Neros' School Key To Success @nerosschool Channel on Telegram

Neros' School Key To Success

@nerosschool


ሰላም የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች
ይህ ቻናል ስለ ኔሮስ ስኩል መረጃዎች የሚለቀቅበት ነው

Neros' School Key To Success (Amharic)

ኔሮስን የትምህርት መልዕክትን እና የመረጃዎችን ስኩል መተናመኛ ቤተሰቦ ለመስራት አንድ ተከታታይ እንደገና ያቀዳጅሱና የሚሸጥ ነው። ለምሳሌ መሳሪያዎችን መጠቀምና የሚስክርና መፈጸም እና በመተንፈሳሪያ ምክር እንደገና የቡድኖችን መጠቀም እንዲህ ለአስቸነፈል ይጠቅማል ። ማስታወቂያዎች በሕግ ከተገናኘው አና ትናንት ጋር እንዲከበሩ ከታች ወደ ባህልም ጥቃት ይዟችሁ ከተማ እንዲቆያ ከታች ወደ አካባቢ ምንጭ ትኩረትም ይጠቅማል ።

Neros' School Key To Success

30 Dec, 08:45


ውድ የኔሮስ ቤተሰቦች 👨‍👩‍👧‍👦
ይህ ሳምንት የ Pre-Kg, Kg አና Preparatory ተማሪዎች ፈተና ሳምንት በመሆኑ፤ ልጅዎትን በቤት ውስጥ 📚 በማስጠናት የበኩልዎን ሀላፊነት እንዲወጡ እናስታውሳለን።

Awragodana and Bole campus

የፈተና ፕሮግራም ከላይ በምስል 📷 አያይዘናል።

🔑 ኔሮስ ስኩል - የልጅዎ የስኬት ቁልፍ 🚀

Neros' School Key To Success

30 Dec, 06:19


ውድ የኔሮስ ቤተሰቦች 👨‍👩‍👧‍👦
ይህ ሳምንት ከ 1-5 እና 7 ኛ ክፍል ተማሪዎች የ Mid-Exam እንደዚሁም ለ 6ተኛ እና 8ተኛ ክፍል ተማሪዎች የ Model ፈተና ሳምንት በመሆኑ፤ ልጅዎትን በቤት ውስጥ 📚 በማስጠናት የበኩልዎን ሀላፊነት እንዲወጡ እናስታውሳለን።

College campus

የፈተና ፕሮግራም ከላይ በምስል 📷 አያይዘናል።

🔑 ኔሮስ ስኩል - የልጅዎ የስኬት ቁልፍ 🚀

Neros' School Key To Success

28 Dec, 06:10


ተጨማሪ ምስሎች ከ አውራጎዳና ካምፓስ።

creative works

🔑 ኔሮስ ስኩል - የልጅዎ የስኬት ቁልፍ 🚀

Neros' School Key To Success

27 Dec, 03:41


🖍 ትልቅ ህልም የሰነቁ ፤ ትንንሽ እጆች 🖍

🎨 በትላንቶናው እለት የ Pre-Kg, Kg እና preparatory ኮከቦቻችን በ creative work  ላይ ሲሳተፉ ውለዋል።

     Bole campus

🔑 ኔሮስ ስኩል - የልጅዎ የስኬት ቁልፍ 🚀

Neros' School Key To Success

12 Nov, 08:21


ጠንካራ አእምሮን ለመገንባት የሚጠቅሙ ምክሮች

ሁሉም ሰው አእምሮውን ጠንካራ ማድረግ ይችላል! የአእምሮን ደህንነት እና ጽናትን ለማሳደግ የሚረዱ ተግባራዊ መንገዶች፦

🧠 አሉታዊ ሀሳቦችን መሞገት

አሉታዊ ሀሳቦች በጭንቅላታችን ሲመጡ ፤ ለራሳችን: “ይሄ ሀሳብ ይጠቅማል?” የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ነው። ሀሳቡ የማይጠቅም ሆኖ ካገኘነው ወደተሻለ ሀሳብ ልንዞር ያስፈልጋል። በጊዜ ሂደት እነዚህ አይነት ትንንሽ ልምዶች አስተሳሰባችንን ላይ አወንታዊ ተጽዕኖ ያሳድራሉ።

🌟 በራስ መተማመንን መገንባት

በራሳችን ልንተማመን ይገባናል! ልዩ የሚያደርጉን ጠንካራ ጎኖች እና የከዚህ ቀደም ውጤቶችን እውቅና መስጠት በራስ መተማመናችን እንዲጨምር ያደርጋል።

🌱 ጽናትን ማዳበር

ሕይወት በውጣውረድ የተሞላ ነው። አሁናዊ የሆኑና መቆጣጠር የምንችላቸው ነገሮች ላይ አትኩሮት በመስጠት፤ያለፈው ውድቀታችንን ደግሞ እንደ ትምህርት ምንጭነት ልንጠቀመው ይገባል። እያንዳንዱ ውጣውረድ የበለጠ ጠንካራ እንድንሆን ይረዳናል። ይህም ጽናትን ያስተምራል።

🤗 ዙሪያችንን በአጋዥ እና አበረታች ሰዎች መክበብ

ምክር እና እገዛ ስንፈልግ እነዚህን ሰዎች እርዳታ መጠየቅ እንድንችል እና የተሻለ ምክርን እንድናገኝ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ጥሩ መሆን ወሳኝነት አለው።

ጠንካራ አእምሮን መገንባት ጊዜ እና ትግስትን ይጠይቃል። እያንዳንዷ ትንሽ እርምጃ ጤናማ እና የበለጠ ጽኑ አእምሮ እንድንገነባ አስተዋጽኦ ታደርጋለች።

ምንጭ፦ www.quora.com
with some modification.

🔑 ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ 🚀

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ምስል - 1

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ምስል - 2

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ምስል - 3

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ምስል - 4

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ምስል - 5

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ምስል - 6

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ምስል - 7

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ምስል - 8

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ምስል - 9

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


🎉 አስደሳች ዜና፤ የትምህርት ቤታችን ድህረ-ገጽ Live ሆነ! 🎉

📱በስልክዎ እንዴት መጠቀም ይችላሉ?📱

🔍 Landing page (Home page)
✔️browser (Chrome) neros.et ብለው search ሲያረጉ መጀመሪያ የሚያገኙት Home page ነው።

በ home page ላይ የሚያገኟቸው ነገሮች:
☑️🎯 የኔሮስ ስኩል Mission, Vision እና Core Values
☑️🎶 የኔሮስ ስኩል መዝሙር
☑️🎶 ላየን እና ኢግል መዝሙር
☑️📸 የፎቶ ጋለሪ
☑️💬 ምስክርነቶች (Testimonials)

👤 እንዴት login ማድረግ ይችላሉ?

🔘 ምስል - 1 ላይ እንደሚመለከቱት፣ በቀኝ ጠርዝ ላይ ያለውን hamburger icon (≡) ወይም Menu ምልክት ይጫኑ።
🔘ይህም ከግራ በኩል የ Menu ዝርዝር ያመጣሎታል ይህም በ ምስል - 2 ላይ ተመላክቷል።

🔘ምስል - 2 ላይ ካሉት የ Menu ዝርዝሮች "LOGIN"የሚለውን ይጫኑ። ከተጫኑ በኋላ ወደ ሌላ ገጽ ይወሰዳሉ። (ምስል - 3)

🔘ምስል - 3 ላይ በ ቴሌግራም የላክንሎትን LogIn Id እና የይለፍ ቃል አስገብተው Log In የሚለውን ቁልፍ (button) ይጫኑ። አሁን ወደ እርሶ Dashboard ገብተዋል። (ምስል - 4)

እንደገቡ Dashboard ላይ፦

🔘ምስል - 4 ላይ ወደታች scroll አድርገው የኔሮስ ስኩል Event Calendar ማየት ይችላሉ።
🔘ምስል - 4 ከቀኝ በኩል ያለውን hamburger (Menu) ≡ ቁልፍ ሲጫኑ ከግራ በኩል የ ማውጫ ዝርዝር ይመጣሎታል። (ምስል - 5)

ምስል - 5 ላይ ያሉትን ዝርዝሮች እንመልከት፦

🔷 📋 Dashboard - ልክ Log In እንዳደረጉ የሚያገኙት የኔሮስ ስኩል Event Calendar እሚያሳይ ገፅ ነው።
🔷 📅 School Calendar - ከዚህ በታች 3 አማራጮች አሉ (ምስል - 6)
🔸School Event Calendar - (ይሄ Dashboard ላይ ያለው ነው)
🔸Moral Values - የኔሮስ ስኩል የየወሩ እሴት የሚታይበት ገፅ
🔸 General Calendar - ትምህርት ቤቱ ዋና ዋና ቀናትን የሚያሳይ
🔷 🔧 Preferences - በዚህ Testimonials መጻፍ ይችላሉ። ምስክርነቶም home page ላይ ይታያል።(ምስል - 7)
🔷 👪 My Children - ይህን በመጫን የልጆን ስም ፣ ዝርዝር መረጃን እና Marksheet ማየት ይችላሉ። (ለአሁን የተሞላ markshert የለም።) (ምስል - 8 እና ምስል - 9)
🔷 ⚙️ My Account - የ profile መረጃዎችን ማሻሻል። (ምሳሌ፦ ምስል መቀየር ወይም password መቀየር)

🔑 ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ 🚀

Neros' School Key To Success

07 Nov, 17:06


ማሳሰቢያ:- ይሄ ሲስተም ተግባራዊ እየሆነ ያለው ለ ኔሮስ ስኩል college campus (ከ 1 - 8 ኛ ክፍል ነው)። በመሆኑም እስካሁን ልጆቻችሁ ከ 1 - 8 የሆኑ ወላጆች ከዚህ በታች ያሉትን ዝርዝር መረጃዎች ያላካችሁልን በ @Nerossch እንዲልኩልን በድጋሜ እናሳስባለን።

1. የልጅዎን ሙሉ ስም
2. የክፍል ደረጃ እና section
3. የልጅዎ ጉርድ photograph
4. ልጅዎ ለመጀመሪያ ጊዜ ኔሮስ ስኩልን የተቀላቀለበት ዓመተ ምህረት።
5.የልጅዎ ልደት ቀን (E.C)
6.የወላጅ ሙሉስም (እናት ፣ አባት ወይም ጠባቂ -የአንዳቸውን )
7.የወላጅ ጉርድ photograph

Neros' School Key To Success

06 Nov, 11:22


Have you visited this page yet?

Neros' School Key To Success

06 Nov, 11:21


https://www.neros.et/

Neros' School Key To Success

05 Nov, 17:02


📅📚 የ 2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አጋማሽ ፈተና መርሐግብር።

Get ready! 💪

1st Quarter Mid Exam Schedule 2017.

🔑 ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ 🚀

Neros' School Key To Success

31 Oct, 13:59


🖍 ትንሽ እጆች፤ትልቅ ህልም 🖍

🎨 ዛሬ የ pre-KG ኮከቦቻችን በ creative work  ላይ በመሳተፍ እያንዳንዷን ደቂቃ በደስታ ውስጥ አሳልፈዋል።

🐰🌳 በእነዚህ ጨዋታዊ የፈጠራ ስራዎች ውስጥ ሲማሩና ሲያድጉ ማየት ያስደስታል። በትንንሽ አርቲስቶቻችን ኮርተናል። 💫

🔑 ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ 🚀

Neros' School Key To Success

30 Oct, 08:38


😱 ሁላችንም ስንጠብቀው የነበረው፤ ላየን Vs ኢግል! 🦁🦅

📅 ትላንት ተካሄደ!

ማን ያሸነፈ ይመስሎታል?

🔊 የላየኖችን የህብረት ጩኸት ፤ የኢግሎችንም የአንድነት ድጋፍ 👏
ለተመለከተ "ባያልቅ" ያሰኛል.

👇 ከታች ያለውን ይጫኑ

🎯 የትላንቱ ፍጥጫ ፤ ላየኖችን በደስታ 😁 ኢግሎችን "በቀጣይ ያገናኘን" በሚያሰኝ እልህ ተቋጭቷል.

🏆 11 ለ 10 ነጥብ በማምጣት በጠባብ ነጥብ
ላየን አሸናፊ ሆኗል! 🎉


🎉 Congrats Team Lions! 🎉

🔑 ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ 🚀

Neros' School Key To Success

28 Oct, 12:31


ኢግል ወይስ ላየን?

እነሆ 1 ቀን ቀረው!

ኢግል እና የላየን ፍጥጫ!

ልጅዎ የየት ቡድን አባል ይሆን/ትሆን?👀

በነገው እለት እነኚህ መሪዎች ይፋለማሉ።

ከኢግል ጎን የሆናችሁ "Eagle" ከላየን ደግሞ "Lion" በማለት  comment ላይ ድጋፋችሁን ግለፁ።

ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ !

Neros' School Key To Success

25 Oct, 14:36


🌟Lion🦁 Vs Eagle🦅🌟

በኔሮስ ስኩል፤ በቡድን ሥራ የሚገኘው ሃይል እና አወንታዊ ተጽዕኖ ተማሪዎችን እንደሚያበረታታ እናምናለን። ለዚህም ነው ተማሪዎቻችንን በ አንበሳ እና በ ንስር በተወከሉ ቡድኖች እንዲሳተፉ በማድረግ ትምህርታዊ ውድድሮችን እንዲወዳደሩ እምናረገው።

አንበሳ በዱር ከሚገኙ እንሰሳት ውስጥ የበላይ ነው። የጥንካሬ እና የመሪነት ምሳሌ ተደርጎ ይወሰዳል፤የጫካ ንጉስም ይባላል። በአንጻሩ፥ ንስር ከሰማይ አዕዋፋት መካከል የሚልቅ ነው። ከዝናብ ለመሸሸግ ወደጎጆው አይገባም፤ የዝናብ ምንጩ ከሆነው ደመና በላይ ይበራል እንጂ።

ተማሪዎችን እነዚህ ሁለት በየፊናቸው ሃያላን በሆኑ እንስሳት ስም በተወከሉ ቡድኖች ውስጥ በመግባት፤ የእነዚህ እንሰሳትን ባህሪያት የሚያንፀባርቁ ተግባራትን በውድድር መልክ ያካሂዳሉ።

ኔሮስ፥በፊታችን ማክሰኞ የአመቱ የመጀመሪያ የሆነውን Lion Vs Eagle ውድድር ያካሂዳል። ተማሪዎች ለግማሽ ቀን ከተማሩ በኋላ፤ተሰጧቸውን በሚያሳዩበት በዚህ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ።

ውድድሩ እሚያካትታቸው፦

🔷ትምህርታዊ ጥያቄ መልስ ውድድሮች
የተማሩትን እውቀታቸውን የሚያሳዩበት ውድድር።

🔷ስፖርታዊ ውድድሮች
ላየን እና ኤግል በተለያዩ የአቶሌቲክስ ውድድሮች ይፋለማሉ። 

በ 2015 ዓ.ም የ ዓመቱ አጠቃላይ ውድድር ድምር አሸናፊው ቡድን Eagle ሲሆን በ2016 ዓ.ም ግን ዋንጫው ወደ Lion ቡድን ዞሯል። የዘንድሮ ዓመት ትንቅንቅም የፊታችን ማክሰኞ ይጀመራል።

በዕለቱ የ አንበሳን የመሪነት መንፈስ፤የ ንስርንም የእይታ ሃይል በተማሪዎቻችን ተሰጥኦ መስታወትነት ምስክር እንሆናልን።

ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ

Neros' School Key To Success

23 Oct, 08:10


የልጆች የአእምሮ እድገት  🌱🧠 

በአእምሮ ጤናማ እና ችግሮችን መቋቋም የሚችል ልጅ ማሳደግ የቤተሰብ እንዲሁም የት/ቤት የጋራ ጉዞ ነው። በልጆች አእምሮአዊ እና ስሜታዊ ብስለት ላይ የቤተሰብ ተሳታፊነት ትልቅ ሚና አለው። ይህም፥ የልጆችን የመማር ችሎታ አቅጣጫ ከማስያዝ ጀምሮ በራሳቸው የሚተማመኑ ልጆች ሆነው እንዲያድጉ መሰረትን ይጥላል።

ይህን ለማድረግ የሚያስችሉ ጠቃሚ ምክሮች :-

🔷የልጆችን የመማር ጥረት መደገፍ🌟
  -በመማር ሂደት ውስጥ መሳሳት የመማር አንዱ አካል እንደሆነ ማስረዳት። ይህ መንገድ ልጆች አዲስ ነገር ለመማር እንዲጓጉ እና እንዲደፍሩ ያደርጋቸዋል።
  -የልጆችን ውጤታቸውን ብቻ ሳይሆን ጥረታቸውንም ማድነቅ።

👉ችሎታ በልምምድ እንደሚያድግ እሚያምኑ ልጆች የተሻለ የችግር ፈቺነት ክህሎት (problem-solving skill) እንደዚሁም በራስ መተማመንን(confidence) ይገነባሉ።

🔷 ስሜታዊ ግንዛቤን (Emotional Awarness) መፍጠር ❤️
-ልጆች ችግራቸውንና ስሜታቸውን  እንዲያጋሩን መርዳት። የተሰማቸውን እንዲያወሩ ያለወቀሳ ወይም ቁጣ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይገባል።

👉የልጆችን ስሜት ወይም ችግር መረዳትና ተገቢውን ምላሽ መስጠት ጠንካራ የማሰብ ችሎታ እና አወንታው ግንኙነት መፍጠር የሚችሉ እንዲሆኑ መሰረትን ይጥላል።

🔷 ጥሩ ተግባቢ እንዲሆኑ ማስቻል 🗣

-ለልጆች ትኩረትን በመስጠት እንዴት ንቁ አዳማጭ መሆን እንደሚችሉ ማስተማር ይቻላል።
-ባለመግባባት ወቅት እንኳን ልጆችን አክብሮት የተመላው ቋንቋ በመጠቀም ማነጋገር ያስፈልጋል። ምክንያቱም ልጆች አዋቂዎችን በማየት ስለሚማሩ።

👉ቤተሰብ ልጆችን ግልጽ ሆኖ ማውራት ከቻለ ፤ ልጆች ሀሳባቸውን እና የገጠማቸውን ነገር ለማውራት ይጋበዛሉ።

🔷ከ እስክሪን የጸዳ(screen-free) ጊዜ ማሳለፍ  📵👨‍👩‍👧 
-ልጆች የሚወዷቸውን ነገሮች አብሮ ማድረግ። ለምሳሌ ወክ ማድረግ ወይም ተመሳሳይ ጨዋታዎችን።
-ልጆች እስክሪን (screen) ላይ የሚያጠፉትን ሰዓት በመገደብ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማድረግ ተገቢ ነው።

👉የቤተሰብ ሰዓት (family time) የቤተሰብ አባላት ጠንካራ ግንኙነት እና ፍቅርን እንዲኖራቸው ያግዛል። ይህ ደግሞ የልጆችን የአእምሮ ደህንነት (mental well-being)  ይደግፋል።

🔷ከፍጹምነት ይልቅ ጥረትን ማድነቅ🎉
-የልጆን ትልልቅ ውጤትን ብቻ ሳይሆን ትንንሽ ውጤታቸውንና ጥረታቸውንም ማድነቅ።
-ውጤታማነት ፍጹም መሆን ሳይሆን መሞከርና መማር እንደሆነ እንዲረዱ ማገዝ።

👉ይህ ሂደት ልጆች ላሳኩት ነገር ብቻ ሳይሆን ለራሳቸውም ዋጋ እንዲሰጡ ይረዳቸዋል።

💎በየዕለቱ የሚደረጉ ልጆችን ያማከሉ ጥቂት እና ጥሩ ተግባራት በልጆች ዘለቄታዊ የአእምሮ እና ስሜታዊ ብስለት ላይ በጎ ተጽዕኖ አላቸው። እኛ በኔሮስ፥ ሁል ጊዜ ከልጆች ቤተሰቦች ጋር በመሆን ልጆች ድጋፍ እንዲያገኙ እንደዚሁም በራስ መተማመናቸው እንዲጨምር ተግተን እንሰራለን።

የኔሮስ ስኩል ኮሚኒቲ ስለሆኑ እናመሰግናለን! 💕

sources:
childrens.com
raisingchildren.net.au

ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ

Neros' School Key To Success

23 Oct, 08:10


የልጆች የአእምሮ እድገት

Neros' School Key To Success

18 Oct, 13:05


📝_ጠቃሚ የጥናት ምክር ለተማሪዎች_📚   

🔹1. የጥናት እቅድ ማውጣት
  የጥናት ልምድን (habit) ለመፍጠር በየዕለቱ የተወሰነ ሰዓት መመደብ ያስፈልጋል። በትኩረት የሚደረግ የ 20-30 ደቂቃ ጥናት እንኳን ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

🔹2. ጥናትን መከፋፈል
  ትልልቅ ሥራዎችን ወደትንንሽ ሥራዎች መከፋፈል። የተከፋፈሉትንም ሥራዎች አንድ በአንድ በቀስታና በመረጋጋት መሥራት ውጤታማ ያደርጋል።🐢 

🔹3. ምቹ ቦታን መምረጥ
  ጸጥታ እና በቂ ብርሃን ያለበትን ቦታን መምረጥ። በምናነብበትም ጊዜ ትኩረትን የሚነፍጉ እንደ ስልክ እና ቴሌቪዥን ያሉትን ማራቅ ወይም መዝጋት እንዳንዘናጋ ይረዳናል።

🔹4.  እረፍት ማድረግ
   በጥናት መካከል ጥቂት እረፍት መውሰድ ሀይላችንን እንድናድስ ይረዳናል። ከ 25-30 ደቂቃ ጥናት በኋላ ለ 5 ወይ 10 ደቂቃ እረፍት ማድረግ አእምሮአችን እንዲፍታታ ይረዳዋል። 🧠💤 
 
🔹5. ሌሎችን ማስረዳት
ያነበብነውን ለሌሎች ጓደኞቻችን ወይም ለቤተሰብ አካል ማስረዳት ወይም ማብራራት መረዳታችንን ያጠነክርልናል። 👩‍🏫

🔹6.  መመገብ እና ውሃ መጠጣት
ጤናማ አዕምሮ  ጤናማ አካል ያስፈልገዋል። ስለዚህ በሠዓቱ ምግብ መመገብ ያስፈልጋል።

🔹7. እርዳታን መጠየቅ
ሁሉንም ማወቅ አይጠበቅብንም። የከበደንን ከክፍል ጓደኞቻችን ወይም ከመምህራን መጠየቅ ተገቢ ነው።

“Education is the passport to the future, for tomorrow belongs to those who prepare for it today.” – Malcolm X

Happy Weekend.

ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ

Neros' School Key To Success

16 Oct, 17:13


ጊዜው ካመጣቸው ጥሩ ነገሮች መካከል በቅድሚያ የሚጠቀሰው ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ሥራን ማቅለል ነው።

በኔሮስ ስኩል ያለውን አሰራር አሁን ካለበት የበለጠ ልናዘምን ስናስብም፤ ዘመኑ ያመጣቸውን የቴክኖሎጂ በጎ ጎኖችን በመጠቀም፦በመምህራን እና በተማሪዎች ወላጆች መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ቀላልና ቅርብ በማድረግ  ለተማሪዎች ልጆቻችን የተሻለ ክትትል ለመስጠት በማለም ነው።

ኔሮስ በቀጣይ ወራት ወይም በዚህ አመት ቀስ በቀስ ተግባራዊ ከሚያደርጋቸው ነገሮች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው።

🔹የተማሪዎችን መረጃ ዲጂታይዝ ማድረግ

🔹የተማሪዎች ውጤት በቀላሉ ለቤተሰቦቻቸው እንዲደርስ፤ አስተማሪዎች ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ ባለው system ውስጥ የተማሪዎችን ውጤት የሚያስገቡበትን መንገድ ማመቻቸት።

🔹ወላጆችም ይህን ተጠቃሚ እንዲሆኑ አቅጣጫ መስጠት።

🔹 እንዲሁም የመምህራን እና የወላጆች መልዕክት መለዋወጫ መጽሐፍ ወይም communication book በ አፕሊኬሽን መልክ ተደራሽ ማድረግን ያካትታል።

የእነዚህ እቅዶች ተግባራዊነትን በመሰረታዊነት የሚወስኑት ባለድርሻ አካላትም፦ መምህራን፣የተማሪዎች ወላጆች እንዲሁም የኔሮስ ት/ቤት አመራር ናቸው።

ይህ ሲስተም በ ኣንድ ኣዳር ወደ ትግበራ የሚገባ እንዳልሆነ ግልፅ ነው ። በመሆኑም በየ ሩብ አመቱ ከሲስተሙ በተጨማሪ የ ውጤት ማሣወቂያ ካርድ አይቀሬ መሆኑን ልናስርግጥ እንወዳለን።

ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ

Neros' School Key To Success

14 Oct, 08:15


🎉 Introducing the Future of Education at Neros School! 🎉
At Neros School, we are excited to announce a major leap forward in enhancing the educational experience for students, teachers, and parents. 📱💻
🔵 Seamless Parent-Teacher Communication
Say goodbye to the traditional parent book! With our new digital platform, homeroom teachers can share students' daily progress directly with parents. No more misplaced messages—parents can easily respond and stay engaged through their personalized accounts.
🔵 Digital Grades and Reports
No more waiting for paper report cards! At the end of each term, teachers will enter grades into the system, and parents can securely access their child’s results online. This modern approach fosters better communication and ensures every student receives the support they need.
💬 Share Your Feedback!
Parents will also have the opportunity to leave their testimonials on the platform, helping us shape the best learning environment for every student.
🌐 Get Ready!
This exciting new system will go online soon—stay tuned for updates! In the meantime, visit the homepage at www.neros.neros.et to explore what’s coming and stay connected.
Together, we’re creating a smarter, more connected learning experience. 🚀

Neros' School Key To Success

02 Oct, 11:40


''የናፈቅናቸውን ልጆቻችንን በማግኘታችን በጣም ተደስተናል''


ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች
የ2017 መደበኛው የመማር ማስተማር ስራ በትላንትናው እለት መስከረም20/2017 ዓ.ም ተጀምሯል።
በሙሉ አቅማችን ለምንጀምረዉ መደበኛ ትምህርት መቃናት የሚሆኑ ስራዋችን እየሰራንም ይገኛል።

🔹 ከትምህርት ቤታችን ህግጋትና የክፍል ዉስጥ የአሰራር ስርዐት ጋር በተያያዘ ከልጆቻችን ጋር እየተመካከርን እና ስልጠና እየሰጠን ይገኛ ።

🔹ተማሪዎቻችን ከረጅም እረፍት ስለተመለሱ ሊኖሩ የሚችሉ ብዥታዎችን ለማጥራት የክህሎት ማሻሻያ እየተሰጣቸው ይገኛል።


📚ውድ ተማሪዎች
ትምህርት ቤታችሁ ኔሮስ ስኩል እውቀት የምትቀስሙበት፣ ህልማችሁ የሚያድግበት፣ ምናባዊ ዕይታችሁ የሚሰፋበት፣ ችሎታችሁ እና ክህሎታችሁ የሚዳብርበት ቦታ መሆኑን እንድታውቁ እንፈልጋለን።

👨‍👩‍👧 ውድ ወላጆች 
በነኔሮስ ስኩል በእያንዳንዱ ቀን ልጆቻችን አዲስ ነገር የሚማሩበት፣ አዳዲስ ጓደኞችን የሚያፈሩበት እና ጠንክሮ በመስራት ውጤት የሚያመጡበት አጋጣሚ ነው ብለን እናምናለን።
ተማሪዎች በትምህርት ቤታችሁ ከፊታችሁ አስደናቂ ጊዜአቶች ይጠብቁአችኋል፣ እነዚህን ጊዜያቶች በሚገባ ተጠቀሙባቸው።
ያላችሁን እምቅ አቅም በመጠቀምና ጠንካሮች በመሆን የሚጎትታችሁ ችግሮች፣ ፈተናዎች ማሸነፍ ትችላላችሁ።
ሁሉም የትምህርት ቤታችሁ ማህበረሰብ እንደምትችሉ ሙሉ በሙሉ እንተማመናለን!

🚌 ከሰርቪስ ጋር የተያያዙ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት በተሻለ እየተንቀሳቀስን ይገኛል።

በጋራ በመስራት መልካም ጅማሮ ፈጥረን የተሳካ አዲስ የትምህርት ዓመት እናሳልፍ
🙏❤️

ኔሮስ ስኩል የልጅዎ የስኬት ቁልፍ

Neros' School Key To Success

20 Sep, 12:51


ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች
እንኳን ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አደረሰን እያልን
በ2017 ዓ.ም ለሚኖረን የትምህርት አመት የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation ) ስለሚኖረን መስከረም 15. 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰአት በኦሊያድ ሲኒማ አዳራሽ ስለሚሆን በለቱ እንዲገኙ ይሁን።
እንዲሁም ትምህርት የሚጀመረው መስከረም 20.2017ዓ.ም ነው። ትምህርት ቀኑን ሙሉ ይሆናል፤ ተማሪዎች ትምህርት ቤት እንድያመጡ(እንዲያስገቡ) የታዘዙትን የትምህርት ጽፈት መሳሪዎችን ያላሟላችሁ ወላጆች ከወዲሁ እንድታሟሉ እናሳስባለን።

Neros' School Key To Success

16 Sep, 05:22


መስከረም 17 የሚለው ሰኞ መስከረም 20 በሚል ይስተካከል።

Neros' School Key To Success

15 Sep, 22:10


​​ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች
እንኳን ለ 2017 ዓ.ም የት/ት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ።

🔴 የ2017 የት/ት ዘመን መስከረም 13 ይጀምራል ።

በመጀመሪያው ሳምንት ትምህር የሚሰጠው ለግማሽ ቀን ይሆናል።

በነዚህ ቀናት
ተማሪዎች ከግቢው ማህበረሰብ እና ከመምህራኖቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ።

በትምህርት ቤቱን ህግ እና ደንብ ላይ ውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣል።

የክህሎት ማሻሻያ የሚሰጥ ይሆናል።

ተማሪዎች የሚማሩበትን ክፍል እና የክፍል ሀላፊዎቻቸውን ያውቃሉ።

ውድ ወላጆች ልጅዎን በስነልቦና እንዲያዘጋጁ አደራ እንላለን።

📚 የ180 ቅርንጫፍ የግንዛቤ መስጫ ሳምንት እና ትምህርት የሚጀመረው የሚሆነው አርብ መስከረም 20 ይሆናል።


🔹የናፈቁንን ዉድ ተማሪዋቻችንን ለማየት በጉጉት እንጠብቃለን ።
ጤና ቆዩን ❤️🙏

Neros' School Key To Success

01 Sep, 13:21


በ0946466088 በመደወል የተማሪዎቹ ን የስፖርት ትጥቅ እና የ ት/ት ቤቱን ዩኒፎርም ማግኘት ይችላሉ ።

Neros' School Key To Success

01 Sep, 13:19


ኔሮስ ስኩል ለተማሪዎች የስፖርት ልብስ ከ ጆኤም ቴይለርስ ጋር በመተባበር አዘጋጅቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ኣቀርቧል።

Neros' School Key To Success

01 Sep, 13:17


Unknown 🦴:
🖐 ሰላም ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች የ❷⓿❶6 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቋጭተን የክረምት ወቅት ላይ እንገኛለን, ቀዝቃዛ እና ዝናባማውን  ወቅትን እንዴት እያሳለፋችሁ ነው ?

👉   ተማሪዎች ለ ❷⓿❶❼ ዓ.ም ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ የሚጠቅማችሁን አንዳንድ ሃሳቦች እንጠቁማችሁ

   ስነልቦናዊ 🧠ዝግጅት

በ❷⓿❶❻ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጠንካራ  🦾 የነበራችሁበትን እና ማሻሻል የሚገባችሁን ከወላጆቻቹሁ 👩‍🦰👦👶👱‍♀ጋር  በመወያየት እና በመለየት ለ ❷⓿❶❼ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል።

ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙ

በዚህ የእረፍት ጊዜ
📖 የጥናት ሰዓት
🏃‍♂️ የጨዋታ ሰዓት እና
👨‍👩‍👧 ከቤተሰባችሁ ጋር ጊዜ የምታሳልፉበትን ፕሮግራም ማዘጋጅት አስፈላጊ ነው።


የንባብ ክህሎታችን እዲሻሻል በቀን ለ1 ሰዓት ማንበብ 📖
የፅህፈት ክህሎታችንን ለማሻሻል ለ30 ደቂቃ መፃፍ ጥሩ ነው።

📚 የትምህርት መርጃ መሣሪያ ዝግጅት 

ውድ ወላጆች ለ2017 የትምህርት ዘመን ዝግጅት ስታደርጉ

👉ተማሪን በተሰጠው የምዝገባ ጊዜ ማስመዝገብ👨‍💻👩‍💻

👉የልጅዎን የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ
👖 👕 ማሰፋት

📚 የመማሪያ መፅሀፍት
🎒ቦርሳ
📓ደብተር
✏️እርሳስ
🖊️ እስኪርቢቶ
መቅረጫ እና ላጲስ ማዘጋጀት።

Nafekot:
🗣ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች እኛ ለ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን አስፈላጊውን ዝግጅት ጨርሰን ውድ ተማሪዎቻችንን በናፍቆት እየጠበቅን ነው።

            መልካም የክረምት ወቅት 🌧

Neros' School Key To Success

19 Jul, 10:08


📣ሰላም ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች

Ergaa ariifachiisaa:
Maatiin barataa Fi barataa dhiifama gaafachaa Qormaatni Herregaa(sorobaan) marsaan 5ffaa kan kennamu Guyyaa 13/11/2016 mb Gadaa kiiloleetti waan kennamuuf mb hundi kan kutaa magaalaa Dambalaas saatii 2:30tti qabdanii Akka dhuftan kabajaan isin beeksifna

🔔ት/ቢሮ በተከታታይ ለአራት ዙሮች አዘጋጅቶ የነበረው የጥያቄና መልስ ውድድር አሁን ለአምስተኛ ዙር በድጋሚ አዘጋጅቷል። ሆኖም ይህንን ውድድር ለመሳተፍ ከላይ ስማችሁ የተዘረዘሩ ልጆቻችን 📅 በቀን 13/11/2016 የሒሳብ ፈተና ይወስዳሉ፡፡
📌ማሳሰቢያ
ፈተናው የሚወሰድበት ቦታ ቁጥር ሁለት ገዳ ኪሎሊ ከገላውድዮስ ፊትለፊት በሚገኘው ት/ቤት ሲሆን ከጠዋቱ 2:30 እንዲገኙ ስንል እንወዳለን፡፡

Neros' School Key To Success

16 Jul, 13:19


🚩🚩🚩 🚩🚩🚩🚩🚩

👍https://vm.tiktok.com/ZMr5WUdPr/

Neros' School Key To Success

15 Jul, 09:12


ሰላም ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች

የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ለተከታታይ ቀን ስንመዘግብ እንደነበር ይታወቃል :: ሆኖም ምዝገባ በዚህ ሳምንት የምናጠናቅቅ በመሆኑ እርስዎም እስከተጠቀሰው ቀን በመምጣት ልጅዎን ማስመዝገብ እንዳለብዎ ማስታወስ እንወዳለን ። ለምዝገባ በሚመጡበት ወቅት ሁለት የልጆውን ጉርድ ፎቶ ይዘው መምጣቶውን አይርሱ❗️
ኔሮስ ስኩል
የልጅዎ የስኬት ቁልፍ !!

Neros' School Key To Success

14 Jul, 17:32


ሰላም ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች

🚩🚩🚩🚩🚩🚩
🚩🚩🚩 🚩🚩🚩🚩🚩🚩
🚩🚩🚩🚩🚩

🌐https://vm.tiktok.com/ZMrPhLgUV/

Neros' School Key To Success

12 Jul, 20:27


ሰላም ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች

🔖ት/ቢሮ በተከታታይ ለሶስት ዙሮች አዘጋጅቶ የነበረው የጥያቄና መልስ ውድድር አሁን ለአራተኛ ዙር በድጋሚ አዘጋጅቷል። ሆኖም ይህንን ውድድር ለመሳተፍ በቀን ማክሰኞ 📅 09/11/2016 የሒሳብ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ ፈተናው ከምዕራፍ 1-5 ብቻ ያጠቃልላል፡፡
ማሳሰቢያ
✔️ፈተናው የሚጀመርበት ሰአት = 3:00
✔️ፈተናው የሚያበቃበት ሰአት = 4:00
➡️ከፍያ ያልከፈላቹ ተማሪዎች በእለቱ ለፈተና ስትመጡ 400 ብር ይዛችሁ እንድትመጡ❗️
😀የሰርቪስ አገልግሎት አይኖርም፡፡ ልጆትን ከ 4:00 ጀምሮ መታቹ እንድትወስዱ ስንል እናሳስባለን ።

Neros' School Key To Success

28 Jun, 09:57


🚩🚩🚩🚩🚩
🚩🚩🚩🚩
🚩🚩🚩 🚩🚩
🚩🚩🚩🚩🚩🚩

🎈ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች 🎈

እንኳን ለኔሮስ ስኩል መዝጊያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🎆፡፡ የኔሮስ ስኩል መዝጊያ በአል ፣ የፕሬፓራቶሪ ተማሪዎች እና የ8ኛ ክፍል የምረቃ በአል ቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰአት ጀምሮ በአዳማ ጀነራል ሜዲካል ኮሌጅ አዳራሽ ይከበራል ፡፡🎇
እሮሶም የልጆቻችን ፕሮግራም እንደይበላሽ ሰአቱን አክብረው እንዲገኙልን እናሳስባለን፡፡ የላክነው የጥሪ ካርድ እንዳይለዮ አደራ እንላለን።
🔔ለ2017 የልጆቻችሁ አዳዲስ እህት/ወንድም ላላችሁ ለፕሪ ኬጂ ተማሪዎች ምዝገባ ከሃምሌ 3/2016 ዓም ጀምሮ ስለሚካሄድ ( ሌሎች አዳዲስ ተማሪዎችን ከመመዝገባችን በፊት በተጠቀሰው ቀን ባለው ሳምንት ልጆን እንዲያስመዘግቡ እናሳስባለን፡፡ )
📌የ 2017 ዓ ም የነባር ተማሪዎች ምዝገባም እንደዚሁ ከ ሃምሌ 3 /2016 —ሃምሌ 12/2016 ስለሚካሄድ ከወዲሁ ራሳችሁን እንድታዘጋጁ እናሳስባለን።
📌ለ 2017 ዓ ም ከፕሪ ኬጂ -7ኛ ክፍል ድረስ ለሚመዘገቡ አዳዲስ ተማሪዎች መረጃውን ከፈለጉ ባሉን ጥቂት ቦታዎች ለመመዝገብ ከ ሃምሌ 3/2016 ዓም ጀምሮ ልጆን ለመግቢያ ፈተና እንዲያስመዘግቡ እናሳስባለን፡፡

‼️ማሳሰቢያ - ለተመራቂ ተማሪዎች ጋዋን መመለሻ ግዜ ከሃምሌ 3 - 5 ብቻ ይሆናል፡፡

👀የክረምት ትምህርት ፕሮግራም
ከሃምሌ 11 እስከ ነሃሴ 15 ለአምስት ሳምንታት የሚቆይ የክረምት ትምህርት በኔሮስ ስኩል💥 የተዘጋጀ ሲሆን ለበለጠ መረጃ የቅርንጫፉ በመሄድ/በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
📞ስልክ 0956566894 / 0222116470 ኮሌጅ ፕራይመሪ
0222114343 / 0975067553 / 0938082185 / 0911655544 ቦሌ ኬጂ 0222126586 / 0911655544 / አውራጎዳና ኬጂ
አጠቃላይ ጉዳዮችን
0994819283 / 0927249501 / 0984981092 / 0911646932

Neros' School Key To Success

21 Jun, 10:15


ሰላም ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች

🔖ት/ቢሮ በተከታታይ ለሁለት ዙሮች አዘጋጅቶ የነበረው የጥያቄና መልስ ውድድር አሁን ለሶስተኛ ዙር በድጋሚ አዘጋጅቷል። ሆኖም ይህንን ውድድር ለመሳተፍ በቀን🗓 15/10/2016 የሒሳብ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ ፈተናው 20 ጥያቄ ሲኖረው ከምዕራፍ 1-4 ብቻ ያጠቃልላል፡፡
ማሳሰቢያ
✔️ፈተናው የሚጀመርበት ሰአት = 2:30
✔️ፈተናው የሚያበቃበት ሰአት = 3:30
➡️ከፍያ ያልከፈላቹ ተማሪዎች ነገ ለፈተና ስትመጡ 360 ብር ይዛችሁ እንድትመጡ❗️
🚫የሰርቪስ አገልግሎት አይኖርም፡፡ ልጆትን ከ 3:30 ጀምሮ መታቹ እንድትወስዱ ስንል እናሳስባለን ።

Neros' School Key To Success

19 Jun, 14:24


🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
🔖ውድ የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች እነሆ የ3ተኛው ሩብ አመት የscholarship award አሸናፊዎች
1️⃣st cycle ፦

🎇ተማሪ አሜን ይልማ ከ 2ተኛ C

2️⃣nd cycle፦

ተማሪ ማክሪያና ለማ ከ 5A

🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ ያላችሁ ከዚህ ለተሻለ ውጤትና ሽልማት በቅታችሁ ማየት ፍላጎታችን ነው ።
🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩