AAU - Muslim Students Union @aaumsu Channel on Telegram

AAU - Muslim Students Union

@aaumsu


This is the official channel of AAU-MSU.

Email: [email protected]
Telegram: @aaumsu
Group: @aaumsu_discussion
Twitter: twitter.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

AAU - Muslim Students Union (English)

Are you a Muslim student looking to connect with like-minded individuals and engage in meaningful discussions? Look no further than AAU - Muslim Students Union! This channel serves as the official platform for AAU-MSU, where students from all backgrounds come together to share ideas, resources, and support.

By joining AAU-MSU, you gain access to a vibrant community that is dedicated to promoting unity, diversity, and understanding among Muslim students. Whether you're looking for study groups, networking opportunities, or simply a space to share your thoughts, AAU-MSU has you covered.

Want to stay updated on the latest events and initiatives from AAU-MSU? Make sure to follow us on our various social media platforms:

Email: [email protected]
Telegram: @aaumsu
Group: @aaumsu_discussion
Twitter: twitter.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Join AAU - Muslim Students Union today and be a part of a supportive community that values your voice and contributions. We look forward to connecting with you!

AAU - Muslim Students Union

22 Nov, 04:10


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)

"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)

اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

21 Nov, 05:07


ምዝገባው ተጠናቋል። የተመዝገባችሁ ሁሉ ትምህርቱ ኢንሻላህ በቅርቡ የሚጀመር ይሆናል።

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

20 Nov, 14:38


በ አዲስ አበባ ዩኒቨረስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የ6ኪሎ ጀመዓ አሚር የሆነው ወንድማችን  ኢስማዒል  አብዱሮ በሲራራ አዋርድ የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ለመወዳደር ሀሳቡን አቅርቧል::

እና ሁላችሁም ከታች ባለው link በመግባት ሀሳቡን አይታችሁ በሒጅራ ባንክ የኮሜንት ሳጥን ላይ ላይክ ታደርጉ እና አስተያየት ትሰጡ ዘንድ ጋበዝኳችሁ!👇

Obboleessi keenya Amiirri Jama'aa Barattoota Musliima Yunivarsiitii Finfinnee Campus 6-kilo baankii hijraa irratti dorgommii business plan dorgomaa jira waan ta’eef fuula Facebook hijra bank link armaan gadii kanaan seenuun comment isaa like akka gootan isin affeera.

👇👇👇👇 like his comment.

https://www.facebook.com/share/p/6DT5WApuMg12fG5K/

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

19 Nov, 14:14


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ከነሲሓ አካዳሚ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የተከታታይ የሸሪዓ ትምህርት ምዝገባ ነገ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ያልተመዘገባችሁ ወንድሞችና እህቶች አሁንም እድሉ ስላለ መመዝገብ ትችላላችሁ!!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

19 Nov, 14:12


وَقُلِ ٱعْمَلُوا۟ فَسَيَرَى ٱللَّهُ عَمَلَكُمْ وَرَسُولُهُۥ وَٱلْمُؤْمِنُونَ ۖ وَسَتُرَدُّونَ إِلَىٰ عَـٰلِمِ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَـٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Tell ˹them, O  Prophet˺, “Do as you will. Your deeds will be observed by Allah, His Messenger, and the believers. And you will be returned to the Knower of the seen and unseen, then He will inform you of what you used to do.”

በላቸውም ሥሩ አላህ ሠራችሁን በእርግጥ ያያልና፡፡ መልክተኛውና ምእምናንም (እንደዚሁ ያያሉ)፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ ዐዋቂ ወደ ኾነውም (አላህ) በእርግጥ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡

“Hojjadhaa; Rabbiin, ergamaan Isaatiifi mu’uminoonnis fuula dura dalagaa keessan ni argu. Gara beekaa wantoota hin mul’anneefi wantoota mul’ataniis fuula dura ni deebitu. Waan isin dalagaa turtanis isinitti odeessa” jedhi.

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

16 Nov, 15:27


በአዲሱ የAAU ተማሪዎች ዲሲፕሊን መመሪያ ዙሪያ የህብረቱ እንቅስቃሴ እና የዩኒቨርሲቲው አቋም!

የሙስሊም ተማሪዎችን መብት የሚረግጠው መመሪያ ከወጣ ጊዜ አንስቶ የአዲስ አበባ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ከተለያዩ አካላት ጋር በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ ለማምጣት ሰፊ እና ጥልቅ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል:: መጀመሪያ ላይ መመሪያው የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ረግጦ ተግባራዊ ሊደረግ በተሞከረበት እለት 6ኪሎ የነበሩ የጀመዓ ተወካዮች ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የዚያኔ አመራሮቹ እንደ ምክንያት የጠቀሱት "ሴኩላሪዝም!" የሚለውን ሰበብ ነበር::

ውይይቱ ያለመስማማት ተቋጭቶ የነበረ ሲሆን በ2ኛው ውይይት ላይ አመራሮቹ ሴኩላሪዝም የሚለውን ምክንያት ሙሉ ለሙሉ "ኒቃብ የደህንነት ስጋት ነው!" ወደሚል ቀየሩ:: ስብሰባው ላይ የነበሩ የህብረቱ ተወካዮች ኒቃብ የደህንነት ስጋት እንደማይሆን በምክንያት እና በማስረጃ ሙግት ሲያቀርቡ እዚያው በዚያው ያንን ምክንያት በመተው "ኒቃብ ክላስ ውስጥ በመምህሩ እና በተማሪዋ መካከል የሚኖረውን መናበብ ያከብደዋል:: ኒቃብ የምትለብስ ተማሪ ሙሉ ለሙሉ መሳተፍ ይከብዳታል::" ወደሚል ቀየሩ:: ለዚህም ውሃ ለማይቋጥር ሰበብ የህብረቱ ተወካዮች አሳማኝ መልስ በማቅረባቸው ውይይቱ ያለስምምነት ተቋጭቶ የመጨረሻ መፍትሔ ለማምጣት ዩኒቨርሲቲውም ሆነ ህብረቱ የመፍትሔ ሀሳብ ይዘው እንዲመጡ ቀጠሮ ተያዘ::

በዚህም ውስጥ ህብረቱ ከአዲስ አበባ መጅሊስ ጋር በመወያየት የደህንነት ስጋት እና የተማሪዎችን ማንነት መለየት አይቻልም ለሚሉት ማሳበቢያዎች መጅሊሱ ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በጣት አሻራ የሚለይበትን ቴክኖሎጂ እንደሚያስገባ ዝግጁ መሆኑን ገልፆ ህብረቱ እንደመፍትሔ ሊያቀርብ በተያዘለት ቀጠሮ ዝግጁ ሆኖ ሳለ ዩኒቨርሲቲው የቀጠረውን ቀጠሮ አልወያይም በማለት ሰረዘ:: ከዚያም ቡሃላ ዩኒቨርሲቲው ያወጣውን መመሪያ ሁለት ጊዜ ያሻሻለ ሲሆን ምክንያት ከመቀያየር ውጭ መብታችንን የሚረግጡ ድንጋጌዎችን አላስተካከለም:: ህብረታችንም መፍትሔ ፍለጋ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከአዲስ አበባ እና ከፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር ውይይቶችን አድርጓል:: እንደ መፍትሔም በቅርቡ አጠቃላይ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ይሆናል::

በዚህ ውስጥ እኛ እንደ ሙስሊም ተማሪዎች የሃይማኖታችንን ድንጋጌ ተከትለን እየደረሰብን ያለውን የመብት ጭቆናና ረገጣ በሰላማዊ መንገድ ልንፈታ መጓዛችን ሰላም ወዳድ ከመሆናችን እንጅ ከፍርሃት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል:: በመብታችን በተለይም እምነት ሃይማኖታችንን አስታኮ በሚመጣ ጭቆና ፈፅሞ አንደራደርም:: ሃይማኖታችን የተፈጠርንበት ብሎም የምንኖርለት እና የምንሞትለት እንቁ የሁለት ሀገር ሀብታችን ነው:: የሚከፈለውን መስዋዕትነት ከፍለን መብታችንን እናስከብራለን:: መብታችንን ሊረግጡ የሚመጡ አካላትንም ተጠያቂ እንዲሆኑ እናደርጋለን::

ነፃነት በነፃ አይገኝም!

ጥያቄ አለን!!
መልስም እንፈልጋለን!!


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!!!!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

16 Nov, 03:12


የኢስላም ጥላቻ ወይስ የደህንነት ስጋት?

እነዚህ ከላይ የተያያዙት ሁለት ምስሎች በሁለት ሳምንት ውስጥ ሁለት ጊዜ ከተሻሻለው አዲሱ የተማሪዎች ዲሲፕሊን መመሪያ የተወሰዱ ናቸ።

የመጀመሪያው በጥቅምት 12፣ 2017 ዓ.ል ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት እንዲጸድቅ የቀረበው የተማሪዎች ዲስፕሊን መመሪያ ነው። በዚያም ላይ ኒቃብን "ከደህንነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ማንነትን ለመለየት ሲባልና ከፀጥታ ጋር በተገናኘ ምክንያት" በሚል ከለከለ።

ነገር ግን ጥቅምት 28፣ 2017 ዓ.ል (ከሁለት ሳምንት በኃላ) "ደህንነት" የምትለዋ ሰብብ ጊዜ ያለፈባት መሆኑን ሲረዱ የክልከላውን ምክንያት ወደ "መማር ማስተማርና አገልግሎት ጋር በተያያዘ" ወደሚል ተቀየረ።

ከዚህ በላይ የኢስላም ጥላቻ ምን አለ?!

ዩኒቨርሲቲው አላማውን ግልጽ አድርጓል፤ "ምክንያት ኖረም አልኖረም መብታችሁን እጋፋለሁ" ብሏል።

እኛም እንላለን፡-
#ጥያቄ_አለን #መልስም_እንፈልጋለን!!

መቼም ወደኃላ አንልም፤ መቼም እጅ አንሰጥም!!


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

16 Nov, 03:04


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሁንም በድጋሚ ጥቅምት 28 አዲሱን የተማሪዎች የስነምግባርና የዲሲፕሊን ደንብ ለሁለተኛ ጊዜ እንደገና ያሻሻለ ቢሆንም፤ አሁንም ግን የሙስሊም ተማሪዎችን ቅሬታና ጥያቄ ችላ በማለት የኒቃብና የጀመዓ ሰላትን አሁንም ከለክላለሁ እያለ ነው።

እኛም እንላለን፡-
#ጥያቄ_አለን #መልስም_እንፈልጋለን!!

መቼም ወደኃላ አንልም፤ መቼም እጅ አንሰጥም!!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

15 Nov, 03:06


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)

"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)

اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 18:53


ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ይገባውና የዛሬ የGrand Da'wa ፕሮግራም ደስ በሚል ሁኔታ ተካሂዷል። ምንም ቢሆን ከሰው ልጅ ስራ ጉድለት አይጠፋምና በፕሮግራሙ ላይ ያያችኃቸውን ጥሩም ይሁን መጥፎ ጎኖች ለወደፊት የተሻሉ ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ይጠቅሙናልና 2 ደቂቃ በመውሰድ ከታች ያለውን ፎርም እንድትሞሉ እንጋብዛለን።

link: https://forms.gle/o6Wa6QpMeLZJEtqu9

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 14:45


ታላቅ የምስራች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ስር ከሚገኘውና ከዚህ በፊት በሐገራችን የሸሪዓ በተለይም የተውሂድ እውቀትን በማስፋፋት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ከነበረው ነሲሃ አካዳሚ ጋር በመተባበር ልዩ የሆነ ተከታታይ የሸሪዓ ትምህርት እንዳዘጋጀ ሲገልፅ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው:: አጠቃላይ ትምህርቱ ለሶስት ወራት የሚቆይ ሲሆን የፊቂህ፣ ሀዲስ፣ አቂዳ እና ተጅዊድን የመሳሰሉ ወሳኝ እና ቁልፍ የሆኑ እስላማዊ የትምህርት ዘርፎችን አካቶ ይዟል።

አጠቃላይ ትምህርቱ በበይነ- መረብ (Online) የሚሰጥ ሲሆን ትምህርቱን በተገቢው ሁኔታ ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ከAAU ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት እና ከነሲሃ አካዳሚ የጋራ የምስክር ወረቀት የሚያገኙ ይሆናል።

ለመመዝገብ፡ https://forms.gle/3tfAJdYGjjx7i1p39

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት በ @Aaumuslimstudentsunion1 ያናግሩን።

የዚህ ልዩ የእውቀት ማዕድ ተቋዳሽ በመሆን እወቅትዎን ያሰፉ ዘንድ ጋበዝንዎ። ለሚወዱት ሁሉም በማጋራት ውዴታዎን ይግለፁ።

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 11:43


በአአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በተዘጋጀው Grand Da'wa - 1 ላይ የቀረበው ፓምፍሌት አማርኛ እና Afaan Oromoo

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 10:28


ማስታወሻ፡-
📌 ፓምፍሌቱ ላይ የቁርዓንና ሐዲስ ጥቅሶች ስላለው ቆሻሻ ቦታ አይጣልም!!

📌 Paamfileeticha irratti jechi Qur'aanaa fi hadiisaa waan jiruuf eddoo balfaa yookiin Xuraawaattii hin gatamu!!!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 09:18


الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات

ፕሮግራሙ ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል። ለፕሮግራሙ ስኬት የተረባረባችሁ ሁሉ የአአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ላቅ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።

ኢንሻላህ በሌሎች ተመሳሳይ ፕሮግራሞች የምንገናኝ ይሆናል።

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 08:49


ኡስታዝ ሙሐመድሐሰን ማሜ እጅግ ጥዑም የሆነ ዳዕዋ አድርገውልናል። አሁን ደግሞ ወንድም ሙስዓብ አጠር ያለ መልዕክት ለማስተላለፍ መድረኩን ይዟል።

https://youtube.com/live/WhJh8cjkRYQ?feature=share

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 07:49


ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ አጭር መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን አሁን ደግሞ ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ መድረኩን ተረክብዋል።

https://youtube.com/live/WhJh8cjkRYQ?feature=share

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 07:34


https://youtube.com/live/WhJh8cjkRYQ?feature=share

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 07:22


The program has started

https://www.youtube.com/live/xdQGGytx7ZQ?si=BFnbdvL9axrpAxgA

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 04:37


only 1 hour left....

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

10 Nov, 03:28


እግሮች ሁሉ ወደ አል-አቅሷ መስጂድ ያመራሉ

2 ሰዓታት ብቻ ቀሩ!!!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

09 Nov, 18:51


Assalaamu alaykum warahmatullaahi wabarakatuh.
Guyyaa Borii sanbata guddaa sa'aa 2:30 irraa kaasee hanga sea,6:00 tti turu saganttaa gorsa guddaa irraa argannu ustaazoota keenya jaalatamoofi kabajamoo ta'aniin qophaa'ee dhufaatii keenya qofa eegaa Jira.
Sagantichiis
1, Sheeka keenya abbaa keenya kanta'an gamttaa barattoota muslimaa university finfinnee wajjin yeroo dheeraa kanturan shee sa'iidiin gorsa abbummaa Kan nuuf dabarsaan yootahu.
Itti aansuun Sheeni keenya Kan gorsi isaanii dhagahamee hinquufamne ustaz Hasan maammeetiin Mataduree taqwallaah jedhu irratti gorsa Kan nuuf kennanu Taha Dhuma irrattis obboleessi keenya musab Ahmad itti aanaa gamttaa barattoota muslimaa university finfinnee kantureefii bara darbe medalia warqiitiin Kan eebbifame iccitii milkaaina Isaa Kan nuuf qoodu Taha.
Kanaaf wol argaa keenya Bor ganama masjiida aqsatti haagodhannu.barattoota Lideta,bishoftu,saferaselam,xuqur anbesaa irraa dhufaniif geejjibni qophaa'ee Jira.
Hafuu mitii barfachuunuu Nama gaabbisiisa.

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

09 Nov, 18:25


A few hours left....

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

09 Nov, 07:54


ቀጠሯችን ነገ እሁድ ከጧቱ 2:30 ነው!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የሚዘጋጀውና ለዚህ አመት የመጀመሪያ የሆነው ታላቁ የዳዕዋ ፕሮግራም ሊዘጋጅ የዛሬን ማለፍ ብቻ እየጠበቀ ነው:: ነገ እሁድ ከጧቱ 2:30 ጀምሮ ከታላላቅ እንግዶች ጋር ልዩ የሆነ ቆይታ አፍንጮ በር በሚገኘው አል- አቅሷ መስጂድ ይኖረናል:: በፕሮግራሙ ላይ ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ የመክፈቻ ምክር ያደርጋሉ:: ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ ሰፋ ያለ ሙሐደራ ያቀርባሉ:: ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በወርቅ ሜዳሊያ የተመረቀው ወንድም ሙስዓብ አህመድ የህይዎት ተሞክሮውን ያቀርባል:: ሌሎች አነቃቂና አስተማሪ ፕሮግራሞችም የሚኖሩን ይሆናል::

በሰዓቱ እንገኝ!
ላልሰሙት እናሰማ!!
ለሌችም share እናድርግ!!!


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

08 Nov, 11:52


2 ቀናት ብቻ ቀርተውታል!

በዚህ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰናዳው Grand Daewa program ሊካሄድ የ2 ቀናት እድሜ ብቻ ቀርቶታል። ፕሮግራሙ ለየት ብሎ የተዘጋጀ ሲሆን የ2017 ዓ.ል አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ከሲንየር ወንድም እህቶቻቸው ጋር ያገናኛል። "እንኳን በደህና መጣችሁ! እንኳንም በደህና ቆያችሁን!" በመባባል ውስጥ ከትልልቅ አሊሞችና ቱባ ልምድ ካላቸው ወንድሞች ምክር እውቀት እና ልምድ ይጋራሉ::

በግቢም ሆነ ከግቢ ውጭ ለሚኖረው ህይዎት ትልቅ ስንቅን ይሰጣልና ቀጠሯችንን ቀጠሯችሁ ታደርጉ ዘንድ ጋበዝን:: በመጪው እሁድ ከጧቱ 2:30 በአል- አቅሷ መስጅድ ሰብሰብ ብለን እንድመቅ::

ላልሰሙት እናሰማ!
ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ለሁሉም Share እናድርግ!!


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

08 Nov, 06:24


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)

"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)

اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

07 Nov, 12:15


3 ቀናት ብቻ ቀሩት!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የሚዘጋጀው ታላቁ የGrand ዳዕዋ ፕሮግራም ከታላላቅ እንግዶቹ ጋር ሊካሄድ 3 ቀናት ብቻ ቀርተውታል!!

ሁላችንም እንገኝ፣ እናሰራጭ

ቀን፡ እሁድ ኅዳር 01፤ 2017 ዓ.ል
ሰዓት፡ ከጠዋቱ 02፡30 - 06፡00
ቦታ፡ ስድስት ኪሎ፣ አል-አቅሷ መስጂድ

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

06 Nov, 06:56


🎉ልዩ የቅዳሜ እና እሁድ የበጋ ስልጠና በኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዳዕዋና ትምህርት ማህበር)🎉


    ኢሙዳት በየአመቱ በክረምት እና በበጋ ወቅት አጠቃላይ የንፅፅር እውቀት ብልፅግና ላይ የሚያተኩሩ ስልጠናዎችን ያለ ምንም ክፍያ በታዋቂ ኡስታዞች እና አሰልጣኞች በመስጠት ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ ይታወቃል።

በመሆኑም በዘንድሮ የበጋ ልዩ የሆነ ስልጠና በዋነኝነት ከዚህ ቀደም በማንኛውም ሁኔታ የንጽጽር ትምህርት መሰረት ያላቸውን እና በሃይማኖት ንጽጽር  ዘርፍ ለኢስላም መስራት የሚፈልጉ 2ኛ ደረጃ ት/ት ተማሪዎች፣ ለዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ  በተጨማሪም በማንኛውም ዘርፍ ላይ ያሉ ወጣቶችን ለይቶ ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል። 

    ስልጠናው የሚያጠነጥነው የንፅፅር እውቀት፣ ኢማንን ማጎልበት፣ የሊደርሽፕ ፣ አርት እና ኢስላማዊ ስልጣኔ፣ የማህበረሰባዊ አይዲዮሎጂዎች እና መሰል የወጣቶችን ንቃተ ሕሊናን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ስልጠናውም ቅዳሜ እና እሁድ ለግማሽ ቀን ከህዳር እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

    በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ትምህርቱን በቋሚነት መከታተል የምትችሉ ወጣቶች (ወንድ እና ሴት) ይህንን ቅፅ በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

🏢ኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊም ዳእዋና ትምህርት ማህበር)

🕹ፒያሳ

02:30-06:00LT

ለበለጠ መረጃ ☎️
0944078334
0945728270
                              ይደውሉ።

ማጋራት አይርሱ

🛑ያለን ቦታ ውስን ነው።

🎉የመመዝገቢያ Link👇

https://forms.gle/xuGxGbhnmtPzWdyd8

AAU - Muslim Students Union

05 Nov, 08:05


ታላቁ የዳዕዋ ፕሮግራም 5 ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል!

ሁላችንንም ከየካምፓሱ አሰባስቦ የወንድም እህትማማችነት ፍቅርን የሚያላብሰው Grand Daewa ፕሮግራም ደርሷል:: መለያችን የሆነው Grand ዳዕዋ ፕሮግራም ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል:: እንዋደድ እንቀራረብ እንማር እንማማር ዘንድ ከ5 ቀናት ቡሃላ በሚመጣውና በሚያሰባስበን ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ እናቅድ::

በፕሮግራሙ አባታችንና መካሪያችን ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ እንደሚገኙ እሙን ነው:: ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜም በጥዑም ዳዕዋቸው የፕሮግራማችን ድምቀት ይሆናሉ:: በወርቅ ሜዳሊያ አጊጦ የተመረቀው የቀድሞው የህብረታችን ም/አሚርም ስለ ስኬት ጉዞው የሚያስቃኘን ይሆናል:: ፈገግታን በመጫር እያስተማሩ ፍቅርን የሚዘሩ አነቃቂ ፕሮግራሞችም ተሰናድተዋል::

ስለሆነም በመጪው እሁድ እንገናኝ!
ቀጠሯችንን በአል-አቅሷ መስጂድ እናድርግ!
ከጧቱ 2:30 ስብስብ ብለን እምር ይበልብን!

ከሰፈረ-ሰላም: ልደታ: ጥቁር አንበሳ እና ቢሾፍቱ ለምትመጡ ወንድም እህቶች ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

03 Nov, 03:37


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድጋሚ ለሙስሊሙ ያለውን ንቀት አሳይቷል!!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ አዲሱን የተማሪዎች የስነምግባርና የዲሲፕሊን ደንብ እንደገና ያሻሻለ ቢሆንም፤ አሁንም ግን የሙስሊም ተማሪዎችን ቅሬታና ጥያቄ ችላ በማለት የኒቃብና የጀመዓ ሰላትን አሁንም ከለክላለሁ እያለ ነው።

እኛም እንላለን፡-
#ጥያቄ_አለን #መልስም_እንፈልጋለን!!

መቼም ወደኃላ አንልም፤ መቼም እጅ አንሰጥም!!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

02 Nov, 14:29


ታላቅ የዳዕዋና ሙሐደራ ፕሮግራም!

እነሆ ቀን ቀናትን ተክቶ የዚህ አመት የመጀመሪያው ታላቅ የዳዕዋ እና የአዲስ ገቢ ተማሪዎች አቀባበል ፕሮግራም (AAUMSU GRAND DA'WA - 1) ከተለያዩ ጣፋጭና ልዩ ትዝታን አሳርፈው ከሚያልፉ ፕሮግራሞችጋ ሊከናዎን ቀናት ብቻ ቀርተውታል:: በፕሮግራሙ

📌 አባታችን እና መካሪያችን የሆኑት ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ የእንኳን መጣችሁ መልዕክት ያስተላልፉልናል፤

📌 በጣፋጭ ዳዕዋቸውና ምክራቸው የምናውቃቸው ሸይኽ ሙሐመድሐሰን ማሜ "አሏህ መፍራት" በሚል ርዕስ ዳዕዋ ያደርጉልናል።

📌 የጀመዓችን ምክትል አሚርና በ2016 ዓ.ል የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የነበረው ወንድማችን ሙስዓብ አህመድ "በአካዳሚና ዲን እንዴት መላቅ እንችላለን?" በሚል ርዕስ ልምዱን ያካፍለናል።

ከፕሮግራም መቅረት አይደለም፤ ማርፈድ ያስቆጫል!!

ፕሮግራሙ:-
🗓 እሁድ ኅዳር 01/2017 ዓ.ል
🕌 6ኪሎ አፍንጮበር በሚገኘው ታላቁ አቅሷ መስጂድ ይካሄዳል::
2:30 ጀምሮ 6:00 ይጠናቀቃል::

🔺 ከሰፈረ-ሰላም፣ ቢሾፍቱ፣ ጥቁር አንበሳና ልደታ ለሚመጡ ተማሪዎች ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል::

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

01 Nov, 03:04


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)

"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)

اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

26 Oct, 11:18


⭐️⭐️ AAUMSU GRAND DA'WA & WELCOME PROGRAM ⭐️⭐️

COMING SOON...


💫 With big guests
💫 With big topics
💫 With big ideas


🚀 Stay tuned❗️❗️

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

26 Oct, 05:49


ዋ ኢስላማ!!!

የኛ ነገር ይገርማል! ያሳዝናልም!! ያስለቅሳልም!!!


ሁልጊዜም አጀንዳዎቻችን ለአንድ ሳምንት ብቻ ይቆያሉ፤ ከዚያም ይረሳሉ። የሙስሊሞች መብት ተገፈፈ ሲባል ለአንድ ሳምንት እንጮሃለን፤ ከዚያስ? የግል ጉዳይ እንድጂ የዲን ጉዳይ እስካይመስል ድረስ ይረሳል!! ይተዋል!! መብታቸው የተገፈፈው ወንድም እና እህቶችም ልባቸው ተሰብሮ ይቀራል። አዲስ አጀንዳ ሲመጣ ያም እንደዚሁ ይሆናል!!!!

ይህ አመት ከገባ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ምን እንደተፈጠረ እንመልከት፦

📌 ሸይኻ ፋጢማ የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት በሙስሊሞች ተሰርቶ ሳለ ግቢ ውስጥ አትሰግዱም፤ ሂጃብ ለብሳችሁ አትንቀሳቀሱም በማለት ተማሪዎቹን አባረረ፤ ሚዲያውም ለአንድ ሳምንት ጮኸ። ከዚያስ? ተረሳ፤ እህት እና ወንድሞቻችን ተባረው ቀሩ!!

📌 ይህንኑ ድክመታችንን የተገነዘበ የሚመስለው የትምህርት ቤቱ አመራር ምንም ሳያፍር የትምህርት ቤቱን ስም ቀየረ፤ እኛም ለአንድ ሰሞን ጮኸን ዝም አልን። እነሱም ቀጠሉና በሐገሪቱ ሐብት በሚተዳደር ቴለቭዥን ላይ በይፋ መለወጣቸውን አሳዩ፤ እኛም ዝም አልን!!!!

📌 ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ከዚህ በፊት ሲጠቀሙበት የነበረውን የካፌ በር በመዝጋትና ከሃይማኖታቸው የአመጋገብ ስርዓት ውጪ ሴቶች ከወንዶች ጋር ተቀላቅለው እንዲመገቡ አደረገ፤ የግቢውን በር መክፈቻና በዝጊያ ጧት 12:00 እና ከማታም 12:00 በማድረግ ተማሪዎች የሱብሂ: መግሪብ እና ኢሻዕ ሶላትን ከመስጂድ እንዳይሰግዱ ከለከለ፤ ከዚያም አልፎ ዶርም የሚሰግዱ ተማሪዎችን ማሳደድ ጀመረ፤ ይባስ ብሎም ተማሪዎች ችግራቸው እንዲፈታ በሰላማዊ መንገድ ሙከራ በሚያደርጉ ጊዜ በግቢው የሚገኙ የፀጥታ አካላት የተለያዩ ማስፈራሪያዎችንና ዛቻዎችን ማድረስ ጀመሩ። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም የሙስሊሙ ጉዳይ ይመለከተኛል ብሎ የተንቀሳቀሰ አካል የለም!!! ሁላችንም ጸጥ ረጭ!!!

📌 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኢሻዕ ሰላት ሰግደው ሊገቡ ሲሉ "ኒቃብ፣ ጀለብያ እና አማኢማ ለደህንነት ስጋት ናቸው" በማለት ኒቃብና ጀለብያ ለብሳችሁ አትገቡም አሉ፤ ተማሪዎችን በዱላ ለማስፈራራትና ለመበተን ሞከሩ። ይህ ሲሆን ግን አንድም ለተማሪዎች መብት ሊቆም የተነሳ አካል የለም!!!

📌 የኛው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "የደህንነት ስጋት" በማለት ኒቃብን ሊከለክል ሞክረ፤ ኒቃብ ለባሽ እህቶችን ለማዋከብ ሞክረ፤ ሁላችንም ለአንድ ሰሞን ጨኸን፤ ለጊዜው ጉዳዩ ረገበ፤ ከዚያም ሁላችንም ረሳነው፤ የኛን መተኛት አሰፍስፎ የሚጠብቅ አካል እንዳለ ዘነጋን!!!

📌 አሁን ደግሞ አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላለፉት ሶስት አመታት ኒቃብ ለብሰው ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎችን ወይ አውልቁ ወይ ትምህርት ቤት አትምጡ አለ፤ 11 የሚሆኑ እህቶችንም አባረረ፤ ነገር ግን ይህ ሁሉ ሆኖ ተማሪዎቹን ሊያግዝ ፈቃደኛ የሆነ ማንም አካል የለም፤ ሁሉም ወደኃላ መሸሽን መረጠ!!

እኒህ እንግዲህ ባለፉት ሁለት ወራት ከተከሰቱት የምናውቃቸው ብቻ ናቸው፤ የማያውቀውን ብንጨምር...

እስከመቼ ነው አጀንዳ ተቀባይ ሆነን የምንቀጥለው? እስከመች ነው የሙስሊሙን መብት እንዲያከብሩ የተቀመጡ አካላት በዝምታቸው የሚቀጥሉት?

አሁንማ የለመድንው ይመስላል!!! የመብታችንን መገፈፍ የተቀብልነው ይመስላል!!

ንቁ ያ ኡመተ ሙሐመድ!!!!


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

26 Oct, 03:16


Last Chance To APPLY!!!

ለስድስት ወራት የሚቆየው የዳሩል አርቀም የአመራርነት ስልጠና ፕሮጀክት ምዝገባ ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ ይቀረዋል።

🔻ለመመዝገብ ፡ ይህን ይጫኑ!

ዳሩል አርቀም የአመራርነት ፕሮጀክት

©6 Kilo Jemea

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

25 Oct, 03:01


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)

"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)

اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

22 Oct, 07:55


🎉ልዩ የቅድመ ትዳር ስልጠና በ 6 ኪሎ ጀመዓ!!!🎉🎉

አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ።

የ 6 ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ በአይነቱ ልዩ የሆነ የቅድመ ትዳር ስልጠና በ ኦንላይን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቅቆ ምዝገባ መጀመሩን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።

ትዳር የአላህ (ሱ.ወ) ስጦታ ነው። የፍጥረተ ዓለሙ አሰራርም ጭምር ነው። የብቁ ማሕበረሰብ ግንባታ ከስኬታማ ቤተሰብ ይጀምራልና ረጅሙን የህይወት ጉዟችንን ለማስዋብ ወጣቱ መሰል ስልጠናዎችን መውሰዱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም፦

📌 ትዳር ምንድን ነው?
📌 የጋብቻ ጥቅም ምን ይመስላል?
📌 ከትዳር በፊት ምን ዓይነት ዝግጅት ያስፈልጋል?
📌 በትዳር ውስጥ ሊገጥሙን የሚችሉ መሰናክሎች ምን ምን ናቸው? እንዴትስ እንወጣቸዋለን? ••• በሚሉትና በሌሎችም ንዑስ ርዕሶች ዙሪያ በዘርፉ የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች ባላችሁበት ሆናችሁ በኦንላይን ትሰለጥኑ ዘንድ ግብዣችንን እንካችሁ እንላለን። ይህንን ወሳኝ ስልጠና በመካፈል መጭው ህይወታችሁን ከአላህ ጋር ብሩህ ለማድረግ ተከታዩን የቦት ሊንክ በመጠቀም ተመዝገቡ። የስልጠናውን ሰዓት እና ሊንክ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ከምዝገባ በኋላ በውስጥ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

ከባባድ ውሳኔዎች ከእውቀት በኋላ መወሰናቸው ትርጉሙ ጥልቅ ነው!

ቅድመ ስልጠና የዳሰሳ ጥናት ቦት
።write your name and your Telegram username 👇👇👇
@skmsj_fb_bot

©️ 6 kilo Jeme'ah

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

22 Oct, 03:16


🗣🗣🗣አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ👋👋

ወድ የ4ኪሎ ግቢ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ እኚህ ከላይ የተዘረዘሩ መፅሀፍት በጀመዓችን የሚገኙ መፅሀፍት ናቸው። መፅሀፍትን የማንበብ ልምድ የአስተሳሰባችንን አድማስ ለማስፋት ከሚያገለግሉ ትልልቅ መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ ነው። እኚህን መፅሀፍት ለማንበብ የምትፈልጉ ተማሪዎች በ +251992546811 ወይም @AbuUsamaZeya1 ላይ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን
ለወንዶች በሰላት ጊዜያት እንዲሁም ለእህቶች ከመግሪብ እስከ ኢሻ ባለው ጊዜ ወይም በሴቶች ተወካዮች በኩል የሚደርሳቹ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

© 4 kilo Jeme'ah

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

21 Oct, 10:59


🗣Good News

📎The tejrid kitab will start today after magrib In shaa Allah

📎Those registered through the form will get their books then

👉Share it to your friends

© 5 kilo Jeme'ah

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

20 Oct, 17:50


🎉🎉 ታላቅ የምስራች ለ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች 🎉🎉

በ 6 ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ አነሳሽነት የሚካሄደው "የዳሩል-አርቀም የአመራርነት ስልጠና" ፕሮጀክት ለሁለተኛ ዙር የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።

ፕሮጀክቱ በመጀመሪያው ዙር ከተለያዩ ካምፓሶች የተውጣጡ 40 ገደማ ተማሪዎችን  ተቀብሎ ለስድስት ወራት ካሰለጠናቸው በኃላ በደማቁ ማስመረቁ ይታወሳል።

ይህ ሙስሊም ተማሪዎችን በያሉበት ዘርፍ መሪ እና ተጽእኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ ማስቻልን አላማው አድርጎ የተነሳው ፕሮጀክት ባለፈው ዙር የተመዘገቡ ስኬቶችን እና ለውጦችን በማየት ራሳቸውን ለመሪነት ብቁ ማድረግ ለሚፈልጉ ጥቂት ተማሪዎች በሮቹን በመክፈት አርሂቡ ይላችሗል።

ፕሮጀክቱ ዘርፈ ብዙ ስልጠናዎችን፣ ሙሃደራዎችን፣ የንፅፅር ትምህርቶችን፣የልምድ ልውውጥ መድረኮችን፣ የመጽሃፍ ዳሰሳዎችን እና የጉብኝት ፕሮግራሞችን የያዘ ሲሆን ሙስሊም ተማሪዎች ያላቸውን የመምራት አቅም እንዲያውቁና እንዲጠቀሙ ለማድረግ የታሰበ ነው።

በመሆኑም የዚህ ፕሮግራም አካል መሆን  የሚፈልግ ተማሪ የሚከተለውን ፎርም በጥንቃቄ በመሙላት ለሰልጣኝነት እንዲታጭ በአክብሮት እንጋብዛለን።

ለመመዝገብ click me

መልካም እድል!
ዳሩል አርቀም የአመራርነት ፕሮጀክት

© 6Kilo Jeme'ah


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

20 Oct, 05:43


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጀመረው ሙስሊም ተማሪዎችን ከሃይማኖታዊ እሴታቸው የማራቅ እና ሃይማኖታዊ መብታቸውንና ነፃነታቸውን የመንጠቅ እንቅስቃሴ መልኩንና ይዘቱን በመቀየር ሰሌላ ዩኒቨርሲቲ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲም ደርሷል:: ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የግቢው በር 12:00 የሚዘጋ በመሆኑ ከግቢ ወጥተው ሶላት መስገድ የማይችሉ ተማሪዎች ከግቢ ውስጥም ሆነው እንዳይሰግድ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገባቸው ነው:: ካፌም ላይ ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ በተቃራኒ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሃይማኖታቸው ከሚያዛቸው የአመጋገብ ስነ-ስርዓት ውጭ ተቀላቅለው እንዲመገቡ በመደረግ ላይ ነው::

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ኒቃብ: ጀለብያ: አማኢማ እና መሠል በእስልምና የሚታዘዙ አለባበሶችን "ለደህንነት ስጋት ስለሆነ መልበስ አትችሉም!" በማለት ተደጋጋሚ የሆነ ወከባ በማድረስ ላይ ይገኛሉ:: ተማሪዎችም "ከዚህ በፊት ስንለብስ የደህንነት ስጋት ሳንሆን ቀርቶ አሁን ምን ተገኝቶ ነው? ይህ ሃይማኖታዊ ግዴታችንና የዜግነት መብታችን ነው::" በማለት ስለ እስልምናቸውና የነፃነት መብታቸው ጥያቄያቸውን ለዩኒቨርሲቲው አቅርበዋል::

በአላህ ፈቃድ የሚያስፈልገው መስዋዕትነት ሁሉ ተከፍሎ በሁሉም ቦታ በየትኛውም ጊዜ መብታችን እንዲከበር ልንተጋ ግድ ይለናል:: ዛሬ እኛ እያለፍንበት ያለውን ሁኔታ ልጆቻችን እንዲኖሩት መፍቀድ የለብንም::

©️EHEMSU

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

20 Oct, 03:39


"አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡ " (አር-ረዕድ 11)

ኢብን ጀሪር አጥ-ጠበሪ ስለዚህች አንቀጽ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦
"ሰዎች እርስ በእርሳቸው በመበዳደልና አንዱ በአንዱ ላይ ድንበርን በማለፍ በነፍሶቻቸው ያለውን ኹኔታ እስከሚለውጡ ድረስ አላህ በነርሱ ዘንድ ያለውን በረከት እና ደህንነት በማንሳት አይለውጥም"

የአት-ተፍሲር አል-ወሲጥ ጸሐፊም እንዲህ ይላሉ፦
"ከዚያም አላህ -ጥራት ይገባውና - ከማይለወጡ ሱናዎቹ አንዱን ሲጠቅስ እንዲህ አለ፡- (በእርግጥ አላህ የሰዎችን ሁኔታ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር እስኪለውጡ ድረስ አይለውጥም) ማለትም ስዎች ራሳቸውን (ስራቸውን፤ ባህሪያቸውን ወዘተ...) ከታዛዥነት ወደ ወንጀል፤ ከቆንጆ ወደ አስቀያሚ፣ ከማስተካከል ወደ ማብላሸት እንስካልቀየሩ ድረስ አላህ - ክብር ለርሱ ይገባው - የሰዎችን ፀጋ፣ ድህንነት እና መልካም ሁኔታ ወደ ተፃራሪው አይለውጥም"

በእርግጥም ጌታችን እውነትን ተናግሯል፤ በሐገራችንም ሆነ በዓለም ላይ ሙስሊሙ ላይ ለሚደርሰው ግፍ የመጀመሪያው መንስዔዎች እኛው ራሳችን ነን!

ከአላህ ዲን ስንርቅ፤ ኃሳብችን ሁሉ ዱንያ ሲሆን፤ አላህ የዚህ ዑማ መገለጫ ያደረገውን በጥሩ ማዘዝን እና ከመጥፎ መከልከልን ስንተው አላህ ውርደትን አከናነበን!

አሁንም መፍትሄው አንድ እና አንድ ብቻ ነው፤ ወደ አላህ በንጹህ ተውባ መመለስ፤ በዲናችን ጉዳይ ላይ የአቅማችንን ያክል መሳተፍ፤ የእውቀት ሓለቃዎችን ማብዛት፤ በአላህ ዲን ጉዳይ እስከመጨረሻው መታገል ብቻ!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

19 Oct, 05:59


የ4ኪሎ ካምፓስ የ2017 ዓ.ል የመጀመሪያ ሴሚስተር ደርስ ፕርግራም

ሁሉም ደርሶች የሚሰጡት ኢኽላስ ህንጻ ምድር ቤት በሚገኘው የ4ኪሎ ተማሪዎች መስጂድ ነው። 4ኪሎ እና አካባቢው ያላችሁ ልጆች ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ ተጠቀሙበት

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

18 Oct, 12:27


ወሳኝ መልዕክት ከዛሬው የጁምዓ ኹጥባ

በሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

18 Oct, 03:17


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)

"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)

اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

17 Oct, 14:54


"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ድምጾቻችሁን ከነቢዩ ድምጽ በላይ ከፍ አታድርጉ፡፡ ከፊላችሁም ለከፊሉ እንደሚጮህ በንግግር ለርሱ አትጩሁ፡፡ እናንተ የማታውቁ ስትኾኑ ሥራዎቻችሁ እንዳይበላሹ (ተከልከሉ)፡፡" (አል-ሑጁራት 2)

ይህች አንቀጽ በወረደች ጊዜ ሳቢት ኢብን ቀይስ የሚባል ሰሃባ ጠንካራ ድምጽ ያለው በመሆኑ ይህች አንቀጽ በእርሱ ላይ የወረደች መሰለው፤ ሁለተኛም ድምጹ ከእርሳቸው ድምጽ ከፍ እንዳይል በመፍራት ነብዩን ላለማግኘት በቤቱ ውስጥ ራሱ ላይ ቀለፈ። የአሏህ መልዕክተኛም ከሰሃቦቻቸው መካከል ሲያጡት "ሳቢት የት ነው?" ብለው ጠየቁ። ሰሃቦችም የሆነውን ነገሯቸው፤ ነብዩም እንዲጠራ በማድረግ "ምስጉን ህይወትን በመኖር፤ ሸሂድ ሆኖ በመሞት ጀነት መግባት አያስደስትህምን?" አሉት። እርሱም "በአሏህ እና መልዕክተኛው ብስራት ተደስቻለሁ" አላቸው።

ሰሃቦች እንደዚህ ነበሩ፤ እነዚያ ብርቅ ትውልዶች አኽላቃቸው እንደዚህ ነበር። ከአሏህ ወቀሳ ሲመጣ ወደሌሎች ሳይሆን ወደራሳቸው ነበር የሚመለከቱት፤ ራሳቸውን ነበር የሚፈትሹት።

የኛስ ትውልድ? አሏህ ከጠበቀው በስተቀር አብዛኞቻችን ጀነት እንደምንገባ ከአሏህ መተማመኛ የተሰጠን እስኪመስል ድረስ የራሳችንን ዓይብ ትተን የሌሎችን ዓይብ በመከታተል ላይ ተጠምደናል፤ ራሳችንን ረስተን የሰዎችን ስራ መዛኝ ሆነናል!!!

عجبت لمن يبكى على موت غيره
دموعا ولا يبكى على موت قلبه دما
وأعجب من ذا أن يرى عيب غيره
عظيما وفى عينيه عن عيبه عمى

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

17 Oct, 03:16


"በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው የሚገሰፅበትን እድሜ አላቆየናችሁምን? አስጠንቃቂውም መጥቶላችኋል።" (ፋጢር 37)

አስጠንቃቂው በሚል በዚህ አንቀጽ የተጠቀሰው የዘምዶች ሞት መሆኑን ከፊል ሙፈሲሮች አብራርተዋል።

መች ይሁን የምንገሰጸው፤ መች ይሁን ወደአላህ ዲን የምንመለሰው፤ መች ይሁን ወደመስጂድ መሄድን የምናዝወትረው፤ መች ይሁን ዲናችንን በአግባቡ መማር የምንጀምረው?

ባለፈው አመት ብቻ ከዚሁ ከግቢያችን ተማሪዎች 6 ያህሉ ተራቸው ደርሶ ወደማይቀረው ቀጠሮ ሄደዋል፤ ያውም የተወሰኑት ያለምንም በሽታ ባላሰቡበትና ባልገመቱት አጋጣሚዎች።

ቀጣይ እኛ እንደማንሆን ምን ማረጋገጫ አለን? ወድ አላህ የምንመለስበት ጊዜ አልደረሰምን? አላህ ፊት ቆመን ዲኑን ለመርዳት ምን አደረክ ስንባል ምን ብለን ልንመልስ ነው?

"ከመካሪም ሞት ይበቃል!"

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

16 Oct, 13:34


አዲሱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጨቋኝ መመሪያ ከየት እስከ የት?

በነሐሴ 2016 ዓ.ል የወጣውና የሙስሊም ተማሪዎችን መሠረታዊ የአለባበስ ብሎም የአምልኮ ተግባራት ከሚከለክለው መመሪያ ጋር ተያይዞ ጀመዓችን የአአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አድርጓል:: መመሪያው የሴት ልጆችን ኒቃብ እንዲሁም የጀመዓ ሶላትንና የሶላት መስገጂያ ቦታ መጠየቅን በግልፅ የሚከለክል በመሆኑ የዩኒቨርሲቲው ሙስሊም ተማሪዎች እንደማይቀበሉት በተደጋጋሚ ገልፀዋል::

ይህንንም ተከትሎ እስካሁን ባለው ሂደት ህብረታችን የሙስሊም ተማሪዎችን ጥያቄ ከበታች አመራሮች እስከ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት አድርሷል:: ከፕሬዚዳንት ፅ/ቤት አመራሮች ጋር በተደረገ ውይይትም ዘላቂ መፍትሔ እስኪደረግ ድረስ ከለከልን ያሉትን ከለከልን ከማለታቸው በፊት ባለው ሁኔታ እንዲቀጥል ስምምነት ላይ የተደረሰ ቢሆንም ዘላቂ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ተይዞ የነበረውን ቀጠሮ ዩኒቨርሲቲው ባቀረባቸው ተቀባይነት በሌላቸው ምክንያቶች ሳቢያ ተሰርዞ መፍትሔ ሳይደረግለት ቀርቷል::

ሆኖም አሁንም ቢሆን ሙስሊሙ ተማሪ እንዲያውቅ የምንፈልገው ነገር ቢኖር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ኒቃብም ሆነ ሌሎች መሠረታዊ ሀይማኖታዊ መብቶችን በነፃነት መተግበር እንደምንችል ነው:: እነርሱ ከዚህ በፊት መመሪያ አውጥተው ሊከለክሉን ሲሞክሩ አልተቀበልናቸውም:: ዛሬም ቢሆን ከትላንት የተለየ ቀንም ሆነ ሁኔታ የለም:: ዛሬም ቢሆን ስለነፃነታችን የምንደራደርበት ምንም ምክንያት የለም:: ዛሬም ቢሆን መብታችንን ለእነርሱ ፍላጎት አሳልፈን አንሰጥም::

በእነርሱ በኩል የተለያዩ ምክንያቶችን ከመደርደር ባሻገር ነገሩ ተድበስብሶ እንዲቀር የተለያዩ መንገዶችን እየቀየሱ ነው:: ይህ የተለመደው አካሄዳቸው ሆኖ ሳለ ከእኛ በኩል መብታችንን የሚደፈጥጡ ድንጋጌዎች ከመመሪያው ተሰርዘው እስኪወጡ ድረስ መታገል ግድ ይለናል:: በዚህ ረገድ ህብረታችን መፍትሔ ለማምጣት ሲል ከተለያዩ አካላት ጋር በመነጋገር ላይ ነው:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ተማሪያችን ጉዳዩን ጉዳዬ ብሎ ሌት ተቀን ከማስታወስና ዱዓ ከማድረግ ባሻገር እህቶቹን በማበርታትና እርስ በዕርስ በመጠነካከር ይበረታ ዘንድ አደራ እንላለን::

ይህ የአላህ መንገድ ነው:: መንገዱም የፍትሕ የነፃነት እና የድል መንገድ ነው::

አአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት !

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

16 Oct, 11:04


"(እናንተ በአላህ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ!) በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት ምዕመናንን ያጋጠመ መከራ የመሰለ ሳይመጣባችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልዕክተኛውና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት 'የአላህ እርዳታ መቼ ነው?' እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ደረሰባቸው። ተርበደበዱም። አስተውሉ የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው ተባሉም።" (አል-በቀራህ 214)

ስኬትና ድል በቀላሉ ያለ ትግል አይገኙም፤ ጀነት በቀላሉ አትገኘም፤ መታገልና መታገስን ትጠይቃለች። አሏህን ምዕመና 'የአላህ እርዳታ መቼ ነው?' እስከሚሉ ድረስ ይፈትናቸዋል።

መብታችን ለማስከበር በምናደርገው ትግል ላይ ስኬት እንቀዳጅ ዘንድ ልክ ከኛ በፊት የነበሩት ምዕመናን እንዳደረጉት ሁሉ ወደአሏህ ልንመለስ ይገባል!

ስለእህትህ የኒቃብ መብት እየታገልክ ከአጅነብይ ጋር የምትጃጃል ከሆነ ነስር እንዴት ይመጣል?
ስለእህትህ የኒቃብ መብት እየታገልክ አሏህ ያዘዘክን የጀመዓ ሰላት የማትሰግድ ከሆነ ነስር ከየት ይመጣል?
ስለእህትህ የኒቃብ መብት እየታገልክ ስለዲንህ ምንም የማታውቅ ከሆንክ ነስር ከዬት ይመጣል?

ስለእህትሽ የኒቃብ መብት እየታገልሽ ከአጅነብይ ወንድ ጋር የምትጃጃይ ከሆነ ነስር እንዴት ይመጣል?
ስለእህትሽ የኒቃብ መብት እየታገልሽ እስልምና ለሴት ልጅ ያዘዘውን የአለባብሰ ስርዓት የማትከተይ ከሆነ ነስር እንዴት ይመጣል?
ስለእህትሽ የኒቃብ መብት እየታገልሽ የዲን እውቀት ለመማር ተነሳሽነት ከሌለሽ ነስር ከየት ይመጣል?


አሏህ የመጨረሻውን አሸናፊነት ለሙዕሚን ባሮቹ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል። ጥያቄው እኛ ከነዚያ ውስጥ ነን ወይ ነው!!!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

15 Oct, 14:28


የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሙስሊም ተማሪዎች ዙሪያ ባወጣው ጨቋኝ መመሪያ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል::

ጥያቄ አለን!!
መልስም እንፈልጋለን!!


@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

15 Oct, 13:48


የደርስ ማስታወቂያ!

የሰሂህ አል-ቡኻሪ ሙኽተሰር የሆነውን التجريد الصريح لأحاديث الجامع الصحيح ኪታብ እነሆ ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ በሸይኻችን ሸይኽ አብዱረሂም ሙሳ ለተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የሚጀመር ስለሆነ ሁላችንም የዚህ እድል ተጠቃሚ እንሁን!!!

ደርሱ የሚሰጥበት ቀን፡ ሰኞ፣ ማክሰኞ እና እሮብ
ሰዓት፡ ከመግሪብ እስከ ዒሻዕ
ቦታ፡ አል-አቅሷ መስጂድ

የምዝገባ ሊንክ፡ link

©️5Kilo Jama'ah

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

15 Oct, 11:33


Afaan Oromoo

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

15 Oct, 11:31


For fresh students, check out this info to know about the activities of our Jama'ah

©️6Kilo Jama'ah

Share it with others too

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

15 Oct, 07:11


«ሕዝቦቼም ሆይ! ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደርሱ ተጸጸቱ፡፡ ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና፡፡ ወደ ኃይላችሁም ኃይልን ይጨምርላችኋል፡፡ አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ፡፡» (ሑድ 52)

ጌታችን እውነትን ተናገረ!! በጠላቶቻችን ላይ ጉልበት ባጠረን ጊዜ፤ ምድርም ከስፋቷ ጋር በጠበበችን ጊዜ፤ የኢስላም ጠላቶች በኛ ላይ በተረባረቡ ጊዜ ወደ አሏህ ከመመለስ ውጪ ምንስ አማራጭ አለን?

ጌታችንም የምትለምኑኝና ወደእኔ የምትመለሱ ከሆነ "ወደ ኃይላችሁም ኃይልን ይጨምርላችኋል" በማለት ቃል ገባ፤ "በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?"

በበትግላችን ስኬት እንቀዳጅ ዘንድ ወደአሏህ በፀፀት እንመለስ፤ ምህረትን እና ድልን እንለምነው!!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

15 Oct, 05:28


ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:-

በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን ::

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል :: ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን ::
    
📌 AAU MUSLIM STUDENTS UNION - 0909524252

Main and FBE Campus
📌 ኢስማዒል አብዱሮ - Main campus - 0936906322
📌 አብዱረሂም አሚን  - FBE Campus - 0995477358

AAiT (5 Kilo) Campus
📌 ማህፉዝ ነጋሽ - AAIT - 0996220264

4 Kilo Campus
📌 ዘይድ ሳዲቅ - 4kilo - +251992546811
📌 መስዑድ ውበቱ - 4kilo - +251905877461

Sefere Selam Campus
📌 ሙሐመድአሚን - s.selam campus - 0917046439
📌 ኑር አወል - s.selam campus - ++251951044287

Ldeta Campus
📌ያህያ አባ ረሻድ - Ldeta Campus - 0965435476 or 0777435476
📌 አብዱልዓዚዝ ሙሄ - Ldeta Campus - 0909534342 or 0777534342

https://t.me/aaumsu

AAU - Muslim Students Union

14 Oct, 14:51


የጥንቃቄ መልዕክት!

"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው፡፡" (አስ-ሰፍ 8)

ነገ እና ከነገ ወዲያ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ግቢ ይገባሉ። በዚህም መሐል የግቢ ጥበቃዎች ልክ ከዚህ ቀደም ሲያደርጉ እንደነበረው ሙስሊም ተማሪዎችን በተለይም ኒቃብ ለባሽ እህቶችን አዲስ በመሆናቸው ለማዋከብ ይሞክራሉ።

ሁላችንም ይህ እንዳይሆን መከላከል አለብን፤ በየግቢያችን መግቢያ በሮች ላይም ይሁን ግቢ እህቶቻችን ላይ የሚደርስ ማንኛውንም በደል ህገ-ወጥ ነውና ልናስቆም ይገባል፤ መረጃ ልንይዝ ይገባል

ከዚህ በኋላ ነገሮችን በትዕግስት የምናልፍበት ምንም ምክንያት የለም፤ ማንም ይሁን ማን ተጠያቂ ይሆናል። በተለይ ተማሪዎችን የምትቀበሉ ወንድሞች እና እህቶች ነገሮችን በትኩረት መከታተል ላይ አደራ!!

@aaumsu

AAU - Muslim Students Union

14 Oct, 12:32


Niqab Update!!

ስለአዲሱ መመሪያ ዩኒቨርሲቲው ከህብረታችን ጋር ለዛሬ ይዞት የነበረውን ቀጠሮ አላከበረም:: ለቀጠሮው አለመከበርም የተለያዩ ተቀባይነት የሌላቸውን ምክንያቶች አስቀምጠዋል:: አሁንም ቢሆን በመብታችን እንደማንደራደር እየገለፅን አሁን ስላለው ነበራዊ ሁኔታና ስለቀጣዩ አቅጣጫችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን:: ሁላችሁም መረጃዎችን በንቃት ጠብቁ:: ዱዓም አድርጉ!

@aaumsu

4,654

subscribers

1,668

photos

77

videos