Awde Sibket @awdesibket Channel on Telegram

Awde Sibket

@awdesibket


Speak, don't be silent.

ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ ❣️!

Awde Sibket (Amharic)

እኛ ለድምፅ ይወዳል። አሽናንት አስቀድሞ አቶ አበራን ሆነን የአደራ ስእሊ ማህበረሰብ ነኝ። 'ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ' በሚለው መስመርያ ለፍጥረት የሚገኝ በታላቁ ደንብ እያቀረ ነው። እዚህ አስቀድሞ የሚጠቀሙበትን መግለጫዎችን በወንድም ቤት አካሄዷል። አምስታዊና ዜና አጋሜን በአንድ የድምፅ ሬዲዮ ከፍተዋል። የህመም ቃል እና ዜናዎችን እያቀረ እና ዜናዎችን ከፍተዋል። ለሀገሬዎቹ በምንለዋወጥ ተጠናቋልዋል። 'ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ' የሚለው ስእሊን አፍተማሊ በሚል ስእሊን ለመከተል አካሄደው።

Awde Sibket

11 Sep, 21:47


ይህ Passion Planner ለ 2017 ለእቅዶቻችን ይጠቅመናል ፤ Print አድርገን እንጠቀምበት ፤ መልካም አዲስ ዓመት !

Awde Sibket

08 Sep, 13:48


🎉የወንድም ዳኒ ቁጥር.08 አልበም እንዴት አያችሁት 🎉

Awde Sibket

08 Sep, 13:39


አንተ አንተ ነህ

“መንፈስን ሁሉ አትመኑ” ተብለናል ። አንድ መንፈስ የምናምንህ አንተ ነህ ። ጊዜ አይገድብህም ፣ መነሻ የለህምና ። ስፍራ አይወስንህም ፤ ሰማያት ባንተ ውስጥ ናቸውና ። ከስፋትህ የሰፋ ፣ ተርፎ የወጣ ማንም የለም ። ብርሃን ፣ ነፋስና ሙቀት ሁሉም ዓለምን ቢሞሉም አይገፋፉም ። ፍጹማን የሦስትነት አካላትህም ዓለምን ሞልተዋል ፣ መገፋፋት የለባቸውም ።

አንተ አንተ ነህ ። ዕጣ አውጥተው ልብስህን የተካፈሉህ ፣ ዕጣ ሳታወጣ ግን ሁሉንም የወደድካቸው አንተ እንደ ራስህ ነህ ። የተደረገለት ያመሰግንሃል ። ትኩስ እንጀራ ከቆረስክላቸው የድሀ ልጆች ወገን ላንተ ምስጋና ይገባሃል ። ባለማወቅ ለጠፋው ዓለም ብርሃን ይሆኑ ዘንድ ሰባክያንን የላክህ እንዴት ድንቅ ነህ ! አንተ አንተ ነህ ፤ ለሚገድሉህም ምሕረት ትሰጣለህ ። ሞት አይለውጥህምና ሞትን ትቋቋማለህ ። እጆቻችን ሲያጥሩ እጅህ በሚያፈስሰው በረከት እንጠግባለን ።

ዲ.አ.መ

Awde Sibket

21 Jul, 14:59


ወዴት ነህ ?

ወዴት ነህ ? ብለህ አዳምን የፈለግህ ፣ ያለበትን እያወቅህ ያለበትን ያሳወቅህ ፣ በቃል ብቻ ሳይሆን በለቢሰ ሥጋ ወዴት ነህ ? ብለህ የፈለግህ ፣ ከገነት ጫካ እስከ ቀራንዮ የጠፋውን ያሰስህ እኛም በተራችን እንጠይቅህ ወዴት ነህ ?

ለመቆምም ለመሄድም ስንፈራ ፣ ለመግጠምም ለመለያየትም ስንሰጋ ፣ ለመጀመርም ለመጨረስም ስንንቀጠቀጥ ፣ መንፈስህ የራቀን ይመስለናል ። እባክህ ወዴት ነህ ? ገጻችን ሲጠቁር ፣ የልጅ አዋቂው ፊት ትካዜ ሲይዘው ፣ የመኖር መላ ጠፍቶ ሞት እንደ መፍትሔ ሲፈለግ ፣ ድሀ ያለችውን ሲነጠቅ ፣ የፈሩት እየደረሰ ፣ የጠሉት ሲወርስ ምነው አንድዬ ጨከነብን ይሉሃል ። እባክህ ራስህን ግለጥ ፤ ወዴት ነህ ? ሳትለየን የተለየኸን ፣ አጠገባችን እያለህ የራቅኸን መስሎ ሲሰማን ወዴት ነህ ? ብለን በተራችን እንጠይቅሃለን ።

መልሱ ጥያቄ ከሆነብን ጥያቄው ምን ሊመስል ነው ? ሽማግሌው በሰላም ማረፍ ፣ ሬሳው አፈር መልበስ ፣ የወጣው መግባት ፣ የተማረው ማምረት ፣ የሠራው ማግኘት ሲሳነው ወዴት ነህ? እንልሃለን ፣ ለመብላት ይከፍለው የሌለው በሰው እጅ ታግቶ ለመኖር ሲከፍል ፣ ፈጥሮ ላልፈጠረ ተወን እንዳትባል እባክህ ወዴት ነህ ? ዓለም ሰላም ሆኖ እኛ ብቻ የታወክን መስሎ ይሰማናልና እባክህ እንፈልግህ ወዴት ነህ ?

የክፋት አማካሪዎች ምድሩን ሞልተውታል ። ገላጋይ ጠፍቶ ቤተሰብ ያልቃል ። አሸናፊ በሌለበት ወንድማማች ይቀላላል ። ከሚደነቅ ወደሚያደቅ ምዕራፍ ስንሸጋገር ፣ ቀኛችን ግራ ሁኖ ግራ ሲያጋባን ወዴት ነህ ? እንልሃለን ። የጠፋውን አዳም ፈልገህ ያገኘኸው ፣ የጠፋብንን እውነት ፈልገን እስክናገኘው እርዳን ። እየጸለይን ካለመሰማት ፣ ስምህን እየጠራን ከመለያየት እባክህ አድነን ። አሁንም በቀረችው ትንሽዋ አቅማችን ወዴት ነህ ? እንልሃለን ። ስለ ድሆች እንባ አለሁ በለን ።

ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም.
ከዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

Awde Sibket

16 Jun, 07:47


#የዕለት_መናችን_01

Awde Sibket

12 May, 16:34


እጅግ ትጠቀሙበታላችሁ ፤ መንፈሳዊው ሰው ፤ 
ጽሑፍ ፦ በሉዊስ ስፔሪ ሼፈር ፤ 
ትርጕም ፦ ዘላለም መንግሥቱ

Awde Sibket

12 May, 12:58


1. ከእግዚአብሔር የሚያስኮበልል ነገር
2. ኃጢአተኛና የማያምን ልብ
3. በኃጢአት መታለል ደግሞም ፥ ልብ መደንደን

በእያንዳንዱ "ዛሬ" በእግዚአብሔር ጸጋ እራሳችንን እንጠብቅ!

🙌 እንጸልይ . . . . . እንጸልይ 🙌

Awde Sibket

03 May, 12:42


እሰይ ኢየሱስ በመስቀሉ ስራ አዳነን

Awde Sibket

07 Apr, 07:09


“እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ አበረታሃለሁ ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ” (ኢሳይያስ 41፡10)።

ለአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ይህ ክፍል አዕምሮአችን ውስጥ የሚስተጋባው ድምጽ ሊሆን ይገባል።

ይሄን ክፍል ጠቃሚ ከሚያደርጉት ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው ስለ እግዚአብሔር በሦስተኛ መደብ (እርሱ ያበረታሀል ይረዳሃል…) ሳይሆን በአንደኛ መደብ (አበረታሃለሁ ፣ እረዳሃለሁ… ብሎ) ስለሚናገር ነው። ሁልጊዜ ስለው ለእራሴ በቀጥታ ሲናገረኝ ይሰማኛል። ወገኖቼ ይህ በሚደንቅ ሁኔታ ኃይል አለው። ከአጠገቤ ሆኖ “ሂድ፤ የምታደርገውን አድርግ እኔ እረዳሀለሁ። አቅምን እሰጥሃለሁ። እደግፍሃለሁ።” እንደሚል አይነት ይሰማኛል።

ሌላ ጠቃሚ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ ሁሉንም ሊያጠቃልል መቻሉ ነው። “እረዳሃለሁ” ለማንኛውም ሁኔታ ሊሆን ይችላል። ሁልጊዜ ደግሞ እርዳታ ያስፈልገኛል። ስለዚህ ይህ ተስፋ ሁልጊዜ ለሁኔታዎቻችን ሁሉ የሚመጥን ነው፤ ላያስፈልገን የሚችልበት ሁኔታ የለም።

ሌላኛው ጠቃሚ ምክንያት ደግሞ በእግዚአብሔር የጽድቅ ባህሪው ክፍሉን ስለሚዘጋው ነው። የእግዚአብሔር ጽድቅ ክብሩን ለማምጣት የሚያደርገው ጠንካራ መሰጠት ነው። ከዛ መንገድ ተዛንፎ አያውቅም። ስለዚህ የስሙ ክብር አደጋ ላይ ባለበት በሚመስል ቦታ ሁሉ በቅንዓት እንደሚገለጥ እርግጥ ነው። ለእምነታችንም ዋስትናው ይህ ነው።

በመጨረሻም ይህ ክፍል ጠቃሚ የሚሆነው ምንም እንኳን ለአይሁዶች የታቀደ ቢሆንም ለእኔ ለአሕዛቡም ስለሚሰራ ነው። ይህም የሚሆንበት ምክንያት እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በ መሲሁ ኢየሱስ ነውና (2 ቆሮንቶስ 1፡20)። ይህም ማለት በወንጌል ምክንያት የእኔ ነው። በእርሱ ለሆኑት ሁሉ ይህ ተስፋ እውነት እንዲሆን ክርስቶስ ሞቷል። በማመኔ ምክንያት በእርሱ ነኝ። ስለዚህ ይህንን ተስፋ ጨምሮ ሌሎች ሁሉም ተስፋዎች የእኔ ናቸው። ለሞተው ደግሞም ለተነሳው ልጁ ታማኝ እንደነበረ ለዚህም ተስፋ የታመነ ይሆናል። የዚህን ያህል እርግጥ ነው።

የእኛ እግዚአብሔር፤ ባለፈ ቀን ረዳታችን

ለመጪው ዘመን ተስፋችን

ከኃይለኛው ወጀብ መጠለያ

የዘላለም ቤታችን ማረፊያ

Awde Sibket

18 Mar, 09:52


➢ አንብቧት