Good Christian Books Shelf @christiangoodbooks Channel on Telegram

Good Christian Books Shelf

@christiangoodbooks


This channel is created for the purpose of sharing good Christian books from the reformed Christianity world.

Good Christian Books Shelf (English)

Are you looking for inspiring and thought-provoking Christian books from the reformed Christianity world? Look no further than the 'Good Christian Books Shelf' Telegram channel! This channel, with the username @christiangoodbooks, is dedicated to sharing a curated collection of high-quality Christian literature that will deepen your faith and enrich your spiritual journey. Whether you are a seasoned reader or new to the world of Christian literature, this channel is perfect for anyone seeking meaningful and impactful reads. The 'Good Christian Books Shelf' channel is a treasure trove of books that cover a wide range of topics, including theology, Christian living, apologetics, and more. The carefully selected books showcased on this channel are written by renowned authors who offer valuable insights and perspectives on various aspects of the Christian faith. From classics by C.S. Lewis and John Calvin to modern bestsellers by Tim Keller and R.C. Sproul, you will find a diverse collection of books that cater to different interests and tastes. Whether you are looking to deepen your understanding of the Bible, explore theological concepts, or seek guidance on living out your faith in today's world, the 'Good Christian Books Shelf' channel has something for everyone. Each book featured on this channel is a testament to the power of literature to inspire, challenge, and transform lives. Joining the 'Good Christian Books Shelf' Telegram channel is like having your own personal library of Christian books at your fingertips. You can easily access book recommendations, reviews, and discussions that will help you discover new authors and titles to add to your reading list. Whether you prefer physical books or e-books, this channel provides a valuable resource for finding the next great read that will deepen your relationship with God and strengthen your Christian walk. Don't miss out on the opportunity to explore a world of Christian literature that will uplift your spirit and nourish your soul. Join the 'Good Christian Books Shelf' channel today and embark on a journey of discovery, growth, and inspiration through the power of words. Happy reading!

Good Christian Books Shelf

07 Dec, 18:31


የኔ ጽድቅ ግን ለብቻው በዛ🤣🤣

ባለፈው አንድ ሶስቴ የመሬት መንቀጥቀጥ ከተማችንን ሲሣለም ለኔ አንዴም ሳይታወቀኝ አጠገቤ ያሉ ሰዎች ሳይቀሩ መሬት አስነጠሰች ምናምን እያሉ ሲያወሩ ሰምቼ ጽድቄ በዛ ብዬ ተመክቼ ነበር። ዛሬ ደግሞ ማብራት በሃገሪቱ ሁሉ ጠፍቶ ……. እኔ ብቻዬን ላይቭ ገባሁ😁😁 @Reformed_think_tank

Good Christian Books Shelf

07 Dec, 06:15


“ያለ ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል; በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉምና. ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤ እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ። ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ በሰው ዘንድ የተሰወረውን በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።
አንተ ግን አይሁዳዊ ብትባል በሕግም ብትደገፍ በእግዚአብሔርም ብትመካ፥ ፈቃዱንም ብታውቅ ከሕግም ተምረህ የሚሻለውን ፈትነህ ብትወድ፤ በሕግም የእውቀትና የእውነት መልክ ስላለህ፥ የዕውሮች መሪ፥ በጨለማም ላሉ ብርሃን፥ የሰነፎችም አስተማሪ፥ የሕፃናትም መምህር እንደ ሆንህ በራስህ ብትታመን፤ እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን? አታመንዝር የምትል ታመነዝራለህን? ጣዖትን የምትጸየፍ ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህን? በሕግ የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታሳፍራለህን? በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባልና ተብሎ እንደ ተጻፈ።”
ሮሜ 2፡ 12/24

Good Christian Books Shelf

06 Dec, 16:17


አንድ የቅርብ ዘመዳችሁ በታላቋ ሃገር አሜሪካ ይኖራል ለአንዴ እንበል። አሜሪካ በሚኖርበት ቀን ሁሉ ወደ አዲስ ሲመጣ ደጋግሞ እንደሚጋብዛችሁ፣ በሚቆይበት ቀናት ሁሉ ከርሱ እንደማትለዩ፣ ሁሉንም ወጪ እርሱ ችሏችሁ በሃገራችን በቅርቡ የተሰሩ ፓርኮችን አብራችሁ እየሄዳችሁ እንደምትዝናኑ ተስፋ ሰጣችሁ ለሁለተኛ ጊዜ እንበል።
እናም በተባለው ቀን ወደ አዲስ መጣ ለሶስተኛ ጊዜ እንበል። ወደ አዲስ ከገባ በኋላ ለአንድ ወር እናንተን አላገኛችሁም፣ በመሄጃ ዋዜማ በሌላ ሰው ስልክ ደውሎ ነገ ወደ አሜሪካ ልመለስ ስለሆነ ምሳ ሊያበላችሁ ዕስካይላይት ሆቴል ወሰዳችሁ ለአራተኛ ጊዜ እንበል። አሪፍ ምግብ ተጋበዛችሁና ሂሳብ ከፈለላችሁ ለአምስተኛ ጊዜ እንበል።
ሂሳቡ አጠቃላይ አምስት ሺህ ብር ሆነና ይህ ዲያስፖራ ዘመዳችሁ ግን አስር ሺህ ብር አስቀምጦ ለአስተናጋጇ ቀሪውን አምስት ሺህ ብር ያዢ የአንቺ ነው አላት ለስድስተኛ ጊዜ እንበል። እናንተ ደግሞ እንደ አንድ ሃበሻ የ አምስት ሺህ ብር ምግብ በመብላታችሁ ራሱ ጸጸታችሁ ለሰባተኛ ጊዜ እንበል። ለምን ከተባለ በአምስት ሺህ ቢያንስ ለሁለት ቀን አሪፍ ምሳና እራት መብላት የምትችሉበት ከተማና ሁኔታ ውስጥ ስላላችሁ….. ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህ ዲያስፖራ ዘመዳችሁ በአይናችሁ እያያችሁ ላስተናጋጇ አምስት ሺህ ብር ከበላችሁት ምግብ ያላነሰ ብር በቲፕ ስም በመስጠቱ እርርር ብላችሁ በውስጣችሁ ፊል አደረጋችሁ ለስምንተኛ ጊዜ እንበል። ምግቡን ከበላችሁና እሳቡ ከተከፈለ በኋላ ዲያስፖራው ዘመዳችሁ እዛው እስካይላይት ተናግሮ የራይድ መቶ ብር እንኳን ሳይሰጣችሁ ሰላምታ ብቻ በመስጠት ሸኛችሁ ለዘጠነኛ ጊዜ እንበል. ከሁለት ቀን በኋላ አሜሪካ ከገባ በኋላ በቪዲዮ ኮል ደውሎ በዘመዳችሁ ውስጥ ካሉ ሰዎች መሃል በጣም በጠባዩና በሌሎች ምክንያት ከምትጠሉ ሰው ጋር ወሩን ሙሉ እንዳጠፋ፣ በገንዘብ ደረጃ ከአንድ ሚሊየን በላይ እንዳጠፋ ነገራችሁ ለአስረኛ ግዜ እንበል…….

የቪዲዮ ኮሉ እንደተጠናቀቀ በቀላሉ ተጽናንቶ ጉዳዩም እንዳልተፈጠረ ራሱን አሳምኖ ወደ ግል ስራው የሚመለሰው ማነው?
ካልቪኒስቱ፣ ሉተራኑ፣ አርሚኒያኑ፣ ሊብራሉ፣ ኤቲስቱ፣ መልካም ስነ ምግባር ያለው? 😁😁

Good Christian Books Shelf

06 Dec, 07:29


በስመአብ ከጠዋቱ ጀምሮ የሃዋዝን ቁጥር ሁለት አልበም እየሰማሁ አንዱን መርጬ መፖሰት አቃተኝ። ያው የመዝሙሮቹ ገጣሚው ጋሼ መላኩ (ማሜ ) ስለሆነ አንዱን ከሌላ መምረጥ ከባድ ያደርገዋል። ማሜ ከ1000 መዝሙሮች በላይ ለሆኑ ግጥም ያዘጋጀ እጅግ የተወደደ ወንድም ነው። እሱ የገጠማቸውን መዝሙር የሚበልጥብኝ የመዝሙር አልበም ሆነ በኮንቴንት ደረጃ ጥልቀት ያላቸው በኔ የህይወት ተሞክሮ አልገጠመኝም



በዚህም ስሪቴን እወቁልኝ😁 ስሪቴ ለእግዚአብሄር ብቻ የቀረቡ መዝሙሮቹን ከኦርቶዶክስ፤ ቲዮሎጂውን ከፕሮማክስ ወስጄ አጣጥሜ የምኖር ሰው ነኝ😀
በቃ ይህንን መዝሙር አድምጡልኝ። ማቅ ሲያስቸግራቸው በነበረ ጊዜ መቼ ነው? በሚለው መቃተት ውስጥ ሆኖ የዘመረው።

Good Christian Books Shelf

06 Dec, 06:47


ባለፈው ሮሜ ሁለትን እያጠናን ስለ እግዚአብሄር ባህርያት (attributes of God) በበለጠ መጸሃፍትን በማንበብ ንባባችሁን አዳብሩ ብዬ ነበር። ይህንን ርእስ ለማጥናት ብዙ መጸሃፍት አሉ። ከዚህ በፊት በሸልፋችን ላይ የተደረደሩትን እያወረዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። ለቅምሻ ያህል ግን አጠር ያለች፣ study guide ያላትን ይችህን የፒንክን ስራ ኮምኩሟት። በተለይ በፋሚሊ፣ በህብረትና ለጥሞና ጊዜ ብታነቧት ደግሞ እጅግ ማለፊያ ናት። የ40 ገጽ ንባብ ግን ወሳኝ ስራ ነው። እሷን ከጨረሳችሁ በኋላ ዋናውን የፒንክ attributes of Godን ወደ ማንበብ ዝለቁ

Good Christian Books Shelf

05 Dec, 14:31


በሰሞኑ ጉዳይ ከሃዋዝ መኮብለል ይልቅ የአሴን የማይነጥፉ የመጋቢነት ምክር፣ ርህራሄ፣ እረኝነት፣ ጥበብና ማስተዋል ገንዘብ ብናደርግ ክርስቲያኖች እንጠቀማለን።
አሴን ከ አንድ ደርዘን አመት በላይ አውቃለሁ። ለክርስቶስ ያለው ቀናይ ልቡ፣ የቃል ሙላቱ፣ መልካም የሆኑ የህይወት ልምምዱ፣ ለዚያ ቤት ያለው የሰፋ የአገልግሎት ምኞቱ ሁሌ እንዳስደነቀኝ ነው። ከሃበሻ አገልጋይ እንደሱ አይነት ትጉ አገልጋይ በግሌ ገጥሞኝ አያውቅም። እንደ ፈረንጅ ሪፎርምድ ባፕቲስት ሰባኪዎች ስብከቶቹ ሁሉ ክርስቶስን ያማከሉ፣ ከገላጭ ስብከቶቹ ተንሸራቶ የማያውቁና በእንባ የታጀቡ ስብከቶቹ የብዙ ሰዎችን ልብ ያጽናኑ ናቸው። ሃዋዝም ችግር ውስጥ ባይገባ ኖሮ ከዚህ አይነት ስብከት የመኮብለል እድል እንደሌለው አምናለሁ።
እርግጠኛ ነኝ ሃዋዝ ሄኖክ ጃንደረባው ጋር ሆኖ ከ አሴ ጋር የነበረው ስብከቱ፣ ህይወቱና ጸሎቱ ትዝ እያለ እንደሚያስጨንቀው ሃዋዝን እንደሚያውቅ ሰው መገመት አይከብደኝም😁

Good Christian Books Shelf

05 Dec, 06:39


ዛሬ ጠዋት ያነበብሁትን የመዝሙረ ዳውት ክፍል ላካፍላችሁ። የቆሬ ልጆች ከዘመሩት መዝሙሮች መሃል አንደኛው ነው። 47ኛው የመዝሙር ክፍል ላይ የሚገኝ መዝሙር።
ዘማሪዎቹ በ ቁጥር 1 ላይ ሌሎች ሰዎች ከነርሱ ጋር ተቀላቅለው ያህዌን በደስታ እንዲያመሰግኑ ግብዣ ያቀርባሉ። እንዲህ እያሉ “አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።”
በሚቀጥሉ ሶስት ቁጥሮች ውስጥ ለምን ይህንን ያህዌ ከነርሱ ጋር ማመስገን እንዳለብን ምክንያቶቹን በዝማሬ ያቀርቡልናል። በመጀመሪያው ያህዌ የሰማይና የምድር ሉአላዊ ንጉስ መሆኑን ይነግሩናል። በማስቀጠል ይህ ያህዌ በምድር ያሉትን አህዛብና ወገኖቻቸውን ከእግራቸው በታች በማስገዛቱና ህዝቡን ደግሞ ለርስቱ ውበት በመምረጡ እንዲመሰገን ለሌሎች ይተርካሉ። ይህ ያህዌ በእልልታ ያረገ ድል አድራጊ አምላክ በመሆኑ በጭብጨባና ከፍ ባለ ምስጋና መወደስ እንዳለበት ለግብዣው ምክንያት አድርገው ይጣራሉ።

አሁንም በድጋሜ ከቁጥር 6 ጀምሮ ከነርሱ ጋር ሆነን የማይቋረጠውን ዝማሬ ለ ሉአላዊው ንጉስ ያህዌ እንድናቀርብ ያሳስቡናል። ያህዌ የምድር ንጉስ መሆኑን፣ በአህዛብ ሁሉ ላይ መንገሱን፣ ዙፋኑ የቅድስና ዙፋን መሆኑን እያስተዋልን እንድንዘምር ይመክሩናል። የርሱ ከፍ ከፍ ማለት በመጨረሻ የምድር ገዢዎች ሳይቀሩ ለአብረሃም አምላክ ርስት እንደሚሆኑ ዘማሪዎቹ በዝማሬው ይነግሩናል።
ከዚህ የመዝሙር ክፍል ፍጥረታት ሁሉ የምድር ገዢ ለሆነው ለ ሉአላዊው ንጉስ ለያህዌ መገዛት እንዳለባቸው ያስተምረናል። መገዛታቸውም እርሱን በማመስገን፣ ለርሱ በመገዛት፣ የተወደደ ርስት በመሆንና በማስተዋል የማይቋረጠውን ዝማሬ በማቅረብ ነው። ይህንን መዝሙር እያሰብን ሜዲቴት እያደረግን እንዋል @Reformed_think_tank

Good Christian Books Shelf

04 Dec, 11:06


ዛሬ ማታ በቲክቶክ የቤተክርስቲያን ጥናታችን እንቀጥላለንhttps://vm.tiktok.com/ZMkJnwhp4/

Good Christian Books Shelf

04 Dec, 09:52


በሰውነቱ ደቃቃ፣ በንግግሩ የማይማርክ፣ በቁመቱ አጭር፣ በመላ ቁመናው ኦድ የሆነ፣ አይኑ ቡናማ፣ ጽሞቹ የተንዠረገጉ፣ ትጉ ሰራተኛ፣ ጸጉሩ የተመለጠ፣ ሰውነቱ በህመም የደከመ፣ እጅግ የተማረ፣ መልቲሊንጓል የሆነ፣ በጽሁፎቹ የክርስትናን ታሪክ ከክርስቶስ ኢየሱስ ቀጥሎ የለወጠ……..

ለጸጋ ደረጃ አይወጣለትም እንጂ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነ ግለሰብ…..

Good Christian Books Shelf

04 Dec, 07:14


አሁን በማሰብ ላይ ያለሁት ነገር ….
ጴጥሮስ ምስት ከነበረችው…..
ፖፑ በጴጥሮስ መንበር ላይ የተቀመጠው ለምን ምስት አልኖረውም?
የማግባት አፖስቶሊክ ሠክሴሽንስ ለምን አልቀጠለም? 😃😃

Good Christian Books Shelf

03 Dec, 15:40


የይቲዩበሮች ዝውውር ቢኖር ጋቪንን አስፈርመን Redeemed zoomerን ለሉተራኖች እንሸጥ ነበር 😁😁
ሊብራል የሆኑ አመለካከቶቹን ለመሸፈን እያለ ባፕቲስቶችን የሚገፋባት መንገዱ ታስቀኛለች😁

ደግሞ ሊብራል ፕሬስባይቴሪያን ሆኖ ኮንሰርቫቲቮችን በማይሆኑ ነገሮች መሸንቆጡ ሁሌ እንዳበሳጨኝ ነው lol

Good Christian Books Shelf

03 Dec, 06:55


የኢየሱስን ጌትነት በአደባባይ ለማያምኑ ሰዎች መስበክ ሃዋሪያዊ ትውፊት ነው። ይህንን ሃዋሪያዊ የወንጌል ስርጭት የሚፈታተኑ ሁለት እንቅፋቶች በክርስትና ማህበረሰብ ውስጥ አሉ…..
የመጀመሪያዎቹ እንደ እብድ ሰው የሚያደርጋቸው፣ በአደባባይ ሲሰብኩ በማይክራፎን የሰዎችን ጆሮ የሚበሱ፣ በጩኸታቸው ወንጌልን እየሰበኩ የሚመስላቸውና ወንጌልን በአደባባይ ለማያምኑ የሚሰብኩበት የተደራጀ ትምህርት የሌላቸው በስሜት ብቻ የሚንቀሳቀሱ ናቸው………

ሁለተኞቹ ደግሞ በስመ ክርስትና የሚመላለሱ ግን ወንጌሉ ሲሰበክ አምርሮ የሚጠሉ፣ ኢየሱስ ጌታችን ነው የሚሉ ግን ስሙ ሲጠራ እንደ ሰይጣን የሚያንዘፈዝፋቸው፣ ከ አእህዛብ በማይለይ አካሄድ አገልግሎቱን የሚቃወሙና በአደባባይ ኢየሱስ ጌታ ነው ከሚለው በበለጠ የአለምን ነውር በዘፈን ለመስማት የሚወዱ ናቸው።
ለዚህ አይነቱ አካሄድ ጳውሎስን ብንሰማ ጥሩ ይመስለኛል።
አንዳንዶች ከቅንአትና ከክርክር እንኳ ሌሎች ግን ከበጎ ፈቃድ የተነሣ ክርስቶስን ይሰብኩታል…….
ምን አለ? ቢሆንም በሁሉ ጎዳና፥ በማመካኘት ቢሆን ወይም በቅንነት ቢሆን፥ ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል።

Good Christian Books Shelf

02 Dec, 18:24


ዘማሪው ይጣራል። ኑ ወደ ብርሃኑ እያለ። ለዘማሪው ወደ ብርሃኑ መምጣትና መመላለስ ማለት በፍቅር የሆነ ህይወትን መልበስ ነው። ለዚህም ሁሉን በሚችል በአምላክ ጥላ እረፍት ስር እርፍ ማለት ነው። እርሱ ሰላም፣ ፍቅርና ህይወትን የሚሰጥ ስለሆነ ወደ ጌታችን እንሂድ እንሩጥ ይለናል። ወደዚህ ጌታ ስንመጣ እየፈጠንን መሆን እንዳለበት ደጋግሞ ኑ ወደ ብርሃኑ ይለናል።
የዚህ ብርሃን ምንጭ ምህረትና ፍርድ በእጁ የያዘው በሰላም ላይ የነገሰ የሰላም አባት የአለም መድሃኒት ነው። መድሃኒቱ ደግሞ በመስቀል ላይ በመዋል ህይወትን ያካፈለን ብርሃን ነው። በርሱ ብርሃን ጨለማችን ተገፈፈ፣ የርሱ የባህርይው የሆነውን ብርሃኑን ሰጠን።

በዚህ ብርሃን ሆነን የሚያስደነግጠን የሚያስጨንቀን ነገሮች ሁሉ ይጠፋሉ። ምክንያቱም በርሱ በመተማመናችን በቀን ከሚበር ሁሉ በቅዱስ ቃሉ ይታደገናል። በዚህ ብርሃን የሚመላለስ ሰው እግሩ በድንጋይ አይመታም፣ በፈተናም ውስጥ ይበረታል፣ መቅሰፍት ከቤቱ ይከለከላል፣ ለሊትና ቀን ሁሉ ጥበቃ ይደረግለታል። ስሙ ህይወት እንደሆነ ያውቃል። ከሃይል ወደ ሃይል ይመላለሳል። በረዥም እድሜ ይጠግባል። የጸጋው ልብሱ ብርሃን ይሆንለታል።
በዚህ ብርሃን የሚመላለስ አምላኩን አንተ ተስፋ ነህ ይለዋል። መናን በፍቅር የመገበው መሆኑን አምላኩ ያደረገለትን መግቦት ያስታውሳል። በማዳኑ ያገኘውን ደስታ እያሰበ አሴት ያደርጋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ እንዲህ አይነት ክብር ካንተ ውጪ የትም አይገኝም እያለ በክብሩ ይደነቃል
እንዳጠቃላይ የዘማሪው ጥሪ እጅግ ውብ ወደሆነው በመለኮታዊ ብርሃን ወደ ተሞላ ህይወት ነው። ከዚህ ጥሪ መጉደል መክሰር ነው። ብርሃናዊ ንጉስ ወደ ነገሰበት ወደ ብርሃን ከተማ ለመድረስ የማትተጋ ነፍስ የጎሰቆለች ናት። ይህ የብርሃን ህይወት ተቋም አይደለም። ክርስቶሳዊ ህይወት ነው። በጸጋ ተጀምሮ በጸጋ የሚያልቅ የህይወት ምልልስ ነው። በጨለማ ላይ ብርሃን ይብራ ያለው አምላክ በሰዎች ልብ ካበራ ቀን ጀምሮ እስከ በጉ ከተማ የተዘረጋ የህይወት መስመር ነው። የማይጠፋ ብርሃን፣ ዘላለማዊ የሆነ፣ ጨለማ የማያሸንፈው፣ በመስቀሉ ለሚያምኑ የተቆረሰ ብርሃን ነው። ከአብ የሆነ በልጁም በኩል የተገለጠ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ለትሩፋን የተከፈለ መለኮታዊ ብርሃን ነው። በዚህ ብርሃን ተፈጠርን። በዚህ ብርሃን እንመላለሳለን። በብርሃኑም ለዘላለም ብርሃናዊ አምላክ ከሆነው ከስሉስ አምላክ ጋር ለዘላለም በዚህ ብርሃን ህብረት እናደርጋለን። ስለዚህ ድንቅ ለሆነው ብርሃን የሚቀርብ የትኛውም ግብዣ ስህተት የለበትም!

Good Christian Books Shelf

02 Dec, 14:54


የንባብ መንፈስን የሚሰልበውን ሰላቢ መንፈስ እስቲ አንዴ ውጉልኝ😁😁 ከንባብ ይልቅ ቪድዮ ማየት የሚያስወድድ አዚም የተመታ ይሁን lol

Good Christian Books Shelf

02 Dec, 14:26


ጋቪያችን ደግሞ በጸዴ ቪድዮ መጥቶልናል 😁😁 እየሰማችሁ 😂 https://youtu.be/t7xn5hyYiKk?si=t5PHe__5M9pGChLD

Good Christian Books Shelf

02 Dec, 09:45


😁😁

Good Christian Books Shelf

02 Dec, 06:51


ከሃይማኖት ቤተኞች እንደ ትዝታው ሳሙኤል ቀልድን የሰቀላት ያለ አይመስለኝም😁😁

ማታ ቲክታክ ላይ አይቼ እስካሁን እያሳቀኝ ያለ ስድቡ/ንግግሩ/ቀልዱ………
“አክሊል በጨርቅ ነው የሚያውቀው እኔ ራቁቱን ነው ማውቀው” 🤣🤣


በዚህ ደረጃ ወርዶ እንካ ሰላንታ መጫወቱን ከማይወዱለት ሰዎች መሃል ነኝ። አርፎ ቃሉን ቢሰብክ፣ ቢዘምር ከሚወዱትም ጭምር ነኝ።

Good Christian Books Shelf

01 Dec, 20:17


ታናሿ እህቴ ና ወደ ብርሃኑ አለችኝ እኮ😁😁

ጌታ ሆይ በሰንበት ምን ታሰማኛለህ? 😃😃 በፍቅር ምን ልበላት? ሎል

Good Christian Books Shelf

19 Nov, 16:10


“We Worship the Word Made Flesh”

Good Christian Books Shelf

19 Nov, 06:17


“የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል። በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል። የተዋረዱትን ወደ ላይ ያወጣል፥ ኀዘንተኞችንም ለደኅንነት ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል። እጃቸውም ምክራቸውን እንዳይፈጽም የተንኰለኞችን አሳብ ከንቱ ያደርገዋል። ጠቢባንን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፤ የጠማሞችንም ምክር ይዘረዝራል……
ድሀውንም ከአፋቸው ሰይፍ ከኃያሉም እጅ ያድነዋል። ለምስኪኑም ተስፋ አለው፤ ክፋት ግን አፍዋን ትዘጋለች። እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ።”

ጻድቁ እዮብ

Good Christian Books Shelf

18 Nov, 17:29


"የደፈረሰ ውሃ ንጹህ ያልሆነውን እንደማያጸዳው ሁሉ፤ እውነተኛ ያልሆነው ኣስተምሮም በሃጢው ጆሮ ሃጢኣቱን ኣያሸንፍም"
ቻርልስ እስፐርጀን

Good Christian Books Shelf

18 Nov, 12:54


አዲስ ቲክቶከር ሸልፈኞችን አያስተኛም ይሉ ነበር ቅድመ አያቴ 😁😁 አሁን ነው አባባላቸው የገባኝ lol
የቤተክርስቲያን ጥናት በቲክቶክ ልንጀምር እያሰብን ነው። እስቲ ቤታችንን ጎብኘት አድርጓት 😃

https://vm.tiktok.com/ZGdYeFtCo/

Good Christian Books Shelf

18 Nov, 06:03


“በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ። ጕልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁ፥ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ። እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው፥…
አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ፤ አቤቱ፥ ቀኝህ ጠላቱን አደቀቀ…. አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ በቅድስና የከበረ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤ በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው……
አቤቱ፥ አንተ ታስገባቸዋለህ፥ በርስትህ ተራራም ትተክላቸዋለህ፥ አቤቱ፥ ለማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፥ አቤቱ፥ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ። እግዚአብሔር ለዘላለሙ እስከ ፍጻሜ ይነግሣል።”
ሙሴና የእስራኤል ልጆች የዘመሩት መዝሙር

Good Christian Books Shelf

17 Nov, 18:06


በዚህ ሁለት አመት ውስጥ የገጠሙኝ በዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ የሚሰሩ የጎረቤቶቻችን ጥያቄዎች 😁😆 ከነዚህ ጥያቄዎች የሚሻገሩበት ዘመን ያምጣልን😁

ኦርቶው ጥምቀት ያድናል?
ፕሮማክሱ በጥምቀት የእግዚአብሄር ጸጋዎችን እንቀበላለን
ኦርቶው እህ እህ እህ….. ባለፈው ሌለኛው ፕሮ አያድንም ብሎኝ ነበር ምን አይነት ባቢሎናዊ ናችሁ ግን?
ኦርቶው ቅዱስ ቁርባን ተራ መታሰቢያ ነው ብላችሁ ነው የምታምኑት?
ፕሮማክሱ ኧረ አይደለም ከመታሰቢያ ያለፈ በቁርባን በምስጥር የክርስቶስን ስጋና ደም ነው የምንቀበለው
ኦርቶው እ ህ እህ እህ እህ እህ
ፕሮማክሱ ሌላ ጥያቄ አለህ?
ኦርቶው ማስረጃ አምጣ
ፕሮማክሱ ኧረ ሌላ ጥያቄ አለህ ነው ያልኩህ
ኦርቶው በቀጥታ ማስረጃህን አቅርብልኝ
ፕሮማክሱ ተጨማሪ ከሁለቱ ጥያቄ ውጪ አለህ?
ኦርቶው አሁን ገባኝ። እሺ ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ ጥምቀት ያድናል?
ፕሮማክሱ ቅድም ነገርሁህ አይደል?
ኦርቶው እሺ አንድ የመጨረሻ ጥያቄ አለኝ። ቅዱስ ቁርባን እውነተኛ የጌታ ስጋ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ?
ፕሮማክሱ እሱንም ቅድም ጠየከኝ እኮ።
ኦርቶው እሺ ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ
ፕሮማክሱ በደስታ
ኦርቶው ሉተር የህጻናት ጥምቀት የማይቀበሉትን መቶ ሺህ አጋንንቶች አለባቸው ይላል።
ፕሮማክሱ እሺ ጥያቄህ ምንድነው?
ሉተር ከዚዊንግሊ ይልቅ ፖፑ ይቀርበኛል ይላል።
ፕሮማክሱ እሺ ጥያቄህ ምንድነው?
ኦርቶው ሉተር ጥምቀት ያድናል ብሎ ያምናል።
ፕሮማክሱ ዕሺ አሁንም ጥያቄህ ምንድነው?
ኦርቶው ሉተር ቅዱስ ቁርባን እውነተኛ የጌታ ስጋና ደም ብሎ ነው የሚያምነው።
ፕሮማክሱ ሌላ ጥያቄ የለህም?
ኦርቶው ኧረ ብዙ ጥያቄ አለኝ። እሺ ልጠይቅህ ቅዱስ ቁርባን ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው ብለህ ታምናለህ?
ፕሮማክሱ ቅድም አልሰማኝም ነግሬህ ነበር እኮ
ኦርቶው ዕሺ ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ። ሉተር አናባፕቲስቶችን መቶ ሺህ አጋንንት አለባቸው ይላል።
ፕሮማክሱ ዕሺ ጥያቄህ ምንድነው?
ኦርቶው ዚውንግሊ ቅዱስ ቁርባንን ተራ መታሰቢያ ነው ይላል።
ፕሮማክሱ ዕሺ እንቅልፌ እያስቸገረኝ ስለሆነ አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ጠይቀኝና ልተኛ
ኦርቶው ብዙ ጥያቄ ነበረኝ ግን እሺ ሌሎችን ነገ እናወራለን። ለአሁኑ ጥምቀት ያድናል?
ፕሮማክሱ ቅድም የነገርኩህን ረስተህ ነው?
ኦርቶው እሺ ገባኝ አንድ ጥያቄ ብቻ። ዚውንግሊ ቅዱስ ቁርባንን መታሰቢያ ነው ይላል። ሉተር ደግሞ እውነተኛ ስጋና ደም ነው ይላል።
ፕሮማክሱ ዕሺ ጥያቄህ ምን ነበር?
ኦርቶው ሉተር ከዚውንጊሊ ይልቅ ከፖፑ ጋር ቁርባን ብወስድ እመርጣለሁ ይላል።
ፕሮማክሱ ኧረ በጌታ ጥያቄ ብዬህ እኮ ጥያቄ እየጠየከኝ አይደለም።
ኦርቶው ብዙ ጥያቄ አለኝ። ግን🤣🤣

Good Christian Books Shelf

17 Nov, 15:57


“የሰው ልጆች ቤዝዎት ከራሱ ከእግዚአብሔር በስተቀር በሌላ ሰው አሊያም መልአክ አማካይነት ሊከናወን አይችልም። ከእግዚአብሔር ሌላ የሆነ አካል ሆኖ ቢሆን ከዘላለም ሞት ያዳናቸው፣ የዳኑት ለዚህ ላዳናቸው አካል (ሰው ወይም መልአክ) አዳኜ ብለው ባርያ በሆኑለት ነበር። እንዲህ ከሆነማ እንዴት መዳን ይባላል! የዳኑት ከእግዚአብሔር ሌላ ለሆነው ባርያ ናቸውና።”
“ለምን አምላክ ሰው ሆነ?” በሚለው ቅዱስ አንሰልም በትክክል እንደገለጠው

Good Christian Books Shelf

17 Nov, 09:58


@christiandogmatics

Good Christian Books Shelf

17 Nov, 05:59


“አቤቱ፥ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ተባረክ። አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።
ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ታላቅ ለማድረግ፥ ለሁሉም ኃይልን ለመስጠት በእጅህ ነው. አሁንም እንግዲህ፥ አምላካችን ሆይ፥ እንገዛልሃለን፥ ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን።”

ንጉሱ ዳዊት

Good Christian Books Shelf

16 Nov, 17:00


የሮሜ ጥናታችንን ጀምረናል ገባ ገባ እያላችሁ 😁

Good Christian Books Shelf

16 Nov, 12:42


“we are blind to God's revelation but not so blind that we can plead ignorance without being convicted of perversity.”

John Calvin

Good Christian Books Shelf

16 Nov, 11:37


“እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤ እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና።
የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ, የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።”

ሮሜ 1: 18/23

Good Christian Books Shelf

16 Nov, 05:55


“የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፥ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።”
ነብዩ እሳይያስ

Good Christian Books Shelf

15 Nov, 18:04


ቅዱስ በርናርድን አሁን ገና ማንበብ መጀመሬ በጣም እየቆጨኝ ነው lol በርናርድን ሳያነቡ አሪፍ አንባቢ መባል እንደማይቻል ተረድቻለሁ😁 ቅዱስ በርናርድ በሰሞኑ ንባቤ ከብዙ አባቶች የሚልቅ፣ ከጆን ክራይሶስቶም ጋር በአንድ መደብ የሚመደብ፣ ከፒውሪታንስና ከነ እስፐርጀን የሚያንስ ቃላት እንዲሁ እንደ ውሃ የሚፈሱለት ደገኛ በመካከለኛው ዘመን የተገኘ የቤተክርስቲያን ዶክተር ነው።
እናም በሰሞኑ ንባቤ ከሱ ብዙ ትምህርቶችን እየጨለፍሁ ነው። ከዚህ በኋላ ስራዎቹን እያሳደድሁ አነባለሁ። ንግግሮቹ ዘላቂ በሆኑ ምክሮች የበለጠጉ ናቸው። ከንግግሮቹ ጥፍጥና የተነሳ መሃልዬን ራሱ አሊጎራይዝ በሆነ መንገድ ለመረዳት መነሳሳቴን አልደብቃችሁም😁😁 ደግሞ ቅዱስ በርናርድ የሉተርና የካልቪን ተወዳጅ አባት ነው😀 እስቲ ጊዜ ስታገኙ በርናርድን በኔ ስም አንብቡት። ሎል አንዳንድ ጽሁፎቹ የተመቱ ስለሆኑ እንጂ ስራዎቹን ወዲህ በማምጣት በሸልፋችን ብደረድር በወደድሁ ነበር😁

Good Christian Books Shelf

15 Nov, 10:44


"Paradoxically, God is both Deus revelatus ("the revealed God") and Deus absconditus ("the hidden God"). He is the God who "is revealed in hiddenness and hidden in his revelation."

Good Christian Books Shelf

15 Nov, 05:40


“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።”

ቅዱስ ዳዊት

Good Christian Books Shelf

14 Nov, 18:49


ሶሻል ሚዲያ ላይ ለሚሰሩ ጎረቤቶቻችን መረጃ ለመስጠት ያህል…ያው አብዛኛው የማንበብ ልምድ የለውም የሆነ ጊዜ ከሰማ እሱን እያመነዠገ፣ በየ ሶሻል ሚዲያው እንደ አዋቂ የሰማውን እያስተጋባ ከሚኖር የእውቀት አድማሳቸውን መረጃ በመስጠት ላስፋ ብዬ ነው 😁😁
1 የህጻናት ጥምቀት የሚቀበሉ የፕሮማክስ ቤተ እምነቶች ሉተራን፣ ፕሬስባይተሪያን፣ ኮንቲነንታል ሪፎርምድ፣ አንግሊካን/ኤፒስኮጳል፣ ሜቶዲስት፣ ፒውሪታንስ….
ስለዚህ ሁሌ አንዴ የሰማቹትን ከምታስተጋቡ ከሉተራን ውጪ እነዚህ ቤተ እምነቶች የህጻናት ጥምቀትና በጥምቀት በኩል ጸጋዎች እንደሚተላለፍ እንደሚያምኑ ከዛሬ ጀምሮ እወቁ😀
2 አፖስቶሊክ ሰክሴሽን የሚቀበሉ የፕሮማክስ ቤተ እምነቶች..።
አንግሊካን/ኤፒስቆጳል፣ የተወሰኑ ሜቶዲስቶችና የተወሰኑ ሉተራኖች።
በፕሮማክሱ አፖስቶሊክ ሰክሴሽን ያላቸው ቤተ እምነቶች የሉም ስትሉ እንዳልሰማችሁ ቀድሜ ነገርኳችሁ😁
3 ካልቪኒዝምን የሚቀበሉ የፕሮማክስ ቤተ እምነቶች….
ፕሬስባይቴሪያን፣ ኮንቲነንታል ሪፎርምድ፣ አንግሊካን/ኤፒስቆጳል በኮንፌሽን፣ የተወሰኑ ሜቶዲስቶች፣ ፓርቲኩላር ባፕቲስቶች
በየ ሶሻል ሚዲያ ያገኛችኋትን እውቀት ከሪፎርምድ ባፕቲስቶች ውጪ ያሉትን ሌሎችን እንግዳውስ ከዛሬ ጀምራችሁ እወቁ 😁

4 በሴቶች አገልግሎት፣ በነቢያትና በሃዋሪያት፣ በሌሎችም የጸጋ ስጦታ ላይ በኮንፌሽኖቻቸው መሰረት strict የሆኑ የፕሮማክስ ቤተ እምነቶች…..
ኮንፌሽናል ፕሬስባይቴሪያን፣ ኮንፌሽናል ሉተራን፣ ኮንፌሽናል ባፕቲስቶች፣ ኮንፌሽናል ኤፒስቆጳል፣ ኮንፌሽናል ኮንቲነንታል ሪፎርምድ ቤተ እምነቶች
ስለዚህ ከላይ የነገርኳችሁን ቤተ እምነቶች ከፔንቲኮስታል፣ ኢቫንጄሊካል በብዛት፣ ነን ዲኖሚኔሽናል ቤተ እምነቶች ጋር ለያይተህ ውዳሴህንና ነቀፋህን በተነሳው ርእስ ላይ አቅርብ ውዱ ጎረቤታችን 😀
5 ኮንሰርቫቲቭ ሉተራን ነህ ተብሎ አይጠየቅም ይልቁን ኮንፌሽናል ሉተራን ነህ? ነው የሚባለው😁
ማሳሰቢያ፤ ከላይ የጻፍከው እኛን ምን ይመለከተናል? ትለኝ ይሆናል ሎል አይጠቅምህም አንብበህ ማውራት ስለማትችል መንገዱን እያቃለልሁልህ ነው 😁
ደግሞ እቀበተ እምነት ስሰራ በእውቀት ማድረግ እፈልጋለሁ ለምትል አስተዋይ ጎረቤታችን እባክህን ኮንፌሽኖቻችንን አንብብልን😄

ከሉተራንና ከሉተር ያለፈ እውቀት ስለ ፕሮማክሱ እንዳስጨበጥኳችሁ ተስፋ አለኝ 😙

Good Christian Books Shelf

14 Nov, 17:14


ፕሮማክሱ ፍቅሩን ሲገልት 😁😁 አንዳንዴም ለሸልፈኞቼ memes ያስፈልጋቿል 😎😊

Good Christian Books Shelf

14 Nov, 11:33


ከላይ የቀጠለ….
4. የጸጋ/የማደጎ ልጅነታችን በስሉስ ኣምላክ ግሩም ምክር የተመከረ፤ ተመክሮም ኣስቀድሞ በእግዚኣብሄር ኣብ ኣማካኝነት ኣለም ሳይፈጠር በፊት የተደነገገልን፤ በዘመኑ ፍጻሜ የባህሪ ልጁ ከሴት ከህግ በታች በመወለድ በመስቀል ላይ እርጉም ሆኖ ከባርነት ግዞት ዋጅቶን በመንፈስ ቅዱስ ስራ ልጅነታችንን በልባችን የታተመና ኣባ ኣባ ብለን እንድንጮህ መብት የተሰጠን መሆናችንን ቃሉ በማያሻማ መልኩ ይነግረናል። ኣብ የልጅነታችንን ድንጋጌ እንደወሰነልን (ኤፌ 1: 5)፤ ወልድ የልጅነታችንን ስራ ሊሰራልን እንደመጣ (ገላ 4: 4-6)፤ መንፈስ ቅዱስ የልጅነታችንን መብት እንድንጠቀም በልባችን ማህተም ማኖሩን( ሮሜ 8:14) ከብዙ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሎች መሃል ጥቂቶቹ ናቸው። ልጅ ደግሞ ከሆንን የእግዚኣብሄር ወራሾች ነን። ወራሽ የሆንን ተገብቶን ኣይደለም፤ እንዲያው በዘላለም ፍቅሩ ስለወደደን እንጂ። ይህ የልጅነት ስልጣናችን ኣሁን ተጀመረ እንጂ ፍጻሜ ላይ የደረሰ ልጅነት ኣይደለም የተጎናጸፍነው። በቃሉና በእውነት ከማይጠፋ ዘር ወልዶናል። ወልዶንም ኣባል ያደረገን በስሉስ ኣምላክ ድንጋጌ በተመሰረተች ቅድስት ማህበር ውስጥ ነው። ኣንድ ኣባት ያለን ልጆች ነን። ኣንድ በኩር ወንድም ልንመስለው የተገባን የማህበሩ ራስ ኣለን። በማህበሩ ውስጥ ገፊና ተገፊ፤ የራበውና የጠገበ፤ ትምክህተኛና ትሁት የሚባሉ ክፍፍሎች ኣይኖሩም። እኔ እበልጥ እሱ ያንስ የሚል የስግብግብነት መንፈስ ያለው ማህበርተኛ ኣይኖርም። ልጅነታችን በሙላት እስኪገለጥ ድረስ ግን በኣለም ከፍጥረታት ሁሉ ጋር እንቃጥታለን። በስጋ ድካም፣ በኣለም ብርታት እና በሰይጣን ፈተና ልጅነታችንን ብንጠራጠርም፤ በውስጣችን በተተከለው ኣዲስ መንፈስ ኣማካኝነት የሚመጣውን ጌታ ከሚገለጠው ልጅነታችን ጋር በናፍቆት እየዛልን እንጠባበቃለን።
5. የጸጋ ልጅነታችን እጅግ ወሳኝ ከሆኑ የመጽሃፍ ቅዱስ ኣስተምህሮች መሃል ኣንዱ ነው። በተለይ በነገረ ድህነት ውስጥ ይህንን ኣለመረዳት ሌሎች ምሶሶ ኣስተምህሮችን ኣለመረዳት ያስከትላል። ነገረ ድህነት በኣንድ ኣስተምህሮ ላይ ብቻ ኣለመቆሙን መጽሃፍ ቅዱስ ደጋግሞ ስለሚነግረን፤ በኣንዱ መሳት በሌሎችም መሳት ስለሆነ በኣስተውሎት ቃሉን ማጥናት ይኖርብናል። ክርስቲያናዊ ነገረ ድህነት በወርቃማ ሰንሰለት የተያያዘ ነው። ዳግም ውልደት፣ ማመን፣ ጽድቅ፣ ልጅነት፣ ቅድስናና ክብር ኣንዱ በሌላው ላይ በድርርብ የቆሙ ናቸው። ከነዚህ ሁሉ ስር ምርጫ/ቅድመ ውሳኔ የሚባል የማይነቃነቅ ንጣፍ መኖሩን ሳንረሳ ማለቴ ነው። ስለዚህ የልጅነታችን ስልጣን ላይ ስሁት ኣረዳድ ካለን ሌሎችም ኣስተምህሮች ላይ ኣደጋ እንደመጣል ይቆጠራል።
6. የባህላችን ተጽኖ እና ወደ ኣማርኛ የተተረጎሙልን የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሎች ይህን እውነታ በቀላሉ ከቃላቶቹ ጋር እንድንላመድ ኣላደረጉንም ብዬ ኣምናለሁ። ለብዙ ሃበሻዎች የማደጎ ልጅ ሲባል ይጎረብጠናል። እውነት ነው ብጎረብጥብን ብዙም ኣይገርመኝም። በባህላችን የጉዲፈቻ ልጅነት ምን ኣይነት ኣስቸጋሪ ነገሮች እንዳሉት መገመት ኣይከብደንም። ያለን ባህላችን የተዋጀ ባህል ኣይደለም። ለክርስቶስ ኣስተምህሮ ደግሞ ያልተዋጀ ባህል ሁሌም ችግር ፈጣሪ ነው። ለዚህ ይመስለኛል በህሊናችን የማደጎ ልጅ ሲባል ኣሉታዊ ነገሮች በኣእምሮኣችን የሚያቃጭሉብን። ከባህላችን በተጨማሪ የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉሞች የቃሉ ብርሃንነት በበለጠ ደምቆ እንዳይታዩን እንዳደረጉብን መገመት ኣይከብድም። ብዙዎቹ የኢንግልዘኛ ቨርዥኖች የጽሩን ቃል ‘Huiothesia’ የሚለውን በትክክል ተርጉሞታል። በኣማርኛችን ትርጉም ይህ ቃል ኣይገኝም። በተርጓሚዎቻችን ላይ የባህል ተጽኖ ደርሶባቸው ይሁን? ኣላውቅም። ሊሆን ይችላል። እነዚህን ክፍሎችን በጥንቃቄ ኣማርኛውን ከኢንግልዘኛ ጋር እያስተያያችሁ እንድታጠኑ እመክራቸዋለሁ። ኤፌሶን 1:5፤ ገላቲያ 4:5፤ ሮሜ 8: ቁ 15, 23እና ሮሜ 9:4ንያነበበ ሰው የጸጋ/የማደጎ ልጅነት ሲባል ኣይጎረብጠውም።
7. ልደምድም መሰለኝ…
ለእግዚኣብሄር የማደጎ ልጁ ነኝ ስል፤ በልጁ የመስቀል ስራ ኣማካኝነት ወደ ሰማያዊ ቤተሰዎች ደምሮኛል እያልሁኝ ነው። እኔ ልጁ ያልነበርኩትን በጸጋው ኣማካኝነት ልጅ ኣደረገኝ እያልሁ ነው። በባህሪዬ የቁጣ ልጅ የነበርኩትን በዘላለም መዋጀት ዋጅቶኝ የስሉስ ኣምላክ ህብረት ኣድርጎኛል እያልሁኝ ነው። ይህን ልጅነት በፍቃዴ ያገኘሁት ሳይሆን እንደ በጎ ፍቃዱ የቸረኝ ልጅነት ነው እያልሁኝ ነው። ይህ ልጅነቴ ከዘላለም በፊት የታቀደልኝ፣ በዘመን ፍጻሜ እውን የሆነልኝና በሚመጣው ኣለምም የሚቀጥል የማይቋረጥ መብት/ፕሪቪሌጅ ነው እያልሁኝ ነው። የሰይጣን ልጅ የነበርሁትን በልጁ የመስቀል ጣር ኣምጦ ወልዶኛል፤ የደም ዋጋ የተከፈለልኝ በዘላለምም የኪዳን ደም እረኛ ጠባቂ የተሾመልኝ ልጁ ነኝ እያልሁኝ ነው። ልጅነቴም ከባህሪ ልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኣንድ ኣይነትነት ያልሆነና በሰጠኝ ስልጣን ምህዋር ላይ ብቻ የምንቀሳቀስ የጸጋው ልጁ ነኝ እያልሁኝ ነው። እሱ ኣባቴ ነው ስል እንደ ምድራዊ ወላጅ ኣባት ቆጥሬው ኣይደለም፤ ይተወኛል፣ ይጥለኛል፣ ፊቱን ያዞርብኛል ብዬ ኣልጠራጠረውም። ሁሌም እሱ ኣባቴ ነው። በራሱ የልጅነት ስልጣኑን ኣድሎኛል። ከብርቱ እጁም የሚፈለቅቀኝ እንደሌለ በማይለወጥ ቃልኪዳን ገብቶልኛል። የኔና የእሱ ኣባትነት ሆነ፤ የኔና የወልድ ልጅነት ድንበር የተበጀለት ነው። ወደ እሱ ስልጣን ከፍ እል ዘንድ ኣይቻለኝም፤ እሱም ስልጣኑን ትቶ በኔ ስልጣን ያጌጥ ዘንድ ኣይቻለውም።

Good Christian Books Shelf

14 Nov, 11:33


ትላንት በላይቭ ስናወራ በዚህ ዘመንም የኛና የክርስቶስ ልጅነት አንድ ነው። የማደጎ ልጅ ሳልሆን የክርስቶስ አይነት ልጅ ነኝ የሚሉ ሰዎች እየበዙ መሆኑን ስሠማ ደንግጫለሁ😁 ተመናምኖ ትምህርቱን የተዉት መስሎኝ ነበር ሎል አረጀን መሰለኝ ከሰባት አመት በፊት በፌስቡክ የጻፍኩትን እንግዲህ ወዲህ ለማምጣት ወደድሁት
ረዘምዛሜ ጽሁፍ ነው ቡና ነገር እየጠጣችሁ አንብቡልኝ 😁
ክርስቲያኖች ለእግዚአብሄር የማደጎ/ጉድፈቻ/የጸጋ ልጆች ነን?
የማደጎ/የጉዲፈቻ/የጸጋ ልጅነት መጽሃፍ ቅዱስ ደመቅ ኣድርጎ ካስቀመጠልን እውነታዎች ዋናው ነው። የሰው ፈጠራ የሚመስላችሁ ሰዎች በጥንቃቄ ጽሁፉን አንብቡልኝ። በዚህ ጽሁፍ ሰባት ኣንኳር ነጥቦችን ብቻ ላንሳ።
1. ሁላችን ከሚያስማማን ነጥብ ልነሳ…
ኣብዛኛዎቻችን ክርስቲያኖች የእግዚኣብሄር ልጆች እንደሆንን በሙሉ ልባችን የምናምን ይመስለኛል። ይህም ልጅነታችን እግዚኣብሄር እንዲያው በጸጋ ቸር በመሆኑ በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ስራ በማመን እንደተቀበለን መረዳት እንችላለን። ሰዎች መልካም ስራዎቻቸውን በሚዛን ኣስመዝኖ የእግዚኣብሄርን ልጅነት መቀበል እንደሚችሉ ቃሉ ኣይነግረንም። በተጨማሪም እግዚኣብሄር የሰጠንን ግብረ-ገባዊ ህግጋትን በመጠበቅም በርሱ ፊት እንደማይጸደቅና የልጅነት ደረጃ ላይም እንደማይደረስ ግልጥ ነው። ልጅነት የወላጆች በጎ ፍቃድ ላይ የሚመሰረት እንጂ በተወላጅ ልጆች ችሮታ ላይ የቆመ ኣይደለም። ውሳኔውም፣ ፍቃዱም፣ ግብሩም የወላጆች ብቻ ነው። ስለዚህ በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ የተገለጠውም ልጅነት ከዚህ እውነታ የራቀ ኣይደለም፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ስራ ብቻ፣ በእምነት ብቻና በእግዚኣብሄር ጸጋ ብቻ እንደሚገኝ ብዙ የቃሉን ምስክርነት ማቅረብ እንችላለን።
2. ከላይ ባስቀመጥሁት ኣጭር እውነታ ሁሉም ክርስቲያኖች ይስማማሉ። የማይስማሙስ ታዲያ በምንድርነው? ከተባለ ዘንዳ…
ልጅ ከሆንን ምን ኣይነት ልጅ ነን? በሚለው ወሳኝ ጥያቄ ስንጠየቅ ይመስለኛል ልዩነታችን ፍንትው ብሎ መገላለጥ የሚጀምረው። በየትኛውም ጊዜ ሆነ ስፍራ ክርስቲያኖች የእግዚኣብሄር ልጆች ነን ሲሉ ሁሌም ታሳቢ የሚያደርጉት የጸጋ//የማደጎ/የጉዲፈቻ ልጅነታቸውን ነው። ክርስቲያኖች ሊጠሩበት የሚገባው በቃሉም ሆነ በቤተክርስቲያንም የምናውቀው የልጅነት ኣይነት ከዚህ ውጪ ጨርሶውንም ኣናገኝም። ነገር ግን፤ ዘመናዊ ‘ክርስትና” በድፍረት ያስተዋወቀን የልጅነት ኣይነት መኖሩን ስንቶቻችሁ ታውቁ ይሆን? “እኔም የኣብ ልጅ ነኝ”… “ኣንዲያ ልጅ ተብዬ ልጠራ መብት ኣለኝ”… “የክርስቶስ ኢየሱስ የልጅነት ስልጣንና የኔም ልጅነት ኣንድ ኣይነትነት ነው”… “ልጅ በመሆኔ የእግዚኣብሄርን DNA ወይም ዘረ-መል በውስጤ ኣለኝ”… የሚሉት የተንሻፈፈውን ኣስተምህሮ የሚያራምዱት ናቸው።
ይህ ሰው ሰራሽ ኣስተምህሮ፤ የራሳቸውን የልጅነት ስልጣን ከፍ በማድረግና የእግዚኣብሄርን ልጅ ስልጣን ጋር በመተካከል ኣማልእክት የመሆን ፍላጎታቸውን የሚያረኩበት ጠያፍ ኣረዳዳቸው ነው። በእውነት እንዲህ ኣይነቱ ከቅዱሱ ቃል ጋር በተቃርኖ የሚቆሙትን ትምህርቶችን መፋለም ይጠበቅብናል። እኛ በታሪካዊ ክርስትና እና በቃሉ ስልጣንነት ለምናምን ግን ከነዚህ ኣረዳድ ጋር ኣንተባበርም፤ በምንፍቅናቸውም ጋር ህብረት የለንም። እኛ የምናውቀው ከቃሉ ያገኘነው ከኣባቶቻችንም የተቀበልነው እውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም የኣብ ልጅ መሆኑን፤ የልጅነቱ ኣይነትም ብቸኛ ልጅነትና ኣንዲያ ልጅ መሆኑን፤ ቃልም ስጋ ለብሶ ሲመጣ ልጅነቱን ትቶ ያልመጣ መሆኑን፤ ክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚኣብሄር ልጅ በመሆኑ የክርስትና መገለጥ በዚህ ኣዋጅ ላይ መቆሙን፤ ልጅ በመሆን ከኣብ ጋር የማንነት ተዋረድ ኣለመኖሩን፤ የሰው ልጆችም በእግዚኣብሄር ወልድ በማመን የዘላለም ህይወትን እንደሚያገኙ እንመሰክራለን። ይህን እውነት በማመንና ኣምኖ በመመስከር የዘላለም ህይወት እንደሚገኝ እናስተምራለን። በ4ኛና በ5ኛ ክፍለ ዘመን የነበረው ቅዱስ ኣውገስጢን እንዲህ ይላል… ‘We are adopted sons by grace of God, but Christ is the Son of God by nature’። እናም ልጆች ነን። ልጅነታችንም በጸጋ ኣማካኝነት እግዚኣብሄር ወደ ቤተሰዎቹ እንደቀላቀለን እናምናለን፤ ለእግዚኣብሄር ኣንዲያ ልጅ ሆኖ በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ስልጣን ላለው ለሄያው እግዚኣብሄር ልጅ ለኢየሱስ ውዳሴኣችንና ኣምልኮኣችንን እናቀርባለን።
3. ይህን ካልሁኝ ዘንድ በኣጭር ስለ ማደጎ/ጸጋ ልጅነታችን ከመዋጀት ታሪክ ኣንጻር ጥቂት ልበል…
በፍጥረታት እና በፈጣሪ መሃል ባለው ግኑኝነት የኣባትና ልጅነት ትስስር ሊፈጠር እንደሚችል ከተወሰኑ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሎች ማስተዋል ይቻላል። እግዚኣብሄር ፈጣሪ ነው። እኛም የእጆቹ ፍጥረታት ነን። እኛን በመፍጠሩ ኣባታችን/ኣስገኚኣችን ነው። ፍጥረታትም በሙሉ መነሾ ኣካል ስላለው እግዚኣብሄርን እንደ ኣባት የመቁጠር መብት ኣለው። የመጀመሪያው ሰው ኣዳም ልጅ ተብሎ የተጠራውም በላይ በተቀመጠው ንድፈ ኣሳብ ነው። እግዚኣብሄር ኣዳምን ኣልወለደውም። ግን ፈጥሮታል። በፈጠረው ፍጥረት ላይ ደግሞ የኣባትነት ስልጣን ይኖረዋል። ፈጣሪ ፍጥረታትን በመፍጠሩ የሁሉም ወላጅ ነው። መላእክት ልጆቹ ናቸው። ባህሩ፣ ተራራው፣ ደኑ፣ ሰማይና ምድሩ፣ ጠፈሩ ልጆቹ ናቸው፤ ፈጥሮኣቸዋልና።
በፍጥረት ኣማካኝነት የተፈጠረው ሰው የእግዚኣብሄርን ልጅነት ከተጎናጸፈ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የተሰጠችውን ትእዛዝ በመተላለፍ ሃጢኣት ወደ ኣለም እንዲገባ ምክንያት ሆነ። ወደቅን። ለእግዚኣብሄር ቃል ከመገዛት ይልቅ ለሰይጣን መገዛት ባህርያችን ሆነ። ለተፈጠርንበት ኣላማ ስተን ለሰይጣን ኣገልጋዩ ሆንን። የሰይጣን የባርነት ቀንበር ስር ገብተን በሃጢኣታችን መንሴ ለሄያው እግዚኣብሄር ሞተን ለጨለማው ስልጣን ለጌታችን ተመላለስን። በፍቃዳችንም እሱን እያገለገልን ለዘመናት በባርነት ጉዞኣችን ተጓዝን። ሁላችን ንጹህ ሆነን ከመወለድ ይልቅ በፍጥረታችን የእግዚኣብሄርን ቁጣ በራሳችንና በፍጥረታት ላይ የምናነሳሳ ሆነን ተገኘን። በደለኞች፣ ለቃሉ የማንገዛ፣ ለፈጠረን ኣምላክ እምብተኞች ሆነን እንደ እንስሳ በምድር የምንርመሰመስ ፍጥረት ሆንን። በዚህ መሃል እያለን ነው እግዚኣብሄር ያህዌ ኤሎሂም ከምድር ወገን መሃል ለርስቱ የሚሆነውን ስሙንም ለኣለም እንዲገልጥ እስራኤልን እንደ በኩር ልጁ በልጅነት ማእረግ የጠራው። ይህም ጥሪ በባርነት ስር ለሚመላለሰው እስራኤል እንጂ በልጅነት ክብር ለሚኖረው እስራኤል ኣልነበረም። በባርነት ፈርኦንን ከሚያገለግልበት ተጠርቶ ለሄያው ኣምላክ በምድር ሁሉ ላይ ምስክር እንዲሆን በጸጋው ጉልበት የተጠራው እስራኤል የማደጎ/የጸጋ ልጅነትን ተጎናጸፈ። እግዚኣብሄርም ወንድ ልጆቹና ሴት ልጆቹን በቃልኪዳኑ ኣማካኝነት ወደ ክብር ሲያመጣ ኣስቀድሞ ያቀደውን እቅዱን በልጁ ኣማካኝነት ተግባራዊ ካደረገና በልጅነት መንፈስ ካተማቸው በኋላ እኔም ኣባት ሆናቸዋለሁ እናንተም ልጅ ትሆኑኛላችሁ ብሎ በጸጋው ኣማካኝነት ዳግም ወለዳቸው። የተወለዱትንም በህጉ ፊት ኣቆማቸውና ኣዲሱን ሰው እንዲለብሱ ኣደረጋቸው፤ የልጅነትንም ስልጣን ካባ ደረበላቸውና በቅድስና ህይወት እንዲመላለሱ ና የበኩር ወንድማቸውን መልክ እስኪኖራቸው ድረስ ሩጫቸውን እንዲሮጡ ኣደረጋቸው። በመጨረሻም የልጅነታቸው መልክና ኣምሳል በኣለም ይገለጣል፤ ከክብር ወደ ክብርም ይሻገራሉ።

Good Christian Books Shelf

14 Nov, 06:07


“አምላክ ያለው ላይቀር ማንም ላይለውጠው፤
ነገን እያሰቡ መጨነቅ ምንድነው? በእምነት መኖሩ መልካም ነው
እቅድ ኣለውና ጌታ ለያንዳንዱ፤
ቸር ነው የሚራራ ዘወትር በኣካሄዱ።
በእምነት መኖሩ መልካም ነው
ዛሬ ከኖርንበት ነገ ራሱን ያውቃል፤
ሰው በሃሳብ ቢዋጥ ምኑን ይለውጣል?
በእምነት መኖሩ መልካም ነው”
ዘማሪ ዶ/ር ደረጀ ከበደ

Good Christian Books Shelf

13 Nov, 17:02


ቤተክርስቲያን በቃሉ የተፈጠረች፣ ለቃሉ እውቅና ሰጪ፣ የቃሉ ባሪያ፣ የቃሉ ተቀባይ፣ የቃሉ ጠባቂ፣ ለቃሉ የምትገዛ፣ ቃሉን የምትተረጉም፣ የቃሉ አስተማሪ፣ እንጂ የቃሉ ጌታ፣ አስገኚ፣ የበላይ አይደለችም

Good Christian Books Shelf

13 Nov, 14:15


አንድ የሚመስሉ ግን ልዩነት ካላቸው መጸሃፍ ቅዱሳዊ ተርሞች መካከል ጥቂቱን…..
Justification እና salvation…..
Once saved always saved እና perseverance of saints…..
Election እና predestination….
Sin እና evil….
Jesus እና Christ……
Sabbath እና Sunday….
Expiation እና propitiation….
እነዚህን ቃላትን በጥንቃቄ ካልተረዳናቸው የዶክትሪን ጥሰት ራሱ ሊያመጡ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል…OSAS በሪፎርምድ ነገረ መለኮት ውስጥ የማይታወቅ ባእድ አነጋገር ነው። ትክክለኛው የተሃድሶ ነገረ መለኮት perseverance of saints ነው። የዳኑ ሰዎች ድህነታቸውን ይፈጽማሉ፣ በምስጥራትና በመልካም ስራ ፍሬ እያፈሩ፣ በመንፈስ ቅዱስም ሃይል የስጋ ስራዎችን እየገደሉ እስከመጨረሻ ድረስ ለክብሩ ይጠበቃሉ።

Good Christian Books Shelf

12 Nov, 20:21


ጋይስ በቲክቶክ የሚኖረንን ሮድማፕ ማወቅ ከፈለጋችሁ ቲክቶካችንን አየት አድርጓት እስቲ 😀😀 https://vm.tiktok.com/ZMhpMhchP/

Good Christian Books Shelf

12 Nov, 18:13


የእግዚአብሄር ጸጋ አሳዳጅ ጸጋ ነው! አሳዶ ሳይዝ የሚመለስ ሳይሆን አሳዶ ሃጢአተኞችን የሚያድን፣ ጠላቶቹን ከመሬት ስበት በላይ በሆነው በሃይሉ ችሎት እንዲያው ወደራሱ የሚስብ፣ ሳይፈልጉ በፍቅሩ ጉልበት የሚያንበረክክ፣ ሳይመርጡት በዘላለም ምክሩ የሚመርጥ፣ ሳይወዱት በርሱ በዘላለም መውደድ የሚወድ ጸጋ ነው!

Good Christian Books Shelf

12 Nov, 05:54


“በግርግም ሆኖ እናከብረዋለን፣ በመስቀሉ ላይ እናከብረዋለን፣ በመቃብሩም እናከብረዋለን።
ለኛ ለደካሞች ሕፃን የሆነውን፣ ለሃጢአታችን የሞተውን፣ ሊያጸድቀንም ከሙታን የተነሳውን እርሱን እናከብረዋለን።
ከሰብአ ሰገል ጋር በአምልኮት እናከብራለን፣ ከቅዱስ ስምዖን ጋር ሕፃኑን አዳኝ ነህ እንለዋለን፣
ስለዚህም "አቤቱ፥ የዘረጋውን ምሕረትህን በቤተ መቅደስህ መካከል እንቀበላለን።”
ቅዱስ በርናርድ

Good Christian Books Shelf

11 Nov, 17:38


በቲክቶክ መንደር በዚህ እንገኛለን😁😁
ሃገራቹ በቲክታክ የሆነ ባለሟሎች ወደ ቤታችን ጎራ ብላችሁ ጠበል ጣድቅ መቅመስ አትርሱ ደግሞ😃😊

https://www.tiktok.com/@reformed_faith?_t=8rHw8LU16G7&_r=1

Good Christian Books Shelf

11 Nov, 14:16


ሶስት ጉራማይሌ የሆኑ የስልጣን እርከን😀
1 ዲያቆን፣ ፕሪስት፣ ቢሾፕ፣ አርክቢሾፕ፣ ፓትሪያልክ፣ ካርዲናል፣ ፖፕ…..
2 መቶ አለቃ፣ ሺህ አለቃ፣ ሌተናንት፣ ኮሮኔል፣ ሜጀር ጄኔራል፣ ጄኔራል፣ እታማዦር ….

3 ወንጌላዊ፣ መጋቢ፣ ፕሮፌት፣ ማይነር ፕሮፌት፣ ሜጀር ፕሮፌት፣ አፖስትል፣ ማን ኦፍ ጋድ….

የመጀመሪያውን የስልጣን ተዋረድ በተመለከተ መጸሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው፣ ታሪካዊና ቤተክርስቲያናዊ ትውፊት ያለው፣ ርቱእ የሆነውን አስተምህሮ ለመጠበቅ ከዩቲሊቲ አንጻር ፈያጅነት ያለው፣ እንደ ዶክትሪን ልንቀበለው የማንችለው ሃዋሪያዊ ትውፊት ላይ ያልተመሰረተ የስልጣን ተዋረድ…..
በነገራችሁ ላይ መጸሃፍ ቅዱሳችን ከዲያቆንና ፕሬስቤተርስ ውጪ ሌሎችን አያውቃቸውም። ከላይ የተጠቀሱት ከሁለቱ በቀር ሁሉም ሰዋዊና ታሪካዊ ፈጠራዎች ብቻ ናቸው


ሁለተኛውን የስልጣን ተዋረድ በተመለከተ ቅቡልነት ያለው፣ እንደ ዜጋ የስልጣን ተዋረዱን ለሚሰጥ ሆነ ለሚቀበል አካል ልንታዘዝ የሚገባ የስልጣን እርከን….
በነገራችሁ ላይ የሸልፋችን እታማዦር ሹም ሆኖ ማገልገል ለሚፈልግ ሹመት መስጠት እችላለሁ😃😃

ሶስተኛዋ በቅርቡ ከኢቫንጄልካል አለም በቅርቡ የበቀለች የስልጣን እርከን ስትሆን ታሪካዊ ዳራ የሌላት፣ ከመንደር ፈጠራ የማትሻገር የብዝነስ ጭዌ፣ የዘረፋ ስልት ነገር ናት😁
በነገራችሁ ላይ ሜጀር ፕሮፌት ወአፖስቶሎ ማን ኦፍ ጋድ በ2030 ለመሆን ለሊትና ቀን እየሰራሁ ነው 😊😊

Good Christian Books Shelf

11 Nov, 06:02


“እውነተኛና “የከበረ የባሕርይ ዕውቀት ትህትናን ይወልዳል እንጂ ከትእቢት ጋር ኣይዳቀልም።”

Good Christian Books Shelf

09 Nov, 14:37


“In an excellent little book entitled All of Grace, the great Baptist preacher Charles Haddon Spurgeon wrote, "Faith is not a blind thing; for faith begins with knowledge. It is not a speculative thing; for faith believes facts of which it is sure. It is not an unpractical, dreamy thing; for faith trusts, and stakes its destiny upon the truth of revelation.... Faith... is the eye which looks.... Faith is the hand which grasps... Faith is the mouth which feeds upon Christ."
James M

Good Christian Books Shelf

09 Nov, 05:38


“በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።”


“እኔ በወንጌል ቃል አላፍርምና። ምክንያቱም በመጀመሪያ የወንጌል ቃል አይሁዳዊያንን ቀጥሎ አረማዊያንን፤ የሚያምኑትን ሰዎች ሁሉ ማዳን የሚችል የእግዚአብሄር ሃይል ነው። ይህም የወንጌል ቃል እግዚአብሄር ሰዎችን የሚያጸድቀው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በእምነት መሆኑን ይገልጣል። ምክንያቱም ጻድቅ ሰው በእምነት ህይወትን ያገኛል ተብሎ ተጽፏል።”
ሮሜ 1: 16/7

Good Christian Books Shelf

08 Nov, 20:59


የህጻናት ጥምቀት ላይ አጠር ያለች audio ሰርተናል። ለምትፈልጉ @christiandogmatics ላይ ታገኛላችሁ 😀

Good Christian Books Shelf

08 Nov, 14:19


"If you could ask thousands in hell, what madness brought them thither? they would most of them answer, “We thought we were sure of being saved till we found ourselves damned. We would have been more earnest seekers of regeneration and the power of godliness, but we verily thought we were Christians already. We have flattered ourselves into these torments, and now there is no remedy.”
Richard Baxter

Good Christian Books Shelf

08 Nov, 06:55


“The fullness of our happiness, beyond which there is none else, is this: to enjoy God the Trinity in whose image we were made”
St. Augustine

Good Christian Books Shelf

07 Nov, 17:30


“እግዚአብሄር አምላክ እኛን በመውደዱ፣
በዘላለም ምክሩ በበጎ ፍቃዱ፡፡
ውድ ልጁን ልኮ ከኃጢአት አዳነን፣
ገንዘቡም ሊያደርገን ዋጋ ከፍሎ ዋጀን፡፡
መዳኒታችን ከኣመጽ ተቤዠን
በደሙ አንጽቶ ለራሱ ቀደሰን፣
የመንግስቱም ወራሽ ወገን አደረገን!”
ዘማሪ ወመጋቢ ጋሽ ተስፋዬ ጋብሶ

Good Christian Books Shelf

07 Nov, 06:29


የባዜልና የግሪጎሪ ኦፍ ኒሳን የስላሴ መረዳት በትክክል ያልተገነዘበ ሰው ወደ ዳይናሚክ ሞናርኪያንዝም (አሪያንዝም) የመግባት እድሉ ከፍተኛ ነው። የአውገስቲንና የአኪውናስን የስላሴ መረዳት በትክክልም ያልተረዳ ሰው ደግሞ ወደ ሞዳሊስቲክ ሞናርኪያኒዝም ሰተት ብሎ የመሄድ እድሉ ከፍ ያለ ነው። ለምሳሌ ያህል… በኔ ጥናትና ቁንጽል ኢምፔሪካል ማስረጃ መሰረት…
በኛ ሃገር ወደ ጆቫ ምስክሮች የሚገቡት በብዛት ከኦርቶዶክስ አማኝ ሲሆኑ፤ የኦንሊ ጂሰስ ቤተ እምነት ደግሞ የሞሉት ከጴንጤ ማህበረሰብ በሚሄዱ ግለሰቦች ነው። የሁለቱ ቤተ እምነት መሰረት በጥቂቱና በንድፈ አሳብ ደረጃ ከላይ የጠቀስኳቸውን አባቶችን መሰረት ማድረጋቸውን ልብ ይለዋል።
ስለዚህ ጤናማ የስላሴ መረዳት አንዱን መለኮታዊ ባህሪ ከሶስትነታዊ አካል ጋር ለመያዝ በሁለቱም በኩል ያለውን የስላሴ ሞዴሎችን ብናጠናቸው ጥሩ ይመስለኛል። በዚህም መሰረት ምን እያልሁ ነው? የሳባሊያኒዝም ርዝራዥ መረዳት ላላቸው ክርስቲያኖች እነ ባዜልና ኒሳን እንዲያነቡ እየመከርሁኝ ነው😀
የአሪያንዝም የስላሴ መረዳት ውስጥ የነበረና ወደ ትሪኒቴሪያን አማኞች ለተጨመረ ሰው አውገስትንና አኪውናስን እንዲያነብ ደግሞ በበለጠ እመክራለሁ😀😀

Good Christian Books Shelf

06 Nov, 19:25


ጋይስ በዚህ ላይ audio ቢሰራበት የምትሉት ርእስ ካላችሁ እስቲ ጻፏትና ከቻልንበት እንሰራበታለን 😁

Good Christian Books Shelf

06 Nov, 15:08


"Treachery is never more treacherous than when it leads a man to stab at a doctrine which he has solemnly engaged to uphold, and for the maintenance of which he receives a livelihood."
-- Charles Spurgeon

Good Christian Books Shelf

06 Nov, 09:55


በዌስትሚኒስተር የእምነት ድንጋጌ ላይ በተደነገጉ ስለ ሳክራመንት በሚያወሩ አናቅጾች ላይ የተሰሩ ሶስት ክፍል ማብራሪያ በቮይስ ከፈለጋችሁ @christiandogmatics ላይ ታገኛላችሁ 😀

Good Christian Books Shelf

05 Nov, 17:58


የምርጫ ትምህርት…….
1 የእግዚአብሄር አሳብ ከ አእምሮአችን በላይ መሆኑን ይነግረናል
2 እግዚአብሄር ለሰዎች ያልገለጠ ብዙ ምስጥራት እንዳሉ ያረጋግጥልናል
3 በኛ በሰዎች አእምሮ መመርመር የማንችላቸው የእግዚአብሄር የልቡ አሳቦች እንዳሉ ያሳየናል።
4 እኛ ሰዎች ያለንን ትምክህታችንን ጥለን በባዶ እጃችን ወደ ጸጋው ዙፋን እንድንቀርብ ያስተምረናል።
5 እግዚአብሄር አስቀድሞ እኛን በመምረጡ የገለጠውን የዘላለም ፍቅሩን በመረዳት እርሱን እንድንወደው፣ በበለጠ ደግሞ በሁለንተናችንን እንድናመልከው ያግዘናል።
6 የተመረጡ ወንድሞቻችን ከሁሉ በላይ እንድንወዳቸው፣ በምስጥራት በኩል የመመረጣችንን በረከቶችን በመቀበል በመንፈስ እንድንተሳሰር ያሳስበናል።
7 ይህ ትምህርት በጸሎት እንድንተጋ፣ ወንጌልን ለሌሎች በጨለማ ላሉት እንድናደርስ፣ በህይወታችን ውስጥ የሚገጥሙንን ችግሮችን በትግእስት እንድናልፍ ብርታት ይሰጠናል።
8 ይህንን ትምህርት ለክርክር፣ የተገለጠውን የእግዚአብሄር ልጅ ህይወቱን በተቋደሱ በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ለክፍፍፍል መጠቀም የምርጫ አምላክ የሆነውን አባታችንን ማሳዘን ነው።
9 የምርጫ አሳብ ተመራጩን አካል ሳይሆን መራጩን አካል እንድናከብር፣ ለ ሉአላዊነቱ እንድንበረከክ የሚያደርግ ነው።
10 በመጸሃፍ ቅዱስ የተገለጠውን ይህንን አስተምህሮ አለመቀበል ትምክህተኝነት ነው፣ በቃሉ ላይ ማመጽ ነው፣ ከእግዚአብሄር በላይ ራስህን ልኡል አድርጎ ማቅረብ ነው!

Good Christian Books Shelf

05 Nov, 12:59


በምርጫ ሰሞን ክርስቲያኖች ልናስባቸው የሚገቡ 10 ነጥቦች በወንድም ዘላለም መንግስቱ የተተረጎመ….

1. መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ከምንም አገር ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር አታስተካክል። የሁለቱን፥ ማለትም የእግዚአብሔርን መንግሥት እና የምድራዊ መንግሥታትን ልዩነት ጠንቅቀን ማወቅ አለብን፤ ሁለቱን ማደባለቅ የለብንም፤ (ዮሐ. 18፥36፤ ማቴ. 6፥33)።
2. ለፖለቲከኞች የመሢሕ [ወይም የታዳጊ] ስፍራ አንስጣቸው። ብዙውን ጊዜ ሰዎች ፖለቲከኞች በገዛ እጃቸው ዲበ ፍጥረታዊ የሆነ ማኅበራዊ ውጤት የሚያመጡ ይመስላቸዋል። እኛ አንድ ጌታ አለን፤ እናም ፖለቲከኞችን ገደብ ወደሌለው ከፍታ ለማውጣት መሞከር የለብንም፤ (ማቴ. 7፥15፤ 1ጴጥ. 3፥15)።
3. ለምርጫ ስንወጣ ድምጽ ብቻ አንስጥ፤ ለፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችም እንጸልይ። ክርስቲያኖች የሚደግፏቸውን ፖለቲከኞች ለመባረክና የነዚህን ተቃዋሚዎች ደግሞ ለመርገም ይፈተናሉ። ልብ እንበል፤ እኛ ለጠላቶቻችንም እንኳ እንድንጸልይ ተነግሮናል፤ (1ጢሞ. 2፥1-2፤ ማቴ. 5፥44)።
4. እኛ የምንፈልገው መሪ ወይም የፖለቲካ ቡድን ካላሸነፈ የዓለም መጨረሻ ነው ብለን አናስብ፤ የእኛ የመጨረሻው ዋስትናችን ያለው በማይናወጠው በእግዚአብሔር መንግሥት መሆኑን አንርሳ፤ (ዕብ. 12፥26-29)።
5. የደጋፊ / ነቃፊ ፖለቲካዊ ወገንተኝነትን ወደ እግዚአብሔር ቤተ ሰብ ውስጥ አናምጣ። እያንዳንዱ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ፊት የኅሊና ነፃነት አለውና ፖለቲካዊ አመለካከታችን ቤተ ክርስቲያንን እንዲከፍል መፍቀድ የለብንም፤ (ሮሜ 16፥17፤ 1ቆሮ. 1፥11-12)።
6. ሰዎችን አናሰይጥን ወይም አካይስታዊ አናድርግ። ማንም ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነውና እንደ ክርስቲያንነታችን ከፖለቲካዊ አቋሙ ጋር ብንስማማም ባንስማማም ሰውን ሰይጣናዊ ወይም ከሰውነት የወረደ ፍጡር አናድርግ፤ (ቆላ. 3፥8፤ ያዕ. 4፥12)።
7. በንዴትና በጠላትነት አተካራ ውስጥ አንግባ፤ ይልቅስ ፖለቲካዊ እምነታችንን ጨዋነትን በተሞላ ክርክርና አእምሮአዊ በሆነ የእርስ በርስ ንግግር (dialogue) ማቅረብ አለብን። የጥላቻ አተካራ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያዋርድ አስቀያሚ ትዕቢትን የሚገልጥ ባህርይ ነው፤ (ያዕ. 1፥19-20፤ 1ጢሞ. 2፥14)።
8. የማንነት ነፃነትህን እስክታጣ ድረስ በአንድ የፖለቲካ ጎራ ውስጥ ተጠላልፈህ አትታሰር። ይህን ካደረግህ በፖለቲከኞችና በፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት ስትናገር የመደመጥ ዕድልህን ታጣዋለህ፤ (1ጢሞ. 3፥15፤ ሮሜ 3፥4)።
9. በዘር ወይም ጎሳ፥ በጾታ፥ በሀብት፥ በዕድሜ የሚለያይ ከፋፋይ ፖለቲካ ከአንድነት ይልቅ መለያየትን የሚያመጣ ነው። ክርስቲያኖች በሕዝባዊ አደባባይ የሰላምና የእርቅ መሣሪያዎች መሆን አለባቸው እንጂ ለፖለቲካዊ ጥቅም ሕዝብን ከሚከፋፍል ቡድናዊ የስሜት ፈተና ሊጠበቁ ይገባል፤ (ማቴ. 5፥9፤ 2ቆሮ. 5፥18-19)።
10. ጨለማውን መርገም ብቻውን መፍትሔ አይደለም፤ [በአብሪነት] መጋፈጥ አለብን። የእግዚአብሔር መንግሥት አመለካከት ያላቸው ክርስቲያኖች ተልእኮ የዓለምን ጨለማ መራገም ሳይሆን እንደሚያበራ መብራት እና ሳይበላሽ እንደሚጠብቅ ጨው በመሆን፤ እንዲሁም መልካም በማድረግና ክፋትን በማሸነፍ የእግዚአብሔርን እውነት ብርሃን በማካፈል የሕዝብን የጋራ ደኅንነት መጠበቅ ነው፤ (ማቴ. 5፥13-16)።
እነዚህ አንኳር ነጥቦች ክርስትናችን እንደተጠበቀና ነፍሳችን ሳትጎሳቆል ፖለቲካዊ አቋማችንን ወይም አመለካከታችንን በጨዋነት ማካፈል እንድንችል ብልጭታ ሊሰጡን ይችላሉ ብዬ አምናለሁ። ፖለቲካዊ ንግግርና ጽሑፍ ከክርስትና መስመርም እንኳ ሊያንሸራትት የሚችል ጉልበት አለውና ክርስቲያኖች ወደ ፖለቲካ መስክ ሲገቡ ብቻ ሳይሆን አሳባቸውን ሲገልጡም ጥንቃቄ ሊያደርጉ የሚገባው ጉዳይ ነው።

Good Christian Books Shelf

04 Nov, 16:43


ነገረ-ኤርፎን (ኤርፎኖሎጂ)
ግቢ ሆኜ ካናዳ የሚኖር ከኣንዱ የፌስቡክ ጓደኛዬ ጋር ተዋወቅን። በእንቦክስ ማውራት ጀመርን። በኣሳብ ተግባባን። መንፈሳዊ ነገሮችን ኣውርተን ስለነበር ደስ ብሎት ካልጸለይሁልህ ኣለኝ። ቁጥር ተለዋውጠን በኢሞ ተደዋውለን ጸለየልኝ። ከዚያ በኋላ በሶስተኛ ቀን ምን ብለኝ ጥሩ ነው? ምን ከዚህ ከካናዳ ልላክልህ? ኣለኝ። በመጀመሪያ ሁሉም በሃገር ውስጥ ስላለ ምፈልገውና ምጠይቅህ ነገር የለኝም ብዬ እምቢ ኣልሁት። ተቆጣኝ። ለምን እንዲህ ትሆናለህ? ለስጦታ እንዲህ ኣይባልም። ይልቁን ደስ እንድለኝ የምልክልህን ነገር ንገረኝና ላሰናዳ ኣለኝ። እኔም ብዙ ነገር ካሰብሁኝ በኋላ ትልቁን ችግሬን ነገርኩት።
ከቻልህ ጥሩ ኤርፎን ላክልኝ። ይህን ከላክልኝ ሌላ ምንም ኣያስፈልገኝም ኣልሁት። ማሾፍበት መሰለው። ለጊዜው ኣውንታዊ መልሱን ሰጥቶኝ ወደ መንፈሳዊ ጫወታችን ተመለስን።
ኤርፎን በማለቴ እንደደበረው በንግግሩ ያሳብቅበታል። ሳቅታ የነበረው በኣንዴ ቀዝቀዝ ኣለብኝ። የእንቅልፍ ሰኣትም እንዳያልፍ ተኛ ብሎኝ ተለያየን። ከዚያ በሳምንቱ በእንቦክስ ሰላም ኣልሁት። ኣልመለሰልኝም። በኢሞም ደጋግሜ ደወልሁለት። እንዳላየው ኣለፈኝ። እንዳኮረፈኝ በመረዳት ተስፋ በመቁረጥ ኣልጨቀጭቀውም ብዬ ተውሁት። ከዚያ ቀን ጀምረን መልሰን ኣልተነጋገርንም። ሰሞኑን ደግሞ ኣንዱን ጠይቄዋለሁ። ይላክልሃል ተቢዬ በጉጉት በመጠበቅ ላይ ያ.ሁ.ነ.ያ
***ከኤርፎን ጋር ፍቅር የያዘኝ በልጅነቴ ነበር። ከልጅነቴ ጀምሮ ሬዲዮ በመስማት ነው ያደግሁት። ያለ ኤርፎን ሬዲዮ መስማት ደግሞ ነውር ነው። ሰው ይረበሻል። ኣንተ ምትሰማውን ፕሮግራም ኣጠገብህ ያለው ሰው ላይመቸው ይችላል። ያለ ፍላጎቱ የማይፈልገውን ኣስገድደህ ማሰማት ደግሞ ኣስገድዶ ከመ**ር ኣይለይም። ካደግሁም በኋላ ይህን የልጅነት ባህሌን ሌጋሲውን ኣስቀጠልሁ። ቤት ውስጥ በኤርፎን መዝሙር፣ ስብከት፣ እና ኤፌሞችን እሰማለሁ። በታክሲም ሆነ የህዝብ መጓጓዣ ስጠቀም ያለ ኤርፎን መንገዱ ራሱ ኣይሄድልኝም። የሸገር ታክሲ ደግሞ ሁላችሁም እንደምታውቁት ኤርፎን ከሌለህ የሚከፈቱት ሙዚቃዎች ጆሮህን ራሱ ማደንቆሩ ነው።
ኤርፎኔ በምግብ ቤት፣ በእንተርኔት ካፌ፣ በመጽሃፍ ቤት፣ በቢሮ እና በሌሎች ቦታ ተለይቶኝ ኣያውቅም። ኤርፎን በማለዳ ከእንቅልፍ እንደነቃሁ ኣሃዱ ብዬ መጠቀም ከጀመርሁ እስከ እንቅልፍ ይዞኝ እስክተኛ ድረስ ከጆሮዎቼ ኣይወርድም። ኤርፎን ከሌለኝ ይደብረኛል። ጸዴ ድብርት ነው የምር የሚወርረኝ። ያለ ኤርፎን የሰማሁት ነገር ራሱ ትንሽ ቆይቼ እንዳልሰማሁት ነው የሚሰማኝ። በተለይ ፒሲዬን ከከፈትሁ ያለ ኤርፎን ስራዬን መስራት ኣይታሰብም። ግቢም ገብተን ማህበራዊ ኣነዋወር ስለነበረ ኑሮኣችን ኤርፎን መጠቀም ተገቢ ከብልህ ሰው የሚጠበቅ ስለነበር ኣካሄዴን ኣልቀየርሁትም። በስራ ቦታዬም ላይ የተለየ ነገር ኣላመጣሁም። እንደ ቀደመው ከኤርፎኔ ጋር ጉዞዬን ቀጥዬኣለሁ። ኤርፎን የሌለኝ ጊዜ በቃ ስራ መስራት ኣልችልም። ኣያቹልኝ ኣይደል ምእመናን? የኤርፎን ኣጠቃቀሜ ስራዬ ላይ ተጽእኖ እስከመፍጠር ሲደርስ? Smile emoticon
***ለጆሮዬ ከምንም በላይ እጠነቀቃለሁ። ኣጠቃቀሜ ኣነስተኛ የድምጽ volume ላይ በማድረግ ነው። በተጨማሪም ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ጉዳቱን በማጥናት ነው የምጠቀመው። ስለዚህ እንደምክር ኤርፎን ኣታብዛ ጆሮህን ይጎዳል የሚለኝ ምእመን ካለ ጤናማ ኣጠቃቀም እንደሆነ የኔ የኤርፎን ኣጠቃቀም ላስታውሳችሁ ይህን እላለሁ።
የሃገር ውስጡን ያልሞከርሁት ኤርፎን ያለ ኣይመስለኝም። በኣመት በቁጥር ልገለጥ የማይችል የኤርፎን ብዛት መንግስታችን ይሸምታል። ከምግብ፣ ከልብስና ከቤት ክራ ቀጥሎ ትልቁ ወጪዬ የሚወጣበት በኤርፎን ላይ ብል ማጋነን ኣይሆንብኝም። ኣስፈላጊነቱም ከነዚህ ከ ቤዚክ ኒድስ ቀጥሎ እጅግ ወሳኝ ነገር እንደሆነ ባለፉት በኣስር ኣመት ውስጥ በተግባር ያየሁት ይመስለኛል። ሃይፐርቦሊ እንዳይሆንብኝ እንጂ ኣይቻልም እንጂ ሰውን ራሱ በኤርፎን ባናግር ደስ ባለኝ። grin emoticon
የነገሩ ፍጻሜ ሶስት ነገር…
1…. ኤርፎን ከመውደድ የተነሳ ኣንዴ ግቢ የማላውቀው ተማሪ ምን ታጠናለህ? ምን ዲፓርትመንት ነህ? ብሎ የጨዋ ጥያቄ ጠየቀኝ
እኔም…. የማጠናው ኤርፎኖሎጂ ይባላል። በፍልስፍና ዲፓርትመንት ስር ነው የሚገኘው ምናምን ብዬ የክፍለ ዘመን ውሸት ወቀልድ ተናግሬኣለሁ።
ይህ ከምን የተነሳ ነው? ከ ኤርፎን ሱሰኝነት ኣይደለምን?
2… ኣንድ ኤርፎን በማስታውሰው ከሶስት ወር በላይ ቆይቶልኝ ኣያውቅም። ብዙ ወር የቆየልኝ ኤርፎን ከጓደኛዬ ስር የሰረቅሁት ኤርፎን ነው። (የስርቆት ነገር ይጣፍጣል የሚባለውን ኣባባል በእውኑ ኣይቻለሁ) grin emoticon
3… ውጪ ያላችሁ ወዳጆች መጽሃፍ እንድትልኩልኝ ኣልጠይቃችሁም። ግን ኤርፎን እንድትልኩልኝ እጠይቃቸዋለሁ። በሃገር ውስጥ ያለውን የኤርፎን ኣይነት ሁሉንም ሞክሬ ተስፋ ስላስቆረጠኝ ነው የማስቸግራችሁ smile emoticon

Good Christian Books Shelf

04 Nov, 13:52


አባ እስጥፋኖስ (ጸዴ አያታችን) ላይ ጋቪን አሪፍ ቪዲዮ ሰራ እኮ 😁😁
የምር አሪፍ አድርጎ ነው ያቀረበው። ከፕሮፍ ጌታቸው መጸሃፍ ላይ ተመስርቶ የሆነ ስለ አባ እስጥፋኖስ የተሃድሶ እንቅስቃሴ ለማሳየት ጥረት አድርጓል። ሃገርኛ ቃላትን ሲናገር ደግሞ ደስ ሲል ሎል ጉንዳጉንዶን ምናምን ሲል በቃ ሳቄን መቆጣጠር አቅቶኝ ነበር 😀
እየገባችሁ ኮመንት ቦክሱ ላይ ከአባ እስጢፋኖስ ሃገር ነኝ በሉት ኮመንቶችን ያነባል😁
ጋሽ ዘበነ ደግሞ መልስ ካልሰጠሁ ብሎ መጥቶ እንዳያለቃቅስብን 😃

ቀጥሎ ደግሞ ከኦሬንታል ጋር የተደረገ ውይይት ሼር አደርጋለሁ ብሏል። ሰምተን ደግሞ ስለ ጎረቤቶቻችን በስም ሳይሆን በተግባር የምናውቀውን እንዴት ሪፕሬዘንት እንዳደረጋቸው እናያለን ማለት ነው ሎል

https://youtu.be/EdGwhsh9pTg?si=0p-3bbzZN_5aqQEo

Good Christian Books Shelf

04 Nov, 05:22


ሮሜ 1_8-15

Good Christian Books Shelf

03 Nov, 18:22


ከፍ ያለ የነገረ ሚስጥራት እና ቤተክርስቲያን መረዳት ባለው፣ ለታሪካዊው ክርስትና እና የክርስቲያን ትውፊት ተገቢውን ቦታ በሰጠው እና ፈፅሞ ከታሪካዊ ክርስትና ባልተፋታው "ተሐድሶአዊው ፕሮቴስታንት" (Reformational or classic Protestantism) እና ሚስጥራት ጠለ በሆነ እና ከታሪካዊው ክርስትና በብዙ በተፋታው "ዘመናዊ" ፕሮቴስታንትነት መካከል ያለውን ልዩነት ሆን ብለን እና ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ አጉልተን ማሳየት ያለብን ጊዜ ላይ የደረስን ይመስለኛል።


ይህን በውጤታማነት የምናደርግበት ብቸኛው መንገድ ደግሞ ይህ ጉዳይ የገባን እና ያሳሰበን ሁላችን በሚቻሉ መንገዶች ሁሉ በመሰባሰብ፣ እርስ በእርሳችን በመተሳሰር ("ኔትዎርክድ" በመሆን)፣ በርካታ የመፅሐፍ ቅዱስ ማጥኛ ብድኖችን በመመስረትና በመምራት በፍፃሜውም በእውነተኛ የፕሮቴስታንትነት መርህ የሚመሩ ትንንሽ እና በርካታ አጥቢያ ቤተክርስትያናትን በየስፍራው በመትከል ነው! ከዚህ ውጭ በተናጥል እና በሶሻል ሚድያ በምንጮኸው ጩኸት ብቻ የምንፈጥረው አንዳች ነገር አይኖርም!

ተሐድሶአዊ ፕሮቴስታንትነት ተሐድሶአዊ በሆኑ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት በኩል ይለምልም!

Good Christian Books Shelf

03 Nov, 07:24


“አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።
ውኆቻቸው ጮኹ ተናወጡም፥ ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ። የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ፤ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ። እግዚአሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል።
አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተመለሱ፤ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች። የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ። እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነት ይሽራል። ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቈርጣል በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል። ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው”
በቆሬ ልጆች የተዘመረ መዝሙር፣ በዳዊት የመዝሙር ክምችት ውስጥ በ46ኛ መዝሙር ላይ የሚገኝ

Good Christian Books Shelf

02 Nov, 19:44


ሶሻል ሚዲያ ላይ በእቀበተ እምነት የምትሰሩ ኦርቶዶክሶች አንዳንዴ ስትናገሩ እባካችሁን እየተጠነቀቃችሁ።
ሁሉን ነገር አጋንንታዊ፣ ምንፍቅና፣ ሃሰተኛ ምናምን ስትሉ ታስቁኛላችሁ😁
የ ሺህ አመት አስተምህሮ አጋንንታዊ ምንፍቅና ነው የምትሉ ሎል የአባባ ጋስጫ አጥንት እንዳይወጋችሁ ተጠንቀቁ 😃

Good Christian Books Shelf

02 Nov, 13:52


“To pray without laboring is to mock God: to labor without prayer is to rob God of His glory. Both prayer and labor ought to go together.”
Robert Haldan

Good Christian Books Shelf

02 Nov, 11:35


ለማስታወስ ያህል……
ማታ ከ2 ሰአት ጀምሮ የሮሜ ጥናታችን በላይቭ እንቀጥላለን። የዛሬው ጥናታችን ሮሜ 1: 8/15 ላይ ይሆናል።
ከመጣችሁ የሆነ ነገር ታተርፋላችሁ 😁😁

Good Christian Books Shelf

02 Nov, 06:02


እነሆ ስምንተኛው ምዕራፍ...
ከጥቂት ወንድሞች ጋር “ተሓድሶው ሲታወስ” ብለን መርኅ ግብር መከወን ከጀመርን ስምንት ዐመት ሞላን። የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያችንን በመቃኘት ከየት እንደወደቅን ማስተዋልና መጠየቅን ማበረታት ነው። የዘመኗ ቤተ ክርስቲያን ማንነቷንና ግብሯን ካደበዘዙባት ባዕድ አስተምህሮዎችና ልምምዶች እንድትጠበቅ ውስጧን እንድትፈትሽ ማስቻል ነው። ምናልባት ጥቂት የማንቂያ ደውል ከሆነ በሚል።
እውነተኛ ተሓድሶ ጠያቂ ነው። ምዕመኑ የሰማውንና ያየውን ሁሉ በቅን መንፈስ እንዲመረምር ያበረታታል። እንደ ቤሪያ ሰዎች “ነገሩ እንደዚህ ይሆንን?” ብሎ መጠየቅ የተሓድሶ መለያ ባህሪ ነው ። “አሜን” ከማለት በፊት “ምን? ለምን? እንዴት?” እንድንል ያስታውሰናል። እስትንፋሰ መለኮት ያለባቸውን ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደ ቱምቢ ዋቢ አድርጎ ይጠራል። ለመንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት የመምራት ዐቅምና ችሎታም ዕውቅና ይሰጣል።
በመካከለኛው ዘመን በሮም ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት መጻሕፍት ተደራሽነት በውስን የቤተ ክህነት ሰዎች አከባቢ ስለታጠረ፥ የሰዎች ወግና ሥርዐት ከቃሉ በላይ ቅቡል ነበሩ ። ይኼም ብዙ ብልሽት አስከትሏል ። ስለ እምነታቸው የማያውቁና የማይጠይቁ አያሌ ምዕመናን አፍርቷል ። በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያኗ በብዙ መንፈሳዊና ሞራላዊ ዝቅጠት ውስጥ ተዘፈቃለች ። ለምሳሌም፡ ፖፑ ለምእመኑ የኅጢአትን ይቅርታ ሰነድ እስከመሸጥ ድረስ ደርሶ ነበር። የመንግሥተ ሰማይን መግቢያ ቊልፍም በእጁ እንደያዘ ይታመን ነበር።
የዛሬ 508 ዓመት በጀርመናዊው መነኩሴ፥ ማርቲን ሉተር ፈር ቀዳጅነት የተቀጣጠለው የተሓድሶው እንቅስቃሴ (The Reformation) በጥያቄ ነበር የጀመረው። በዋናነት “የወደቀው የሰው ልጅ በቅዱሱ እግዚአብሔር ፊት እንዴት ሊጸድቅ (እና ሊቆም) ይችላል?” በሚል ወሳኝ ጥያቄ ነበር። በርግጥ የጥያቄው መልስ ዐዲስ ነገር አላመጣም። ይልቁንስ ከተዳፈነው እውነት ላይ አቧራው እንዲራገፍና በጭጋጉ ላይም የቃሉ ብርሃን እንዲፈነጥቅ ምክንያት ሆነ። ምስባኩን ለቃሉ ፍጹም ሥልጣን በማስገዛት ቀደሰው ። ቤተ ክርስቲያንን ወደ እውነተኛ አምልኮና የወንጌል ተልዕኮዋ መለሰ። ከዚያም በኋላ ብዙ ፈያጅ ጥያቄዎች ቤተ ክርስቲያንን ከእንቅልፏ እያባነኗት ወደ መስመር ሲመልሷት ከታሪክ ድርሳናት አንብበናል። ላቲኑ “Ecclesia reformata, semper reformanda” እንዲል!
በዘንድሮው 8ኛው የተሓድሶ ሲታወስ መርኅ ግብር “የወንጌላቱ ኢየሱስ” ብለን ወደ ቀደመው እውነት ለመመለስ እንማትራለን። ይህንን ማወቅስ ከወደቅንበት ለመነሳት ፋይዳው ምንድነው ብለን እንጠይቃለን። ቅን ጥያቄ ባለበት በዚያ እውነተኛ ተሓድሶ (የግለሰብም የማኅበርም) ያቆጠቊጣል ብለን እናምናለን!
ዛሬ (ጥቅምት 23) በ8፡30 ሰዓት
በካዛንቺዝ ዑራኤል መካነ ኢየሱስ እንገናኝ!
የወንጌላውያን ተሓድሶ እንቅስቃሴ።

Good Christian Books Shelf

01 Nov, 17:01


እግዚአብሄር የሚታወቀው ባለመታወቁ ሳይሆን በመታወቁ ነው። በመታወቁ በበለጠ ታወቀ። ባለመታወቁ በበለጠ አለመታወቁን ነገረን። አውቀነው እንወደውና እናመልከው ዘንድ መታወቁን በመገለጡ አሳወቀን። ባለመታወቁ በበለጠ እንድንፈራውና ምጡቅ መሆኑን በመገለጡ አለመታወቁን አወቀን።
የሰወረውን እንድናውቅ ፍቃድ አልተሰጠንም። የገለጠውን ልናውቅ ፍቃዱ ሆነ። ባወቅነው ቁጥር በርሱ እየተደሰትን፣ በፊቱ በተሰበረ ልቡና እያመለክን እንድንኖር የማወቅ ብርሃን በውስጣችን በመንፈስ ቅዱስ አበራልን። እርሱን ማወቅ የዘላለም ህይወትን ማጣጣም ነው። እርሱን አለማወቅ የዘላለም ጥፋት በራስ ላይ ማከማቸት ነው።
በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ወልድን አወቅን፣ በወልድ እውቀት ከሁሉ በላይ የሆነውን አብን አወቅን። ከአብ በሆነው እውቀት ልጁን እንድናውቅ በመንፈስ ቅዱስ እውቀት ሰጪነት የእውቀት ብርሃን ተቀበልን። በዚህም ምክንያት መንፈስ ቅዱስ አብና ወልድን ወደ ማወቅ አማኞችን የሚያመጣና አማኞችንም በአብና በወልድ ውስጥ ለዘላለም እንዲጨመሩ የሚያደርግ እውቀት የሚሰጥ መለኮታዊ አካል ነው

Good Christian Books Shelf

01 Nov, 15:12


“From the day whereon I renounced the things of the world to consecrate my soul to luminous and heavenly contemplation, when the supreme intelligence carried me hence to set me down far from all that pertains to the flesh, to hide me in the secret places of the heavenly tabernacle; from that day my eyes have been blinded by the light of the Trinity, whose brightness surpasses all that the mind can conceive; for from a throne high exalted the Trinity pours upon all, the ineffable radiance common to the Three. This is the source of all that is here below, separated by time from the things on high.... From that day forth I was dead to the world and the world was dead to me.”
Gregory Nazianzen

Good Christian Books Shelf

31 Oct, 18:27


ሸልፈኛው ቲክቶክ ጠርቶኛል እያለ ነው ሎል እስቲ እየገባችሁ ፎሎ አድርጓት 😁😁 በተሃድሶ ቀን የተጀመረ ነገር ሌላ ተሃድሶ ሳያመጣ አይመለስም 😁
የኔ
በሆኑ ቀናት ውስጥ 1ኬ ካላስገባቹት ወደ እናት ቤተክርስቲያን እሸበለላለሁ 🤣
ደግሞ የቤተክርስቲያን ጥናት የምንጀምርባት ይሆናል
https://www.tiktok.com/@reformedfaith5?_t=8r0fMEaK9wQ

Good Christian Books Shelf

31 Oct, 06:13


እንኳን አደረሰን ዘመዶቼ 🤗🥰

Good Christian Books Shelf

30 Oct, 17:13


“The summary of the gospel is that our Lord Jesus Christ, the true Son of God, has revealed the will of his heavenly Father to us, and with his innocence has redeemed us from death, and has reconciled us with God. Therefore, Christ is the only way to salvation for all those who have been, are, and will be።”
Ulrich Zwingli

Good Christian Books Shelf

30 Oct, 08:39


“Christianity is the only philosophy which I have found certain and adequate.”
Justin Martyr

Good Christian Books Shelf

30 Oct, 05:47


ተሃድሶው መጸሃፍ ቅዱስ ብቻ ሲል ሃዋሪያዊውን ትውፊት በማግለል አይደለም….
ተሃድሶው ጽድቅ በእምነት ብቻ ሲል ከእምነት መታዘዝ የሚመነጨውን የፍቅር ስራን በማጣጣል አይደለም….
ተሃድሶው መዳን በጸጋው ሲል የሰዎችን ሃላፊነት ያላማከለ አይደለም….
ተሃድሶው የዘላለም ህይወት በክርስቶስ ብቻ ነው ሲል በምስጥራት በኩል የሚገኘውን ጸጋ አሽቀንጥሮ በመጣል አይደለም…..
ተሃድሶው ክብር ለእግዚአብብሄር ብቻ ሲል በቃሉ የመሰረታቸውን ለሁለቱ መንግስታት የሚደረጉና ለወንድሞች የሚደረገውን ክብር በማናናቅ አይደለም…..
ይልቁን የተሃድሶ ነገረ እሳቤ ሃዋሪያዊውን ትውፊት የሚያጎላ፣ መልካም ስራን የሚያደምቅ፣ ከጸጋው ተቀባይ ሃላፊነት የሚፈልግ፣ በምስጥራት በኩል ለምርጦቹ አምላክ ጸጋዎቹን የሚያካፍልና ያህዌ ለመሰረታቸው ለሁለቱ መንግስታት ክብር እየሰጠን ለቅዱሳን ክብር እንድንኖር የሚያደርገን ነው።

Good Christian Books Shelf

29 Oct, 18:26


Amen!🙏🫡 እስቲ ከኒቂያና ከሃዋሪያት ሃይማኖት ድንጋጌ መሃል አንዱን መርጣችሁ ሁሌ በየቀኑ ለመጸለይ ሞክሩ። እኔ ከልጅነቴ እስከ ዛሬ ድረስ ያላቆምሁት አንድ ነገር ምንድነው ቢባል "ጸሎተ ሃይማኖት" የሚለውን በ ግእዝ የኒቂያን የእምነት ድንጋጌ መጸለይ ነው። ለዚህ ጌታዬን አመሰግናለሁ። የምናምነውን እምነት መጸለይ እንዴት አይነት ድንቅ ነገር እንደሆነ 😁😁

Good Christian Books Shelf

29 Oct, 17:23


ለሁለቱ በሪፎርሜሽን ዘመን ለተወለዱ ወንድማሞች ትልቅ ክብር አለኝ! በሚመጡ ዘመናትም በሃገራችን እንዲያብቡ፣ ብዙዎች እንዲያውቋቸው፣ ትምህርቶቻቸው ከሌሎች በበለጠ ደራሽ እንዲሆኑ፣ ወንጌላዊው ወጣት ከሌሎች ነገረ መለኮታዊ እሳቤ ተጠብቆ በነዚህ በሁለቱ ጥላ መከለል እንዲችል ጥልቅ ምኞት አለኝ!

Good Christian Books Shelf

29 Oct, 12:01


በፒሲ ፋይሎቼ መሃል በትክክል የተደራጁ የካቶሊኮች ሜሮሎጂ አላገኘሁም?😀 ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግልኝ ወደ ምርመራ ክፍል ልሂድ መሰለኝ😃
በዚህ ደረጃ ጽድት ያሉትን ፋይሎችማ መላእክቶች በኔ ፋይሎች ውስጥ ሳይሰውሩ አልቀረም 🤣🤣
የካቶሊክ ሜሮሎጂ ደግሞ በምድር ከተፈጠሩ ክፉ አስተምህሮዎች መሃል አንዱ እኮ ነው ሎል በፒሲዬ ላይ በዚህ መንገድ ማግኘቴ የሆነ መልእክት ሳይሆን አይቀርም 😊

Good Christian Books Shelf

28 Oct, 17:41


በማቴዎስ የቅዱሳት መጸሃፍት ሁሉ ፍጻሜ የሆነውን ኢየሱስ፣
በማርቆስ መከራ ተቀባዩን ኢየሱስ፣
በሉቃስ አዳኙን ኢየሱስ፣
በዮሃንስ ስጋ በመልበስ በመካከላችን ድንኳኑን የዘረጋውን ኢየሱስ፣
በሮሜ ሃጢአተኞችን የሚያጸድቀውን ኢየሱስ፣
በቆሮንጦስ በትንሳኤው የፍጥረታት በኩር ሆኖ ሞትን ድል የነሳው ኢየሱስ፣
በገላቲያ ከህግ አርነት የሚያወጣውን ኢየሱስ፣
በኤፌሶን የቤተክርስቲያን ራስ የሆነውን ኢየሱስ፣
በፍልጵሲዩስ ራሱን ባዋረደው መጠን ከፍ ከፍ የተደረገውን ኢየሱስ፣
በቆላስይስ የበላይ የሆነውን የፍጥረት በኩር የሆነውን ኢየሱስ፣
በተሰሎንቄ በአለም ሁሉ ላይ ሊፈርድ የሚመጣውን ኢየሱስ፣
በእብራዊያን ለዘላለም በማይለወጥ ክህነት የተሾመውን ኢየሱስ፣
በያእቆብ የስነ ምግባር አስተማሪ የሆነውን ኢየሱስ፣
በጴጥሮስ መከራን በመቀበል ለክርስቲያኖች ሁሉ ምሳሌ የሆነውን ኢየሱስ፣
በ ራእይ የጌታዎች ጌታ ሆኖ ሊነግስ የሚመጣውን ኢየሱስን ያልተቀበለች ነፍስ ከእግዚአብሄር መንግስት እድል ፋንታ የላትም! ለዚያች ነፍስ ወዮላት! ንጉሱ ሳይመጣ በእምነትና በንሰሃ ወደ ንጉሱ ትመልከት ዘንድ ወንጌል ለፍጥረታት ሁሉ ይሰበካል! ብቻውን የድህነት መንገድ የሆነውን የገፋች ነፍስ የተረገመች ናት!
@ኢየሱስ_ብቻ

Good Christian Books Shelf

28 Oct, 15:57


“እንኖር ዘንድ መኖርን ስጠን፣ ሕይወትንም እናስብ ዘንድ፤ ደስ የሚያሰኝህንም እናውቅ ዘንድ።
ጸሎታችንን ብትከለክልም፣ ጩኸታችንን ባትሰማም፥ አንተ የታመንክ ነህና ለዘላለምም አትጥለንም። ደግሞም እኛ የቱንም ያህል ብንርቅ፥ አንተ ሩቅ አይደለህምና ትሰማናለህ፤ እኛም እንጮኻለን። አቤቱ ጌታ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ ማረን። የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሰምተህ ማረን። አይተህ፣ ራርተህ ማረን። ባክህ ጌታ ሆይ፥ ስለምን ተስፋ እንቁረጥ? ደግሞ ብንቆርጥስ፥ ሌላ ምን እንጥፍጣፊ ተስፋ ይኖረንና ነው?
አዎ፥ በከፋን፣ ካንተም ሸስተን በሮጥን ጊዜ ለዘላለሙ አልጣልከንም፤ ይልቁኑም በልጅህ ጎበኘኸን። በድቅድቅ ጨለማና በሞት ጥላ ለምንኖር ለእኛ፥ እኛን ሆነህ ታየህልን። አዎ፥ አንተው ቅዱስ እግዚአብሔር፥ በመንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆነ ያንድ ልጅህን፣ የጌታችንንና ያምላካችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን፥ በእኛ ላይ አበራህ።
እርሱም ፈጽሞ ሰው ሆነ የሕይወት መንገድንም አስተማረን። ከላይ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድንም ሰጠን፤ ስለዚህም አብዝተን ስምህን እንባርካለን።
እግዚአብሔር ሆይ፥ ስምህን የምንጠራ ሁሉ ራሳችንን በፊትህ ዝቅ እንናደርግ ዘንድ እርዳን። በኛ ላይ እደር፣ ከኛም ጋር ሂድ። በበጎና በመልካሙ ሥራ ሁሉ እርዳን፤ ልቡናችንንም ምድራዊ ከሚሆን ከክፉ ሥራ ሁሉ አንጻልን። እውነተኛና ያንተ የሆነውን ሕይወት እንኖር ዘንድ፥ መኖርን ስጠን፤ ደግሞም ይህኑን ካንተ የተቀበልነውን ሕይወት እናስብ ዘንድ፤ አንተንም በእውነት ደስ የሚያሰኝህንም እናውቅ ዘንድ እርዳን።
በዚህ በአንድ፣ ብቸኛ ልጅህ በጌታችንና በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፥ እኛ ሁላችን «እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለን» ብለን ወደሱ የምንጮኽለት እርሱ ነው፤ ለዘላለሙ አሜን።
[ጌታ ለዘላለም አይጥልምና፤ ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራልና፤ የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅም፥ አያሳዝንምም።]
— ሰቆቃው ኤርምያስ 3:31-32”

Good Christian Books Shelf

28 Oct, 06:21


እነሆኝ ሉተርና ነገረ መለኮታዊ እሳቤዎቹ 😁😁

Good Christian Books Shelf

27 Oct, 15:00


🫡🫡😅

Good Christian Books Shelf

25 Oct, 19:21


ጴንጤ ሆነው ለሊትና ቀን ስለ ገድላትና ድርሳናት የሚያወሩ ሰዎች የሆነ ነገር ሳይጎድላቸው አይቀርም😃

አንድም ቀን የሆነ መጸሃፍ ቅዱስ ክፍል ከፍተው ሰዎችን አያስተምሩም። ስለ ፕሮማክሱ ዶክትሪን ግድ አይላቸውም። እነ ሉተር ካልቪን ሲነሱ ስለነርሱ እኛን አያገባንም የሚሉ ናቸው። በቃ የምር ሶሻል ሚዲያ ላይ እውነተኛ የሚሉትን ወንጌል ከማስተማር ይልቅ የማይረቡ ትርክቶችን እያነሱ የሰሚዎቻቸውን ልብ ያደነዝዛሉ። እኛ ጋር ደግሞ በውስጥ ይመጡና ሃይማኖት አትስበኩን፣ ፕሮቴስታንት ምናምን እያላችሁ ለተቋም አትሟገቱ፣ ስለ ኢየሱስ ብቻ ነው መስማት የምንፈልገው ይላሉ። ያው ከነዚህ ሰዎች ጋር ነው እንግዲህ በ ባላንጣዎቻችን የምንወቀጠው 😂😂

Good Christian Books Shelf

25 Oct, 06:31


በpapal bull መሰረት ፖፑ ሉተርን አንተ የፖፑ ጠላት፣ የሃዋሪያት ጠላት፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢየሱስ ጠላት ነህ ብሎት ነበር 😢😢
በ16ኛ ክፍለ ዘመን የነበረችው ካቶሊክና የነበረው የቤተክርስቲያን ብልሹ አሰራርና አስተምህሮችን በትክክል ላጠና ሰው ግን የፖፑ ንግግር ተቃራኒ ነበር። ፖፑ የሃዋሪያትና የኢየሱስ ጠላት የነበረና ተራ መኖክሴ የነበረው ሉተር ደግሞ ቃሉን የሚያነብ፣ ያነበበውን ቃሉን ከቤተክርስቲያን ሊያገኝ ያልቻለና ወደ ጥንቱ አስተምህሮ እንመለስ እያለ በምድረ በዳ ብቻውን የሚጮህ ግለሰብ ነበር።
በዚህም መሰረት የመጸሃፍት ፕሮፌሰሩ ሉተር የፖፑ ጠላት እንደሆነና ደግሞ የሃዋሪያትና የኢየሱስ ወዳጅ እንደነበር በስራዎቹ ሁሉ አስመስክሯል። የተለየ ዶክትሪን አልፈጠረም፣ ከጥንት ከነበረው ዶክትሪን አላፈነገጠም፣ በሃዋሪያት ከተገለጠው መገለጥ በመሸሽ የራሱን መገለጥ አላቆመም፣ ቃሉን በማጉላት፣ የጸጋ አስተምህሮን በመግለጥ፣ የሰዎች የሃጢአት ብልሹነት በማስተማር፣ የዘመኑን የቤተክርስቲያን ችግሮችን በማሳየት መስታወት ለመሆን ጥረት አደረገ እንጂ 😀
ሰው ሰራሽ አስተምህሮዎችን ወደ ቤተክርስቲያን የሚያስገቡ ሰዎች ትልቁ ጥፋታቸው በቃሉ ድጋፍ የሌላቸው እንክርዳድ አስተምህሮዎችን ሰዎች እንዲነኩባቸው አይፈልጉም። ተሳስታችኋል ሲባሉ መጀመሪያ ላይ ከሰሩት ስህተት ያላነሰ ሌሎች ድርርብ ጥፋቶችን ይሰራሉ። ፖፑም ያደረገው ተመሳሳይ ድርጊት ነው። ከፐርጋቶሪ (የሃጢአት ማንጻት ክፍል) የበደል ይቅርታን ለመቀበል ካርድ እንዲሻሻጥ ትእዛዝ የሰጠው ፖፑ ሉተርን የሃዋሪያትና የኢየሱስ ጠላት ሲል ያስገርማል። ዛሬም በስህተት አስተምህሮ ውስጥ ያሉ ግለሰቦችና ቤተክርስቲያናት ለመታደስ ፍላጎት የላቸውም። ከቃሉ ይልቅ የራሳቸውን ገለባ ትምህርቶችን መከተል ምርጫቸው ያደርጋሉ። የተሃድሶ መንገድን ለሚያሳይዋቸው ጸረ ሃዋሪያትና ጸረ ክርስቶስ ነው እያሉ ተሃድሶን ያጣጥላሉ።

Good Christian Books Shelf

24 Oct, 15:43


በኦግስበርግ፣ ቀኖቹ ሌሊት በኾኑበት የብቸኝነት ወራት መዝሙር አርባ ስድስትን መሠረት በማድረግ "አምላካችን ዐምባችን ነው" (A Mighty Fortress is Our God) በማለት ማርቲን ሉተር የጻፈው መዝሙር ወደ ብዙ ቋንቋዎች ተመልሷል። በወቅቱ ስደት ላይ ለነበረችው ቤተ ክርስቲያን ጉልበትና መጽናናት ነበር። ታሪክ ተሻግሮ እኛንም ያጽናናል!
1) አምላካችን ዐምባችን ነው ብርቱ ዕቃ ጦራችን
በመከራችን እርሱ ነው ጽኑ መጠጊያችን
የጥንት ጠላታችን ሊያጠፋን ሲሻ፤
በኀይል በተንኮል ቃል ጥላቻንም ለብሶ፣ የሰው ኀይል አይችለውም
2) በኀይላችን ብንታመን በቶሎ እንጠፋለን
ግን እግዚአብሔር የመረጠው እርሱ በእኛ [ከእኛ ጋር] በኩል ነው
ስሙንም ብትጠይቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
እግዚአብሔር ጸባኦት የማይለወጠው እርሱ ነው ድል አድራጊው…
ሉተር መዝሙር 46ን የጻፈው ማብቂያ በሌለው ስደት፣ በብቸኝነት፣ በጤና ዕጦት፣ በመከራና ሕጻናት ልጆቹን ሞት በሕመም ድንገት ሲነጥቀው በገጠመው ጥልቅ ሐዘን እያለፈ ነበር።
”አምላካችን ዐምባችን ነው” - በርግጥ ዐውዳዊ አግባብነትና ትልቅ መልእክት መዝሙር ነበር። በወቅቱ ስለ ወንጌል የሚሰደዱ፣ ወደ እስር የሚወሰዱና ሰማዕት የሚሆኑ ይጽናኑበት ነበር። እግዚአብሔር የማይናወጥ አስተማማኝ መጠጊያና በተፈለገ ጊዜ ሁሉ የሚገኝ የቅርብ ረዳት ነው! እርሱ በክፉ ቀን የመሽሻ ግንብ - "to flee to" - הסה châsâh - ነው!
ስፐርጀን መዝሙር አርባ ስድስትን “የዳዊት ዕንቁ” በማለት ይገልጸዋል። እግዚአብሔር ካስጨነቀን ነውጥ በላይ ‘የአሁንና የቅርብ ረዳት ነው። የእግዚአብሔር ጽኑ መጠጊያነት ለዘላለም ነው።
ስፐርጀን እንደገለጸው "እርሱ ብቻውን ኹሉ በኹሉ ነውና!” እውነት ነው። የእኛን የግል ኾነ የዓለምን ታሪክ በሉጋም የያዘ ጌታ ነው የምናመልከው። እርሱ በሰማይና በምድር ኹሉ ላይ ሉዓላዊ ነው! አይናወጥም! ምንም እንኳን የዚህ ዓለም ኑሮ ከሰልፍ ጋር የተቈራኘ ቢኾንም፣ ተስፋችን የተመሠረተው "ምድርና ሕዝቦቿ ሁሉ በሚናወጡበት ጊዜ፣ ምሰሶቿን አጽንቼ የምይዝ እኔ ነኝ" ባለው ጌታ ላይ ነው። (መዝ 75፥3)።
ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ እንኳ፦ ማለትም በምድር ላይ ያሉ ግዑዛንና እሰትንፋስ ያላቸው ኹሉ መሠረታቸው ቢናወጥ እንኳን፣ እግዚአብሔር የማይናወጥ የመቆሚያ ጽኑ ዐለት ነው። "ተራሮችም ወደ ባሕር ጥልቅ ቢሰምጡ፤ ውሆች ቢያስገመግሙ፣ ዐረፋ ቢደፍቁም፣ ተራሮችም ከውሆቹ ሙላት የተነሣ ቢንቀጠቀጡም አንደናገጥም።" እግዚአብሔር “ይሁን አለ . . . ሆነም” በሚለው የፍጥረት መገኛ ሥርዐት ውስጥ፣ ምድር ነቁጥ (ዐዮታ) ናት። አጽናፈ ዓለሙ ኹሉ - የሚታየውንም የማይታየውንም- በሥልጣኑ ቃል በፈጠረበትና ደግፎ በያዘበት በዚያው ሉዓላዊ ማዕቀፉ፣ ምድርም ሆነ በእርሷም ውስጥ ያለው ኹሉ ተይዟል።
በዚህ “ኹሉ” ውስጥ - ግዙፋንና ረቂቃን፣ ያለፈው፣ የአሁኑና የሚመጣው ታሪክ ኹሉ ተካተዋል! በዚህ ምድር ላይ "ጽኑዕነታቸው" እንደ ተራራ የተመሰሉ ኀይላት (ሕዝቦች፣ ፓለቲካም ኢኮኖሚም) ሲናወጡ፣ ከዐቅማቸው በላይ በሆነ ጉልበት ሲብረከረኩና ሲናዋጡ፣ እግዚአብሔርን መጠጊያ ያደረገ ግን ተስፋው ጽኑ ነው። ምክንያቱም እምነቱ ያረፈው በማይናወጠው ልዑል ላይ ነውና! እርሱ “ውሆችን በዕፍኙ የሰፈረ፣ ሰማያትን በስንዝሩ የለካ፣ የምድርን ዐፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን፣ ኰረብቶችንም በመድሎት የመዘነ” ነውና (ኢሳ 40፥12)። በአጭሩ ዳዊት፣ በሸምበቆ ጥንካሬ አትደገፉ ነው የሚለን!
ሴላ - Selah (ቆም በሎ ማስብ - pause) - ዳዊት ቆም ብሎ ያስባል። መዝሙሩ በአንድ ትንፋሽ ሳይሆን፣ ሦስት ጊዚ (ቁጥር 3፣ 7፣ 11) ቆም ብሎ በማሰብና በአስተውሎት የተዘመረ ነው። ዳዊት በዚህ የሚናወጥ ዓለም የዋስትናውንና የደስታውን ምንጭ ቆም ብሎ ያስባል። በሚናወጠው ዓለም ውስጥ መኖራችን የማይካድ እውነት የኾነውን ያኽል፣ በዚህ ነውጥ ውስጥ የእግዚአብሔር ሀልዎት ደግሞ የማይካድ የእውነቶች ሁሉ እውነት ነው። የዚህም እውነት ርግጠኝነት በሰላምና የደስታ ወንዝ ተምሳሌነት ተገልጧል። “የእግዚአብሔርን ከተማ፣ የልዑልን የተቀደሰ ማደሪያ ደስ የሚያሰኝ የወንዝ ፈሳሾች አሉ”። (ቁ. 4)። በሕዝቦች ዐመፅ፣ በመንግሥታት መውደቅና በምድር መቅለጥ በተገለጸው መናወጥ ውስጥ፣ እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም በመካከል አለ። "እግዚአብሔር በመካከሏ ነው፤ አትናወጥም፤ አምላክ በማለዳ ይረዳታል" (ቁ.5)
ሴላ - Selah (ሌላ ቆም በሎ ማስብ) “ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደሆንሁ ዕወቁ” - አሁን ተናጋሪው እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ነው! "ዕረፉ" (ቁ.10) የሚለው የዕብራይስጥ ቃል “ራፋኽ ( רפה - râphâh) የሚያሳየን፣ ራስን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ኹሉን ገዢነት አሳልፎ መስጠት፣ በእርሱ ላይ መውደቅ። እርሱ (1) ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል። ማለትም በኹሉ አቅጣጫ የተነሣን ጦርነት ማስወገድ የሚችል እሱ ብቻ ነው። (2) ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርን ያነክታል፤ ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል። ይኽም ማለት የጉዳትና የጥፋት መሣሪያዎችን ዐቅም ያመክናል ማለት ነው። (3) ይህ አምላክ - ያህዌ - ጅማሪም ፍጻሜም የሌለው፣ ያለና የነበረ፣ ሁልጊዜም የአሁን አምላክ ነው። ሌሎች አማልክት ምንጫቸው ከሚናወጠው ዓለም ሰለሆነ ከንቱ ናቸው! (4) ይህ አምላክ የሰራዊት አምላክ፤ የሚታየውና የማይታየው ፍጥረት ኹሉ መገኛና ገዢ፣ የያዕቆብ አምላክ፣ የእኛም አምላክ ነው። “የያዕቆብ አምላክነት"፣ ወሰን የሌለውን የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ ምሕረት፣ ይቅር ባይነትና የተትረፈረፈ ጸጋ ብቻ ሳይሆን፣ የእርሱን “የቅርብ ረዳትነት” ያሳያል።
ፈርጀ ብዙ በኾነ የግልና የጋራ ነውጥ ስናልፍ በዙፋኑ ለዘላለም የተቀመጠውን አምላካችንን በማሰብና በእውነት መዘመር ይኹንልን። በጽኑ መከራ ውስጥ እያለፋችሁ በታማኝነትና በትጋት ለምታገለግሉ ሁሉ - ሉተር እንደ ዘመረው በርግጥ እግዚአብሔር የማይናወጥ አምባ፣ ዐለትና መጠጊያ ነው! ብድራታችሁ ታላቅ ነውና፣ በርቱ፤ ዘምሩም - አምላካችን ዐምባችን ነው።
“ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ደስ ይበላችሁ።” (1 ጴጥሮስ 4፥13። እስከዚያው "በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ።" (ሮሜ 12፥12)።
አሜን! (በዶ/ር ግርማ በቀለ የተጻፈ)
በ አማርኛ የተዘመረውን ከዚህ ታገኛላችሁ https://youtu.be/JkTVxPBhXOI?si=Swp6JOJAtxFX0d7 -

Good Christian Books Shelf

24 Oct, 12:12


የስራ ማስታወቂያ😁😁
1 ስራው፤ የቅዱስ አውገስጢኖስ ኑዛዜ በአማርኛ የተጻፈውን በማንበብ ሪከርድ ማድረግ።
2 የሚፈለገው የሰው ቁጥር 1።
3 ጾታ፤ ለሁለቱም ክፍት ነው (ሴቶች ቢሆኑ ይመረጣል) 🤣🤣
4 አድራሻው፤ እዚህ አዲስ አበባ የሚገኝ/የምትገኝ ቢሆን ይመረጣል።
5 የስራ ልምድ፤ ከዚህ በፊት ሪከርድ በማድረግ ልምድ ያለው/ ያላት፣ ያው ኑዛዜ አማርኛው ጠጠር ያለ ስለሆነ የአማርኛ ንባብ ላይ ጎበዝ የሆነ/የሆነች፣ መሳጭ ቮይስ ያለው/ያላት ቢሆን ይመረጣል።
6 የጊዜ ቆይታ፤ ቢበዛ በሁለት ሳምንት አንብቦ ሪከርድ አድርጎ የሚጨርስ።
7 የሪከርዱን ጥራት በተመለከተ፤ በአሪፍ ስልክ ወይም በአሪፍ ሪከርደር ማድረግ የሚችል😁
8 የሚያገኛቸው መብቶችና ጥቅሞች፤
8.1 ሪከርድ በሚያደርግበት ጊዜ ጎሮሮው እንዳይደርቅ የጠጣቸውን ውሃ እስከ 15 ሌትር እንዲሸፈንለት የመጠየቅ መብት አለው
8.2 ሪከርድ በሚያደርግበት ለመነቃቃት ብሎ የጠጣቸው ቡና ሆነ ትኩስ ነገሮችን ደረሰኝ በማቅረብ እንዲሸፈንለት የመጠየቅ መብት አለው።
8.3 ያነበበውን መጸሃፍ ማለትም ኑዛዜን በሃርድኮፒ የግሉ ማድረግ ይችላል።
8.4 ተጨማሪ ነገር ከተጠየቀ ሸልፈኛው በሚችለው እንደ አቅሙ ለማድረግ ፍላጎት አለው።
9 የማመልከቻ ቀናት፤ ዛሬና ነገ @maclloyd ላይ ማስገባት ትችላላችሁ lol
10 ማስታወቂያው ዘና ስላደረገኝ በፍቃደኝነት ሪከርድ አደርጋለሁ የሚል ሰውን አስቀድማችሁ ባርኩልኝ 😁😁

Good Christian Books Shelf

24 Oct, 10:21


እስቲ ስለ ተሃድሶ ከተሰሩ አሪፍ ሙቪዎች መሃል አንዱን ልጋብዛችሁ 😁😁

Good Christian Books Shelf

24 Oct, 05:49


“ጸጋ ስንል ያኔ ስለዳንንበት ብቻ ሳይሆን አሁን ስለምንኖርበትም ጭምር ነው። ያኔ ርቀን የነበርነውን ያቀረበን፥ ሞተን የነበርነውን ሕያው ያደረገን ጸጋ አሁን ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን በጽድቅ እግዚአብሔርንም መስለን እንድንኖር የሚያስተምረንም ነው።
ጸጋ የሚተነተን ዕውቀት ሳይሆን በሕይወታችን የምንለማመደው መለኮታዊ ባርኮት ነው።
ጸጋ በኃጢአቱ ሙት ለሆነው (ሊሰጠው ለማይገባው) ሰው የተበረከተ አምላካዊ ገጸ በረከት ነው።”

Good Christian Books Shelf

23 Oct, 18:30


"It is the necessary consequence of his [God's] delighting in the glory of his nature that he delights in the emanation and effulgence of it."
—Jonathan Edwards

Good Christian Books Shelf

23 Oct, 16:32


የሚለውጥ ጸጋ! ምሉዕ የሆነው ጸጋ! ክቡር ጸጋ! አዳሹ ጸጋ! ቀዳሹ ጸጋ! አዳኙ ጸጋ! ሉአላዊው ጸጋ! አስደናቂው ጸጋ! ወሰን የሌለው ጸጋ! የተትረፈረፈው ጸጋ! የሚበዛው ጸጋ! ከመታወቅ የሚያልፈው ጸጋ! የማይሻረው ጸጋ! ከስላሴ የሚፈልቅ ጸጋ! የማይመዘን ጸጋ! የሚመርጥ ጸጋ! ጸጋ ብቻ!

Good Christian Books Shelf

23 Oct, 10:36


“ተሐድሶው ወደ አያቶች ተመለከተ። አውገስጢኖስንም አገኘ። አጠናው፤ አነበበው፤ ተንትኖ ወሰደው። ሲተነትነው ከዘመኑ ጋር ግርምቢጥ ሆነበት። ስለዚህም ከአባቶች ዘሎ ወደ አያቶች ተመለከተ። አውገስጢኖስ ተገኘ። ቅዱስ አውገስጢኖስ የተሐድሶው መስታወትና መስፈንጠሪያ ‘ቦርድ’ ነው። ተሐድሶው አዲስ ነገር ሳይሆን ያነሳው ወደ አያቶች ነው የነጎደው። ተሐድሶ ወደ ኋላ ተመልካች ነው!”

Good Christian Books Shelf

22 Oct, 19:12


ኔት እያስመረረኝ ነው ሎል ሌላ ጊዜ የማይጠፋው ኔት እኔ ላይቭ ስገባ ብቻ ጠብቆ የሚጠፋ ክፉ ኔትዎርክ 😜😜 እስቲ ውጉልኝ ሎል ካልሆነ ሁለተኛ ላይቭ እንዳልገባ እያስማለኝ ነው 😁😁

Good Christian Books Shelf

22 Oct, 15:42


የተሃድሶ ወር ልታልቅብን ነው ምንም ሳንል ሎል በኋላ 2:30 ላይ ላይቭ እንገባለን። የሚመቻችሁ ሰዎች ልትመጡ ትችላላችሁ 😁

Good Christian Books Shelf

21 Oct, 17:50


“ከሁሉም በላይ የሚያስደንቀኝ እግዚአብሄር ብዙዎችን አለመምረጡ ሳይሆን እኔን መምረጡ ነው”
እስፐርጀን

Good Christian Books Shelf

21 Oct, 15:28


ከተሐድሶ ወቅት አባቶች ውስጥ ማርቲን ሉተር ፈገግ በሚያደርጉ ንግግሮቹ ይታወቃል። በሕይወቱና በሥራው ውስጥ ፈገግታን በሚያጭሩ አገላለጾች መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታን ለማብራራት፣ የሚቃወሙትን የቤተ-ክህነት ሰዎች በነገር ሸንቈጥ ለማድረግ፣ እንዲሁም በሞትና በዲያቢሎስ ላይ ሊሳለቅ ይጠቀምባቸው ነበር።
(አንዳንድ የሚያሽኮረምሙ ነቈራዎቹን ለጊዜው ትተን፥ ገብስ ገብሱን እናውራ...😃)
1—
በአንድ ወቅት "ኩልትዝ" የሚባለው የሉተር ውሻ ለሥጋ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት በመመልከት፥ መንፈሳዊ ጥማትን ከውሻው ስግብግብነት ጋር እያነጻጸረ ሲያስረዳ... ‹‹ኩልትዝ ሥጋን በሚፈልግበት ልክ እኔም ትኩረት ሰጥቼ መጸለይ ብችል እንዴት ጥሩ ነበር?! ሃሳቡ ሙሉ በሙሉ በዚህ የሥጋ ሙዳ ላይ ብቻ መሆኑ ሁሌ ይገርመኛል። ከዚህ ውጪ ሃሳብም...ምኞትም እንዲሁም ተስፋ የለውም!››
2—
ሉተር ወፎችን የሥነ-ፍጥረት የውበት ፈርጥና ሥርዓት ማሳያ ናቸው ብሎ ስለሚያምን በጣም ይወዳቸዋል። በመጨረሻው ዘመን በሚታደሰው የእግዚአብሔር መልካም ፍጥረት ምሳሌ አድርጎም ይመለከታቸዋል። አንድ ጊዜ፥ ዎልፍጋንግ የሚባል የሉተር አገልጋይ ወፎችን እያጠመደ እንደሚሸጥ ሉተር ሲሰማ ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ ለማድረግ አንድ አስገራሚ ደብዳቤ ጽፎለታል። ደብዳቤው የአዕዋፋት ማኅበር፥ ዎልፍጋንግ የሚያደርስባቸውን የመብት ረገጣ እንዲያቆምና ነጻነታቸውን እንዲያከብር እንዳስጠነቀቁት ከወፎቹ የተላከ አስመስሎ ጽፎለታል።
ደብዳቤው ሲጀምር ...‹‹እኛ የአዕዋፋት ማኅበር አባላት— ጥቁር ወፎች፥ እርግቦች፥ ዋኖሶች፥ እና ሌሎችም መልካምና የተከበርን ወፎች...›› በሚል መደበኛ የደብዳቤ አጻጻፍ ዘይቤ ይጀምራል 😃ቀጥሎም...ዎልፍጋንግ እያደረሰባቸው ባለው የጭካኔ ወንጀል ምክንያት በየመንደሩ ተንቀሳቅሰው የየዕለት ጉርሳቸውን ጥራጥሬ መጠርጠር (መልቀም) እንዳልቻሉ ምሬታቸውን ይገልጻሉ። ከድርጊቱ ካልታቀበ...ቀን ቀን ወጥመዱ እንቁራሪትና አንበጣ እንዲያጠምድ፥ በሌሊት ደግሞ ቅማልና ትኋን ሰውነቱን እንዲወሩት ይራገማሉ 😃 የደብዳቤው ግርጌ ላይ የተጻፈው የላኪዎቹ አድራሻ፡- ‹‹ከዛፎች ሥር ከሚገኘው ሰማያዊ ቦታችንና፥ ከተለመደው የላባ ማኅተም ጋር!›› 😃ይላል። ዎልፍጋንግ ይኼን ደብዳቤ ካነበበበት ቀን ጀምሮ ወፎችን ማጥመድ እርግፍ አድርጎ ትቷል።
3—
ከሉተር ተማሪዎቹ አንዱ፥ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከመፍጠሩ በፊት የት እንደነበር ይጠይቀዋል። ሉተርም (የሚወደውን የቤተ ክርስቲያን አባት፥ ቅዱስ አውግስጢኖስን በመጥቀስ)፥ ‹‹ከአቅማቸው በላይ ለማወቅ ለሚጣጣሩ ሰዎች ገሃነምን እየፈጠረ ነበር›› ብሎ ቀልዶ መልሷል ይባላል 😃 (በፍጹማን ግርማ የተጻፈ)

Good Christian Books Shelf

21 Oct, 06:38


የሃዋሪያት እምነት ድንጋጌን እስቲ በዜማ እናዜመው 😁😁

Good Christian Books Shelf

20 Oct, 17:12


በአውሮጳ የተቀጣጠለውን ተሃድሶ፣ ተሃድሶውን ያቀጣጠሉ አባቶች፣ በተሃድሶው የተመሰረቱ ቤተ እምነቶችና የተሃድሶ ዋና ዋና የሆኑ የእምነት ድንጋጌዎችን ልናወራ ከ37 ደቂቃ በኋላ ላይቭ እንገባለን። የሪፎርሜሽን ታሪክ የሚመስጣችሁ ሸልፈኞች ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ 😁😁

Good Christian Books Shelf

20 Oct, 14:22


“The first thing I ask is that people should not make use of my name, and should not call themselves Lutherans but Christians. What is Luther? The teaching is not mine. Nor was I crucified for anyone...How did I, poor stinking bag of maggots that I am, come to the point where people call the children of Christ by my evil name?”
Martin Luther

Good Christian Books Shelf

20 Oct, 11:55


ማታ የሮሜ ጥናት ላመለጣችሁ እነሆኝ 😁😁

Good Christian Books Shelf

19 Oct, 17:02


ገብተናል ላይቭ ገባ ገባ እያላችሁ 😁😁

Good Christian Books Shelf

19 Oct, 11:55


ሸልፈኞቼ ቀጠሮአችን አልተረሳም አይደል?😊
ከ2ሰአት በኋላ ሮሜን ልናጠና እዚሁ ቻናላችን ላይ ላይቭ እንገናኛለን አይደል?
ትመጣላችሁ አይደል? 😁😁
ለመንኋችሁ አይደል? 😃
ለሚያጠኑ ወዳጆቻችሁ ሼር ታደርጋላችሁ አይደል? 😄
በቃ ሸልፈኛው ፕሮሞሽን አይስራ 🤣🤣

Good Christian Books Shelf

19 Oct, 08:24


በቋሚነት የቤተክርስቲያን ታሪክ(church history እና ታሪካዊ ነገረ መለኮት (historical theologyን ማጥናት የሚፈልግ ሰው ብቻ እዚህ ፍቃደኝነቱን ይግለጥ 😁 ወደ ጥናት ግሩፑ ከሆነ ጊዜ በኋላ አስገባችኋለሁ 😁 50 ሰው ብቻ ይበቃል። ገባ ወጣ ማለት ያስወግዛል ሎል @christiandogmatics

Good Christian Books Shelf

19 Oct, 06:39


ሉተር የተሃድሶን እሳት በ95 thesisኡ ካቀጣጠለ ከአመት በኋላ በሃይደርበርግ ያቀረበው የመስቀል ስነ መለኮት እጅግ ግሩም ነበር። ያንን መኖክሴ የውተንበርጉ የመጸሃፍት ፕሮፌሰር የትምህርቱንcenter ለመረዳት የሃይደርበርግ መከራከሪያዎችን ማንበብ በጣም ወሳኝ ነው። በሃይደርበርግ ያቀረባቸው ሙግቶች በዋነኝነት ስለ ሃጢአት፣ ጸጋ፣ ስለ ህግ፣ ነጻ ፍቃድ እና ስለ መስቀል የሚያወሱ ነበር።
የሃይደልበርግ ክርክርን መረዳት የሉተርን ነገረ መለኮትን በትክክል መረዳት ነው። በሙግቱ ካቀረባቸው ዋና መከራከሪያዎች የተወሰኑትን thesis ታነቡ ዘንድ እንደ incitement ጥቂቱን ላቅርብ
0. “የእግዚአብሔር ሕግ፣ እጅግ ሰላም ያለው የሕይወት ትምህርት ቢሆንም ሰውን ወደ ጽድቅ መንገድ መምራት አይችልም፣ ይልቁንስ ሰዎች ሃጢአተኛ እንደሆኑ በማሳየት ይኮንናቸዋል….”
1. “ምንም እንኳን የሰው ስራዎች ሁል ጊዜ ማራኪ እና ጥሩ ቢመስሉም፣ ነገር ግን እነዚህ ስራዎች በራሳቸው የመርገም ጨርቅ የሆኑገዳይ ኃጢያት ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም፤ የእግዚአብሄር ስራዎች ሁል ጊዜ የማይስቡ እና ደካማ ቢመስሉም ግን ስራዎቹ በእውነት ዘላለማዊ ጸጋዎች ናቸው….”
2. “በየሥራው ሁሉ የኩነኔ ፍርድ ካልተፈራ ትዕቢትን ማስወገድ ወይም እውነተኛ ተስፋ ሊኖር አይችልም፤ በእግዚአብሔር ፊት ሃጢአተኛ ሰዎች ፍርደኛ እንደሆኑ ሲያምኑ በእውነት የተጸጸቱ ናቸው….””
3. “ነፃ ፈቃድ ከውድቀት በኋላ በስም ብቻ ይኖራል፤ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል። ማድረግ የሚችለው እርሱ ግን ገዳይ ሃጢአትን ብቻ ነው….”
4. “ነፃ ፈቃድ፣ ከውድቀት በኋላ፣ በጎ ነገር ለማድረግ ኃይል ያለው በደካማ አቅሙ ብቻ ነው፣ ነገር ግን ሁልጊዜም በበረታው አቅሙ ክፋትን በንቃት ማድረግ ይችላል….”
5. “በእርሱ ያለውን በማድረግ ጸጋን እንደሚያገኝ የሚያምን ሰው በኃጢአት ላይ ኃጢአትን በመጨመር በደለኛ ይሆናል እንጂ ጻድቅ ተብሎ አይቆጠርለትም….”
6. “ሰው የክርስቶስን ጸጋ ለመቀበል ከመዘጋጀቱ በፊት በራሱ ችሎታ ሙሉ በሙሉ ተስፋ መቁረጥ እንዳለበት እርግጠኛ መሆን አለበት፤ እንዲህም መናገር ራስን ዝቅ ለማድረግና የክርስቶስን ጸጋ ለመሻት ነው እንጂ ለተስፋ መቁረጥ አያበቃም…”
7. “የእግዚአብሔርን "የማይታዩ" ነገሮችን በትክክል በሚታዩ ነገሮች በግልጽ የሚመለከት ሰው የነገረ መለኮት ምሁር ተብሎ ሊጠራ አይገባውም፤ ነገር ግን በመከራና በመስቀል የታዩትን የእግዚአብሔርን የሚታየውንና የተገለጠውን ነገር የሚያስተውል የሥነ መለኮት ሊቅ ተብሎ ሊጠራ ይገባዋል….”
8. “የክብር ሥነ-መለኮት ክፉን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ይለዋል፤ የመስቀል ሥነ-መለኮት ግን ክፉን ክፉ መልካሙን መልካም ይለዋል….”
9. “የእግዚአብሔርን የማይታየውን ነገር በሰው ዘንድ እንደ ተገለጠ በሥራ የምታይ ጥበብ ፈጽሞ የታበየች፥ የታወረች፥ የደነደነች ናት፤ ነገር ግን ጥበብ በራስዋ ክፉ አይደለችም፥ ከሕግም የራቀች አይደለም፤ ነገር ግን ያለ መስቀል ሥነ-መለኮት ሰው ምርጡን ጥበብ በከፋ መልኩ አላግባብ ይጠቀምባታል…”
10. “ጻድቅ ብዙ የሚያደርግ አይደለም፤ ነገር ግን ያለ ሥራ በክርስቶስ ብዙ የሚያምን እንጂ….. ሕጉ ይህን አድርጉ ይላል እንጂ ፈጽሞ ቀድሞ አልተደረገም። ጸጋው "በዚህ እመኑ" ይላል, እና ሁሉም ነገር አስቀድሞ ተከናውኗል…”

Good Christian Books Shelf

18 Oct, 13:26


ስለ አምስቱ ሶላዎች ከኦርቶዶክሶች ወይም ከካቶሊኮች ጋር ስንከራከር መጀመሪያ መስማማት ያለብን ከሶላዎች ዋናው #ክብር ለእግዚአብሄር ብቻ በሚለው መሆን አለበት
ክብር ለእግዚአብሄር ብቻ የሚለውን ከተቀበሉ ያለ ምንም ጥርጥር ሌሎችንም ይቀበላሉ። እስፐርጀን በትክክል እንደሚለው ሰዎች ሁሉ የጸጋን አስተምህሮ በትክክል መቀበል የማይችሉት ክብር ለእግዚአብሄር ብቻ የሚለውን ስለማይቀበሉ ነው። በእውነቱ የወንድማችን የእስፐርጀን አሳብ ገዢ ነው ብዬ አምናለሁ። ሶላ ፊዴን ወይም ሶላ ግራሺያን ወይም ሶላስ ክርስተስን የማይቀበሉት በትክክል ሶላ ዲዮግሎሪያን መቀበል ስለማይችሉ ነው። ስለዚህ ሌሎችን ሶላዎችን ለክርክር ከማቅረባችን በፊት ክብር ለእግዚአብሄር ብቻ የሚለውን መቀበላቸውን ቼክ ማድረግ ይጠበቅብናል
ያው ወዳጆቻችን በዚህ ላይ ካልተስማሙ ሌሎችን ሶላዎችን የመቀበል እድላቸው ጠባብ ስለሚሆን ሌሎችን አለመቀበላቸው ችግራቸው ይህ ሶላ እንደሆነ እንድትረዱ ነው 😁😁 ደግሞ ቫን ቲል እንደሚመክረን ከሆነ በ እቅበተ እምነት ስራ ላይ ስንሰማራ የመጀመሪያው ነገር የባላንጣችንን ለእግዚአብሄር ክብር ያለውን አቋም ካወቅን በኋላ ነው ቱክስ እምንጀምረው 😎😎

Good Christian Books Shelf

18 Oct, 07:25


"ሃይማኖትስ ይታደሳል?"
ክርስትና በአስተርእዮተ እግዚአብሔር ላይ የተመሰረተ እምነት ነው (ለምሳሌ ዩሐ. 1፥18፤ ገላ. 2፥2 ይመ.)። ጌታ እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የገለጠው እውነትና የሰጣቸው ተስፋዎች ሁሉ ፍጻሜም ነው። በክርስቶስ መገለጥ ያልተፈጸመ ምንም የለም፤ "በእግዚአብሔር የተሰጡ ተስፋዎች ሁሉ 'አዎን' የሚኾኑት በእርሱ ነውና" (2ቆሮ. 1፥20 ዐመት)። በእግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የመጣው አስተርእዮ የቀዳሚዎቹ ፍጻሜ ብቻ ሳይኾን፣ የመጨረሻውና ከሁሉ በላይ የላቀ መገለጥ ነው (ዕብ. 1)። እንግዲህ ይህ መገለጥና እምነት እውነተኛ ፍጹም ቢኾንም፣ እኛ ሰዎች በምንሰጠው ምላሽና ተግባር ላይ ግን ጉድለት ሊከሠት መቻሉ እውነት ነው፤ የሰው ልጅ መሳሳቱ አይቀርም። የመታረሙና መታደሱ አስፈላጊነትም የሚመነጨው ከዚሁ የሰው ድካም ውስጥ ነው።
[...] የሰው ልጅ እውነተኛን እምነት በመበረዝ በኑፋቄ ጮረቃ ሲያልኮሰኩሰው እግዚአብሔር በተሐድሶ ውሃ ያጠራዋል። በዚያን ጊዜ ምርቱን ከግርዱ መለየት ይኖራል። ፍሬውን ከገለባው ማበጠር ይከተላል። ለዚህም ዐላማ ሲል እግዚአብሔር በምሕረቱ የተሐድሶ ነፋስ ያነፍስበታል። በዚህ ማጥራትና ማንፈስ ሂደት ደግሞ የሚሠራ ብቻ ሳይኾን የሚፈርስ የቁሻሻ ክምር ይኖራል። ይህን መሳይ ታላቅ ተግባር ለማከናወን ብሩህ አእምሮ የታደሉ ዐዳሾች ያስፈልጋሉ ማለት ነው። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንዳሉት፣ "አሕይዎና ተሐድሶ (Revival and Renewal or Reformation) ተደላድሎና ተመቻችቶ በተቀመጠ ሥርዐት (Establishement) ውስጥ የዛገና የሚራገፍ ነገር የሚያይ የአእምሮ ችሎታና የተፈጥሮ ተሰጥዎ ካላቸው ታላላቅ ሰዎች ዘንድ የሚመጡ ሐሳቦች ናቸው።"*
ስለዚህ ሃይማኖትም ቢኾን "በዛገና በሚራገፍ ነገር" ብልሽት ከገጠመው ይታደሳል። እግዚአብሔር ራሱ አሮጌውን በዐዲሱ ዐድሷል። አሮጌውን በዐዲሱ ሰው ተክቶታል (ኤፌ. 4፥24፤ ቆላ. 3፥10)። ነቀፋ የተገኘበትን ፊተኛውን ኪዳን (ኤር. 31፥ 31-34) ለዐዲሱ ስፍራ አስለቅቆታል (ዕብ. 8፥6-7)። ስለዚህም፣ "ዐዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌውና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል" (ዕብ.8፥13) የተባለው ቃል ተጻፈ። አዎን! ሃይማኖትም ቢኾን ቅይጥነት ሲገዳደረው፣ አደፋ ሲጠናወተው መለኮተ መድኀኒት ያዝዝለታል።
(*ጌታቸው ኃይሌ ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ:- በሕግ አምላክ)
------------------------
"ማፍረስም መስራት ነው" ከሚለው ጽሁፍ የተቀነጨቡ ሃሳቦች
ከእግዚአብሔር የተቀበልናቸውን ጠቃሚ ሀብታት አንድም በማበላሸት ካቆሸሽናቸው፣ ደግሞም ለእርሱ ክብር ከማድረግ ይልቅ ለሥጋዊ ትምክሕትና ሌላውን ወገን ለማክፋፋት ካዋልናቸው ዐላማቸውን ስተዋልና የተሐድሶ ነፋስ ያሻቸዋል።
**********
መጽሐፍ ቅዱሳችን ራሱ የተሐድሶ መጽሐፍ ነው። እግዚአብሔር በታሪከ ድነት ውስጥ ያቆመው ዋነኛ መርሕም የተሐድሶ ምልሰት ነው።
********
ቅዱሱን መጽሐፍ የልብ ዐይኖቻችን ተከፍተውልን ካነበብነው ተሐድሶን እንናፍቀው እንደኾነ እንጂ እናክፋፋው ዘንድ ዐቅም አይኖረንም። ... ይህም[በክርስቶስ የሆነው ድነት] በእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ አማካይነት ወደ ቀደመው ክብር፣ ጸጋና ቦታ የመመለስና የመታደስ ወንጌል ነው። ከውድቀት በኃላ ለአዳም የተሰጠው ያ ተስፋ ቤዝዎታዊ ተሐድሶ ነበር።
***********
ተሐድሶን ለማምጣትና ወደ እውነቱ ለመመለስ ሲባል የሐሰት ትምህርት ላይ መጨከን ግዴታ ነው እንጂ፣ አማራጭ አልነበረም፤ ዛሬም ሊሆን አይችልም።
****************
"ልዩ ወንጌል" ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሲያቀና እንቢ ማለትና አዋኪዎች ያስገቡትን ኑፋቄና የአጋንንት ትምህርት ማፍረስ ተሐድሶ ነው። ይህ ሊኮነን ሳይኾን ሊወደስ የሚገባው ዘመቻ ነው። ጥያቄው ለምን፣ መቼ፣ የት፣ ምንና እንዴት ይታደስ የሚለው እንጂ "ዝንቡ እሽ የሚባል የለም" ብሎ ማፍጠጥ መፍትሔ አይኾንም። በደፈናው "ሃይማኖት አይታደስም" እያልን ከማገንገን፣ ለምን እንደማይታደስ ብናስረዳ ጥሩ ነበር። ጌታ ኢየሱስ አዳሽ አልነበረምን? ሐዋርያቱስ? የአሮጌው መነካት ባይመቸንም እንኳ፣ ለተሻለው ስፍራ እንዲለቅ ውራጅ የኾነው ትምህርትና ልምምድ ይፈርሳል።
*************
ማንኛውንም ነገር በደባልነት ደርበን ለማምለክ ብንሞክር፣ ይህ ብክለት ነውና ሃይማኖት ይታደሳል። ማንኛውም ነገር ከመለኮታዊው አስተምህሮ በተፃሮ ሲቆም፣ ወይም ቅይጥነት ሲዳበለው ተሐድሶ ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ሰው ነኝ የሚል ሁሉ አምልኮተ ባዕድን፣ ርኩሰትን፣ ጥንቆላን፣ ኑፋቄን። በወንጌል ስም መነገድን፣ ወዘተ. ማፍረስ ግድ ይለዋል። በእግዚአብሔር ከተሰጠው መመሪያ ውጭ በሰው የተገነቡ መሠዊያዎች እስከሚሰነጠቁና ዐመዳቸው እስከሚፈስ ድረስ ቢሰነጣጠቁ እንደነቃለንን(1ነገ. 13)?
ሰሎሞን አበበ ገብረ መድሕን፤ የትሩፋን ናፍቆት፣ ማፍረስም መስራት ነው

Good Christian Books Shelf

17 Oct, 18:53


https://youtu.be/NkBOawfmw3w?si=pSfwoi7yTNsVHIDD

Good Christian Books Shelf

17 Oct, 18:16


ሐዋሪያቶች ከሠበኩት የኃጢያት ይቅርታ እውነት ውጪ የሚያስተምር እርሱ ይወገዝ፤ ይረገምም!!!

Good Christian Books Shelf

17 Oct, 13:33


“የእግዚአብሔር ምኅረቱ ብዙ
ደካሞችንም ማገዙ
በጀርባው አዝሎ መሸከሙ
ከኃጢዓት ማንጻት በደሙ”

Good Christian Books Shelf

17 Oct, 08:33


ማታ ላልነበራችሁ ድጌ ሪከርድ የተደረገ 😁 አንዱ አዳሽና ተሃድሶ 😊

Good Christian Books Shelf

17 Oct, 05:14


ጆን ካልቪን ከካርዲናል ሳደሊቶ ጋር ባደረገው ሙግት ውስጥ በትክክል እንዳስቀመጠው ጽድቅ በእምነት ብቻ የሚለው አስተምህሮ ከተዛነፈ…. “the glory of Christ is extinguished, religion is abolished, the church destroyed, and the hope of salvation utterly overthrown”

ስለዚህ ጽድቅ በእምነት ብቻ ነው የሚለው መረዳት ላይ ያልደረሰ ግለሰብ ሆነ የትኛውም አስተምህሮ ከእውነተኛ ሃይማኖት ማለትም ከእግዚአብሄር ዘንድ ከተገለጠው ማፈንገጥ ነው። በእግዚአብሄር ፊት ያለ ምንም ዋስትና መመላለስ ነው። በአባትና በልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት አሽቀንጥሮ መጣል ነው። የተገለጠውን የያህዌ የቁጣውን መጠን አለመረዳት ነው። የፈሰሰውን የአምላካችን ደም በትክክል አለማስተዋል ነው።
የተገለጠውን ጽድቅ መቀበል አሻፈረኝ ብለህ የራስህን ጽድቅ የምታቆም፣ በስራህ በአምላክ የዙፋን ፍርድ ፊት በብቃት ለመቆም የምታስብ፣ በአምላክ ጽድቅ ላይ የራስህን የእርግማን ጽድቅ ለመጨመር የምትጣጣር፣ የተገለጠው የአምላክ ጽድቅ አላረካኝም ብለህ እብቅ የሆነውን መልካም ያልሆነውን ግን በአንተ አእምሮ መልካም መስሎህ የምታየውን ስራህን የራስ ገዝ ኢምፓየር አድርገህ ለመገንባት ሙከራ የምታደርግ ግለሰብ ወይም ተቋም ተሃድሶ ያስፈልግሃል

ጽድቅ በእምነት ብቻ ነው የሚለው አስተምህሮ የወንጌል አስኳል አስተምህሮ ነው። ወንጌል ደግሞ የድህነታችን መሰረትና የክርስትናችን አእማድ አስተምህሮ ነው። የድህነት ተስፋ ሙሉ በሙሉ የቆመው ጻድቁ እግዚአብሄር ሃጢአተኞችን እንዲያው በጸጋው ያጸድቃል በሚለው የተደላደለ የወንጌል እውነት ላይ ነው። በዚህ እውነተኛ ወንጌል ቤተክርስቲያን ትቆማለች። በዘላለም ኪዳን በኩል በተገለጠው ጽድቅ በኩል እግዚአብሄር ጽድቃቸው ተብሎ ሊጠራ ልጆቹን በጸጋው ወደራሱ ይስባችዋል። ጽድቅ በእምነት ብቻ ነው የሚለውን አስተምህሮ የማትቀበል ቤተክርስቲያን የወንጌል ጠበኛ ናት። የተሃድሶ ጥሪ ሊደረግላት ግድ ይሆናል ማለት ነው!

Good Christian Books Shelf

16 Oct, 15:17


ስለ ጆን ካልቪን ቀለል ያሉ 10 ነገሮች lol
1 የተወለደበት ዘመን ሚካኤል አንጄሎ የሲስቲን ቻፕልን paint ያደረገበት አመትና የሞተበት ዘመን ደግሞ ታላቁ ባለ ብእር ሼክስፒር የተወለደበት አመት ነው😲
2 ሉተር 95ቱን አናቅስት በውትንበርግ በር ላይ ሲለጥፍ ካልቪን የ8 አመት ጩጬ ነበር🥰
3 ጆን ካልቪን በ22 አመቱ የህግ ዶክትሬት ተቀብሏል 🤭
4 ቅስና ለመማር ገብቶ በዘመኑ ስነ ጽሁፍ በመማረኩ የላቲን፣ የግሪክና የ እብራይስጥ ቋንቋዎችን ጠንቅቆ የተማረ ባለ ብልህ አእምሮ አዳሽ ነበር🤔
5 በመጀመሪያ ጊዜ ያሳተመው መጸሃፍ ከስጦሶካዊያን ወገን የሆነው የሮሙ የሴኔካ መጸሃፍ ላይ የተሰራ ኮመንተሪ ነው። በዚህም ሂውማኒስት ምሁር ነበር 😑
6 ካልቪን ወደ አገልግሎቱ ጠልቆ እንዲገባ በተለይ መጋቢ እንዲሆን ያደረገው የጓደኛው የፋሬል እርግማን እንደነበር ይታመናል😨
7 ካልቪን ሉተርን በአካል ለማየት እንደጓጓ፣ እጅግ የምወደው አባቴ እያለ በፍሊፕ ሜላንክተን በኩል መጸሃፍና ሰላምታ ብዙ ጊዜ እየላከለት አንድም ቀን ከሉተር ጋር ሳይገናኙ ነው የሞተው😥
8 ካልቪን በጣም የሚጠየፈው ከመጸሃፍ ቅዱስ አሳብ ተሻግሮ ማሰብን (speculationን) ነው lol
9 ከአባቶች ታላቁ ጎርጎሪዮስና በርናንድ ክላርቮስ ከሁሉም በላይ የካልቪን የነፍስ ወዳጆቹ ናቸው 🤗
10 ካልቪን ለመጥበስ ያወጣው መስፈርት ይህ ብቻ ነው…. “እኔን የሚማርከኝ ብቸኛ ውበቷ _ ጭምትነቷ፣ ለመገዛት መሰጠቷ፣ ልታይ ልታይ ባይ አለመሆኗ፣ ስግብግብ ያለመሆኗ እና ለጤንነቴ አብዝታ የመጨነቋ ጉዳይ ነው!!"😁😁

Good Christian Books Shelf

16 Oct, 06:40


ጽድቅ በእምነት ብቻ የሚለው የተሃድሶ ቁልፍ አስተምህሮ ለነፍስ ዋስትና የሚሰጥ መለኮታዊ መገለጥ ነው።
ለተጨነቀች ነፍስ በሃጢአት ለተጎሳቆለች፣ ከሚመጣው የአምላክ ቁጣ ማን ያድነኛል እያለች ለምትባክን ነፍስ ጻድቁ እግዚአብሄር እንዲያው ያጸድቅሻል ስትባል አቤት የሚሰማት ደስታ! ያጸደቀሽ ምንም ሳታደርጊ በምህረቱ እንዲያው ስለወደደሽ ነው፤ ተቆጥሮ በማያልቅ በጎነቱ በመንግስቱ አሰበሽ ስትባል አቤት ያለው እርካታ! አጽድቆ ብቻ ሳይሆን እስከ መክበር ድረስ ይጠብቅሻል፣ መንፈሱን በሙላት ይሰጥሻል፣ በልጅነት ማእረግ ያኖርሻል፣ አብዝተሽ ፍሬ ታፈሪ ዘንድ ያጠራሻል፣ ከአለም ከንቱ ነገር ይቀድስሻል፣ አዳፋውን መልክሽን ወደ መልኩ ይለውጣል ከሚል መለኮታዊ ዋስትና የበለጠ ምን የሚታመንና በ አሴት የሚሞላ ነገር አለ!

Good Christian Books Shelf

15 Oct, 15:55


ሰላም ሸልፈኞች፤
ከሚመጣው ቅዳሜ ጀምሮ የሮሜ መልእክት ጥናት እንጀምራለን። ከኛ ጋር ለማጥናት አሳብ ያላችሁ ቅዳሜ ማታ ከ 2 ሰአት አንስቶ በዚህ ቻናላችን ላይቭ ላይ ስለምናጠና ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።
ምናልባት ሌሎች ማጥናት አለባቸው ብላችሁ ለምታስቡ ወዳጆቻችሁ ሼር አድርጉላቸው 🤗🤗

Good Christian Books Shelf

15 Oct, 07:30


ተሃድሶው በሃይል መስፋፋት በጀመረበት ወቅት ኣንዱ ወደ መነኩሴው ይቀርብና…
‘ይህን ታላቅ ገድል/ለውጥ እንዴት ፈጸምኸው?’ ይለዋል
መኖክሴውም፤ ‘ቃሉን ኣስተማርሁ፣ ሰበክሁ ጻፍሁት። ይህን ብቻ ነው ያደረግሁት፤ ሌላ ከዚህ ውጪ የሰራሁት ምንም የለም። እኔ ይህን ኣድርጌ ስተኛ ቃሉ ጳጳሳትን፣ የሃይማኖት ፕሮፌሰሮችን እና ህዝቡን ሲያነቃ ነው ያየሁት። እኔ ሳይሆን ቃሉ ነው ይህን ሁሉ ያደረገው!’

Good Christian Books Shelf

14 Oct, 19:01


"Ambiguity is the fortress of heretics."
- John Calvin

Good Christian Books Shelf

14 Oct, 15:34


Trials are intended:
1. To make us think
2. To wean us from the world
3. To send us to the Scriptures
4. To drive us to our knees
— J. C. Ryle

Good Christian Books Shelf

14 Oct, 05:32


የተሐድሶን ዝክር ስናስብ ድነት ያስገኘልንን የክርስቶስ ፍጹም መታዘዝና ዝምታ እናስብ!
በጥንት የሮማውያን የቅጣት መለኪያ የመስቀል ሞት ቃል ሊገልጠው ከሚችለው በላይ ስቃይ ያለበት ነው። ሮምን የከዳ፣ የመንግሥቷንና ነገሥታቶቿን ክብር የነካ ወይም ከፍተኛ ወንጀል የፈጸመ የማይቀርለት ቅጣት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽን ሞት የተቀበለው በፈቃዱ ነው፦ “ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳን የታዘዘ ሆነ።” (ፊል 2:8)።
ለዕርድ እንደሚነዳ በግ፣ ያለምንም ተቃውሞ ለአሰቃዮቹ ወሰን የሌለው የጭከና ፈቃድ ራሱን ሙሉ ለሙሉ እያወቀ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። በግ እንኳን ልክ መታረድ ሲጀምር ባለው ኀይል ሁሉ ለማመልጥ ይታገላል እንጂ በፍቃደኝነት ራሱን አይሰጥም! ክርስቶስ በቃላት ተዋርዷል፤ መለኮታዊ ማንነቱን በኀይል እንዲገልጥ፣ ስለራሱ ንጽሕና በመሟገት ከመስቀል ሞት እንዲሸሽ ፈታኝ ጥያቄዎች ቀርበውለታል። ይኽም የመጨረሻው ሥነ-ልቦናዊ ጦርነት በመለኮታዊ ማንነቱ ላይ የታወጀና ወደ መስቀል ከመሄዱም በፊት፣ እንዲሁም በመስቀልም ላይ እያለ በዝምታ የታገሠውና ያሳለፈው የመጨረሻው ፈተና ነበር፦
● አትነግረኝምን? ልሰቅልህ ሥልጣን እንዳለኝ ወይም ልፈታህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅምን? (ዮሐ 19:10)
● ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም። (ማር 15:3)
● የካህናት አለቆችም ብዙ ያሳጡት ነበር፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰም። (ማር 15:4)
● ከመስቀል ወርደህ ራስህን አድን አሉ። (ማር 15:30)
በዚህ ሁሉ መድኅናችን “ኢየሱስ ግን ዝም አለ! ለመናገር በሞከረባቸው ወቅት ሁሉ፣ ስለ ምስክርነቱ፣ ራሱን በፈቃዱ አሳልፎ በፈቃደኝነት ከመስጠት አንጻር እንጂ፣ ከማጉረምረም ወይም ለራስ መብት ከመሞገት አንጻር አልነበረም -- "ከላይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልነበረህም" (ዮሐ 19:11)።
በእግዚአብሔር የድነት ሥራ ዕቅድ ውስጥ፣ መስቀሉ መካከለኛ ነው። በመስቀሉ ላይ፣ የእግዚአብሔርም ፍጹም ፍትሕና ፍጹም ፍቅር መገናኘት ነበረባቸው። ኀጢአት ያመጣብንና ልንቀበለው የተገባውን የእግዚአብሔር ቁጣና የሞት ፍርድ፣ ክርስቶስ ቤዛ በመሆን ወሰደልን። ኀጢአታችንን ተሸከመ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ ወሰደልን። ለዘላለም ስሙ ብሩክ ይሁን!
ክርስቶስን ከዚሁ የመስቀሉ ቤዝዎት ሥራ ለማስተጓጎል፣ ከካህናት አለቆችና ከነገሥታት ጀርባ በመሆን የመጨረሻውን የሥነ-ልቦና ጦርነት ያወጀው ሰይጣን ነበር። ይኸው የቀደመው ጠላት ነበር፣ ከአርባ ቀናት ጾምና ጸሎት በኋላ ዝሎና ደክሞ የነበረውን ክርስቶስን በምድረ በዳ የፈተነው። ከጴጥሮስ ጀርባ ሆኖ የክርስቶስን የመስቀል ሞት የተቃወመው፣ ይኸው የቀደመው ጠላት ነበር። ክርስቶስም፣ “ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን” (ማቴ 16:23) በማለት በጽናት ተቃውሞታል። በፈተናዎቹ ሁሉ ጌታችን፣ ከፊቱ ያለውን የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ የድነት ዐላማ በማሰብ “ዝም አለ”። ዐይኑ የበራለትም ጴጥሮስ በኋላ እንዲህ አለ፦
“እርሱም ኀጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤” (1ጴጥ 2:22-23)።
ተሐድሶን ስናስብ ያዳነን ዝምታውም መሆኑንን እናስብ - ኢፍትሐዊ የሆነውን መከራ በትዕግሥት መቀበሉን! በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር ሳይቆጥር፥ ራሱን በፈቃዱ ባዶ የማድረጉ ጫፍ በፍጹም ዝምታውና ትዕግሥቱ ተገልጧል። ከሥላሴ አካል አንዱ ሆኖ ሳለ፣ ዐቅም እንደሌለው ዝም አለ። ፍጡር ጲላጦስ በአምላክ ላይ ያልተገደበ ስልጣን እንዳለው ሲናገር፣ አምላክ ዝም አለ! ኢሳይያስም በመገረም “እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።” አለ። ክርስቶስ ባሳለፈው መከራ ውስጥ፣ ትልቁ የመታገሡ ጉልበት ያረፈው፣ “በጽድቅ ለሚፈርደው ሁሉን አሳልፎ” ለእግዚአብሔር በመስጠት ላይ ነበር።
ይኽን ያስተዋለው ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ እንደ እሳት በመተሰለ መከራ ውስጥ ያልፉ ለነበሩት አማኞች፣ ክርስቶስን ተመልክቱ አለ፦
“ስለ እግዚአብሔር ሲል የግፍ መከራን የሚቀበል ሰው ምስጋናን ያገኛል . . . መልካም ሥራ ሠርታችሁ መከራ ብትቀበሉና ብትታገሡ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ያስገኝላችኋል። የተጠራችሁትም ለዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የእርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌን ሊተውላችሁ ነው።" (1ጴጥ 2:19-21)።
የክርስትና ኑሮ ብርቱ ሰልፍ ያለበት መሆኑን ልብ ልንል ይገባል። ሐዋርያው እንደሚል፣ “…በዚህ ድንኳን እስካለን ድረስ [ሕይወት] ከብዶን እንቃትታለን . . .” (2ቆሮ 5÷4)። መከራን እንዴት አንታገስ? ክርስቶስን በመመልከት! እርሱ፣ ሕይወቱን ሁሉ በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ማዕቀፍ ውስጥ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ ማለቴ ነው።
"ጌታ ሆይ ስለታገሥኸው መከራና ቤዛዊ ሞት ተመስገን፤ በመከራ ውስጥ በታማኝነት ለሚያገለግሉህ ጸጋህን አፍስስ፤ አቤቱ ለክብርህ የሚገባ ሕይወት እንድንኖር ጸጋህን አብዛልን!” አሜን!
(በዶ/ር ግርማ በቀለ የተጻፈ)

Good Christian Books Shelf

13 Oct, 20:59


ይህን መዝሙር ሁሌ ስሠማ ውልብ የሚልብኝ ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? lol ካልነገርኳችሁ አታውቁም 😁 እና ነቢዩ ሙሴ ስለ ራስህ ዘምር ቢባል ራሱ እንዲህ ከሽኖ የሚዘምር አይመስለኝም 😊😊 ቀልዴን ነው ደግሞ ሎል ታላቁን ሙሴን ከተስፋዬ ጫላ ጋር እንዴት ታወዳድራለህ ብላችሁ ጥርሳችሁን አታፏጩብኝ 😁😀