Mereja መረጃ @mereja_tv Channel on Telegram

Mereja መረጃ

@mereja_tv


Mereja መረጃ (Amharic)

መረጃ የሚኖሩት ዜናዎችን እና ምርጫዎችን በኢትዮጵያም እና በተለያዩ ወቅታዊ ስቴዲዮ በብዛት ለሆነ የተለያዩ ቅንብሮች ናቸው። በመረጃ የአዲስ ዓመት ቀን እና የማኅፀፍ ፈቃድ መንገድን የምረቃ ዜናዋን ልናሺን ይከታተሉ። Mereja መረጃ በኢትዮጵያ እና በተለያዩ ውድ ስቴዲዎች ላይ በደጋሚ እና በሚገርመው ጊዜ ተገልጿል።

Mereja መረጃ

24 Feb, 11:10


የአለም የሀይልና የፖለቲካ አቅጣጫ ተቀይሮ አድሯል።

የተናገረውን ይኖራል የሚሉት ፑቲን በመጨረሻም ሰአት ጦሩ ወደ ዩክሬን እንዲገባ አዟል። ሰይጣን የሚል ቅጥል ስም ያለው የኒኩሊየር ቦንቦ መታዘዣው በፑቲን የእጅ ሰአት ላይ አብሮ ታስሯል፣ ይላል የሩሲያው ላይን (አንባሳ) ጋዜጣ።

አሁን ላይ ከምዕራባውያን የተገዙ የዩክሬን ራዳርና ጀቶች ፀረ ሚሳኤል ድሮች ከሲስተም ውጭ ሆነዋል። ቀይ ለባሽ የሚባል ስም የተሰጠው መናጢው የሩሲያ ጦር ዩክሬን በፈጣሪ ባረኬያታለሁ፣ 5 ሰአት ብቻ ስጡኝ፣ የእግር ሹራብ (ካልያስችንን) የምንቀይረው በአርቲስቱ የዩክሬን ቤተመንግሥት ውስጥ ይሆናል ብሏል።
.
ዩክሬናውያን በበኩላቸው የያዙትን መሳሪያ እየወረወሩ በሰማይና በመሬት የመጣባቸውን የምድራችን ክፉ ማዕበል እጃቸውን በመስጠት የሩሲን ወታደር መቀበል ጀምረዋል። ምዕራባውያን አለንልህ ብለው ልቡን ያሳበጡት የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዋና ከተማዋን ለቆ ከወጣ 7 ሰአት ሆኖታል። አሁን የራሽያ ወታደር ወደ ዩክሬን ዋና ከተማ እየገሰገሰ ነው።
.
እንቅልፎ (ባይደን) የአለም ህዝብ ለዩክሬናዊያን ፀሎት (ዱአ) እንዲያደርግላቸው መልዕክት አስተላልፎ ተኝኋል ። እስካሁን ከእንቅልፍ አልተነሳም።
ተንስቶ ምንም ነገር እንዳይወስን፣ ቆፍጣናው ፑቲን አስጠንቅቀዋል። የሩሲያን አንድ እርምጃ አደናቅፋለሁ የሚል ካለ አለም አይቶት የማያቀው እርምጃ ይጠብቀዋል ብለዋል።
.
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ J ትራምፕ በበኩሉ፣ እኔ ስልጣን ላይ ሆኘ ብሆን ምንም ነገር አይከሰትም ነበር እያለ በባይደን እየተሳለቀበት ይገኛል።

ሱሌማን አብደላ

Mereja መረጃ

24 Feb, 11:04


ጦርነቱ ተጀመሯል

3ኛ የዓለም ጦርነት ይሆን የሚለው ዛሬ ለሊት ተጀመሯል::

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን

ዩክሬን ድንበሯ ላይ የነበረው ጦራቸውን ወደ ዮክሬን ሙሉ ለሙሉ እንዲገባ አዘዋል

* ዩክሬን ሰማይ ላይ ጭስ በጭስ ሆኗል

* ሩሲያ እጅግ ዘመናዊ መሳሪያዎች እየጠቀመች ነው ተብሏል

* የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት የዩክሬን ህዝብ በቻለው መጠን ወደ ውጊያ ይግባ ብለዋል

* በዚህም በዓለም ላይ ያሉ ንግዶች ቀዝቅዘዋል

* ነዳጅ አንድ በርሜል ከ100 ዶላር በላይ ሆኗል ይህም እጅግ ውድ አድርጏታል

* ይህ ጦርነት በአለም ላይ ላሉ ንፁሀን ና ድሀው ህዝብ እጅግ ይጎዳል

እጅግ የሚገርመው ደሞ አይዞሽ ዩክሬን እኛ አለንልሽ እያሉ የነበሩት

* አውሮፓውያንና አሜሪካውያን ከመአቀም በቀር እስካሁን ዝምታን መርጠዋል

አሜሪካኖችን ና አውሮፓውያን ባላቸው ሚዲያ በሙሉ ሩሲያን እየወነጀሉ ይገኛል

እነሱ ዓላማቸው መጀመሪያ በሚዲያ ዘመቻ ያደርጉና ጥላቻን ፈጥረው ወደ ውጊያ ሊገብ ይችላል እየተባለ ይገኛል::

* አሜሪካ
* እንግሊዝ
* ፈረንሳይ
* ጀርመንና ሌሎችም ወጊያውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከገቡ 3ኛ የዓለም ጦርነት ይነሳል

በጣም የተፈራው ግን ታላቅና ግዙፍ ጦር ያላት ቻይና ወደዚህ ጦርነት ለሩሲያ ተደርባ እንዳትገባ ነው:: ቻይና ወደዚህ ገባች ማለት ትልቅ እልቂት ይፈጠራል

የአሜሪካው መሪ ጆይ ባይድን ዛሬ መግለጫ ይሰጣል

ዓለም ይሄ ሰውዬ ምን ሊል ይሆን እያለ በጉጉት እየጠበቀው ይገኛል::

ጦርነት አስክፊ ቢሆንም ሩሲያውያን ግን ለአሜሪካውያን ና ለአውሮፓውያን ደንታ እንደሌላቸው ያመነችበትን ነገር ማድረግ እንደምትችል ማሳየት ችለዋል

ሱለይማን አብደላ

Mereja መረጃ

12 Feb, 18:28


ሰበር ዜና
.
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ አመነጨ። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከተሳካ የኤሌክትሪክ ሀይል ሙከራ ቡኋላ ወደ ሙሉ በመሉ የኤለክትሪክ ሀይል ማመንጫ ተሸጋግሯል። ግድቡ በዘንድሮው አመት ያመነጨዋል ከተባለው 300 ሜጋዋት ውስጥ 180 ሜጋውቱ አምንጭቶ ከጣና በለስ ቅርጫፍ መስመር ጋር እየሰራ ሲሆን፣ ከዋናው የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጋር ተገናቶ መሉ መሉ በስራ ላይ መሆኑን አረጋግጫለሁ።

እንኳን ደስ ያላችሁ !

ሱሌማን አብደላ

Mereja መረጃ

09 Feb, 17:52


ሕወሓት በአፋር ክልል የጅቡቲ መስመርን ለመቁረጥ ቢሞክርም አልተሳካለትም ተባለ!!

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)በአፋር ክልል ሰርዶ የፍተሻ ኬላን ለመቁረጥ ጥረት ቢያደርግም እንዳልተሳካለት የአፋር ክልል ዛሬ ዐስታወቀ።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ፦ አቶ አህመድ ኮሎይታ ለዶይቸ ቬለ (DW) ዛሬ ከሰአት አካባቢ እንደተናገሩት ሕወሓት «እስካሁን ድረስ ሰርዶን አልቆረጠም» ብለዋል። «ከተሳካለት ግን ያንን አካባቢ ቆርጦ አሁንም መጀመሪያ ያልተሳካለትን ሕልም የማሳካት ዓላማ አለው» ሲሉም አክለዋል። የአፋር ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ የመከላከል ሥራ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በክልሉ በዞን 1፤ 4 እና 5 በኩል ሕወሓት ሚሌን ለመቁረጥ ከፍተኛ ጥረት አድርጎ የነበረ ቢሆንም፤ እንዳልተሳካለት ኃላፊው ገልጠው «ያ ሳይሳካለት ሲቀር እና እዚያ አካባቢ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ የበቀል ርምጃ ነው አሁን ዞን 2 ላይ መልሶ እየወሰደ ያለው» ብለዋል።

አቶ አህመድ፦ «በአፋር አካባቢ በተለይ በሰሜናዊ ዞን፤ በዞን 2፤ ኪልቤት ራሱ በሚባለው አካባቢ» ጦርነቱ እየተካኼደ መሆኑን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። አካባቢው ከትግራይ ክልል አዋሳኝ ዞኖች አንዱ ነው። ከመጋሌ ወረዳ ጀምሮ እስከ ኮነባ ድረስ ጦርነት በአሁኑ ወቅት እንዳለም ተናግረዋል። «በመጋሌ፣ አብአላ፣ ኢሬብቲ፣ በራህሌ እና ኮነባ ወረዳዎች ላይ የሕወሓት ኃይል በከባድ ጦር መሣሪያ በተለይ ሕጻናት እና ሴቶች ሕይወታቸው እንዲጠፋ» አድርጓል ብለዋል።

ምንጭ፣ የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ

Mereja መረጃ

31 Jan, 15:10


#ሰበር ችሎት

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ታስረው እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጠ።

ከህዳር 4 ቀን 2011ዓ/ም ጀምሮ በስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሜቴክ ዳሪክተር ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ከዕርሻ መሳሪያ ግዢ ጋር ተያይዞ በዓቃቢህግ በቀረበባቸውባቸው የሙስና ክስ የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መጀመራቸው ይታወሳል።

በዚህ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ትዛዝ ተሰቶባቸው የነበሩት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይገኙበታል። ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መጥሪያ እንዲያደርስ የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በኩል አፈላልጌ ላገኛቸው አልቻልኩም ሲል መልስ ሰቶ ነበር።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግላቸው የሮማን ፉውንድሽን እንደሚሰሩና በመንግስ ፖሊስ እጀባ እየተደረገላቸው እንደሚቀሳቀሱ ጠቅሰው ይህ በሆነበት ሁኔታ ፖሊስ ላገኛቸው አልቻልኩም በማለት የሰጠው ምላሽ  አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ በድጋሚ ትዛዝ እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ፖሊስ አቶ ሀይለማርያምን ደሳለኝን ካሉበት አፈላልጎ አስሮ እንዲያቀርባቸው ትዛዝ ሰቷል።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja
 

Mereja መረጃ

24 Jan, 18:01


ሰበር ዜና❗️

ህወሓት በአፋር ክልል የጀመረውን ውጊያ አጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ‼️

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ውስጥ ገብቶ የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት ለማካካስ በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል በአብአላ እና በመጋሌ ወረዳ የከፈተውን ውጊያ አጠናክሮ መቀጠሉን የአፋር ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አስታወቀ።

ምንም ዓይነት ሰብዓዊነት እና ርህራሄ ፈፅሞ የሌለው አሸባሪው ቡድን በንፁሀን ዜጎች ላይ ከባድ መሳሪያ በመክፈት እያሸበረ ይገኛል ብሏል የክልሉ መንግሥት።

ሁሌም ከትንኮሳ አርፎ የማያውቀው የሽብር ቡድኑ ለዘመናት የቆየውን በድንበር የሚዋሰኑ የአፋር እና የትግራይ ሕዝቦችን ግንኙነት ከምንም ሳይቆጥረው ሁለቱን ሕዝቦች በማጋጨት የማይረባ ትርፍ ለማግኘት ሌት ተቀን እየጣረ ይገኛል። እያደረሰ ባለው ጥቃትም የአፋር ንፁሃን ኢላማ በማድረግ የሽብር ተግባሩን በማስፋት ላይ ነው።

በዛሬው ዕለት እንኳን በኪልበቲ ረሱ ዞን በተለያዩ ቦታዎች የአፋር ክልልን ወሰን ጥሶ በመግባት በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በመክፈት በርካታ ንፁሀንን ለጉዳት ዳርጓል።

በአፋር በተለያዩ አካባቢዎች ወረራ አካሂዶ በሁሉም ግንባሮች ሽንፈትን አስተናግዶ የወጣው አሸባሪው ህወሓት አሁንም እንደ አዲስ በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል በከፈታቸው ግንባሮች የምድር ድሮኖቹ አስፈላጊውን መከታ እና ማጥቃት በማካሄድ የጁንታውን እብደት የሚያመክን በመሆኑ አሸባሪው ቡድን ዘልቆ ገብቶ ለመውረር ያስገባውን ኃይሉን አስቀድሞ ሊያወጣ ይገባል ሲል የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ባወጣው መግለጫ አሳሰቧል።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ

Mereja መረጃ

07 Jan, 18:04


#ሰበር

መንግስት ከፍተኛ የህወሓት አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች የተወሰኑ እስረኞችን በምህረት ፈታ

1.አቶ ስብሐት ነጋ
2.ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ
3. አቶ ዓባይ ወልዱ
4. አቶ አባዲ ዘሙ
5. ወሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር
አቶ ኪሮስ ሐጎስ
6. አቶ ጁሐር መሐመድና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ
7. አቶ እስክንድር ነጋና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ ከእስር መለቀቃቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

Mereja መረጃ

07 Jan, 18:02


#ሰበር

እስክንድር ነጋን ጨምሮ ታስረው የነበሩ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር ተለቀቁ


እስክንድር ነጋን ጨምሮ ታስረው የነበሩ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ (ባልደራስ) የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት ከእስር ተለቀቁ።

የፓርቲውን ሊቀመንበር እስክንድር ነጋን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮልን መሠል የፓርቲው አመራሮች ከእስር መፈታታቸውን ባልደራስ በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።

ጀዋር መሃመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራሮች ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአል ዐይን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።

Mereja መረጃ

05 Jan, 13:43


ቻይና ለፕሬዝዳት ኢሳያስ አፈወርቂ የጉብኝት ግብዣ አቀረበች!!

የቻይናው ፕሬዝዳት ሺን ጂንፒንግ ለኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ የጉብኝት ግብዣን አቀረቡ፡፡ ግብዣው የቀረበላቸው የፕሬዝዳንቱን መልዕክት እና ልዑክ ይዘው በአስመራ በሚገኙት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኩል ነው፡፡

ሚኒስትሩ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በሺን ጂንፒንግ የተላከን ደብዳቤም አስረክበዋል፡፡ ደብዳቤው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወደ ቤጂንግ አቅንተው በሁለትዮሽና ስልታዊ አጋርነት ዙሪያ ጥልቅ ውይይት እንዲያደርጉ የሚጠይቅ መሆኑን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገጻቸው አሳውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በበኩላቸው የቻይናን የ100 ዓመታት የጋራ ተጠቃነት መርህ ጉዞ እና በዓለም ዐቀፍ ሕጎች ማዕቀፍ ውስጥ ሆና ዓለምን ሚዛናዊ ለማድረግ የምታደርውን ጥረት አድንቀዋል፡፡*ፕሬዝዳንቱ የኤርትራን የልማት ፕሮግራሞች፣ ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ጉዳዮች እንዲሁም በቀጣናዊና ዓለም ዐቀፋዊ ጉዳዮች የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያላትን አተያይ በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ሁለቱ ወገኖች በምፅዋና አሰብ ወደቦች ልማት፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በመሰረተ ልማትና ማዕድን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማላቅ ተስማምተዋል፡፡
T.me/ethio_mereja

Mereja መረጃ

05 Jan, 11:44


"መከላከያ በያዛቸው አካበቢዎች እንዲጸና የተደረገው የትግራይ ህዝብ በድጋሚ የጥሞና ጊዜ አግኝቶ የሽብር ቡድኑ ትክክለኛ ማንነት እንዲገነዘብ ለማስቻል ነው" --የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በ “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” የመከላከያ ሰራዊት በያዛቸው አካበቢዎች እንዲጸና የተደረገው የትግራይ ህዝብ በድጋሚ የጥሞና ጊዜ አግኝቶ የሽብር ቡድኑ ትክክለኛ ማንነት እንዲገነዘብ ለማስቻል መሆኑን መንግስት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ፥ የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ለተጨማሪ ጦርነት ከመማገድ እንዲቆጠብ መንግስት ያሳስባል ብለዋል። በሽብር ቡድኑ ተወረው በነበሩና ከፍተኛ ውድመት በደረሰባቸው አካበቢዎችም ዜጎችን ለማቋቋም ሁሉም ሊረባረብ ይገባዋል ተብሏል።

@Mereja_Tv

Mereja መረጃ

24 Dec, 06:54


አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ በይፋ ሰረዘች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትናንት ሐሙስ ምሽት ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት የአፍሪቃ ሀገራትን Africa Growth Opportunity Act (Agoa) የቀረጥና ታሪፍ ነፃ መብት መሰረዛቸውን ይፋ አድርገዋል!!

ኢትዮጵያ የተሰረዘችው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ተፈፅሟል ለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከአማፅያን ጋር ድርድር እንድትቀመጥ ለማስገደድ ያለመ መሆኑንና ሁለት ወራት የማሰቢያ ጊዜ ገደብ ተሰጥቷት ነበረ። የኢትዮጵያ መንግስት ለአሜሪካ ጫና ባለመንበርከኩ እገዳው ተግባራዊ እንዲሆን ፕሬዝዳንት ባይደን በፊርማቸው አፅድቀውታል።

ከፈረንጆቹ አዲስ አመት ጀምሮም ውሳኔው ይፀናል።

የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያን ከንግድ ፕሮግራሙ እንዳይሰርዝ ጥቂት የኮንግረስ አባላት ለፕሬዝዳንት ባይደን ጥያቄ ቢያቀርቡም ፕሬዝዳንቱ ጥያቄውን ቸል ብለው ኢትዮጵያን ማሊንና ጊኒን በመሰረዙ ፀንተዋል። አጎዋ የቀረጥና የታሪፍ መብት ለ38 የአፍሪቃ ሀገራት የተሰጠ ዕድል ሲሆን እንዲቀጥል ካልተወሰነ ከሶስት ዓመት በኋላ ሙሉ ፕሮግራሙ ይጠናቀቃል።

አሁን በኢትዮጵያ ላይ የተወሰደው እርምጃ የአልባሳትና ጨርቃጨርቅ እንደስትሪው ባለፉት አመታት ያሳየውን ዕድገት የሚገታና የባለሀብቶችን እንቅስቃሴ የሚደድብ ነው።

በአንፃሩ ቻይና 300 ቢሊየን ዶላር ለሚገመት ንግድ ለአፍሪቃ ሀገራት በሯን ክፍት ለማድረግ በቅርቡ መወሰኗ ለአንዳንድ ሀገራት ተስፋ ሰጪ ሆኖ ታይቷል።

@Mereja_Tv

Mereja መረጃ

23 Dec, 14:47


ወደ ትግራይ ክልል የመከላከያ ሰራዊቱ እንዳይገባ ከመንግስት ውሳኔ ተላለፈ።
****
ለዘመቻ ህብረ-ብሄራዊ ግዳጅ የተሰጠው የመከላከያ ሰራዊት ባለበት ስፍራ ረግቶ እንዲቆይ ከመንግስት ትዕዛዝ ተላለፈ።

Mereja መረጃ

22 Dec, 16:11


ሰበር ዜና

ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የሰቆጣ ከተማን ተቆጣጣሩ

በአንጸባራቂ ድል ወደፊት እየገሠገሡ የሚገኙት ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ የጸጥታ ኃይሎች አብዛኞቹን የዋግ ኅምራ አካባቢዎች ነጻ በማውጣት የዞኑን ዋና ከተማ ሰቆጣን ተቆጣጥረዋል፡፡ አካባቢው ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በሚወጣበት ጊዜ የዋግ ኅምራ ሚሊሻዎች አስደናቂ ጀብዱ የፈጸሙ ሲሆን፣ የአካባቢው ሕዝብም ከመከላከያ ሠራዊትና ከአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመጣመር ደጀንነቱን በብቃት አሳይቷል፡፡

የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ የጸጥታ ኃይሎች ቀሪዎቹን ሥፍራ እያጸዱ፣ የፈረጠጠውን የአሸባሪውን ጀሌ እየደመሰሱ፣ ወደ አበርገሌ በመገሥገሥ ላይ ይገኛሉ፡፡

በተያያዘም ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች፣ በቆቦ ግንባር በአንድ በኩል ዋጃና ጥሙጋ ላይ የሠፈረውን የጠላት ኃይል በመጥረግ ወደ አላማጣ ከተማ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተኩለሽን ተቆጣጥረው በማጽዳት፣ ወደ መረዋና ኮረም እየገሠገሡ ይገኛሉ፡፡

በእሳታማው የጀግኖች ክንድ የተደቆሰው አሸባሪው ሕወሐት፣ ተቸካይና ኋላ ቀር በሆነ የጦር ዘይቤ፣ ዕብሪትን እንደ መሣሪያ በመጠቀም፣ ከገባባቸው የአማራና የአፋር ክልል አካባቢዎች እንደገባ መውጣት አቅቶት፣ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሣራ ደርሶበት ተደመስሷል፡፡ ይሄንን ሐፍረቱን መሸፈን ሲያቅተው በአንድ በኩል ለሰላም ሲል የወጣ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሽንፈቱ ውኃ የማይቋጥር ምክንያት እያቀረበ፣ አድኑኝ የሚል እሪታ እያሰማ፣ በለመደው ውሸት የትግራይን ሕዝብና የዓለምን ማኅበረሰብ ለማደናገር እየሞከረ ይገኛል፡፡

በዚህ ጦርነት የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ የሆነውና አሸባሪውን ሕወሐት በጀግንነት የታገለው የዋግ ኅምራ ሕዝብ፣ በጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ የጸጥታ ኃይሎች፣ እንዲሁም በራሱ በዋግ ኅምራ ሕዝብ ትግል፣ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በመውጣቱ፣ በዚሁ አጋጣሚ መንግሥት እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡

ነጻነታችንን የምናስከብረው በተባበረው ክንዳችን ነው!
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

@Mereja_Tv

Mereja መረጃ

22 Dec, 07:25


መረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት
Mereja Tv satellite broadcast
Eutelsat 8 West B
Freq: 11.636 Vertical
SR: 27.000
FRC: 5/6

https://t.me/Mereja_Tv

@Mereja_Tv

Mereja መረጃ

21 Dec, 10:46


ሰበር ዜና‼️

አላማጣ ከተማ ከወራሪው ሀይል ነፃ ወጣች!!

አላማጣ ከተማ በጀግናው የወገን ጦር ቁጥጥር ስር ውላለች። ጀግናው የኢትዮጵያ የፀጥታ ሀይሎች ጥምረት የአላማጣ ከተማን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተረጋግጧል። ጥምር ጦሩ ሌሎች አከባቢዎችንም በመቆጣጠር ወደፊት እየገሰገሰ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ራያ አላማጣ በኢትዮጵያ የ[አማራ] ክልል በሰሜን ወሎ የምትገኝ ውብ ከተማ ስትሆን ከአዲስ አበባ 600ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ45,632 ህዝብ መኖሪያ ስትሆን ከነሱም 22,712 ወንዶችና 22,920 ሴቶች ይኖሩባታል። (ኢትዮ-መረጃ)
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja

Mereja መረጃ

21 Dec, 06:35


ሽብርተኛው ህወሓት በቆቦ ከተማ ከ120 በላይ ንጹሃንን በጅምላ መጨፍጨፉን እና የ9 ወር ነፍሰጡርም መድፈሩ ተሰማ!!

አሸባሪ ቡድኑ በቆቦ ከተማ ከ120 በላይ ንጹሃንን በጅምላ በመጨፍጨፍ አረመኔነቱን በተግባር አሳይቷል ሲሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል። ከዚህ በፊት አሸባሪ ቡድኑ በቆቦ ከተማ ላይ ከፍተኛ በደል ሲፈጽም መቆየቱን ያስታወሱት ነዋሪዎቹ፥ የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡርን ጨምሮ በርካታ ሴቶችን አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ የጭካኔ በትሩን ማሳረፉን ጠቁመዋል።

ቡድኑ ወንዶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸሙን ጠቅሰው፥ የቡድኑ ታጣቂዎች ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ንብረት መዝረፍና ማውደምን ጨምሮ ያልፈጸሙት ግፍ እንደሌለም ነው የተናገሩት። በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎችን በአደባባይ ያለ ርህራሄ በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ጥምር ጦሩ አሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ አካባቢውን ከወራሪው #ነጻ በማውጣቱ መደሰታቸውንም አስታውቀዋል።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja

Mereja መረጃ

20 Dec, 17:47


የደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የድረሱልኝ ጥሪ❗️❗️

የአሸባሪው ህወሀት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፃፉት የተማፅኖ ደብዳቤ ህወሓት ኃይሎቹ ወደ ትግራይ እንዲመለሱ ማዘዙን እና ለሰላማዊ ድርድር ዝግጁ እንደሆነ ፅፏል።

ይህም ውሳኔ "ወዲያው ተግባራዊ" እንደሚሆን በደብዳቤያቸው ላይ አመልክተው፤ በአስቸኳይ ግጭቶች ቆመው ድርድር እንዲጀመር ጠይቀዋል።

ደብረጽዮን በደብዳቤያቸው ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሲቪል አገልግሎትና ለእርዳታ አቅርቦት ከሚደረጉ በረራዎች ውጪ በትግራይ የድሮን እና አይሮፕላን በረራዎች እንዲቆሙ እንዲሁም በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲጣል ጠይቀዋል።

በሌላ ዜና ጀግናው የኢትዮጵያ የፀጥታ ሀይሎች ጥምረት አብዛኛውን የአማራ ክልል ከተሞች እና አከባቢዎች ከአሸባሪው ሀይል ያስለቀቀ ሲሆን በዛሬው እለትም #አላማጣን መቆጣጠሩን ተሰምቷል። ከመንግስት የተሰጠ ዝርዝር መረጃ ባይኖርም የወገን ጦር አላማጣን በመቆጣጠር ወደ ፊት እየገሰገሰ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ከህወሓት በኩል ተጻፈ ስለተባለው ደብዳቤ ከተባበሩት መንግሥታትም ሆነ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

ኢትዮመረጃ

T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja

Mereja መረጃ

20 Dec, 15:46


ሰበርዜና‼️

አሸባሪው ህወሀት ለሠላማዊ ድርድር በር ለመክፈት ከትግራይ ውጭ ካሉ ሁሉም አካባቢዎች ሠራዊቱን እንዲወጣ ማዘዙን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጻፈው የተማፅኖ ደብዳቤ አመላከተ!!

በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወሀት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴክረታሪ ጀነራል አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለ50 ሀገራት በጻፉት የአድኑኝ ተማፅኖ ደብዳቤ ሠራዊታችን ከሌሎች ክልሎች እንዲወጣ የቀረበልንን አለም አቀፍ ጥሪ ተቀብለን ኃይላችን ከትግራይ ውጭ ካሉ ሁሉም አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ አዝዣለሁ ብሏል።

የተማፅኖው ደብዳቤው የትግራይ ህዝብ የኢትዮ-ኤርትራ ጥምር ጦር፣ የአማራ ሚሊሺያና ልዩ ሀይል፣ እንዲሁም ከውጭ አገራት የመጡ ድሮኖችን ለብቻው መቋቋሙን ያትታል።

አሸባሪው ህወሀት ከማንም አንዲት ጥይት፣ ተሽከርካሪ፣ ዩኒፎርም ሳይቀበሉ ከዓመት በላይ ይህን ሁሉ ሀይል እንደተቋቋሙ የሚያስረዳው ደብዳቤው፥ ከራሳችን ውጭ የማንንም አጀንዳ አላስፈጸምንም፤ የማንም ዕዳ የለብንም ይላል። ከዚህም በተጨማሪ በደብዳቤው በትግራይ ከውጊያ ነጻ በረራ ነጻ ዞን እንዲቋቋም እና በኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ የመሳሪያ ግዥ ማዕቀብ እንዲጣል ይጠይቃል።

አሸባሪው ህወሀት በሊቀመንበሩ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል በፃፈው የአድኑኝ ደብዳቤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ እና ትግራይ ክልል መካከል የUN ሰላም አስከባሪ እንዲያሰማራ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja