Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺 @drhaileleul Channel on Telegram

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

@drhaileleul


👨‍⚕️ MD | 🎓 3 Master’s Degrees | Health & Wellness Tips

🔹 ለህክምና እና ቀጠሮ ለማስያዝ ይሄን ተጭነዉ
👇👇
@drhaileleulmd ስም እና ስልክዎን ያስቀምጡ!

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ (Amharic)

እንችላለን ወይም ደህንነት እናቀመጥኩታለን? ይቅርታ አይሁን! የዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ ቡድን ከፍተኛ መረጃዎችን የሚሰጠንን አቶ እና ውድ ይሐንክን ለእኛ እመልከቱ። ስለዚህም, ብዙ አቶ እና ውድ ይሐንክናቸው አካባቢዎችን ይመልከቱ። እስከ መስከረም 0974013612 ብር ላይ ንዴት ይውላል። ህልሞ ለሁለትና ሌሎች መርከብዎች ከዚህ ታላላቅ ዓረቦች ይቀርባል። @drhaileleulmd ለማስቀም በሚያደርግን ስልክት ተጠቀሙ።

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

15 Jan, 17:30


🔎"ዶክተር ጥያቄ አለኝ???"

🔹ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ(Hepatitis B Virus)  ከተያዘ ሰው ወደ ጤናማ ሰው  እንዴት ይተላለፋል ?

- ጥንቃቄ የጎደለዉ ግብረስጋ ግንኙነት፣
- በወሊድ ወቅት ( ከእናት ወደ ልጅ)፣
- በደም ንክኪ እንዲሁም ከብልት በሚወጡ ፈሳሾች፣

- የጥርስ ብሩሽ በጋራ በመጠቀም፣
- የንቅሳት ወይም ሰውነትን ለመብሳት በሚያገለግል መሣሪያ፣

- በተገቢው መንገድ ከጀርም ያልጸዳ የሕክምና መሳሪያዎች (በህክምና ተቋማት)፣

- ምላጭ፣ የጥፍር መሞረጃ ወይም መቁረጫ በጋራ በመጠቀም (በተለይም በውበት ሳሎን)፣

- በቆሰለ የአካል ክፍል በኩል የደም ቅንጣትን ሊያስተላልፍ የሚችል ማንኛውንም ሌላ መሣሪያ በጋራ በመጠቀም።

🔹 የማይተላለፍባቸው መንገዶችስ?

- በትናንሽ ነፍሳት ወይም በሳል፣
- እጅ በመጨባበጥ፣ በመተቃቀፍ፣
- ጉንጭ ላይ በመሳሳም ፣
- ጡት በማጥባት ፣
- አብሮ በመብላትና በመጠጣት፣

🔹መከላከያ መንገድ አለው ?

ከላይ የተጠቀሱትን የመተላለፊያ መንገዶች ካስወገድን በቀላሉ መከላከል እንችላለን ።በተጨማሪ ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ በክትባት መከላከል ይቻላል።

    ⊰━━━━━━⊱🌸⊰━━━━━━⊰
        🙏🙏መልካም ምሽት🙏🙏
    ⊰━━━━━━⊱🌸⊰━━━━━━⊱

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

07 Jan, 05:50


“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።” (ሉቃስ 2፡11)

🌲 እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ።🌲

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

31 Dec, 13:37


በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መደረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ያውቃሉ?

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ከታች የተዘረዘሩትን ጥንቃቄዎች መተግበር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡

📌 በተለያየ ምክንያት ከቤት ውጭ ከሆኑ፦ ከዛፎች፣ ከሕንጻዎች፣ ከኤሌክትሪክ ምሦሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መሆን ይመከራል፡፡

📌 በቤት ውስጥ ከሆኑ፦ በበር መቃኖች፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ እንዲሁም ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች ፣ ከመስኮት አካባቢ መራቅ እና የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

📌 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

📌 መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ፦ የኤሌክትሪክ መተላለፊያ ምሦሶዎች፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌክትሪክ መስመር ምሦሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም እና መሰል የጥንቃቄ መንገዶችን መከተል እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ መክሯል፡፡

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

23 Dec, 17:36


ካንሰር ቢሆንስ!

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

15 Dec, 11:25


#ያሳስበን

ህፃናት የወሲብ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን ለመገመት የሚረዱ ምልክቶች


የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው ህፃናት በተደጋጋሚ የሚያሳዩት ምልክቶች ውስጥ የመገለል ስሜት ፣ ብቸኝነት ፣ትካዜ ፣ የተጋነነ አዲስ የፍርሀት ስሜት፣ የትምህርት ዉጤት እና ፍላጎት ማሽቆልቆል፣ ድሮ የሚወዱትን ቤተዘመድ ወይም የቤተሰብ አባል ሲመለከቱ የመረበሽ/የመደንገጥ ስሜት።

መሸሽ፣ መፍራት፣መራቅ፣ እንደ አዲስ የጀመረ ከመጠን ያለፈ ተደጋጋሚ ጊዜን ከአንድ የቤተሰብ አባል ጋር የማሳለፍ ዝንባሌ፣ ከቤተሰብ ኮብልሎ መጥፋት፣ የአደንዥ እፅ እና  አልኮል መጠቀም።

የማህጸን ወይም የፊንጢጣ መድማት፣ ለመሽናት እና አይነምድር ለመዉጣት መቸገር፣ የማህጸን አካባቢ መድማት፣ መሰንጠቅ እና መላላጥ።

የክብረ ንጽህና መገሰስ/መስፋት/ የቅርጽ መቀየር፣ የወንድ የዘር ፈሳሽ ወይም ጸጉር ብልታቸዉ አካባቢ መገኘት፣ የማህጸን ፈሳሽ እና ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮት፡ እና መሸብሸብ፣ ድሮ የሚቆጣጠሩትን ሽንት እና አይነምድርን በተደጋጋሚ ለመቆጣጠር መቸገር ወዘተ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

አብዛኛዎቹ ጥቃት የደረሠባቸው ህፃናት የደረሰባቸውን በደል የመናገር እድላቸው በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች በልጆዎ ከተመለከቱ ጉዳዩን በሚገባ ማስተዋል እና ለተጨማሪ ምርመራዎች ወደ ጤና ተቋማት መውሰድ ይገባቸዋል፡፡

#ያሳስበን
#ይሰቆረና
#Nu_haa_yaaddessu
#Ha_ina_wada_qusayso #let_us_be_concerned

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

14 Dec, 13:52


ጠቃሚ መረጃ

አልኮል መጠጥ

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

04 Dec, 08:22


የጆሮ ማዳመጫ (Earphones) የሚያስከትለው ጎጂ ውጤቶች!!

ከመጠን በላይ ድምጽ በጆሮ ሴሎች ላይ ዘላቂ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ይህም የድምፅ ማስተላለፊያ ዘዴን ያቋርጣል።

የጆሮ ማዳመጫዎች በጆሮዎቻችን ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩባቸው ጎጂ መንገዶች ጥቂቶቹ፡-

• በጩኸት የሚፈጠር የመስማት ችግር(NIHL)

• በጩኸት የሚፈጠር የጆሮ ህመም(Tinnitus)

• የመስማት ችግር

• ማዞር

• የጆሮ ኢንፌክሽን

• ከመጠን በላይ የጆሮ ሰም

ከማዳመጫዎች የሚመጣዉን የመስማት ችግር ለመከላከል

• የባክቴሪያ መከማቸትን ለማስቆም፣የጆሮ ማዳመጫዎችን በመደበኛነት ያፅዱ።

• የድምጽ መጠን ማስጠንቀቂያዎች አስፈላጊ ናቸው።

• እረፍት ይውሰዱ

• በመኪና፣ በአውቶቡስ፣ በባቡር ወይም በእግር ሲጓዙ የጆሮ ማዳመጫዎችን ከመጠቀም ይቆጠቡ።

ሼር በማድረግ ለሌሎች እንዲደርስ ያድርጉ!!

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

02 Dec, 06:53


በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ህፃን ያቤፅ ይባላል ። እድሜዉ 14 ሲሆን ሲወለድ በአንድ ኩላሊት ነበር ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ያለችዉም አንዷ ኩላሊት ሙሉ በሙሉ ደክሞ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በዚህ ምክንያት ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ እንዲታከም እና በአፋጣኝ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዲያደርግ ተወስኗል።

ቤተሰቦቹ ከአቅማቸዉ በላይ ስለሆነ  ከስር በተቀመጡ የባንክ አካዉንት እና gofund me የአቅማችሁን እንድታበረክቱ በትህትና እንጠይቃችኋለን።

Account Holder: Solomon Alemayehu

CBE: 1000057164143

Awash :01320037587500

Abyssinia bank:102845781

Cooperative Bank;1000072492677

Go fund me: https://gofund.me/698c8f50

Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺

22 Nov, 17:06


“RELIEF የተባለ መድኃኒት እንዳትጠቀሙ!”
- የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን

#Ethiopia | የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በሕገወጥ መንገድ ለገበያ ቀርቧል ያለውን “RELIEF የተባለ መድኃኒት ህብረተሰቡ ከመጠቀም እንዲቆጠብ” ሲል አሳሰበ።

መድሃኒቱ በህገወጥ መንገድ ገብቶ “በኢትዮጵያ ገበያ እየተዘዋወሩ መሆኑን ደርሸበታለሁ” ያለው ባለስልጣኑ “በመስሪያ ቤታችን ያልተመዘገበ በመሆኑ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ አይታወቅም” ሲል አስጠንቅቋል።

የዚህ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች በሚል በባለስልጣኑ ከተዘረዘሩት መካከል “የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ድካም፤ የእይታ መዛባት፤ መፍዘዝ፣ ራስ ምታት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመር” የሚሉት ይገኝበታል።

መድሃኒቱ ለረጅም ጊዜ መጠቀም “ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ” ብሏል።

ባለስልጣኑ በሕገወጥ መንገድ የገባ ነው ሲል የገለጸው “RELIEF” የተባለው መድኃኒት “በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው ይገመታል” ሲል በላከው መግለጫ አስጠንቅቋል።

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

06 Nov, 19:53


#ጥንቃቄ🚨

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት የጨቅላ ህፃናት እንዳይጠቀሙት የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት ኖቫርቲስ ፋርማ ሽዌይዝ AG/ Novartis Pharma Schweiz AG በተባለ የገበያ ፍቃድ ባለው የመድኃኒት አምራች ፋብሪካ የሚመረት ነው።

ቴግሬቶል (ካርባማዜፔይን) 100 mg/5ml Oral Suspension (OS) የተሰኘው መድኃኒት አብዛኛውን ጊዜ አጠቃላይ ለሚጥልና ከፊል መንቀጥቀጥ/ management of generalized tonic clonic and partial seizures ለማከም የሚያገለግል ነው።

ይሁን እንጂ የተጠቀሰው መድኃኒት በውስጡ በሚይዘው ፕሮፓይሊን ግላይኮል (propylene glycol) የሚባል ንጥረ-ነገር መጠን ምክንያት ለጨቅላ ሕፃናት ማለትም ከ4 ሳምንታት በታች ለሆኑ ሕፃናት ወይም በሶስት ወራት የመወለድ ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት ሊወስዱት እንደማይመከር ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

ይሁንና በዚህ ምርት ውስጥ ያለው መጠን በዚህ የማሳወቂያ መልዕከት ላይ ከተጠቀሱት ለጨቅላ ሕፃናት እና ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ ከደህንነት ገደብ በላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ነው ያለው።

ስለሆነም ይህንን መድኃኒት በጨቅላ ሕፃናት ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ መጠቀም ጉዳቱ ከጥቅሙ የሚያመዝን በመሆኑ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች መድኃኒቱን ለተጠቀሱት የእድሜ ክልል ከማዘዝ እና ከማከፋፈል እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

10 Oct, 11:59


#WorldMentalHealthDay

° "ሥራ የመስራት እድሜ ላይ ከደረሱ ስድስት አዋቂዎች አንዱ የአዕምሮ ጤና ችግር ያጋጥማቸዋል" - ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም

የ2024 #የዓለም_የአእምሮ_ጤና_ቀን በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል።

ከአለም ህዝብ 60 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በስራ አለም ላይ እንደሆኑ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

በስራ ላይ ካሉት ሰራተኞች ውስጥም ግማሽ የሚሆኑት የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥማቸው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዛሬው እለት የዓለም የአእምሮ ጤና ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።


ሰራተኞችን ለአእምሮ ጤና ችግር የሚዳርገው ምንድነው?

-  ዝቅተኛ የስራ ክህሎት፣ ችሎታ እና አፈፃፀም

- ከመጠን በላይ የሆነ የሥራ ጫና፤ የሰራተኞች እጥረት፤ አድልዎ፣ መገለል፣ ጥቃትና ትንኮሳ

- ረጅም፣ ያልተገደቡ እና ተለዋዋጭ የስራ ሰዓቶች

- አሉታዊ ድርጊቶችን የሚደግፍ ድርጅታዊ ባህል

- ከሥራ ባልደረቦች በቂ ድጋፍ አለማግኘት

- በቂ ያልሆነ ክፍያ፣ የሚጋጩ የሥራ ፍላጎቶች
የአእምሮ ጤና እንደሚያስከትሉ የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል።


ሰራተኞች የአእምሮ ጤና ችግር በሚገጥማቸው ጊዜም ሰዎችን ማውራት፣ ባለሙያ ማማከር ወይም እራሳቸውን ማረጋጋት እንደሚኖርባቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ ገልፀዋል።

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

28 Sep, 10:15


#እንድታውቁት🚨

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡

መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡

በዚህም ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

መድኃኒቱ ' ሻይንፋርም ' በተባለ የቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር (Artemether 80mg/1ml) የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ነው።

(የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

10 Sep, 18:14


🌼🌼 እንኳን ወደ 2017 ዓ.ም በሰላምና በጤና አሸጋገራችሁ! 🌼🌼

ዓመቱን ሙሉ ኖረው ይህችን ቀን ሳያዩ ትላንት የሞቱ አሉ። የኖርነው ስለፈለግን ሳይሆን ስለ ተፈቀደልን ነው።

ይህች ቀን ከሰው የምትሰጥ ብትሆን ኖሮ ባላገኘናት ነበር። እነዚያ የሞቱት በሞኝነት ፣ እኛ የቀረነው በብልጠት አይደለም::

መኖር የአንድ አምላክ ስጦታ ነው::

እንኳን ለዚህች ቀን አበቃን!

🌼 ዓመቱ የእናንተ ይሁን!🌼

🌼🌼🌼 2017 🌼🌼🌼

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

21 Aug, 18:04


አቦጊዳ ሮትራክት ክለብ ከብሄራዊ ደም ባንክ እና ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ለ65ኛ ዙር የደም ልገሳ ኘሮግራም በመስቀል አደባባይ በሚገኘው የቀይ መስቀል ማዕከል  የፊታችን እሁድ ነሀሴ 19 አዘጋጅቷል።

እርሶ የሚለግሱት ደም የ3 ሰዎችን ህይወት ያድናልና ለብዙ ታካሚዎች በህይወት መኖር የእናንተ ደም አስፈላጊ ነው።

ስለዚህ በዚህ ታሪካዊ ቀን ተገኝተው ደም በመለገስ በየጤና ተቋማቱ በተለያየ ህመም የሚሠቃዩትን ህጻናት እና አዋቂ ህሙማን ፣ ወላድ እናቶችን እንዲሁም በካንሠር ህመም የተጠቁ ወገኖችን ህይወት እንዲታደጉ ተጋብዘዋል።

#BloodDonation
#RACAbugida

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

16 Aug, 10:39


#Mpox_Update

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የዓለም የህብረተሰብ የጤና ሥጋት ተብሎ ከተበየነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፍሪካ ውጪ በስዊድን በበሽታው የተያዘ ሰው መገኘቱ ሪፖርት ተደርጓል።

የሀገሪቱ የህብረተሰብ ጤና ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የተያዘው ግለሰብ በሽታው ሪፖርት በተደረገበት የአፍረካ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ሲሆን አሁን ላይ በስቶክሆልም የማገገሚያ ሥፍራ ክትትል እየተደረገለት ነው ተብሏል።

ይህ በስዊድን የተገኘው የMpox ዝርያ  በአፍሪካ ሀገራት ሥርጭቱ የጨመረው  #ክላድ1 (Clade_1) ቫይረስ ዝርያ መሆኑ ተገልጿል።

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

30 Jun, 14:01


የጭንቅላት ካንሰር(Brain Cancer)

(በ ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

በአመት በካንሰር ምክንያት ከሚሞተው ሰው በጭንቅላት ካንሰር ብቻ 3% የሚያህሉቱ ህይወታቸውን ያጣሉ። ብዙ አይነት የ ጭንቅላት እጢዎች አሉ የተወሰኑቱ በፍጥነት ሲያድጉ የተወሰኑቱ ደሞ በዝግታ ያድጋሉ::

የካንሰር ሴሎች ቁጥራቸው ሲጨምርና በመጠንም ሲያድጉ ወደ ጤነኛው ሴል ይዛመታሉ::በተጨማሪ ጭንቅላት ውስጥ እብጠት በመፍጠር ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል::

የጭንቅላት ካንሰር ምልክቶቹ ምንድናቸው?

🔻ብዙ ጊዜ የመጀመሪያው ምልክት ሰውነት #ማንቀጥቀጥ(seizure) ነው::

🔻ከማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ጋር የሚከሰት ተደጋግሞ የሚመጣ #ራስ ምታት

🔻የ ዕይታ ለውጥ ፦ የምስል መደብዘዝ እና ለእይታ መቸገር

🔻የማስታወስ ችሎታ መቀነስ

🔻የሰውነት መስነፍ(paralysis)

🔻የባህሪይ ለውጥ ማምጣት

ለጭንቅላት ካንሰር የሚሆን ምርመራ አለ?

ኢሜጂንግ ከምንላቸው ውስጥ እንደ MRI እና CT SCAN በብዛት በሽታውን ለመለየት እንጠቀማለን::እንዲሁም ከ ኢሜጂንግ በኋላ እንደየ አስፈላጊነቱ የናሙና(Biopsy) ምርመራ ይደረጋል::

የጭንቅላት ካንሰር ህክምና አለው?

የተለያዩ የህክምና ዘዴዎች አሉት ከነዚህም ውስጥ ቀዶ ጥገና ፣ የጨረር ህክምና፣ ኬሞቴራፒ ይጠቀሳሉ።

ከ ህክምና በኋላ ምን መደረግ አለበት?

💠የካንሰር ሴሎቹ ድጋሚ እንዳይከሰቱ የህክምና ክትትል ያስፈልጋል::እንዲሁም በተጨማሪ ከሃኪሙ የሚሰጡትን የትኛውንም መልክት እና ትዕዛዝ መተግበር አስፈላጊ ነው::

እነዚህ ምልክቶች ከታዩ በቀላሉ በሽታው ስር ሳይሰድ የጤና ባለሙያዎችን ማማከር ብልህነት ነው::

https://t.me/DrHaileleul

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

26 Jun, 11:23


ለተመረዘ ሰው ምን ማድረግ አለብን?

🔹የሚጠጣ/ የሚዋጥ መርዝ (ምሳሌ፡ የቤት ውስጥ የፅዳት ፈሳሾች፣ ፀረ-ነፍሳትና ፀረ -ተባይ መድሃኒቶች ፣ የሥራ ቦታ ኬሚካሎች፣ መድኃኒቶች…ወዘተ)

•የህክምና ዕርዳታ እስከሚመጣ ድረስ ግለሰቡን በግራ ጎኑ አስተኝተው መከታተል ÷ ማስመለስም ሆነ ማንቀጥቀጥ ከተከሰተ ትንታ እንዳይፈጠር ይከላከላል።

•የተመረዘው ሰው ካስመለሰ ወይም በአፉ ውስጥ የቀረ መርዝ ካለ በጣት ላይ ጨርቅ በመጠቅለል የግለሰቡን አፍ ማጽዳት ይገባል።

•የመርዙ መያዣ ዕቃን በማንበብ ለድንገተኛ መመረዝ ማድረግ የሚገባዎትን መመሪያዎች ከያዘ በመከተል÷ የመርዙን ዕቃ የጤና ባለሙያ እስኪያየው ድረስ በቅርብ ማቆየት።

•ራሱን ለሳተ ሰው በአፍ ምንም ነገር አለመስጠት!

•ለሁሉም መርዞች በተለምዶ ‘ፈውስ ናቸው’ ተብለው የሚታሰቡ ማርከሻዎችን (እንደ ወተት ያሉ) አለመጠቀም!

🔹በፍጥነት ወደ ህክምና ቦታ በመዉሰድ የአንድን ሰዉ ህይወት መታደግ እንችላለን ።

www.doctorhaileleul.com

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

16 Jun, 12:47


በመላው ዓለም ሆናችሁ 1445ተኛውን የኢድ-አላድሃ (አረፋ) ክብረ-በዓል በማክበር ላይ ያላችሁ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ እንኳን አደረሳችሁ። አደረሰን።
ኢድ-ሙባረክ!

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

05 May, 05:54


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች!

እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

16 Apr, 13:25


ሻወር በየስንት ጊዜ ይወሰዳል?

የቆዳን ጤንነት ለመጠበቅ የሚመከረዉ ?

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

10 Apr, 06:35


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ::


ዒድ ሙባረክ

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

08 Apr, 15:28


ህፃኗ እንዲ እንድትሆን ጥፋቱ የማነዉ

ነፃነት ወይስ አግድም አስተዳደግ

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

07 Apr, 06:40


የሱስ ዉጤት

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

10 Mar, 12:05


ለተመረዘ ሰው ምን ማድረግ አለብን?

🔹የሚጠጣ/ የሚዋጥ መርዝ (ምሳሌ፡ የቤት ውስጥ የፅዳት ፈሳሾች፣ ፀረ-ነፍሳትና ፀረ -ተባይ መድሃኒቶች ፣ የሥራ ቦታ ኬሚካሎች፣ መድኃኒቶች…ወዘተ)

•የህክምና ዕርዳታ እስከሚመጣ ድረስ ግለሰቡን በግራ ጎኑ አስተኝተው መከታተል ÷ ማስመለስም ሆነ ማንቀጥቀጥ ከተከሰተ ትንታ እንዳይፈጠር ይከላከላል።

•የተመረዘው ሰው ካስመለሰ ወይም በአፉ ውስጥ የቀረ መርዝ ካለ በጣት ላይ ጨርቅ በመጠቅለል የግለሰቡን አፍ ማጽዳት ይገባል።

•የመርዙ መያዣ ዕቃን በማንበብ ለድንገተኛ መመረዝ ማድረግ የሚገባዎትን መመሪያዎች ከያዘ በመከተል÷ የመርዙን ዕቃ የጤና ባለሙያ እስኪያየው ድረስ በቅርብ ማቆየት።

•ራሱን ለሳተ ሰው በአፍ ምንም ነገር አለመስጠት!

•ለሁሉም መርዞች በተለምዶ ‘ፈውስ ናቸው’ ተብለው የሚታሰቡ ማርከሻዎችን (እንደ ወተት ያሉ) አለመጠቀም!

🔹በፍጥነት ወደ ህክምና ቦታ በመዉሰድ የአንድን ሰዉ ህይወት መታደግ እንችላለን ።

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

07 Jan, 08:03


🙏🙏መልካም በዓል🙏🙏

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

06 Dec, 07:27


ከሰሞኑን የኤችአይቪ መከላከያ መድሀኒት ተገኘ የሚሉ መረጃዎች ሲንሸራሸሩ ቆይቷል ።

ለመሆኑ ተገኘ ስለተባለዉ የኤችአይቪ መከላከያ መድሀኒት እዉነታዉ ምንድን ነዉ?

'pre exposure prophylaxis ' እንደ ስሙ አንድ ሰዉ ለኤችአይቪ ከመጋለጡ አስቀድሞ የሚሰጥ እና ኤችአይቪ በሰዉነት ዉስጥ ካለዉ ሰዉ ወደ ሌላኛዉ ሰዉ እንዳይተላለፍ እንዲሁም በሰዉነት ውስጥ እንዳይሰራጭ የሚያደርግ  መድሀኒት ነዉ።

በእንግሊዝ ሀገር  ከ24 ሺህ በላይ ሰዎች የተካተቱበት ጥናት መድኃኒቱ ውጤታማ መሆኑን አረጋግጧል።

የቅድመ-መጋለጥ መከላከያ (PrEP) መዉሰድ የሚችሉት እነማን ናቸዉ ?

ከኤችአይቪ ቫይረስ ነፃ ሆነዉ ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ PrEP ሊወስዱ ይችላሉ።

 እድሜያቸዉ ከ12 ዓመት በታች ለሆኑ አይሰጥም።

PrEP መውሰድ የማይችሉ እነማን ናቸዉ?

ኤችአይቪ ፖዘቲቭ የሆኑ(በቫይረሱ የተጠቁ)፣

ከባድ የጉበት ወይም የኩላሊት ችግር ያለበት ሰዉ ፣

ነፍሰጡር  እና ጡት የምታጠባ እናት፣

የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ለምሳሌ የካንሰር ህክምና ላይ ያሉ ፣

ሄፓታይተስ ቫይረስ ያለባቸው መዉሰድ የሌለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸዉ ።

መድሀኒቱ በዋነኛነት ለኤችአይቪ በሽታ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጥ እንጂ  ቀድመዉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ከቫይረሱ ነፃ የሚያደርግ መድሀኒት አይደለም።

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

11 Nov, 16:23


የወገብ ህመም (BACK PAIN)

(በ ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

በአማካኝ 80% የሚሆኑ ሰዎች ላይ በህይወታቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ የጀርባ ህመም ያጋጥማቸዋል::

🔹የወገብ ህመም በሽታ እንዴት ይከሰታል?

ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን 85% የሚሆነው የጀርባ ህመም መነሻው አይታወቅም ።
የወገብ ህመም ከብዙ ህመሞች ጋር ተያይዞ ሊመጣ ይችላል፦

የወገብ አጥንት መዛነፍ
የመገጣጠሚያ አካባቢዎች መቆጣት
የአጥንት መብቀል
የተለያዩ ኢንፌክሽኖች ጋር
አደጋ (መደብደብ፤ ምት ወዘተ)

🔸የወገብ ህመም ሲፈጠር ወደ ሀኪም መቼ ልሂድ?

የእግር መደንዘዝ ካለ ወይንም መስነፍ
ሽንትና ሰገራ የመቆጣጠር ችግር ካለ
ትኩሳት ካለ
ከዚህ በፊት የአጥንት መሳሳት ወይንም ካንሰር በሽተኛ ከሆኑ

🔸ህመሜን ለማስታገስ ምን ማድረግ አለብኝ?

ህመሙ በሳምንት ውስጥ ለውጥ ከሌለው የወገብ ህመም ሲፈጠር ቀላል የህመም ማስታገሻ በመውሰድ ማስታገስ ይቻላል::

🔹በሽታው ቶሎ እንዲተፋ ምን ማድረግ አለብኝ?

ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ያለውን ነገር ከሃኪሞ ጋር መማከር

ምንም ያህል ህመም ቢሰማዎትም እንቅስቃሴ ባደረጉ ቁጥር የወገብ ህመም የመሻል እድሉ እየቸመረ ይሄዳል፡፡
እንዲሁም እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ከበሽታው በፍጥነት የምስገገም እድሉ አላቸው::
ማሳጅ
የእንቅሳቃሴ ህክምና (ፊዚዮቴራፒ)

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

20 Oct, 15:19


ሰዎች ራሳቸውን ለምን ያጠፋሉ?

በ ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን

ራስን ማጥፋት ማለት አንድ ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ህይወቱን በራሱ ፍላጎት በተለያዩ ዘዴዎች ተጠቅሞ ራስን የመግደል ድርጊት ነው::

በአለማችን ከ 800,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ራሳቸውን በየአመቱ ያጠፋሉ(World health organization) 79% ራስን ማጥፋት የሚፈፀመው ደግሞ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ነው::

ከ15-19 የ እድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች ህይወታቸውን ከሚያጡበት ምክንያቶች መካከል ራስን ማጥፋት በ ሶስተኛ ደረጃ ይቀመጣል::

ራሳቸውን ከሚያጠፉበት መንገዶች ውስጥ 20% የሚሸፍነው ደግሞ ገዳይ መርዞችን በመጠቀም ነው።

🔹ሰዎች ራሳቸውን ለምን ያጠፋሉ?

አንዳንድ ግለሰቦች ራስን ማጥፋት  የሰይጣን ግፊት፣ የሞራል ግድፈት እንዲሁም ጥጋብ ይመስላቸዋል::

ነገር ግን ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረው ከከሸፈባቸው ሰዎች መካከል ለድርጊታቸው እንደዋና ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት ከዘጠና ፐርሰንት በላይ የሚሆኑት የጀርባ ታሪካቸው ሲጠና የአዕምሮ ህመም እንደነበረባቸው ጥናቶች ያሳያሉ::

🔸ራሳቸውን ለማጥፋት ተጋላጭ የሆኑ እነማን ናቸው?

ራሳቸውን ለማጥፋት ከሚሞክሩ ግለሰቦች መካከል ከ 90% በላይ የሚሆኑት  አንድ የአዕምሮ ህመም ሊኖርባቸው ይችላል::ከዚህ ዉስጥም 80% የሚሆነው የድብርት በሽታ(Major Depressive Disorder)ይሸፍናል::

በተጨማሪ:-

-ከልክ ያለፈ ጭንቀት
-ቋሚ የሆነ አካላዊ ህመም(የስኳር፣ የነርቭ ፣ የካንሰር ህመም )

-ብቻቸውን የሚኖሩ ፣ከሌሎች ሰዎች ድጋፍ የማያገኙ ፣ያላገቡ

-ከቤተሰብ አባል ዉስጥ ከዚህ በፊት ራሱን ያጠፋ ሰው ካለ

-ከዚ በፊት ራስን ለማጥፋት ሙከራ ያደረገ

-መጥፎ የህይወት ጠባሳ ያሳለፈ ( መደፈር ፣ጉልበት ብዝበዛ)

-እስረኞች

በአንፃሩ ተጋላጭነታቸዉ ይጨምራል ።

🔹ራሱን ለማጥፋት ያሰበ ሰው እንዴት ልናውቅ እንችላለን?

ከታች የተዘረዘሩት ግለሰቡ ራሱን ሊያጠፋ እንደሆነ  አመላካች ንግግሮች  ስለሚሆን ቤተሰብ ወይም የቅርብ ሰዉ ትኩረት ሊሰጥባቸዉ ይገባል:-

-ከፍተኛ የሆነ ተስፋ የመቁረት ስሜት እንዳላቸው አዘውትረው መናገር ፤

-ህይወት አሰልቺ እና አድካሚ እንደሆነ በተደጋጋሚ መናገር ፤

-ለቤተሰብ ሸክም እንደሆኑ ማሰማት፤

-ወደ መኝታ ሲሄዱ "ምነው ተኝቼ በቀረሁ"  ማለት፣

-"ምነው ፈጣሪ ህይወቴን በወሰዳት" የሚል ቃል ማዘዉተር ይጠቀሳሉ።

🔹ራስን ማጥፋጥ እንዴት መከላከል ይቻላል?

ከላይ የተጠቀሱት አጋላጭ ሁኔታዎች ካሉ እና ራስን የማጥፋት ሀሳብ በተደጋጋሚ የሚመጣ ከሆነ ወደ አዕምሮ ህክምና ተቋም በፍጥነት በመሄድ እና አስፈላጊዉን ምክር እና ህክምና በማግኘት መከላከል ይቻላል ።

7,458

subscribers

685

photos

12

videos