«ነቢ ረሱለሏህን ወዶ የቀረበ ኹሉ፣የላቀ ክበር’ና ራሕመትን መቋደሱ ነው።»ከሰው ዘር የሶሓቦቹ ማሳያ ነው። ጨለምተኛ ነበር ብርሃኃን ሞሉት። ለክብረቱ ምሳሌ ሰይዲና ቢላልን ያነሷል።ነቢ በመውደዱ ከውርደት ወጣ።በክብር ዙፋን ተደላደለ። ነቢን አገኘ’ና ተውሒድን፣ ኑርን፣ ጀነትን ተጎናፀፈ። ገድሉን ታሪክ ለፊት ገፁ፣አድምቆ ሚዘክረው ሰው ሆነ።
ሀሳቡ ከሰው ልጅ ውጪ ሲታይ ልብ ገዥ ነው።የቴምር ጉቶ ተላምዷቸው በልሳን ከማውራት ጀነት እስከመሰጠት።ለፍቅር ታሪክ ሕያው ማሳያ ሆኖ መወሳት አገኘ።
"ያዕፈር"? የሚባለው መጓጓዣ አሕያቸው የአብሮነት ታሪክ ስለነበረው በዘገባዎች፣ የእስልምና ጉዞ ታሪክ ተካፋይ ሆኖ በክብር እየተወሳ ይኖራል።አፍቃሪዋ ግመላቸው ቀስዋ ስለ ነቢ ረሱለሏህ ፍቅር ተምሳሌታዊ ምስክር በመሆን፣ከልዩ ክብርና ስስት ጋር ስሟ ይወሳል።ከክፍለ ዘመናት በኋላ ሳይቋረጥ እንደ ሁሉም አፍቃሪ ፍቅሯ በክብር ይተረካል።
የተገለገሉበትት ቁስ፣የተጓዙበት መንገድ፣ ያረፉበት ዋሻ፣ የለበሱት፣የኖሩበት ሌላም ሌላው ግዑዝ እቃ እንኳን…በዑመቱ ልብ ውስጥ ቅዱስ ቅርሶች ሆነው ለመከበር ያበቃቸው፣ በነቢ ረሱለሏህ ዙርያ መገኘታቸው፣ከነቢ መቅረባቸው፣በሳቸው መነካታቸው ነው። ምናልናት የ አንድ ጊዜ የመዳፋቸው ዳበሳን በመታደላቸው!
አሏህም ይኸው እድያ በሁሉም ዘመን የማይቋረጥ እንዲሆን፣ወደ’ሳቸው ፍቅር መጠጊያ ትልቁን የቅርበት ገመድ የሆነውን ሰላዋትን ለዑመታቸው ከመስጠቱ። በረካው ማ’ድ የተደረገ የፍቅር፣የራሕመት ግብዣ ጥሪ ነው!
አላሁመሰሊ ወሰሊም ወባሪክ ኣላ ሰይዲና ሙሐመድ!💜