Ahmed Habib Alzarkawi @alzarkawi_habib Channel on Telegram

Ahmed Habib Alzarkawi

@alzarkawi_habib


Hello World

Ahmed Habib Alzarkawi (English)

Are you looking for an inspiring and educational Telegram channel to follow? Look no further than Ahmed Habib Alzarkawi! This channel, with the username @alzarkawi_habib, is dedicated to sharing knowledge, motivation, and positivity with its followers. Whether you are interested in personal development, entrepreneurship, or simply looking for daily inspiration, this channel has got you covered

Ahmed Habib Alzarkawi is a renowned figure in the world of personal development and entrepreneurship. With years of experience in coaching and mentoring, Ahmed has helped countless individuals unlock their full potential and achieve their goals. Through this Telegram channel, he shares valuable insights, tips, and advice to help you on your own journey to success

What sets Ahmed Habib Alzarkawi apart from other channels is his unique approach to personal growth. Instead of offering generic advice, he provides practical strategies that are easy to implement in your daily life. Whether you are looking to improve your productivity, enhance your leadership skills, or boost your confidence, Ahmed has the tools you need to succeed

Joining Ahmed Habib Alzarkawi on Telegram is like having a personal mentor right at your fingertips. You will receive daily updates, inspirational quotes, and exclusive content that will empower you to take control of your life and achieve your dreams. It's a community of like-minded individuals who are committed to personal growth and success

So, if you're ready to take your life to the next level, make sure to follow Ahmed Habib Alzarkawi on Telegram today. Join a community of motivated individuals who are serious about making positive changes in their lives. Get ready to be inspired, educated, and empowered on your journey to success with Ahmed Habib Alzarkawi!

Ahmed Habib Alzarkawi

11 Jan, 17:17


የኢትዮጵያ መንግስት እና የሶማሊያ መንግስት ያወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ

#PMOEthiopia

Ahmed Habib Alzarkawi

11 Jan, 13:40


የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፑብሊክ መንግስት ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባሉ !

በኢትዮጵያ ቆይታቸው በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ፣ አሕጉራዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

Ahmed Habib Alzarkawi

11 Jan, 12:08


ይህ የምትመለከቱት በመተሀራ የደረስ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ነው አላህ ህዝባችንን ይጠብቅ

Ahmed Habib Alzarkawi

09 Jan, 18:30


በጋሞ ሰማይ ሥር የታየው ያልተለመደ ብርሃን በሰማይ ላይ እንደታየ ከአካባቢው የደረሱኝ ምስሎች ያመላክታሉ። ነገሩ ተፈጥሯዊ ይሁን ሌላ ሰው ሰራሽ ክስተት አልታወቀም።

ባለፈው ሳምንት በኬኒያ ምድር ወደ 500k.g የሚጠጋ ምንነቱ ያልታወቀ ብረት ከሰማይ መውደቁ ይታወቃል።

Ahmed Habib Alzarkawi

09 Jan, 18:01


🔥🇺🇸

12.9 ሚሊዮን ዶላር ቤት

የታዋቂው ሆሊውድ ፊልም አክተር
Harrison Ford በቅርቡ በ12 .9 ሚሊዮን ዶላር

ወደ ብር ሲመነዘር :-

* 1 ቢሊዮን 622 ሚሊዮን 820 ሺህ ብር ሲሆን

በዚህ ሁሉ ብር የገዛው ቤት አይኑ እያየ ሙሉ ለሙሉ ውድሞበታል ፖሊስም በመኪና ወስደውት በእሳቱ ምክንያት ከቤታቸው ከተፈናቀሉት ስዎች ጋር ተቀላቅሏል

የእሳቱ ሰደድ ከጫቃ የተነሳ
ከተማዋን እያጥለቀለቃት ይገኛል።

Ahmed Habib Alzarkawi

09 Jan, 13:50


ስደተኛዋ አፍሪካዊት በስደት ላይ ስደተኛ ህጻን ተገላገለች

በስደተኞች ተጨናንቃ ወደ ስፔን ካናሪ ደሴት ስታቀና በነበረችው ታንኳ ላይ ተጭና የነበረችው ወሯ የገባ አፍካዊት ነብሰጡር ስደተኛ በጉዞዋ ማጠናቀቂያ ላይ ሴት ልጅ ተገላግላለች፡፡

አራሷ ከነልጇ ካናሪ ደሴት ዳርቻ በሰላም መድረሳቸውን የስፔን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ገልጸዋል፡፡

Ahmed Habib Alzarkawi

09 Jan, 13:42


ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን ለመንግስት ለማስመለስ ያስችላል የተባለው አዋጅ በፓርላማው ጸደቀ

14ኛ መደበኛ ስብሰባው ያካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ የነበረው አዋጅ ግለሰቦች በወንጀልና በሙስና እንዲሁም ሌሎች ምንጫቸው ባልታወቁ መንገዶች ያፈሩትን ንብረት የሚያስመልስ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ 10 ዓመት ወደኃላ በመሄድ የመንግስትና የህዝብ ንብረትን የሚያስመልስ የሕግ-ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ድንጋጌዎችን የያዘ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ በረቂቅ አዋጁ የተደረጉ ማስተካከያዎችና የተጨመሩ አንቀጾችን እንዲሁም ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

ሰብሳቢዋ ረቂቅ አዋጁ በወንጀል የተገኘ ንብረትና ገንዘብን ለመያዝ፣ ለማገድ፣ ለመውረስ ወይም ለማስተዳደር የሚያስችል ግልጽና ዝርዝር የንብረት ማስመለስና የማስተዳደር ሥርዓት መዘርጋትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የንብረት ማስመለስ እና መውረስ መሰረታዊ ድንጋጌዎች ወጥ የሆነ ዝርዝር የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት በንብረት ማስመለስና መውረስ ሂደት ውስጥም ሆነ ንብረቱ ከተወረሰ በኋላ የንብረቱን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ረቂቅ አዋጁ አስፈላጊ መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡

ያለ አግባብ በግለሰብ፣ በዘመድ አዝማድና ሌሎች ሰዎች ስም የተደበቀ የመንግስት እና የህዝብ ሀብትና ንብረት ለማስመለስ ከዚህ ቀደም የነበረውን የህግ ክፍተት አዋጁ እንደሚሞላ ተነግሮለታል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በአዋጁ ላይ በአስረጅ፣ በህዝብና የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ግብዓት እንደሰበሰበ አክለው ገልጸዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው ሕገ ወጥ የሆነ ሀብትን በዘመድ አዝማድ የተደበቀ፣ የተሸሸገና ምንጩ ያልታወቀ የሀገር ሃብት ወደ ኋላ ሂዶ ለማስመለስ አዋጁ ሚና እንደሚኖረው መናገራቸውን ከምክር ቤቱ ይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል አዋጁን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በዜጎች እና በባለሃብቶች ላይ ስጋት የሚፈጥር አሰራር እንዳይኖር ጥንቃቄ እንዲደረግ ፤የፍትህ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ ሆነው ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የምክር ቤት አባላት አሳስበዋል፡፡

ምክር ቤቱ የቀረበለትን የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1364/2017 አድረጎ በሶስት ተቃውሞ ፣በአራት ድምፅ ተአቅቦ ፣ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል፡፡

Ahmed Habib Alzarkawi

09 Jan, 12:13


እብዱ ትራምፕ ፣ ፍልስጤምን ገሀነም አደርጋታለሁ ብሎ ሲፎክር ሀገሩ እየነደደለት ነዉ።

Ahmed Habib Alzarkawi

09 Jan, 12:05


" በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ፡ ቤታችን ሲወድም አየሁት "
........
ሰሞኑን ካሊፎርኒያን እያመሳት ባለው የሰደድ እሳት እየተጎዱ ካሉ ከተሞች መሀል ከካሊፎርኒያ በስተ ምእራብ 48 ኪ/ሜትር ላይ የምትገኘውና ፡ ከሆሊውድ ዝነኞች ጀምሮ ታዋቂና ሚሊየነር ሰወች መርጠው የሚኖሩባት ከተማ ማሊቡ አንዷ ናት ።
........
በዚህ የ Los Angeles ሰደድ ሰደድ እሳት ምክንያት ከዚህ ከተማ ቤታቸውን ለቀው በአስቸኳይ ከወጡት መሀከል አንዷ ደግሞ ዝነኛዋ ፓሪስ ሂልተን ትገኝበታለች ።
ፓሪስ በዚህ አደጋ ቤቷን ለቃ ከወጣች በኋላ ፡ አደጋውን በተመለከተ የሚተላለፈውን የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ከቤተሰቦቿ ጋር ተሰብስበው ነበር ።
ይህ ከሆነ ከደቂቃዎች በኋላም በሰአት 80 ኪ/ሜትር የሚሄደው ሰደድ እሳት በቀጥታ ስርጭት እያየች ብዙ ትዝታ ያሳለፈችበትን የሚሊዮን ዶላሮች ዋጋ ያለውን ቤቷን ማቃጠል ጀመረ ።
.....
ይህን በተመለከተ ፓሪስ ሂልተን ስትናገር ፡ ከባለቤቴና ከልጆቼ ጋር ሆኜ ፡ ቤታችን ሲቃጠል ሳይ የተሰማኝ ሀዘን ቃላት ሊገልፁት ከሚችሉት በላይ ነው ። አሁን ብዙ አስደሳች ነገሮች ያሳለፍንበት ቤት አመድ ሆኗል ። ልጄ ፎኔክስ ዳዴ እያለ ከወዲያ ወዲህ ይልባቸው የነበሩት የቤታችን ክፍሎች በሙሉ አሁን ተረት ሆነዋል
ነበር ያለችው ።
......
ይህ ሰደድ እሳት አሁንም ግስጋሴውን አላቆመም ፡ በአለም የተደራጀ የእሳት አደጋ ማጥፊያ ካላቸው ከተሞች አንዷ የሆነችው ካሊ ባላት በሌላት አቅም እሳቱን ለማጥፋት እየሞከረች ሲሆን ለዚህም ከ223 በላይ የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪኖች ፡ ብዛት ያላቸው የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተሮች ፡ ለዚሁ የሚረዳ አሁናዊ መረጃ የሚያቀብሉ ድሮኖች ፡ እና የተለያዩ ዘዴዎች ስራ ላይ ውለዋል ።
ከዋሽንግተን 45 ተጨማሪ የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪናዎች. .ከኦሪገን 75 እና ከኒው ሜክሲኮ የተላኩ የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪኖች ዘመቻውን ተቀላቅለዋል ።
መቶ ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል ።
እንደዛም ሆኖ የሰደድ እሳቱን ማቆም አልተቻለም ። የአንቶኒ ሆፕኪንስ ቤት ፡ የጆን ጉድማን ቪላ ፡ የማይልስ ቴለር ውድ ቤቶችን ጨምሮ እስካሁን ከሁለት ሺህ በላይ መኖሪያ ወደ አመድነት ተቀይረዋል ።
.........
የማሊቡ ቅንጡ ሬስቶራንቶች የዝነኞች መናኻሪያ የነበሩ ውድ ሆቴሎች እና መደብሮች አሁን ላይ የሉም ።
.....
እስካሁን ባለው መረጃም የማሊቡ ግዛት 21 ፐርሰንት የሚሆነው በዚህ የእሳት አደጋ ተጎድቷል ።

Wasihun Tesfaye

Ahmed Habib Alzarkawi

08 Jan, 08:30


⭐️እ.ኤ.አ በ1989 በኮስታ ሪካ በሙያቸው አሳ አጥማጅ፣ አስጎብኚ እና የተፈጥሮ ተመራማሪ የሆኑት ቺቶ በሬቬንታዞን ወንዝ ዳርቻ ላይ 70 ኪሎ ግራም የሚመዝን ህይወቱን ያጣ አንድ አዞ ያገኛሉ።

⭐️በግራ አይኑ በኩል ጭንቅላቱ ላይ በጥይት ተመትቷል ። አዞው ብዙ ላሞችን እየበላባቸው ሲያስቸግራቸው በአካባቢው ከብት አርቢ ሰዎች በጥይት ተመትቶ ነበር።

⭐️በዚ መሀል Gilberto Shedden የተባለ አንድ ወጣት ይህን አዞ ቀረብ ብሎ ይመለከታል ። Shedden አዞው ሞቷል ተብሎ ቢነገረውም ደመነብሱ የአዞው እስትንፋስ አሁንም እንዳልተቋረጠች ይነግረዋል።

⭐️ከዛም Shedden አዞውን በጀልባው አድርጎ ወደ ቤቱ ይወስደዋል። Shedden ለስድስት ወራት ያህል አዞውን በሳምንት 30 ኪሎ ግራም ዶሮ እና አሳ በአፉ እያደቀቀለት መመገብ ጀመረ። ከዛም Shedden ከፈጣሪ በታች ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ የአዞው እስትንፋስ ቀጥላ አዞው እንቅስቃሴ ማሳየት ጀመረ።

⭐️Shedden አዞውን ቤቱ ውስጥ ማታ ማታ ያስተኛዋል ሼዴን እንደ ድመት እና ውሻ እንክብካቤ እያደረገለት የአዞውን ቁስል ማስታገስ ቻለ። ሼዴን በኋላ ላይ ያለውን እምነት ሲናገር ምግብ ማቅረብ ብቻውን እንዲያገግም እንደማይረዳው እና አዞው የመኖር አቅሙን ለመመለስ ፍቅሬን ይፈልጋል ብሎ ማሰቡ ለዚህ እንዳበቃው ተናገረ።

⭐️የአዞው ጤና ከተሻሻለ በኋላ ሼድን አሁን "Pocho" የሚል መጠሪያ ስም አውጥቶለት ያስታመመውን አዞ ወደ ዱር ለመመለስ በአቅራቢያው በሚገኝ ወንዝ ላይ ለቀቀው።

⭐️ነገርግን በማግስቱ ጠዋት ሼዴን ከእንቅልፉ ሲነቃ አዞው ወደ ቤቱ ተከትሎት መጥቶ በረንዳው ላይ እንደተኛ አወቀ። Shedden አዞው እንዲቆይ ለማድረግ ወሰነ፣ ሸዴንም አዞው ከቤቱ ውጭ ባለ ውሃ ውስጥ እንዲኖር ወሰነ።የሼዴን ሚስትም ሼደን ከአዞ ጋር ብዙ ጊዜ ስለሚያሳልፍ ጥላው ሄደች።

⭐️ ሼዴን መጀመሪያ ላይ ባወጣለት ስሙ መሰረት አዞው ስሙ ሲጠራ ምላሽ እንዲሰጥ አሠለጠነው። ከሃያ አመታት በላይ ሼድን ከቤቱ ውጭ ባለው ወንዝ ውስጥ በአብዛኛው ምሽት ላይ ከፖቾ ጋር ሲጫወት ሲያቅፈው፣ ሲስመው እና እየዳበሰው ይዋኝ ነበር።

⭐️በመጨረሻም ፖቾ በወርሀ ጥቅምት 2011 በሲኩሬስ ከሼደን ቤት ውጭ ባለው ውሃ ውስጥ በተፈጥሮ ምክንያት ህይወቱ አለፈ።ይሄን ግንኘነታቸውን ያወቁ የሼደን ወዳጆቹ በተገኙበት ለአዞው የተካሄደውን ህዝባዊ የቀብር ስነስርዓት ተከትሎ ሼዴን እጁን ይዞ ለአዞው ዘፈነ። የፖቾ ቅሪተአካሎቹ በሴኩረስ ከተማ ሙዚየም ውስጥ ከመስታወት በስተጀርባ ለጎብኞች ክፍት ሆነ።

Ahmed Habib Alzarkawi

07 Jan, 17:54


ጤና ሚኒስቴር የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር የአምቡላስ እንዲሁም 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የመድኃኒት እና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ ከጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ @MekdesDaba ተረክበዋል።

መቄዶኒያ ከቀናት በፊት ለሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ15 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

Ahmed Habib Alzarkawi

05 Jan, 14:22


“የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ይግባ ማለታችን የሚያበሳጩ አካላት፥ ከሻዕብያ ጋር እየተሞዳሞዱ ያሉ ሃይሎች ናቸው” -ጀነራል ፃድቃን

Ahmed Habib Alzarkawi

04 Jan, 14:25


የወንድምነት ጥግ

የጉበት ካንሰር እንዳለብኝ ሲነገረኝ ወንድሜ የሱን ግማሽ ጉበት እንደሚሰጠኝ ቃል ገባልኝ ነገርግን ከሰጠኝ በኃላ የመትረፍ እድሌ 50% ብቻ እንደሆነ ተነገረኝ የሱንም ህይወት አደጋ ላይ ጥየ ብሞት ቤተሰቦቼ ሁለት ፀፀት ይሆንባቸዋል ነገርግን የሁለታችንንም ህይወት አስይዤ ቁማር አልጫወትም ብየ መታከም እንደማልፈልግ ነገርኩት እሱ ግን በጭራሽ አንተ ሞተህ እኔ አልኖርም ሁለታችንም ጎንለጎን እኩል ሰርጀሪ ተደረግን ነገር ግን አንድ ከባድ ችግር ተፈጠረ የእኔ ቀዶ ጥገና በስኬት ቢጠናቀቅም እሱን ሰርጀሪ ሲያደርጉ ስህተት ተፈጥሮ ለ 15 ቀን ያክል በሞት እና በህይወት መካከል ሆኖ በፈጣሪ እርዳታ ከ15ቀን በኃላ ነቃ እንደነቃ ዶክተሮቹን ለማናገር አስፈቅጄ ሳናግረው ትንሽ ደክሞኝ ስለሆነ ነው አሁን ደህና ስለሆንኩ እኔን ሰርጀሪ አድርገው ይሰጡሃል አለኝ ነገር ግን በሱ ጉበት እንደቆምኩ እና በህይወት እንደተረፍኩ አላወቀም ነበር ወንድምነት እና ሰብዓዊነት መገለጫው ይህ ነው ለሰው ሲል ራሱን ያስቀደመ ሁሌም ቀዳሚ ነው
Via Underrated Thoughts

Ahmed Habib Alzarkawi

04 Jan, 13:40


ያአላህ 😱😱

Ahmed Habib Alzarkawi

03 Jan, 17:11


ብታምኑም ባታምኑም!
አዲስ ዓመትን እንዲያከብሩ እስረኞችን ፈቶ የለቀቀው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
***
ድርጊቱ ፈገግታን ቢጭርም በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ የአዲስ አመት ዋዜማን እንዲያከብሩ 13 ታሳሪዎችን ከፖሊስ ጣቢያ የለቀቀው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ የሀገሪቱ ፖሊስ የተለቀቁትን እስረኞች እያፈላለገ ነው ተብሏል፡፡

የዛምቢያ ፖሊስ አባል የሆነው መርማሪ ኢንስፔክተር ቲተስ ፊሪ የተባለው ፖሊስ በቁጥጥር ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎቹን በዋና ከተማዋ ሉሳካ ከሚገኘው ሊዮናርድ ቼሎ ፖሊስ ጣቢያ ነው ፈቶ የለቀቃቸው፡፡

ለረጅም ሰአታት በጠጣው መጠጥ በአልኮል ተጽዕኖ ውስጥ የነበረው ኢንስፔክተሩ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ከህግ ለማምለጥ ጥረት አድርጓል፡፡

ባልጠበቁት ሁኔታ ከእስር ቤት እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ታሳሪዎች በዝርፊያ ፣ ስርቆት እና አካላዊ ጥቃት በማድረስ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙ ነበሩ፡፡

በአሁኑ ወቅት ሉሳካ የሚገኘው የሊዮናርድ ቼሎ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊስ አባላት ያመለጡትን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል በአደን ላይ ይገኛሉ፡፡

የፖሊስ ቃል አቀባይ ሬ ሀሙንጋ ድርጊቱን የፈጸመው ኢንስፔክተር ቲተስ ፊሪ በአዲስ አመት ዋዜማ ተረኛ የእስረኞች ጠባቂ ከሆነችው የፖሊስ አባል የእስር ቤቶቹን ቁልፍ በሀይል እንደቀማት ተናግረዋል፡፡

በመቀጠልም ኢንስፔክተሩ የወንድ እና ሴት የእስር ቤት ክፍሎችን በመክፈት "ወደ አዲሱ አመት ለመሻገር ነፃ ሆናችኋል" በማለት ከእስር ቤቱ እንዲወጡ እንዳዘዛቸው ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡

በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ ያልተጠበቀውን ድርጊት የፈጸመው መርማሪ ኢንስፔክተር ወዲያው ከአካባቢው ለመሸሽ ቢሞክርም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ኢንስፔክተሩ ድርጊቱን ለምን እንደፈጸመ እስካሁን ቃሉን እንዳልሰጠ የተገለጸ ሲሆን ፖሊስ በበኩሉ ከእስረኞቹ መለቀቅ ጀርባ የስካር ስህተት ወይስ ድብቅ ዓላማ ያለው የተቀነባባረ ድርጊት የሚለውን ለማጣራት በምርመራ ላይ እገኛለሁ ብሏል፡፡
አልአይን

Ahmed Habib Alzarkawi

03 Jan, 16:05


> "መልእክተኛው የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት የከለከላችሁንም ነገር ራቁ" (አል-ሐሽር 7)።

ይህ የአላህ ቃል ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያመጡትን ሁሉ ወስዶ ከከለከሉት ነገር እንድንታቀብ ግልጽ ትእዛዝ ነው።

3."مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ" [النساء: 80].
> "መልእክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህንም ታዘዘ።" [አን-ኒሳእ 80]።

ከዚህ አንቀጽ ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መታዘዝ ሁሉን ቻይ ለሆነውን አላህ ከመታዘዝ ጋር እኩል መሆኑን እንረዳለን ።

4. "فَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَن تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ" [النور: 63].

> "እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ ፈተና እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳትደርስባቸው ይጠንቀቁ።" (አል-ኑር፡ 63)።

ይህ አንቀጽ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አለመታዘዝ በፈተናም ይሁን በስቃይ ከባድ መዘዝ የሚያስከት መሆኑን የሚያስገነዝብ ማስጠንቀቂያ ነው ።

5. "لَقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ" [الأحزاب: 21].

> "በላህንና በመጨረሻው ቀን ለሚያምን ሰው እንዲሁም ከአላህ መልካምን ለሚከጅል ሰው በአላህ መልእክተኛ መልካም ምሳሌ አልላችሁ።" [አል-አህዛብ፡ 21]

ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ፍፁም አርአያ ናቸው።

Ahmed Habib Alzarkawi

03 Jan, 13:40


500 ኪ.ግ የሚመዝን የጋለ ብረት መውደቁ ተነገረ
በአጎራባቿ ኬንያ 500 ኪሎ ግራም ሊመዝን የሚችል ብረት ከሰማይ ወድቋል ነው የተባለው።

ቀለበታማ ብረቱ የወደቀው ሙኩኩ በተሰኘች መንደር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ብረቱ የ2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ወይም ዲያሜትር ያለው መሆኑ ተመላክቷል።

የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ብረቱ በስፔስ ላይ ከሚገኙ ሮኬቶች ተገንጥሎ የወደቀ ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።

Ahmed Habib Alzarkawi

03 Jan, 08:27


#አፋር በተደጋጋሚ ሲከሰት የነበረን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ዛሬ ጧዋት በአፋር በዱለሳ ወረዳ ሰገንቶ ቀበሌ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ተከስቷል።

Ahmed Habib Alzarkawi

01 Jan, 15:40


በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚፈፀሙትን የመብትና የሃይማኖት ጥሰቶችን በሚመለከት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ !!

Ahmed Habib Alzarkawi

29 Dec, 18:09


ኢሳያስን እንደ አሳድ

ኤርትራ ኢትዮጵያን ከባህር ለመነጠል የተመሰረተች አጥር እንጂ ሀገር አይደለችም ሆናም አታቅም ። የኤርትራ ህዝብም በነፃነት ስም ከሁለት ያጣ ሀገር አልባ ስደተኛ እንጂ የኤርትራ ዜጋ ሚባል የለም ። ኢሳያስም ቢሆን በገንጣይ አስገንጣዮች ጀርባ ታዝሎ የኢትዮጵያን ህዝብ አለመግባባት ተጠቅሞ ኢትዮጵያን ባህር አልባ ከማድረግ ያላላፈ ሽፍታ እንጂ 34 ዓመት ሙሉ መሪ ሆኖ አያቅም መሆንም አይችልም ።

እነኚህን እውነታዎች ማንም ቢሆን የሚክደው ሀቅ አይደለም ኤርትራ በአሁን ዘመን በምድሯ ምንም ዩኒቨርስቲ ገብቶ ተምሮ ዲግሪ ያለው
ወጣት የሌለባት የአለማችን ብቸዋ ማህይምነት የዋጣት አጥር ናት።

ኢሳያስ ካይሮ ከመሰረተችው ጄባሃ ተፈልቅቆ በትግሪኝ ወጣቶች ደም ኢትዮጵያን ባህር የማሳጣት ተልዕኮውን ተወጥቶ ካበቃና ስራውን ጨርሶ አዲ-ሃሎ ቤተመንግሥት ከገባ በውሃላ የኤርትራን ህዝብ ጣሊያን በባርነት ከያዘው በላይ አደድቦ በስቃይ ከዓለም ነጥሎ ከመያዝ ውጪ የሰራውም መስራት የሚችለውም የፈጠረው የሚፈጥረው ሀገር የለም! ያለፉት 34 ዓመታት ምስክር ናቸው ።

በመሆኑም ይህ የኢትዮጵያን ከባህር ነጥሎ የኤርትራን ህዝብ የባህር ሻርክ እራት ያደረገው ኢሳያስ አፈወርቂ ልክ እንደ አሳድ ሁሉ ከውስጥም ከውጭም በሚደርግ ብዙ ግዜ የማይጠይቅ እንቅስቃሴ መወገድ አለበት ።

እንዴት :- እንደሚታወቀው ኢሳያስ የደርግ መንግስትን ከአደዋ ጀሌዎቹ ጋር ሆኖ አስወግዶ ኢትዮጵያ ባህር አልባ አርጎ በተገነጠለበት መንገድ ።

አዎ ኢሳያስ በራሳችን ዜጎች ላኪዎቹ ባዘጋጁልን ገዢ አዲስ አበባና አስመራ ላይ ዶልተው የኢትዮጵያን ባህር ይዞ እንዲገነጠል ተፈራርመው ባደረጉበት መንገድ ኢትዮጽያ የኤርትራን ህዝብና የኢትዮጵያን ባህር ነፃ የሚያወጣ ፈርሞም ወደ ኢትዮጵያ ሚመልስ መሪ አዘጋጅተን ወደ ስራ መግባት አለብን።

ተመናምኖ አሮጊትና ጥቂት ሴቶች የቀሩት የኤርትራ ህዝብና የሳዋ ርሃብ ያጠወለጋቸው ጦሩም ቢሆኑ በአሁኗ ቅፅበት ከኢሳያስ ባርነት ነፃ የሚያወጣው ሰይጣንም መልዓክም ቢመጣ በእልልታ ከመቀበል ወደ ኋላ አይልም ። ምን የኤርትራ ህዝብ ብቻ የአለም አቀፉ መሃበረሰብና ተቋማትም ጭምር ይህን የቀጠናውን ነቀርሳ መወገድ ልክ እንደ አሳድ ሁሉ በጭብጨባና በእልልታ ነው ሚቀበለው ።

ቱርክዬ አሳድን ለማስወገድ የተጠቀመችውን ቀመር ኢትዮጵያ እንደ ልምድ በመውሰድ የጃጀው ኢሳያስ ላይ መጠቀምና የኢትዮጵያን ባህር ፈርሞ የሚመልስ መሪ ህዝቦቻችንን በጋራ የሚያሳድግ ስትራቴጂ መጠቀም ይርባታል።

ለብዙዎች ኢሳያስ ጠንካራ መስሎ ለመታየት ጥረት ቢያረግም ነገር ግን እውነታው ለኢሳያስ ልክ እንደ ባድመው መስዕዋት የሚሆን በቂ የቆረቆዘ ጦር እንኳን የለውም ፤ በዛ ላይ የባድመው ጦርነት ላይ የነበረ የፖለቲካ የኢኮኖሚና የስነ ልቦና አቅም የለም፤ ኢሳያስ የህዝባዊ ድጋፍና የወጣት ጉልበት አቅሙም ዜሮ ገብቷል ። ለዚህም ነው ትንሽ ኮሽ ባለ ቁጥር ወደ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ካይሮ ተንደርድሮ ሄዶ ሚወሸቀው ነገር ግን ግብፅ የአህያ ባል ናት ከምንም አታስጥልም በዚህም የሱዳኑን አልቡርሃንን ግብፅን ተማምኖ ከኖረበት ከካርቱም ቤተ-መንግስት መፈናቀልን ማመሳከር የቅር ግዜ እውነታ ነው።

ወደ ዋናው ጉዳይ ስንገባ ኢሳያስና ላኪዎቹ ኢትዮጵያ ብትንትኗ ካልወጣ ኢትዮጵያን እንደህልውና ስጋት ቆጥሮ ማሴሩን ተኝቶ አለማደሩን አያቆምም። ኢትዮጵያ ይህ የሰሜኑ የመርዝ ሰንኮፍ ካልተነቀለ ሰላም ሚባል አታገኝም። ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ አይደል ሚባለው ።

የኢትዮጵያ በራሷ ሰዎች ባህሯን ተፈርሞ ባጣችበት መንገድ በተመሳሳይ ፈርሞ ሚመልስ መሪ አዘጋጅታ በራሷ ሃይ እንደተዋጋችው ኢሳያስን በራሱ መዋቅርና ሃይል ከውጪም ከውስጥም ለመጣል ቆርጣ በይፋ መነሳት አለባት። ይህንን የሚያክል ህዝብና ሀገር ያላት ኢትዮጵያ የሚጢጢዎች መጫዎቻ መሆኗ ሊያበቃ ይገባል።

የሚጢጢዬ ተላላኪ ጠላቶቻችንን አጀንዳ መቀበል የየዋህና የፈሪ ፖለቲካ አቁመን አጀንዳችንን ወደ የኢትዮጵያ ሰላም ማጣት ምንጮች ማዞር አለብን ።
አሰብ የኢትዮጵያ መሆኑን በአደባባይ መናገር በአደባባይ መፃፍ በአደባባይ ታጥቀንም አስታጥቀንም መንቀሳቀስ አለብን ! አለበዚያ ብንፈልግም ባንፈልግም ከ120 ሚሊየን ህዝባችን ላይ የተነጠቀው ባህራችን ኑና አስመልሱኝ እያለ እኛኑ ሰላም መንሳቱን አያቆምም።

ኢሳያስ በየትኛውም መንገድ በኢትዮጵያ ፊት አውራሪነት ቢወገድ ..ከተመድ እስከ ኢጋድ በጭብጨባና እልልታ የሚቀበሉት፣የኤርትራ ህዝብ በከበሮ የሚጨፍርበት፣
የግብፅ እጅ ሚቆረጥበት ምስራቅ አፍሪካ ሰላም የሚያገኝበት ፣ኢትዮጵያ ባህሯን ተረክባ በእውነትም የተስፋይቱ ምድር የምትሆንበት እውነታ ብቻ ነው ሚፈጠረው ።

እንንቃ ሰላማችንን ከምንጩ እናስመልስ !

Ahmed Habib Alzarkawi

29 Dec, 16:28


ቻይና የምድራችን ግዙፉ ግድብ ልትገነባ ነው ..🇨🇳

ቻይና በራስ ገዟ ቲቤት ውስጥ ያሉ ማህበረሰቦችን መፈናቀል እና በህንድ እና በባንግላዲሽ የታችኛው ተፋሰስ ላይ ያለውን የአካባቢ ተፅእኖ ስጋት ለመቀነስ የዓለማችንን ትልቅ የውሃ ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ አድርጋለች።

በያርንግ ቻንግፖ ወንዝ ታችኛው ተፋሰስ ላይ የሚገነባው ግድቡ በአሁኑ ጊዜ በአለም ትልቁ የውሃ ሃይል ማመንጫ ከተባለው `የስሪ ጎርጅስ ግድብ'' በሶስት እጥፍ የሚበልጥ ሃይል ሊያመነጭ ይችላል ተብሏል።

የቻይና መንግስት ልማቱን "ሥነ-ምህዳራዊ ጥበቃን ቅድሚያ የሚሰጥና ደህንነቱ የተጠበቀ ፕሮጀክት" ሲል ገልጾታል። ይህም የአካባቢ ብልጽግናን እንደሚያሳድግ እና ለቤጂንግ የአየር ንብረት ግቦች አስተዋፅኦ ያደርጋል ብሏል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ባለሙያዎች ልማቱ እያስከተለ ስላለው ጉዳት ስጋት አለን ያሉ ሲሆን፤ የግድቡ ግንባታ እኤአ በ2020 መገባደጃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ሲሆን የአካባቢውን ማህበረሰቦች ያፈናቅላል። አልፎ ተርፎም የተፈጥሮን ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ የሚለውጥና በተፈጥሮ የበለፀገ ነው የሚባልለትን የቲቤት ሸለቆ ስነ-ምህዳር የሚጎዳ ነው ብለዋል።

የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቤጂንግ በቲቤት እና በመሬታቸው ላይ የምታደርሰው ምዝበራ እየጨመረ መጥቷል ሲሉ ይከሳሉ፡፡

አንዳንዶች በርካታ መንደሮችን የሚያፈናቅል እና ጥንታዊ ገዳማትን በንዋየ ቅድሳት ላይ ጉዳት ያደርሳል ያሉትን የጋንግቱኦ ግድብ እና የውሃ ሃይል ማመንጫ የመገንባት እቅድን ሲቃወሙ ቆይተዋል።

ቤጂንግ ግን በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ አካባቢ ከማዛወሯ ባሻገር ለነዋሪዎቹ በቂ ካሳ እንደከፈለች አስታውቃለች።

የያርንግ ቻንግፖ ግድብን በተመለከተ የቻይና ባለስልጣናት ፕሮጀክቱ የአካባቢ ተፅእኖ እንደማይኖረው ተናግረው ምን ያህል ሰዎችን እንደሚያፈናቀል ግን አልገለጹም።

የወንዙን ኃይል እንደ ታዳሽ የኃይል ምንጭነት በመጠቀም ቻይና ባለፉት አስር አመታት በያርንግ ዛንግፖ ግዛት ውስጥ በርካታ የውሃ ሃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ገንብታለች።

የወንዙ አስደናቂ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ግን ትልቅ የምህንድስና ጥበብ ይዞ ይመጣል የተባለ ሲሆን ግንባታው በስኬት ከተጠናቀቀ በቻይና ትልቁ እና ከፍተኛ ሀይል የሚያመነጭ ግድብ እንደሚሆን ይጠበቃል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ፕሮጀክቱ አንድ ትሪሊየን ዩዋን ወይም 127 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በጀት ተይዞለታል።

Gazette Plus

Ahmed Habib Alzarkawi

26 Dec, 16:01


አሁን በአለም ላይ በስፋት የተሰራጨ ዜና.💔💔

በአዘርባጃን የደረሰው የአውሮፕላን አደጋ አሳዛኝ ክስተት ነው።

በአውሮፕላኑ ውስጥ ወደ 67 የሚጠጉ ተሳፋሪዎች የነበሩ ሲሆን ወደ 30 የሚጠጉ መንገደኞች ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ መትረፋቸውን እና በምስሉ የሚታየውን ሰው ጨምሮ በርካታ ሙስሊም መንገደኞች እንደነበሩ ታውቋል።

ከአውሮፕላኑ አደጋ ደቂቃዎች በፊት ይህ ሰው በአውሮፕላኑ አደጋ እንደሚሞት በማመኑ ሸሀዳ ሲይዝና ተክቢራ ሲያደርግ የሚያሳይ ቪዲዮ ቀርፆ ለሚስቱ ልኮ ነበር ።

ነገር ግን በተአምር ከአውሮፕላኑ አደጋ ከተረፉት ሰዎች አንዱ ይህ ሰው ሆኗል። #ሱብሃን_አላህ

Ahmed Habib Alzarkawi

22 Dec, 18:40


የቢቢሲው ጋዜጠኛ አስገራሚ ጥያቄ


አርባ ሺህ ንፁሐን በሃማ ከተማ በሃፊዝ አል አሰድ በግፍ እየተሞሸለቁ ከመሬቱ ተጣሉ። ጀናዛቸው ተቃጥሎ አመዱ ይደፋ ዘንድ ተፈረደባቸው። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ በልጁ የቀብር ጉርጓዳቸው ተማሰላቸው። አስራ ሶስት ሚሊዮን ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ተፈናቀሉ። በኬሚካልና በፈንጂ በርሜል ነደዱ። ስደተኛ ካምፕ ውስጥ የተጠለሉ ደካሞች እንኳ አልቀሯቸውም ከሰማይ ከምድሩ በቦምብ እየደበደቡ ዕለት ተዕለታቸውን በሰቀቀን ሰቆቃ አኖሯቸው። ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች የገቡበት ታጣ። ስለ እጣ ፈንታቸው ከአላህ በስተቀር ማንም የሚያውቅ ጠፋ። የሰይደናያ እስር ቤት በሮቹ ሲከፈቱ ስለ እስር ቤት የተፃፉ ድርሳናት ሁሉ ገፆቻቸው በአንድ ተጨፍልቀው የዚህን እስር ቤት አንድ ምዕራፍ እንኳ እንደማይወጣቸው ዓለም ተገነዘበ።

ከሃምሳ የግፍ ዓመታት በኋላ የሶሪያ አብዮት አሸነፈ። የቤት ባለቤቶቹ ወደየቀያቸው ተመለሱ። ከቤተሰቦቻቸው ጋር ዳግም ወደ ትዝታቸው አቀኑ። ድላቸው እጅግ ምህረትን ከተላበሱ ድሎች አንዱ ሆነ። ለሃምሳ አመታት በመከራዎች እቶን ሲቀጧቸው የነበሩትን ሁሉ ይቅር አሏቸው። መሳርያ ያነሱባቸው እንኳ ሳይቀሩ ኢዝሀቡ ፈአንቱሙ ጡለቃእ እያሉ ሸኟቸው።

ደማስቆ ከመላው አለም በመጡ ዲፕሎማቶች ተጥለቀለቀች። የቴሌቭዥን ቻናሎች ስለእነሱ ለፈፉ። የዜና ማሰራጫዎች ቀዳሚ ሆነው ከፊት ተሰለፉ። ቢቢሲ ከአህመድ አሽ-ሸርዕ ጋር ቃለ ምልልስ አደረገ። አስገራሚ ጥያቄዎችን ይዞ ብቅ አለ። አህመድ በሚሰጠው መልሶቹ ይህ አለም ምን መስማት እንደሚፈልግ ያወቀ ይመስላል። ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ መልስ ለመስጠት እንዳሰበ ያሳብቃል። ሁለት ጥያቄዎች ግን አስገረሙኝ፡-
"ሴቶች እንዲማሩ፣ ሰዎች አልኮል እንዲጠጡ ትፈቅዳላችሁ?" ሲል የቢቢሲው ጋዜጠኛ ጠየቀ።

ስለሶሪያ ሴቶች በህይወት የመኖር መብት ደንታም የሌለው የምዕራቡ ዓለም ስለሶሪያ ሴቶች የመማር መብት ተጨነቀ። አስራ ሶስት አመታት በፈንጂ በርሜል በኬሚካልና በድሮን ሲጨፈጨፉ ድምፁ ያልተሰማው፣ አሥራ ሦስት ዓመታት ልጆቻቸው ታስረው ሲደፈሩ ዝም ጭጭ ያለው፣ አንድም ጉባኤ ያላደረጉት ፌሚኒስቶች ዛሬ ከየተደበቁበት ወጡ። አሳቢ መስለው ብቅ አሉ። የሶሪያ ሴቶች የመማር መብት ይኖራቸው ይሆን?! ሲሉ ጠየቁ።
ውሸታም! ቀጣፊ!

የአፍጋኒስታን ሴቶችን ገድለው ደፍረው ጨፍጭፈው ሲያበቁ ሀገሩን ለቀው ሲወጡ ሴቶች እዚያ ምድር ይበደላሉ የመማር መብታቸው ይከበር ሲሉ በሚዲያቸው የጮኹት ማን ሆኑና?!

440 ቀናት የጋዛ ሴቶች ሲያለቅሱ የተደበቁ፣ እንደ ሰወኛ አዝነው ዱቄት እንኳ ያልላኩ፣ ጦርነቱ ሲያበቃ የጋዛ ሴቶች ሊጠየቅላቸው የሚገቡ መብቶች አሏቸው ሊሉን ይመጣሉ።

"ሰዎች አልኮል እንዲጠጡ ትፈቅዳላችሁ?!"
ገዳያቸው አይኖቻችሁ እያየ ደማቸውን ሲጠጡ የት ነበራችሁ?! ወንዶቻቸው እስር ቤት ውስጥ ሲዋረዱ፣ ሴቶቻቸው ግፍን ከመራራው ሲጎነጩ፣ ልጆች በእንባቸው ሲታነቁ፣ ልጃገረዶች ሲደፈሩ ሰቆቃቸው እንዲሰማ በመስጂድ ድምፅ ማጉያ እያስተጋቡ በስቃያቸው ሲረኩ ከቶ የት ነበራችሁ?!

ለሃምሳ አመታት የፈለጉትን ያደርጓቸው ዘንድ ለገዳዮቻቸው አልተዋችኋቸውምን?! ህዝቡ ባመፀ ጊዜ ወታደሮቻችሁን ልካችሁ የነዳጅ ትቦውን እንዲጠብቁ ሰራዊታችሁን አላሰማራችሁምን?! አሁን ስለሴቶች የመማር መብት ልትጠይቁ እንዴት ብቅ አላችሁ?! ማፈርያ!


Mahi Mahisho

Ahmed Habib Alzarkawi

20 Dec, 13:37


የ10 ሚሊዮን ብር አሸናፊ የሚያደርገው የመጨረሻና ወሳኝ ድምጽ በእርሶ እጅ ነው። BIW02 በማለት ወደ 9355 አጭር ቁጥር ድምጽ ይስጡ።

በአንቴክስ ኢትዮጵያ ሸላሚነት በተዘጋጀው BIWs Prize የሽልማት ፕሮግራም በኢኮኖሚ ዘርፍ

ከሌሎች አራት ተወዳዳሪዎች ጋር እጩ ሆኜ በመቅረቤ የተሰማኝ ደስታ

በትላንትና የአፍላ እድሜ ህልም እና ትጋት ፣ በዛሬ ውጤት እና በነገ ተስፋዬ መዳረሻ ላይ አብራችሁን ስታበረቱኝና አቅም ስትሆኙ የነበራችሁ በሙሉ እናንተው ነበራችሁና ይህ የእናንተም ድምር ውጤት ነው።

ይህንን ታሪካዊ ውድድር በጋራ እናሸንፍ ዘንድ የተሰጠንን መልካም እድልና አጋጣሚ እንድንጠቀምና አሸናፊ መሆን የሚያስችለን የድምጽ አገኝ ዘንድ በቴክስት አጭር ቁጥር 9355 BIW02 ብለው በማለት መምረጦን ሚያረጋግጥ አጭር መልዕክትን ልብ በማለት ድምጾን እንዲሰጡኝ ከታላቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ።

ድምጾን ስለሚሰጡ ልባዊ ምስጋናዬንና አክብሮቴን አቀርባለሁ።

የኔ ትውልድ ያሸንፋል

Ahmed Habib Alzarkawi

11 Dec, 18:17


Breaking news : ሶማሊያ የግብጽና ኤርትራን እገዛ ተጠቅማ በኢትዮዺያ ቦርደር አከባቢ ለግብፅ ካንፕ ለመመስረት የነበረው ህልም ተግባራዊ ለማድረግ ያሰበችው መክሸፉ ይታወሳል ። በሌላ በኩል በቅርቡ ሀሰን ሸክ ግብፅን ተጠቅሞ ላለፉት 10 ቀን በራስ ካንቦኒ ያራገፈው ጦር በጁባ ላንድ ጀግኖች ተደምስሰዋል ።

Ahmed Habib Alzarkawi

10 Dec, 17:37


ሰበር!!

የሶማሌላንዱ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎችን ስራ አስጀመረ።

Ahmed Habib Alzarkawi

07 Dec, 18:19


የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
****

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማዕከሉን ጠቅሶ እንዳለው፥ የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጠይቋል።

Ahmed Habib Alzarkawi

25 Nov, 14:42


ከኢትዮጵያ ጋር የተጋጨው የሞቃዲሹው ፕሬዚዳንት ከባድ ችግር ውስጥ ገብቷል!!

በማይመለከተው ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር የተጋጨው የሞቃዲሹው ፕሬዚዳንት ሃሰን መሐመድ ከባድ ችግር ውስጥ ገብቷል። የቤተመንግሥቱን አካባቢ እንኳን መጠበቅ የማይችለው የፕሬዚዳንት ሃሰን ሼኅ መሐሙድ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ በማይመለከተው ጉዳይ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳውን ሲነዛ ከርሟል። አሁን ለራሱም ችግር ውስጥ ገብቷል። ለሶማሌላንድ እያለቀሰ ተጨማሪ ሁለት ክልሎች ከእጁ ወጥቷል። ፑንትላንደ በቅርቡ ምርጫ አካሂዳ የነበረ ሲሆን ጁባላንድም በዛሬው ዕለት ምርጫ በማካሄድ አህመድ ማዶቤ የጁባላንድ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመርጧል።

አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/alzarkawi_habib

Ahmed Habib Alzarkawi

24 Nov, 16:44


የማይተኙልን ጠ*ላ*ቶቻችን!!

የኤርትራ መንግስት ለግብፅ በአሰብ የጦር ቤዝ እንድትገነባ ፍቃድ መስጠቱን ተከትሎ የግብፅ ከፍተኛ የጦር ጀነራሎችና ባለስልጣናት ላለፉት ቀናት በአሰብ ኦፊሻል ያልሆነ ጉብኝት ማድረጋቸው ከአሰብ ምንጮቼ ደርሶኛል። የኢትዮጵያ ቋሚ ጠ*ላ*ት ለሆነችው ግብፅ ኢትዮጵያ አፍንጫ ስር የጦር ቤዝ መስጠት በነሱ ቤት ኢትዮጵያን ለማስፈራራት መሆኑ ነው።

ግን ይሄ ጊዜ ያለፈበት የአይምሮ መቀንጨር ያጋጠማቸው አረጋውያን መሪዎች ሃሳብ። ኢትዮጵያ በቀጠናው ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር የምትደርገውን እንቅስቃሴን የሚያደናቅፍ አለመሆኑን ቢያወቁ ይሻላቸዋል።

Ahmed Habib Alzarkawi

🇪🇹🇪🇹 ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹

Ahmed Habib Alzarkawi

14 Nov, 14:36


መልካም ዜና ከአፋር ...🇪🇹🙏

የአፋር ህዝብ እና መሪው ሃጅ አወል አርባ የሀገር ጉዳይ ሲነሳ እንደ ንብ ናቸው። የሰላም ጥሪ ሲመጣ ደግሞ ከማንም በላይ ለሰላም ይጨነቃሉ። አሁንም የፈለገ የፖለቲካ አጀንዳ ልዩነት ቢኖርም። እንደሚታወቀው የአፋር ህዝብ ይቅርታን ያስቀድማል። በዛሬው እለትም የክልሉ ቀድም ፕሬዝዳንት ሀጅ #ስዩም ወደ ክልላቸው ተመልሰው ከፕሬዚደንት ሃጅ አወል አርባ ጋር ተገናኝተዋል። የፌዴራሊስት ሃይል ታጣቂዎችም በሰላም ትጥቃቸውን አስረክበዋል። በሰላም ወደ ህዝባቸው ለመመለስ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እና የክልሉ የፀጥታ መዋቅርም በብቃት እየሰራና ሰላማዊ ርክክቡን እየመራ ይገኛል የክልሉ ፕሪዝዳንት ሀጂ አወል አርባ ለሰላም ያላቸው ቦታ ትልቅ ስለሆነ በቦታው ተገኝተዋል።
ሰላም ለሀገራችን
ሰላም ለአፋር ህዝብ
ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ።

Ahmed Habib Alzarkawi

Ahmed Habib Alzarkawi

08 Nov, 13:51


የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ሀጅ አወል አርባ የሰመራ የኮሪደር ልማት ስራ በይፋ አስጀምረዋል!!!

ፕሬዝደንት ሀጅ አወል አርባ እንደገለፁት የኮሪደር ልማት የሰመራ ከተማን የመሠረተ ልማት አውታሮችን ለማስፋፋት እና የህዝብ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ከማገዝም በላይ የከተማችንን ገፅታ ውብ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
Ahmed Habib Alzarkawi

Ahmed Habib Alzarkawi

01 Nov, 19:57


ሰበር !
አስፈሪና ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ከምሽቱ 3:55 ደቂቃ ላይ አፋር ክልል በአዋሽ ተከስቷል አላህ ይጠብቀን😭

Ahmed Habib Alzarkawi

11 Oct, 17:58


ወይ ው'ር'ደ'ት 😜 ኤርትራ የሶማሊያን ሰንደቅ አጥታ ሰማያዊ ልብስ ላይ በወረቀት የተሰራ ኮከብ በፕላስተር ለጥፋ ዱቅ አድርጋለች። የተንኮልና የሴራ የማስመሰል የውሸት ጋብቻ መጨረሻ ው'ር'ደ'ት ነው 😜😜

Ahmed Habib Alzarkawi

10 Oct, 20:01


በአፋር ክልል ከመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ የተፈጠረው አስደንጋጭ ክስተት ሊንኩ ላይ ገብታችሁ ተመልከቱ Follow ማድረጉን አትርሱ መረጃዎችን ታገኙበታላችሁ 👇👇
https://www.tiktok.com/@alzarkawi96?_t=8qR5x1QjVHJ&_r=1

Ahmed Habib Alzarkawi

08 Oct, 19:28


የአሜሪካ መንግስት በአስቸኳይ ከተማውን ለቃችሁ ውጡ ብልዋል 🌀🇺🇸

Hurricane Milton
እስካሁን ከተከሰቱ አውሎ ንፋሶች እጅግ የላቀ ደረጃ 5 ያሟላ ነው የተባለው ከፍተኛ ፍጥነትና ጉልበት ያለው ያገኘውን ሁሉ ጠራርጎ የሚወስድ Hurricane Milton እጅግ አደገኛ አውሎ ንፋስ አሜሪካን እያመሳት ይገኛል የአሜሪካ መንግስት ዛሬ በሰጠው መግለጫው አውሎንፋሱ በከፍተኛ ወደ ፎሎሪዳ #ታምፓ ከተማ እየመጣ ስለሆነ የከተማው ነዋሪዎች በአስቸኳይ ከተማውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መተላለፉን ዴይሊሜይል ዘግቧል።

አለማችን እንግዳ የሆነ የተፈጥሮ ክስተቶችን እያስተናገደች ትገኛለች አላህ ይጠብቀን።

Ahmed Habib Alzarkawi

Ahmed Habib Alzarkawi

08 Oct, 16:09


የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ...🇪🇹

የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ለፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት መካከል ያለውን የትብብር መንፈስ ወዳጅነት እና ግንኙነት አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ተመኝተዋል።

Ahmed Habib Alzarkawi

Ahmed Habib Alzarkawi

08 Oct, 16:08


#የነዳች_ምርቶች_የችርቻሮ_መሸጫ_ዋጋ

ከመስከረም 28 ቀን 2017 ዓም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሚተገበር በሁሉም የነዳች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣዊ ትስስር ሚኒስቴር ለኢፕድ በላከው መረጃ አሰታውቋል።

Ahmed Habib Alzarkawi

08 Oct, 14:34


ሰበር!!

ሰሞኑን በአፋር ክልል በዞን ሶስት በተለየዩ አካባቢዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ መፈጠሩ የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህ ቦታዎቹ ሰጋንቶ ቀበሌ አንዱ የእዚህ ተጋላጭ ነበር በመሆኑም በዛሬው እለት ቀን 28/1/2017 በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከመሬት ወስጥ የወጣው ፍል ወሃ በምስሉ ይሄን ይመስላል።በዚህ አከባቢ እሳተጎሞራ ሊፈጠር ስለሚችል የዘርፉ ባለሞያዎች እዚህ አከባቢ ትኩረት ቢያደርጉ እንላለን።

Ahmed Habib Alzarkawi

Ahmed Habib Alzarkawi

06 Oct, 18:35


ተረጋግጧል....🩸🩸

በፈንታሌ ተራራ ላይ የተከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ ሲሆን በአፋር፣ ምእራብ ሀረርጌ፣ ምስራቅ ሸዋ እስከ አዲስ አበባ ንዝረቱ ተሰምቷል።

Ahmed Habib Alzarkawi

06 Oct, 17:59


በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች!!