ሲዲ ስፖርት/CD Sport @dc4544 Channel on Telegram

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

@dc4544

ክላሲክ እና ዳይናሚክ ስፖርት በዩ-ቱብ https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=Yk8kAbDyLZZzoTp-
ሲዲ ስፖርት በአራዳ ራዲዮ 95.1 - ትክክለኛ የሀገር ዉስጥ እና የባህርማዶ ስፖርታዊ መረጃዎችን የሚያገኙበት ቻናል።
"ሙያን ለሙያተኛ"

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት (Amharic)

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት ለእርስዎ ያለት ስለሆነ አዲስ በዩ-ቱብ የዳይናሜክ ውጤታዊ ስፖርት ነው። በአራዳ ራዲዮ 95.1 የትክክለኛ የሀገር ዉስጥና የባህርማዶ ስፖርት መረጃዎችን ለማየት ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን በመከራ ላይ በማከናወን ሙያን ለሙያተኛ ለተለያዩ ክላሲክ ስፖርት ይታያል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

02 Feb, 08:55

https://vm.tiktok.com/ZMkqYCkSP/

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

02 Feb, 08:54

የአርሰናሉ ግብጠባቂ ዴቪድ ራያ ከጉዳቱ አገግሞ ከቡድኑ ጋር ሆቴል ገብቷል።ለምሽቱ የማንችስተር ሲቲ ፍልሚያም ዝግጁ እንደሆነ ታውቋል።

ሲዲ ስፖርት/cd sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

02 Feb, 08:54

አስቶንቪላ በመጨረሻው ቀን 3ት አጥቂ ተጫዋቾችን ሊያስፈርም ጫፍ ላይ ደርሷል።ራሽፎርድን ከማንችስተር ዩናይትድ፣ማርኮ አሴንሲዮን ከፒ ኤስ ጅ እና ዥዋ ፍሊክሽን ከቸልሲ ለማዘዋወር የወረቀት ስራዎችን እያጠናቀቁ ነው።

ሲዲ ስፖርት/cd sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

26 Dec, 09:42

#ማስታወቂያ
ለስራ ፈላጊዎች አስቸኳይ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
1.የስራ መደቡ - ሴኒየር አካውንታንት
የስራ ልምድ - ከ5 አመታት በላይ
ብዛት - 3
ደመወዝ በድርድር ሲሆን አጓጊ ጥቅማጥቅሞችም አለው።

2.የስራ መጠሪያ - ሴኒየር መሀንዲስ
የስራ ልምድ - ከ5 አመታት በላይ
ብዛት - 3
ደመወዝ በድርድር ሲሆን አጓጊ ጥቅማጥቅሞችም አለው።

አመልካቾች ሲሺያችሁን ይዛችሁ መገናኛ አካባቢ እንግሊዝ ኢምባሲ ከመድረስዎ 100 ሜትር ቀደም ብሎ ባለው ሜናሮል ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ።ለበለጠ መረጃ በ0911404917 ላይ ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
ይፍጠኑ ቅድሚያ ለሚመጣ ቅድሚያ ይሰጣል!

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

16 Dec, 05:02

ባርሴሎና በሜዳው ለሌጋኜስ 1 ለ 0 እጅ በሰጠበት ጨዋታ ፈርሚን ሎፔዝ ጥርሱን አጥቷል። ላሚን ያማል የቁርጭምጭሚት ጉዳት አስተናግዷል። የላሊጋው ትንቅንቅ አስደናቂ ሆኗል። ሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እያላቸው ከላሊጋው መሪ ባርሴሎና ጋር አትሌቲኮ ነጥቡን እኩል ሲያደርግ ሪያልማድሪዶች ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ አጥበውታል። አትሌቲኮ ማድሪድ በ11 ተከታታይ የላሊጋ ጨዋታ በተከታታይ ድል አስመዝግቧል። የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ ከባለፉት 6 ጨዋታዎች 3 ተሸንፈው ሁለት አቻ ወጥተው አንድ ጨዋታ አሸንፈዋል ።9 ጎሎችም ተቆጥረውባቸዋል።

ሲዲ ስፖርት/cd sport

👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

15 Dec, 16:44

https://www.youtube.com/live/olXcoyGFplY?si=-RiDD-ry8X4yzSWU

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

11 Dec, 05:38

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል። ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ያሉት ቡድኖች በቀጥታ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ የሚገቡ ይሆናል።

ሲዲ ስፖርት/cd sport

👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

26 Nov, 07:26

አማራ ክልል ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ ጠንካራ እጩዎችን አቀረበ።

ታህሳስ 12 እና 13 ለሚካሄደው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ አማራ ክልል አቶ ያየህ አዲስን ለፕሬዝደንትነት እጩ አድርጎ አቅርቧል። አቶ ያየህ አዲስ የቀድሞ የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ እና የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው አገልግለዋል። በስፖርት አመራርነት ረዥም ጊዜ የቆዩት አቶ ያየህ አዲስ የባህርዳር ስቴዲየምን በማስገንባት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ።

አቶ ቢልልኝ መቆያ እና ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ ክልሉ ለስራ አስፈፃሚነት በእጩነት ያቀረባቸው ናቸው። አቶ ቢልልኝ መቆያ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽ/ቤት ሀላፊ ሆነው አገልግለዋል። የአማራ ክልል ምክትል ስፖርት ኮሚሽነር ሆነው በአመራርነት ረዥም ጊዜ ሰርተዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በስርአት እንዲመራ ሪፎርም በማዘጋጀት እና በመተግበር ከፍተኛ ስራም አከናውነዋል። ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ አሁንም በፌዴሬሽኑ ውስጥ በስራ አስፈፃሚነት የሚገኙ ናቸው።

ሲዲ ስፖርት/cd sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

19 Nov, 08:46

በአለም ላይ እለት በእለት የሚሰማው ዜና እጅን አፍ ላይ ያስጭናል።

የቸልሲዋ ተጫዋች ሳም ኬር እና የዌስትሀሟ ክርስቲ ሜዊስ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት የመጀመሪያ ልጃቸውን እንደሚጠብቁ ተናገሩ። ከሁለቱ ፍቅረኛማቾች የትኛዋ እንዳረገዘች እና ያስረገዘው ወንድስ ማን እንደሆነ ስካይ ስፖርት ያለው ነገር የለም። አጃኢብ !! ከማለት ውጭ ሌላ ምን ይባላል። ይህ ሲዲ ስፖርት ነው ።

ሲዲ ስፖርት/cd sport

👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

19 Nov, 04:44

የ58 አመቱ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ሰሞኑን አስገራሚ ቃለ ምልልስ ሰጥቷል።

"አሁን ላይ በህይወት መኖሬ በጣም እድለኛ ነኝ። በአንድ ወቅት ከጓደኛዬ ጋር በመሆን አንዲት ሴት ጋር ጥንቃቄ የጎደለው እና ልቅ ወሲብ ፈፀምኩኝ። እሱም እሷም በHIV ኤድስ ህይወታቸው አልፏል። እኔ ግን በህይወት አለሁኝ ። የሚያስገርመው ደግሞ በደሜ ውስጥ ቫይረሱ አለመኖሩ ወይም ነፃ መሆኔ ነው። ይህንን ባለሙያዎች ምን እንደሚሉት አላውቅም ። ግን ጥናት እንዲያደርጉብኝ እፈቅድላቸዋለሁ። " ብሏል።

ሲዲ ስፖርት/cd sport

👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

19 Nov, 04:43

ትንሿ አገር ትልቅ እና ታሪካዊ ድል አስመዘገበች።

ከሁለት ወር በፊት ሴፕቴምበር 5፣ 2024 እ.ኤ.አ በወዳጅነት ጨዋታ ሳን ማሪኖ በ20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሊችተንስታይንን 1-0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ታሪካዊ ድል አስመዝግባለች ። 🤯

ትናንት ኖቬምበር 18፣ 2024 እ.ኤ.አ ሳን ማሪኖ ሊችተንስታይንን 3-1 ከረታች በኋላ ወደ ኔሽንስ ሊግ ሲ ማደጓን አረጋግጣለች።

የሳን ማሪኖ የ3 ለ1 ድልን ተከትሎ:-

በታሪካቸው ትልቁ ድል
ከሜዳቸው ውጭ የመጀመሪያ ድል
የ UEFA እና የፊፋ አባል ከሆነች በኋላ የመጀመሪያ የፉክክር ጨዋታ ድል ሆኖ ተመዝግቦላታል።

ታሪካዊ ምሽት ለሳንማሪኖ። 👏

ሲዲ ስፖርት/cd sport

👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

19 Nov, 04:43

ሌላዋ የሴካፋዋ ሱዳን 🇸🇩 የ2025ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በብቃት በማጠናቀቅ ወደ ሞሮኮ ትኬት ቆርጣለች 🇲🇦 👏

ምንም እንኳን በሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በሜዳዋ ጨዋታ ሳታደርግ እና ሁሉንም ግጥሚያዎች ከሜዳዋ ውጭ ብትጫወትም በጋናዊው አሰልጣኝ ክዌሲ አፒያ ስር ጠንካራ አቋም አሳይታለች። ከምድቧ 8 ነጥብ ይዛ አንጎላን ተከትላ አፍሪካ ዋንጫ አልፋለች። ሱዳን በምድቧ ጋናን 2 ለ 0 በማሸነፍ እና 0ለ0 በማጠናቀት ከእግር ኳሷ ጠንካራ ሀገር ጋና 4 ነጥብ መውሰድ ችላለች ። ኒጀር ላይ 3 ነጥብ አንጎላ ላይ ላይ 1 ነጥብ አግኝታለች።

ሲዲ ስፖርት/cd sport

👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

14 Nov, 02:43

ዌስትሀም ፔናሊቲ አይገባውም።
(ሲዲ ስፖርት/ CD Sport:ህዳር 5/2017)የዳኞች አለቃ ሃዋርድ ዌብ ጥቅምት 27 የኤሪክ ቴን ሃግ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ ዌስትሃም ፍፁም ቅጣት ምት ሊሰጠው አይገባም ነበር ብለዋል።

መዶሻዎቹ ውሳኔውን ያገኙት በቫር ዳኛ ማይክል ኦሊቨር ጥቆማ ማቲያስ ዴሊት በዳኒ ኢንግስ ላይ ጥፋት ሰርቷል በሚል ነው። ዋናው ዳኛ ዴቪድ ኩት የቫር ጥሪን ከሰማ በኋላ ፍፁም ቅጣት ምቱን ሰጥቷል።

ጃሮድ ቦወን ወደጎልነት ቀይሮት ዌስትሃም ማንችስተር ዩናይትድን 2-1 በማሸነፍ አሰልጣኝ ቴን ሃግ ከጨዋታው በኋላ ከ24 ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከክለቡ አሰልጣኝነት ሊባረር ችሏል።

"በVAR የተሳሳተ ውሳኔ ፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል። መሆን አልነበረበትም። VAR እምነት የሚጣልበት ነበር ። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ የዴሊት እግር ወደ ዳኒ ኢንግስ እየተጠጋ እንጂ ምንም እግሩን አልጠለፈውም። ኳሱን ስላላገኘው ለቫር ዳኞች ንክኪ ያለው መስሏቸው ነው። " ሲል ሀዋርድ ዌብ ለስካይ ስፖርት ተናግሯል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport
👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

14 Nov, 02:13

ቤንታንኩር ከባድ ቅጣት ሊጣልበት ነው ።
(ሲዲ ስፖርት/ CD Sport: ህዳር 5/2017)የቶተንሀሙ አማካኝ ዩራጓዊው ሮድሪጎ ቤንታንኩር ሰባት ጨዋታዎች እንደሚቀጣ ይጠበቃል።

ቤንታንኩር በዩራጓይ ቴሌቪዥን በተደረገለት ቃለምልልስ ላይ ጋዜጠኛው ስለቶተንሀም ተጫዋቾች ማሊያ በጠየቀበት ወቅት ስለ ደቡብ ኮሪያዊው ሰን ሂዩንግ ሚን "ሰን ሜዳ ላይ ይኑር አይኑር እርግጠኛ አይደለንም ። የሰን አክስት ልጅ ሜዳ ውስጥ እየተጫወተ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም ደቡብ ኮሪያዎች መልካቸው አንድ አይነት ነው።" ብሏል ።

ቤንታንኩር በኋላ ላይ ደስ የማይል ቀልድ ነው የተናገርኩት በማለት ሰንሂዩንግ ሚንን ይቅርታ ጠይቆታል ሰንም "እኔ ሮድሪጎን እወደዋለሁ እያለቀሰ የጠየቀኝን ይቅርታውን ተቀብያለሁ ብሏል ።"

ይሁን እንጂ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የዘረኝነት ቃል ነው በሚል ቤንታንኩር ክስ እንዲመሰረትበት ተደርጓል። ቀድሞ በወጣው የውስጥ አዋቂዎች መረጃ ሮድሪጎ ቤንታንኩር የሰባት ጨዋታዎች ቅጣት እንደሚጣልበት ታውቋል። የቅጣቱ ውሳኔ ሲተላለፍ ቶተንሀም ከማንሲቲ፣ ፉልሀም ፣ በርንመዝ፣ ቸልሲ፣ ሳውዝሀምፕተን፣ ማንዩናይትድ እና ሊቨርፑል ጋር የሚያደርገው ጨዋታ እንደሚያመልጠው ተገልፆል። ቦታውን ቢሱማ አለያም የ18 አመቱ አርክ ግሬይ እንደሚሸፍኑት ይጠበቃል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport
👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

14 Nov, 02:12

ዘጠነኛ የእንግሊዝ ተጫዋች የጉዳት ሪፖርት ቀረበ።

(ሲዲ ስፖርት / CD Sport:ህዳር 5/2017)ጃራድ ብራንትዋይት ሌዊ ኮልዊልን ለመተካት ከተጠራ ከሁለት ቀናት በኋላ በደረሰበት ጉዳት ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ውጪ ሆኗል።

በዚህ ኢንተርናሽናል ጨዋታ ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ውጭ የሆኑት ዘጠኝ ተጫዋቾች ሆነዋል። እነሱም:-

ትሬንት አሌክሳንደር-አርኖልድ
ጃራድ ብራንትዋይት
ሌዊ ኮልዊል
ፊል ፎደን
ጃክ ግሪሊሽ
ኮል ፓልመር
አሮን ራምስዴል
ዲክላን ራይስ እና
ቡካዮ ሳካ ናቸው።

እንግሊዝ ዛሬ ምሽት ከግሪክ እንዲሁም እሁድ ከሪፐብሊክ ኦፍ አየርላንድ ጋር በኔሽንስ ሊግ ትጫወታለች።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport
👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

11 Nov, 14:34

ሩበን አሞሪም የአሰልጣኝ አባላቶቻቸው ይዘው አሁን ማንችስተር ኤርፖርት ደርሰዋል።አዲሱን የህይወት ምዕራፋቸውን ዛሬ ይጀምራሉ።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

10 Nov, 13:03

ዲክላን ራይስ ከአርሰናል ጋር ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ተጉዟል።ምሽት 1:30 ላይ ቸልሲን ከሚገጥመው የአርሰናል ስብስብ ውስጥ መካተቱ ተረጋግጧል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

10 Nov, 06:31

https://vm.tiktok.com/ZMhbCtjmA/

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

10 Nov, 06:31

ለንደን ደርቢ...ቸልሲ ከ አርሰናል ይገምቱ ይሸለሙ!

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

10 Nov, 06:28

https://vm.tiktok.com/ZMhbCwSMk/

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

10 Nov, 06:18

ለልጇ ስትል ኮሜንታተር የሆነችው እናት...

ኒኮላስ ይባላል 11 አመቱ ሲሆን አይነ ስውር ነው።ይህ ብራዚላዊ ታዳጊ ታዲያ ከልጅነቱ ጀምሮ የፓልሜራስ እግርኳስ ክለብ ደጋፊ ነው።እናቱ ሲልቪያም የፓልሜራስ የልብ ደጋፊ ስትሆን እያንዳንዱን ጨዋታ ከልጇ ጋር ትታደማለች።ሲልቪያ ጨዋታውን መመልከት ብቻ ሳይሆን የጨዋታውን ኮሜንተሪ መስራትም ግዴታው ነው።ምክንያቱም እግርኳስን ከልቡ ለሚወደው አይነ ስውር ልጇ ይህን ማድረግ ያስደስታታልና።በስቴዲየሙ ውስጥም ከልጇ ጎን ቁጭ ብላ የጨዋታውን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ወደ ጀሮው ጮህ ብላ ትነግረዋለች።ፓልሜራስ በተጫዎተ ቁጥርም በእያንዳንዱ ጨዋታ ከ90 ደቂቃ በላይ ኮሜንተሪ ትሰራለች።እናት ሲልቪያ ለዚህ ድንቅ ተግባሯም በፊፋ 2019 ላይ የአመቱ ምርጥ ደጋፊ ሽልማት ተበርክቶላታል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

10 Nov, 06:17

ዦዜ ሞሪኒዮ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሊመለሱ ነው።ኒውካስትል ከውጤት መራቅ ጋር በተያያዘ ኢዲ ሆውን አሰናብቶ ሞሪኒዮን ለመቅጠር ውስጥ ለ ውስጥ እየተነጋጋሩ ነው።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

09 Nov, 19:49

ከ18 አመት በኋላ አራተኛ ሽንፈት !!
ማንችስተር ሲቲ አራተኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ። ዛሬ በአሜክስ ስቴዲየም ብራይተንን የገጠመው የፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ በሀላንድ ጎል መርቶ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ በተቆጠሩበት ሁለት ጎሎች 2ለ1 ተሸንፏል። ጋርዲዮላ በአሰልጣኝነት ታሪኩ አጋጥሞት የማያውቅ አራተኛ ተከታታይ ሽንፈት ሆኗል። ማንችስተር ሲቲ ከ2006 በኋላ የተመዘገበበት አራተኛ ሽንፈቱ ነው።

CD Sport / ሲዲ ስፖርት

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

09 Nov, 08:43

ዦዜ ሞሪኒሆ ቅጣት ተላለፈባቸው። የቱርኩ ፌነርባቼ አሰልጣኝ ሞሪኒሆ ቡድናቸው ፌነርባቼ በቱርክ ሊግ ትራብዞንስፖርን ባለቀ ሰአት አስቆጥሮ 3 ለ 2 ማሸነፉን ተከትሎ እና ለትራብዞንስፖር የተሰጡትን ሁለት ፍፁም ቅጣት ምት በመቃወም የቱርክን ዳኞች መዝለፋቸው ይታወሳል። በዚህም የ 1 ጨዋታ እና የ15 ሺ ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

CD Sport / ሲዲ ስፖርት

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

09 Nov, 08:42

የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በዚህ አመት ይጠናቀቃል።

የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲዮም የካፍንና የፊፋን ስታንዳርድ ባሟላ መልኩ በዚህ አመት እንደሚጠናቀቅ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የጉብኝት ፕሮግራም ላይ ተገልጿል።

ስታዲዮሙ የዲዛይን ማሻሻያ ተደርጎለት 2000 ቪ.አይ.ፒ እና 25 ሽህ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ሆኖ ተሰርቷል።ስቴዲየሙ አጠቃላይ 87% አፈጻጸም ላይ ይገኛል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

09 Nov, 08:41

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጫዋች የኖቲንግሀሙ አጥቂ ክሪስ ውድ እና የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪንቶ ሳንቶ ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

08 Nov, 14:48

ፖርቹጋል ከ ፖላንድ እና ክሮሽያ ጋር በኔሽንስ ሊግ ላለባት ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ቡድኗ ውስጥ አካታለች።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

08 Nov, 14:48

ሉክ ሾ ከጉዳቱ አገግሞ ሙሉ ልምምድ ጀምሯል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

08 Nov, 14:47

በአርሰናል የስፖርቲንግ ዳይሬክተር ቦታ የኤዱ ምትክ ይሆናሉ በሚል በእጩነት ከተያዙት መካከል አንዱ ቶማስ ሮዝስኪ ሆኗል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

07 Nov, 15:00

ክርስቲያኖ ሮናናዶ ከሳውዲው ክለብ አልናስር ጋር ያለው ኮንትራት በመጭው ሰኔ ወር ይጠናቀቃል።እስካሁን አልናስር የሮናልዶን ኮንትራት ለማራዘም ፍላጎት አለማሳየቱን ተከትሎ ሌላኛው የሳውዲ ክለብ አልሂላል ፖርቹጋላዊውን ኮከብ ለማስፈረም ጥያቄ አቅርቦለታል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

05 Nov, 10:55

በሳምንቱ መጨረሻ ቸልሲ ከ አርሰናል የሚያደርጉትን ጨዋታ ማይክል ኦሊቨር በዋና ዳኘነት ይመሩታል።እኘህ ዳኛ አርሰናል ከ ማንችስተር ሲቲ ሲጫዎቱ ለሊያንድሮ ትሮሳርድ ቀይ ካርድ ማሳየታቸው ይታወሳል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

05 Nov, 10:55

"እንደ ቅርጫታ ኳስ ተጫዋቾች በአመት 70 ጨዋታዎች እንድንጫዋት ተገደናል።አሰገራሚው ነገር ትልቁ የቅርጫት ኳስ ሊግ/NBA/ በአመት የ4 ወር እረፍቶች አሏቸው።እኛ ከ3 ሳምንት ያነሰ ጊዜ ነው በአመት እረፍት ያለን።"ፔፕ ጋርዲዮላ

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

05 Nov, 10:41

https://www.facebook.com/share/p/EAAwTsuvsaQsVmKZ/?mibextid=qi2Omg

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

04 Nov, 13:08

አርሰናልን ለመልቀቅ የወሰነው ኤዱ ጋስፐር ወደ ኖቲንግሀም ፎረስት እግርኳስ ክለብ የሚያመራ ሲሆን የኖቲንግሀም ክለብ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን በአርሰናል ይከፈለው ከነበረው 3 እጥፍ ደመወዝ እንደሚያገኘ ታውቋል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

04 Nov, 06:05

የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ ልጃቸውን ጊዮሊያኖ ሲሞኔን ወደ ሜዳ በማስገባት ልጃቸው ባስቆጠረው ጎል ጨዋታውን አሸንፈዋል።ጊዮሊያኖ ጎሏን ካስቆጠረ በኃላ መታሰቢያነቱን ሰሞኑን በጎርፍ አደጋ ለተጠቁት ቫሌንሽያዎች ይሁንልኝ ብሏል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

01 Nov, 17:15

አርሰናል ነገ ከቀኑ 9:30 ላይ ከኒውካስትል ጋር ከሜዳው ውጭ በሚያደርገው ጨዋታ ወሳኝ ተከላካዩ ጋብሬል ማጋሌዥ እንደሚደርስ አስታውቋል።ኋይት፣ሳሌባ፣ጋብሬል እና ቲምበር የተከላካይ መስመሩን እንደሚመሩት ይጠበቃል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

01 Nov, 13:55

ሮቢን አሞሪም በይፋ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኘ ሁነው ተሹመዋል።በቀጣይ ሳምንት መጨረሻ ማንችስተር ዩናይትድን የሚረከቡ ሲሆን ከብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎች እረፍት በኃላ ማለትም ከ23 ቀናት በኃላ ማንችስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ከኢፕሲዊች ታውን ጋር ሲጫዎት ቀያዩቹ ሰይጣኖቹን የሚመሩ ይሆናል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

29 Oct, 08:58

ማርቲን ኦደጋርድ ከጉዳቱ አገግሞ ሜዳ ላይ ዛሬ ልምምድ ጀምሯል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

28 Oct, 12:12

ሠበር...
ኤሪክ ቴን ሀግ ከማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነት ተሰናብተዋል።በጊዜያዊነት ሩድ ቫን ኒስትሮይ ቡድኑን የሚያሰለጥኑ ይሆናል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

27 Oct, 16:37

https://www.youtube.com/live/AHP9TpuTBpo?si=DRtNVnwwJ-ls9yfq

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

27 Oct, 12:13

ማሪዮ ባሎቲሊ በጣሊያን ሴሪ ኤ የሚገኘውን ጅንዋ እግርኳስ ክለብን በ1 አመት ውል ተቀላቅሏል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

27 Oct, 12:13

ላሚን ያማል በትናንቱ የኤልክላሲኮ ጨዋታ በሪያልማድሪድ ጥቂት ደጋፊዎች የዘረኝነት ስድብ አስተናግዷል።ማድሪድ እና ላሊጋው ይህንን ያደረጉት ደጋፊዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ እንወስዳለን ብሏል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

27 Oct, 12:12

ሳካ እና ቲምበር ዛሬ ሊቨርፑልን የሚገጥመው የአርሰናል ቡድን ስብስብ ውስጥ ተካተዋል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

26 Oct, 11:13

ማንችስተር ዩናይትድ ኤሪክ ቴን ሀግን ለመተካት በድብቅ አሰልጣኞችን እያናገረ ነው።የቀድሞው የባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪ ቁጥር 1 እቅዳቸው ሁኗል።ቶማስ ፍራንክ፣ሮቢን አሞሪም እና ኢዲን ተርዚችም ዝርዝሩ ውስጥ አሉ።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

26 Oct, 11:12

የብራዚሉ ክለብ ቫስኮ ደጋማ የልምምድ ቦታ ላይ አዞ መገኘቱን ተከትሎ ክለቡ የልምምድ ቦታውን ለመቀየር ተገዷል።

ሲዲ ስፖርት/CD sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

26 Oct, 11:11

😲🛩️ ለባላንዶር ሽልማት ወደ ፓሪስ ከሚሄዱት የማንችስተር ሲቲ ተጫዋቾች ጋር ጋርናቾ እና ኮቢ ማይኖ አብረው እንዲጓዙ ማንችስተር ዩናይትዶች ቢጠይቁም ማንችስተር ሲቲዎች በረራችን ሙሉ ነው በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርገውታል።የባላንዶር ሽልማት ሰኞ ምሽት በፓሪስ ይከናወናል። 😳

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

26 Oct, 11:10

Channel name was changed to «ሲዲ ስፖርት/CD Sport»

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

19 Oct, 16:42

https://www.youtube.com/live/TmwH6_KUm6E?si=kIZxUq6bwOVwktn7

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

19 Oct, 07:36

የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ የታገቢኛለሽ ወይ? ጥያቄ ተቀባይነት አግኘቷል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

19 Oct, 07:36

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጎል ማምረቱን ቀጥሏል።1000 ጎል ለመሙላት 93 ጎሎች ብቻ ይቀሩታል።ትናንት 907ኛ ጎሉን አልናስር 2-1 አልሻባብን ባሸነፈበት ጨዋታ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

18 Oct, 09:58

"ቡካዮ ሳካ እና ቶማስ ፓርቴ ለነገው ጨዋታ ዝግጁ ናቸው።ማርቲኔሊ እና ሀቨርዝ በተመለከተ ዛሬ እንወስናለን።ቲምበር፣ኋይት እና ዚንቸንኮ ሰሞኑን በሚኖሩ ጨዋታዎች ላይ ይሳተፋሉ።ማርቲን ኦዲጋርድ ቀጣይ ሳምንት በሊጉ በሚኖረን ጨዋታ የመድረስ እድሉ ሰፊ ነው።" ሚኬል አርቴታ

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

18 Oct, 07:43

ማንችስተር ዩናይትድ ዘጠነኛ ደረጃን ይዞ እንደሚጨርስ Opta ተነበየ።

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሲጠናቀቅ ዘንድሮም ሻምፒዮን የሚሆነው ማንችስተር ሲቲ ነው ሲል የOPta የጥቅምት ወር ቅድመ ትንበያ ጠቁሟል። አርሰናል ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደሚጨርስ ትንበያው ያሳያል። ሊቨርፑል ሶስተኛ፣ቸልሲ አራተኛ ፣ቶተንሀም አምስተኛ፣ ኒውካስትል ስድስተኛ፣ አስቶንቪላ ሰባተኛ ፣ ብራይተን ስምንተኛ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው ይጨርሳሉ ይላል ትንበያው። ሌስተር ሲቲ ወይም ወልቭስ ፣ ኢፕሲዊች ታውን እና ሳውዝሀምፕተን ከ18ኛ እስከ 20ኛ ደረጃን ይዘው ይወርዳሉ ሲል የOpta የጥቅምት ወር ትንበያ ይጠቁማል።

ሰዲ ስፖርት / CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

18 Oct, 07:42

" ተስፋ አልቆርጥም / እጅ አልሰጥም / Never give up "

የአርሰናል እና የጣሊያን ተከላካይ የ22 አመቱ ሪካርዶ ካላፊዮሪ ክንዱ ላይ "never give up" ስለሚለው ንቅሳት ተጠይቆ እንዲህ ብሏል።

" በዩኤፋ የወጣቶች ውድድር ላይ በ16 አመቴ ለሮማ ስጫወት ከባድ የጉልበት ጉዳት አስተናገድኩኝ። ጉልበቴ ላይ ሊጋመንቶቼ ተበጣጠሱ። አይደለም ለመጫወት ይቅርና መራመድ አቃተኝ። ኳስ በድጋሚ እንደማልነካ ተሰማኝ። ቀስ በቀስ ግን ራሴን አሳመንኩትና ኳስ መጫወት አለብኝ ብየ ወሰንኩኝ ። ይህንን ስወስን መራመድ እንኳን አልችልም ነበር። እንደምንም ብየ በክራንች ንቅሳት ቤት ሄጄ የመጀመሪያየ የሆነውን "Never give up " የሚል ንቅሳት ተነቀስኩኝ ። ከብዙ ትግል በኋላ ከዛ ፈተና አልፌ በታላቁ አርሰናል ቤት እገኛለሁ ። " ብሏል።

ሲዲ ስፖርት / CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

18 Oct, 06:48

ሊዮኔል ሜሲ የአለማችን የምንግዜም ምርጡ ተጫዋች ተብሎ በማርካ አሜሪካ ተሸልሟል።

1. Lionel Messi 🇦🇷
2. Cristiano Ronaldo
3. Pelé
4. Di Stefano 🇦🇷
5. Maradona 🇦🇷
6. Cruyff

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

18 Oct, 06:48

ባየርሙኒክ አዲስ ሎጎ አስተዋውቋል።የድሮውን እና የአሁኑን አያይዘናል።በሁለቱ ሎጎዎች መካከል 7 ልዩነቶች እንዳሉ አሳውቋል።እስኪ ጎበዝ የሆነ 7ቱን ልዩነቶች የሚነግረን?

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

17 Oct, 17:20

በዛሬው የአርሰናል ልምምድ ላይ ማርቲኔሊ፣ሳካ፣ቲምበር፣ቤን ኋይት፣ኦድጋርድ፣ቶሚያሱ እና ኬረን ቲርኒ አልተሳተፉም።

ሲዲ ስርአት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

17 Oct, 17:08

🚨 ፖል ፖግባ: "ህይወት ምን እንደሆነ በደምብ የገባኝ ቅጣቱ ከተላለፈብኝ በኃላ ነው።በየ ሳምንቱ ፋሽን ሾው ካላሳየህ እያሉ እግሬን ሲልሱ የነበሩ ድርጅቶች እንኳን ሊለምኑኝ እኔ እነሱ ጋር ስሄድ በራቸውን ይዘጉብኛል።የልብ የምላቸው ጓድኞቸ እንኳን ሊያገኙኝ ስድውልላቸው ስልኬን አያነሱም።ከዚህ በኃላ ፖግባ በሁለት ይከፈላል ከቅጣቱ በፊት እና ከቅጣቱ በኃላ በሚል...

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

17 Oct, 17:07

ጃክ ዊልሸር የኖርዊች እግርኳስ ክለብ አሰልጣኝ ለመሆን ተቃርቧል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

17 Oct, 17:07

ክልያን ምባፔ ሰሞኑን በስዊድን በነበረው ቆይታ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተጠርጥሮ ፖሊስ ምርመራ እያደረገበት ነው።የስዊድን ፖሊስ ምባፔ አርፎበት በነበረበት ሆቴል ጥርጣሬውን የሚያጠናክር አዲስ ማስረጃ ማግኘቱን አስታውቋል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

17 Oct, 17:06

ዋይኒ ሩኒ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ በእድሜ በስምንት ወር ያንሳል ።

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

16 Sep, 15:07

አሰልጣኝ ስዮም ከበደ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሁኖ ተሹሟል!

በታንዛንያ አስተናጋጅነት በሚካሄው ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣርያ ውድድር ላይ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ሹመት ተከናውኗል። በዚህም መሠረት በዋና አሰልጣኝነት ሥዩም ከበደ ፣ በረዳት አሰልጣኝነት ደግሞ ዐቢይ ካሣሁን እና አምሳሉ እስመለዓለም ሆነው ተሹመዋል።

ለውድድሩ ዝግጅት የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር ዛሬ ይፋ የሚደረግ ሲሆን ከነገ ጀምሮ በመሰባሰብ ዝግጅት የሚጀምሩ ይሆናል።

©️EFF

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

16 Sep, 14:56

የቡካዮ ሳካ ጉዳት ለክፉ እንደማይሰጥ ተረጋግጧል።የፊታችን ሀሙስ በሻምፒዮንስ ሊግ ከአትላንታ ጋር አርሰናል ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጁ ነው።ሚኬል ሜሪኖም ከታሰበው ቀድሞ ልምምድ ጀምሯል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport
👉 youtube:
https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J
👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1
👉 telegram:
https://t.me/DC4544
👉 facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

15 Sep, 08:30

"ይህንን ፎቶ ያነሳን ዜነዲን ዚዳን ነው።" ክልያን ምባፔ

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

15 Sep, 08:29

ለመላው ኢትዮጵያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ቤተሰቦቻችን እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ !!
መልካም በዓል!

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ክላሲክና ዳይናሚክ ስፖርት/ Classic & Dynamic sport ሲዲ ስፖርት/CD Sport/

13 Sep, 15:21

ጋርዲዮላ ስለ ማንችስተር ሲቲ 115 ክስ

"ክሱን መስማት በፍጥነት ጀምረዋል።ውሳኔውም በተመሳሳይ በፍጥነት ያልቃል።የተከሰሰ ሁሉ ጥፋተኛ አይደለም።በህግ ጥፋተኛ እስካልተባልን ድረስ ንፁህ ነን።"

ሲዲ ስፖርት/CD Sport