RN.05 - Channel @rnzerofive Channel on Telegram

RN.05 - Channel

@rnzerofive


ከኢትዮጵያና አዉሮፓ የሚተላለፍ የራድዮ ፕሮግራም
አዲሱን ዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ:
https://www.youtube.com/c/RN05Channel

ፌስቡክ ገፃችንን like ያድርጉ:
https://www.facebook.com/RNZeroFive/

https://twitter.com/RNZeroFive

Support Us:
http://bit.ly/3c09jfJ

https://RNZeroFive.com

RN.05 - Channel (Amharic)

የRN.05 - Channel ቻናሎች የሚተላለፉ አዲሱን እና በአሠሪና አዲስ ተከታታዮችን ለማናገር በደረሰው ተሳካሚ ጽሁፎችን ይመልከቱ። የኢትዮጵያና አዉሮፓ አባላትን ከእኛ እና በደም እንድታደርጉ እንወራለን። በነገር ግን የRN.05 - Channel ቻናሎች በተጨባጭ ሰብስክራይብ በማድረግ የኢትዮጵያና አዉሮፓ የሚበጅባቸው ፕሮግራሞችን በተከታታዮች መለዋወጫ ማቅረብ እና በእርስዎ አንድነት መንከሳዊ እንቅስቃሴ በሚለዋወጥ መረጃዎችን ያቀረብነው። ስለዚህ እናመሰግናለን ፌስቡክን ለመግባት በሚያግዝና ለጽሁፉ ተጨማሪ ይከታተሉ: https://www.facebook.com/RNZeroFive/ እና https://twitter.com/RNZeroFive እንድታሳል ያደርጉ። በትክክለኛ በሚፈልግበት መረጃ መንከሳዊም የሚሰራ ለማየት ለሚለዋወጥ እና ከሚያስፈልግ እንደሚገኝ እናመሰግናለን። ይህም በሀገር ከተማውያን ውስጥ ያሉ በቀላሉ የምግብ ፕሮግራምን በመጠቀም እናቀርባለን። እናመሰግናለን ለአንድ ላይ ወደ ገፅ መቆጣጠር እና ከዚህ ደግሞ የሚከተሉ ቻናሎችም በመረጃዎችና በተለዋዋጮ ሳይከታተሉ እና መንከሳዊ ከተሞቹ በመከታታተል እንዲያቀርብ ነው። በትክክለኛ ለመግባት፣ ስለሚከተሉ ፕሮግራሞችን እና ተጨማሪ ቻናሎችን ከሚለዋወጥ ቀለም አስቀምጥ ማጠናከር እና ለጽሁፉ ለመረጃዎች በጣም ማስነሳት እንዳልሰጣቸው እንደሚረዳ ሰማው። ከእናንተም ፕሮግራም ለእኛ ተልባለን።

RN.05 - Channel

21 Nov, 17:17


🚩 አዉሮፓ ናታንያሁን ለማሰር ይዘጋጅ ተባለ!
~~~~~~~~~~~
#RN05
.
ዛሬ በእስራኤሉ ጠ/ሚር በናታንያሁና የቀድሞ የጦር አዛዣቸው ጋላንት ላይ የወጣዉን የአለማቀፉ ከፍተኛ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዘን በተመለከተ የአዉሮፓ ህብረት የዉጭ ፖሊሲ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል👉 https://youtu.be/G1F_27F7I7c
.
"ይህ ICC ያወጣው የእስር ማዘዣ ፍ/ቤቱ ከየአዉሮፓ ህብረት ጋር ባለው ስምምነት መሰረት የሚያስገድድ አሳሪ ህግ በመሆኑና 27ቱ አባል ሃገራትን የሚመለከት በመሆኑ ፣ሁሉም አባል ሃገራት ለፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ተገዢ በመሆን ለተፈጻሚነቱ ሊተባበሩ ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

.
@followers @highlight
-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

RN.05 - Channel

21 Nov, 12:58


ሰበር መረጃ
~~
#RN05

ናትያንያሁ የእስር ማዘዣ ወጣባቸው
--------------------
.
የአለም አቀፉ ከፍተኛ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ICC ናታንያሁንና የቀድሞ ጦር ሚንስትሩ ጋላንት ላይ በተገኙበት እንዲታሰሩ ማዘዣ ማውጣቱ ታውፕቀ።

አምስተርዳም ህዳር 21/2011 የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዳኞች የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የቀድሞ የመከላከያ ሃላፊቸው እንዲሁም የሃማስ መሪ ኢብራሂም
በጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ሲል የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸዋል። .

እርምጃው የመጣው የአይሲሲ አቃቤ ህግ ካሪም ካን እ.ኤ.አ በሜይ 20 ላይ በሃማስ በእስራኤል ላይ ከደረሰው ጥቃት Oct.7, 2023 ጋር በተገናኘ በተጠረጠሩ ወንጀሎች የእስር ማዘዣ እየጠየቀ መሆኑን እና በጋዛ የእስራኤል ወታደራዊ ካወቀ በኋላ ነው።

እስራኤል ክሱን ውድቅ ብታደርግም አይ ሲ ሲ እስራኤል የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ስልጣን መቀበሏና አለመቀበሏ አያሳስበኝም ነው ያለው።

ይህ ለ6 ወራት ያህል ሲጠበቅ የነበረው ውሳኔ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የICC አባል ሀገራት ሁሉ ወንጀለኞቹን በተገኘበት ለማሰር እንደሚገደዱ ስምምነታቸው የሚያረጋግጥ በመሆኑ ናታንያሁን ማሰር የማይፈልጉት አውሮፓ ሀገራት ቢያንስ እነ ናታንያሁ ወደ ሀገራችን እንዳይገቡ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

እስራኤልና አሜሪካን ይህ ማዘዣ እንዳይወጣ ከወጣ ግን በተለይ በዋና አቃቤህግ ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ሲዝቱ እንደነበር ይታወሳል።
.
**** ይህ ውሳኔ እደምታው፣ ጠቀሜታውና ተፈጻሚነቱን እንዴት ያኩታል? ጻፉልን!!!

---------
***ይሄው ነው! በመሆኑም ባለስልጣኖቻችን ሶማሌላንድ መመላለስ ያለባቸው ከወደብ ይልቅ ስለ ዲሞክራሲ ለመማር ቢሆን ጥሩ ነው - ይህ መልካም ጥቆማ ነው!
.
@followers @highlight
-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

RN.05 - Channel

19 Nov, 07:03


ባለስልጣኖቻችን ሶማሌላንድ መመላለስ ያለባቸው ከወደብ ይልቅ ስለ ዲሞክራሲ ለመማር ቢሆን ጥሩ ነው!
~~
#RN05
.
ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት በመሆን መመረጣቸው ተሰምቷል፡፡

የሶማሊላንድ ምርጫ ኮሚሽን የዋዳኒ ፓርቲ እጩ አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።

አብዲራህማን በምርጫው 63 ነጥብ 92 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፉ ሲሆን፥ የወቅቱ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ 34 ነጥብ 81 በመቶ ድምጽ በማግኘት ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

በምርጫው ሂደት ውስጥ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ዋዳኒ፣ ኩልሚዬ እና ካህ ቁልፍ ተዋናዮች ሆነው መታየታቸው ተጠቁሟል።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በሶማሊላንድ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን በመግለጽ ህዝቡ ላሳየው ተሳትፎ አመስግኗል።

አዲስ የተመረጡት ፕሬዚዳንት በሚቀጥሉት ቀናት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ያሳውቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሙስታክባል ሚዲያ ነው የዘገበው፡፡

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ባለፈው ሳምንት ሕዳር 4 ቀን 2017 መካሄዱ ይታወቃል።

---------
***ይሄው ነው! በመሆኑም ባለስልጣኖቻችን ሶማሌላንድ መመላለስ ያለባቸው ከወደብ ይልቅ ስለ ዲሞክራሲ ለመማር ቢሆን ጥሩ ነው - ይህ መልካም ጥቆማ ነው!
.
@followers @highlight
-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

RN.05 - Channel

17 Nov, 22:04


ናታንያሁ ቤታቸው ላይ ዳግም ጥቃት ተፈጸመ
~~~~~~~~~~~~
#RN05
.
የሂዝቡላህን ቃል አቀባይን መግደሏን ያሳወቀችው እስራኤል በሌላ በኩል በሰሜን እስራኤል በሚገኘው የናታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ ተዘግቧል።
የእስራኤል ፖሊስ እንዳሳወቀው በሰሜን እስራኤል ካሳሪያ ከተማ ወደ ሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንያሚን ናታንያሁ መኖሪያ ቤት ነው ሁለት ቦምቦች የተወረወሩትና ግቢ ውስጥ ያረፉት፡፡
.
የቦምቡ ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት ናታንያሁም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው በቤት ዉስጥ እንዳልነበሩ የጠቀሰው የሃገሪቱ ፖሊስ በጥቃቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 3 ሰዎችን መያዙን አሳውቋል፡፡
.
አንዳንድ ባለስልጣናት በጥቃቱ የናትያንያሁ ተቀናቃኝ ፓርቲ ሰዎች እጅ ሊኖርበት ይችላል ብለው እንደሚያምኑ እንደሚችሉ በመግለጽ ወቀሳ የሰነዘሩ ቢሆንም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በበኩላቸው ጥቃቱን የሚያወግዙ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
.
ባለፈው ወር በሄዝቡላህ ተሞከረ ከተባለው ጥቃት ጋር የናትያንያሁ መኖርያ ቤቶችን ያማከለ ጥቃት ሲደረግ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል፡፡
.
@followers @highlight
-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

RN.05 - Channel

17 Nov, 21:29


በሴራ የተሞላዉና ችላ የተባለው የሱዳኑ ቀዉስ
~~~~~
#RN05
.
የሱዳን ጦርነት አሁንም ቀጥሏል በጣም ውስብስብ እና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
.
ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡
.
#የተቀጣጠለ_ግጭት: የሱዳን ጦር (SAF) እና ተቃዋሚው (RSF) መካከል ያለው ግጭት አሁንም ቀጥሏል በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊቆም ይችላል የሚያስብል ምልክት ከቶ አይታይም።
.
#ሰብዓዊ_ቀውስ: በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በጦርነቱ ሞተዋል፣ ቆስለዋል አካላቸው ጎሏል፣ ተጎድተዋል፣ በአጠቃላይ ወደ 14 ሚልዮን የሚጠጉ ዜጎች ከቤታቸው ተፈናቅለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። የምግብ፣ ውሃ እና መድሃኒት እጥረት ከባድ ችግር ሆኗል።
.
#የመሠረተ_ልማት_ውድመት: ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች የህብረተሰብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተጎድተዋል ወይም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። ይህም የህዝቡን ህይወት አስቸጋሪ አድርጎታል።
.
#ኢኮኖሚያዊ_ቀውስ: ጦርነቱ ቀድሞውኑ የተዳከመዉን የሱዳንን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቷል። ዋጋ ግሽበቱ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፣ ይህ በመሆኑም ብዙ ሰዎች በድህነት ውስጥ ወድቀዋል።
.
#ክልላዊ_ተጽእኖ: የሱዳን ጦርነት በአጎራባች አገራት ላይም ተጽእኖ እያሳደረ ነው። በተለይ ወደ አጎራባች ሃገራት በተለይም ወደ ቻድ ብዙ የሱዳን ስደተኞች ፈልሰዋል። ይህም አድሮ የሚፈነዳ ቀዉስ አሳድሯል፡፡
.
#አለም_አቀፍ_ጥረቶች: አለም አቀፉ ማህበረሰብ የሱዳንን ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ ነው ቢባልም በእስራኤልና በዩክሬይን ላይ ያተኮረው የምእራቡ አለም የሱዳኑን ቀዉስ የሚገባዉን ያህል ብዙም ትኩረት የሰጠው አይመስልም። የአፍሪካ ህብረትም ሆነ የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ አጀንዳና በጀቱን ከምዕራቡ አለም ስለሚጠብቁ ይመስላል በራስ ተነሳሽነት ጦርነቱን ለማስቆም እያደረጉ ያሉት ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አልሆነም፡፡ እስራኤልንና ሊባኖስን፣ ራሽያንና ዩክሬንን ለማሸማገል የሚጥሩት የአረብ ሃገራት የሱዳኑን ጦርነት ለማስቆም ከመስራት ይልቅ ባላቸው የተለያዩ አጀንዳዎች ሰበብ ጦርነቱ ላይ ቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ስለመሆናቸው እየተነገረ ይገኛል።
.
ዋና ዋና ስጋቶች:
.
#የሲቪሎች_መጠቃት: በሲቪሎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸው በጣም አሳሳቢ ሆኗል።
#የክልሉ_አለመረጋጋት: የሱዳን ጦርነት በክልሉ አለመረጋጋትን ሊያባብስ ይችላል።
#የሰብአዊ_ቀውሱ_መባባስ: በሚቀጥሉት ወራቶች ሰብዓዊ ቀውሱ ሊባባስ ይችላል።
.
ይህ ቀድሞ በጋራ ሃገሪቱን ሲመሩ በነበሩ አሁን ግን አንጃ ፈጥረው ሀገሪቱን ወደማይኖርባት የሰቆቃ ቀጠና እየቀየሯት ያሉበት የእርስ በእርስ ጦርነት የተጀመረው በረመዳን ወር ወይንም እንደ አዉሮፓዊያኖቹ አፕሪል 15 2023 እንደነበር ይታወሳል፡፡
.
****እርሶስ ስለሱዳን ምን ያስባሉ? ኢትዮጵያስ ላይ የሚፈጥረው ተጸኖ ይኖር እንደሁ እንዴት ያዩታል ይጻፉልን!!
.
@followers @highlight
-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

RN.05 - Channel

17 Nov, 09:35


👆

RN.05 - Channel

17 Nov, 09:34


https://www.youtube.com/c/RN05channel

RN.05 - Channel

16 Nov, 22:43


👆 እግረመንገዳችሁንም ዩትዩብ ቻናላችንን ሱብስክራይብ እያደረጋችሁ!

RN.05 - Channel

16 Nov, 19:56


https://youtu.be/EbzWcXlXPn8 RN.05 || ሳማርካንት(#SAMARKANT) ዘመናት ያልሻሩት ታሪካዊ አሻራ! የRN05 ታሪካዊ ጉዞ በኡዝቤክስታን Nov 2024

RN.05 - Channel

13 Nov, 21:15


🚩የፋሺስታዊ አቋም ቀለብ መርህ አልባነት ነው!
~~~~~~~~~~~
#የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለRN05
.
በሃገር ወዳድነት ስም ራሳቸዉን ከሌላው የተሻሉ አድርገው የሚያዩና በእነሱ የሚወከሉ ሌሎችም ትናንትናቸውና ዛሬያቸው ይህንን በእስክሪን ሾት የተወሰዱትንና የተያያዙትን ሁለት ፎቶዎች ይመስላል! የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት ተግተው እንደሰሩት ሁሉ አሁንም በሌላ መልኩም ቢሆን የአማራንም ህዝብ እንዲጠፋ እየሰሩ ነው፡፡ ራሳቸዉን "የኢትዮጵያዊነት ልክ " አድርገው የሚያዩ ምሁርም ይሁኑ ጋዜጠኛ ፣ፖለቲከኛ ነኝም ይበሉ ጀሌ አክቲቪስቶች ሁሌም ይሄው ናቸው፡፡ ደስታቸዉንም ሆነ ሃዘናቸዉን መጥነው አይደቁሱም፡፡ ያለበቂ አመክንያዮ ለማጎብደድ እንደሚሽቀዳደሙት ሁሉ መልሰው ጠላን ሲሉም ያለ አመክንዮ ነው፡፡
.
አላማና ፍላጎታቸው እዉነትም ኢትዮጵያዊያን በአንድ ሃገረ ህዝብ ህሳቤ ህልዉናቸዉ ተጠብቆ ፣መብታቸው ተከብሮ እኩል በሰላምና በፍቅር እንዲኖሩ አይደለም፡፡ ከዛ ይልቅ እነሱ የሚፈልጉት ሁሉ ይሆን ዘንድ እንጂ! እነሱ የሚፈልጉት ደግሞ የእነርሱ ሃሳብ፣ ታሪክ፣ ባህልና ትርክት ገዢ ሆኖ በዚሁ መመዘኛ የጠሉት እንዲጠፋ የወደዱት እንዲከርም ማድረግ ነው፡፡ ያ ባይሆንማ ኖሮ በትግራይ ሲደረግ ትክክል ነው፣ በኦሮምያም ሲደረግ ትክክል ነው! መንግስት ሊታገዝ ይገባል! ተጨማሪ ግድያ እንዲፈጸም ገንዘብ ሰብስበን እንስጠው ወዘተ ሲሉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ መንግስት ተመሳሳይ ግፍ አማራ ክልል ዉስጥ ሲፈጽም በተመሳሳይ በደገፉት እንጂ ባልተቃወሙ ወይንም ደግሞ ጦርነቱ ትግራይና ኦሮምያ ክልል ዉስጥ ሲደረግ ትክክል - አማራ ክልል ዉስጥ ሲደረግ ደግሞ ስህተት የሆነበትን ምክንያት በበቂ ማስረዳት በቻሉ ነበር፡፡ ለዚህ ነው መርሃቸው ስለ ዜግነት መብት መጣስ ፣ ስለ ሰብዓዊ መብት መሸርሸር መጨነቅ አይደለም የምንለው፡፡ እነሱን እስካስደሰተ ድረስ የዜጎች ሰብዓዊ መብት ሲጣስ ዋነኛዉን ከለላና ድጋፍ የሚሰጡ፣ "ይበለው! ይጥረገው!" ከማለት ዉጭ ለህጻናት እና ሴቶች እንኳ የማይራሩ ፕሮፌሰሮች፣ ተንታኞች፣ የሚድያ፣ የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ሰዎችና መሰል ጨካኝ የሃገርንና የዜጋን ክብር በፋሺስታዊና በጥላቻ ስካር የሚመዝኑ ሰዎችን በበቂ መታዘብ ተችሏል፡፡
.
አሁን ደግሞ እነዚሁ ሃይሎችና ሚድያዎቻቸው ትላንት ያለ መርህና መመዘኛ በጭፍን ሲደግፉት የነበረዉን መንግስት ከመቃወም አልፈው እንደግፍሃለን ፣አይዞህ ሲሉት የነበሩትና እንደ ልዩ ፍጡር ሲስሉት የነበረው ፋኖ ላይ ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ ይህንን እያደረጉ ያሉት ደግሞ መንግስት የሚከተለው ፖሊሲ ትክክል፣ ፋኖ የሚከተለው ግን የተሳሳተ ሆኖ አግኝተዉት ሳይሆን፣ ፋኖ እነሱ እንደጠበቁት በፍጥነት ድል ሊቀዳጅላቸዉና ጥማቸዉን ሊቆርጥላቸው ብሎም ሊያነግሳቸው ባለመቻሉ ነው፡፡ የአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው መከራ ቆርቁራቸው ግን በፍጹም አይደለም፣ ያ ቢሆንማ ኖሮ ጦርነቱንም ገና ከጅምሩ ህዝቡ ላይ ሊያመጣ የሚችለዉን መዓት በማሰብ በቅጡ በመቱት ነበር! ያኔ ግን ጦርነት የአንድዮሽ መንገድ ብቻ ይመስል እሳቱ በማይነካቸው ርቀት ላይ ሆነው ወሬያቸው ሁሉ "ይጀመር እንጂ ድል የኛ ነው!" የሚል ብቻ ነበር፡፡
.
እነዚሁ መርህ አልቦዎች ታድያ የጠሉትን ሁሉ "ጸረ ኢትዮጵያዊና የግብጽ ቅጥረኛ" ሲሉ እንዳልነበር አሁን አሁን "ግብጽ ሆይ ድረሺልን!"፣ "ኢሳያስ ሆይ እባክህ ቶሎ ና!" ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ መርህ አልባ የሆነ አካል ቋሚ መመዘኛ ስለሌለው እየተቀያየረ ምንንም ነገር ሊያደርግ ይችላልና!!
.
ከምስኪኑ የክልሉ ህዝብ ዉጭ እና ከጥቂት አርቆ አሳቢዎች በቀር አብዛኞቹ የሰሜን ምሁራን እና ኤሊቶች ባህሪያቸው እንደዚሁ ነው፡፡ እንደ መርህ አልባ አባወራ ያሻቸዉን ማድረግ የሚችሉ፣ አርፈህ ተቀመጥ ከማለት አንስቶ ያሻቸዉን በቁንጥጫ፣ ያሻቸዉን በቀበቶም ልክ የሚያስገቡ አድርገው ራሳቸዉን መሳል ይቀናቸዋል፡፡ ትልቁ ስንፈተ ባህሪያቸው መርህ አልባ መሆን ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ባልተመጠነና ሌላዉን በሚወጋ ፋሺስታዊ ዲስኩራቸው ሰበብ ምስኪኑ የአማራ ገበሬ በሌሎች ዘንድ በሌላ አይን እንዲታይ ማድረጋቸው ነው፡፡
.
ፋሽስታዊ አቋም ቀለቡ መርህ አልባነት ሲሆን ምክንያቶቹ ደግሞ ብዙ ናቸው ከነዝያ ዉስጥ ራስን ፍጹምና ከሌላው የበለጠ ወይንም የተለየ ሃገር ወዳድና ተቆርቋሪ አድርጎ በመዉሰድ ሌላዉ ግን የሚጠረጠር ፣የማይታመን፣ሃገር አፍራሽ፣ ባንዳ የመሆን እድሉ የሰፋ አድርጎ በማየት የእነሱ ጥበቃና ክትትል ብሎም ማረምያ የሚያስፈልገው አድርጎ ማሰብ አንዱ ሲሆን በማያቋርጡ የበላይነት ፍላጎትቶች መታወርና እኩልነትን መጥላት ከጥቂቱ መሃል የሚጠቀሱት ናቸው!
.
ይሄው ነው!
.
.
@followers @highlight
-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

RN.05 - Channel

12 Nov, 20:42


🚩በአንድ የእስራኤል ባለስልጣን ጡጫ የሚረግፈው የአረብ ሃገራት መሪዎች የጋራ መግለጫ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
#የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለRN05
የአረብ እና የሙስሊም ሀገራት እስራኤል ከያዘችባቸው ግዛቶች እንድትወጣ ጠየቁ። ይህንን የጠየቁት ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ ዉስጥ የአረብ እና የሙስሊም ሀገራት መሪዎች ባካሄዱት የመሪዎች ጉባኤ ማጠናቀቅያ ላይ ሲሆን ትላንት ሰኞ 10/11/2024 ባወጡት የጋራ መግለጫ ነው፡፡
.
እነዚሁ መሪዎች በመግለጫቸው እስራኤል ከያዘችባቸው የተለያዩ የአረብ ሃገራት ግዛቶች ሙሉ በሙሉ ለቃ እንድትወጣ ነው የጠየቁት። እንደፈረንጆቹ ከሰኔ 4 ቀን 1967 በፊት በነበረው የድንበር አከላለል ላይ በመመስረት "እስራኤል ከዛ በኋላ በሃይል የያዘቻቸው የተለይዩ የአረብ ግዛቶችን ይዞታ" ለቃ ካልወጣች በቀር በአካባቢው "ፍትሃዊ እና ሁሉን አቀፍ ሰላም ሊመጣ አይችልም “ ነው ያሉት በመግለጫቸው፡፡ ይህም ማለት ዌስት ባንክን ፣ምስራቅ እየሩሳሌምን ፣ የጋዛ ሰርጥን እና የጎላን ኮረብታዎችን መልሳ ትለቅላቸው ዘንድ ነው እስራኤልን በመግለጫቸው የጠየቁት፡፡
.
ከዚህ በተጨማሪም መግለጫቸው “እስራኤል የከፈለቻቸዉ የፍልስጤም አካባቢዎች ማለትም የጋዛ ሰርጥ እና ዌስት ባንክ የአንድ ፍልስጤም ግዛቶች ስለሆኑ እንዲቀላቀሉና ዋና ከተማቸዉም ምስራቅ እየሩሳሌም መሆን አለበት” ይላል። መሪዎቹ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ባስተላለፉት መልእክት ደግሞ ለእስራኤል የጦር መሳርያ ድጋፍ የሚያደርጉ ሃገራት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠይቀዋል፡፡
_____________
እነዚህ መሬት ላይ ያለዉን እዉነታ ያልተገነዘቡ የሚመስሉ ወይንም ተገንዝበዉም ቢሆን ከመግለጫና ከመጠየቅ ዉጭ ምንም አይነት ተጽእኖ መፍጠር የማይችሉ የሚመስሉት ሃገሮች መሪዎች ያወጡትን መግለጫ የማይከተልና የማይፈጽም አካል ላይ ምን አይነት ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ አልያም ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ለመግለጫችው ድምቀት ሲሉ እንኳን ሳይጠቅሱ ቀርተዋል፡፡
.
ይህ በእንዲሁ እንዳለ ሁሌም ከፈለጉትና ከተናገሩት በላይ በመፈጸም የሚታወቁት የእስራኤል መንግስት ባለስልጣናት በተቃራኒው እንኳን የያዟቸዉን የአረብ ሃገራት ቦታዎችን ሊመልሱ ቀርቶ ተጨማሪ መሬቶችን በሰፈራ ሊይዙ እንዳቀዱ በይፋ መናገር ብቻ ሳይሆን መርሃ ግብር መንደፋቸዉን አሳውቀዋል፡፡
.
በዶናልድ ትራምፕ የመጀመርያ የስልጣን ዘመን እንዲቆም የተደረገዉን በሰፈራ አማካኝነት የፍልስጤም ቀሪ መሬትን የመዉረር ዘመቻ በማስቀጠል በዌስት ባንክ አዲስ ሰፈራ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ነው የእስራኤል ቀኝ አክራሪው የፋይናንስ ሚኒስትር ስሞትሪች ያሳወቀው፡፡
.
የተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት፣ በሚቀጥለው ዓመት ለዚሁ የሰፈራ ዕርምጃ ያመች ዘንድ አስፈላጊው መሠረተ ልማት እንዲዘጋጅ በመከላከያ ሚኒስቴርና በሲቪል አስተዳደር በኩል ላሉት የሰፈራ ክፍሎች መመሪያ መሰጠቱ ነው የታወቀው፡፡ ጽንፈኛው ስሞትሪች አሁን ተግባራዊ ማድረግ የሚሻው እ.ኤ.አ. በ 2020 እንዲቋረጥ የተደረገዉንና ከ 1967 ጀምሮ ቀስ በቀስ እያካሄዱ በአሁኑ ጊዜ 30 ከመቶ ያህሉን የሸፈነዉን የዌስት ባንክ የሰፈራ ፕሮግራም ማስቀጥረል ነው፡፡ የሰፈራ ፕሮግራም ማለት በፍልስጤም ምድር ባለቤቶቹን እያባረሩ መሬታቸው ላይ ይሁዲዎችን ማስፈር ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው የእስራኤል ቀኝ አክራሪው የፋይናንስ ሚኒስትር ስሞትሪች ዌስት ባንክን የእስራኤል ሉዓላዊ አካል ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው ያለው!
.
ይህ ነው እንግዲህ የአረብ ሃገራት መሪዎች ስብስብን መግለጫ ቀልድ የእስራኤልን የአንድ ባለስልጣን ፍላጎት ደግሞ የሚጨበጥና የሚዳሰስ የሚያድርገው ዜና!
*** ከዚሁ ሳንወጣ እስራኤል በፍልስጤምና በሶርያ እየወሰደችው ያለዉን የጅምላ ጭረሳ እርምጃ አምርረው የሚቃወሙ እንዳሉ ሁሉ ከመግለጫው ጀርባ እስካሁን ድረስ በሚስጥር እስራኤልን በንግድም በዲፕሎማሲም የሚያግዙ በተለይ የአረብ ሃገራት መሪዎች መኖራቸው በስፋት ይነገራል፡፡
.
@followers @highlight
-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

RN.05 - Channel

07 Nov, 19:18


በበለጸጉ ሙስሊም ሀገሮች እየተመኩ" እስልምና አላበለጠገንም" ማለት ምን የሚሉት ነው?
~~~~~~~~~~~~~~~~
#የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለRN05
.
በሙስሊም ሀብታም ሀገሮች የገንዘብ ድጋፍ እየተመኩ ፕሮጀክቶችን የሚቀርጹት ጠቅላያችን " እስልምና በሀገራችን እንደ ቆይታው ለብልጽግና አልጠቀመንም! ድህነታችንን አላስወገደልንም!" ሲሉ ማድመጥ ከሰሞኑ ገራሚ ትዝብቶቼ መሀል አንዱ ሆኗል!
.
ጠቅላያችን በዚህ ንግግራቸው አላበለጸጉንም ያሏቸው ሀይማኖቶች እስልምናና ኦርቶዶክስ ክርስትና ናቸው። ምናልባት እሳቸው ስለሚከተሉት ስለ ፕሮቴስታንቲዝም ዝም ያሉን ወይ በሀገራችን እድሜው የሚቆጠረው ከ1950ዎቹ መጨረሻ በመሆኑ በንጽጽር ገና ለጋ ስለሆነ ሊገመገም አይገባም ብለው ይሁን አልያም "እያበለጸገን" ያለው እሱ ስለሆነ እንደሁ አላብራሩልንም!
.
ለነገሩ ሀገር ያበለጽጉ፣ ፍትህን ያነግሱ ዘንድ ተከጅለውም ሆነ በጉልበት ወንበር የሚሻሙ ነገር ግን ሀገራቸውንና ህዝብቻውን አደህይተው ራሳቸውን የሚያበለጽጉ ፖለቲከኞች ያሏት ሀገር ሁሌም ለድክመታቸው፣ ለወንጀላቸውና ለክሽፈታቸው የሆነ ሀይማኖት ወይንም ማህበረሰብን ሰበብ ማድረጋቸው የተለመደ ነው።
.
ውድ ጠቅላያችን ሆይ እሺ እነዚህ ሀይማኖቶች ናቸው ያደኸዩንና ያስራቡን እንበልና ከእርሶ ጋር እንስማማ። አሁን መንበሩ ላይ ያሉት እርሶና በሀይማኖት ከተሰላ ደግሞ ፕሮቴስታንቲዝም ነው እንበል። እንግድያው ሜዳውም ፈረሱም ይኼው እንደሚባለው ከበለጸጉ ሙስሊም ሀገሮችም ቢሆን እየወሰዱ ከቀድሞዎቹ በተሻለ ስራ ይፍጠሩልን፣ ያብሉን፣ ያበልጥጉን፣ ሀገራችንን ሰላምን እንጂ ጦርነትን የማንሰማባት ሀገር ያድርጉልን፣ሀገር ጥሎ ከመሰደድ ወጥተን ወደ ሀገራችን ለመመለስ የምንጋፋ ያድርጉን ወዘተ።
.
ያ ካልሆነ ግን ነገ እርሶ ተሰናብተው ተረኛው ሲመጣ እዛው እፓርላማ ውስጥ ዛሬ እርሶ በተቀመጡበት ወንበር ላይ ተቀምጦ እርሶንም ሀይማኖቶንም እርሶ ሌሎቹን በሰፈሩበት ቁና ሲሰፍር ፣ልክ ዛሬ እንደታዘብነው ተረኞች መታዘባቸው አይቀሬ ነው።
.
እነሆ ታሪካችን ይሄው ነው!
.
@followers @highlight
-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

1,926

subscribers

877

photos

100

videos