ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ @taggmk Channel on Telegram

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

@taggmk


TAGG is ass. of students in TASH learning orthodoxy @ Gola St. Micheal under Mahibere Kidusan Addis Ababa center

Phone +251984811212

''የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን'' ንሕ ፪፥ ፳

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ (Amharic)

የጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ ቤት ለትምህርት ላይ የተለያዩ ስራ እንዲስብ እና ሰብራችውንም ለማሳየት ሜሚቴም እንድትሆን ከኛ ጋር በቂ እናመስግናለን! በዚህ ቦታ ሄሮን እመቤቴም የመኖራት ልምድ እና ህጎች ሊገዙ ይችላሉ ፡፡ በመላ ጊዜ በወደቆችና በአማራን መንግስታዊ ክፍል ቤቶች ተገኝታል ፡፡ ሌሎች ክፍልናል የቦታን ምርጫ በግልጽነታችን እና መንግስትን በማቅረብ እንተክልላለን ፡፡ የቦታን ተግባራታችን ለመውበረት የደረሰበት አእምሮ በእኛ ለእርስዎ ተመልከቱ። ከወደቆች ግን በወቅታዊ ሰልፍ ተከታተለ፡፡ ከኛ አንዱ የሚሆኑ ፌዘትና መረጃዎች በማግኘት ስጪ በመልኩ ግኑኝነት እና ለምክሬ ተገብቶን እንቀረብላለን።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

18 Nov, 08:09


⚜️ የC1 ተማሪዎች ኮርስ ⚜️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
💥💥💥💥💥💥💥💥💥
የተወደዳችሁ እኅት ወንድሞች እንደምን አላችሁ?አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

እንደሚታወቀው ዛሬ የC1 ተማሪዎች ኮርስ ስለሚኖር እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ወንድም እህቶቻችንን ይዘን በሰዓት እንገኝ።

ሰዓት 12:00
📍ቦታ  ጽ.ጽ. ሐዋርያት እና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

15 Nov, 10:04


የአንድነት መርሐ ግብር

ሰላም የልዑል እግዚአብሔር ቤተሠቦች እንደምን ቆያችሁ?
አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

እንደሚታወቀው ዛሬ የአንድነት መርሐግብር ስለሚኖር ሁላችንም
እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ወንድም እህቶቻችንን ይዘን በሰዓት እንገኝ።

📍 ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
🕕 12:00

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

13 Nov, 11:23


⚜️ የፋርማሲ እና የ new C2ተማሪዎች ኮርስ ⚜️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
💥💥💥💥💥💥💥💥💥
የተወደዳችሁ እኅት ወንድሞች እንደምን አላችሁ?አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

እንደሚታወቀው ዛሬ የፋርማሲ እና የnew C2 ተማሪዎች ኮርስ ስለሚኖር እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ወንድም እህቶቻችንን ይዘን በሰዓት እንገኝ።


ሰዓት 12:00
📍ቦታ  ጽ.ጽ. ሐዋርያት እና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

11 Nov, 08:14


⚜️ የC1 ተማሪዎች ኮርስ ⚜️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
💥💥💥💥💥💥💥💥💥
የተወደዳችሁ እኅት ወንድሞች እንደምን አላችሁ?አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

እንደሚታወቀው ዛሬ የC1 ተማሪዎች ኮርስ ስለሚኖር እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ወንድም እህቶቻችንን ይዘን በሰዓት እንገኝ።

ሰዓት 12:00
📍ቦታ  ጽ.ጽ. ሐዋርያት እና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

09 Nov, 10:40


መልስ ለጥያቄዎ

ጥያቄ፡ የማቴዎስ ወንጌል ላይ የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ይላል ይህ ምን ማለት ነው?

መልስ፡ ይህ ማለት በነቢይ ድንግል የተባለች እሷ ወልድ የተባለ ልጇ እንደ ሆነ አላወቃትም። ከወለደች በኋላ ግን ድንግል የተባለች እሷ እንደሆነች አወቀ ማለት ነው። ኢሳ. 7፡14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች። የተባለዉን።
አንድም አዳም ሔዋንን እንዳወቃት አላወቃትም ማለት ነው። ከወለደችስ በኋላ አውቆአታልን ቢሉ አይደለም! ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ‘’ፍጻሜ ያለው እስከ’’ አለ ‘’ፍጻሜ የሌለው እስከ’’ አለ። ለምሳሌ 2ኛ ሳሙ. 6፥23 የሳኦልም ልጅ ሜልኮል እስከሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም ይላል። ከሞተች በኋላ ወለደች ማለት ነውን? አይደለም! ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው። ጌታችን ማቴ. 28፥20 ያዘዝኋችኹንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው እንሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ዅልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ። ከአለም ፍጻሜ በኋላ ይለያቸዋል ማለት ነውን? በፍጹም አይደለም! ቅዱስ ጳውሎስ ከትንሳኤ በኋላ ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን ይላልና።
ሌላው በትንቢት ስለ እመቤታችን ዘለዓለማዊ ድንግልና የተጻፈ ምስክር አለ። ሕዝ. 44፥2 ‘’ወደ ምስራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም፦ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና፥ተዘግቶ ይኖራል።’’ ይላል። ይህ ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያም ዘለዓለማዊ ድንግልና ምስክር የሚሆን ቃል ነው። ከእመቤታችን ማህጸን በስተቀር የእስራኤል አምላክ የገባበት መቅደስ ሰውም ያልገባበት የት ይኖር ይሆን? የለም ተወዳጆች!

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

09 Nov, 10:40


መልስ ለጥያቄዎ

ጥያቄ፡ Normalizing sin ኃጢአትን normal ስለማድረግ ኃጢአትን መልመድ ከምን ይመጣል? በሕይወታችንስ ምን ጉዳት ያመጣል? እንዴት እንውጣ?

መልስ፡ ኃጢአትን መልመድ የሚመጣው አንድ ጊዜ አድርገው እና ትተወዋለህ ከሚል የሰይጣን የተንኮል ምክር ነው። ሰይጣን አንድም ኃጢአት አንድ ጊዜ ካደረነው ለቀጣይም ሁለተኛ ለመውደቅ ምክንያት እንደሚሆን ስለሚያውቅ አንድ ጊዜ ብቻ ሞክረው እስኪ ምን እንደሚመስል እየው፣ ሞክረው በሚል ምክር የኃጢአትን ልምድ ያስጀምራል ከዚያ በኋላ ሁለተኛ ጊዜ ደግመን እንድናደርገው የመጀመሪያውን ስህተታችንን ምክንያት አድርጎ ያቀርብልናል። ስለዚህም ደግመን እንወድቃለን ከዚያም በኋላ ደግመን ደጋግመን እንወድቃለን። ስለዚህም ወዳጀ በመጽሐፈ መነኮሳት ላይ ያለዉን ትምህርት ልብ በል ተግብረዉም እሱም እንዲህ ይላል። ‘’አንድ ክፉ ልማድ አንድ ጊዜ ካደረግከው በቀጣይ ባንተ ላይ ያይልብሃል። አንድ በጎ ልማድ አንድ ጊዜ ካደረግከው በቀጣይ ባንተ ላይ ያይላል።’’ በጎ ልማድም ክፉ ልማድም አንድ ጊዜ ከተቀበልነው በእኛ ላይ በጎ ልማድ እንደሚጸናልን ክፉ ልማድ እንደሚጸናብንም ልንረዳ ይገባል። የልማድን ኃይል ልንረዳ ያስፈልጋል። ስለዚህም ወደ ኃጢአት ልማድ እንዳንገባ ኃጢአትን ከመሞከር ልንሸሽ ይገባል።
ሌላው ኃጢአትን መልመድ ከቸልተኝነት ይመጣል። ማለትም ሰው በአካባቢው የሚሰማውንና የሚያየውን ነገር ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ሳይመረምር ዝም ብሎ በቸልተኝነት ከአካባቢው ጋር የሚመሳሰል ከሆነ የልምድ ኃጢአት ላይ ይወድቃል። ሲነቃም ራሱን ገብቶበት(የልምድ ኃጢአት ዉስጥ) ያገኘዋል። ሮሜ. 12፥2 የእግዚአብሔር ፈቃድ ርሱም በጎና ደስ የሚያሠኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችኹ ታውቁ ዘንድ በልባችኹ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ኃጢአትን መልመድ/የኃጢአት ልማድ በሕይወታችን ዉስጥ ብዙ ጉዳት ያመጣል አንደኛ ኃጢአት በራሱ ጎጅ ስለሆነ ከእግዚአብሔር ስለሚለይ በዚያ ይጎዳናል። የልምድ ኃጢአት በነፍስም በስጋም ይጎዳናል። ሁለተኛ የኃጢአት ልማድ ሰላማችንን እንድናጣ እና ራሳችንን መግዛት ስለማንችልም እንድንጨነቅ እንድንታወክ ያደርገናል። ሶስተኛ አንድ የኃጢአት ልማድ ወደሌላ የባሰ ኃጢአት ሊያድግ ይችላል ይህም እጅግ ይበልጥ አደገኛ ያደርገዋል። ስለዚህም ለሰይጣን እድል አትስጡት።
ከኃጢአት ልምድ እንዴት እንውጣ? ይሄን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ወደ ኃጢአት ልምድ እንዳንገባ ከላይ ኃጢአትን normal እንድናደርገው የሚያደርጉን እና ወደ መልመድ የሚያደርሱንን ነገሮች ማስወገድ ልክ በህክምናው እንዳለው disease prevention ማለት ነው። መጽሐፈ ሲራክም ሳትታመም ዳን ይላል።

እንዴት እንውጣ?
በመጀመሪያ ራስን/ህይወትን በቃለ እግዚአብሔር መመርመር ልብ ካላልናቸው ግን ከገባንባቸው የልምድ ኃጢአቶች እንድንነቃ ያደርገናል።

ሁለተኛው አባ እንጦንስ (የመጀሪያው መነኩሴ) የልማድ ኃጢአት በሥጋችን ካሉ ኃጢአቶች መካከል አንዱ ነው ይላሉ። ''ከሰይጣን ትጋትና ከክፉ ምክሩ የተነሳ ልናውቅ ይገባል። ሦስት ኃጢአቶች በሥጋችን እንዳሉ። አንደኛው ልማድ። ሁለተኛው ምክንያት። ሦስተኛው ፍላጎት ናቸው። እኛ ከወደድን እንቀበላቸዋለን ካልወደድን እናባርራቸዋለን።'' ዜና አበው ት/ት 27። ስለዚህም በቁርጥ ፈቃድ ከአንድ ልምድ ለመውጣት መወሰን እንዲሁም ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል።

የልምድ ኃጢአት አስገዳጅ ነው በጠባዩ ማለትም ልውጣ ብላችሁ ወስናችሁ እዚያው መልሶ ይከታችኋል! እኔንም ይመለከታል። ወዳጆቼ አንድ ሰው በአንድ ከተማ ዉስጥ ሲኖር እንደማንኛውም ሰው ሲኖር ምንም ስልጣን የለዉም ነገር ግን መሪ ሁነን ተብሎ ከተመረጠ በኋላ ግን መግዛት መንዳት ይችላል። የልምድ ኃጢአትም እንደ አምባገነን መሪ ነው። በቃ ስልጣን ልቀቅ ሲባል በቀላሉ እሺ አይልም። ስለዚህም መልሶ ወደዚያው ወደ ክፉ ልማድ ይከተናል። ስለዚህም ደካሞች እንደሆንን በትሕትና ለራሳችን አውቀን በጸሎት አምላካችንን ከዚህ ክፉ ልማድ አውጣኝ! ጌታ ሆይ እኔ ሞክሬ ነበር አልቻልኩም አንተ እርዳኝ እንበለው። ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ‘’በእኔ ማለት በስጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና ፈቃድ አለኝና መልካሙን ግን ማድረግ የለኝም። የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገር አላደገውም። የማልወደውን የማደርግ ከሆንሁ ግን ያን የማደርገው እኔ አይደለሁም በእኔ የሚኖር ኃጢአት ነው እንጅ።’’ ሮሜ. 7፡ 18-20 ይላል። አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ቅዱስ ጳውሎስ ‘’እኔ አይደለሁም በእኔ የሚኖር ኃጢአት ነው እንጂ’’ ያለው ልማድ እንደሆነ ያስተምሩናል። ከዚህ የልምድ ኃጢአት ለመላቀቅ መፍትሔውም ራስን በጌታ ፊት ዝቅ አድርጎ በጸሎት መማጸን ነው። እግዚአብሔር ሆይ ማረኝ! እግዚአብሔር ሆይ ሞክሬ ነበር ግን አልቻልኩም። እግዚአብሔር ሆይ ስነሳ ተመልሸ እወድቃለሁ። እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ እግዚአብሔር ሆይ ማረኝ በሉት ካንተ የሆነውን መንፈስ ስጠኝ እኔ አልቻልኩም በሉት ይላሉ። ስለዚህም የልምድ ኃጢአትን ለማሸነፍ የጸሎት ረዳትነት ልንይዝ ያስፈልጋል።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

09 Nov, 06:56


🌹ማኅሌተ ጽጌን በሕብረት🌹

ሰላም ውድ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ቆያችሁ?

እንኳን ለወርኃ ጽጌ የመጨረሻ ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!🌹


ውድ የጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ ልጆች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በረከትን እናገኝ ዘንድ ዛሬ  እና ቀሪዎቹን ሳምንታት

⚡️ ከቤተሰብ ጋር

⚡️ ከወንድም እና ከእኅቶቻችን እንዲሁም

⚡️ ከጓደኞቻችን ጋር በመሆን
በደስታ ማኅሌትን እንቆም ዘንድ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

 
መሰብሰቢያ ቦታ ፦ እዚሁ ግቢ ውስጥ ካፌ በር ጋር

ሰዓት ፦ 2:45 ላይ (አደራ ሰዓት ይከበር!)ቦታ ስለሚያዝ በሰዓቱ እንገኝ

ጥቁር አንበሳ ግቢ  ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

09 Nov, 06:34


ዘሳድሳይ ሣምንት ጽጌ(ተፈጸመ) ወበዓለ ልደታ ወራጉኤል ሊቀ መላእክት ሥርዓተ ማኅሌት (የስድስተኛ ሳምንት ጽጌ ፣ የልደታና የሊቀ መላእክት ራጉኤል በዓል ማኅሌት)

ነግሥ

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።


አቤቱ ጽሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ  በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።

መልክአ ሥላሴ

ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።

" አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ሆይ የሰላም መድረክ ለኾነ መለኮታዊ አፋችሁ ሰላምታ ይባል ለተዋሕዶ ሃይማኖት ዱር አበባው ጌጡ ናቸው ሥሉስ ቅዱስ ሆይ በአንድ ከተቀረጸ የጣዖት አምልኮት በፍጹም ቸርነታችሁ በሚመጣው ዓለም ገንዘብ ወደ እውነተኛው አምላክ አምልኮቴን ለውጡልኝ"

ዚቅ፦
አሠርገወ ገዳማት ሥን በመንክር ኪን አርአያሁ ዘገብረ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ በኩሉ ክብሩ ከመ እሎን ጽጌያት ኢቀደምት ወኢደኃርት :ዓራዛተ ሰርጎ ነሢኦሙ ኢክህሉ ከመ ክርስቶስ መዊአ።


ምድረ በዳውን በድንቅ ጥበቡ ውበትን አስጌጠ፤ በእርሱ የተመሰለው ሰሎሞን እንኳን እንደነዚህ አበቦች አለበሰም ከርሱ በፊትም የለበሰ የለም ወደፊትም አይለበስም፤ ልብሶቹን እንኳን ወስደው ክርስቶስ እንዳሸነፈው ማሸነፍ አይችሉም።

መልክአ ሥላሴ (ሌላ)፤
ሰላም  ለኲልያቲክሙ  እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ  አመ ሐወጸ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም  ድንግል፤ወበቀራንዮ  ተተክለ መድኃኒት መስቀል።


አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ ኩልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ ከእናንተ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ቃል ይቅርታ ለማድረግ ዓለምን በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም፣ ተፈጸመ። የነፃነት ዓርማ መስቀልም በቀራንዮ አደባባይ ተተከለ።

ዚቅ፦
እምሥርወ ዕሤይ ሠሪፃ ዘእምዘርዓ ዳዊት ተወሊዳ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ከመ ፍሥሖ ቀይሕ ከናፍሪሃ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ወከመ ሮማን መላትሒሃ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ኅብስተ ሕይወት በየማና ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ወጽዋዓ ወይን በጸጋማ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ጸሎታ ወበረከታ ይኩነነ ወልታ።


ከእሴይ ሥር ሠርፃ ከዳዊት ዘርም ተወልዳ ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች፤ ከንፈሮቿ እንደ ሚያስደስት ቀይ ነው፤ ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች ጉንጮቿ እንደ ሮማን ናቸው ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች፤ የሕይወት እንጀራ በቀኟ ነው ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች፤ የወይን ጽዋም በግራዋ ነው ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች፤ ጸሎቷና በረከቷ ጋሻ ይኹነን።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡


በማያልቅ ምስጋናሽ አብዝቼ ሳመሰግንሽ፤ ዘመነ ጽጌ ቢያልቅም በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም፤ ማርያም ሆይ ተአምርሽ እንደሚያስረዳው፤ ስም አጠራርሽ የወደቀውን ያስነሣል፤ ኃጢአተኛውንም ጻድቅ ያደርጋል።

💐ወረብ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ/፪/
ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ/፪/

ዚቅ
እለትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፤ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ጸልዩ ቅድመ ሥዕላ ለቅድስት ድንግል ፤መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡


የተቀመጣችሁ ተነሡ ዝም ያላችሁም ተናገሩ ፤ ማርያምን በምስጋና ቃል ጥሯት ፤ የድንግልን ተአምር ትሰሙ ዘንድ ቆማችሁም አድምጡ ፤ የቅድስት ድንግል ሥዕል ፊት ጸልዩ ፤ የአብ ሙሽራ የበጉ እናት ናትና።

💐ወረብ
እለ ትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ተረምሙ አውስዑ ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ/፪/
ጸልዩ ቅድመ ሥዕላ ለቅድስት ድንግል እመ በግዕ ወመርዓተ አብ/፪/


🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ፤በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ፤ማዕከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ ዘይነቡ፤እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ፤ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ።


ሙሽሪት ሆይ ከትንቢት አንበሳ ጉድጓድ በወጣሽ ቀን፤ የነገሥታት ንጉሥ የሰሎሞን ልብ እንደተደሰተ፤
የሐና አበባ ሆይ በደስተኞች ማኅበር መካከል፤ ተአምርሽን እየተናገርኩ አመሰግንሻለሁ፤
እንደሚጠባ እንቦሳም በማስተዋል ጐዳና እዘላለሁ።

💐ወረብ
እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ ፍኖተ ነፈርዓፅ/፪/
ማዕከለ ማኅበር እዜምር ማዕከለ ማኅበር/፪/

ዚቅ
ሰሎሞን ይቤላ ለማርያም፤ወለተ ሐና ወኢያቄም፤ ጽጌ ደመና ዘብርሃን።


ሰሎሞን ማርያምን የሐናና የኢያቄም ልጅ ሆይ ብርሃናማ የደመና አበባ ነሽ ይላታል።

ዓዲ ዚቅ፦
ወትወፅእ እምግበበ አናብስት ፤ እምታዕካ ዘነገሥት እምቅድመ ሃይማኖት ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ኵለንታኪ ሠናይት አልብኪ ነውር ፤ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ንዒ ርግብየ።


ከአንበሶች ጉድጓድ፣ ከነገሥታት አዳራሽ ከሃይማኖት ፊት ይወጣለች፤ መልካሟ ርግብ ሆይ ነይ ኹለንተናሽ መልካም ነው ባንቺ ላይ አንድም እንኳን ነውር የለብሽም ፤ መልካሟ ርግቤ ሆይ ነይ ፤ ርግቤ ሆይ ነይ።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ  ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል  ከማኪ ርኅሩኅ ፡፡ 


በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።

💐ወረብ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/


ዚቅ
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ


ድንግል ሆይ ከተወዳጁ ልጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ትባርኪን ዘንድ ወደ እኔ ነይ።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

08 Nov, 15:36


https://youtu.be/wxfKeFFyiuk?si=vqF2y87GPNoUQ83e

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

06 Nov, 06:59


⚜️ የፋርማሲ እና የ new C2ተማሪዎች ኮርስ ⚜️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
💥💥💥💥💥💥💥💥💥
የተወደዳችሁ እኅት ወንድሞች እንደምን አላችሁ?አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

እንደሚታወቀው ዛሬ የፋርማሲ እና የnew C2 ተማሪዎች ኮርስ ስለሚኖር እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ወንድም እህቶቻችንን ይዘን በሰዓት እንገኝ።


ሰዓት 12:00
📍ቦታ  ጽ.ጽ. ሐዋርያት እና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

05 Nov, 18:59


🔔ተንሥኡ ለጸሎት 🔔

ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።

📖የማቴዎስ ወንጌል 26 : 41

ነገ (ረቡዕ) ጠዋት 12:30 ላይ የጋራ የጸሎት መርሐ ግብር ስላለን በግቢ ያለን እንድንመጣ!

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

04 Nov, 12:45


⚜️ የC1 ተማሪዎች ኮርስ ⚜️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
💥💥💥💥💥💥💥💥💥
የተወደዳችሁ እኅት ወንድሞች እንደምን አላችሁ?አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

እንደሚታወቀው ዛሬ የC1 ተማሪዎች ኮርስ ስለሚኖር እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ወንድም እህቶቻችንን ይዘን በሰዓት እንገኝ።

ሰዓት 12:00
📍ቦታ  ጽ.ጽ. ሐዋርያት እና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

03 Nov, 06:01


"ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ህግ ፈፀሙ።
  ገላትያ 6:2"


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

የተወደዳችሁ እኅት ወንድሞች እንደምን አላችሁ? አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

📌ግቢ-ጉባኤያችን ከጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ሚካኤል (ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ት) ጋር በመተባበር ከ 4-8ኛ ክፍል ላሉ የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች በበጎ ፈቃድ የማስጠናት ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

📌አንድ ግለሰብ የፈለገውን ቀን መርጦ ከ 11:30-12:30 ባለው 1ሰዓት አገልግሎቱን በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይሰጣል። የማስጠኛ ቀናትን እንደፍላጎት በመናገር የምንወስን ይሆናል።

በዚህም መሠረት ማንኛውም በዚህ የነፍስ ዋጋ በሚያሰጥ አገልግሎት ላይ መሳተፍ የሚፈልግ የግቢ-ጉባኤያችን አባል በዚህ @hermela_desalegn እና @Hyab16 ላይ በ መጻፍ መመዝገብ ይችላል።

በረከቱ አያምልጣችሁ‼️🤗

ጥ.አ.ግ.ጉ. የሙያና በጎ አድራጎት ክፍል።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

02 Nov, 10:20


ሥርዓተ ማኅሌት ዘጽጌ ዘሐምሳይ ሳምንት ወበዓለ ተክለ ሃይማኖት (የአምስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌና የተክለ ሃይማኖት በዓል)

ነግሥ

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

አቤቱ ጽሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ  በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።

ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዓለምን ለፈጠረ ለአብ ሰላምታ ይገባል፣ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስም ሰላምታ ይገባል ፣ ለማርያም እና ለመላእክት ሰላምታ ይገባል ፣ ለነቢያትና ለሐዋርያትም ሰላምታ ይገባል ፣ ለሰማዕታትና ለጻድቃንም ሰላምታ ይገባል።

ዚቅ

ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት።

እርሷ የትጉሃን መላእክት እህታቸው ፣ የደጋግ ነቢያት ልጃቸው ፣ ለሐዋርያት እናታቸው ፣ ለጻድቃን እና ሰማዕታት ሞገሳቸው ናት።

ወቦ መልክዓ ሥላሴ(ሌላ)

ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከውስጣዊ ባሕርችሁ የሚገኝ ቸርነታችሁን ሰላምታ እላለሁ። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ የትሩፋት አበጋዝ እንደመሆችሁ የገድል ትሩፋትን አጎናጽፉኝ። ከድላቸው ገድል እሳተፍ ዘንድ በሄድኩ ጊዜ ጊዮርጊስ ከደሙ ጠብታ ሊሰጠኝ አልፈቀደም። ተክለ ሃይኖትም ከስባረ ዐፅሙ አንዲት ስንጥር እንኳ ከልክሎኛልና።

ዚቅ

ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ንዕዱ ማዕዶተ ንትካፈል ርስተ ኀበ ጽጌ ዘሠምረ ኀበ አስተዳለወ ዓለመ ክቡረ ምስለ ተክለሃይማኖት ንትፈሳሕ ሀገረ

ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ወደአማረው እንሻገር ርስትንም እንካፈል ወደ አማረው አበባ ዓለምን ወደ አዘጋጀው ክቡር ከተክለ ሃይማኖትም ጋር በሃገር ደስ ይበለን።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።

🌷ወረብ፦

ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሠናይትየ  ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት/፪/

ዚቅ፦

በሰላም ንዒ ማርያም፤ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም።

ማርያም ሆይ በሰላም ነይ፤ ከልቤ ኃዘን ታጽናኒኝ ዘንድ፤ ማርያም ሆይ በሰላም ነይ ከሚካኤልና ከገብርኤል ጋር፤ማርያም ሆይ በሰላም ነይ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ጋር፤ ማርያም ሆይ በሰላም ነይ ከቅዱሳን ኹሉ ጋር፤ ማርያም ሆይ በሰላም ነይ አማኑኤል ከተባለ ልጅሽ ጋር፤ ማርያም ሆይ ዓለምን ለማጽናናት በሰላም ነይ።

🌹ማኅሌተ ጽጌ፦🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

እመቤቴ! የሞቱ መታሰቢያ፤ የስሙ ምልክት የተጻፈብሽ፤ ከሚያበራ የባሕርይ እንቊ የጠራሽ የራስ ወርቅ ክበብ ነሽ፤
የአበባ ጉንጉን የተሣለብሽየጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ ማርያም ሆይ!!
አንቺ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።

🌷ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘይኀቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ

ሰአሊ ለነ ማርያም አክሊለ ንጹሐን ብርሃነ ቅዱሳን።

የንጹሐን አክሊል የቅዱሳን ብርሃን ማርያም ሆይ ለምኚልን።

ዓዲ ዚቅ፦

አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት

የሰማዕት አክሊል የመነኮሳት ተስፋ የካህናት ሿሚ፤ እነኋት ጽዮን መድኃኒት።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ፤ ወፈድፋድሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ፤ እስመ አንሥአ ሙታነ ወሕሙማነ ፈውሰ፤ ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ፤ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ።

ማርያም ሆይ! የፍቅርሽ ተአምር በጻድቃን ማኅበር ተመሰገነ፤ ይልቁንም በኃጥኣን ላይ በእጅጉ ነገሠ፤ ሕሙማንን ፈውሷልና፣ ሙታንንም አስነሥቷልና፤ የደረቀውንም አለመለመ የሚል አለ፤ ተራራውንም አፈለሰ የሚል አለ።

🌷ወረብ፦

ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ ተአምረ ፍቅርኪ/፪/
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ/፪/

ዚቅ፡

ይዌድስዋ ኵሎሙ ወይብልዋ እኅትነ ነያ ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ በሰማያት ኵሎሙ መላእክት

በሰማያት ያሉ መላእክት ኹሉ ያመሰግኗታል እነኋት እኅታችን ይሏታል ዳግመኛም አዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል።

🌹ማኅሌተ ፅጌ፦🌹

ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ፤ ይበቁዓኒ ዘብየ እምአፈ ጻድቃን ቅዳሴ፤ጽጌ መድኃኒት ማርያም ዘሠረፅኪ እምሥርወ እሴ፤ እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ፤ተአምረኪ የአኵት ብናሴ።

ከእሴይ ሥር የተገኘሽ የመድኃኒት አበባ ማርያም ሆይ! ከጻድቃን አንደበት የተገኘ፣ ያለኝ ምስጋና ይበቃኛልና፤ ከኃጢአተኛ አንደበት ውዳሴ አያስፈልገኝም አትበይ፤ እኔን በደለኛውን ከተቀበልሽም፤ ተአምርሽን ጨረቃ ታመሰግናለችና።

🌷ወረብ፦

ለምንት ሊተ ኢትበሊ ድንግል ውዳሴ እምአፈ ኃጥእ/፪/
ይበቁዓኒ ዘብየ ቅዳሴ እምአፈ ጻድቃን/፪/

ዚቅ፦

አዘክሪ ለኃጥአን ወአኮ ለጻድቃን አዘክሪ ለርሱሐን ወአኮ ለንጹሐን

ለጻድቃን አይደለም ለኃጥአን አሳስቢ፤ ለንጹሑን አይደለም ለአደፉት አሳስቢ።

🍂ሰቆቃወ ድንግል🍂

እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

እመቤቴ ማርያም ሆይ እስከ መቼ በባዕድ ምድር ትኖሪያለሽ ወደ ሃገርሽ ገሊላ ተመለሽ ፣ ዜናዊው ኦዝያን እንደተናገረው ናዝራዊ የተባለ ሕፃን ልጅሽን ለቅዱሳን ክንብር ይኾን ዘንድ ራማዊ(ሰማያዊ) አባቱ ከግብጽ ይጠራዋልና።

🌷ወረብ
በከመ ይቤ ኦዝያን ኦዝያን ክብረ ቅዱሳን/፪/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/፪/

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

02 Nov, 06:20


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
💥💥💥💥💥💥💥

የተወደዳችሁ እኅት ወንድሞች እንደምን ቆያችሁ? አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

ዮዲትም አለች፥ " አምላኬን በከበሮ አመስግኑት፤ ለጌታዬም በጸናጽል ዘምሩለት፤ በገና እየደረደራችሁ አመስግኑት፤ በምስጋና ከፍ ከፍ አድርጉት፤ስሙንም ጥሩ።"
መጽሐፈ ዮዲት 16፡2

ዛሬ 12:00 ሰዓት ላይ ልዩ የሆነ የጽጌ ወረብ ጥናት ስለሚኖር

ኹላችንም የጥናቱ ተሳታፊ እንሆን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

💥💥💥💥💥💥💥
ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን!🙏🙏

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

02 Nov, 04:18




🙏🏽የንስሐ ሳምንት🙏🏽
ቀን ፮

ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ግባ ኃጢአትህንም አርቃት፡፡ በአደባባይ የምትወድቀው ቊጥሩ ከምትነሣው ጋር እኩል ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ በደል ኃጢአት የምትሠራውን ያህልም ፍጹም ተስፋ ሳትቈርጥ ንስሐ ግባ፡፡ ኹለተኛ ብትበድል ኹለተኛ ንስሐ ግባ፡፡ በስንፍና ተይዘህ በፍጹም ምግባር ትሩፋት መሥራት አይቻለኝም አትበል፡፡ በእርግና ዘመን ብትኾንና ብትበድልም እንኳን ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሆስፒታል እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡ እዚህ ስትመጣ ካህናት [“እግዚአብሔር ይፍታሕ” ብለው] ከኃጢአት እስራት ፈትተው ይቅርታ ይሰጡሃል እንጂ “ለምን በደልህ?” ብለው አይፈርዱብህምና፡፡ ስለዚህ፡- “አንተን ብቻ በደልሁ፤ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፤ ኃጢአትህም ይቀርልሃል (መዝ.50፡4)፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ሁላችንንም ለንስሐ ሞት ያብቃን አሜን።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

01 Nov, 06:33


የአንድነት መርሐ ግብር

ሰላም የልዑል እግዚአብሔር ቤተሠቦች እንደምን ቆያችሁ?
አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

እንደሚታወቀው ዛሬ የአንድነት መርሐግብር ስለሚኖር ሁላችንም
እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ወንድም እህቶቻችንን ይዘን በሰዓት እንገኝ።

📍 ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን፣ ፀበል ቤት አዳራሽ
🕕 12:00

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

01 Nov, 03:53


🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

🙏🏽የንስሐ ሳምንት🙏🏽
ቀን ፭

እንዴት ንስሐ ይገባል?

🔴 ከራስ ጋር መሆን ነው

ንስሐ መግባት የራስን ፈቃድ ይጠይቃል፤ ሰው ንስሐ ለመግባት ፈቃዱ የራሱ ነው። የእግዚአብሔር ፍቃድ ሰው ንስሐ እንዲገባ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ‹‹እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደማወቅ ሊደርሱ ይወዳል›› በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው፡፡ 1ጢሞ. 2፥4
ከራሳችን ጋር የሆንን እንደሆነ ድካማችንንና ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር መናገር አይከብደንም መዝ. 50፥1-17 ለእግዚአብሔር የነገርነውን ኃጢአት ለመምህረ ንስሐችን መናገር አያሳፍርም ይህም ጸሎተ ንስሐ ከተደረገልን በኋላ ስጋውን ደሙን ለመቀበል የተዘጋጀን ያደርገናል፡፡

🔴 ምክንያትንና ለራስ ይቅርታ ማድረግን ማስወገድ

በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም፡፡ በዚህ አይነት ለኃጢአቱ ምክንያት እየደረደረ የሚጽናና ሰው ኃጢአትን እየለመደ ወደ ባሰ አዘቅት ከመውደቅ በቀር ንስሐ ለመግባት አይችልም ምንም ምክንያት ቢደረድር ኃጢአት ምንም ጊዜ ኃጢአት ነውና ለሰራነው ኃጢአት የተለያዩ ምክንያቶችን ለማበጀት ራሳችንን እያጽናናን ነጻ ለመሆን መጣር የለብንም አዳምና ሔዋን ባቀረቡት ምክንያት ከቅጣት አልዳኑም፡፡ አዳም ስላቀረበው ምክንያት ‹‹የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና ከእርሱ እንዳትበላ ካልኩህ ዛፍ በልተሃልና . . . ›› በማለት ለኃጢአቱ የሚገባውን ቅጣት ሰጠው እንጂ አልተወውም ዘፍ. 3፥17
ጌታው እንዲያተርፍበት አንድ መክሊት የሰጠው ሰው ጌታው በመጣና በጠየቀው ጊዜ ላለመነገዱና ላለማትረፉ ምክንያት ከመስጠት ወደ ኋላ አላለም፡፡ ይሁን እንጂ ጌታው ያቀረበውን ምክንያት አልተቀበለውም ወደ እሳት እንዲጣል አዘዘ እንጂ ማቴ. 25፥24 በእግዚአብሔር ዘንድ ለኃጢአት ምክንያት መደርደር መልካም አይደለም፡፡ ከዚህም ይልቅ በደልን ማመንና በኃጢአት ላይ መናዘዝ እግዚአብሔርን ያስደስተዋል ስርየትም ያስገኛል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ ሁላችንንም ለንስሐ ሞት ያብቃን አሜን::

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

31 Oct, 13:27


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
   💥💥💥💥💥💥💥

የተወደዳችሁ እኅት ወንድሞች እንደምን ቆያችሁ? አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

ዮዲትም አለች፥ " አምላኬን በከበሮ አመስግኑት፤ ለጌታዬም በጸናጽል ዘምሩለት፤ በገና እየደረደራችሁ አመስግኑት፤ በምስጋና ከፍ ከፍ አድርጉት፤ስሙንም ጥሩ።"
           መጽሐፈ ዮዲት 16፡2

ዛሬ 12 ሰዓት ላይ ልዩ የሆነ የጽጌ ወረብ ጥናት ስለሚኖር

ኹላችንም የጥናቱ ተሳታፊ እንሆን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

💥💥💥💥💥💥💥
ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን!🙏🙏

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

31 Oct, 04:09


ቀሲስ ክብሩ 0910909393
-5th pharma, old c2
ቀሲስ ካሳይ 0917300709
-4th pharma, c1, new c2, intern

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

31 Oct, 04:09


🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁

የንስሐ ሳምንት
ቀን ፬

ስንት ሰዓት ነው ???

የዘመናችን ኮከብ አባ እንጦንዮስ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አባ እንጦንዮስ ዝምተኛው መነኩሴ በዘመናቸው ስንት ሰአት ነው እያሉ ይጠይቁ ነበር ። ብዙዎች ግራ ይገባቸው ነበር ሲቆይ ግን ሁሉም ገባቸው ።

ስንት ሰዓት ነው ማለት በዚህ ምድር ለመኖር ስንት ሰዓት ነው የቀረን ለማለት ፈልገው ነው። በእየደቂቃው ንስሀ ግቡ ይሉ ነበር ። ሰው እንደወጣ እየቀረ ነው የእኛ ተራ መቼ እንደሆነ አናውቅም እያሉ ሰአታቸውን በምክር በተግሳጽ የሚያሳልፉት አባ እንጦንዮስ እነኚህ ናቸው በረከታቸው ይደርብን

ንሰሐ ግቡ ከኃጢአታችሁም ተመለሱ… ሕዝ. 14፡6

ንስሐ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው ከእግዚአብሔር መለየት ኃጢአት ነውና ንስሐ የሚገባ ሰው ከሠራው ኃጢአት በሙሉ ልቡ ይመለሳል፡፡ የበደለውን ፈጣሪውን ስለበደሉ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በነቢያት አድሮ ሕዝቡ ከኃጢአት ንስሐ እንዲገቡ እና ወደ እርሱ እንዲመለሱ ተናግሯል፡፡ ‹‹ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል እርሷንም አልጠበቃችሁም ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ›› ሚል. 3፥7 በማለት ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ በመጽሐፈ ምሳሌም ‹‹ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል›› በማለት ተጽፈዋል፡፡ ምሳ. 28፥13 በሉቃስ ወንጌል ላይ የምናገኘው አባካኙ ልጅ ኃጢአቱ በመረረውና በጸጸተው ጊዜ ወደ ልቡ ሲመለስ ወደ አባቱ ለመምጣት ወሰነ አባቱም በሐሴት ተቀበለው ሉቃ.15፥18 እውነተኛ ንስሐም ሰዎች በበደልና ኃጢአት ምክንያት ወደ አጡት ሥፍራ ለመመለስ የሚኖራቸው ናፍቆትና የሚወስኑት ውሳኔ ነው፡፡

እግዚአብሔር ሁላችንንም የንስሐ ሰዎች ያድርገን አሜን::

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

30 Oct, 10:18


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
💥💥💥💥💥💥💥💥💥
የተወደዳችሁ እኅት ወንድሞች እንደምን አላችሁ?አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን።

ዛሬ የፋርማሲ እና የ new C2 ተማሪዎች ኮርስ አይኖርም::

💥💥💥💥💥💥💥
ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን!🙏🙏
ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

30 Oct, 05:00


🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

🤲🏻የንስሐ ሳምንት🤲🏻
ቀን ፫

የእግዚአብሔር ይቅርታ

እናንተ #ከእግዚአብሔር ባሕርያት መካከል አንዱን ውሰዱና ቀስ በቀስ የተመስጣችሁ መስክ አድርጉት።

ለምሳሌ፡- #የእግዚአብሔር_ይቅርታና ሐጢአትን የሚሸሽግ አምላክ መሆኑን ውሰዱ … ከዚያም የነነዌ ሰዎች ለሐጢአታቸው ንሰሓ በገቡና በጸሙ ግዜ ሊመጣባቸው ካለው ቅጣት ይልቅ እንዴት #እግዚአብሔር እንዳዳናቸው በተመስጦ ትመለከታላችሁ። ሌላው ቢቀር እግዚአብሔር አምላክ ለዮናስ "እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?"(ዮና 4 ፡11) ብሎታል። #እግዚአብሔር በፍቅሩና በይቅርታው ታላቅ ከተማ ብሎ ለጠራት ለነነዌ ይህን ማድረጉ አስደናቂ ነገር ነው፥ልጆቿ ቀኝ እጃቸውን ከግራ እጃቸው ለይተው ባያውቁም እንኳ።ከዚህ ቀደም ብሎ #እግዚአብሔር ይህን ነቢይ ወደዚህች ከተማ እንዲሄዱና ስለ ጥፋትዋ ከእግዚአብሔር የተላከውን መልእክት እንዲሰብካት ነግሮት ነበር፥ ዮና 3 ፡4።

🌷 እናንተ ይቅር የሚለውን የእግዚአብሔር ልብ ስትገነዘቡ እርሱን ትወዱታላችሁ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ ሁላችንንም ለንስሐ ሞት ያብቃን አሜን!

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

29 Oct, 06:04


🔔ዝክረ ቅዱስ ገብርኤል🔔
         

እንኳን ለመላዕኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

 ዘካሪ የ 5ተኛ ዓመት ፋርማሲ ተማሪዎች

በዕለቱ የሚኖሩን መርሐ ግብራት

⚜️ጸሎት
⚜️ምስባክ
⚜️ መዝሙር
⚜️ ትምህርተ-ወንጌል
⚜️ ሥነ ጽሑፍ
⚜️ መዝጊያ ጸሎት ይኖራል::

📍፦ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ትልቁ አዳራሽ
🕕፦ 12:00
🗓️ :- ማክሰኞ ጥቅምት 19

እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ይህንን ሰማያዊ ደስታ እና በረከት ተካፋይ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ስም ጠርተንዎታል።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

29 Oct, 04:53


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

🤲🏻የንስሐ ሳምንት🤲🏻
ቀን ፪

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ወርኀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

==> #ንስሐ_ምንድ_ነው ?

~~ ንስሐ ማለት አንድ ሰው በሰራው ጥፋት፤ ባደረገው ስህተት፤ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑንና መቆርቆሩን፤ መጸጸቱ ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው።
==> ንስሐ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው መ.ሚል. 3:7
==> ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ነው 2ኛ ቆሮ. 6:19
==> ንስሐ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ እግዚአብሔር የሚያስወድድ ከንፁህ ልብ የሚመነጭ ጸጋ ነው ሕዝቅኤል.36:25-27
==> ንስሐ ከኃጢአት እንቅልፍ መንቃት ነው ሮሜ 13:11

==> ንስሐ ወደ መንፈሳዊ ህይወት መመለስ ነው ኤፌ. 5:14
==> ንስሐ ከኃጢአትና ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ መውጣት ነው ዮሐ. 8:34-26
==> ንስሐ ሰለ እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ቅድስና ብሎ ኃጢአትን መተው ነው ምሳ. 28:13
==> ንስሐ ኃጢአትን ከተወ በኋላ በፍጹም መልሶ አለመስራት ነው።
==> ንስሐ ስላለፈው ስህተት አብዝቶ ማልቀስ ያለፈውን የኃጢአት ኑሮ ማውገዝና መኮነን ነው። ኢዩኤል 2:12

==> ንስሐ ፍጹም የሆነ የህይወት ለውጥ እንጂ ጊዜአዊ ስሜት አይደለም ሮሜ 12:2
==> ንስሐ ኃጢአትን ሲሰሩ ከመኖር ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር መኖርን መሻት ነው። መዝ. 73:28

==> ንስሐ የአዕምሮ መታደስ ነው። ሮሜ 12:2

==> ንስሐ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ የሚያስችል ወደ መንግስተ እግዚአብሔር የሚያስገባ ቁልፍ ነው። ማቴ. 25:1-13
==> ንስሐ በቀራንዮ መስቀል ላይ እኛን ለማዳንና ከኃጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት የፈሰሰልንን የክርስቶስን ደም እንድናስብ የሚያደርግ መንፈሳዊ ሃብት ነው።
==> ንስሐ ከኃጢአት የሚያነጻ ሱራፌል ከመንበረ ሥላሴ የወሰዱት የእሳት ፍም ነው። ኢሳ. 6:4

==> ንስሐ ከሚመጣው የመጨረሻ መከራና ሀዘን መዳኛ ወይም ማምለጫ መንገድ ነው። ዮናስ 3:10

==> ንስሐ እግዚአብሔር የሰውን ኃጢአት ይቅር የሚልበትና ከኃጢአት ውጤት የሚያድንበት መሳሪያ ነው
==> ንስሐ ከሰዎች ጋር ለመታረቅ የተዘረጋ የእግዚአብሔር እጅ ነው። መዝ. 50/51

==> ንስሐ እግዚአብሔር ወደ ሰው የሚጣራውን ጥሪ ሰምቶ ወደ እርሱ መመለስ ነው። ዮሐ. 7:51 , ኤፌ. 4:30
==> ንስሐ ስለ አለፈው ኃጢአት ከመጸጸት የተነሳ የተሰበረ ልብ ነው። መዝ. 50/51:17
==> ንስሐ ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው ተጸጽተው ከእግዚአብሔር ጋር እንዳይታረቁ በብርቱ በሚጥለው ሰይጣን ላይ የተገኘ ድል ነው። መዝ. 123/124:6-7

ወስበሀት ለእግዚአብሔር ሁላችንን ለንሰሐ ሞት ያብቃን አሜን!

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

29 Oct, 04:53


ቀሲስ ክብሩ 0910909393
-5th pharma, old c2
ቀሲስ ካሳይ 0917300709
-4th pharma, c1, new c2, intern

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

28 Oct, 12:53


ቀሲስ ክብሩ 0910909393
-5th pharma, old c2
ቀሲስ ካሳይ 0917300709
-4th pharma, c1, new c2, intern

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

28 Oct, 12:53


🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🤲🏻የንስሐ ሳምንት🤲🏻
          ቀን ፩

እግዚአብሔር ሲቀጣን

"[አንድ] ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡

"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገ. 36

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

26 Oct, 14:49


ሥርዓተ ማኅሌት ዘራብዕ ሳምንት ጽጌ ወበዓለ እስጢፋኖስ (የአራተኛ ሳምንት ጽጌና የእስጢፋኖስ በዓል ማኅሌት)

ግእዝና አማርኛ 

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።


አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ  በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።

📖መልክአ ሥላሴ

ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።


" አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ሆይ የሰላም መድረክ ለኾነ መለኮታዊ አፋችሁ ሰላምታ ይገባል ለተዋሕዶ ሃይማኖት ዱር አበባው ጌጡ ናቸው ሥሉስ ቅዱስ ሆይ በአንድ ከተቀረጸ የጣዖት አምልኮት በፍጹም ቸርነታችሁ በሚመጣው ዓለም ገንዘብ ወደ እውነተኛው አምላክ አምልኮቴን ለውጡልኝ"

ዚቅ፦

ብፁዕ እስጢፋኖስ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን፤ለከ የዓርጉ ስብሐተ እግዚአ ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር በሥነ ጽጌያት፤ወሠራዕከ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ።


ብጽዕ እስጢፋኖስ ከቅዱሳን ኹሉ ጋር፤ ለአንተ ለሰንበት ጌታዋ ምስጋናን ያሳርጉልሃል ምድር በአበቦች ውበት አስጌጥህ፤ ለሰው ልጆች ዕረፍት እንዲኾን ሰንበትን ሠርትሃልና።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።


" በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።"

🌷ወረብ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ/፪/
ንዒ ርግብየ  ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ

ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናግሮ በዓምደ ደመና እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና።

ርግቤ ሆይ ነይ መልካሚቷ ሆይ ነይ ቃልሽ ያማረ ነው ከወይን ዘለላ በላይ ይትመኛል፤ ለሙሴ የድንኳናን አሠራር አሳየው በደመና አምድም ኾኖ ተናገረው፤ ለሰማዕታት እናታቸው ናት ለመላእክትም እኅታቸው ፤ ለሙሴ የድንኳናን አሠራር አሳየው በደመና አምድም ኾኖ ተናገረው።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።


"እመቤቴ! የሞቱ መታሰቢያ፤ የስሙ ምልክት የተጻፈብሽ፤ ከሚያበራ የባሕርይ እንቊ የጠራሽ የራስ ወርቅ ክበብ ነሽ፤
የአበባ ጉንጉን የተሣለብሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ ማርያም ሆይ!! አንቺ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።"

🌷ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ  ማርያም  ቀጸላ  መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ

ይእቲ ተዓቢ እምአንስት እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንጹሕ ለካህናት ብርሃኖሙ ለከዋክብት ።

ይህቺ ከሴቶች ኹሉ ትበልጣለች ለሰማዕታት እናታቸው ለመላእክት እኅታቸው ለነገሥታት መድኃኒታቸው የካህናት ንጹሕ አክሊል የከዋክብትም ብርሃናቸው ናት።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም ይገብር መንክረ፤እንዘ ጻእረ ሞት ያረስዕ ወያሰተጥዕም መሪረ፤በመአዛ ጽጌኪሰ ለዘበአውደ ስምዕ ሰክረ፤ውግረተ አዕባን ይመስሎ ኀሠረ፤እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ።


ማርያም ሆይ! የፍቅርሽ ተአምር መራራውን አጣፍጦ፤ የሞትንም ጣር አስረስቶ፣ ድንቅ ነገር ይሰራል፤ በልጅሽ የፍቅር መዓዛ ለሰከረ ሰው ደግሞ፤ በድንጊያ መወገር ገለባ፤ በእሳትም መቃጠል ቀዝቃዛ ባሕር ይመስለዋል፡፡

🌷ወረብ

ውግረተ አዕባን ውግረተ አዕባን ኀሠረ ይመስሎ ይመስሎ ኀሠረ/፪/
ለዘበአውደ ስምዕ ሰክረ በመአዛ ጽጌኪ እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ/፪/

ዚቅ

ሐሙ ርኀቡ ጸምዑ ወተመንደቡ፤ ዘኢይደልዎ ለዓለም ረከቡ፤ ቦ እለ በእሳት ወቦ እለ በኵናት፤ ቦ እለ በውግረተ ዕብን ወቦ እለ በመጥባሕት ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ አስበ ፃማሆሙ ነሥኡ ሰማዕት ።

ታመሙ ተጠሙ ተቸገሩ፤ ለዓለምም የማይገባውን አገኙ፤ አንዳቸው በእሳት አንዳቸውም በጦር ፤ አንዳቸው በድንጋይ በመወገር ሌሎችም በመታረድ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሰማዕታት መከራቸውን ተቀበሉ።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ዘንተ(ዘኒ) ስብሐተ ወዘንተ(ወዘኒ) ማኅሌተ፤ተአምርኪ ጸገየ ወፈረየ ሊተ፤ከመ እሰብሕ ዳግመ እንዘ እጸውር ፀበርተ፤ምስለ እለ ሐፀቡ ኣልባሲሆሙ በደመ በግዑ ድርገተ፤ውስተ ባሕረ ማኅው ድንግል ክፍልኒ ቁመተ።


ይህን ምስጋና ይህንንም ማኅሌት፤ ተአምርሽ አብቦ አፈራልኝ፤ ድንግል ሆይ! ዘንባባ ተሸክሜ ዳግመኛ አመሰግን ዘንድ፤ በበጉ ደም ልብሳቸውን ከአጡበት ጋር በአንድነት፤ በብርሌ ባሕር መቆምን አድይኝ።

🌷ወረብ

ምስለ እለ ሐጸቡ አልባሲሆሙ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ/፪/
ክፍልኒ ቁመተ ድንግል ድንግል ውስተ ባህረ ማኅው/፪/

ዚቅ

ገጹ ብሩህ ከመ ፀሐይ ወእምኵሉ ስነ ሠርጐ ሰማይ ለጊዮርጊስ ኅሩይ ዘተወልደ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ አልባሲሁ በደመ በግዕ ዘሐፀበ ወእምሠረቅት መርዔቶ ዓቀበ ።

ፊቱ እንደ ፀሐይ ያበራል ውበቱም ወደ ሰማይ ኹሉ ገብቷል የተመረጠ ጊዮርጊስ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ተወልዷል ልብሶቹን በበጉ ደም አጥቧል መንጋውንም ከሌቦች ጠብቋል።

ሰቆቃወ ድንግል

ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤ኢየሱስ ግፉዕ  ምስካዮሙ ለግፉዓን፤እግዚአብሔር ማኅደር  ዘአልቦ  ከመ  ነዳያን፤ ኢየሱስ ነግድ  ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን፤ወልደ አብ ፍቁር  ዘበኀበ ሰብእ ምኑን፤መኃልየ  ብካይ ኮነኒ ዘእሙ  ኃዘን።

ስደተኛው ኢየሱስ ለተሰደዱት ተስፋቸው ነህ ፤ የተገፋኸው ኢየሱስ ለተገፉትም መጠጊያቸው ነህ፤ እግዚአብሔር እንደ ደኾች ማደሪያ አጣህ፤ ኢየሱስ ገና በሕፃንነትህ እንግዳና ስደተኛ ኾንህ፤ በሰው ዘንድ የተናቅህ ተወዳጁ የአብ ልጅ ሆይ፤ የእናትህ ኃዘን የእንባ መዝሙር ኾነኝ።

🌷ወረብ

ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን/፪/
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን/፪/

ዚቅ፦
አንተ ውእቱ ምርጕዞሙ ለጻድቃን፤ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤መርሶሙ ለእለ ይትሀወኩ፤ብርሃነ ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው ።


ለጻድቃን መደገፊያቸው፤ ለስደተኞች ተስፋቸው ፤ ለሚታወኩት መልሕቃቸው ፤ የፍጹማን ብርሃን የሕያው አምላክ ልጅ አንተ ነህ።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

26 Oct, 14:49


መዝሙር
በ፭
ጳጳሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት፤ሊቃነ ካህናት ሥዩማነ ቤተክርስቲያን፤እለ ሎሙ ሕግ ወሎሙ ሥርዓት፤ብፁዕ እስጢፋኖስ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን፤ለከ የዓርጉ ስብሐተ፤ እግዚኣ ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር በስነ ጽጌያት፤ወሠራዕኮ ሰንበተ ለሰብአ ዕረፍተ፤ ወብውህ ለከ ትኅድግ ኃጢአተ ረቢ ንብለከ ረቢ፤ሊቅ ነአምን ብከ ።


ጳጳሳት ቀሳውስትና ዲያቆናት፤ የቤተክርስቲያን ተጠሪዎች ሊቃነ ካህናት፤ ሕግና ሥርዓት ያላቸውና፤ ብፅዕ እስጢፋኖስም ከቅዱሳን ኹሉ ጋር፤ የሰንበት ጌታዋ ሆይ ላንተ ምስጋናን ያሳርጋሉ፤ ምድርን በአበቦች ውበት አስጌጥክ፤ ሰንበትን ለሰው ዕረፍት ሠራህ፤ ኃጢአትን ታስተሰርይ ዘንድ ተሰትቶካል ፤ ረቢ እንልሃለን ረቢ ፤ መምህር በአንተ እናምናለን።

🌹ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤl እንኳን አደረሳችሁ!

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

26 Oct, 09:08


🌹ማኅሌተ ጽጌን በሕብረት🌹

ሰላም ውድ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ቆያችሁ?

እንኳን ለወርኃ ጽጌ ፬ተኛ ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!🌹


ውድ የጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ ልጆች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በረከትን እናገኝ ዘንድ ዛሬ  እና ቀሪዎቹን ሳምንታት

⚡️ ከቤተሰብ ጋር

⚡️ ከወንድም እና ከእኅቶቻችን እንዲሁም

⚡️ ከጓደኞቻችን ጋር በመሆን
በደስታ ማኅሌትን እንቆም ዘንድ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

-> ስንመጣ አዲስ የገቡ ተማሪዎችን አብረን ይዘን እንምጣ።


 
መሰብሰቢያ ቦታ ፦ እዚሁ ግቢ ውስጥ ካፌ በር ጋር

ሰዓት ፦ 2:45 ላይ (አደራ ሰዓት ይከበር!)ቦታ ስለሚያዝ በሰዓቱ እንገኝ

ጥቁር አንበሳ ግቢ  ጉባኤ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

26 Oct, 07:23


ሰላም እንደምን አደራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች?
አሜን የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን!
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ዛሬ  ጥቅምት 16 የንስሐ መርሐግብር ከቀሲስ ክብሩ ጋር ስለሚኖር ኁላችንም ተሰባስበን እንገኝ::

ቅዳሜ 10:00 ሰዓት (በጊዜ እንገኝ)  

📱📱0910909393 ቀሲስ ክብሩ

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

20 Oct, 10:00


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ናችሁ?

ዛሬ 9:00ስዓት ላይ የአብነት ትምህርት ስላለን ሁላችንም ተቀሳቅሰን በሰዓቱ እንገኝ።


ማስታወሻ

👉ቅዳሴ
👉ቁጥር
እና ሌሎችንም እንማራለን
መልካም ቀን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

19 Oct, 07:20


ሥርዓተ ማኅሌት ዘሣልሳይ ጽጌ ወበዓለ መስቀል (የሦስተኛ ሳምንት ጽጌና የመስቀል ማኅሌት)

ግእዝና አማርኛ 

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

አቤቱ ጽሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ  በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስግነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።

📖መልክአ ሥላሴ

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ ኩልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ ከእናንተ ከሦስቱ
አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ቃል ይቅርታ ለማድረግ ዓለምን በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ። የነፃነት ዓርማ መስቀልም በቀራንዮ አደባባይ ተተከለ።

ዚቅ፦

ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤ ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ሕይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።

ይህ የእውነት ቃል በመስቀል ትምህክትነት የተዘራ ነው፤ ፍሬውም የሕይወት መንፈስ ኾነ፤ ለሚድኑም ተስፋቸው ነው፤ በአበባውም (በክርስቶስም) መለኮት መልበሱን በመልኩ በግልጥ አሳየ፤ ማየ ልብን የተባለ ዕጣንን የያዘ ሲኾን የወይን አበባ የጻድቃንም ተስፋቸው ነው።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤ ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤ ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል።

ሳይተክሏት የበቀለች የለመለመች! ውኃ ሳያጠጧት ያበበች፣ ያፈራች፣ የአሮን በትር ማርያም ሆይ! ተአምር አሳየሽ፤ ስለዚህም ጥዑመ ልሳን ያሬድ፤ የወንጌል አጥር ይከባታል፤ ጽጌረዳም በመስቀል አምሳል ብሎ ከሱራፌል ጋራ አመሰገነሽ፡፡

🌷ወረብ

በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል/፪/
ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ያሬድ ወይብል ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል/፪/

ዚቅ

በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ በውስተ አሕዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይዕቲ።

የአሮን በትር ለመለመች በርሷም በአሕዛብ መካከል ተአምርን ያደርጋሉ የመስቀል ምሳሌ ናትና።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።

ማርያም ሆይ እናትሽ አበባን ያስገኘች ዕለተ ማክሰኞን፣ ብሩህ ፀሐይን ያስገኘች ዕለተ ረቡዕን ትመስላለች፤ ዳግመኛም ሰባተኛውን ቀን ትመስላለች፤ በሰማይና በምድር ላሉ ዕረፍት የኾንሽ፤ የነፃነት ቀን ዕለተ ሰንበት አንቺን በተአምር አፍርታለችና።

🌷 ወረብ

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/

ዚቅ

እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።

ከዕለታት ኹሉ ሰንበትን አከበረ ፤ ከሴቶች ኹሉም ማርያምን ወደደ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያውና የዓለም ኹሉ መስገጃው ትኾነው ዘንድ።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

" በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።"

🌷ወረብ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ

ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤ ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።

ሰላማዊቷ ርግቤ ሆይ ነይ፤ ተመለሽና በአንቺ ሰላምን እንይ፤ በወርቅ አምሳል የብር ገንቦ ይሥሩልሽ ፤ በወለደችው ጊዜ በመስቀል ምልክት የመውሰዷ ተምሳሌት ነው፤ እርሱ ደስታሽ ፣ ብርሃንሽና ሰላምሽ ነው።

ዓዲ ዚቅ

ወይቤላ ንዒ ንሑር፤ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ አውግረ ስኂን፤ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት

እኅቴ ሙሽራዬ መልካሟ ርግቤ ሆይ ወደ ከርቤ ተራራ የሉባንጃ ኮረብቶች መካከል ነይ እንሒድ ይላታል።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

"እመቤቴ! የሞቱ መታሰቢያ፤ የስሙ ምልክት የተጻፈብሽ፤ ከሚያበራ የባሕርይ እንቊ የጠራሽ የራስ ወርቅ ክበብ ነሽ፤
የአበባ ጉንጉን የተሣለብሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ ማርያም ሆይ!! አንቺ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።"

🌷ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ

ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤  ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ በትምህርተ መስቀል።


እነኋት መልካሚቱ እነኋት ውቢቱ፤ ንጽሒቷ አዳራሽ ነጻ አውጪዋ ማርያም፤ በወርቅ ልብስ የተጎናጸፈች የተሸፋፈነች ፤ በራሷም ላይ በመስቀል ምልክት የተጻፈ አክሊል አላት።

ዓዲ ዚቅ

በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት።

" በወርቅ ከርከዴን በተባለ ዕንቍ በምስጋናም ያጌጥሽ ነገሥታት ላንቺ ይገዙልሻል የመንግስታቸው ክብር ጌጥ ለነገሥታትም መድኃኒታቸው አንቺ ነሽ"

ሰቆቃወ ድንግል

ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።


ያዘናችሁ ሆይ ስደቷን እያሰባችሁ አልቅሱ፤ ደስተኞችም የበዛ መልካምነቷን እያስታወሳችሁ እዘኑ፤ ማርያም የአባቷን ሃገር ኤፍራታን አጥታ እንደ ወፍ ብቻዋን በግብጽ ተራሮች መካከል ትጮሃለችና ፤ የሕፃናት ደምም በመንገዷ ኹሉ ይፈሳል።

🌷ወረብ

ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 09:38


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ዋላችሁ?

ዛሬ 11፡00 ሰዓት ላይ የአብነት ትምህርት ይኖረናል።ለጽጌ መርሃግብር የሚሆን ወረብ ጥናት እንጀምራለን እና ግቢ ያላችሁ ልጆች ተጠራርታችሁ ኑ።

መልካም ቀን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

15 Oct, 06:00


ለጥቁር  አንበሳ ግቢ ተማሪዎች በሙሉ:
ዲቫ ሳሙና በ65 ብር እንዲሁም ብስኩት በ20 ብር ያቀረብን መሆኑን እያበሰርን ውድ ደንበኞቻችን እንደእናንተ ፍላጎት እያየን ሌሎች የፍጆታ እቃዎችንም ስለምናመጣ÷ ግብይታችሁን ከኛ ሱቅ በማድረግ ህይወትዎን ያቅልሉ ÷ ግቢ ጉባኤችሁንም ይደግፋ እንልዎታለን።

መገኛ÷ በወንዶች ዶርም  first floor ዶርም ቁጥር 19 እና
በሴቶች  second floor ዶርም ቁጥር 117 ነው።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

14 Oct, 06:23


ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ pinned «»

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 10:57


ሰቆቃወ ድንግል

በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ሥሩዓ፣ ኅብስተ ኅቡዓ ወጽዋዓ ወይን ምሉዓ፤እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ዘኃጥአ፤ተአገሠት በብሔረ ግብጽ ረኃበ ወጽምዓ፤አልቦ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ።


ተሠርቶ የተዘጋጀ ሥውር ኅብስትን ምሉዕ የወይን ጽዋን እየተመገበች በቤተ መቅደስ ያደገች የካህናት ልጅ ፤ እንዴት የዕለት ምግቡን እንደ አጣ ደሃ በግብጽ ሃገር ረኃብና ጥምን ታገሰች፤ እንደርሷ ግፍስ ያገኘው ማንም የለም።

🌷ወረብ

እፎ ከመ ነዳይ ዘኃጥአ ሲሳየ ዕለት/፪/
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ኅብስተ መና ኅቡዓ/፪/

ዚቅ

እሴብሕ ጸጋኪ ኦ ዑጽፍተ ልብሰ ወርቅ እግዝዕትየ ወለተ ዳዊት ንጉሥ ዘተሐፀንኪ በቤተ መቅደስ ወተዓንገድኪ በፈሊስ እምሀገር ለሀገር እንዘ ተዓውዲ በተፅናስ።

በቤተመቅደስ ያደግሽ የንጉሥ ዳዊት ልጅ ከሃገር ለሃገር በመሰደድም ዕንግዳ በመሆን በችግር ዙሪያ የዞርሽ፤ የወርቅ ልብስን የተጎናጸፍሽ እመቤቴ ሆይ ጸጋሽን አመሰግናለሁ።

መዝሙር

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።


ኪነ ጥበቡ ድንቅና ዕጹብ በአርያም ከፍታ ያለው ኪነ ጥበቡ ድንቅና ዕጹብ ነው። ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ ብሩህ በሆኑ ከዋክብት ሰማይን የጋረደው ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ ምድርንም በንፁሕ አበቦች ያስዋበ ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ሰንበትንም ያርፉባት ዘንድ የሠራ ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ (በኅብረት)፡ በዱር ውስጥ እንዳሉ የቆላ አበቦች የቅዱሳን መአዛቸው ቀንሞስና ናርዶስ የተባሉ ሽቱዎችን አፈሩልን።

አመላለስ

መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/
ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/

እንኳን አደረሳችሁ! በአካባቢያችን ካለ አጥቢያ በመሄድ የዚህ ድንቅ ምስጢር ተሳታፊ እንሁን!

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 10:57


ሥርዓተ ማኅሌት ዘካልዓይ ጽጌ ወበዓለ በዓታ ለማርያም (የኹለተኛ ሳምንት ጽጌና የበዓታ ለማርያም ማኅሌት)

ግእዝና አማርኛ 

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

አቤቱ ጽሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ  በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።

📖መልክአ ሥላሴ

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ ኩልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ ከእናንተ ከሦስቱ
አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ቃል ይቅርታ ለማድረግ ዓለምን በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ። የነፃነት ዓርማ መስቀልም በቀራንዮ አደባባይ ተተከለ።

ዚቅ፦

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከተ፤ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ።

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ የወይን ሐረግ፤ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ የወይን ሐረግ ፤ በሥሉስ ተቆርጣ የበረከት ዘለላ የምታፈራ የወይን ሐረግ ፤ የቅዱሳን ምግባቸው የወይን ሐረግ ፤ በቃሉ ሰንበትን ሠራ ሰላምንም ለኹሉ ሰጠ።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ(ጽላተ) ኪዳን፤ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡

" መጽሐፍ በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የተሾምሽ የቃል ኪዳን ምልክት ነሽ ብሎ እንደተናገረ፣ የሰንበታት ሰንበት የብርሃን ቀን ማርያም ሆይ፤ አበባ ያላት የገነት ጻድቃን በአንቺ ይደሰታሉ፤ ኃጥአንም በአንቺ ከኩነኔ ይወጣሉ"

🌷ወረብ

በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/

ዚቅ

ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ኅቡረ ንትፈሳሕ ዮም በዛቲ ዕለት፡፡

" ለጻድቃን የደስታቸው ሰንበት ለኃጥአንም የዕረፍታቸው ሰንበት ይህቺ ናት በዚህች ዕለት በኅብረት እንደሰት"

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ፤በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ።

ማርያም ሆይ በአረብና በተርሴስ ወርቅ እንደ ተለበጠች ታቦት፣ በነፍስና በሥጋ በድንግልና የተለበጥሽ ነሽ፤ ኢያቄምና ሐና ቀንሞስና ቀናንሞስ የተባሉ ሽቱዎች ፤ መለኮት የጠበቀሽን አንቺን በሦስት ዓመት ካስገኙ በኋላ በቤተመቅደስ መኖር ተአምርን አሳየሽ።

🌷 ወረብ

እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ  ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ/፪/
ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ/፪/

ዚቅ

አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን ድንግል ኅሪት ዘነበረኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ሥርግው በወርቅ ንጡፍ ወልቡጥ በዕንቍ ባሕርይ ዘየኃቱ ዘብዙኅ ሤጡ ከመዝ ነበርኪ በቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽሑ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ አሠርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ።

ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የሆንሽ አንቺ ነሽ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደ ተሠራ በወርቅ እንደ ተጌጠና ዋጋው ብዙ በሆነ በሚያበራ ዕንቁ እነደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ። እንዲህ ሆነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ መላእክትም ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር በመላእክት እየተጽናናሽ እንዲህ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖርሽ። መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

" በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።"

🌷ወረብ

ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/

ዚቅ

ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎሕ ሠናይት ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጣስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት

እንደ ማለዳ ብርሃን መልካም የሆንሽ ፤ ቅድስተ ቅዱሳን የተባልሽ የመቅደስ ታቦት ፤ የማትቃጠለዋ ቁጥቋጦ ተክል፤ የመለኮት ማደርያ ፍጽምት ድንኳን ነጻ አውጪዋ ርግቤ ሆይ ነይ።

ዓዲ ዚቅ

ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።

ኹለመናሽ መልካም ፤ እድፍ የሌለብሽ ነጭ ፀምር ፣ መና ያለብሽ መሶበ ወርቅ፤ የበቀለች የአሮች በትር የተባልሽ ርግቤ ሆይ ነይ።

ወቦ ዘይቤ ዚቅ

ይዌድስዋ ትጉሃን፤ይቄድስዋ ቅዱሳን፤ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርይዪ ወአጽምዒ ዕዝንኪ

ትጉሃን ያወድሷታል ፤ ቅዱሳን ይቀድሷታል(ያመሰግኗታል) ፤ ሰሎሞን መልካሟ ርግቤ ይላታል ፤ ጳውሎስ ፍጽምት ድንኳን ይላታል፤ ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮዎችሽንም አዘንብዪ ይላታል።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

"እመቤቴ! የሞቱ መታሰቢያ፤ የስሙ ምልክት የተጻፈብሽ፤ ከሚያበራ የባሕርይ እንቊ የጠራሽ የራስ ወርቅ ክበብ ነሽ፤
የአበባ ጉንጉን የተሣለብሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ ማርያም ሆይ!! አንቺ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።"

🌷ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/

ዚቅ

ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤መራኁቱ ለጴጥሮስ፤አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ


በቤተ መቅደስ የተተከለች ሎሚ ፤ የጴጥሮስ መክፈቻ ቁልፍ ፤ አንቺ የጳውሎስ ምሥክር ድንኳን በእውነትም የጊዮርጊስ አክሊሉ ነሽ።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 05:41


ሰላም የእግዚአብሄር ቤተሰቦች

📖መጽሀፍ ቅዱስ
📚የቤተክርስቲያን መፅሐፍት
📚የፀሎት መፅሐፍት
🙏ነጠላ
👍 በገና
🙏ክራር

የት ልግዛ ብለዉ ተቸግረዋል? እንግድያዉስ የ ግቢ ጉባኤ ሱቃችን ስራዉን ስለጀመረ ይደዉሉ ይዘዙን

📞0945294421
@Hann_Be
@Hailemaryam_21

ሰላመ እግዚአብሔር ከናንተጋር ይሁን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

11 Oct, 07:42


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ዋላችሁ?

ዛሬ 11፡00 ሰዓት ላይ የአብነት ትምህርት ይኖረናል።እንደ ባለፈው የዚህን ሳምንት የጽጌ ወረቦች እናጠናለን እና ግቢ ያላችሁ ልጆች ተጠራርታችሁ ኑ።

መልካም ቀን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

06 Oct, 16:35



🌿የአንድነት መርሐ ግብር

ሰላም የልዑል እግዚአብሔር ቤተሠቦች እንደምን አመሻችሁ?

ነገ የአንድነት መርሐ ግብር ስለሚኖር እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ወንድም እህቶቻችንን ይዘን በሰዓት እንገኝ።

📍 ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን፣ ትልቁ አዳራሽ
🕕ከምሽቱ 12:00


ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ