"ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወደ መርከብ ገባ።
ዘፍጥረት 7:7
በኖህ ዘመን ሰዎች በሀጢያታቸው ምክንያት እግዚአብሔርን ስላሳዘኑ በውሃ ሊያጠፋቸው ባሰበ ጊዜ እግዚአብሔር ኖህን መርክብን ስራ አለው በዚያም ኖህ እና የኖህ ቤተሰብ እንዲሁም ከየእንስሳቱ ወገን ሁሉ ሁለት ሁለት አድርጎ በኖህ መርከብ ውስጥ በማስገባት የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ እግዚአብሔር አዳናቸው ::
ዛሬም በእኛ ዘመን በዚህ አስከፊ እና ከባድ ጊዜ ሰዎች በሀጢያታቸው ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር በተጣሉበት ወቅት ከጥፋት : ከሞት : ከሲኦል ማምለጥ የሚቻለው በኢየሱስ ነው ::
ስለዚህ የዚህ ዘመን ማምለጫ መርከብ ጌታችን ኢየሱስ ነው ::
ሰላም የኔዎች እንደሚታወቀው ይህ ሳምንት Gospel Week ነው ስለሆነም ሁላችንም ይሄንን ምስል Profile picture , Share በማድረግ እንዲሁም #መርከቡ_ኢየሱስ_ነው የሚል ፅሁፍ እጃችን ላይ በመፃፍ ፎቶ በመነሳት post በማድረግ ማምለጫ መርከብ የሆነውን #ኢየሱስን እንድንሰብክ ጥሪ እናቀርባለን ::
ተባረኩ
#የተልዕኮ_አስተማባሪዎች
#yenefellow
#vlm