ኢትዮ መረጃ - NEWS @ethio_mereja_news Channel on Telegram

ኢትዮ መረጃ - NEWS

@ethio_mereja_news


ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት

ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@B_promotor

ኢትዮ መረጃ - NEWS (Amharic)

ኢትዮ መረጃ - NEWS ከአዲስ አበባ እና ታሪካዊ አለም አቀፍ ኢትዮጵያን ለመውደድ የሚረታቸውን መረጃዎችን የሚያግዝ ፍቅር አልበምም። በተጨማሪም የዓለም አቀፍ መረጃዎችን ለማቅረብ በተከታታይ ነገር ተካተተ። ታሪክን መከታት። ታሪክን ወደተቃወሞ አስተያየት እና መንገድ እና ሰጥቶአል። ይህን በማድረግ ለመከታት እና ለሰጥቶአል።

ኢትዮ መረጃ - NEWS

23 Nov, 16:16


ባንኩ የብድር ወለድ እና የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ ሊያደረግ ነው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ በሚያደርግበት ወቅት ለደንበኞቹ ቀደም ብሎ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ባንኩ በሚሰጣቸው የብድር፣ የቅርንጫፍ እና የዲጂታል እንዲሁም በዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች ላይ በቅርቡ የብድር ወለድ እና የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

ኢትዮ መረጃ - NEWS

23 Nov, 09:03


መረጃ‼️

በሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መከሰቱ ተሰማ

በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መድረሱን  የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

አደጋው አለልቱ አቅራቢያ ጮሌ ጸበል ጋር የተከሰተ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን በስፍራው ያሉ ነዋሪዎች  ተናግረዋል፡፡

በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን እንዲሁም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ለአሃዱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት መንገዱ ለእረጅም ሰዓት መዘጋቱ የተነገረ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደሆስፒታል የማድረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

23 Nov, 09:02


ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ያለህ እግዚአብሔር ቸርነትህን ይጠብቃል!


ከአለም ርቀው ስለፍቅሩ ሲሉ በየበርሀው እና በየገዳማቱ ባዕታቸውን ቀልሰው ሌት ከቀን ለሚማፀኑልን ሰርክ የሚጸልዩ ስለ ዓለሙ ምልጃ የሚተጉ የሚያነቡ  ገዳማውያን የልጆቻቸውን እጅ ናፍቀው ተጨነቁ ቢባል እግዜሩስ እንዴት ያየናል?!
ስለእኛ ለነፍሳችን በመድከም በመንፈሳዊ ህይወት መምህር የሚሆኑን የክርስቶስ እውነተኛ ሙሽሮች ገዳማውያን፣ ዛሬ ላይ ባለው  ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ ነባራዊ ሁኔታዎች የሚቀመስ እፍኝ ቆሎም ጠፍቶ ረሀብ ጥማቱ በብርቱ እየተፈታተናቸው ለጾም ለጸሎት መቆም ተስኗቸው  ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብን ይዘዋል።


እግዚአብሔርን የምትወዱ እርሱን ለመምሰል የምትተጉ ብጹዓን  ጥቂት በመራራት የቸርነት እጃችሁን ለእነዚህ  ገዳማውያን በመዘርጋት በረከተ እግዚአብሔርን ታገኙ ዘንድ እንጠይቃቹኋለን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
                       

ኢትዮ መረጃ - NEWS

23 Nov, 08:46


በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የተሰጠ ውክልና የለም - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

ለሥራ ዜጎችን እንልካለን በማለት የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጿል።

ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ሚኒስቴሩ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና እንደሌለ ገልጿል።

ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣እንግልትና ከሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

ዜጎች የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ለማግኘት (lmis.gov.et) የተሰኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

23 Nov, 07:59


ህገ-ወጥ እርድ ባካሄደ ድርጅት ላይ የ15 ሺህ ብር ቅጣት እና የማሸግ እርምጃ ተወሰደ

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወሪዳ 7 ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ እንስሳት በማረድ ለህብረተሰቡ ሊያቀርብ የነበረው ድርጅትና ግለሰብ ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት ላይ በደረሰው የህብረተሰቡ ጥቆማ ከታረደው በሬ እና ለእርድ ከተዘጋጁት በሬዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ።

ድርጅቱና ግለሰቦቹ የደንብ ማስከበር አባላት ከፀጥታ ጥምር ግብረ ሀይል ጋር በቦታው የተገኙ የታረደ የአንድ በሬ ስጋ ለቄራዎች ድርጅት እንዲወገድ ያስረከቡ ሲሆን በተጨማሪም ለእርድ ተዘጋጅተው የነበረ 5 በሬዎች ለቄራዎች ድርጅት በማስረከብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን አድርገዋል።

ድርጊቱ ሲፈፅም የነበረ ድርጅት እንዲታሸግ በማድረግ 15 ሺህ ብር የተቀጣ ሲሆን በቦታው የተገኙ በሬ አራጅ ግለሰቦች እያንዳንዳቸው ሦስት ሦስት መቶ ብር ተቀጥተዋል።

ባለስልጣኑ ጥቆማ ለሰጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ምስጋና እያቀረበ በሌሎች አካባቢዎችም ለህብረተሰቡ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ ስጋ በማቅረብ የህብረተሰቡን ጤና ችግር ውስጥ የሚጥሉ ግለሰቦችን መረጃ በመስጠት ማህበራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ መልዕክት ማስተላለፉን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎች ነፃ የስልክ መስመር 9995 መረጃ እንዲያቀብሉት ተቋሙ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

23 Nov, 07:48


መረጃ ‼️

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ የሰራተኞችን ሞራል የሚነካ ተግባር ፈፅመዋል በሚል የቅሬታ ደብዳቤ ደረሳቸዉ

የኢት ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የሰራተኞችን ሞራል የሚነካ ተግባር ፈፅመዋል በሚል በሰራተኛ ማህበር አቤቱታ ቀረበባቸው ፡፡

ማህበሩ ከኩባንያዉ ጋር የተፈራረምኩት የህብረት  ዉል ተጥሶል ብሎል

የሰራተኞች ማህበሩ ደብዳቤ እንደሚለዉ ኢትዬ ቴሌ አመቱን በትርፍ የሚያጠናቅቅ ከሆነ ለሰራተኞቹ ደመወዝ መጨመር ግዴታ ያለበት ቢሆንም ያንን አላደረገም ሲል ቅሬታ አቅርቧል ፡፡

ኢትዬ ቴሌኮም በአመቱ 27 ቢሊዬን ብር ማትረፉን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ መናገራቸዉ የሚታወስ ነዉ ፡፡(አንኳር መረጃ)

⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇⬇️⬇️
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+YDgfSLOXodJkODg0
https://t.me/+YDgfSLOXodJkODg0

ኢትዮ መረጃ - NEWS

23 Nov, 07:14


መንግሥት አሰቃቂ ግድያውን በኦሮሞና አማራ ሕዝቦች መካከል ቁርሾ ለመፍጠር ተጠቅሞበታል - የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ባንድ ወጣት ላይ የተፈጸመውን ግድያ መንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና ፋኖ በአካባቢው ሕዝብ ላይ በጋራ ጥቃት ይፈጽማሉ ለሚል ቅስቀሳ ወደፊት ሊጠቀምበት አቅዶ ነበር ሲልም ወቅሷል።

ሆኖም የግድያው ተንቀሳቃሽ ምስል በድንገት ይፋ መሆኑን ተከትሎ፤ መንግሥት በኦሮሞና አማራ ሕዝቦች መካከል ቁርሾ ለመፍጠር ተጠቅሞበታል በማለት ቡድኑ ከሷል።

ቡድኑ፤ በወጣቱ ላይ ግድያውን የፈጸሙት፣ ባካባቢው በመንግሥት ወኪሎች የሚደገፉ ራሳቸውን ፋኖ ብለው የሚጠሩ ቡድኖች መሆናቸው ደርሼበታለሁ ብሏል።

የመንግሥት አካሄድ በአገሪቱ ሕልውና ላይ ከባድ አደጋ ደቅኗል ያለው ቡድኑ፤ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ በመንግሥት ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድር ጠይቋል ሲል ዋዜማ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

23 Nov, 06:17


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ፖሊስ ከፍላጎታችን ውጭ ደሞዛችን ለመዋጮ ተቆርጧል  በሚል ሥራ የማቆም አድማ ያደረጉ 66 መምህራንን ማሠሩን ቪኦኤ ዘግቧል። መምህራኑ የታሠሩት፣ መንግሥት ያለፍቃዳችን ከደሞዛችን ላይ መዋጮ ቆርጦብናል በማለት እንደኾነ ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች መስማቱን ዘገባው አመልክቷል። የወረዳ አስተዳደር በበኩሉ፣ መምህራንን አስተባብረው በማሳመጽ ተጠርጥረው የታሠሩ መምህራን መኖራቸውን ገልጧል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Nov, 19:31


በአማራ ክልል በተለያዩ መጠለያዎች የተጠለሉ ኤርትራዊያንና ሱዳናዊያን ስደተኞች ደኅንነታቸው አደጋ ላይ መውደቁን መናገራቸውን ኒው ሂውማኒተሪያን ድረገጽ ዘግቧል።

ስደተኞቹ ታጣቂዎች ጥቃት እንደሚፈጽሙባቸውና የግዳጅ ጉልበት እንደሚያሠሯቸው መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ደምቢያ ወረዳ በሚገኘው አለምዋች መጠያ የተጠለሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች፣ የታጠቁ ኃይሎች አካላዊ ጥቃትና ዘረፋ እንደሚፈጽሙባቸው፣ አፍነው እንደሚወስዷቸውና ባንድ ዓመት ውስጥ ዘጠኝ ስደተኞች በጥይት ተመትተው እንደሞቱ ዘገባው ጠቅሷል።

በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ሰባት ሕጻናትን ጨምሮ 12 ስደተኞች ታግተው፣ ለማስለቀቂያ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደተጠየቀባቸው የመጠለያው አመራሮች ተናግረዋል ተብሏል።

@Sheger_press
@Sheger_press

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Nov, 18:09


"ዛሬ ከጠዋቱ 1 ሰአት ላይ በመቐለ ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት አንድ ተማሪ መምህሩን አምስት ቦታዎች ላይ በስለት ወግቷል።"

"ደረቱ ላይ ሁለት ጊዜ፣ ሆዱ፣ ጀርባውና ጎኑን ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ ወግቶታል። ይህ ክስተት የተፈጠረው በትምህርት ቤቱ በር ላይ ነው።"

"መምህሩ ረጅም ቀዶ ጥገና ተደርጎለት ህይወቱ ለማትረፍ ተችሏል ነገር ግን በከባድ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል።"

"ብዙ ተማሪዎች ቢላ ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ እየሰማን እንገኛለን እንደ ማህበረሰብ አንድ ነገር ልናደርግ ይገባል"

ዶ/ር ፋሲካ አምደስላሴ የዓይደር ኮምፐርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባልደረባ

#ዳጉ_ጆርናል

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Nov, 17:45


ጥቆማ‼️

“RELIEF የተባለ መድኃኒት እንዳትጠቀሙ” የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በሕገወጥ መንገድ ለገበያ ቀርቧል ያለውን “RELIEF የተባለ መድኃኒት ህብረተሰቡ ከመጠቀም እንዲቆጠብ” ሲል አሳሰበ።

መድሃኒቱ በህገወጥ መንገድ ገብቶ “በኢትዮጵያ ገበያ እየተዘዋወሩ መሆኑን ደርሸበታለሁ” ያለው ባለስልጣኑ “በመስሪያ ቤታችን ያልተመዘገበ በመሆኑ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ አይታወቅም” ሲል አስጠንቅቋል።

የዚህ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች በሚል በባለስልጣኑ ከተዘረዘሩት መካከል “የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ድካም፤ የእይታ መዛባት፤ መፍዘዝ፣ ራስ ምታት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመር” የሚሉት ይገኝበታል።

መድሃኒቱ ለረጅም ጊዜ መጠቀም “ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ” ብሏል።

ባለስልጣኑ በሕገወጥ መንገድ የገባ ነው ሲል የገለጸው “RELIEF” የተባለው መድኃኒት “በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው ይገመታል” ሲል አስጠንቅቋል።

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Nov, 17:44


“በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለሁለት ተሰነጠቀ”

ታላቁ ጻድቅ አባት አባ ሣሉሲ ዜና ሕይወታቸው እጅግ ከሚያስገርሙ ገዳማውያን አንዱ ናቸው። መጽሐፈ ስንክሳር እንደሚገልጸው የዘመነ ከዋክብት ፍሬ ከሚባሉት ጻድቃን አንዱ ሲሆኑ በነበሩበት ገዳም የሚታወቁት ግን 'የማይጾመው፣ የማይጸልየው፣ ሥራ ፈቱ መነኩሴ' በሚል ነበር።


ገዳሙ ውስጥ ከሚኖሩ መነኮሳት መካከል አንድም ቀን ቢሆን አባ ሣሉሲ ሲጸልዩና ሲሰግዱ ያያቸው የለም። ሁሌ ብቻ እንደ ሞኝ ቁጭ ብለው ያኝካሉ። በዚህ ምክንያትም ሥጋ ወደሙን ወስደው አያውቁም።

አንድ ቀን ግን በገዳሙ በዓል ላይ አበምኔቱና መነኮሳቱ መከሩ። "አባ ሣሉሲን አሥረን አውለን ቢያንስ ለቁርባን እናብቃቸው።" ሲሉ ወሰኑ። በውሳኔው መሠረትም በጧት ሒደው ጻድቁን አሠሯቸው።

አባ ሣሉሲም "ፍቱኝ ቁርሴን ልብላበት?" ሲሉ ተቆጡ። መነኮሳቱ ግን "ሳትቆርብ አንለቅህም።" አሏቸው። በዚህ ጊዜ ጻድቁ ቆባቸውን አውልቀው "እመቤቴ የሰው ልጅስ ጨካኝ ነው። አንቺ ግን ርኅርኅት ነሽ።" ብለው በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለሁለት ተሰነጠቀ።


እርሳቸውም ሁለት ክንፍ አውጥተው በረው ተሰወሩ። ባዩት ነገር የደነገጡ መነኮሳት እያለቀሱ ሦስት መቶ ጊዜ "እግዚኦ....." አሉ። በዚህ ጊዜ የጻድቁን ቆብ አገኙ። በዚህች ቆብም አጋንንትን አሳደዱ ተአምራትንም ሠሩ።

አባ ሣሉሲ ግን ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ በተመስጦ በልባቸው ስለሚጸልዩና ይህ ቅድስናቸው እንዳይታወቅ ነበር የሚጥሩት፡፡ በጧት ተነስተው የሚያኝኩትም ደረቅ ሣር እንጂ ምግብ አልነበረም። ከውዳሴ ከንቱ መራቅ ማለት ይሔው ነው።


ስንቶቻችን ጥቂቷን በጎነታችን ሰው ሁሉ እንዲያውቅልን ስንጥር ገዳማውያን አባቶቻችን ግን ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ግርማ ሌሊቱን ጸብአ አራዊቱን ታግሰው ሀገርንና ሕዝብን ሌት ተቀን በጸሎት ሊያስምሩ እየተጉ መንፈሳዊ ጸጋና ክብር ሲያገኙ ትሕትናቸው ይበልጥ ከፍ ይላል፡፡

የጸሎታቸው ረድኤት አብሮን እንዲሆን ገዳማትን ማገዝ ደግሞ የእኛ ድርሻ ነው፡፡ የገዳማውያኑን በረከትና ጸሎት አይለየን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም
                        ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                        1000442598391

                        አቢሲኒያ ባንክ
                        141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Nov, 11:26


BreakingNews‼️

መንግሥት ሁለት ታዋቂ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን አገደ

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን ዋዜማ አረጋግጣለች። ከታገዱት ድርጅቶች መካከልም “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል” (በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃሉ “CARD” እና “ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” (AHRE) ይገኙበታል።
ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አስታውቋቸዋል።

ዋዜማ የተመለከተችው ደብዳቤ ለእገዳው የሰጠው ምክንያት “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ማረጋገጥ ተችሏል” የሚል ነው። ዋዜማ የደረሳት መረጃ የታገዱት ድርጅቶች ቁጥር ከሁለት እንደሚበልጥ ቢጠቁምም፣ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻልንም።

ይህ እርምጃ መንግሥት በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በሚሠሩ ድርጅቶች ላይ ሲያደረግ የቆየው ጫና የመጨረሻ ከፍታ ነው ሲሉ ስለጉዳዩ በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። የእግድ እርምጃው በድርጅቶቹ መሪዎች አካባቢ የተጠበቀ እንዳልነበር ለመረዳት ችለናል።

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን መያዶችን የማገድ ስልጣን ቢኖረውም “የአሁኑ እርምጃ በሕጉ የተዘረዘረውን ቅደም ተከተልና ቅድመ ሁኔታ የሚጥስ ነው” ብለዋል ሌላ የሕግ ባለሞያ። ድርጅቶቹ እግዱን በሕግ የመቃወም መብት ይኖራቸዋል።

ለባለሥልጣኑ ቅርብ የሆኑ የዋዜማ ምንጮች እገዳው የተላለፈበት ሂደት ለእርሱም ግልጽ እንዳልሆነ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ድርጅቶቹን እና ባለሥልጣኑን ለማነጋገር እየሞከርን ነው።

[ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Nov, 11:05


20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ  መንገድ  ላይ ይፀዳዳል ተባለ‼️

በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊዮን በላይ ህዝብ  ጥራቱን ከጠበቀ ሽንት ቤት ዉጭ መንገድ ላይ   ይፀዳዳል ተብሏል ፡፡

በጤና ሚኒስቴር አካባቢ ጤና ፕሮግራም ዴስክ ሃላፊ አቶ አለሙ ቀጀላ በአለም ጤና ድርጅት እና በዩኒሴፍ በ2022 በተደረገ ጥናት መሠረት 17 ፐርሰንት የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከመፀዳጃ ቤት ዉጭ መንገድ ላይ ይፀዳዳል ብለዋል ፡፡

በዚህም ህዝቡ ለኮሌራ እና መሰል  በሽታዎች  ተጋላጭነቱ እንደጨመረ ተነግረዋል ።

ጤና ሚኒስቴር የተለያዩ ስትራቴጅዎችን ቀርጾ ህዝቡ መሰረታዊ መፀዳጃ ቤት እንዲጠቀም እየሰራ መሆኑ አቶ አለሙ ቀጀላ ገልፀዋል ፡፡

@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Nov, 10:51


ለ 614 ጫኝ እና አውራጆች ፍቃድ ተሰቷል።

በከተማዋ 614 የጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት ህጋዊ ፍቃድ አግኝተዋል ተባለ።

በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ የምሬት ምንጭ ሆኖ የቀጠለዉ የጫኝ እና አዉራጅ አደረጃጀት ህጋዊ አካሄድ እንዲኖረዉ እየተደረገ ነዉ ተብሏል።

ከአንድ አመት ወዲህ የጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት መመሪያ ህግ እንዲወጣ መደረጉ ተነግሯል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ የከተማዋ መታወቂያ አላቸዉ የተባሉ 7228 ወጣቶችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ሰምተናል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እየመራዉ ነዉ በተባለዉ መመሪያ በእያንዳንዱ እቃዎች የመጫን እና የማዉረድ ሂደት  ላይ የገበያ ጥናት የተደረገበት የዋጋ ተመን ማዉጣቱን የቢሮዉ ምክትል ሀላፊው አቶ ሚደቅሳ ተናግረዋል።

ሆኖም በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ተነሺዎችን ተከትሎ የሚጠየቁ የጫኝ እና አዉራጅ የዋጋ ተመን ክፍያዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ ተነስቶበታል።

ቢሮዉ በዚህ ዙሪያ ያሉ የቁጥጥር ክፍተቶችን ለማስተካከል ምን እየሰራ ነዉ ብለን ላነሳንላቸዉ ጥያቄ " ህጋዊ ማህበራቱ ለባለንብረቶች ንብረት ሀላፊነት እንዲወስዱ በማስገደድ  እንዲሁም የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ክትትል እያደረኩ ነዉ" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በከተማዋ አራብሳ እና ከከተማዋ መውጫ ላይ የሚገኙ ሰፈሮች ህገወጥ  የጫኝ እና አዉራጅ አደረጃጀቶች በስፋት መታየታቸዉ ሰምተናል።

ይህንን ተከትሎ ማህበረሰብ ለአገልግሎቱ ህጋዊ ደረሰኝ እንዲጠይቅ ያስፈልጋል ተብሏል።

ሆኖም ህብረተሰቡ ንብረቱን ከጫኝ እና አዉራጅ አካላት ዉጪ በራሱ አቅም የማዉረድም ሆነ የመጫኝ ሙሉ ፍቃዱ ተሰቶታል።

ማህበረሰብ ይህን ያልተከተሉ ማህበራት በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊሲ ኮምሽን ነፃ የስልክ መስመሮችን በመጠቀም ጥቆማዎችን መስጠት የሚችሉ መሆኑን ቢሮዉ አሳዉቋል።

(ethio fm)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Nov, 10:51


የቻናል ማስታወቂያ ‼️

ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0