...................ኦርቶዶክሳዊነት.መባልዕት
.. በኢትዮጵያዊነት ዐይን እና ትውፊት.............. ..............
የማያነብ ሰው ጥያቄው አያልቅም።ጥያቄዎ እንዲቀንስ ይፈልጋሉ? እንግዳማ ትንሽ ትንሽ ያንብቡ መልካም ንባብ
.........የሚበሉ እና የማይበሉ መብሎች አሉን?
............... በትክክል..። ...............................
..........የመጀመሪያው የቤ/ክርስቲያን ጉባኤ !!!
በታሪክ ሰው የወደቀው በመብል ምክንያት ሲሆን ሰው ደግሞ የዳነው በመብል ነው።በታሪክ"የመጀመሪያውን የሐዋርያትጉብባኤ እንዲደረገ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የሚበላና የማይበላ ነበር ። ፍጥረት ሁሉ ለሰው የተፈጠረ ነው። ሰውም በመጨረሻ 22ኛ ፍጥረት ሁኖ መፈጠሩ የሚወዱትን እንግዳ ሁሉን ካዘጋጁ በኋላ ወደ ቤት እዲጠሩት አዳምንም ሥላሴ ሁሉን ከአዘጋጁለት በኋላ እንደ ፈጠሩት ያጠይቃል። ቅ/ኤፍ ድር"
አትባላ" ሕግ ቀዳማዊ ነው። #
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ" ብሎ አዘዘው ። ከገነት ዛፍ ኹሉ ትበላለህ። ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ። ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና ዘፍ ፪፥፲፮
ከላይ በአንቀጹ እንደተመልከትነው በሰው ልጅ ውስጥ ከተሠሩ ሕጎች ቀዳሚው ሕግ " ብላ እና አትብላ " ናቸው። ይህንን ብላ ይህንን አትብላ " የሚል ሕግን የተሸከመ፤ የፍጡር እና የፈጣሪ ፦ የገዢና የተገዢ የፍቅር ምልክት ሁኖ የተቀመጠው ጥንተ ጾም የነበረው ይህ አትብላ" የሚለው ሕግ ነው።ስለዚህ ያ ሕግ በመፍረሱ ሰው ወደዚህ አይናት አሁናዊ ጉዞ እንዲመጣ ግድ ሁኗል።
"ያ" እጸ በለስ ርኩስ ሁኖ መርዝ ኑሮበት አይደለም። እንዲያውም የፍቅር ምልክት ነው። እግዚአብሔር
ተቆጥረው የማያልቁ ዛፎችን ሰጥቶ፤ 99% ፐርሰንት ብላ" ብሎ፥ እንዲያው አንድ ፐርሰንት የማይሆነውን (የግሌ) ግን ለፍቅራችን ምልክት ተውልኝ ነበር ያለው። "ያ " መብል" መብል ብቻ ሳይሆን ውስጡ ሕግ ነበር። ።
ሄዋንም ቅጠሉን ስትቆርጥ በቅጠሉ ውስጥ የነበረውን ሕግ አብራ ቆረጠችው። ሞትን ውድቀትን የጸጋ ጉድለትን ፥በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስን፥ በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሀነምን፤ ወደ ሲኦል መውረድን አመጣባት። << የሰው ልጅ ሕግ ሁሉ እንደ አዲስ ሌላ ጉዞ ሁኗል። ሀገሩ ገነትን ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሮቹን አጥቷል። ከሥርዐተ ልደቱ እስከ ሥርዐተ ሞቱ ኅጢአት ያመጣበት አዲስ ጉዞ ሁኗል። ስለዚህ አንድ እጸበለስን አትብላ ተብሎ፣ ያንን አንዱን መጾም አልችል" ያለው አዳም ብዙ ጾም መጣበት። አንድ ነገር አትብላ" ተብሎ የነበረው አዳም ብዙ ነገሮችን እንዳይበላ ተከለከለ። ይህን ብላ።
ይህንን አትብላ የተባላቸው ብዙ ሁኑዋል።ዮ ፥አፈ
ስለዚህ ጥንቱን አንድ ነገር ብቻ እንዳይበላ የታዘዘው አዳም" ከአንዱ ነገር ባለመከልከሉ ከብዙ ነገር እንዲከለከል ሕግ መጣ። ንጹሕ ክቡር የነበረው በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረው የሰው ልጅ ወደ ርክሰት እና ወደ ጉስቁልና ሲገባ። ስለ እርሱ የተፈጠሩ ፍጥረታትም የዚሁ ርክሰት ተካፋይ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ። ለምሳሌ" ፍጥረት
ሁሉ ሙልካም ነው። እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ መልካም ነው። ሰው ደግሞ የመልካም መልካም ነው። ርኩስ ሁኖ የተፈጠረ ፍጡር የለም።
እግዚአብሔርም የፈጠረው ፍጥረት መልካም እንደ ሆነ አየ "ይላል ዘፍ ፩፥፴፩ 🌷። ስለዚህ በጥንተ ፍጥረት አይጥም ፦ድምቢጥም ጅብም ፈረስም አህያ። ስለዚህ በጥንተ ፍጥረት አይጥም ፦ድምቢጥም ጅብም ፈረስም አህያም ሁሉ መልካም ነው። በእግራቸው የሚሽከረከሩ በልባቸው የሚሳቡ በደመ ነፍስ ሕያዋን ሁነው የሚኖሩ ፍጥሩታት ሁሉ መልካም ናቸው። እግዚአብሔርም ሲፈጥር አልናቃቸውምና እኛ ደካሞቹ አንንቃቸውም። ዘፍ፩፥፳
ሰው ግን" በግብሩ በነገሩ ወደ እንስሳነት ሲወርድ መዝ ፵፭፥፳ 🌷፥ ወደ አራዊትነት ሲያድግ ..🌷.ኤፍሬም ምናሴን፤ ምናሴ ኤፍሬምን ሲበላው፤ዘፍ በገነት ሳለ ስም ሲያወጣላቸው...ሲያገለግሉት፥የነበሩ፦አራዊት ጠባያቸውን ለውጠውበታል...። በነገራችን ላይ ሰው ወደ ክብር ሲለወጥ ዐለሙን ሁሉ ወደ ክቡርነት እንዲለወጥ እንዳደረገው ሁሉ ፤ ሰው ወደ ኅሳር ሲወርድም ዐለሙን ሁሉ ይዞት ወርዷል። አራዊት ተናካሽ ሁነዋል።" መጽ ቀሌ"
መልካም የነበሩ እንስሳትም ተዋጊ ተራጋጭ ሁነዋል "
እነርሱም ርኩሳን ወደ መባል ወርደዋል።
## እንግዲህ በዚህ ምክንያት "በአዳም ምክንያት መርገም ወደ ዐለም ገብቷል ። ማን ማን ተረገመ ?
1ኛ አዳም እና ሄዋን እባቡም ከተረገሙ በኋላ " ምድር ተረግማለች። ከአንተ የተነሣ ምድር የተረገመች ትሁን ።እሾህ አሜከላ ይብቀልብህ" ተብሎ እሾህ አሜከላ
ያልነበራት ምድር እሾህ አሜከላ በቅሎባታል።ዘፍ ፫፥፲፯
ምድር ማለት ግን ። ተራራው ኮረብታው ብቻ አይደለም። በምድር ያለው ፍጥረት ሁሉ ነው እንጅ። በሌላ ትርጓሜ ምድር የተባለ የአዳም ልጅ ሁሉ ሲሆን እሾህ አሜከላ ደግሞ ፍትወታት እኩያት ናቸው። ዘፍ 🌷3 ፥ 18 ስለዚህ ርኩስና ርኩስ ያልሆነ ፥ መርዝ ያለው እና መርዝ የሌለው ፍጥረት በመባል ተከፈለ። የሚናከስ እና የማይናከስ ቁጡ ገራም በመሆን እንስሳት አራዊት ቀዳማዊ ጠባይዓዊ ግብራቸውን በአዳም ላይ ለወጡበት።ባሕርያቸው ፈጽሞ ተለወጠ ሳይሆን ፍጥረት ሁሉ እንዲፈራው የተሰጠው ጸጋ ሲገፈፍ ፍጥረት ሁሉ ደፈረው። በገነት ሳለ ያከበረው ሁሉ አዋረደው ። የሚሰግድለት አሳደደው" ማለት ነው።
ስሰዚህ እባብ ተረገመ ።
ሄዋን ተረገመች ።
አዳም ተረገመ
ከእርሱ የተነሳ ምድር ሁሉ ተረግመች።
........እነዚህ ሁሉ በመርገሙ ሥር ወደቁ። ...........
በጥፋት ውሃ ጊዜ ቁራ ትእዛዙን ሳይፈጽም ሲቀር ርግብ ደግሞ ትእዛዟን ፈጽማለች። ስለዚ ለሰው ሁሉ በሚባል ደረጃ የሚታዘዘው አልነበረም። ሁሉ ይገዛልህ ቢባልም ሲስት ግን ሁሉን መግዛት፥ ሁሉን ማዘዝ አልቻለው ብሎ ነበር። ዘፍ ፰፥፮
2ኛ የሚበላው ምግብ እና የማይበላው ምግብ ተለየለት። ወርዶ ወርዶ የልብስ ጉዳይ አስጨነቀው።
የሚለብሰው እያጣ የልብስ ጉዳይ የሚያስጨንቀው ሆነ
ዘፍ ፫፥፮
መጽ ቀሌ
3ኛ ደም ያለችበትን ሥጋ አትብሉ "ተባለ። ዘፍ 9፥4
ደማዊት ነፍስ በደም ታድራላች። ነባቢት ነፍስ ደግሞ በደማዊት ነፍስ አድራ ትኖራለችና ።
4ኛ እስራኤል፥ እርሾ ያለባትን አትብሉ፤ የቦካ እንጀራ አትብሉ።ዘጸ..
የፍየል ስብ አትብሉ ።ዘጸ...
አውሬ የሰበረውን አትብሉ።.....ዘጸ.. ተመልከት።
የወፍም ሆነ የእንስሳ ደም አትብሉ የተባሉ ሲሆን።
በዋናነት ደግሞ ለሚበሉት እና ለማይበሉት እንስሳት ምልክት የነበረው የተረከዝ መሰንጠቅና አለመሰንጠቅ፤ ምንዝሃ መመለስ እና አለመመለስ ነበር...።
ነገር ግን በኦሪት አትብሉ የተባሉት ሁሉ ርኩሳን ሁነው አይደለም። ለልዩ ልዩ ምሥጢር እና አላማ ነው። .። ለምሳሌ የእንስሳ ደም አትብሉ ሲል የየትኛውንም እንስሳ ደም ነው። ደሙ ወይም እንስሳው" ርኩስ ሁኖ አይደለም። የነፍስ ማደሪያ ስለሆነች አትብሉ ተባለ ሕግ ነውና አክብረው ያዙት ፤ ተቀበሉትም ።