በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢኒስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር የተመራው የጤና ሚኒስትር ደጋፋዊ ክትትል ቡድን ከማዕከላዊ ኢት/ያ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በክልሉ የወባ በሽታ መከላከልና የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ክትትል ቡድን ከማዕከላዊ ኢት/ያ ክልል ኃላፊዎች የማናጅመንት አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሁሉም የጤና አጠባበቅ እና የወባ ወረርሽኝ መከላከል ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የወባ ወረርሽኝን ከመከላከል ከመቆጣጠር አኳያ በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን በመጠቆም ከዚሁ ስራ በተያያዘ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች, የፌደራል ባለድርሻ ተቋማት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አስከታችኛው መዋቅር ያሉ የተለያዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አመራር አካላትና የጤናው ሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ማህበረሰቡ ያደረጉት ድጋፍና ክትትል ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል ብሎም ለመግታት በክልሉ የሚገኙ ጤና ተቋማት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
በጤና ሚኒስቴር የአርማወር ሀንሰን ኢኒስቲትዩት የተመራው የድጋፋዊ ክትትል ቡድን የህብረተሰቡን ጤና የማስጠበቅ ጉዳይ ለጤና ቢሮ ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻን ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን አስረድተው በክልሉ እየተደረገ ያለው ስራ በጥሩነት አንስተዋል፡፡
የድጋፋዊ ክትትል ቡድኑ በክልሉ ውስጥ በተለያዩ የክልሉ መዋቅሮች በቀጣይ ለተከታታይ ሳምንት በዞን በልዩ ወረዳዎች በጤና ተቋማት እና ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ የድጋፍ ክትትል ስራውን ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል።
የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ