አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ @abuyusra3 Channel on Telegram

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

@abuyusra3


የአቡ ዩስራ ንጽጽራዊ ሀይማኖት ላይ ያተኮሩ የፁሁፍና የድምጽ ስራዎች ይቀርቡበታል።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ (Amharic)

አቡ ዩስራ የንጽጽራዊ ሀይማኖት ሀላፊዎችን እና የፁሁፍና የድምጽ ስራዎችን እንዴት አትምህርተው ያቢሱ የሆነ ነው። እኛ እናምልናለን ያስተዳደርነው የሚፈልጉትን ሀይማኖት እና ድምጽ የስራዎችን ስራዎችን ይቀርበናል። ከዚህ የአቡ ዩስራ በተጨማሪም አገራት በተመሰረቱና በገና የመረጡት ሁላችንን ለመቆጣጠር በሙሉ የመረጠው አገልግሎት እንድናድርግ ይህን ቦታ እንረዳለን።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

15 Feb, 05:05


© Copy

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

14 Feb, 19:12


ጥያቄ: —
ቁርኣን በሱራ 2:7 ላይ  ያላመኑትን ሰዎች አይን ሸፍኖ፣ጆሮና ልብ ላይ  አትሞ ለምንድ ነው በእኔ አላመናችሁም ብሎ የሚቀጣቸው? ይሄ  ከኣምላክ የማይጥበቅ የፍትህ መዛባት ነው።


خَتَمَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ وَعَلَىٰ سَمۡعِهِمۡۖ وَعَلَىٰٓ أَبۡصَٰرِهِمۡ غِشَٰوَةࣱۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمࣱ

አላህ በልቦቻቸው ላይ በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አልለ፤ ለነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡

መልስ:—

1) በመጀመሪያ የአንቀፁ  ሙሉ ሃሳብ ለማግኘት ከቁጥር 6 ጀምሮ መነበብ አለበት። ሰለዚህ " እነዚያ የካዱት ሰዎች ብታስፈራራቸውም ባታስፈራራቸውም በነርሱ ላይ እኩል ነው አያምኑም " ካለ በዃላ ነው ።እንደነዚህ አይነት ሰዎች በ"ክህደታቸው " ምክንያት ነው ይህ ቅጣት የሚጣልባቸው። [ቁርኣን 4:155]


2) አላህ ሱወ ምንግዜም ቅን የሆኑ ሰዎችን ያውቃል ይመራቸዋልም። ለሰው እንጂ ለአምላክ ይህ ቀላል ነገር ነው። ከኛ ውስጥ ማን መመራትን (ቅናቻን) እንደሚፈልግ። ማን መጥመምን እንደሚፈልግ አስቀድሞ ያውቃል። ከዚህም የተነሳ  አይደለም ምድር ላይ አቆይቶን ፣ ዛሬ ፈጥሮን ዛሬውኑ ፍርድ ቢሰጥ ፍርዱ ፍትሃዊ ነው።

3) አምላክ የሰውን ልጅ ሁለት ምርጫ ሰጥቶ የፈለገውን እንዲመርጥ ከነጥቅሙና ጉዳቱ ግልፅ አድርጓል [ ቁርኣን 76:3 እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን መራነው፤ (ገለጽንለት) ] በዚህ ሒደት ውስጥ የነብያት ተልእኮ መልእክቱን ማደረስ ብቻ ነው። መመራት በአላህ ሱወ እጅ ያለ ጉዳይ ነው።እርሱ ቅኖቹን ዐዋቂ ነውና። [ቁርኣን 28:56 አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው]

4.  ሰለዚህ ከላይ የተገለፁ ሰዎች [ ከሃዲዎች] ከክህደታቸው ከተመለሱ ወደ ቅኑ  መንገድ ይመራሉ ምክንያቱም ። አላህ ሱወ ለባሮቹ ክህደትን አይሻምና።[ቁርኣን 49:7]

እንዲህማ ባይሆን ትላንት የሌላ እምነት ተከታይ  የነበሩ ሰዎች በዚህ አንቀፅ እያሳበቡ ባልሰለሙ ነበር። ለእውነት ያደረጉት ጥረት ፍሬ እያፈራ በየግዜው ሰዎች ወደ እስልምና ይገባሉ።

ቁርኣን 8:38 ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ሥራ) ምሕረት ይደረግላቸዋል።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

12 Feb, 18:24


ከትላንቱ በቀጠለው ስልጠናችን ከስቅለት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች የተመለከተው ስልጠና ተሰጥቷል። በኡስታዝ አቡ ዩስራ አማካኝነት የተሰጠው ይህ ስልጠና "The Non-Crucifixion Verse Q 4:157" በሚል ርዕስ የተሰጠ ሲሆን ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

https://t.me/Hidayaic8212

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

11 Feb, 08:10


If you tell the truth, you don't have to remember anything.

©Mark Twain

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

09 Feb, 18:57


ክርስቲያኖችና ሦስት ቁጥር ያላቸው ጠብ

"ልክ ስላሴ ለመረዳት እንደሚቸግረው ሁሉ ኢየሱስ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ሆድ ውስጥ ቆይቷል የሚለው ሌላኛው ስላሴ ነው"

ሁለቱም ለመረዳት የሚቸግሩ ናቸው።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

04 Feb, 09:35


በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አማካኝነት የተዘጋጀውን ይህንን ስልጠና መውሰድ ለምትሹ ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ መመዝገብ ትችላላችሁ። እያንዳንዱ ስልጠና ለአንድ ቀን የሚሰጥ ሲሆን ከተመዘገባችሁ በኃላ በሚደወልላችሁ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ስልክ ቁጥር አማካኝነት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በቴሌግራም ወይንም በዋትስአፕ ቀድመው መላክ ይኖርብዎታል።

- ለስልጠናው የምንፈልገው 15 ሰልጣኝ ብቻ ስለሆነ ስልጠናውን የመውሰድ እርግጠኛ እቅድ ከሌለዎት አይመዝገቡ።

https://bit.ly/4aK4Pq5

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

30 Jan, 15:08


ታቦቴ ተፌዘበት ባሉበት አፋቸው ቁርኣንን እንኳን አቃጠለ ብለው ያዜማሉ።

የጥምቀት በዓል ተከትሎ በሃይማኖታዊ ስርዓቱ ላይ ያፌዙ ልጆች ነበሩ። አሁንም ድርስ እያፌዙ ያሉ አሉ።ልጆቹ አሁን እልህ ይዟቸው ፊታቸውን እየሸፈኑ ማሾፉን ቀጥለዋል።ልጆቹ ቢያገኙዋቸው ምን ሊያደርጉዋቸው እንደሚችሉ ሰሞኑን በተለያየ ቦታዎች ላይ እየተሰጡ ያሉ ኮመንቶች መመልከት በቂ ነው ። አለፍ ሲልም ቤተክርስትያኗም በግልፅ ይህን ድርጊት ብላ ባትገልፀውም ፣ከዚህ ድርጊት በዃላ በሃይማኖታዊ ስርኣቶቼ ላይ የሚቀልድ ከአሁን በዃላ አልታገሰም ብላ ገልፃለች።

አንድ ግዜ ክርስቲያን ነኝ ሌላ ግዜ ሃይማኖት አልባ ነኝ ያለ ኢራቃዊ ሲውዲን ውስጥ በ 2023 በሙስሊሞች በአል ቀን ( ኢደል አደሐ) ቁርኣንን በአደባባይ በፖሊስ ተጠብቆ አቃጥሏል። ይህ ግለሰብ በዚህም ክስ ዛሬ ሀሙስ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ነበረው። የመጨረሻው ፍርድ ቀድሞ ትላንትና ጀግኖች ወደ ጀሀነም ሸኝተውታል።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

26 Jan, 18:00


ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ከጉረባዕ ኢስላማዊ ድርጅት ጋር በመተባበር ላለፉት 6 ሳምንታት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል። በስልጠናው መሠረታዊ የንጽጽር አስተምህሮ የተዳሰሰ ሲሆን በቀጣይ በትብብር ስለሚሰሩ ስራዎችም ውይይትና ስምምነት ላይ ተደርሷል። ማዕከሉ ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰጣቸው ስልጠናዎችም በአላህ ፍቃድ ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

19 Jan, 14:29


ወንድማችን ኡስታዝ ወሒድ ዑመር አዲሱን መጽሀፉን (አልገደሉትም፣ አልሰቀሉትም) ሶስት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ እህቶች ወጭውን እንዲሸፍኑ በማስተባበር 100 መጽሀፍትን ለሒዳያ ላይብረሪ አስረክቦናል። በተጨማሪም በራሱ በኩል የእሱን መጽሀፍ የኦሮምኛ ትርጉም 100 ፍሬ የለገሰን ሲሆን ኡስታዝ ጀማል ደግሞ የአህመዲን ጀበልን "ክርስቶስ ማነው?" መጽሀፍ የኦሮምኛ ትርጉም ስራውን 100 ፍሬ አበርክቶልናል። እያንዳንዳቸው 100 መጽሀፍ በድምሩ 300 መጽሀፍትን ለግሰውናል። አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው፣ ከዚህ የበለጠ የሚተጉበትን ብርታትም ይወፍቃቸው።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

17 Jan, 07:57


እስልምና ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎችንና በሀይማኖት ንጽጽር ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችን ጥልቅ በሆነ መልኩ ስራዎችን ለመስራት እንዲያግዝ በማሰብ ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በስሩ የጥናትና ምርምር ዘርፍ አቋቁሟል።

በዚህ ዘርፍ ውስጥ የንጽጽር ዱዓቶችን ጨምሮ ተተኪ ወንድምና እህቶች ሰፊ ጊዜዎችን በመውሰድ ስራዎችን እንዲያጠኑ፣ በየቋንቋቸው የጥናት ውጤታቸውን እንዲያዘጋጁ በማመቻቸት ላይ ይገኛል።

ለስራውም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛ የተጻፉ መጽሀፍትን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ሲሆን ለዚህ የሚያግዙ እናንተ ጋር የተቀመጡና ለተቋማችን ይጠቅማል የምትሏቸው መጽሀፍት ካሉ በሚከተለው ስልክ ቁጥር ለአስተባባሪዎች በመደወል መስጠት የምትችሉ ሲሆን ቢሮ መጥቶ መስጠት የሚችሉም ይበረታታሉ።

አድራሻ፦ ቤተል
ስልክ፦ 0910858830

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

14 Jan, 08:30


ከዚህ በፊት አምላክ ተገርዟልን? ብለን ስንጠይቅ የሚሰድቡን ነበሩ ።አሁን ግን የግዝረቱ ቀንም ይከበራል።

"ጥር 6 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪት ሕግ የሆነውን ግዝረት የፈጸመበት ዕለት ጥር ስድስት ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋ ግዝረትን ተቀበለ፣ ለአባቶች የተሰጠውን ቃልኪዳን ይፈጽም ዘንድ›› ብሎ መስክሯል፡፡ (ሮሜ 15፥8)
መጽሐፈ ስንክሳር "

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

12 Jan, 20:51


"ክርስቲያኖች ለምን ብዙ ሚስት ታገባላቹ በሚለው ጥያቄ Busy ከመሆናቸው የተነሳ ብዙ አምላክ እያመለኩ መሆናቸውን ረስተዋል። "


https://t.me/Abuyusra3

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

12 Jan, 12:11


ክርስቲያን የሆነ ሀኪም ብለህ የስራ ማስታወቂያ ከምታወጣ፣ የሆስፒታሉን ራዕይ፣ተልእኮ እና እሴቶች የሚቀበል ብለህ ታለዝበዋለህ።

ትርጉሙ ግን ያው ነው።

ምስሎቹን ይመልከቱ

https://t.me/Abuyusra3

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

07 Jan, 14:01


"Don't waste your energy on people that are committed to misunderstanding you! "

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

22 Dec, 19:37


የአዳም ሀጢኣት ወይንስ የሔዋን ሐጢኣት ?

እንደ ኦርቶዶክሱ መፅሀፍ ከሆነ አዳምን ያሳሰተችው ሴቷ ነች ፣#ሞትንም ያመጣችበት ሴቷ ስትሆን። የሰው ልጅ አዳምንም ጨምሮ የምንሞተው በሴቷ ምክንያት ነው። ስለዚህ ሞት የመጣው በአዳም ሳይሆን በሔዋን ነው።


መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ 3፥6

"የበለስ ፍሬን ከበላች በኋላ መጥታ የእግዚአብሔር  መጀመሪያ ፍጥረቱ አዳምን አሳተችው የፈጣሪዋን ትእዛዝ ስለ ተደፋፈረች በሱም በልጆቿም ሞትን አመጣች"


ከዚህ በላይ ሴትን ከመጀመሪያ ጀምሮ ጥፋተኛ የሚያደረግ ነገር ከየት ይመጣል? 

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

22 Dec, 09:42


በቁርኣን ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከነገ ጀምሮ በአላህ ﷻ ፍቃድ በተከታታይ መመለስ እንጀምራለን። በተለይም በጥንታዊ እደ ክታባት/Manuscripts/ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች የትኩረት አጀንዳዎች ናቸው። ቲክቶክ የምትጠቀሙ ወንድምና እህቶች ተከታተሉት።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

21 Dec, 16:43


🇩🇪Germany
𝐃𝐮𝐫𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐨𝐟 𝐚𝐭𝐭𝐚𝐜𝐤: Few minutes
𝐓𝐞𝐫𝐫𝐨𝐫𝐢𝐬𝐭: Arab atheist
𝐕𝐢𝐜𝐭𝐢𝐦𝐬: 5 (five)
𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭𝐢𝐨𝐧:😡😭

🇵🇸Palestine
𝐃𝐮𝐫𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐨𝐟 𝐚𝐭𝐭𝐚𝐜𝐤: +1 yr (ongoing)
𝐓𝐞𝐫𝐫𝐨𝐫𝐢𝐬𝐭: Zionists
𝐕𝐢𝐜𝐭𝐢𝐦𝐬:+55,000
𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭𝐢𝐨𝐧: Meh 🫤

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

21 Dec, 16:07


የበኒ ቁረይዛን ክስተት አስመልክቶ ተዛብቶ ለቀረበው ትችት የተሰጠ መልስ | የሕያ ኢብኑ ኑህ

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

17 Dec, 13:26


ነገ እሮብ ማታ ከምሽቱ 3:00 ላይ እንገናኝ።

https://t.me/path_of_the_prophets
ቴሌ ግራም

https://www.tiktok.com/@abdulkerim1100  ቲክቶክ

ማንም እንዳይቀር !

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

07 Dec, 16:52


ዛሬ ማታ በወንድማችን አብዱልከሪም ቤት የነበረን የላይቭ ፕሮግራም በመብራት ችግር ምክንያት ለሌላ ቀን ተራዝሟል። ኢንሻአላህ ቀኑን እናሳውቃለን።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

03 Dec, 10:13


ሙሉ ቁርኣን በአንድ ገፅ

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

01 Dec, 11:31


ሶሂህ —አልቡኻሪን

መቅራት ለምትፈልጉ


@Zhara_mustefa

ወይንም

@Zehar678

ያናግሩ።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

01 Dec, 07:24


"አምላክ" አይደለሁም ያለበት ቦታ!

አንዱ ነብይ ነኝ ብሎ ተነሳ፣ ህዝቡ ግን አላመነበትም። ስለዚህ ሰበሰባቸውና ዛሬ እኔ ነብይ መሆኔ በአደባባይ አረጋግጥላችዃለው አላቸው።

በል ማስረጃህን አቅርብ ሲሉት።

እሱ: እኔ በአሁን ሰአት በአዕምሮአቹ  የምታስቡትን አውቃለው አላቸው።

ህዝቡ ማጉረምረም ጀመር ፣ በል ንገረንና እንመንህ አሉት።

እሱ፦ አሁን በዚህ  ሰአት እያሰባቹ ያላችሁት ይህ ሰው ቀጣፊ  ነው እያላቹ ነው አላቸው ይባላል።

እኛ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ኢየሱስ  "እኔ አምላክ ነኝ" የሚል ስለራሱ የተናገረበት ንግግር መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የለም ብለን ስንጠይቅ መልሱ እንደሌለ የሚያውቁ ሰዎች የሚሰጡን ምላሽ፦

① አምላክነቱን ሊገልፅ አልመጣም ይላሉ

ሰው የሆነው ለእኛ ብሎ እስከሆነ ድረስ ፣ አምላክነቱን ለመግለፅ ምንድ ነው የሚያስፈራው?  ምን እንዳይሆን ነው ሚስጢሩን የደበቀበት ምክንያት?  ሞት ከሆነ እንደ እናንተ አስተምህሮ አልቀረለትም። ከግዜው በፊት እንዳይገሉት ፈርቶ ነው እንዳይባል "አምላክ ነው"  ያለ ግዜው ቢገሉትም መነሳት ይችላል። ይህ ምላሽ አሳማኝ አይደለም።

②  ነብያቶች ሲመጡ ነብይነታቸውን እንደሚገልፁ ሁሉ አምላክነቱን መግለፁ እና ማብራራቱ የሚጠበቅና ተገቢ ነው። ነብያቶቹን ግልፅ አድርጎ ራሱ ሲመጣ ግን "ተደብቆ " ለምን መጣ?


③ሌላኛው አምላክነቱን በግልፅ ለምን አልተናገረም? ተብለው ሲጠየቁ። "አምላክ አይደለሁም" ያለበትን ቦታ አምጡ  አይደለሁም ካላለ ነው ማለት ነው የሚል አሲቂኝ  መከራከሪያ  ያመጣሉ።

እንዲያማ ከሆነ "አብርሀምም አምላክ አይደለሁም" ብሎ ቃል በቃል ስላልተናገረ አምላክ ነው ማለት ነው? ይሄ እጅና እግር የሌለው ሙግት ነው።

እናም እባካችሁ እንደ ሀሰተኛው "ነብይ ነኝ" ባይ የራሳችሁን መልስ ሳይሆን መሠረታዊ ሙግቱን ተከትላችሁ መልስ ስጡ!

https://t.me/Abuyusra3

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

27 Nov, 18:20


ኢየሱስ "አምላክ ነው!" እና ሰሞነኛ ወሬው!

ስራ ሲቀዘቅዝበት ማስታወቂያ እንደሚያበዛ ነጋዴ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ብሎ ለሙስሊሞች ለማስረዳት ክርስቲያኖች ሰበብ በተገኘ ቁጥር ሁሉ ይደክማሉ።  ከዛሬ 20 አመት በፊት የተደረገ ጥናትን በማቅረብ ሰሞኑን በሙስሊሞች ላይ ሊሳለቁ ከርመዋል።

ጉዳዩን እንደ አዲስ በማራገብ "ኢየሱስ አምላክ መሆኑን የሚያሳይ የተቀረፀ ፅሁፍ ነብያችሁ ሙሐመድ ከመወለዱ በፊት  እስራኤል ውስጥ በቁፋሮ ተገኝቷል" በማለት ስሁት ሀተታ እየሰሩ  ይገኛሉ። የስነ ቁፋሮ ባለሙያዎቹ እስራኤል ውስጥ በሚገኝ ሜጊዶ ወህኒ ቤት ላይ ባደረጉት ጥናት እስር ቤቱ ወለል ላይ በግሪክ ቋንቋ የተቀረፀ ፅሁፍ አግኝተዋል ¹

በዚህ ጥናት ወለል ላይ ሶስት ፁሁፎችን ያገኙ ሲሆን እነሱም፦

1. The Gaianus Inscription - ወለሉ እንዲሰራ ክፍያ የፈፀመውን ወታደር ስም እና የሰራው ባለሞያ ስም

2. The Akeptous Inscription - አምላክ ወዳድ የሆነችው አኬፕቶስ አምላክ ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ይህን ጠረፔዛ አቅርቧል - የሚል እና

3. The Women Inscription - ፕሪሚላ እና ሳይሪያካ እና ዶሮቲያ፣ እና በተጨማሪ ክረስቴን አስታውሱ - የሚል ፁሁፎች ተገኝተዋል።

ጥናቱ  ያደረጉ ሰዎች በመጽሀፋቸው ሲያጠቃልሉ በገፅ 54 እንዲህ ይላሉ፦

“በከፋር ‘ኦትናይ’ የሚገኘው የክርስቲያን የጸሎት አዳራሽ መገኘቱ ከቆስጠንጢኖስ ዘመን በፊት በእስራኤል ምድር ክርስቲያን መገኘቱንና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዋናነት በሥነ ጽሑፍ ምንጮች ሲዳሰስ በነበረበት ወቅት፣ በእስራኤል ምድር ለነበረው ክርስቲያን መገኘት ትልቅ ጠቀሜታ ያለው አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃ ነው። በተጨማሪም የሕንፃው ጥናት በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከአይሁድ እምነት ይልቅ አረማዊ የሆነ የክርስቲያን ማኅበረሰብ መኖሩን ያረጋግጣል” 

ልብ በሉ! ይሄ ኢየሱስ ካረገ ከ200 አመታት በሗላ ነው!!! በዚያን ወቅት ታዲያ “ኢየሱስ አምላክ ነው” የሚል ፅሁፍ መገኘቱ ምን ያስገርማል  ታዲያ? ይህ ጥናት ምን አዲስ ነገር ኖሮት ነው? ከ 1800 አመት በፊት በክርስትያኑ ዘንድ የሚታወቁ የቤተክርስቲያን አባቶች/Church Fathers/ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ብለው መጻፋቸው የሚታወቅ ነው። ታዲያ ምኑ ይሄ ይገርማል?

ምናልባት ከኒቂያ ጉባኤ (325) ጋር ተያይዞ ከሆነ ወቀሳው በኒቂያ ጉባኤ ወልድ “አምላክነቱ” በድምፅ ብልጫ ከመፅደቁ በፊት በአርዮስ እና ተከታዮቹ የነበረ ሃሳብ መኖሩን ከመግለፅ ውጪ የተለየ ትርጉም አይሰጥም።

አርዮስ ብቸኛ አምላክ አብ ነው ወልድ ግን የተወለደ፤ መጀመሪያ ያልነበረ ነው ሲል ያምናል። አባት ልጁን እንደማይቀድመው ሁሉ ወልድም አብን አይቀድምም የሚለው ሙግት የአርዮስ ሙግት ነበር። ስለዚህ በዚህ ጉባዔ አሪዮስን ተሳስተሃል፤ ከመጀመሪያም ጀምሮ ነበረ ፤ ከአብም ጋር እኩል አምላክ እንጂ ሁለተኛ አምላክ  አይደለም ብለው ነው በድምፅ ብልጫ ያፀደቁት።

እናም "ኢየሱስ አምላክ ነው" የሚል ፅሁፍ በተገኘ ቁጥር ሙስሊሞች ላይ መሳላቁ ትርጉም አልባ የሆነና እናንተንም ትዝብት ውስጥ የሚከታችሁ ነው።

1- A CHRISTIAN PRAYER HALL OF THE THIRD CENTURY CE AT KEFAR ‘OTHNAY (LEGIO) Excavations at the Megiddo Prison 2005)

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

23 Nov, 20:21


 
በማቴዎስ 4:1—10 በተቀመጠው ዘገባ መሰረት በኢየሱስና በሴይጣን መካከል የተደረገውን የቃላት ምልልስ መፈፀሙን ምን አይነት ምስክር አለ? ማቴዎስ በቦታው አልነበረም? የነበሩት ሴይጣንና ኢየሱስ ብቻ ናቸው። ኢየሱስን እንዳንጠይቀው አርጓል።ምናልባት ምድርን እየገዛ ያለው ሴይጣን ይረዳን ይሆን?


የማቴዎስ ወንጌል 4
1  ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
2  አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።
3  ፈታኝም ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።
4  እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።
5  ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፦
6  መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።
7  ኢየሱስም፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው።
8  ደግሞ ዲያብሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፦
9  ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።
10  ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

22 Nov, 09:34


ክፍል ሁለት

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

22 Nov, 09:33


ከአራት አመት በፊት 26 አይነት ቁርዓን ሙስሊሞች አላችሁ በሚል ለቀረበ ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ ክፍል አንድ

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

13 Nov, 06:43


መሳሳት የማይደክማቸው ሰዎች!


ቁርዓን 3:44

ይኸ ወደ አንተ የምናወርደው የኾነ ከሩቅ ወሬዎች ነው፡፡ መርየምንም ማን እንደሚያሳድግ ብርኦቻቸውን (ለዕጣ) በጣሉ ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም፡፡ በሚከራከሩም ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም፡፡


ذَٰلِكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلْغَيْبِ نُوحِيهِ إِلَيْكَۚ وَمَا كُنتَ لَدَيْهِمْ إِذْ يُلْقُونَ أَقْلَٰمَهُمْ أَيُّهُمْ يَكْفُلُ مَرْيَمَ وَمَا كُنتَ لَدَيْهِمْ إِذْ يَخْتَصِمُونَ

የኢየሱስ እናት መርየም (ዐ.ሰ) በቁርኣን ውስጥ በስሟ የተሰየመ ምእራፍ መኖሩን አስመልክቶ "ይሄ ምን ያስገርማል ታዲያ? ቁርኣን እኮ ብዙ አስገራሚ እና አስቂኝ የምእራፍ ስሞች የያዘ መፅሀፍ ነው" በማለት አንዳንድ ክርስቲያኖች ሲሳለቁ ከርመዋል።

ከዚህ በፊት የኢየሱስ (ዐ.ሰ) ስም   ከነብዩ ሙሐመድ (ዐ.ሰ.ወ) ስም ይበልጥ በቁርኣናችሁ ተጠቅሷል፣ ነብያችሁ ግን በስም ከ 4 ግዜ በላይ አልተጠቀሰም እያሉ ሲያደርቁን የነበሩ ሰዎች ዛሬ ተገልብጠው የማርያምን ስም መጠቀስ ለማንቋሸሽ የሄዱበት ርቀት ይገርማል።

የኢየሱስ እናት ስሟ መጠቀሱ እንዲሁ ትርጉም አልባ ገለጻም አልነበረም። ከዚህ ጋ ተያይዞ ለየት የሚያደርገውን ሁለት ምክንያቶችን ልጥቀስ።

① በአረቦች  እና በእስራኤላያውያን  መካከል ያለው አለመግባባት ዘመናትን የዘለቀ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ነብዩ (አሰወ) በነበሩበት ዘመን ጥላቻውም በግልፅ ይንፀባረቅ ነበር። ታዲያ በዚሁ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ነብዩ (ዐ.ሰ.ወ) በዚያ ዘመን ከምዕተ አመታት በፊት የነበረችውንና አይሁዳዊቷን ማርያምን እንዴት ሊያሞግሷት ቻሉ?


② ነብዩ (ዐ.ሰ.ወ) በአጠገባቸው ሚስቶቻቸው ወይንም ሴት ልጆቻቸው እያሉ እንዴት ቢያንስ አንድ ምእራፍ እንኳን በነሱ ስም አልሰየሙም? ከዚያም በተጨማሪ በቁርኣኑ ውስጥ ስማቸውን እንኳን ገልጸው ለማሞገስ እንዴት አልሞከሩም?

ዋናው ነጥብ በምእራፍ ስም መሰየሙ አለመሰየሙ አይደለም፣ መሠረታዊ መልዕክቱ ቁርኣን የሰጣት ክብር ነው። ይህ ደግሞ ከመለኮታዊ መልዕክት የወጣና የግል ዝንባሌ የተጨመረበት ቢሆን ፈጽሞ ሊደረግ የሚችል አልነበረም።

https://t.me/Abuyusra3

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

23 Oct, 11:58


ዛሬ ኢንሻአላህ ለ2 ሰኣት ገደማ የሚቆይ ፕሮግራም በቲክቶክ ይኖረናል። በአጀንዳው ዙሪያ ምላሽ ወይንም ማብራሪያ መስጠት የምትፈልጉ ክርስቲያኖች በፕሮግራሙ ላይ ትገኙ ዘንድ ተጋብዛችኃል።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

19 Oct, 11:57


በሀድያ ዞን ሆሳዕናን ጨምሮ በርካታ የሚሽነሪ ት/ቤቶች አሉ። በዞኑ ያለው የሙስሊም ት/ቤት ግን አንድ ብቻ ነው። እሱም በሻሾጎወረዳ ቦኖሻ ከተማ የሚገኘው ኑር ት/ቤት ነው። በዚህ ት/ቤት በሚሽነሪ ት/ቤቶች ሊማሩ የነበሩ በርካታ ሙስሊም ልጆች ይማሩበታል።

ይህ ት/ቤት ግን በርካታ ወጭዎች ገጥመውት እየተንገዳገደ ይገኛል። ሁሉኑም ወጭዎች መሸፈን እንኳን ቢከብድ አሁን ላይ አንገብጋቢ ማነቆ የሆነባቸውን የመምህራን ደሞዝ ተባብረን እንድንሸፍንላቸው ለመማጸን ወደ እናንተ መጣሁ። የአንድ አመት የመምህራን ደሞዝ 600ሺ ብር ነው። ይህ በእርግጥ በአንድ ሰው ሊሸፈን ይገባው የነበረ ቢሆንም በአቅማችን ልክ ሁላችንም አኽለል ኸይር በመሆን እንድንሸፍነው እጠይቃችኃለው።

ከዚህ በታች የተቋሙን አካውንት አስቀምጣለሁ፣ ከ100 ብር ጀምሮ የአቅማችሁን በመነያት የኸይር ስራው ተጋሪ ይሁኑ።

CBE: 1000655472006

ቦኖሻ ከተማ አስተዳደር እ/ጉ የግንባታ ማንቀሳቀሻ አካውንት

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

18 Oct, 07:14


We'll never surrender, we'll win or die you've to fight the next generation and the next ..... and I'll live more than my hanger. Omar mukhtar.

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

15 Oct, 05:24


አልሐምዱሊላህ...!

በሀድያ ዞን ወረዳዎችን ማዕከል ባደረገ መልኩ ቦኖሻ ላይ የነበረው ኮርስ በሰላም ተጠናቋል፣ አልሐምዱሊላህ። ባለፉት 6 ወራት ውስጥ በሀድያ ዞን ብቻ ሶስት ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች መሠረታዊ የንጽጽር ኮርሶችን በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አማካኝነት መስጠት ተችሏል።

ይህኛው ስራ በአካባቢው በዳዕዋ ለመስራት በማሰብ በቅርቡ ከተመሰረተው አል-ሰባት የንጽጽር ማዕከል ጋር በመተባበር የተሰራ ሲሆን ከትምህርቱ በተጨማሪ ለወደፊት የዳዕዋ ስራዎቻቸው የልምድ ልውውጦችም የተካሔዱበት ነበር። እንደ ሁሉም አካባቢዎች ለሰልጣኞች የሚያሰራጩት ፓምፍሌትና በጋራ የሚያጠኗቸው መጽሀፍትም ተበርክቶላቸዋል። በአሏህ ﷻ ፍቃድ መሠል ስልጠናዎችና የዳዕዋ ስራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል እና የዳዕዋው አካል ለመሆን፦

https://bit.ly/4aGr93u

በቴሌግራም በኩል ሊያገኙን ከፈለጉ፦
@Hidayaislamiccenter

1000499318212
Hidaya Islamic Center
አጭር የንግድ ባንክ ቁጥር - 8212

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

02 Oct, 18:41


ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የቀረበ የትምህርት እድል

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በተለያዩ አካባቢዎች ከሚሰጣቸው የንጽጽራዊ ሀይማኖት ስልጠናዎች በተጨማሪ፣ በአዲስ አበባ እና በሸገር ሲቲ ለሚገኙ የተለያዩ መርከዞችና ኢስላማዊ የትምህርት ተቋማትን አወዳድሮ ከፊል የትምህርት እድል ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል። 

የንጽጽር ትምህርት ስልጠናው ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ለአንድ አመት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ማዕከሉ ባዘጋጀው ስርአተ ትምህርት/Curriculum/ መሠረት በዘርፉ ልምድ ባላቸው ኡስታዞች አማካኝነት ይሰጣል።

በዚህ የትምህርት እድል ለመስጠት የታቀደው የመርከዞችና የትምህርት ተቋማት ብዛት 6 ሲሆን በዚህ ዘርፍ ተማሪዎቻቸውን ማብቃት ለሚፈልጉ ተቋማት ባስቀመጥነው መስፈርት መሠረት አወዳድረን እድሉን እንሰጣለን።

በዚህም መሠረት በተቋማችሁ ውስጥ የኃላፊነት ወይንም የውሳኔ ሰጭነት ሚና ያላችሁ ወንድምና እህቶች ብቻ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ፎርም በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፦

https://bit.ly/4dvInRv

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

11 Sep, 15:14


አንዳንዶች ዘመን መለወጫ እንዴት አታከብሩም ? ሃይማኖታዊ እኮ አይደለም እያሉን መልሰው ዛሬ ግን ቀኑን በፆም ነው ያሳለፉት 😁

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

11 Sep, 11:46


በቅርቡ አንድ ክርስቲያን የቲክቶክ "ሰባኪ" በእጮኛው ላይ መማገጡን ተከትሎ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ሰፊ መነጋገሪያ መሆን ችሎ ነበር። ግለሰቡ "አቃቢ እምነት ነኝ" ይል ስለነበርና በጻድቅ መታበይ ሁሉኑም በምላሱ ይጎነትል ስለነበር ጉዳዩ ቢገንበት አይገርምም። እዚህ ጋር ስለልጁ ድካም ማውራት ባልፈልግም በዚያች ወቅት የሰራት "ብልሀት" ግን የቲክቶክ ዘመዶቹን ባህሪ የገለጠ ስለነበርና እንደ ሙስሊምም ስለሚጠቅመን ትንሽ ነገር ልበላችሁ፦

ይህ ተግባሩ በእጮኛው አማካኝነት በተወራበት ቀን አካባቢ ከአንድ ሙስሊም ጋር ክርክር አለኝ ብሎ አወጀ። በወቅቱ ከጀርባው በፋይናንስ የሚደግፉት (የራሱ ቸርች እንደመሰከረችው) እንዲሁም አብረውም የሚሰሩት ሁሉ የተደናገጡበት ጊዜ ስለነበር "አታስቡ፣ እንደምታዩት ወንጌልን እየሰራሁ ነው" የሚል ማደናገሪያ ለመልቀቅ የተጠቀመባት ስልት ነበረች። ውይይቱን ሲያደርግም በየዋህነት የተወሰኑት ከጎኑ ሆኑለት፤ ግን የፈጸመው ጥፋት በቀላል ሽወዳ የሚስተባበል አልነበረምና እንዳሰበው ሊዳፈንለት ባለመቻሉ እቅዱ ከሸፈ። በስተመጨረሻም ተግባሩን መፈጸሙን አምኖና ይቅርታ ጠይቆ ከማኅበራዊ ሚዲያው ገለል አለ።

ይህ ልጅ ከቲክቶክ በፊት በተለይ በፌስቡክ ከእኔም ከሌሎችም ወንድሞች ጋር በተደጋጋሚ ውይይት ያደረገና ከመነሻው ጀምሮ የምንተዋወቅ ሁነን ሳለ በተደጋጋሚ ቲክቶክ ላይ እንደ እንግዳ "Debate Challenge" እያለ ሲለፍፍና ሰዎች ሲልኩልኝ ሳይ ይገርመኝ ነበር። በሌላ ሰፈር እንደ አንበሳ ለመምሰል ከመሞከር የዘለለ ምን እንደሚፈይድለት አይገባኝም ነበር። ካልኩሌሽኑ የገባኝ ቲክቶክን ከተቀላቀልኩ በኃላ ነበር። ቲክቶክ በጀመርኩበት ሰአት ይህንን ሲል ሰምቸው ስለነበር አንድ ቀን ላይቭ ሲመጣልኝ ጆይን ላደርግ ላይቩ ውስጥ ብገባ አብረውት ካሉ ሰዎች ጋር የሚያወራው እጅግ የሚቀፍ ስድብ ክርፋቱ አራቀኝ። ጭራሽ ኸዲጃና አዒሻ ሲምታቱበት ስመለከት ከእውቀትም ከምግባርም የተጣላ በመሆኑ በማልቆጣጠረው መድረክ ረሱልን "ﷺ" ማሰደብ ተገቢ ባለመሆኑ ተውኩት።

ታዲያ አሁን ላይ እነዚህ ሰዎች ውይይት ከፈለጉ ላይቭ የሚገባው ሰው በሚገባበት ወቅት ጠብቀው አልያም በግል አናግረው ለምን በስርአቱ አይወያዩም?የሚል ጤነኛ ጥያቄ ካለዎት መልሱ የሚከተለው ነው።

ሰዎቹ የሚፈልጉት ውይይት አይደለም፣ የሚፈልጉት ትኩረት ነው። ይህ ትኩረት ደግሞ እንደገጠማቸው ሁኔታ ይለያያል። አንዳንዱ በግሉ ለሰራው ቅሌት አንድ ሙስሊምን ጠርቶ ውይይት በማድረግ ለርሱ ጥፋት ያንን ሰው የመስዋዕት በግ በማድረግ ጥፋቱን ሊያዳፍን ይፈልጋል። አንዳንዱ ደግሞ ለገጠመው የተመልካች እጥረት መፍትሄ ከሆነልኝ በሚል ሊጠቀምብህ ይፈልጋል። በዚህ ሁሉ ሒደት ውስጥ መልካም ውይይት ፈልገው የሚመስለው ሙስሊም ካለ የዋህ ነው። የነሱ አላማ ፈጽሞ ከዚህ የሚዘል አይደለም።

▣ ሙስሊም ወንድምና እህቶች በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ውይይት ስትፈልጉ ማጯጯህ አይጠበቅባችሁም። ስርአት ያለው ውይይት ከሆነ ጆይን አድርጋችሁ፣ ካልሆነ ደግሞ በራሳችሁ ሜዳ ላይቭ ስትገቡ ገስት ተቀብላችሁ መወያየት ትችላላችሁ። እናንተ የምትወያዩት በተግባራችሁ ሰበብ አሏህ ሰዎችን ከመራላችሁ በመጨነቅ እንጅ ጉልበታችሁን በማሳየት ሙገሳን ሽታችሁ አይደለም። በዚህ መሀል የሚሰጧችሁ "ሸሸ፣ ፈራ ወዘተ" የሚሉ ግላዊ ውረፋዎችን ሁሉ ፕሩፍ ለማድረግ አትጋጋጡ፣ እንደዛ አለመሆኑ ለማሳየትም የነፍስያችሁን ንዴት ለማብሸቅ ወጥመዳቸው ውስጥ አትውደቁ።

ሙስሊም የመርኅ ሰው ነው። መርኅ/Principle/ ደግሞ በሰዎች ጉትጎታ ውስጥ የሚናወጥ መሆን የለበትም። የመርኅ ሰው ለቆመበት አላማ ግልጽና የማያወላዳ ነው። የፈለግነውን ትምህርትም ሆነ ውይይት በራሳችን መንገድ ማድረግ አስፈላጊ ነው። የማንም ትኩረት ፈላጊ መጠቀሚያ መሆን ግን ልክ አይደለም።

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

06 Sep, 10:34


ብዙ ግዜ ክረስቲያኖች ይህን አንቀፅ በመጥቀስ ቁርኣን ዒሳ አልተሰቀለም አልሞተም አይልም ብለው ይሞግታሉ።

ቁርዓን 4:157

وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا ٱلْمَسِيحَ عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ ٱللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْۚ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ لَفِى شَكٍّ مِّنْهُۚ مَا لَهُم بِهِۦ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا ٱتِّبَاعَ ٱلظَّنِّۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًۢا


«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡


እነሱ እንደሚሉት ይህ አንቀፅ ዒሳ ተሰቅሏል ወይንም ሞቷል የሚል መልእክት ካለው።  ሶስታችንም( አይሁድ/ክርስቲያን/ሙስሊም)  በመሰቀሉና በመሞቱ ተስማማን ማለት ነው።

ታዲያ ክርስትያን ፣አይሁድ እንዲሁም ሙስሊሞች በዒሳ መሰቀል እና  መሞት ከተስማማን አንቀፁ ላይ በመጠራጠር ውስጥ ያሉትና ጥርጣሬን ከመከተል እውቀት የላቸውም ተብለው የተወቀሱት እነማን ናቸው?

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

29 Aug, 20:00


ከሰሞኑ የታተሙት አራቱ ፓምፍሌቶች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተበትነዋል። በተለይም በሀድያ አካባቢ የነበረው እንቅስቃሴ የቅርብ ጊዜ ጥሩ ስኬት ነበር፣ አልሐምዱሊላህ። ቀሪ ፓምፍሌቶችም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ተልከው ሙስሊም ላልሆኑ ወገኖች እየተሰራጩ ይገኛሉ። ዛሬ ደግሞ ፓምፍሌቱ ያልደረሳችሁና ማንበብ ለምትፈልጉ፣ ፕሪንት አድርጋችሁ ለአካባቢያችሁ ሰዎች ማዳረስ ለምትፈልጉ ፋይሉን ድረ ገጻችን ላይ ጭነንላችኃል። ገብተው ዳውንሎድ በማድረግ መጠቀም ይችላሉ።

https://hidayacomparative.org/?p=1148

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል እና የዳዕዋው አካል ለመሆን፦

https://bit.ly/4aGr93u

በቴሌግራም በኩል ሊያገኙን ከፈለጉ፦
@Hidayaislamiccenter

1000499318212
Hidaya Islamic Center
አጭር የንግድ ባንክ ቁጥር - 8212

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

22 Aug, 10:13


ዛሬ በምንም ጉዳይ ላይ ላወጋ አይደለም፤ ግን አንድ ወንድም ድንገት ችግር አገኘችውና ምናልባት እዚሁ ላላችኹ ጥቂት ሰዎች ጉዳዩን ባካፍላቹኹና የምንዳው ተቋዳሽ ብንኾን ብዬ አሰብኹ፡፡

ግልሰቡ የአላህ ፍላጎት ኾነና እናቱንና ኹለት ሴት ልጆቹን በተከታታይ በሞት አጣ፡፡ ቀጠለና ከገጠር የነበረው የአባቱ መሬት በቅርብ ዘመዱ ተነጠቀ፡፡ ለጠቀና እሱም በተለያዩ የጤና እንከኖች ተጎዳ፡፡ አኹን ላይ ደግሞ ችግሩን ለራሱ ብቻ ደብቆ ከሕይወት ጋር ግብግብ ላይ ነው፡፡ መንገድ ላይ ብቻውን እያወራ በምሽት አገኘኹት፡፡  ከዚያ በኋላ ያለውን አላውራው...

ኹላችንም የዚህ ምስኪን ልጅ ሕይወት ይመለከተናል ብዬ አስባለኹ፡፡ ቢቻልና ምስሉን በሚዲያ ለቀን ዕርዳታ ብናሰባስብለት በወደድኹ፤ ግን እሱ እምቢኝ አለ፡፡ በዚህ ልክ እንኳ ተጨኜው እንጂ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ለማንኛውም የምንችለውን ብናደርግና አንድን ሰው ወደ ሕይወት ብንመልስ ከአላህ ዘንድ እናገኘዋለን፡፡

وَمَا تُقَدِّمُوا لأنْفُسِكُمْ مِنْ خَيْرٍ تَجِدُوهُ عِنْدَ اللَّهِ هُوَ خَيْرًا وَأَعْظَمَ أَجْرًا

የንግድ ባንክ ኣካውንት
1000370662553
ዓብዲ ሰዒድ

© Eliyah Mahmud

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

22 Aug, 06:10


ታዋቂው የአሜሪካን ጋዜጣ New York Times ከዛሬ 135 በፊት በ 1889  ማለትም እስራኤል የምትባል ሀገር ከመፈጠሯ በፊት አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ ፅንፈኛ አይሁዶች ፍልስጤምን ለመውረር እና ያቀደቡት ዜና።

Conference of Zionists
Elect Delegates at their meeting in baltimore
Will colonize Palestine.

https://archive.org/details/NYTimes-Jun-Jul-1899/page/n401/mode/2up

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

12 Aug, 16:48


የቁርኣን አሰባሰብና ጥበቃ /Qur'an preservation and compilation/ በተደጋጋሚ ከሌላ እምነት ተከታዮች ጥያቄ የሚነሳበት ሲሆን ይህጠቃሚ ትምህርቶችን ያካተተ አዲስ ኮርስ በኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ አማካኝነት ይሰጣል።

በአጀንዳው ዙሪያ ጥልቅ እውቀቶችን መቅሰም የምትፈልጉ ኮርሱን በመመዝገብ መውሰድ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ በቴሌግራም
t.me/ZHARA_MUSTEFA

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

11 Aug, 09:34


ጉድ ተሰምቶ መስከረም ጠብቶ
.....

ሚዲያው ላይ ከተቃራኒ ጾታ ጋር የወደቁ የክርስቲያን ዐቃቤያንን ስታይ ኢስላም ዝሙትን እንዳትቀርቡ ብሎ ከመንደርደሪያው ጀምሮ የዘጋው በር ምንኛ ሰላማዊ እንደኾነ ትረዳለኽ።

በኢየሱስ ስም ወንድምና እህት ነን ያሉ ስጋ አሸናፊ መኾኑን ዘንግተው እንዳልኾነ ዕሙን ነው። ግን ደግሞ አጋጣሚዎችን ለፍቃደ- ስጋና ለጉልሙትና መጠቀሙ የተሻለና ወረቃማ ዕድልም  ስለኾነላቸው ነው።

ለዛ ሰፈር ዐቃቤያን "በኢየሱስ ደም" ኹሉም ዕዳ ከተከፈለ፣ደጋግሞ ዝሙት -ወ-ምርዐት( ምርዐት= የድብቅ ድሪያና ንክኪ) ውስጥ መገኘት  በ"ንስሐ" የሚሰረይ ከንቱ ነገር ነው።

ከካቶሊክ እስከ ጴንጤ እስከ አስጠማቂ የነፍስ አባት ኦርቶዎች በስጋው ረክሶ ተቋሙን ያላሰደበ አንድስ እንኳ የለም።

ዛሬ ላይ ደግሞ ሚዲያ ላይ የምናውቃቸው ትናንሽ አጋንንቶች በፍትወተ ስጋ -ወ-ነፍስ ጎጆአቸው ሲፈርስ አጓጉል የደመቁ ስሞቻቸው እንዳልኾነ ሲደበዝዙና ሲጠፉ እየታዘብን ነው።

ወዳጄ ልብ ይበሉ! በኢስላም ላይ ጦሩን የሰበቀ ኹሉ ይዘገያል እንጂ በገዛ ጦሩ መወጋቱ አይቀርም።

እኛ ባልጠበቅነው መንገድ ኢስላምን ለምን ያሉ ኹሉ መጨረሻቸዉ መቀመቅ ነው።

إنا لننصر رسلنا والذين آمنوا في الحيات الدنيا ويوم يقوم الآشهاد

አላህ እርዳታውን እንዴትና በነማን በኩል እንደሚያደርገው አናቅም። ከኾነ በኋላ ግን እንዳስሰዋለን።

وما يعلم جنود ربك إلا هو

© ኢልያህ ማህሙድ

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

01 Aug, 19:08


በነገራችን ላይ

1) ዲያቆን ዳንኤል ከ .... በፊት የፃፈው " ከኣክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና " ላይ የተገለፀችው ናህድ ሙተዋሊ ክርስትናን ለቃ ወደ እስልምና በቅርብ ግዜ ተመልሳለች።ከዘካሪያ ቡትሮስ ጋር ፕሮግራም አቅራቢ ነበረች።

2) ሰውየው እያንዳንዱ የግል ህይወቱን እንዴት አድርጎ ከክረስትናው ጋር ማያያዝ እንዳለበት እና አድማጭን መያዝ እንደሚቻል በደንብ ገብቶታል። ሰለዚህ ይሸቅልበት 😊

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

01 Aug, 18:57


አብዶ ጃሮ አስቂኙ ግለሰብ

አብዶ ጃሮ ከአንድ ፖድካስት ጋር የነበረውን ቆይታ አንድ ወንድም ላከልኝና አየሁት። ክርስትናን እንዲቀበል ያደረገው እስልምና መሆኑን ለዚህ ሚስኪን ምዕመን ሊያስረዳው ይሞክራል። የክርስትና ትምህርቶችን እስልምና ውስጥ ከዚያም ከዚህም እየቀደደ በመስፋት "አያችሁ እስልምና ስለ እናንተ ምን እንደሚናገር?" እያለ ለክርስትናው ከእስልምና አፕሩቫል ማግኘቱን ይጠቅሳል። በዚህ ውስጥ የፈጸማቸውን አያሌ የሎጂክ መፋለሶች ግን እሱም አብሮ ተቀምጦ ጭንቅላቱን የሚወዘውዘው ግለሰብም ከነአካቴው አያውቁትም። የሰውየውን የአስተሳሰብ ደረጃ ለመረዳት ከቪዲዮው የተወሰኑትን ከዚህ በታች ልጻፍላችሁ፦

▣ የሰለመው በህልሙ አንድ ድንጋይ ኢየሱስን ተቀበል ብሎት ነው። ይህ ድንጋይም እንደ እሱ አገላለጽ ከሆነ ኢየሱስ እራሱ ነው። በህልሙ በምን ቋንቋ እንዳወራው እንደማያውቅ መጀመሪያ ላይ ቢገልጽም ኃላ ግን "ሀል ተዓረፍተል ቁርዓን" ብሎ ጠይቆኛል ሲል "አረብኛ" መሆኑን ተናግሯል። ከድሮ የግሪክ ፈላስፋዎች ንግግር ውስጥ አንድ የሚጠቀስ ንግግር አለ "ጎበዝ አስታዋሽ ካልሆንክ ውሸትን አትሞክረው" የሚል ነው።

▣ ኢየሱስን በህልም አይተን ነው ጴንጤ የሆነው የሚሉ ሰዎችን በተመለከተ ታዋቂው የክርስቲያን አፖሎጂስት ጄምስ ዋይት (ዶ/ር) "የሚታመኑ ሰዎች አይደሉም" ሲል ይገልጻቸዋል። እያንዳንዳቸው ኢየሱስን አየን የሚሉ ሰዎች "ኢየሱስን ግለጽልን" ብትሏቸው አብዛኛዎቹ የሚጠቅሱት የሜል ጊብሰን ፊልም ያለው ያለውን ተዋናይ መልክ ነው። አንዳንዶቹም ፈጽሞ የሚያስቅና እርስበርሱ የተደበላለቀ ምስል ይሰጧችኃል። እንዲህ አይነት ማታለያ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማታለል ይመጥናል ብለው ስለሚያስቡ ያለሰቀቀን በአደባባይ ይነግሩታል።

▣ "ቸርች ላቃጥል ስል ነው ኢየሱስ የተገለጠልኝ" ሲልም በ1970ዎቹ የቀረ ትረካ ይዞ መጥቷል። እንደሱ አይነት ጮሌ ሰዎች "ሙስሊም ነበርን" ከሚሉ ይልቅ "አክራሪ ሙስሊም ነበርን" ቢሉ የድራማው ድምቀት ከፍ እንደሚል ያቃሉ። ምዕመኑ አብሮት እንደተቀመጠው ሰው አንገቱን እየነቀነቀ "አየኸው ተራ ምዕመን አልነበረም፣ ቸርች ሊያቃጥል የነበረ "ዋና ሙስሊም" ነው ኢየሱስ ያመጣልን" እያለ በግርምት እንደሚሸወድለት ያውቃል። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቀደመ ህይወቱ ለተረጎመው አንድ መጽሀፍ የሰጠው ስምም "ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና" የሚልን ነው። መጽሀፉን ስታነቡ ግን የድርሰቷ ዋና ገጸ ባህሪ ናህድ ማሕሙድ ሙተዋሊ በፍጹም ከሳሉት ስዕል ጋር የማይሄድ ስብዕና ኑሯት ታያላችሁ። እናም አክራሪ የምትለዋ አሁን ላይ የቀረች ብትሆንም አብዶ ጃሮ ግን ብዙ ነገሩ የሆነ ዘመን ላይ የተቸነከረ ከመሆኑ ጋር ካርዷን መዟት አሁንም ሊጠቀማት ሞክሯል።

▣ "ሙስሊም እያለሁ ከኦሮምኛ ውጭ አማርኛ ቋንቋ ጆሮየን ብትቆርጡት አልሰማም ነበር" አለን። ታዲያ ጴንጤ ሲሆን ግን ቋንቋውን በቀላሉ እንደቻለውና ኢየሱስ እንደገለጠለት አድርጎ አቀረበው። ሌሎችንም የሀገራችንም ቋንቋዎች ኢየሱስ ለምን እንዳላስለመደው ግን አልነገረንም፤ ኢየሱስን በዚህ መልኩ በፍጥነት ወስዶ ብሔርተኛ ማድረጉን ግን ስክሪፕቱን በጭንቅላቱ ሲተይብ የረሳው ይመስለኛል።

▣ በተገኘበት መድረክ ሁሉ አረብኛ መናገሩን እንደ ትልቅ የአዋቂነት ጉልበት አድርጎ ለማሳየት ፍዳውን ሲበላ እናስተውላለን። ከጉሮሮ የሚወጡ ቃላትን ያለቅጥ በመጫን ይህንኑ ለማያቁ ሰዎች ፕሩፍ ለማድረግ ይደክማል። በቅርብ ርቀት የሚገኙት የግብጽ ኦርቶዶክሶች ቅዳሴያቸው ሁሉ አረብኛ መሆኑን የዘነጋው ይመስላል። አረብኛ መቻል እስልምናን ለማወቅ ይጠቅማል እንጅ አረብኛ ማወቅ ብቻውን የእስልምና አዋቂ ያደርጋል ማለት አይደለም። በዚያ ላይ ቲክቶክ ከወንድሞች ጋር በነበረው ክርክር መሠረታዊ የአረብኛ ህግጋት የሆኑትን ሙአነስና ሙዘከርን እንኳን በቅጡ መለየት ያልቻለ ሰው እንደነበር አስተውለናል።

▣ ሌላው አስገራሚው ነገር "ሼይኽ ነበርኩ፣ ልጆችን ቁርአን በማስቀራቴ የማገኘው የገንዘብ ጥቅም ክርስቲያን በመሆኔ አጥቸው ተቸግሬያለሁ" ይለናል። ሰው በዚህ ደረጃ ኮሜዲ ይሆናል?ይህንን የሚለው እጅግ ዘመናዊ ታብ በእጁ ይዞ ነው። ሌላው ቢቀር እራሱ እንተደተናገረው ለተወሰኑ አመታት ውጭ ሀገር ልከው ያስተማሩትን ከበርቴ ወንጌላውያን እጅ መንከስም ጭምር ነው። ይህችን ኮፍያና አማይማ ለብሰህ ለምን እንደምትመጣ ሁሉም ሰው ያቀዋል። ጥሩ ሽቀላ ስለሚገኝባት ነው። ይህንን ለማለባበስ የቁርአን አቅሪ ደሞዝን ማጋነን አስገራሚም አስተዛዛቢም ነው። ቁርአን አቅሪዎች የሚከፈላቸው ክፍያ እንኳን ሊጋነን ለቤተሰብ እንኳን በመከራ እንደሚብቃቃ ሁሉም ያውቀዋል፣ ያውም ገጠር የሚገኙት ደግሞ ከዚህም የከፋ ነው።

◾️ በጥቅሉ አብዶ ጃሮ ያነሳቸው ነጥቦች ፕሮግራም ተይዞ በቁምነገር ምላሽ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ሁነው አላገኘኃቸውም። አብዛኛው ሰው እያራገበው ከመሆኑ አንጻር ግን እንደ አስፈላጊነቱ በአሏህ ፍቃድ በቪዲዮ መልስ እንሰጥበታለን።

© የሕያ ኢብኑ ኑህ

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

01 Aug, 18:14


ንፅፅር ላይ ለምትሰሩ ወንድሞችና እህቶች።

1)አላህና መልእክተኛው ላይ ከሚያላግጥ ሰው ጋር ውይይትም ሆነ ክርክር  በፍፁም በፍፁም ማደረግ አያስፈልግም።

አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል

ቁርኣን 4:140

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِى ٱلْكِتَٰبِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا۟ مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا۟ فِى حَدِيثٍ غَيْرِهِۦٓۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْۗ إِنَّ ٱللَّهَ جَامِعُ ٱلْمُنَٰفِقِينَ وَٱلْكَٰفِرِينَ فِى جَهَنَّمَ جَمِيعًا

በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነሱ ጋር አትቀመጡ፡፡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡ አላህ መናፍቃንን እና ከሓዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና፡፡

2) መልካም ውይይት ማደረግ ግን አልተከለከለም።

ቁርኣን 16:125

ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ

ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ #መልካም #በኾነችው (ዘዴ) #ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡

3,175

subscribers

129

photos

39

videos