INFO - 24 @information1005 Channel on Telegram

INFO - 24

@information1005


Get fast and secure information and share more people

@information10005 Inbox all information

INFO - 24 (English)

Are you always looking for fast and secure information to stay updated on the latest news, trends, and events? Look no further than INFO-24! This Telegram channel, with the username @information1005, is your go-to source for all things information-related

INFO-24 is dedicated to providing its subscribers with accurate and timely information on a wide range of topics, including news, technology, lifestyle, entertainment, and more. Whether you're interested in current events, want to learn about new gadgets, or simply enjoy reading about interesting facts, this channel has got you covered

With a team of knowledgeable and experienced contributors, INFO-24 ensures that all the information shared is reliable and up-to-date. You can trust that you're getting the most relevant and valuable content when you follow this channel

Moreover, INFO-24 encourages its subscribers to share the information they find interesting with more people. By doing so, you can help create a community of individuals who are passionate about staying informed and connected. After all, knowledge is meant to be shared!
So, if you want to stay informed, learn something new, and connect with like-minded individuals, join INFO-24 on Telegram today! Simply search for @information1005 in your Telegram app and hit that subscribe button. Get ready to dive into a world of information at your fingertips. Don't miss out on this opportunity to expand your knowledge and connect with others who share your interests. Join INFO-24 now and start exploring the vast world of information that awaits you!

INFO - 24

26 Sep, 15:57


ሰበር ኢንፓየር
የሱማሊያ ናሽናሊስት ጥምር ሃይል ወደ ኢትዮጵያ በሚጓጓዙ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ተዘጋጅተናል አሉ።

ባህር ሃይላችን ተዘጋጅ እንግዲህ

INFO - 24

26 Sep, 12:44


ሰበር
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ሰላማ ጋር በእምነቱ እና ቀኖና ዙርያ አብሮ ለመስራት ተገናኝተው ለመነጋገር ፍላጎት እንዳላቸው በአባቶች በኩል መልዕክት ልከዋል።

INFO - 24

25 Sep, 17:49


የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን የህወሓት ቡድን አስጠነቀቁ።

ፕሬዜዳንቱ በማስጠንቀቂያቸው „ ቡድን „ ሲሉ የጠሩት ሃይል የወረዳና የከተማ የህዝብ ምክር ቤቶች ለመረበሽ እየሄደበት ያለው ርቀትና በማድረግ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት ብለዋል።

መስከረም 14/2017 ዓ.ም በፕሬዜዳንቱ ፊርማ ተፈርሞ ለሁሉም የወረዳና የከተማ ም/ቤቶች የተፃፈው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ „ የህዝብ ምክር ቤቶች የትግራይ ጊዚያዊ መንግስትና የህዝቡ አካል እንጂ የህወሓት መዋቅር አለመሆናቸው አውቆ ‚ ቡድኑ ‚ የራሱ መሳሪያ ለማድረግ እያካሄደ ያለውን መሯሯጥና ውንብድና ማቆም አለበት „ ይላል።

ስለሆነም ምክር ቤቶቹ የመንግስትና የህዝብ መዋቅር መሆናቸው በማመን ‚ ቡድኑ‘ ምክር ቤቶቹ በመጠቀም ያልደገፉትንና ሃሳቡ ያልተቀበሉት የመንግስት ሹመኞች ጥላሸት ለመቀባትና ከሃላፊነት ለማውረድ የሚያደርገው ጥረት መቆም አለበት ሲል አስጠንቅቋል።

ምክር ቤቶቹም ይህንን የመንግሰትና የፓለቲካ ድርጅት የሚቀላቅል ህገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት ማውገዝ አለባቸው ብሏል።

„ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ህግና ስርዓት ለማስከበር ሲባል ወደ ህጋዊ ተጠያቂነት መሸጋገር የግድ ይሆናል „ በማለት አክለዋል።  

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ከቀናት በፊት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ  ያወጣውን የአቋም መግለጫ የሚቃወም መግለጫ  አውጥቷል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት መስከረም 14/2017 ዓ.ም ያወጣው  ባለ 4 ነጥብ የተቋውሞ መግለጫ ፤ „ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጊዚያዊ  ስራዎች ለመስራት መቋቋሙ ተዘንግቶ ከተቀመጠለት የቆይታ የጊዜ ሰሌዳ በላይ እንዲቆይና ራሱን ወደ ተሟላ የመንግስት ሃላፊነት  ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ፀረ ዴሞክራሲና ኢ-ህገመንግስታዊ ነው „ ብሏል።

ምንም እንኳን „ ኢ-ህገመንግስታዊ „ ብሎ ቢገልጽም የአገር ወይም የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀፆችን አላጣቀሰም።

የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ቡድን „ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ተልእኮ ወደ ጎን በመተው ህወሓት ለማፍረስ ፣ ሰራዊት ለማዘዝና የመንግስትና ህዝብ ሃብት በመጠቀም የትግራይ ህዝብ አንድነት ለመበተን እየሄደበት ያለውን የተሳሳተ መንገድ ሊያቆም ይገባል „ ሲል አሳስቧል።

INFO - 24

25 Sep, 14:00


https://t.me/empirebot/game?startapp=hero1936519657

በዚህ BOT ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ትሰራላችሁ ሞክሩት ወዳጆቼ🙏

INFO - 24

25 Sep, 07:21


እንዴት አደራችሁ ምእመናን!
"የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የተለየ የቤተክርስቲያን ሕግ በማፅደቅ መሰረቱን አርቆ እየተከለ መሆኑን ሰማን!

በእውነቱ አንዳንድ ትውልዱን አንቆ የያዙት ሕጎችም አብሮ እንደምሻሻሉና ፈር እንደሚቀዱ ተስፋ እናደርጋለን!

INFO - 24

24 Sep, 06:02


#በትግራይ ጦርነት በታወጀበት ወቅት ግርር ብለው አገልግሎት ለሰጡ ተሽከርካሪዎች መንግሥት ያልከፈለውን 300 ሚሊዮን ብር እንዲከፈል ባለሀብቶች ለትራንስፖርት ሚንስቴር አቤቱታ ቢያቀርቡም መንግስት " እግር ብሉ " አላቸው ።😁

INFO - 24

23 Sep, 18:21


"እኛ ኢትዮጵያውያን ጭንብላሞች ነን/ ሰው መሳይ በሸንጎ"
~ በዓሉ ግርማ ~ የዛሬ 50 ዓመት ገደማ የቀይ ኮከብ ጥሪ ከሚለው መጽሐፋቸው የተወሰደ! 🤔
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
❝እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ። በጭንብል ተሸፍነን የምንኖር ህዝቦች ነን። ለሰው የምናሳየው ገፅታና እውነተኛው ባህሪያችን የተለያዩ ናቸው።

እንደ ተረታችን ፣ ስነ ፅሁፋችንና ንግግራችን ባህርያችንም ሰምና ወርቅ ነው ...

❝በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት መለኪያ የለንም ፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን የግል ጥቅማችን ነው።

ለዚህም ነው ተንኮል የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው ፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው።

ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው መርህ አንድ ብቻ ነው ፤ የግል ጥቅም! ከራስ በላይ ነፋስ ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል... ሰውን ማመን ቀብሮ ፥ ይሉታል ከነተረቱ። የሚያሳዝን ነው...

❝ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን። ስንዋሽ ህሊናችንን ቅንጣት ታህል አይቆረቁረንም። እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል ?

❝ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን ፤ የስጋ ዘመድን አይለይም ቅናት ባህላችን ነው።

❝ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም።

የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም? በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው።

በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው። በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ ፣ ከምቀኝነት ፣ ከተንኮል፣ ከቅናት ፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም። መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው።

የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው። ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!

በዓሉ ግርማ ፥ የቀይ ኮከብ ጥሪ መጽሐፍ ፥ ገፅ 234 የተወሰደ!

INFO - 24

23 Sep, 16:58


#ሶማሊላንድ #ግብፅ ወደ ሞቃዲሹ  ከባድ የጦር መሳሪያ ማስገባቷን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ ሰጠች‼️

የሶማሌ ላንድ መንግስት ግብፅ ለሶማሊያ የምታቀርበውን ከባድ የጦር መሳሪያ አሳሳቢነት በመግለጽ እርምጃው ቀድሞውንም ደካማ የነበረውን የቀጠናውን ደህንነት ይበልጥ አደጋ ላይ ይጥላል ስትል አስጠንቅቃለች።

የሶማሊላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ “በተለይ የሞቃዲሾ አስተዳደር በብቃት ለማስተዳደር ወይም ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም ስለሌለው የእነዚህ መሳሪያዎች ዝውውር በእጅጉ አስደንግጦናል ብለዋል።

ሶማሊላንድ በተጨማሪም ይህ የጦር መሳሪያ ዝውውር የአፍሪካ ቀንድን ወደ አልተረጋጋ ቀውስ እና የጦር መሳሪያ እሽቅድምድም እድልን ከፍ እንደሚያደርግ አፅንዖት ሰጥታለች።

INFO - 24

23 Sep, 16:58


ዜና: #ግብጽ በግዙፍ ወታደራዊ መርከብ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለሶማሊያ ማድረጓ ተገለጸ

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ከባድ መሳሪያዎች እና ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎች የጫነ የግብጽ ግዙፍ ወታደራዊ የጭነት መርከብ #ሞቃዲሾ ወደብ መድረሱ ተገለጸ።

በቪዶዮ በማስደገፍ በርካታ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ባሰራጩት ዘገባ አንድ የግብፅ ወታደራዊ ጭነት መርከብ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሳሪያ በሞቃዲሾ ወደብ ትላንት መስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም ማራገፉን አመላክተዋል፤ ወታደራዊ መርከቡ ጭነቱን እንዲያራግፍ በሚል ወደቡ ለንግድ መርከቦች ዝግ ተደርጎ እንደነበርም ጠቁመዋል።

ይህ የግብጽ እንቅስቃሴ #በሶማሊያ የምታደርገውን ወታደራዊ ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱን ያሳያል ያሉት መገናኛ ብዙሃኑ ውጥረት በሰፈነበት የአፍሪካ ቀን ላይ ስጋት የሚያጭር ነው ሲሉ ገልጸዋል።

INFO - 24

23 Sep, 16:39


ሼር አድርጉላቸው

በሊባኖስ እና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ
ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ
በሊባኖስ፤ የቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤት የጥንቃቄ መልዕከት አስተላልፏል።

ፅ/ቤቱ "በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ እንዲሁም በቤይሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተጠናከረው ቀጥለዋል" ብሏል።

ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤቱ የሁኔታውን አሳሳቢነት ተረድቶ፣ የዜጎቻችን ደህንነት ለማስጠበቅ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን እየተከታተለ እንደሚገኝም አሳውቋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች ዜጎች እንድትወስዱ ሲል አሳስቧል።

1. በአብዛኛው የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይቻላሉ ተብለው ከሚታሰቡ ቦታዎች እራስን ማራቅ፣

2. ከሊባኖስ መንግስት የሚሰጡ መመሪያዎችን እና አቅጣጫዎችን መተግበር ወይም ማከበር፤

3. አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ የበለጠ እየከፋ የሚሄድ ከሆነ በቀጣይ የምንወስዳቸውን እርምጃዎችን ይፋ ስለምናደግ ከቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ የፌስ-ቡክ ፔጅ የሚለቀቁ መረጃዎችን በየጊዜው መከታተል፣

4. ማንኛውንም የከፋ ሁኔታ በሚገጥማችሁ ወቅት በቆንስላው ቀጥታ የስልክ መስመር +9615467166 እና በWhatsapp ቁጥር ማሳወቅ ጠቃሚ ይሆናል።

INFO - 24

23 Sep, 10:58


#ኢትዮጵያ አምባሳደሯን ጨምሮ ሌሎች ዲፕሎማቶች ላይ የተፈጸመውን የቦምብ ጥቃት አወገዘች

#ኢትዮጵያ በ #ፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ዲፕሎማቶች ላይ በ #ፓኪስታን የተፈጸመውን የቦምብ ጥቃት አወገዘች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በፓኪስታን ኺቤር ፓኽቱንኽዋ ክልል የተፈጸመውን “የሽብር ጥቃት” ታወግዛለች ብሏል።

ጥቃቱ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ በርካታ ዲፕሎማቶች ልዑክ ላይ መፈጸሙን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ዲፕሎማቶቹ የስዋት ግዛት ያለን ቱሪስት ስፍራ ለመጎብኘት በመጓዝ ላይ እያሉ መንገድ ዳር በተጠመደ ቦምብ ጥቃት እንደደረሰ ሮይተርስ ዘግቧል።

በተጠመደው ቦንብ ጥቃት ሁሉም ዲፕሎማቶች ጉዳት ባይደርስም ዲፕሎማቶቹን እየመሩ ከነበሩ የፖሊስ አባላት ውስጥ አንድ ኦፊሰር ህይወቱ ሲያልስ ሶስት ፖሊሶች ቆስለዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው በጥቃቱ ህይወቱ ላለፈው ፖሊስ መኮንን ቤተሰቦች፣ ለፓኪስታ ህዝብ እና መንግስት መጽናናትን ተመኝቷል።

INFO - 24

23 Sep, 09:45


ዜና: #የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር “የክልሉ የጸጥታ አካላት በስሬ ሁነው እየተመሩ ይሰራሉ” ሲል አስታወቀ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም አካሄድኩት ባለው መደበኛ ስብሰባ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ በመምከር ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ይፋ አድርጓል፤ ከውሳኔዎቹ መካከልም በክልሉ የሚገኙ “የጸጥታ አካላት እንደ አንድ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል” መሆናቸውን ጠቁሟል።

“አግባብነት ባለው ጥናት እና ምክክር እየተደረገበት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት እና በካቢኔው እየተመሩ በህግ እና በስርአት ተልዕኮ እየተሰጣቸው ይፈጽማሉ” ሲል አስታውቋል።

በትግራይ ክልል የተፈጠረው ችግር በህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ተደርጎ እየቀረበ ያለው ነገር ፍጹም የተሳሳተ እና የችግሩ ተወናዮች እንዲሁም አሰላለፋቸውን በሳተ መልኩ የቀረበ መሆኑን ህዝቡ በግልጽ ሊያውቅ ይገባል ብሏል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራዎቹን እና እንቅስቃሴዎቹን ለማሳለጥ ይረዳው ዘንድ በተለያዩ እርከኖች የሚያካሂደውን የሃላፊነት ምደባ እንደሚቀጥልበትም አስታውቋል፤ ይህ እንዳይካሄድ በማንኛውም መልኩ እንቅፋት በሚፈጥሩ አካላት ላይ በህጋዊ መንገድ መልክ ለማስያዝ እሰራለሁ ሲል ገልጿል።

INFO - 24

22 Sep, 20:47


ትግራይ ላይ ጦርነት እንደተከፈተ በመንግስት ተይዘው ለአራት አመት በእስር ላይ ቆይተው ሰሞኑን በውይይት እንዲፈቱ የተደረጉ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየሄዱ ባለበት ደብረታቦር ላይ በፋኖ ሀይሎች ታፍነው ለድርድር ገንዘብ እየጠየቁባቸው ይገኛል።
የታጋቾች ስም...
.
1 ኮሎኔል ብርሀነ ሀይሌ
2 ኮሎኔል ገብሩ ወልደማርያም
3, ሻምበል አርአያ ፍስሀ
4 ሻምበል ምሩጽ
5, 50/ አለቃ ዜናዊ ዮሀንስ

INFO - 24

22 Sep, 12:12


#የጦና ፈረሰኞች በዓሉን እያደመቁ ይገኛሉ ።

ታላቁ የዎላይታ ህዝብ ዘመን መለወጫ የሆነው Gifaataa/ጊፋታ በዓል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል ።

Hashshu gattes
#Yoo_Yoo_Gifaataa
❤️💛🖤