Ministry of Mines- Ethiopia @momethi Channel on Telegram

Ministry of Mines- Ethiopia

@momethi

ይህ የማዕድን ሚኒስቴር ትክክለኛ የTelegram Channel ነው።

Exploring the Riches of Ethiopia with the Ministry of Mines (Amharic)

ኢትዮጵያን በማዕድን ሚኒስቴር ተከታታይ እና በመስራት ከተማ ታሪኩን ይከታተሉ እንደሆነ ይህ የማዕድን ሚኒስቴር ትክክለኛ የTelegram Channel በሚባለው ሁኔታ በአማርኛ ለማክበር ይረዳናል። "momethi" የተለያዩ መረጃዎችን ለመረዳት እና የሚያግዝባቸውን ተጠቃሚ አገልግሎቶችን በትክክለኛ እና በደረሰው አገልግሎት ያዳምጡ። ከአንድ ሚኒስትሩ ላይ መመልከት ይጀምራል እና ከሌሎች ሚኒስቴሮች ጋር እናረጋጋለን። ለተከሰተ መረጃዎች እና መብቶች ለመመልከት "momethi" የTelegram Channel ሰልፍ እና ለመረዳት እንጠቀማለን። በየቀኑ ከተለያዩ መነሻ እና መረጃዎች እንቀመጣለን። እባኮትን ይህ ከፋይል የተጠቃሚ ምንጭ የስራ ልምድ የሚያደርገውን ሰዎች እና ጥንቃቄ ሊቀጥለን ይችላሉ። በተጨማሪም ስለ "momethi" የTelegram Channel እና ሌሎች ሚኒስቴሮች ላይ መመልከትና መረጃ ለማረጋጋት እንስከል በተጠቃሚ ፕሮፌሰንሽንሽንሽንሽንት ላይ ጠይቁን። ከዚህ በታች ለእኛ በተጠቃሚ እና በደረሰው ስለ ጥንቃቄ ለመመልከት እና ለሌላው ሚኒስቴር ትክክለኛ ማህበረሰብን ያገናኙ።

Ministry of Mines- Ethiopia

29 Jan, 11:21

ET Mineral coal washing process

Ministry of Mines- Ethiopia

25 Jan, 20:25

ለማዕድን ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተደብቀው የነበሩ የተፈጥሮ ፀጋዎች ለህዝብ ጥቅም መዋል ጀምረዋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)                              
(ጥር 17/2017 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር)፡- ለማዕድን ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተደብቀው የነበሩ የተፈጥሮ ፀጋዎች ለህዝብ ጥቅም መዋል መጀመራቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አክሲዮን ማህበር የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን ትናንት መርቀው ስራ ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡                
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እምቅ የማዕድን ጸጋ የሚገኝበት መሆኑንም ተናግረዋል።
እንደ ሀገር ለማዕድን ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተደብቀው የቆዩ የከበሩ የማዕድን ጸጋዎች ለህዝብ ጥቅም መዋል መጀመራቸውንም ገልጸዋል።      ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email:  [email protected]

Ministry of Mines- Ethiopia

24 Jan, 17:18

Et mineral inauguration

Ministry of Mines- Ethiopia

24 Jan, 12:41

ፋብሪካው የድንጋይ ከሰል ምርት የሚያሻሻልና ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
(ጥር 16/2017 ዓ.ም) የኢቲ ማዕድን ልማት አክሲዮን ማህበር የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ተመረቀ፡፡ ፋብሪካው የድንጋይ ከሰል ምርትን የሚያሻሻል እና የአካባቢውን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር ዐቢይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን ፋብሪካ ዛሬ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ ዕድል ፈጥሯል።
ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]

Ministry of Mines- Ethiopia

21 Jan, 11:17

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈረመ፡፡
(ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር) የማዕድን ሚኒስቴር እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ በማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) እና ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የተፈረመ ሲሆን የስራ ውሉ በማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሃኒባል ለማ ተፈርሟል፡፡
ስምምነቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ትግበራ፣ በአቅም ግንባታ፣ በእውቀት ሽግግርና መጋራት፣ የዲጂታል መሰረተ ልማትን ለመጠበቅና የተሳለጠ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ለመዘርጋት ያለመ ነው፡፡
ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]

Ministry of Mines- Ethiopia

14 Jan, 06:30

የደረጃ I የጂኦተርማል ሀብት

ደረጃ አንድ ጂኦተርማል የሀብት ማለት የክምችቱ የሙቀት መጠን ከ1200C በላይ ሲሆን እና የኤሌክትሪክ ኃይልን ለማመንጨት የሚያስችል ሙቀት (Temperature)፣ ግፊት (Pressure) እና ዝውውር (Permeability) ሲኖረው ነው፡፡ ጂኦተርማል ከሌሎች የኃይል ምንጮች አንጻር ሲታይ ጥቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ በሀገራችን በስፋት ጥቅም ላይ ከሚውለው ሃይድሮ ፓወር አንጻር ሲወዳደር ጂኦተርማል ወቅትን እየጠበቀ የማይቆራረጥ መሆኑ እንዲሁም አካባቢ ላይ የሚያደርሰው ጉዳትም በጣም አነስተኛ መሆኑ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ጂኦተርማል ሀብትን ጥቅም ላይ ለማዋል የመነሻ ካፒታሉ ከፍተኛ ቢሆንም ስራው አንዴ ከተጠናቀቀ እና ወደ ምርት ከተገባ የሚያስገኘው ጥቅም ከፍተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም የጂኦተርማል ሃብት አጠቃቀም ሂደት በአግባቡ መቆጣጠር ከተቻለ ሀብቱን በድጋሚ የመጠቀም ሂደት (Re-injecting and use) ዘዴን ስለሚጠቀም ለብክነትም ሆነ አሟጦ በመጠቀም ከሚመጣ ክስረት የፀዳ በመሆኑ ታዳሽ ኢነርጂ ይባላል፡፡
ማህበራዊ ሚዲያዎቻችን በመከተል ተጨማሪ መረጃዎችን ያግኙ
ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]

Ministry of Mines- Ethiopia

13 Jan, 07:59

የጂኦተርማል ሃብት
የሰው ልጅ ተፈጥሮ ከለገሰችው ታዳሽ ኃይል መካከል ጥቂቱን ብቻ እንደተጠቀመበት ይታወቃል፡፡ ለዚህም የተለያዩ ነጥቦች እንደምክንያት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ለዛሬ ግን ከጥቅሙ አንጻር ብዙም ስላልተባለለት የጂኦተርማ ሀብት ጥቂት እንበል፡፡ የጂኦተርማል ኢነርጂ ማለት ምድር አምቃ ከያዘችው ሙቀት የሚመነጭ ሃይል ማለት ነው፡፡ በአለማችን ሙሉ ለሙሉ ባይባል እንኳን ጥቂት የማይባሉ ሃገራት በጂኦተርማል ሃብት የታደሉ ናቸው፡፡ ታዲያ ይህንን ሀብት በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል፡፡ ይህም የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት እንዲሁም ሀብቱን በቀጥታ መጠቀም ነው፡፡ ኢትዮጵያ የጂኦተርማል ሀብትን ለማልማት በተቀመጠው አዋጅ መሠረት የጂኦተርማል ሀብትን በሁለት ይከፈላል፡፡ የደረጃ I የጂኦተርማል ሀብት እና የደረጃ II የጂኦተርማ ሀብት በመባል፡፡ በቀጣይ ክፍል ይቀጥላል…
ማህበራዊ ሚዲያዎቻችን በመከተል ተጨማሪ መረጃዎችን ያግኙ
ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]

Ministry of Mines- Ethiopia

08 Jan, 06:43

የማዕድን ናሙና
የማዕድን ናሙና ማለት ለንግድ ባልሆነ መጠን ከተፈጥሮ ስራው የተወሰደ ለጥናትና ምርምር፣ ለላቦራቶሪ ምርመራ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ፕሮሰስ ተደርጎ ለገበያ ለማስተዋወቅ ወይም አግባብ ላለው ሌላ ዓላማ የተዘጋጀ ማዕድን ማለት ነው፡፡
ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email:- [email protected]

Ministry of Mines- Ethiopia

06 Jan, 17:56

02 Jan, 06:48

“የማዕድን ላኪነት” ማለት ወርቅና ብር ሲሆን የመጨረሻ ቅርፃቸዉን የያዙ ፣ሌሎች ማዕድናት ሲሆን በጥሬ ወይም በከፊል የተሰናዳዉን ከአምራች፣ዕደጥበብ ወይም ከአቅራቢነት ባለፍቃድ በመግዛት ወደ ዉጭ ሀገር የመላክ ስራ ነዉ፡፡
“ማሰናዳት” ማለት ማዕድናት የመጨረሻ ቅርፃቸዉን እንዲይዙ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ማጠብ፣ማቅለጥ፣ማንጠር፣መፍጨት፣መቁረጥ፣ቅርፅ ማዉጣት፣ማስዋብ እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን ማከናወን ነዉ፡፡
ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email:- [email protected]

Ministry of Mines- Ethiopia

31 Dec, 14:13

ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]

Ministry of Mines- Ethiopia

30 Dec, 08:58

በትናንትናው ዕለት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት የተመረቀው ዕድሳት የተደረገለት ብሔራዊ ቤተ መንግሥት - በምስል ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]

1,120

subscribers

696

photos

15

videos