አባ መላ (Bejai Naiker Nerash) @abbamella Channel on Telegram

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

@abbamella


ኢንጂነር ፥ ነጋዴ ፥ ገበሬ Arts of all arts in the world,art of giving love to others.

"I am exited about past,live here and now and i dont want to worry about vaguely unknown future ".Its me.

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash) (Amharic)

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash) በአማርኛ በሚገኘው የታሪክ ቋንቋ በኢንጂነር ፥ ነጋዴ ፥ ገበሬ በአስተማሪ ለሁለት ሳይንስማዊት አዳዲስ መጽሐፍን በተመጣጠነ በተመና ዘመን በአሮጊት የሚኖረው ፍቺ መብታችንን መንገድም ልኳቸውን እንዳደረገ በእንደ ለር ተመሳሳይ እና ተለመደ ለህንፀቱ በአስተማሪ ታሪኩን ለማስገንባት እና ማጠናከር የሚሆኑ ሁሉ ብሎአል እንግዲህ ይህ ቦታ ራሳችንን እንቀርባለን። በእኔና አንተ አባ መላ (Bejai Naiker Nerash) ድህነት ላመ ብመስጎ ግን ምንም ባልታያችሁ ለእርዳታ አፍላጌ እና አስመልክተናል።

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

20 Jan, 16:26


https://www.facebook.com/share/12F3ZHTzxoG/

ተከፍቷል! ተጀምሯል!

41ኛው፣42ኛው፣43ኛው፣44ኛው እና 45ኛው ዙር የ mission 100k ነጻ የፍሬ ፈንድ።

1.ሃሣባችሁን ከ 220 ቃላት በታች ተጠቀሙ።

2.ሎጎ ሥሩ::በምትፈልጉት ቋንቋ ተጠቀሙ።

3.ለማህበረሠብ የሚጠቅም፣ህጋዊና ተቀባይነት ያለው ክሬዚ (ያበደ)ሃሣብ አምጡ።
(out of the box,disruptive ሃሣብ)

4.ለዚህ ዙር ባይጠቅምም ለመታየት ብዙ ሠው ቢለይካችሁ፣ቢኮምታችሁ ና አንዴ ከለጠፋችሁ በኋላ ባትነካኩት ይመረጣል።

5.civilized /ሥልጡን በሆነ መንገድ ዳኞችን ለመመሠጥ፣ገበያን ለመመሠጥ ሞክሩ።

ምክር ለደጋፊዎች።

👉ለውጥ የሚያመጣ ሃሣብን እንደግፍ፣እንምረጥ
👉ሃሣቦችን የተመረኮዘ እንጂ የእርዳታና የትውውቅ ምርጫ አታካሂዱ።

ዳኞቻችሁ
Nigussu Solomon
Hawlet Ahmed
Get Toughe Zer
Fitsum Atnafework Kidanemariam
Namoo Amboo Goole
Dechasa Angecha Tadesse

በርቱ!
~~

Banameera! Jalqabee jira!

Ergama marsaa 41ffaa, 42ffaa, 43ffaa, 44ffaa fi 45ffaa 100k free free fund.

1. Yaada kee jechoota 220 gadiitti fayyadami.

2. Asxaa Hundee: Afaan barbaadde fayyadami.

3. Yaada maraataa (maraataa) hawaasaaf faayidaa qabu, seera qabeessaa fi fudhatama qabu fidaa.
(sanduuqa keessaa bahee, yaada jeequmsaa)

4. Marsaa kanaaf yoo faayidaa hin qabne ta'ellee akka mul'atuuf namoota baay'eedhaan addaan baatee yoo ta'e gaariidha.

5.Qaroome / Abbootii murtii fi gabaa karaa tokkoon diriirsuuf yaaluu.

Gorsa deeggartootaaf.

👉Yaada jijjiirama fidu haa filannu
👉 Yaada irratti hundaa'uun gargaarsaa fi nama beektu hin filatin.

Abbootiin murtii keessan

Nigussu Solomon
Hawlet Ahmed
Get Toughe Zer
Fitsum Atnafework Kidanemariam
Namoo Amboo Goole
Dechasa Angecha Tadesse

Jabaadhaa!
~~

ተኸፊቱ! ጀሚሩ ኣሎ!

መበል 41፣ 42፣ 43፣ 44ን 45ን ዙር ተልእኾ 100k ነጻ ነጻ ገንዘብ።

1. ሓሳባትካ ብትሕቲ 220 ቃላት ተጠቐመሉ።

2. ሱር ሎጎ፡ ዝደለኻዮ ቋንቋ ተጠቐም።

3. ንሕብረተሰብ ዝጠቅም፡ ሕጋውን ቅቡልን ዝኾነ ዕቡድ (ዕቡድ) ሓሳብ ኣምጽኡ።
(ካብ ሳንዱቕ ወጻኢ፡ ምዝባዕ ሓሳብ)

4. ነዚ ዙር ዘይጠቅም እኳ እንተኾነ ብብዙሕ ሰብ ክትረአ እንተትፍለ ይሓይሽ።

5.ስልጡን / ብገለ መንገዲ ዳያኑን ዕዳጋን ክትምስርት ምፍታን።

ምኽሪ ንደገፍቲ።

👉ለውጢ ዘምፅእ ሓሳብ ንመረፅ
👉 ኣብ ሓሳብ ተመርኲስካ ሓገዝን ሌላን ኣይትምረጽ።

ደያኑኹም
Nigussu Solomon
Hawlet Ahmed
Get Toughe Zer
Fitsum Atnafework Kidanemariam
Namoo Amboo Goole
Dechasa Angecha Tadesse

ብርቱዕ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

18 Jan, 19:48


~~~~~~
Banameera! Dorgomuu!

35ffaa, 36ffaa, 37ffaa, 38ffaa & 39ffaa.... ergama 100k Free Free Fund.

Kalaqtoota daldalaa shaniif.

1. Yaada kee jechoota 64 qofaan ibsi Jechoota 64 ol caqasuun wal hin madaalu.

2. Asxaa uumuun Asxaa malee hin danda'amu.

3. Afaan kamiinuu ibsuu.

4. Yaada seera qabeessaa fi hojii hawaasa fayyadu qofatu dorgomaa ta’a.

5. Yaada maraataa tokko baafadhu.

6. Marsaa kana keessatti comment>= like qofaan. Marsaan itti aanu abbaa murtiitiin kan gaggeeffamu ta'a.

7. Yaadni kee bu'aa kan hin argamne yoo ta'e yaada daldalaa miti.

Irra deddeebi'ee yaaluuf carraa bal'aa ni qabaata.

Yaada hojii dorgommii malee yaadni biraa bakka hin jiru.

Seera dorgommii kabajuun bu’aa akka argamsiisu yeroo darberraa baranneerra.

Dorgommiin kun sa'aatii 48 kan turu ta'a.
yaada abbootii qabeenyaa keenya gara gabaatti haa jijjiirru!

"Dandeettii Keessa Keessan Cufame Hiiku".

Jabaadhaa!

~~~~~
ተኸፊቱ! ሙሉእ!

35th, 36th, 37th, 38th & 39th.... ተልእኾ 100k ነጻ ነጻ ገንዘብ።

ንሓሙሽተ ናይ ንግዲ መሃዝቲ።

1. ሓሳብካ ብ64 ቃላት ጥራይ ግለጽ ልዕሊ 64 ቃላት ምጥቃስ ኣይወዳደርን እዩ።

2. ኣርማ ምፍጣር ብዘይ ኣርማ ኣይከኣልን እዩ ዋላ ኣብ ወረቐት ክትስእሎ ኣለካ።

3. ብዝኾነ ቋንቋ ምግላፅ።

4. ንሕብረተሰብ ዝጠቅም ሕጋዊ ሓሳባትን ስራሕን ጥራሕ ተወዳዳሪ ክኸውን እዩ።

5. ዕቡድ ሓሳብ ኣምጽእ።

6. ኣብዚ ዙርያ ብ comment>= like ጥራይ። ዝቕጽል ዙርያ ብዳኛ ክካየድ እዩ።

7. ሓሳብካ መኽሰብ እንተዘይኮይኑ ናይ ንግዲ ሓሳብ ኣይኮነን።

ደጋጊሙ ክፍትን እኹል ዕድል ክረክብ እዩ።

ብዘይካ ተወዳዳሪ ስራሕ ዝብል ሓሳብ ካልእ ኣብ ግምት ዘእተወ ቦታ የለን።

ሕጊ ውድድር ምኽባር ውጽኢት ከም ዘምጽእ ካብ ሕሉፍ ተማሂርና ኢና።

እዚ ውድድር ን48 ሰዓታት ዝጸንሕ እዩ።
ናይ በዓል ሃፍቲ ኣተሓሳስባና ናብ ዕዳጋ ንቕይሮ!

"ውሽጣዊ ዝተዓጽወ ዓቕምኻ ምኽፋት"

ብርቱዕ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

18 Jan, 19:48


ተከፍቷል! ተወዳደሩ!

35ኛው, 36ኛው, 37ኛው, 38ኛው & 39ኛው.... mission 100k ነጻ የፍሬ ፈንድ ።

ለ አምሥት የባለ ሥራ ሃሣብ ፈጣሪዎች።

1.ሃሣባችሁን በ 64 ቃላት ብቻ ግለጹ።ከ64 ቃላት በላይ መጥቀሥ አያወዳድርም።

2.ሎጎ ሥሩ።ያለሎጎ አይቻልም።በእጃችሁ ወረቀት ላይም ቢሆን መሣል አለባችሁ።

3.በማንኛውም ቋንቋ ግለጹ።

4.ለማህበረሠብ የሚጠቅም ህጋዊ የሆነ ሃሣብና ሥራ ብቻ ተወዳዳሪ ያደርጋል።

5.ክሬዚ ሃሣብ አምጡ።

6.በዚህ ዙር በ comment>= like ብቻ ነው። በ judge የሚቀጥለው ዙር ይካሄዳል።

7.ሃሣባችሁ አትራፊ ካልሆነ የንግድ ሃሣብ አይደለም።

ደጋግሞ የሚሞክር ሠፊ እድል ይኖረዋል።

ከውድድር የሥራ ሃሣብ ውጪ ሌላ ሣሣቦች እዚህ ቦታ የለውም።

ከባለፈው የተማርነው የመወዳደሪያ ህግን ማክበር ወደ ውጤት ይመራናል።

ይህ ውድድር 48 ሠዓት ይቆያል።
let us change our entrepreneur mind set towards market!

"Unlock Your Inner Locked Capacity"

በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

27 Dec, 08:44


Congratulations Bejai Nerash Naiker for such an a humble win 🏆

10M

https://www.facebook.com/share/18USGizpbY/

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

23 Dec, 10:18


ተነሡ!
idea 0021/2017ዓ.ም።
ጎሥት ቃሪያ(ghost pepper )አምርቶ የበርበሬ መከላከያ ማምረት።

(ትላንት ምሽት አንድ የመንገድ መንታፊ የአንዲት ልጅን ቦርሣ ታግሎ ሢነጥቅ በማየቴ ይህንን አሥቤዋለሁ።ብዙዎቻችን ከጃችን የማንለየው ንጥቂያ፣ዘረፋን፣አካላዊ ጥቃትን መከላከያ።)

ጎሥት ቃሪያ እጅግ እጅግ የሚያቃጥል ቃሪያ ሢሆን በመለሥተኛ ማሣ ላይ በማብቀልና በጥንቃቄ በመሠብሠብ፤ አድርቆ በውሃ ዘፍዝፎ ወደ ሥፕረየር መያዣ በመክተት የፔፐር ሥፕረየር መሥራት ይቻላል። ብዙ ሠዎች ከዘረፋና ከተለያዩ ጥቃት እራሣቸውን መከላከያነት ይጠቀሙበታል።

በተጨማሪም ቃሪያው ለብዙ ጥቅሞች ይውላል።ሜታቦሊዝምን የሚያቀላጥፍ ንጥረ ነገር ሥላለው በጥንቃቄ ምግብ ውሥጥ ይጨመራል።ክብደትን ለመቀነሥ ይረዳል።

ሥታመርቱትም በብዛት ሊሸጥ የሚችል መገልገያ ነው።

ሃሣብ የማመንጫው ዘዴ ብዙ ቢሆንም አንዱ አካባቢን ተገንዝቦ ለችግር መፍትሄ በመፈለግ ነው።

ዳይ ወደ ሡቢ....ከዛም ወደ ርዝቅ .....
የሚካኤም፣የአቡነ ሣሙኤል ቅዳሤም ይሠማል...

Abi A. Adeye ደሞ በዚህ ዳጣ ለመሥራት እንዳትሞክሪ 😍🙏

በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

23 Dec, 10:18


ተነሡ
Get to work
ተነሡ!
idea 0020/2017 ዓ.ም።
ሥፔሻሊቲ ሬሥትራንት።

የሥራ-ሥርና የጥራጥሬ ቅቅል ድብልቅ ሥፔሻሊቲ ሬሥቶራንት።

አሥቡት ከጤናማ ምግብ ውሥጥ የሚቀቀሉ ነገሮች አሪፍ ናቸው።
የተለያዩ አይነት ድንቾች፣ቀይ ሥር፣ካሮት፣ሥኳር ድንች፣ጎደሬ
...ወዘተ አጥቦና በአንድ ሣህን ሣይላጥ ቀርቦ የሚበላበት ሥፔሻሊቲ ሬሥቶራንት ።

የተለያዩ አይነት አዝእርት ንፍሮ ...ሽምብራ፣ባቄላ፣ቦሎቄ፣ፋጆሊ (አባጮማ)፣ሥንዴ፣በቆሎ፣አተር....ወዘተ ተቀቅሎና በቅመም ተረሥቶ የሚበላበት ሥፔሻሊቲ ሬሥቶራንት ....ቢከፈት።

ለጤናማ አመጋገብ፣ከወዳጅ ጋር ቁጭ ብሎ እየላጡ እና እየዘገኑ የሚበሉበት  እሥፔሻሊቲ ሬሥቶራንት ቢከፈት ለከተማው ለየት ያለ ነገር ተሠራ ማለት ነው።ቱሪሥትም ሊጎበኛችሁ ይችል ይሆናል።ደሊቨርም ልታደርጉ ትችላላችሁ።ለተለያየ ዝግጅትም ልታቀርቡ ትችላላችሁ።

ከ ፎቶዎቹ ውሥጥ ቦነያ፣አምቾ፣ጎደሬ፣የጉሙዝ ዱባ....ይታዩዋችኋል?
(በነገራችን ላይ አምቾ ብዙ የጤና ጥቅም አለው  Emu Ti   እና     Abi A. Adeye ከልሟቸው እሥኪ።ለልምድ ልውውጥ)

እንደ ቁርጥ ቤት ትዝናኑበታላችሁ።በጤንነት።

ንፍሮውን አድርቃችሁ እንደኢንዶሜ አሽጋችሁ መሸጥም ትችላላችሁ።

በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

21 Dec, 15:35


Bejai Nerash Naiker Gave this vote for Ezedin, follow the lead.

ድምፃችሁ ለኢዘዲን ይሁን ተብሎዋል።

Let's Do It !

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

21 Dec, 08:55


ተነሡ!
idea 0019/2017 ዓ.ም።...(ለሡብሂ ሠላት ሥትነሡ...)
(ቆጮ፣ቡላና አምቾ በማሽን ፕሮሠሥ አድርጎ እና አሽጎ ለገበያ ማቅረብ)...
የቆጮ መፋቂያ፣መጭመቂያ፣ፈርመንት ማድረጊያና መክተፊያ ማሽን ሠርቶ።ቆጮን እና ቡላን በሥፋት ሃገር ውሥጥ ማቅረብ።አምቾን አሽጎ ለገበያ ማቅረብ።
ቆጮ አ ከእንሠት ግንድና ሥር ተፍቆ፣ፈርመንት ተደርጎና ተከትፎ የሚሠራ የኢትዮጵያን ምግብ ነው። ቡላም ከቆጮ ጭማቂ ተሠብሥቦና ፈርመንት ተደርጎ የሚገኝ ነው።
ይህንን ሂደት ከጉልበት ነጻ በማድረግ ቆጮን ፍቆ፣ፈርመንት አድርጎና ከትፎ ማሸግ የሚያገለግል ማሽን በመጠቀም የቆጮ ምርትን ማዘመን አሪፍ የቢዝነሥ አይዲያ ነው።
አምቾ ደግሞ ከእንሠት ግንድ የሚገኝ እንደድንች ተቀቅሎ በወተት የሚበላ እጅግ ለጤና ተሥማሚ የሆነ ነው።እሡንም በማሸግ ለገበያ ማቅረብ።
ማሽኑን እኛ ጋር ታገኙታላችሁ።
'ዳዕዋ ውጣ ዝሁር ሥገድ....' Yoni Balcha
በርቱ!
በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

21 Dec, 08:52


Vote for Bejai Nerash Naiker With SMS ✉️9355 CODE - BIW 01📩 https://web.facebook.com/vijai.naiker

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

11 Nov, 10:35


87ኛው multi function animal feeds ፋብሪካ ለጅማ የገበሬዎች ህ/ሥ/ማ ተተክሏል።
www.bejaiethio.com

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

26 Oct, 19:36


ተነሡ!
Idea 013/2017 ዓ.ም።
የግዛዋ ሥር በዱቄት ወይም በሌላ መልክ አምርቶ በማሸግ መሸጥ።
ግዛዋ (ashwagendha or Vernonia amygdalina)
ሠዎች ከ 600 እሥከ 1200mg/day ሊወሥዱ ይችላሉ።
በአሜሪካ ሠው እንዲረጋጋ፣ፓርኪንሠን ያለበት፣የማሥታወሥ ችግር ያለበት፣ሥኳር፣ግፊት፣ ለሤክሹዋል ኢንፖተንት ወዘተ ይወሠዳል::አሜሪካ፣ዩሮፕና ሚድል ኢሥት ገበያው ተጧጡፏል።በኪሎ አሪፍ ዝግ አለው።
.......
Reduces Anxiety.
Boosts Cognitive Abilities.
Enhances Exercise Performance.
Increases Sperm Health and Testosterone Levels.
Improves Sleep Quality.
Reduces Blood Sugar Levels.
Improves Arthritis Symptoms.
Blood pressure
ከቡና፣ከቆዳና ሌጦ ኤክሥፖርት ባሻገር የመድሃኒት ዛፎችን በመትከል ሥራችሁን ማቀላጠፍ ትችላላችሁ።
ቢሾፍቱ በብዛት ይገኛል።
በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

26 Oct, 19:35


ተነሡ!
012/2017ዓ.ም።
የፍራፍሬ ጃም መሥራት።
ብርቱኳን፣እንጆሪ፣ማንጎ ወዘተ ግብአቶች ናቸው።ንጽህና ይፈልጋል።ህጋዊ ሆናችሁ ሥሩ።
መርካሞ የሚፍታህ እና Salim M Ahmed ሥለአሠራሩ በሚሤጅ ከታች ጠቁመዋችኋል። ሌሎቻችሁም ልምዳችሁን አካፍሉ 🙏
በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

26 Oct, 19:33


Data Analysis, Machine Learning,Machine design, Artificial Intelligence, Cloud Computing, Cybersecurity, Blockchain Development, 3D Modeling, Graphic Design, Video Editing, Animation, Web Development, Mobile App Development, Digital Marketing, Social Media Management, Search Engine Optimization (SEO), Content Writing, Copywriting, UX/UI Design, Front-End Development, Back-End Development, DevOps, Data Science, Python Programming, Java Programming, C++ Programming, JavaScript Programming, SQL Database Management, NoSQL Databases, IT Project Management, Product Management, Agile Methodologies, Scrum Mastery, Virtual Reality Development, Augmented Reality Development, Game Development, Network Security, Ethical Hacking, Penetration Testing, Cyber Forensics, Cloud Architecture, Cloud Storage Solutions, SaaS Development, E-commerce Development, Online Advertising, PPC Management, Influencer Marketing, Affiliate Marketing, Branding Strategies, Email Marketing, Business Analytics, Financial Modeling, Business Intelligence, Accounting Principles, Human Resources Management, Leadership Training, Public Speaking, Negotiation Skills, Conflict Resolution, Strategic Planning, Entrepreneurship....በመጠኑ ናቸው።
በርቱ! 2/2

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

26 Oct, 19:33


ተነሡ!
idea 011/2017ዓ.ም።
የክህሎት ሥልጠና የሚሠጥ የኦንላይን መተግበሪያ/ ፕላትፎርም ሥራ።
ወጪው .....የፕላትፎርም መተግበሪያ ማሠራት፣ቁሣቁሦች ማደራጀት፣ፈጣን ዳታ መግዛት፣ ኔትዎርክ መገንባት።
ገቢው ከsubscription እና ከማሥታወቂያ።
ዘመኑ የክህሎት ነው።
"Skills Just Rather Than Degrees" የሚል መጽሃፍ በ ፕሮፌሠር Isa Ali Panthami...አንብቡት
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
~~ ለምሣሌ ለዘመኑ የሚመጥኑ -ሥልጠናው ሊያካትታቸው የሚችለው .....(ሊኖራችሁ የሚገባ ክህሎት)
~~~~
1/2

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

24 Oct, 19:22


ተነሡ!
idea 010ዓ.ም።
ለንግሥቲቷ የሚሠራውን Royal jelly ሠብሥቦና አሽጎ መሸጥ።
ንቦች ለንግሥቲቷ ብቻ የሚሠሩት ምግብ ሮያል ጄሊ ይባላል።
ይህ ሮያል ጄሊ የአለም ገበያ ላይ አንዱ ኪሎ እሥከ 25,000 ብር ድረሥ ይሸጣል።
ለቆዳ ውበት፣የደም ሥኳርን ለመቆጣጠር፣ለፈርቲሊቲ፣ለሃይልና ኢሚዩኒቲ ቡሥተር፣ኮሌሥትሮልን ለመቀነሥ፣ለብሬይን ፈንክሽን ወዘተ ይጠቅማል።በፈሣሽ፣በዱቄትና በሚዋጥ መልኩ ማዘጋጀት ይቻላል።
በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

24 Oct, 19:20


ተነሡ!
009/2017ዓ.ም።
ፒክል አምርቱ።
ኩኩምበር፣ካሮት፣ሎሚ፣ቃሪያ፣የወይራ ፍሬ፣የመሣሠሉት....ተዘፍዝፈው ከተፈለገም ፈርመንት ተደርገው ለገበያ በጥሩ ማሸጊያ ይቀርባሉ።
ይታጠባል፣በጨው ወይም ባቼቶ ይዘፈዘፋል፣ተፈላጊ ቅመም ይገባበታል፣ሥተራላይዝ በሆነ እቃ ይታሸግና ገበያ ይወጣል።ኤክሥፖርትም ሊደረግ ይችላል።
ፕሮ ባዮቲክ ለጤና ይጠቅማል።ኤሌክትሮ ላይት ባላንሥ ያመጣል።ሎው ካሎሪ ነው።ቫይታሚን፣ሚኒራል አለው።አንቲ ኦክሢዳንት ነው። ወዘተ
እንደ ኢንተርናሽናል ፒክል አምራች እንደነ Kraft Heinz, Pinnacle Foods, and regional brands offering traditional and artisanal pickle products.
በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

22 Oct, 20:09


ተነሡ!
idea 008/2017ዓ.ም።
ከባኦባብ(Adansonia digitata) ፍሬ ዱቄት ማምረት እና ኤክሥፖርት ማድረግ።
ባኦባብ(Adansonia digitata)ዛፍ በኛ ሃገር ሠሜኑ ክልል ለምሣሌ ሠቆጣ አይቼዋለሁ። ከፍሬው የሚገኘውን ፐልፕ አድርቆ፣ፈጭቶና አሽጎ ለሃገር ውሥጥም ለውጪም ገበያ ማቅረብ ይቻላል።

ልክ እንደሞሪንጋ ባኦባብ ዱቄት ድንቅ ነው። ለምግብነት፣ለጤንነት፣ለውበት፣ለመድሃኒትነት ይጠቅማል።
የfruit pulp ኡ rich in vitamin C, antioxidants&other essential minerals, such as potassium, magnesium, iron, and zinc.የ Leaves ኡcontain calcium and high-quality proteins that can be digested easily.Seeds ኡ high in fiber, fat, and macronutrients, such as thiamine, calcium, and iron.Baobab oil contains antioxidants and nutrients, such as omega-3 fatty acids, vitamins A, D, and E.Baobab powder is highly nutritious with high vitamin C content, vitamin B6, niacin, Fe, and K.

ለ ሥኳር ታማሚዎች፣ለውፍረት ቀናሾች፣ለልብ ፣ለጨጓራ፣ወዘተ ይጠቅማል።ፍራፍሬ እንደሚበላው መውሠድ ይቻላል።
The high fiber content, particularly soluble fiber, acts as a prebiotic, promoting a healthy gut microbiome.

በዓለም ገበያ በኪሎ ከ 100እሥከ 200 ዳላር ይሸጣል።ሠርቲፋይድ ሁኑ፣ህጋዊ ሁኑ።ከተማ ያላችሁ በብዛት እየተረከባችሁ በማሸግና በመሸጥ ትሥሥር መፍጠር ትችላላችሁ።
በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

22 Oct, 20:03


ተነሡ!
(ድሮ ቀዝቃዛ ውሃ በጣሣ ሢቸለሥባችሁ 😍 imagine ነፍ ጩኸት።ዳይ ወደ ት/ቤት፣አሁን ግን ወደ ሃሣብ )

idea 007/2017 ዓ.ም።
የንቦች ምግብ አምርቶ መሸጥ::

አሁን ባለው ኢኮሎጂ ሠው ሢበዛ ንቦች ይቀንሣሉ የማር እጥረት ይከሠታል።አበቦች ይጠፋሉ።እናሥ ማር እንዴት እናመርታለን???

የአበባ ፖለን ሠብሣቢ ቀፎ (የቀፎ መግቢያቸው ላይ መሹለኪያ ቀዳዶች/ወንፊት በማሥቀመጥ...)ጫካ ወይንም አበባ ያለበት እናሥቀምጣለን።50gm ድረሥ በቀን ከአንድ ቀፎ ቢሠበሠብ አሪፍ ነው።ክፍለሃገር ያሉ ወጣቶች በዚህ ግብአት ትሥሥር መፍጠር ይችላሉ።

ከተሞች ውሥጥ ንብ ቀፎ ለማሥቀመጥ የንቦች ምግብ እጅጉን አሥፈላጊ ነው።አረብ ሃገራት፣ቻይና፣አውሮፓ፣አሜሪካ፣አንድ አፍሪካ ሃገራት፣ላቲን ከሜሪካ ወዘተ።

የኛ ሃገር የማር ምርት መጨመር አለበት።የንቦች ምግብ ማዘጋጀት ደግሞ አንዱ እርምጃ ነው።

እናዘጋጅ.....

ምግቡ ለክረምት፣ለበጋ፣ለፀደይና ለመጸው ሦሥት አምድ አለው።

የሥኳር ሽሮፕ፣ፖለን ሠብሥቲቲውት፣የፕሮቲን ፓቲሥ።

1-ሥኳር ሽሮፕ: ሞቅ ባለ ውሃ (50% ) ውሥጥ 50% ሥኳር መበጥበጥ።
2.ፖለን ሠብሥቲቲውት:የአኩሪ አተር ዱቄት 30%፣የወተት ዱቄት30%፣የቢራ እርሾ29% ፣ትንሽ ፖለን 1% አቡክቶ ማድረቅ።
3.ፕሮቲን ፓቲሥ: ትንሽ ዋክሥ/ሠምና 1 እና ሁለትን እሽት አድርጎ መቀላቀል።
አሽጋችሁ መሸጥ።

በዚህ ምርት ንቦች ድካማቸውንና ግዜአቸውን ሥለሚቀንሥላቸው ጀምረው የሚያቋርጡት ሠም አይኖርም ።እሥከ ጥግ በመግባት ሰሙንና ምግቡን ያመርቱታል፣ጥናቶች የሚያሣዩት በእጥፍ የማር ምርትን ይጨምራል።የንብን ድካም የቀነሠ ሡፐር ማርኬት በሉት ።
በጣም አዋጪ ነው።

በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

22 Oct, 20:02


ተሥፋ መቁረጥ መራራ መርዝ ነው!

(ብዙ ወጣቶች በገቢ እጦት፣በገቢ ማነሥ፣በሥራ እጦት- ተሥፋ እየቆረጡ ማየት... የተለመደ እየሆነ መጥቷል)
በመላ/በሥራ
          ✍️ እንዴት ገቢ እናግኝ?
          ✍️ እንዴት ገቢ እናሣድግ?
           ✍️እንዴት ገቢ እንፍጠር?
           ✍️እንዴት ጸጋን እንላበሥ?
~~~~
ከብዙ የቤት ሥራዎች እና ከሃሣብ ቀጥሎ እንዴት የሥራ መነሻ ካፒታል/ገንዘብ እናግኝ የሚለው ትልቁ ያልተመለሠ እንቆቅልሽ ነው ??????በምን አይነት ዘዴ ካፒታል እናግኝ???

ልመና፣ፈለጣ፣ አራጣ፣ምንተፋ፣ሙሥና፣ጉቦ፣መባ፣ እድር፣ደቦ፣መሦብ፣አቆልቋይ፣ቅንጃ፣አሥራት፣በኩራት፣ እቁብ [አፎቻ፣ቂሊ (በአደሪኛ)፣ቁቢ (ኦሮሚኛ)፣ሃግባድ (በሡማሊኛ)፣ ዕቁብ(በትግሪኛ) ...በሌላ ቋንቋ ጨምሩበት ] ፣ቡት ትራፕ፣ቬንቸር ካፒታል፣ኤንጅል ኢንቨሥተር፣ ባንክ፦(አይዲያ ፋይናንሢንግ፣ሊዝ ፋይናንሥ፣ፕሮጀክት ፋይናንሥ፣ኢኪዩቲ ፋይናንሢንግ፣ዴፕት ፋይናንሥ፣ትሬድ ፋይናንሥ፣ሚዛኔን ፋይናንሥ፣አሤት ቤዝድ ፋይናንሥ፣ቬንቸር ዴፕት ፋይናንሥ፣ግራንትና ሠብሢዲያሪ ፋይናንሥ፣ኮንቨርቴብል ዴብት  ፋይናንሥ)፣ክራውድ ፈንድ፣ጎ ፈንድ ሚ፣ኪክ ሥታርተር፣ኢንዲጎ....ብላ ብላ የካፒታል ምንጭ ናቸው።በአይነት፣በጉልበት፣በሃሣብ ወዘተ..

ግን ሁሉም አይጠቅሙም፣አንዳንዶቹ ከህግና ማህበረሠባዊ ሞራል አንጻር ፈጽሞ አይሞከሩም። ከሚሞከር ውሥጥ የትኛው ለኛ ላለንበት ሃገርና ገበያ ይመቻል????
~~~
መነሻ ካፒታል የሌለው  ሃሣብ ኦክሥጅን እንዳጠረው ሞተር መንተፋተፉ አይቀርም።
ደሞዝ የለህም፣ሥራም የለህም፣ደሞዝህ አይበቃሆም.....ግን ሃሣብ አለህ፣የመለወጥ ፍላጎት አለህ፣የመለወጥ እድል አለህ።

ሆኖም ቅሉ ብታት ያላቸው በጀንብ የታጨቁ፣በጅምላ የተደረደሩ ችግሮችና ተግዳሮቶች በውሥጥህ ሞልተዋል።ያሥፈራሩሃል፣ያሣዝኑሃል፣ያናድዱሃል፣ንፉግ አድርገውሃል። አንዱ ትልቁ ተግዳሮት ደሞ በቂ ካፒታል አለመኖሩ ነው።
ተዲያ መነሻ ካፒታል ከየት እናምጣ????
ሠሞኑን በኦንላይን እንወያይበትና መቋጫ እንሠጠዋለን።እንፈልጠዋለን።የሮኬት ሣይንሥ አይደለም።
👌👌👌
በርቱ!

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

22 Oct, 19:59


ለምሣሌ፦

1. Ordinary Portland Cement (OPC)
Clinker: 90-95%,Gypsum: 5%...ነበረ አይደል?ይህን ፋብሪካዎቹ ይሥሩት....

እናንተ ደግሞ.....

2. Portland Pozzolana Cement (PPC)

Clinker: 50-70%,Gypsum: 5%,Pozzolana (e.g., fly ash, volcanic ash): 15-30%,Additives <0.1%like sika.
ፈጭቶ መቀላቀል ብቻ።

3. Portland Slag Cement (PSC)
Clinker: 45-55%,Gypsum: 3-5%,ፑሚሥ/Slag: 35-50%,
Additives:< 0.1% sika ፈጭቶ መቀላቀል ብቻ።

4. Composite Cement
Clinker: 50-70%,Gypsum: 3-5%,Pozzolana/Slag: 20-35%,Other Additives: <0.1%sika ፈጭቶ መቀላቀል ብቻ።

Sika ብራንድ  add muxture ነው። ለ አንድ ቶን አንድ ኪሎ አካባቢ የሚገባ።

ቢዝነሡን ለመሥራት ቨርቲካል ሬይሞንድ ሚል(ወፍጮና) ማሸጊያ ብቻ ያሥፈልጋችኋል።እናም ከሚፈጩት ጥሬ እቃዎች ዋነኛው ፑሚሥ(ፖዞላና) ያሥፈልጋል።

ሢሚንቶ ፋብሪካዎች ለምሣሌ ክሊንከር ለመሥራት ግብአታቸው ከዛው ከፋብሪካው አካባቢ ሢሆን፤ፑሚሥ ፈጭቶ ለመቀላቀል ግን ከፋብሪካው ረጅም ጉዞ አድርገው ነው።ለምሣሌ ሙገር ያለ ሢሚንቶ ፋብሪካ ጂፕሠምና ፑሚሥ የሚያመጡት ...ፑሚሥ ከተለያየ ቦታ ሊሆን ይችላል።በአማካይ 40% ጥሬ እቃ ለመፍጨትና ለመቀላቀል  አጓጉዘው ያመጣሉ ማለት ነው።
አሥቡት 40% ወፍጮ ብቻ የሚፈልግን ምርት  ከማጓጓዝ ጥሬው እቃ ያለበት አካባቢ ወፍጮ አቋቁም ክሊንከር ብቻ ማምጣት ለአካባቢው ወጣቶች ሃብት እንዲፈጠር ያደርጋል የሥራ እድል ይፈጥራል፣አላሥፈላጊ የትራንሥፖርት ወጪን ይቆጥባል።(ከ 40% በላይ የማይጠበሥ ፑሚሥ ተወሥዶ፣ተፈጭቶ እና ከ ክሊንከር ጋር ቀላቅሎ  PPC አድርጎ ወደ ቦታው መመለሡ  የትራንሥፓርት ወጪ ነው።
~~~
በነገራችን ላይ እዚህ አንድ ወዳጃችን አለ የዳንጎቴ ሢሚንቶ ፋብሪካ ፕላንት ዳይሬክተር ነው።ብዙ ሥለ ሢሚንቶ አሠራር ሊያሥረዳን ይችላል።አሪፍ ሠው ነው።ሜክሢኮአዊ ነው።በእጅጉ ላካባቢ ሠዎች፣ለወጣቶች የሚያሥብ ሠው ነው።ኢትዮጵያን ይወዳል።ብዙ አመት እዚህ ኖረ። Jacinto Leyva M.  ይባላል ተወዳጁት ። ሠሞኑን ለናቶችና ላባቶች 'ጥቅምት ብርድ ነው' እያለ አበባ፣ብርድልብስና ፍራሽ በነጻ ሢያድል ተመልክቼው በደግነቱ እንዴት እንደቀናሁ? የሢሚንቶ ሣይንቲሥት ነው።ሥኪል ይለከቅላችኋል።
~~~~
ሥለዚህ...
ቢዝነሡ ከገባችሁ.. ህጋዊ ሆናችሁ.. ፑሚሥ(ኮሚቼ) ባካባቢያችሁ ያለ...ወፍጮውን ገዝታችሁ...ከOPC ጋር 40% በላይ ኮሚቼ እንደየ ሥታንዳርዱ እየጨመራችሁ፣እየፈጫችሁ እና እየቀላቀላችሁ ሸቃቅሉ ለማለት ነው።
በነገራችን ላይ የአንድ ሢሚንቶ ፋብሪካ የማምረት(የማቃጠል) አቅም የሚለካው በክሊንከር ሢሆን ።የመፍጨት አቅሙ ደግሞ በ ሢሚንቶ( PPC )ነው

በርቱ!
2/2

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

22 Oct, 19:58


ተነሡ!

idea 006/2017 ዓ.ም.
(በወፎጮ ብቻ..........)
ፖርትላንድ ፖዞላና ሢሚንቶ (ppc)፤ፖርት ላንድ ሥላግ ሢሚንት (psc) እና ኮምፖዛይት ሢሚንት(CC) ን...ከ ኦርድነሪ ፖርትላንድ ሢሚንት (OPC) በወፍጮ ብቻ ማምረት።

(PPC or PSC or CC production from OPC )

ትንሽ ሥለ ሢሚንቶ የገባው እጅግ ትርፋማ ሥራ ይሠራል።

ሢሚንቶ....

ለምሣሌ፦

ከ 75% ላይም (ጥሬ ኖራ)፣17% አፈር(ክሌይ)፤ 7% አሸዋ(ሢልካ )፤1% የብረት መዓድን(አይረን ኦር) በ 1400 ºC ጠብሦ ክሊንከር ይሠራል እና ከ 5% ጥሬ ጂፕሠም ጋር አድቅቆ በመፍጨት እና ቀመቀላቀል ደግሞ OPC (95%clinker:5%gypsum)ተሠራ ማለት ነው።OPC ለማምረት ከ 40% በላይ ወጪው ለኢነርጂ የሚወጣው ነው። ለምሣሌ በኩንታል 600 ብር OPC ለማምረት ከሚወጣው ወጪ ውሥጥ ከ200 ብር በላይ ወጪውን ኢነርጂ ይወሥደዋል ማለት ነው። ለግድብ፣ለሥፔሻል ሥራ ወዘተ ካልሆነ የሢሚንቶ ፋብሪካዎች OPC ን አይሸጡላችሁም rather ከ40% በላይ ያልተጠበሠ ኮሚቼ(ፑሚሥ) PPCን ወይንም PSC ን ወይንም CC ን እንጂ ።

ለምን
PPC or PSC or CC ሢሚንቶዎች ከተለያዩ የማይጠበሡ(ኢነርጂ ከማይወሥዱ) ግብአቶች ... ከመጠነኛ ክሊንከር ወይም OPC ጋር ፈጭታችሁ አታመርቱም?
ወፍጮ፣ፑሚሥ ጥሬ እቃ እና OPC ብቻ ተጠቅማችሁ!

1/2

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

22 Oct, 19:55


እናንተ ሥንት ሥንት ብታዋጡ...ይህ ይሆናል ?premitive capital accumulation by share ተጠቀሙ።

ባንኮች ሠልጥነው አይዲያ ፋይናንሢንግን እሥኪገባቸው ድረሥ....አደራ ሃሣባችሁን አኮርተው  እንዳያዝጋችሁ ተጠንቀቁ። ማታ Kefe Hailu  ሊያሣትመው ባዘጋጀው አሪፍ የቢዝነሥ አጀማመር  መጽሃፍ ውሥጥ አንድ ሃሣብ አወራን። ባንኮች በፕሮጀክትም ሆነ፣በሊዝም ሆነ ፣አይዲያ/ኢኩቲ ፋይናንሥ  እንዴት እንደማያበድሩ ሥናወራ ነበር። አንድ ግዜ አንድ ባንከር ምን አለኝ መሠላችሁ ቁጠባ ከሠፊው ማህበረሠብ ይልቅ 3 ....4 ትልልቅ ባለሃብቶች ቢቆጥቡ ያዋጣል ....ባለሃብቱም አሪፍ ወለድ 'ሣይለፋ'/'ሣይሠራ'  ያገኝበታል እኛም አሪፍ እንሸቅላለን አለልሃ።

ይህ ሃሣብ ላለው  መነሻ ገንዘብ ለሌለው ወጣት ምን እንድምታ አለው?

በርቱ!
2/2

አባ መላ (Bejai Naiker Nerash)

22 Oct, 19:55


ተነሡ!

idea 005/2017 ዓ.ም።
ተንቀሣቃሽ የ ህክምና ላቦራቶሪና ዲያግኖሥቲክ ኢሜጂንግ ሥራ።

በሽታን ማወቅ ግማሽ መድሃኒት ነው ይባል የለ?.....

አሥቡት ትልቅ ባሥ ውሥጥ cbc ላቦራቶሪ፣ሢቲ ሥካን፣ኤክሥ ሬይ፣ኤም አር አይ፣አልትራሣውንድ፣ኢኬጂ ፣ኢሢጂ፣አንጂዎ ግራፍ ወዘተ ቢኖር። ፋሢሊቲ ደግሞ 80kw ጀነሬተር ቢኖራችሁ።
ተገልጋይ ሣይጓዝ በመኖሪያው አካባቢ የሆሥፒታሉን ትልቁን አገልግሎት ሢያገኝ።

አንድ 20 ወይም 30 ሆናችሁ ተደራጅታችሁ ይህንን በባሥ ውሥጥ የሚገጠም...የ ላብራቶሪናና ኢሜጂንግ ኢኩፕመንት ከ አሪፍ አሪፍ ነርሦችና ሃኪሞች ጋር ቢኖራችሁ፤በቀን 200 ሠው በ 3000 ብር በአማካይ በየከተማው/በየወረዳው ብትሠሩ በአመት 200 ሚሊዮን ብር በላይ ሸያጭ ፣በአመት የጥናት መረጃን በ 5 ሚሊዮን ሽያጭ ብትሠሩ፣ከክሊኒክና ከሆሥፒታሎች ጋር በአመት የ 5 ሚሊዮን አገልግሎት ሽያጭ ብትሠሩ፤ከመሥሪያ ቤቶች ጋር ተነጋግራችሁ ኮርፖሬት አገልሎት 5 ሚሊዮን ሽያጭ ብትሠሩ፤በሠብሥክሪፕሽን 2 ሚሊዮን በአመት ብትሠሩ።217 ሚሊዮን ብር በላይ በዓመት ሽያጭ ይኖረዋል። ከዚህ ውሥጥ 180 ሚሊዮን ብር በአማካይ አመታዊ ትርፍ ይኖረዋል ።

ይህንን ለ 20 አዋጥታችሁ ብትሠሩት በአመት ጥሩ ብር ገቢ ለያንዳንዳችሁ ይደርሣል፤በዛውም ማህበረሠቡን በደንብ አገለገላችሁ ማለት ነው። በዚህ ዘመን የህክምናው ኳሊቲ በላብና በኢሜጂንግ ቴክኖሎጂ ላይ ጥገኛ ሆኗል።