Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB / @aacahbc Channel on Telegram

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

@aacahbc


ጤና ለሁሉም!! ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ጤና ጣቢያ ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የጤና መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Addis Ababa City Administration Health Bureau (Amharic)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጤና ለሁሉም!! ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ጤና ጣቢያ ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የጤና መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡ ይህ ቻናል ከዚህ በታች የከተማ አሰሳ ጤና እንደገና የቴሌግራም ቻናል በነፃነት ሲሆን በሁሉም ጊዜ ለመድሃኒትን ከዚህ ባለው እርምጃ ተጠቃሚ በቴሌግራም ቻናል ሊኖረው ይችላል፡፡ እናንተም ጤና መረጃ ማዳመጥን እና አስገባ፤ እኛም በእኛ ሁሉ መከላከያ እንሂድ፡፡

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

10 Jan, 14:29


ለህብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ተግባራትን በታቀዱት አግባብ በትኩረት መሰራቱ ተገለፀ ።

አአ ጤና ቢሮ ጥር 2/2017ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዉ ግማሽ አመት የተከናወኑ ተግባራትን የቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል።

ቢሮው ባለፉት 6 ወራት የታቀዱ ተግባራትን በተለይም በጤና ማጎልበት እና በሽታ መከላከል ዘርፍ ፣ የእናቶች እና ህጻናትን ጤና ከበጠበቅ፣ማህበረሰብ አቀፋ ጤና መድህን አገልግሎት እና በፈውስ ህክምና አገልግሎት ዘርፍ የተለያዩ ተግባራት በዕቅድ ተይዘው መከናወናቸው በእቅድ ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ሪፖርት ቀርቧል ።

በቀረበው ሪፖርትም የእናቶችን ጤና ከመጠበቅ አንፃር 246 ሺህ 192 የሚሆኑትን የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሰራቱና የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም የቤት ለቤት የምክር እና ድጋፍ አገልግሎት 208 ሺህ 749 እናቶችን መድረስ መቻሉ ተገልጿል።

ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ከመከላከል እና ከመቆጣጠር አንጻር 3 ሺህ 620የቲቢ ፣ 1 ሚሊዮን 234 ሺህ 434 የደም ግፊት ፣ 223 ሺህ 784 የስኳር ፣ 50ሺህ 242 የማህፀን ጫፍ ካንሰር ልየታ ተደርጎላቸው አስፈላጊው ህክምና እና ክትትል እንዲያገኙ ማድረግ እንደተቻለ ተገልፆል።

ለኤች አይ ቪ ይበልጥ ተጋላጭ ነት አንጻ የሶስቱ 95 በመቶ አፈጻፀም በተመለከተ ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲመረመሩ ከማድረግ በመቶ ፐርሰንት እንዲመረመሩ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ፣ ተመርምረው ራሳቸውን ካወቁት እና ቫይረሱ በደማቸው ከሚገኙት ውስጥ 89 በመቶ የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት እንዲወስዱ ማድረግ እንዲሁም የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት ከሚወስዱ 96 በመቶ የሚሆኑት በአግባቡ በመውሰድ በደማቸው ውስጥ ያለውን የቫይረስ መጠን እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉ ተመላክቷል ።

በፈውስ ህክምና አገልግሎት በመጀመሪያው ግማሽ መት 118ሺህ910 የአስተኝቶ ህክምና ፣ 7ሚሊዮን 800ሺህ በላይ በተመላላሽ ህክምና አገልግሎት መስጠት የተቻለ ሲሆን ፣ የአንቡላንስ አገልግሎት መስጫ ማዕከላን ከነበሩት 3 ማዕከላት ወደ 8 ማሳደግ መቻሉ እንዲሁሞ የህመም ማስታገሻ እንክብካብ አገልግሎት/palative care/ እና የጤና ስርአት ማነቆዎች መሠረት ያደረገ ሪፎርም /SBFR/ በስፋት ተግባራዊ መደረጉ ለአገልግሎት አሰጣጡ መሻሻል ጉልህ አስተዋፅዎ እንደነበረዉ ተመላክቷል።

የድንገተኛ በሽታወች ቅኝት እና መከላከልን በተመለከተ የኩፍኝ እና ሌሎች ወረርሽኝን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን እነዚህን ወርሽኞች ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር እና የመከላከል ስራ መሰራቱ እንዲሁም 92 ጤና ጣቢያዎች ላብራቶሪ አገልግሎትን ባለ ሶስት ኮከብ እኖዲሆኑ ሆስፒታሎች ደግሞ ባለ አራት ኮከብ እንዲሆኑ መሰራቱ ተመላክቷል።

ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ቢሮው በግማሽ ዓመቱ ከፋይ አባላት እና ከተማ አስተዳደሩ መክፈል የማይችሉ የማህበረሰብ ክፋሎች ድጎማ የተሸፈነላቸው በአጠቃላይ 1 ሚሊየን 330ሺህ 562 አባወራእና እማወራ ተጠቃሚ መሆናቸዉ ተገልፆል ።

የፋርማሲ አገልግሎት በተመለከተ የህይወት አድን መድሀኒት 97 በመቶ የመሰረታዊ መድሀኒት አቅርቦት 96 በመቶ እንዲሁም የታዘዘውን መድሀኒት ሙሉ በሙሉ ያገኙ 94 በመቶ መሆናቸዉ ተመላክቷል።

የጤና አገልግሎትን ዲጂታል /ወረቀት አልባ/ ለማድረግ በተሰራው ተግባር በሁሉም ሆስፒታሎችና በ51 ጤና ጣቢያዎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ የተቻለ መሆኑ ተገልፆል።

ቢሮው ከመደበኛ ተግባራት ጎን ለጎን ባለፉት 6 ወራት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአቅመ ደካሞችን ቤት ዕድሳት የበጎ ፈቃድ የነፃ የህክምና አገልግሎቶችን እና ሌሎች ተግባራትን በትኩረት መከናወናቸዉ ተገልጿል ።

በዕለቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ምክትል ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ በ2017 በጀት አመት የመጀመሪያዉ ግማሽ አመት አፈፃፀም ዉጤታማ እንደሆነ ገልፀዉ የእቅድ አፈፃፀም በወቅቱ መገምገም መቻሉ ያሉትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል እና መሻሻል የሚገባቸዉን በሚገባዉ ፍጥነት በማሻሻል ለቀጣይ 6ወራት የተሻለ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ያስችላል ብለዋል።

ህብረተሰቡ የሚፈልገዉን የጤና አገልግሎት መነሻ በማድረግ መተግበር እንደተቻለና የጤና አገልግሎት በጤናዉ ሴክተር ብቻ የማይሰራ በመሆኑ ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ዶክተር ሙሉጌታ ተናግረዋል።

በቢሮው የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ስምአነሰዉ በበኩላቸው በመጀመሪያዉ ግማሽ አመት ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በትኩረት በመሰራቱ ጥሩ ዉጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልፀዉ የመረጃ አያያዝና ጥራት ላይ በትኩረት መሰራት ይገባል ብለዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት 👇

Facebook፡ https://www.facebook.com/www.aahb.gov.et
Twitter : http://twitter.com/ @AACAHBC
YouTube: https://youtube.com/@addisababacityadministrationhe
Telegram: https://t.me/AACAHBC

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

06 Jan, 11:17


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለከተማችን እና ለመላው ሀገራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆን እየተመኘን በበዓሉ ወቅት ለጤናዎ ይበልጥ ጥንቃቄ በማድረግ በተለይም ቅባቶችን በብዛት ከመመገብ እና ምግብን በደንብ ሳያበስሉ በመመገብ የጤና እክል እንዳይገጥመን ፣ ቅባቶችን መጥኖ በመመገብ እንዲሁም ምግብን በደንብ አብስሎ በመመገብ ጤናዎን እንዲጠብቁ እያሳሰብን ለሚገጥማችሁ ማንኛውም የጤና እክል ጤና ተቋማቶቻችን እንደሁልጊዜው እናንተን ለማገልገል 24 ሰዓት አገልግሎት ላይ መሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን መልካም በዓል ይሁን!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ !!

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት 👇

Facebook፡ https://www.facebook.com/www.aahb.gov.et
Twitter : http://twitter.com/ @AACAHBC
YouTube: https://youtube.com/@addisababacityadministrationhe
Telegram: https://t.me/AACAHBC

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

06 Jan, 11:17


በለሚ ኩራ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ከባለሃብቶች ጋር በመተባበር የገነባናቸው ቤቶች እና የስራ እድል ለተፈጠረላቸው የልማት ተነሺ የከተማችን ነዋሪዎች የመስሪያ ቦታዎችን አስተላልፈን እንኳን አደረሳችሁ ብለን ማዕድ አጋርተናል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብቻ በኮሪደር ልማትና በመንገድ ወሰን ማስከበር ለተነሱ 4ሺ 510 እማወራ እና አባወራዎች ንጹህ እና መሠረተ ልማት የተሟሉላቸው መኖሪያ ቤቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብተን ያስተላለፍን ሲሆን 1264 በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች ደግሞ የስራ እድል ፈጥረን የመስሪያ ቦታዎችን አስረክበናል::
አዳዲስ 4 ህንጻዎች በአያት ሪል ስቴት፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ጄ ኤፍ ኤም ፔትሮሊየም ዲስትሪቢዩሽን እንዲሁም በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የተገነቡ ሲሆን በተጨማሪም በላይነህ ክንዴ ግሩፕ በአቃቂ ቃሊቲ 48 ቤቶችን እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ 141 ቤቶችን ገንብተን ለነዋሪዎች አስተላልፈናል::

መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን የተወጡ ባለሃብቶችን በነዋሪዎቹ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት 👇

Facebook፡ https://www.facebook.com/www.aahb.gov.et
Twitter : http://twitter.com/ @AACAHBC
YouTube: https://youtube.com/@addisababacityadministrationhe
Telegram: https://t.me/AACAHBC

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

06 Jan, 11:14


እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን ሕግ ጥሶ ከእግዚአብሔር ጋር የታጣላው ራሱ የሰው ልጅ ነበረ፡፡ ዕርቅን አውርዶ ሰላምን ለማስፈን በረት ድረስ የመጣው ግን እግዚአብሔር ነው፡፡ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ፣ አሸናፊ፣ የሚሳነው አንዳች የሌለ ነው፡፡ ነገር ግን ለዕርቅ እና ለሰላም ሲል ወደ ማይገባው ሥፍራ መጣ፡፡ አሸናፊ ቢሆንም እንደ ተሸናፊ ሆነ፡፡ ዐቅም ቢኖረው እንደ ዐቅመ ቢስ ሆኖ ታየ፡፡ በሁሉ ሀብታም ሲሆን፣ ራሱን ታናሽ አደረገ፡፡ ይህ ሁሉ ለዕርቅና ለሰላም የተከፈለ የታላቅነት ዋጋ ነው፡፡

እግዚአብሔር ለዕርቅ እና ለሰላም ሲል በደካማዋ ከተማ በቤተልሔም፣ በተናቀችው ሥፍራ በበረት መገኘቱ የገባቸውም ያልገባቸውም ነበሩ፡፡ የገባቸው፤ ከሰማየ ሰማያት ወርደው “ሰላም እና ዕርቅ በምድር ይሁን” ብለው ዘመሩ፡፡ የገባቸው፤ ከምሥራቅ ኮከቡን አይተው፣ እጅ መንሻውን ይዘው መጡ፡፡ የገባቸው፤ በረታቸውን ለቅቀው ለድንግል ማርያም እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጡ፡፡ የገባቸው፤ የሰማይ መላእክቱን ተከትለው ወደ በረት ሄደው እርቅና ሰላምን አመሰገኑ፡፡

ያልገባቸው ሰዎች፣ የዕርቅ እና የሰላሙ ዐዋጅ እየታወጀ እነርሱ ግን ተኝተው ነበር፡፡ የመንደር ጌቶች እነ ሄሮድስ፣ የሰው ልጅ ሰላም ማግኘት ሳይሆን ከጠላት ያገኙት ሥልጣን ያስጨንቃቸው ነበር፡፡ የይሁዳ ሰዎች፤ ዓለም በማይመለስበት ሁኔታ እየተቀየረ፣ እነርሱ ግን እየሆነ ያለውን ለውጥ አያዩም አይሰሙም ነበር፡፡ ከሰማይ መላእክት ወርደው፣ ከምድር እረኞች ነቅተው ተአምር ሲሠራ፤ እነርሱ ግን በዕንቅልፍ ደንዝዘው ነበር፡፡እ ነርሱ እያንቀላፉ ከተማቸው ቤተልሔም ተቀይራለች፡፡ የእንጀራ ቤት ሆናለች፡፡ ታሪኳ ተቀይሯል፡፡ ታናሽ ከተማነቷ ተቀይሯል፡፡

ያልገባቸው፣ ሰላምና ዕርቅ ሲባሉ የድካምና የዐቅመ ቢስነት ምልክት አድርገው ተመለከቱት፡፡ ሰይፍና ጎራዴ የለመዱ፤ መግደልና ማጥፋት ጀግንነት የሚመስላቸው ነበሩና፡፡ ሰላም ድካም፣ ዕርቅም ሽንፈት ይመስላቸው ነበር፡፡ ስለዚህም በእኩለ ሌሊት ከመሸ፣ በከብቶች በረት ለሁሉ የመጣውን ሰላም አቅለው አንቀበልም አሉ፡፡ እነ ሄሮድስ ሰይፍ መዘዙ፡፡ ሰላምን አሳደዱ፤ ሰላማዊ ሕጻናትንም ፈጁ፡፡ ሄሮድስ የገዛ ሕዝቡን ለመጨፍጨፍና ለመግዛት በጠላት የተሾመ ሰው ነበር፡፡ የሚያስፈጽመው የእሥራኤል ጠላቶችን ዓላማ ነበረ፡፡

ይሄንን በዓል የምናከብር፤ ወይ ሰላምና ዕርቅን ከሚወዱት ወገን ነን፡፡ አለያም ሰላምንና ዕርቅን ከሚያሳድዱት ወገን ነን፡፡ መንግሥት ሰላምና ዕርቅን ደጋግሞ የሚያውጀው ዐቅም ከማጣት፣ ጉልበቱ ከመድከም የተነሣ አይደለም፡፡ ሁሉም ዓይነት መንግሥታዊ ዐቅሞች በእጁና በደጁ አሉ፡፡ ሰላምና ዕርቅ ግን ከሁሉ በበለጠ፤ ዘመን አሻጋሪ፣ ታሪክ ቀያሪ፣ የችግርና መከራ ዘመን ማብቂያ መፍትሔዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ሁሉን አሸናፊ፣ ሁሉን አሻጋሪ ያደርጋሉ፡፡ ጠባሳ ሳይተዉ ቁስልን ያሽራሉ፤ ለልጅ ልጅ ቂምን ሳይሆን ሐሴትን ያወርሳሉ፤ ከመጠፋፋት ይታደጋሉ፡፡ የሰላምና የዕርቅ መንገድ የሚመረጠውም ለዚህ ነው፡፡

ሰላምና ዕርቅን መምረጥ፤ የኃያል ባለ-ራዕይ፣ የፍጹማዊ-አሸናፊና ባለታላቅ-ዐቅም በውዴታ የሚሸከመው የከፍታ ግዳጅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችል ነበር፡፡ ሰላምን እያወጀ ወደ ከብቶች በረት የመጣው ግን እርሱ ኃያሉ ነው፡፡ የአዳም ልጆች በሠገነት ሲወለዱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው በበረት የተወለደው፡፡ እግዚአብሔር ነው ለሰላምና ለዕርቅ ሲባል ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ መከራን የተቀበለው፡፡
መንግሥት ዛሬም ለሰላም እና ለዕርቅ እጁ እንደተዘረጋ ነው፡፡ ለሁሉ የሚሆን ሰላም በኃይል ሳይሆን በፍቅር መንገድ እንደሚመጣ ያውቃል፡፡ ለሰላምና ለዕርቅ በመሸነፍ ውስጥ ፍጹማዊ ማሸነፍ እንዳለ ያምናል፡፡ ጥቂቶች እንጂ ብዙኃኑ ከሰላም የሚገኘውን ክፍያ የሚሹ እንደሆነ ይረዳል፡፡
የጠላት መሣሪያ የነበረውን የሄሮድስን መጨረሻ ማየት ነው፡፡ ለሰላምና ለዕርቅ ጀርባቸውን የሰጡ የቤተልሔም ከተማ ሰዎችን ፍጻሜ ማሰብ ነው፡፡ እግዚአብሔር በረት ድረስ ሲፈልጋቸው አሻፈረኝ ብለው ነበር፡፡ ከዓመታት በኋላ በኃይልና በጉልበት ሲጎበኛቸው ግን፣ ፈልገው ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ ቤታቸው የተፈታ ሆኖ ቀረ፡፡ ከዚያ በኋላ ፍለጋቸው መባከንና መቅበዝበዝ ሆነ ፡፡ ዕርቅና ሰላምን የሚገፋ ሁሉ መጨረሻው እንደዚህ ነው፡፡

ሁሉም ጊዜ አለው፡፡ በጊዜው መጠቀም የጠቢባን ድርሻ ነው፡፡ ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንደተዘረጉ አይቀሩም፡፡ ለሰላም ሲባል ወደ ምድር የወረዱ ሁሉ እንደ ወረዱ አይቀሩም፡፡ ለሰላም ሲባል ደካሞች መስለው የታዩ ሁሉ፣ ኃይላቸው በጊዜው ይገልጣሉ፡፡ የግድግዳው ጽሑፍ ይመጣል፡፡ የተዘረጋው ብራና ይጠቀለላል፡፡

ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ሦስቱ ሰላማውያን ቦታ አላገኙም ነበር፡፡ የጥበብ ሰዎች፣ እረኞች እና መላእክት፡፡ ሦስቱም ብዙዎቹ ያደረጉትን ለማድረግ የመጡ አልነበሩም፡፡ ትክለኛውን ነገር ለማድረግ እንጂ፡፡ ሦስቱም ዘመን የወለደውን ጊዜ የወደደውን አልተከተሉም፡፡ የሚጠቅመውን ነገር እንጂ፡፡ ታሪክ እንደሚያስተምረን ግን የእነዚህ የሦስቱ እውነት በጊዜው ተገልጧል፡፡ ዓለምም በየዓመቱ የክርስቶስን ልደት ሲያከብር እነዚህን ሦስቱን ሰላማውያን ያስታውሳል፡፡

ለሰላም ስትሉ ዋጋ የምትከፍሉ፣ የምትዋረዱና የምትቃለሉ ሁሉ ከሦስቱ ሰላማውያን መማር አለባችሁ፡፡ የጠላት መሣሪያዎች የሆኑት ሄሮድሳውያን ቢገድሉም፤ የቤተልሔም ሰዎች እምቢ ቢሉም፣ የተማሩ የተባሉት የአይሁድ ሊቃውንት ቢቀልዱም፣ ለሰላም ዋጋ መክፈል ያዋጣል፡፡ ቢያንስ ሰማያዊና ታሪካዊ ዋጋ ያስገኛል፡፡

ይሄንን በዓል ስናከብር ከሦስቱ ሰላማውያን ጋር ሆነን ሰላምና ዕርቅ በሀገራችን እንዲሰፍን የበኩላችንን በማድረግ እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ እርስ በርስ ከመሸናነፍ ስለሰላም ሁላችንም ብንሸነፍ ሁላችንንም አሸናፊ ያደርገናል፡፡ መንግሥት ለሰላማዊ መንገዶች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ ለሰላም ከሚሠሩት ጋር ሁሉ አብሮ ይሠራል፡፡ ሰላማውያን ለሚከፍሉት መሥዋዕትነት ክብርና ዋጋ ይሰጣል፡፡


በድጋሜ መልካም በዓል ይሁን፡፡


ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ታህሳስ 28፣ 2017 ዓ.ም

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት 👇

Facebook፡ https://www.facebook.com/www.aahb.gov.et
Twitter : http://twitter.com/ @AACAHBC
YouTube: https://youtube.com/@addisababacityadministrationhe
Telegram: https://t.me/AACAHBC

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

06 Jan, 08:39


የሰኞ ማለዳ የስራ እና የህይወት ተሞክሮ ልውውጥ በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።

አ/አ/ ጤና ቢሮ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች ዘወትር ሰኞ ማለዳ "ወርቃማው ሰኞ" በሚል ስያሜ ሰራተኞች ሳምንቱን በተነቃቃና በመልካም ስሜት ወደስራ እንዳገቡ የተለያዩ የስራ እና የህይወት ተሞክሮ ልምድ ልውውጥ የሚካሄድበት መድረክ ነው ።

የዕለቱን ፕሮግራም መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ምክትል ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ በሰኞ ማለዳ የስራ እና የህይወት ተሞክሮ እርስ በእርስ የምንማማርበት የአንድን ሰው ልምድ ወስደን ጥንካሬውን ያሳለፉትን ፈተናዎችን በመጋፈጥ ወደ ድል እና ስኬት እንዴት መቀየር እንደሚቻል የምንማርበ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

በዕለቱ የህይወት እና የስራ ተሞክሯቸውን ያቀረቡት በቢሮው የፋርማሲ አገልግሎት ዳይሬክቶረት ውስጥ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌታሁን ሲሳይ በገጠራማ የሰሜን ወሎ ክፍለ ሀገር የጁ ተወልደው ትምህርታቸን በአስቸጋሪ ሁኔታ ከሶስት ሰአት በላይ በእግራቸው በመመላለስ ቤተሰቦቻቸው ሳይማሩ እንዳስተማሯቸው ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

አቶ ጌታሁን የ12 ክፍል ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መግባት ሲገባቸው ወደ ብሄራዊ ውትድርና እንዲገቡ ተደርገው በውትድርና ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

በወቅቱ ዩንቨርሲቲ የሚያስገባ ከፍተኛ ውጤት ቢያመጡም በውትድርና ሀገራቸውን እያለገሉ ጥሪውን ባለስማተቸው አልፏቸው ከአንድ አመት በኃላ ቢጠጥቁም ባለመሳካቱ ሀገራቸውን በመምህርነት ማማልገላቸውን ልምድ አካፍለዋል፡፡

አቶ ጌታሁን በመምህርነት ላይ እያሉ በዩክሬን ሀገር የትምህርት እድል በማግኘ ታቸው የፋርማሲ ትምህርታቸውን ተከታተለው በመምጣት በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በመተማ ፣ በባህርዳር ፣ በገጎንደር እና በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በፋርማሲ አገልግሎት በሀላፊነት በመስራት የሀገራችን የፋርማሲ አገልግሎት መሻሻል መሪ ተዋናኝ በመሆን ማገልገላቸውን ልምዳቸውን አከፍለዋል፡፡

አቶ ጌታሁን በስራው አለም ከ29 ዓመት በላያ ሀገራቸውን ያገለገሉና በማገልገል ላይ ያሉ አጋፋ ባለሙያ ሲሆኑ በፋርማሲ አዳዲስ አሰራሮች እና ዘመኑ የሚጠይቀውን አገልግሎት በመተግበር ለአሁኑ የመድሀኒት ቁጥጥር እና አስተዳደር የሚጠቅም አሰራሮችን በመተግበር መሰረት የጣሉ እንደሆነም ከልምዳቸው አካፍለዋል ።

ልጀቸው የሳቸውም የሳቸውን ጠንካራ ፈለግ በመከተል በህከምና የ4ኛ አመት ተማሪ ያደረሱ ሲሆን አሁን ለደረሱበት ትልቁን አስተዋፅዎ ላደረጉት ወላጀቻቸው ትልቅ ክብር እና ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት 👇

Facebook፡ https://www.facebook.com/www.aahb.gov.et
Twitter : http://twitter.com/ @AACAHBC
YouTube: https://youtube.com/@addisababacityadministrationhe
Telegram: https://t.me/AACAHBC

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

04 Jan, 16:10


ኤች አይ ቪ/ኤድስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሚደረገው ሂደት የትምህርት ማህበረሰቡ ሚና ከፍተኛ ነው።

አ/አ/ጤና ቢሮ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኤች አይ ቪ /ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ስርጭቱን በመግታት ለማህበረሰቡ የጤና ችግር ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት የትምህርት ማህበረሰቡ ሚና ከፍተኛ ነው።

ቢሮው በተለይ በትምህርት ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን እና የትምህርት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ በጋራ እየተሰራ ይገኛል ።

ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን እና ምክትል ርዕሰ መምህራን ፣ የኤድስ ክበብ ተጠሪዎች እና የተማሪዎች ተወጋዮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በትምህርት ቤት ለተማሪዎች ኤች አይ ቪ ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች እና ባህሪያት ራሳቸውን በመጠበቅ ራሳቸውን ከኤች አይ ቪ እንዲጠብቁ እና የነገ ሃገር ተረካቢ ጤናማ ትውልድ እንዲሆኑ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ በውይይቱ ተነግሯል።

የቢሮው የኤች አይ ቪ ዘርፈ-ብዙ ምላሽ ቡድን መሪ ሲስተር ሒሩት አለማየሁ ባለፉት ዓመታት የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመቀነስ በርካታ ተግባራት ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በትምህርት ቤቶች መከናወናቸውን ገልፀው ለዚህ ደግሞ የትምህርት ማህበረሰቡ ሚና ከፍተኛ ነበር ብለዋል።

ኤች አይ ቪ አሁንም የማህበረሰቡ የጤና እና ተጓዳኝ ችግር ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ በባህሪ ለውጥ እና በህክምና አገልግሎት ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለፁት ሲስተር ሒሩት ለውጤታማነቱ የትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኤች አይ ቪ /ኤድስ ፕሮግራም ባለሞያ ወይዘሪት ገንዘብ ደሳለኝ በበኩላቸው ተማሪዎችን ለኤች አይ ቪ ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች እና ባህሪያት ለመጠበቅ የሚያስችሉ በትምህርት ቤቶች የኤድስ ክበባትን በማጠናከር የግንዛቤ ማስጨበጥ እና የአቻ ለአቻ ውይይቶች ተጠናክረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት 👇

Facebook፡ https://www.facebook.com/www.aahb.gov.et
Twitter : http://twitter.com/ @AACAHBC
YouTube: https://youtube.com/@addisababacityadministrationhe
Telegram: https://t.me/AACAHBC

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

04 Jan, 08:56


የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 26/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያስገነባውን የድንገተኛ ህክምና ማዕከል አስመርቋል።

ማዕከሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ነው የተመረቀው።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንዳሉት፥ ማዕከሉ የሆስፒታሉን የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

ለድንገተኛና ህክምና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶችና ባለሙያዎች ማፍራት ላይ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።

የህክምና ተቋማትንና ባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት በተሰሩ ስራዎች ውጤት መገኘቱንም አመልክተዋል።

ለድንገተኛ ህክምና የሚመጡ ህሙማንን ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ግብዓቶች ማሟላት ላይ በትኩረት እንሰራለን ነው ያሉት።

የትምህርት ሚኒስትርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው፥ በጤናና በትምህርት ዘርፍ የተጀመሩ ሪፎርሞች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።

የመንግሥት የህክምና ተቋማትን አቅም ለማጠናከርና የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አቅሞችን ለመፍጠር ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፥ ዩኒቨርሲቲው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በዩኒቨርሲቲው ስር ያሉ ፕርጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባለፉት ስድስት ወራት ግማሽ ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች የህክምና አገልግሎቶችን መስጠቱ ተገልጿል።

#Ethiopian_News_Agency #Ethiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

03 Jan, 15:38


ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት 👇

Facebook፡ https://www.facebook.com/www.aahb.gov.et
Twitter : http://twitter.com/ @AACAHBC
YouTube: https://youtube.com/@addisababacityadministrationhe
Telegram: https://t.me/AACAHBC

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

02 Jan, 17:12


"አዲስ አበባ ከተማን በጤናው ዘርፍ ከሌሎች አለም ሃገራት ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው" የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ

አ/አ/ ጤና ቢሮ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የማስፈፀም ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ የተመራው ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጡ የክትትል እና ድጋፍ ቡድን የጤና ቢሮን የ2017 በጀት ዓመት በ6 ወራት የተከናወኑ የመንግስት እና የፓርቲ ተግባራትን ክትትል እና ድጋፍ አድርጓል ።

ቢሮው በ6 ወሩ በተለይ የእናቶች እና ህፃናት ጤና ከመጠበቅ ፣ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ፣በበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ፣ በህክምና አገልግሎት ፣ በመልካም አስተዳደር ፣ በመድሃኒት አቅርቦት እና ስርጭት ፣ በዲጂታል ጤና አገልግሎት ላይ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ በክትትል እና ድጋፉ ተመላክቷል።

በፓርቲ ስራም የአባላትን አቅም በመገንባት ግንባር ቀደም በመሆን ተግባራትን መፈጸም እንዲቻል የተሰራ ሲሆን መልካም ስነምግባርን በመላበስ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የተሻለ እንዲሆን በስፋት መሰራቱ ተገልጿል።

በክትትል እና ድጋፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ እንደገለጹት ቢሮው የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት በዕቅድ ተይዘው መከናወናቸውን እና አዲስ አበባን በጤናው ዘርፍ ከሌሎች የአለም ሃገራት ከተሞች ተወዳዳሪ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ።

በክትትል እና ድጋፉ የተሰጡ አስተያየቶችን እንደ ግብዓት በመውሰድ በቀጣይ የተሻለ ተግባር ለማከናወን እንደሚሰራ ዶክተር ዮሐንስ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ደረጃ የማስፈፀም ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ በበኩላቸው ቢሮው ለህብረተሰቡ የሚፈለገውን የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሰራቸው ተግባራት ለሌሎች ተቋማት አርዓያ የሚሆን መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ቢሮው በስሩ በሚገኙ የጤና ተቋማት ዲጂታል /ወረቀት አልባ/ የጤና አገልግሎት መስጠት መቻሉ አዲስ አበባ ከተማን በቴክኖሎጂ የዘመነች እና ተመራጭ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ ላለው ስራ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት የጠቀሱት ወይዘሮ ፍቅርተ ቢሮው ከሌሎች ተቋማት ጋር ያለውን ውጤታማ ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ እንዲቀጥልም አመልክተዋል።

በክትትል እና ድጋፉ የቢሮው አመራሮች፣ የማናጅመንት አባላት እና ባለሙያዎች በቡድኑ የተሰጡ ጠንካራ አፈጻጸሞችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ያሉ ውስንነቶችን በትኩረት ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት 👇

Facebook፡ https://www.facebook.com/www.aahb.gov.et
Twitter : http://twitter.com/ @AACAHBC
YouTube: https://youtube.com/@addisababacityadministrationhe
Telegram: https://t.me/AACAHBC

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

01 Jan, 15:09


በገዳይነቱ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠ በሽታ

ምንጭ :- ፋና ቴሌቪዥን

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት 👇

Facebook፡ https://www.facebook.com/www.aahb.gov.et
Twitter : http://twitter.com/ @AACAHBC
YouTube: https://youtube.com/@addisababacityadministrationhe
Telegram: https://t.me/AACAHBC

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

30 Dec, 05:40


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻን በይፋ አስጀምሯል ።

አአ ጤና ቢሮ ታህሳስ 21/2017 ዓም

የክትባት ማስጀመሪያው በአራዳ ክፍለከተማ መስከረም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና የክፍለከማው የስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታሁን አበራ ፤ የቢሮው የማኔጅመንት አባላት እና ባለሙያዎች ባለድርሻ አካላት እና የሃይማኖት መሪዎች ፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች በተገኙበት ተጀምሯል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ የማህጸን በር ካንሰር በሽታ በሴት እህቶቻችን ብሎም በማህበረሰቡ ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመረዳት እና ይህን የከፋ የጤና ችግር መከላከል ይቻል ዘንድ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረው
በሽታውን ከምንከላከልባቸው የተለያዩ ስልቶች አንዱ ታዳጊ ሴት ልጆችን በት/ቤት እና ከት/ቤት ውጭ ክትባት እንዲያገኙ ማድረግ ሲሆን ክትባቱን በሀገራችን ብሎም በከተማችን የሚመለከታቸውን ታላሚዎች ተደራሽ ማድረግ ከጀመርንበት 2011 ዓ.ም አንስቶ በርካታ ሴት ልጆች የክትባቱ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ዶክተር ዮሐንስ በማስጀመሪያው አመልክተዋል፡፡

በክትባት ዘመቻው 177,933 ለሆኑ ታዳጊ ሴት ልጆች ክትባቱን እንዲወስዱ መታቀዱን እና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በየክ/ከተማውና ጤና ጣቢያዎች በበቂ መጠን የደረሰ ሲሆን 381 የክትባት ቡድኖችን በማዋቀርና የሚመለከታቸው ሁሉ በት/ቤቶችና ከት/ቤት ውጭ የሚገኙ ሴት ልጆችን ከዛሬ ታህሳስ 21ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ስለሚሰጥ ለስኬታማነቱ ሁሉም እንዲተባበር ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ዛሬ በማለዳ በመስከረም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስጀመርነው የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባ በሁሉም የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች ከማር ማስተማሩ ጎን ለጎን ይሰጣል ።

ለዚህ ክትባት ስኬት የትምህርት አመራሩ አጠቃላይ ወላጆች እና የትምህርት ማህበረሰቡ እድሜቸው ከ9እስከ 14አመት ያሉ ሁሉ ክትባቱን በመውሰድ ጤናቸውን ከዚህ አስከፊ በሽታ እዲጠብቁ አደራ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

09 Dec, 13:56


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዜጎች የስምምነት ቻርተርን በመከለስ በማዘጋጀት ላይ ነው።

አ/አ/ ጤና ቢሮ ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የከተማውን የጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማ ለማድረግ በየ ሁለት ዓመቱ የዜጎች የስምምነት ቻርተርን ያዘጋጃል።

ቢሮው በማዕከል እና በስሩ በሚገኙ የጤና ተቋማት መሰረት ያደረገ የዜጎች የስምምነት ሰነድ ቻርተርን በመከለስ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።

እያዘጋጀ የሚገኘው ይህ የዜጎች የስምምነት ቻርተር በከተማዋ ያለው የጤና ዘርፍ አገልግሎት ቀልጣፋ እና ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑን በቢሮው የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ፣ ድጋፍ እና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ ደለሳ ተናግረዋል።

ቢሮው ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት እና ተገልጋዮችም ወደ ጤና ተቋም ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸውን ሁሉ የያዘ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አቶ ኤርሚያስ ገልፀዋል።

የስምምነት ቻርተሩ ግልፀኝነት ፣ ፍትሐዊነትን እና ተጠያቂነትን በማስፈን አሁን ላይ ያለው የጤና አገልግሎት አሰጣጥ እንደሚያሻሽለው የተናገሩት ዳይሬክተሩ አቶ ኤርሚያስ ደለሳ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ለሁለም የጤና ተቋማት ተደራሽ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

07 Dec, 15:48


ቢሮው የዓለም ኤድስ ቀንን በቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ከታራሚዎች ጋር  በተለያዩ ዝግጅቶች አስቧል ።

አ/አ/ ጤና ቢሮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ጋር በመተባበር  የዓለም ኤድስ ቀን  በቃሊቲ  ማረሚያ ማዕከል ከታራሚዎች ፣ የማዕከሉ አመራር እና ሰራተኞች በተገኙበት  በተለያዩ ዝግጅቶች አስበው ውለዋል፡፡

በዕለቱ የተገኙት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ  ጤና ቢሮ የዘርፈ ብዙ የኤች አይ ቪ ኤድስ ባለሙያ ወይዘሮ  ሰፊና መሐመድ  ባስተላለፋት መልዕክት የዓለም ኤድስ ቀንን አስበን ስንውል በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን በማሰብ እና በቀጣይ ስርጭቱን ለመግታት ግንዛቤ በማስጨበጥ ነው ብለዋል።

ቢሮው ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት ወይዘሮ ሰፊና የኤች አይ ቪ አገልግሎቶች ማግለል እና  መድሎ ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የጤና አገልግሎት ሰብዓዊነት በተሞላበት ሁኔታ ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እንደሚከናወኑም ገልፀዋል።

እ.ኤ.አ በ2030 ኤች አይ ቪ የማህበረሰቡ የጤና ችግር ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ እና ከቫይረሱ ነፃ የሆነ ትውልድ   እንዲኖር ከምንጊዜውም በላይ እንደሚሰራ ወይዘሮ ሰፊና መሐመድ ተናግረዋል።

የየማረሚያ ቤቱ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኮማንደር  ዶክተር ተስፋዬ አበራ በበኩላቸው ቢሮው የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመግታት የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እያከናወነ ያለውን ተግባር  አድንቀው  በተለይ ወጣቶችን  እና ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ  የማህበረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ባደረገ መልኩ በተቋማቸው በጋራ ግንዛቤ መፈጠሩ ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት  አመልክተዋል።

ለኤች አይ ቪ አጋላጭ ሁኔታዎች እና ባህሪያት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የገለፁት ኮማንደር ዶክተር ተስፋዬ ግንዛቤ ከማስጨበጥ አንፃር ኮሚሽኑ የድርሻውን እንደሚወጣ ተናግረዋል።

በዕለቱ በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሙዚቃ እና ቲያትር ቡድን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች ቀርበዋል።

የዘንድሮው የዓለም ኤድስ ቀን ''ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ  ዝግጅቶች እየታሰበ ይገኛል ።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

05 Dec, 17:56


ሴቶች የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመቀነስ በሚደረገው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

አ.አ.ጤና ቢሮ ህዳር 26/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የአለም የኤድስ ቀንን በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የሴቶች ማህበር አባላት ጋር የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ አድርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሀንጋቱ መሀመድ ባስተላለፍት መልእክት ቢሮው ልዩ ትኩረት ተሰቶት እየተሰራ ካሉ ስራዎች አንዱ የሴቶችና ህጻናትን ጤና መጠበቅ መሆኑን ገልጸው በዚህም ሴቶች ካላቸው የኤች አይ ቪ ተጋላጭነት አንጻር የተለያዩ የባህሪ ለውጥ ግንዛቤዎችን በመስጠት እና የህክምና አገልግሎቶችን በሁሉም ጤና ተቋማት ተደራሽ እንዲሆን መሰራቱን ተናግረዋል ።

ወላጆቻቸዉን በኤች አይ ቪ ምክንያት ምክንያት ያጡ ህፆናትን በመደገፍ ከናት ወደ ልጅ ኤች አይ ቪ እንዳይተላለፍ በትኩረት በመሰራቱ ውጤት መመዝገቡንም ነው ወይዘሮ ሀንጋቱ የገለፁተሰ ።

ቢሮው እ.ኤ.አ. በ2030 ከኤች አይ ቪ ነፃ የሆነ ትዉልድ የማፍራት ግብን ለማሳካት በተለይ የሴቶችን ተጋላጭነት መቀነስ እና ራሳቸውን ከበሽታው እንዲጠብቁ በማህበራት ተደራጅተው በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሁለንተናዊ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ እየተሰራ ያለው ተግባር ጤናቸውን ከመጠበቅ አንጻር ከፍተኛ ውጤት ለው ብለዋል ።

ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ደግሞ የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ በከተመረ አስተዳደሩ የተሰራው ማሳያ እንደሆነ ገልፀዉ ተቋሙ ሴቶች የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ በተለያዩ የሙያ አይነቶች በማሰልጠን በገቢ ማስገኛ ስራ ተሰማርተው ራሳቸዉን እንዲችሉ እየተደረገ ያለዉ ስራ ትልቀሰ ውጤት ማምጣቱን እና ከተማ አስተዳደሩ የሰራው ስራ ትልቅ ስኬት ሲሆን ይህ ተግባር ከጤናው ሴክተር ዉጤታማነት አንጻር ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

በቢሮ የኤች አይ ቪ ዘርፈ-ብዙ ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲስተር ፈለቀች አንዳርጌ ኤች አይ ቪ አሁንም የህብረተሰቡ የጤና ችግር በመሆኑ እና ስርጭቱን ለመከላከል ሴቶች ትልቁን ድርሻ የሚይዙ እና ያለውን ተጋላጭነት ለመከላከል ቢሮዉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅታዊ እየሰራ መሆኑን ገልፀዉ ።

በቀጣይም የሴቶች አደረጃጀት እና ማህበራት የሴቶች ወጣቶችና አፍላ ወጣቶችን ተጋላጭነት ለመከላከል በሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የድርሻቸውን እንዲወጡ ገልፀው የዘንድሮው የአለም ኤድስ ቀን መሪ ቃልም "ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም" የሚል በመሆኑ ከሴት ማህበራት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክረን መቀጠል ይገባል ብለዋል።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

23 Nov, 13:04


የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓቱን በማዘመን እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ ።

አ/አ/ጤና ቢሮ ህዳር 14/2017 ዓ.ም

በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥ እንዲኖር እና የጤናው ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ውጤታማ እንዲሆን የዲጅታል መረጃ አያያዝ ስርዓቱ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱ ተመላክቷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮም ዘርፉን ይበልጥ ለማዘመን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን JSI/DUP ዘርፉን በመደገ የጤና መረጃ አያያዝ ጥራት የተሻለ እንዲሆን ከቢሮው ጋር በአጋርነት እየሰራ የሚገኝ ይገኛል ።

ቢሮው የጤና ተቋማትን የመረጃ ስርዓት ለማዘመን የሰራቸውን Health Information systems / HIS / አጠቃላይ ተግባራት ከJSI/DUP እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ገምግሟል።

የጤና ተቋማት ያለው የመረጃ አያያዝ ስርዓት በማዘምን ቀልጣፋ ፣ ጊዜ ቆጣቢ እና የህብረተሰቡን እርካታ ለመጨመር የተቻለ ሲሆን ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲያመች በማድረግም የጤና አገልግሎቱ የተሻለ እንዲሆን ማስቻሉ በግምገማው ተመላክቷል።

የግል የጤና ተቋማትም የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን በዲጂታል እንዲያደራጁ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በትኩረት በመሰራቱ በከተማዋ ያለው አጠቃላይ የጤና አገልግሎት እና የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ወጥነት ያለው እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተጠቅሷል።

በፕሮግራሙላይ የተገኙት የቢሮው የዕቅድ በጀት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ስምአነሰው የጤና መረጃ ስርዓት አጠቃላይ ለጤናው ዘርፍ ውጤታማነት ቁልፍ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልፀው ለዲጂታል /ወረቀት አልባ/ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትም ከፍተኛ ድርሻ አለው ብለዋል።

በቢሮው የJSI/DUP አስተባባሪ ወይዘሮ ደብሪቱ ከበደ በበኩላቸው በጤና ተቋማት ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲዘምን እና የጤና መረጃ ስርዓቱን ተደራሽነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የቢሮው የJSI/DUP የዲጅታል ጤና ቴክኒካል ስፔሻሊስት የሆኑት አቶ አየለ ሐይሉ ጤና ተቋማት ጥራቱን የጠበቀ የመረጃ ስርዓት እንዲኖራቸው ግብዓትን ጨምሮ የአቅም ግንባታ እና የክህሎት ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

ባለፈው በጀት ዓመት በዘርፋ የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ ለማሳደግ እና በቀጣይ አስፈላጊውን ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ የታዩ ክፍተቶችን በአግባቡ በመለየት ውጤታማ ተግባር ለማከናወን በትኩረት እንደሚሰራ አቶ አየለ ተናግረዋል።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

20 Nov, 13:28


አዲስ አበባ በፈጣን የልማት ግስጋሴ ላይ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

20 Nov, 13:21


"ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት " በሚል መሪ ቃል 19ኛዉ የኢትዮጽያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ የጋራ መድረክ ተከያሄደ።

መድረኩ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትና በጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት በጋራ በመሆን በታላቅ ድምቀት አክብረዋል ።

በአሉን ያከበሩት ሁለቱ ምክር ቤቶች ህብረ ብሔራዊ ፌደራል ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሃሳቦች በሚል በጋራ በተዘጋጀ መድረክ የፓናል ዉይይት ጭምር በማቅረብ መድረኩን በድምቀት አከናውነዋል።

በበዓሉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ እና የሸገር ከተማ ምክር ቤት አፈጉባዔዎች አባላት የሁለቱ እህትማማች ከተሞች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች አባገዳዎች፣ ሀደሲንቄዎች የሀይማኖት አባቶችና የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሁነዋል ።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እንደተናገሩት የዚህ ዝግጅት ዋና አላማዉ በብዙሃነት ላይ የተመሠረተ አንድነትን በማጠናከር ህብረ ብሔራዊነታችንን ማስቀጠል መሆነን ገልፀዉ የአዲስ አበበ እና የኦሮምያ ክልል ሸገር ከተማ ህዝብን በማስተሳሰር ህብረ ብሔራዊ አንድነትን አጉልተዉ ያሳዩበትና መፃይ እድል ብሩህ መሆኑን ያበሰርንበት ዝግጅት ነዉ ብለዋል።

ይህ ታላቅ በዓል በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ እንደሚገኝ የጠቆሙት አፈጉባዔዋ የዛሬዉ በዓል የእህትማማቸነትና እና የወንድማማችነት የህዝብ ለህዝብ የፖናል ዉይይት መድረክ መሆኑና ለሀገራችን የፌደራል ስርዓት ግንባታ እንቅስቃሴ ላይ ህዝብ የማይተካ ሚና ስላለዉ የጋራ ግንዛቤ ፈጥረን ህብረብሔራዊ አንድነታችን ላይ መሠረት የሚጥል ነዉ ብለዋል።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

20 Nov, 04:28


ኤች አይ ቪን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሚደረገው ሂደት ኤች አይ ቪ በደማቸው የሚገኝ ማህበራት ሚና ከፍተኛ ነው።

አ/አ / ጤና ቢሮ ህዳር 11/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኤች አይ ቪን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዘር-ብዙ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በተለይ ኤች አይ ቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች  የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል እና ተጽኖውን ለመቀነስ  በሚሰሩ ተግባራት  የማህበራቱ ሚና ከፍተኛ ነው።

ቢሮው በአዲስ አበባ ከሚገኙ ኤች አይ ቪ በደማቸው የሚገኝባቸው  ማህበራት ጥምረት ጋር ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱ ኤች አይ ቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ህክምናቸውን በአግባቡ በመከታተል እና ስርጭቱን በመቀነስ  ጤናማ ህይወት እንዲኖሩና  ሌሎች ግንዛቤ በመፍጠር የበኩላቸውን ድርሻ  ማድረሻ እንዲወጡ  ያስችላል ሲሉ  በቢሮው የኤች አይ ቪ ተፅዕኖ ቅነሳ ቡድን መሪ አቶ የማነ ገብረመስቀል ገልፀዋል።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

19 Nov, 13:07


በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዉስጥ ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች አንዱ የሆነዉ ሰርጢ ጤና ጣቢያ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ /ወረቀት አልባ/ አደረገ።

አ/አ ጤና ቢሮ ህዳር 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዉ በስሩ የሚገኙ ጤና ተቋማቶች ሙሉ በሙሉ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ/ወረቀት አልባ /ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል

በዛሬዉ እለትም ሰርጢ ጤና ጣቢያ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ / ወረቀት አልባ አድርጓል።

በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአቃቂ ቃሊቲ ጤና ፅፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ አዕምሮ ጥላሁን እንደገለፁት መንግስት የጤና አገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማሻሻል በርካታ የጤና ፓሊሲዎችና አቅጣጫዋችን ማስቀመጡን ገልፀዉ ይህም ተግባራዊ መደረጉ በተገልጋዩ ማህበረሰብ ላይ እርካታን እያስገኘ ይገኛል ብለዋል።

ወይዘሮ አዕምሮ አክለዉም በክፍለ ከተማዉ ስር ከሚገኙ 7 ጤና ጣቢያዎች 5 ወረቀት አልባ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ገልፀዉ በተጨማሪም ከነዚህ ጤና ተቋማት ዉስጥ የቀዶ ህክምና ማዋለድ አገልግሎት ከሚሰጡ 3 ጤና ጣቢያዎች አንዱ ሰርጢ ጤና ጣቢያ በመሆኑ ይህንን አገልግሎት ይበልጥ ለማሻሻልና ከከተማዋ ለዉጥ ጋር አብሮ የሚሄድ ዘመናዊና ከተማዋን የሚመጥን የጤና አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰሩ እንደሚገኝ ገልፀዉ በቀጣይም ይህንን አገልግሎት በተቀሩት ጤና ጣቢያዎች ላይ ለማስጀመር በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀዋስ አስፋዉ በበኩላቸው ጤና ጣቢያው እያከናወነ ያለዉ ተግባር አበረታች እንደሆነ ገልፀዉ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ወረዳው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የጤና ጣቢያው ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ቶፊቅ ባበንጋ ጤና ጣቢያው ዲጂታል /ወረቀት አልባ/ የጤና አገልግሎት ከማስጀመሩ ባሻገር ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ስፔሻሊስት ሀኪሞችን በመመደብ በሳምንት 2ቀን በቀን 40 ለሚሆኑ ታካሚዎች የቆዳ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

ከዚህም በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በተሰጣቸዉ ማሽን የዴንታል ስፔሻሊቲ(የጥርስ ህክምና ) ለመስጠት ዝግጅታቸዉን መጨረሳቸዉንና በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አቶ ቶፊቅ ገልጸው ቢሮዉ እያደረገላቸዉ ላለዉም ድጋፍ አመስግነዋል።

የጡሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳሬክተር ዶክተር ሳምሶን ጉዱ ሰርጢ ጤና ጣቢያ ከሆስፒታል ባልተናነሰ በርካታ ተግባራትን እያከናወና እንደሚገኝ እና ይህም ሆስፒታሎች ላይ ያለዉን ጫና በመቀነስ የህብረተሰቡን እንግልት እንደሚቀንስ ገልፀዉ ሆስፒታሉም ከጤና ጣቢያዎች ጋር ያለዉን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ።

በዕለቱ ጤና ጣቢያው እያከናወነ ላለው ውጤታማ ተግባር አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና እና ምስጋና ሰርተፍኬት የተሰጠ ሲሆን በእለቱ ለወለዱ እናቶችም ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

12 Nov, 03:31


የወርቃማው ሰኞ የስራ እና የህይወት ተሞክሮ ልምድ ልውውጥ ተካሂዷል።

አ /አ ጤና ቢሮ ህዳር/ 2/2017ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማት እና አስተዳደር ኤጄንሲ አመራሮች እና ሰራተኞች ዘወትር ሰኞ ጠዋት የሚያካሂዱትን የስራ እና የህይወት ተሞክሮ ልውውጥ ዛሬም አጠናክረው ቀጥለዋል።

በፕሮግራሙ ለይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አማካሪ ወይዘሮ ብርቱካን አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ሁለሰ ጊዜ ሰኞ ሰራተኛው ሳምንቱን በተሻለና በተነቃቃ ስሜት ስራን ለማከናወን የተለያዩ ተሞክሮዎችና ልምድ የምንለዋወጥበት እና ልምዱን በመውሰድ ለተገልጋዩ ማህበረሰብ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥላል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በቢሮ የስነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መስፍን ሽመልስ የስነ-አዕምሮ ውቅር/Mind SET/ ላይ ያላቸውን ልምድ አካፍለዋል ፡፡

በጎ አስተሳሰብ ለራስ፣ለቤተሰብ ብሎም ለሀገር ሰላምና ህልውና አወንታዊ ተፅእኖ ያለው በመሆኑ ሁሉም ሰው ተግባራዊ ቢያደርገው የሚያተርፍበት መሆኑን ልምድ አካፍለዋል፡፡

በተቋማችን በየትኛውም ደረጃ በተሰማራንበት የስራ መደብ በቀናነትና በሀቀኝነት መንፈስ በመስራት ለትውልድ የሚጠቅም ተግባር በማበርከት ሁለንተናዊ እድገትን ማረጋጥ እንደሚገባ አቶ መስፍን ልመምድ አካፍለዋል፡፡

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

02 Nov, 17:55


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የ4 አቅመደከማ አባወራ/ እማወራ ቤቶችን እድሳት ለማድረግ አስጀምሯል ።

አከ ጤና ቢሮ ጥቅምት 23/2017 ዓም

እድሳቱን ያስ ጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ወንድሙ ቢሮው በክረምት መርሀ ግብሩ ለህብረተሰቡ የተለያዩ ተግባራትን መስራቱን ገልፀው ባለፉት አመታት ለቢሮው ተጠሪ የሆኑ ተቋማት አመራሩ እና ሰራተኛው ከወር ደመወዙ ባዋጣዉ ገንዘብ የ27 አቅመ ደካማ አባወራና እማወራ ቤቶችን በማደስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

ይህንን መሰል ሰውተኮር የሆኑ ተግባራት በቢሮውና ለቢሮው ተጠሪ በሆኑ ተቋማት በጀት አመት 13 የአቅመ ደካማ ቤቶችን እያደሰ መሆኑን የገለጹት አቶ አለማየሁ አነዚህ እና ዛሬ የተጀመሩ ቤቶች ደረጃውን የጠበቀ ሙሉ እድሳት በማድረግና ባጭር ጊዜ ተጠናቀው ለነዋሪዎቹ እንደሚያረከብ እና መሰል ተግባራት ተጠናክረው እንደሚሰሩም ተናግረዋል ።

በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል ተረክበ በበኩላቸዉ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እያደረገ የሚገኘዉ በጎ ስራ የሚበረታታ ሰብዓዊ ተግባር እነደሆነ እና እድሳት የሚደረግላቸውን ግለሰቦች በተገቢዉ መንገድ በመለየት በስራቸዉ በርካታ ቤተሰቦችን የያዙ በመሆናቸዉ የብዙዎች ጫና የሚቀንስ እንደሆነም ተናግረዋል ።

እድሳቱ ከሚደረገላቸ መካከል አንድ እናት ቤቱ በማርጀቱና በላያቸው ላይ በመፍረሱ ለዝናብ ፣ ብርድ እና ለከፋ ተያያዥ ለጤና ችግር መጋለጣቸውን ገልጸው እድሳቱን ለሚያደርጉላቸው ለጤና ቢሮ አመራርና ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

02 Nov, 13:26


የማህጸን በር ካንሰር በሽታን ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተጠቆመ ።

አአ ጤና ቢሮ ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ከሚሰራቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል የእናቶችና ህጻናት ጤና ዋነኛው ነው ።

ቢሮ የማህጸን በር መከላከያ ክትባት እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ዓበት ለሚገኙ ታዳጊ ሴቶች ላይ በዘመቻ መልክ ለመስጠት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል ።

የማህጸን ካንሰር በወቅቱ ካልተከላከልነውና ካልታከመ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ሴቶችን ለከፍተኛ ህመምና ሞት የሚያደርስ በሽታ መሆኑን በውይይቱ ተመላክቷል ።

በሽታው ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ላይ በከፍተኛው በማጥቃት ላይ ያለና ይህንን ለመከላከል ከሚሰሩ ተግባራት መካከል እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ዓመት ላይ ያሉ ታዳጊ ሴቶች ክትባት መስጠት በመሆኑ ይህንን ተግባር በተለይ ከትምህት ቢሮ ጋር በመቀናጀት ለመስራት ውይይቱ በጋራ ተመርቷል ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ ህጻናት ክትባት ማግኘት መብታቸው በመሆኑና ትምህርት ቢሮም አንዱ ተልዕኮው ሁለንተናዊ ስብእናው የተሟላ ዜጋ ለመፍጠር ጤና ዋነኛው በመሆኑ በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራሩ ጉዳዩን በመያዝ ከወላጅ መምህራን ህብረት ጋር በማስተሳሰር ግንዛቤ በመፍጠር በትኩረት መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል ።

በክትባቱ በትምህርት ተቋማት ያሉ እድሜያቸው በዚህ ክልል ያሉ አንድም ህጻን ሳይከተብ እንዳይቀር እና ተግባሩን ውጤታማ እንዲሆን ከክፍለከተማ እስከ ትምህርት ቤት ያለው አመራር በባለቤትነት በመወስድ ተጠሪ /ፎካሎችን / በማዋቀር በመንግስት ትምህርት ቤት ፣ በመደበኛ እና በማታው ፕሮግራም ትምህርት ላይ ያሉት እንዲሁም በግል ተቋማት በሁሉም ደረጃ ያሉት ታዳጊዎች በሽታውን ለመከላከል የሚሰጠውን ክትባት እንዲወስዱ በኃላፊነት እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ስንዱ መኩሪያ በበኩላቸው የማህጸን በር ካንሰር በሽታ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው በሽታውን ለመከላከል ከሚሰራው ስራ መከላከያ ክትባት መስጠት አንዱና ዋነኛው ሲሆን ይህንንም እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ዓመት ያሉ ታዳጊ ሴቶችን ክትባት እንደሚሰጥ ገልጸው በዚህም ባለፈው አመት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመሰራቱ አፈጻጸሙ ውጤታማ እንደሆነ ተናግረዋል ።

ባለፈው አዓት ውጤታማ በሆነ መልኩ ከትምህርት ቢሮ ጋር በቅንጅት በመሰራቱ አመራሩ በወሰደው ከፍተኛ ድርሻ አፈጻጸሙ ስኬታማ መሆኑንም ገልጸዋል ።

በዚህ አመትም ጤና ቢሮ ተግባሩን በከተማው የሚገኙ ሴት ታዳጊዎችን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመከተብ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ስንዱ በዚህ እድሜ ክልል ያሉት ታዳጊዎች በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች ላይ ያሉ በመሆናቸው ክትባቱን መውሰድ ያለባቸው ታዳጊዎች እንዲከተቡ ሁሉም የትምህርት አመራሩ የድርሻውን በመወጣት የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎችን ጤና ለመጠበቅ በጋራ እንዲሰራ አሳስበዋል።

በውይይት መድረኩ የትምህርት ቢሮ እና የጤና ቢሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን ተግባሩን ውጤታማ ለማድረግ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

01 Nov, 07:32


የጡት ካንሰርን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

አአ ጤና ቢሮ ጥቅም 21/2017 ዓ.ም

የጥቅምት ወር በአለም አቀፋ ደረጃ በየአመቱ የጡት ካንሰር የሚያደርሰውን ህመም እና ሞት ለመከላከልና ለመቆጣጠር በበሽታው ዙሪያ የማህበረሰቡ ግንዛቤን ለማሳደግ የግንዛቤ፣ የምርመራና ህክምና አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ወር ነዉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በሀገር አቀፋ ደረጃ የሚከበረዉን የጥቅምት ወር የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘርን በአራዳ ክፋለ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ስር በሚገኘዉ በቸርችል ጤና ጣቢያ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፣ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተከብሯል።

በቢሮዉ የጤና ማጎልበትና በሽታ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ቢሳ ቢሮ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በርካታ ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዉ የጡት ካንሰር በሽታ በወቅቱ በሽታው ሳይሰራጭ ታካሚዎች ቶሎ ወደ ጤና ተቋም ለህክምና አለመምጣታቸዉ እና በህብረተሰቡ ዉስጥ ያለዉ ግንዛቤ ባለማደጉ በሽታውን አክሞ ለማዳን አስቸጋሪ እንደሚያደርገዉ ተናግረዋል።

የበዓለምአቀፍ ደረጃ የ2022 ሪፖርት እንደሚያሳየዉ በየአመቱ 2.3 ሚሊዮን ሰዎች በጡት ካንሰር በሽታ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን 666ሺህ 103 ሴቶች ደግሞ ህይወታቸውን በበሽታው እንዳጡ ያመለክታል ።

በሀገራችን በየአመቱ 16ሺህ 904 ሴቶች በጡት ካንሰር እንደሚያዙና 9ሺህ 626 የሚሆኑ ህይወታቸዉን በበሽታው እንደሚያጡ መረጃው ያመለክታል ።

የጡት ካንሰር በሽታ በወቅቱ ካልታከመ በገዳይነቱ ቅድሚውን ስፋራ የሚወስድ የካንሰር አይነት በመሆኑ ህብረተሰቡ አሳሳቢነቱን በመረዳት በየጊዜው ምርመራ በማድረግ እና ህክምናውን በመውሰድ መከላከል እንደሚገባ አቶ ጌቱ አክለዉ ገልፀዋል፡፡

የአራዳ ክፋለ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ ጌታቸው በበኩላቸው ህብረተሰቡ በጡት ካንሰር ላይ ያለዉ ግንዛቤ ለማሳደግ በርካታ ስራዎች መከናወናቸዉን ገልፀዉ የጡት ካንሰር እያደረሰ ያለዉን ጉዳት ለመቀነስ በየደረጃዉ ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል ።

ጡትን በእጅ በመዳሰስ እና በመመርመር የጡት ካንሰርን ቀድሞ መለየትና መከላከል ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ እና ይህ ዘዴ ጡታችን ላይ ለዉጦችን ስናስተውል ወደ ሕክምና ተቋማት በመሄድ ተጨማሪ ምርመራ በማድረግ ውጤታማ ህክምናን ለማግኘት እንደሚረዳ ተመልክቷል ።

በእለቱ ንጋት የጡት ካንሰርን ለመከላከል የሚሰራ ማህበር አባላት የሆኑ እና የጡት ካንሰርን በወቅቱ ታክመው የዳኑ ቀድሞ ወደጤና ተቋም ሄዶ ምርመራ ማድረግ ህይወትን መታደግ እንደሚቻ ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን በእለቱ የተለያዩ አጋር አካላ እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተው መልእክታቸዉ አስተላልፈዋል።

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

31 Oct, 18:55


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ሰልጣኝ አመራሮች ደም ለግሰዋል፡፡

አ/አ/ጤና ቢሮ ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአድዋ ሙዚየም የሚሰለጥኑ አመራሮች በስልጠና ቦታው ጊዜያዊ የህክምና ክሊኒክ በማቋቋም በሁለቱም ዙር የህክምና አገልግሎት መስጠት ችሏል፡፡

ቢሮው ለአመራሮቹ የደም ግፊት ፣ የስኳር ፣ የዓይን ፣ የጥርስ እና ሌሎች ህክምና አይነቶችን መስጠት መቻሉን እና ከጊዜዊ ክሊኒ በተጨማሪ ሪፈራል አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ወደ ሆስፒታል በመላክ ምርመራ እና ህከምና መስጠት መቻሉን የቢሮው የሜዲካል ሰርቪስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ሰልጣኞቹ በስልጠናው መጨረሻ ለወገን በማሰብ በዋጋ የማይተመነውን ውድ ስጦታ ደም በመለገስ የተሳተፉ ሲሆን በዚህም 127 ዩኒት ደም መለገስ በመቻላቸው ሰብዓዊነት የታየበት መልካም ተግባር መሆኑን አቶ መልካሙ ተናግረዋል ፡፡

ቢሮው አገልግሎቱን ለመስጠት አስፈላጊውን ባለሞያ ፣ የህክምና ግብዓት ፣ አምቡላስ እና ተንቀሳሰቃሽ ክሊኒክ በማሟላት የህክምና አገልግሎት መስጠት መቻሉን የጠቀሱት አቶ መልካሙ ከመደበኛው የህክምና አገልግሎት ባለፈ በሃገራዊ እና ከተማ አቀፍ ሁነቶችን በማስመልከት የጤና አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነም አያይዘው ገልጸዋል፡፡

Addis Ababa City Administration Health Bureau / የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ / AACAHB /

30 Oct, 11:34


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች ፣ ወጣቶች ፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የስራ ምልከታ አድርጓል።

አ/አ/ ጤና ቢሮ ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም

ቋሚ ኮሚቴው የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን ምክንያት በማድረግ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የተከናወኑ ተግባራትን ምልከታ አድርገዋል።

ቢሮው በበጀት አመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል ለምክር ቤት አባሉ ሪፖርት ቀርቧል ።
በዚህም ቢሮው ዲጂታል የጤና አገልግሎትከማስፋፋት ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ከማጠናከር ፣ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ፣ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ፣ በእናቶች እና ህፃናት ጤና ፣ በበሽታ መከላከል ፣ በአስተኝቶ እና በተመላላሽ ህክምና አገልግሎት ፣ በመድሃኒት አቅርቦት እና አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥ የተሰሩ ስራዎች አፈጻፀም ከጊዜ ወደጊዜ መሻሻሉን ቋሚ ኮሚቴው አባላት መመልከታቸውን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች ፣ ወጣቶች ፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩር ቢሮው የህብረሰቡን የጤና አገልግሎት ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ - ብዙ እና ውጤታማ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀው በተለይ በየደረጃው ካለው መዋቅር እና ባለድርሻ አካላት ላይ ከእቅድ ጀምሮ ተሳስሮ መሠራቱን ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮ ሊሆን የሚችል መሆኑን ተናግረዋል ።

እነዚህን ተግባራት በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የገለጹት ክብርት ወይዘሮ ዘይነባ ከአገልግሎት አሰጣጥ እና ከመድሃኒት አቅርቦት የህክምና መሳሪያዎች አልትራሳውድ እና ራጅ አገልግሎቶች ላይ ያለውን የአገልግሎት ውስንነት የባለሙያ ስነምግባር ወርዶ በመፈተሽ መሰራት እንዳለበት አመላክተዋል።

በበጀት ዓመቱ እንደ ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጥ ልዩ ትይኩረት ተሰጥቶት እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት ክብርት ወይዘሮ ዘይነባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮም ይህንን ታሳቢ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ሰራዎች እና ለውጦችን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ቋሚ ኮሚቴው በቢሮ ላደረገው ምልከታ ምስጋናቸውን አቅርበው ምክርቤቱ ላነሷቸው በጤና ተቋማትና በቢሮ ደረጃ የታዩ ጠንካራ ስራዎችን በመውሰድ ያሉ ውስንነቶችን በቀጣይ በመለየት እና በማስተካከል ውጤታማ ስራ ለማከናወን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀዋል።

በ2017 በጀት ዓመት ቢሮው በትኩረት ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል የህክምና አገልግሎቱን በማዘመን ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት መሆኑን የገለጹት ዶክተር ዮሐንስ እንደከተማ የጤናተደራሽነት ላይ አለማቀፍና የጤና ሚኒስቴር ካስቀመጣቸው መስፈርት ማሳካት መቻሉንና ከፍትሀዊነት አንጻር ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብ አዳዲስ የጤናተቋማት ግንባታ እና የነባር ተቋማት ማስፋፊያ እየተከናወነ ሲሆን እነዚህን በማጠናቀቅ አገልግሎቱን ፍትሀዊ በሆነ ለማዳረስ ከማስቻሉም በላይ ከተማዋን የሚመጥንና የጤና ቱሪዝም መዓከል ለማድረግ ለሚሰራው ስራ ትልቅ አስተዋጽኦ እንሚበረክት ገልፀዋል።

ቢሮው የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተግባሩን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የተሰጡ አስተያየቶችን በመውሰድ እከታች በመውረድና በመደገፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።)