🔷የሲሚንቶ ግብይት ላይ በተወሰደ የአሰራር ስርዓት ማሻሻያ የተረጋጋ አቅርቦትና ግብይት እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር ዋጋው በግማሽ እንዲቀንስ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
🔷ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የፌደራልና የክልሎች የንግድ ዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ዛሬ አካሂደናል ብለዋል፡፡
🔷በ6 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ሚሊየን 50 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦንላይን መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
🔷ከጠቅላላው ሀገራዊ የወጪ ንግድ 3 ነጥብ 28 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸው፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 1 ነጥብ 71 ቢሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።
🔷የቅዳሜና እሁድ ግብይት ማዕከላትን 1 ሺህ 213 ማድረስ መቻሉንም ተናግረዋል።
🔷የሲሚንቶ ግብይት ላይ በተወሰደ የአሰራር ስርዓት ማሻሻያ የተረጋጋ አቅርቦትና ግብይት እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር ዋጋው በግማሽ እንዲቀንስ መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡
🔷በስድስት ወሩ ዓለም አቀፍ ጥራቱን የጠበቀ የጥራት መንደር በ7 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተገንብቶ ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰው÷ በተቋሙ ቅጥር ግቢ 730 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ የወጪ ንግድ ማሳያ ማዕከል ተገንብቶ የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት አቅሞችን በማስተዋወቅ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
🔷ዓለም አቀፍ የንግድ ትስስርን በማጠናከር አስተማማኝ የገበያ እድል ከመፍጠር አንጻር የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግም እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
(ኤፍቢሲ)