ ፈልገዉ የመጡበት ነገር አንድ ቀን እንዳይመጣብን ምንደበቅበት ቅፅበት ይመጣል። አሁን እኔና እሷ እዛች ቀጭን ግን የከረረች ቅፅበት ላይ ነን ልትበጥሰዉ ስትታገል ለቅቄዉ እንዲተርፍ እየተጣጣርኩ ነው። ከምታሳየኝ ፉንጋ ማንነት የሚስብ የደስ ደስ እየፈለኩ


( ካሊድ አቅሉ)

ካሊድ አቅሉ

02 Oct, 18:01


- You smile in the dark then ready to see every thing.


(Kalidakelu)