ከ መናኙ አንደበት

@mikre_haymanot


የአባቶች ምክር ታሪክ እንዲሁም ተግሳፅ ይቀርቡላችኋል።
ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት @Ab_man2121
https://www.youtube.com/@herantube7506
በ facebook ይከተሉን https://m.facebook.com/profile.php/?id=100067719306101

ከ መናኙ አንደበት

23 Oct, 10:30


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

ከ መናኙ አንደበት

23 Oct, 08:50


. #ጥያቄ ስለ ከበሮ .

💁 ከበሮ ማለት ምን ማለት ነው
🥁 ከበሮ የምን ተምሳሌት ነው ⁉️
💁 የከበሮ ጨርቅ ለምን ቀይ ብቻ ሆነ
💁 ከበሮ ዉስጡ ለምን ባዶ ሆነ ⁉️

👉ሌሎችም ጥያቄዎች......የቀሩትንም ለማየት

ከ መናኙ አንደበት

23 Oct, 08:07


አሟሟቴን አሳምሪዉ!?


በማስተዋል እንከታተል

በቸሩ ዋሉ


💖

ከ መናኙ አንደበት

23 Oct, 07:46


ስድቤን አርቀሽ

ስድቤን አርቀሽ ነውሬን ሸፈንሽው
እመ አምላክ በአንቺ መቼም አላፍር
ስምሽን ጠርቼ እጽናናለሁኝ
ሀዘኔን በአንቺ እረሳለሁኝ
አዝ።።።
ነውር አለብኝ ብዙ ስድብ
አንጀት የሚልጥ ልብ የሚያቆስል
ስሜን ለውጠው ቢያንቋሽሹኝ
በሀዘን በለቅሶ ድንግል መጣሁኝ
እንደ ሃና ሆኜ ከቤተ መቅደስ
በመረረ ሐዘን ነው የማለቅስ
ፍረጅልኝና ልመለስ ከቤቴ
ሐዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ
በግራም በቀኝም ጠላት ቢከበኝ
አብዝቼ እጮሃለው እናቴ ስሚኝ
አዝ።።።
መከራው በዝቶ ግራ ገብቶኛል 
ድምፅሽን ልስማ ያረጋጋኛል 
የሰው ህይወቱ ብርቱ ሰልፍ ነው      
ደስታና ሐዘን የማይለየው
በእጃችን ወድቋል ሲሉ ጠላቶቼ
አመለጥኳቸው ስምሽን ጠርቼ
ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል
በቆፈረው ጉድጓድ ራሱ ይገባል
እናቴ እመቤቴ ብዬ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጪኛለሽ
አዝ
በምርኮ ሳለሁ በሰው ሀገር     
ግፍ ውለውብኝ ስኖር በእስር      
ምልጃሽ ደርሶልኝ ተፈትቻለሁ      
በታምራትሽ እኔ ድኛለሁ
ቃልሽን ሰምቶ ጽንሱ ሰገደ
ብላለች ኤልሳቤጥ ነውሬ ተወገደ
የጌታዬ እናት እኔን አሰበችኝ
ታሪኬን ቀይራ ይኽው ባረከችኝ
የእመቤቴ ከሆንኩ ማን ይቃወመኛል
ወጀቡም ማእበሉም ይታዘዝልኛል
አዝ።።።።
ወይን እኮ አልቋል የዶኪማስ ቤት      
ድንግል አማልጅው ነይ የእኛ እመቤት      
ስምሽ ሲጠራ በየቦታው      
ይሞላልና የጎደለው           
ግራ የገባው የቸገረው            
ድንግልን ይጥራት እንድትረዳው            
ሳዝን ስተክዝ የምታጽናና            
እናት አለችኝ እርህርህይተ ልቦና
እናቴ እመቤቴ ብዬ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጪኛለሽ

ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

ከ መናኙ አንደበት

23 Oct, 07:36


🔔 ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዘበነ ለማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር እዮብ ይመኑ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

ከ መናኙ አንደበት

23 Oct, 03:45


"አቤቱ ጥበብንና ኃይልን ልብንና እና ልቡናን ዕውቀትንም ስጠን። እንግዲህ ከሚፈታተነን ከሰይጣን ሥራ ሁሉ እስከ ዘላለሙ እንርቅ እንሸሽም ዘንድ። አቤቱ ሁልጊዜ ፈቃድህን ውድህንም እንሠራ ዘንድ ስጠን።"
 
መጽሐፈ ቅዳሴ




እንደምን አደራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰብች💖

ከ መናኙ አንደበት

22 Oct, 07:06


እጅግ ድንቅ ትምህርት!!


ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ


በማስተዋል እናዳምጥ ሰናይ ቀን


💖

ከ መናኙ አንደበት

22 Oct, 04:33


ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው ወደ ዓለም ምንም እንኳን አላመጣንምና አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም ምግብና ልብስ ከኖረን ግን ርሱ ይበቃናል።

ዳሩ፡ግን፡ባለጠጋዎች ሊኾኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጐዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።

ገንዘብን መውደድ የክፋት ዅሉ ሥር ነውና አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት፡ተሳስተው
በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።
1ኛ ጢሞ 6፥6-10




💖

ከ መናኙ አንደበት

22 Oct, 03:11


ቅዱስ ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ
ዛሬም ቆመሀል በኪዳንህ ላሉ
አዝ።።።።።
ክንፍህን ዘርጋ ሚካኤል ቅደም ከፊቴ
ምራኝ መንገዱን እንዳይመሽ ልድረስ ከአባቴ
እንዴት ይገፋል ጎዳናው ያላንተ እርዳታ
ጥሜን ቁረጠው በትርህ ጭንጫውን ምታ
አዝ።።።።
ተጠመጠመ ጠላቴ በእሳት ሰንሰለት
የጌታ መልአክ ሚካኤል በሰይፍ ወድቆበት
የለም በቦታው ስመለስ አጥቼዋለሁ
የሚረዳኝን ተሹሞ አይቼዋለሁ
አዝ።።።።
ከመቃብሩ ድንጋዩን አንከባለሃል
ስለረዳኸው ዳንኤል እጅግ ወዶሃል
ይነዋወጻል ባሕሩም አንተ ስትመጣ
እግዚአብሔር ይንገስ ዲያብሎስ መድረሻ ይጣ
አዝ።።።።።።
አለኝ ትዝታ በቤትህ ከልጅነቴ
ስትሳሳልኝ እያየሁ ፀንቷል ጉልበቴ
ልዘምር እንጂ ላመስግን ታላቁን ጌታ
አንተን የሰጠኝ ጠባቂ በቀን በማታ

ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

ከ መናኙ አንደበት

21 Oct, 15:00


መንፈሳዊነት ምንድን ነው ?


፩. መንፈሳዊነት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ኅብረትና አንድነት ነው፡፡

፪. መንፈሳዊነት ስሜትን፣አእምሮንና መንፈስን ሲገዛ ነው፡፡

፫. መንፈሳዊነት ጥረት፣ተጋድሎ፣ ውጣ ውረድ ነው

፬. መንፈሳዊነት ጊዜና ቦታ የማይወስነው ነው፡፡

፭. መንፈሳዊነት የኑሮ ሁኔታ የማይወስነው ነው፡፡

በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
በእዉነት መምህራችን እግዚአብሔር በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን!!❤️

ከ መናኙ አንደበት

21 Oct, 10:03


🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[     ❝    ፈጽሞ አይከፈልም !   ❞    ]

🕊

❝ እርሱ [ መድኃኒታችን ] ከድንግል እንደ ተወለደ ፤ ሕገ ኦሪትንም እንደ ፈጸመ ሐዋርያው ተናገረ። [ገላ.፬፥፬-፮]

ትስብእትና መለኮት በተዋሐዱ ጊዜ ሳይሳሳቡ ጸንተው ይኖራሉ ፤ እርሱ ቃል ፍጹም ሰው ሆኖአልና ፤ እርሱ የኦሪትን ሥራ ሠራ ፥ በሐሰት ፤ መስሎ በመታየት አይደለም ፤ ከኃጢአት በቀር ሰው እንደ መሆኑ የሰውነትን ሥራ ለመሥራት ፍጹም ነው እንጂ ፤ በማይረባ ድንቁርና ተይዞ ማንም ማን ከናንተ ወገን እንዲህ ባለ ነገር አይካድ።

ቅድመ ዓለም ከአብ የተወለደው እርሱ ፤ ዳግመኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው እርሱ ነው ፤ እርሱ ፍጹም አምላክ ፣ ፍጹም ሰው ከሆነ ፤ በሰማያዊ ልደቱ በምድራዊ ልደቱ ፍጹም ነውና ፥ ፍጹም በፍጹም ፤ ለምን አደረ ይባላል ? ለራሱ ገንዘብ ያደረገውን የተዋሕዶውን ሥራ ፈጸመ እንጂ ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ አይከፈልም።  ❞

[      ቅዱስ ኤጲፋንዮስ      ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

ከ መናኙ አንደበት

21 Oct, 08:47


አትጨነቁ


መ/ር እዮብ ይመኑ

ከ መናኙ አንደበት

20 Oct, 12:23


እዚህ ቻናል ላይ አድሚን ሆኖ መስራት የሚፈልግ ለእናንተም ጥቅም ነው በሰበቡ ብዙ ትማራላችሁ

@Ab_man2121
እዚህ ላይ አናግሩኝ

ከ መናኙ አንደበት

15 Oct, 20:51


ክርስቶስን አንዘንጋ ፤🙏 የሚገባውን ስጦታ ከሱ አናስቀርበት።

ከ መናኙ አንደበት

15 Oct, 08:41


ታዛዥነትና ተዘክሮተ እግዚአብሔር+

አባ ዮሐንስ ኃፂር ከሚታወቅባቸው መልካም ምግባራት መካከል የሚጠቀሱለት ናቸው ታዛዥነትና ተዘክሮተ እግዚአብሔር፡፡ አንደ ቀን አባ ባሞይ ዮሐንስ ኃፂርን የደረቀ እንጨት ተክሎ ለምልማ እስክታፈራ ድረስ ውኃ እንዲያጠጣት አዘዘው፡፡ ያለማንገራገር በትኅትና ሆኖ አሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል ከሚርቅ ቦታ በቀን ሁለት ጊዜ ውኃ እያመላለሰ ያጠጣ ጀመር፡፡ በሦስተኛው ዓመት ያቺ በትር ለምልማና አብባ ያማረ ፍሬ አፈራች፡፡ አባ ባሞይ በዮሐንስ ታዛዥነት እጅግ ተደሰተ፡፡ ፍሬውን ለቅሞ ለገዳሙ መነኮሳት እንካችሁ ይህ የታዛዥነት ፍሬ ነው እያለ ሰጣቸው፡፡ መነኮሳቱም ይህን ተአምር ባዩ ጊዜ አደነቁ፡፡ ለቅን እና ታዛዥ ሰው ይህን ጸጋ የሰጠ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፡፡

"መልካም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያገኛል፡፡'' ምሳሌ 12፤2

15,969

subscribers

89

photos

7

videos