kewser Media_ከውሰር ሚድያ @kewsertubeofficial Channel on Telegram

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

@kewsertubeofficial


You Tube ላይ እንገኛለን👉👉https://youtube.com/@am2media1?si=r-fGZbnW47oDUtHA

kewser Media_ከውሰር ሚድያ (Amharic)

ከውሰር ሚድያ በቀን የወረደው እስር ቤት ሚድዮ ነኝ፡፡ የጠቅላላ ሚድያዎቹን በቀናችን እናመለከታለን፡፡ kewsertubeofficial ከተማ እንደ Youtube ብቻ ይገኛል፡፡ በቀን ከታች እናሳያለን፡፡ በድጋሚ ከውሰር ሚድያ እስር ቤት ሚድዮ ላይ ከድምፅ እንዲሰጥ እንዲረዳን መመልከት ነው፡፡ በመሆን አዲሱን መረጃዎቹን እንደገና ጠብቋት 👉👉https://youtube.com/@am2media1?si=r-fGZbnW47oDUtHA

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

11 Feb, 20:24


ጠቃሚ ጥቆማ
#ሼር_አድርጉት
በተለይ አዲስ አበባ ያላችሁ እና ታዳጊ የሆነች (ቢያንስ እድሜዋ 11 ያለፋት ) ተማሪ ሴት ልጃችሁን …

ምን ችግር አለው ህጻን ናት… በሚል መዘናጋት… በፋሽን ሰበብ ሰውነት አጋላጭ ልብስ አልብሳችሁ ወደ ሶሻል ሚድያ ባታወጧት አይን ባታስገቧት ጥሩ ነው …ትምህርት ቤትም ጓደኞቿ ጭምር እነ ማን እንደሆኑ ክትትል ብታደርጉ ሗላ ከመጸጸት ትድናላችሁ

👉አሁን ላይ አደገኛ ሰይጣን አምላኪ አውሬዎች …ከወትሮው በተለየ…ታዳጊዎች ላይ በተለይ ለጋ ጨቅላ ሴት ልጆች ላይ ትኩረት አድርገው በአደገኛና ለስላሳ እጅግ የረቀቀ ወጥመዳቸው አጥምደው ጉድ እየሰሩ ይገኛሉ…

👉በርካታ ለጋ ልጆችን ለቀናት አፍነው ወስደው እየሰወሩ …በሃሽሽ አደንዝዘው ህይወታቸውን አበላሽተው ይለቃሉ…ከዚያም ቤተሰብ ስለ ጉዳዩ ለማንም ትንፍሽ እንዳይል ከባድ ማስፈራሪያና ዛቻ ይሰነዝራሉ ያጨናንቃሉ

👉በየ ቤቱ ብዙ ጉድ ታፍኖ ተቀምጧል…በተለይ ብዙም ቤተሰብም ኢኮኖሚም የሌላቸው በተለየ ደግሞ ብቻቸውን ያለ አባት ልጅ እያሳደጉ ያሉ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ…እናቶች ከሚገመተው በላይ ፈተናቸው በዝቷል …ጥቃትና በደላቸውን እፍን አድርገው… ተሰብረው… ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው እየኖሩ ይገኛሉ 😥😥

አሏህ ይጠብቀን

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

06 Feb, 01:03


ትንሽ ጊዜ አጥቼ ሳልፅፍላችሁ ቆየሁ በዛዉም ለጥንቃቄ ይሆናችኋል !
እሁድ ቀን ነዉ ከሰአት አካባቢ ስልክ ተደወለልኝ እና አንድ ሰዉ አፕታሚል ወተት 2 ቁጥር 10 ፍሬ እንደሚፈልግ ነገረኝ ዋጋም ሳይከራከረኝ ተስማማን እቤት ነበርኩ 10 ላይሞላ ይችላል 8 ግን አለኝ በእርግጠኝነት አልኩት እሺ ይበቃኛል 8 አምጪልኝ ቤተል ወይም ተይዉ መኪና እልካለዉ አለኝ ብሩን አሁን ልላክልሽ ሲል አይ እቃዉን እንደሰጠዉልህ ትልካለህ ስለዉ እሺ አካዉንትሽን ላኪልኝ አለኝ እኔ ሞባይል ባንኪንግ ስላዘጋሁ (ስልክ ተሰርቄ ስለነበር አልተስተካከለም) የጓደኛዬን ላኩለት ከዛም እየተንቀዠቀዥኩ በታክሲ ቢሮ እስከምደርስ በመሀል የተላከዉ ሹፌር ደወለ ፒያሳ ነበር ቢሮዬ ከዛ ጠብቀኝ ደርሻለሁ ብዬዉ እሁድ ስለነበር ታክሲዉ ሰዉ እንዲሞላለት ቆሞ መጥራት ጀመረ በቃ ልቤ ተሰቀለ ወይኔ ተናዶ ተይዉ እንዳይለኝ በራይድ እንዳልሄድ ብር የለኝም ጨነቀኝ ከዛ በግድ ተነስቶ ሄድን እና ደረስኩ ስደዉልለት ሄጃለሁ አለ ያ የሚገዛዉ ሰዉ ደወለ እና ሌላ ራይድ ጠርቻለሁ አሁን ይደዉልልሻል አለኝ እሺ ትንሽ ቆየሁበት ያኛዉን ይቅርታ ምናምን አልኩ እና እቃዉን ይዤ ወረድኩ አገኘሁት ተቀባዩን ባለራይድ ከዛ እቃዉን ከኋላ አስገባሁ እና ከዛ ደዉዬ አሁን ብሩን አስገባ ሰጥቼዋለሁ አልኩት። እሺ ብሎ ትንሽ ቆየ ከዛ ሹፌሩን ሳያስገባልኝ እንዳትሄድ ቆይ እሺ አልኩትና ዉጪ ቆሜ ነበር የሆነ ነገር ነገረኝ በቃ ቢነዳዉስ ቆይ መኪናዉን ብዬ ዉስጥ ግቢ አለኝ እሱም ባጋጣሚ ከዛ ቁጭ አልኩ ሰዉዬዉም ደዉሎ አስገብቼልሻለሁ ላኪዉ በቃ አለ እሺ ብዬ ጓደኛዬ ጋር ደዉዬ ቼክ አርግ አልኩት አልገባም አለ ቆይ እሁድ ስለሆነ ይሆናል ደጋግመህ ቼክ አርግ አልኩት ቼክ አረገ የለም ከዛ ደዉዬ አልገባም ስለዉ ጮኸ እንዴ ከኔ ላይ እኮ ቆርጧል እንዴት እንደዚ ይሆናል ምናምን አለ ከፈለግሽ ስክሪንሻት ልላክልሽ አለኝ ላክልኝ ረጋ ብዬ ከዛ ላከ (ከታች አያይዘዋለሁ ለጥንቃቄ ይሆናችኋል) ከዛ አየሁት አንዴ ብቻ ደዉዬ ጓደኛዬ ጋር ቼክ አርገህ ካልገባ 951 ደዉል አልኩት እስከዛ በደንብ አየሁት የላከልኝን ነጭ ነገር ነዉ በዚ ላይ የወተቱ ዋጋ 27,200 ነበር እና ባንክ ኮሚሽን እና ቫት ይቆርጣል እዚኛዉ ላይ የለም 0 ነዉ ከዛ አሳየሁት ለሹፌሩ (በዚህ አጋጣሚ በጣም ነዉ የተባበረኝ አመሠግናለሁ ) ከዛ ደወለ ጓደኛዬ አልተላከም ብለዉኛል እቃዉን እንዳሰጪ እያለ ይጮሃል ትሸወዳለች ብሎ ስላሰበ ምክንያቱም በአንድ ወር ዉስጥ 2 ስልክ ነዉ የተሰረኩት እና አላገገምኩም ገና ከዛ ሹፌሩ ቆይ እኔ ልደዉል ብሎ ደወለለት ላዉድ አርጎ አስቆምከኝ እኮ አባት ላክላት እና ልሂድ እንጂ ሲለዉ ልኬላታለሁ እኮ ምናምን ብሎ ጮኸ እንደዉም አገናኘኝ አለዉ ያዉ ላዉድ ነዉ አዉራት አለዉ ከዛ እናት ልኬልሻለሁ እኮ ለምን አትልኪዉም አለ ብሩ ሳይገባ አልከዉም በስልክም 951ም ደዉዬ አልገባም እና ለምንድን ነዉ የምልከዉ አልኩት በቃ እሺ እኔ መጥቼ እንነጋገር እና ችግሩን እንፈታለን አንተ በቃ ሂድ የቆምክበትን እከፍላለሁ ብሎ እቃዬን አወረድኩ እላችኋለሁ እግዚአብሔር ረዳኝ እንጂ አስቡት በደሞዝ ነዉ የምሰራዉ የሰዉ ወደ 20ሺ እዳ አለብኝ 2 ስልክ ጥዬ ስራዬ ሁሉ ተበላሽቷል ድጋሚ 27ሺ ብር ባጣ ለዛዉም በዚ መንገድ መኪና ዉስጥ ገብቼ ነበር የምሞተዉ ስለዚህ ፈተናዉን እንደማልችል ስላወቀ እግዚአብሔር አሳለፈልኝ ከዛ ጓደኛዬ መጣ ቢሮ እና ደዉሎ ና እንጂ እየጠበቅንህ ነዉ ብርህ ተቆርጦብህ የለ እንተማመን እና ዉሰድ ሲለዉ ቆይ መኪና ተጋጭቶብኝ ነዉ እደዉላለሁ ብሎ ቀረ ከዛ ስክሪንሻቱንም ፎቶዉንም አጠፋ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

06 Feb, 01:03


ለጥንቃቄ ይሁናችሁ

ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪን የምትጠቀሙ ሁሉ

👉ያው ብዙ ግዜ ተደጋግሞ ቢነገርም ብዙ ሰው ስለሚቸኩል በተመሳሳይ መንገድ ብዙ ኪሳራ ይደርሳል ብዙ ሰው ይሸወዳል

ለማንኛውም አሁንም ቢሆን ተጠንቀቁ

ከታች ያለውን የአንዲት እህታችንን ገጠመኝ አንብቡትና ልብ ግዙ😅😍

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

01 Feb, 15:24


👆በርካታ ሰው ቦታው ላይ ቪድዮ ስራላን ባለው መሰረት እነሆ ቦታው ላይ ተገኝተን ተጨማሪ ማብራሪያ ይዘናል

ያለን ቦታ ውስን ነው እድሉ እንዳያመልጣችሁ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

30 Jan, 09:08


ሰበር ዜና
ሄልኮተርና አውሮፕላን ተላትሞ 19 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

2025 ገና ከጅምሩ ለአሜሪካና አሜሪካውያን ሞትና ሃዘን ውድመትና ኪሳራ ያጠላበት ሆኖ ቀጥሏል …

ከሎሳንጀለሱ አሰቃቂ ሃዘን ሳይወጡ እነሆ አሁን ደግሞ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ አውሮፕላንና ሄልኮፕተር ተላትመው 19 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

30 Jan, 07:08


ይህ የምንመለከተው መኪና ቦሌ ሚካኤል ሊነጋጋ 11:30 አካባቢ አራት ሆነው መንገደኛኝ ሀንግ ሰርተው ሲያመልጡ ከሲኖ ጋር ተጋጭተዉ ሶስቱ ሲያመልጡ ሹፌሩ ግን ተይዟል!! አንቀውት የነበረውም ልጅ እራሱን ስቶ የነበረ ቢሆን ግን ተርፏል።

እንዲህ አይነት ወንጀል በከተማችን እጅግ እየተበራከተ ነውና እባካችሁ በለሊት በእግር እየተጎዛችሁ በድንገት ወደ አጠገባችሁ የሚመጣ መኪና ወይም የሰዎች ብዛት ሲኖር ተጠንቀቁ በልልኝ!!

Via Driving in Addis

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

30 Jan, 07:08


ለጥንቃቄ በተለይ አዲስ አበባ ለምትኖሩ ምሽትና ንጋት ላይ በመኪና ከሚንቀሳቀሱ ዘራፊዎች ተጠንቀቁ

👇👇

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

25 Jan, 06:28


https://youtu.be/ifD160990ls

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

25 Jan, 00:31


ህይወት…የማለዳ ጤዛ
40 ነፍሶችን የበሉት ደቂቃዎች…

መቼም የአሏህ ስራ አጂብ ነው…

ሃሙስ ማለዳ
ተማሪዎች… ነጋዴዎች …አርሶ አደሮች …ባለ ጉዳዮች …ከ60 በላይ ሰዎች ከሰሜን ወሎ ዳውንት ኩርባ ከተማ በጥዋት ተነስተውና ተጉዘው…ደሴ ከተማ ገብተው ወደየ ጉዳያቸው ለመሄድ ቸኩለዋል…

የተረኛ አውቶብስ ሹፌርና ረዳትም በዚያ ጉዞ ከ60 ተሳፋሪ ሰው የሚገኘውን ገቢ…ደምረው የነዳጅና ምሳ ወጭ ቀንሰው የቀን ትርፋቸውን እያሰሉ ነው……በዚያ ጠመዝማዛ እጅግ አስቸጋሪ መንገድ ላይ ሰዎችን ተሸክሞ የሚጓዘውና የቴክኒክ ምርመራ በቅጡ ያልተደረገለት እድሳት የናፈቀው መለስተኛ የህዝብ መጓጓዣ አውቶብስ 28 ሰው ብቻ የመጫን ልክ እና ገደብ ቢኖረውም

…ሹፌርና ረዳቱ ግን ከ60 በላይ ሰው እንዲሸከም ያለ ይግባኝ በግድ ፈርደውበታልና በሰው ታጭቆ እያቃሰተ…ከመናኸሪያው ወጥቶ ወደ ደሴ መጓዙን ቀጥሏል…

ተፋፍጎ የታጨቀውና የተጫነው ተሳፋሪም… ገሚሱ በየ ራሱ ሃሳብ ተጠምዶ እኩሉም ወሬ ይዞ …ሌላውም ተኝቶ …ወዘተ ይጓዛል…

ሁሉም ተሳፋሪ የመዳረሻ እቅዱ ተመሳሳይ ነው…ደሴ…ነገር ግን ደግሞ ከመሃላቸው ማንኛው ሰው ደሴ ደርሶ ወደ ጉዳዩ ይሄድ ይሆን? …ማንኛው ሰው በድንገት እስከ ወዲያኛው በሞት ያንቀላፋ ይሆን…ማንኛውስ ወደ ሆስፒታል ይገባ ይሆን…አሏህ እንጅ እነርሱ አያውቁም…ግን በጋራ እየተጓዙ ነው

ከማለዳው 12:30
የሞት ቀጠሮ…
ከዋናው ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው "ሰጎራ" የተባለ ጠመዝማዛ ቦታ ላይ የሞት መንጋ አድፍጧል…ተልዕኮውን ሊፈጽም ተዘጋጅቷል…እነ ማንን ሊወስድ እንዳደፈጠ ከፈጣሪው ተነግሮታል …የሚወስዳቸውን ሰዎችም ለይቶ አውቋል…እነሱ ባያውቁትም ቅሉ

👉እናም የውሳው ሰአት ደቂቃና ሴኮንድ ደረሰና… 60 ሰው አጭቆ እያቃሰተ የሚንፏቀቀው አውቶብስ …መንገዱን ድንገት ለቀቀ …ሹፌሩ ታገለ…ግን አልቻለም…60ዎቹ ሰዎችም ተጯጯሁ …አማተቡ …ያ አሏህ አሉ…ተተራመሱ…አውቶብሱ …አልቆመም በገደሉ በኩል ወደ ጎን አጋድሎ ወደቀ…ብረቱ ጮኸ መስታወቱ ተሰባበረ…ያለ ማቋረጥ እያጓራ…ድንጋይ ጋር እየየላተመ…እየተገለባበጠ … እየተምዘገዘገ…ተራራማውን አስፈሪውን ገደል ጨርሶ ከታች የሚገኝ ሰፊ እርሻ ላይ ዘጭ ብሎ አረፈ …ጣዕር …ዋይታ…ለቅሶ…አስተጋባ…

ቀድሞ ያደፈጠው ሞትም…ለዚያን ቀን ቀጠሮ ለይቶ መዝገቡ ላይ ያሰፈራቸውን ሰዎች ያውቃልና…ከ60ዎቹ ውስጥ እገሌ እገሌ እገሌ ብሎ…መርጦ የ40ዎቹን ነፍስ ይዞ በድናቸውን እዚያው ትቶ ከነፈ …

ቀሪዎቹና መሰል እጣቸው መችና የት በምን ሁኔታ እንደሚደርስ ያላወቁቱ…ለግዜው በመቁሰል ብቻ የተረፉቱ ደግሞ መዳረሻቸው …ሳይሆን ተመልሰው ወደ መጡበት ከተማ ሆስፒታል ሆነ…

አዲዮስ…ተፈጸመ 😥😥

ይህ የሆነው ትላንት ሃሙስ ማለዳ አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ ኩርባ የተባለው የገጠር ከተማ አቅራቢያ ነው …

👉ዱንያ እንዲህ ናት …ህይወትም እንዲሁ…የጥዋት ጤዛ…መነሻዋን እንጅ መድረሻ ቀኗን የማታውቅ …ባተሌ …ሞትም እንዲህ ነው …ሁሌ አዲስ…

አሏህ መጨረሻችንን ያሳምረው

ሙሐጅሩ መሃመድ አቡ ከውሰር

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

24 Jan, 19:11


አዲስና አደገኛ ሌላ ተጨማሪ እሳት አሜሪካ ላይ ተከስቷል …ወዲህም በርካታው አካባቢ በከባድ በረዶ ተወሯል …በዚህ ወቅት አሜሪካ ፈተናው መቅሰፍቱ በዝቶባታል
https://youtu.be/nHf9UoV4u7c
ከቆይታ ቡሃላ ወሳኝ መረጃዎችን ይዘን እንመጣለን kewser Mediaን ሰብስክራይብ ላይክና ሼር በማድረግ ወዳጅ ቤተኛ ይሁኑ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

24 Jan, 11:28


የሰው ስጋን የከተፈው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት

#Ethiopia | ፀሃዬ ቦጋለ በየነ የተባለ ተከሳሽ ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኋላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት እራሷን እንድትስት ካደረገ በኋላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራሷን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት በማስገባት አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ ሽንት ቤት ውስጥ በመጨመር የቆረጠውን እግሯ ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ 30/12/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ከቆየ በኋላ ከ1/13/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/1/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ በመሰወሩ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ539/1/ሀ/ መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሒደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነ የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የወሰነውን የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ በመሻር ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡#የፍትህ ሚኒስቴር

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

24 Jan, 11:28


ማሳሰቢያ🚨
ከዚህ በታች የሚፖሰተው የወንጀል ታሪክ አስፈሪና ዘግናኝ ስለሆነ እንዲህ ያለ መረጃ ማንበብ የማትወዱ ወዳጆቼ እለፉት 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

23 Jan, 16:47


👆👆አዲስ አበባ መሳለሚያ ላይ ለመኖር ምቹ ቦታ እንዳያመልጣችሁ ፈጥናችሁ ደውሉ

👉90 ካሬ ባለ ሁለት መኝታ ምቹ ቤት

  👉የጋራ 20 ቤቶች ባለ መብትነት

  👉ቋሚ የገቢ ምንጭ የሚሆኑ የጋራ ሱቆችን ባለ መብት ለመሆን

ምቾት ሪል ስቴት ፈጥነው ይመዝገቡ…

ለበለጠ መረጃ
09 48 35 65 00

09 22 47 44 44

አልያም
09 60 04 91 91

ይደውሉ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

23 Jan, 06:44


https://youtu.be/nHf9UoV4u7c

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

22 Jan, 21:30


አሜሪካም እንደ አረብ ሃገር…መሆኗ ነው…የስደተኛ አፈሳው ፍርሃትና ጭንቀቱ…አሳሳቢ ሆኗል
የትራምፕ እብደት አሳሳቢ ሆኗል
ከዚህ ቀደም የስደተኞች አፈሳ አሳሳቢ የሚሆነውና የሆነው አረብ ሃገራት በተለይ ሳኡዲ አረቢያ ነበር… እነሆ አሁን ደግሞ ስጋቱና ውጥረቱ አሜሪካ ላይ ሆኗል
https://t.me/kewsertubeofficial/1822
የነጭ አክራሪ ብሄርተኛው ዶናልድ ትራም…ስደተኞች እየመረዙን ይገኛሉ ስለዚህ ሃገራችንን ለቀው ይውጡ ብሎ ተናግሯል…በተለይ ደግሞ በፈረንጆቹ ከ1998 ጀምሮ በፍርድ ቤት ውሳኔ ስራ ላይ የዋለው እና

👉"አሜሪካ ላይ የተወለደ ስደተኛ ሁሉ አሜሪካዊ ዜግነት ያገኛል"የሚለውን ትልቅ ህግ እሽረዋለሁ ማለታቸው …ብዙ ቤተሰቦችን ያፈርሳል በርካቶች ላይ ዱብ እዳ ሆኖ …አለማቀፍ ቀውስ ይፈጥራል ተብሎ ተሰግቷል

ሰውየው በዚህ ብቻም አላበቁም
… የምናባቱ የአለም ጤና ድርጅት ነው…ከዚህ ቡሃላ አምስ ሳንቲም አናቀምሰውም በሚል የአለም ጤና ድርጅትን ላሽ ብለው ፈርመዋል…

👉እርዳታ ብሎ ነገርም አይኖርም መጀመሪያ እኛ ጠግበን መብላት አለብን 😅 ጦረኝነትም በቃን …ወዘተ …በሚል ኢትዮጲያን ጨምሮ በርካያ ሃገሮች ላይ ትልቅ እርዳታ ሲያደርግ የኖረው USAID ከእንግዲህ እርዳታው ይቆማል …ወዘተ ብለዋል

ባጭሩ ትራም ይዞት የመጣው ከባድ መዘዝ በተዘዋሪ እኛንም የሚነካ ነውና አሏህ ያብጀው 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Jan, 22:54


👆🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Jan, 22:48


በተለይ አረብ ሃገር ሆናችሁ ህገ ወጥ ቤት እየገዛችሁ እየፈረሰ ኪሳራ ላይ ስትወድቁ የኖራችሁ ይህ እድል በተለይ ለእናንተ አዋጭ ነው …አንድ ሆናችሁ አቅማችሁ ካልቻለ እንኳን ሁለት ሶስት ሆናችሁ ህጋዊ ውል ተፈራርማችሁ ብትመዘገቡና ብትገቡ ትልቅ እድል ነው …አጋጣሚ በመሃል አቅማችሁ ካልቻለ እንኳን ምቾት ሪል ስቴት የእናንተን እጣ በወቅቱ ባለው ዋጋ እጥፍ አትርፎ ገንዘባችሁን ያስረክባችሗል …ግንባታው በ3 አመት ውስጥ ሲጠናቀቅ …አንድ ሰው 90 ካሬ ባለ ሁለት መኝታ ቤት ይደርሰዋል ከዚህም ባሻገር …ከተገነቡት ቤቶች ውስጥ 20ዎቹ የጋራ ንብረት ስለሚሆኑ ከነርሱም ላይ ድርሻ ይኖረዋል …

ይሄም ብቻም አይደለም
ግራውንድ ፍሎር ላይ እና 1ኛና 2ኛ ፎቅ ድረስ 3ቱ ወለሎች ለሱቅ እና ለባንክ የሚከራዩ 105 ሱቆች ይኖራሉ ከነዚህም ወርሃዊ ኪራይ ቋሚ የሆነ የወር ገቢ ያገኛል ማለት ነው …ይህ የሚሆነው ግን ቀድመው አሁኑ ተመዝግበው መሰአች አባላት ለሚሆኑት ብቻ ነው …ግንባታው ከተጀመረ ዘግይተው የሚመጡና የሚገቡ…የ20 ቤቶቹና የሱቆቹ ተጠቃሚ አይሆኑም…90 ካሬ ባለ ሁለት መኝታ ቤት ብቻ ያገኛሉ

👉በዚህ እድል መመዝገብ በራሱ ትልቅ እድልና ትርፋማ ያደርጋል ይፍጠኑ …ቪድዮው ላይ ባለው ስልክ ይደውሉ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Jan, 22:35


ሰላም ወዳጆቼ
በተለይ ውጭ ሃገር ሆናችሁ …አረብ ሃገራት አውሮፓና አሜሪካ ሆናችሁ …አዲስ አበባ ላይ ለመኖሪያና ለስራ ቦታ ምቹ የሆነ አካባቢ ላይ የመኖሪያ ቤት እንዲኖራችሁ የምትፈልጉና ቋሚ ንብረት ለመያዝ ሃሳብ ያላችሁ በሙሉ
ይሄ በአይነቱ ልዩ የሆነ እድል እንዳያልፋችሁ ፈጥናችሁ ተመዝገቡ

ምቾት ሪል ስቴት ደሴና አካባቢው ቤት ገንብተው በማስረከብ የተመሰገኑ ስመ ስጥ ባለ ሃብቶችና ኢንጂኔሮች የመሰረቱት ካምፓኒ ነው …አዲስ አበባ ላይ ይዘውት የመጡት ወሳኝ እድል ነው …

ተረጋግታችሁ ሳትጨናነቁ በየሁለትና ሶስት ወሩ በምትከፍሉት መዋጮ በጋራ ራሳችሁ የምትገነቡት የቤት ግንባታ እድል ነው

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች ያለውን አጭር ቪድዮ ተመልከቱት 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

17 Jan, 04:39


ተመልከቱ ይሄንን ጉድ

የአሜሪካ ካሊፎርኒያ ሎሳንጀለስ የሰደድ እሳት መቅሰፍት የፈጣሪ ቁጣ ዛሬ 10ኛ ቀኑን ይዟል…የእሳቱ ጉልበት አሁንም እንዳለ ነው

በዚህ ምድር ላይ በዲሞክራሲና ነጻነት ስም ብዙ ጸያፍ ሃጢያትና ወንጀል የሚፈጸምባት የአሜሪካ ምድር በተለየ ደግሞ ቀደምት ህዝቦች በመሬት መገለባበጥና በውሃ ስጥመት የጠፉበትን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት (ግብረ ሰዶማዊነትን) የሙጥኝ ብለው ተያይዘውታል

ጥቂት ፈሪሃ ፈጣሪ ያላቸው ሰዎች መኖራቸው እንዳለ ሆኖ ይህንን መሰሉን አደገኛ ወንጀል የሚፈጽሙ ከመብዛታቸው አንጻር የባለፈው ከወራት በፊት ያተራመሳቸው አደገኛ አውሎ ነፋስ ዝናብና ጎርፍ እንዲሁም የአሁኑ ሰደድ እሳት በርግጥ የፈጣሪ ቁጣ ነው ቢባል ማጋነን ይሆናልን???

በውስጣቸው ያሉትን ንጹሃን አሏህ በችሎታው ይጠብቃቸውና

ለማሳያ ያክል ከታች ያለውን እና ደይሊ ሜል በገጹ ያጋራውን ቪድዮ ተመልከቱና ታዘቡ 😢😢😓

https://youtu.be/-yfDESFOqGs

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

16 Jan, 02:59


ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተለይ አዲስ አበባና ዙሪያው ላይ የቤትና መሬት ጉዳይ ያለባችሁ ጉዳያችሁን በህጋዊ መንገድ ለማስጨረስ የባለሙያ እገዛ የምትፈልጉ ወዳጆቼ በዚህ በኩል በውስጥ አናግሩኝ ባለሙያ ጋር ላገናኛችሁ እችላለሁ
👉@Muh_3990

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

13 Jan, 22:57


መረጃ
#Ethiopia
ከሰአታት በፊት ሰኞ ጥር 5/2017 ምሽት 5:24 ላይ…በሬክተር ስኬል 4,8 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 17 km ርቀት ላይ ባለ ቦታ ተከስቷል ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎችም ከተሞች ላይ ተሰምቷል

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

13 Jan, 19:30


ሰላም ወዳጆቼ
የከውሰር ሚድያን ምርጫችሁ አድርጋችሁ ስለምትከታተሉን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን …በዚህ ሁለት ቀን የሰራናቸው ዜናዎች በyou tube በመቶ ሺዎች እይታን አግኝተው በሁለቱ ፕሮግራሞች ብቻ ከ6ሺህ በላይ አዳዲስ ወዳጆች ቻናላችንን ሰብስክራይብ አድርገው ተቀላቅለውናል…

በሁለት ቀናት ውስጥ ይህን ያክል ከፍተኛ ቁጥር ያለው አዳዲስ ተከታይ ማግኘታችን በርትተን እንድንሰራ ሞራል ሆኖናል እናመሰግናለን ከልብ እናመሰግናለን 🙏

ዛሬም ያሰናዳነውን ወቅታቂ መረጃ ከቆይታ ቡሃላ ይዘን እንቀርባለን

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

12 Jan, 06:09


ይህንን ወሳኝ ፕሮግራም አድምጡት
ሙሉ ቪድዮው

👉 እዚህ ሊንክ ላይ
https://youtu.be/W2YxZvhNjI4

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

11 Jan, 15:10


በጣም ያሳዝናል ፈጣሪ ይፍረድባችሁ ከማለት ውጭ ምን ይባላል?? 😢😢

ከታች በፎቶው እንደሚታየው በአማራ ክልል በተለይም ሰሜን ወሎ አካባቢ ከፍተኛ ርሃብ መከሰቱ ይታወቃል …

ይህ ከባድ የርሃብ አደጋ ባለበትና ህጻናት አጥንታቸው አግጥጦ የሞት አፋፍ ላይ ባሉበት ተጨባጭ ላይ 😢😢

ከሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ 11 ቀበሌዎች ላይ …"ምክንያቱ ባልታወቀ"… በሚል አሳፋሪ ሽፋን የ154 ሚስኪን አርሶ አደሮች የልፋታቸው ውጤት የሰብል ምርት የሆነ 152 ክምር እህል በእሳት ተቃጥሎ ወድሟል 😥😥

ግምቱ 560 ኩንታል ይሆናል የተባለው የሰብል ክምር የወደመባቸው ሚስኪን ለፍቶ አደር ገበሬዎች ወደ 32 ሚሊየን የሚገመት የገንዘብ ኪሳራ ደርሶባቸዋል ማለት ነው በጣም ያሳፍራል

እርሃብና ድርቅ ህዝቡን እየፈጀ ባለበት በዚህ አስከፊ ግዜ የደረሰ ሰብል ማቃጠልና ማውደም ምን የሚሉት ሰይጣንነት ይሆን ከቶ??

አቃጣዮች ሆይ አሏህ የማትችሉትን እሳት በቁማችሁ ይልቀቅባችሁ አቦ 😥😥😥


👇
ከታች ያለው ምስል የተቃጠለው የእህል ክምርና በርሃብ እየተሰቃዩ ያሉት ህጻናትን ያመላክታል

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

10 Jan, 05:46


https://youtu.be/TNzjg71m1Wk?si=Idqe_wIyiXQts242

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

07 Jan, 17:36


😢😢 ሁኔታዎች አስፈሪ እየሆኑ ይገኛሉ ሁላችንም ወደ ፈጣሪ እንመለስ ወደ ጌታችን አቤት እንበል ነገሩ እንደ ቀላል የሚቆም አይመስልም

ከታች ያለውን ቪድዮ ተመልከቱት ለሌሎችም ሼር አድርጉት

👇👇

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

06 Jan, 04:07


https://youtu.be/bWPxShfGzTk

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

04 Jan, 12:56


👆👆በርካታ ቤቶችና መስሪያ ቤቶች በዚህ መልኩ ወድመዋል😥😥

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

04 Jan, 12:44


👆👆😢😢የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ አፋር ላይ የታየው አስፈሪው ክስተት

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

03 Jan, 20:11


ሰላም ወዳጆቼ

ሙሐጅሩ መሃመድ አቡ ከውሰር የሚለው ከ109 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ኦፊሻል የፌስ ቡክ አካውንቴን

2 ወር ከ15 ቀን በፈጀ አሰልችና አድካሚ ብርቱ ክርክርና ትግል ዛሬ ማስመለስ ችያለሁ …አልሃምዱሊላህ

ፌስ ቡክ ላይ ፎሎ በማድረግ ወዳጅ ቤተኛ ጓደኛ ይሁኑ ስል እጋብዛለሁ 🙏

https://www.facebook.com/share/p/15mtdTigfw/

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

03 Jan, 19:22


እናትነት
ናፍቆት
እዝነት 😥😥

ለእናቶች አባቶች ሲል አሏህ መከራ ጦርነትና ስደት ስቃይን በቃ ይበለን አቦ 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

03 Jan, 10:25


👆👆
በአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የተከሰተው እሳተ ገሞራ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

03 Jan, 10:24


መረጃ

አፋር ክልል የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰሞኑን በተከታታይ የተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ወደ ከባድና አስፈሪ እሳተ ጋሞራ እየተቀየረ ይገኛል

ሲታይ በጣም ያስፈራል

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

02 Jan, 14:54


ሰላም ወዳጆቼ በውጭ ሃገርም ሆነ ሃገር ቤት ሆናችሁ በግላችሁ ቤት እያስገነባችሁ ያላችሁና የግንባታ አማካሪ አጥታችሁ የተቸገራችሁ ወዳጆቼ

ዛሬ አንድ ባለሙያ ላስተዋውቃችሁ ነው ከታች ያለውን ቪድዮ ተመልከቱና ደውሉለት 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

25 Dec, 20:25


ይሄ ወሳኝ እድል እንዳያመልጣችሁ በተለይ አረብ ሃገር ሆናችሁ ሃገር ገብቼ ምን ልስራ በሚል የተጨነቃችሁ እህትና ወንድሞች ሁለት ሶስት አራት ሆናችሁ በዚህ ማህበር ውስጥ ብትገቡና ግንባታ ብትጀምሩ ትልቅና አዋጭ አትራፊ እድል ነው…

ምዝገባውን ተመዝግባችሁና ግንባታውን ጀምራችሁ ለመቀጠል አቅም ቢያጥራችሁና አትርፋችሁ ለመሸጥ ለመለወጥ ብትፈልጉ …ምቾት ሪል ስቴት ሁኔታዎችን ያመቻችላችሗል …

ያለን ቦታ ውስጥ ስለሆነ ፍጠኑ

ቦታው ተዘጋጅቶ የግንባታ ፈቃድ ተጨርሶ ቁፋሮ ተጀምሯል …በቀጥታ ወደ ስራ ነው…

ኢንሻ አሏህ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን በlive እንሰጣለን

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

25 Dec, 19:42


ይሄ እድል እንዳያመልጠዎ
     ይፍጠኑ


   👉ምቾት ሪል ስቴት ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ …አዲስ እና ልዩ ብስራት ይዞ ብቅ ብሏል …

እስካሁን ያልታየ እና አዲስ ወሳኝ እድል ከምቾት ሪል ስቴት

የግንባታው ቦታ
👉 አዲስ አበባ …በመሃል መሳለሚያ የንግድ የትምህርትና የጤና ተቋማትን ታሳቢ ባደረገ ምቹ ቦታ ላይ
 
👉ለአንድ ሰው
120 ካሬ (የጋራ ሱቆችን እና የመኪና ፓርኪንግ ጨምሮ) ባለ ሁለት መኝታ ምቹና ዘመናዊ መኖሪያ ቤት

👉ከመሬት እስከ  ሁለተኛ ፎቅ ድረስ የሚገነቡ ሱቆች ላይ ከኪራይ ወይም ከሽያጭ …የጋራ ተጠቃሚት መብት ባለቤት ይሆናል ( ከሱቅ ኪራይ ያልተቋረጠ ቋሚ የገቢ ምንጭ ይኖረዋል )

👉 ከታች ቤዝመንት ላይ የጋራ የመኪና ማቆሚያ ለአንድ ሰው አንድ መኪና ማቆሚያ ( ፓርኪንግ ) ተጠቃሚ ይሆናል

በጣም የተለየው እድል ደግሞ
👉 ከሚገነቡት የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ለአንድ ሰው ከሚደርሰው 120 ካሬ (የጋራ ሱቆችን እና መኪና ማቆሚያን ጨምሮ)ባለ ሁለት መኝታ ምቹ መኖሪያ ቤት በተጨማሪ 20 ቤቶች የጋራ ንብረት ሆነው ለሽያጭ ይቀርቡና የሚገኘው ገንዘብ  ለማህበሩ አባላቶች ገቢ ሆኖ የቤታቸውን ግንባታ ወጭ ለመሸፈን ይውላል …ይህ በጣም ለየት ያለና እስካሁን ያልታየ ልዩ እድል ነው …ይፍጠኑ

👉የምቾት ሪል ስቴት የቤቶች ግንባታ ማህበር አባል ለመሆን በቅድሚያ የመግቢያ ክፍያው 1,5 ሚሊየን ብር ሲሆን …ቀሪውን የግንባታ ክፍያ ብር በማህበሩ አባላት ስምምነትና ውሳኔ መሰረት …በሶስት አመታት ውስጥ በየወሩ ወይም በየ ሶስት ወሩ እየከፈሉ ቤትዎን ሳይጨናነቁ ተረጋግተው በጋራ ራስዎ ይገነባሉ

ለበለጠ መረጃ
09 48 35 65 00
09 55 61 61 61

  ወይም
09 22 47 44 44
እንዲሁም
09 11 64 20 52
ይደውሉ

ቢሯችን አዲስ አበባ ፒያሳ ከኤልያና ሞል ገባ ብሎ ከቶሞካ ቡና ጎን
👉 ካንትሪ ታወር 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 ላይ ብቅ ይበሉ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

25 Dec, 19:42


ሰላም ወዳጆቼ

በተለይ አረብ ሃገርና አውሮፓ አሜሪካ የምትኖሩና ቤት ለመገንባት ያሰባችሁና ቋሚ ንብረት እንዲኖራችሁ የምትፈልጉ… እህትና ወንድሞቼ ይሄንን ልዩ እድል ተጠቀሙበት እንዳያመልጣችሁ

ከታች ቪድዮና አጭር ማብራሪያ አስቀምጫለሁ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

20 Dec, 20:21


የአዲስ አበባ ሌቦች አላህ ይይላችሁ
ዛሬ ጀሙ 1 የገጠመኝኝ አንድ አሳዛኝ ታሪክ ልንገራችሁ ከቢሮ ወጥቼ ወደ መኪናዬ እየሄድኩ መንገድ ላይ አንዲት ሴት ወድቃ አረፋ ደፍቃ ተመለከትኩ አውድቅ መስሎኝ ቶሎ ክብሪት ገዛሁና በአፍንጫዋ መሸተት ጀመርኩ ከዚያም ከ2 ደቂቃ ቡኋላ ነቃች ስትነቃ መጀመሪያ ያወጣችው ቃል ልጄ ሞባይሌ የሚል ነበር ከዚያ በቦታው ላይ ከመጀመሪያው ጀምረው ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎችን ሰለሁኔታው ስጠይቅ ልጇስ የት ነው ስል አሳዮኝ ልጇን ስመለከት የኦቲዝም ተጠቂ መሆኑን ሳይ በጣም አዘንኩ😭 ስለሁኔታው ሳጣራ ይች ሚስኪን ሴት ከቤት የወጣችው ልጇን ለማሳከም ነበር ግን አልሆነም አረመኔዎች እጅ ወደቀች ለህክምና የያዘቸውን 8ሺ ብርና ሞባይል ሰርቀው ከጦር ሃይሎች ጭነዋት አደንዝዘው ጀሙ 1 ላይ ከነታመሚ ልጇ ጥለዋት ሄደው እንደሆነ ነገሩኝ በጣም አዘንኩ ግን አስከመቼ ፖሊስስ እንደው በጠራራ ፀሃይ አንዲህ የተደራጀ ወንጀል የሚሰሩ ሰዎችን በዝምታ ማለፍ ከተያዙም በሳምንት መለቀቅ ለወንጀሉ መባባስ ትልቅ ሚና አለው እና እባካችሁ ተጠንቀቁ

ምስል google
© Ahmed Ebrahim Mohammed

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

20 Dec, 14:31


ከ2መቶ 78ሺህ ብር በላይ ከደንበኞች አካውንት በመቀነስ ለግል ጥቅሙ ያዋለ የባንክ የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
***                                                                                       
ተከሳሹ ግለሰብ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በሻሌ 72 አካባቢ ከሚገኝ የግል ባንክ ውስጥ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን ሆኖ በሚሰራበት ባንክ ውስጥ በተደጋጋሚ ከተለያዩ ግለሰቦች የባንክ ሂሳብ ወደ ግል ሂሳቡ በሞባይል ባንኪንግ እና በቀጥታ  በማስተላለፍ ሲጠቀም እንደነበረ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የበሻሌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።                                          

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር እስከ ዋለበት ጊዜ ድረስ ከ5 የባንኩ ደንበኞች ያለ ፈቃዳቸው ከግል ሂሳባቸው 2መቶ 78 ሺህ 6 መቶ 91 ብር ከ7 ሳንቲም (278.691.7 ) በጥሬ ገንዘብ ወጪ በማድረግ፣ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ እና በሞባይል ባንኪንግ በማስተላለፍ የወሰደ መሆኑ በምርመራ መረጋገጡን እና ተከሳሹ ያለ ምንም ተፅዕኖ በሰጠው የእምነት ቃል በተደጋጋሚ ድርጊቱን የፈፀመ መሆኑን ያመነ ሲሆን ድርጊቱ የኃላፊዎቹን አለመኖር በመጠቀም ለደንበኞች መልዕክት እንዳይደርስ ሲስተም ላይ የራሱን ስልክ ቁጥር በማስገባት በፈፀመው ወንጀል ክስ እንደተመሰረተበት ተገልጿል።                                

ተከሳሹ የአንደኛ የግል ተበዳይ ለወላጅ አባታቸው በባንክ ቤቱ በአካል ቀርበው ገንዘብ አስተላልፈው ሊሄዱ ሲሉ ስልኮትን ይስጡኝ ሞባይል ባንኪንግ እንዲጠቀሙ ላስተካክል  በማለት ተቀብሎ ለኃላፊው የግል ተበዳይ የስልክ ቁጥር መቀየራቸውን ዋሽቶ በመግለፅ አዲስ ስልክ ላይ መልዕክት እንዲደርሳቸው ጠይቀውኛል በማለት ኃላፊውን በማታለል የራሱን ስልክ በመሙላት ከ35ሺህ ብር በላይ ወደ ግል ሂሳቡ ያስተላለፈ እና የሌሎችን ግለሰቦችንም ስልክ ቁጥር በመቀየር የተጣለበትን ኃላፊነት ወደ ጎን በማለት በፈፀመው ወንጀል አንደኛ ከሳሽ ወደ ፖሊስ ጣቢያው ቀርበው ባመለከቱት መሰረት በቁጥጥር ስር ሊውልም ችሏል።                              

በግልም ሆነ በመንግስት ባንኮች ላይ ያሉ ኃላፊዎች በተገቢው የኮምፒተራቸውን ሚስጥራዊ ቁጥር  በመሰወር እንዲሁም በሰራተኞቻቸው ላይ ተገቢውን ቁጥጥር የማድረግ ስራ በመስራት ከደንበኞቻቸው የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል ሊሰሩ እንደሚገባና ህብረተሰቡም የባንክ ሂሳቡን ሲያንቀሳቅስ በስልኩ ላይ ምንም አይነት መልዕክት ካልደረሰው በአካል ወደ ባንኩ ቀርቦ ሊያመለክት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ  መልዕክቱን አስተላልፏል።

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

20 Dec, 14:30


ወዳጆቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን

ባንክ ቤት ላይ ገንዘብ አስቀምጣችሁ ቸክ ሳታደርጉ ረጅም ግዜ የምትቆዩ ወዳጆች ገንዘባችሁ ሊሰረቅ ይችላል በየግዜው ቸክ አድርጉ …ይህ የሁልግዜ መልዕክታችን ነው

ከታች ያለውን የጥንቃቄ መረጃ አንብቡት

👇👇

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

14 Dec, 12:16


በጂንካ ከተማ በመግደል ሙከራ የተጠረጠረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዉላ የወንጀል ምርመራ እየተጣራባት መሆኑን የከተማው የወንጀል ምርመራ ቡድን አስታወቀ ።
ተጠርጣሪ ወይዘሮ ሰብለወንጌል አብርሃም የተባለችው ግለሰብ ከ3ወር በፊት ከዳውሮ ዞን ከታርጨ ከተማ መናኸሪያ ተበዳይ ህፃን ይዲድያ ደነቀን ጨምሮ ሁለት ህፃናት ልጆችን ወደ ጂንካ ይዛ ማምጣቷን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኃላፊ ኢ/ር ጌታቸው ሽፈራው አሳውቀዋል ።

ህፃናቶች በዕለት ግጭት ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ወደ መነኸሪያ አከባቢ ስንቀሳቀሱ ተጠርጣሪዋ ህፃናቶችን አግኝታ ሥራ እኔ ጋር ትሠራላችሁ በማለት አባብላ ወደ ጂንካ ዩንቨርስቲ አከባቢ ባላት ሻይ ቡና መስሪያ ቤት ውስጥ አምጥታ እያስራች መቆየቷን የምርመራ ቡድኑ አስታውቋል ።

በቀን 2/4/2017 ዓ/ም ዕለቱ ዕሮብ በግምት ከምሽቱ 2:30 አከባቢ በጂንካ ከተማ በጤናአደም ቀበሌ አልጋ ቀጠና ልዩ ስሙ ዩኒቨርስቲ ሠፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ውስጥ ቀደም ሲልም ተጠርጣሪዋ ህፃናቶችን ስትበድል እንደቆየች የግል ተበዳይ አስረድታለች።

ተበዳይ አክላ ወደ ቤተሰብ እንሄዳለን በማለት ስጠይቁ አትሄዱም የወር ደመወዛችውንም አልከፍልም እያለች ማቆየቷን አሳውቃለች።

ከሰው ማሳ በምሽት እንጨት እናመጣለን በማለት ይዛ ሄዳ እንጨቱን ውሰጂ በማለት ህፃኗ እንጨቱን ልትወስድ ስትል ተጠርጣሪዋ ሰውዬው መጣ መጣ በማለት አደጋ ማድረሷን አሳውቃለች።

ተጠርጣሪዋ እንጨት አንሺ ብላ ስትናገር ህፃኗ ለማንሳት ዝቅ ስትል በእግሯ ጀርበዋ ላይ በመርገጥ መሬት ላይ ከጣለች በኋላ በህፃኗ ጀርባ ላይ በመቀመጥ በሻርብ አፏን አፊና ዝም በይ ሰውዬው እየመጣ ነው ድምፅ አታሰሚ እያለች ቤት ውስጥ የነበሬን ድንጋይ በማንሳት በህፃኗ መላ ፊቷ ላይ እየመታች መላ ፊቷ ቆስሎ ደም በደም ከሆኔ በኋላ ከቤቱ ግርግዳ ላይ እንጨት በማንሳት 3 ጊዜ ሰንዝራ ጭንቅላቷን መትታ ህፃኗ የለበሰችውን ጉርድ በማውለቅ ሁለቱን እግሮቿን በጉርዱ ካሰረች በኋላ

ተጠርጣሪዋ ይዛ በመጣችው ድንች መቁረጫ ብላዋ 3 ጊዜ ሰንዝራ በጀርባዋ ላይ ወግታ በጥርሷ እና በጥፍሮቿ ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ በጆሮዋ እና ጀርባዋ ስትቧጭር እና ስትነክስ ተበዳይ ህፃኗ ራሷን ስታ እንደነበር ተገልጿል ።

ተጠርጣሪዋ ሞታለች ብላ በማሰብ በአንሶላ ሸፍና ሙዝ ለማብሰል ተብሎ በተዘጋጄ ጉድጓድ ውስጥ ቀብረዋት የቤቱን ዙሪያ በሻራ ሸፍና ከለሊቱ 8፡30 ገደማ ወደ ተከራየችው ቤት በመሄድ ተኝታለች።

ተጠሪጣሪዋ በለሊት ሻንጣዋን ይዛ የጂንካ ከተማ መነኽሪያ መጥታ ያልሞላ መኪናን የ 4 ሰው ሂሳብ እከፍላለሁ ንዳልን ብላ ስትጨቃጨቅ ባለመኪናዎቹ ሳይሞላ አንወጣም ከፈለግሽ መጀመሪያ ዙር የወጣ መኪና አለ በሞተር መድረስ ትችያለሽ ስሏት በሞቴር እየሄደች እያለችበጂንካ ከተማ ፖሊስ በክትትል እና በጥቆማ ከሲንጋል መያዟን የምረመራ ቡድኑ ስገልፅ ተበዳይ አሁን ላይ አስቾካይ የህክምና እርዳታ እንድታገኝ መደረጉን ጭምር ገልፀዋል።

በግምት ይህ ዜና ከተዘገበቤበት 15 ቀን በፊት ከሦስቱ ህፃናት አንዱ የሆነውን ህፃን ዮሐንስ የተባለውን ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት አከባቢ ህፃኑን ወደ ቤተሰቦቹ እሸኛለሁ በማለት ከህፃናቶች መካከል የወሰደች ስሆን ነገር ግን ህፃኑ ወደ ቤተሰቦቹ መድረሱንና ያለመድረሱን በምርመራ እየተጣራ መሆኑንም ጭምር የምርመራ ቡድኑ አስታውቋል ።

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

14 Dec, 12:16


በጣም ያሳዝናል!!

የሃገራችን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ እርባና ቢስ በመሆኑ በየቀኑ የሚታየው የሚሰማው ወንጀል ሁሉ ይሰቀጥጣል !!

አሰቃቂ ወንጀል የፈጸሙ ገዳዮች ተያዙ ሲባል ብንሰማም ቅጣት ግን ሲፈጸምባቸው አይታይም …ወይም እዚህ ግባ የሚባል እስራት ይፈረድባቸዋል

ይህም በመሆኑ በየቀኑ አሰቃቂ ወንጀል ፈጻሚዎች እየተበራከቱ ይገኛል

ወዳጆቼ ከዚህ በታች ፖስት የማደርገውን መረጃ ተመልከቱት

👇👇

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

12 Dec, 02:02


https://youtu.be/W9c9rNdAU9g?si=awUFiejcHOp_4gKx

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

27 Nov, 19:39


👆👆
አስቸኳይና ወሳኝ መረጃ ነው ሁላችንም በፌስ ቡክና በቴሌግራም ግሩፖች ሼር በማድረግ እንተባበር

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

04 Nov, 15:21


ወዳጆቼ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን
ባጋጠመኝ ችግር ሳቢያ መረጃና ፕሮግራሞቻችን ተቋርጠዋል

ኢንሻ አሏህ !! አሏህ ፈቃዱ ከሆነ እንደገና በድጋሜ ወደ ተለመደው ስራችን እንመለሳለን !! ኢንሻ አሏህ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

02 Nov, 17:56


በቤሩት ሊባኖስ የሚገኙ በርካታ ሺህ ኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን እህት ወንድሞቻችን ከሚገመተው በላይ ከባድ ጭብቀት ርሃብና የሞት ስጋት ውስጥ ይገኛሉ …ሁላችንም በቻልነው ድምጽ እንሁናቸው …ሁላችንም እንደየ እምነታችን በዱዓና ጾለት እናስታውሳቸው

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

01 Nov, 20:49


https://youtube.com/live/EN4LZu_cvhQ?feature=share

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

01 Nov, 20:08


ዛሬ እዚህ ከባድ አደጋ ውስጥ ነበርኩ አልሃምዱሊላህ በአሏህ እዝነት ተርፌያለሁ
https://youtube.com/live/ZjOdkdTvppE?feature=share
Kewser Media ላይ ከደቂቃዎች ቡሃላ Live ጠብቁኝ ስለ ዛሬው አደገኛ አደጋ መነሻና ያደረሰውን አደጋ ዝርዝር መረጃ አዘጋጅታለሁ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

01 Nov, 11:38


ዛሬ አርብ ሰፈራችን እና ቤታችን አካባቢ ድንገተኛ ከባድ የእሳት አደጋ ደረሶብናል

አልሃምዱሊላህ እኛ ተርፈናል በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

31 Oct, 23:20


ማስታወቂያ
የስራ You Tube ቻናል ሞኒታይዝ የሆነና ገንዘብ እየሰራ ያለ You tube ቻናል መግዛት የምትፈልጉ በውስጥ አናግሩን 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

31 Oct, 21:13


በተደጋጋሚ እየተናገርን ነው አሁንም አንሰማም ያሉ ሰዎች እየተሸወዱ እየተጭበረበሩ ነው …

በኦንላይን በቴሌግራም ወይም በቲክቶክ የማታውቁት ሰው…ሎተሪ ደርሶሃል እጣ ወጣልህ …ትልቅ ትርፍ የሚገኝበት ስራ አለ አብረን እንስራ የሚሉ ሰዎች አጭበርባሪዎች ናቸው እባካችሁ ተጠንቀቁ

ይህንን ብዙ ግዜ ምናልባትም ለሁለትና ሶስት አመት ደጋግመን ብንናገርም አሁንም ዛሬም ድረስ ገንዘብ የሚበሉ የሚጭበረበሩ አሉ …በጣም ያሳዝናል ሰው እንዴት እየሰማ እየተነግረው ዘሎ ገብቶ ይበላል

ከዚሁ ጋር ሌላው በጣም የሚያናድደው ደግሞ …ሙሃጅሩ ስትናገር አልሰማ ብየ ብሬን ተበላሁ እባክህ እንዴት ላስመልስ?? የሚሉ ሰዎች በውስጥ ሲመጡ ሳይ ነው

ኧረ እናንተንስ ቆዳችሁንም በገፈፏችሁ አቦ !!

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

31 Oct, 14:09


ወዳጆቼ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን

በፕሮግራሞቻችን ላይ ሃሳብ አስተያየት ጥቆማና መረጃ መስጠት ለምትፈልጉ ሁሉ በዚህ ከታች ባለው የቴሌግራም ዩዘር ልታገኙኝ ትችላላችሁ

👉@Muh_3990

ይህ ከታች የሚገኘው ደግሞ የKewser Media ሁለተኛው ቻናላችን ነው

https://youtu.be/41HCoWM5YZ8
ተከታታይ የሆኑ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች በቅርቡ ይጀመሩበታል ሰብስክራይብ በማድረግ ወዳጅና ቤተሰኛ ትሆኑ ዘንድ የአክብሮት ግብዣችን ነው 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

30 Oct, 20:41


https://youtube.com/live/ZjOdkdTvppE?feature=share

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

30 Oct, 18:45


ሰላም ወዳጆች

በመላው አረብ ሃገራት አውሮፓና አሜሪካ የምትኖሩ እንዲሁም ሌሎች ቦታዎች ላይ ያላችሁ ቤተሰቦች ወዳጆች ሊያመልጣችሁ የማይገባ አንገባጋቢና ወሳኝ ልዩ መረጃ
https://youtube.com/live/KMCAoYhnP-k?feature=share
ከደቂቃዎች ቡሓላ በKewser Media ላይ Live ይዘን እንቀርባለን ጠብቁን 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

30 Oct, 16:30


👆ከመሰል አደጋ አሏህ ይጠብቀን👏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

30 Oct, 14:11


ሰበር መረጃ
አንጋፋው ንግድ ባንክ ከቀኑ 11 ጀምሮ በአዲስ አበባ የሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ የAtm ማሽን ግልጋሎት እንዲሁም በባንክ ቤቶች የሚሰጠው ግልጋሎት ሲስተሙ ተቋርጧል !!

በተደጋጋሚ የሲስተም መመታት እያጋጠመው ያለው ንግድ ባንክ የደንበኞቹ ስጋት ከሆነ ውሎ አድሯል

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

29 Oct, 21:10


የከውሰር ሚድያን
https://youtu.be/FM2dHpRejVs
ሰብስክራይብ በማድረግ ወዳጅና ቤተኛ ሆነው እለታዊ ሃገራዊና የውጭ መረጃዎችን ይከታተሉ 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

29 Oct, 20:52


ሰበር መረጃ
ሶማሊያ የኢትዮጲያን አምባሳደር በ72 ሰአታት ውስጥ ሃገሬን ይልቀቅና ይውጣ ማለቷ ተሰምቷል…ብሉምበርግ በድህረ ገጹ ላይ እንደዘገበውና …

የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትም በ X ( ትዊተር ገጹ ) እንዳስታወቀው… ከሞቃዲሾ በ72 ሰአታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ የተባሉት አምባሳደር አሊ ሞሃመድ አዳን ናቸው
ዝርዝሩን በመደበኛው የዛሬው ፕሮግራማችን ላይ እንመለስበታለን

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

24 Oct, 20:07


https://youtube.com/live/KMCAoYhnP-k?feature=share

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

24 Oct, 18:58


አስቸኳይ መረጃ አለኝ
በተለይም አረብ ሃገራት ሳኡዲ ዱባይ ኢማራት ኳታር ወዘተ የምትገኙ ሁሉ ከደቂቃዎች ቡሃላ kewser Media ላይ በLive ጠብቁኝ …አልሰማንም እንዳትሉ እንዳያመልጣችሁ
https://youtu.be/gVQldkSkHWU

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

24 Oct, 09:29


በሀላባ ዞን የምፈልጋትን ሴት ሌላ ሰው እንዲያገባት አድርጓል በሚል የገዛ ልጃቸውን በወንድሞቹ ያስገደሉ አባት በእስራት ተቀጡ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን በሰው ግድያ እና አስክሬን በማንገላታት ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች ላይ የእስራት ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

1ኛ ተከሳሽ ከድር ከማል ፣ 2ኛ ዱባለ ከድር  ፣ 3ኛ ከይራቱ ከድር ፣ 4ኛ አብድልፈታ መሀመድ የተባሉት ተከሳሾች ነዋሪነታቸው በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ መጃ ቀበሌ እንደሆነ ተገልጿል ። ሟች አባድር ከድር ከመገደሉ በፊት የ60 ዓመት እድሜ ያላቸው 1ኛ ተከሳሽ ከድር ከማል ለኔ የምትገባኝን ወ/ሮ ለይላ ከማልን ሟች ልጄ እኔ እንዳላገባት ከልክሎኝ ዘይኔ ሁሴንን እንድታግባ አድርጓል ። ነገር ግን ሟችን የሚገድል አንድ ልጅ አጣሁ እኔ ልጅም አልወለድኩም በማለት ልጆቹ ሟች ወንድማቸውን እንዲገድሉት ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ማድረጋቸው ተጠቁሟል ።

በዚህ መነሻነት የ1ኛ ተከሳሽ ልጅ የሆነው 2ኛ ተከሳሽ ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በአባቱ ንግግር በመነሳሳት በእናት የማይገናኘውን ወንድሙን ከማሳ ወደ ቤቱ እስኪ መለስ ድረስ በበቆሎ ማሳ ውስጥ ሆኖ እንደጠበቀው ተገልጿል ። በመቀጠል ሟችን አንገቱን ሁለት ጊዜ በዱላ በመምታት መሬት ላይ ወድቆ  ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በዚህም 1ኛ እና 2ኛ  ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት ተራ የነብስ ግድያ ወንጀል እንዲሁም 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ደግሞ መረጃ ለማጥፋት በሚል የሟችን ልብሱን በማውለቅ አስከሬን በመወርወርና በማንገላታት ወንጀል ዓቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል ። ክሱን ሲመለከት የቆዬው የሀላባ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰው እና የህክምና የሰነድ ማስረጃዎችን መነሻ በማድረግ በተከሳሾቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል ።

ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾችን በ12 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት የተላለፈባቸው ሲሆን አስክሬን በማንገላታት ጥፋተኛ የተባሉ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ደግሞ በአንድ ዓመት ከ10 ወር ቀላል እስራት ቅጣት ተላልፎባቸዋል ።

በአበረ ስሜነህ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

24 Oct, 09:29


ይሄንን ጉድ ተመልከቱ መቼም የደረስንበት ግዜ ይገርማል

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

24 Oct, 02:07


https://youtu.be/gVQldkSkHWU

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

23 Oct, 19:02


" አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ነው የደረሰው ፤ እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ' አዲሱ ገበያ ' አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መድረሱን ፖሊስ ጠቁሟል።

በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ገልጿል።

" እስካሁን በአደጋው የ1 ሰው ህይወት አልፏል " ያለው ፖሊስ " የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው " ብሏል።

ፖሊስ ከአደጋው ጋር የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገልጽም ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃል አሳውቋል።

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

23 Oct, 19:02


አሳዛኝ መረጃ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

23 Oct, 14:05


መንግሥት ዜጎችን ወደማይታወቅ ቦታ እየወሰደ ማሠር ያቁም - ኢሰመኮ

ኮሚሽኑ በማይታወቅ ማቆያ ሥፍራ ተይዘዉ ከተለቀቁ ሰዎች ጋር ያገኘዉን  መረጃ ጠቅሶ ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት  ሰዎች እየተገደዱ እንደሚያዙና በየማቆያዉ ሥፍራ የተለያዩ በደሎች እንደሚደርስባቸዉ አስታዉቋል።

ኮሚሽኑ ያነጋገራቸዉ አብዛኞቹ ከማቆያ ቦታ የተለቀቁ ሰዎች የሰሌዳ ቁጥር በሌላቸዉ መኪኖች፣  የደንብ ልብስ ወይም ሲቢል በለበሱ የመንግስት ታጣቂዎች እየታፈኑ እንደሚወሰዱ በየማቆያዉ ሥፍራ የተለያየ ግፍና በደል እንደሚደርስባቸዉ ገልፀዋል።

የመንግሥት የጦርና የፖሊስ ኃይላት አዛዦች ከያዟቸዉ ወይም ካስያዟቸዉ ሰዎች ወይም ከቤተ-ሰቦቻቸዉ ጉቦ እየጠየቁ፣ መክፈል የቻሉትን እንደሚለቅቁ መረጃ ማግኘቱንም ኮሚሽኑ አስታዉቋል።

በተለይም ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከ1 ወር እስከ ዘጠኝ ወር ታስረዉ የነበሩ 44 ሰዎች አንድም ጉቦ ሰጥተዉ አለያም በሌላ አጋጣሚ ተለቅቀዋል ሲል ኢሰመኮ በሪፖርቱ አመልክቷል።

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

23 Oct, 11:15


የአለማችን ወስላታው ባል አለም አቀፍ ትችት እያስተናገደ ነው 😅

ይህ በስም ያልተጠቀሰ ኤንዶኖዢያዊ ሰው የመኪና አደጋ ደርሶበት መላው አካሉ ከንቱ ሆኖበት ለ6አመታት የአልጋ ቁራኛ ሲሆን የአንዲት ሴት ልጅ ሚስቱ ነበረች ብቸኛዋ አጠገቡ የተገኘች ሰው …ዳይፐሩን በመቀየር ገላውን በማጠብ በማብላትና በማጠጣት ያለመሰልቸት ስታስታምመው ቆይታለት
ይህ ወስላታ ኤንዶኖዢያዊም ፈጣሪ አዝኖለት ከ6 አመታት ተስፋ መቁረጥ ቡሃላ ጤናው ተመልሶ ድኖ ሲነሳ የመጀመሪያ ተግባሩ ፈጣሪውን ከዚያም ከጎኑ ሆና ያስታመመችውን ሚስቱን ማመስገን ሲገባው ለክህደት ነበር የፈጠነው
ተንከባካቢ ሚስቱን በመፍታትና ከቤት በማባረር ሌላ አዲስ ሚስት አግብቶ አለምን ጉድ አስብሏል …ሁኔታውን የተመከቱ ሁሉ አይንህን ላፈር ሲሉ እርግማን ስድብና አለፍ ሲልም ዛቻ ሰንዝረውበታል …
የሰው ልጅ ባህሪ ይገርማል😢

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

23 Oct, 00:54


ሄዝቦላህ አምርሮ የቆረጠ ይመስላል እስራኤል በበኩሏ እንደ ዋዛ ዘላ የገባችበት የወረራ ጦርነት ጨቀጨቅ እየዋጣት እያስጨነቃት ይመስላል …ተመልሳ አትወጣ ነገር አርፍዳለች …ህዝቧን የፍርሃትና ጭንቀት እጣ እያደለችው ትገኛለች ሰላማዊ ኑሮ ከራቀ ከራርሟል 😅

ትላንት ምሽቱን ጀምሮ የእስራኤል በርካታ ከተሞች በሄዝቦላህ ሮኬቶች እየተመቱ ነው …ዋና ከተማዋ ቴላቪቭን ጨምሮ ሃይፋና ሌሎችም ከ60 በላይ ከተሞች የአደጋ ግዜ ደውል ደውለው …ህዝቤ ሆይ ምሽግ ያዝ …መሬት ያዝ …ተደበቅ… ራስህን ከሄዝቦላህ ጥቃት ጠብቅ ሲሉ በጩኸት ምድር ሰማዩን አናውጠውታል የሄዝቦላህ ሮኬት ፍንዳታ ድምጽ ጋር ተዳምሮም እራኤላውያንን የምጽዓት ቀን የተቃረበ ያህል በሽብርና ጭንቀት አራውጠዋቸዋል

ከሄዝቦላህ ጥቃት እጅግ አስገራሚው አለፍ ሲልም አስቂኙ ነገር ደግሞ😄 እስራኤላውያንን ከሚሳኤልና ሮኬት ጥቃት ይመክታል ተብሎ ብዙ ሲወራለት የነበረው …አይረን ዶም …የተሰኘው የሚሳኤል መከላከያ ምድብ በሄዝቦላህ የሮኬት ጥቃት ኢላማ መሆኑ ነው 😅

የጎላን ተራራን ተጠግተው የተመሰረቱት የዋቭና ኪላ ከተሞችም የሄዝቦላህን ሮኬት ከሰማይ አንጋጠው እያዩ ምሽቱን በፍርሃትና ጭንቀት አሳልፈዋል …

ብዙ የተባለለት የእስራኤል ጸረ ሚሳኤል መከላከያ ነሁልሎና ጀልፎ እንኳን ሌላውን ሊጠብቅ ራሱንም እያዳነ እንዳልሆነ የታዘበችው ወዳጇ አሜሪካ ታሃድ የተሰኘ እጅግ ዘመናዊ ሚሳኤልና ሮኬት መመከቻ ዘመናዊ መሳሪያን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል አስገብታለች ዘዋሪና ኻዳም 100 ወታደሮች ጋር

😅 አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒዮ ብሊንከንም እዚያው ናቸው ፈጣን በራሪ ጀታቸውን አክንፈው ቴላቪቭ ገብተዋል …ዋና የጉዟቸው ምክንያት የእስራኤል ደጋግሞ መጠቃት የፈጠረው ጭንቀትና ምጥ ነው …ቢባልም እሳቸው ግን ግዴላችሁም ጎበዝ ስለ ሰላም እና ተኩስ አቁም ብንመካከር ይበጃል ሲሉ ተደምጠዋል …

በአንድ በኩል ግፋ በለው እያሉ ትጥቅ አግዘው ስንቅ ቋጥረው እያታኮሱ ወዳጃቸው እስራኤል ዱላው ሲበረታባት ስለ ሰላም እንማከር እንጅ ጃል ! …ማለታቸው ጭንቀትና ተንኮል የወለደው ሴራ ለበስ ጥሪ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው
  ሲፋጅ በማንኪያ ሲበርድ በእጅ …ማለት አሁን አይደል 😅

ወዳጆቼ ሆይ …ፌስ ቡኬ ተወስዶብኛል እስካሁን አላስመለስኩ 😐

እናም
ከቢቢሲ ከcnn ከአልጀዚራ ከስካይ ኒውስና ከሮይተርስ ወዘተ የመረጃ ምንጮች አሰባስቤ ያዘጋጀሁት የእለቱ ዝርዝር መረጃ በተለመደው ሰአት እዚህ ቴሌግራሜ ላይና You Tube ላይ ይቀርባል ኢንሻ አሏህ ሼር በማድረግ አግዙኝ የፌስ ቡኩን ክፍተት በመሙላት አግዙኝ ቤተሰብ🙏

https://youtube.com/live/sTLmicF6-Sg?feature=share
  የkewser Mediaን ሰብስክራይብ ሼር በማድረግ ቤተሰኛ ወዳጅ ይሁኑ 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

22 Oct, 22:13


https://youtube.com/live/sTLmicF6-Sg?feature=share

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

22 Oct, 19:15


ከመርካቶው የምሽቱ ቃጠሎ ጀርባ ምንድነው ያለው ሴራ?? የጉዳቱ መጠን ምን ያህል ነው ምን ያህል ሰው ተጎዳ ……
በተመሳሳይ ሰአትና ቀን ባህር ዳርና ጎንደር ላይ በተመሳሳይ የገበያ ማዕከል ቃጠሎ ለምን? እንዴት??

የሚሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ከጥቂት ቆይታ ቡሃላ kewser Media ላይ Live እገባለሁ ጠብቁኝ 🙏

https://youtu.be/-gJUEQnZRAQ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

22 Oct, 11:06


በርካታ ወንድም እና እህቶች በአንድ ቀን ጀንበር ድንገተኛ ቅጽበት የአመታት ልፋታቸውን በሙሉ ያጡበት የመርካቶ ሸማ ተራ ቃጠሎ😥😥

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

22 Oct, 03:21


https://youtu.be/-gJUEQnZRAQ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Oct, 21:30


ሰበር መረጃ
እስራኤል ISO2 በተባለ ወታደራዊ ሚስጥራዊ ኮድ ስምሪቷ ኢራንን በድንገት ለመደብደብ አቅዳ የተዘጋጀችበት ሰነድ በአጋሯ አሜሪካ በኩል ሾልኮ እንዲወጣ እና እንዲጋለጥ በመደረጉ በአሜሪካና እስራኤል መካከል ከባድ ቅራኔ መፍጠሩ ተሰማ

ከባድ ጦርነት ውስጥ የተዘፈቀችው እና አስጨናቂ ውጥረት ውስጥ የወደቀችው እስራኤል ከሲቪሉ አስተዳደር ጎን ለጎን በወታደራዊ ኮማንድ ካቢኔ ጭምርም ለመመራት ግድ ብሏታል

ዛሬ በወጡ መረጃዎች ይሄው ከሲቪሉ ካቢኔ ጎን ለጎን የእስራኤልን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲወስን የተዋቀረው ወታደራዊ ኮማንድ ዛሬ ያደረገውን ስብሰባውን ያለ ውጤትና በከፍተኛ ሃሳብ ግጭት ያለ ስምምነት በትኗል

እስራኤል በኮድ ISO2 ሚስጥራዊ ኮድ ስምሪት የጥቃት እቅዷ 16 ያክል ጎልደን ሆራይዘን እና ከ40 በላይ ሮክስ የተሰኙ ከአየር ላይ የሚወነጨፉ ባላስቲክ ሚሳኤሎችን ለኢራኑ ጥቃት ያዘጋጀት ሲሆን …አየር ላይ ነዳጅ የሚቀበሉ በርካታ የውጊያ ጀቶችን እና ግዙፍ የነዳጅ ታንከር ያላቸው ለተዋጊ ጀቶቹ አየር ላይ ነዳጅ መውላት የሚችሉ KC-707 ግዙፍ ቦይንግ አውሮፕላኖችን እና ለተጨማሪ ሎጀአቲክ ስራ የሚውሉ G-550 ገልፍ ስትሪም ጀቶችን በተጠንቀቅ ላይ ማድረጓ ነው የተጋለጠባት

ተጨማሪ ትንታኔና ዝርዝሩን አሁን ከቆይታ ቡሃላ በሚለቀቀው የዛሬ ምሽት መረጃ መሰናዶ ይዘን እንቀርባለን ኢንሻ አሏህ

https://youtu.be/DL5zv-EouFQ

ከውሰር ሚድያን ሰብስክራይብ ላይክና ሼር በማድረግ ወዳጅ ቤተኛ ሆነው አለም አቀፍ መረጃዎችን ይከታተሉ 🙏

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Oct, 20:34


እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የቤካም ሸለቆ መንደሮችና የደሂየ ግዛቶች ላይ ከባድና ተከታታይ የአየር ላይ ጥቃት ሰንዝራለች …የጥቃቱ ኢላማ የንግድ ማዕከላትና ባንኮች መሆናቸውም ተጨምሮ ታውቋል …
https://youtu.be/DL5zv-EouFQ
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን በዛሬው ምሽት የkewser Media ላይ ይጠብቁን

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Oct, 18:31


በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለማጥፋት ሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣረ መሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አሳነች አበቤ አስታወቁ

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Oct, 17:04


አዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ ከባድ ቃጠሎ ተነስቷል 😥 አሏህ ይድረስላቸው

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Oct, 15:59


👉ከሌሎች ተጨማሪ ወሳኝ የውጭና የሃገር ውስጥ መረጃዎች ጋር ዛሬ ምሽት በከውሰር ሚድያ ይጠብቁን

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Oct, 14:25


ሰበር መረጃ
የፍልስጤሙ ሃማስ እስራኤልን ክፉኛ ተበቀላት…የእራኤልን ወሳኝና ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዧን ገደለባት መረጃው ተረጋግጦ ወጥቷል

እስራኤላውያን ቤት ሃዘን ነግሷል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ …መሪር ሃዘን ተሰምቶናል ልባችን ቆስሏል ብለዋል …

ውጊያን በሚገባ ያውቃል ተዋግቶ ያዋጋል የተባለለት የእስራኤል መከላከያ ሃይል 401ኛው ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ኤህሻን ዳቅሳ አሸልቧል !!

አስገራሚው ነገር ይሄው ኮሎኔል የሞተበት ቦታና ሁኔታው ከቀናት በፊት ሃማሶች የተገደለባቸው ወሳኝ መሪያቸው ያህያ ሲንዋር ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው
https://youtu.be/1EiiXAbw-IU
አስገራሚውን ክስተትና ሁኔታ ዝርዝር መረጃ በዛሬው ምሽት የkewser Media ዘገባችን ይጠብቁን

kewser Media_ከውሰር ሚድያ

21 Oct, 12:17


ሰበር ዜና
ፈቱሏህ ጉለን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ አዛውንቱ ሰው በቱርክ ተሞክሮ በከሸፈው አለም አነጋግሮ በነበረው መፈንቅለ መንግስት አስተባባሪነት በጠይብ ኤርዶጋን አስተዳደር ተከሳሽና ተፈላጊ ሰው ነበሩ
https://youtu.be/DL5zv-EouFQ

ዝርዝሩን በምሽት የkewser Media ይጠብቁን

21,649

subscribers

746

photos

162

videos