Hadiya zone communication @hadiya_zone_communication Channel on Telegram

Hadiya zone communication

@hadiya_zone_communication


This is Hadiya Zone Govern. Comm. official Telegram channel.
የሀድያ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ የሆነ የመንግሥት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሥርዓት በመገንባት መንግ

Hadiya zone communication (Amharic)

ይህን የሀድያ ዞን አስተካክሎ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች እና የሙሉ ግንኙነት እንዲሆን እና ያላቸው እንዴት ምሳሌ ያንጋግሩበትን ወንጀላውን እንረዳለን? ምን እንማ ላቸው? ለአንዲት መንገድ፣ ለሀድያ ዞን እናምናለው በኮሚዩናዊነት፣ በአንዳንድ ተደጋጋሚነት እና ይከብሩላቸው። ሀድያ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮችና የመንግሥት አንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሥርዓት አሉት። በሌንጮን እና በተቀማጭ ቦዾና ማስተካከል በተገለፀ ተወስነው በቅርቡ ማህበራዊ ውጤት አሉት።

Hadiya zone communication

07 Dec, 18:10


https://youtu.be/PQ2WclgrvFQ

Hadiya zone communication

07 Dec, 17:59


በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
***********

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።
https://www.instagram.com/share/p/_2k61poVu

Hadiya zone communication

07 Dec, 17:50


"19ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ነገ ለማክበር የተዘጋጀችው እንግዳ ተቀባይዋ የአርባ ምንጭ ከተማ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ለከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርጋለች!" - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ለተጨማሪ መረጃ
1. ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/Hadiyazonegcap
2.ቴሌግራም፦
https://t.me/Hadiya_zone_communication
3. ዩትዩብ፦
www.youtube.com@HadiyaZoneCommunication
4. ቲክ ቶክ ፦ tiktok.com/@hz.communication
5. ቲዩተር፦
https://x.com/HadiyagovCom
6. ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029ValTNIfICVfnAR9ZzS0o
7.ኢንስታግራም https://instagram.com/@hadiyazone

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!
https://www.instagram.com/share/p/BAKsiV72o_

Hadiya zone communication

07 Dec, 14:57


Channel name was changed to «Hadiya zone communication»

Hadiya zone communication

06 Dec, 15:17


የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የሚሳተፉ ልዑካኖች አርባ ምንጭ ከተማ እየገቡ ነው

(ሆሳዕና፣ኅዳር 27/2017 ) ዘንድሮ 19ኛ ጊዜ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተሳታፊ የባህል ልዑካን ቡድኖች ወደ አርባ ምጭ ከተማ እየገቡ ነው።

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ወደ አርባ ምንጭ ከተማ የሚጓዙ ልዑካን ቡድኖች አቋርጠው በሚያልፉባቸው አከባቢዎች፥ የአከባቢው ነዋሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች መንገድ ላይ ዝግጅት በማድረግ አቀባበል ሲደረግላቸው እንደነበር ከደቡብ ምእራብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በአርባምንጭ ከተማ በተደረገው የአቀባበል መርሃ ግብር ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።(ኤፍ ኤም ሲ)
https://www.instagram.com/share/p/BACUAHH_1I

Hadiya zone communication

06 Dec, 15:17


አገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ
ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን
ህዳር 29/2017 ዓ.ም
https://www.instagram.com/share/p/BALfQwSAfP

Hadiya zone communication

05 Dec, 14:23


የሆሳዕና ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ከዞኑ ሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር የኢትዮ ኮደርስ የስልጠና መድረክ አካሄዷል ።

።።።።።።።። ህዳር 26/2017 ዓ.ም።።።።።።።

በመድረኩ ላይ የሀዲያ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የሀዲያ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊና ከከተማው ከሁሉም ቀበሌዎች የተወጣጡ ከ100 በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

የሆሳዕና ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት አስመላሽ ኤርገኖ እንደገለፀው የስጠናው ዋና ዓላማ የወጣቶች የሰራ ዕድል ፈጠራ ግንዛቤ በማሳደግ በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ሁለተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ከፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ተናግረው ።

አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከስልጠናው ያገኙት ግንዛቤ ወደ ተግባር በመቀየር የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚጥሩ በመግለፅ የመድረኩ አዘጋጆችን አመስግነዋል ።

#የሆሳዕና ከተማ ኮሙኒኬሽን
https://www.instagram.com/share/p/_w5JWGUVg

Hadiya zone communication

02 Dec, 15:13


ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ምርት በመሰብሰብ የምርት ብክነትና አላስፈላጊ እንግልት ማስቀረት መቻላቸውን የሌሞ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።

የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰው ጉልበት በመጠቀም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ከ5ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉንም አስታውቋል።

።።።።።።።።።።።።።።።።።23/03/2017 ዓ.ም።።።።።።።።።።።።።።።።

በሌሞ ወረዳ በጀዌ ቀበሌ ምርት ሲሰበስቡ አግኝተን ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች የዘመኑን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ምርት እየሰበሰቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የደረሱ ሰብሎችን ኮምባይነር በመጠቀም በመሰብሰብ ከምርት ብክነትና ከአላስፈላጊ እንግልት መዳናቸውን ነው ያብራሩት።

አርሶአደሮቹ ከዚህ ቀደም የሰው ጉልበት በመጠቀም ምርት ሲበስቡ ለእንግልት ሲዳረጉ እንደነበር አስታውሰው አርሶአደሮቹ በአሁን ወቅት ከመሰል ችግሮች መለቀቃቸውን ተናግረዋል።

ሌሎች አርሶ አደሮችም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ምርት በመሰብሰብ ከብክነትና እንግልት እንዲድኑ ምክራቸውን ለግሰዋል።

በሌሞ ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት የሰብል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ጦናሞ በበኩላቸው፤ በወረዳው በአሁኑ ወቅት ከሌሎች ተግባራት በተለየ መልኩ ለምርት አሰባሰብ ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

ምርት አሰባሰብን ለማፋጠን በየቀበሌው አደረጃጀት ተፈጥሮ በአግባቡ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

በቀሪው ግዜያትም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊጥል ስለሚችል ሁሉም አርሶ አደሮች የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ምርት እንዲያሰባስቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሌሞ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰልፋሞ ወ/ዮሀንስ እንደገለጹት፤ በወረዳው በ2016/2017 የምርት ዘመን በመኸር እርሻ 16 ሺህ 928 ሄክተር ማሳ በዘር መሸፈን መቻሉንና ከዚህም ውስጥ 8 ሺህ 428 ሄክተር ማሳ በስንዴ የተሸፈነ መሆኑን አብራርተዋል።

280 ሺህ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሎ እየተሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።

እንደ አቶ ሰልፋሞ ማብራሪያ፤ በምርት ዘመኑም 8 ሺህ 700 ኩንታል ምርት ኮምባይነር በመጠቀም ለማሰባሰብ ታቅዶ እስካሁን ከ 5 ሺህ 82 ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ ተችሏል።

በአሁን ወቅትም በወረዳው በተለያዩ አከባቢዎች የደረሱ ሰብሎችን የማሰባሰብ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ያብራሩት ኃላፊው በተለይም ኮምባይነር በመጠቀም በፍጥነት እየተሰበሰበ ነው ብለዋል።

በወረደውም የኮምባይነር አጠቃቀምን በተመለከተ ለአርሶ አደሮች ግንዛቤ በመፍጠር አርሶ አደሮች አላስፈላጊ ወጪ ውስጥ እንዳይገቡ አደረጃጀቶች ተፈጥረው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑንን ተናግረዋል።

አርሶ አደሮችም ከተለመደው የምርት አሰባሰብ ባሻገር ኮምባይነር ተጠቅመው ምርት እንዲሰበስቡና የምርት ብክነቱንም እንዲቀንሱ አቶ ሰልፋሞ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሰብል የደረሰባቸው አከባቢዎች አርሶ አደሮች ያለምንም መዘናጋት ሁሉንም አማራጮችን ተጠቅመው ምርት እንዲያሰባስቡ ጥሪ አቅርበዋል ።
#የሀድያ ቴሌቪዥን

Hadiya zone communication

26 Nov, 19:13


የግብር አላማዎች

ሕዳር 17/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ግብር የተለያዩ አላማዎችን ለማስፈጸም የሚሰበሰብ ሲሆን ጥቂቶቹን ለማየት ያክል፡-

#ገቢን_ለመፍጠር
👉መንግስት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አድገትን ለማፋጠን የራሱ ገቢ ያስፈልገዋል፡፡ በመሆኑም ገቢ ከሚሰበሰብባቸው ምንጮች መካከል ግብር አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ነው ግብር ወይም ታክስ ዋናው የመንግስት ገቢ ምንጭ እና ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት የጀርባ አጥንት ነው የሚባለው፡፡

#የገቢ_እና_የሀብት_ልዩነትን_ለመቀነስ
👉ሀገራት በሀብታምና በደሀ መካከል ያለውን ልዩነት ለመቀነስ እየጨመረ ወይንም እየቀነሰ የሚሄድ የታክስ ስርዓት ተግባራዊ ያደረጋሉ፡፡ በዚሁም መሰረት ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙ ከፍተኛ ታክስ ይከፍላሉ፣ መካከለኛ ገቢ የሚያገኙ መካከለኛ ታክስ ሲከፍሉ፣ ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኙ ደግሞ ከታክስ ነጻ ይደረጋሉ፡፡

#ኢኮኖሚን_ለማረጋጋት
👉ከዚህ አንፃር ደግሞ መንግስት ታክስን በመጨመር ወይንም በመቀነስ አሊያም ሙሉ በሙል ታክስን በማንሳት የዋጋ ግሽበትን እና የእኮኖሚ መቀዛቀዝን ሊቆጣጠር ይችላል፡፡ የሄውም የሚፈጸመው የታክስ መጠንን በጨመር ወይም በመቀነስ ወይም አዲስ ታክስ በመጣል ወይም በማንሳት ሊሆን ይችላል፡፡

#ጎጂ_ወይም_መሰረታዊ_ያልሆኑ_ምርቶች_ፍጆታን_ለመቀነስ
👉በህብረተሰቡ ጤና ላይ ችግር ይፈጠራሉ ተብለው የሚታሰቡ ምርቶች ወይም መሰረታዊ የልሆኑ ምርቶች ፍጆታን ለመቀነስ እና አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል እነኘህን ምርቶች ከመግዛት እንዲቆጠብ ለማድረግ ከፍተኛ ታክስ ሊጣል ይችላል፡፡

#ኢንቨስትመንትን_ለማበረታታት
👉መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ሴክተሮችን በመለየት ለተወሰነ ጊዜ የታክስ እፎይታ ሊፈቅድ ወይም ታክስ ሊቀንስላቸው ይችላል፡፡

#ለሀገር_ውስጥ_ምርት_እና_አምራቾች_ጥበቃ_ለማድረግ
👉መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ላይ ከፍ ያለ ታክስ በመጣል ለሀገር ውስጠ ምርት እና አምራቾች ጥበቃ ሊያድርግ ይችላል::

#የውጭ_ንግድን_ለማበረታታት
👉መንግስት የውጭ ንግድን ለማበረታታት እና የውጭ ምንዛሬን ለመጨመር ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ከታክስ ነጻ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡

#የፌደራል ገቢዎች ሚኒስቴር
https://www.instagram.com/p/DC2IqTntBwU/?igsh=MWo3YjJrcG51ODF6Yg==

Hadiya zone communication

26 Nov, 18:52


በህገ-ወጥ መንገድ ጥቅም ላይ ሲውሉ በነበሩ ሼዶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ሆሳዕና 17/03/2017

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ ተከተል እንደገለፁት ስራ አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማሠማራት በ2017 ዓ/ም ከ16ሺህ 600 በላይ ወጣቶችን በመለየት ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድሎች በማመቻቸት ወደ ስራ ለማሰማራት በትኩረት አየተሠራ ይገኛል።

ለዚህም በከተማው ውስጥ የተገነቡ ሼዶችና የገበያ ማዕከላት ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በህገወጥ መንገድ ጥቅም ለይ እየዋሉ ያሉ ሼዶች ከህገ ወጥ ተጠቃሚዎች ለማስለቀቅ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም መሰረት በከተማው በስድስቱም ቀበሌያት በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ፣ የቆይታ ጊዜ ያለፈባቸውና ከተሠጠበት ዓላማ ውጪ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ 90 ሼዶች መለየታቸውን የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፤ በዚህ ሁለት ሳምንት ውስጥ በ46 ሼዶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።

ሼዶቹ አዲስ ተደራጅተው የስራ ዕድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶች የማስተላለፍ ስራ እንደደሚሠራም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።

በከተማው በዓመቱ ባለፉት አራት ወራትም ከ5ሺህ በላይ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ጠቁመዋል።

#የሀድያ ቴሌቪዥን
https://www.instagram.com/p/DC2GJWANUfR/?igsh=cjJ3OHI5cHNxcjY2

Hadiya zone communication

26 Nov, 12:21


በሀዲያ ዞን የሆመቾ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተገልጋዮች በመድኃኒት እጥረት መቸገራቸውን ተናገሩ።

በሀዲያ ዞን ሆማቾ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ጥሩ ቢሆንም በመድኃኒት እጥረት መቸገራቸውን ተገልጋዮች ተናገሩ።
።።።።።።።።።። 17/03/2017 ዓ.ም።።።።።።።።።።

በሆስፒታሉ በድንገተኛ፣ ተኝተው ታካሚዎች እና ተመላላሽ ታካሚዎች ካነጋገርናቸው መካከል አቶ አየለ ኤራንጎና ሙሉነሽ ከበደ አስተያየት እንደሰጡት አገልግሎት አሰጣጡ ጥሩ ቢሆንም የመድኃኒት እጥረት በመኖሩ መቸገራቸውን ተገልጋዮች አንስተው

ባለድርሻ አካላት የአምቡላንስ ክፍያ፣ መድኃኒት እጥረት ችግር ፣ የምርመራ ቁሳቁስ በበቂ ሁኔታ ያለመኖር እና ሌሎች የግብዓት እጥረት ችግሮችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

ከነጋገርነቸው ከሆስፒታሉ ሀኪሞች መካከል ሲ/ር ሙሉነሽ ደዊትና ዱታሞ ቶቴ በበኩላቸው እንደተናገሩት ባለሙያዎች አቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን በቅንጅትና በመመካከር በሆስፒታሉ ለሚጠቀሙ ተገልጋዮች አገልግሎት እየሰጡ  መሆኑን ገልፀው

በተግዳሮት ውስጥም ሆነው በሆስፒታሉ የሚሰጠውን አገልግሎት አሠጣጥ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን እየሠሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

የሆመቾ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መድኃኒት ክፍል አስተባባሪው አቶ ላምቦሬ ኮርማ እንደተናገሩት በሆስፒታሉ የመድኃኒት ግዥ በዕቅድ የሚፈፀም ሲሆን በወቅቱ በተከሰተው ወረርሽኝ ምክኒያት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የመድኃኒት እጥረት መኖሩንም ተናግረዋል።

የሆመቾ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድንገተኛና ጠቅላላ ህክምና ክፍል ዶ/ር አዲሴ ሀንድኖ እንደተናገሩት ቀድሞ መከላከልና እና ማከም ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሆነ አንስተው

የሆስፒታሉን የማኔጅመንት፣ የአገልግሎት ጥራት እና ተገልጋይ ተኮር አገልግሎቶችን በጥራትና በቅንጅት መሠረት እየሠሩ እንደሆነም ተናግረዋል።

አክለውም ሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋይ እርካታንና የመረጃ ጥራት መሠረት ቢሠራም የመድኃኒት እጥረትን የሚመለከታቸው አካላት እንዲፈቱ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የሆማቾ መካከለኛ ሆስፒታል ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ምስጋና ዓለሙ እንደተናገሩት የማይተካውን የሰው ህይወት የማዳን ሥራ  ለማሳለጥ የሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አንስተው

በሆስፒታሉ የጤና ተግባርን በሚገባ ለመፈጸም  የተሽከርካሪ እጥረት፣ የመድኃኒት እጥረት፣ የምርመራ መሣሪያ በበቂ ያለመኖር ፣ ሌሎች የግብዓት እጥረቶች ፣ የባለሙያ ጥቅማጥቅም ያለመከበር ችግሮች በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑንም አንስተው

ችግሩን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ወሳኝ የመፍትሄ አቅጣጫ መሆኑንም ተናግረዋል።
በጫኬቦ ኤርጫፎ

Hadiya zone communication

23 Nov, 16:44


ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት ማሰባሰብ እንደሚያስፈልግ የሀድያ ዞን ግብርና መምሪያ አሳሰበ።

።።።።።።።።።።።።ሆሳዕና 14/03/2017 ዓ.ም።።።።።።።።

የሀድያ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ሀብታሙ ታደሰ እንደተናገሩት፤ በዞኑ በ2016/2017 የምርት ዘመን 149ሺህ ሄክተር ማሳ በዘር ለመሸፈን ታቅዶ ከ150ሺህ ሄክተር ማሳ በላይ በዘር መሸፈን መቻሉንና ከዚህም ከ7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ግብ ተጥሎ እየተሠራ መቆየቱን አብራርተዋል።

በአሁን ወቅትም በቆላማ አካባቢዎች የደረሱ ሰብሎችን የማሰባሰብ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት የመምሪያው ሃላፊ፤ እስከአሁን ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመዋል።

ዶ/ር ሀብታሙ አክለውም ስንዴ በብዛት የሚመረትባቸው ወረዳዎች ኮምባይነር በመጠቀም ምርት በመሰበሰብ የምርት ብክነት መቀነስ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

የምርት የማሰባሰብ ሂደቱንም የተሳለጠ ለማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን መጠቀም እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል።

#የሀድያ ቴሌቪዥን
https://www.instagram.com/p/DCuJNg5tjyw/?igsh=MTFmZ2Zkc2s4aTd3aA==

Hadiya zone communication

23 Nov, 16:07


በዞኑ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች መንግስት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ ተናገሩ።

።።።።።።።።።።ሆሳዕና 14/03/2017 ዓ.ም።።።።።።።።

በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ሸቻ ሮማ ቀበሌ ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው አይዛክ ዴልታ የነዳጅ ማደያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በምረቃ ስርዓት ላይ የተገኙት የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ በበኩላቸው የመጣውን ነዳጅ በአግባቡ በመጠቀም ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚያስፈልግና በህገ ወጥ መንገድ የሚሰሩ ተግባራት እንዳይከናወን መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።

በዞኑ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ስራ ለሚጀምሩት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ገልፀዋል።

የሀዲያ ዞን የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት ሜጊሶ በበኩላቸው ፤ በዞኑ 429 ባለሃብቶች በግብርና፣በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ መሰማራታቸውን ጠቅሰው፣ በፕሮጀክቶቹም በስራ ዕድል ፈጠራና በቴክኖሎጂ ሽግግር ለዜጎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል::

በዞኑ በኢንቨስትመንት ፈቃድ መሬት ወስደው ሳያለሙ የቆዩ ባለሀብቶች መሬቱን ወደ መሬት ባንክ የመመለስ ስራ እየተሰራ እንደሆነም ገልፀዋል።

የሌሞ ወረዳ ዋና አስተደደሪ አቶ ታደለ ደምሴ በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ እንደተናገሩት፤ መንግስት የኢንቨስትመንት እና የንግዱን ማህበረሰብ ለማበረታታትና ለመደገፍ ባለሃብቶች በመረጡት የስራ ዘርፎች እንዲሰማሩ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል::

ባለሃብቱ በዚህ ብቻ ሳይረኩና ሳይዘናጉ ተጨማሪ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በመሰማራት ተጨማሪ የስራ ዕድል በመፍጠር ለአአባቢው ልማት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አቶ ታደለ ጥሪ አቅርበዋል::

የነዳጅ ማደያው ባለቤት በርከፈት ጌታቸው ገዕናሞ በበኩላቸው፤ የነዳጅ ማደያው ግንባታ 85 ሚሊዮን ብር በላይ እንደፈጀ ገልጸው፤ በግንባታ ሂደቱ ለበርካታ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት 15 ቋሚና 50 ጊዜያዊ ሰራተኞች እንዳሉና በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት በርከፈት ጌታቸው በቀጣይም ከማደያው ጎን ለጎን የፋብሪካ ግንባታ ስራ ለመጀመር ዕቅድ እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

በነዳጅ ማደያው የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች በበኩላቸው፤ የማደያው መገንባት ከነዳጅ አቅርቦት ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል።

በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎችም ተመሳሳይ ተግባራት ቢከናወኑ የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ወጣቶቹ ገልፀዋል።

#ሀድያ ቴሌቪዥን
https://www.instagram.com/p/DCuE6YqtgRV/?igsh=OGZvcnliMTExZWN0

Hadiya zone communication

16 Nov, 15:30


ከዞናችን ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ለወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር በላይ አንገብጋቢ ሥራ የሌለ በመሆኑ አመራሩ ተግባሩን በቁርጠኝነት ሊመራ ይገባል፦የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ።

የሀዲያ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ከዞኑ ቴክኒክና ሙያ ትም/ትና ስልጠና መምሪያ ጋር በመተባበር በወጣቶች ልየታ፣የክህሎት ስልጠናና በስራ ስምሪት ዙሪያ የሚመክር የስራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት ጉባኤ አካሂዷል።

።።።።።።።።።።።ህዳር7/2017።።።።።

በምክር ቤቱ ጉባኤ የተገኙት የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ ባስተላለፉት መልዕክት፣ለወጣቶች የስራ ዕድል የመፍጠር ስራ የሁሉንም አመራር ትጋትና ቁርጠኝነት የሚፈልግ ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዉ፦በተለያዩ ምክኒያቶች ተግባሩን ችላ በማለት በዉጤት ቀዉስ ዉስጥ ያላችሁ መዋቅሮች ፈጥናችሁ መታረም አለባችሁ ብለዋል፥

ዋና አስተዳዳሪዉ አያይዘዉ፦ለወጣቱ ከይገባኛል ነፃ የሆነ መሬት ተለይቶ ተዘጋጅቶ የክህሎት ስልጠና ለወሰዱና ፍቃደኛ ለሆኑ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ እንዲተላለፍና በህገወጥ መንገድ ባማይገባቸዉ ግለሰቦች እጅ ያለ መሬት፣ሼድና ብድር በአስቸኳይ ተመላሽ እንዲደረግ ያሳሰቡት ዋና አስተዳዳሪዉ፦

ከዞናችን ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ለወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር በላይ አንገብጋቢ ስራ የሌለ በመሆኑ አመራሩ ተግባሩን በቁርጠኝነት ሊመራ ይገባል ብለዋል።

የዞኑ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሊረንሶ በበኩላቸዉ፤ መንግስት የወጣቱን ጉዳይ እንደ ዋና አጀንዳ በመያዝ በገጠርና በከተማ የሚገኙትን የተማሩትንና ያልተማሩትን ስራ ኣጥ ወጣቶች የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባላቸዉ መስኮች እያሰማራ ይገኛል ብለዉ፤

መምሪያችን ባለፉት አራት ወራት ያስመዘገበዉ የስራ ዕድል ፈጠራ አፈፃፀም 21% ሲሆን ቀሪዉን 79% ባለን ጊዜ ለመፈፀም ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

እንደ 2017 የስራ ዘመን 1 መቶ 11 ሺህ 6 መቶ 82 ወጣቶች ልየታ መደረጉን ጠቁመዉ፦93 ሺህ 37 ወጣቶችን ወደ ስራ ለማሰማራት እየተሰራ እንደሆነ በማሳወቅ፤ይህ ዕቅድ እዉን እንዲሆን
የስራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት አባላትና የሚመለከታቸዉ አካላት ለጉዳዩ አፅንዖት እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን የ2017 የስራ ዘመን አዳዲስና ነባር ሰልጣኞችን ቅበላ በሚመለከት መግለጫ የሰጡት የዞኑ ቴክኒክና ሙያ ትም/ትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ርስቱ እንደተናገሩት፤እንደ ዘንድሮ በዞናችን 15 ሺህ 4 መቶ 34 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደዉ 3መቶ 67 ተማሪዎች ብቻ ዩንቨርስቲ ስለመግባታቸዉ አንስተዉ፤ከፍተኛዉን ቁጥር የያዙት ቀሪ ወጣቶች በየአካባቢዉ ባሉ ኮሌጆች በመሄድ የክህሎት ስልጠና እንዲወስዱ አሳስበዋል።

አያይዘዉም በማንኛዉም ስራ ለመሰማራት የክህሎት ስልጠና ወሳኝ ስለሆነ በዞናችን 8 የሙያና ቴክኒክ ኮሌጆች ያለ በመሆኑ በአቅራቢያ ወዳሉት በመሄድ እንሰለጥኑ እንዲደረግ ጠቁመዋል

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ፥በልየታ ወቅት የመይገባቸዉ አካላት እንዳይካተቱ ጥንቃቄ መደሰግ አለበት ያሉት ተሳታፊዎች፥ረጂም ጊዜ ስጠቀሙ የቆዩ ማህበራትን አስለቅቆ ለአዳዲስ ወጣቶች መሰጠት ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የማዕከላዊ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ታምራት ተስፋሁንን ጨምሮ የዞንና ወረዳ/ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በኤልያስ ተሰማ

Hadiya zone communication

16 Nov, 08:33


አደጋዉን በዘላቂነት ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሰረተ ዘላቂ መፍትሔ ሊበጅና የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በአካባቢው መሠራት አለበት፦ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ

በሀዲያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ በጎርፍ እየደረሰ ያለዉን ጉዳት በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት ዘለቂ መፍትሄ እንዳያበጅ የአካባባዉ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

።።።።።።።።ህዳር 6/2017።።።።።።።።።

በሀዲያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ምክኒያት በወረዳዉ ነዋሪዎች ለይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ሎቤ በሰጡት አስተያዬት ከዚህ በፊት እንድህ በመጠኑ ሰፈ ያለ የጎርፍ አደጋ ተከስቶ እንደማያውቅ አንስተዉ፤

በወረዳዉ አደጋው የተከሰተው ከጥቅምት 22 እስከ 23/2017 ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ የብላቴ ወንዝ ሞልቶ በወረዳው ከ785 በላይ አባወራዎችና እመወራዎች ያፈናቀለ እና ከ876 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የተዘራ ሰብል፣አትክልትና ፍራፍሬ ያወደመ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

አክለውም በጎርፉ በወረዳው በ13 ቀበሌያት የሚኖሩትን ከ3ሺህ 200 በላይ ነዋሪዎችን ያፈናቀለ ሲሆን ከዚህ በፊት እየተደረጉ የሚገኙ የተቀናጁ የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ተጠናክረዉ እንድቀጥሉ ለሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት አሳስበዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አደጋ ስጋት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ማዕረጉ ማቴዎስ በበኩላቸው በወረዳው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ከተከሰተ በኃላ ሁለት የአስቸኳይ ጊዜ ቲም እና ፈጣን ዳሰሳ ጥናት ቡድን መቋቋሙንና ሰብዓዊ ድጋፍ 3 መቶ የበቆሎ ዱቄትና 1500 ሊትር ዘይት እንዲሁም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የዕለት ደራሽ ድጋፍ መደረጉን አሳውቀው ፤

ለጎርፉ ተጎጂ ህብረተሰብ የክልሉና የፌደራሉ መንግስት በቀጣይ የተቀናጀ ጥረት እንደሚያደርግናና ችግሩን ለመከላከል አስፈላጊ ቁሳቁስና ማሽነሪዎች እንደሚያመቻች አሳውቀወዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ እንደተናገሩት አደጋዉን በዘላቂነት ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሰረተ መፍትሔ ሊበጅና የተቀናጀ የተፋሰስ ስራ በአካባቢዉ መሰራት አለበት ብለዉ፤የዕለት ተዕለት ደራሽ ድጋፍ ሥራ የክልሉ መንግስት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተው ፥

የጎርፍ አደጋን በዘላቂነት ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሰረተ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በአካባቢው መሠራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

እንዲሁም በብላቴ ወንዝ ላይ ሞልቶ የነበረውን ደለል መጥረግ፣ ካናል የመገንባት እና የመከላከል ሥራ ከአሁን ጀምሮ በመስራት ተጨማሪ ጉዳት እንዳይከሰት መጠንቀቅ እንደማገባ አስገንዝበዉ

በአደጋው ለተጎዱ አካላት ድጋፍ እንዲደረግ በክልሉ የተጠናውን የጥናት ሰነድ ለአገሪቱ አደጋ ስጋት አመራር እና ለዓለም ሰብዓዊ ድጋፍ ለጋሾች ሪፖርት መደረጉን አሳውቀው፤ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተዟዙረን ካነጋገርናቸዉ ተጎጂዎች አቶ ጌታቸዉ አቦ እንደምሉት፦በአደጋዉ በወረዳዉ ዘርፈ ብዙ ጉዳት መድረሱን በመጠቆም፤ባለን መሬት የዘረነዉ ዘር እና የነበረን አትክልትና ፍራፍሬ ከመበላሸቱም በላይ ዝናቡ የጣለዉ ምሽት በመሆኑ እንድ ሕፃን ልጅ ከቤተሰብ መኻል በርግጋ ወጥታ በጅብ መበላቷን ገልፀዋል።

በጉብኝቱ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤልና ፣የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮን ጨምሮ የክልል የዞንና የወረዳ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በጫኬቦ ኤርጫፎ

Hadiya zone communication

11 Nov, 23:16


የበጋ መስኖ ሥራዎችን በማስፋትና የሌማት ትሩፋት ላይ በትኩረት በመስራት በግብርናው ዘርፍ እንደ ሀገር አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅብናል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ።

"የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ የ2017 የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራዎች ንቅናቄ መድረ ተካሄደ።

።።።።።።።።።። ቀን 02/03/2017 ዓ/ም ።።።።።።።።።።

የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ በበጋ መስኖ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸው ግብርና ወሰን የለውም ስለዚህ የከተማ ግብርና ላይም አመራሩ ከራሱ ጀምሮ ተጠናክሮ በመስራት አርዓያ ሊሆን ይገባል ብለዋል ።

በግብርና ሥራ ችግኝ በማፍላት፣በመስኖ ሥራ፣በእርባታው ዘርፍና በንብ ማነቡ ዘርፍ ላይ ለወጣቱ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደ ሚያስፈልግ አንስተው በችግኝ ማፍላት ዘርፍ ለምግብነት የሚያገለግሉ የፍራፍሬ ምርቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የበጋ መስኖ ሥራዎችን በማስፋትና የሌማት ትሩፋት ላይ በትኩረት በመስራት እንደ ሀገር በግብርናው ዘርፍ የተሻለ ምርት በማቅረብ አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅብናል ያሉት አቶ ማቴዎስ አኒዮ ለዚህም ዞኑ የግብዓትና የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት በበቂ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።

የቡና ምርት ላይ ውጤታማ ለሞሆን የአተካከል ፓኬጅ ተጠብቆ ሊተከል እንደሚገባ እና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ገልጸው የቡና ምርትን በህገወጥ መንገድ እንዳይወጣ በማድረግ ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ዶ/ር ሀብታሙ ታደሰ የግብርና ጣብያ ሰራተኞች በዚህ የበጋ መስኖ ወቅት ሥራቸውን በአግባቡ በመስራት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ የቁጥጥር ስርዓቱ ላይ ተጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በቀጣይ በጥብቅ ክትትል በሥራ ሞዴል የሆኑትን ወረዳዎች ለይተን እናወጣለን በማለት የሁሉም መዋቅር አመራርና የግብርና በለሙያዎች በተቀናጀ አሰራር የደረሱ ምርቶችን ከመሰብሰብ ጀምሮ የመስኖ ሥራዎችንም አጠናክሮ መቀጠል በመስራት የህብረተሰባችንን የምግብ ዋስትና ልናረጋግጥ ይገባል በማለት ተናግረዋል።

ከተሳታፊዎች የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ በግብርናው ሥራ ላይ የተሰጠው ትኩረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አንስተው በተለያዩ መዋቅሮች ለበጋ መስኖ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ጠቅሰዋል።
የግብዓት አቅርቦት ዝግጁ ከሆነ የመስኖ ሥራው ውጤታማ እንዲሆን ወደ አርሶ አደሩ በመውረድ እንሰራለን ብለዋል።

አክለውም የዛሬው የበጋ መስኖ ንቅናቄ መድረክ የበጋ መስኖ ምርትን በስፋት በማምረት ከራስ አልፎ ወደ ገበያ በማቅረብ ገበያን ለማረጋጋት ቤት ለቤት ወርደን ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ እስከ ሰርቶ ማሳየት ድረስ መጓዝ በምንችለው ልክ ግንዛቤ ፈጥሮልናል በማለት

የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ ለመሰብሰብ እንዲሁም የቡና ምርት በህገወጥ መንገድ እንዳይወጣ በማድረግ የቡና ምርታችንን የማስተዋወቅ ሥራ እንሰራለን በማለት ተናግረዋል።

በመጨረሻም በሰብል ምርት፣በሌማት ትሩፋት እና በዕንቁላል አቅረቦት ዘርፍ ውጤታማ ለሆኑ ሦስት ሥራ ፈጣሪዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

በታከለ አጋፋሪ
https://www.instagram.com/p/DCP8XqiNZPs/?igsh=ZTA4OHF0OGhheWt6

Hadiya zone communication

11 Nov, 18:40


ሰላም እስትንፋሳችንና የዛሬም ሆነ የወደፊቱ የትውልድ የህልውና መሰረት መሆኑን በመገንዘብ  ሰላምን በዘላቂነት በማስፈን በዞናችን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ፡- የሀዲያ ዞን የመንግስት ዋና ተጣሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሃንዲሶ

የሀዲያ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2017 ዓ/ም በጀት እቅድ ላይ የምክክር ሴክተር ጉባኤ አካሂዷል።

።።።።።።02/03/2017 ዓ.ም።።።።።።።።።።።

በጉባኤው የፀጥታ መረጃ አስተዳደር ፣ የሰላም እሴት ግንባታ ፣የወሳኝ ኩነት ፣ የሀይማኖትና የእምነት ጉዳዮች፣ የግጭት መንስኤ ጥናትና አፈታት እና የፖሊስና የምልሻ ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገለፃ ተደርጓል ።

በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት መሰረት በአንዳንድ ተግባራት ላይ ክፍተቶች ጎልተው የታዩባቸው መዋቅሮችን በመለየት በቀጣይ ተግባራትን በማከናወን የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር ለማድረግ በነበሩ ክፍተቶች ላይ የጋራ  ውይይት ተደርጎበታል ።

በበጀት ዓመቱ የአፈጻጸም ጉድለት የታዩባቸው መዋቅሮችን በመለየት በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቁጭት ወደ ስራ እንደሚገባ በውይይቱ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።

በሴክተር ጉባኤ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የዞኑ የመንግስት ዋና ተጣሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሃንዳሶ እንደተናገሩት ሰላም እስትንፋሳችን በመሆኑ  የዛሬም ሆነ የወደፊቱ የትውልድ የህልውና መሰረት መሆኑን በመገንዘብ  ሰላምን በዘላቂነት በማስፈን በዞናችን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

አቶ ይርጋ ሀንዲሶ እንዳሉት በየትኛውም ዘርፍ ለውጥ በዘላቂነት መምጣት የሚቻለው አንፃራዊ ሰላም ሲኖር መሆኑን አንስተው በዞኑ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው እርብርብ የሰላም መስፈን ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሰላምን ለማስጠበቅ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በተለይም ሰላምን በዘላቂነት በማስፈን ልማትን በቀጣይነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ ላይ የሀይማኖት ተቋማትና የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ አካባቢያችን ብሎም አካባቢያችን ከሰላም አምባሳደርነት በተጨማሪ ልማታዊ ቀጠና እንዲትሆን ለማድረግ እየተሰራ ባለው ስራዎች ከግብ ለማድረስ የሀይማኖት ተቋማት ከምንጊዜም በላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በትኩራት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አቶ ይርጋ አሳስበዋል ።

አቶ ይርጋ አክልውም በዞኑ በየአካባቢው የህብረተሰብ ፖሊሲንግ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በዛለቂነት በማስጠበቅ ሀለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በቁርጠኝነት መስራት የሚጠበቅብን የዕለት ተዕለት ተግባራችን ነው ሲሉ አስገንዝባዋል ።

በሴክተር ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ እንደተናገሩት የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ለነገ የሚተው ባለመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታ መዋቅሮች የህብረተሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ሕግና ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ በተቀመጠው የአሠራር ሥርዓት በመታገዝ ለተሻለ ውጤት መሥራት ይገባል ብለዋል ።

የሰላም ድርሻ የሁለችንም ነው ያሉት አቶ ሳሙኤል የዞናችንን ሰላም ለማደፍረስ የተለያዩ አጀንዳዎችን በመፍጠር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን ተገንዝበን ነቅተን ሠላማችንን  ልንጠብቅ ይገባል ብለዋል።

ሰላማችን አስተማማኝና ቀጣይነት እንዲኖረው ህዝቡን ማሳተፍ ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም የዞናችንን የሰላም ተምሳሌትነት ለማስጠበቅና ለማስቀጠል ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ ሲሉም አቶ ሳሙኤል አስገንዝባዋል ።

በምክክሩ ከ13 ወረዳዎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች  የተገኙ ተሳታፊዎች በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም የጋራ ውይይት በማድረግ በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ የጋራ ውይይት ተደርጓል ።

በጉባኤም በበጀት ዓመቱ በሦስቱም ዘርፍ ማለትም በሰላምና ፀጥታ ፣ በፖሊስ እና በምልሻ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መዋቅሮች የማበረታቸው የዋንጫና ሰርትፊኬት በመምሪያው አዘጋጅነት በዞኑ በዋና አስተዳደር ተበርክቶላቸዋል።
በሰለሞን ወልዴ

Hadiya zone communication

03 Nov, 16:51


የገዥ ትርክት ውቅሮች

Hadiya zone communication

03 Nov, 12:58


የወባ በሽታ ምልክቶችና መከላከያ መንገዶች

በኢትዮጵያ በአሁን ወቅት የክረምት ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ የወባ ወረርሽ በስፋት መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

ስለ ወባ ወረርሽኝ መንስኤና ህክምናውን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የውስጥ ደዌ እና ተላላፊ በሽታ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ወንድወሰን አሞኘ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

ዶ/ር ወንድወሰን አሞኘ፤ የወባ በሽታ በትንኝ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ በዋነኛነት በትኩሳት የሚገለጥ ተወሳስቦ ለከፍተኛ አደጋ ሊዳርግ የሚችል በሽታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዓለም ላይ ሰዎችን በብዛት ከሚያጠቁ እና ጉዳት ከሚያደርሱ ሶስት በሽታዎች መካከል አንደኛው ቲቢ ሲሆን ከኤች አይ ቪ ቫይረስ በመቀጠል የወባ በሽታ ሶስተኛውን ደርጃ ይይዛል ብለዋል ዶ/ር ወንድወሰን፡፡

የወባ በሽታ በዓለም ላይ የበርካቶችን ህይወት የሚቀጥፍ በትንኝ አማካኝትት የሚከሰት ተላላፊ በሽታ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

የወባ በሽታ ሲታሰብ ትንኟ ከታማሚ ሰው የበሽታውን ተህዋስ በተለይ በኢትዮጵያ ፕላዝሞዴም ፋሲፋረም በተለምዶ ቢጫ ወባ የሚባለውን እና አንድ ሶስተኛው ደግሞ ቫይቫክስ በተባለ ተህዋስ ዝርያ የሚከሰት ስለመሆኑ አንስተው፤ ወባዋ የበሽታውን ተህዋስ ከታመመ ሰው አሊያም ታሞ ከዳነ ሰው እንደምትወስድም ገልጸዋል፡፡

ወንድ እና ሴቴ ተህዋስ በወባ ውስጥ አንድ ሳምንት ያድግና ትንኟ ለመራባት የሰው ደም የሚያስፈልጋት በመሆኑ በዚህ ሁኔታ ሰውን በምትነክስበት ጊዜ በሽታውን ወደ ሌላ ሰው እንደምታስተላልፍ ጠቁመዋል፡፡

ትንኟ ለመራባት እንቁላሏን ውሃ ላይ ትጥላለች የሚሉት የህክምና ባለሞያው፤ ይህም ደረጃ በደረጃ ወደ ትንኝ ይቀየራል ብለዋል፡፡

ትንኟ ለመራባት ቆላማ አከባቢ በመምረጥ ከባህር ጠለል በላይ 1ሺህ 400 ሜትር በታች በሆኑ አካባቢዎች ላይ እንደምትገኝና ከዛ በላይ ባለ ከፍታ የመራባት ምጣኔዋ እንደሚቀንስ ዶ/ር ወንድወሰን አመላክተዋል፡፡

በሽታው ከዚህ በፊት ለተያዘ ሰው እንዲሁም በተለይ ነብሰ ጡር እና ህፃናት ላይ የመከላከል አቅማቸው አናሳ በመሆኑ የከፋ ጉዳት እንደሚያደርስም ጠቁመዋል፡፡

በአብዛኛው የክረምት ወቅት አልፎ የበጋ ወቅት ሲጀምር ውሀዎች ሙሉ ለሙሉ ስለማይደርቁ እና የታቆሩ ውሀዎች ስለሚኖሩ እንዲሁም በትንንሽም ውሀዎች የመራባት እድል ስለሚኖር ለትንኞች መራባት አመቺ ይሆናልም ብለዋል፡፡

የወባ በሽታ ምልክቶች፦

• ትኩሳት
• ቁርጥማት
• ማስመለስ
• ማስቀመጥ
• ብርድ ብርድ ማለት
• የከፋ ሲሆን ደግሞ አይን ቢጫ እንደሚሆነ ተናግረዋል፡፡

የወባን በሽታን ለመከላከል ትንኟ የምትራባባቸውን ቦታዎች ማጽዳት ያስፈልጋል የሚሉት ዶ/ር ወንድወሰን፤ ያቆሩ የቆሸሹ ነገሮችን ማስወገድ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

ጸረ-ትንኝ ኬሚካሎች በሚረጩበት ጊዜ ቀለም መቀባት፣ ማጠብ እንደማይገባ እንዲሁም በጸረ ትንኝ የተነከረ አጎበር መጠቀም እንደሚገባ አያይዘው አንስተዋል፡፡

የወባ በሽታ በቂ ህክምና እና ክትትል ከተደረገለት እንደሚድንም የህክምና ባለሞያው ተናግረዋል፡፡

#ኢቢሲ ኢቢሲ

Hadiya zone communication

03 Nov, 12:55


ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ እንዲሰበሰብ ጥሪ ቀረበ

ሆሳዕና ፣ ጥቅምት 24/ 2017 በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ እንዲሰበሰብ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡

ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እየጣለ እንደሚገኝ ጠቁመው ፤ ይህ ጉዳትም ጥቅምም አለው ብለዋል፡፡

የመኸር አዝመራ በደረሰባቸው እና ሰብል መሰብሰብ በተጀመረባቸው አካባቢዎች ጉዳት ሊያደርስ እንሚችልም አሳስበዋል፡፡

በነዚህ አካባቢዎች ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም ሰብሉ ጉዳት እና ብክነት ሳይደርስበት በወቅት መሰብሰብ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዚህም ዘመቻ "ሰብል መሰብሰብ" በማወጅ በንቅናቄ ሰብሉን በወቅትና በጊዜ መሰብሰብ እንሚደባ ተናግረዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ ሙያተኞች፣ ሠራተኞች፣ የፀጥታ አካላት፣ ተማሪዎች፣ አርሶአደሮች፣ ወዘተ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

ባለሙያዎች የሚሰጡትን የጥንቃቄ ምክሮችንም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

ሰብል ገና ባልደረሰባቸው፣ የመጀመሪያውን ዙር የበልግ አዝመራ በሚካሄድበት፣ የበጋ መስኖ በተጀመረበት አካባቢ ደግሞ እየጣለ የሚገኘውን ዝናብ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ነው ያሉት።

የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ዕቅድ ከግብ የሚደርሰው የሚያጋጥሙንን ሁሉንም ችግሮች በተባበረ መንገድ በመሻገር ፣ መልካም አጋጣሚዎችን ደግሞ አሟጠን መጠቀም ስንችል ነው ብለዋል።#ኤፍቢሲ

Hadiya zone communication

03 Nov, 12:45


በሀድያ ዞን ሶሮ ወረዳ በጊዳቸሞ ቀበሌ የፓፓዬና የሙዝና ፍራፍሬ ልማት አሁናዊ ገፅታ ከፊል ማሳያ

Hadiya zone communication

02 Nov, 18:39


ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ የገቢ አቅሞችን መለየትና መረጃ መሰብሰብ ወሳኝ ነው:- የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ማቴዎስ አኒዮ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የደንበኞች አገልግሎትና የገቢ አሰበሰብ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደግፍ መለሠ በተገኙበት የሀዲያ ዞን የእስካሁን ገቢ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄዷል።

።።።።።።።።።።23/02/2017 ዓ.ም።።።።።።።።።።

ገቢን በዘመቻ መልክ መሰብሰብ ከልተቻለ የዞኑን ልማትና ዕድገት ማፋጠን አዳጋች እንደሚሆን ተገልጿል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የደንበኞች አገልግሎትና የገቢ አሰበሰብ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደግፍ መለሠ በመድረኩ እንደተናገሩት በከተሞች ግብር አካፋፈል ላይ ደረጃ ሽግግር ፣ ያለደረሰኝ ንግድ እና ደረሳኝ ቁጥጥር ላይ የአመራር ቁርጠኝነት ማነስ መኖሩን አንስተው

ደረሰኝ የማይቆርጡ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም አሳስበዋል።

የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ማቴዎስ አኒዮ እንደተናገሩት ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ የገቢ አቅሞችን መለየትና መረጃ መሰብሰብ ወሳኝ መሆኑን ተናግረው

በዞኑ ያለውን የገቢ አቅሞችን በመለየት ገቢ ምንጮችን አሟጥተን ከልሰበሰብን የዞኑን ልማት ማፋጠን እንደማይቻል ገልፀው ግብር የማይከፍሉ አካለት ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መመራት እንዳለበትም አበክረው አሳስበዋል።

አክለውም በገጠር መሬት አጠቃቀም ላይ እኩል ተልዕኮ ተቀብለው ሙሉ በሙሉ መረጃ የሰበሰቡትን መዋቅሮችን አመስግነው

መረጃ ሕይወት በመሆኑ በጥንቃቄ መሰብሰብ እንዳለበት ለባለድርሻ አካላት መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የሀዲያ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ መሳይ መኮንን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በገጠር መሬት አጠቃቀም ላይ በጠቅላላ 349 ቀበሌያት ከነበረው 215 ቀበሌያት መረጃ የመሰብሰብ ሥራ መጠናቀቁን አብራርተዋል ።

እንዲሁም በዞኑ እስካሁን በጠቅላላ ይሰበሰባል ተብሎ የታቀደው 115 ሚሊየን 347 ሺህ 955.4 ስሆን የተሰበሰበው 28 ሚሊየን 525 ሺህ 277.7(24.7%) መሆኑም በሪፖርቱ ተገልጿል።

መረጃ መሰብሰብ ሥራ ላይ 100% የባዳዋቾ ክላስተርና
92.5% ጎምቦራ ወረዳ በከፍተኛ ደረጃ መሆኑንና ሌሎች መካከለኛ እና ዝቅተኛ ደረጃ መሆኑ ተገምግሟል ።

ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸው መዋቅሮች የመረጃ አሰባሰብ ተሞክሮዎች አቀርበዋል።

የከተማና የገጠር ግብር ከፋዮችን ለይተው እያስከፈሉ እንደሆነም ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ አስቀምጠው የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።
በጫኬቦ ኤርጫፎ

Hadiya zone communication

02 Nov, 13:07


በሀድያ ዞን አመካ ወረዳ ፎርቆሴ ቀበሌ የፍራፍሬ ልማት በከፊል ማሳያ

Hadiya zone communication

24 Oct, 11:59


ሆሳዕና፣ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም

በሀድያ ዞን ዱና ወረዳ እየለማ ያለ የባቄላ ማሳ በከፊል ማሳያ

በሀድያ ዞን ዱና ወረዳ በ 2 ሺህ 9 መቶ 40 ሄ/ር መሬት ላይ በኩታ ገጠም እርሻ የለማ ባቄላ ነው።

በወረዳው እየለማ ባለው የባቄላ ሰብል በሄክታር 20 ኩንታል ምርት ይመረታል ተብሎ ይጠበቃል።

Hadiya zone communication

24 Oct, 11:58


በሀድያ ዞን ዱና ወረዳ የለማ የአተር ማሳ አሁን ማሳያ በከፊል
በሀድያ ዞን ዱና ወረዳ በ 1 ሺ 3 ሄ/ር መሬት ላይ የለማ የአተር ማሳ ማሳያ ሲሆን
በወረዳው እየለማ ባለው የአተር ምርት በሄክታር 12 ኩንታል ምርት ይመረታል ተብሎ ይጠበቃል።

Hadiya zone communication

23 Oct, 18:04


#የብሪክስ_አባል_ሀገራት‼️

16ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ በሩሲያ ካዛን ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በ16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸው ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ የምታደርገውን ተሳትፎ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓም
#ኢትዮጵያ ፕሬስ

Hadiya zone communication

23 Oct, 17:36


#ደሬቴድ አመራሩ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ማሳካት እንዲችል የጋራ ግንዛቤ ሊፈጠር እንደሚገባ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቁ

ምንጭ ደሬቴድ