==============================
ጥር 2/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በስሩ ያሉ ተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በጥራት መንደር ውስጥ የሚገኙ ተቋማትን አሰራርና በውስጣቸው ያሉ ዘመናዊ የመስሪያ ቁሳቁሶችን ጎብኝተዋል፡፡
በጥራት መንደር ውስጥ የተስማሚነትና ምዘና ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ጥራት ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ኢነርጅ ባለስልጣንና የኢትዮጵያ አክሪዲኬሽን አገልግሎት የሚገኙ ሲሆን አምስቱ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት በአንድ ቦታ መደራጀታቸው ብሔራዊ የምርት ጥራትን ለማስጠበቅ እንደ ሚረዳ በአስጎብኝዎች ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም ተቋማቱ በዚህ መልኩ የተደራጁት በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንዱስትሪያላይዜሽን መሰረት እንዲሆኑ ታስቦ እንደ መሆኑ መጠን የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የኢንዱስትሪያላይዜሽንን ፅንሰ ሀሳብ ለሌላው ማህበረሰብ የማስተዋወቅ ሀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አቶ እንዳለ መኮንን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi