ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2 @philsopy Channel on Telegram

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

@philsopy


እዉቀት ነፃ ያወጣል!

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2 (Amharic)

ከአምስቱ ወራት በፊት በፈረሶች ተመልከቱ፣ በልዩ ወር በመፋሰስ የኖርና የሥጋ ጉዳይን ተለውጦ የሚያሳርፉ ፍልስፍናዎች እና ማንኛውንም ነገር ለነገሩ አስተማሪ ጽሁፎች በማሰብ ይሄ ተመሳሳይ ነው። ፍልስፍና ለይህ ቁጥሩ ባለው የፍልስፍና አባባ ቁጥር 2፣ ከዚህ በፊት ሀምሌ 2021፣ ቸርኩባል የሚይዙና የሚረዱ ፍልስፍና ነው።nnከዚህ በፊት ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2 በቆይ፣ ብዙ ሰዎች ተማሪ ስለሆኑ ፍልስፍናዎች አጋሙን፣ አዳዲስ ግንኙነት እና ሚስጥሩን እያሳቅመተ ድረ-ገጽዎችን ለማስገንባት ይህ ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2 ከሚያበቃ፣ ከአርብ በሚሄዱ ያዳብርከው ሰዎች ላይ ምልክታቸውን ያቀናጅሉ ይሆናል።nnለፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2 ይመልከቱና ለማግኘት የሚሆኑ ሰዎች መረጃዎቹን ለመስራት እና መረጃዎቹን እንመለከታለን።

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

21 Nov, 17:42


በእዉነት በእዉነት እንጠብቃችኋለን

🙏ነገ
በ11: 00 ሰዓት በ'ወመዘክር'

መግቢያው ነፃ ነው 🙏

ላለመምጣት ብዙ ምክንያት ይኖራችሁ ይሆናል ፣ ታክሲው እንደልብ ላይሆን ይችላል ፣ ስራ ሊደራረብ ይችላል ፣ ዱካካም ቀን ልናሳልፍ እንችላለን ፣ ካላችሁበት ቦታ ወመዘክር ራቅ ሊል ይችላል...ይሄ ሁሉ ሊገጥም እንደሚችል እያወቅኩ

እኛ ግን እንጠብቃችኋለን 🙏

በዛ ላይ እኔ እኮ ንግግር አደርጋለሁ እስኪ በአጋጣሚዉ እንተዋወቅ ኑ!
💛

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

21 Nov, 16:37


Sigmund Freud አንድ ቆንጆ ነገር ፅፎ ነበር።

" ሰዎች ብዙ የሚያወሩት የሆነን ነገር ለመግለፅ ይመስለኝ ነበር ። ነገር ግን ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚያወሩት የሆነ ነገር ለመደበቅ እንደሆነ ገብቶኛል" ይላል ።

ብዙ የሚያወራ ሰው ከባድ የውስጥ ጩኸትና ግጭት ያለበት ሰው ነው። ብዙ የሚያወራ ሰው ብዙ የመዋሸት እድል አለው። ብዙ በማውራት የውስጥ ግጭቱን እና ውሸቱን መደበቅ አለበት። ብቸኝነት የሚሰማቸው ሰዎች ትንሽ የሚቀርባቸው ሰው ሲያገኙ በጣም ሳቂታና ተጫዋች ይሆናሉ። ምክንያቱም የብቸኝነታቸውን ጩኸት የሚደብቁት በሳቅ እና ብዙ በማውራት ውስጥ ነው። ድምፅን በድምፅ መዋጥ አይነት።

አየህ ለዚያ ነው ካህሊል "የሰዎችን ትክክለኛ ማንነት ማወቅ ከፈለክ የሚናገሩትን ሳይሆን የማይናገሩትን አድምጥ" የሚለው።

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

21 Nov, 16:20


የምትወዳትን ሴት ለመርሳት በጣም ቀላሉ መንገድ

እርሷን ማግባት ነው
አለበለዚያ ሁሌ ስትወዳት ትኖራለህ።
(ዶስቶቭስኪ)

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

17 Nov, 16:13


ከጅምሩ እራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ ማወዳደር ትልቅ በሽታ ነው ፤ እንደ ካንሰር ነው ነፍስህን እያጠፋ ይሄዳል? ምክንያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ ልዩ ነው ፣ እና ማወዳደር አይቻልም። እኔ እኔ ነኝ አንተም አንተ ነህ ፡፡ በዓለም ላይ አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለምና ፡፡
* ኦሾ *

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

14 Nov, 16:31


#ኸሚስ_አመሻሹ🌿
የከሚስ ደመና ፣ አለው ራህመት ፤
አዱሩሱን አጪሺው ፣ በእነነየ ሞት🤗

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

13 Nov, 11:07


The Good God and The Evil God"

መልካሙ አምላክና ክፉው አምላክ አንድ ቀን በተራራ ጫፍ ላይ ተገናኙ∶:

መልካሙ አምላክ፡- መልካም ቀን ይሁንልህ! ወንድሜ! አለው:: ክፉው አምላክ መልስ አልሰጠም::

መልካሙ አምላክም፡- ዛሬ ደስተኛ አትመስልም አለው::

አዎ› አለ ክፉው አምላክ፡- ‹ብዙውን ጊዜ ሰዎች ከአንተ ጋር ያሳስቱኛል፤ በስምህም ይጠሩኛል፤ አንተንም ያደርጉኛል፤ ያ ደግሞ ያበሳጨኛል› አለው::

መልካሙ አምላክም፡- ‹እኔንም እኮ ከአንተ ጋር እያምታቱ ይጠሩኛል፤ በአንተ ስምም የሚጠሩኝ ብዙዎች ናቸው፤ አትበሳጭ› አለው::

ክፉው አምላክ የሰውን አላዋቂነት እየረገመ ጥሎት ሄደ::

ኢየሱስ የሰው ልጅ
https://t.me/philsopy

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

05 Nov, 20:18


አይምሯችሁ ከታመመ አካላችሁም ይታመማል።አካላችሁ ከታመመም አይምሯችሁ ይታመማል።ወይን እንድትጠጡ ባደርጋችሁ የማጠጣው አይምሯችሁን አይደለም።መጠጡ ግን ወደ ጨጓራችሁና ጉበታችሁ ይሄዳል።ወደ አይምሯችሁ አይሄድም።ነገር ግን ወይን ወደ አካል በገባ ቅፅበት አይምሮ የባጥ የቆጡን መቀባጠር ይጀመራል።እንደዛ መሆን የለበትም፤ግን ይሆናል።ወይኑ የዘለቀው ወደ አካል ሲሆን ውጤቶቹ ግን ወደ አይምሮ ደርሰዋል።አይምሮ በስጋትና በድብርት ሲታመም ደግሞ አካልም ወዲያው ያዘነና የታመመ ይሆናል።በሽታ ወደ አይምሮ ከገባ አካልም ይከተለዋል።

📙ርዕስ፦የመጨረሻው ሕግ
✍️ፀሀፊ፦ኦሾ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

31 Oct, 15:23


➟የአንድ ዘመን የምድራችን ታላቅ አሳቢና ደፋር::
➟ከክርስቶስ በኋላ የተፈጠረ በጣም አደገኛ ሰው::
➟ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ከ1000ቹ ታላላቅ ሰዎች መሀል አንዱ::
➟ከመላው አስቀያሚ ሰብዓዊነት ጋር አንድ ብቻውን ሆኖ ትግል የገጠመና አለምን ያናወጠ::

እነዚህ በተለያዩ ግዜ ስለ'ሱ ከተነገሩ አባባሎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ክህሎት የላቀ የአዕምሮ ባለቤት ለመሆን የበቃው ገና በ21 አመቱ ነበር፡፡ በዚህ የወጣትነት ዕድሜ ላይ መንፈሳዊ ብቃትን የተጎናፀፈ ግለሰብ እስካሁን እንዳልታየም ይነገራል:: ፍልስፍና ፒኤች ዲግሪ አግኝቷል፡፡ በተለያዩ የህንድ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት አገልግሏል፡፡ ድፍረቱ የትየለሌ ነው::

በለየለት ድፍረቱ ያየውን የሰማውን ያነበበውን እውነት ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ሁሉ አውጥቶ ይዘከዝከዋል፡፡ በንግግሮቹ ያልዳሰሰው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ህይወት፣ ያላፈረጠው ባህላዊ ቁስለት ከቶም የለም፡፡ እምነትን፣ ባህልን፣ ሀይማኖትን፣ ጋብቻን፣ ወሲብን፣ ማህበራዊ፣ ስርዐተ ትምህርትን በሚገርም አሳማኝ ንግግሮቹ ያብጠለጥላቸዋል፡፡

"መላው አለም ከኔ በተቃራኒው ቢቆም እንኳን በውስጤ አንድም ጥርጣሬ አይፈጠርም ምክንያቱም የማውቀውን አውቃለሁ የሆንኩትን ሆኛለሁ!!” ይል ነበር:: እጅግ መሳጭ በሆነ የንግግር ጥበቡና በማስረጃ በተደገፈ የክርክር ዘይቤ አለምን ውድቅ ያደርግና የራሱን ብሩህ አዲስ የህይወት አቅጣጫ የሚለውን ያስተዋውቃል፡፡

ለየትኛውም እምነት፣ አስተሳሰብ፣ ባህልና ወግ ሐይማኖት ግድየለሽ እንዲያውም ፈፅሞ አላስፈላጊ ነው ባይ ሲሆን ከዚህ በላይ ግን ውስጣዊ ማንነትን ፍለጋ ላይ መድከም ብቸኛው የሰው ልጅ ከተያዘበት የባርነት ሰንሰለት የሚወጣበት መንገድ መሆኑን ደጋግሞ ይናገራል፡፡ መሰረታዊ ችግሩም ይህም ከግዜው ቀድሞ መምጣቱ እንደሆነ የሚዘግብም አልታጡም፡፡

በልጅነቱ ግዜ ከሌሎች የዕድሜ እኩዮች የሚለይበት በአንባቢነቱ ነበር፡፡ በአለም ላይ ያሉ በርካታ መፅሐፍትን ያነበበ ሰው መሆኑ ብዙዎች የሚስማሙበትና የሚመሰክርለት ነው፡፡ በፑና ማዕከልም ባለው የግል ላይብረሪው ውስጥ 100,000 በላይ የግል የመፃሕፍት ስብስቦች ነበሩት፡፡

ከ 600 በላይ መፃሕፍት ታትመውለታል፡፡7,000 ሰዐታት የሚፈጁ የኦዲዮቴፖች ንግግሮች አሉት፡፡ እነዚህም ለደቀመዛሙርቱ (ሳንያሲንስ) በጥያቄና መልስ ፕሮግራም የሰጠው የረጅም አመታት ትምህርቶች እንዲሁም በታላላቅ መድረኮች ላይ ያደረጋቸው ንግግሮች ተውጣጥተው የተፃፉ ናቸው፡፡

ስራዎቹ በመላ አለም በተለያዩ ቋንቋዎች እየተተረጎሙ እስካሁን በመሰራጨት ላይ ናቸው፡፡ “እኔ አንድም ተከታይ እንዲኖረኝ አልሻም ሌሎችን የምትከተሉ ከሆናችሁ ትጠፋላችሁ!!” እያለ ዘውትር ለተከታዮቹና ለአድናቂዎቹ የሚናገር ቢሆንም በአለም ዙሪያ አያሌ ተከታዮችንም አፍርቷል ለዚህም ተቀዳሚው ማስረጃ በአሜሪካ በአውሮፓ በእሲያ በህንድ የተቋቋሙት (Osho Commune International) የተሰኙት ማዕከላት ናቸው፡፡

ከሞተ በኋላ ህንድ ፑና ውስጥ ወደ አቋቋመው ማዕከልም በበርካታ አድናቂቹና ተከታዩቹ ከተለያዪ ሀገራት ወደ ስፍራው አሁንም ድረስ ይጓዛሉ፡፡ በማዕከሉም እራሱ የፈጠራቸው የተለያዩ የተመስጦ ዘዴዎችንም እንደትምህርት የሚሰጡበት ማዕከልም ሆኖል፡፡

የአለማችን ታላቅ አወዛጋቢ ሰው!! ህንድ ውስጥ ኩችዋይ በምትባል መንደር ዲሴንበር 11፣ 1931 ነው የተወለደው:፡ በቤተሰብ የወጣለት መጠሪያ ስሙ ቻንድር ዋሀን ጄይን ሲሆን በሁላ ላይ ስሙን ባግዋን ሸሪ ራጅኒሽ በሚል ቀይሮታል፡፡ አለም የሚያውቀውም “ኦሾ”በሚለው ስሙ ነው፡፡

ህንድ ፑና ውስጥ ጀንዋሪ 19 1990 በ 58 ዓመቱ ሲሞት የሞቱ መነሻ አሜሪካ ሀገር በነበረበት ግዜ በአሜሪካ የስለላ ድርጅት (CIA) ታሊየም በተባለ መድሀኒት መርዘውት እንደነበረና በሱ ህምም መነሻነት እንደሞተ ተከታዩች ያምናሉ፡፡ ክሮኒክ ፋቲግ ሲንድረም የተባለ የጤና ችግርም እንደነበረበትና ይህም በሽታው ለሞት እንዳበቃው የሚናገሩ ወገኖችም አሉ፡፡

Osho! Never born Never died only visited this planet earth between December 11, 1931to January 19, 1990 ተከታዮቹ እንዲህ ነው የሚያስብት

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

27 Oct, 17:49


...ስለ ሴት ና ስለ ሀገር ማሰብን ያህል አስጨናቂ ነገር የለም...! "

#ይስመዕከ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

27 Oct, 16:38


ተናጋሪው ብዙም ስላማያውቀው ነገር አንተ ግን በደንብ ስለምታውቀው ነገር ሲያወራህ በጥሞና ማዳመጥህ፣
ትልቅ የስነ ምግባር ከፍታ ነው።
(መጅሁል)

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

22 Oct, 19:47


ምድር ውብ ነች። ውበቷን መኖር ከጀመራችሁ ልባችሁ ውስጥ ጥፋትን ሳታምቁ ደስታዋን ማጣጣም ከቻላችሁ ገነት ውስጥ ናቸው።

ሁሉንም ነገር ካወገዛችሁና እያንዳንድዋን የደስታ ቀዳዳ ከነቀፋችሁ ግን ያችው ምድር ተመላሳ ገሀነም ትሆናለች።

የምትኖሩበትን ቦታ መወሰን በእራሳችሁ ምርጫ ላይ የተመረኮዘ ነገር ነው። አስፈላጊው ነገር የቦታ ለውጥ ሳይሆን የውስጠታችሁ ለውጥ ነው።

       በደስታ በምሉእነትና በጥልቀት ኑሩ።
ያን ጊዜ ገነት ህልም መሆኑ ቀርቶ የህይወት ልምድ ይሆናል።
               ኦሾ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

20 Oct, 16:49


ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል የሚለው ስህተትም ትክክልም ነው። ማንበብ ሙሉ ሰው አያደርግም። ስለዚህ ስህተት ነው። ማንበብ ጉድለትን ያሳያል። እዚህ ላይ ትክክል ነው። ማንበብ ሙሉ ሰው የሚያደርገው የጎደለውን ስለሚያሳውቅ ነው። ካላነበብክ ጎደሎህን አታውቅን። የጎደለህን ካላወቅክ ሙሉ አትሆንም። ጉዳዩ አለማወቅን ከማወቅ የሶቅራጥስ አሳብ ጋር የሚገናኝ ነው። ካላነበብክ አለማወቅህን አታውቅም። የጎደለህን ካላወቅህ ሙሉ ለመሆን የጎደለህ የለም። ስለዚህ ማንበብ ሙሉ የሚያደርገው በራሱ ሳይሆን አንተ የጎደለህን እንድታውቅ በማድረግ ነው። ይህን ጥያቂያችንን ይመልስ ዘንድ ወዳጄ አዲስ መጽሐፉን ጀባ ብሎናል ልጁ በጣም ጥልቅ አሳቢ ሲበዛ አንባቢ ጎበዝ ጸሐፊም ነዉና መጽሐፉን ገዝታችሁ እዉቀት ተሸምቱ ዘንድ ግብዣዬ ነዉ።

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

19 Oct, 11:21


"ሳያስቡ ከመኖር እያሰቡ መሞት ይሻላል!"

"ሰውን ከእንሰሳ የሚለየው በማሰቡ ነው" የሚለው ህግ ለሶቅራጥስ ቦታ የለውም። ምነው ቢሉ "ማሰብ የለየው ሰውን ከእንስሳ ሳይሆን ሰውን ከሰው ነው" ይለናል።
"ለግሪክ አማልክት ህዝቡ የሚሰግደው ስለሚያምንባቸው ሳይሆን ማሰብ ስለማይችል ነው" በማለት ይሳለቅባቸው ነበር።
በዚሁ ቁጭትም ከፕሌቶ ጀምሮ ተከታዮቹ የነበሩት በሙሉ በዚህ  "የማሰብ እውቀት" ሊያጠምቃቸው ተነሳ።

"ሰው በውስጡ ያለውን ብቃት ቢረዳ አሁን ያለበት ቦታ ባሳፈረው ነበር... ማሰብ የሚችል ፍጡር ማሰብ ለማይችሉ አማልዕክት እንዴት ይሰግዳል?"  በማለት ጠይቆ ለመስዋዕትነት ያበቃውን ተጠይቃዊ አስተሳሰብ (ሎጂክ) በተከታዮቹ ልብ ውስጥ ዘራ።

ጥበብ ከጲላጦስ ቅጽ ፩
(ሃይለጊዮርጊስ ማሞ)

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

17 Oct, 18:46


...

<< የልጄ የዘወትር ምኞትና ፍላጎቱ የእስራኤልን ክብር ማየት ብቻ ነበር >>

( የ ይ ሁ ዳ ፡ እ ና ት ፡ ሲ ቦ ራ )

ልጄ ይሁዳ ቅንና ፃድቅ ሰው እንደነበር አውቃለሁ። ለእኔ ለእናቱ የነበረው አዛኝነትና ርኀሩኀነት ደግሞ እስከመቼውም የሚረሳኝ አይሆንም። ወዳጆቹንና የሃገሩን ልጆችም አጥብቆ የሚያፈቅር ሰው ነበር። እርጉም የሆኑትን የሀገራችንን ጠላቶች ሮማማውያንን ደግሞ ከማንም በላይ ይጠላ እንደነበር አውቃለሁ፤ ሮማውያን ያልሰፉትን የሚለብሱ፣ ያላከማችሁትን የሚሰበስቡ፣ ያልዘሩትን የሚያጭዱና በአይሁድ ሀብት የከበሩ መሆናቸውን ዘወትር ሲናገር እሰማው ነበር።

ልጄ ይሁዳ በአንድ ሮማዊ ወታደር ላይ ቀስቱን በመወርወር አቁስሎት እንደነበር አስታውሳለሁ። ይኸም ወንጀል ሆኖበት ሲታሰር 17 ዓመቱ ብቻ ነበር።

በዚያ ዕድሜው የአይሁድን ወጣቶች ልብ ስለነፃነት እያስተማረ ሲያነቃቃና ሲያደፋፍር ይውላል፤ የእስራኤልንም ክብር በየአደባባዩ ይመሰክር ነበር፤ ምንም እንኳን በዛ የወጣትነቱ እድሜ ታላላቅ ነገሮችን ይናገር እንጂ እኔ የእናቱን ጨምሮ ብዙዎቻችን ስለሚናገረው ነገር መረዳት ያቅተን ነበር።

ልጄ..ብቸኛው ልጄ እሱ እንደነበር ታውቁልኝ ዘንድ እወዳለሁ፤

ዛሬ እንዲህ ደርቀው ምታይዋቸውን ጡቶቼን የጠባ፤ በአትክልት ስፍራዎቼም እነዚህ እጆቼን በትንሽ ጣቶቹ ይዞ ይዞ መሄድ የለመደ ብቸኛው ልጄ ነው። እነዚያ የሚያማምሩ የህፃንነት እግሮቹ ላይም የመጀመርያውን ሰንደል ያደረግሁለት እነዚህ አሁን የምታይዋቸው እጆቼ ናቸው። በሕፃንነት ወራቱ ያደረግሁለትን እነዚያ ሰንደል ጫማዎች ዛሬም ዛሬም ለመታሰቢያ በቤቴ መስኮት አጠገብ አስቀምጬ ዘወትር አያቸዋለሁ።

የመጀመርያውና ብቸኛው ልጄ ነቀርና በህይወቱ ውስጥ በሚጨምራት እያንዳንዱ የእድገት ደረጃ ልክ የእኔም ህይወት ትጨመር ነበር። ማንኛዋም እናት ከወለደች በኋላ የእርምጃዋ ልክ በልጇ እርምጃ እንደሚወሰን ሁሉ የእኔም እንዲሁ ነበር።

እነሆ! አሁን ግን ልጅሽ ራሱን ገደለ ይሉኛል፤ ወዳጁን የናዝሬቱን እየሱስን በመካዱ ተፀፅቶ ከታላቅ አለት ላይ በመውደቅ ራሱን ፈጥፍጦ ገደለም በማለት ይነግሩኛል።

የልጄን መሞት አውቃለሁ፤ በዚያውም ልክ ግን ማንንም እንዳልከዳና እንዳላታለለ አውቃለሁ። በእሱ ዓይን ከሮማውያን በቀር ክፉና የሚጠላ ሰው እንዳልነበረም አውቃለሁ።

ልጄ የዘወትር ምኞትና ፍላጎት የእስራኤልን ክብር ማየት ብቻ ነበር፤ ስለእስራኤል ክብር ማውራትም ከከንፈሩ አይለየውም፤ በተግባሩም ለሃገሩ ልጆች ይህንን አሳይቷል። አንድ ቀን በጎዳና ላይ አብረን ስንሄድ ይሄን አሁን ከዳው የሚባለውን ኢየሱስን አገኘውና እኔን ጥሎ እሱን ተከትሎት ሄደ። በልቤ ግን ልጄ ማንንም ሊከተል እንደማይገባው አውቅ ነበር።

ተመልሶም ደህና ሁኚ በማለት ሲሰናበተኝ መሳሳቱን ነግሬዋለሁ፤ ነገር ግን ሊሰማኝ ደግሞ አልፈቀደም ነበር።

ልጆቻችን የምንነግራቸውን አይሰሙንም፤ ትናንት የትኛውንም ምክር ከወላጆችሁ መቀበል እንደማይሹት ሁሉ ዛሬም ሲቀበሉ አይታይም።ከእንግዲህ ስለልጄ እንዳትጠይቁኝ እለምናችኋለሁ።እወደው ነበር። እስከዘለዓለምም እወደዋለሁ።

ፍቅር ከስጋ ቢሆን ስጋዬን አቃጥዬ በመጣል እገላገል ነበር፤ ነገር ግን ከነፍስ ሆነና ልደርስበት አልቻልኩም።

ከእንግዲህም አንዳች ቃል አይወጣኝም። ከይሁዳ እናት በላይ ክብር ወዳገኙት እናቶች ሄዳችሁ እነርሱን ጠይቁ።

ወደኢየሱስ እናት ሂዱ። የእኔን ልብ ያለፈው ልጅ-የማጣቴ-ሰይፍ በእሷም ልብ ውስጥ አልፏልና የሚሰማኝን በሚገባ ልትነግራችሁ ትችላለች፤ ያን ግዜም ትረዱኝ ይሆናል።

፨ኢየሱስ የሰው ልጅ፨ ካልተጻፈው ወንጌል
ካህሊል ጂብራን

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

13 Oct, 18:57


አንድ ቀን ዲዮጋን የቀብር ቤት ገልብጦ ገብቶ የሰው አጽም እያነሳ እንደመመርመር እያደረገ ይጥላል ደሞ ያነሳል።
በዚያ ጋ ታላቁ እስክንድር ሲያልፍ ዲዮጋንን ስላየው
"ዲዮጋን ምን እያደረክ ነው ? ሲል ይጠይቀዋል ።
ዲዮጋን ቀናም ሳይል " የአባትህን አጥንት እየፈለኩ ነው ከባሮቹ ጋ ተደባልቆ ሊለይልኝ አልቻለም " አለው ይባላል ።
ዓለምን ገዛ የተባለለት ታላቁ እስክንድር ከዚህ ፈላስፋ ተምሮ ቀሪ ዘመኑን ተጠቅሞበት ይሆን ?
እኛስ የዚህ ዘመን ተረኞች የታላላቆችን አጽም ከባሮቻቸው ለመለየት ምን አቅም አለን ። አለም የድንበር ኬላ ባነሳበት በዚህ ዘመን የመንደር መንግስት ለመመስረት የሚዳዳን ትንንሾች ፥ ዘር እየቆጠርን ክርስቶስ የሞተለትን የሰው ልጅ የምናሳድድ ኃላ ቀሮች ...
የሁላችንም መጨረሻ ማንም ከማንም ወደማይለይበት ሞት መሆኑን አውቀን በተጨመረችልን አንዲት ቀን ለሰው የሚመች ስራ ሰርተን እንለፍ ።

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

10 Oct, 18:59


“ውስጥ ያሉት መውጣት ካልቻሉ ፥ ውጭ ያሉት መግባት ካልፈለጉ፤ መቃብር ስፍራ ለምን በግርግዳ እንደሚከለል ግራ ይጋባኛል።” 🧐


                       ፦Mark twain

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

10 Oct, 17:34


--------
"ለሁሉም ሕያው ፍጡር በልቡ መሐሪና አዛኝ ያልሆነ ምንኛ የሚያሳዝን ሰው ነው!"

- ዓብዱልቃድር ጀይላኒ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

03 Oct, 19:12


የፖለቲካና የሀይማኖት ሰዎች ብልህ ግለሰብ እንድትሆን
አይሹም ምክንያቱም ብልህ ከሆንክ ሊበዘብዙህ
አይችሉም ።

ኦሾ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

03 Oct, 17:16


ካህሊል ጅብራን አንድ ወቅት እንደዚህ ብሎ ነበር ፦

"ከአንድ ሰው ጋር ለመጋጨት አንድ ደቂቃ በቂ ሊሆን ይችላል።”

" አንድን ሰው ለመውደድም አንድ ሰዓት አስተማማኝ ሊሆን ይችላል።"

" አንድን ሰው ለማፍቀርም አንድ ቀን ብቻዋን በቂ ልትሆን ትችላለች .….......ግን ግን አንድን ሰው ለመርሳት የእድሜ ልክ ጥረት ይጠይቃል"

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

29 Sep, 16:27


ሰይፉ
"ያንቺ የምንጊዜም 4 መጽሃፍት እነማናቸው?"

መቅዲ
"አንደኛ Rich Dad poor Dad
ሁለተኛ Poor Dad Rich Dad
ሶስተኛ አልወለድም
አራተኛ አቤ ጉበኛ"
በፈጣሪ😥 ቢቀርባትስ😥

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ቁጥር 2

26 Sep, 20:00


ሶቅራጥስ፡
ማንኛውም የተሳሳተ ድርጊት የሚመጣው ካለማወቅ ነው አእምሮ ደግሞ አይሳሳትም!።

አርስቶትል፡
አብዛኛው የሰው ልጅ ድርጊት የሚመጣው ምክንያታዊ ካልሆነው እብደት ወይንም የነፍስ ክፍሎች ውስጥ ነው።

ስፒኖዛ፡
ምኞት የድርጊት ምንጭ ነው እና አእምሮ ለምኞት ኃይል ይጋብዝሃል።

ሾፐንሃወር፡
የሰው ልጅ ድርጊት መረዳት አይቻልም ምክንያቱም ዓላማውን ከማይረዳ ከጭፍን ፍላጎት የመጣ ስለሆነ ነው።

ፍሮይድ፡-
አእምሮ እራሱን እንደ ተጽኖ ፈጣሪና እንደ ተዋናይ ይገልጣል የሰው ልጅ ድርጊቶች instinctive roots/የደመነፍስ ጉዞ ነው!።

ዶስቶየቭስኪ፡
አንድ ሰው የለመደውን ድርጊት ሲፈጽም እንኳን ምንም አያውቀውም!።

ኒቼ፡
ድርጊቱን አስተውሎ አሮጌውን አለም የማያጠፋ አእምሮ፤ እርሱ ባርነት ነው!።

 
 
በማን ሀሳብ እንስማማ¿