Dr. Eyob Mamo @dreyob Channel on Telegram

Dr. Eyob Mamo

@dreyob

Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo (English)

Are you looking to improve your life skills and reach your full potential? Look no further than the Dr. Eyob Mamo Telegram channel! With a focus on life skill development, this channel provides valuable insights and tips on how to enhance various aspects of your life. Whether you want to improve your communication skills, boost your confidence, or learn how to manage your time more effectively, Dr. Eyob Mamo is here to help you succeed.
Who is Dr. Eyob Mamo? Dr. Mamo is a renowned expert in personal development and has helped countless individuals achieve their goals and live more fulfilling lives. What is the channel about? The Dr. Eyob Mamo channel is dedicated to providing practical advice and strategies for personal growth and self-improvement. With regular updates and engaging content, you'll find inspiration and motivation to become the best version of yourself. Join the Dr. Eyob Mamo Telegram channel today and start your journey towards becoming a better you! You can contact Dr. Mamo directly through the channel @DrEyobmamo for personalized guidance and support. Don't wait, unlock your full potential with Dr. Eyob Mamo!

Dr. Eyob Mamo

21 Feb, 16:15

ነጻ የስሜት ብልህነት ስልጠና!
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በሕይወታችን ከ80 በመቶው በላይ ስኬታማነታችንን የሚይዘው የአእምሮ ብልህነት (IQ - Intelligence Quotient) ሳይሆን የስሜት ብልህነታችን (EQ - Emotional Quotient) ነው፡፡

ይህ ማለት በስራው አለምም ሆነ በማሕበራዊው ስምሪታችን ብዙ እውቀት እያላቸው የስሜት ብልህነት ከጎደላቸው ሰዎች ይልቅ አናሳ እውቀት ይዘው ከፍተኛ የስሜት ብልህነት ያላቸው ሰዎች ልቀው ይገኛሉ፡፡

በዚህ እውነታ ላይ መሰረታዊውን ግንዛቤ እንድትጨብጡ የአንድ ምሽት ስልጠናን አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

ለዚህ የቴሌግራም ግሩፕ ተከታታዮቼ በሙሉ፡፡

ቀን - ኃሙስ የካቲት 20

ሰዓት - ማታ ከ2፡30 – 3፡30

የስልጠናው ርእስ - የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence)

ክፍያ - በነጻ!!!

ወዳጆቻችሁም ይህንን telegram channel join በማድረግ እንዲከታተሉ ጋብዟቸው፡፡

በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዚሁ ቻናል በመግባት ስልጠናውን live መከታተል ትችላላችሁ!

Dr. Eyob Mamo

21 Feb, 08:17

https://youtu.be/9jzLlmjWIVY

Dr. Eyob Mamo

21 Feb, 02:00

የአፋልጉኝ ጩኸት!

የበፊቱ “እኔ” ስለጠፋብኝና ስለናፈቀኝ አፋልጉኝ!

• ደስተኛና ተጫዋች የነበረው “እኔ”!

• ብሩህና የሚገባው የነበረው “እኔ”!

• ፈገግተኛና ሳቂታ የነበረው “እኔ”!

• ሰዎችን ያምንና ይቀበል የነበረው “እኔ”!

• ያፈቅርና ይፈቀር የነበረው “እኔ”!

• በሰላም ይተኛና ይነሳ የነበረው “እኔ”!

• ለነገ ይጓጓና ዓላማ-መር የነበረው “እኔ”!

• ላመነበት እውነት ቆራጥና ጽኑ የነበረው “እኔ”!

• ልኩንና ሚዛኑን ያውቅ የነበረው “እኔ”!

• ራሱን ተቀብሎና ሆኖ ይኖር የነበረው እኔ!

ቀድሞ የነበረው አሁን ግን የጠፋብኝና እዚህ የሌለው ትክክለኛው እኔነቴ ናፈቀኝ!

• ሰውን ሁሉ በማስደሰት ለመኖር ስሯሯጥ የጠፋብኝ ማንነቴ!

• አንድ ሰው ስለተለየኝ ብቻ ኑሮ ያከተመለት ያህል በማሰብ የጠፋብኝ ማንነቴ!

• ስኬትን ፍለጋ ይህንና ያንን ስሞክር የጠፋብኝ ማንነቴ!

• የሰውን ሁሉ ሃሳብ ሳስተናግድ አንድም ቀን ራሴን ሳላዳምጥ የጠፋብኝ ማንነቴ!

• አብዛኛውን ጊዜዬን በአካል እንኳን ማንነታቸው ከማላውቃቸው ሰዎች ጋር በማሕበራዊ ሚዲያ ሳሳልፍ የጠፋብኝ ማንነቴ!

• ማንነቴን ወደመኖር ካመጣው ከፈጣሪዬ ጋር ያለኝን ግንኙነት ችላ በማለቴ የጠፋብኝ ማንነቴ!

ይመለስ!!!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

20 Feb, 14:05

ነጻ የስሜት ብልህነት ስልጠና!
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በሕይወታችን ከ80 በመቶው በላይ ስኬታማነታችንን የሚይዘው የአእምሮ ብልህነት (IQ - Intelligence Quotient) ሳይሆን የስሜት ብልህነታችን (EQ - Emotional Quotient) ነው፡፡

ይህ ማለት በስራው አለምም ሆነ በማሕበራዊው ስምሪታችን ብዙ እውቀት እያላቸው የስሜት ብልህነት ከጎደላቸው ሰዎች ይልቅ አናሳ እውቀት ይዘው ከፍተኛ የስሜት ብልህነት ያላቸው ሰዎች ልቀው ይገኛሉ፡፡

በዚህ እውነታ ላይ መሰረታዊውን ግንዛቤ እንድትጨብጡ የአንድ ምሽት ስልጠናን አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

ለዚህ የቴሌግራም ግሩፕ ተከታታዮቼ በሙሉ፡፡

ቀን - ኃሙስ የካቲት 20

ሰዓት - ማታ ከ2፡30 – 3፡30

የስልጠናው ርእስ - የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence)

ክፍያ - በነጻ!!!

ወዳጆቻችሁም ይህንን telegram channel join በማድረግ እንዲከታተሉ ጋብዟቸው፡፡

በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዚሁ ቻናል በመግባት ስልጠናውን live መከታተል ትችላላችሁ!

Dr. Eyob Mamo

20 Feb, 12:04

https://vm.tiktok.com/ZMkv4DQja/

Dr. Eyob Mamo

20 Feb, 01:59

ደጋግሞ ለምን እንደማይሳካልን!

አብዛኛውን ጊዜ የምንጀምራቸው ነገሮች የማይሳኩልን ከሆነ፣ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማጤን ተገቢውን ማስተካከያ እናድረግ፡፡

1. ጽናት ማጣት

ማንኛውንም በአንድ አቅጣጫ ስኬት ያገኘን ሰው ጠይቁ፣ የስኬት ጎዳና የፈተና ጎዳና ነው፡፡ የጀመርነውን ነገር በማድረግ ካልጸናን ስኬት የሚባል ነገር የለም፡፡

2. የጽኑ ፍላጎት እጦት

በአንድ በጀመርነው ነገር ዙሪያ ገና ከመጀመሪያው በጽኑ ፍጎት ካልተነሳን የመጣው እንቅፋት ሁሉ የማቆሚያ ምክንያት ስለሚሆነን እስኪሳካ ድረስ መቀጠል ያስቸግረናል፡፡

3. ምክንያት ማብዛት

በሕይወታችን ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ሙሉ ሃላፊነቱን ካልወሰድን፣ ሌሎችን ስንወቅስ ራሳችንን ስለምናገኘው ለችግሮች መፍትሄ የማግኘት ብቃታችን ይወሰዳል፡፡

4. ያለፉትን ስህተቶች መካድ

ከዚህ በፊት የሰራናቸውን ስህተቶች ለማስታወስ ከማፈራችን የተነሳ እንዳልተከናወኑ በማሰብ አይናችንን ስንጨፍን ከትምህርት ይልቅ ውድቀትን እናስተናግዳለን፡፡

5. ፍጸሜያችን ተወስኖ እንደተወለድን ማሰብ

አንዳንድ ሰዎች የሕይወታቸው አቅጣጫና ፍጻሜ ገና ሳይወለዱ እንደተመደበና ከዚያ ሁኔታ ንቅንቅ የማለት አቅም እንደሌላቸው ስለሚያስቡ የመጣውን ነገር ለመለወጥ ከመስራት ይልቅ እንዲሁ በመቀበል ያስተናግዱታል፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

19 Feb, 14:21

ነጻ የስልጠና እድል!
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

ለዚህ የቴሌግራም ግሩፕ ተከታታዮቼ በሙሉ፡፡

ቀን - ኃሙስ የካቲት 20

ሰዓት - ማታ ከ2፡30 – 3፡30

የስልጠናው ርእስ - የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence)

ክፍያ - በነጻ!!!

ወዳጆቻችሁም ይህንን telegram channel join በማድረግ እንዲከታተሉ ጋብዟቸው፡፡

በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዚሁ ቻናል በመግባት ስልጠናውን live መከታተል ትችላላችሁ!

Dr. Eyob Mamo

19 Feb, 08:19

የብዙ ሰዎች ጥያቄ!

ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡

በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-

1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)

2. እሴት-ተኮር (Value-based)

እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡

ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

https://t.me/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

19 Feb, 01:59

“የመገፋት ስስነት”
(“የመገፋት ህመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በስነ-ልቦናው ቋንቋ “የመገፋት ስስነት” (Rejection Sensitivity) የተሰኘው ሃሳብ ሰዎች በየእለት ኑሯቸው የሚያጋጥማቸውን ጥቃቅን የሰዎች ሁኔታ ከመገፋትና ከመገለል ጋር የማዛመድ ስስነትንና ዝንባሌን የሚያሳይ ጽንሰ-ሃሳባ ያመለክታል፡፡

አንዳንድ ሰዎች በመገፋት ዙሪያ እጅግ ስስ ከመሆናቸው የተነሳ እንደተገፉ የመሰላቸው ማንኛውም አይነት ሁኔታ ሲመለከቱ የመደናገጥና የመዋረድ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ ሰዎች ሲያስጠብቋቸው፣ ስልካቸውን ካልመለሱላቸውና እንደዚህ የመሳሰሉ “አናሳ” የሆኑ ክስተቶች የዝቅተኝትን፣ የመናቅንና የመገለልን ስሜት ያመጣባቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ዝንባሌን አስመልክቶ በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ፣ የዚህ ተጽእኖ ሰለባዎች፣ ሰዎች በፊት ገጽታቸው የሚያሳዩት ሁኔታ እነሱን ያለመቀበልና የመግፋት ምልክት እንዳለው ሲሰማቸው የአንጎል እንቅስቃሴያቸው (Brain Activity) በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር ጥናቶቹ ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪም፣ እነሱን የመግፋት ወይም የማግለል ገጽታ ሊኖረው የሚችልን ማንኛንም እንቀስቃሴም ሆነ ንግግር በንቃትና ሁኔታዎችን በማዛመድ የመመልከትና የመጠባበቅ ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡

የዚህ ዝንባሌ አንዱ ጫና፣ አድልዎ-ተኮር ምላሽ (Attention Bias) ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ለአስር ሰዎች የፍቅር ጥያቄ አቅርበው ዘጠኙ ተቀብለዋቸው አንዱ ብቻ ፍላጎት እንደሌለው ቢገልጽላቸው፣ እነሱ የሚያተኩሩትና ስሜታቸውን የሚነካው የዘጠኙ እሺታ ሳይሆን የአንዱ እምቢታ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትኩረትን ከመገፋት አንጻር ብቻ የመቃኘት አድሎአዊ አመለካከት የሚያስከትልባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ በግል ሕይወታቸውም ሆነ በማሕበራዊ ግንኙነታቸው ላይ የሚስከትለው መዘዝ ቀላል አይደለም (ምንጭ፡- verywellmind.com)፡፡

ሁኔታውን ስንጨምቀው፣ በመገፋት ስቃይ ውስጥ ያለፈ ሰው የሰዎችን፣ በተለይም በእነሱ ሕይወት ስፍራ እንዳላቸው የሚሰማቸውን ሰዎች እያንዳንዱን ተግባር በመገመት በመላ-ምት የመኖር ዝንባሌ ያጠቃቸዋል፡፡ ይህ አሉታዊ-ገማችነት ገደብ የሌለው ሃሳብ-ወለድ አለም ውስጥ እንዲዋዥቁና የሌለንና ያልተፈጠረን ነገር በውስጣቸው እንዲያሰላስሉ ያደርጋቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች አንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት አለም ውስጥ ከገቡ በኋላ ሲያሰላስሉት ውለው ያደሩት ነገር በእነሱ ውስጥ “የሌለ እውነታ” ሆኖ ይኖራል፡፡ የዚህ ስሜት ውጤት ሰዎች የሚያደርጓቸውንም ሆነ የማያደርጓቸውን ነገሮች እየለቀሙና እየቆጠሩ ካለባቸው “የመገፋት ስስነት” ጋር የማዛመዝ ሁኔታ ነው፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች የሚሰማቸው ስሜት በእርግጥም ከእውነተኛ የመገፋት ልምምድ የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ለመገፋት ስሜት ስስ እንዲሆኑ ከዳረጋቸው ከእውነታ የራቀ እይታም ሊነሳ ይችላል፡፡ መነሻው ያም ሆነ ይህ፣ ሰዎች በዚህ የስሜት ተጽእኖ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላለባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ ትክክለኛውን መፍትሄ እንዲፈልጉ ይመከራሉ፡፡

(ከመገፋት ህመም የመላቀቂያውን እውቀት ለማግኘት መጽሐፉ ይነበብ)

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

19 Feb, 01:58

“የመገፋት ስስነት”

Dr. Eyob Mamo

18 Feb, 02:03

ፍርሃት የገዛው ትውልድ!

ይህ ትውልድ ፍርሃት የገዛው ትውልድ ነው፡፡ ፍርሃት የገዛው ትውልድ በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ፍርሃት ያገኘዋል፡፡

ሰዎች አይወዱኝም ብሎ ይፈራል፤ የሚወደው ሰው ሲያገኝ ደግሞ የወደደው ሰው መልሶ እንዳይጠላው ይፈራል፡፡

ተቀባይነት አጣለሁ ብሎ ይፈራል፤ ተቀባይነት የሚሰጠው ሰው ሲያገኝ ደግሞ መልሶ እንዳይገፋው ይፈራል፡፡

ከሰው ጋር መሆን ይፈራል፤ ከሰው ሸሽቶ ብቻውንም ቢሆንም ይፈራል፡፡

የቀረበው ሰው እንዳይጎዳው ይፈራል፤ ሰውየው ከጎዳው ደግሞ እንደገና ላለመጎዳት ሲል ከዚያ ሰው መለየትን ሲያስብ ሰውየውን እጎዳዋለሁ ብሎ ደግሞ ይፈራል፡፡

ሳላገባ ብቻዬን ልቀር ነው ብሎ ይፈራል፤ ካገባሁ ግን እጎዳለሁ ብሎ ስለሚያስብ ማግባትን ይፈራል፡፡

ስለሚፈራ እንቅልፍ አይወስደውም፤ እንቅልፍ ስላልወሰደው ደግሞ ይፈራል፡፡

እንዳይነግድ ክስረትን ይፈራል፤ እንዲሁ ቁጭ እንዳይል ድህነትን ይፈራል፡፡

ደፍሮ ከወጣ አደጋን ይፈራል፤ ፈርቶ ከቀረ ደግሞ ሰዎች ፈሪ ነው ብለው ያስባሉ ብሎ ይፈራል፡፡

ከፍርሃት የተነሳ መሆንና ማድረግ ያለብህን ሳታደርግ አንድ መቶ አመት ከምትኖር ፍርሃትህን ተጋፍጠህና ቀና ብለህ አስር አመት በዓላማ ኖረህ ብታልፍ ይሻልሃል፡፡

ከፍርሃት ነጻ የሆነ ሕይወት ሊኖር ያለመቻሉን ያህል ፍርሃትን ተጋፍጦ ከመኖር ውጪ ስኬት የለም!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

17 Feb, 14:33

ከሰዎች ንግግር ይልቅ ለተግባራቸው ቦታ ስጡ!

አንዳንድ ሰዎች የሚናገሯችሁ የፍቅር፣ የአክብሮት፣ የአድናቆትና የናፍቆት ሃሳቦች አስገራሚና አስደማሚ ናቸው፡፡ ተግባራቸው ግን ምን ያህል ተቃራኒ ሆኖ ግራ እያጋባችሁና እየጎዳችሁ እንደሆነ ታውቁታላችሁ፡፡

በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ግራ ከተጋባቸሁ፣ ምላሻችሁንና ውሳኔያችሁን ከንግግራቸው አንጻር ሳይሆን ከተግባራቸው አንጻር እንድታደርጉ ትመከራላችሁ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ደግሞ የሚናገሯችሁ ቃላት ጠንከር ያሉና የሚያቀርቡላችሁ ሃሳቦች ትንሽ ጫን የሚሏችሁ አይነት ናቸው፡፡ በተግባራቸው ግን ሁል ጊዜ ለእናንተ የሚጠቅምንና እናንተን የሚደግፍ ሁኔታን በግልጽ ያሳይዋችኋል፡፡

እነዚህንም ቢሆን ምንም እንኳን የሚናገሯችሁ ንግግሮችና የሚሰጧችሁ ሃሳቦች ጠንከር ቢልባችሁም፣ ከእነሱ ጋር ያላችሁን አቅርቦት ለመወሰን ተግባራቸው ላይ እንድታተኩሩ ትበረታታላችሁ፡፡

መልካም ምሽት!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

17 Feb, 02:04

የትኩረት ጉልበት!

• ችግሩ እያለ፣ ትኩረታችንን ትክክለኛውን መፍትሄ መፈለግ ላይ ስናደርግ . . .

• ፍርሃቱ እያለ፣ ትኩረታችንን በጥንቃቄ ወደ ፊት በመራመድ አልፎ መሄድ ላይ ስናደርግ . . .

• የሰዎች ክፋት እያለ፣ ትኩረታችንን ስናስባቸው የሚያበረታቱን ጨዋ ወዳጆቻችን ላይ ስደርግ . . .

• የተለወጠብን ሰው እያለ፣ ትኩረታችንን አብሮነቱ የማይለዋወጠው ሰው ላይ ስናደርግ . . .

• ያልተሳካው ነገር እያለ፣ ትኩረታችንን የተሳካው ላይ እና ወደ ፊትም ሰርተን የምናሳካው ነገር ላይ ስደርግ . . .

• ስህተትና ስህተቱ ያስከተለው ጉዳት እያለ፣ ትኩረታችንን ከስህተቱ ያገኘነው የእድሜ ልክ ትምህርት ላይ ስናደርግ . . .

• በምርጫ ግራ መጋባቱ እያለ፣ ትኩረታችንን ምንም ምርጫ የሌለው ኑሮ ከሚኖሩ ሰዎች የመሻላችን ሁኔታ ላይ ስናደርግ . . .

ኃይላችንን እቆጥባለን፣ ነገን ለመጋፈጥ ጉልበት እናገኛለን፣ በሆነ ባልሆነው ግራ አንጋባም፣ ከልክ ካለፈ የሃሳብ ግልቢያ (overthinking) ረገብ እንላለን፡፡

የትኩረት ለውጥ እናድርግ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

16 Feb, 05:36

https://vm.tiktok.com/ZMkW19Yq7/

Dr. Eyob Mamo

15 Feb, 05:59

የሚያነሳሳችሁ (Motivate የሚያደርጋችሁ) ምንድን ነው?

አንድን ማድረግ የምፈልጉትን ነገር ለማድረግ የሚያነሳሳችሁ ነገር ስለማንነታችሁ፣ ስላላችሁ ዲሲፕሊንና ስለ ንጽረተ-ዓለማችሁ ብዙ ይናገርል፡፡

1. የሌሎች ሰዎች አለመሳካት ወይም ወደ ኋላ መቅረት ያነሳሰችኋል?

እንደዚህ አይነት ሰዎች የመበለጥና የበታችነት ስሜት ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ስሜት የተነሳ ሌሎች ሰዎች እንዳልተሳካላቸው ሲያዩ ጥሩ ስሜት ሰማቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጽናት የሚከታተሉት የግል ዓላማ እንደሌላቸው አመልካች ነው፡፡

2. አንድ ነገር እንዳይደረስባችሁ መፍራት ያነሳሳችኋል?

እንደዚህ አይነት ሰዎች ከፍተኛ የሆነ የፍርሃት ችግር ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ አንድ ነገር እንደሚደርስባቸው ሲያስቡና ሲፈሩ ምንም ነገር ከማድረግ አይመለሱም፡፡ ፍርሃት ከሌለ መነሳሳቱም አይኖራቸውም፡፡

3. ሰዎች ስለ እናንተ የሚያስቡትና የሚናገሩት ነገር ያነሳሳችኋል?

እንደዚህ አይነት ሰዎች የሰውን አመለካከት ትልቅ ስፍራ የመስጠት ችግር ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ሌሎች ሰዎች ስለ እነሱ ጥሩ ሃሳብ ሲሰነዝሩ ደስ በመሰኘት ይነሳሳሉ፡፡ መጥፎ ሃሳብ ሲሰነዘርባቸው በዚያ እልህ ምክንያትም ሊነሳሱ ይችላሉ፡፡

4. በፊታችሁ ለመድረስ በውስጠ-ህሊናችሁ ያያችሁት ራእይ፣ ሕልምና ዓላማ ያነሳሳችኋል?

እንደዚህ አይነት ሰዎች ትክክለኛውን የመነሳሳት መንገድ የተገነዘቡ ሰዎች ናቸው፡፡ በዙሪያቸው ምንም ሆነ ምን እነሱ ከታያቸው ራእይና ከያዙት ዓላማ አንጻር ካለማቋረጥ ጉዟቸውን ይቀጥላል፡፡

ራሳችሁን የትኛው ላይ እንዳገኛችሁት በመመልከት ማስተካከያ ብታደርጉ ምን ይመስላችኋል?

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

Dr. Eyob Mamo

14 Feb, 01:59

ማን ነኝ?

ይህንን ጥያቄ ከተወለድክበት እለት አንስቶ ካሳለፍካቸው ሁኔታዎችና ታሪኮች በመነሳት ምን ወደመሆን እንደመጣህ ራስህን ለመመልከት ተጠቀምበት፡፡ አወላለድህ፣ አስተዳደግህ፣ ኖሮህና ሳይኖርህ ያደከው፣ ተደርጎልህና ተደርጎብህ ያደከው . . . ተደምሮ ምን ወደመሆን እንደመጣህ ይሰማሃል?
ይህንን መለስ ብሎ የራስን ማንነት የመጠየቅና የመገምገም ሂደት በፍጹም እውነተኛነትና ድፍረት ልታደርገው ይገባሃል፡፡

እውነተኛነት የሚያስፈልገው አንዳንድ ማሰብ የማንፈልጋቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉና በክህደት አለም ውስጥ የመደበቅ ፈተና ውስጥ ልንገባ ስለምንችል ነው፡፡ ድፍረት የሚጠይቀው ደግሞ አንዳንድ ታሪኮቻችንና አሁን ያለንባቸው ሁኔታዎች ስናስባቸው አቅም አሳጪ ሊሆኑ ስለሚችሉ ያንን ለመጋፈጥ ራስን የመሞገት ቁርጠኝነት ስለሚጠይቁ ነው፡፡

ማንኛውም ሰው ቢሆን ሁለንተናውን ተጋፍጦና ከታሪኩ ጋር ተፋጦ፣ እውነቱን አውጥቶና አውርዶ፣ “አሁን የሆንኩትን የሆንኩት ከእነዚህ ሁኔታዎች የተነሳ ነው” በማለት ማሰብ እስከሚጀምር ድረስ መስመር የያዘ የወደፊት አቅጣጫ ውስጥ መግባት ያስቸግረዋል፡፡

- የሚያስፈሩኝ ነገሮች የሚያስፈሩኝ ለምንድ ነው?

- ማሰብ የማልፈልጋቸው ምእራፎቼን ማሰብ የማልፈልገው ለምንድነው?

- ከየትኛው ጤናማ ታሪኬ የተነሳ ነው አሁን ያለኝ መልካም ነገር የበቀለው?

- ከየትኛውስ አስቸጋሪ ታሪኬ የተነሳ ነው አሁን ያለኝ ቀውስ የተከሰተው?

- ዝንባሌዬዎቼና ልገነባባቸው የምችላቸው ጠንካራ ጎኖቼ ምን ምን ናቸው?

- ላርማቸው፣ ላስተካክላቸውና ልቀርፋቸው እንደሚገባኝ የማስባቸው ደካማ ጎኖቼ ምን ምን ናቸው?

- ከእነዚህ ልምምዶቼና ታሪኮቼ ውስጥ ተደብቆ ያለውን እውነተኛ ማንነቴን እንዴት ፈልፍዬ ላወጣው እችላለሁ?

- ከላይ ካነበብኳቸውና ከመሰል ሂደቶች አንጻር እኔ ማን ነኝ?

እስቲ ይህንን ጥያቄ ቀኑን ውለህ ሌሊቱን እደርበትና፡፡ ከቻልክ የየቀን ማስታወሻ (Diary) ለመጻፍ ሞክር፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

14 Feb, 01:58

ማን ነኝ?

Dr. Eyob Mamo

13 Feb, 01:59

ራሳችንን ከራሳችን የሚጋርዱ ነገሮች

1. ራስን አለመቀበል

ራስን መቀበል ማለት ዘሬን፣ መልኬን፣ ቁመናየን . . . እና የመሳሰሉትን ልቀይራቸው የማልችላቸውን የማንነቴ አካሎች በመቀበል መደላደል ማለት ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች ሲታገሉና ሲሸፋፍኑ መኖር ከዋናው ነገር ወደኋላ ይስቀረናል፡

2. ባለፈው ታሪክ መቆለፍ

ያለፈ ታሪክ ማለት ከዛሬ በፊት የነበሩኝን ስኬቶችንና ስህተቶችን የሚያካትት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬታማ ነበርኩ፣ ምንም አያስፈልገኝም ካልን፣ እንዲሁም ደግሞ ስህተተኛ ነበርኩ ስለዚህም ለምንም ነገር አልበቃም ብለን ካሰብን ራስን የማግኘት ትክክለኛ እያታችን ይጋረዳል፡፡

3. ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር

ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማለት ማንነቴን፣ ዓላማዬንና ስኬታማነቴን ሌሎች አቻዎቼ ሆነዋል፣ ደርሰውበታል ብዬ ከማስበው አንጻር መገምገም ማለት ነው፡፡ ይህ ዝንባሌ የራሴ ደረጃና ግብ እንዳይኖረኝ ያግደኛል፡፡

4. የተዛባ የስኬት ልኬት

ስኬት ማለት ማንነትን ማወቅና መቀበል፣ ዓላማን መለየትና ለዚያ መኖር፣ ያለንን ነገር ማሳደግና ለሕብረተሰቡ ጥቅም ማዋል ሆኖ ሳለ፣ ስኬትን ከገንዘብ፣ ከእውቀት፣ ከዝና፣ ከስልጣን . . . ጋር ብቻ ማዛመድ ከራስ ጋር የሚያፋታ እይታ ነው፡፡

5. ወቃሽነት

ወቃሽነት ማለት በዙሪያችን ለሚሆነው ነገር ሁሉ የሚወቀስ ሰው መፈለግና ኃይለኛ አቋሞችን መያዝና ቃላቶችን መናገር ማለት ነው፡፡ ሰዎችን የመውቀስ ልመዳ የእኛን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ወደማሳበብ አዘቅት ውስጥ ያወርደናል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት እንቅፋቶች ራሳችሁን ያገኛችሁበት ነጥብ ላይ ለመስራትና ለማሻሻል ሞክሩ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

Dr. Eyob Mamo

12 Feb, 15:07

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ባለፈው ሰኞ የተጀመረው “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline) የተሰኘው ስልጠና ነገ (ኃሙስ) ይቀጥላል፡፡

የመጀመሪያው ክፍል ቢያመልጣችሁም፣ ያለፋችሁን በ note እና በ audio ቅጂ በመከታተል ከነገ ጀምሮ መቀላቀል ፍላጎት ያላችሁ ያንን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

12 Feb, 11:09

ምንም አሰባችሁ ምንም፣ ሃሳቡ የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

ምንም ተሰማችሁ ምንም፣ ስሜቱ የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

ምንም አቀዳችሁ ምንም፣ እቅዱ የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

ምንም ወሰናችሁ ምንም፣ ውሳኔው የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

ከፈጣሪያችሁ ጋር መማከር የመቅደሙ ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በማንም ሰው ሃሳብ እና ሁኔታ ተጽእኖ ስር ከመውደቃችሁ በፊት ከራሳችሁ ጋር ተማከሩ፡፡

Have A Wonderful Afternoon!!!

Dr. Eyob Mamo

12 Feb, 02:00

የግል ሕልማችሁ ጉዳይ

(“የተደራጀ ሕይወት” ከተሰኘው ሰሞኑን ከታተመው አዲስ የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ)

የተደራጀ ሕይወት ከመኖር አንጻር ሕልማችን ላይ የመስራታችንን አስፈላጊነት ትኩረት ሰጥተን እንመለከታለን፡፡ በቅድሚያ ግን “የግል ሕልም” ስንል ትርጉሙ ምን ማለት እንደሆነ በመስማማት እንጀምር፡፡

“የግል ሕልም ማለት በተለያዩ የግል ሕይወታችን ዘርፎች ስኬታማ እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ለመኖር የሚያስችሉንን መርሆች በመከተል የልህቀት ከፍታ ውስጥ የሚከቱንን ሁኔታዎች መገንባት ማለት ነው፡፡”

በዚህ ትርጉም መሰረት በሕልም ላይ ስለመስራት ማሰብ ማለት የራስን ሕይወት መገንባትና ማሻሻል ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ ራእይ የሰውን ሕይወት የመገንባትን፣ የማሳደግንና የመለወጥን ሁኔታ ሲነካ፣ ሕልም ደግሞ የራስን ሕይወት የመገንባትን፣ የማሳደግንና የመለወጥን ሁኔታ ይነካል፡፡

ይህ ሕልም ብለን የምንጠራው ጉዳይ የራሳችንን ሁለንተናዊ ሕይወት ከማሳደግ ጋር የሚገናኝ ልምምድ ሲሆን፣ ሁኔታው እንዲሁ በሃሳባችን የፈጠርነውን ነገር ሁሉ እንደሚሆን በጭፍንነት የማሰብ ጉዳይ ሳይሆን ተግባራዊ ሂደትን ተከትሎ ስኬታማ ሕይወት ውስጥ የመግባት ጉዳይ ነው፡፡

ሕልሞቻችን ቅዠት ሆነው እንዳይቀሩ መውሰድ ከሚገቡን ወሳኝ እርምጃዎች መካከል የሚከተሉትን ቀላል መርሆች ማስታወስና መለማመድ ይጠቅናል፡፡

1. አልመው - እያንዳንዱ ታላቅ ስኬት የሚጀምረው በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ ሲፈጠር ነው።

2. እመነው - ሕልም ጋር የሚደረሰው ያለምነውን ሕልም ልንደርስበት እንደምንችል በማመን ነው፡፡

3. እየው - ሕልማችንን በገሃዱ አለም ከማየታችን በፊት በአይነ-ህሊናችን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

4. አጋራው - ሕልማችንን በውስጣችን አምቀን ከምንይዝ ይልቅ ለተገቢ ሰዎች ማጋራት ወደ ስኬት ያስጠጋናል፡፡

5. አቅደው - ያለምነውና አምነን በውስጠ-ህሊናችን ያየነውን ሕልም በእቅድ ደረጃ ማውረድ አለብን፡፡

6. ስራው - ሕልማችንን ካመንነውና ካቀድነው በኋላ ወደ እንቅስቃሴ መግባት ይኖረብናል፡፡

7. አጣጥመው - በሕልም ተጀምሮ ጠንክሮ በመስራት እጃችን የገባውን ውጤት ማጣጣምና መደሰት ያስፈልጋል፡፡

መጽሐፉን በቅናሽ ለማግኘት በ 0947930369

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

12 Feb, 01:59

የግል ሕልማችሁ ጉዳይ

Dr. Eyob Mamo

11 Feb, 02:00

የምትሰሩት ስራ ጉዳይ

በአሁኑ ወቅት በስራ አለም ውስጥ ከተሰማራችሁና የወደፊት የስራ ቆይታችሁ ስኬታማና እድገት ያለበት እንዲሆን ከፈለጋችሁ ስለጉዳዩ ማሰብ ያለባችሁ ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ አእምሯችሁን ተጠቅማችሁ ካላሰባችሁ፣ ነገ ስሜታችሁ መጨነቅና መዛባት ይጀምራል፡፡

በስራው አለም ውስጥ በቆያችሁ ቁጥር በሁለት መልኩ ማደግ አለባችሁ፡- 1) በገንዘብ ብቃት፣ 2) በአእምሮ እድገት

1. የገንዘብ ብቃት

የሚከፈላችሁ ክፍያ አናሳ እንደሆነ ካሰባችሁ፣ ለስራው ካላችሁ ብቃት አንጻር እየተከፈላችሁ ሊሆን ስለሚችል ብቃታችሁን የምትጨምሩበትን መንገድ ፈልጉ፡፡ ብቁ ሆናችሁ መስሪያ ቤቱ የመክፈል ባህሉ ወይም አቅሙ አናሳ ሆኖ ካገኛችሁት ደግሞ፣ የመስሪያ ቤቱን አሰራር ለማስቀየር ከመታገል ወይም ከመነጫነጭ ይልቅ የስራ መስካችሁን መቀየር ቀለል እንደሚል አትዘንጉ፡፡

2. የአእምሮ እድገት

የስራው ጸባይ አእምሮን የሚያሰራ፣ የሚሞግትና የሚያሳድግ ከመሆን ይልቅ ድግግሞሽ የሞላው ከሆነ፣ ምንም እንኳን ገንዘብን ብታኙበትም ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚራመድ የአእምሮ እድገት እንደማይኖራችሁ አትዘንጉ፡፡ በስራው ለመቆየት ከፈለጋችሁ፣ በግላችሁ የምታድጉበትን ሌላ መንገድ መፈለግ አለባችሁ፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን የሚሞግት፣ አእምሮን የሚያሰራና የሚያሳድጋችሁን ስራ ወደመፈለግ ማዘንበል ወሳኝ ነው፡፡

እድሜያችሁ በጨመረ ቁጥር ቤተሰብን ከመመስረት የሚመጣ ሃላፊነትና የተለያዩ ፍላጎቶች መጨመር ሁኔታዎች አብረው ስለሚመጡ ካለማቋረጥ የማደጋችሁን ጉዳይ በሚገባ አስቡበት፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 14:54

ጥያቄ፡-

ሰላም ዶክተር፡፡ የ 23 አመት ወጣት ነኝ። ፍቅር በጣም በቶሎ ነዉ የሚይዘኝ ከአብዛኞቹ በቅርቤ ካሉ ሴቶች ፍቅር ይዞኝ ተጎድቻለሁ እየተጎዳሁ ነው።

መልስ፡-

በቅርብህ ከሚገኙ ሴቶች ሁሉ ጋር ወይም ከአብዛኛዎቹ ጋር ፍቅር የያዘህ ከመሰለህ፣ ይህንን ስሜትህን ፍቅር ብለህ ጠራኸው እንጂ የፍቅር ስሜት አይደለም፡፡

ከዚህ በታች ያሰፈርኳቸው ሁኔታዎች ተከስተውብህ እንዳይሆን እስቲ አስብበት፡-

1. አንተ ባለህበት እድሜ ከፍተኛ የሆነ ወሲብ የማድረግ ፍላጎት ሊኖር የሚችልበት እድሜ ስለሆነ ይህንን የተፈጥሮ ሂደትና ወሲብ ለመፈጸም የመፈለግ ስሜት ከፍቅር ስሜት ጋር አምታተኸው ይሆናል፡፡

2. ምናልባት በዚህ እድሜህ ፍቅረኛ የማግኘት ፍላጎትህ የጎላ ስለሆነ ያንን ከመፈለግህ የተነሳ የሚቀርቡህን ሴቶች ሁሉ በዚያ አይን የመመልከትና ፍቅረኛ የማድረግ ጥረትና ዝንባሌ ኖሮህ ሊሆን ይችላል፡፡

3. ምናልባት በሕይወትህ የመገፋት ስሜት ካለህና ተቀባይነትን አጥብቀህ የምትፈልግ ከሆነ ከቀረቡህ ሴቶች ሁሉ ጋር የመቅረብና ተቀባይነት ማግኘት የመፈለግ ዝንባሌ ኖሮህ ሁኔታው ከፍቅር ስሜት ጋር ተምታቶብህ ይሆናል፡፡

4. ምናልባት ፍቅር (Love) ማለት ከተቃራኒ ጾታ ጋር መቀራረብ (Attachment) ብቻ እንደሆነ ጠበብ ያለ ምልከታ ኖሮህ ልክ እንደቀረብካቸው ፍቅር እንደያዘህ እያሰብክ ሳለህ በእነሱ ውስጥ ግን ከቀላል ጓደኝነት ያላለፈ ስሜት ኖሮ በዚያ እየተጎዳህ እንዳይሆን፡፡

ያም ሆነ ይህ፣ ካገኘሃት ሴት ሁሉ ጋር ፍቅር ስሜት እየተሰማህ ከተጎዳህ ክፍተቱ ያለው አንተ ጋር ነው፡፡ ስለዚህ፣ ለተወሰነ ጊዜ ፍቅረኛ ፍለጋህን ትንሽ ተወት አድርገውና ማንነትህን ማወቅ፣ መቀበልና የፍቅር ግኙነት ምን ማለት እንደሆነ መብሰል ላይ ለመስራት ሞክር፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 14:54

ፍቅር በጣም በቶሎ ነዉ የሚይዘኝ

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 14:39

https://vm.tiktok.com/ZMkstk2W4/

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 13:03

ዛሬ ምሽት የሚጀምረው ስልጠና ምዝገባው በአንድ ሰዓት ውስጥ ይቆማል!

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 12:05

ዛሬ ምሽት የሚጀምረው ስልጠና ምዝገባ
በሁለት ሰዓት ውስጥ ይቆማል!

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 10:32

ለስልጠናው የተመዘገባችሁ

ዛሬ ማታ በ2፡30 የሚጀምረውን ስልጠና እንዳትዘነጉ፡፡

የሚጀምረው 2፡30

የሚጠናቀቀው 4፡00

See you tonight!

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 10:03

ዛሬ ማታ ለሚጀምረው ስልጠና ተመዝቢዎች ለመሰልጠን በመዘጋጀት ላይ ናቸው፡፡ እናንተም አያምልጣችሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 06:55

ለመመዝገብ ሰዓታት ነው የቀራችሁ!

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 05:00

የስልጠናው ቀን ዛሬ ነው!

ዛሬ በ telegram (online live) የሚጀምረውና ለአራት ቀናት (ሰኞ እና ኃሙስ ምሽቶች) የምሰጠው ስልጠና፣ መጽሐፍን የመጻፍ ክህሎትና ዲሲፕሊን በሚገባ ያሳያችኋል፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ ምዝገባ ስለምናቆም አሁኑኑ ተመዝገቡ!

ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ መመሪያውን መቀበል ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

10 Feb, 02:00

ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው!

ዛሬ የመደሰትና በሕይወት ስላላችሁ ብቻ ፈጣሪን እያመሰገናችሁ የመዋል ምርጫው የእናንተው ነው፡፡

ደስታ የሁኔታ ጉዳይ ሳይሆን የምርጫ፣ የአመለካትና የዝንባሌ ጉዳይ ስለሆነ ማለት ነው! በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ደስታ ሁኔታዎች ሲለዋወጡ አብሮ ይለወጣል፡፡ ፈጣሪን በማሰብና እሱ በሰጠን ነገር የመደሰት ልምምድ ግን ሁነታ እና ዘመን ዘለል ነው፡፡

• ዛሬ ለመደሰት ምንም ነገር ሊኖችሁ አያስፈልግም፤ ያላችሁን ነገር እያሰባችሁና እየተጠቀማችሁ መደሰት ትችላላችሁ፡፡ የሌላችሁ ነገር ላይ ሳይሆን ያላችሁ ላይ በማተኮር ያንን ተጠቅማችሁ ለማደግ ስሩ፡፡

• ዛሬ ለመደሰት ማንም ሰው አጠገባችሁ ሊኖር አያስፈልገውም፤ ካገኛችሁት ሰው ጋር ደስታን መፍጠር ትችላላችሁ፡፡ ከእናንተ ዘወር ብለው የሄዱ ሰዎች ላይ ትኩረታችሁን ማድረግ ተውና አጠገባችሁ ባሉ ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ በሚወዷችሁ ሰወች ተደሰቱ፡፡

• ዛሬ ለመደሰት የትኛውም ችግራችሁ መቃለል አያስፈልገውም፤ ብዙ ሰዎች ላይ የደረሱ ብዙ አስከፊ ሁኔታዎች እናንተ ላይ እንዳልደረሱ በማሰብ መደሰት ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ስታደርጉ አዲስ ምልከታና ትኩስ ጉልበት ታገኛላችሁ፡፡

• ዛሬ ለመደሰት የትኛውም ሰው የእናንተን ሁኔታ መቀበል የለበትም፤ ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ ራሳችሁን በመቀበል ደስተኛ መሆን ትችላላችሁ! በራሳችሁ ላይ ያላችሁን አመለካከት በማስተካከልና ራሳችሁን ስትቀበሉ ሰዎችም እየተቀሏችሁ ይሄዳሉ፡፡

ደስ ይበላችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

09 Feb, 17:25

ለመመዝገብ አንድ ቀን ብቻ ቀራችሁ

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

08 Feb, 16:34

08 Feb, 16:31

ጤንነት ከገንዘብ ይበልጣል!

1. የአካል ጤንነት - ገንዘብ ለማግኘት ብላችሁ የአካል ጤንነታችሁን አትክፈሉ፡፡

ገንዘብ ለማግኘት ብላችሁ ያጣችሁትን የአካል ጤንነት ለመመለስ ያገኛችሁትንና ከዚያም በላይ ገንዘብ ታወጣላችሁ፡፡ ለዚያው ከተመለሰ ነው፡፡

2. የስነ-ልቦና ጤንነት - ገንዘብ ለማግኘት ብላችሁ የስነ-ልቦና ጤንነታችሁን አትክፈሉ፡፡

ገንዘብ ለማግኘት ብላችሁ ያጣችሁትን የስነ-ልቦና ጤንነት ለመመለስ ያገኛችሁትንና ከዚያም በላይ ገንዘብ ታወጣላችሁ፡፡ ለዚያው ከተመለሰ ነው፡፡

3. ማሕበራዊ ጤንነት - ገንዘብ ለማግኘት ብላችሁ የማሕበራዊ (ቤተሰብንና ትዳርን ጨምሮ) ጤንነታችሁን አትክፈሉ፡፡

ገንዘብ ለማግኘት ብላችሁ ያጣችሁትን የማሕበራዊ ጤንነት ለመመለስ ያገኛችሁትንና ከዚያም በላይ ገንዘብ ታወጣላችሁ፡፡ ለዚያው ከተመለሰ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

08 Feb, 12:11

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

08 Feb, 04:52

08 Feb, 02:01

ለራሳችሁ መልካም ሁኑ!
Be nice to yourself!

1. ስህተት ከሰራችሁ በኋላ ራሳችሁን ይቅር በሉና እንደገና የቀደመውን ተስፋችሁን አንሱ፡፡

2. ብዙ ከሰራችሁ በኋላ አረፍ በማለት ጉልበታችሁን አድሱ፡፡

3. ከምታገኙት ገንዘብ ላይ የሚያስፈልጋችሁንም ሆነ የምትፈልጉትን ነገሮችን በመግዛት ራሳችሁን ተንከባከቡ፡፡

4. አቅማችሁ በፈቀደና በተቻላችሁ መጠን ጤናማ ምግብን ተመገቡ፡፡

5. ከአቅማችሁ በላይ የሆነን የሰዎችን ሸክም አትሸከሙ፡፡

6. በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እየደጋገመ ከሚጎዳችሁ ሰው ራሳችሁን ጠብቁ፡፡

7. በሚገባ ለማታውቁትና ባህሪው ላልተፈተነ ሰው ራሳችሁን አጋልጣችሁ አትስጡ፡፡

በዚህ ሁሉ የራስ-በራስ መልካምነት መካከል ሃላፊነት ላለባችሁ የቤተሰብ እና የሕብረተሰብ ክፍሎች ያላችሁን የበጎነት አደራ በፍጹም አትጣሉ፡፡

መልካም ቅዳሜ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

07 Feb, 14:19

ለመመዝገብ ሁለት ቀን ቀራችሁ!

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

07 Feb, 10:24

ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)

1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመወጣት ስላቃታችሁ እገዛ ከፈለጋችሁ፣

2. የሕይወታችሁን ራእይ ወይም ዓላማ ባለማወቅ ከተወዛገባችሁና አቅጣጫን መያዝ ከፈለጋችሁ፣

3. ካለባችሁ አጉል ልማድ በመውጣ አዲስ ልማድን ማዳበር ካስቸገራችሁና ምክርና ድጋፍ ከፈለጋችሁ፣

4. መመለስ ያቃታችሁ የሕይወት ጥያቄዎች ከበዙባችሁና በአንድ ለአንድ ውይይት የመፍትሄ መንገድ ከፈለጋችሁ፣

5. በራሳችሁ መወጣት ያልቻላችሁት የተያዩ የስሜትና የስነ-ልቦና ጥያቄዎች ውስጥ እንዳላችሁ ከተሰማችሁና ከሁኔታው ለመውጣት ምክር ከፈለጋችሁ፣

ከግል በተጨማሪም ቁጥራችሁ ከአስር ባልበለጠ ሁኔታ በመሰባሰብ የGroup Coaching and Training ጥያቄም ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡

በቴሌግራም @DrEyobmamo inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

07 Feb, 09:52

https://youtu.be/LpOYhLs02oo

Dr. Eyob Mamo

07 Feb, 06:45

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

07 Feb, 02:05

ጊዜን በጥበብ ያለመጠቀም ጉዳቶች

የአንድ ሰው የሕይወት ጥራት ከሚለካባቸው ሁኔታዎች መካከል ጊዜን በሚገባ የመጠቀሙ ጉዳይ ቀንደኛው ነው፡፡ ጊዜውን በሚገባ የሚጠቀም ሰው አስገራሚና ስኬታማ ሕይወትን የተቀዳጀ ሰው ነው፡፡ ጊዜን በአግባቡና ስኬታማ በሆነ መልኩ መጠቀም ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ጊዜውን በሚገባ የማይጠቀም ሰው ለብዙ ጉዳቶች የተጋለጠ ነው፡፡

ጊዜውን በአግባቡ የማይጠቀም ሰው “ተራ”፣ የተለመደና አማካኝ ሕይወትን ለመኖር ራሱን አሳልፎ የሰጠ ሰው ነው፡፡ ይህ “ተራ” ሕይወት የሚከተሉትን መለወጥ ያለባቸውን ሁኔታዎች ያካትታል፡፡

1. የባከነ ሕይወት፡- ጊዜውን በአግባቡ የማይጠቀም ሰው የባከነ ሰው የትኛውን ተግባሩን መቼ ማከናወን እንዳለበትና ያም ተግባር ምን ያህል ጊዜውን እንደሚወስድበት በቅጡ ስለማያውቅ እንደባከነ ይኖራል፡፡

2. የተበታተነ ሕይወት፡- የተበታተነ ሕይወት ያለው ሰው ማለት ዋነኛ ተግባሩ ላይ ከማተኮር ይልቅ በእለቱ በፊቱ ቀርቦ ባገኘው ነገር የሚወሰድ ሰው ማለት ነው፡፡

3. የድካም ሕይወት፡- ጊዜውን በአግባቡ የመጠቀምን ባህል ያላዳበረ ሰው ብዙ የሚለፋ ሰው ነው፡፡ ብዙ ይንቀሳቀሳል እንጂ ብዙ ውጤትን አያስመዘግብም፡፡

4. የማይረካ ሕይወት፡- ጊዜውን በቁጥጥሩ ስር ያላዋለ ሰው በቀኑ መጨረሻ እቤቱ ሲገባ ምንም እንዳላከናወነ የሚሰማው ሰው ነው፡፡ ሰርቷል፣ ነገር ግን አላከናወነም፣ ሮጧል ነገር ግን አልደረሰም፣ ብዙ አስቧል ውሳኔ ላይ ግን አልደረሰም፡፡

5. ተፈላጊነት የሌለው ሕይወት፡- በሰዓቱ የማይገኝን ሰው ማን ይፈልገዋል? አንድን ተግባር በተፈለገበት ሰዓት የማያደርስን ሰው ማን ያስጠጋዋል? በዚህ ዘመን ተፈላጊው ሰው እንደ ቃሉ የሚገኝና የጀመረውን ነገር እፈጽማለሁ ባለው ሰዓት የሚፈጽም ሰው ነው፡፡

6. ያልተረጋጋ ሕይወት፡- በጊዜ አጠቃቀም ያልበሰለ ሰው ያልተረጋጋ ሰው ነው፡፡ የጊዜ አያያዝ ብልሃቱ የገባው ሰው ፕሮግራም ለማውጣት ለፍቶ በኑሮውና በስራ መስኩ ግን መረጋጋትን የመረጠ ሰው ነው፡፡

7. በግዳጅ ውስጥ የሚኖር ሕይወት፡- ጊዜውን በጥንቃቄ የማይጠቀም ሰው “እምቢ” ለማለት የማይችል ሰው ነው፡፡ ሰዎች የጠየቁትን ነገር ሁሉ ቢመቸውም ባይመቸውም እሺ በማለት ራሱን ሳይፈልግ ግዳጅ ውስጥ ይጨምራል፡፡

8. እቅድ-የለሽ ሕይወት፡- የጊዜና አጠቃቀም ያልገባው ሰው ሕይወትን የሚኖራት በመላ- ምትና በዘፈቀደ ነው፡፡

9. ግምገማ-የለሽ ሕይወት፡- ጊዜውን የሚጠቀም ሰው እያንዳንዱ ቀን፣ ሳምንት፣ ወርና አመት ካፈ በኋላ መለስ በማለት ራሱንና ስኬታማነቱን ይገመግማል፡፡

10. “መዘዘኛ” ሕይወት፡- ሰአቱን በሚገባ የማይጠቀምና ራሱን፣ አመለካከቱንና ተግባሩን ያልሰበሰበ ሰው ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለትዳር ጓደኛው፣ ለስራ ባልደረባውም ሆነ ለወዳጆቹ ሁሉ የኋላ ቀርነት ምክንያት ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

07 Feb, 01:59

ጊዜን በጥበብ ያለመጠቀም ጉዳቶች

Dr. Eyob Mamo

06 Feb, 11:02

https://vm.tiktok.com/ZMkg5soN5/

Dr. Eyob Mamo

06 Feb, 07:35

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

06 Feb, 02:04

ከምክንያት ወደ ውጤት!

ስላላችሁበት ሁኔታ ምክንያት እየሰጣችሁ ባላችሁበት ከመርገጥ ይልቅ ለውጤት ወደመስራት አለፋችሁ እንድትሄዱ . . .

1. በዚህ አመት የሚሰራ ስራ ካጣችሁ በአንድ ዘርፍ ላይ ያተኮረን ክህሎት ያለማዳበራችሁን ጉዳይ አስቡብ፡፡ በተቃራኒው፣ መስራት የምታስቡት ነገር በዝቶባችሁ ከየትኛው እንደምትጀምሩ ግራ ከገባችሁ የትኩረት ችግር አለባችሁና እሱ ላይ ስሩ፡፡

2. በዚህ አመት ጊዜያችሁን የምታሳልፉበት ነገር ካጣችሁ ራእይና ዓላማ እንደሌላችሁ ጠቋሚ ነውና እሱ ላይ ስሩ፡፡ በተቃራኒው፣ የማሕበራዊው ግንኙነትና የስራው ብዛት ጊዜ ካሳጣችሁ ነገሮችን ቅደም-ተከተል የማስያዝ ብቃተችሁን አስቡበት፡፡

3. በዚህ አመት ጓደኛ ካጣችሁና ብቸኝነት ከተሰማችሁ የባህሪያችሁን ጉዳይ በሚገባ አስቡበት፡፡ በተቃራኒው፣ ጓደኛ በዝቶ ለራሳችሁ ጊዜ እስከማጣት ድረስ ከደረሳችሁ እንደዚህ የሚያጦዛችሁ የብቸኝነት ስሜት እንዳይሆን ሁኔታውን ለማጤን ሞክሩ፡፡

4. በዚህ አመት ገንዘብ ካጣችሁ የሰዎችን ችግር የመፍታት ብቃታችሁን አስቡበት፤ ገንዘብ የምናገኘው ለፈታነው የሰዎች ችግር ስለሆነ ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ገንዘብ በዝቶ በምን ላይ እንደምታውሉት አጠቃቀሙን ግራ ከገባችሁ የፈጠራ ብቃታችሁ ላይ ስሩ፡፡

ዝም ብላችሁ የመጣውን እየተቀበላችሁ፣ የሚሄደውን ደግሞ እየሸኛችሁ አትኑሩ! አስቡ! ጠይቁ! መልስ እስከምታገኙ አትረፉ! ሞክሩ! ተንቀሳቀሱ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

05 Feb, 17:27

የፊታችን ሰኞ ሳምንት (የካቲት 3/2017) ለአራት ቀናት (ሰኞ እና ኃሙስ ምሽቶች) የምሰጠው ስልጠና፣ መጽሐፍን የመጻፍ ክህሎትና ዲሲፕሊን በሚገባ ያሳያችኋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፣ ከ30 በላይ መጽሐፍት ለመጻፍ ያስቻለኝን የግል ልምምዴን የማጋራበት ስልጠና ይሆናል፡፡

ስልጠናው ልክ እንደሌሎቹ ስልጠናዎች በ telegram (online live) ለአራት ቀናት (ሰኞ እና ኃሙስ ምሽቶች) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

05 Feb, 04:31

አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ያገኙታል!
Available at bookstores!

“የተደራጀ ሕይወት” (“Organized Life”)

የግል ሕይወታችንን እንዴት ማደራጀት እንደሚቻል መንገዱን የሚያመላክታችሁ አዲስ እይታ!

በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

በቅናሽ ዋጋ ለማግኘት ከፈለጋች በዚህ ስልክ መደወል ትችላላችሁ - 0947930369 (ሄኖክ)

Dr. Eyob

Dr. Eyob Mamo

05 Feb, 01:59

የተሸከመህ ሸክም

ገና ከጫጩትነቱ ጀምሮ ብረር ብረር የሚለውና በፍጥነቱ ታዋቂ ለመሆን የሚመኝ ወፍ ነበረ ይባላል፣ ምንጩ የማይታወቅ አፈ-ታሪክ፡፡ እናቱ ከልምዷ በመነሳትና ለእርሱ በመጠንቀቅ ተረጋጋ ትለው ነበር፡፡ እርሱ ግን ፈጽሞ አይሰማትም ነበር፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ ሄደና በእርግጥም እንደተመኘው ፈጣን በራሪ ሆነ፡፡

ይህ ወፍ በቃ መብረር ይወዳል፡፡ መብረር ከመውደዱ የተነሳ ማታ ሁሉም በጊዜ ወደጎጆው ሲመለስ አይኑ ለማየት የማይችልበት ደረጃ እስኪመሽ ድረስ ሲበር፣ ሲከንፍ ውሎ እያለከለከ ወደ ጎጆው ይገባል፡፡ ማለዳም ቢሆን ለመነሳት የሚቀድመው ወፍ የለም፡፡ ከእርሱ ዘግየት ብለው የወጡ አቻ ወፎቹን ካልተወዳደርን እያለ ስቃያቸውን ነው የሚያላቸው፡፡ ሁሉንም ግን ይቀድማቸው ነበር፡፡

ይህ ወፍ ሌሎቹን ወፎች ሁሉ የመቅደሙ ሁኔታ ስላላረካው አሁንም ከዚያ በበለጠ ሁኔታ ለመፍጠንና ከእርሱ የላቁ የወፍ ዝርያዎች ጋር ለመወዳደር ምኞት አደረበት፡፡ አንድ ቀን አንድ ሃሳብ ብልጭ ያለለት መሰለው፡፡ ብዙ ካሰበ በኋላ፣ “ችግሬ ክብደቴ ነው” ወደማለት ሃሳብ መጣ፡፡ ክብደቱን ለመቀነስ ሲል በየቀኑ አንድ ላባ ከክንፉ ላይ በመንቀል ፍጥነቱን መለካት ጀመረ፡፡ የተወሰኑ ላባዎች ሲነቅል እውነት ይሁን ወይም የስነ-ልቦና እይታ ያመጣው ምልከታ ይሁን ባይታወቅም ፍጥነቱ የጨመረ መሰለው፡፡

ይህ ተግባሩ እንደማያዛልቀው እናቱ በየቀኑ ብትመክረውም፣ “እንደናንተ ያለ ወደኋላ የቀረ አመለካከት ያለው ሰው ነው የጎተተኝ” በማለት አልሰማ አለ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ መብረር እስከሚያስቸግረው ድረስ አብዛኛዎቹን የክንፉን ላባዎች ነቀላቸው፡፡ ከዚያ የተከተለውን ውጤት መገመት ቀላል ነው፡፡ እውነታው የገባው በኋላ ነው፡፡

ለካ ሸክም ሆነብኝ ያለው ነገር እሱን የተሸከመው ነው . . . ሸክሜ ነው ያለው ነገር የመብረሪያ አቅሙ ነው . . . አዎ ሸክም ነው፣ ነገር ግን የጉልበት ምንጭ ነው . . . አዎ ሸክም ነው፣ ነገር ግን ወደከፍታ ለመብረር የተነሳበት መነሻና እንደገና የማረፊያ ምክንያት ነው፡፡

• ይህ የልጆች የሚመስል ታሪክ “ሸክም ሆናችሁብኛል” በማለት ቀድሞውኑ የጉልበት ምንጭ የሆኑትን ቤተቦቹን ነቅሎ የጣለውን ሰው አስታወሰኝ፡፡

• ታሪኩ ውጪ ለተከፈተለት የስኬትና የተቀባይነት እድል መነሻው ቤተሰቡ፣ ትዳሩ፣ ልጆቹና የቅርብ አጋሮቹ ሆነው ሳሉ፣ የሚደርስበትን የስኬት ከፍታ ሲያይ መነሻውን እንደሸክም በመቁጠር ጎድቶ የተነሳውን ሰው አስታወሰኝ፡፡

• ይህ የወፉ ታሪክ ጡንቻ ሲያወጣ፣ አይኖቹ ሲገለጡ፣ ዙሪያውን መመልከት ሲጀምርና ለጋ አቋሙን የሚያደንቁለት ሲበዙ እዚያ ያደረሱትን ወላጆቹንና አሳዳጊዎቹን እንደሸክም የቆጠረውንና ከሕይወቱ ነቅሎ የጣላቸውን ወጣት አስታወሰኝ፡፡

• ይህ ቀላል የሚመስል ታሪክ ተሸክመውት ሳለ እርሱ ግን እንደሸክም የቆጠራቸውን ከእሱ ለየት የሚሉትን የሃገሩን ሰዎች ገንጥሎ ለመጣል የሚቃጣውን የህብረተሰብ ክፍል አስታወሰኝ፡፡

የተሸከመህን ሸክምህን አትጣል!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

05 Feb, 01:58

የተሸከመህ ሸክም

Dr. Eyob Mamo

04 Feb, 18:14

ጽሑፍ ስትጽፉ!

1. በሌላ በምንም መልኩ ስለ እናንተ፣ ስለተሰጧችሁና ስላላችሁ መልእክት ማወቅ የማይችሉ ሰዎች እናንተን ወደ ማወቅ ይመጣሉ፡፡

2. አንዱ ጽሑፋችሁ ሌላ ጽሑፍን ስለሚወልድ ስራችሁ እያደገ፣ እየበዛና እየሰፋ ይሄዳል፡፡

3. የጽሑፍ ስራ ከፍተኛ ዲሲፕሊን ስለሚጠይቅ ለእሱ ያዳበራችሁት ዲሲፕሊን ለሌሎች ስራዎቻችሁ ግብዓት ይሆንላችኋል፡፡

4. ከፍተኛ የሆነ የመረጋጋትና የታመቀ ስሜትን ፈታ የማድረግ ሕክምና-ነክ (therapeutic) ጥቅም ታገኛላችሁ፡፡

5. ጽሑፉን በመጻፍ ሂደት ውስጥ የምትለማመዱት የማዋቀርና የማደራጀት ችሎታ ሕይወታችሁና ስራችሁንም እንድታደራጁ ያለማምዳችኋል፡፡

የፊታችን ሰኞ ሳምንት (የካቲት 3/2017) ለአራት ቀናት (ሰኞ እና ኃሙስ ምሽቶች) የምሰጠው ስልጠና፣ መጽሐፍን የመጻፍ ክህሎትና ዲሲፕሊን በሚገባ ያሳያችኋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፣ ከ30 በላይ መጽሐፍት ለመጻፍ ያስቻለኝን የግል ልምምዴን የማጋራበት ስልጠና ይሆናል፡፡

ስልጠናው ልክ እንደሌሎቹ ስልጠናዎች በ telegram (online live) ለአራት ቀናት (ሰኞ እና ኃሙስ ምሽቶች) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

04 Feb, 08:07

መጽሐፍ አጻጻፍ ደረጃ በደረጃ!

ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን በጽሑፍ ለሌሎች የማጋራት ፍላጎቱ አላቸው፣ ነገር ግን ከየት ጀምረው ወደ የት እንደሚወስዱት ስለማያውቁት ብቻ ቁጭ ብለዋል፡፡

ይህ ሃሳብ እንደሚመለከታችሁ ካሰባችሁ ከዚህ በታች ያሰፈርኳቸውን ደረጃዎች ከተመለከታችሁ በኋላ የቱ ደረጃ ላይ እንዳላችሁ ለመለየት ሞክሩ፡፡

1. አንዳንድ ሰዎች የመጻፍ ፍላጎትና የሚጽፉበት ዋና ርእሰ-ጉዳይ ብቻ ነው ያላቸው፡፡ ከዚያ ባለፈ ምን እንደሚያደርጉም አያውቁትም፡፡

2. አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት ሃሳብ ሲመጣላቸው እዚህም እዚያም በመጻፍ ያጠራቀሟቸው ጽሑፎች ቢኖሩም እንዴት ወደ አንድ ወጥ መጽሐፍ እንደሚሰበስቡት አያውቁበትም፡፡

3. አንዳንድ ሰዎች ሃሳባቸውንም በሚገባ አውቀውና በየተራ ጽፈውት ሳሉ፣ ፍሰቱ፣ ከአንዱ ወደሌላኛው ሽግግሩ፣ አወቃቀሩና መልክ የመያዙ ጉዳይ ግራ ገብቷቸው ቁጭ አድርገውታል፡፡

4. አንዳንድ ሰዎች ምንም እንኳን ሙሉ ለሙሉ በመጽሐፍ መለክ እንደጻፉት ቢያውቁም ገጾቹን (page layout)፣ ሽፋኑን (cover design) እና አጠቃላይ የመጽሐፉን ሁኔታ ለሕትመት በሚደርስ መልኩ ማሻገር ግር ይላቸዋል፡፡

መጽሐፍን በመጻፍና በማሳተም አቅጣጫ ከላይ ከተጠቀሱት የትኛው ደረጃ ላይ እንዳላችሁ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚያም ወደሚቀጥለው ደረጃ እንዴት አልፋችሁ እንደምትሄዱ መገንዘብ፣ አስፈላጊም ከሆነ መሰልጠን የግድ ነው፡፡

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

04 Feb, 08:07

መጽሐፍ አጻጻፍ ደረጃ በደረጃ!

Dr. Eyob Mamo

04 Feb, 02:01

ቀንደኛው የግንኙነት ቀውስ ምንጭ!

ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት አብዛኛውን ቀውስ በመፍጠር ከሚታወቁ ነገሮች መካከል አንዱ የተዛባና የሌለ ነገር የመጠባበቅ (Unrealistic Expectation) ሁኔታ ነው፡፡

1. ሰዎች ከእናንተ የሚጠብቁት ነገር ሲዛባ፡፡

እናንተ በፍጹም በሃሳባችሁ ውስጥ የሌለን ነገር ሰዎች ከእናንተ ጠብቀው ሲቀርቧችሁ የግንኙነት ቀውስን ስለሚፈጥር ውስጥን ያውካል፡፡ ሰዎች ከእናንት ምን እደሚጠብቁ ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር አቅም ባይኖራችሁም፣ በተቻላችሁ መጠን የግንኙነትን ሁኔታ ግልጽ ማድረግ ቀውሱን ይቀንሰዋል፡፡

2. እናንተ ከሰዎች የምትጠብቁት ነገር ሲዛባ፡፡

ሰዎች በፍጹም በሃሳባቸው ውስጥ የሌለን ነገር ከእነሱ ጠብቃችሁ ስትቀርቧቸው የኋላ ኋላ የግንኙነት ቀውስ መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ከሰዎች የምትጠብቁትን ነገር የመቆጣጠር አቅሙ ስላላችሁ ከሰዎች ምን እንደምትጠብቁ ለይቶ በማወቅና ሚዛናዊ በማድረግ ቀውስን መቆጣጠር ትችላላችሁ፡፡

አንድ ሰው ከሌላው ሰው እንደሚያገኝ የሚጠባበቀው ነገር በውስጡ የሌለን “እውነታ” የመፍጠር አቅም አለው፡፡ ይህ የሌለ “እውነታ” እንደሌለ የሚገለጽበት ቀን ሲደርስ ነው ቀውሱ የሚጀምረው፡፡

ሰዎች እንዲሆኑላችሁና እንዲያደርጉላችሁ የምትጠብቁትን ነገር ሚዛናዊ አድርጉ፤ ከእውነታው ጋር አጣጥሙ፡፡ መሆንና ማድረግ የማትችሉትን ነገር ሰዎች ከእናንተ በመጠባበቅ የኋላ ኋላ ቀውስ እንዳይፈጠር ደግሞ ለሰዎች የምታሳዩትን ሁኔታ በጥበብ ማድረግን አትዘንጉ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

03 Feb, 17:08

የፊታችን ሰኞ ሳምንት (የካቲት 3/2017) ለአራት ቀናት (ሰኞ እና ኃሙስ ምሽቶች) የምሰጠው ስልጠና፣ መጽሐፍን የመጻፍ ክህሎትና ዲሲፕሊን በሚገባ ያሳያችኋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፣ ከ30 በላይ መጽሐፍት ለመጻፍ ያስቻለኝን የግል ልምምዴን የማጋራበት ስልጠና ይሆናል፡፡

ስልጠናው ልክ እንደሌሎቹ ስልጠናዎች በ telegram (online live) ለአራት ቀናት (ሰኞ እና ኃሙስ ምሽቶች) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

03 Feb, 02:04

በመጠበቅ ጊዜያችሁን አታባክኑ!

• ደስተኛ ለመሆን ሰዎች በሚያሳይዋችሁ ሁኔታ ደስተኛ እስከሚያያደርጓችሁ አትጠብቁ፡፡ ከማንም ሰው ውጪ ደስተኛ የመሆን ብቃት አላችሁ፡፡

• ችግራችሁን ለማሸነፍ ችግራችሁን ሰዎች እስኪፈቱላችሁ አትጠብቁ፡፡ በመጀመሪያ ችግራችሁን ለመፍታት በራሳችሁ የመንቀሳቀስ ብቃት አላችሁ፡፡

• ሙሉ ሰው ለመሆን በሰዎች ተቀባይነት እስከምታገኙ አትጠብቁ፡፡ ሰዎች ቢቀበሏችሁም ሆነ ባይቀበሏችሁም ሙሉ ሰው ናችሁ፡፡

• የተሟላ ኑሮ ለመኖር ሁሉም ነገር እስኪሟላ አትጠብቁ፡፡ ነገር ሞላም አልሞላም ከዚያ ጋር ባልተነካካ ሁኔታ ከፈጣሪ ጋር ሙሉ ሰው ናችሁ፡፡

• ውስጣችሁ እንዲያርፍ ያሰባችሁበት ዓላማ ላይ እስከምትደርሱ አትጠብቁ፡፡ ከጅማሬው አርፋችሁና በጉዞው እየተደሰታችሁ ወደ ዓላማችሁ የመገስገስ ብቃት አላችሁ፡፡

ሕይወት ሂደት እንጂ የአንድ ቀን ክስተት አይደለችም!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

02 Feb, 17:30

ባልፈራ ኖሮ . . .

• “መጀመር የምፈልገው አንድ ዓላማ ነበር” የምትሉት ነገር አለ?

• “ስለማውቀው እውነት በቅንነት ልሞግተው የምፈልገው ሰው ነበር” ብላችሁ ታስባላችሁ?

• “እውነቱን ነግሬ ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ ሰው ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ?

• “ለአንድ ሰው እውነቱ ተናግሬ እርዳታ ማግኘት ያለብኝ የሆነ አጉል ልምምድ እንዳለኝ አውቃለሁ” ብላችሁ ታስባላችሁ?

• “እንደማፈቅራት/ረው ልነግራት/ረው የምፈልገው አንድ ሰው ነበር” ብላችሁ ታስባላችሁ?

እነዚህንና መሰል ትክክለኛ የሆኑ እርምጃዎች ከመውሰዳችሁ በፊት ፍርሃታችሁ እንዲወገድ የምትጠብቁ ከሆነ መቼም እንደማታደርጓቸው ላስታውሳችሁ፡፡ ድፍረት ማለት ፍርሃትን አልፎ መሄድ ማለት ነው እንጂ የፍርሃት አለመኖር ማለት አይደለም፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

01 Feb, 04:22

የፊታችን ሰኞ ሳምንት (የካቲት 3/2017) ለአራት ቀናት (ሰኞ እና ኃሙስ ምሽቶች) የምሰጠው ስልጠና፣ መጽሐፍን የመጻፍ ክህሎትና ዲሲፕሊን በሚገባ ያሳያችኋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፣ ከ30 በላይ መጽሐፍት ለመጻፍ ያስቻለኝን የግል ልምምዴን የማጋራበት ስልጠና ይሆናል፡፡

ስልጠናው ልክ እንደሌሎቹ ስልጠናዎች በ telegram (online live) ለአራት ቀናት (ሰኞ እና ኃሙስ ምሽቶች) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

31 Jan, 09:29

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

31 Jan, 02:00

የልዩነቴ ዋጋ!

ልዩ ሰው መሆኔ ሁለት አይነት ዋጋን ያስከፍለኛል፡፡ ከሁለቱ አንዱን የመምረጥ መብቱ ግን አለኝ፡፡

አንደኛው ዋጋ፣ ፈጣሪ የሰጠኝን እኔነቴንና ራሴን በመሆኔና እንዲሁም የማምንበትን እውነት በመኖሬ ምክንያት ያንን የማይቀበሉ ሰዎችን ሲለዩኝና እንደእነሱ ስላልሆንኩኝ ሲቃወሙኝ የምከፍው ዋጋ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ሰዎችን የማጣት ዋጋ ነው፡፡

ሌላኛው ደግሞ ልዩነቴን ላልተቀበሉ ሰዎቸ ስል ራሴን ትቼ እንደሌላው ሰው ለመኖር በመሞከሬ የምከፍለው ዋጋ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ራስን የማጣት ዋጋ ነው፡፡

ለሰዎች ብሎ ማንነትን ትቶ መሄድ እጅግ የከፋ ዋጋ ያስከፍላ፡፡ ራስን ሆኖ በመኖር ግን ምንም እንኳን ሰዎች ባጣቸውና ሰዎች ቢቃወሙኝ ራሴንና ዓላማዬን አገኛለሁ፡፡ ምንም እኳን ከእነሱ ጋር ባልስማማም፣ ከራሴ ጋር ግን እስማማለሁ፡፡

የብዙ ሰዎች ማሕበራዊ ችግርና ቀውስ ያለው እዚህ ላይ ነው፤ ሌላውን ሰው ላለማጣት ሲሉ ራሳቸውን ማጣታቸው!

እንግዲህ ምረጡ! ለሰው ብላችሁ ማንነታችሁን ትታችሁ በመሄድ ሰዎችን አግኝታችሁ በሂደቱ ራሳችሁን ማጣት ይሻላችኋል ወይስ ማንነታችሁን ኖራችሁ በሂደቱ አንዳንድ ሰዎችን አጥታችሁ ራሳችሁን ብታገኙ?

ሰዎችን ላለማጣት ብሎ ራስን የማጣት ሁኔታ . . .

1. ሰዎችን ሁሉ አስደሳች ለመሆን ከመፈለግ ይመጣል

2. ውጥረት ወይም አለመግባባት እንዳይከሰት ከመታገል ዝንባሌ ይመጣል

3. ለሰዎች የቀይ መስመር የማስመር አቅም ከማጣት ወይም ብልሃቱን ካለማወቅ ይመጣል

4. የራስ ዓላማ እና አቋም ካመኖር ይመጣል

ለመደምደም ያህል፡- ራስንና ያመኑበትን መኖር፣ አላስፈላጊ ሰዎችን ከሕይወታችሁ የማጥራት ከፍተኛ አቅም እንዳለው በመገንዘብ ይህንን ከባድ፣ ነገር ግን አስገራሚ ጉዞ አሁኑኑ እድትጀምሩ ላነሳሳችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

31 Jan, 01:59

የልዩነቴ ዋጋ!

Dr. Eyob Mamo

30 Jan, 16:39

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

30 Jan, 15:50

ጥያቄ፡-

ሰላም ላንተ ይሁን ዶ/ር! በህይወቴ በጣም ከሚያስቸግሩኝ ነገሮች አንዱ ዉሳኔ መስጠት ነዉ፡፡ በተለይ እምቢ አይሆንም ማለት በጣም ነዉ እሚያስፈራኝ፡፡ ከዛ ቆይቶ እበሳጭና ዉስጤ ይረበሻል፡፡ በሆነው ባልሆነዉ እጨነቃለዉ፡፡ ይሄንን ካደረኩ ይሄ ቢሆንስ፤ እንዲህ ካደረኩ እንዲያ ቢሆንስ እያልኩ እጨነቃለዉ፡፡ ሌላዉ እራሴን ከሌሎች እያነፃፀርኩ ምንም እማልጠቅም ትንሽ ሰዉ እንደሆንኩ ይሰማኛል፡፡ self confidence በጣም ዝቅተኛ ነዉ፡፡ አመሰግናለሁ!!!

መልስ፡-

ሰዎች ለሚያቀርቡልን ጥያቄዎች በሙሉ “እሺ” ብንላቸውና ያንንም ብናደርግላቸው የሚመረጥ መንገድ ነው፡፡ እውነታው ግን ያንን አይፈቅድልም፡፡ በመጀመሪያ፣ ሰዎች የሚጠይቁን ነገር ሁሉ ትክክለኛና ሊደረግ የሚገባው ነገር ስላልሆነ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የሁሉንም የሰው ፍላጎት የማሟላት አቅሙም ስለሌለን ነው፡፡ በተጨማሪም፣ ለሁሉም ሰው ሁሉንም ነገር ለመሆን መሞከር የገንዘብ፣ የጊዜና የስሜት ከስረት ውስጥ ስለሚጨምረን ነው፡፡

ይህንን ዝንባሌ ለማቆም ከፈለክ በቅድሚያ ለምን እንደዚያ እንደምታደርግ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ተቀባይነትን የማጣት (Rejection) ፍርሃት ነው እንደዚያ የሚያደርገን፡፡ “እምቢ” ካልን ሰዎቹ እንዳይለዩን እንፈራለን፡፡

በተጨማሪም ሰዎች በእኛ ላይ ስላላቸው አመለካከት ከመጠን በላይ የምንጨነቅ ከሆነም “እምቢ” ስንላቸው ስለእኛ የሚያስቡት ነገር እንዳይበላሽ ስንል ሁል ጊዜ “እሺ” እንላለን፡፡ በልጅነት ከቤተሰብ ለተነገረን ነገር ሁሉ “እሺ” ካላልን ከባድ ቅጣት ስንቀበል ካደግንም የዚያን ተጽእኖ ይዘን ልናድግ እንችላለን፡፡

1. በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ላይ ስራ፡- ሰዎች ቢቀበሉህም ሆነ ባይቀበሉህም፣ ቢደሰቱብህም ሆነ ባይደሰቱብህም አንተ ሙሉ ሰው ነህ፡፡ ለተገቢው ነገር “እምቢ” ማለት ያለመቻል ሁኔታ በራሳችን ላይ ካለን የወረደ አመለካት ሊመነጭ ይችላል፡፡

2. “እምቢ” ስላካቸው አቋምህን የማያከብሩ ሰዎች እሺ ብትላቸውም ቀድሞውኑ አንተን የማያከብሩ ሰዎች ናቸው፡- የሚወዱህና የሚያከብሩህ ሰዎች አቋምህንም የማክበር ባህሪይ አላቸው፡፡ ያንን የማያደርጉ ሰዎች አይመጥኑህም፡፡

3. “የእምቢ” አባባል ብልሃቶችንና አነጋገሮችን አዳብር፡- አንዳንድ ጊዜ አንዴት “እምቢ” ማለት ስለማንችል ነው ለሁልም ነገር “እሺ” የምንለው፡፡ ፊት ለፊት እምቢታ፣ ምክንያት የመስጠት እምቢታ፣ “የላስብበት” እምቢታ . . . የምእቢታ መንገዱ ብዙ ነው (“የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” በተሰኘው መጽሐፌ ውስጥ በዝርዝር ተገልጸዋል)፡፡

መልካም ቀን ይሁንልህ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

30 Jan, 15:50

እምቢ አይሆንም ማለት በጣም ነዉ እሚያስፈራኝ፡፡ ከዛ ቆይቶ እበሳጭና ዉስጤ ይረበሻል፡፡

Dr. Eyob Mamo

30 Jan, 10:33

አካሄዳችንን እናመዛዝን!

• ከሰዎች ጋር የመፎካከራችን ልምምድ በበዛ ቁጥር የመበለጥና የመሸነፍ ስሜታች እየጨመረ ይሄዳል፡፡

• “የእኔ ነው” የምንለው ነገር በበዛ ቁጥር የምንሰረቀውና ተወሰደብን የምንለው ነገር እየጨመረ ይሄዳል፡፡

• የምንደገፍበት ሰው በበዛ ቁጥር የመገፋት ስሜትና የሰዎችን ትኩረት የመፈለግ ስሜታችን እየጨመረ ይሄዳል፡፡

• ከሰዎች የምንጠባበቀው ነገር በበዛ ቁጥር በሰዎች የመጎዳትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜታችን እየጨመረ ይሄዳል፡፡

• ተገቢ ላልሆኑ ነገሮች ለሰዎች “ክልከላ” ያለማድረግ ልምምዳችን በበዛ ቁጥር በሰዎች የቁጥጥር ሰለባ የመሆናችን ሁኔታ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ብናመዛዝነው ምን ይመስላችኋል?

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

30 Jan, 06:19

የሚጽፉ ሰዎች ሰባት ባህሪያት

1. በውስጣቸው የተረጋጉ ሰዎች ናቸው፡፡

2. ብቻቸውን የማሳለፍ አቅም ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡

3. በአእምሯቸው ከፍተኛ የሆነ አዳዲስ ነገር የመፍጠር አቅም ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡

4. ካለአግባብ ከመናገር በመቆጠብ ስሜታቸውን በጽሑፍ ማስተንፈስ ያወቁበት ሰዎች ናቸው፡፡

5. ሃሳባቸውን እና ተግባራቸውን የማደራጀት ብቃት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡

6. እነሱ በማያውቋቸው ሰዎች ላይ ሳይቀር ተጽእኗቸው ርቆ የሚሄድ ሰዎች ናቸው፡፡

7. የማንበብን ልማድ ለማዳበር ክፍት የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

30 Jan, 02:04

ካለምክ አይቀር ትልቅ ሕልም ይኑርህ!!!

“ቺክን ሱፕ ፎር ዘ ሶል” ("Chicken Soup For the Soul") ዝነኛ መጽሃፉ ላይ ጃክ ካንፊልድ (Jack Canfield) አንድን አስገራሚ እውነተኛ ታሪክ አስፍሯል፡፡ በካሊፎንያ ግዛት ውስጥ ሳን ሲድሮ በተሰኘ ስፍራ አንድ ሞንቴ ሮበርትስ (Monty Roberts) የተባለ ሰው ትልቅ ፈረስ የሚያረባበትና የሚያሰለጥንበት እርሻ አለው፡፡ የዚህ ባለሃብት ጅማሬ ድንቅ ታሪክን ያዘለ ነው፡፡

የሞንቴ አባት ከስፍራ ወደ ስፍራ እየተዘዋወረ ፈረሶችን በማሰልጠን የሚተዳደር ሰው ነበር፡፡ የሞንቴም ሕይወት ወዲህና ወዲያ ከሚዘዋወር አባቱ ጋር የተቆራኘ ስለነበር ትምህርት ቤቱን በማቋረጥ ደጋግሞ ከአባቱ ጋር ይዘዋወር ነበር፡፡

አንድ ጊዜ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ ሳለ አስተማሪያቸው ወደፊት መሆን የሚፈልጉትን ሕልማቸውን በጽሑፍ አቀናብረው እንዲመጡ የቤት ስራ ሰጣቸው፡፡

ሞንቴ ማታ እቤቱ በመግባት ሰባት ገጽ ሙሉ ወደፊት ማድረግና መሆን ስለሚፈልገው ነገር ጻፈ፡፡ ወደፊት የፈረስ እርባታና ማሰልጠኛ ያቀፈ ትልቅ እርሻ እንዲኖረው እንደሚፈልግና ያንንም ግቡን የሚገልጽ ጽሑፍ ነበር፡፡ ከዚህ ግቡ ጋር የእርሻውን ንድፍ በስእል መልክ በማስፈር ለተመልካቹ ግልጽ በሆነ መልኩ አስፍሮት ነበር፡፡

ከ80 ሄክታር ያላነሰ ስፍራን አልሞ ነበር፡፡ ይህ ሕልም ቀድሞውኑ በውስጡ ሲብላላ የነበረ ጉዳይ ስለነበረ ጊዜን ሰጥቶትና በጥራት በመስራት በሚቀጥለው ቀን ለአስተማሪ አስረከበው፡፡

ከሁለት ቀናት በኋላ ውጤት የያዘውን ወረቀቱን አገኘ፡፡ በወረቀቱ ፊት ለፊት ገጽ ላይ በቀይ “F” ተጽፎበታል፡፡ ከውጤቱ በታች ደግሞ፣ “ክፍለ ጊዜው ሲያልቅ ወደ ኋላ ቀርተህ አነጋግረኝ” ይላል፡፡

ሕልመኛው ሞንቴ ከክፍለ ጊዜው በኋላ አስተማሪውን ለማግኘት ሄደ፡፡ ገና አስተማሪውን እንዳገኘው፣ “F ያገኘሁት ለምንድን ነው?” በማለት ጠየቀው፡፡

አስተማሪውም በመመለስ፣ “እንዳንተ ላለ ወጣት ይህ ሕልም ትንሽ ቅጥ ያጣ ነው፡፡ ገንዘብ የለህም፣ ኑሮን ለመግፋት ወዲህና ወዲያ በመዞር የሚሰራ ቤተሰብ ነው ያለህ፡፡ ባጭሩ ምንም ነገር የለህም፡፡ የፈረስ ማርቢያ እርሻ ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ መሬት መግዛት አለብህ፣ እርባታውን ለመጀመር ቅድመ ክፍያ ያስፈልግሃል፣ ለእርባታ የሚሆኑ ፈረሶችን ለማግኘት ገንዘብ ይጠይቅሃል” በማለት ሕልሙ ላይ መድረስ የማይችልበትን የምክንያት አይነት ደረደረለት፡፡

በመጨመርም፣ “ይህንን ምኞትህን እውን ልታደርግበት የምትችልበት ምንም መንገድ ሊኖር አይችልም፡፡ ቀለል ያለ ግብን ጽፈህ ከመጣህ የሰጠሁህን ውጠት አሻሽልልሃለሁ” በማለት ወረቀቱን ሰጠው፡፡

ሞንቴ እቤቱ በመሄድ አስተማሪው የነገረውን ነገር ለረጅም ጊዜ ቁጭ ብሉ በጣም አሰበበት፡፡ አባቱንም ሃሳብ እንዲሰጠው ጠየቀው፡፡

የአባቱ መልስ፣ “ልጄ ሆይ፣ በጉዳዩ ላይ የራስህን አመለካከት መወሰን አለብህ፡፡ ሆኖም፣ ይህ የምትወስነው ውሳኔ በጣም አስፈላጊ ውሳኔ እንደሆነ አስባለሁ” የሚል ነበር፡፡

ሞንቴ በነገሩ ላይ ለአንድ ሳምንት ብዙ ካሰበበት በኋላ ያንኑ ወረቀት ለአስተማሪው መለሰለት፡፡ በወረቀቱ ላይ እንዲህ ሲል ጽፎ ነበር፣ “ለቤት ስራዬ የሰጠኸኝን የ F ውጤት ከአንተ ጋር አቆየው፣ እኔ ከሕልሜ ጋር እቆያለሁ”፡፡

ይህ ታሪክ ከተከሰተ ከብዙ አመታት በኋላ በአሁን ጊዜ ሞንቴ ሮበርትስ በ80 ሄክታር ላይ ያረፈ ትልቅ የፈረስ ማርቢያ እርሻ አለው፡፡ በዚያም እርሻ ውስጥ 370 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የግል መኖሪያ አለው፡፡ ያንን F ያገኘበትንና ሕልሙ የተጻፈበትን ወረቀት በፍሬም አድርጎ በሳሎን ቤቱ ግድግዳ ላይ ሰቅሎታል፡፡ ሞንቴ በውስጡ የነበረውንና ከልቡ ያመነበትን ሕልም ከአስተማሪው የግል አመለካከት የተነሳ ለመጣል እምቢ ያለ ሰው ነበር፡፡

ከላይ የተጠቀሰው ሞንቴ እና በአለማችን የሚገኙ ሌሎች በርካታ እሱን መሰል ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎችና ሰዎች፣ “ከዚህ ማለፍ አትችሉም” በመባል የተሰመረባቸውን የገደብ መስመር አልፎ ለመሄድ የቆረጡ ሰዎች ናቸው፡፡

ሰዎች ከራሳቸው እይታ በመነሳት ማድረግ ወይም መሆን የምንችለውንና የማንችለውን የመገመት መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ በዚያ ገደብ ውስጥ የመቆየትና ያለመቆየት ውሳኔው ያለው ግን እኛው ጋር ነው፡፡

“አይቻልም” ሲሉን በውስጣችን “ይቻላል” በማለት፤ “ያንተ ነገር አከተመ” ሲሉን ለራሳችን “የእኔ ነገር አላከተመም” እያልን በመንገር ወደፊት የመገስገስ ሙሉ መብትና ብቃቱም አለን፡፡ በሌላ አባባል፣ ሊገታን የሚችል ገደብ እኛው ያበጀነው ገደብ ነው፡፡

የይቻላል እይታ ማለት በአንድ ሙከራ ሳንገታና ሰዎችና ሁኔታዎች በሚሰጡን “አትችልም” የሚል መልእክት ሳንገደብ ወደ ፊት ለመገስገስና የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ አላማችን ጋር ለመድረስ መትጋት ማለት ነው፡፡ ሆኖም፣ አብዛኛውን ጊዜ አንድን ነገር ለማከናወን ሁሉ ነገር የተሟላልን አይነት ሰዎች መሆን እንዳለብን እንድናስብና ቀድሞውኑ ተስፋ ቆርጠን እንቀመጣለን፡፡

በሕይወታችን ግን ስኬታማ ለመሆን ሁሉ ነገር የተሟላ መሆን የለበትም፤ ያመንንበትን መልካም ዓላማ ለመከተል ውስጣችን ሙሉ መሆን ነው ያለበት፡፡ ይቻላል!!!

(እይታ ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

Dr. Eyob Mamo

30 Jan, 01:59

ካለምክ አይቀር ትልቅ ሕልም ይኑርህ!!!

Dr. Eyob Mamo

29 Jan, 15:33

ቆም በሉ!

የምትሄዱበት አቅጣጫ ትክክለኛ የመሆኑን ጉዳይ ከተጠራጠራችሁ፣ ርቃችሁ ከመሄዳችሁ በፊት ቆም በሉ፡፡

የምትሄዱበት አቅጣጫ ማለት፣ የፍቅር ግንኑነት፣ የአዲስ ስራ ስምሪት እና ሌሎች አዳዲስ ምርጫና ውሳኔዎችን አመልካች ነው፡፡

ቆም ስትሉ . . .

1. የውስጥ ሃሳባችሁን በማሰላሰል ለማወቅና ለማጣራት ጊዜ ታገኛላችሁ

2. በጉዳዩ ላይ ልምድና እውቀት ያለውን ሰው ምክር የማግኘት ጊዜ ታገኛላችሁ

3. ጊዜ እና ቆይታ ብቻ የሚፋታው ነገር መስመር እንዲይዝ ጊዜ ታገኛላችሁ

ጥቆማዎች

• የግራ መጋባት ስሜት

• የውስጥ መረበሽና አለመረጋጋት

• ማታ እንቅልፍ ማጣት ወይም ከተኙ በኋላ በድንገት በመንቃት እንደገና ለመተኛት አለመቻል

ግድ የላችሁም፣ ቆም በሉ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

29 Jan, 07:40

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

29 Jan, 02:00

ስህተት እና ስኬት

“ሰዎች በእናንተ እንዲደነቁና እንዲገረሙ ከፈለጋችሁ ስለ ስኬታችሁ ብቻ ንገሯቸው፡፡ በሰዎች ላይ ተጽእኖ ማምጣት ከፈለጋችሁ ግን የሰራችኋቸውን ስህተቶችና እነዚያን ስህተቶች እንዴት አድርጋችሁ በማረም እዚህ ደረጃ እንደደረሳችሁ ንገሯቸው” (ካልታወቀ ምንጭ)፡፡

• ስህተት የሌለበት ስኬት ተፈልጎ አይገኝም፡፡

• ሰዎች ከስኬታችን ከሚማሩት በበለጠ ሁኔታ ተምረንባቸው ካረምናቸው ስህተቶቻችን ይማራሉ፡፡

• ስኬታችንን ብቻ ሳይሆን ስህተታችንንም ለሰዎች በማጋራት ማስተማር “ሰው” የመሆናችን ምልክት ነው፡፡

• ስህተት የሚያሳፍረው ካላረምነውና አሁንም ደጋግመን የምንሰራው ከሆነ ነው፡፡

• የታረመ ስህተት በሌላኛው ስሙ ሲጠራ፣ “ለእኛም ሆነ ለሌሎች አስተማሪ የሆነ ልምምድ” ይባላል፡፡

• ሞክራችሁ ስትሳሳቱ ከሚደርስባችሁ ችግር የበለጠው ችግር ስህተትን ፈርታችሁ ካለመሞከር የሚመጣው ችግር ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

28 Jan, 08:29

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

28 Jan, 06:27

አዲስ መጽሐፍ በቅርብ ቀን ይጠብቁ!

New Book Coming Soon
!

“የተደራጀ ሕይወት” (“Organized Life”)

የግል ሕይወታችንን እንዴት ማደራጀት እንደሚቻል መንገዱን የሚያመላክታችሁ አዲስ እይታ!

በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

በጥሩ ዋጋ ለማግኘት ከፈለጋች በዚህ ስልክ መደወል ትችላላችሁ - 0947930369 (ሄኖክ)

Dr. Eyob Mamo

28 Jan, 02:00

የአስተዳደጋችን ተጽእኖ

ሁላችንም ምንም እንኳን በቃላት አቀነባብረን ማስረዳት ባንችልም፣ በልምምዳችን የምናውቀውን እውነታ የስነ-ልቦና አዋቂዎች ሲያስታውሱን፣ አንድ ሰው በኑሮ ላይ የሚኖረውን እይታ የሚቀርጸው ዋነኛ ሁኔታ የልጅነት አስተዳደጉ እንደሆነ ይጠቁሙናል፡፡

በሌላ አባባል ልጅ ሲያይና ሲሰማ ያደገውን አይነት እይታ ነው አዳብሮ የሚያድገው፤ የሚኖርባት አለምመ እንደዚያ ትመስለዋለችና፡፡ እይታና አመለካከት ከልጅነት ጀምሮ ቀስ በቀስ በውስጣችን የሚመሰረትና የሚደላደል ጉዳይ ነው፡፡

ለምሳሌ፡-

• ልጅ ጥላቻ በሞላበት አካባቢ ካደገ፣ ጸበኝነትን ይማራል፡፡

• ልጅ ሃፍረት በነገሰበት አካባቢ ካደገ፣ የጥፋተኝነት ስሜትን ይማራል፡፡

• ልጅ ምስጋና በተለመደበት አካባቢ ካደገ፣ ሰዎችን ማድነቅና ማመስገን ይማራል፡፡

• ልጅ በሚያበረታታ አካባቢ ካደገ፣ ድፍረትን ይማራል፡፡

• ልጅ አንድ ሰው ሌላውን በሚገነዘብበት አካበቢ ካደገ፣ ትእግስትን ይማራል፡፡

• ልጅ እውነተኛ ፍርድ ባለበት አካባቢ ካደገ፣ ፍትሃዊነትን ይማራል፡፡

• ልጅ ከአደጋ ነጻ በሆነ አካባቢ ካደገ፣ መታመንን ይማራል፡፡

• ልጅ ድጋፍን በሚያገኝበት አካባቢ ካደገ፣ በራስ መተማመንን ይማራል፡፡

• ልጅ ተቀባይነትና ጓደኝነት ባለበት አካባቢ ካደገ፣ በሰዎች ውስጥ ፍቅርን ማየትን ይማራል፡፡

ዛሬ በወጣትነት እድሜያችሁም ሆነ ከዚያም እድሜ አለፍ ብላች ወደ ስራውና ወደ ትዳሩ አለም ስትገቡ የሚያታግሏችሁ አንዳንድ ስሜቶች ምናልባት የአስተዳደጋችሁ ተጽእኖ እንደሆነ ጥርጥራችሁ ታውቁ ይሆን?

በልጅነት፣ በተለይም ከ0 እስከ 7 ዓመታችን የንጽረተ-ዓለምን የመቅረጫ (formative age) አመታት ያሳለፍናቸው ሁኔታዎች ካመጡበን የምልከታም ሆነ የስነ-ልቦና ቀውስ ካልወጣን . . .

• የራሳችን ሕይወት የተዘባረቀና ዓላማ ቢስ ይሆናል፤

• ለቅርብ ወዳጆችም ሆነ ጓደኞች የችግር ምንጭ እንደሆንን እንኖራን፤

• የግልም ሆነ የቅጥር ስራ መስካችንን ያበላሸዋል፤

• የፍቅር፣ አልፎም የትዳር ግንኙነትን ያደፈርሳል፤ . . . ጣጣው ብዙ ነው!!!

መፍቴ ለማምጣት . . .

1. ያለብንን ችግር ባለመካድና ባለመሸፋን አምነን መቀበል፡፡

2. ላለብን ችግር መንስእና ምክንያት እንደሆኑ የምናስባቸውን ሰዎች ከመውቀስና በእነሱ ላይ ቂም ከመያዝን መቆጠብ፡፡

3. ችግሩ በጊዜ ካልተፈታ በዛሬውም ሆነ በወደፊት ሕይወታችን ላይ የሚያመጣውን አጉል ተጽእኖ በሚገባ መገንበዝ፡፡

4. ከውልደት በኋላ የመጣ ማንኛውም ችግር በእድገትና በብስለት ሊቀረፍ እንሚችል በሙሉ ልብ ማመን፡፡

5. ችግሩን ለመቅረፍ ሆን ተብሎ የታሰበበትና በእቅድ የታገዘ እርምጃ መውሰድ፡፡

6. በራሳችንን መቅረፍ ያልቻልነውን ችግር የሌሎችን እርዳታ መፈለግና ድጋፍን ማግኘት፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

28 Jan, 01:59

የአስተዳደጋችን ተጽእኖ

Dr. Eyob Mamo

27 Jan, 13:59

መጽሐፍ አጻጻፍ ደረጃ በደረጃ!

ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን በጽሑፍ ለሌሎች የማጋራት ፍላጎቱ አላቸው፣ ነገር ግን ከየት ጀምረው ወደ የት እንደሚወስዱት ስለማያውቁት ብቻ ቁጭ ብለዋል፡፡

ይህ ሃሳብ እንደሚመለከታችሁ ካሰባችሁ ከዚህ በታች ያሰፈርኳቸውን ደረጃዎች ከተመለከታችሁ በኋላ የቱ ደረጃ ላይ እንዳላችሁ ለመለየት ሞክሩ፡፡

1. አንዳንድ ሰዎች የመጻፍ ፍላጎትና የሚጽፉበት ዋና ርእሰ-ጉዳይ ብቻ ነው ያላቸው፡፡ ከዚያ ባለፈ ምን እንደሚያደርጉም አያውቁትም፡፡

2. አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት ሃሳብ ሲመጣላቸው እዚህም እዚያም በመጻፍ ያጠራቀሟቸው ጽሑፎች ቢኖሩም እንዴት ወደ አንድ ወጥ መጽሐፍ እንደሚሰበስቡት አያውቁበትም፡፡

3. አንዳንድ ሰዎች ሃሳባቸውንም በሚገባ አውቀውና በየተራ ጽፈውት ሳሉ፣ ፍሰቱ፣ ከአንዱ ወደሌላኛው ሽግግሩ፣ አወቃቀሩና መልክ የመያዙ ጉዳይ ግራ ገብቷቸው ቁጭ አድርገውታል፡፡

4. አንዳንድ ሰዎች ምንም እንኳን ሙሉ ለሙሉ በመጽሐፍ መለክ እንደጻፉት ቢያውቁም ገጾቹን (page layout)፣ ሽፋኑን (cover design) እና አጠቃላይ የመጽሐፉን ሁኔታ ለሕትመት በሚደርስ መልኩ ማሻገር ግር ይላቸዋል፡፡

መጽሐፍን በመጻፍና በማሳተም አቅጣጫ ከላይ ከተጠቀሱት የትኛው ደረጃ ላይ እንዳላችሁ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚያም ወደሚቀጥለው ደረጃ እንዴት አልፋችሁ እንደምትሄዱ መገንዘብ፣ አስፈላጊም ከሆነ መሰልጠን የግድ ነው፡፡

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

27 Jan, 13:59

መጽሐፍ አጻጻፍ ደረጃ በደረጃ!

Dr. Eyob Mamo

27 Jan, 07:02

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

27 Jan, 02:03

አንገብጋቢ ጥያቄ አለኝ!

ስለ እናንተ ከሌሎች ሰዎች ከሰሙት ነገር ብቻ ተነስተው በእናነተ ጎን ያለውን እውነታ እና ስሜታችሁን ከእናንተ ለመስማት ጊዜን ሳይሰጡ በእናነት ላይ መጥፎ አመለካከትን ስለሚይዙና ወሬን ስሚያናፍሱ ሰዎች ለምን ትጨነቃላችሁ?

እናንተ ለእነሱ በሆናችሁላቸውና ባደረጋችሁላቸው መጠን ምላሽ የመስጠት ፍላጎቱም ሆነ ጥረቱ ስለሌላቸው ሰዎች ስለምን ትጨነቃላችሁ?

ሁል ጊዜ እናንተ እነሱን ካልፈለጋችኋቸው ስለማይፈልጓችሁ፣ ካልደወላችሁላቸውም ሆነ Chat የማድረግ ሙከራ ስታደርጉ ትዝም ስለማትሏቸው ሰዎች ለምን ትወጣጠራላችሁ?

ጥፋቱ የእናንተም ሆነ የእነሱ፣ ባጠፋችሁትም ሆነ ባላጠፋችሁት ነገር ዘወትር ይቅርታ ጠያቂዎቹ እናንት ብቻ ስለሆናችሁበት ሰው በመጨነቅ እንቅልፍ የምታጡት ለምንድን ነው?

ከእናንተ ጋር ያላቸውን ግንኙነት መቀጠል እንደማይፈልጉ በሁኔታቸው፣ በአንደበታቸው ወይም ደግሞ በሁለቱም እየገለጹላችሁ ሳለ ቀን-ተሌት ስለእነሱ ስታወጡና ስታወርዱ መማር፣ መስራትና መተኛት እስከማትች ድረስ ከራሳችሁ የምትለያዩት ለምንድን ነው?

ለምንድን ነው ውስጣችሁን ጠንከር የማታደርጉት?

ለምንድን ነው በራሳችሁ መቆም እንደማትችሉ ራሳችሁን ያሳመናችሁት?

ለምንድን ነው የራሳችሁ አቋም፣ ዓላማና ጥንካሬ የማይኖራችሁ?

ራስን ያለመቀበል ስሜት ይሆን?

የዝቅተኝት ስሜት ይሆን?

የመገፋት ፍርሃት ይሆን?

ብቻ የመቅረት ስጋት ይሆን?

የከዚህ በፊቱ ያልዳነ ቁስል ይሆን?

. . . ወይስ ሌላ ይሆን?

ከትንሽ ጊዜ በኋላ ስትባንኑ ዓመቶቻችሁ የት እንደገቡ ሳትጸጸቱና የማይቀለበስ መራራነት ውስጥ ሳትገቡ የምር አስቡበት!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

27 Jan, 01:59

አንገብጋቢ ጥያቄ አለኝ!

Dr. Eyob Mamo

26 Jan, 10:13

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

26 Jan, 05:36

ቀለማችን ለዩ!

አንድ ወጥ ቀለም ይኑራችሁ!

• ክልከላ ያላደረጋችሁበት ነገር፣ ይሁንታ እንደሰጣችሁት ጠቋሚ ነው፡፡

• ያልተቃወማችሁትን ነገር፣ እንደደገፋችሁት ጠቋሚ ነው፡፡

• የግል አመለካከታችሁን ያልገለጻችሁበት ነገር፣ በሃሳቡ እንደተስማማችሁ ጠቋሚ ነው፡፡

• ምርጫና ውሳኔ ያላደረጋችሁበት ነገር፣ ያለመምረጥና ያመወሰን ምርጫና ውሳኔ የማድረጋችሁ ጠቋሚ ነው፡፡

• ወደ ፊት ለመራመድ አለማቀዳችሁና አለመንቀሳቀሳችሁ፣ ያላችሁበት ቦታና ሁኔታ እንደተመቻችሁ ጠቋሚ ነው፡፡

• ፍቅራችሁን የማትገልጹበት ግንኙነት፣ ግንኙነቱ ቢቀጥልም ሆነ ባይቀጥል ግድ እንደሌላችሁ ጠቋሚ ነው፡፡

የምትፈልጉትንና የማትፈልጉትን ለዩና አንድ መልክ ይዛችሁ የመኖርን፣ ያንንም በግለጽ የማሳየትን ጉዞ ጀምሩ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

25 Jan, 18:28

የሕልማችሁ ጉዳይ!

ወደመኝታ ሄዳችሁ የሌሊቱን ሕልም ከማለማችሁ በፊት፣ ቀን ስታልሙ የዋላችሁትን የሕይወታችሁን ሕልም የምትተገብሩበትን እቅድ ማውጣታችሁን አትዘንጉ፡፡

የሰላም እንቅልፍ ለሁላችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

25 Jan, 08:20

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

24 Jan, 17:02

ምናልባት!

ሰዎች ችግራቸውን የሚነግሯችሁ ከሆነ፣ ፈጣሪ የሰዎችን ምስጢር እንደምትጠብቁ እናንተን የማመኑ ምልክቱ ሊሆን ስለሚችል ተጠንቀቁላቸው!

ሰዎች ጥፋታችሁን እያዩ አሁን የማይለወጡባችሁ ከሆነ፣ ፈጣሪ ከስህተታችሁ ተመልሳችሁ ሁለተኛ እድል እንድታገኙ መንገዱን የማመቻቸቱ ምልክቱ ሊሆን ስለሚችል እድሉን ተጠቀሙበት!

ሰዎችን ደጋግማችሁ ታግሳችኋቸው አሁን የስነ-ልቦና ወይም አካላዊ ጥቃት በማድረሳቸው እየቀጠሉ ከሆነ፣ ፈጣሪ ለከፋ አደጋ ሳትጋለጡ ከዚያ ሰው ዘወር በመራቅ ራሳችሁን እንድትጠብቁ ጊዜን እየገዛላችሁ እንደሆነ ምልክቱ ሊሆን ስለሚችል ራቅ በሉ!

ሰዎችን አምናችኋቸው በተደጋጋሚ ታማኝነታቸውን እያጎደሉ ከሆነ፣ ምናልባት ፈጣሪ ከመጎዳታችሁ በፊት አመኔታችሁን ሚዛናዊ እንድታደርጉ የማስታወሱ ምልክቱ ሊሆን ይችላልና ጠንቀቅ በሉ!

ሰዎች ሁሉ ለተወሰነ ጊዜ ከቀረቧችሁ በኋላ በድንገት የሚለይዋችሁ ከሆነ፣ ምናልባት ፈጣሪ ማስተካከል ያለባችሁ የባህሪይ ጽንፍ እንዳባችሁ የመጠቆሙ ምልክት ሊሆን ስለሚችል ራሳችን ተመልከቱና መለስ በሉ!

መልካም ምሽት! መልካም እንቅልፍ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

24 Jan, 15:07

ነቃ በሉ!

ወጣቶች፡-

አሁን ያላችሁን በፈለጋችሁበት ጊዜ ተነስታችሁ የፈለጋችሁበት ቦታ የመሄድ፣ የማለም፣ የማቀድ፣ ተሯሩጦ የመስራት፣ የመማር፣ የመጫወት፣ ከባድ ነገር የመጋፈጥ (Risk Taking) . . . አቅምም ሆነ ፍላጎት የማይኖራችሁ ጊዜ በምን ያህል ፍጥነት እንደሚመጣና ይህንን ጊዜ ብትናፍቁትም ተመልሳችሁ የማታገኙበት ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ ላሳስባችሁ፡፡ በሆነ ባልሆነ አትጨናነቁ፣ ውጡና ሞክሩ፣ ተጫወቱ፣ በጤናማ ልምምዶች ተደሰቱ፣ ለማይረባ ነገር ራሳችሁን አሳልፋች አትስጡ፡፡

ወላጆች፡-

ዛሬ የሚጮሁት፣ የሚረብሹት፣ የሚጫወቱት፣ የሚያስቸግሩት፣ ቤቱን የሚያቆሽሹት፣ የሚያደክሟችሁ . . . ልጆቻችሁ አድገው ብትመኙም እነሱን በዚህ መልኩ የማታገኙበት ቀን በምን ያህል ፍጥነት እንደሚደርስና ብዙም ሩቅ እንዳልሆነ ላስታውሳችሁ፡፡ ነገር አታካብዱ፣ አትነጫነጩ፣ በሆነ ባልሆነ ልጆችሁን በመቆጣት አታመርሯቸው፣ ይህችን የልጅነታቸውን ጊዜ ተደሰቱባት፣ አብራችኋቸው ተጫወቱ፣ ልጆቹም ልጆች እንዲሆኑ ፍቀዱላቸው፡፡፡፡

ነቃ በሉ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

24 Jan, 08:03

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

24 Jan, 02:02

ከአማካኝ ሰዎች ቀጠና አልፋችሁ ሂዱ!

ለአማካኝ (Average) ነገር ስትሰክኑ አማካኝ (Average) ሕይወት ትኖራላችሁ፡፡ ከአማካኙ ባሻገር አልፋችሁ ለመሄድ ሰትወስኑ የላቀ ሕይወት ውስጥ ትገባላችሁ፡፡

• አማካኝ ሰዎች ከሚነሱበት ሰዓት በፊት በመነሳት ቀናችሁን ካልጀመራችሁ፣ አማካኝ የሕይወት ሂደት ይዛችሁ ከዓመት ወደ ዓመት ትሸጋገራላችሁ፡፡

• አማካኝ ሰዎች ካላቸው ዲሲፕሊን የበለጠ ዲሲፕሊን በማዳበር በየእለቱ የምታደጓቸው ድግግሞሾች ከሌሏችሁ አማካኝ ሰዎች ያገኙትን ውጤት ታገኛላችሁ፡፡

• አማካኝ ሰዎች ካላቸው ትኩረት በላቀ መልኩ በሕይወታችሁ ራእይና ዓላማ ላይ ካላተኮራችሁ አማካኝ ሰዎች ለሰከኑት ተርታ ሕይወት ሰክናችሁ ትቀራላችሁ፡፡

• አማካኝ ሰዎች ካላቸው ቁርጠኝነት የጠነከረ ቁርጠኝነት ከሌላችሁ አማካኝ ሰዎች የቆሙት ደረጃ ትቆማላች፡፡

ዛሬውኑ አማካኝ ሕይወት ላለመኖር ውስኑ፡፡ ከደካማው ወደ አማካኙ፣ ከአማካኙ ደግሞ ወደ ጥሩው፣ ከጥሩው ወደ ላቀው ካለማቋረጥ ተንቀሳቀሱ፡፡

ይህንን ለመለማመድ . . .

አንድን ነገር ካለማቋረጥ ለአመታት ማድረግ፡፡ ብዙ ነገሮች በድንገተኛ መነቃቃትና በዘመቻ ይጀመሩና ቀስ በቀስ ይቆማሉ፡፡

አንድን ነገር በተመሳሳይ ሁኔታ የጥራት ደረጃውን በማሳደግ ደጋግሞ ማድረግ፡፡ ብዙ ነገሮች ሲጀመሩ ድንቅና ውብ፣ እየቆዩ ሲሄዱ ግን ጥራታቸው እየወረደ ይሄዳሉ፡፡

አንድን ነገር ሌሎች ከደረሱበት ደረጃ አንጻር ሳይሆን ካወጣው ከፍ ያለ ግብ አንጻር መተግባር፡፡ ብዙ ነገሮች የሚጀመሩትና የሚቀጥት ከሌሎች በለጥ ብሎ ለመገኘት ስለሆነ የጥራት ደረጃው እንዳካባቢው ተለዋዋጭ ይሆናል፡፡

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

23 Jan, 16:32

ሙሉ ሰው ናችሁ!

በዚህ ምሽት፣ ጥሩ ያልሆነው ስሜታችሁ እያለ፣ በዙሪያችሁ ያው አስቸጋሪው ሰው እያለ፣ ያልተፈታው ችግራችሁ እያለ . . .

• ወደፊት ትቀጥላላችሁ!

• ሕይወትን በማጣጣም ትኖራላችሁ!

• በሰላም ተኝታችሁ ነገ ደግሞ ቀና ብላችሁ ትውላላችሁ!

እንጂ በፍጹም አንገታችሁን ደፍታችሁ፣ ተደብታችሁ፣ ግራ ተጋብታችሁ፣ ተጨናንቃችሁ አትኖሩም፡፡

ሁኔታችሁ ቢጎድልም ፈጣሪ የሰጣችሁ ሰው የመሆናችሁና የማንነታችሁ እውነታ አሁንም ያው ነው፣ አልተለወጠም፣ ሙሉ ነው!

መልካም አዳር የተወደዳችሁ የሃገሬ ሰዎች!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

23 Jan, 08:09

መቆጣጠር የምትችሉትና የማትችሉት

ትኩረታችሁን መቆጣጠር ከማትችሉት ነገር ላይ አንሱና መቆጣጠር በምትችሉት ነገር ላይ አድርጉ

• ሰዎች ስለ እናንተ የሚያስቡትን መቆጣጠር አትችሉም፡፡ እናንተ የምታስቡትን የራሳችሁን ሃሳብ ግን መቆጣጠር ትችላላችሁና እሱ ላይ አተኩሩ፡፡

• ሰዎች የሚሰማቸውንና የሚገልጹትን ስሜት መቆጣጠር አትችሉም፡፡ እናንተ በዚያ ስሜታቸው ምክንያት የሚሰማችሁን ስሜትና ምላሻችሁን ግን መቆጣጠር ትችላላችሁና እሱ ላይ አተኩሩ፡፡

• በአካባባቢያችሁ በድንገት ሊሆን የሚችለውን ነገር መቆጣጠር አትችሉም፡፡ ለማንኛውም ነገር የተዘጋጀ ማንነትና ጠንካራነትን የማዳበርን ሁኔታ ግን መቆጣጠር ትችላላችሁና እሱ ላይ አተኩሩ፡፡

• በአካባቢያችሁ የሚወራውን ወሬ መቆጣጠር አትችሉም፡፡ መስማት የምትፈልጉትንና የማትፈልጉትን እንዲሁም የትኛውን እንደምታምኑና እንደማታምኑ ግን መቆጣጠር ትችላላችሁና እሱ ላይ አተኩሩ፡፡

እነዚህንና መሰል ሁኔታዎችን በሚገባ ስትገነዘቡ . . .

ከብዙ የስሜት ቀውስ ራሳችሁን ትጠብቃላችሁ፡፡

ብዙ የስሜት አቅም (energy) ትቆጥባላችሁ፡፡

ከሚኖራችሁ የትኩት መሰብሰብ የተነሳ ብዙ ተግባር ታከናውናላችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

23 Jan, 05:42

የሚጽፉ ሰዎች ሰባት ባህሪያት

1. በውስጣቸው የተረጋጉ ሰዎች ናቸው፡፡

2. ብቻቸውን የማሳለፍ አቅም ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡

3. በአእምሯቸው ከፍተኛ የሆነ አዳዲስ ነገር የመፍጠር አቅም ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡

4. ካለአግባብ ከመናገር በመቆጠብ ስሜታቸውን በጽሑፍ ማስተንፈስ ያወቁበት ሰዎች ናቸው፡፡

5. ሃሳባቸውን እና ተግባራቸውን የማደራጀት ብቃት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡

6. እነሱ በማያውቋቸው ሰዎች ላይ ሳይቀር ተጽእኗቸው ርቆ የሚሄድ ሰዎች ናቸው፡፡

7. የማንበብን ልማድ ለማዳበር ክፍት የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

የስልጠናውን መረጃ ቀደም ሲል ባስተላለፍኩት ፖስት ላይ ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ መረጃ በሚከተለው አድራሻ inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

23 Jan, 02:00

ሶስቱ የወዳጅነት ጠንቆች (ክፍል ሶስት)

የመጠበቅ (Expectation) ንክኪ

ባለፉት ሁለት ቀናት “ፖስቶቼ” “ሶስቱ የወዳጅነት ጠንቆች” በሚል ሃሳብ ስር የመጀመሪያውን ማለትም፣ “የገንዘብ ንክኪ” የተሰኘው እና ሁለተኛውን “የምስጢር ንክኪ” የተሰኙትን ሃሳቦች አጋርቻችኋለሁ፡፡

ለማስታወስ ያህል፡ በአካባቢያችሁ የሚገኙ ሰዎች ከእናንተ ጋር ያላቸው ቅርበት የተለያየ ደረጃ እንዳለው ግልጽ ነው፡፡ የልብ ወዳጅ፣ የቅርብ ጓደኛ፣ የስራ ባልደረባ፣ የየእለት ውሏችን የሚያገናኘን ሰው፣ የሩቅ ትውውቅ . . . እያለ ግንኙነቱ ይጠብቃል፣ ይላላል፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች የራሳቸው የሆነ ባህሪይ ስላላቸው አያያዛቸውን በሚገባ ካላወቅንበት ለተለያዩ ማሕበራዊና የስሜት ቀውሶች ያጋልጡናል፡፡

የዛሬው ሃሳብ፣ “የመጠበቅ (Expectation) ንክኪ” የተሰኘ ይሆናል፡፡

ከሰዎች ጋር የቅርብ ወዳጅነት ስትመሰርቱ ከሚለወጡ ሁኔታዎች አንዱ እናንተ ከእነሱ የምትጠብቁት፣ እነሱ ደግሞ ከእናንት የሚጠብቁት ነገር የመጨመሩ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ ቅርበት የተነሳ የምንጠብቅን ነገር ካላገኘን ደግሞ ቅሬታ ይፈጠራል፡፡ በተለይም ደግሞ አንዱ የሚጠብቀው ነገር ሲበዛና ያንን ካላገኘ፣ ስስ የመሆንና ቅር የመሰኘት ባህሪይ ካለበት ሁኔታውን ያከብደዋል፡፡

ይህንን የወዳጅነት ጠንቅ በአግባቡ ለመያዝ ያሉን አማራጮች ሁለት ናቸው፡-

አንደኛውና የተሻለው ምርጫ:-

በመጀመሪያ በቅርብ ወዳጅነት ደረጃ የምንቀርባቸውን ሰዎች በጥንቃቄ ማጤን ነው፡፡ ያንን የቤት ስራችንን በሚገባ ከሰራንና ሰዎችን የቅርብ ወዳጅ ወይም ጓደኛ ካደረግናቸው በኋለ ግን ፍጹም አመኔታ በማዳበር ሁለታችንም የምንችለውን ሁሉ እንደምናደርግ መግባባትን መፍጠረና በቀረው ነገር መተማመን ነው፡፡ ይህ አይነቱ ግንኙነት እጅግ የበሰሉ ሰዎች የሚለማመዱት አይነት ግንኙነት ነው፡፡

ሁለተኛው አማራጭ:-

ግልጽ በሆነ መልኩ አንዱ የሌላኛውን የቀይ መስር (Boundary) ሊያከብር እንደሚገባው መወያየት ነው፡፡ በእርግጥ በቅርብ ወዳጅነት ውስጥ ይህ አይነቱ መደበኛ (Formal) የሆነ የመነጋገርን ሁኔታ ማምጣት ከባድ ሊሆንና ውጥረትን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ሆኖም፣ የመጀመሪያው ምርጫ ካልሰራ ይህኛውን እንደ አማራጭ መጠቀም ይቻላል፡፡ የቅርብ ወዳጆችንን የግል የቀይ መስመራችንን (Boundary) እንደጣሱ ሲሰማን በትህትና እና በግልጽነት ስለሁኔታው ማሳወቅን መለማመድ እንችላለን፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እኛም የወዳጃችንን የቀይ መስመር (Boundary) እንደጣስን ሲገባን ወይም ያኛው ወገን ሲያሳውቀን ያንን የማክበርን ጨዋነት መለማመድ ነው፡፡

ተፈጸመ!

የተወደዳችሁ ናችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

23 Jan, 01:59

ሶስቱ የወዳጅነት ጠንቆች (ክፍል ሶስት)

የመጠበቅ (Expectation) ንክኪ

Dr. Eyob Mamo

22 Jan, 17:49

አይኖቻችሁን ጨፍኑና . . . !

ዛሬ ከመተኛታችሁ በፊት (ካልቻላችሁ ጠዋት ከቤት ከመውጣታችሁ በፊት) ለተወሰኑ ደቂቃዎች አይኖቻችሁን ጨፍኑና የሚከተሉትን ሃሳቦች ለማሰብና በእውነተኛነትና በሃቅ ለመተግበር ሞክሩ . . .

1. ውስጤ የሚያውቀውና የሚነግረኝ ማቆም ያለብኝ መጥፎ ተግባር ምንድን ነው?

2. ውስጤ የሚያውቀውና የሚያመላክተኝ መለየት የሚገባኝ ሰው ማን ነው?

3. ውስጤ የሚያውቀውና የሚጠቁመኝ መሄድ የሌለብኝ ስፍራ የትኛው ነው?

“ልክ ነው፣ ግን . . .” የሚለውን ፍሬ ቢስ ምክንያት ተወት አድረጉና ውስጣችሁ የሚያውቀውን እውነት ተግብሩትና ረሳችሁን አድኑ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

22 Jan, 12:11

እነዚህን ሁኔታዎች ያሸነፋችሁ እለት!

• ከሰዎች የምትጠብቁትን መልካም ነገር አለማግኘታችሁ መራራ እንድሆኑ እስካላደረጋችሁ ድረስ፣

• ሰዎች አብረዋችሁ ከረሙም፣ ጥለዋችሁም ሄዱ ከራሳችሁ ጋር ማሳለፍ እስኪያስጠላችሁ ድረስ እስካልጎዳችሁ ድረስ፣

• ከሰዎች ጋር ብዙ ካሳለፋችሁና እንምታውቋቸው ካሰባችሁ በኋላ ሌላ ማንነት ስታገኙባቸው ሰው ሁሉ እንደዚያ እንደሆነ እንድታስቡ እስካላደረጋችሁ ድረስ፣

• የሚጎዳችሁ ሰውም ሆነ ሁኔታ ፈጽሞ ያልሆናችሁትን ማንነት ወደመሆን እስካልገፋፋችሁ ድረስ፣

• አሁን ያላችሁበት አስቸጋሪ ሁኔታ እናንተ ላይ ብቻ እንደደረሰና በቶሎ እንደማይቀረፍ እስክታስ ድረስ እስካላስፈራችሁ ድረስ፣

• በአንድ ነገር ስለወደቃችሁ ብቻ ውዳቂ ነኝ ብላችሁ እስካላሰባችሁ ድረሰ፣

በእርግጥም እናነተ አሸናፊዎች ናችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

22 Jan, 09:30

መጽሐፍን የመጻፍ ሰባት ጥቅሞች

1. ለአሁኑ ትውልድ እውቀትንና ልምድን ማካፈል - እኛ ጋር ያለውን እውቀትና ልምምድ ለሌሎች የማካፈያው ዋነኛው መንገድ ጽሑፍ ነው፡፡

2. ለመጪው ትውልድ የእውቀት ቅርስን ማስተላለፍ - ከትውልድ ወደ ትውልድ የትም የማይሄድ እውቀትን የማቆየት እድል ማግኘት፡፡

3. በሕብረተሰቡ መከካል ያለውን ችግር የመቋቋም እገዛ - በሕብረተሰቡ መካከል የምናያቸውንና የሚያሳስቡንን ችግሮች አስመልክቶ መፍትሄን በጽሑፍ በማቅረብ ራስን የማስተንፈስ አቅም ማግኘት፡፡

4. ሕይወትን የማደራጀት ቀላሉ መንገድ - ጽሑፍን በወረቀት ላይ ማደራጀት የቻለ ሰው ሕይወቱንና ተግባሩን ማደራጀት ስለሚችል ያንን እድል ማግኘት፡፡

5. የበለጠ እውቀት ማግኘት - እውቀትን ለሌሎች ለማካፈል በሚደረግ ጥረትና ተጨማሪ ጥናት ውስጥ ያለ የበለጠ እውቀትን የመገብየት እድል፡፡

6. እውቀትን በማካፈል ገንዘብ ማግኘት - ተፈላጊ እውቀቶችን በጽሑፍ በማቅረብና በገበያ ላይ በማዋል ገንዘብ የማግኘት እድል ማግኘት፡፡

7. ከመጠን በላይ ከማሰብ (overthinking) ማረፍ -
ከመጠን በላይ ከማሰብ ዋነኛ የመፍትሄ መንገድ ጽሑፍን መጻፍ እንደሆነ ባለው ጥናት መሰረት ያንን እድል ማግኘት፡፡

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

የስልጠናውን መረጃ ቀደም ሲል ባስተላለፍኩት ፖስት ላይ ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ መረጃ በሚከተለው አድራሻ inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

22 Jan, 05:14

“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)

ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

1. የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች

2. የጽሑፍ ጥቅሞች

3. የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)

4. ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?

5. የጽሑፍ አይነቶች

6. የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት

7. ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

22 Jan, 02:00

ሶስቱ የወዳጅነት ጠንቆች (ክፍል ሁለት)

የምስጢር ንክኪ

በትናንትናው “ፖስቴ” “ሶስቱ የወዳጅነት ጠንቆች” በሚል ሃሳብ ስር የመጀመሪያውን ማለትም፣ “የገንዘብ ንክኪ” የተሰኘው ሃሳብ አጋርቻችኋለሁ፡፡

ለማስታወስ ያህል፡- በአካባቢያችሁ የሚገኙ ሰዎች ከእናንተ ጋር ያላቸው ቅርበት የተለያየ ደረጃ እንዳለው ግልጽ ነው፡፡ የልብ ወዳጅ፣ የቅርብ ጓደኛ፣ የስራ ባልደረባ፣ የየእለት ውሏችን የሚያገናኘን ሰው፣ የሩቅ ትውውቅ . . . እያለ ግንኙነቱ ይጠብቃል፣ ይላላል፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች የራሳቸው የሆነ ባህሪይ ስላላቸው አያያዛቸውን በሚገባ ካላወቅንበት ለተለያዩ ማሕበራዊና የስሜት ቀውሶች ያጋልጡናል፡፡

የዛሬው ሃሳብ፣ “የምስጢር ንክኪ” የተሰኘ ይሆናል፡፡

ከአንድ ሰው ጋር በቅርብ ወዳጅነት የመተሳሰራችሁ የመጀመሪያው ውጤት ለማንም የማንነግረውን ምስጢር የመናገር ሁኔታ ነው፡፡ ከአንድ ሰው ጋር አንድ ጊዜ ምስጦርን ከተለዋወጣችሁ በኋላ የግንኙነታችሁ ቀለም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደተለወጠ አስታውሱ፡፡ ሁል ጊዜ፣ ምስጢር ነጋሪው እንደተሸማቀቀ ይኖራል፡፡ ግንኙነቱ ከተበላሸ የሚከተለውን ሁኔታ በመፍራት በስጋት ይኖራል፡፡

ይህንን የወዳጅነት ጠንቅ በአግባቡ ለመያዝ ያሉን አማራጮች ሁለት ናቸው፡-

አንደኛውና የተሻለው ምርጫ:-

ለየትኛው የቅርብ ወዳጅ የትኛውን ምስጢራችሁን እንደምትነግሩ በሚገባ በማጤን ከነገራችሁ በኃላ ይህ ሰው ጨዋና የበሰለ እንደሆነ በማመን መረጋጋት ነው፡፡ እንደዚያ ካልሆነና ያልጠበቃችሁትን ነገር ካደረገ ችግሩ እናንተ ጋር ሳይሆን የዚያ ሰው አጉል ባህሪይ ጋር እንደሆነ መቀበል ነው፡፡

ሁለተኛውና ምናልባት ከበድ ያለው ምርጫ:-

ሰው ቢሰማው ችግር ይፈጥራ የምትሉትን ምስጢራችሁን በሙሉ ለራሳችሁ መያዝ ነው፡፡ ይህንን ምርጫ ከበድ የሚያደርገው ምስጢርን ሁሉ በራሳችን አምቆን መያዝ የውስጥ ውጥረትን ስሚያስከትልና አልፎም የትክክለኛ የማሕበራዊ ሂደትን ስለሚገታ ነው፡፡

ይቀጥላል . . .

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

22 Jan, 01:59

ሶስቱ የወዳጅነት ጠንቆች (ክፍል ሁለት)

የምስጢር ንክኪ

Dr. Eyob Mamo

21 Jan, 12:57

አማራጩ መጠንከር ብቻ ሲሆን!

ያላችሁ ምርጫ ብርቱና ጠንካራ መሆን ብቻ ሲሆን፣ ያን ጊዜ በእርግጥም ምን ያህል ብርቱና ጠንካራ ሰዎች እንደሆናችሁ ታውቁታላችሁ፡፡

ሁሉም ነገር ተስፋ አጥቶ፣ አንዱን ችግር ተወጣሁት ስትሉ ሌላው ችግር ሲተካና ግራ ሲያጋባችሁ፡፡ ከሰዎች የምትጠብቁትን መልካም ነገር ሳታገኙ ስትቀሩና የማትጠብቁትን ጥሩ ያልሆነ ነገር ስታገኙ፣ ያላችሁ አማራጭ መጠንከር ብቻ ነው፡፡

ያን ጊዜ ነው ምን ያህል ብርቱና ጠንካራ እንደሆናችሁ የምታውቁት፡፡ ሁሉም ነገር የከዳችሁና መስመር የሳተ ሲመስላችሁ ምን ያህል ጠንካራና ጎበዝ እንደሆናችሁ የምታውቁበት ጊዜ ነውና ተስፋ አትቁረጡ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

21 Jan, 07:52

ከሚመጡልኝ ጥያቄዎች መካከል
“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

አብዛኛውን ጊዜ ከምጠየቃቸው ጥያቄዎች መካከል ስንት መጽሐፍ እንደጻፍኩ እና ይህንን ያህል መጽሐፍ በስኬታማነት ለመጻፍ ምን አይነት መንገድ እንደምጠቀም ለማወቅ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ይገኙበታል፡፡

በቀላሉ ለመመለስ ያህል፣ የሕይወትን ክህሎት በማሳደግ (self development) ዙሪያ 28 ማጻህፍቶችን ለአንባቢያን አድርሻለሁ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ብዙ ሰዎች የመጻፍን ክህሎት እና ዲሲፕሊን የማዳበርን ስልጠና መውሰድ እንደሚፈልጉ ይገልጹልኛል፡፡

በዚህ ርእስ ዙሪያ “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline) የተሰኘ ስልጠና ዝግ ለሆኑ ግሩፖች አልፎ አልፎ እሰጣለሁ፡፡

ይህንን ስልጠና በቂ የሆኑ ሰልጣኞችን ፍላጎታቸውን ሲገልጹልኝ ለማዘጋጀት ስለማስብ ፍላጎቱ ያላችሁ inbox ብታደርጉልኝ ወደፊት ስልጠናውን ለማቅረብ ስዘጋጅ ላሳውቃችሁ እችላለሁ፡፡

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

21 Jan, 04:53

የብዙ ሰዎች ጥያቄ!

ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡

በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-

1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)

2. እሴት-ተኮር (Value-based)

እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡

ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

https://t.me/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

19 Jan, 12:18

18 Jan, 15:06

ሲበቃ ይበቃል!

ለሰዎች ለስለስ፣ ቀለል በሉላቸው፡፡ ሆኖም፣ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ጠንካራ ጎናችሁንም ማየት አለባቸው፡፡

ለሰዎች የምትችሉትን አድርጉላቸው፡፡ ሆኖም፣ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ “NO” በማለት ክልከላ የሚያደርገውን ጎናችሁን ማየት አለባቸው፡፡

ለሰዎች ያላችሁን ከእነሱ ጋር አብሮ የመሆን ፍላጎት አሳይዋቸው፡፡ ሆኖም፣ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ከእነሱ ውጪ ሙሉ ሰው ሆናችሁ መኖር እንደምትችሉም ማየት አለባቸው፡፡

ለሰዎች ቅድሚያ ስጧቸው፡፡ ሆኖም፣ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ለራሳችሁ ቅድሚያ የምትሰጡበት ጊዜና ሁኔታ እንዳለም ማየት አለባቸው፡፡

ለሰዎች የፈለጉትን እንዲናገሩ እድል ስጧቸው፡፡ ሆኖም፣ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ አቋማችሁን መግለጥ እንደምትችሉበትም ማየት አለባቸው፡፡

ለሰዎች ሲፈልጉ እንዲሄዱ፣ ሰፈልጉ ደግሞ እንዲመጡ ፍቀዱላቸው፡፡ ሆኖም፣ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ከሄዳችሁ በቀላሉ ያለመመለስና እንደድሮው ያለመሆን ቆራጥነትና አቅማችሁን እንዳላችሁም ማየት አለባቸው፡፡

መልካም ምሽት !

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

18 Jan, 03:59

እስቲ ሆን ብላችሁ (intentionally) አስቡ እና ጀምሩ!

አንድን የከራረመ አባባል ላስታውሳችሁ፡-
“ሁሉም ነገር የሚፈጠረው ሁለት ጊዜ ነው፣ መጀመሪያ በሃሳባችን ከዚያም በገሃዱ አለም”፡፡

ያላሰባችሁት ነገር ላይ መነሳሳቱ ሊኖራችሁ አይችልም፡፡ መነሳሳቱ ከሌላችሁ ደግሞ አንድን ነገር መጀመር አትችሉም፡፡

እስቲ ዛሬ ለረጅም ጊዜ በሃሳብ ደረጃ አስቀምጣችሁት ስለነበረ ስለ አንድ ነገር እንድታስቡ ላደፋፍራችሁ፡፡

1. ለመጀመርና ወደ መኖር እንዲመጣ ለማድረግ የምፈልገው ነገር ምንድን ነው?

2. ይህንን ነገር ለመጀመር የሚያስፈልጉኝ ነገሮች ምን ምን ናቸው?

3. በዚህ ጉዳይ ላይ ሊያማክረኝ የሚችል ሰው ማን ነው ይህንን ሰው መቼ ላግኘውና ላነጋግረው?

4. ይህንን ነገር ከትንሹ መጀመር የምችለው እንዴት ነው?

5. መቼ መንቀሳቀስ ልጀምር?

እስቲ እነዚህንና ሌለች ተዛማጅ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እና መልስ በማግኘት ሆን ብላችሁ አስቡ! ሆን ብላችሁ ተንቀሳቀሱ!

መልካም የማሰብ፣ የማቀድና የመንቀሳቀስ ቅዳሜ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

17 Jan, 16:18

Relax!!!

• ያመለጣችሁን “እድል” ስታሰላስሉ፣ በፊታችሁ ያለውን ድንቅ ነገር እንዳታባክኑት!

• ትተዋችሁ ስለሄዱት ሰዎች ስታወጡና ስታወርዱ፣ አጠገባችሁ ያሉትን አስገራሚ ሰዎች እንዳታቷቸው!

• ገና ለገና ይሆንብኛል ብላችሁ ስለምትሰጉት ነገር ስትጨነቁ፣ ለሚመሆንላችሁ ድንቅ ነገር ሳትዘጋጁ ጊዜ እንዳያልፍባችሁ!

• ሰዎች ሊያዝኑባችሁ ስለሚችሉት ነገር በማሰብ እነሱን ለማስደሰት ስትታገሉ ራሳችሁን እንዳታጡት!

እስቲ ትንሽ ፈታ፣ ዘና በሉ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

17 Jan, 02:00

የራእይ ጉልበት

በሕይወታችሁ በፍጹም መፍትሄ ሊያገኙ እንደማይች እስከሚመስላችሁ ድረስ የሚመጡ ፈተናዎችና ችግሮች አሉ?

እነዚህ ፈተናዎችና ችግሮች ብዙ ነገር ሞክራችሁ እንኳና ልባችሁን ከመጎተትና ተስፋ ከማስቆረጥ ላያባሩ ይችላሉ፡፡ ለእንደዚህ አይነቶች ከባድ ፈተናዎች መፍትሄ እንዲሆን ፈጣሪ የሰጣችሁ ታላቁ ስጦታ የራእይ ስጦታ ነው፡፡

ለተለያዩ ችሮች የተለያዩ የመፍትሄ አማራጮችን የመውሰዳችሁ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለሁሉም ነገር መነሻ የሆነው ራእያችሁን የማወቅና የመከታተል ጉዳይ እጅጉን ሊታሰብበት ይገባል፡፡

• ከዚህ በፊት በሰራችሁት ስህተትና በወሰናችሁት አጉል ውሳኔ ምክንያት ጸጸት ውስጥ ካላችሁ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ ያለፈውን ትታችሁ የወደፊቱ ላይ ማተኮር ትጀምራላችሁ፡፡

• ሕይወታችሁን ሁሉ ሰጥታችሁት ሳለ ትቷችሁ የሄደ ወዳጅ፣ ጓደኛ፣ ፍቅረኛ ወይም የትዳር አጋር ሁኔታ እጅጉን ከጎዳችሁ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ ሕይወታችሁ በአንድ እናንተን ባልፈለገ ሰው ላይ ብቻ ከመንጠልጠል ይላቀቅና ራሳችሁን መምራትና ማሻሻል ትጀምራላችሁ፡፡

• ያላችሁበት የኑሮ ደረጃ በጣም የሚያታግልና ከባድ ከሆነባችሁና በዚሁ ሁኔታ እስከወዲያኛው እንደምትቀጥሉ እያሰባችሁ ከሰጋችሁ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ የዛሬውን ኑሯችሁን አልፋችሁ የተሻለ የወደፊት ውስጥ እንደምትገቡ ተስፋን ትጨብጣላችሁ፡፡

• በሆነ ባልሆነው የሚናወጥ ስሜትና ተስፋ-ቢስነት የሚያጠቃችሁ ከሆነ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ ውስጣችሁ ራእያችሁን በማሰብ፣ ስለእሱ በማቀድና ወደ ተግባር በመግባት ስለሚሞላ ለተስፋ ለመቁረጥ ጊዜም አይሰጣችሁም፡፡

ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላችሁም የተፈጠራችሁለትን ራእያችሁን ለማወቅ ጊዜን ውሰዱ! ራሳችሁን አሰልጥኑ! እሱን ተከታተሉ! መላውን ካላወቃችሁበት አጋዥ አግኙ!

ይህንን በማድረግ ሕይወታችሁ ሲለወጥ ተመልከቱ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

17 Jan, 01:59

የራእይ ጉልበት

Dr. Eyob Mamo

16 Jan, 14:14

እውተኛው ችግራችን!

• ችግራችን ሰዎች በእኛ ላይ ያላቸው አመለካከት አይደለም፡፡ ችግራችን እኛው በራሳችን ላይ ያለን አመለካከት ነው፡፡

• ችግራችን ሰዎች በእኛ ላይ የሚያወሩት ነገር አይደለም፡፡ ችግራችን እኛው ለእኛው የምንናገረው ነው፡፡

• ችግራችን ሰዎች ለእኛ ያላደረጉልን ነገር አይደለም፡፡ ችግራችን እኛው ራሳችንንን ችላ ማለታችን ነው፡፡

• ችግራችን ከሰዎች ማነሳችን አይደለም፡፡ ችግራችን ከሰው ሁሉ ልዩ የሚያደርገንን ነገር አለመለየታችንና አለማሳደጋችን ነው፡፡

• ችግራችን ሰዎች ያላቸው ነገር እኛ ስለሌለን አይደለም፡፡ ችግራችን የሰዎችን ሁኔታ ተወት አድርገን እኛ ያለን ላይ አለማተኮራችንንና እሱ ላይ አለመስራታችን ነው፡፡

ትክክለኛውን ችግራችሁን ለዩት፣ እሱ ላይ ስሩና ካላችሁበት ደረጃ አለፍ፣ ከፍ በሉ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

16 Jan, 07:08

Thank you!!!

ትናንትና አንዲትን የuniversity ተማሪ እህታችንን እንድንደግፋት ያደረኩትን ጥሪ ሰምታችሁ ምላሽ እየሰጧችኋት ላላችሁና ያንንም ለመግለጽ screenshot በማድረግ ያረጋገጣችሁልኝ ተከታታዮቼ ምስጋናዬ ታላቅ ነው፡፡

የቀራችሁትም ምላሽ እንደምትሰጧትና እንድትደግፏት አደራ፡፡

Dr. Eyob

Dr. Eyob Mamo

16 Jan, 02:03

ኃውልት ሆናችሁ እንዳትቀሩ!

በዚህ ሁሉም ነገር በፍጥነት በሚጓዝበትና በሚለዋወጥበት ዓለም ውስጥ ባሉበት ቆሞ መቅረት የሚባል ነገር የለም፡፡

ከዘመኑ ጋር ወደ ፊት ከመራመድ ይልቅ እንደ ኃውልት ባለንበት የቆምንባቸው እያንዳንዶቹ ቀናት ወደ ኋላ የቀረንባቸው ቀናት መሆኑ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ ከቆሞ-ቀርንት ከሚመጣ ኋላ-ቀርነት ለመዳን . . .

1. ካለማቋረጥ አሁን ካላችሁበት የእውቀት ደረጃ አልፎ በመሄድ በአዲሱና ከዘመኑ ጋር በሚራመደው ተራማጅ እውቀት ራሳችሁን አዘምኑ፡፡

2. ዘወትር በምታደርጉት እንቅስቃሴ ከሰው ጋር ከመፎካከር ራሳችሁን በመጠበቅ ካወጣችሁት ከፍ ያለ ግብ አንጻር ተንቀሳቀሱ፡፡

3. ካለማቋረጥ የራሳችሁን እድገት፣ የስራችሁን ስኬታማነትና የአቅጣጫችሁን ትክክለኛነት መገምገምን አትርሱ፡፡

4. ሁል ጊዜ ካለፈው ስህታችሁ በመማር ራሳችሁን አሻሽሉ፡፡

5. ዘወትር ከሚሆነውና ከማይሆነው ነገር ይልቅ በነገሩ ላይ ያላችሁ አመለካከት ወሳኝ እንደሆነ በመገንዘብ አመለካከታችሁን ጠብቁ፡፡

6. ሁል ጊዜ ወደ እናንተ ለሚመጡ እድሎች የተዘጋጃችሁ ሁኑ፡፡

7. በመጨረሻም ሁል ጊዜ ራሳችሁን ባለመገደብ አዳዲስ ነገሮችን ሞክሩ፣ ምናልባት የማታውቁትን ማንነታችሁንና እምቅ ብቃታችሁን ታገኙት ይሆናልና፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

15 Jan, 13:43

አንድን ሰው እንደግፍ!

በጣም የማከብራችሁ የማሕበራዊ ሚዲያ ተከታታዮቼ፡፡

በአንዲት እሷንም፣ ወላጆቿንም በቅርብ በማውቃቸውና በግልም ድጋፍ ባደረኩላቸው ወጣት ሴት ሕይወት ላይ የተወሰነ መዋጮ እንድታደርጉ ይህንን ጥሪ አቀርብላችኋለሁ፡፡

ስሟ: Nyabuol Saymen Deng ይባላል፡፡

ከትውልድ ቦታዋ ጋምቤላ ከሚኖሩ ወላጆችና ቤተሰቦቿ ተለይታ አዲስ አበባ ነው የምትማረው፡፡

በአሁኑ ጊዜ እዚህ አዲስ አበባ ሆና ትምህርቷን ለመከታተል የገንዘብ ጫና ስላለባት እንድትደግፏጽ እድሉን እከፍትላችኋለሁ፡፡

የምትማርበት University: New Generation University College

የትምህርት ዘርፍ (Department): Business Administration

ዓመት፡ Freshman (1st Year)

የBank መረጃ፡ ንግድ ባንክ / Account No: 1000595681255 (ስም Nyabuol Saymen Deng)

ይህችን እህታችንን ለመደገፍ የምትፈልጉ ሁሉ በቀጥታ በአካውንቷ የምትችሉትን ያህል እንድትልኩላት አበረታታለሁ፡፡

ድጋፍ ማድረጋችሁን inbox ለማድረግ ፈቃደኛ የሆናችሁ ያንን ብታደርጉልኝ በግሌ የማመስገን እድል ባገኝ ደስ ይለኛል፡፡

ለእኛ ቀላል የሆነ ነገር፣ የሌላውን ሰው ከባድ ችግር እንደሚቀርፍ አትዘንጉ!

Dr. Eyob

Dr. Eyob Mamo

15 Jan, 13:14

Question:

I have this question for you Dr .

I used to date a woman (her age is 26th), and we had a good time. We were together for almost 3 years, but in the last 6 months, she has been putting pressure to scale up the relationship to marriage.

I ignored her interest and kept the relationship as it is. Now her love drifted away to another man who I guess can provide her with money.

Shall I try to take her back or it is already passed that stage?

Answer:

A 26-year-old woman who has been in love with you for more than 3 years and who openly expressed her desire for you to take the relationship to the next level has all the right to move on with her life if you ignored her request.

Whether she left you for that man because of his financial status is not the issue here. The issue here is that she is at that stage where most women feel alarmed about their age in relation to their marital status. That is why she had to move on with her life.

You can try to apologize and win her back if she has not committed to the guy. However, the likelihood of her coming back is very low.

I would suggest that you learn your lesson from this experience and move on with your life.

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

15 Jan, 13:13

Question: The woman I dated for three years left me for another man

Dr. Eyob Mamo

15 Jan, 02:00

ስላለፈው ውሳኔያችሁ በጸጸት አትኑሩ!

ከዚህ በፊት የወሰናችሁትን ውሳኔ አሁን ስትመለከቱት፣ “ምነው ባልወሰንኩት!” የሚያሰኝ ውሳኔ ከሆነ በዚህ ውሳኔ መሰረት እየተጸጸቱ መኖር ምንም አያዋጣም፡፡ በታትነን እንመልከተው፡፡

1. ምናልባት ትክክለኛውን ውሳኔ እያወቃችሁ የተሳሳተ ውሳኔ ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡

2. ምናልባት በወቅቱ የነበራችሁን እውቀት፣ መረጃም፣ የኑሮ አቅምም ሆነ የስሜት ሁኔታ አሰባስባችሁ በተቻለ መጠን ትክክለኛ ነው ብላችሁ ያመናችሁበትን ውሳኔ ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡

3. ምናልባት በሰው ተታላችሁ ወይም በሁኔታዎች ተወዛግባችሁ ምኑንም ሳታውቁት ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡

ዛሬ ለጸጸት የዳረጋችሁ ያለፈው ውሳኔ መንስኤ ከላይ ከተዘረዘሩት መካከልም ሆነ ከዚያ ውጪ፣ ዋናው ነገር ያለፈው ውሳኔ ዛሬ ያመጣባችሁን የጸጸት ስሜት አልፋችሁ ለመሄድ ያላችሁ ቁርጠኝነት ነው፡፡

መፍትሄዎች፡-

1. በትናንትናው ውሳኔ ዛሬ፣ በዛሬ ውሳኔ ደግሞ ነገ የመጸጸት ነገር እድሜ ልክ የሚከተል እውነታ መሆኑን አትዘንጉ፡፡

2. በውሳኔያችሁ ስትጸጸቱ፣ እንደገና ማስተካከል የምትችሉትን የውሳኔውን ውጤት ለማስካከል ሞክሩ፡፡

3. በውሳኔያችሁ ስትጸጸቱ፣ እንደገና ለማስተካከል የማትችሉትን የውሳኔ ውጤት ተቀበሉት፣ ትምህርታችሁን አግኙ፣ ብሰሉበት . . . እና ወደፊት ተራመዱ፡፡

4. በውሳኔው ምክንያት ስለመጣው ችግር ከማሰላሰል ላይ ሃሳባችሁን አንሱና ስለወደፊት ራእያችሁና እቅዶቻቸው ማሰብ ጀምሩ፡፡
ፈጣሪ ጤና ይስጣችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

14 Jan, 16:54

ወቅት (Season) የሚባል ነገር አለ!

አንዳንድ ስፍራዎች፣ አንዳንድ ስራዎች፣ እንዲሁም አንዳንድ ማሕበራዊ ግንኙነቶች ወቅታቸው ያልቃል፡፡

ልክ ሌሉቱ አልፎ የቀን ወቅት እንደሚመጣ፡፡ ልክ ክረምቱ አልፎ የበጋው ወቅት እንደሚመጣ፣ ልክ የልጅነት ወቅት አልቆ የወጣትነት ወቅት እንደሚመጣ፣ ልክ የወጣትነት ወቅት አልፎ የአዋቂነት ወቅት እንደሚመጣ፣ በሕይወታችሁም አንዳንድ ሁኔታዎች በቃ ወቅታቸው ያልቅና ሌላ አዲስ ወቅት ይመጣል፡፡

አዲስ ወቅት እንደመጣ ጠቋሚዎች . . .

• ቀድሞ ያጓጓችሁ የነበረው ነገር አሁን ሳያጓጓችሁ ሲቀርና ለውጥ ስትፈልጉ፡፡

• ቀድሞ ትልቅ የነበረ ነገር አሁን ሲያንስባችሁና የላቀ ነገርን ስትናፍቁ፡፡

• ቀድሞ “ከዚህ ሁኔታና ነገር ውጪ መኖር አልችልም” ብላችሁ ታስቡ የነበረውን ነገር አሁን ከዚያ ሁኔታና ነገር ውጪ መኖር እንደምትችሉ ውስጣችሁ ሲያውቀውና አቅም ሲሰማችሁ፡፡

አዲስ ወቅት ሲመጣ አታጣድፉት፣ አትጋፉትም! ዝም ብላችሁ አስተናግዱት! ለአዲስ ነገር ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

ከሚመጣው ለውጥ ጋርም በጥቃቄና በተረጋጋ ሁኔታ ተራመዱ፡፡

መልካም እንቅልፍ ይሁንላችሁ የምወዳችሁ የሃገሬ ሰዎች!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

14 Jan, 16:40

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” ("Organizing Personal Life")

ባለፈው ኃሙስ ምሽት የተጀመረው የ telegram online (live) ስልጠና ካመለጣችሁና ያንን ያመለጣችሁን ክፍል በ audio እና በ note በመከታተል ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መቀጠል ከፈለጋችሁ ይህንን እድል የምንሰጠው ዛሬ ምሽት ድረስ ነው፡፡

ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox በማድረግ ፍላጎችሁን መጠየቅና መረጃ መቀበል ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

14 Jan, 14:09

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” ("Organizing Personal Life")

ባለፈው ኃሙስ ምሽት የተጀመረው የ telegram online (live) ስልጠና ካመለጣችሁና ያንን ያመለጣችሁን ክፍል በ audio እና በ note በመከታተል ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መቀጠል ከፈለጋችሁ ይህንን እድል የምንሰጠው ዛሬ ማክሰኞ ምሽት ድረስ ነው፡፡

ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox በማድረግ ፍላጎችሁን መጠየቅና መረጃ መቀበል ትችላላችሁ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

14 Jan, 10:53

14 Jan, 02:00

ምርጫና ውሳኔ

የትናንት ምርጫህን ዛሬ እየኖርክ ነው፡፡ የዛሬ ምርጫህን ደግሞ ነገ ትኖረዋለህ፡፡ ሆኖም፣ አንዳንድ ጊዜ የሌሎች ምርጫዎች ወደ አንተ አልፈው የሚመጡበትም ጊዜ አለ፡፡ ለዚያም ቢሆን የምትሰጠውን ምላሽ የመለየትና የመምረጥ አቅሙ አለህ፡፡ ስለምርጫና ውሳኔ ትርጉም፣ ተጽእኖና ስለ ትክክለኛ ምርጫ ምስጢር ለመገንዘብ ወደ መጽሐፉ ጎራ በልና አንብበው፡፡

ከመጽሐፉ የተቀነጨበ . . .

የምርጫ ደረጃዎች

ምርጫ ካለ ውጥረት አለ፡፡ እነዚህ ሁለት ጉዳዮች በፍጹም ሊለያዩ አይችሉም፡፡ ማንኛው አይነት የምርጫ ዘርፍ ውጥረትን ይዞ ወደ እኛ ስለሚመጣ ሂደቱን አድካሚ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ሶስቱን አይነት የምርጫ አይነቶች በደረጃቸው በማየት ግንዛቤአችንን ማስፋት አስፈላጊ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ቀላል ምርጫ፡- በክፉና በመልካም ነገር መካከል መምረጥ

ሁለት ነገሮች በፊታችን ለምርጫ ሲቀርቡና፣ አንዱ ምርጫ ጤና-ቢስ፣ ሌላኛው ምርጫ ግን ጤናማ እንደሆነ በግልጽ በምናውቅበት ጊዜ ይህ ምርጫ ቀላል ከተሰኘው የምርጫ ዘርፍ ይመደባል፡፡ በፊታችን ከተቀመጡት ምርጫዎች መካከል የትኛው የሚጠቅመንንና መልካም፣ የትኛው ደግሞ የሚጎዳንና ክፉ እንደሆነ በግልጽ ስለምናውቀው ምርጫውን ቀለል ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሆኖም፣ አንዳንድ ጊዜ ክፉና ደጉ በፊታችን በግልጽ ተቀምጦልን እንኳን ለመምረጥ እንቸገራለን፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የመነሻ ሃሳባችን ሲዛባና አንዳንድ ስሜቶቻችን ሲያሸንፉን ነው፡፡

መጠነኛ ምርጫ፡- በሁለት “ክፉ” ነገሮች መከካል መምረጥ

ከላይ የጠቀስነው በክፉና በመልካም መካከል የሚደረግ ቀላል የምርጫ ሂደት ከተዛባና በትክክል ካልተመረጠ የሚቀጥለው ምርጫችን በሁለት “ክፉ” ነገሮች መካከል ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፣ ጤና ቢስ ምግብን በመመገብና ባለመመገብ መካከል ባለን ምርጫ እያወቅን ጤና-ቢሱን ከመረጥን፣ ከሚከተለው የጤና ቀውስ የተነሳ አጣብቂኝ ምርጫ ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡ ያኛው “ቀላል” ምርጫ በትክክል ባለመያዙ ምክንያት አሁን ምናልባት በሁለት ምቹ ባልሆኑ የሕክምና ምርጫዎች መካከል መምረጥ ሊኖርብን ይችላል፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ በአንድ ጎኑ አንድ ጤናማ ነገር፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ አንድ ጤና ቢስ ነገር ለምርጫ ቀርቦልን ሳለ፣ ከስሜትም ሆነ ከአመለካከት መዛባት የተነሳ ጤና ቢሱን ስንመርጥ የኋላ ኋላ በሁለት አስቸጋሪ ነገሮች መካከል ወደመምረጥ ግዴታ ውስጥ ይጨምረናል ማለት ነው፡፡

ከባድ ምርጫ፡- በሁለት መልካም ነገሮች መካከል መምረጥ

ለአንዳንድ ሰዎች ግር ቢልም፣ ከላይ ከተጠቀሱት የምርጫ አይነቶች ይልቅ ከበድ የሚለው የምርጫ አይነት፣ ሁለት መልካም ምርጫዎች በፊታችን ሲቀርቡ ነው፡፡ ይህ የምርጫ ሁኔታ ለብዙ ግራ መጋባት ሊዳርገን ይችላል፡፡ ምርጫችን በክፉና በደጉ መካከል ሲሆን ደጉን መምረጥ እንዳለብን ግልጽ ነው፡፡

ምርጫችን በሁለት ክፉ ነገሮች መካከል ሲሆንና አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ስንገባ ደግሞ “የተሻለውን ክፉ” የመምረጣችን ሁኔታ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫችን በሁለት መልካምና ምርጥ ነገሮች መካከል ሲሆን ግን ያለብን የምርጫ ጫና ቀላል አይሆንም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በዚህ የምርጫ “ፍዘት” ውስጥ ስንሆን በግራ መጋባትና በመወላወል ምክንያት ብዙ አመታትን ልናቃጥል እንችላለን፡፡

ይህንን አትርሳ፣ ዛሬ የምትኖረው የትናንትናውን ምርጫህን ነው፤ ነገ ደግሞ የዛሬ ምርጫህን መኖርህ አይቀርም፡፡ ሕይወትን የመቀየሪያው ቀላሉ መንገድ ምርጫን ማስተካከል ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

14 Jan, 01:59

የትናንት ምርጫህን ዛሬ እየኖርክ ነው፡፡ የዛሬ ምርጫህን ደግሞ ነገ ትኖረዋለህ፡፡

Dr. Eyob Mamo

13 Jan, 17:18

በፍጹም!

• እስከ ሕይወቴ ፍጻሜ ድረስ የምከተለው ዓላማ ሳይኖረኝ ውሎ ማደር በፍጹም አይታሰብም!

• ራሴን፣ ዓላማዬንና ስራዬን በማሻሻል ላይ ከማተኮር ይልቅ ስለሰዎች ሳስብና ሳወራ ውሎ ማደር በፍጹም አይታሰብም!

• ቢያንስ በአንድ ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ ሳላሳድር ውሎ ማደር በፍጹም አይታሰብም!

• በየእለቱ ሳልለወጥ በአንድ አይነት አመለካከት፣ ስፍራና ልምምድ እየረገጥኩ ውሎ ማደር በፍጹም አይታሰብም!

• መንቀሳቀስ እስከማልችል ድረስ በፍርሃት ታስሬ ውሎ ማደር በፍጹም አይታሰብም!

• በሰዎች ላይ ቂም ይዤ እነሱን ካልተበቀልኩኝ በስተቀር ውስጤ አላርፍ እያለኝና እየነደደ ውሎ ማደር በፍጹም አይታሰብም!

• አንድ ሰው ስለገፋኝና ትቶኝ ስለሄደ ብቻ ነገን ማየት እስከማልችል ድረስ የወደቀ ስሜት ይዤ ውሎ ማደር በፍጹም አይታሰብም!

• ይህንን አቋም ካነበነብኩት በኋላ ከመፈክር ባላለፈ ሁኔታ ለውጥን ሳላመጣ ራሴን እዚያው ነገር ላይ በማግኘት ውሎ ማደር በፍጹም አይታሰብም!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

11 Jan, 17:57

ከሰዎች ቁጥጥር ነጻ የመሆኛው መንገድ

ሰዎችን ለመቆጠጠር በሞከራችሁ ቁጥር እናንተ በእነሱ ቁጥጥር ስር እየሆናችሁ ትሄዳላችሁ፡፡

ይህ የሚሆነው፣ ትኩረታችሁን በራሳችሁ ዓላማ እና ጉዳይ ላይ ከማድረግ ይልቅ እነሱን በመከታተል ላይ ስለምታሳልፉ ነው፡፡

ሰዎች ምርጫና ውሳኔቸውን እንዲኖሩ ፍቀዱላቸው!

መልካም እንቅልፍ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

11 Jan, 07:43

የብዙ ሰዎች ጥያቄ!

ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡

በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-

1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)

2. እሴት-ተኮር (Value-based)

እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡

ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

https://t.me/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

10 Jan, 18:25

መልካም እንቅልፍ!

መቶ በመቶ እውነተኛ እና ትክክለኛ እንደሆናችሁ በምታውቁት ነገር ላይ ሰዎች እንዲገነዘቧችሁ ስትታገሉ ጊዜያችሁን ማባከን ሰላማችሁን ይነሳችኋል፣ እንቅልፋችሁንም ይነፍጋችኋል፡፡

ሰዎች ማመን የሚፈልጉትን እንዲያምኑ ተዋቸውና እናንተ ከምታውቁት እውነት ጋር በሰላም ተኙ፡፡

መልካም እንቅልፍ የምወዳችሁ የሃገሬ ሰዎች፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

10 Jan, 16:27

ስልጠናውን የመቀላቀል እድል!

የስልጠናውን የመጀመሪያ ክፍል ባለፈው ኃሙስ (ጥር 1) ምሽት ተምረናል፡፡

ይህ ክፈለ-ጊዜ ላመለጣችሁ ስልጠና ፈላጊዎች ሁለተኛ እድል እሰጣለሁ ባልኩት መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

ክፍያውን ከፍላችሁ screenshot inbox ስታደርጉ . . .

1. የስልጠናው የቴሌግራም ቡድን ውስጥ እንቀላቅላችኋለን

2. ያለፈውን ትምህርት audio recording እና ዋና ዋና ነጥቦችን የያዘ note እንልክላችኋለን

የክፍያ መረጃ

ክፍያው አንድ ሺ ብር ነው

ንግድ ባንክ
Eyob Mamo
Account # 1000614499056

ቴሌብር
Dr. Eyob
ስልክ ቁጥር 0945087238

Thank you.

Dr. Eyob Mamo

10 Jan, 09:08

ፍቅር ስራን ይጠይቃል!

ለፍቅረኛሞች፣ ለእጮኛሞችና ለባለትዳሮች . . .

አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “የዘመኑ አሳዛኝ ሁኔታ፣ አንዳንድ ሰዎች እየተፋቀሩ አብረው ግን መሆን አለመቻላቸው፣ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ አብረው ሆነው አለመፋቀራቸው ነው”፡፡

የብዙ ሰዎችን ወቅታዊ ሁኔታ የሚገልጽ አባባል!

እየውላችሁ፣ በፍቅር፣ በእጮኝነትም ሆነ በትዳር አብራችሁ ከሆናችሁ አይቀር ተፋቀሩ፡፡

ፍቅር ደግሞ በምትሃት የሚመጣና በተአምራት የሚቀጥል ጉዳይ አይደለም፡፡

በፍቅር የተጀመረው ግንኙነት በፍቅር እንዲቀጥል ስራን ይጠይቃል፡፡ ፍቅርን የሚያሳዩ ተግባሮችን መስራት፣ የፍቅር ንግግሮችን መናገር፣ ለአጋር መጠንቀቅ፣ ችግርን መፍታት፣ መወያየት፣ ማቀድ . . . ምናምን የሚባሉ ስራዎች አሉ፡፡

ምናልባት “እንፋቀራለን ነገር ግን አብረን አይደለንም” የምትሉ ከሆነ፣ ይህም ሁኔታ ስራን እንደሚጠይቅ አትርሱ፡፡ ይህ ሁኔታ የተከሰተው ከጋብቻ በኋላ በመጣ መለያየትም ሆነ የተጀመረን የፍቅር ግንኙነት ወደፊት ለማራመድ ከማቃት ይሁን ስሌቱ ያው ነው፡፡

በሚገባ መተዋወቅ፣ ወደፊት አብሮ የመሆንን እቅድ አብሮ መንደፍ፣ በየጊዜው ወደ አብሮነት ለመምጣት አንድ ተግባራዊ እርምጃን መራመድ . . . ምናምን የሚባሉ ስራዎች አሉ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

10 Jan, 05:26

ስልጠናው ተጀምሯል!

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life" የተሰኘው የቴሌግራም (Online Live) ስልጠና ትናንትና ማታ በተሳካ ሁታ ተጀምሯል፡፡

ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞች መከታተል ጀምረዋል፡፡

ስልጠናውን ሳትመዘገቡ ያመለጣችሁ በርካታ ሰዎች በinbox ሁለተኛ እድል እንዲሰጣችሁ በጠየቃችሁት መሰረት ከሚቀጥለው ኃሙስ (ከክፍል ሁለት) ጀምሮ ለመቀጠል የሚያስችላችሁን የማካካሻ ክፍ-ጊዜ በመስጠት ለመቀላቀል እንሞክራለን፡፡

በዚህ መልኩ ለመቀላቀል የምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን መግለጽ ትችላላችሁ፡፡

በ @DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

10 Jan, 03:30

የራስ-በራስ ምልከታ ወሳኝነት

ማንም ሰው ስለ እኛ ካለው አመለካከት ይልቅ እኛው በራሳችን ላይ ያለን አመለካከት የላቀ ተጽእኖ አለው፡፡

ከሚከተሉት ሁለት እጅግ ጎጂ ከሆኑ የራስ-በራስ ምልከታዎች ጠንቀቅ!

1. ሁሉም ሰው (አብዛኛው ሰው) እንደሚወደንና እንደሚያደንቀን ማሰብ፡፡

ይህ አመለካከት ከእውነታ የራቀ የቅዠት አለም ውስጥ እንድንኖር አጋልጦ ይሰጠናል፡፡ ምንም አይነት ውብ፣ ድንቅና ጎበዝ ሰዎች ብንሆን የሚወዱንና የሚቀበሉን ሰዎች የመኖራቸውን ያህል የማይወዱንና የማይቀበሉንም ሰዎች ሞልተዋል፡፡ ከዚህ እውነታ ሊያመልጥ የሚችል ማንም ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ ሁሉም ሰው እንደሚወደንና እንደሚቀበለን ማሰብ ላልተፈለገ የስሜት ቁስል አሳልፎ ይሰጠናል፡፡ ይህ ቀውስ የሚመጣው እውነታውን ቀስ በቀስ እያየነው ስንመጣ ነው፡፡

2. ሁሉም ሰው (አብዛኛው ሰው) እንደማይወደንና እንደማይቀበለን ማሰብ፡፡

ይህ አመለካከት ተቀባይነት ለማግኘት ያልሆነውን ሆነን፣ የሌለንን ደግሞ እንዳለን አስመስለን እንድንኖር ይገፋፋናል፡፡ እዚህ ጋርም ማስታወስ ያለብን ነገር፣ ምንም አይነት ሰዎች ብንሆንና በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን የማይወዱንና የማይቀበሉን ሰዎች የመኖራችውን ያህል የሚወዱንና የሚቀበሉን ሰዎች እንዳሉ ነው፡፡ ይህ እውነት የገባቸው ሰዎች አስገራሚ የሆነ በሚወዷቸውና በሚቀበሏቸው ሰዎች ላይ የማተኮርና በዚያ ላይ የመገንባት ብቃት አላቸው፡፡

በሉ እንግዲህ፣ የማይቀበሏችሁ ሰዎች ካሉ፣ ይህንን አመለካከታቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ መሞከሩ አይከፋም፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን ስለ እነሱ እያሰቡ መዋልና ማደር ተውና በሚቀበሏች ሰዎች ላይ ትኩራትችሁን አድርጉ፡፡

በሌላ ጎኑ ደግሞ፣ የሚቀበሏችሁን ሰዎች በማሰብ መደሰትና በሁኔታው ላይ በመገንባት አንድን መልካም ነገር ለማከናወን መጠቀም ተመራጭ መንገድ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

10 Jan, 03:30

የራስ-በራስ ምልከታ ወሳኝነት

Dr. Eyob Mamo

09 Jan, 14:12

እስከ 12 ሰዓት!

በስራ መጨናነቅ ምክንያት ሳትመዘገቡ ጊዜው ያለፈባችሁ በጠየቃችሁት መሰረት የምዝገባውን ጊዜ እስከ 12 ሰዓት ድረስ አራዝመነዋል፡፡

ልክ በ12 ሰዓት ላይ ምዝገባ እናቆምና የስልጠናው ዝግጅታችን ላይ እናተኩራለን፡፡

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

09 Jan, 12:59

ምዝገባው ከአንድ ሰዓት በኋላ ይጠናቀቃል!

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life" ለተሰኘው ዛሬ ምሽት የሚጀምረው የ Online ስልጠና ለመውሰድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፡፡

ለመመዝገብ የቀራችሁ ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ፡፡

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

09 Jan, 11:59

ምዝገባው ከሁለት ሰዓት በኋላ ይጠናቀቃል!

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life" ለተሰኘው ዛሬ ምሽት የሚጀምረው የ Online ስልጠና ለመውሰድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፡፡

ለመመዝገብ የቀራችሁ ጊዜ ሁለት ሰዓት ብቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ፡፡

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

09 Jan, 10:00

የመጨረሻ እድል!

ዛሬ ማታ ለሚጀምረው ስልጠና ለመመዝገብ ፈልጋችሁ በስራ መጨናነቅ ምክንያት ሳትመዘገቡ ያለፋችሁ ሰዎች በኢንቦክስ አንድ እድል እንዲሰጥ በጠየቃችሁት መሰረት የምዝገባውን እድል እስከ ዛሬ ከሰዓት 11 ሰዓት ድረስ ክፍት በማድረግ እናስተናግዳችኋለን፡፡

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

09 Jan, 07:00

ሰዓታት ብቻ ቀራችሁ!

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life" ለተሰኘው ዛሬ ምሽት የሚጀምረው የ Online ስልጠና ለመውሰድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፡፡

ለመመዝገብ የቀራችሁ ጊዜ በሰዓታት የሚቆጠር መሆኑን ላስታውሳችሁ፡፡

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

09 Jan, 03:59

09 Jan, 02:00

ራስን ማወቅ

(“ራስን ማወቅ እና መምራት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

“ራስን በትክክል ማወቅ የግል ሕይወት እድገትን ለማስጀመር ኃይለኛ መሳሪያ ነው። በአመታት ውስጥ አብሬ የሰራኋቸው አብዛኛዎቹ ምርጥ የንግዱ ዘርፍ መሪዎች ሁልጊዜም ለራሳቸው ጥሩ ስሜት ነበራቸው - ይህ ሁሉም የሚጋሩት የተለመደ ባህሪ ነው። እነዚህ ሰዎች ጥንካሬዎቻቸውን እና ድክመቶቻቸውን ያውቁ ነበር፣ በግል ሕይወታቸውም ሆነ በሙያ ዘርፋቸው ለመከታተል የሚፈልጉትን ነገርና ምን እንደሚወዱ አጥርተው ያውቃሉ፣ እሴቶቻቸውንም ይኖራሉ፡፡” ይለናል ታዋቂ ጆን፡፡

በመቀጠልም የሚከተለውን ሃሳብ ያጋራናል፡

በርካታ የእውቀት ደረጃዎች እንዳሉ ይነገራል።

1. አንድን ነገር በእርግጠኝነት ማወቅ የመጀመሪያው ነው።

2. ሁለተኛው፣ አንድ ነገር እንደምታውቅ ማሰብ ነው።

3. ሦስተኛው፣ አንድ ነገር እንደማታውቀው በእርግጠኝነት ማወቅ ነው።

4. አራተኛው እጅግ አደገኛው ሲሆን እሱም፣ አንድ ነገር እንደማታውቅ አለማወቅ ነው፡፡

ይህ የመጨረሻው የእውቀት ሁኔታ በጣም አደገኛ ነው፡፡ ምናልባት ሌሎች ስለ አንተ በሚገባ የሚያውቁትና አንተ ግን ስለራስህ የማታውቀው ነገር ምንድን ነው? (Manning, 2015, P. 29-30)፡፡

ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን ምክረ-ሃሳብ እንደ መንደርደሪያ በመጠቀም የተለያዩ ራስን የማወቅ እውነታዎችን በዚህ ክፍላችን እንመለከታለን፡፡

እነዚህ እውነታዎች መነሻቸው የትናንትናው ሕይወታችን፣ ማለፊያው የዛሬው ደረጃችን፣ መዳረሻው ደግሞ የነገውና የወደፊታች ነው፡፡

1. የትናንትናው፡- እንዴት እዚህ ደረስኩ?

ባለፈው ሕይወታችን የነበሩ ሰዎች፣ ያሳለፍናቸው ሁኔታዎችና የተለማመድናቸው ልምምዶች በአስተሳሰባችንና ተግባራችን ላይ ምን አይነት ተጽእኖ እንዳመጡ የመገንዘብ ሁኔታ ነው፡፡

2. የዛሬው፡- ዛሬ የት ነው ያለሁት?

ይህ ስለአሁኑ ማንነታችን ግንዛቤን የሚሰጠን ሃሳብ ነው። በአሁን ወቅት በሕይታችን የሚሰራውን እና የማይሰራውን ነገር በመመርመር ለውጥን ለማስተናገድ ያለንን ፈቃደኝነት ያመለክታል፡፡

3. የወደፊቱ፡- ነገ የት መሆንና መድረስ እፈልጋለሁ?

ያለፈውን በሚገባ ስናውቅና የአሁኑን ሁኔታችንን በጥልቀት ስንገነዘብ ወደፊት መድረስና መሆን ስለምንፈልገው ነገር ግልጽ የሆነን ግንዛቤ እናተርፋለን፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

Dr. Eyob Mamo

09 Jan, 01:58

ራስን ማወቅ

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

08 Jan, 17:00

ስልጠናው አንድ ቀን ብቻ ቀረው!

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

08 Jan, 15:00

ሕይወትን ማደራጀት ማለት ፍጹም መሆን ማለት አይደለም!

የግል ሕይወትንም ሆነ አንድን ስራ ማደራጀት ማለት እኮ ፍጹምና ስህተት-የለሽ መሆን ማለት አይደለም፡፡

መደራጀት ማለት የሚያደርጉትን ማወቅ፣ ከየት ጀምረው ወደ የት እንደሚሄዱ አቅጣጫን መለየት፣ ለዚያ ለለየነው ነገር ደግሞ ካለን አቅርቦ በመነሳትና አቅማችን በሚፈቅደው መልኩ ማቀድና በታቀደው መሰረት ካለማቋረጥ መስራት ማለት ነው፡፡

ይህ ከላይ የተገለጸው ሂደት ስንከተል፣ ስህተታችን ለትምህርት ይሆናል፣ ስኬታችን ለእድገት ይሆናል፣ አቅማ ማጣታችን ደግሞ ለጥንካሬ ይሆናል፡፡ ለዚህ በአደረጃጀት ዙሪያ በሚገባ በመብሰል ቀደም ብለን መገኘት ያለብን፡፡

የነገው ስልጠና የሚያግዘንም ይህንንው ነው፡፡

የስልጠናውን መረጃ ከቀደሙት በተያያዘው ፖስተር ላይ ይልከቱና ይመዝገቡ!

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ባለው link inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

08 Jan, 12:59

የ“ሃሳባዊነት” እና የ“ተጨባጫዊነት” ሚዛናዊነት

ማንኛውንም ተግባር ከመጀመራችንም ሆነ ከመፈጸማችን በፊት ሊቀድም የሚገባው ነገር የእቅድ አወጣጥ ሂደት እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

በመጀመሪያ እናስባለን፣ በመቀጠልም እቅድን እናወጣለን፣ ከዚያም ወደ ተግባር በመግባት ዓላማችንን እንፈጽማለን፡፡

ሆኖም፣ ይህ እቅድን የማውጣት ሂደት ስኬታማ እንዲሆን ካስፈለገ የምናወጣው እቅድ ፍላጎታችንን እና እውነታውን ባስታረቀ መልኩ ሚዛናዊ ሊሆን ይገባዋል፡፡

እቅድን በሚዛናዊነት ማውጣት ከሚያጠቃልላቸው ሃሳቦች አንዱ፣ ለማከናወን የፈለግናቸውን ማንኛቸውንም ተግባሮች አስመልክቶ እቅድን በምናወጣበት ጊዜ፣ “ሃሳባዊነትን” (Idealism) እና “ተጨባጫዊነትን” (Realism) የማመዛዘንን ሁኔታ ነው፡፡

የዚህን ሃሳብ በሚገባ ለመግዘብና በትክክለኛው መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ ከፈለግን፣ የሁለቱን፣ ማለትም “ሃሳባዊነትን” (Idealism) እና “ተጨባጫዊነትን” (Realism) ጽንሰ-ሃሳቦች ትርጉም በሚገባ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡

እነዚህ ሁለት የእሳቤ ዝንባሌዎች በሚዛናዊነት ከተያዙ የራሳቸው የሆነ ጥቅም አላቸው፡፡

ከሁለቱ የአመለካከት ዝንባሌዎች አንዱ ሲጎላ የሚሰጠውን ጥቅም ያህል ለጉዳትም ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

በዚህ በግል ሕይወትም ሆነ በስራው አለም አደረጃጀት ውስጥ እጅ ወሳኝ በሆነው ሂደት ላይ በቂ ግንዛቤን ለማግኘት ነገ የሚጀምረውን ስልጠና በመመዝብ ይሳተፉ::

የስልጠናውን መረጃ ከቀደሙት ፖስቶች በማየት ይመዝገቡ!

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ባለው link inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

08 Jan, 08:00

የየእለት ድግግሞሾች (daily routines)!

የየእለት ድግግሞሾች (daily routines) የሌለው ሰው ሕይወቱን ያላደራጀ ሰው ነው፡፡

አንድ ሰው መገንባት ከሚፈልገው የሕይወት ጥራት፣ ማከናወን ከሚፈልገው አንድ ስራም ሆነ ማጠናቀቅ ካለበት አንድ ፕሮጀክት አንጻር ሊመሰርት የሚገባው የየእለት ድግሞሾች ሊኖሩት ይገባል፡፡

ይህ ልምምድ በአንድ ጎኑ ዲሲፕሊንን ሲጠይቅ፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ክህሎትን ይጠይቃል፡፡

ነገ በምንጀምረው የስልጠና መርሃ-ግብር ውስጥ ከምንመለከታቸው የተደራጀ ሕይወት ወሳኝ ልምምዶች መካከል አንዱ፣ የየእለት ድግግሞሾችን (daily routines) አስፈላጊነትንና እንዴት ማዳበር እንደሚገባን ነው፡፡

የስልጠናውን መረጃ ከቀደሙት ፖስቶች በማየት ይመዝገቡ!
ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ባለው link inbox ያድርጉ
@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

08 Jan, 06:00

አእምሯችሁ (ሃሳባችሁን) አደራጁ!

ምንም ነገራችሁን የማደራጀትን ሂደት ከመጀመራችሁ በፊት በቅድሚያ መደራጀት ያለበት አእምሯችሁ (ሃሳባችሁ) ነው፡፡

ስሜት ከመፈጠሩ በፊት፣ ተግባር ከመግባታችን በፊት እና ከዚያ አልፎ ያሉትን ሂደቶች ተሻግረን ውጤቱን በሕይወታችን ከማየታችን በፊት ሁሉም ነገር የሚጀምረው ሃሳብ ጋር ነው፡፡

ሃሳብ ሲደራጅ፣ ሕይወት ይደራጃል፡፡

ነገ በሚጀምረው የስልጠና መርሃ-ግብር የመጀመሪያው ክፍል የሚያስተምረን ለተደራጀ ሕይወት የሃሳባችን መደራጀት አስፈላጊነት ነው፡፡

የስልጠናውን መረጃ ከቀደሙት ፖስቶች በማየት ይመዝገቡ!

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ባለው link inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

08 Jan, 04:00

ስልጠናው አንድ ቀን ብቻ ቀረው!

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

06 Jan, 15:49

መርከቦች የሚሰጥሙት!

“መርከቦች የሚሰጥሙት በዙሪያቸው ካለው ውኃ የተነሳ አይደለም፡፡ መርከቦች የሚሰጥሙት ውስጣቸው ከገባው ውኃ የተነሳ ነው” (Wisdom For Living)

በዙሪያችሁ የሚሆነው ነገር ውስጣችሁ እንዲገባና እንዲያደክማችሁ አትፍቀዱለት፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

06 Jan, 14:34

እንደገና አስቡበት!

የጤንነት ቀውሱን የአእምሮም በሉት፣ የስነ-ልቦናም በሉት የስሜት . . . ያላችሁ የሰው ለሰው ግንኙነት ለዚህ አይነቱ የጤንነት ቀውስ የሚዳርጋችሁ ከሆነ ያንን ግንኙነት (relationship) እንደገና ልታስቡበት ይገባል፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

06 Jan, 11:40

ስልጠና በቤቴ!!!

በሞቀ ቤታችሁ ሆናችሁ ራሳችሁን የመለወጥ ታላቅ እድል!

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

ሰልጥኑ! ተሸሻሉ! እደጉ! ሕይወታችሁን ለውጡ!

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

06 Jan, 07:59

ለየት የሚደርጋችሁ ነገር!

ሁሉም መረጃ ማንኛው ሰው በሚያገኝበትና ያልተሰራ ስራ የሌለ በሚመስልበት በዚህ ዘመን፣ ሁሉም ነገር የተወሰደ፣ “የተበላ” እና ምንም የሚሰራ አዲስ ነገር እንደሌለ እንዲሰማን ሊሰማን ይችላል፡፡

ይህንን ብዙ ሰዎች የሚጋፉትን ስሜት ለማሸነፍ የሚረዳን አመለካከትና ልምምድ አለ፡፡

በአንድ አይነት ዓለም ውስጥ ለየት የሚደርጋችሁ ነገር . . .

• ሁሉም ሰው የሚያደርገውን የተለመደውን ነገር ባልተለመደ መንገድ ማድረግ!

• ሁሉም ሰው በግድ የለሽነት የሚሰራውን ስራ በከፍተኛ ዲሲፕሊን መስራት!

• ሁሉም የሚውቀውን ነገር መሬት በማውረድ በልዩ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ!

• ሁሉም የሚጀምረውን ነገር ጀምሮ ባለማቆም በመቀጠል ማከናወን!

• ሁሉም በተበታተነ መልኩ የሚያደርገውን ነገር በተደራጀ ሂደት ማድረግ!

ትችላላችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

06 Jan, 05:59

አቅም እያላችሁ እንደሌለው ሰው አትቀመጡ!

ብዙ ሰዎች ብዙ አቅም እያላቸው ምንም አቅም እንደሌላቸው ሆነው ይኖራሉ፡፡

ያለፉበት የሕይወት ውጣ ውረድ፣ የአስተዳደጋቸው አስቸጋሪ ሁኔታ፣ ያነበቡት፣ ያላቸው የሰው ግንኙነት ሃብት፣ የተፈጥሮ ዝንባሌያቸው . . . አቅማቸው ብዙ ነው፡፡

እነዚህ ነገሮች ግን እንዲሁ ተዘርግፎና ተዝረክርኮ እንደተቀመጠ እቃ ሳይደራጁ፣ መልክ መልክ ሳያዙና በአንድ ላይ ተገንብተው ለዓላማ ሰይውሉ እንዲሁ ይባክናሉ፡፡

ሕይወታችሁን ሰብሰብ አድርጉ፣ አቅማችሁን በአንድ ላይ አደራጁት!

ይህንን ስታደርጉ የውስጥ እርካታ ከማግኘታችሁም ባሻገር ለፈታችሁት ችግር ክፍያን በማግኘት ኑሯችሁን ታሳድጋላችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

06 Jan, 04:00

ስልጠናው ሶስት ቀን ብቻ ቀረው!

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

06 Jan, 01:59

የመደራጀት ወሳኝነት

“አንድ ነገር ለማደራጀት (Organize ለማድረግ) የምታጠፏት አንዲት ደቂቃ ወደ ስራው ስትሰማሩ አንድ ሰዓት ታተርፍላችኋለች” – Benjamin Franklin

በሕይወታችን ስኬታማ መሆን ከፈለግን ማዳበር ከሚገቡን ስልቶች አንዱ የማደራጀት ስልት ነው፡፡

ሁኔታውን ሰፋ አድርገን ከተመለከትነው ግን ከስልት ክልል ያለፈና ወደ ልማድ ቀጠና የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

ምንም እንኳን ስልቱን ብናውቀውም ልማዱን የማዳበር ደረጃ ካልደረስን ስለማይጠቅመን ማለት ነው፡፡

በአጭሩ ሲቀመጥ አንድን ነገር ማደራጀት ማለት ቀድሞ ፊታችን የቀረበልንን ከማድረግ ልማድ በመውጣ አንድን ነገር ሆን ብለን በማሰብና በማቀድ (intentional በመሆን) ማድረግ ማለት ነው፡፡

ምንድን ነው የማደርገው? እንዴት ነው የማደርገው? መቼ ነው ማድረግ ያለብኝ? እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች መሰራዊ የመነሻ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ጥያቄዎች በመጠየቅና ትክክለኛ መልስ ለመስጠት ግን በግር-ግር ተነስተን፣ በግር-ግር ውለንና በግር-ግር አምሽተን አንችለውም፡፡ በቀን ውስጥ ለብቻችን በጸጥታ የምናስብበትና የምናቅድበት ጊዜ ያስፈልገናል፡፡

ለብቻችሁ መሆንን ልመዱ፡፡ ማሰብን ተለማመዱ፡፡ ነገ ለሚሰራው ስራ ዛሬ ማቀድና ማደራጀትን ተለማመዱ፡፡ ከየት ጀምራችሁ ወደ የት እንደምትሄዱ በሚገባ አስቡ፡፡ በደመ-ነፍስ አትኑሩ፡፡

ይህንን ጠቃሚ ልምምድ እንዳትለማመዱ የሚያደርጓችሁን የግል ሁኔታዎች ቅረፉ፡፡

• አንዳንዶቻችን ያደግንበት ቤትና ሕብረተሰብ ያንን ስላላሳየንና ስላላስተማረን ያንን አንለማመደውም፡፡

• አንዳንዶቻችን የግንዛቤ ጉድለት አለብን፡፡ ሕይወትንና ስራን ማደራጀት ያለው ጥቅም አልገባንም፡፡

• አንዳንዶቻችን በአማካኙ መስከን ለምደናል፡፡ አንድ ነገር በሚገባ ቢደራጅ የሚመጣውን ውጤት ከመፈለግ ይልቅ በለመድነው በመቀጠል በውጤቱ መርካት እንመርጣለን፡፡

• አንዳንዶቻችን ፍላጎቱና አቅሙ እያለን የምኖርት ቤትና የምንሰራበት መስሪያ ቤት አይመቸንም፡፡
እነዚህ ምክንያቶች የየራሳቸው መዘዝ ቢኖራቸውም፣ ሁኔታውን ለይተን ብልሃት መፈለጉ ግን የእኛው ሃላፊነት ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

06 Jan, 01:58

የመደራጀት ወሳኝነት

Dr. Eyob Mamo

05 Jan, 17:35

እንዴት አመሻችሁ?

“ሁለት ነገር አስታውሱ፡- ለብቻችሁ ስትሆኑ የምታስቡትን ነገር ተጠንቀቁ፤ ከሰው ጋር ስትሆኑ ደግሞ የምትናገሩትን ነገር ተጠንቀቁ” (Quote From "The Wise You")

ነገ በ11 ሰዓት እንገናኝ!

መልካም እንቅልፍ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

05 Jan, 17:15

ስልጠናው አራት ቀን ብቻ ቀረው!

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

05 Jan, 14:19

Certificate of Participation!

ከጥር 1 እስከ ጥር 29 ለአምስት ተከታታይ ኃሙሶች ለሚሰጠው ስልጠና ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ያገኛሉ ወይ የሚል ጥያቄ ያላቸው ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡

መልሱ፣ አዎን! ነው፡፡ ለሰልጣኞች ከዚህ መልእክት ጋር ለ sample የቀረበው ዓይነት የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

ማሳሰቢያ፡- የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ለተሳታፊዎች የሚላከው በ soft copy መሆኑንና በ hard copy እንደማንሰጥ የታወቀ ይሁን፡፡
ስልጠናው አራት ቀን ብቻ ቀረው!

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

የክፍያ መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁ በኋላ ለዚሁ ስልጠና ወደሚዘጋጀው ቴሌግራም ግሩፕ ውስጥ እንጨምራችኋለን (add እናደርጋችኋለን)፡፡

Dr. Eyob Mamo

05 Jan, 04:00

ስልጠናው አራት ቀን ብቻ ቀረው!

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

05 Jan, 02:28

ግብ አውጡ እንጂ!

“አማካኝ ተሰጥኦ፣ አማካኝ ምኞት እና አማካኝ የትምህርት ደረጃ ያለው ሰው ግራና ቀኝ የማይልና ያተኮረ ግብን ይዞ ከተከተለ በሕብረተሰቡ መካከለ ከሚገኝ አለ የተባለ አስደናቂና ሊቅ ከሆነ ሰው አልፎና ልቆ ሊገኝ ይችላል” – Mary Kay Ash

እስቲ ዛሬዋን የእረፍት ቀን አንድን ቁም ነገር ለራሳችሁ እንድትሰሩ ልሞግታችሁ፡፡

ብዙ ሰዎች በሕይወታቸው ካለ ምንም ግብ ነው የሚኖሩት፡፡ ከእነዚህ ካለምንም ግብ ከሚኖሩት ብዙ ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ደግሞ ግብን የማያወጡበት ምክንያት ግብን እንዲያወጡ የሚያደርግ የራእይ አቅጣጫ ስለሌላቸው ነው፡፡

ስለሆነም፣ ብዙ የእውቀት፣ የገንዘብ፣ የልምድ እና የወዳጅ (Connection) ባለጠግነት እያላቸው እንኳን በየቀኑ ፊታቸው የመጣላቸውንና ያገኙትን እያደረጉ፣ አንድም ነገር ሳይገነቡ ጊዜያቸውን ያባክናሉ፡፡

ሕይወታችሁ አቅጣጫ እና ጣእም ያለው እንዲሁን ከፈለጋችሁ፡-

1. ራእያችሁ ምን እንደሆነ ለይታችሁ እወቁ፡፡

ራእያችሁን ለማወቅ ባላችሁ ጉዞ ትልቁ እንቅፋት የራእይን ትክክለኛ ትርጉም ያለማወቅ መሆኑን አትዘንጉ፡፡

2. ባወቃችሁት ራእያችሁ መሰረት ግቦችን አውጡ፡፡

ግቦቻችሁ የአንድ አመት፣ የአምስት አመትና፣ የአስር አመት የጊዜ ሁኔታዎችን ያካተቱ መሆናቸውን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

3. ባወጣችኋቸው ግቦች መሰረት የየእለት ተግባራዊ እርምጃን ጀምሩ፡፡

ግብ ማለት ነገ የሚደረስበት እቅድ ሲሆን፣ የተግባር እርምጃ ደግሞ ወደ ግቡ የሚወስድ የየእለት እንቅስቃሴ መሆኑን እወቁ፡፡

ራእይ የሌለው ግብ የማውጣት ሙከራ ግራ ያጋባችኋል፡፡ ተግባራዊ እርምጃ የሌለውም ግብ ደግሞ ከምኞት አያልፍም፡፡

ከራእያችሁ አንጻር ግብ አውጡ! ከግቡ አንጻር ደግሞ ስራ ጀምሩ! አንዴ ከጀመራችሁ ደግሞ አታቁሙ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

05 Jan, 02:28

ግብ አውጡ እንጂ!

Dr. Eyob Mamo

04 Jan, 16:29

ስልጠናው አምስት ቀን ብቻ ቀረው!

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

04 Jan, 14:37

የአደረጃጀት ጉድለት ጣጣ!

ሕይወቱን፣ ጊዜውንና ተግባሩን በፍጹም ማደራጀት የማይችል ሰው የእሱ መዘዝ ወደ ሌላ ሰው አልፎ እንደሚሄድ ታውቃላችሁ?

ስለአደረጃጀት የማያውቅ፣ ማወቅ የማይፈልግ ወይም እያወቀ ያንን ማድረግ የማይፈልግ ሰው የእሱ ጣጣ . .

• በስራ ባልደረባው ላይ አጉል ተጽእኖ ስለሚያመጣ ስራው ይበደላል፣ ባልደረባውም አብሮ ተወቃሽ ይሆናል፡፡

• በንግድ አጋሩ ላይ ጤና-ቢስ ጫና ስላለው ንግዱ ይከስራል፣ አጋሩም አብሮ ይጎዳል፡፡

• በትዳር ጓደኛው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ስለሚያስከትል ሁል ጊዜ ውጥረትና ጭቅጭቅ ያስከትላል፣ አጋሩም እየደከመው ይሄዳል፡፡

ስለራሳችሁ እና አጠገባችሁ ስላሉ ሰዎች ብላችሁ ሕይወታችሁን አደራጁ!

በጉዳዩ ላይ የተዘጋጀውን ስልጠና ለመካፈል በፖስተሩ ላይ ያለውን መረጃ ይመልከቱ!

ለተጨማሪ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Dr. Eyob Mamo

04 Jan, 10:47

የማይካድ ሀቅ!!!

• ከዋና ዓላማችሁ በመነሳት ለራሳችሁ ፕሮግራም ካላወጣችሁ፣ ሰዎች ፕሮግራም ያወጡላችኋል፡፡

• የራሳችሁን ሕይወት ካልመራችሁ፣ ሰዎች ወደፈለጉበት ይመሯችኋል፡፡

• ሕይወታችሁን በመልክ በመልኩ ካላደረጃችሁት፣ የመጣውን ሁኔታ ሁሉ እየተቀበላችሁ ለመኖር ትገደዳላችሁ፡፡

• እቅድ አውጥታችሁ የምትከተሉት ነገር ከሌላችሁ፣ ከሁኔታዎች እንደሸሻችሁ ትኖራላችሁ፡፡

• ብዙ እምቅ ብቃት ኖሯችሁ ካለምንም እቅድ እና አደረጃጀት ከኖራችሁ፣ ምንም እውቀት የሌላቸውና የተደራጁት እንደነዷችሁ ትኖላችሁ፡፡

የዚህ እውነታ ተጽእኖ ከምታስቡት በላይ እጅጉን ጠንካራ እና ለማስተካከል ጊዜው ካለፈ በኋላ እንድትባንኑ የሚያደርችሁ ጉዳይ መሆኑን አስታውሱ፡፡

ሁኔታው ካሳሰባችሁ፣ የተዘጋጀላችሁን ስልጠና ለመሳተፍ ወሰኑ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

04 Jan, 03:59

ስልጠናው አምስት ቀን ብቻ ቀረው!

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

04 Jan, 02:14

መልካም ጠዋት!!! መልካም ቅዳሜ!!!

የዛሬው ቀን . . .

• የራቀው ሰላማችሁ የሚመለስበት ቀን . . .

• ከወደቃችሁበት የምትነሱበት ቀን . . .

• ጀምራችሁ ያቆማችሁትን መልካም ነገር እንደገና የምትጀምሩበት ቀን . . .

• ግራ የገባችሁ ነገር መልክ የሚይዝበት ቀን . . .

• ተስፋ በቆረጣችሁበት ነገር ላይ የተስፋ ጭላንጭል የምታዩበት ቀን . . .

• ፍርሃታችሁን አሸንፋችሁ የምትሄዱበት ቀን . . .

ይሁንላችሁ!!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

03 Jan, 16:18

ለውጥ!

ለውጥ ሁል ጊዜ ህመም አለው! ባሉበት መቆየትም እንዲሁ ህመም አለው!

ለውጥ አሁን ለአጭር ጊዜ ያመናል፣ ነገ ግን ለረጅም ጊዜ ይከፍለናል፣ ያስደስተናል!

ባሉበት መቆየት አሁን ለአጭር ጊዜ ይመቸናል፣ ነገ ግን ለረጅም ጊዜ ዋጋ ያስከፍለናል!

በዙሪያችሁ እና በላያችሁ ላይ ነገሮች ሲከናወኑና ሲለወጡ ዝም ብላችሁ አትመልከቱ፡፡

ተነሱና አቅዱ፣ ለውጥን አነሳሱ! የነጋችሁን ዛሬ አቅዱ!

መልካም አዳር ለሁላችሁ!

Dr. Eyob Mamo

03 Jan, 13:13

ያልተደራጀ አመለካከት!

ከምልክቶቹ ጥቂቶቹ . . .

1. አንድ አቅጣጫ የመከተል ውሳኔ ላይ መወዛገብ

2. የተሳሳቱ ምርጫዎችን በመምረጥ መጨረሻ መባነን

3. በሌሎች ሰዎች ሃሳብ መመራትና ሃሳብን መቀያየር

4. አንድን ነገር ለመጀመር አለመቻልና የጀመሩትን ማቋረጥ

5. ብዙ እምቅ አቅም እያለን ከዚያ በታች የመኖር ስሜት

6. እጅግ የወረደ በራስ የመተማመን ስሜት

እነዚህና መሰል ልምምዶች እንዳሉበችሁ ካሰባችሁ የተዘጋጀው ስልጠና ይመለከታችኋል፡፡

ባለፈው ከነበረን የtelegram (online) ስልጠና በኋላ ባደረግነው ጥናት አብዛኛዎቻችሁ በየሶት ወሩ ስልጠና እንዲሰጥ በጠየቃችሁት መሰረት የተዘጋጀ!

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

03 Jan, 09:00

ያለኝ ነገር + አደረጃጀት = ስኬት!

• ምንም አይነት እውቀት ቢኖረኝ - በሚገባ አደራጅቼ ወደ ተግባር ካልለወጥኩት . . .

• የትኛውንም ያህል ገንዘብ ቢኖረኝ - አስቤበትና እቅድ አውጥቼ ስራ ላይ ካላዋልኩት . . .

• ምንም ያህል ስፋት ያለው ማሕበራዊ ግንኑነት ቢኖረኝ -
ከማን ጋር ምን ማድረግ እንዳለብኝ በማወቅ ካልተጠቀምኩበት . . .

• የትኛውንም አይነት ልምድ ባዳብርና ቢኖረኝ - አንድን ነገር ከመገንባት አንጻር አዋቅሬ ካልተጠቀምኩበት . . .

• ምንም አይነት አስገራሚ አዳዲስ ሃሳብ ባፈልቅ - ከየት ጀምሬ ወደ የት እንደምወስደው በማወቅ ወደ መሬት ማውረድነ ካላወኩበት . . .

ከአመት ዓመት ባሉበት ከመቅረት የሚመጣን ኋላ ቀርነት ከማስተናገድ የትም አላመልጥም፡፡

እነዚህን ሃሳቦች ስታነቡ በአሳባችሁ ከእናንተ ሁኔታ ጋር የሚነካካ ነጥብ እንዳለ ካሰባችሁ በሚቀጥለው ሳምንት የሚጀምረው ስልጠና ይመለከታችኋል፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

03 Jan, 05:30

ስልጠናው ስድስት ቀን ብቻ ቀረው!

የተደራጀ ሕይወት ከሚሰጡት ጥቅች መካከል

1. የውጥረትና የጭንቀት መቀነስ

ተግባርና ጊዜ በሚገባ ሲደራጅ ከስራ ብዛትና መጨናነቅ የሚመጣን ውጥረት ስለሚቀንስ ብዙ የማከናወን እድል አለን፡፡

2. የአእምሮ መረጋጋት እና የመከናወን ስሜት

የተደራጀ ሕይወት ጥበብ የሞላው የጊዜ አጠቃቀም ስለሚሰጠን የአእምሮ መረጋጋትና የመከናወን ስሜት የሰጠናል፡፡

3. የጉልበት መጨመር

በሚገባ የተደራጀ ሰው ሁሉንም ነገር በተዋጣለት መልኩ ስለሚሰራ ለብዙ ነገር የሚተርፍ ጉልበት ይኖረዋል፡፡

4. የገንዘብ መደላደልና ነጻነት

ሁሉን ነገር ማደራጀት ጊዜያችንን በአግባቡ ጥቅም ላይ ስለሚያውው በገንዘብ አያያዝ ላይ እና በገቢ ላይ ታላቅ ተጽእኖ አለው፡፡

5. ጥራት ያለውና ጠንካራ የቤተሰብ ትስስር

ራስን፣ ስራንና ጊዜን ማደራጀት ከሚሰጠን ታላቅና ጠቃሚ ውጤቶች መካከል ለቤተሰብ ጥራት ያለውን ጊዜ ማግኘት ይገኝበታል፡፡

6. የተሻለ ጤንነት

ተግባርን እና ጊዜን በሚገባ ስንጠቀም ስራችንን በሚገባ ካጠናቀቅን በኋላ በቂ ጊዜ ስለሚኖረን ስለ ግል ጤንነታችን ለማሰብ እድል እናገኛለን፡፡

በሚቀጥለው ሳምንት ኃሙስ (ጥር 1) የሚሰጠው ስልጠና አያምልጣችሁ!

የምዝባ መረጃውን በፖስተሩ ላይ ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

03 Jan, 02:04

ሰዎች የነዱት ሰው ጸጸት

“ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!”

(“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

ብሮኒ በመጀመሪያ የምትተርከው ግሬስ ስለምትባል በታላቅ ጸጸት ውስጥ ስላለች ሴት ነው፡፡ ግሬስ ከሃምሳ አመታት በላይ በጋብቻ ሕይወት አሳልፋለች፡፡ ግሬስ ከልቧ ከምትወዳቸው ልጆቿ ከምታገኘው ደስታ ባሻገር “የአስራዎቹ” አመታት ወጣት የልጅ ልጆች ማግኘቷ የማይጠገብ የደስታ ምንጭ ሆኖላታል፡፡ ሆኖም፣ ይህ ደስታዋ ሙሉ እንዳይሆን ያደረገባት አንድ ጥቁር ነጥብ ግን በሕይወቷ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ የባለቤቷ ጉዳይ ነበር፡፡

አምባ ገነንና ጨካኝ የሆነው ባለቤቷ ባሳለፉት አመታት ውስጥ ጋብቻን አስቸጋሪ ያደረገባት ሰው ነበር፡፡ ወደጋብቻ ከመጡበት እለት ጀምሮ የቅስም ሰባሪ ቃላትና የተለያዩ የክፉ ተግባሮች ሰለባ አድርጓታል፡፡ ይህንንም ሁኔታውን ለማስተካከል መውሰድ የነበረባት እርምጃዎች እንዳሉ ብታውቅም፣ አንዱንም ምርጫ ለመውሰድ ድፍረቱ ሳይኖራት ለአመታት ተቀጥቅጣ ኖራለች፡፡ የባለቤቷ አስቸጋሪነት እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ ከጥቂት አመታት በፊት ከእርጅና የተነሳ በአረጋውያን መጦሪያ ማእከል በመግባቱ እርሷ ብቻ ሳትሆን ሁኔታውን የሚያወቁ ሰዎች ሁሉ ደስተኛ ነበሩ፡፡

ግሬስ በትዳር አመታቶቿ በሙሉ አንድ ቀን ከባሏ ክፉ ተጽእኖና ጨካኝ ሁኔታ ውጪ ሆና ደስተኛ ሕይወትን ለብቻዋ የምታጣጥምበትን ቀን እንደናፈቀች ኖራለች፡፡ አሁን በሰማኒያዎች አመታት ውስጥ ብትሆንም፣ ለእድሜዋ የሚመጥን መጠነኛ ጤንነትና የአካል ብቃት ነበራት፡፡ ወደማእከሉ ስትመጣ ወዲህ ወዲያ ለማለት የሚያበቃት አቅም ነበራት፡፡

እድሜዋን በሙሉ “በድብደባ” ያሳለፈው አእምሮዋ አሁን ለዚህ ሁኔታ ከዳረጋት ባለቤቷ በመለየቷ ምክንያት የእረፍትን ጭላንጭል ያየ ይመስላል፡፡ ለብዙ ዘመናት የጠበቀችውን ይህንን ለብቻ የመሆንና ካለምንም የውጪ ሰው ተጽእኖ የማሰብ “ነጻነት” ባገኘች በአጭር ጊዜ ውስጥ በድንገት በጽኑ መታመም ጀመረች፡፡ ሕመሙ ከተሰማት ከጥቂት ቀናት በኋላ ብዙም እድሜ እንደማይኖራት የሚጠቁም ምልክት ተገኘባት፡፡ ሁኔታውን እጅግ ልብን የሚሰብር ያደረገባት፣ የህመሙ መንስኤ ለብዙ አመታት ባለቤቷ በቤት ውስጥ ሲያጨስ ከነበረው የሲጃራ ጭስ እንደሆነም ማወቋ ነው፡፡ የበሽታው ደረጃ እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ በአንድ ወር ውስጥ አቅሟን ሁሉ አጥታ የአልጋ ቁራኛ ሆነች፡፡

“ለምን ያንን ዘመን ሁሉ እኔ ያመንኩበትንና የፈለግሁትን ነገር አላደረኩም? ለምን እንደፈለገ እንዲገዛኝና እንዲያንገላታኝ ፈቀድኩለት?” የሚሉት ጥያቄዎች ካለማቋረጥ ከግሬስ አንደበት ሲወጣ ይደመጥ ነበር፡፡ ያመነችበትን ትክክለኛ ሕይወት ለመኖር ድፍረት ሳይኖራት ዘመኗ በማለፉ ምክንያት በራሷ ላይ እጅግ በጣም ትበሳጭ ነበር፡፡ ልጆቿም ቢሆኑ እንደፈለገ ባደረጋትና ባደረገባት ባሏ ምክንያት ስላሳለፈችው ከባድ ሕይወት በግልጽ ይመሰክሩ ነበር፡፡

“አንቺ ማድረግ የምትፈልጊውን ትክክለኛ ነገር ከማድረግ ማንም ሰው እንዲከለክልሽ አትፍቀጂለት” በማለት ለተንከባካቢዋ ለብሮኒ ደጋግማ ትነግራት ነበር፡፡ “እባክሽን ይህንን እኔ የሰራሁትን ስህተት እንዳትሰሪ ቃል ግቢልኝ” በማለት ታሳስባት ነበር፡፡ አንድ ቀን ግሬስ ይህንኑ ምክር ደግማ ከነገረቻት በኋላ፣ ብሮኒ በእሺታ ምክሯን ተቀብላ እንደምትተገብረው ቃል በመግባት፣ “ራስን የመቻልና ያመኑበትን ትክክለኛ ነገር የማድረግን ትምህርት ያስተማረችኝ እናት ስለነበረችኝ እድለኛ ነኝ” በማለት ለግሬስ ነገረቻት፡፡

“አሁን ያለሁበትን ሁኔታ ተመልከችው” አለች፣ ግሬስ በመቀጠል፡፡ “በመሞት ላይ ነኝ፡፡ በሞት አፋፍ! እንዴት ቢሆን ነው እነዚያን አመታት ሁሉ ነጻና ራሴን የቻልኩ ሆኜ ለመሆን ስጠብቅ ኖሬ፣ አሁን እዚያ የተመኘሁበት የሕይወት ምእራፍ ላይ የደረስኩ ሲመስለኝ ጊዜው ያለፈብኝ?” እነዚህን መራራ ቃላት የሰማችው ብሮኒ የግሬስ ሁኔታና ጸጸት እንድታስብ ያነሳሳትን እውነታ ማሰላሰል ጀመረች፡፡

የደረሰችበትም ድምዳሜ፣ “ማንኛውም ሰው የራሱን አመለካከት ማወቅ፣ ትክክለኛውን መንገድ መለየትና ያንንም ያመነበትን ትክክለኛ ጎዳና መከተል አለበት” የሚል ነበር፡፡

ግሬስ በውስጧ የምታምንበትንና የሚሰማትን ስሜት ሳይሆን የዚያን ተቃራኒ ገጽታን በውጪ እያንጸባረቀች ዘመኗን አባከነች፡፡ እድሜዋን በሙሉ እርሷ ያመነችበትንና ከነበረባት የጭካኔ ሰለባ የሚያወጣትን ሕይወት ሳይሆን ሌሎች ሰዎች ከእርሷ የሚጠብቁባትን አይነት ሕይወት ስትኖር ካሳለፈች በኋላ፣ አሁን በመጨረሻዎቹ አመቶቿ ምርጫው የእርሷ እንደነበርና፣ ፍርሃት ከትክክለኛው ምርጫ እንደገታት ተገነዘበች፡፡ ራሷን ይቅር የማለት አስፈላጊነት ቢነገራትም እንኳን አሁን ሌላ ምርጫ ያለውን ሕይወት ለመኖር ጊዜው ያለፈባት መሆኑን ስታስብ ከአቅሟ በላይ የሆነ ስሜት ይወርሳታል፡፡

ብሮኒ በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎች በሚኖሩበት ማእከል ውስጥ ስትሰራ ካጠናቻቸው የሰዎች ጸጸቶች ይህኛው፣ “ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!” የሚለው ጸጸት አብዛኛዎቹን ሰዎች የሚያጠቃውና ቀንደኛው ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የሕልማቸውን ግማሽ እንኳን ሳያጣጥሙ ዘመናቸው የሚያልፈው ያመኑበትን ትክክለኛ የሕይወት አቅጣጫ ለመከተል ምርጫ እንዳላቸው ካለማወቅና ወይም ትክክለኛውን ምርጫ እያወቁ ያንን ምርጫ ለመከተል ጉልበት ከማጣት የተነሳ ነው፡፡

ጊዜው ካለፈብህ በኋላ እዳትጸጸት ሰዎች ከአንተ የሚጠብቁትን ሳይሆን አንተ ራስህው ያመንክበትን ትክክለኛ ሕይወት የመኖርን ጉዳይ ዛሬውኑ አስብበት!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

03 Jan, 01:59

ሰዎች የነዱት ሰው ጸጸት

Dr. Eyob Mamo

02 Jan, 14:01

መቅደም ያለበት ነገር

ሰዎች አከበሩኝም አላከበሩኝም፣ በመጀመሪያ ራሴን ከማክበር፣ ከዚያም ሌሎች ሰዎችን ከማክበር በፍጹም አይመልሰኝም፡፡

ሰዎች ወደዱኝም ጠሉኝም፣ በመጀመሪያ ራሴን ከመውደድ፣ ከዚያም ሌሎች ሰዎችን ከመውደድ በፍጹም አያግደኝም፡፡

ሰዎች አገዙኝ አላገዙኝም፣ በመጀመሪያ ራሴን ከማገዝ፣ ከዚያም ሌሎች ሰዎችን ከመደገፍ በፍጹም አያስቆመኝም፡፡

ሰዎች ተንከባከቡኝም አልተንከባከቡኝም፣ በመጀመሪያ ራሴን ከመንከባከብ፣ ከዚያም ሌሎች ሰዎችን ከመንከባከብ በፍጹም አይከለክለኝም፡፡

ሰዎች ተገነዘቡኝም አልተገነዘቡኝም፣ በመጀመሪያ ራሴን ከመገንዘብ፣ ከዚያም ሌሎች ሰዎችን ከመገንዘብ በፍጹም አያግደኝም፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

02 Jan, 09:54

ሶስቱ ሃብቶች!

ከምንም አይነት ሁኔታና ደረጃ ተነስታችሁ የትኛውም አይነት የስኬት ከፍታ ላይ መድረስ እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

ይህንን ሃሳብ እውን ለማድረግ ግን ሶስቱ ሃብቶቻችሁ ምን ምን እንደሆኑ እና እንዴት እንደምትጠቀሙባቸው በሚገባ ማወቅ አለባችሁ፡፡

አንድ ሰው በሚገባ ከተጠቀመባቸው ሕይወቱን ስኬታማ ሊያደርለት የሚችሉ ሶስት ሃብቶች አሉ፡፡

እነዚህ ሃብቶች፣

1) የጊዜ፣

2) የእውቀት፣ እና

3) የገንዘብ ሃብቶች ናቸው፡፡

ሆኖም በሚሳዝን ሁኔታ ሰዎች ከእነዚህ አንዱ፣ ሁለቱ፣ አንዳንዴ ደግሞ ሶስቱም እያላቸው ባለበት የሚረግጥ ሕይወት መኖራቸው ነው፡፡

ከእነዚህ ከሶስቱ ሃብቶች ቢያንስ በአንዱ ባለጠጋ እንደሆችሁ እና በእጃችሁ እንዳለ እርግጠኛ ነኝ፡፡

ከዚህ በእጃችሁ ካለው ከአንዱ ሃብተ በመነሳትና እነዚህን ሶስት ሃብቶች አደራጅቶ በመስራት ከፍተኛ የሆነ ስኬት ውስጥ መግባት ትችላላችሁ፡፡

በዚህና በመሰል ጉዳይ ላይ ቀጥታ ወደ ተግባር የምትገቡበት ስልጠና የዛሬ ሳምንት ኃሙስ (ጥር 1) ይጀምራል፡፡

የምዝባ መረጃውን በፖስተሩ ላይ ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

02 Jan, 05:44

ስልጠናው አንድ ሳምንት ብቻ ቀረው!

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

በስልጠናው ከምንዳስሳቸው ነጥቦች የተወሰኑት

1. ሃሳብን ስለማደራጀት እንሰለጥናለን

ይህ ክፍል፣ የሁሉም መነሻ የሆነውን ሃሳባችን ካልተደራጀ በስሜታችን፣ በተግባራች፣ በልማዳችንና በወደፊት ፍጻሜያችን ላይ ያለውን ተጽእኖ ያመላክተናል፡፡

2. ሃብታችንን ስለማደራጀት እንሰለጥናለን

ይህ ክፍል፣ በዛም አነሰም ሁላችንም ያሉንን ሶስት ሃብቶቻችን ምን ምን እንደሆኑና እንዴት እንደምናደራጃቸውና በሕይወታችን ስኬታማ እንደምንሆን ያሳየናል፡፡

3. ጊዜያችንን እና ተግባራችንን ስለማደራጀት እንሰለጥናለን

ይህ ክፍል፣ ያለንን ውስን ጊዜ እና በዚህ ጊዜ ውስጥ ማከናወን ያለብንን ነገር በምን መልኩ በማደራጀት ቀደም ብለን የምንገኝበትን መንገድ ይጠቁመናል፡፡

4. የተደራጀን ሕይወት ተግባራዊ የማድረጊያ መንገዶችን እንሰለጥናለን

ይህ ክፍል፣ ሕይወታችንን እና ተግባራችንን በማደራጀት ጉዞ ውስጥ ሂደቱን ስኬታማ የሚያደርጉልንን ሚዛናዊ የአተገባበር መርሆች አንድ በአንድ ያብራራልናል

የምዝባ መረጃውን በፖስተሩ ላይ ይመልከቱ
ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

02 Jan, 02:01

አዳጋች ነገርን ተጋፍጦ የማለፍ መርሆች
(Principles Of Risk Taking)

የምታደርጓቸው መልካም ነገሮች ሁሉ አነሰም በዛም አደጋ (Risk) አላቸው፡፡

• ሳቂታ መሆን፣ ሞኝ ሆኖ የመታየት፣

• ማልቀስ ስስና አቅመ-ቢስ ሆኖ የመታየት፣

• ሰዎችን መቅረብ፣ ጣልቃ-ገብ ሆኖ የመታየት፣

• ስሜትን መግለጽ፣ ስሜታዊ ሆኖ የመታየትና የመናቅ፣

• ራእይንና ሕልምን ማካፈል፣ የሰዎች ማሾፊያ የመሆን፣

• መውደድና ማፍቀር፣ መሄጃ እንደሌላቸው የመታየትና የመገፋት፣

• ዓላማን ይዞ ወደፊት መራመድ፣ ለእንቅፋትና ለተቃውሞ የመጋለጥ . . . አደጋ አላቸው፡፡

አደጋ ተፈርቶ ግን ያመንንበትን ከማድረግ አንመለስም፡፡ አደጋን ፈርቶ ያመኑበትን ትክክለኛ ነገር አለመኖርን የመሰለ አደገኛ ነገር የለም፡፡

ቅድመ-ጥያቄዎች

1. ይህ እርምጃው ከዋናው ራእዬና ዓላማዬ ጋር ይስማማል?

2. ይህንን እርምጃ በመውሰዴ ምክንያት ሊመጣ ያለውን የአደጋ ጥግ ተገንዝቤ ውስጤን አዘጋጅቻለሁ?

3. ይህንን እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሳሁት አንድን ነገር በመፍራት እየሸሸሁ ነው?

4. ይህንን እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሳሁት አንድን የማያዛልቅና ጊዜያዊ ጥቅም ለማግኘት ተታልዬ ነው?

5. ይህንን እርምጃ ለመውሰድ ምንም የጥቅም ወይም የጉዳት ትስስር ከሌለው አማካሪ ጋር ተማክሬአለሁ?

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

01 Jan, 17:00

“በራስ መተማመን” (Self Confidence) እና “በራስ ላይ ያለ ግምት” (Self Esteem)

ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ ሰዎች ዓላማቸውን ለማሳካት አስገራሚ አቅም እና የጋለ ፍላጎት እያላቸው እንኳን ብዙ ወደ ፊት መንቀሳቀስ ሲያስቸግራቸው ራሳቸውን ያገኙታል፡፡

ይህ ከሚሆንበት ዋና ዋና ምክንያቶች አንደኛው “በራስ መተማመን” (Self Confidence) ወይም “በራስ ላይ ያለ ግምት” (Self Esteem) ወይም ደግሞ ሁለቱም የወረዱ ሲሆኑ ነው፡፡

እዚህ ላይ ያለው አስቸጋሪ ነገር፣ ሰዎች በእነዚህ በሁለቱ መካከል ለይቶ አለማወቅና፣ የየትኛው ጉድለት ምን አይነት ችግር እንደሚያስከትል አለማወቅ ነው፡፡

“በራስ መተማመን” (Self Confidence) ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ሁኔታ ሚዛናዊ ካልሆነ ምልክቱ ምንድን ነው? የሚያስከትለውስ መዘዝ ምንድን ነው?

ወይም “በራስ ላይ ያለ ግምት” (Self Esteem) ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ሁኔታ ሚዛናዊ ካልሆነ ምልክቱ ምንድን ነው? የሚያስከትለውስ መዘዝ ምንድን ነው?

በሚቀጥለው ሳምንት ኃሙስ ጥር 1 ቀን የሚጀምረው ስልጠና ከሚያስገነዝባችሁ እውታዎች አንዱ ይህ ከላይ የተገለጸው ሃሳብ ነው፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

01 Jan, 10:30

ያልተደራጀ እሳቤ የተዘባረቀ ሕይወትን ይወልዳል

1. ከዚህ በፊት አስበንባቸው የተውናቸውን ነገሮች እንደገና እያሰቡ በመተው ዑደት ውስጥ መመላለስ፡፡

2. አንዴ በብርታት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በተስፋ መቁረጥ ስሜት መካከል መዋዠቅ፡፡

3. የሌሎች ሰዎችን እንቅስቃሴና ስኬት መሰል ተግባር ስንመለከት መነሳሳት፡፡

4. በነገሮች ላይ እርግጠኛ አለመሆንና መወላወል፡፡

5. አንድን ነገር ከየት ጀምረን ወደ የት እንደምንወስደው እርግጠኛ አለመሆን፡፡

6. በሃሳብ ደረጃ የምናውቃቸውን ነገሮች ወደተግባር ለመለወጥ መቸገር፡፡

7. በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር ላይ ለመስራናት ለመለወጥ መሞከር፡፡

ለዚህ የሚረዳችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

01 Jan, 10:00

“የአንድን ሰው አቅም የሚያደክመው ሰዎች ስለ እሱ የሚያስቡትና በእሱ ላይ ያላቸው ግምት ሳይሆን እሱ አምኖ የተቀበለው የሰዎች አመለካከት እና ንግግር ነው” (Today’s Wisdom)

• ጨዋ ጨዋዎችን ሰዎች በአጠገባችሁ አድርጉ!

• ጥሩ ጥሩውን አስቡ!

• መልካም መልካሙን ስራ ስሩ!

• ከፍ ያለውንና የላቀውን እቅድ አውጡ!

• በዙሪያችሁ የሚከናወነውን ነገር ተወት አድርጉና ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ!

• እውቀታችሁን፣ ልምምዳችሁን፣ የተፈጥሮ ስጦታችሁን፣ ጊዜያችሁን፣ ገንዘባችሁን ሰብስቡና አደራጁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/https://t.me/Dreyob

Dr. Eyob Mamo

01 Jan, 05:31

"የአንድ ሰው ማንነት በግልጽ የሚታየው ሰዎች ስለ እሱ በሚያወሩበት ነገር ሳይሆን እሱ ስለ ሌሎች ሰዎች በሚያወራቸው ነገሮች ነው” (Today’s Wisdom)

• ዝም ብላችሁ ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ!

• ዝም ብላችሁ ሕይወታችሁን አደራጁ!

• ዝም ብላችሁ ወደ ፊት ገስግሱ!

• ዝም ብላችሁ በስራችሁ አስመስክሩ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/https://t.me/Dreyob

Dr. Eyob Mamo

01 Jan, 05:17

አዲስ የtelegram (online / Live) ስልጠና!

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

• ሕይወታችሁ ዝብርቅር እንዳለ የሚሰማችሁ ከሆነ፣

• የየእለት ተግባራችሁን በስርአት ማደራጀት ግር የሚላችሁ ከሆነ፣

• አንድን የጀመራችሁትን ነገር እስከፍጻሜ መቀጠል የሚያታግላችሁ ከሆነ፣

• ሃሳባችሁን ማደራጀት፣ መሰብሰብ እና ወደ ተግባር መለወጥ ግራ የሚገባችሁ ከሆነ፣

• ማሕበራዊ ግንኑነታችሁ መልክ ያጣና ግራ የሚያጋ ከሆነ፣

• በአጭሩ ሕይወታችሁን ማደራጀት የምትፈልጉ ከሆነ፣

ይህ ስልጠና ለእናንተ ነው፡፡

ፍላጎቶትን ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link inbox ያድርጉና መረጃ ይቀበሉ፡፡

@DrEyobmamo

ለበለጠ መረጃ ፖስተሩን ይመልከቱ፡፡

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

01 Jan, 02:00

ሃላፊነታችሁን ለዩ!

1. ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እናንተ በፍጹም ሃላፈነትን መውሰድ የለባችሁም

እናንተ ከሰዎቹ ጋር ያላችሁን ግንኙነት በተቻላችሁ መጠን ጤናማ የማድረግ ሃላፊነታችሁነ ተወጡ እንጂ እነሱ ለሚሰማቸው ስሜት ተጠያቂው እናንተ እንደሆናችሁ በማሰብ በፍጹም እናንተ መሸከም የለባችሁም፡፡ እናንተም ብትሆኑ ለሚሰማችሁ ስሜት ሌሎችን ተጠያቂ ማድረግ የለባችሁም፡፡

2. ሰዎችን ላላጠፋችኋቸው ነገር በፍጹም ይቅርታ መጠየቅ የለባችሁም፡፡

ሰዎችን አንድ ጥፋት ካጠፋችኋቸው፣ ይቅርታ የመጠየቅና ተግባራችሁን የማረም ሃላፊነት አለባችሁ እንጂ እናንተ ምንም ባላጠፋችሁት ጥፋት ገና ለገና እነሱ ስለከፋቸው ይቅርታ መጠየቅ የለባችሁም፡፡ እናንተም ብትሆኑ ሰዎችን በሆነ ባልሆነ በመኮነን ይቅርታ እንዲጠይቋችሁ መጫን የለባችሁም፡፡

3. ደጋግመው ከሚጎዷችሁ ሰዎች ጋር አብሮነታችሁን እንደ ቀድሞው የማድረግ ግዴታ የለባችሁም፡፡

ሰዎች ከጎዷችሁ በኋላ ይቅርታን ቢጠይቋችሁ ይቅር ማለታችሁ በጣም ጤናማ አካሄድ ሆኖ ሳለ፣ ግንኙነታችሁን ግን እንደቀድሞው የማድረግ ግዴታ የለባችሁም፡፡ ይቅርታ የግንኙነት ጤናማነትን ሲያመለክት፣ አብሮነት ደግሞ የግንኙነትን አጋርነት ጠቋሚ ነው፡፡ ሰዎችን ይቅር በማለት ነገሩን መተው ይጠበቅባችኋል እንጂ ከእነሱ ጋር አብሮ መዋልና መስራት የለባችሁም፡፡ (ይህ ነጥብ የትዳር ግንኑነትን አይወክልም)

ሰዎች ለሚያስቡት፣ ለሚያደርጉትና ለሚሰማቸው ስሜት ሃላፊነት እንዲወስዱ መተውን ልመዱ፡፡ ያንን ስታደርጓቸው ሁል ጊዜ ለሰው በመጨነቅና የእናንተ ያልሆነውን ሸክም በመሸከም ከሚመጣ ከራስ ጋር የመለያየት አጉል ተጽእኖ ነጻ ትሆናላችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/https://t.me/Dreyob

Dr. Eyob Mamo

01 Jan, 01:59

ሃላፊነታችሁን ለዩ!

Dr. Eyob Mamo

31 Dec, 06:59

የብዙ ሰዎች ጥያቄ!

ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡

በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-

1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)

2. እሴት-ተኮር (Value-based)

እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡

ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

https://t.me/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

31 Dec, 04:51

ፉክክር ወይሰ ውድድር?

ፉክክር የሚለው ሃሳብ አሉታዊ ገጽታ አለው፡፡ ሌላውን ሰው ጥሎ ለመነሳት መሞከርን፣ የግልን ውጤት ከሌላው ሰው ጋረ ከማነጻጸር የሚመጣ የዝቅተኛነት ስሜትን፣ ሌላው ሰው ሲሳካለት ጥሩ ስሜት ያለመሰማት ሁኔታንና የመሳሰሉትን ያመለክታል፡፡

ውድድር የሚለው ሃሳብ አዎንታዊ ገጽታ አለው፡፡ ሌላው ሰው የራሱን ሩጫ እንደሚሮጥ ሁሉ እኛም የራሳችንን ሮጠን ተሽሎ መገኘትን፣ የግልን ውጤት ለራሳችን ካወጣነው የልህቀጥ ጣሪያ አንጻር በማነጻጸር ካለማቋረጥ ማደግን፣ ሌላው ሰው ሲሳካለት ደስተኛ በመሆን ከዚያ ሰው ትምህርት ማግኘትንና የመሳሰሉትን ያመለክታል፡፡

የፉክክር ባህሪይ ሲኖረን የራሳችን ግብ ስለማይኖረን ሁሉን ነገር የምናነጻጽረው ሌላው ሰው ከደረሰበት አንጻር ነው፡፡ ውጤቱም፣ ተስፋ መቁረጥና ከየት ተጀምሮ ወደ የት አቅጣጫ እንደሚሄድ የማይታወቅ ሕይወት መኖር ነው፡፡

የውድድር ባህሪይ ሲኖረን ግልጽ የሆነን ግን ካወጣን በኋላ ሁሉንም ከዚያ ግብ አንጻር እንቃኘዋለን፡፡ ውጤቱም ዓላማ-መር የሆነ እና በሚገባ የተደራጀ ሕይወት መኖር ነው፡፡

ይህንን አስገራሚ ልምምድ ለመለማመድ የሚግዛችሁ ስልጠና ተዘጋጅተላችኋል፣ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎችም ተመዝግበዋል፡፡ አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

31 Dec, 02:00

የኃይልና የስልጣንህ ጉዳይ!

“የአንድን ሰው እውነተኛ ባህሪይ ለማወቅ ከፈለግህ ኃይል (ስልጣን) ስጠው” - Abraham Lincoln

የአንድ ሰው እውነተኛ ባህሪይና ማንነት ከሚታይባቸው ሁኔዎች መካከል አንዱ፣ በእጁ የገባውን ኃይልና ስልጣን አያያዙ ሁኔታ ነው፡፡ ሰው አንድን ነገር ለማድረግ ወይም ለመከልከል ሙሉ ኃይልና ስልጣን እንዳለው ሲያስብ የሚገልጠው ባህሪይ ስለማንነቱ ብዙ ይናገራል፡፡ በተቸገረና የሰዎችን ድጋፍ በፈለገበት ጊዜ የነበረው ባህሪይና አሁን ኃይልና ስልጣን ሲኖረው የሚያንጸባርቀውን ባህሪይ ተመልክተን ስለሰውየው ማንነት መናገር ይቻላል፡፡

የአንድ ሰው እውነተኛ ማንነት የሚገለጠው ኃይልና ስልጣን በእጁ ሲገባ ነው፡፡ ስልጣኑን ተጠቅሞ ይታበያል ወይስ ትህትና ይታይበታል? ኃይልንና ጉልበቱን ተጠቅሞ ሰዎችን ያበረታል ወይስ ያደቅቃል? ስልጣኑ የቁጣ መግለጫ ነው ወይስ የትእግስት ምሳሌ? እነዚህ ጥያቄዎች የሰውን ማንነት በግልጽ ስለሚያሳዩ መልስ ሊያገኙ የሚገባቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡

• አንድ ሰው ከአንተ ውጪ ኑሮውን መግፋት እንደማይችል ስታውቅ በዚያ ሰው ላይ ስልጣን አለህ፡፡

• የአንድ ሰው ጤንነት አንተ በምትሰጠው የህክምና እርዳታ ላይ የተደገፈ ሲሆን በዚያ ሰው ላይ ስልጣን አለህ፡፡

• አንድን ሰው ስራው ላይ እንዲቆይ ወይም እንዳይቆይ የማድረግ የአለቅነት አቅም ሲኖርህ በዚያ ሰው ላይ ስልጣን አለህ፡፡

• በአንድን ሰው መፍረድ፣ ወደ እስር ማውድ፣ ባለህ ሹመት መጉዳት ስትችል በዚያ ሰው ላይ ስልጣን አለህ፡፡

• የአንድን ተማሪ የውጤት ሁኔታ እንደፈለክ ማድረግ የምትችልበት አቅሙ ካለህ በዚያ ሰው ላይ ስልጣን አለህ፡፡

ይህንን ስልጣንህን ስታስብ ምን እንደሚሰማህና ምን እንደምታደርግ ንገረኝና ስለማንነትህ ልንገርህ!

Dr. Eyob Mamo

30 Dec, 17:01

ከልምምዳችን ባሻገር!

በአለም ላይ አብዛኛዎቹ በስራ፣ በንግድ፣ በማሕበራዊ ተጽእኖና በሌሎችም ዘርፎች የተሳካላቸው ሰዎች . . .

1. አጀማመራቸው ላይ ብዙም እንደማይሳካላቸው የተነገራችው ሰዎች ናቸው

2. አስተዳደጋቸው ላይ በቤተሰብ ጥሩ ድጋፍ ያላገኙ ናቸው

3. በወቅቱ በእነሱ እድሜ ከነበሩት አብዛኛዎቹ ሰዎች በቅልጥፍና ዘገም ያሉ ሰዎች ነበሩ

እዚህ ሰዎች ግን እነዚህን አሉታዊ ሁኔታዎች አልፈው ለመሄድ የቆረጡ፣ ሰዎች ከሚነግሯቸው አሉታዊ ንግግር ይልቅ ለራሳቸው የሚናገሩት አዎንታዊ ነገር ወሳኝ እንደሆነ የገባቸው እና የወደፊታቸውን ካቀዱ በኋላ ግራ እና ቀኝ ሳይሉ የተንቀሳቀሱ ሰዎች ናቸው፡፡

ከምንም አይነት ሁኔታ ተነስታችሁ የትኛውም ደረጃ መድረስ እንደምትችል አስባችሁ ወደ መኝታችሁ ሂዱ፡፡

መልካም እንቅልፍ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/https://t.me/Dreyob

Dr. Eyob Mamo

29 Dec, 12:13

አዲስ የtelegram (online) ስልጠና!

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ባለፈው ከነበረን የtelegram (online) ስልጠና በኋላ ባደረግነው ጥናት አብዛኛዎቻችሁ በየሶት ወሩ ስልጠና እንዲሰጥ በጠየቃችሁት መሰረት የተዘጋጀ!

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

29 Dec, 04:41

ተመችቶኝ ነው ተቀርቅሬ?

በአንድ ሁኔታ ወይም ቦታ ለረጅም ጊዜ እንደቆያችሁ ከተሰማችሁና ስለ ለውጥ እያሰባችሁ ካልተንቀሳቀሳችሁ ሁኔታችሁ ከሁለቱ ስለማያልፍ እዚህን ጥያቄዎች ጠይቁ፡-

1. ምቹ ቀጠና ውስጥ ሆኜ ይሆን?

ምቹ ቀጠና ማለት በአንድ ሁኔታ ወይም ቦታ ላይ ለረጅም ጊዜ ከመቆየታችን የተነሳ ሁኔታውን ስንለምደው፣ ሲመቸንና አዲስ ነገር ለመጀመር መነሳሳቱን ስናጣው ማለት ነው፡፡

ከዚህ ምቹ ስፍራ ለመውጣት አለመቻል የተለያዩ መንስኤዎች ሊኖሩት ይችላል፡፡

ለምሳሌ፣ ማደግና መለወጥ እንዳለብን ብናውቅም ያለንበትን ሁኔታ መውደድ፣ ወደ አዲስ ነገር መግባትን መፍራት፣ የሰዎች አጉል ወሬና ምክር መስማት እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከዚህ አይነቱ ሁኔታ ወጥተን ወደ ተሻለ ሁኔታ ውስጥ ለመግባት የመነሻው መንገድ ቁርጠኛ ውሳኔን ማድረግ ነው፡፡

2. ቅርቃሮ ውስጥ ሆኜ ይሆን?

ቅርቃሮ ማለት ፈጽሞ የማንቀበለውና የማንፈልገው ሁኔታ ውስጥ በጊዜው አምነንበት ወይም ከአቅማችን በላይ በሆነ ምክንያት ለጊዜው ብለን ገብተን ከዚያ ለመውጣት አለመቻል ማለት ነው፡፡

ከዚህ ሁኔታ ለመውጣት አለመቻል የተለያዩ መንስኤዎች ሊኖሩት ይችላል፡፡

ለምሳሌ፣ የሰው ድጋፍ ማጣት፣ የገንዘብ እጥረትና ተስፋ መቁረጥ አይነት ልምምዶች እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከዚህ አይነቱ ሁኔታ ወጥተን ወደ ተሻለ ሁኔታ ውስጥ ለመግባት የመነሻው መንገድ የሰዎችን ምክርና እገዛ መፈልግ ነው፡፡

በተጠቀሰውና በመሰል ሃሳቦች ላይ የሚረዳችሁ ስልጠና በቅርቡ እንደሚሰጥና በርካቶች እየተመዘገቡ እንደሆነም አትዘንጉ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

29 Dec, 04:41

ተመችቶኝ ነው ተቀርቅሬ?

Dr. Eyob Mamo

29 Dec, 03:01

https://www.youtube.com/watch?v=V7NB1UHdH14

Dr. Eyob Mamo

28 Dec, 16:47

የማይመዘን ነገር ስኬታማነቱ አይታወቅም

በሕይወታችሁ የምታከናውኗቸውን ማንኛውም ነገሮች ስኬታማነት ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ መመዘኛ እና መለኪያ ይኑራቸው፡፡

ለምሳሌ የሚከተሉትን አባባሎች አስቧቸው . . .

“በሚቀጥለው አመት እውቀቴን ማሳደግ እፈልጋለሁ” የሚል ሰው በእውቀት ማደጉን የሚመዝንበት አንድ መመዘኛ ካላስቀመጠ የማደጉን ስኬታማነት በምን ይመዝነዋል?

“ከአምስት አመት በኋላ ሃብታም መሆን እፈልጋለሁ” የሚል ሰው ከአምስት አመት በኋላ የሃብቱ መጠን ስንት እንዲሆን መጠኑን እደፈለገ ካላስቀመጠ ስኬታማነቱን በምን ይለካዋል?

እነዚህና መሰል አባባሎች በፍጹም መለኪያ እና መመዘኛ ስለሌላቸው ስኬታማነታቸው ማነታቸውን የምናውቅበት መንገድ የለንም፡፡

• መመዘንና መለካት የማንችላቸውን ነገሮች መቆጣጠር አንችልም፡፡

• መቆጣጠር የማንችላቸውን ነገሮች ደግሞ አቅጣጫና መልክ ማስያዝ አንችልም፡፡

• አቅጣጫ ማስያዝ የማንችላቸውን ነገሮች ደግሞ ማሳደግና ምርታማ ማድረግ አንችልም፡፡

• ያላሳደግናቸውን ነገሮች ደግሞ ፍሬያቸውንና ውጤታቸውን መሰብሰብ አንችልም፡፡

ይህንን አይነቱን ስኬታማ ጉዞ ለመጀመር በሕይወታችን የተደራጀ አመለካከትና ሕይወት ያስፈልገናል፡፡ ለዚህ ነው መንገዱን የሚያመላክታችሁ ስጠናን ያዘጋጀሁላችሁ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

28 Dec, 14:00

የሚያነቡ እና የሚሰለጥኑ ሰዎች . . .

1. ካለማቋረጥ ራሳቸውን ያሻሽላሉ

2. ጊዜያቸውን በተራ ነገር ከማሳለፍ ይጠበቃሉ

3. ጸሃፊዎቹ እና አሰልጣኞቹ ብዙ ጊዜ ወስደው በልምምድና በጥናት ያገኙትን እውቀት በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ይቀስማሉ

4. አእምሯቸው በንባብ እና በስልጠና ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ስለሚል ለተራ ወሬና ለወረዱ ነገሮች ጊዜውም ሆነ ፍላጎቱ አይኖራቸውም

5. የውስጥ እርካታ፣ መረጋጋትን እና በራስ መተማን ያዳብራሉ

አንብቡ! ሰልጥኑ! እደጉ! ተለወጡ! ከተራውና ከማይጠቅማችሁ ወሬ ውጡ! በሃገራችንም ሆነ በውጪ ሃገር ሰዎች የተጻፉ መልካም ነገር የያዙ መጽሐፎችን እየመረጣችሁ አንብቡ!

ይህንን ምክር ተግባራዊ ማድረግን ለመጀመር ከፈለጋችሁ ጥር 1 ቀን የተዘጋጀላችሁ ስልጠና መካፈል ትችላላችሁ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

28 Dec, 11:35

የሚጀመረው፣ የሚቀጠለውና የሚቆመው!

መጀመር፡- አንዳንዶቻችን አንድን ነር መጀመር ነው የሚያስቸግረን፡፡ ይህ ሲሆን፣ የምናስባቸውና የምናቅዳቸው ነገሮች ሁሉ እየተንከባለሉ ከንቱ ሆነው ይቀራሉ፡፡

መቀጠል፡- ሌሎቻችን ደግሞ መነቃቃትና መጀመር ችግር የለብንም፣ የጀመርነውን መቀጠል ግን ያስቸግረናል፡፡ ይህ ሲሆን፣ ነገሮችን እየጀመርንን እያቆምም ጊዜን፣ ስሜትን፣ ገንዘብንና በሰዎች የመታመንን ሁኔታ እየከሰርን እንሄዳለን፡፡

እንደገና መጀመር፡- ከዚህ በተጨማሪ፣ አንድን ያቆምነውን ነገር በእንዴት አይነት ሁኔታ እንደገና መጀመር እንዳብን የማናውቅና የሚያስቸግረን ሰዎች አለብ፡፡ ይህ ሲሆን፣ ጀምረን ያቆምናቸውን ነገሮች ምነው ባላቆምኩኝ በሚል ጸጸት ውስጥ እንኖራለን፡፡

ማቆም፡- ከላይ ከተጠቀሱት ትንሽ ለየት ያለው ደግሞ ካቆምናቸው ነገሮች መካከል የትኞቹ እንደገና መቀጠል፣ የትኞቹ ደግሞ በዚያ መተው እደሚገባቸው የመለየጥ ጥበብ የሚጎድለን አለን፡፡ ይህ ሲሆን፣ ካቆምነው በኋላ ጊዜው ያለፈበትን ነገር እንደገና ለመጀመር እንታገላለን፡፡

ጥር 1 ቀን የተዘጋጀላችሁ ስልጠና ከሚያስተምራችሁ በርካታ እውነታዎች አንዱ እነዚህን የሚያስተምራችሁ ክፍል ይገኝበታል፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

27 Dec, 04:43

ሶስቱ የግል ሕይወት አደረጃጀት መነሻዎች

ሕይወታቸውን ያደራ ሰዎች ቤታቸውን፣ ስራቸውን፣ ንግዳቸውንም ሆነ ማሕበራዊ ግንኙነታቸውን መልክ መልክ አስይዘው መኖር አያስቸግራቸውም፡፡ ይህንን አስገራሚ ልምምድ የማዳበር መነሻዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ማወቅ

ከሁሉም በፊት ምን አይነት ሕይወት መኖር እንደምንፈልግ፣ ምን ማከናወን እንዳሰብንና የሕይወታችን ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ ማወቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ካላወቅን ሕይወታችንን በምን ዙሪያ ማደራጅ እንዳለብን ማሰብ ያስቸግረናል፡፡

2. ማቀድ

ምን አይነት ሕይወት መኖር እንደምንፈልግና ማከናወን የምንፈልገውን ተግባር ከለየን በኋላ በእነዚህ እውቀቶች ዙሪያ ተግባራዊ የሆኑና ከጊዜ ገደብ ጋር የተቀመጡ እቅዶችን ማውጣት አስፈላጊ ነው፡፡

3. ማደራጀት

በሚገባ ያወቅነውን ዓላማችንን ይዘን እቅዶችን ካወጣን በኋላ ሁኔታው ቀጣይነትና ጥራት እንዲኖረው ካስፈለገ ከፍተኛ የሆነ የአደረጃጀት ብቃት የግድ ነው፡፡ አደረጃጀት የሚስፈልገው ለድርጅቶች ብቻ አይደለም፡፡ ምንም ነገር ከመደራጀቱ በፊት የግል ሕይወት መደራጀት አለበት፡፡

እግረ መንገዴን በዚህ ጉዳይ ላይ ስር-ነቀል እውቀት ሊሰጣችሁ የሚችል የስልጠና ጊዜ እንዳዘጋጀሁላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡

መረጃውን ለማግኘት ሰሞኑን በመለቀቅ ላይ ያለውን ማስታወቂያ ወደኋላ መለስ ብላችሁ (scroll አድርጋችሁ) ተመልከቱ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

27 Dec, 02:00

ኩራት የሚወድ ትውልድ!

በቀላሉ የምናገኛቸው ሰዎችና ነገሮች ርካሽ እንደሆኑ የማሰብ ዝንባሌ ያለው ባህል ውስጥ ነው ያደግነው፡፡ በዚህ እሳቤ ተጽእኖ ስር የመውደቅ አደገኛነት ዘርፈ-ብዙ ነው፡፡

ለሰዎች ብዙ ጠቃሚ ነገር ይዘን ሳለን ቀለል ብለን ከተገኘን ሕብረተሰቡ ያራክሰናል የሚል ስጋት ስለሚያድርብን እንዳካበድን እና እንደኮራን አንድም ነገር ሳንሰራ ዘመናችንን እናባክናለን፡፡

በነገራችን ላይ ለመከበርና ተፈላጊ ለመሆን የግድ ማካበድ እንደሌለባችሁና ጨዋ ማንነትና የከበረ ተግባር ማከናወን ብቻ እንደሚስፈልጋችሁ ታውቃላችሁ?

እኛም ብንሆን በቀላሉ የሚገኙ ሰዎችንና ሁኔታዎችን እንደ ርካሽና እንደ ቀላል ስለምንቆጥራቸው ብዙ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው እድሎች ያመልጡናል፡፡

በነገራችን ላይ በሕይወታችሁ እጅግ ወሳኝና ጠቃሚ የሚባሉት ሰዎች በየቀኑ በቀላሉ የሚገኙላችሁ ሰዎች (ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ የትዳር አጋር . . .) እንደሆኑ ታውቃላችሁ? በቀላሉ ስለተገኙ አይቅለሉባችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

26 Dec, 17:14

የተለያዩ አዋቂዎች የሚነግሩን በጥቂቱ ቢለያይም አንድ ጤናማ ሰው በደቂቃ በአማካኝ በደቂቃ ከ 20 ጊዜ በላይ ሊተነፍስ ይችላል፡፡

ይህ የመተንፈስ ስጦታ በዚህች ምድር ላይ በሕይወት እንድንኖር ፈጣሪ ከሰጠን ታላላቅ ስጦታዎች መካከል ዋነኛው ነው፡፡

ይህንን ሰዎች ከእነሱ እንዳይወሰድባቸው ምንም ነገር ከመክፈል ወደኋላ የማይሉትን በደቂቃ ከ 20 ጊዜ በላይ የመተንፈስ ስጦታ በየደቂቃው እደጋገመ ከ 20 ጊዜ በላይ ፈጣሪ ከሰጠን፣ ለህልውናችን እምብዛም መዋጮ ለሌላቸው ነገሮች መጨናነቃችንን ትንሽ ቀነስ አድርገነው ወደ መኝታ ብንሄድ ምን ይመስላችኋል?

መልካም እንቅልፍ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

26 Dec, 10:48

ስለተመኛችሁ ሳይሆን ስለሰራችሁ!

ለሕልውናችሁ፣ አልፎም ለእናንትም ሆነ ለቤተሰቦቻችሁ እድገት ወሳኝ የሆኑትን ነገሮች የምታገኙት እኮ ስለተመኛችሁ ሳይሆን ሆን ብላችሁ በማቀድ፣ በመስራትና ውጤት እስከሚያገኙ ድረስ በመታገል ነው፡፡

እድል ከመጣ ይምጣ፣ እስከሚመጣ ግን ጠንክራችሁ ስሩ፡፡

የሰዎች ስጦታ ከመጣ ይምጣ፣ እስከሚመጣ ግን በርቱና ስሩ፡፡

መልካም ከሰዓት በኋላ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

26 Dec, 05:07

አራቱ የግል ሕይወትን የማደራጀት ልምምዶች

1. መነሳሳት

ሕይወታችሁን ለማደራጀት ከፈለጋችሁ ከሁሉ በፊት የተደራጀ ሕይወትን አስፈላጊነትና ጥቅም፣ በተጨማሪም ያልተደራጀ ሕይወትን ጉዳት በማሰብ መነሳሳትን ይጠይቃል፡፡

2. ውሳኔ

ሕይወታችሁን ለማደራጀት በቀጣይነት የሚያስፈልጋችሁ ከምቹ ስፍራችሁ የመውጣት ውሳኔ ነው፡፡ ምቹ ስፍራ ልክ እንደ ስያሜው ይመቻል፡፡ ስለሆነም ከዚያ ስፍራ ለመውጣትና ወደ አዲስ የሕይወት ዘይቤ ለመግባት ውሳኔ ይጠይቃል፡፡

3. ክህሎት

ምንም ያህል ብንነሳሳ እና ብንወስንም፣ የአደረጃጀት ሂደት እንዴት እንደሆነ ካላወቅን ግራ ከመጋባት አናልፍም፡፡ ብዙ ሰዎች ያላቸው ችግር ይህ ነው፡፡ ሕይወታቸውን እንዴት ማደራጀት እንዳለባቸው አያውቁትም፡፡

4. ዲሲፕሊን

ሕይወትን የማደራጃው ወሳኙና የመጨረሻው ነገር ዲሲፕሊንን የማዳበር ጉዳይ ነው፡፡ መነሳሳቱ፣ ውሳኔውና ክህሎቱ ኖሮን ሳለ፣ የመጀመር፣ የመቀጠልና እስከጥጉ የመውሰድ ዲሲፕሊን ከሌለን የተደራጀ ሕይወት ለመኖር ያስቸግረናል፡፡

አንባቢዎቼ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ በቂ ንባብና ስልጠና በመውሰድ ሕይወታችሁን መስመር እንድታስይዙ ትመከራላችሁ፡፡

በነገራችን ላይ “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life" በሚል ርእስ ስር በዶ/ር ኢዮብ ማሞ የተዘጋጀ ስልጠና ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29 ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 በonline (telegram live) ይሰጣልና አያምልጣችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

26 Dec, 02:00

ሕይወት ከባድም ቀላልም ነች!

“ዛሬ ሕይወት ከበድ ተደርጋ ስትያዝ ነገ ቀለል ትላለች፣ ዛሬ ቀለል ተደርጋ ስትያዝ ደግሞ ነገ ከበድ ትላለች” – Dave Kekich

ሕይወትን ከበድ አድርጎ መያዝ ማለት የግል ዲሲፕሊንን በማዳበር ለመልካም ውጤት ሲባል ከበድ ያሉ ነገሮችን መጋፈጥና ማድረግ ማለት ነው፡፡ ሕይወትን ቀለል አድርጎ መያዝ ማለት ደግሞ ካለምንም ዲሲፕሊን የመጣልንን፣ የቀለለንንና ለጊዜው ብቻ ጥሩ ስሜት የሰጠንን በማድረግ መኖር ማለት ነው፡፡

ከላይ በተጠቀሰው አውድ መሰረት ዛሬ ሕይወትን ቀለል አድርጎ መኖር ማለት ዛሬ ለመደሰትና ዛሬ ሁሉም ነገር እንዲቀለን ስንል ከነገ የተቀማጭ ሂሳባችን አውጥቶ መክፈል እንደማለት ነው፡፡ ስለሆነም “ዛሬ” አልፎ “ነገ” ሲመጣና “ዛሬ” “ትናንት” ሲሆን አሁን የደረሰውን “ዛሬን” “ትናንትና” ቀላል ኑሮ ለመኖር ስንል ስለከፈልነው ኑሮ እጅጉን ይከብደናል፡፡

በጣም ደካማ ፈቃድ ያለውን ሰው አስቡት፡፡ አንድ ነገር ለማድረግ ያስብና ሁኔታው ከበድ ካለው ይተወውና ወደቀለለው ነገር ዞር ይላል፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሰው ምንም ነገር ማከናወን ካለመቻም በላይ ዛሬ የቀለለው ሕይወት ነገ እንደሚከብደው ግልጽ ነው፡፡

በተቃራኒው ዛሬ ሆን ብሎ ከባባድ ምርጫዎችን በመምረጥ ተግቶ የሚማር፣ ጠንክሮ የሚሰራ፣ ወጥሮ የሚያጠራቅምና ታግሶ ችግርን የሚያልፈውን ሰው ተመልከቱት፤ ይህ ሰው ዛሬ ስለሚከፍል ቢከብደውም ነገ ግን ስለሚከፈለው ይቀለዋል፡፡

መልካም ውሎ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

25 Dec, 16:00

Best Gift Ever!

ለቅርብ ወዳጆቻችን ልንሰጣቸው ከምንችላቸው የቁሳቁስ ስጦታዎች ይልቅ የላቀው ስጦታ የአብሮነት ስጦታ ነው፡፡

እውነተኛ የሆኑ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ ፍቅረኞች፣ የትዳር አጋሮች . . . ከሁሉም በፊት የሚፈልጉት የእኛን አብሮነት ነው፡፡

ይህ አብሮነት ጊዜን በመስጠት፣ የሚያሳስባቸውን ነገር በማድመጥ፣ በስሜታቸው ላይ ሳይፈርዱ በመገንዘብ፣ ደስ ሲላቸው ሳንቀና አብሮ ደስ በመሰኘትና በችግራቸው ጊዜ ባለመሸሽ ይገለጣል፡፡

ምንም ነገር ባንሰጣቸውም እንኳን ለምንም ነገር አሳልፈን እንደማንሰጣቸው ማወቃቸው ብቻ ይበቃቸዋል፡፡ ምንም አቅርቦት ባይኖረን እንኳን ራሳችንን ካቀረብንላቸው ያረካቸዋል፡፡

ጣፋጭ እንቅልፍ ይሁንላችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

25 Dec, 08:49

አዲስ የtelegram (online) ስልጠና!

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ባለፈው ከነበረን የtelegram (online) ስልጠና በኋላ ባደረግነው ጥናት አብዛኛዎቻችሁ በየሶት ወሩ ስልጠና እንዲሰጥ በጠየቃችሁት መሰረት የተዘጋጀ!

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

25 Dec, 08:11

እውነተኛው ሰው!

በሕይወታችሁ ከምንም አይነት የግል ፍላጎትና ጥቅም ሳይነሳ እውነቱንና የሚነግራችሁ ቢያንስ አንድ ሰው የመኖሩን ጉዳይ እርግጠኞች ሁኑ፡፡

• ከሰጣችሁ ሃሳብና ከነገራችሁ የግሉ አመለካከት የተነሳ ቅር ብትሰኙበትም እንኳን እናነተን ለማትረፍ ሲል ያንን የሚያደርግ ሰው ያስፈልጋችኋል፡፡

• ከመከራችሁ ምክር የተነሳ በምትወስኑት ውሳኔ ውስጥ ምንም ጥቅም እንደማያገኝ እያወቀ ሃሳቡን የሚነግራችሁ ሰው ያስፈልጋችኋል፡፡

• ምክሩን ብትሰሙትም ሆነ ባትሰሙት በእናንተ ላይ ያለው አመለካከት ፈጽሞ የማይለወጥ ሰው ያስፈልጋችኋል፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

25 Dec, 02:00

ከመወሰናችሁ በፊት!

ዛሬ የምትኖሩት ኑሮ የትናንትና ምርጫና ውሳኔያችሁን አመልካች ነው፡፡ የዛሬው ደግሞ የነገውን ኑሮ ይወስናል፡፡ እናንተ ባትመርጡና ባትወስኑ እንኳን እሱ በራሱ “ያለመምረጥ ውሳኔ” ይባላል፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲወስኑላችሁ የመምረጥ ውሳኔ!

አንድን ነገር የማድረግ ወይም የመተው ውሳኔ ሲኖርባችሁ፣ ከአንድ ሰው ጋር የመቀጠል ወይም የመለየት ውሳኔንም ስትጋፈጡ፣ መመለስ ያለባችሁ የመጀመሪያ ጥያቄ፣ “ይህንን ውሳኔ የግድ መወሰን ያለብኝ ጊዜ መቼ ነው?” የሚለውን ነው፡፡

የግድ ለመወሰንና ለመቁረጥ የተወሰነ ጊዜ ካላችሁ አሁኑኑ መወሰን እንደሌለባችሁ አስታውሱ፡፡

• መውሰድ የምትችሉትን ያህል ጊዜ ውሰዱ - ይህንን ማድረግ ጊዜ በራሱ የሚያሳያችሁን እውነታ የማየትን እድል ይሰጣችኋል፡፡

• ማሰብ የሚገባችሁን ሁሉ አስቡ - ይህንን ማድረግ ስሜታችሁን በማረጋጋት ውሳኔያችሁ ስሜታዊ ከመሆን ይልቅ ምክንያታዊ እንዲሆን ያግዛችኋል፡፡

• ማማከር የሚገባችሁን ተገቢ ሰው ሁሉ አማክሩ - ይህንን ማድረግ እናንተ ያላያችሁትን ሌላ ጎንና ገጽታ ከጥበበኛ መካሪ እንድታገኙ መንገዱን ያመቻችላችኋል፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

24 Dec, 16:52

ብቻውን የቀረ ማንነት!

“ሰዎችን በውጪ ለማስቀረት በዙሪያችሁ የገነባችሁት ግንብ እናንተንም በውስጥ አጥሮ እንደሚያስቀራችሁ አስታውሱ” (Today's Wisdom)

ከአላስፈላጊ ሰዎች ለመራቅ የምታደርጉት ውሳኔ አስፈላጊ የመሆኑን ያህል፣ በማሕበራዊ ብልህነት ከሰዎች ጋር ተቻችሎ የመኖርንም ልምምድ አክሉበት፡፡

አለዚያ ብቻችሁን መቅረታችሁ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

24 Dec, 12:17

የግል ሕይወትን ማደራጀት!

ዘመኑ የሚጠይቀው አይነት የተደራጀ ሕይወት መኖርና ተግባር ማከናወን ከፈለጋችሁ እነዚህ ጥያቄዎች መመለስ የግ ነው፡-

1. የግል ሕይወቴን እንዴት ላደራጀው?

2. ሃሳቤን እንዴት መስመር ላይዘውና ላደራጀው?

3. ማሕበራዊ ሕይወቴን እንዴት በተደራጀ መልኩ ልያዘው?

4. ጊዜዬን እንዴት ላደራጀውና ለስኬት ልጠቀምበት?

5. ሃብቴን እንዴት በማደራጀት ላሳድገው?

6. የየእለት ተግባሮቼን እንደት ላደራጃቸውና ውጤታማ ላድርጋቸው?

በዚህ ርእስ ላይ ወሳኝ የሆኑ የክህሎት ግንዛቤዎችን የሚሰጣችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና ዛሬውኑ ተመዝገቡ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

24 Dec, 11:57

የጭንቀት ጅዋጅዌ

“ጭንቀት ማለት ልክ እንደ ጅዋጅዌ ጨዋታ ነው፡ ወዲህና ወዲያ ያደርጋችኋል፣ ነገር ግን የትም አያደርሳችሁም” (Quote of the day)

መፍትሄ የሚገኝለትን መፍትሄ ፈልጉለት፡፡ መፍትሄ የማይገኝለትን ለፈጣሪ ተውለት!

አዎን ከባድ ነው! አማራጩ ግን እሱ ነው!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

24 Dec, 08:00

ከዶ/ር ኢዮብ በሚከተሉት መንገዶች አገልግሎትን ማግኘት ትችላላችሁ

1. ጥያቄ እና መልስ

በዶ/ር ኢዮብ በየቀኑ ማለዳ በነጻ በሚሰጡት ትምህርቶች አማካኝነት ጥያቄ ካላችሁ በግሉ inbox በማድረ ለጥያቄያችሁ በነጻ መልስን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

2. የምክር አገልግሎት

በአንዳንድ ግራ በገባችሁ የሕይወት ሁኔታዎች ላይ የአንድ ወይም የተወሰኑ የምክር ክፍለ ጊዜያት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ጥያቄ ለማቅረብና መረጃ ለማግኘት inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

3. ስልጠና

በቴሌግራም (live) በሚሰጠው ስልጠና ላይ በመመዝገብ ስልጠናውን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ስልጠና ለመውሰድ በመተላለፍ ላይ ያለውን ማስታወቂያ በመመልከት በመመሪያው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

4. የቡድን የአካል (in person) ስልጠና

ከጓደኞቻችሁ ጋር ቁጥራችሁ ከ10 ባላነሰ ሁኔታ በግሩፕ በመደራጀት ዶ/ር ኢዮብን በማግኘት ስልጠናን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

5. ኮቺንግ

ከዶ/ር ኢዮብ ጋር ለተወሰኑ ሳምንታት በግል ሕይወታችሁ፣ በስራችሁና በመሳሰሉት ዘርፎች ላይ የኮቺንግ አገልግሎት መቀበል ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ጥያቄ ለማቅረብና መረጃ ለማግኘት inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

ለዶ/ር ኢዮብ መልእክት ለመላክ የሚከተለውን ይጠቀሙ

https://t.me/DrEyobmamo

Dr. Eyob Mamo

24 Dec, 05:00

ምርጫ ማድረግን ምረጡ! ለመወሰን ወስኑ!

ጥሩ ጥሩ ምርጫና ውሳኔዎች የሚመጡት ከልምድ ነው፡፡

ልምድ ደግሞ የሚመጣው ሕይወትን በመጋፈጥ፣ በመኖርና ከባባድ ውሳኔዎችን በመወሰን ከሚሰሩ ስህተቶችና ትምህርቶች ነው፡፡

ጸሎት አድርጉ! አስቡ! ወስኑ! ውጡ! ስሩ!

የተሳካው ያሻሽላችኋል፡፡

ያልተሳካው ያስተምራችኋል፡፡

ከዚህ ውጪ ሌላ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

24 Dec, 02:27

ማንነት ሲጨመቅ!

“ሎሚ ትክክለኛ ማንነቱ እና መራራው ጣእሙ የሚወጣው ሲጨመቅ ነው” ይባላል፡፡

የሚያጋጥማችሁ ነገርና የምትገቡበት ሁኔታ የውስጥ ማንነታችሁን ያወጣዋል እንጂ የሌላችሁን ማንነት አይሰጣችሁም፡፡

የማንነት ለውጥ ሆን ተብሎ ተሰርቶበት የሚመጣ ነገር ነው፡፡

ለምሳሌ . . .

• ገንዘብ ማግኘት ለጋስም ስግብግብም አያደርገንም፣ በውስጣችን የነበረውን ለጋስነት ወይም ስግብግብነት እድል ሰጥቶ ነው የሚያወጣው፡፡

• ማሕበራዊ ሚዲያ የመጠቀም መድረክ አስተማሪም ተሳዳቢም አያደርገንም፣ በውስጣችን የነበረውን አስተማሪነት ወይም ተሳዳቢነት እድል ሰጥቶ ነው የሚያወጣው፡፡

• በሰው መተው እና ብቻ መሆን ጠንካራም መራራም አያደርገንም፣ በውስጣችን የነበረውን ጠንካራን ወይም መራራነት እድል ሰጥቶ ነው የሚያወጣው፡፡

• ስልጣን ማግኘት ትሁትና ሰው ጠቃሚም ሙሰኛና በሰው ተጠቃሚ አያደርገንም፣ በውስጣችን የነበረውን ጠቃሚነት ወይም ጥቅመኛነት እድል ሰጥቶ ነው የሚያወጣው፡፡

ምንም አይነት ነገር ከማግኘታችሁና የትኛውም ሁኔታ ውስጥ ከመግባችሁ በፊት ራሳችሁን ፈትሹ፣ ራሳችሁ ላይ ስሩ!

ራስ ላይ መስራት ማለት . . .

1. ጨዋ የሆነ፣ የከበረ እና ለሕብረተሰቡ የሚጠቅምን ዓላማ መያዝ

2. ለዚያ የከበረ ዓላማ የሚጥን ባህሪይ ላይ መስራት

3. ለዚያ ዓላማ የሚመጥን ዲሲፕሊን ማዳበር
ማለት ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

06 Dec, 02:00

በራእይህ ትለካለህ

(“የማንነትህ መለኪያ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

“ማንነትህ የሚለካው ለወደፊቱ ባለህ ራእይ ነው እንጂ ባለፈው ታሪክህና ባለህበት ሁኔታ አይደለም” – Anonymous
ዋልት ዲዝኒ አስገራሚ የሆነ የራእይ ሰው በመሆኑና በፍጹም ተስፋ ባለመቁረጥ የሚታወቅ ሰው ነበር፡፡ ገና በለጋነቱ ለአንድ ጋዜጣ ካርቱን ስእሎችን በማቅረብ ሲሰራ፣ “ምንም አይነት ጠቃሚ ሃሳብን ማፍለቅ አትችልም” ተብሎ ነበር የተባረረው፡፡

ሁኔታው ግን ዋልት ዲዝኒን የባሰ እንዲጣጣር አነሳሳው፡፡ ካንሳስ (Kansas City) በምትባል ከተማ ውስጥ ስእሎቹን ለመሸጥ አድርጎ የነበረው የመጀመሪያ ሙከራ ሳይሳካለት ቀረ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ችሎታው እንደሌለው ጥቆማ ቢያደርጉለትም ከችሎታው ይልቅ ሕልሙ ነበረውና ተቀራኒ ሃሳቦችን ሁሉ አልፎ ለመሄድ ወሰነ፡፡

አንድ የሃይማኖት ሰው ለሚያወጣው ማስታወቂያ ትንንሽ ስእሎችን እንዲስልለት በጥቂት ክፍያ ቀጠረው፡፡ ዋልት ዲዝኒ የሚኖበት ቤት ስላልነበረው ይህ የቀጠረው ሰው አይጦች በሞሉበት የመኪና ማቆሚያ ጋራዥ ውስጥ እንዲተኛ ፈቀደለት፡፡ በዚያ አይጥ በተሞላ መጠለያ ውስጥ ሆኖ ካያቸው አይጦች መካከል የአንዷን ሚኪ (Mickey) የሚል ቅጽል ስም አወጣላት - ታዋቂዋ ሚኪ ማውስ (Mickey Mouse)፡፡

የዋልት ዲዝኒ የመጀመሪያዎች አመታት እጅግ ፈታኝ ነበሩ፡፡ ባለራእዩ ዋልት ዲዝኒ ግን ተስፋ አልቆርጥ አለ፡፡ አልፎ አልፎ ለቦርድ አባለቱ አንዳንድ በሃሳቡ የሚያፈልቃቸውን ከተለመደው ወጣ እና ሰፋ ያሉ ፈጠራዎችን ያቀርብላቸው ነበር፡፡ ከቦርድ አባላቱ አንዱም ሳይቀር የድካም ስሜት ያሳዩትና ተቀባይነት የማያገኝ ሃሳብ እንደሆነ ለመጠቆም ያፈጡበትና እንደዚህ አይነት ሃሳብ ማፍለቁ እንኳ ተቀባይነት እንደሌለው በተቃውሞ ይጋፉት ነበር፡፡ ዋልት ዲዝኒ ግን አንድን ያፈለቀውን ሃሳብ ወደፊት ለማራመድ የሚወስነው ሁሉም እንደተቃወሙት እርግጠኛ ሲሆን ነበር፡፡ ያፈለቀው ሃሳብ ትልቅና ልዩ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች ሁሉ ማመን ካልተሳናቸው በስተቀር ሕልሙ ትልቅ ነው ብሎ አያምንም ነበር፡፡

ሕልሙ አድጎና እውን ሆኖ በመጀመሪያ የተከፈተው በካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ የሚገኘውና ዲዝኒ ላንድ ሲሆን ስራ የጀመረው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1955 ዓ/ም ነው፡፡ የሚቀጥለው ግንባታ በፍሎሪዳ ከመደረጉ በፊት በፈረንጆቹ 1966 ዓ/ም ዋልት ዲዝኒ በሕመም ምክንያት በሞት ይለያል፡፡

በፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ በምትገኘው በኦርላንዶ ከተማ (Orlando, FL.) የሚገኘውና በ1970ዎቹ የተከፈተው በቀላል አጠራሩ “ዲዝኒ ወርልድ” (Disney World) በመባል የሚታወቀው መዝናኛ በአመት ከ52 ሚልየን በላይ ጎብኝዎችን ያሰተናግዳል፡፡ ይህኛው ዲዝኒ መዝናኛ በተመረቀበት ቀን የዋልት ዲዝኒ ባለቤት ከአንድ ታዋቂ ሰው ጋር ተቀምጣ ነበር፡፡

ባሏ ዋልት ዲዝኒ አሁን በመከናወን ላይ ያለውን አስገራሚ የራእዩ ውጤት ሳያይ ከጥቂት አመታት በፊት አልፏል፡፡ ይህ በዋልት ዲዝኒ ሚስት አጠቀገብ ተቀምጦ የነበረ ሰው ወደ እሷ ዘንበል በማለት፣ “ዛሬ የምናየውን ይህንን ግሩም ነገር ለማየት ባለቤትሽ ዋልት ዲዝኒ እዚህ ቢኖር እንዴት መልካም ነበር” አላት፡፡ የዋልት ዲዝኒ ባለቤት ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ እንዲህ ስትል መለሰችለት፣ “ባለቤቴ ዋልት ዲዝን ቀድሞውኑ በአይነ-ሕሊናው ይህንን አይቶት ባይሆን ኖሮ አንተ ዛሬ በአይነ-ስጋህ አታየውም ነበር”፡፡

ራእይ ማለት አንድን ነገር በአይነ-ስጋና በገሃዱ አለም ከማየት በፊት በአይነ-ሕሊና በማየት ለመስራት መንቀሳቀስ ማለት ነው፡፡

ራእይ ማለት ጊዜህን፣ ገንዘብህን፣ እውቀትህንና ያለህን ሁሉ ለመስጠት የሚያነሳሳህ ጉዳይ ነው፡፡

ራእይ ማለት ከነበረህና ካለህ ነገር በላይ መኖር ማለት ነው፡፡

ራእይ ማለት ለሌሎች ጥቅም የሚያልፍን ነገር ገንብቶ ለማለፍ መነሳሳት ማለት ነው፡፡

በዓለም ራሳቸውን አክብረው ሰዎች እንዲያከብሯቸው ያደረጉ ሰዎችን ተመልከታቸው፡፡

እነዚህ ሁሉ ሰዎች አንድ የጋራ ባህሪይ አላቸው፡፡ ይህ ባህሪይ ራእይ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

06 Dec, 01:58

በራእይህ ትለካለህ

Dr. Eyob Mamo

05 Dec, 16:36

ልቀቋቸው!!!

ምንም ነገር ብታደርጉ መለወጥ የማትችሏቸውን ነገሮች ልቀቋቸው!

ምንም ብትታገሉ የራሳችሁ ልታደርጓቸው የማትችሏቸውን ሰዎች ልቀቋቸው!

ምንም ብታሰላስሏቸው እንደገና የማትመልሷቸውን ያለፉ ሁኔታዎች ልቀቋቸው!

በቃ ልቀቋቸው! ለፈጣሪ ስጧቸው!

መልካም ምሽትና የእረፍት እንቅልፍ ለሃገሬ ሰዎች!!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

05 Dec, 15:31

ማሳሰቢያ!!!

ከዚህ ከእኔ፣ ከዶ/ር ኢዪብ ማሞ ማሕበራዊ ገጽ ላይ ነው ያገኘሁህ/ሽ በማለት መልእክት የሚልኩላችሁ ሰዎች በፍጹም ከእኔ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸውና ለራሳቸው አጀንዳና ፍላጎት ሊያገኟችሁ እንደሚፈልጉ እወቁ፡፡

የማትፈልጓቸውን Block ማድረግ የእናንተው መብት፣ ሃላፊነትና ድርሻ ነው፡፡

የመጣላችሁን ሁሉ በማስተናገድ ሞኞች አትሁኑ! ብልህ ሁኑ!

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

05 Dec, 11:59

ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)

1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመወጣት ስላቃታችሁ እገዛ ከፈለጋችሁ፣

2. የሕይወታችሁን ራእይ ወይም ዓላማ ባለማወቅ ከተወዛገባችሁና አቅጣጫን መያዝ ከፈለጋችሁ፣

3. ካለባችሁ አጉል ልማድ በመውጣ አዲስ ልማድን ማዳበር ካስቸገራችሁና ምክርና ድጋፍ ከፈለጋችሁ፣

4. መመለስ ያቃታችሁ የሕይወት ጥያቄዎች ከበዙባችሁና በአንድ ለአንድ ውይይት የመፍትሄ መንገድ ከፈለጋችሁ፣

5. በራሳችሁ መወጣት ያልቻላችሁት የተያዩ የስሜትና የስነ-ልቦና ጥያቄዎች ውስጥ እንዳላችሁ ከተሰማችሁና ከሁኔታው ለመውጣት ምክር ከፈለጋችሁ፣

ከግል በተጨማሪም ቁጥራችሁ ከአስር ባልበለጠ ሁኔታ በመሰባሰብ የGroup Coaching and Training ጥያቄም ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡

በቴሌግራም @DrEyobmamo inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

05 Dec, 02:01

ለውጥ አይቀሬ ነው!
(“የትራንስፎርሜሽን አመራር” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ))

“አንድን ነገር ካልወደድከው ለውጠው፤ ለመለወጥ ካልቻልክ ደግሞ በነገሩ ላይ ያለህን አመለካከት ለውጥ” – Maya Angelou

ከዕለት ተዕለት ወጪው አልፎ ወደ ንግዱ አለም ሊገባ የሚያስችለው በቂ ገንዘብ በእጁ ላይ የነበረው አንድ ሰው ብዙ ካወጣና ካወረደ በኋላ ቤቶችን ሰርቶ በማከራየት ለመነገድ ወሰነ፡፡ ስለዚህም ጥሩ ባለሞያ ከፈለገና ካማከረ በኋላ ሶስት ቤቶችን ለመስራት የሚያስችለው በቂ ገንዘብ እንዳለው ስለተረዳ ሶስት ቤቶችን በአንድ አካባቢ አስገነባ፡፡ ቤቶቹን ለማከራየት ሲሞክር ሳለ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ለአንድ አመት ወደ ውጪ ሃገር የሚሄድበት ጉዳይ ስላጋጠመው ባፋጣኝ የማከራየቱን ስራ አጣድፎ ሁለቱን ቤቶች አከራይቶና የአመት ክፍያ ተቀብሎ፣ አንዱን ደግሞ ተከራይ ስላጣ ዘጋግቶና ቆልፎበት ሄደ፡፡

ይህ ሰው ከአንድ አመት በኋላ ሲመለስ በመጀመሪያ ማድረግ የፈለገው ወደ ሶስቱም ቤቶች ሄዶ ሁኔታቸውን ማየትና ለተከራዩት ቤቶች ሌላ የአንድ አመት ኮንትራት ለማደስ መሞከር፣ ላልተከራየው ደግሞ ተከራይ መፈለግ ነው፡፡ ወደ እነዚህ ቤቶች ሲሄድ በውስጡ ቤቶቹ ምንም ሳይለወጡ እንዲያገኛቸው እየተመኘ ነበር፡፡ ነገር ግን ሶስቱም ቤቶች ተለውጠው አገኛቸው፡፡

በመጀመሪያ ሄዶ ያየው ቤት የተከራየው ሰው ከገባበት በኋላ ብዙ ገንዘብን በማውጣት ከቀድሞው የበለጠ ውብ አድርጎ ለወጠው፡፡ አዲስ ቀለም ተቀብቷል፣ ግቢው ከውጪም ሆነ ከውስጥ በአበባዎች ተውቧል፣ የቤቱ የውስጥ ክፍሎች ከሳሎን ጀምሮ በግሩም እቃዎችና በአዲስ ሁኔታ በተቀባ ቀለም ድንቅ ሆኗል፡፡ ይህ ቤት ተለውጧል - ለመልካም!

ወደ ሁለተኛው ቤት ሲሄድ በተደባለቀ ስሜት ነበር የሄደው፡፡ “ይህኛው ተከራይ ቤቴን እንዳለ ሳይለወጥ ይዞት እንደሚጠብቀኝ ተስፋ አደርጋለሁ” በማለት ሲጠጋ፣ ገና ከውጪ ያየው ነገር አስደነገጠው፡፡ የውጪው አጥር ግንብ በተለያዩ ቅጥ ያጡ ቀለሞችና የተከራዩ ልጆች በጻፏቸው ምንም ትርጉም በማይሰጡ ጽሑፎችና ስእሎች ተበላሽቷል፡፡ አንኳኩቶ ወደ ውስጥ ሲገባ ከግቢው ጀምሮ እስከ ውስጠኛው ቤት ድረስ ያየው ሁኔታ አስደንጋጭና እጅግ አስቀያሚ ነበር፡፡ ይህኛውም ቤቱ ተለውጧል - ለመጥፎ!

ሁለተኛውን ቤት አይቶ፣ ተከራይ በቤት ስላልነበረ ሌላ ጊዜ ለመመለስ ወስኖ ወደ ሶስተኛው ቤት ለመሄድ ተነሳ፡፡ ወደዚያ ቤት ሲሄድ ብዙም አልፈራም፤ ምክንያቱም ለማንም ስላላከራየው ቤቱን እንዳለ እንደሚያገኘው ተማምኖ ስለነበር ነው፡፡ ወደ ሶስተኛው ቤት ገና ሲጠጋ አይኖቹን ማመን አልቻለም፡፡ በፍጹም አይለወጥም ብሎ ያሰበው ቤት ማመን ከሚችለው በላይ ተለውጧል፡፡

እዚያ ቤት ማንም ነዋሪ እንደሌለ ያዩ የአካባቢው ሰዎች በሩና ግንቡ አካባቢ የቆሻሻ መጣያ አድርገውታል፡፡ ለአይን የሚቀፍና ለአፍንጫ የሚያጸይፍ ቆሻሻ ተከምሯል፡፡ የአጥሩ ግንብ በውጪ በኩል በተለያዩ ቦታዎች ተቦርቡሯል፡፡ በሩን ከፍቶ ሲገባ በተለያዩ ወፍ ዘራሽ ተክሎችና አረሞች የተሞላው ግቢ ያስፈራል፡፡ የቤቱ ቀለም አርጅቷል፡፡ የውስጥ ክፍሎቹ በሸረሪት ድርና ወዲያና ወዲህ በሚንሸራሸሩ ተባዮችና አይጦች ተሞልቷል፡፡ በአጭሩ፣ ይህም ቤት ተለውጧል - እጅግ ለመጥፎ!

ይህ አጭር ታሪክ እንደሚያሳየን፣ እነዚህ ሶስት ቤቶች ከመለወጥ አላመለጡም፡፡ አንዱን ቤት ለመልካም ለውጥ የተነሳሳ ሰው ወደተሻለ ደረጃ ሲለውጠው፣ ሁለተኛውን ደግሞ ግድ የለሽነት የተሞላ ሰው ለመጥፎ ለውጦታል፡፡ ሶስተኛውም ቤት ከመለወጥ አልዳነም፡፡ ይህ ቤት ማንም ሳይነካውና እንዳለ ስለተተወ ተለውጧል፡፡ የሶስቱ ቤቶች የጋራ ሁኔታ መለወጥ የሚባለው ጉዳይ ነው፡፡

መልእክቱ ይህ ነው፡- በግል ኑሯችን፣ በቤተሰብ ሁኔታችን፣ በምንመራው ድርጅትም ሆነ በሌሎች ማሕበራዊ ኑሮአችን መለወጥ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ፣ መለወጥ ካልቀረ ፈቅደንና ለመልካም ለውጥ ሰርተን ለውጥን እናምጣ፡፡ የለውጥ ሰው ለውጥ መምጣቱ እንደማይቀር የገባውና ሁኔታዎች አስገድደውት ወይም ሁኔታዎች ችላ ስለተባሉ ለመጥፎ የሆነ ለውጥ ከሚመጣ ራሱ ለውጥን አነሳስቶ መልካም ለውጥን የሚያመጣ ሰው ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

05 Dec, 01:59

ለውጥ አይቀሬ ነው!

Dr. Eyob Mamo

04 Dec, 16:05

ጥያቄ፡-

Dr. ብዙ መልካም የሆኑ አሳቦች አሉኝ ግን ብዙን ግዜ እነዚን አሳቦች ወደ ተግባር ማምጣትና መተግባር አልቻልኩም ። Dr. ምን ባረግ እንዚህ መልካም አሳቦች ወደተግባር ማምጣት እችላለው።

መልስ፡-

የጠየከው ጥያቄ ብዙ ሰዎች የሚታገሉበት ጉዳይ ነው፡፡ ከሁሉም በፊት የችግሩን መንስኤ መለየት አስፈላጊ ነው፡፡

ምናልባት ችግርህ . . .

• የምትፈልገውን ለይተህ አለማወቅ ይሆናል፡፡

• ወይም ያየኸውን፣ የሰማኸውና ያሰብከው መልካም ነገር ሁሉ ለማድግ የመጓጓት ባህሪይ ሊሆን ይችላል፡፡

• ወይም ደግሞ የምታደርገውን አውቀህ ሳለ የመጀመርና የመቀጠል ዲሲፕሊን አይኖርህ ይሆናል፡፡

• አለዚያም ነገሮችን የማቀድና ተግባር ላይ የማዋል ክህሎት አጥሮህ ይሆናል፡፡

ከእነዚህ ከተጠቀሱት መካከል የትኛው ላይ ጉድለት እንዳለህ አስበህ ለመቅረፍ ሞክር፡፡

በመቀጠል ግን መልካም ሃሳብ ሁሉ ትክክለኛ ሃሳብ ነው ማለት እንዳልሆነ ላስታውስሀ፡፡ መልካም ሃሳብ ማለት ለራስህም ሆነ ለሌሎች የሚጠቅም ሃሳብ ማለት ነው፡፡ ይህ መልካም ሃሳብ ትክክለኛ የሚሆነው ግን ከአንተ አቅም፣ ብቃትና ዓላማ የሚጣጣምና ሃሳብ ከሆነ ለመጀመር ወቅቱ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ መልካም ሃሳብህን የማጣራትና አንዳንዶቹን ውድቅ የማድረግ፣ ሌሎቹን የማዘግየትና በወቅቱ ከአንተ ጋር የሚስማሙትን ወደ ተግባር የመለወጥ ስራ ይጠብቅሃል፡፡

ያንን ለማጣራት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅና መልስን በማግኘት ወደ እንቅስቃሴ መግባት ትችላለህ፡፡

1. ከመልካም ሃሳቦቼ መካከል ከዋናው የሕይወቴ ዓላማ ጋር የሚጣጣሙት የትኞቹ ናቸው?

2. ከእነዚህ ከዓላማዬ ጋር ከሚጣጣሙት መልካም ሃሳቦች መካከል ከወቅታዊ ሁኔታዬ አንጻር መጀመር የምችላቸው የትኞቹን ነው?

3. እነዚህን ለመጀመር የምችላቸውንና የምፈልጋቸውን መልካም አሳቦች ለመጀመር ምን አይነት እቅድ ላውጣ?

4. የማወጣው እቅድ መቼ መጀመር፣ እንዴት መቀጠልና መቼ መጠናቀቅ አለበት?

እግረ መንገዴን በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሚሰጥህን በቅር ያወጣሁትን፣ “ጀምሮ መጨረስ” የሚለውን መጽሐፌን አንብበው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

04 Dec, 16:05

ብዙ መልካም የሆኑ አሳቦች አሉኝ ግን ወደ ተግባር ማምጣት አልቻልኩም።

Dr. Eyob Mamo

04 Dec, 02:00

ለራሳችሁ ያልሰጣችሁትን ነገር ከሰው አትጠብቁ!

ሰዎች እንዲሰጧችሁ የምትፈልጉትን ማንኛውም ነገር በመጀመሪያ ለራሳችሁ መስጠትን ተማሩ፡፡

• በሰዎች መወደድ ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ራሳችሁን ውደዱ፡፡

• በሰዎች ተቀባይነት ማግኘት ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ራሳችሁን ተቀበሉ፡፡

• በሰዎች መከበር ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ራሳችሁን አክብሩ፡፡

• ሰዎች ከእናንተ ጋር እንዲያሳልፉ ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ከራሳችሁ ጋር በቂ ጊዜን አሳልፉ፡፡

ይህንን ስታደርጉ ሰዎቹ ያንን ነገር ከሰጧችሁ፣ በሞላው ማንነታችሁ ላይ ስለጨመሩላችሁ አመስጋኝ ሆናችሁ መንገዳችሁን ትቀጥላላችሁ፡፡ የጠበቃችሁትን ከከለከሏችሁ ደግሞ ነገሩን ከራሳችሁ ስላገኛችሁት ሁኔታው ለጉዳት አይጥላችሁም፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ ለራሳችሁ ያልሰጣችሁትንና ከራሳችሁ የከለከላችሁትን ምንም ነገር ከሰዎች መጠበቅ በጣም ሞኝነትና የተዛባ አመለካከት ነው፡፡

ለራሳችሁ ያልሰጣችሁትን ነገር እንዴት ሌሎች ሰዎች ይስጧችሁ?

በነገራችን ላይ፣ ከላይ የተጠቀሱት፣ ራሳችሁን ያለመውደድ፣ ያለመቀበል፣ ያለማክበርና ለራሳችሁ ትኩረት ያለመስጠት ሁኔታ ካለባችሁ ይህ ችግራችሁ ለሰዎች በግልጽ እንደሚታይ ታውቃላችሁ?

ይህ ብቻ አይደለም፣ ይህ በራሳችሁ ላይ ያላችሁ አመለካከት ሌሎች ሰዎችም እንደዚያው እንዲመለከቷችሁ የማድረግ አጉል ተጽእኖ ለው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

03 Dec, 14:35

ከነማንነታችሁ የሚወዷችሁ!

በምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለብቻችሁ እየታገላችሁና እየለፋችሁ እንደሆነ ቢሰማችሁም፣ ስለእናንተ ሁኔታ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች ከመኖራቸው በበለጠ ሁኔታ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚወዷችሁ ሰዎች እንዳሉ በማሰብ ልባችሁን ደግፉ፡፡

አይዟችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

03 Dec, 09:48

“የግል ሕይወትን ማደራጀት”
(Organizing personal life)

የonline (telegram) ስልጠና ቅድመ-ማስታወቂያ!

የግል ሕይወታችንን ካላደራጀን የትኛውም ስራችንን ማደራጀት ያስቸግረናል፡፡

በሃገራችን የምናያቸውና ሌላው ሕብረተሰብ የሚመኛቸው መልካም ልምምዶቻችን እንደተጠበቁ ሆነው፣ እኛም ራሳችንን መለስ ብለን ስንመለከት እንዲስተካከሉ የምንፈልጋቸው በርካታ ጎድለቶች አሉብን፡፡

ከእነዚህ ሊቃኙ ከሚገባቸው የሕይወት ዘይቤዎቻችን አንዱና አንጋፋው የግል ሕይወት አደረጃጀት ጉዳይ ነው፡፡

የዚህ ክህሎት ጉድለት ከሚንጸባረቅባቸው ሁኔታዎች ዋነኛው፣ አንድን ነገር ለመጀመር መታገላችን፣ የጀመርነውን ነገር የማቋረጣችን ሁኔታ ነው፡፡

በተጨማሪም የቱ ጋር ተጀምሮ ወደየት አቅጣጫ እንደሚሄድ አለማወቅ፣ በሕይወት አለማደግና ያላደግንበትን ምክንያት አለማወቅ፣ የኋላ ቀርነት ስሜትና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ያልተደራጀ ሕይወት ምልክቶች ናቸው፡፡

የምንኖረው ውድድር በሞላበት ዘመን ነው፡፡ ተሻሽሎና ተሽሎ ለመገኘት ሕይወትን ማደራጀት የግድ ነው፡፡

ሙሉ ማስታወቂያውን በሚቀጥለው ሳምንት ይጠብቁ፡፡

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

03 Dec, 02:00

በቀላሉ አልናወጥም!

የሚከተለውን የአቋም መግለጫ ከእኔ እንድትጋሩ ልሞግታችሁ!

ማንም ሰው ስለእምነቴ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር ስሜቴን አይነካውም፤ ምክንያቱም የማምነውን በሚገባ ስለማውቅ!

ማንም ሰው ስለ ዘሬና ስለቆዳ ቀለሜ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር በራሴ ላይ ያለኝን አመለካከት አይነካውም፤ ምክንያቱም የራሴንም ሆነ የሌላውን ዘርና የቆዳ ቀለም በመቀበልና በማክበር ስለተደላደልኩኝ፡፡

ማንም ሰው ስለመልክና ቁመናዬ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር ስነ-ልቦናዬን አያቃውሰውም፤ ምክንያቱም ራሴን የተቀበልኩና ፈጣሪ በሰጠኝ ማንነቴ የምተማመን ሰው ስለሆንኩኝ!

ማንም ሰው ስለችሎታዬ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር እምቅ አቅሜን አይቀንሰውም፤ ምክንያቱም ብርቱና ደካማ ጎኔን በሚገባ ለይቼ በብርታቴ ላይ ካለማቋረጥ እሰራሁ በመሆኔ!

ማንም ሰው ስለ ዓላማዬና ስለራእዬ ምንም ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር ከመንገዴ አይመልሰኝም፤ ምክንያቱም ዓላማዬ በሚገባ የማውቅና በዚያም የጸናሁ ሰው በመሆኔ!

እኔ ሙሉ የሆንኩኝ፣ ነገሩ በሚገባ የገባኝና በሕብረተሰቡ መካከል ከሚገኝ አጉል ተጽእኖ ነጻ የሆነኩኝ ሰው ነኝ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

02 Dec, 02:01

ዓላማችሁ ላይ እስከምትደርሱ ድረስ!

• ዛሬ ጥሩ ያልሆኑ ሁኔታዎችን ታግሳችሁ ለማለፍ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!

• ዛሬ ማግኘት የማትፈልጉትን ሰው ለጊዜው ለማግኘት ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!

• ዛሬ መስራት የማትፈልጉትን የስራ ዓይነት ለጊዜው ለመስራት ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!

• ዛሬ እጅግ አስቸጋሪ ከሆነ “አለቃ” ስር ለጊዜው ለመቆየት ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!

• ዛሬ መኖር በማትፈልጉበት ቤት ለጊዜው ለመኖር ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!

• ዛሬ መናገር የሚያምራችሁን ነገር ለጊዜው ዝም ብላችሁ ለማለፍ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!

ዓላማችሁን ከመከተል ግን በፍጹም ወደ ኋላ እንዳትሉ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

01 Dec, 02:30

መቅደም ያለበት ነገር!

• ማንንም ከማድመጣችሁ በፊት በቅድሚያ ትክክል እንደሆነ ህሊናችሁ የሚመሰክርላችሁን እውነት አድምጡ፡፡

• ማንንም ከመፍራታችሁ በፊት በቅድሚያ ፈጣሪን ፍሩ!

• ስለማንም ሰው ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከማውራታችሁ በፊት በቅድሚያ ስለራሳችሁ ጉዳይ ከራሳችሁ ጋር አውሩ!

• ማንንም ሰው ከማገዛችሁ በፊት በቅድሚያ ራሳችሁን አግዙ!

• ያልሆነላችሁንና የሆነባችሁን ከማሰላሰላችሁ በፊት በቅድሚያ የሆነላችሁንና ያልሆነባችሁን አሰላስሉ!

መልካም እሁድ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

30 Nov, 02:24

ውብ ቀን እንዲሆንልን!

ፈጣሪ አዲስን ቀን ውብ አድጎና ያስለመደንን የጸሃይ ብርሃን፣ እስትንፋስና የሚያስብ አእምሮ ሲሰጠን የቀረው ስራ የእኛ ነው፡፡ ይህ ስራ ግማሹ ውሳኔያችን፣ ግማሹ ደግሞ ጥንካሬያችን ነው!

የዛሬዋ ቀን ውብ እንድትሆን ውሳኔን ይጠይቃል፡፡ ይህ ውሳኔ፣ ለአናሳ ነገር አለመደላደልን፣ በጎ በጎውን ማሰብን፣ ያለፈውንና ፈጽሞ የማይመለሰውን መርሳትን፣ በእቅድ መኖርንና የመሳሰሉት ያካትታል፡፡

የዛሬዋ ቀን ውብ እንድትሆን ጥንካሬንም ይጠይቃል፡፡ ይህ ጥንካሬ፣ ምንም ነገር ብናደርግ መለወጥና ማስወገድ የማንችላቸውን ነገሮች ተቋቁሞ ማለፍን፣ መውጣትና መስራትን፣ በተከፈተልን መስክ ንቁ ተሳትፎ ማድረግንና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡

የቀናችሁን ውበት የሰዎች አመለካከትና ንግግር አይወስንላችሁ፡፡ በተሳካውና ባልተሳካው ምክንያትም ቢሆን የቀናችሁን ውበት አትወስኑት፡፡

“ቀኔ ውብ ነው!!!” ብላችሁ ጀምሩ፡፡

ውብ እና የተባረከ ቅዳሜ ይሁንላችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

29 Nov, 04:51

ጥያቄ፡-

ዶ/ር አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሃገራችን የምንመለከተው ነገር ግራ ይገባኛል፡፡ በአንዳንድ መስሪያቤቶችና አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በሃገር ደረጃ አንድ ከሕዝብ ጋር የተገናኘ ሕግ ሲወጣ ሕዝቡ ሕጉን ተከትሎ ማስተካከል ላለበት ነገር የሚሰጠው ጊዜ በጣም አጭር ነው፡፡ ይህን ሁኔታ ከአመራር አንጻር ሲታይ መንስኤው ምን ይመስልሃል?

መልስ፡-

የጠቀስከውን ሃሳብ ሰዎች ከብዙ አቅጣጫ ተመልክተው ማብራሪያ ሊሰጡበት ይችላሉ፡፡ ከአመራር አንጻር ሲታይ ግን የሚከተሉትን መንስኤዎች መመልከት እንችላለን

1. ያልተደራጀ የአሰራር ስልት (system)

ማንኛውም ሕዝብ-ነክ አመራር በሚገባ የተደራጀና በየጊዜው የማይለዋወጥ የአሰራር ስልት ከሌለው፣ በታሰበበት መልኩ (proactive በመሆን) አቅዶ ከመስራት ይልቅ፣ ለመጣው ችግር ምልሽ በመስጠት (reactive በመሆን) ድንገተኛ ሕግን ያወጣል፡፡ ይህ ሕግ ደግሞ፣ “ከዛሬ ጀምሮ ይህ ነገር አይፈቀድም. . . ከነገ ጀምሮ ያኛው ነገር ተከልክሏል . . .” አይነት ባህሪይ ይኖረውን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

2. የመሪዎች መለዋወጥና የቅብብሎች ጉድለት

በማንኛውም ሕዝብ-ነክ ተቋማት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች መሪዎች በቦታቸው የማይጸኑ ከሆነ፣ በሄደው የተተካው መሪ የተረከበውን ስራ በራሱ መንገድ ለመተግበር ይነሳል፡፡ የመሪዎች በቶሎ መለዋወጥ፣ ካለፈው እንዲቀጥል የሚያደርገው የቅብብሎሽ ሂደት እንዲከተል ስለማይፈቅድ ድንገተኛ ሕጎችንና መመሪያዎችን እያስፈጸመ ይኖራል፡፡

3. ሕጉ የሚወጣበት የመነሻ ሃሳብ

አንዳንድ ሕጎች ፈጥነው ብቅ ብለው፣ ፈጥነው የሚያልፉት ሕጉን የሚያወጡት ሰዎች በስሜታዊነት፣ ከአንድ ጥቅም አንጻር ወይም ከተለያዩ የተዛቡ የመነሻ ሃሳቦች ሲያደርጉት ነው፡፡ ከትክክለኛ ግምገማ፣ ጥናት እና ለአጠቃላይ ባለድርሻዎች ከመጥቀሙ አንጻር ከልተነሳ ሁሉም ነገር አሁን በአሁን ይሆናል፡፡

4. የግንዛቤ አቅም ማነስ

በሕዝብ-ነክ አመራር ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ማሕበራዊ ሂደትን አስመልክቶ ከፍተኛ ግንዛቤን ሊያዳብሩ ይገባቸዋል፡፡ ሕጉ ሲወጣ ሕጉ የሚነካቸውን ሰዎችን ሁኔታ በሚገባ ያለመገንዘብ፣ የሕጉን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የጎንዮሽ ጉዳት አለማሰብና አለመዘጋጀት፣ የሕጉ ተፈጻሚነት የሚነካቸው ሰዎች ለስነ-ልቦናም ሆነ ለሌሎች ዝግጅቶች ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈልጉ በትክክል አለመገንዘብ የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

5. በሕግ አውጪዎቹና በአስፈጻሚች መካከል ያለ ክፍተት

አንዳንድ ጊዜ ሕግ አውጪዎቹና መመሪያ የሚያስተላልፉት መሪዎች ትክክለኛ መመሪያና የታሰበበትን መንገድ ተከትለው ሳለ፣ አስፈጻሚዎቹ ያንን ተገንዝበው የተጠበቀውን መንገድ ካልተከተሉ መሪዎቹ ምንም ያህል የተስተካከለን ነገር ቢያወጡም አፈጻጸሙ ግን የተቻኮለና ጎጂ ይሆናል፡፡ አንዳንዶቹ በግድ-የለሽነት፣ ሌሎቹ ደግሞ የሕጉን ሂደት ለመገንዘብ ብቃት ካመኖር ይህ ሁኔታ ይከሰታል፡፡

በጥያቄው የተጠቀሰው ችግር መነሻ ያም ሆነ ይህ፣ ሕዝብ-ነክ አመራር እጅግ ማስተዋልን፣ መረጋጋትንና ነገሮችን ግራና ቀኝ በማየት ከማመዛዘን ሊነሳ ይገባዋል፡፡

ሆኖም፣ መሪዎች ምንም ያህል ጥንቃቄ ቢያደርጉም፣ ሁሉንም ቀዳዳ ደፍነው ላይጨርሱ እንደሚችሉና ስህተት ሊሰሩ እንደሚችሉ ማሰብም መልካም ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

29 Nov, 04:51

አንዳንድ ጊዜ በሃገራችን ሕግ ሲወጣ ሕዝቡ ሕጉን ተከትሎ ማስተካከል ላለበት ነገር የሚሰጠው ጊዜ በጣም አጭር የሚሆነው ለምን ይመስልሃል?

Dr. Eyob Mamo

29 Nov, 02:00

መርጣቸሁ ንገሩ

1. የወደፊት እቅዳችሁንና ዓላማችሁን
ጤናማዎቹ በማበረታታት ይደግፏችኋል፣ ቀናተኞቹ ግን ይቀኑባችሁና ያሰናክሉባችኋል፡፡

2. ስጋቶችና ፍርሃቶቻችሁን
ጤናማዎቹ በርቱ ብለው ያደፍፍሯችኋል፣ ጤናቢሶቹ ግን ይንቋችኋል፡፡

3. የሰራችኋቸውን ስህተቶችና ደካማ ጎናችሁን
ጤናማዎቹ በፍጹም ሳይለወጡባችሁ ከነስህተታችሁ ይቀበሏችኋል፣ ጤና ቢሶቹ ግን ከጀርባችሁ ሆነው ያወሩባችኋል፣ አንድ ቀን ጠብቀው ደግሞ ደካማ ጎናችሁን እናንተን ለመጉዳት ይጠቀሙበታል፡፡

የሚነገረውንና የማይነገረውን ለዩ፡፡ ለማን እንደሚነገርና ለማን እንደማይነገር ለዩ፡፡ ብልህ ሁኑ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

28 Nov, 02:00

የስራና የትርፍ ሰዓቶቻችን ጉዳይ!

“በስራ ሰዓቶቻችን ወቅት የምናደርገው ነገር፣ የሚኖረንን ነገር ይወስናል፣ በትርፍ ሰዓታችን የምናደርገው ነገር ደግሞ ማንነታችንን ይወስናል” (Today's Wisdom)

የስራ ሰዓትን አስመልክቶ

በኑሮ ደረጃችሁና በገንዘብ አቅማችሁ ለማደግ ከፈለጋችሁ በስራ ሰዓታችሁ ወቅት የምትሰሩትን በሚገባ እወቁ፡፡ የሚያሳድጋችሁ ስራ ፍጠሩ፣ ያንንም በትጋት ስሩ፡፡

1. ብዙ ለፍታችሁ ጥቂት የሚከፍላችሁን ስራ ጉዳይ አስቡበት፡፡

2. ድግግሞሽና የበዛበትና በአመለካከት ወይም በእውቀት እንድታድጉ የማይሞግታችሁን ስራ ጉዳይ አስቡበት፡፡

የትርፍ ሰዓትን አስመልክቶ

በማንነትና በባህሪይ ልህቀት ለማደግ ከፈለጋችሁ በትርፍ ሰዓታችሁ የምታደርጓቸው ነገሮች ልክና ገደብ ያላቸው መሆናቸውን እርግጠኞች ሁኑ፡፡

1. የምትዝናኑባቸው ነገሮች ከአጉል ልማድና ሱስ የጸዱ የመሆናቸውን ጉዳይ አስቡበት፡፡

2. የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎቻችሁ የአእምሮ እና የአካል እረፍትንም ጭምር የሚሰጧችሁ መሆናቸውን እርግጠኞች ሁኑ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

27 Nov, 02:00

የአንደበታችን ጉልበት!

አንድ ቀን የአምፖል ፈጣሪው ቶማስ ኤዲሰን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ሲመጣ ለእናቱ አንድን ወረቀት ሰጣትና “መምህሬ ይህንን ወረቀት ሰጠኝ እና ለእናትህ ብቻ በእጇ ስጥ ብሎ ነገረችኝ” አላት።

እናትዬው አይኖቿ እምባ እያቀረራቸው እንዲህ ስትል ለልጇ አነበበችለት፣ “ልጅሽ እጅግ አዋቂና ሊቅ ነው። ይህ ትምህርት ቤት ለእሱ በጣም የማይመጥንና ትንሽ ነው እና እሱን ለማሰልጠን ብቁ የሆኑ አስተማሪዎች ባለመኖራቸው ተመልሶ እንዳይመጣ፣ እዚያው እቤቱ አስተምሩት”፡፡

ከብዙ አመታት በኋላ፣ የቶማስ ኤዲሰን እናት ከሞተች በኋላ እና እሱም በአለም ላይ ካሉት ታላላቅ ፈጣሪዎች አንዱ ወደመሆን ከመጣ በኋላ፣ አንድ ቀን የቤተሰቡን የቆዩ ነገሮች ሲመለከት በድንገት በጠረጴዛው መሳቢያው ውስጥ በጥግ በኩል አንድ የታጠፈ ወረቀት አየ።

አንስቶም ከፈተው። በወረቀቱ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አለ፡- “ልጅሽ ቶማስ ኤዲሰን የዘገምተኛነት ችግር ያለበት ልጅ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጣ አንፈቅድለትም”፡፡

ትዝ ሲለው፣ ለካስ ያን ጊዜ ከትምህርት ቤት ይዞ የመጣው ትክክለኛ ጽሑፍ ይህ ነበር፡፡ እናት ግን ያን ጊዜ ይህንን ሃሳብ ባለመቀበልና በእሱ ላይ ላለመናገር በመወሰን ለውጣ እንዳነበበችለት ተገነዘበ፡፡

ቶማስ ኤዲሰን ለሰዓታት ካለቀሰ በኋላ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ እንዲህ ሲል ጻፈበት፣ "ቶማስ ኤዲሰን የአዕምሮ ጉድለት ያለበት ልጅ ነበር፣ ጀግና እናቱ ግን የክፍለ ዘመኑ ሊቅ ወደመሆን ቀየረችው"፡፡

• ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር ስላላችሁ መስተጋብር (interaction) ከዚህ ታሪክ ምን ተማራችሁ?

• መምህራን በተማሪዎች ላይ ሊኖችሁ ስለሚገባ አመለካከትና አቀራረብ ከዚህ ታሪክ ምን ፍሬ ነገር አገኛችሁ?

• የሃገር መሪዎች የምትመሩትን ሕዝብ በምን አይን ልትመለከቱትና እንዴትስ ልታስተናግዱት እንደሚገባችሁ ከዚህ ታሪክ ምን ቁምነገር አገኛችሁ?

• አንባቢዎቼስ በዙሪያችሁ የሚገኙ የቅርብና የሩቅ ሰዎችን በምን መልኩ ማስተናገድ እንደሚገባችሁ ከዚህ ታሪክ ምን ቁም ነገር ቀረላችሁ?

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

27 Nov, 01:59

የአንደበታችን ጉልበት!

Dr. Eyob Mamo

26 Nov, 02:00

የጠፋብን ውስጥ፣ የምንፈልገው ውጭ

አንድ ሰው አንድ ቀን ማታ እቤቱ እያለ ውድ የተባሉ እቃዎቹን ከሚያስቀምጠበት ሳጥን ውስጥ አንድ በጣም የሚወደውን ዳይመንድ መርጦ አወጣና በእጁ ይዞ እየተመለከተው ሳለ፣ በድንገት መብራጥ ጠፋበት፡፡

ልክ መብራቱ እንደጠፋበት በእጁ የያዘው ውድ ዳይመን ከእጁ አመለጠውና ወደቀ፡፡ ወዲያውኑ ሊፈልገው ቢሞክርም ጨለማ ነበረና የት እንደገባ እስከማይገኝ ድረስ ጠፋበት፡፡ ብዙ ሞክሮ ሲደክመው ከቤቱ ወጣ ሲል የመንገድ መብራቶች አካባቢውን ደመቅ አድርገው አብርተውት ተመለከተ፡፡ ከዚያም፣ “የጠፋብኝን ዳይመንድ እቤቴ ጨለማ ስለሆነ ስላላገኘሁት እዚህ ብርሃን ያለበት ቦታ ልፈልገው” ብሎ በማሰብ መፈለጉን ተያያዘው፡፡

ያንን በማድረግ ላይ እያለ አንድ በአካባቢው የሚዘዋወር ፖሊስ አገኘውና፣” ምን እየፈለክ ነው” አለው፡፡

ሰውዬውም መልሶ፣ “ዳይመን ከእጄ ወድቆ ጠፍቶብኝ ነው” አለው፡፡

ፖሊሱም ትንሽ ካፋለገው በኋላ ሲደክመው፣ “ለመሆኑ የቱ ጋር ነው የጠፋብህ” ብሎ ጠየቀው፣ ሰውየው፣ የጠፋብኝማ እቤቴ ነው፣ ነገር ግን እቤቴ መብራት ስለሌለና ጨለማ ስለሆነብኝ ነው እዚህ መብራት ያለበት ቦታ መፈለግ የጀመርኩት” አለው ይባላል፡፡

የብዙዎቻችን ችግር ይህ ይሆን! እኛው ውስጥ የጠፋብንን ነገር ሌላ ቦታ፣ ሌላ ሰው ጋር፣ ሌላ ሁኔታ ውስጥ ስንፈልግ መባዘናችን! እኛው ጋር ካለው የዝቅተኝነት ስሜት፣ ራስን ያለመቀበል ቀውስ፣ የመገፋት ህመምና የመሳሰሉት “ጨለማዎች” የሰወረብንን ውድ ነገር ሌላ ቦታ እንፈልገዋለን፡፡

“ሰዎች ቢቀበሉኝ እኮ . . .” እንላለን፣ ከተቀበሉን በኋላ ደግሞ ሰዎቹ ትተውን እንዳይዱ እንጨነቃለን፡፡ “ሃብት ብናገኝ እኮ . . .” እንላለን፣ ካገኘን በኋለ ደግሞ ሃብቱ እንዳይከስር ስንጨነቅ ቁጭ ብለን እናድራለን፡፡ “ዝነኛ ብሆንና Follower ባገኝ እኮ . . .” እንላለን፣ ካገኘን በኋላ ግን እያንድንዱ unfollow ያደረገን ሰው ሁኔታ ይጫጫነናል፡፡

ውስጣችሁ የጠፋባችሁን ነገር ሌላ ቦታ አትፈልጉት፤ ፈጽሞ አታገኙትም፡፡ በመጀመሪያ የጨለመባችሁንና ግራ የገባችሁን ነገር ፈጣሪ ይፍታላችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

26 Nov, 01:58

የጠፋብን ውስጥ፣ የምንፈልገው ውጭ

Dr. Eyob Mamo

25 Nov, 02:00

ራሳችሁን ምነው ችላ አላችሁት ??? !!!

• ሌሎች ሰዎችን የምትወዱትን ያህል ራሳችሁን ብትወዱ . . .

• የሌሎች ሰዎች ሰሜት እንዳየጎዳ የምትጠነቀቁትን ያህል የራሳችሁ ስሜት እንዳይጎዳ ብትጠነቀቁ . . .

• ለሰዎች ጥቅምና እድገት የመሯሯጣችሁን ያህል ራሳችሁን ለመጥቀምና ለማሳደግ ብትተጉ . . .

• ሰዎችን ለማስደሰት ስትሉ ጊዜን የመስጠታችሁን ያህል ለራሳችሁ ጊዜን ብትሰጡ . . .

• ሰዎቹን ላለማጣት ስትሉ ተገቢ ላልሆነው ነገር ሁሉ እሺ የማለታችሁን ያህል ራሳችሁን ላለማጣት ደግሞ እምቢ ማለትን ብትለማዱ . . .

ራሳችሁን አክብራችሁ፣ አሳድጋችሁና ጠብቃችሁ ለእነሱም በተረፋችሁ ነበር፡፡ አለዚያ ግን በቅድሚያ ራሳችሁን፣ ሲቀጥል ደግሞ ሌሎችን መጉዳታችሁ አይቀርም፡፡

እነዚህን ልምምዶች እስከምታዳብሩ ድረስ የትክክለኛ ነጻነትን ሕይወት ጣእም አታውቁትም፡፡

በአንዴ ላይሆን ቢችልም ቀስ በቀስ ልመዱት!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

22 Nov, 12:30

እኔ እና ፈጣሪዬ!!!

እኔ ከፈጣሪዬ ጋር ሆኜ ብቻዬን በመሆን ሙሉ ሰው ነኝ!

ከእኔ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ሁኔታዎች እያሉ እንኳን ሙሉ ሰው ነኝ!

ከእኔ ጋር መሆን የማይፈልጉ ሰዎች እያሉ እንኳን ሙሉ ሰው ነኝ!

ይሳካሉ ብዬ የጠበቀኳቸው ነገሮች ባይሳኩም እንኳን ሙሉ ሰው ነኝ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

22 Nov, 02:00

ከስህተት ወደ ስኬት!

“በፍጹም ልቀይራቸው የማልችላቸውን ስህተቶች ሰርቼ አውቃሁ፡፡ ነገር ግን፣ ያንንው ስህተት ደግሜ መስራት እስከማልችል ድረስ ለመልካም ተለውጬበታለሁ” (Steve Harvey)

ሕይወታችሁ “ከስህተት ወደ ስህተት” ሳይሆን “ከስህተት ወደ ስኬት” እንዲሆን ከፈለጋችሁ እኔ እንዳደረኩት የSteve Harveyን ምክር እንድትሰሙ ላደፋፍራቸሁ፡፡

የሚንቀሳቀስ ሰው ስህተትን የሚሰራ ሰው ነው፡፡ ስህተትን ላለመስራት ካለው ፍርሃት የተነሳ የማይንቀሰቀስ ሰው ደግሞ በፍርሃት ያለመንቀሳቀስንና የኋላ ቀርነትን ስህተት እየሰራ ነው፡፡

አንዳንዶቹ ስህተቶቻችን ምንም ብንታገል ውጤቱን መቀየር አንችልም፡፡ ስለሆነም፣ ከሁኔታው ትምህርትን አግኝተን ወደፊት ተመሳሳይ ስህተት እንዳይደገም በመጠንቀቅ ወደፊት እንድንቀጥ እንመከራለን፡፡

እባካችሁ በፍጹም ሊተካ የማይችለውን ውድ ጊዜያችሁን፣ መቀየር የማትችሉትን ስህተት ባመብሰልሰል አታባክኑት፡፡

እባካችሁ አንዴ ከተዛባ ሌላ ቀውስን ሊወልድ የሚችለውን የጤንነታችሁን ሁኔታ፣ መቀየር ስለማትችሉት ስህተት በመጨነቅ አታበላሹት፡፡

እባካችሁ ብትጠቀሙበት የወደፊት ሕይወታችሁን ስኬታማ ሊያደርግ የሚችለውን እምቅ አቅማችሁን፣ መቀየር የማትችሉትን ስህተት ስታወጡና ስታወርዱ አታዳፍኑት፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

21 Nov, 14:30

የሚለቀቀውና የሚያዘው!

ላላገባችሁ . . .

. . . ካለፈው የቀጠለ

“የሰውን አእምሮ የሚያዞሩ ሁለት አስቸጋሪ ጉዳዮች አሉ፡፡ ከእኛ ጋር አብሮ መቆየት የማይፈልግን ሰው እንዴት እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል? ከእኛ ተለይቶ ለመሄድ የማይፈልግን ሰውስ እንዴት እንዲሄድ ማድረግ ይቻላል? - Danny Devito

አሁን ባለንበት ዘመን ያላገቡ ወጣቶችን ስሜት ለቀውስ የሚዳርጉ ሁለት ልምምዶችን የሚገልጽ አባባል ነው፡፡

ቀደም ባለው “ፖስቴ” የዚህን ሃሳብ ክፍል አንድ ያሰፈርኩኝ ስለሆነ እሱን መለስ በማለት ማንበባችሁን አትርሱ፡፡

እንደዚህ ብለን ነበር፡- ያፈቀራችሁት ሰው “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ሲል ወይም “አልፈልግም እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው “ሞቼ እገኛለሁ” ሲል ማድረግ የሚገባችሁን ካላወቃችሁ የሚደርስባችሁ የስሜት ቀውስ ረጅም ዘመን የሚከተል ሊሆን ይችላል፡፡

“አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው ሞቼ እገኛለሁ ሲል ያላችሁ ምርጫዎች፡-

1. ስሜታቸው እንዳይጎዳ በማለት የማትፈልጉት አይነት ግንኙነት ውስጥ መግባት፡፡

2. ስለ እኔ ያላቸውን መረጃ በመጠቀም ወይም በሌሎች መንገዶች ይበቀሉኛል በሚል ፍርሃት መንቀሳቀስ አለመቻል፡፡

3. ስሜትን በትክክል ከገለጹ በኋላና በቂ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ተገቢውንና ትክክለኛውን ውሳኔ በማድረግ ሰዎች የራሳቸው ስሜት ላይ እንዲሰሩ ጊዜ መስጠት፡፡

የትኛው ውሳኔ ይሻላል? ለምን?

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

21 Nov, 12:34

የሚለቀቀውና የሚያዘው!

ላላገባችሁ . . .

“የሰውን አእምሮ የሚያዞሩ ሁለት አስቸጋሪ ጉዳዮች አሉ፡፡ ከእኛ ጋር አብሮ መቆየት የማይፈልግን ሰው እንዴት እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል? ከእኛ ተለይቶ ለመሄድ የማይፈልግን ሰውስ እንዴት እንዲሄድ ማድረግ ይቻላል? - Danny Devito

አሁን ባለንበት ዘመን ያላገቡ ወጣቶችን ስሜት ለቀውስ የሚዳርጉ ሁለት ልምምዶችን የሚገልጽ አባባል ነው፡፡

1) ያፈቀራችሁት ሰው “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ሲል ወይም 2) “አልፈልግም እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው “ሞቼ እገኛለሁ” ሲል ማድረግ የሚገባችሁን ካላወቃችሁ የሚደርስባችሁ የስሜት ቀውስ ረጅም ዘመን የሚከተል ሊሆን ይችላል፡፡

ያፈቀራችሁት ሰው “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ሲል ያላችሁ ምርጫዎች:-

1. በልመና፣ በለቅሶና በተስፋ-ቢስነት እንዳይሄዱ ለማድረግ ሲታገሉ መክረም፡፡

2. በግዳጅ፣ በዛቻና መግቢያ መውጪያ በማሳጣት እንዳይሄዱ ለማድረግ መታገል፡፡

3. ስሜትን በትክክል ከገለጹ በኋላ እምቢታቸውን በመቀበል መልቀቅና ራስ ላይ በመስራት ጉዞን መቀጠል፡፡

የትኛው ውሳኔ ይሻላል? ለምን?

“አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው “ሞቼ እገኛለሁ” ሲል ያላችሁን ምርጫ እንመለስበታለን፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

21 Nov, 02:00

ትችሉ ነበር አሁንም ትችላላችሁ!

አንዳንድ ሰዎች የእሳቤ ሂደት ይህንን ይመስላል፡-

“እንደምችል አውቀዋለሁ” በሚል ጠንካራ እሳቤ ይጀምራሉ፡፡

ትንሽ ተራምደው ያልጠበቁት ሁኔታ ሲገጥማቸው ቀስ በቀስ፣ “የምችል ይመስለኛል” ወደሚለው የጥርጣሬ ዘር ወዳለበት እሳቤ ወረድ ይላሉ፡፡

ብዙም ሳይቆዩ፣ “የምችል ይመስለኝ ነበር” ወደሚለው ደከም ወዳለ እሳቤ ይንሸራተታሉ፡፡

በመጨረሻ “አልችል” በማለት ጭራሹኑ ያቆሙታል፡፡

አንባቢዎቼ!!! ይህ ለብዙዎች ውድቀት ምክንያት የሆነ የእሳቤ ሂደት ለእናንተ አልተፈቀደላችሁም፡፡

እንደምንችል እናውቀው ነበር! እንችል ነበር! አሁንም እንችላለን!
በርቱና . . .

1. አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ደካማ ጎናችሁ ላይ ሳይሆን ዝንባሌያችሁና ብርቱ ጎናችሁ ላይ አተኩሩ፡፡

2. የምትጀምሩት ነገር ውጤታማ የሚያደርጋችሁ እስከሆነ ድረስ እንቅፋት እንደሚያጋጥማችሁ አትዘንጉ፡፡

3. ካለማቋረጥ ራሳችሁን አሻሽሉ፡፡

4. ስትወድቁም ሆነ ስትሳሳቱ ከልምምዱ የምታገኙትን ትምህርታችሁን ያዙና ወደፊት ቀጥሉ፡፡

5. በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

20 Nov, 02:00

ሁለት ነገር አስታውሱ!

ሰሞኑን ካነበብኳቸው አስተማሪ ታሪኮች አንዱን ወደ አማርኛ መልሼ ላጋራችሁ፡፡

በአንድ እጅግ በሚበርድ ምሽት አንድ የናጠጠ ባለሃብት አንድን በመንገድ ላይ የሚያድር ችግረኛ አገኘና፣ “በዚህ በብርድ ውጪ በመሆንህና በቂ ልብስ ባለመልበስህ አይበርድህም ?” ብሎ ጠየቀው፡፡

ችግረኛውም፣ “ብርዳማውን የአየር ጸባይ ከመቋቋም ውጪ ምርጫ ስለሌለኝና ስለተላመድኩት አይበርደኝም” ብሎ መለሰለት፡፡ ባለጠጋውም፣ “ጠብቀኝ የሚሞቅ ልብስ ከቤት ይዤልህ እመጣለሁ” አለውና ሄደ፡፡ ችግረኛው ሰውዬ በጣም በመደሰት፣ በተስፋ እንደሚጠባበቅ ነገረው፡፡

ባለጠጋው ግን እቤቱ ገብቶ በስራ በመጠመዱ ምክንያት ችግረኛውን ረሳው፡፡ ጠዋት እንደተነሳ ለችግረኛው የገባው ቃል ትዝ አለውና ፈጥኖ ሊፈልገው ወጣ፡፡ ሆኖም፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ከብርዱ የተነሳ ሕይወቱ አልፋ ነበር፡፡ አጠገቡ ግን እንደዚህ የሚልን ጽሑፍ ትቶ ነበር፣ “የሚሞቅ ልብስ ባልነበረኝ ጊዜ ብርዱን የመቋቋም ኃይል ነበረኝ፡፡ ነገር ግን እንደምትረዳኝ ቃል ስትገባልኝ፣ ቃል ኪዳንህ ከአሁን ከአሁን ይመጣል ብዬ በተስፋ ስጠባበቅ ብርዱን የመቋቋም አቅሜን ወሰደብኝ”፡፡

ከታሪኩ የምንማረው

1. የማንጠብቀውንና የማንፈጽመውን ቃል በፍጹም አንግባ፡፡ ለእኛ እንደ ቀላል ቢመስለንም፣ ለሌላው ሰው ግን የሕልውና ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡

2. ሰዎች ከሚገቡልን ቃል የተነሳ ማድረግ የሚገባንን ከማድረግ አንዘናጋ፡፡ ሰዎች ሁል ጊዜ ሰዎች ናቸውና አውቀውም ሆነ ሳያውቁት ችላ ሊሉን ይችላሉ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

19 Nov, 01:59

የምናጭደው የዘራነውን ነው

አንድ ሰው ወደ አንድ ገበሬ ተጠጋና በመጪው የመከር ወራት ምን አይነት ሰብል እንደምታጭድ ካለምንም ስህተት ልተነብይልህ እችላለሁ አለው፡፡ ከዚያም በኋላ ገለል ብሎ የሚዘራው ዘር ስንዴ መሆኑን በሚገባ ካጤነ በኋላ ጠጋ ብሎ፣ “በሚቀጥለው የምታጭደው ስንዴ ነው” አለው፡፡ እውነትም ወቅቱ ሲመጣ ያጨደው ስንዴ ነው፡፡

ገበሬ ስንዴ ዘርቶ ጤፍ፣ ገብስ ዘርቶ ማሽላ እንደማያጭድ ሁሉ የእኔና የአንተም ጉዳይ ይኸው ነው፡፡ ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸውን ሁኔታዎች ከራስህ ገለል ብለህ ተመልከታቸውና ምን እንደምታጭድ እቅጩን ይተነብዩልሃል፡፡

1. ዝም ለማለት የወሰንከውና ለመናገር የወሰንከው

መናገር ሲገባህ ዝም ያልካቸውን ሁኔታዎች ተመልከታቸው፡፡ ባለመናገርህ አንድ ቀን ውጤቱን ታጭዳለህ፡፡ ከዚያው ጋር ዝም ማለት ሲገባህ የተናገርካቸውን ሁኔታዎች አጢናቸው፡፡ መናገር ሳይገባህ በመናገርህ ምክንያት አንድ ቀን ውጤቱን ትታቀፋለህ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ዘር የሚዘራው በመናገር ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ሆኖም ዝም በማለትም ዘር ይዘራል፡፡ ዝምታ በራሱ ቃል-አልባ “ንግግር” ነውና! አብዛኛውን ጊዜ የሃገር፣ የድርጅትና የቤተሰብ መሪዎች የሚሰሩት ስህተት ዝም ብለው ያለፉት ነገር እዚያው የሚቀር ሲመስላቸው ነው፡፡

2. ላለማድረግ የወሰንከውና ለማድረግ የወሰንከው

ዛሬ ማድረግ ሲገባህ ያላደረካቸውን ነገሮች ተመልከታቸው፡፡ ማድረግ ሲገባህ ያለማድረግህን ውጤት ይዘህ እቤትህ የምትገባበት ቀን ይመጣል፡፡ ከዚያው ጋር ከማድረግ መቆጠብ ሲገባህ ያልተውካቸውን አንዳንድ ተግባሮች አስተውላቸው፡፡ ማቆም እንደሚገባህ አውቀህ በተግባር የጸናህባቸው ነገሮች ውጤት አንድ ቀን ብቅ ሲል ታየዋለህ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ዘር የሚዘራው አንድን ነገር በማድረግ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ማድረግ የሚገባንን ተገቢን ነገር አለማድረግም እኮ በራሱ ዘር ነው፡፡

3. ለመቆየት የወሰንክበትና ትተህ ለመሄድ የወሰንክበት ሁኔታ

ማንኛውም ስፍራም ሆነ ግንኙነት ትተህ መሄድ እንዳለብህ ውስጥህ እያወቀው ለራስህ የተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት የከረምክበትን ሁኔታ ተመልከተው፡፡ መቆየት በማይገባህ ቦታና ግንኙነት ውስጥ የመቆየትህን ፍሬ የምትበላበት ቀን ብዙም አይቆይም፡፡ ከዚያው ጋር በትእግስት መቆየት ሲገባህ በስሜታዊነትና በችኮላ ትተሃቸው የሄድካቸውን ሁኔታዎች፣ ስፍራዎችና ግንኙነቶች አጢናቸው፡፡ ፈጠነም ዘገየም የተግባርህን ጽዋ መጎንጨትህ አይቀረም፡፡

አንዳንድ ሰዎች ዘር የሚዘራው ከአንድ ነገር በመሄድ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ትተን መሄድ እንደሚገባን እያወቅን በቆየንበት ሁኔታና ግንኙነት ውስጥም ዘር ይዘራል፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

19 Nov, 01:58

የምናጭደው የዘራነውን ነው

Dr. Eyob Mamo

18 Nov, 17:01

ሰላም ለሁላችሁ!

ከማንም ሰው ጋር ለመኖር ከመሞከራችሁ በፊት ከራሳችሁ ጋር መኖርን ልመዱ፡፡ ያን ጊዜ ሰዎች ትተዋችሁ ሄዱም፣ አልሄዱም ከራሳችሁ ጋር በሰላም ትኖራላችሁ፡፡

ማንንም ሰው ለማሸነፍ ከመሞከራችሁ በፊት ራሳችሁን የማሸነፍ አቅም አዳብሩ፡፡ ያን ጊዜ ሰዎችን ብታሸንፉም፣ ባታሸንፉም ከራሳችሁ ጋር በሰላም ትኖራላችሁ፡፡

ማንም ሰው ይቅር እንዲላችሁ ከመታገላችሁ በፊት ራሳችሁን ይቅር በሉ፡፡ ያን ጊዜ ሰዎች አኮረፏችሁም፣ አላኮረፏችሁም ከራሳችሁ ጋር በሰላም ትኖራላችሁ፡፡

ማንም ሰው እንዲቀበላችሁ ከመታገላችሁ በፊት ራሳችሁን ተቀበሉ፡፡ ያን ጊዜ ሰው ተቀበላችሁም፣ አልተቀበላችሁም ከራሳችሁ ጋር በሰላም ትኖራላችሁ፡፡

የሰላም እንቅልፍ ይሁንላችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

18 Nov, 01:59

ከ “ብሆን” ወደ “ስሆን”

አሁን ያልሆናችሁትን ማንነት፣ ያላገኛችሁት ነገር፣ ያልደረሳችሁበትን ደረጃ፣ ያላወቃችሁትን እውቀትም ሆነ ሌሎች ወሳኝ ነገሮች አስመልክቶ “ብሆን” በማለት የምታስቡትንና የምትናገሩትን፣ “ስሆን” ወደሚለው እንድትቀይሩት ላነሳሳችሁ፡፡

“ብሆን” የሚለው ሃሳብ ምኞት-ተኮር ሃሳብ ነው፣ “ስሆን” የሚለው አባባል እቅድ-ተኮር ሃሳብ ነው፡፡

“ብሆን” የሚለው ሃሳብ ተስፋ-ቢስነትን ያመለክታል፣ “ስሆን” የሚለው አባባል ጽኑ እምነትን ያሳያል፡፡

“ብሆን” የሚለው አመለካከት ባሉበት ያስቀራል፣ “ስሆን” የሚለው እሳቤ ግን ወደስራ ያንቀሳቅሳል፡፡

ለምሳሌ፣ እሳቤያችሁንም ሆነ ንግግራችሁን . . .

• የተማርኩ “ብሆን” ከሚለው፣ የተማርኩ “ስሆን” ወደሚለው፣

• ባለሃብት “ብሆን” ከሚለው፣ ባለሃብት “ስሆን” ወደሚለው፣

• ነጋዴ “ብሆን” ከሚለው፣ ነጋዴ “ስሆን” ወደሚለው፣

• ባለትዳር “ብሆን” ከሚለው፣ ባለትዳር “ስሆን” ወደሚለው . . .

የቀረውን ከእናንተው የወቅቱ ሁኔታ ጋር በማገናኘት ቀጥላችሁ ከጻፋችሁ በኋላ፣ ሁኔታው ቅዠት ሆኖ እንዳይቀር . . .

1. “ስሆን” ብላችሁ ያሰባችሁትና የተናገራችሁት ሁኔታ በእርግጥም መሆን የምትፈልጉት መሁኑን እርግጠኞች ሁኑ፣

2. “ስሆን” ብላችሁ ባሰባችሁትና በተናገራችሁት ሁኔታ አንጻር ተግባራዊ እቅዶችን አውጡ፣

3. ባወጣችሁት እቅድ መሰረት ቀስ በቀስ እርምጃን ጀምሩ፣

4. በዚህ ሂደት ውስጥ ሊያግዛችሁ ከሚችል ሰው እውቀትንና ልምድን ለማግኘት መክፈል ያለባችሁን ዋጋ ክፈሉ፣

5. “ስሆን” ብላችሁ የምታስቡትን ሃሳብና እቅድ ላገኛችሁት ሰው ሁሉ አትንገሩ፣

6. አሉታዊና ተስፋ አስቆራጭ ሃሳብ ለሚናገሩ ሰዎች ደካማ ሃሳብ ቦታ አትስጡ፣

7. “ስሆን” ብላችሁና አይታችሁ የተነሳችሁበት ደረጃ እስከምትደርሱ በፍጹም አታቁሙ፡፡

በውስጠ-ህሊናችሁ አጥርታችሁ ያያችሁትንና አጥብቃችሁ የተከታተላችሁትን ነገር ወደመሆን ማደጋችሁ አይቀርም!!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

18 Nov, 01:58

ከ “ብሆን” ወደ “ስሆን”

Dr. Eyob Mamo

15 Nov, 16:52

አመሰግናለሁ!

በአካል ባላውቃችሁም ባበረከታችሁት መጽሐፍቶቻችሁ ብቻ ሕይወቴን የለወጣችሁ የሃገራችንና የውጪ ደራሲዎች፣ ፈጽሞ በማታውቁት ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ ማድረግ እንደሚቻል ተምሬባችኋለሁና አመሰግናለሁ!

ከሕይወት ተሞክሮዬ በመነሳት ከማስተላልፋቸው ሃሳቦች የሚጠቅማችሁን እየወሰዳችሁ፣ ወቅታዊ ያልሆነላችሁን ደግሞ እየታገሳችሁ ለበለጠ ነገር የምታነሳሱኝን፣ ልበ-ሰፊነትን ከእናንተ ተምሬአለሁና አመሰግናለሁ!

ሁል ጊዜ ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ የምትቀበሉኝንና የምታከብሩኝን የቅርብ ወዳጆቼንና የሩቅ አድናቂዎቼን፣ እውነተኛነትንና ጨዋነትን ተምሬባችኋለሁና አመሰግናለሁ!

ትንሽ ስህተት ያያችሁብኝ ስለመሰላችሁ ብቻ የብዙ አመታት መልካም ስራዬ ትዝ እስከማይላችሁ ድረስ የተለወጣችሁብኝን፣ ከማንም ሰው ውጪ መኖርና ዓላማን መፈጸም እደሚቻል አስተምራችሁኛልና አመሰግናለሁ!

በሕይወታችሁ የምታልፉበትንና ለማንም ሰው ለመናገር ያልደፈራችሁበትን የግላችሁን ምስጢር ለእኔ አስከማጋራት ላመናችሁብኝ፣ ላመነብኝ ሰው ታማኝ የመሆንን ልምምድ እንዳዳብር ሞግታችሁኛልና አመሰግናለሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

15 Nov, 12:17

https://youtu.be/mwlJWUpkoZA

Dr. Eyob Mamo

15 Nov, 02:13

የወቅት ባህሪይ

ወቅት ወቅት ነው! ይለዋወጣል! ይመጣል፣ ይሄዳል፡፡

ስለዚህ . . .

አንደኛ፡-
አሁን ያላችሁበት አስቸጋሪ የወቅቱ ሁኔታችሁ እንደመጣ ሁሉ ይሄዳል፡፡ እስከሚሄድ ግን ታገሱ፣ ተረጋጉ፣ የማይዘልቀው አስቸጋሪ ሁኔታችሁ ዘላቂ ጠባሳ እንዳይተውባችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡

ሁለተኛ፡-
አሁን ያላችሁበት ደስ የሚልና ስኬታማ ሁኔታችሁ እንደመጣ ሁሉ ጊዜው ይለወጥና ፈታኝ ሁኔታ ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህ የከፍታችሁ ጊዜ እስካለ ድረስ ግን አትዘናጉ፣ እቅድ አውጡ፣ ጠንክራችሁ ስሩ፣ ነገ ላይዘልቅ የሚችለው ይህ መልካም ሁኔታችሁን ተጠቅማችሁ ዘላቂ የሆነንና ነገ የሚሸከማችን ነገር ገንቡ፡፡

ፈጣሪ ያግዛችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

14 Nov, 02:00

ከልዩነት ባሻገር!

ልዩነቱ የዘር፣ የቋንቋ፣ የመልክ፣ የቁመናም ሆነ የእምነት . . . ከእናንተ ለየት የሚለው ሰው በአካባቢያችሁ ሲሰራም ሆነ ሲኖር፣ ለየት ያለ ሰው በመሆኑ ምክንያት ከእናንተ ምንም አይነት ጥቃት፣ በደልና መገለል እንደማይደርስበት እንዲሰማው የማድረግ ሃላፊነት እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ፡፡ ይህንን ሃላፊነት መወጣት የትክክለኛ ስብእና ምልክቱ ነው፡፡

የእኛ ዘር፣ ቋንቋ፣ መልክ፣ ቁመና እና እምነት ያለው እኛን መሰል ሰው የሚጠቃበት፣ የሚበደልበትና የሚገለልበት አካባቢ እንዳለ አትዘንጉ፡፡ እኛ እዚህ በሌላው ላይ የምናደርገውን ሌሎች እዚያ በእኛ እና እኛን በመሰሉት ላይ ያደርጉታል፡፡ ዑደቱ ይኸው ነው፡፡

የጨዋነት ሁሉ ጨዋነት ከእኛ ለየት ያሉትን የመቻልና የመቀበል ጨዋነት ነው!

መልካም ቀን!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

13 Nov, 02:00

አድናቂያችሁ ነኝ!

• ሌላ አማራጭ መከተል ስትችሉ የምትወዷቸውን ቤተሰቦቻችሁን መርዳት ስላለባችሁ ብቻ የማትፈልጉትን ስራ ለምትሰሩ፣

• ትዳር ይዛችሁ የግል ሕይወታችሁን መኖር ስትችሉ እናንተ ከሄዳችሁ ደጋፊ ለሌላቸው ሰዎች ስትሉ እቅዳችሁን ይቆይልኝ ላላችሁ፣

• ሌላ ስፍራ ሄዳችሁ መኖር ስትችሉ የእናንተ በአካባቢው መገኘት ለሕልውናቸው ወሳኝ ለሆነላቸው ሰዎች ስትሉ እግራችሁን ለሰበሰባችሁ፣

• ሌላ ሕይወት መጀመር ስትችሉ ለልጆችሁ ስትሉ ለጊዜውም ቢሆን የብቸኝነትን ኑሮ ይዛችሁ ለምትታገሉ ብቸኛ ወላጆች (Single Parents)፣

• ለተደረገባችሁ ክፉ ነገር አጸፋ ብትመልሱ ለብዙ አመታት የተገነባ ነገር እንዳይፈርስ በማለት ብዙ ነገር በትእግስትና በዝምታ ለተሸከማችሁ፣

ለእናንተና መሰሎቻችሁ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት አለኝ!

ፈጣሪ ያግዛችሁ! ይካሳችሁ! ለሌላው ብላችሁ ለእናንተ የሚበጀውን በተዋችሁት ሁሉ በብዙ እጥፍ ይስጣችሁ!

ሁሌም አድናቂያችሁ ነኝ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

12 Nov, 16:48

https://vm.tiktok.com/ZMhpF9BeY/

Dr. Eyob Mamo

12 Nov, 02:00

እንኳን በሕይወት ነቃችሁ!

በሰላም ስላደራችሁ ደስ ይበላችሁ!

በዓለም ላይ በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ አይሮፕላኖች እየተነሱ በሰላም ያሰቡበት በመድረስ ያርፋሉ፡፡ ከእነዚህ በረራዎች መካከል ግን የአንዱም እንኳን በሰላም መግባት በዜናዎች ላይ ሲነገር አንሰማም፡፡ ሆኖም፣ አንድ በረራ ላይ አደጋ ከደረሰ ግን ትኩረት ይስባል፣ ዜናውን ይሞላዋል፣ ወሬው ይሸጣል፡፡

የአንድ ጤናማ ሰው ልብም ቢሆን በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ ይመታል፡፡ ይህንን ያህል ጠንክሮ የሚሰራው አካላችን ግን በቀን ውስጥ ትዝም አይለን፡፡ የምናስታውሰው መምታት ለማቆም ሲዳዳውና የምቱ ድግግሞሽ ሲለይብን ነው፡፡ ለምን? መልካሙ ነገር ተለምዷል፡፡ የምስራች የሆነው ነገር ትዝም አይለን፡፡

ዛሬ መልካም መልካሙን ላስታውሳችሁ፡፡ ዛሬ የምስራቹ ትዝ ይበላችሁ፡፡ በሰላም የመንቃታችሁ ጉዳይ፣ በሌሎች ላይ የደረሰ እናንተ ላይ ያለመድረሱ ጉዳይ፣ የደረሰባችሁ ነገር ከዚህ የከፋ ያለመሆኑ ጉዳይ . . . ትዝ ይበላችሁ፡፡

ከደረሰብን ክፉ ነገር የሆነልን መልካም ነገር ይበዛልና ደስ ይበላችሁ፡፡

ፈጣሪን አመስግኑ! ቤተሰቦቻችሁን፣ ጓደኞቻችሁንና በሕይወታችሁ ላይ መልካም ተጽእኖ ያደረጉ ሰዎችን አድንቁ!

መልካም ቀን!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

11 Nov, 02:00

ስሜት ይመጣል፣ ስሜት ይሄዳል!

ማናልባት እንደ ስሜታችን ተለዋዋጭ የሆነ ነገር በሕይወታችን አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ በተለዋዋጭነቱ ከምናውቀው ከአየር ጸባይ በፈጠነ ሁኔታ የሚለዋወጥ ነገር ቢኖር ስሜታችን ነው፡፡

ከእውነታው ስንጀምር . . .

ስሜታዊ ፍጥረቶች የመሆናችንን፣ ስሜታችን ደግሞ በየጊዜው (አንዳንዴም በየሰዓቱ) እንደሚቀያየር፣ የስሜታችንን መቀያየር ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር እንደማንችል እና የስሜቶቻችን ጉዳይ ችላ ካልን የፍጻሜያችንን ሁኔታ እንደሚነካው እናስታውስ፡፡

በየጊዜው፣ እንደሰማነው፣ እንዳየነውና በዙሪያችን እንዳለው ሁኔታ የሚነካውንና የሚለዋወጠውን ስሜታችን በተገቢው መልክ ለመያዝና የወደፊት ሕይወታችንን እንዳያበላሽ ከፈለግን የሚከተሉት ልምምዶች ይጠቅሙናል፡፡

1. ስሜት በተለዋወጠ ቁጥር ሃሳብን አለመለዋወጥ፡፡
አንድ ጥሩም ሆነ መጥፎ ስሜት ሲሰማን፣ ፈጥነን የሃሳብ ለውጥ ከማድረግ መቆጠብ ስሜት ከሚያመጣው ጫና ራሳችንን እንድንጠብቅ ያግዘናል፡፡

2. ስሜት በተለዋወጠ ቁጥር ዓላማን አለመለዋወጥ፡፡
ስሜታችን ጥሩ ሆነም መጥፎ ከዓላማችን ለይተን ማየትና ማስተናገድ አስፈላጊ ነው፡፡ ማንኛውም ስሜት እያለ ዓላማችንን መከታተላችንን መቀጠል ስኬታማ ሰዎች ያደርገናል፡፡

3. ስሜት በተለዋወጠ ቁጥር ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት አለመዋወጥ፡፡
ስሜቴ ጥሩ በሆነና መጥፎ በሆነ ቁጥር ከሰዎች ጋር ያለኝን ግንኙነት የሚነካው ከሆነ የተበላሸ ማሕበራ ሕይወትና የሕይወት አቅጣጫ ውስጥ መግባቴ አይቀርም፡፡

ስሜት ሲመጣና ሲሄድ የያዝነውን ትክክለኛ ሃሳብ ይዘን እንቀጥል፤ ዓላማችንን ይዘን እንዝለቅ፤ ከሰዎች ጋር ያለንን ጤናማ ግንኙነት ይዘን እንኑር፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

11 Nov, 01:59

ስሜት ይመጣል፣ ስሜት ይሄዳል!

Dr. Eyob Mamo

08 Nov, 02:01

እንደምንም ብላችሁ ጀምሩት!

አንድን ማድረግ ያለባችሁ ነገር ትክክለኛ ነገር መሆኑን እና ወቅቱ እንደሆነ እርግጠኛ ከሆናችሁ . . .

• ሰዎች ሁሉ እስከሚደግፏችሁና በርቱ እስከሚሏችሁ ድረስ አትጠብቁ! ብቻችሁንም ቢሆን ጀምሩት!

• የፍርሃት ስሜት ሙሉ ለሙሉ ከእናንተ እስከሚወገድ ድረስ አትጠብቁ! እየሰጋችሁም ቢሆን ጀምሩት!

• ሁሉም ነገር እስከሚሟላላችሁ ድረስ አትጠብቁ! የአቅርቦት እጥረት እያላችሁም ቢሆን ጀምሩት!

• ሙዳችሁ ጥሩ እስከሚሆን አትጠብቁ! የስሜት ውጣውረድ እያለባችሁም ቢሆን ጀምሩት!

ያልተጀመረ ነገር አይቀጥልምና ጀምሩት!

ያልተሞከረ ነገር ይሳካና አይሳካ አይታወቅምና ሞክሩት!

ያልተንቀሳቀሰ ነገር እንደቆመ ይቀራልና አንቀሳቅሱት!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

07 Nov, 11:16

https://youtu.be/pP_ErJeIzvw?si=6u2yPrlF3XH99knb

Dr. Eyob Mamo

07 Nov, 02:00

ሁለት የደስታ እውነታዎች

ለራሳችሁ ደስተኛነት ሃላፊነቱን መውሰድ ያለባችሁ ራሳችሁ መሆናችሁን ለአፍታም አትዘንጉ፡፡

ሰዎች ደስተኛ እንዲያደርጓችሁ በጠበቃችሁ ቁጥር እንዳዘናችሁና እንደተጎዳችሁ ትኖራላችሁ፡፡

በዚያ ምትክ፣ ሰዎች ደስ የሚያሰኛችሁን ሲያደርጉላችሁ አመስግኑ፣ የጠበቃችሁትን ካላገኛች ግን ከራሳችሁ ጋር በደስተኛነት መኖርል ልመዱ፡፡

በሌላ አገላለጸ፣ ከሰዎች ውጪ ደስተኛ መሆንን ተለማመዱ!

ሰዎች ያደረጉትንና ያላደረጉትን ከመቁጠር ይልቅ ፈጣሪ ያደረገላችሁን እያሰባችሁ በደስተኛነት መኖር ልመዱ!

በተመሳሳይ ሁኔታ ለሌሎች ሰዎች ደስተኛነት እናንተ ሃላፊነትን አትውሰዱ፡፡

ሰዎችን ደስተኛ ለማድረግ በታገላችሁ ቁጥር ከማንነታችሁ፣ ከዓላማችሁና ራሳችሁን ሆናችሁ ከመኖር እየራቃችሁ ትሄዳላችሁ፡፡

በዚያ ምትክ፣ ለሰዎች መልካም ነገር አድርጉ፣ ደስተኛ የመሆንንና ያለመሆንን ምርጫ ግን ለእነሱ መተውን ተለማመዱ፡፡

በሌላ አገላለጸ፣ ከሰዎች ደስተኛነት ውጪ ሙሉ ሕይወት መኖርን ተለማመዱ!

ሰዎች በእናንተ የመደሰታቸውንና ያለመደሰታቸውን ሁኔታ ከመቁጠር ይልቅ ለሰዎቹ ማድረግ የቻላችሁትን ነገር ለማድረግ ፈጣሪ ስለረዳችሁ እያሰባችሁ በደስተኛነት መኖር ልመዱ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

06 Nov, 17:24

“ስለሌሎች ሰዎች የምትናገሩት ነገር ስለ እናንተ ብዙ ይናገራል” (Today's Wisdom)

Dr. Eyob Mamo

06 Nov, 02:02

እድሜያችሁን እያጣጣማችሁ ኑሩ!“

“30 ዓመት የሞላው ሰው እንደ ሽማግሌ ይቆጠራል፣ በ 30 ዓመቱ የሞተ ሰው ደግሞ በለጋ እድሜው እንደተቀጠፈ ይታያል፡፡ በእድሜያችሁ ምክንያት ማንም ሰው ግፊት እንዲያደርግባችሁ አትፍቀዱ” (Vibes)

ለእድሜያችሁ የሚመጥን የጥበብና የብስለት ደረጃ ላይ የመድረሳችሁና ያለመድረሳችሁ ሁኔታ ያሳስባችሁ እንጂ የእድሜ ደረጃችሁ አያሳስባችሁ፡፡

ለእድሜያችሁ በሚመጥን ሁኔታ በራእይና በእቅድ ኑሩ እንጂ እድሜያችሁ ስንት እንደደረሰ ስትጨነቁ ጊዜያችሁን አታባክኑ፡፡

እድሜዬ ፈጥኖ ያልፋል ብላችሁ መጨነቅ አቁሙና፣ ያለሁበትን እድሜ ሳላጣጥመው ሊያልፍ ነው የሚለው ጉዳይ ያሳስባችሁ፡፡

እድሜን በማጣጣም መኖር ማለት፣ ካለፈው በመማርና ለነገው በማቀድ የወቅቱ እድሜያችን የሰጠንን እድል መጠቀምና ባለን አቅም መኖር ማለት ነው፡፡

እግረ መንገዴን እናንተ የደረሳችሁበትን እድሜ ሳያዩ ያለፉና የሚያልፈ ብዙ ናቸውና ፈጣሪን ማመስገንን እንዳትረሱ ላስታውሳችሁ፡፡

ዋናው ነገር በሕይወታችሁ ውስጥ ያሉት ዓመታት ጉዳይ ሳይሆን በዓመታቶቻችሁ ውስጥ የኖራችሁት ጥራት ያለው ሕይወት መሆኑን አትርሱ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

05 Nov, 14:14

https://vm.tiktok.com/ZMh4VS8SY/

Dr. Eyob Mamo

05 Nov, 02:00

ሁለቱ እስረኞች

ማሕበራዊ ግንኙነታችንን አስመልክቶ ሁለት አይነት እስረኞችን ቆልፈው የሚያስቀምጡ ሁለት አይነት እስር ቤቶች አሉ፡፡

የመጀመሪያው እስር ቤት የጸጸትና የጥፋተኝነት ስሜት እስር ቤት ነው፡፡ ይህ እስር ቤት ሌላውን ሰው ካለአግባብ በመጉዳታችንና በመበደላችን ምክንያት የምንገባበት እስር ቤት ነው፡፡

በዚህ እስር ቤት ውስጥ ራሳችንን ስናገኘው ትክክለኛውን ውሳኔና እርምጃ እስከምንወስድ ድረስ ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡

አንድን ሰው እንደበደላችሁት ከተሰማችሁና ሁል ጊዜ የመጸጸት ስሜት ከተሰማችሁ ከዚህ እስር ቤት በነጻ የምትፈቱበት ቀላሉ መንገድ ሰዎቹን ይቅርታ መጠየቅና ምናልባትም ባጠፋችሁት ጥፋት ምክንያት ያባከናችሁባቸው ወይ የወሰዳችሁባቸው ነገር ካለ በተቻላችሁ መጠን ካሳ መክፈል ነው፡፡

ሁለተኛው እስር ቤት የቂምና የመራራነት እስር ቤት ነው፡፡ ይህ እስር ቤት ሰዎች ካለአግባብ ሲበድሉንና ጉዳት ሲያደርሱብን የምንገባበት እርስ ቤት ነው፡፡

በዚህ እስር ቤት ውስጥ ራሳችንን ስናገኘው ምንም እንኳን የተበደልነው እኛው ብንሆንም ሰዎቹ ያደረጉብንን ሁኔታ ከውስጣችን በማውጣት ካላስወገድነው ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡

አንድ ሰው ጥፋት ስላጠፋችሁ ጉዳት ካለባችሁና በዚያ ሰው ላይ ቂምና መራራነት ካለባችሁ ከዚህ እስር ቤት በነጻ የምትፈቱበት ቀላሉ መንገድ ሰዎቹን ይቅር ማለትና ምናልባት ለወደፊቱ ግንኙነታችሁ የማያዛልቅ መስሎ ከታያችሁ ግንኙነቱን በጥበብ ማድረግ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ በእነዚህ እስር ቤቶች ቆልፎ የሚያስቀምጠን ሁኔታ ከቅርብ ቤተሰባችን ብዙም እንደማይርቅ ላስታውሳችሁ፡፡

ሰዎችን ይቅርታ ጠይቁ! ሰዎችን ይቅር በሉ! ነጻ ውጡ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

Dr. Eyob Mamo

04 Nov, 02:00

ሚዛናዊ የስሜት አገላለጥ

ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት ስሜታችሁን የሚነካ ነገር ሲያጋጥማችሁ ከሁለት ስህቶች ተጠንቀቁ፡፡

1. ስሜታችሁን እንደወረደ ከመልቀቅ መጠንቀቅ

አንድ ስሜት ሲሰማን ያንን ስሜት ካለምንም ገደብና ሚዛናዊነት እንደወረደ ስንለቀው ያልተጠበቀና ልንቆጣጠረው የማንችለው ውጤት ሊያስከትልብን ይችላል፡፡ ከእነዚህ አጉል ውጤቶች መካከል፣ ሰዎችን መጉዳት፣ ከቁጥጥር ውጪ የሆነና ነገሩን የሚያባብስ የሰዎች ምላሽ መከሰት እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ነገሮች እየተባባሱ የኋላ ኋላ የማንፈልጋቸውንና መዘዝ የሚያመጡ ሁኔታዎችን ሊወልዱ ይችላሉ፡፡

2. ስሜታችሁን ከማፈን መጠንቀቅ

ሰዎች ስሜታዊ የሚያደርገንን ነገር ሲያደርጉብን፣ የሚሰማንን ስሜት አምቀን በያዝነው ቁጥር ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን በራሳችን ላይ ያስከትላል፡፡ ከእነዚህ ጉዳቶች አንዱ፣ በታመቀው ስሜት ምክንያት የሚመጣ የውስጥ መጎዳት ነው፡፡ ከዚህ የተለየውና ብዙዎች የማያስተውሉት ሌላው ጉዳት፣ ስሜታችንን አምቀን ከቆየን በኋላ ሲብስን ድንገት “የመፈንዳት” ሁኔታ የሚያስከትለው መዘዝ ነው፡፡

የዚህ ሁኔታ ችግሩ፣ አምቀን የቆየነውንና ማንም ሰው የማያውቀውን ስሜት በድንገት ስንለቀው ሰዎች እስካሁን ያለፍንበትን ሁኔታ እና ያመቅነውን ስሜት ስለማያውቁት፣ እንደ አጉል ስሜታዊ ይቆጥሩንና ጥፋቱን ሁሉ በእኛ ላይ ያደርጉታል፡፡ ይህ ደግሞ ሌላ ጉዳትን ያስከትልብናል፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጎጂ ሁኔታዎች እንዳይከሰቱ ለማድረግ ከፈለግን ስሜታችንን ለትክክለኛው ሰው፣ በትክክለኛው ቦታ፣ በትክክለኛው ጊዜ እና በትክክለኛው መጠን መግለጥን መለማመድ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ የተለማመደ ሰው ከፍተኛ የስሜት ብልህነት ደረጃ ላይ ያለ ሰው ነው፡፡ ምንም እንኳን ሙሉ ለሙሉ ከስሜታዊነት ነጻ የሆነ ልምምድ ባይኖረንም በተቻለን መጠን ግን ይህንን መመሪያ መከተል ለግልም ሆነ ለማሕበራ ስኬታማነታች አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

04 Nov, 01:59

ሚዛናዊ የስሜት አገላለጥ

Dr. Eyob Mamo

02 Nov, 02:00

ብዙ ጊዜ ያላችሁ እንዳይመስላቸሁ!

በሕይወታችን ልንሰራቸው ከምንችላቸው ስህተቶች አንዱና ከሰራነው ደግሞ የሚያደርስብን “ቅጣት” ጠሊቅ የሆነ ስህተት ቢኖር አሁን ያለንበት የእድሜ ደረጃና ሁኔታ ብዙ እንደሚቆይ የማሰብ ስህተት ነው፡፡

• የማሕጸን ውስጥ እድሜያችን ቢበዛ ዘጠኝ ወር ነች፡፡ ከዚያም መውጣ ሳንፈልግ እያለቀስን ወደሚቀጥለው የሕጻንነት ምእራፍ በምጥ ተገፍተን ወጣን፡፡

• የሕጻንነት እድሜያችን ቢበዛ አምስት ነች፡፡ ከዚያም ብዙም ባያጓጓንም እያለቀስንም ቢሆን ወደሚቀጥለው የትምህርት ቤት አለም ተገፍተን እንገባለን፡፡

• የልጅነትን የትምህርት ቤት አለም ብዙም ሳናጣጥመው ከስምንት ባልበለጡ ዓመታት ውስጥ ወደ ቲንኤጅ እድሜያችን ተሸጋገርን፡፡

• ከሰባት ዓመታት የማይበልጠው የቲን ኤጅ እድሜያችን በብዙ ራስን የማግኘት ውጥረት ተጣድፎ በማለፍ ለጉልምስና እድሜ አሳልፎ ሰጠን፡፡

• የጉልምስና ዓመታቶቻችንም ቢሆኑ ሰባት ዓመታት ሳይሞሉ “አዋቂ” ወደተሰኘው ሕይወትን በመመስረትና በመምራት ሸክም ወደተሞላው የእድሜ ክልል ውስጥ ገፍቶ ያስገባናል፡፡

• የአዋቂነትና የሃላፊነት እድሜያችንን አንዱን በመጣልና ሌላውን በማንሳት ስንታገል የሽምግልና ዘመን ጀንበር ብቅ ስትል እናያታለን፡፡

እውነታው ይህ ከሆነ ምን እናድረግ?

1. ለእድሜያችን የሚመጥን የእድገት ደረጃ ላይ መሆናችንን እርግጠኞች እንሁን፡፡

2. አሁን ያለንበት እድሜና ከእሱ ጋር የሚመጣው እድል ዳግም ስለማይገኝ በሙሉ ኃይላችን እንጠቀምበት፣ እንደሰትበት፣ እንደግበት፡፡

3. እድሜያችን እየጨመረ በሄደ ቁጥር በአእምሮና በጥበብ የመብሰላችንም ጉዳይ ይታሰብበት፡፡

4. መቼም ቢሆን ፈጣሪን ማሰብና መፍራት አንተው።

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

Dr. Eyob Mamo

01 Nov, 02:01

የመኖርህና ያለመኖርህ ጉዳይ

በአንድ ቦታ ወይም ግንኙነት ውስጥ አለመኖርህ የሚያጎድለው ነገር ከሌለ፣ መኖርህ የሚሞላው ነገር የለም ማለት ነው፡፡ በተቃራኒ ደግሞ በአንድ ቦታ ወይም ግንኙነት ውስጥ መኖርህ የሚሞላው ነገር ካለ፣ አለመኖርህ የሚያጎድለው ነገር አለ ማለት ነው፡፡

ይህንን ለማወቅ ከፈለክ ደግሞ ሁለት ጥያቄዎችን ጠይቅ፡-

1) መኖሬን የሚያደንቁ ሰዎችና ቦታዎች የትኞቹ ናቸው?

2) አለመኖሬ ምንም እንዳላጎደለባቸው የሚያሳዩኝ ሰዎችና ቦታዎችስ የትኞቹ ናቸው?

በሕይወትህ እንደቀፈፈህ፣ የውስጥ አቅም እንዳጣህና ሰላምህን እንዳጣህ እንድትኖር ከሚያደርጉህ ልምምዶች መካከል አንዱ ብትኖር የማትደነቅበት፣ ባትኖር ደግሞ የማትናፈቅበት አካባቢ በግድ የመገኘት ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን ልምምድ በሚሰጥህ አካባቢ ወይም ጓደኝነት ውስጥ መቆየት በማንነትህ ላይ ይህ ነው የማይባል የራስ-በራስ ንቀትን ከማስከተሉም በተጨማሪ ራስህን በመናቅ ሌሎች እንዲንቁህና እንዲቆጣጠሩህ ፈቃድ እንድትሰጣቸው መንገድን ይጠርጋል፡፡

መኖርህ የሚሞላው ነገር፣ አለመኖርህ ደግሞ የሚያጎድለው ነገር እንዳለ በማመን በብርቱ የሚፈልጉህ ሰዎች እያሉ፣ ብትኖርም ባትኖርም ምንም የምትሞላውም ሆነ የምታጎድለው ነገር እንደሌለ ከሚያስቡና ያንንም ከሚያሳዩህ ሰዎች አካባቢ ጊዜህን አታባክን፡፡

በዚህ ምድር ላይ ሁል ጊዜ ተለጣፊ፣ ተንጠልጣይ፣ ለማኝና ተለማማጭ ሆነህ ለመኖር አልተፈጠርክም፡፡ የራስህ ስፍራ ያለህ ሰው ነህ፡፡ የምትወደድበት፣ የምትደነቅበትና የምትፈለግበት ቦታ ያለህ ሰው ነው፡፡

ዛሬ ከአንተ ጋር ምንም ግንኙነት ባለማድረግ ውስጥ ምቾት ከሚሰጣቸው ሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት እንደገና የምትፈትሽበት ቀን ይሁንልህ!

ዛሬ መኖርህ የማያጓጓቸው፣ አለመኖርህ ደግሞ የማይናፍቃቸው ሰዎች ጉዳይ ይታሰብበት!

ያን ጊዜ ለራስህ ያለህን ክብር ትመልሳለህ፡፡ ያን ጊዜ ሰውን መለማመጥ አቁመህ ቀና ብለህ ከዓላማህ አንጻር መኖር ትጀምራለህ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

01 Nov, 01:59

የመኖርህና ያለመኖርህ ጉዳይ

Dr. Eyob Mamo

31 Oct, 02:00

ላልተጠበቀው ነገር መዘጋጀት

ሁል ጊዜ አንድን ነገር ስትጀምሩ በመንገድህ ላይ ያልተጠበቀ ነገር እንደሚገጥማችሁ አትዘንጉ፡፡ እነዚህ የማትጠብቋቸው ነገሮች አብዛኛዎቹ ምንጫቸው ከእናንተ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡ ሊገመት የማይችል የሁኔታዎች መለዋወጥ፣ ሊተነበይ የማይችል የሰዎች ባህሪይ መቀያየርና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ከመንገዳችሁ ላይ እንቅፋት እንዳይጠፋ ያደርጉታል፡፡

እነዚህ ሁኔታዎች አንድን ነገር ለመጀመር፣ ከጀመርን በኋለ ለመቀጠል፣ አልፎም ወደፍጻሜ ስንደርስ እንዳንጨርስ ሲጋረጡብን እናገኛቸዋለን፡፡ ይህንን አይነቱን የማይቀር የሕይወት ሂደት የተለያዩ ሰዎች በተለያየ መልኩ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ አንዳንዶች ለደረሰብን እንቅፋት ሁሉ በሰዎች፣ በሁኔታዎችና በፈጣሪ የማማረር ልማድ ልማድ አለብን፡፡ በዚያም ሁኔታ ተደብቀን በተስፋ መቁረጥ እርምጃችንን እንተዋለን ወይም ለሌላ ጊዜ እናስተላልፈዋለን፡፡

ሶስት አይነት እንቅፋቶች አሉ . . .

1. አንዳንዱ እንቅፋቶች ቀድሞውን ሊደርሱ የሚችሉ እንቅፋቶችን በማጤንና በማቀድ ልታስወግዷቸው የምትችሏቸው ናቸው፡፡

2. ሌሎቹ እንቅፋቶች አስቀድማችሁ አቀዳችሁም አላቀዳችሁም ከመምጣት የማታስወግዷቸው እንቅፋቶችና እንደአመጣጣቸው ልትመልሷቸው የምትችሏቸው ናቸው፡፡

3. ሌሎቹ ግን እንቀፋቱና ችግሩ እያለ መንገዳችሁ ላይ ብቻ በማተኮር ወደፊት ልትቀጥሉ የሚገባችሁ አይነት እንቅፋቶች ናቸው፡፡

ከላይ በተጠቀሱት የእንቅፋት አይነቶች መካከል የመለየታችሁ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በተጨማሪ እነዚህን አትርሱ፡-

1. ሁል ጊዜ አንድ ነገር ለመጀመር እቅድ ሰታወጡ በእቅዳችሁ ውስጥ ለድንገተኛውና ላልተጠበቀው እንቅፋት ማቀድን አትርሱ፡፡

2. ያልተጠበቀና ድንገተኛ እንቅፋት ሲያጋጥማችሁ ትክክለኛውን ምላሽ በመምረጥ ምላሽን ለመስጠት ሞክሩ፡፡

3. አንድ እንቅፋት ካጋጠማችሁና አስፈላጊውን ምላሽ ከሰጣችሁ በኋላ ወደ ዓላማችሁና ወደስራችሁ በመመለስ እሱ ላይ ማተኮርን አትርሱ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

31 Oct, 01:59

ላልተጠበቀው ነገር መዘጋጀት

Dr. Eyob Mamo

30 Oct, 14:07

“በራእይ የሚመራ ሕይወት” ስልጠና!!!

ያለፈው ኃሙስ ምሽት በTelegram (Online) የጀመረው ስልጠና ነገም ይቀጥላል፡፡

ያለፈው ያመለጠን ምን እናድረግ ብላችሁ በጠየቃችሁት መሰረት፣ ዛሬንና ነገን በመመዝገብና ያለፈውን ትምህርት ቅጅ በማዳመጥ በመቶ የሚቆጠሩ ሰልጣኞችን መቀላቀል ትችላላችሁ፡፡

የነገውን ትምህርት ይዘት በቪዲዮ ላይ የመልከቱ፡፡

በቴሌግራም @DrEyobmamo inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ የመመዝገብ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

30 Oct, 02:00

ራስን መግፋትና አለመቀበል

አብዛኛው ራስን ያለመቀበል መዘዝ መንስኤው የአስተዳደግ ሁኔታ ነው፡፡ ከዚያም ጋር ተያይዞ ሕብረተሰቡ አንድ ሰው “ሙሉ” ነው በማለት ያስቀመጠው መስፈርት በሰዎች ላይ ይህ ነው የማይባል ጫናን ያስከትላል፡፡ ይህ ጫና ከፈቀድንለትና መላውን ፈልገን መፍትሄ ካልሰጠነው በራሳችን ላይ ያለንን አመለካከት የሚቀርጽና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሊወስድ የሚችል ጠንቅ ነው፡፡

በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ውስጥ የሰዎችን እውነተኛ የማንነት ተመን (Value) በማዛባት የተዛባ ዋጋ (Price) የመለጠፍ ልማድ ይታያል፡፡ ይህ ለሰዎች የሚሰጥ ዋጋ የሕብረተሰቡን ክፍል በእርከን በመከፋፈል መደብ በማበጀት ይታወቃል፡፡ አብዛኛዎቹ መስፈርቶች ከቁሳቁስና ከውጫዊ ገጽታ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ደግሞ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡

ገንዘብና ቁሳቁስ ነክ ሃሳቦችን እዚህ አንዳስስም፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ባላቸውና በሌላቸው ሃብትና ንብረት ራሳቸውን ያልተቀበሉ ቢመስላቸውም ያልተቀበሉት ራሳቸውን ሳይሆን ውጫዊ ሁኔታቸውን ነው፡፡ ከዚህ በታች ራስን በራስ የመግፋት ወይም ራስን ያለመቀበል ሁኔታ ሊከሰትባቸውን የሚችሉትን የተለመዱ ሁኔታዎች ጠቀስ አድርገን እናልፋለን፡፡

መልክና ቁመናን አለመቀበል

በአለማችን ውስጥ ቅጡን ያጣና መስመሩን የሳተ በመልክ፣ በቁመናና በውጪ ገጽታ ላይ ያተኮረ ደረጃ መዳቢነት አለ፡፡ ይህ፣ “ሰው ሁሉ ሙሉ ለመሆን ይህ አይነቱ መልክ፣ ቁመና፣ የቆዳ ቀለም፣ የጸጉር አይነት . . . ሊኖረው ይገባዋል” የሚለው የማያቋርጥ መልእክት ለደረጃ መዳቢዎቹ ታላቅ የሆነ የገቢ ምንጭ ነው፡፡ በተቃራኒው ግን ለተቀረው ለእነዚህ መልእክሮት ራሱን አጋልጦ ለሰወጠው ሕዝብ ደግሞ ገንዘቡንና ስሜቱን የሚያፈስበት የማያልቅ የክስረት ጎዳና ነው፡፡

አንድ ሰው ሕብረተሰቡ በየጊዜው የሚያነሳና የሚጥለውን ተለዋዋጭና ዘመን አመጣሽ የገጽታ ሁኔታ ካልመሰለና ለዚያ ካልመጠነ የዝቅተኝነት ስሜት ሰለባ ወደመሆን እንዲወርድ ተደርጎ በሕብረተሰቡ ጭንቅላት ላይ በሚገባ ተሰርቷል፡፡ ለዚህ ሁኔታ ራሱን ያጋለጠ ሰው ቀስ በቀስ ራሱን ወደመግፋት፣ ወደመጥላትና ወዳለመቀበል ያዘቅጣል፡፡

ዘርን አመቀበል

ዘረኝነት የአለማችን አጥፊ ነቀርሳ ነው፡፡ ዘረኝነት የነጭ፣ የቢጫ፣ የቡናማና የጥቁር ቆዳ ቀለም ልዩነት ችግር ብቻ አይደለም፡፡ በጥቁሮችም መካከል አንዱን ከአንዱ በቆዳ ቀለም በመለየት ይህ ነው የማይባል የዘረኝነት በደል ይፈጸማል፡፡ አስገራሚው ነገር፣ ነጮች ሃገር ሄዶ ጥቁር ስለሆንኩኝ አገለሉኝ የሚለው ሰው በራሱ ሃገር “የእኔ የቆዳ ቀለም ከእርሱ ይሻላል” ብሎ በሚፈርጀው ሰው ላይ መገለልን ሲያደርግ ይታያል፡፡

ችግሩ ያም ሆነ ይህ በአለም ላይ ያለው ሰዎችን በዘራቸውና በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት የምንሰጣቸው ግልጽም ሆነ ስውር ደረጃ ራስን በመቀበል ላይ ይህ ነው የማይበል ጫና ሲያደርግ ማየት የተለመደ ነው፡፡

አንድ ሰው ራሱን በማይቀበልበትና በሚጥልበት ጊዜ የሚታዩበት በርካታ ምልክቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ ምልክቶች መካከል፣ ራስን መጉዳት፣ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ለሚፈልጉን ሰዎች ራስን አጋልጦ መስጠት፣ ትክክለኛ እንክብካቤ ከሚሰጡን ሰዎች ራስን ማግለልና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪ ራሱን በማይቀበል ሰው ላይ ከሚታዩ ምልክቶ መካከል የሚከተሉት ሊጠቀሱ ይገባቸዋል፡፡

• የውስጣችንን ዓላማ፣ ግብና ምኞት ከመከታተል መገታት

• የትም በማይደርስና በማንቀሳቀስ ወዳጅነት ወይም የስራ ዘርፍ ውስጥ ደንዝዞ መቀመጥ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ስለተላመድናቸው ብቻ ምቾት ቢሰጡንም ምንም የእድገት ምንጭ ሊሆኑን ግን አይችሉም፡፡

• በሕይወት የምናገኛቸውን እድሎች ችላ በማለት ማሳለፍ፡፡

• “ፍጹማዊነት” እና በሁሉም ነገር ትክክለኛ ሆኖ የመገኘጥ ጡዘት

• የረጅም ርቀትን እቅድ ይዞ ከመራመድ ይልቅ ለጊዜው ምቾት የማይሰጡ ስሜቶችን ለማሸነፍ የአጭር ጊዜ መፍትሄዎች ላይ ብቻ ማተኮር፡፡
• ሌላውን በመግፋትና በመጣል የበላይ ሆኖ ለመታየት መሞከር

ማንኛውም ጤናማ ማሕበራዊ ጉዞ የሚጀምረው ጤናማ ከሆነ የራስ-በራስ ምልከታ ነው፡፡ አንድ ሰው በራሱ ላይ ያለው አመለካከት ሲዛባ በአካባቢው ላይ ያለው ንጽረተ-ዓለምና በዙሪያው ካሉት የማሕበረሰብ ክፍሎች ጋር ያለው ግንኙነት ይዛባል፡፡ ስለሆነም፣ ሰው በመጀመሪያ መስራት ያለበት በራሱ ላይ ያለው አመለካከት ላይ እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡

“የመገፋት ሕመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮበ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ፡፡
(መጽሐፉን አሁን በጃፋር መጻሕፍት መደብር (ሜክሲኮ አደባባይ) ያገኙታል)
https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

30 Oct, 01:59

ራስን መግፋትና አለመቀበል

Dr. Eyob Mamo

29 Oct, 14:34

ያለፈው እንዳለፈ ሁሉ፣ ይህም ያልፋል!!!

Dr. Eyob Mamo

29 Oct, 02:00

ጀምሮ ለመጨረስ፣ ጨርሶ መጀመር አስፈላጊ ነው

“ተጀምሮ ያልተጠናቀቀን ተግባር እልባት ሳይሰጡ እንደመኖር አድካሚ ነገር የለም - William James

አንድ ጀምረን ያላጠናቀቅነው ተግባር በእኛ ላይ ያለውን አጉል ተጽእኖ ብዙ ጊዜ አናስተውለም፡፡ አንድን ተግባር ጀምረን ሳናጠናቅቀው አንጠልጥለን ስንተወው የምናባክነው ተግባሩን ብቻ አይደለም፡፡

ሁኔታው ሁለት ነገሮችን ይነካል፡-

1. በራሳችን ላይ ያለንን አመለካከት ይነካል፡፡

ያልተጨረሱ ስራዎች በውስጠ ህሊናህ ራስህን እንድትንቅና የማይችልና የማይመጥን ሰው እንደሆንክ እንድታስብ የማድረግ ተጽእኖ አለው፡፡ በተቃራኒው የተጠናቀቁ ስራዎችህ ራስህን እንድታከብርና ቀና ብለህ እንድትሄድ ያግዙሃል፡፡

2. ሰዎች በእኛ ላይ ያላቸውን አመለካከት ይነካል፡፡

ሰዎች አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት የሚመለከቱት ከዚህ በፊት ጀምረህ የጨረስካቸውን ስራዎች ነው፡፡ እዚህም እዚያም ጀምረህ ያልቀጨረስካቸው ስራዎች ባለህ ማሕበራዊ ተቀባይነትህና እርከንህ ላይ ትልቅ ተጽእኖ አለው፡፡

አብዛኛው ጀምሮ ያለመጨረስ ችግር ያለው “በጀትን” በትክክል አለመጠቀም ነው፡፡ በጀት ስንል ስለሁለት ነገሮች ነው የምናወራው፡-

1. የጊዜ በጀት፡- ዋና ዋና ለሆኑትና ሊቀድሙ ለሚገባቸው ስራዎች በቂ የጊዜ በጀትን አለመመደብ ወይም መድቦ በትክክል አለመጠቀም፡፡

2. የጉልበት በጀት፡- ዋና ዋና ለሆኑትና ሊቀድሙ ለሚገባቸው ስራዎች ሊውል የሚገባን አካላዊና ስሜታዊ ጉልበት በቂ በጀትን አለመመደብ ወይም መድቦ በትክክል አለመጠቀም፡፡

አንድን ነገር ጀምረህ ለመጨረስ ከፈለክ ስትጀምረው ገና በሚገባ አስበህበትና በውስጥ በጥሩ እቅድና ዝግጅት ጨርሰኸ መጀመር አስፈላጊ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

Dr. Eyob Mamo

28 Oct, 02:00

“የምገዛው ራሴን ነው”

የታላቂቱ ፕሩሺያ ንጉስ የነበረው ታላቁ ፍሬደሪክ አንድ ጊዜ በበርሊን መንገድ ላይ ሲሄድ ሳለ አንድ በእድሜው እጅግ የሸመገለ ሰው ልክ እንደሱ በመንገድ ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ ይህ እድሜ-ጠገብ ሰው የነበረው አረማመድ የንጉሱን ትኩረት ሳበው፡፡ ይህ ሰው ቀና ብሎ፣ ደረቱን ገልብጦና አይኖቹ በትኩረት እያዩ ግርማ-ሞገስ ያለው ገዢ አይነት አካሄድ እየሄደ ነበር፡፡ ንጉስ ፍሬደሪክ የሰውየውን በራስ መተማመን በመመልከት ለማነጋገር ፈለገ፡፡

ንጉስ ፍሬደሪክ፡- “አንተ ማን ነህ?”

ሽማግሌው፡- “እኔ ንጉስ ነኝ”

ንጉስ ፍሬደሪክ፡- “ግዛትህ ምንድን ነው?

ሽማግሌው፡- “የምገዛው ራሴን ነው”

ይህ ታላቅ ገዢና ንጉስ በዚህ አዛውንት አነጋገር የማይረሳውን ትምህርት አግኝቶ መንገዱን ሄደ፡፡

ለካ፣ የገዢነት ሁሉ ገዢነት ራስን መግዛት ነው!

ለካ፣ የአመራር ሁሉ አመራር ራስን መምራት ነው!

ለካ፣ የኋላ ቀርነት ሁሉ ኋላ ቀርነት ራስን ሳይገዙ ሰውንና ሕብረተሰብን ለመግዛት መሞከር ነው!

ለካ፣ የውድቀት ሁሉ ውድቀት ራስን ሳይመሩ ሌላውን ለመምራት መሞከር ነው!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

27 Oct, 13:10

ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)

1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመወጣት ስላቃታችሁ እገዛ ከፈለጋችሁ፣

2. የሕይወታችሁን ራእይ ወይም ዓላማ ባለማወቅ ከተወዛገባችሁና አቅጣጫን መያዝ ከፈለጋችሁ፣

3. ካለባችሁ አጉል ልማድ በመውጣ አዲስ ልማድን ማዳበር ካስቸገራችሁና ምክርና ድጋፍ ከፈለጋችሁ፣

4. መመለስ ያቃታችሁ የሕይወት ጥያቄዎች ከበዙባችሁና በአንድ ለአንድ ውይይት የመፍትሄ መንገድ ከፈለጋችሁ፣

5. በራሳችሁ መወጣት ያልቻላችሁት የተያዩ የስሜትና የስነ-ልቦና ጥያቄዎች ውስጥ እንዳላችሁ ከተሰማችሁና ከሁኔታው ለመውጣት ምክር ከፈለጋችሁ፣

ከግል በተጨማሪም ቁጥራችሁ ከአስር ባልበለጠ ሁኔታ በመሰባሰብ የGroup Coaching and Training ጥያቄም ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡

በቴሌግራም @DrEyobmamo inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

27 Oct, 04:26

በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጡ!!!

ጸሎት አድርጉ!

ተረጋጉ!

አስቡ!

አቅዱ!

ማድረግ ያለባችሁን ነገር ከማድረገ አታቁሙ!

ተስፋ መቁረጥ የሚባል ነገር አልተፈቀደላችሁም!

መልካም ቀን!!!

Dr. Eyob Mamo

26 Oct, 07:47

ሁለተኛ የምዝገባ እድል

ባለፈው ኃሙስ ምሽት የተጀመረውን የአምስት ሳምንት “በራእይ የሚመራ ሕይወት” የተሰኘ የ Telegram (online) ስልጠና በፊታችን ኃሙስ (ክፍል ሁለት) ጀምሮ ለመቀላቀል ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ይህንን መረጃ ልከናል፡፡

የስልጠናው ክፍያ 1,000 (አንድ ሺ ብር) ሲሆን ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ የከፈሉበትን ደረሰኝ screenshot በማድረግ እዚሁ inbox ያድርጉ፡፡

ይህንን ሲያደርጉ፡-

1. ወደ ስልጠናው የቴሌግራም ቡድን እንቀላቅሎታለን፣

2. ያመለጦትን ያለፈውን ክፍል-አንድ ትምህርትና ውይይት በድምጽ (audio) ቅጂ እንልክሎታለን፡፡

ክፍያ ለመፈጸም ከዚህ በታች ያለውን መንገድ መጠቀም ይችላሉ፡፡

ንግድ ባንክ

Eyob Mamo
Account # 1000614499056

ቴሌብር
Dr. Eyob
ስልክ ቁጥር 0945087238

እናመሰግናን!

Dr. Eyob Mamo

26 Oct, 03:07

ስልጠናው ላመለጣችሁ

ባለፈው ኃሙስ ምሽት የተጀመረውን የአምስት ሳምንት “በራእይ የሚመራ ሕይወት” የተሰኘ የ Telegram (online) ስልጠና መመዝገብና መማር ፈልጋችሁ ያመለጣችሁ በርካታ ሰዎች ከሁለተኛው ኃሙስ ጀምሮ መቀላቀል እንደምትፈልጉ በ inbox በጠየቃችሁት መሰረት አንድ እድል ክፍት እናደርለን፡፡

ከፊታችን ኃሙስ ለመጀመር ከፈለጋችሁ ያለፈውን ክፍል-አንድ ትምህርትና ውይይት በድምጽ (audio) ቅጂ በማዳመጥ ስልጠናውን መቀላቀል ትችላላችሁ፡፡

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

25 Oct, 02:38

የሕብረተሰቡ ክፍተት ሲተነተን
(“ሁለቱ ክህሎቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

የትምህርት ተቋማት መደበኛ በሆነ መልኩ በመቋቋም ተማሪዎችን ማሰልጠን ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ትኩረታቸው ተማሪዎችን በእውቀትና በሞያ ማስታጠቅ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ እነዚህ የትምህርት ተቋሞች ታዋቂነትን የሚያዳብሩት በማሰልጠንና በማስመረቅ ወደ ስራው አለም የሚያሰማሯቸው ተመራቂዎች ባላቸው የሞያ ልህቀት ነው፡፡

ሆኖም፣ ምንም እንኳን በሞያቸው የተዋጣላቸውና የሚሰሩትን የሚያውቁ ተመራቂዎች ቢያፈሩም፣ ተመራቂዎቹ ወደ ስራው ዓለም ሲገቡ በእንዴት መልኩ ከሌላው ሰው ጋር መኖርና ማደር እንሚችሉ አያስተምሯቸውም፡፡ ይህ ሁኔታ በስራው መስክ ውስጥም ሆነ ሕዝብን በመምራት መስኮች ውስጥ እያመጣ ያለውን ክፍተት መገንዘብ የጀመርነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፡፡

አስቡት . . .

የሕክምና ባለሞያው ምን ያህል አዋቂና “ፈዋሽ” ቢሆን፣ ለሕመምተኞች ካለው ርህራሄ ተነስቶ ሕብረተሰቡን ከማገልገል ይልቅ ለክብሩና ለጥቅሙ ካደረ ምን ዋጋ አለው …

የሕግ ባለሞያው ሕግን ጠንቅቆ ቢያውቅ፣ ከፍትህ ይልቅ በጠማማነት የሚገኘውን የግል ጥቅም ካስቀደመ ምን ዋጋ አለው …

መሃንዲሱ በፈጠራ ብቃቱና በቅልጥፍናው በሰው ሁሉ ተፈላጊ ቢሆን፣ ከጥራትና ከደህንነት ይልቅ አስተርፎ የሚያተርፈውን ካሳደደ ምን ዋጋ አለው …

ሂሳብ አዋቂዋ ቁጥርን ከቁጥር በማጋጨትና በማስማማት ብቃቷ ወደር ባይገኝላት፣ በስንፍናዋና በግድ የለሽነቷ የድርጅቱን ስራ በሰዓቱ የማድረስ ፍላጎትና ዲሲፕሊን ከሌላት ምን ዋጋ አለው …

የሕብረተሰቡና የሃገር መሪዎች ምን ያህል ፖለቲካን ቢያውቁ፣ ደጋፊ ቢሰበስቡና በፖለቲካ ሳይንስ ቢራቀቁ፣ እውነተኞች፣ ሕዝብን አስቀዳሚና ሕብረተሰቡን አገልጋይ ለመሆን ራሳቸውን ካላቀረቡ ምን ዋጋ አለው …

በእውቀት፣ በብቃትና በሞያ ላይ ብቻ የምናተኩርበት ጊዜ አልፎ የስነ-ምግባር፣ የተግባቦትና የመልካም ዜግነት ጉዳይ እያሳሰበን የመጣበት ዘመን ነው፡፡ አንዱን ይዘን ሌላኛውን ችላ ስንል የሚያስከትለውን ቀውስም እጅ በእጅ እየተቀበልን ስለሆነ መፍትሄውን ፍለጋ በሚገባ ልናስብበት ይገባል፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

25 Oct, 02:38

የሕብረተሰቡ ክፍተት ሲተነተን

Dr. Eyob Mamo

24 Oct, 13:50

ዛሬ ምሽት ለሚጀምረው ስልጠና ለመመዝገብ ያላችሁ 15 ደቂቃ ብቻ ነው!!!

Dr. Eyob Mamo

24 Oct, 13:01

አንድ ሰዓት ብቻ ቀራችሁ!

ዛሬ ማታ ለሚጀምረው ስልጠና ለመመዝገብ ፈልጋችሁ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገያችሁ ምዝገባው ከሰዓት በኋላ በ11 ሰዓት ስለሚዘጋ ያላችሁ ጊዜ 1 ሰዓት መሆኑን አስታውሱ፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

@DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

24 Oct, 12:01

ሁለት ሰዓት ብቻ ቀራችሁ!

ዛሬ ማታ ለሚጀምረው ስልጠና ለመመዝገብ ፈልጋችሁ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገያችሁ ምዝገባው ከሰዓት በኋላ በ11 ሰዓት ስለሚዘጋ ያላችሁ ጊዜ 2 ሰዓት መሆኑን አስታውሱ፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

@DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

24 Oct, 11:01

ሶስት ሰዓት ብቻ ቀራችሁ!

ዛሬ ማታ ለሚጀምረው ስልጠና ለመመዝገብ ፈልጋችሁ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገያችሁ ምዝገባው ከሰዓት በኋላ በ11 ሰዓት ስለሚዘጋ ያላችሁ ጊዜ 3 ሰዓት መሆኑን አስታውሱ፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

@DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

24 Oct, 07:18

የመጨረሻ እድል!

ዛሬ ማታ ለሚጀምረው ስልጠና ለመመዝገብ ፈልጋችሁ በስራ መጨናነቅ ምክንያት ሳትመዘገቡ ያለፋችሁ በርካታ ሰዎች በኢንቦክስ አንድ እድል እንዲሰጥ በጠየቃችሁት መሰረት ዛሬን ለመመዝገብ እንድትችሉ ክፍት እናደርጋለን፡፡

የምዝገባውን እድል እስከ ዛሬ ከሰዓት 11 ሰዓት ድረስ ክፍት በማድረግ እናስተናግዳችኋለን፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

@DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

24 Oct, 04:24

24 Oct, 02:01

መማርን አታቁሙ!

ሁል ጊዜ ትክክል እንደሆናችሁ የምታስቡ ከሆነ ከሕይወት የምትማሩት አንድም ትምህርት እንደማይኖር አትዘንጉ፡፡ መማር ስታቆሙ ደግሞ ማደግ ታቆማላችሁ፡፡

ለመማር ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች . . .

• ስልጠናን ውሰዱ

• የተግባራችሁ ውጤት የሚነግራችሁን አስተውሉ፣

• ሰዎች የሚነግሯችሁን ነገር አድምጡ፣

• አንብቡ፣

• የሰዎችን የሕይወት ተሞክሮ አጢኑ፣

• በየጊዜው ከተለመደው ስፍራ ዘወር በማለት የማሰላሰያ ጊዜ ይኑራችሁ፡፡

• ከፈጣን ሃሳብ ሰጪነት ቆጠብ በሉ፣

• ክርክርን አታብዙ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

23 Oct, 16:35

ማስታወሻ!

ነገ ማታ በሚጀመረውና ለአምስት ተከታታይ ኃሙስ ምሽቶች በሚሰጠው ስልጠና ላይ ለመሳተፍ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡

ለመመዝገብ አስባችሁ የተዘናጋችሁ ይህ መልእክት ማስታወሻ ይሁናችሁ፡፡

ይህ “በራእይ የሚመራ ሕይወት” የተሰኘው ሳምንታዊ ስልጠና ነገ ኃሙስ በኢትዮጲያ አቆጣጠር ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ልክ በሰዓቱ ይጀምራል፡፡ የሚጠናቀቀውም ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ነው፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

23 Oct, 12:56

ዛሬ ብቻ ቀራችሁ!

“በራእይ የሚመራ ሕይወት” ለተሰኘው የፊታችን ኃሙስ የሚጀምረው የ Online ስልጠና ለመውሰድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፡፡

ለመመዝገብ የቀራችሁ ቀን ዛሬ ብቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

@DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

23 Oct, 09:25

ዛሬ ብቻ ቀራችሁ!

“በራእይ የሚመራ ሕይወት” ለተሰኘው የፊታችን ኃሙስ የሚጀምረው የ Online ስልጠና ለመውሰድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፡፡

ለመመዝገብ የቀራችሁ ቀን ዛሬ ብቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

23 Oct, 08:04

የከፋው ጉዳት!

በሕይወታችሁ ምንም ነገር ከሚያደርስባችሁ የጉዳት መጠን በብዙ እጥፍ የሚጎዳችሁ ነገር ቢኖር ማወቅ የሚገባችሁን ነገር አለማወቅ ነው፡፡

ከአስርት አመታት በፊትና ከዚያ በላይ የኖሩ ሰዎች አሁን እኛ ያወቅነውን እውቀት አውቀው ቢሆን ኖሮ ያን ጊዜ ያጠፋቸው ነገር አያጠፋቸውም ነበር፤ ያን ጊዜ የኖሩትን የኑሮ ደረጃ አይኖረኑም ነበር፡፡ ወደማወቅ የመጣው ነገር አሻሽሎ እዚህ አድርሶናል፡፡

በግል ሕይወታችሁም እንደዚሁ ነው፡፡ የምታውቁትና የማታውቁት ነገር የኑሮ ጥራታችሁን ይወስናል፡፡

ማንኛውንም እውቀት ከማወቃችሁ በፊት ደግሞ ራእያችሁን የማወቃችሁ ጉዳይ ወሳኝ ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የዘጋጀውና ነገ የሚጀመረው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች የተመዘገቡበት ስልጠና፣ ካለማወቅ ወደማወቅ እንደሚያሻግራችሁና የሕይወታችሁን ጥራት እንደሚለውጠው እርግጠኛ ነኝ፡፡

ለመመዝገብ የቀራችሁ ቀን ዛሬ ብቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

23 Oct, 04:06

ዛሬ ብቻ ቀራችሁ!

“በራእይ የሚመራ ሕይወት” ለተሰኘው የፊታችን ኃሙስ የሚጀምረው የ Online ስልጠና ለመውሰድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፡፡

ለመመዝገብ የቀራችሁ ቀን ዛሬ ብቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

23 Oct, 02:00

ከጀግንነት መገለጫዎች አንዱ!

“የምትሞትለት ዓላማ ከሌለህ የምትኖርለት ዓላማ የለህም ማለት ነው” ይሉናል አንዳንድ በነገሩ ያሰቡበት ሰዎች፡፡ ነገ ሕይወትን እስከመክፈል ድረስ ራሳችንን የሰጠንለት ዓላማ፣ ዛሬ ሕይወትን እንድናጣጥማት የማድረግ ጉልበት አለው፡፡

እንደየተሰማራንበት መስክ በርካታ የጀግንነት መገለጫዎች አሉ፡፡ ከሁሉም የጀግንነት መገለጫዎች አንዱና ለሕይወት ይህ ነው የማያባልን ጣእም የሚሰጣት ጀግንነት፣ ምንም ነገራችንን ከመክፈል የማንመለሰልትን ዓላማ መያዝና ለዚያ መኖር፣ ለዚያ ደግሞ መሞት ነው፡፡

ምንም ነገር ቢያስከፍለንም ከእኛ ለበለጠ ራእይና ዓላማ እስከመኖርና “ስንጀግን” ለዚያ ነገር ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን፣ ገንዘባችንን . . . አስፈላጊ ከሆነም ሕይወታችንን እንሰዋለን፡፡

ጊዜያችሁን እስከመሰዋት የምትኖሩለት ነገር ምንድን ነው? ሕወታችሁን እስከመሰዋት ድረስ የምትሩለትስ ነገር ምንድን ነው?

ብዙ ሰዎች በየእለት ኑሯቸው ስልችት የሚላቸውና ባዶነት የሚሰማቸው ከዚህ አይነቱ “ጀግንነት” ውጪ ሕይወትን ለመኖር ስለሚሞክሩ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በኑሯቸው ደስ የሚላቸውና ሙሉነት የሚሰማቸው ይህንን አይነት “ጀግንነት” ስላዳበሩና ጊዜያቸውንም ሆነ ሕይወታቸውን እስከመክፈል ድረስ የሚኖሩለትን ነገር ስላገኙት ነው፡፡

የጀግንነቶች ሁሉ ጀግንነት ምንም ነገር ለመክፈል የተዘጋጀንለትን ዓላማ ማግኘትና እስከሞት ድረስ ለዚያ መኖር!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

22 Oct, 16:41

አንድ ቀን ብቻ ቀራችሁ!

“በራእይ የሚመራ ሕይወት”
ለተሰኘው የፊታችን ኃሙስ የሚጀምረው የ Online ስልጠና ለመውሰድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፡፡

ለመመዝገብ የቀራችሁ 1 ቀን ብቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

@DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡

Dr. Eyob Mamo

22 Oct, 10:44

22 Oct, 05:00

22 Oct, 02:00

ልክ እንደ አዲስ መጀመር ይቻላል!

ሁሉም ነገር አሁንና ዛሬ እንደ አዲስ እንዲጀምር ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ለማድረግ ግን ሶስት ነገሮች አቅጣጫ መብሰልና መስራት የግድ ነው፡፡

የትናትናው፡-

ዛሬ አዲስ የመጀመርን ፍላጎት ያሳደረባችሁ ትናንትና የተበላሹ ሁኔታዎች ተጽእኖ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ስለዚህ ሁሉንም ነገር ዛሬ እንደ አዲስ ለመጀመር የትናንትናውን አሮጌ ነገር አያያዝ በሚገባ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ መለወጥና ማስተካከል የምትችሉት ያንን አድርጉ፣ የማትችሉትን ደግሞ አልፋችሁት ሂዱ!

የዛሬው፡-

ሁሉን ነገር እንደ አዲስ ለመጀመር ዛሬ ላይ ቆራጥ ውሳኔን ይጠይቃችኋል፡፡ የትናንትናውን በሚገባ አያያዙን ካወቃችሁ በኋላ፣ በመቀጠል የዛሬውን ወቅታዊ ጫና ለማሸነፍ ቆራጥ ካልሆናችሁ እንደገና እንደ አዲስ መጀመር ያስቸግራችኋል፡፡ ቆራጥ ሁኑ!

የነገው፡-

ሁሉን ነገር እንደ አዲስ ለመጀመር ስትወስኑ ጉልበት ሊሰጣችሁ የሚችለው ትልቁ ነገር እንደገና በመጀመራችሁ ምክንያት ነገ ልትደርሱበት የምትችሉበትን ደረጃና ልታመጡ የምትችሉትን ለውጥ የማየት ጉዳይ ነው፡፡ የሚያጓጓ የወደፊትን ፍጠሩ! ነገን ተመልከቱ! ለዚያ ደግሞ ስሩ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo

21 Oct, 16:49

ሁለት ቀን ብቻ ቀራችሁ!

“በራእይ የሚመራ ሕይወት”
ለተሰኘው የፊታችን ኃሙስ የሚጀምረው የ Online ስልጠና ለመውሰድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፡፡

ለመመዝገብ የቀራችሁ 2 ቀን ብቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ፡፡

ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ!

@DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ እንልክላችኋለን፡፡