የቅዱሳን ታሪክ @yekidusantarik1 Channel on Telegram

የቅዱሳን ታሪክ

@yekidusantarik1


ሰማያት የእግዚአብሔር ክብር ይገልፃሉ

የቅዱሳን ታሪክ (Amharic)

የቅዱሳን ታሪክ ማንኛውም እናት ወይም እናቶ እና ልጆች ለምን ታሪክ አለው? በርሱ እንዴት እንደሚደርስ ተጠናቋል? የቅዱሳን ታሪክ እንዴት እና ላስፈቀረበት መረጃ ለምን ታሪክ ውስጥ ይገኛል? ይህ ታሪክ ስለሆነ የእግዚአብሔር በሙሉ በርሱ የፀነሰውን አንድ የትዕግስት ብር የሚወዘንና የዘለዓለም ታሪክን ያበረታል። የሚቀርብ በማለፍ መንካት አይደለም። 'የቅዱሳን ታሪክ' ታሪክ በሊንክ ማድረግ ሲስተም እናቶችን እና ልጆችን ከአብሺሁን በሀገር ለመመልከት ያስፈልጓል። የእግዚአብሔር ክብር እና መላእክትን መልክ የሚጠቀሙባቸው ለምሳሌ ታርኮችን እና የቅዱሳን ልጅ ልጆች ከሚገኙበት ዕርምባዊ እና ጥንቃቄ ታሪክታቸውን እንዴት ማስከበራ መኖሪያን ይሰጡት። የቅዱሳን ታሪክ የእግዚአብሔር ክብር እና ታሪክ አቅምን እንደሚያነቡ ድምጽ እና መረጃ እናትን እና ልጆችን ስኬት እንደገለፁ ለማሳየት እናት ማህበረሰብ ተጠቅመለት።

የቅዱሳን ታሪክ

18 Nov, 17:12


በኦሪት አባት እና እናት የሰደበ ይገደል ይላል። እንዴት አንቺ የሰደበ አይገደል

   አባ ፅጌ ድንግል 

የቅዱሳን ታሪክ

17 Nov, 14:46


"ዲያብሎስ በእናንተ ላይ እጅግ ክፉ ነገርን በማምጣት አሳዝኖአችኋልን? እናንተም ኢዮብን አብነት አድርጋችሁ እግዚአብሔር ይመስገን በማለት አሳዝኑት፡፡ ዲያብሎስን ድል ማድረግ ስትሹ ይህን መሣርያ ዘወትር ያዙ፤ ምስጋና፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የቅዱሳን ታሪክ

17 Nov, 14:39


ሰውን የሚያተርፈው ምርጫው እንጂ ቦታው አይደለም።

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
             

የቅዱሳን ታሪክ

16 Nov, 05:36


ጸሎት

ነፍስ የሌለው ስጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ጸሎት የማታደርግ ነፍስ ሕይወት የላትም

ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ

የቅዱሳን ታሪክ

13 Nov, 04:25


ከፅሎት በቀር ንስሐ መግቢያ በር አለ ብሎ የሚናገር ቢኖር እርሱ በሰይጣን የተታለለ
ነው 

ማር ይስሐቅ

የቅዱሳን ታሪክ

10 Nov, 09:17


እግዚአብሔር በማታውቀው መንገድ የልቦናህን መሻት ይፈጽምልሃል። ስለዚህ በሰላም ሁን እና እግዚአብሔርን ጥራው።

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 05:03


ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፣ እጁን እግሩን ተቸነከረ ጎኑ በጦር ተወጋ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደም ውኃ ፈሰሰ።

ሃይማኖተ አበው 34 ፥ 14

የቅዱሳን ታሪክ

07 Nov, 13:03


ብሂለ አበዉ (የቅዱሳን ወርቃማ አባባሎች)

ሰው ሆይ እያንዳንዷ ድርጊትህን የሚመለከት የሰማይና የምድር ንጉስ እንዳለ ፈፅመህ አትርሳ  

ቅዱስ ዩሀንስ  አፈወርቅ



ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ 

አባ ኤፍሬም አረጋዊ




<< ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናለሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።>>
               
                      - ቅዱስ አርሳንዮስ-

የቅዱሳን ታሪክ

05 Nov, 15:33


ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት"

ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን

የቅዱሳን ታሪክ

03 Nov, 04:16


‹‹እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ
ሀገረኪናሁ ገሊላ እትዊ
ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ
እምግብፅ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ፡፡››

ትርጉም፡-
እመቤቴ ማርያም ሆይ! ስሙ ናዝራዊ የሚባል ልጅሽን ለአዳምና ለሔዋን ክብር የባሕርይ አባቱ አብ ከግብጽ ይጠራዋል፣ማለት በግብጽ ስደት አይሞትም ኋላ በቀራንዮ ተሰቅሎ ዓለምን ያድናል ብሎ ነቢዩ ዖዝያን (ሆሴዕ) ትንቢት እንደተናገረ እስከ መቼ በባይድ አገር ትኖሪያለሽ? እነሆ ወደ አገርሽ ናዝሬት ተመለሽ፡፡

(ሰቆቃወ ድንግል)

የቅዱሳን ታሪክ

03 Nov, 04:13


እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ  ባሕርን ተናገረው

እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት

ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር

እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"

ልብ አድርጉ :-

ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል

ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል::  ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ  ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::

ይህንንም እናስታውስ

ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::

ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-

"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 23 2013 ዓ/ም

Share like subscribe 🙏

https://t.me/yekidusantarik1

2,714

subscribers

244

photos

60

videos