ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt @kdusan_melaekt Channel on Telegram

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

@kdusan_melaekt


#ቅዱሳን_መላዕክት

እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል!
ግሩፕ:- @zmare_melaekt

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt (Amharic)

እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaektnnቅዱሳን መላዕክት is a channel dedicated to providing educational content and resources for students and learners. With a focus on various subjects and topics, this channel aims to help individuals enhance their knowledge and skills. From exam preparation materials to informative articles and tips, users can find valuable resources to support their learning journey. Additionally, the channel also shares updates and announcements related to educational events and opportunities. Don't miss out on the chance to improve your education and stay informed - join ቅዱሳን መላዕክት today!

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

10 Nov, 09:54


🌹#ናሁ_ተፈፀመ_ማህሌተ_ፅጌ🌹
#ተመስገን!
🙏🙏🙏

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

07 Nov, 11:58


❤️ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ🥰

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

24 Oct, 06:34


#ቅምሻ
#አሐቲ_ድንግል
#ማርያም ማለት ምን ማለት ነው?

ማርያም ማለት፦
እግዝእት:- እመቤት ማለት ነው የዓለሙን ንጉስ በመውለዷ ከፈጣሪ በታች የፍጥረት ንግስት ሆናለችና፤

ጸጋ ዘተውኅበት ለኩሉ ዓለም፦ ለዓለሙ ሁሉ የተሰጠች ጸጋ ማለት ነው። ለአበው በተስፋ የሰጣቸው ሲሆን ለእኛ ደግሞ ከመስቀሉ ሥር እናት ትሁናችሁ ብሎ ሰጥቶናልና። (ዮሐ ፲፱፤፳፮) ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ንግሲቲቱ በቀኝህ ትቆማለች የሚለውን የዳዊት መዝሙር ሲተረጉም In becoming the mother of creator she become the Mistress of all creation (የፈጣሪ እናት በሆነች ጊዜ የፍጥረታት ሁሉ ንግስት እመቤት ሆናለችና በማለት ተርጉሞታል። (መዝ 44፤9)

ተስፋ ማለት ነው፦ ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ካለው ጀምሮ መድኃኒቴን የምትወልጅልኝ ልጄ እያለ ተስፋ አድርጓት በልቦናው መዝገብነት ይዟት የኖረ ስንቁ ናት። አበውም ድንግል ማርያምን መቼ ፀሐይ ክርስቶስን ወልዳልን ከቁረ መርገም ድነን አይተነው እያሉ ተስፋ አድርገዋት ነበር። ተስፋቸው ክርስቶስም ከእርስዋ ተወልዶ ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ገብተዋል። ለዚህ ምስክር የሚሆነን አረጋዊ ስምዖን "ጌታ ሆይ አገልጋይህን ዛሬ ታሰናብተዋለህ፥ አቤቱ በሰላም እንዳዘዝክ አይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና በህዝብ ፊት ሁሉ ያዘጋጀኸውን ለአህዛብ ብርሃንን ትገልጽ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ክብርን" በማለት ተስፋውን አይቶ አርፏል። (ሉቃ 2፥29)

የባህር ከርቤ (Myrrh of the sea) ማለት ነው። ይህ ከርቤ እጅግ ውድ ዋጋ ያለው ከዘይት ጋር ተጨምሮ  በጠበብተ ኦሪት ተቀምሞ ለንዋያተ ቅድሳት ማክበሪያ የታዘዘ ሽቱ ነው። ሙሴ ደብተራ ኦሪቱን በኦሪት መቅደሱ ያሉትን ሁሉ በዚህ ሽቱ እንዲቀባ ታዟል። ሽቱ ያረፈባቸውን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮታል። ባህር የተባለ ይህ ዓለም ሲሆን እመቤታችንም ከእርስዋ ስጋን ነስቶ ክርስቶስ ተብሎ ስሙ እንደ ዘይት ተዋህዶን ክርስቲያን ተብለን እንድንጣፍጥ የድኅነት መሳሪያ የመዓዛ መንፈሳዊ ምንጭ ናትና የባህር ሽቱ ትባላለች።

ሽቱ ያረፈበትን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ በልጇ ስም አምነው ተጠምቀው በእምነት የሚቀርብ ሁሉ ይጣፍጣልና ይላሉ አበው!

የባህር ኮከብ (Star of the seas) ማለት ነው። ባህር የተባለ ይህ ዓለም ነው፥ በባህር የሚበላም የማይበላም ደግሞ ክፉም ፍጥረት እንዳለ በዚህ ዓለምም አማኒም ከሓዲም መናፍቅም ጻድቅም ኃጥእም ይኖራልና፥ ዳግመኛም ባህር ከሁከት አይርቅም ይች ዓለምም ከሁከት አትርቅምና፥ በባህር ላይ ሲጓዙ በመርከብ ላይ ሆነው የንጋት ኮከብን አብነት አድርገው ከተጓዙ ካሰቡት ይደረሳል። ሰብአ ሰገልን ኮከብ እየመራ ቤተልሔም እንዳደረሳቸው ማለት ነው። እንዲሁም ሁሉ እመቤታችን በዚህ ዓለም የክህደት የኃጢአት  ምገድ እንዳያጠፋን የተረፍንባት መርከባችን ናት።

ብርህት (Illuminated) ማለት ነው። ብርሃኗ ከፀሐይ ይበልጣል፤ መለወጥ የሌለባት የድህነት በር ናት ውበቷም በፍፁም ክብርና ሞገስ የተሸለመ ነው፤ እውነት በእውነት የመና መሶብ ነች። ጽድልት መባሏ ነውርና ነቀፋ የሌለበት የእግዚአብሔር እናት በመሆኗ ነው።

አሐቲ ፍቅርት፦ ብቻውን የምትወደድ (Beloved One) ማለት ነው። ንጉስ ውበትሽን ወዷልና ተብሎ የተዘመረላት እግዚአብሔር መዓዛ ድንግልናዋን ወዶ ከእርሷ ሰው እስኪሆን ድረስ፥ ፍጥረትን ሁሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብቅሎ የሚመግብ ጌታ ጡቶቿን ጠብቶ እስከማደግ ድረስ ደርሶ ብቻዋን በእግዚአብሔር የተወደደች ናትና።

የባህር ምንጭ (Drop of the sea) ማለት ነው። እመቤታችን በዚህ ዓለም በሦስት ዋና ዋና የድኅነት ምንጭ ሆናለችና። የጥምቀት፥ የቁርባን፥ የቅዳሴ ናቸው። ይህም ማለት ከጎኑ የፈሰሰው ውሃ፥ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ከእርሷ ባህሪ የተገኘ ነውና ጌታ የተጠመቀውም ከእርሷ በነሳው ስጋ ነው የምንበላው ቅዱስ ስጋው የምንጠጣው ክቡር ደሙ ከእርሷ የነሳው ነውና የቁርባን ምንጭ ትባላለች።

ዳግመኛም ማርያም ማለት ልዕልት ማለት ነው።.... (ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)


(አሐቲ ድንግል በአባ ገብረኪዳን ግርማ ከገፅ 257-260 ላይ የተቀነጨበ)

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

22 Oct, 08:33


#አሐቲ_ድንግል!

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

22 Oct, 08:22


ቅምሻ ፪ - ከአሐቲ ድንግል

ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ስለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው ወይስ ንጽሕት ስለሆነች ነው እግዚአብሔር የመረጣት?

አንዳንዶች ስለ ድንግል መመረጥ ሲነገር ሲሰሙ ሲመርጣት ላትመረጥ ነውን? እርሱ ጠበቃት እንጂ እርስዋ ምን አደረገች ሲሉ ይሰማሉ። እግዚአብሔር ሰለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው የሚለው አደገኛ ክህደት ነው። ለምን ቢሉ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ነፃ ፈቃድ የሚንድ ነውና። ዳግመኛ እርሷ እግዚአብሔር ስለመረጣት ብቻ ከሆነ ንጽሕት የሆነችው እያንዳንዱ ሰው ንጹሕ የማይሆነው እግዚአብሔር ስላልመረጠው ነው ወደሚል የቅድመ ውሳኔ ክህደት የሚያመራ ጠማማ መንገድ ነው።

እንዲህ ከሆነ ደግሞ በዓለም ላይ ለሚሠሩ የርኩሰትና የአመፅ የበደል ውድቀቶች ሁሉ ተጠያቂው እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም ብሎ እግዚአብሔርን መሳደብ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የመረጠው ብቻ ንጹሕ ከሆነ ሁሉም የመንጻት ሥልጣን ካልተሰጠው በበደለኛነት ዘመናቸውን የፈፀሙ ሰዎች ተጠያቂ መሆን የለባቸውም፤ ከኃጢአት ለመንጻት ቢፈልጉ እንኳን አልተመረጡምና አይችሉም ማለት ነዋ! እንዲህ ከሆነ ሰዎች ሁሉ ሊድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ የሚወድ እግዚአብሔር (ጢሞ. ፪፥፫) ፈቃዱ ወዴት አለ? እርሱ የመረጣቸው ብቻ የሚነጹ ከሆነ ባልመረጣቸው ላይ ለምን ይፈርድባቸዋል? ፈታሒ በጽድቅነቱስ ወዴት አለ?

ነገር ግን ርቱዕ የሆነው የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የቀና የጸና አስተምህሮዋ እንዲህ አይደለም። እግዚአብሔር ሰዎችን ፍጻሜያቸውን አስቀድሞ አይቶ ይመርጣል እንጂ ወስኖ መርጦ የፈጠረው ሰው የለም። በወንጌል የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናት ማለቱም ሰው ለመዳን የሚያስችለው ለመምረጥ የሚያበቃው ኃይል በእጁ እንዳለ ሲያጠይቅ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው የተባለውም ለዚህ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የተሰጣቸው ስልጣን  የተባለው ለመዳንም ላለመዳንም የሰው ነፃ ፈቃድና ልጅነት እንደተሰጠ ሲያስረዳ ነው። እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መስዕዋቱ ተመለከተ የተባለውም አቤል የልቡን ቅንነት የመስዕዋቱን መበጀት ስሙርነት አይቶ ተመልክቶ አቤልን ተቀበለው እንጂ አቤል እንዲያ እንዲሆን አድርጎ ወሰኖ መርጦ አልፈጠረውም። በአንፃሩ ወደ ቃየልና መስዕዋቱ አልተመለከተም ማለት የቃየልን የልቡን ጥመት አየና የመስዕዋቱን አለመበጀት አይቶ አልተቀበለውም  ነገር ግን እግዚአብሔር ለክፋት ወስኖ አልፈጠረውም። እግዚአብሔር ሲኦል የሚገቡ ሰዎች እንዳሉ አውቆ ሲኦልን አዘጋጀ እንጂ ሲኦል በሚገቡ ሰዎች ላይ አስቀድሞ እንዲገቡ አድርጎ ወስኖ አልፈጠረም።

እናቱ ድንግል ማርያምን ከእናቷ ማሕፀን መርገም እንዳይኖርባት የጠበቃት እርሱ ነው ቅድመ ዓለም የአምላክ እናት እንድትሆን የመረጣትም እርሱ ነው። ነገር ግን ፍፃሜዋን በነፍስ በስጋ በአፍኣ ንጽሕት እንድትሆን አውቆ መረጣት እንጂ እርሱ ሰለወሰነ የጠበቃት የመረጣት አይደለችም። በዘመኗ ሁሉ በቅድስናዋ ተሸልማ እንደምትኖር አውቆ ከመርገም አነጻት፥ ኖሮባት አይደለም እንዳይኖርባት ጠበቃት እንጂ!

መንፈስ ቅዱስ ጠበቃት አነፃት መባሉም ፍፃሜዋን አይቶ መርገም እንዳይኖርባት ጠበቃት ማለት ነው እንጂ በዓለም ኃጢአት እንዳትሰራ ከለከላት ማለት አይደለም። ንጹህ ሆኖ መፈጠርማ አዳምም ተፈጥሮ ነበር በተፈጥሮ የተሰጠውን ንጹህ ጠባይ በቅድስና መጠቀም አልተቻለውም እንጂ እርሷ ግን ንጽሕናን ቅድስናን ደራርባ ይዛ ተገኝታለችና በዛው ድንግልናዋ ለአምላክ እናትነት በቃች። የሕይወት ፍሬን አፈራችበት እንዲመርጣት እግዚአብሔርን የሳበ በአምላክ ዘንድ ሞገስን የያዘ ንጽሕና ይዛ ተገኝታለችና እንድትመረጥ ሆና ተገኝታለች። ንጹሃንን ለክብር መምረጥማ ለፈጣሪ ድንቅ አይደለም ከእርስዋ ይልቅ ጠላቶቹን እኛን በደሙ ፈሳሽነት ይቅር ማለቱ አይደንቅምን?.......(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል ገፅ 272-277 ላይ የተቀነጨበ)


https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

20 Oct, 09:32


ቅምሻ - ፩

#አሐቲ_ድንግል(አንዲት ድንግል)

ድንግል ማርያም ለምን አንዲት ድንግል ትባላለች?

እመቤታችን ድንግል ማርያም በምድርም በሰማይም አቻ የማይገኝላት አንዲት ድንግል ናት። ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌልም የምትልቅ በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች በወንጌል የተፃፈች አንዲት ድንግል አለች። ይላል ቅዱስ ያሬድ።

ከዚህም ተነስቶ አንድ ሰው ተነስቶ በወንጌል ሌሎች ደናግል የሉምን? ስለምን በወንጌል የተጻፈች አንዲት ድንግል ትላለህ? ብሎ ቢጠይቀው ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌል የምትበልጥበት የድንግልና ዘውድ ያላት አንዲት ድንግል አልኩህ እንጂ ደናግላንማ ብዙ ደናግል አሉ ብሎ ይመልስለታል።

ቀጥሎም በመላዕክት ክንፍ የምትጋረድ በክብሩ መንበር በፊት ምህረት የምትለምን በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊል የተቀዳጀች አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል አለች።

አሁንም ቅዱስ ያሬድን ስለምን አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል ትላለህ አርሱ የመረጣቸው ብዙ ደናግላን የሉምን? ብሎ የሚጠይቀው ቢኖር፥ አማኑኤል ሥጋን ይለብስ ዘንድ የመረጣት፤ ከእርስዋም ሥጋን ለብሶ አማኑኤል የተባለባት፥ በመላእክት ክንፍ የምትጋረድ፥ እግዚአብሔር በክብሩ ዙፋን በፊቱ ለመቆም የመረጣት፥ በእናትነት የሰለጠነ የባለሟልነት ዘውድን የተቀዳጀች አንዲት ድንግል አልኩ እንጂ እርሱ የመረጣቸው ደናግላንማ ስንቱ! ብሎ ይመልስለታል።

ደግሞም ፀጉሯ እንደ ሐር ፈትል ያማረ፥ የአንደበቷ መዓዛ እንደ እንኮይ የጣፈጠ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች የልዑል ንጽሕት አዳራሽ የሆነች አንዲት ድንግል አለች።

የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆኑ ሌሎች ደናግላን የሉምን ስለምን ለይቶ እርሷን አንዲት ድንግል አለ ቢሉ? ከእርሷ ስጋ ይነሳ ዘንድ እግዚአብሔርን በማህፀኗ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የወሰነች እውነተኛ የእርሱ ማደሪያ ሌላ ድንግል ከማርያም በቀር ወዴት አለ ይለዋል! ብቻዋን የእግዚአብሔር መቅደስ ለመሆን የበቃች እንደሆነች ሁሉ ከቅዱሳን ሁሉ ተለይታ በእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው እንደ እንኮይ የጣፈጠ አማላጅነት ያላት አንዲት ድንግል እርሷ ብቻ ናት! ስለዚህ እንደ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችን ብቻዋን አንዲት ድንግል የተሰኘችበት  ወላዲተ አምላክነቷ፤ ንፅሕናዋ ፤ማኅደረ መለኮትነቷ አማላጅነቷ እና ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ ናቸው ማለት ነው።

፩.በድንጋሌ ሥጋ ዘለዓለማዊ
በተፈትሆ የማይመረመር ድንግልናዋ ነው። ይህም ሥስት የማይመረመሩ ግብራት አሉት። ድንግል እንደሆነች መፀነስ፥ ድንግል ሆና ሳለ መውለዷ፥ ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና መኖሯ ናቸው። እነዚህ በህገ ተፈጥሮ የማይታሰቡ ረቂቅ ግብራት ናቸው። ሰው ድንግል ሆኖ ያለ ወንድ ዘር መፀነስ አይቻለውም፥ በድንግልና እያለ የፀነሰ መሆን አይችልም፥ ሰው በድንግልና መውለድ አይቻለውም፥ ከወለደ በኋላ ደግሞ ድንግል መሆን እንዴት ይችላል? ድንግል የሆነች ሌላ ሰው እናት አይደለችም፥ እናትም ከሆነች ድንግል አይደለችም። ይህ ለአንዲቱ ለድንግል ማርያም ብቻ የተቻለ ነው።

፪. ድንግል በቃሏ - በቃሏም ድንግል
የቃል ድንግልና በሦስት ወገን ነው። እኒህም ክፉ አለመናገር፥ ምስጋና አለመብላትና በጎውን መናገር ናቸው። ሰው በንግግሩ ብዙ ኃጢአቶች ይሰራል። ሐሜት፣ ማጉረምረም፥ ቁጣ፥ ብስጭት፥ መዋሸት፥ መርገም፥ መሳደብ፥ ዋዛ ፈዛዛ፥ ያለጊዜው መሳቅ መሳለቅ፥ ዘፈን፥ ተውኔት፥ ድንፋታ፥ መንፈግ ነገር ማመላለስ፥ ቃል መለዋወጥ፥ አደራ መብላት፥ በሀሰት መማል፥ ሰጥቶ መንሳት፥ ክህደት፥ ማታለል፥ ማስነወር፥ አድልዎ፥ መጠራጠር፥ ማሽሟጠጥ፥ አሽሙር፥ ኃጢአትን ማመስገንና ማስፈራራት እነዚህን የመሳሰሉ ሁሉ ናቸው።

እመቤታችን በማንም ክፋትን ተናግራ አታውቅም አንደበቷ የለዘበ የለመለመ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና የማይታሰብ ዕፁብ ድንቅ የመውለዷን ዜና ሲነግራትም እኔ ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል ብላ ነገሩን ወደ መረዳት ተሻገረች እንጂ ይህ የማይሆን ነገር ነው ብላ ወደ መጠራጠር ወይም መልአኩን ወደ መንቀፍ አልቃጣችም። የአንደበት ድንግልና ማለት የማይቻል ጭንቅ ፍጹም ከተፈጥሮ ህግ በላይ የሆነን ነገር በመስማት ጊዜም ቢሆን ያለመጠራጠር በሃይማኖት መጠየቅና ፍፃሜውን በትዕግሥት መጠበቅ ነው።

መከራ በደረሰ ጊዜ ብዙ የቃል ድንግልና ያላቸው ቅዱሳን ችግሩን የፈጠሩትን ከመንቀፍ ይልቅ በእኔ ችግር የተከሰተ ነው ብለው ራሳቸውን ይወቅሳሉ። ነገር ግን እነርሱ ቀድሞ መበደላቸውን እያስታወሱ ነው። የድንግል ማርያም ግን የሚደንቀው ምንም ነውር የሌለባት ስትሆን በቃሏ ድንግል ስለሆነች እኔ ኃጢተኛ ነኝ ትል ነበር። በብስራተ መልአክ አምላክን የፀነስኩ እናት ነኝ ስትል ገናንነቷን አትናገርም። መልካም በመናገር ንግግሯ ሁሉ ሃይማኖት ተስፋና ፍቅር ናቸው።

፫. ድንግል በኅሊናሃ - በኅሊና ድንግልና የፀናች አንዲት ድንግል፦
ሰው በተግባር ቢነጻ በንግግር አይነጻም፥ በንግግር ቢነጻ በኅሊናው መንፃት አይቻለውም። ጻድቃንም ቢሆኑ ወድቀው ተነስተው በተጋድሎ ለክብር ይበቃሉ እንጂ ከጅማሬ እስከ ፍፃሜው አለመበደል ከቶ የተቻለው የለም። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በኅሊናዋ እንኳን ያልበደለች ፍጽምት  አንዲት ድንግል ነች። ጽድቅን ሁሉ የተሞላች ድንግል ማርያም ንጽሕት በመሆኗ በኅሊናዋን ድንግልና፤ የቃሏን ድንግልና፤ የስጋዋን  ድንግልና በአንድ ላይ "እንዘ ኢይአምር ብእሴ" "ወንድ ስለማላውቅ" በሚል የንፅህና ሸማ ጠቅልላ ተናገረች (ሉቃ.፩፥፴፬) በዚህ ድንግልናዋም አምላክን ለመፀነስ በቃች።.....(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል መጽሐፍ ገፅ 241-251 የተቀነጨበ)


https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

20 Oct, 09:27


#አሐቲ_ድንግል

#ይህን_ድንቅ_መጽሐፍ በተገኘበት አድናችሁ ትገዙ ዘንድ እጋብዛችኋለሁ!

#ለጥቆማ መጽሐፉን
5ኪሎ ቅድስት ማርያም አሐዱ ባንክ ፊት ለፊት
ባኮስ መጻሕፍት መደብር - Bakos Book Store ያገኙታል።

    
#ለበለጠ_መረጃ
          👇👇👇
☎️ 
0920888887

#መጽሐፉ እጄ ላይ ባይገባም እጃቸው ከገባ የቀነጫጨቡትን ለቅምሻ #አካፍላችኋለሁ...

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

15 Oct, 09:52


#ጥቅምት_

#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)

ጥቅምት አምስት በዚህች ቀን የታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ። ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ። አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።

ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው፤ ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።

የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።

ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።

ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ። "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ።" እንዲል።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(ስንክሳር ዘተዋሕዶ - ፌስቡክ ገጽ)

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

15 Oct, 09:52


🌹💚🌹💛🌹
#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

05 Oct, 10:31


#ወርኃ_ጽጌ
"ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16)

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

05 Oct, 10:26


#ወርኃ_ጽጌ
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልላክነት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ፡፡

በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡


https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

03 Oct, 14:06


#ልጄ_ሆይ
ማናቸውንም ነገር በምትፈፅምበት ጊዜ ሥራህን በፀሎት ጀምር። የምትሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በትምህርተ መስቀል ባርካቸው።

በምትበላም፣ በምትጠጣም ጊዜ፣ በምትተኛም፣ በምትነቃም ጊዜ፣ በቤት ውስጥም ሳለህ ይሁን በጎዳና፣ ማማተብን አትዘንጋ። የጌታህን ስቅለት አስታውሶ ከክፋት የሚጠብቅህ ይህን የመሰለ ጠባቂ ከቶ አታገኝም።

እርሱ ለምታደርጋቸው ድርጊቶችህ ሁሉ እንደ ግንብ ነው (ማስተዋልን ይሰጥኻል)። ማማተብን በስርዓት ይፈፅሙት ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሁሌም በፊታቸው ይስሉ ዘንድ ለልጆችህ በጥንቃቄ አስተምራቸው።

#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

01 Oct, 06:22


#አማላጂቱ_ሆይ፦ በጭንቅ፣ በኃጢአትና በበደል ውስጥ ያለን እኛ ምልጃሽን እንፈልጋለንና ይቅር ባዩ ተወዳጅ ልጅሽ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙን፣ ይቅርታውንና ምህረቱን ይልክልን ዘንድ ለምኝልን።

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

27 Sep, 04:30


#ንግሥት_እሌኒን_እናወድሳት_ዘንድ_ይገባል፡፡
ክብር የሚገባውን የአምላካችንን የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኝ እንደሆነ ብላ በእምነት ለመፈለግ ተግታለችና፡፡

የጌታችን መስቀል ቅዱስ ስጋው የተቆረሰበት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት ከሁሉ የተለየ ከሁሉ የተቀደሰ ሁሉንም የሚቀድስ እንደሆነ አስቀድማ ተገንዝባለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

ንግሥትነቷን በዓለማዊ ቅምጥልናና ምቾት ታሳልፈው ዘንድ አልወደደችም፤ ይልቁንስ የተወደደውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ በመንፈስ ብርቱ ሆና በስጋ ደከማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

እጅግ የከበረውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ ስትጀምር በራሷ መታመን አልታበየችም ይልቁንስ ሁሉን ስለክርስቶስ ትቶ የወጣ ባህታዊ ኪራኮስን ታማክር ዘንድ ወዳለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

በተዋህዶ የከበረ የአብ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ይዞ እንዳላስቀረው ሞትንም ድል አድርጎ እንደተነሳ ሁሉ ክቡር መስቀሉም ተቀብሮ ለዘላለም እንደማይኖርና ከተቀበረበትም እንደሚወጣ አምናለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

ከጌታችን መስቀል ጋር የተቀበሩት መስቀሎች ብዙ ናቸው የጌታየን እንዴት እለየዋለሁ? ብላ ሳትጨነቅ የክርስቶስ መስቀል ክብሩን ራሱ እንደሚገልፅ በልቧ ተማምና እስክታገኝው ደክማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

26 Sep, 16:14


#እንኳን_ለብርሃነ_መስቀሉ_በሰላም_አደረሰን_አደረሳችሁ!!

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

25 Sep, 17:57


#መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው።
#መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው።
#መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው።
#መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው።

መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው።

መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው።

መስቀል ማኅተመ ሥላሴ የሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው።

መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው።

መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው።
መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው።

መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው።
መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው።

መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው።

መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው።

(ውዳሴ መስቀል - በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

10 Sep, 04:28



#አዲሱ_ዓመት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

#የምወዳችሁ_ልጆቼ! እኛ ግን ይህን ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ በዓለም ላይ ከኀጢአት በቀር ክፉ ነገር እንደሌለ ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ ከምግባር ከትሩፋት በቀርም መልካም ነገር እንደሌለ ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ በዚህም ዘወትር እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተን ልንኖር እንዲገባን ማወቅ መረዳት ይገባናል፡፡
መጠጥ ደስታን አያመጣም፤ ደስታን የሚያመጣው ጸሎት ነው፡፡ ደስታን የምናገነኘው ቃለ እግዚአብሔርን ከመስማት እንጂ ከስካር አይደለም፡፡ ስካር የነፍስ መታወክን ያመጣል፤ ቃሉን መስማት ግን ተመስጦን ያመጣል፡፡ ስካር ሁካታን ያመጣል፤ ቃሉን መስማት ግን ሁካታን ያርቃል፡፡ ስካር ዓይነ ልቡና እንዲጨልም ያደርጋል፤ ቃለ እግዚአብሔር ግን የጨለመው ዓይነ ልቡናችን ብሩህ እንዲኾን ያደርጋል፡፡ ስካር የኀጢአት ጓዝ ይዞ ይመጣል፤ ቃለ እግዚአብሔር ግን አዲስ የሚመጡትን ብቻ ሳይኾን የነበሩትንም ያስወግዳል፡፡

ልጆቼ! የዚህን ዓለም ደስታ ንቆ ሰማያዊ ደስታን እንደ መሻት ያለ ጥበብ ምንም የለም ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡ ይህን ገንዘብ የምናደርግ ከኾነ፣ ለሰማያዊ ሕይታችን ቅድሚያን የምንሰጥ ከኾነ የዚህ ዓለም ዝባዝንኬ ቢቀርም አይከፋንም፡፡ አንድ ሰው ባለጸጋ ስለኾነ ቅናት አይይዘንም፡፡ ምንም ምድራዊ ሀብት ባይኖረንም ድኾች እንደኾንን አናስብም፡፡ ባለ ጸጋውን ክርስቶስ የያዘ ሰውስ እንዴት ድኻ ይባላል? በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይኾን በየዕለቱ በዓል ማድረግ ማለትም ይኸው ነው፡፡

#እግዚአብሔር_የሚወዳችሁ_አንድም_እግዚአብሔርን1የምትወዱት_ሆይ! አንድ ክርስቲያን በዓልን ሲያከብር ሳምንትን ወይም ወርን ወይም ዓመትን ጠብቆ መኾን የለበትም፡፡ ከክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ጋር እንደሚስማማ አድርጐ ዕለት ዕለት በዓል ሊያደርግ ይገቧል እንጂ፡፡ ከክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ጋር የሚስማማ በዓል ማለትስ ምን ማለት ነው? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ምን እንደሚለን አብረን እናድምጠው፡- “በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም” (1ኛ ቆሮ.5፡8)፡፡ ንጽሐ ልቡናን ገንዘብ ያደረገ ሰው ዕለት ዕለት በዓልን ያከብራል፡፡ ተስፋ መንግሥተ ሰማያት የተጠበቀለት ነው፡፡ ከሰማያዊው ማዕድና መጠጥ ተካፍሎ ሐሴት ያደርጋል፡፡ በዚህ ምድር ላይ የሚደረጉ ጊዜያዊ ክንውኖች ስለቀረበት የኾነ ነገር እንደቀረበት አያስብም፤ እርሱ ያገኘው ከዚህ በእጅጉ የሚልቅ ነውና፡፡ ነፍሱን ከሚያቆሽሹ ገቢረ ኀጢአቶች ራሱን ይጠብቃል፡፡

በገቢረ ኀጢአት ተሰማርተን ሳለ ሺሕ ጊዜ በዓላትን ብናከብር ግን እንዳከበርን ልንቈጥረው አይገባንም፡፡ ያከበርነው የበዓል ቀን (በዓል ማለት ደስታ ማለት ነው) ሳይኾን የኀዘን ቀን ነውና፡፡ ነፍሴ በኀጢአት ቀንበር ተይዛ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሳለች የደስታን ቀን ባከብር ለእኔ ምን ጥቅም ያመጣልኛል?.....ይቀጥላል

#ሰማዕትነት_አያምለጣችሁ መጽሐፍ ገጽ 13-19
#ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ_የተረጎመው

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

09 Sep, 19:10



#አዲሱ_ዓመት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

#ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡

የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡ በትግሃ ሌሊት፣ በቀዊም፣ በጾም በጸሎት እንድንበረታ ስንቅ ይኾነናል፡፡ በስካር፣ በዘፈን፣ በኀዘን የምንጀምረው ከኾነ ግን ዓመቱ ሙሉ እንዲህ የተጐሳቈለ ዓመትን እናሳልፋለን፡፡ ሕይወታችንን በከንቱ እንገፋለን፡፡ ዲያብሎስም ይህን ጥንቅቅ አድረጐ ስለሚያውቅ ዓመቱን በገቢረ ኀጢአት እንድንጀምረው እየቀሰቀሰ ነው፡፡ ፈቃዳችንን አጥፍቶ፣ ዓይነ ልቡናችንን አሳውሮ በዘፈን፣ በስካር፣ በዋይታ እንድንጀምረው በተለያየ መንገድ እየለፈፈ ነው፡፡

ሰነፍ ሰው “ቀኑ ክፉ ወይም መልካም የሚኾነው በእኔ ምክንያት አይደለም” ብሎ ያምናል፡፡ እንዲህ በማመኑም ክፉ ነው ብሎ በሚያስበው ቀን ገቢረ ጽድቅ መሥራት እንደሚቻል አያስብም። ቢያደርግም ትርጕም እንደሌለው አድርጐ ይቈጥሯል፡፡ የጽድቅ ሥራ ለመሥራት በተመቻቸለት ቀንም ልል ዘሊል ከመኾኑ የተነሣ ምግባር ትሩፋት ለመሥራት አይሽቀዳደምም፡፡ ስንፍናው ምን ዓይነት ጉዳት እንደሚያመጣበት አይረዳም፡፡ ድኅነቱን ሳይፈጽም ዕድሜውን ኹሉ በከንቱ ይገፋል፡፡ እንዲህ ያለ የሥጋም የነፍስም ጕዳት እንደሚያገኘው ዲያብሎስ ዓይነ ልቡናውን ስለሚያሳውርበት ከአጋንንት ወጥመድ ለመሸሽ ዓቅምን ያጣል፡፡

ዲያብሎስም ዕለት ዕለት ይህን እንዳንገነዘብ በተለያየ ማጥመጃ መንገዶች እኛን ለመጣል ይሯሯጣል፡፡ አንዱ መንገድም ስለ ክርስትና ሕይወታችን ግድ እንዳይኖረን ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ክርስቲያናዊ ተፈጥሮአችንን ያሳጣናል፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ በገቢር እንድንሰድብ ያደርገናል፡፡ ነፍሳችንን በቆሸሸ ስፍራ ተወሽቃ እንድትቀር ያደርጋታል፡፡.....ይቀጥላል

#ሰማዕትነት_አያምለጣችሁ መጽሐፍ ገጽ 13-19  በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

06 Sep, 09:57


#የጳጉሜ_ወር_አበይት_በዓላት፩-፮

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

31 Aug, 09:34


#ሰውን_የሚጥለው_መመካቱ_ነው

ወንድሜ ሆይ በሥራህ ሁሉ የታመንህ ሁን አገልጋይ ባልንጅሮችህን ውደዳቸው። ንጹሑን አረጋዊ መቼም መች አክብረው።

ወንድሜ ሆይ በታላላቆች መሃል አትቀመጥ። ተቀመጥ እስኪሉህ ድረስ ቁም እንጅ በሽማግሌዎች መካከል አትቀመጥ፤ በዝቀተኛው ማዕርግ ተቀመጥ እንጅ።

ወንድሜ ሆይ ቁጡ ወይም አንጎራጓሪ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ሐኬተኛ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ምንም ተግባር ለመፈጸም ወዲያና ወዲህ አትናወጽ። እንዳትዋረድ በሊቅ በአዋቂ መሃል አትናገር።

ልጄ ሆይ በጽድቅህ አትመካ፤ ራስህን አታመስግን፤ ሰይጣን ትምክሕትን እንዳያመጣብህ ራስህን በፈቃድህ አዋርድ እንጅ። በትዕቢትና ትምክሕት ሰዶምና ገሞራ ወደቁ። ከእግዚአብሔር መንገድም ተሰናከሉ። ትምክሕተኛውን መነኩሴ ፈተና ያገኘዋል፤ መንፈስ ቅዱስም ይለየዋል፤ የዲያብሎስ መንፈስም ያድርበታል። በሥራችሁ ሁሉ አትመኩ፤ ሁሉም ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን ይሠራል እንጅ ከራሱ የሆነ ምንም የለምና። ነቢይ የተናገረውን አልሰማችሁምን? ፈጽማችሁ አትመኩ ታላላቅ ነገርንም አትናገሩ፤ ክፉ ነገርም ከአንደበታችሁ አይውጣ።

#መጽሐፈ_ወግሪስ - ገጽ 84-85
#በአባ_ገብረ_ኪዳን

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

30 Aug, 10:30


https://t.me/kdusan_melaekt
      ❍ㅤ         ⎙ㅤ       ⌲
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

22 Aug, 14:02


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹#ዐረገች_በስብሐት 🌹
🌹#ዐረገች_በዕልልታ🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

22 Aug, 14:00


"#የህይወት_እናት_ድንግል_ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል፤ የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለአለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና፤ ሆኖም እመቤቴ ሆይ፦ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም እንደ ዮሃንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ የዮሃንስ ፀጋ ግን የለኝም።

እናቴ ሆይ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳዕ በፀሎት ሃይል የግያዝን አይን እንዳበራ አንቺም አይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ሃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡

ድንግል ሆይ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም በልጅሽ መሰረትነት የታነፅኩኝ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"


https://t.me/kdusan_melaekt
       ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡
  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   

1,715

subscribers

279

photos

78

videos