ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan @mahbere_kidusan Channel on Telegram

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

@mahbere_kidusan


ማህበረ ቅዱሳን
ማህበረ ቅዱሳን ወንጌልን በመላው አለም ለማስፋፋት በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ እየሰራ ይገኛ። እርሶም ለወገኖ በማጋራት ወንጌልን በመላው አለም እንዲሰበክ የድርሻዎትን ይወጡ
..
የሰማነውን እንናገራልርን ያየነውን እንመሰክራለን!
ማህበረ ቅዱሳን
https://t.me/mahbere_kidusan

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan (Amharic)

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan እናንተ ለመሆን ወደ የማህበረ ቅዱሳን ወንጌል ተመልከቱ። ይህ የተለያዩ ማህበራዊ ትስር ገፅ ከቶ ነው? ምን ነው እና ምንድን ነው? እንዴት እንደሚወጣቸው ያልጠነቀቁትን ነገሮች ምን እናመሰግናለን? በዚህ የተነሳ ችግሮችን መለወጥ ለናቸው። ማህበረ ቅዱሳን ወንጌል በመላው አለም ድምጽ እየገነት ነው። የሁሉን ድምጽ እና መረጃዎችን እንከታተለን ከግምት እንሂድና ማሰደድ አቅምዎችን መወዳደር እና እየገነት አጠንኩለን። ከዚያም በእኛ ላይ የሚያምኑን የእኅቷን ቃልና የእኛን መልእክት ስለጠላን ከሰማይ ጋር ውስጥ እንሆናለን። ይህንን ችግሮችን የቅዱስ ግንብ ለማወቅ ማግኘት እንፈልጋለን። በተጨማሪ የሚመጣውን ለማወቅ የመጪውን መረጃ ከለሊቱ በቀላሉ ይፈልጋሉ።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

10 Feb, 19:00


ማኅበረ ቅዱሳን በወላይታ ማእከል  ለቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የጉዞ  መርሐ ግብር ማካሄዱ ተገለጸ፡፡

የካቲት ፫/፳፻፲፯ ዓ.ም


በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኙት በግልና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የቅድመ ግቢ ጉባኤ ሥልጠና የሚከታተሉ ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ወደ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም የካቲት 1/ 2017 ዓ.ም አከናውነዋል፡፡

በጉዞም የሊቃ ፣የቆንቶ ልጃገረድ እና ጮራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች  ተሳትፈዋል፡፡

በዕለቱ ከወላይታ ማእከል የተመደቡ የኦቶና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ሰበካ ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ዲ/ን አቤነዘር መስፍን “ልባም ሰው” ማቴ 7፡24 በሚል ርዕስ ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም ከገዳማዊያን አባቶች  ምክር እና ቡራኬ ተሰጥቷል፡፡

መረጃው የማኅበረ ቅዱሳን ወላይታ ማእከል  ሕ/ግ እና ሚዲያ ክፍል ነው

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

10 Feb, 19:00


በሲዳመኛ ቋንቋ የሠለጠኑ ሰባኪያነ ወንጌል መመረቃቸው ተገለጸ

የካቲት ፫/፳፻፲፯ ዓ.ም 

ማኅበረ ቅዱሳን በሐዋሳ ማእከል ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል አዘጋጅነት ከሲዳማ ሀገረ ስብከት ሥር ካሉ ወረዳ ቤተ ክህነቶች ለተውጣጡ የሲዳምኛ ቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ለደረጃ አንድ ተተኪ መምህራን የሠለጠኑ ሰባኪያነ ወንጌል በትናትናው ዕለት የካቲት 02 ቀን 2017 ዓ.ም በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን መመረቃቸው ተገልጿል።

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደሪ መላከ ሰላም ቀሲስ ታረቀኝ በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት “ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኩላዊት እንደመሆኗ መጠን በቋንቋ ወንጌልን ማስተማር ለሁሉም ተደራሽ እንድትሆን ያደርጋታል” ያሉ ሲሆን የዛሬ ተመራቂ ሰባኪያነ ወንጌል መምህራን የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በመቋቋም የቀደሙትን ሐዋርያት አባቶችን አርዓያ አድርገው በአገልግሎት እንዲተጉ አሳስበዋል።

የሥልጠናው ተመራቂ የሆኑት የሐዋሳ ሎቄ መስቀለ ክርሰቶስ አገልጋይ ቀሲስ ክፍለ ዮሐንስ ቂርቆስ እንደተናገሩት “የተሰጠን ኃላፊነት ትልቅ ነው” ሲሉ ተናግረው ሥልጠናውን ያዘጋጀውን ማኅበረ ቅዱሳንን አመስግነዋል።

ሌላኛው ከበንሳ ወረዳ ማእከል የመጡት የሥልጠናው ተሳታፊ ዲያቆን ዋስይሁን በቀለ በበኩላቸው ከተሰጠው ሥልጠና በርካታ ትምህርቶችን እንዲሁም የተለያዩ ልምዶችን እንዳገኙ ገልጸዋል፡፡

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

10 Feb, 10:35


ኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት የተመሠረተበትን 61ኛ ዓመት በዓል ማክበሩ ተገለጸ።

የካቲት ፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

የኢየሩሳሌም ገዳማትና ቅዱሳን መካናትን የሚያስጎበኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን መታሰቢያ ድርጅት ለኢየሩሳሌም የተመሠረተበትን 61ኛ ዓመት በዓል በትናትናው ዕለት የካቲት 2/2017 ዓ.ም በድርጅቱ አዳራሽ አክብሯል ።

በበዓሉ የአዊ ዞንና የመተከል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ቶማስ፣ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ በኩረ ምዕመናን ጌታሁን በሻህ፣ የሥራ አመራር ቦርድ ዋና ሰብሳቢ መጋቢ ሠናያት ሠርፀ ወልድ ፈለቀ፣ የኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የድርጅቱ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል ።

በመርሐ ግብሩ መዝሙርና ስብከተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን የጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ታደሰ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ።

አቶ ሳሙኤል እንደገለጹት ድርጅቱ በ1956 "ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን መታሰቢያ ድርጅት ለኢየሩሳሌም እንደተቋቋመ ገልፀው ድርጅቱ በዋናነት በቅድስት ኢየሩሳሌም የሚገኙ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማትን ደኅንነት ለመጠበቅ፣ ከገዳማዊያን አባቶችና እናቶች ጎን በመቆም በማንኛውም ነገር ለመርዳትና ለመደገፍ እንደሆነ ገልጸዋል።

አክለውም ድርጅቱ ላለፉት ዓመታት በርካታ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ለቀጣይ እንደ ዕቅድ ከያዛቸው መካከል የሀገር ውስጥ ጉዞ ማካሄድ ነው ብለዋል ።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ቶማስ አባታዊ ምክር፣ ቃለ ምዕዳና ቡራኬ ተሰጥቷል ።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

08 Feb, 19:24


✍️✍️ሐመር መጽሔት በየካቲት ወር እትሟ!  
  ".. እጅግ ብዙ የመከራ ማዕበል ቢጎርፍም ሁልጊዜም አምላኳ ከእርሷ ጋር ስለሆነ ይገፏት ይሆናል እንጂ አትወድቅም "  የካቲት ዕትም በ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዐምድ
 #የኅትመት ዘመን ፦#የካቲት ፳፻፲፯  ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል  በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
•  ሐመር መጽሔት ፴፪ኛ ዓመት  ቁጥር ፪  # የካቲት ፳፻፲፯  ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን " # ‹‹  #የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም ››  በሚል ጠንንካራ መልእክት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ምእመናን የክፋት ጠማቂዎችን ሤራ በመታገስና በታላቅ ንቃት በመመልከት ትኩረታቸውን በበዓላቸው ላይ፣ ልባቸውንም ከአምላካቸው ጋር በማድረግ በዓሉን በሰላም እንዳሰለፋና ትንኮሳዎቹ ትዕግሥትን የሚፈታተኑ ቢሆንም ‹‹ራሳቸው አምጥተው፣ ራሳቸው በሚያሮጡ›› ተንኮለኞች ሤራ ላለመጠለፍ ያደረጉት ጥንቃቄ የሚያስመሰግን እንደነበረ ።
       በአጠቃላይ ሲታይ ግን እንዲህ ዓይነቱ የክፉዎች መዳፈር ለሀገርም፣ ለመንግሥትም፣ ለቤተ እምነቶች ግንኙነትም አይጠቅምም፡፡ ድፍረቱ ደግሞ በሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሉን በሚችል አምላክ ላይ የተፈጸመ ደፍረት በመሆኑ ሀገርና ወገንን የሚያስከፍለው  ዋጋ አሁን እየተቀበልን ካለው በላይ እንዳይሆን መጠንቀቅ  እንደሚገባ ሐመር በመልእክት ዐምድ ታስነብባለች።
   

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

08 Feb, 19:24


  .#ዐውደ ስብከት  ሥር” # “በእንተ ጾም ”  በሚል ርእስ  ጾም ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፣ጾም በብሉይ ኪዳን ፣ጾም በሐዲስ ኪዳን ፣የጾም አይነቶች ፣የጾም መሠረታዊ ጥቅሞች ፣ዐቢይ ጾምን የምንጾምበት ምክንያት  በስፋት  ታስነብባለች።
  #በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# “መኑ ይእቲ ዛቲ   ክፍል አንድ " በሚል ዐቢይ ርእስ  እመቤታችን ማን  እንደሆነች፣ የእመቤታችን ከሴቶች መለየት እንዴት እንደሆነ ፤በነገረ ድኅነት የእመቤታችን ድርሻ  የሊቃውንት መጽሐፍ በማጣቀስ ትምህርት ይሰጣል ።

    #ዐቢይ ጉዳይ  ዐምድ  ሥር  ደግሞ “# መከራው እንጂ ፣ለሞት ጣር እንዳይሆን እንሥራ" በሚል ርእስ  የመከራው ዶፍ መገለጫዎችና ማድረግ ያለብን ጉዳዮች በዝርዝር ያሳያል
   •  #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር  ደግሞ  "#የኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ትምህርት "በሚል ርእስ   ዐቢይ ርእስ  በመልአከ ሰላም  ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው  ስለ ምሥጢረ ተክሊል፣ጋብቻ እንዴት እንደተጀመረ፣የጋብቻ ዓላማው ፣ከመጀመሪያው ጋብቻ ምን እንማራለን? ጋብቻ ብዙኃኑ የሚመኘው ሲሆን እንደምኞቱ ጸሎቱ የደረሰለት ስእለቱ የሰመረለት ስንቱ ይሆን? በሚል ሰፊት ትምህርት  ታሰተምራለች።
   • #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#ቅዱስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ፣ወላዴ አእላፍ አበ ብዙኃን" በሚል ርእስ  ስለ ቅዱሱ መጠራት፣ አገልግሎት በስፋትታስቃኛለች ።
   •  #በነገዋ  ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ  ሥር “ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን " በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ክፍል ፫   በሚል ርእስ በ፭ መቶ ክፍለ ዘመን፤በዘመነ ላስታና ድኅረ ላስታ ፣ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን በ21ኛው ክ/ዘመን ፣መንፈሳውያን ማኅበራት በአሁኑ ዘመን የሚሉ ርእሶች ይዛለች ።
  #በኪነ ጥበብ ዐምድ "#ጥሪ_ክፍል _፪ "በሚል  ታስነብባለች ።
•  #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “የማዕረግ ስም አሰጣጥ # ክፍል ፩ " በሚል ርእስ #በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን የአንድምታ ትርጓሜ መምህር የሆኑትን #መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ አዳምጤን ጋር የተደረገ  ጥያቄና መልስ ይዛለች።  ።
   ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት   ቁጥር ፲፪ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

magazine @eotcmk.org  #ሐመር #መጽሔት  ዝግጅት  ክፍል

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

07 Feb, 04:42


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ
ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው፡፡

ጥር ፳፱/፳፻፲፯ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባዔ፡-
‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)
    ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣ መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፤ ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፤ የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፤ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠንቅቆአቸዋል፤ የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፤
•  የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን !
እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ ኣለብን፣

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

07 Feb, 04:42


አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል፤ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፤ አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፤ ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፤ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣ በድርቅ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን፤
እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፤ እንድናበጃት፣ እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፤ ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣ በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ . . . ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው፤

   በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው፤ በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፤በዚህ ሁሉ ተግባራችን  እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፤ ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል፤
  የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤ ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ  ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤
እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፤ ምህላችንንም ይቀበልልን፤
   “እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ምንጭ:- EOTC Broadcasting Service Agency

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

07 Feb, 04:42


የአውስትራሊያ ማእከል  ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን መደገፍ በሚቻልበት መልኩ  ውይይት ማድረጉ ተገለጸ።

ጥር ፳፱/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኀበረ ቅዱሳን በአውስትራሊያ ማእከል ከ10 የጽዋዕ ማኀበራት ጋር ገዳማትን እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን መደገፍ በሚቻልበት መንገድ እንዲሁም የገዳማት ነባራዊ ሁኔታን አስመልክቶ በቨርችዋል(በበይነ መረብ)  የግንዛቤ ማስጨበጫ ዉይይት መካሄዱ ተገልጿል፡፡

አቶ ፍጹም መንገሻ የአውስትራሊያ ማእከል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ከማኀበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት የገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ተጨባጭ ሁኔታቸውን ለማሳወቅና ድጋፍ እንዲደረግላቸው ውይይቱ በመሠረታዊነት ተከናውኗል ብለዋል።

ኃላፊው አክለዉም በጦርነትና በድርቅ ምክንያት በከፍተኛ ችግር ያሉ በተለይም በሰሜኑና በምስራቅ የሚገኙ ገዳማትን ከጽዋዕ ማኀበራት ጋር በመሆን ድጋፉ ተደራሽ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል፡፡

ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ እንዲያገኙ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በውይይቱ ላይ የተገኙት የማኀበራቱ ተወካዮች ለተግባሩ ቁርጠኛ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ድጋፉ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በጦርነትና በድርቅ ለተጎዱ ገዳማትንና አብነት ትምህርት ቤቶችን የሚያካትት መሆኑ ተጠቅሷል።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

28 Jan, 10:35


https://youtu.be/HLbtSkhIBUY?si=mCm91okVAj5YcRYJ

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

28 Jan, 07:18


በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ የታነጸው የሀዋሳ አየር ማረፊያ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተመረቀ።

ጥር ፲፱/፳፻፲፯ ዓ.ም

በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ማኀበረሰብ፣በCAPAT ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የበረራ ሠራተኞች መንፈሳዊ ጉባኤ እና በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት የታነጸው የሀዋሳ አየር ማረፊያ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በትናንትናው ዕለት ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ ውሏል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በክልል ትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨው የደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይ  አህጉረ ስብከት እና በመንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየም መምሪያ የማኅበራት መምሪያ  የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ፣መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ሞላልኝ መርጊያ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሀገረ ስብከቱ የመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች፣መ/ፀ/መ/ር/ቆ/አባ ኪዳነማርያም የሀዋሳ ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪን ጨምሮ የሌሎች ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንደተናገሩት ይህ ቤተክርስቲያን የተሰራው የእግዚአብሔር ስም እንዲጠራበት እንዲሁም ምእመናን እንዲባረኩበት ነው ያሉ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜም ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በዓለ ንግሡም ተከብሯል፡፡

በተጨማሪም በቦታው በርካታ ቁጥር ያላቸው ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ውጭ የሆኑ ምእመናን በታደሙበት ለተግባሩ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀትና ስጦታዎች ተበርክቷል።

የተመረቀው ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በሚያዝያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም መሠረት ድንጋይ መቀመጡ ይታወሳል።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

28 Jan, 07:18


“መከራ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ለእኛ  ለልጆቿ  አዲስ አይደለም!!”፡- ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ

ጥር ፲፱/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ማእከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ለብፁዕ አቡነ ቄርሎስን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጥር 17 ቀን 2017 ዓ.ም  የገና እና የጥምቀት በዓላትን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደርሰዎ መርሐ ግብር አከናውነዋል።

ብፁዕነታቸው እንደተናገሩት “መከራ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ለእኛ ለልጆቿ  አዲስ አይደለም” ስለዚህ  ሁላችሁም በመከራው ተስፋ ሳትቆርጡ በመጽናት የምትችሉትን ሥራ ሥሩ  በማለት የተናገሩ ሲሆን እንደ ማኅበርም አንድነታችሁን አጽኑ በማለት አባታዊ መመሪያ እና ቡራኬ ሰጥተው ስለጠየቃችሁኝ አመሠግናለሁ ብለዋል።

በተጨማሪነትም በመርሐ ግብሩ ላይ በማእከሉ መዘምራን መዝሙር የቀረበ ሲሆን  አጠቃላይ የማኅበሩን የሥራ እንቅስቃሴ እና የአባላትን ሁኔታ  ጠይቀዋል፡፡

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

26 Jan, 18:34


የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም ለማስከበር እና የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየተሰራ ነው።

ጥንታዊት፣ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማስፋፋት በምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሌሎችን መብትና ጥቅም ባለመንካት በትዕግሥትና በማስተዋል የምትጓዝ አገራዊ ኃላፊነት የሚሰማት ሰላምን አብዝታ የምትሰብክ መንፈሳዊት ተቋም መሆኗ ይታወቃል።

ቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮቷን ለማስፋፋት በተጓዘችባቸው አያሌ ዓመታት አገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ፊደላትና የራሷ የቀን አቆጣጠር ባለቤት እንድትሆን ያስቻለች፣በሊቃውንቶቿ የመጠቀ እውቀት አማካኝነት የሥነ ጥበብ፣የሥነ ስዕል፣የዕጽዋትና የጠፈር ምርምርና ጥናቶችን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ለዓለም ያበረከተች ጥንታዊት ተቋም ስለመሆኗም አያሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ይሁን እንጂ ይህች ለአገረ መንግስት መመስረትና መጽናት፣ለእውቀት መስፋፋት፣ ለአብሮነት መጎልበት፣ ትውልድን በሥነ ምግባር ቀርጻ ፍቅርና አንድነትን በተግባር የሰበከች እናት ቤተክርስቲያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ፣በአስተምህሮቿ፣በዕምነቷ፣በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

26 Jan, 18:34


ስለሆነም በተደጋጋሚ እየተፈጸሙባት የሚገኙትን እነዚህን እኩይ ተግባራት ከዚህ በላይ በዝምታና በትዕግስት ማለፍ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ የሚያደርጋት ከመሆኑም በላይ መብቷን በእጅጉ የሚጋፋ፣ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቶቿን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።

ስለሆነም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ማጥናት፣መከታተልና ሕግን መሰረት ያደረገ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድግ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘችው ወቅታዊ ሁኔታውን በዝርዝር በማጥናት ተቋማዊ እልባት የሚያገኝበትን መንገድ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ያደረገች ሲሆን የቤተ ክርስቲያናችን የሕግ አገልግሎት መምሪያም በሕግ አግባብ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ፍትሕ ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብና በማደራጀት ክስ መመስረት የሚያስችለውን ሁኔታ በማመቻቸት ወደ ተግባር ለመለወጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ከዚህ ጎን ለጎንም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በጠቅላይ ቤተክህነት ከሚገኙ መምሪያዎች መካከል ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን መምሪያዎች በማካተት የተቋቋመው ኮሚቴም ዝርዝር ጥናቶችን በሚገባ በማጥናትና ችግሮቹን ለይቶ ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ በማቅረብ በቤተክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ አስተዳደር አማካኝነት ተቋማዊ አቋም የሚወሰድበትና በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የማያዳግም መፍትሔ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል ሥራ በመሥራት ላይ መሆኑን እየገለጸች በሁለቱም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ በተከታታይ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲገለጽ የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እያስታወቀች በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምዕመናንና ምዕመናት በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት የሚደረግላቸውን ጥሪ ተቀብለው ለቤተክርስቲያናችን መብት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እናት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ጥር ፲፯ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

26 Jan, 18:34


''ቦሩ ሜዳ'' የፊት ለፊት የጥያቄና መልስ መድረክ

''ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለምን የአዋልድ መጻሕፍትን ትጠቀማለች ?''

“ቦሩ ሜዳ” በማኅበረ ቅዱሳን ወርኃዊ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ላይ

ቀን፡- ጥር 25/2017 ዓ/ም
ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ

በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ

እርስዎም ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በመገኘት ከአዋልድ ማጻሕፍት ጋር ተያይዞ ያለዎትን ጥያቄ በማንሳት ምላሽ ያገኙ ዘንድ ተጋብዘዋል፡፡

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

22 Jan, 18:33


✝️ለቡግና ወገኖቻችን እንድረስላቸው።✝️
+++
በሰሜን ወሎ ዞን #ቡግና ወረዳ በድርቅ በመጎዳታቸው ለከፋ ማኅበራዊ ቀውስ የተጋለጡ ወገኖቻችንን በመርዳት ሰብአዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ድጋፍ ለማድረግም፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

20 Jan, 17:04


በቃና ዘገሊላ በዓል የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊው ክብረ በዓል ላይ የአዲሱ ሚካኤል ታቦት ወደ መንበሩ ሲመለስ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በመግባት ሕሙማንን ጎብኝቷል።

ፎቶ፡- ከኢቢሲ

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

20 Jan, 17:04


የየካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ታቦት ወደ መንበረ ክብሩ እየተመለሰ ነው። Eotc pr

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

20 Jan, 17:04


በደብረ ብርሃን!

የቃና ዘገሊላ በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ በታሪካዊው አጼ ዘርዓያዕቆብ አደባባይ በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

12 Jan, 16:29


https://youtube.com/shorts/wevu-U4S_E0?si=cj7sgFRyZurQBe83

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

12 Jan, 16:25


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት  ወቅታዊ  ጉዳዮችን አስመልክተው  አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

10 Jan, 12:30


በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል “አደራ አለብኝ” በሚል መሪ ቃል መርሐ ግብር አከናወነ።

ጥር ፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም

“አደራ አለብኝ” በሚል መሪ ቃል የማኅበረ ቅዱሳን ጎንደር ማእከል ታኅሣሥ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በማእከሉ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የድኅረ ግቢ ጉባኤ መርሐ ግብር ማካሄዱ ተገልጿል፡፡

በመርሐ ግብሩ ከ140 በላይ የግቢ ምሩቃን የተሳተፉ ሲሆን "የአገልግሎት በር" በሚል ርዕስ ሥልጠና ተሰጥቷል።

በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ አባላት የልምድ ልውውጥ በማካፈል አባላት ሥራ፣ ሁኔታ፣ ቦታና ጊዜ ሳይገድባቸው ባሉበት ሆነው ሐዊርያዊ አገልግሎታቸውን መፈጸም እንደሚገባቸው መልእክት ተላልፏል።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

09 Jan, 19:13


የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ተከናወነ።

ጥር ፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር በጽርሐ ተዋሕዶ ተካሂዷል።

በመርሐ-ግብሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የየመምሪያ ኀላፊዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በጽሑፍ የተደገፈ የእንኳን አደረሰዎ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በዓሉን የተመለከተ ዝማሬ በሊቃውንት ቀርቧል።

ቅዱስ ፓትርያርኩም በመርሐ ግብሩ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት/EOTC

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

09 Jan, 08:58


አዕላፋት ዝማሬ
https://youtube.com/shorts/0i5RsBuRTMs?si=OmeLRRX3qTjb8fXm

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

04 Jan, 20:08


በደብረ ዘመዳ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ለሚገኙ 80 የአብነት ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ።

ታኅሣሥ ፳፮/ ፳፻፲፯ ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በራያ ቆቦ ወረዳ ስር ለምትገኘው ለደብረ ዘመዳ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ለሚገኙ 80 የቅዳሴ ጉባኤ ቤት ተማሪዎች የምግብ ቁሳቁስ በትናንትናው ዕለት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

በማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ማእከል የጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ መለሰ አያሌው እንደገለጹት  ማእከሉ ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚገኙ በጎ ፍቃደኛ ምእመናን የሰበሰበውን  ድጋፍ ማድረጉን  የገለጹ ሲሆን አሁን ካለው የኑሮ ውድነት እና የሰላም እጦት አንጻር ጉባኤ ቤቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመሆናቸው በተጠናከረ ሁኔታ ተጨማሪ ድጋፎች ሊደረጉ ይገባል ብለዋል።

በተመሳሳይም መሰል ድጋፍ በጋዞ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር ለሚገኘው የዋሮ ቅዱስ ሚካኤል ለ30 የዜማ ጉባኤ ቤት የአብነት ተማሪዎችም ተበርክቷል በዚህም በአጠቃላይ ለሁለቱም ጉባኤ ቤቶች 170‚000 (ከአንድ መቶ ሰባ ሺ ብር በላይ ወጭ መደረጉን ተገልጿል፡፡

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

29 Dec, 18:47


ከሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት የተወጣጡ ደቀ መዛሙርት ተመረቁ

ማኅበረ ቅዱሳን ከደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ገብረ ክርስቶስ ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት እና ከደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት የተወጣጡ ደቀ መዛሙርትን አሠልጥኖ አስመርቋል።

ለአንድ ወር በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎች ዙሪያ ሥልጠና ሲወስዱ ለቆዩት ሠልጣኞች በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የምርቃት መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የደብሩ ሰ/ት/ቤት የሠልጣኞችን የትራንስፖርት እና የምግብ ወጪ ከመሸፈን ጀምሮ የመኝታ እና የሕክምና አገልግሎቶች በሙሉ በማሟላት ሥልጠናው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ ተገልጿል።

የደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት ሥልጠናው እንዲከናወን ፈቃድ ከመሥጠት ጀምሮ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱም በመርሐ ግብሩ ላይ ተነግሯል።

የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ ዶ/ር ሄኖክ ፍቅሬ እንደተናገሩት ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎቶች የምታከናውነውን አገልግሎት ለማጠናከር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ያሉ ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ ሰ/ት/ቤቶች በዚህ አገልግሎት ላይ ከማኅበሩ ጋር በመተባበር እየሠሩ በመሆናቸው ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበ እንደሆነ ገልጸዋል።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

29 Dec, 18:47


ምክትል ሰብሳቢው ጨምረው እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ሠልጣኞቹን ከመመልመል ጀምሮ  መምህራን በመመደብ ተሳትፎ እንዳደረገ አንስተው  የደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጽ/ቤት እና የፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት ሥልጠናው በታቀደለት መልኩ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለሠልጣኞቹ አባታዊ የአገልግሎት መመሪያ የሰጡት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ  በጠረፋማ አካባቢ ያለውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መደገፍ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሁሉም አካላት ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባው ገልጸው የደብሩ አስተዳደር እና ሰ/ት/ቤት ያከናወኑት ተግባር ሊበረታታ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ሥልጠናውን ለተከታተሉ ተተኪ መምህራን የመጽሐፍ ቅዱስ እና የምስክር ወረቀት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

27 Dec, 18:15


https://youtu.be/bOcSlhDkmIU?si=dJX_34VijzXi6dXR

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

19 Dec, 18:32


“የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል መሪ ቃል ከኅዳር ፲፭ እስከ ታኅሣሥ ፴ ቀን  ፳፻፲፯ ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያና የስጦታ ዘመቻ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ተገለጸ::

የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ወልደ እግዚአብሔር ፍጹም ሰው ሆኖ ዓለሙን ለማዳን መምጣቱን አሕዛብ ዓይተው ያመኑበት ዕለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሰብአሰገል ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ እጅ መንሻ ያቀረቡት በዚህ ታላቅ ዕለት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ምእመናን በጾመ ነቢያት “የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶችን ይደግፉ ዘንድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተሰናድቷል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማት እና በአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ የሚያከናውናቸውን ፕሮጀክቶች ለማጠናከር “የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል መሪ ቃል ከኅዳር ፲፭  እስከ ታኅሣሥ ፴ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መርሐ ግብር እያካሄደ እንደሆነ ማስተባበሪያው ቀደም ሲል ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

የስጦታ መርሐ ግብሩም ከ፳፻፲፬ ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን የ፳፻፲፯ ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል “ስጦታዬን ለእራሴ” ሳይሉ ሁለ ነገራቸውን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰጥተው ለሚያገለግሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ገዳማውያን እንድናበርክት ማስተባበሪያው ጥሪ ያስተላልፋል፡፡

ማኅበሩ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የሚኖሩ ምእመናንን በማስተባበር በገዳማትና በአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ ከመቶ ስልሳ አምስት በላይ ፕሮጀክቶችን መተግበር እንደቻለና በዚህም በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ማፍራት እንዲሁም ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች እንዲጠናከሩ ማድረጉ ይታወቃል።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

18 Dec, 13:33


በጌዲኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል እና የአብነት ትምህርት አገልግሎቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ምክክር ተከናወነ።

በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ  መምህር ዋሲሁን በላይ የተመራ ልዑክ ከጌዲኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ እና ከሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደርጓል።

በዲላ ከተማ በተደረገው ውይይት ማኅበረ ቅዱሳን በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ብፁዕነታችው በውይይቱ ላይ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት ማድረጉ እጅግ እንዳስደሰታቸው የተናገሩ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ በተጠናከረ ሁኔታ ለቤተ ክርስቲያን እና ለምዕመናን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም የአቅም ውስንነት አለበት ብለዋል።

ብፁዕነታቸው ጨምረው እንደተናገሩት ማኅበሩ አሁን በሀገረ ስብከቱ ሊያከናውናቸው ያሰባቸው ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

በዕለቱ ብፁዕነታቸው  በሀገረ ስብከቱ የተከናወኑ ተግባራትን ለልዑካኑ ያስጎበኙ ሲሆን ማኅበሩ በሀገረ ስብከቱ የመጀመርያ የሆነና በ2018 ዓ.ም ለሚያስገነባው የአብነት ትምህርት ቤት የሚሆን 450 ካሬ ሜትር ቦታ መዘጋጀቱን አረጋግጠዋል።

በማኅበረ ቅዱሳን  የደቡብ ማእከላት ማስተባበርያ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ቀሲስ አሰፋ በበኩላቸው  ብፁዕነታቸው ወደ ሀገረ ስብከቱ ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ገልጸው በተለይም በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉ ሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት እየዞሩ በመመልከት የተዘጉት እንዲከፈቱ አድርገዋል ብለዋል።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

14 Dec, 15:55


https://youtu.be/YlIf2QpqqEs?si=0taogJi9lxwXERMd

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

08 Dec, 16:17


በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን ምዕራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተቋማዊ ምክክር እየተካሄደ ይገኛል።

ተቋማዊ ምክክሩ በማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን ምዕራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሥር የሚገኙ ማእከላት በዋናው ማእከል የሀገር ውስጥ ማእከላት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

የባሕር ዳር ማእከል፣ የግልገል በለስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራና ደብረ ታቦርን ያካተተው ይህ መርሐ ግብር ከማኅበረ ቅዱሳን አዲሱ መዋቅራዊ ለውጥ አኳያ የማእከላትን የአፈጻጸም አቅም ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተጠቅሷል።

የማእከላቱን ሥራ አስፈጻሚዎች የሥልጠና መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ኅዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመ/ር ዋስይሁን በላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ተላልፏል።

መ/ር ዋስይሁን በላይ በመልእክታቸው ከዓለም ተለዋዋጭ ባሕርይ እና ቤተ ክርስቲያን ካለባት ጫና አንጻር ማኅበሩ ዘመኑን የሚዋጅ መዋቅራዊ ለውጥ ማድረግ እንደነበረበትና በዚህም በማኅበረ ቅዱሳን አባላትና መዋቅር፣ በግቢ ጉባኤያት፣ በሰ/ት/ቤቶች እና በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚጠበቁ የለውጥ ታሳቢዎችን ጠቁመዋል።

መርሐ ግብሩ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

05 Dec, 05:48


Now is Giving Season. The $25 you donate to Mahibere Kidusan can
•  help some soul become an Ethiopian Orthodox Tewahedo believer
•  prevent someone from dying from hunger
•  energize the now-Deacon to become the future ArchBishop
•  help a lot of people hear the word of God
•  shield our children here in USA from the rising worldly noise
Please spare few seconds and donate just $25 so that the services that rely on these donations resume as planned. Small money, but big impact, even bigger blessing.
When you donate, make sure to change the tip amount to 0.
https://t.me/mahbere_kidusan
"ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" ሐዋ 20፡35
https://www.every.org/mkus/f/2024-giving-tuesday

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

02 Dec, 10:42


“ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ” በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡


በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ወደ ቀደመ ነገር እንመለስ በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር በደብረ ሰላም ቦሌ መድኃኔዓለም እና መጥምቀ መለኮት ቤተ ክርስቲያን በትላንትናው ዕለት አከናውኗል፡፡


በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ የማኅበሩ የሥራ አመራር አባላት እና ከ2000 በላይ የአዲስ አበባ ማእከል አባላት ታድመዋል፡፡


በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ኃ/ማርያም መድኅን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ  “ አዲስ አበባ ማእከል በተቋማዊ ለውጡ ትግበራ መሠረት የጀመረውን አዲሱን መዋቅራዊ አደረጃጀት ውጤታማ ለማድረግ ቀዳሚው ተግባር የአባላትን አገልግሎት ማጠናከር ነው” ብለዋል፡፡  ቀጥለውም “ አባላት ቃል ኪዳናቸውን አድሰው የአገልግሎት ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወደ ማኅበሩ ሲቀላቀሉ የገቡትን ቃል ሊፈጽሙ ይገባል “ ሲሉ የአጽንዖት መልዕክታቸውን አስተላለፍዋል፡፡


የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ በዕለቱ ለተገኙ ታዳሚዎች ስለ ጉባኤው ዓላማ እና የአባላት ድርሻን በተመለከተ “የአባላት የአገልግሎት በር” በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን አባላት በተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ተሳትፏቸው የጎላ እንዲሆን የሚሳተፉባቸው የአገልግሎት አማራጭ በሮች ክፍት ሁነው እንደሚጠብቋቸውና ገብተው እንዲያገለግሉ አማራጭ የአገልግሎት በሮችን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

02 Dec, 10:42


በዚሁ የአባላት ልዩ መርሐ ግብር ላይ በመ/ር ብርሃኑ አድማስ " እግዚአብሔርን ማየት" በሚል ትምህርተ ወንጌል፣ በቀ/ዶ/ር ይቻለዋል ጎሽሜ የማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ፈተናዎችና ጉዞን በተመለከተ ልምድ የማካፈል እና  በቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ ብርሃኑ እና በዘማሪት ብዙዓየሁ ተክሉ የመዝሙር  መርሐ ግብራት ተከናውነዋል፡፡


በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አማካኝነት “እርፍ ይዞ ወደ ኋላ የለም፣ ማኅበራችሁን ጠብቁ ፣በገባችሁት ቃል መሠረት ቤተ ክርስቲያናችሁን አገልግሉ፡፡” በሚል አባታዊ ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

22 Nov, 07:00


"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር


በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማጽኛ  መርሐ ግብር

በዕለቱም፦

👉 የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ማስጀመሪያ ልዩ መርሐ ግብር ይካሄዳል
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች ይቀርባል
👉 በተቋማዊ ለውጡ ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች ጥናት ይቀርባል
👉 እንዲሁም ሌሎች ከአባላት ጋር የተያያዙ መርሐ ግብራት ይከናወናሉ።

እርስዎም በማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

መረጃውን ለሌሎች አባላት በማጋራት የአገልግሎት ግዴታዎን ይወጡ!

ቀን፡ ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ

ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990

"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

17 Nov, 03:52


" ..በዚህ ወቅት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በስፋት የሚሰማውን ብልሹ አሠራር ማረምና ለቀጣዩ አገልግሎት መልክ ማስያዝ የካህናቱ ትልቅ ድርሻ ነው፡ ፡ ፡"#ሐመር መጽሔት
ሐመር መጽሔት #የኀዳር ወር ዕትም በሁሉም የማኅበሩ ሱቆች ትገኛለች
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦#ኀዳር ፳፻፲፯ ዓ.ም ቁ.፲ ፩
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል #በየወሩ የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

17 Nov, 03:52


• ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር -፲፩ ኀዳር ፳፻፲፯ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ “#እናንተ ግን የሌቦችና የቀማኞች ዋሻ አደረጋችሁት፤” በሚል ዐቢይ ርእስ በሁሉም መስክ ከወሬ ባለፈ ብልሹ አሠራርንና ዘረኝነትን በተግባር የሚፀየፍ አገልጋይ በታሰበው መጠንና ፍጥነት መፍጠር እንዳልተቻለ ፤በተቀደሰው ሥፍራ የጥፋት ርኵሰትን ማከናወን ሊቋቋሙት የማይችሉትን የእግዚአብሔር ቍጣ በራስ ላይ መጥራት ነው።
ሲገሠጹም ከመመለስ ይልቅ ለምን ታወቀብኝ ብሎ ሌላ በደል ለመጨመር መሯሯጣቸውና የእግዚአብሔርን ትዕግሥት መፈታተን መሆኑን አለመረዳታቸው ደግሞ ሌላው ጉዳይ እንደሆነ ፤ ችግር ዳር ሆኖ በማውራት፣ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በማንሸራሸር፣ ከንፈር በመምጠጥና በተናጠልም እዚህም እዚያም በማለት የሚፈታ እንዳልሆነ ልንገነዘብና ሁላችንም ተገቢውን ሥራ ልንሠራ እንደሚገባ ፤ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለአጥፊዎች መከታ፣ ሽፋንና ዋሻ የሆኑ አካላትም ከእነርሱ ጋር ከተሳሰሩበት ምድራዊ ማሰሪያ ይልቅ አባታቸው እግዚአብሔርና እናታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደምትበልጥባቸው አስታውሰው አካሄዳቸውን በማስተካከል ከእውነት ጐን እንዲቆሙ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
. #ዐውደ ስብከት ሥር ‹‹ወዳጄ በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ ነሽ››(መኃ.፪፥፪) በሚልርእስ ከመዝሙራት ሁሉ በሚበልጥ መዝሙሩ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ቅዱሳን ጻድቃን ስለ እውነተኞቹ ምእመናን (ክርስቲያኖች)፣ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር ወዘተ. የተናገረው ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ትንቢቱን ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር ተናግሮታል፡ መሆኑን ያሳያል።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ (ዕብ.፲፫፥፰)" በሚል ዐቢይ ርእስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን በኦሪት፣በነቢያት ፣በወንጌል፣ እንዴት እንደምስብከው ሰፊ ትምህርት ይሰጣል፡፡ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዓተ አምልኮቷ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በልዩ ልዩ መልኩ ታስረዳለች።
በሥርዓተ ቅዳሴዋ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን እንደምትሰብከው ሁሉ ሥርዓተ ቅዳሴዋን እና ማኅሌት በምትፈጽምባቸው ንዋየ ቅድሳትም ትሰብከዋለች ።ቤተ ክርስቲያንን ሳያውቋት ሰዎች ስሟን እንዲሁ እናጠፋለን ብለው የሚያስቡበትን ልቡናቸውን ሽህ ጊዜ እንደገና መልሰው መላልሰው ሊያስቡበት ይገባል ። ይህን ሁሉ ቤተክርስቲያን ስታስተምር እየታየች ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ አታስተምርም ማለት ባላዩት ምስክር መሆን፤ ለራሱ ሳያውቅ እኔ ላሳውቅህ ማለትና ከአንተ ይልቅ እኔ ስለ አንተ አዋቂ ነኝ እንደ ማለት ይቆጠራል፡፡
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “‹‹ወይሠረዉ መፍቀርያነ ወርቅ፤ ወርቅን የሚወዱ ይነቀሉ›› (ቅዳሴ እግዚእ ቁ.፭) በሚል ዐቢይ ርእስ የወቅቱ የቤተ ክህነታችን ፈተና በጥልቀት ትዳስሳለች ።በአሁኑ ዘመን አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ባለሥልጣናት እንደ መንፈሳዊ መሪነት ሚናቸውን መወጣት ተስኗቸው እንደሚታዩ በመረጃ ትሞግታለች፡፡አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን መሪዎች ብዙውን ጊዜ ከእግዚአብሔር አገልጋይነት ይልቅ እንደ ምድራዊ ምንደኛ፣ እንደ ፖለቲከኛ፣ እንደ ቢዝነስ ሰው ያለ የአካሄድ ዝንባሌን የሚያሳዩም መኖራቸውን ትጠቁማለች፡፡
በተለይ ገንዘብን በመሰብሰብና በማከማቸት ጥማት የታወሩትን ዛሬ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፈተና ሆነውብኛል ብላ እስከ ማወጅ ደርሳለች፡፡-አንዳንድ የቤተ ክህነቱ ባለሥልጣናት የቅድስት ቤተክርስቲያን የመንፈሳዊ ኃላፊነት ቦታዎችን፣ የአገልጋዮችን ቦታ ገንዘብ ለሚሹ ሰዎች በገንዘብ የሚሸጡ እየተበራከቱ እንደሆነ በመረጃ ትሞግታለች፡፡-በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት መደቦችንና የክህነትን ሥልጣን እንደ ቢዝነስ የሥራ መደቦችን የመሸጥ እና የመግዛት አካሄድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ እየፈተናት ነው፡፡
የካህናት ቅጥርና ዝውውር፣ ስእለትና የምጽዋት ገንዘብ አስተዳደር፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰበሰበችው ገንዘብ የምታውልበት ዓላማ፣ የጥቂት አገልጋዮች ማካበት የብዙ አገልጋይ ካህናት መጎስቆል፣ የገንዘቡ አወጣጥና አገባብ፣ በግንባታ ሥራዎች ላይ ያለው የግዢና የገንዘብ አወጣጥ ሥርዓት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የኪራይ ቤቶች አስተዳደር፣ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማቀላጠፊያ ብለው የሚሰጡት ገንዘብ የሚተዳደርበት መንገድ፣ የቤተ ክህነቱ የአገልግሎት መደቦች ስያሜና ቁጥር፣ የንዋየ ቅድሳት አስተዳደር ጥያቄ፣ የሚነሣበት እየሆነ መምጣቱን ታሳያለች ፡፡ ሙሉውን #ከመጽሔቱ ይነበብ
#ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ጭንቀት ክፍል_፪ "በሚል ርእስ መጋቤ ሐዲስ #አእምሮ ደምሴ #የኳታር ጸርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ መ/ር ደግሞ መንፈሳዊ ጭንቀት ስለሰማያዊው እና ዘለዓለማዊው ሕይወት መጨነቅና ማሰብ እንደሆነ በጥልቀት ያስተምራሉ፡፡ከመንፈሳዊ ጭንቀቶች ስቀምጣሉ፡፡ ሙሉውን ከሐመር መጽሔት ታገኛላችሁ፡፡
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “ከገነተ ልዑል እስከ መንበረ ልዑል”በሚል ዐቢይ ርእስ በሚል ርእስ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረቱ ምክንያቶችና የአመሠራረት ሁኔታውን የሰንበትትምህርት ቤቱ አመሠራረት፣ የሊቃውንት አሻራ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም የምረቃ መጽሔትን በምንጭነት በመጠቀም ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳውያን ምሩቃን ለቤተ ክርስቲያን ያላቸው አስተዋፅኦ" በሚል ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በመላው ዓለም በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግቢ ጉባኤያትን በመመሥረት ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ ዶግማ እና ቀኖና እንዲሁም ሥርዓት እንዲያውቁ፣ ራሳቸውንም ከክፉ ነገር በመጠበቅ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ማነጽ እንዲችሉ አገልገሎቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ያሳያል ። የግቢ ጉባኤ ተመራቂዎች ከምረቃ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ያላቸው ድርሻ ዘርፈ ብዙ ቢሆንም ዓበይት የሆኑትን ሐመር መጽሔት ታስቃኛለች፡:
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "#በፍላጻ የተወጋ ልብ-ክፍል ፩ "በሚል እጅብ ባሉ ሀገር በቀል የተፈጥሮ ዛፎች በተከበበ ዐፀደ ቤተክርስቲያን ውስጥ መጸለይ እጅግ ይወዳል፡፡ ከዚያ ውጣ ውጣ አያሰኘውም፡፡ አንድ ቀን እንደልማዱ ሲጸልይ ቆይቶ ጸሎቱን ሲያበቃ ከአንድ ዛፍ ሥር አረፍ አለ፡፡ እጅግ የሚያስደስት መዐዛ ቢያውደው የትመጣውን ለማወቅ ከአንገቱ ተቃንቶ ዙሪያውን ሊቃኝ ጀመረ በማለት ግሩም የኪነጥበብ ጹሑፍ ታስነብባለች ።
• #በጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምዳችን “ወርኀ ጽጌን” ክፍል አንድን በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ ይሰጡን ዘንድ መጋቤ ሐዲስ ተስፋ ሚካኤል ታከለን በወርኃ ጥቅምት ዝግጅታችን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ቀጣይና የመጨረሻውን ክፍል ደግሞ ጌታ ወደ ግብፅ የተሰደደበት ምክንያት ለምንድ ነው?

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

11 Nov, 12:58


https://youtu.be/kvRLNvnTUaE

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

11 Nov, 03:13


የማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማእከል በከተማው ከሚገኙ የመንፈሳውያን ማኅበራት ኅብረት እና ከሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር የደም ልገሳ እና የጽዳት መርሐ ግብር አከናወነ።

ኅዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም የማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማእከል ከመንፈሳውያን ማኅበራት ኅብረት እና ከሰ/ት/ቤት አንደንት ጋር በመተባበር በከተማዋ ሠፊ ንቅናቄ የተደረገበት የጽዳት እና የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናውኗል።

የአዳማ ከተማ መስተዳደር እና የከተማው  ደም ባንክ ጋር በተባባሪነት በተሳተፉበት የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ አቶ በሪሶ ዶሪ የአዳማ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ ሀብታሙ ግዛው የአዳማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ም/ኃላፊ እና አቶ ኤልያስ ታደሰ የአዳማ ከተማ ጸጥታ ዘርፍ እና የሃይማኖቶች ጉዳይ ኃላፊን ጨምሮ  ከ2000 በላይ  የአዳማ ማእከል አባላት፣ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች ፤የአዳማ ከተማ የሰ/ት/ቤቶች አባላት እና በአዳማ ከተማ የሚገኙ የመንፈሳውያን ማኅበራት አባላት ተገኘተው ደም ለግሰዋል።

" መልካም ሥራ ለመሥራት አንታክት" ገላ 6፥9 በሚል መሪ ቃል የተከናወነው መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ የሚያሳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።

ማህበረ ቅዱሳን
..
የሰማነውን እንናገራልርን ያየነውን እንመሰክራለን!
Offical Telegram page
https://t.me/mahbere_kidusan

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

02 Nov, 22:58


https://youtu.be/Idq7NOKxml0

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

28 Oct, 14:46


በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል የኢንዲያና ግንኙነት ጣቢያ 5ተኛውን ሐዊረ ሕይወት አካሄደ::

የግንኙነት ጣቢያው ጽ/ቤት እንደገለጸው መነሻውን ከኢንዲያና ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በማድረግ ቺካጎ ወደሚገኘው የደብረ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ. ም በኢንዲያና ዙሪያ የሚገኙ ከ185 በላይ ምእመናንን ያሳተፈ መንፈሳዊ ጉዞ አካሂዷል።

በዕለቱ ምክረ አበውና በርካታ መርሐ ግብራት መከናወናቸው የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም ክርስቲያናዊ ቤተሰብ ምን መምሰል እንዳለበት የሕይወት ልምድና ትምህርት ተሰጥቷል ተብሏል፡፡

በመርሐ ግብሩ የአሜሪካ ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባልና አቅም ማጎልበቻና የሰው ሀብት ዋና ክፍል ኀላፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ፍስሐ እሸቱ፣ የኢንዲያና ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ቀሲስ ንጉሤ ገብሬ፣ ሰባኬ ወንጌል ብርሃኑ አድማስ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ኢንዲያና ግንኙነት ጣቢያ አባላት እንዲሁም ምእመናን ተገኝተዋል፡፡

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

23 Oct, 09:20


https://youtu.be/92zEkENM-RY

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

23 Oct, 09:20


https://youtu.be/92zEkENM-RY

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

23 Oct, 09:20


https://youtu.be/fw2-29_zQ1s

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

22 Oct, 11:08


https://youtu.be/wYVM2hfhbm0

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

19 Oct, 18:54


የማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማእከል ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ዩኒቨርስቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የሽኝት መርሐ ግብር አከናወነ፡፡

በመርሐ ግብሩ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሲገቡ ስለሚጠበቅባቸው አካላዊ እና መንፈሳዊ ዝግጅት ሰፋ ያለ ምክር የተሰጣቸው ሲሆን 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በመጨረሻም በከፍተኛ ት/ት ተቋም በሚኖራቸው ቆይታ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው እና ጎን ለጎን በግቢ ጉባኤ የሚሰጠውን መንፈሳዊ ትምህርት በመከታተል በሁለት መልኩ የተሳለ ሰይፍ መሆን እንዲችሉ የአዳራ መልዕክት ተሰጥቷቸዋል፡፡

#subscribe eotcmk telegram channel
@mahbere_kidusan

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

17 Oct, 07:41


https://youtu.be/oQG_3UV6Drg

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

11 Oct, 17:24


https://youtu.be/5MTvIDSaKWY

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

09 Oct, 17:04


https://youtu.be/vY6lF-hcBLs

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

09 Oct, 14:01


ሐመር መጽሔት በጥቅምት ወር እትሟ!

✍️".....በዚህ ዓመት  ምን ያህል ገንዘብ ፈሰስ አደረገ ከሚለው ይልቅ በዚህ ዓመት ስንት ነፍስ በንስሓ አተረፍን? ስንት የሥላሴ ልጆችን በጥምቀት አፈራን  ወይም ቅድስት  ቤተ ክርስቲያን ስንት ኢአማንያንን በጥምቀት ወለደች??  ...."✍️ #ሐመር #መጽሔት ዐቢይ ጉዳይ ጥቅምት  ፳፻፲፯ ዓ.ም  )
                      ༺ ༻ 
#የኅትመት ዘመን ፦#ጥቅምት ፳፻፲፯ ዓ.ም ቁ.፲ 
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል #በየወሩ የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል  በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

09 Oct, 14:01


ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር -፲ ጥቅምት ፳፻፲ ፯ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ "#የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ነባራዊ ሁኔታ የሚረዳ፣ ከሥጋትም የሚታደግ ትውልድ እናፍራ "በሚለል ዐቢይ ርእስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የደረሰባትን ፈተና ሁሉ እያለፈች ዛሬ ላይ የደረሰችው ከእግዚአብሔር ጥበቃ ጋር የዘመኑን ፍልስፍና ተረድተውና ዘመኑን ዋጅተው ሃይማኖትን ከሥነ ምግባር ጋር አዋሕደው ይዘው ጠላት ዲያብሎስ የሚዋጉ ጠንካራ አባቶች ስለነበሯት ነው፡፡ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካትና ለህልውናዋ የሚተጋ፣ ሁለንተናዊ ዕድገትን የተላበሰ ትውልድ ለማፍራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ መሥራትም ጊዜ የማይሰጠው ተግባር መሆኑን መረዳት ይገባል። በማኅበረ ቅዱሳን ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተስተዋለውን የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች ተሳትፎ በማጠንከር እና የየማዕከላቱ ተወካዮች በተለያየ ችግር ውስጥ ሁነው ሳላ ስለ አገልግሎት ለመመካከር ብዙ ነገሮችን ተቋቁመው መምጣታቸው፣ለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመናበብ ማገልገል ከማኅበረ ቅዱሳን የሚጠበቅ ተግባር ነው ። ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ ከአባቶቹ መመሪያ እየተቀበለ ለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መጠናከርና ተደራሽነት እያደረገ ያለውን ጥረት ከአሁኑ በተጠናከረና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ማከናወን ይጠበቅበታል።"በማለት ታስነብባለች።

.#ዐውደ ስብከት ሥር” #ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊት ” በሚል ርእስ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ሰፊ ጽንሰ ሐሳብ ያለው ከመሆኑ የተነሣ በአጭር ዐረፍተ ነገር ለመግለጽ አስቸጋሪ እንደሆነ ያሳያል ። ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን አንዲት፣ ጋራ ተራራ፣ ድንበር ወሰን፣ ቋንቋ፣ ዘርና ቀለም የማይገድባት ዓለም ዐቀፋዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት፣ ሰላማዊት፣ እና ርትዕት ናት፡፡ “ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ” ነት ከዓለም ፈጣሪና መጋቢ ከልዑል እግዚአብሔር እና ካከበራቸው ቅዱሳን ጋር አሁን በረድኤት ኋላም በመንግሥተ ሰማያት በክብር መንግሥቱ አብሮ መኖር ማለት መሆኑን ያሳያል።

#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# "ዘመነ ጽጌ " በሚል ዐቢይ ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ #ደጀኔ ሺፈራው #የደንቨር ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ይህን ወቅት(ዘመነ ጽጌን) ቤተ ክርስቲያን:-እመቤታችንን በምድር አንድም በአበባ፥ተወዳጅ ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስንም በአበባ አንድም በፍሬ እየመሰለች ዘመነ ስደታቸውን በየዓመቱ በማኅሌት፥ በቅዳሴ በመዝሙርና በትምህርት በልዩ ኹኔታ ታስበዋለች።የሚፈጸመውም አገልግሎት ለጊዜው ዘመነ ጽጌ ምነው ባላለቀ የሚያሰኝ፥ ለፍጻሜው ደግሞ የከርሞው መቼ በደረሰ የሚያስብል አገልግሎት እንዳላት ያስተምራሉ ።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#ለመማከር ተሰበሰቡ "በሚል ዐቢይ ርእስ ብፁዓን አባቶችም ከሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚቀርበው ሪፖርት ምን ያህል በአደራ የተቀበሏቸውን የክርስቶስን ግልገሎች ጠቦቶችንና፣ በጎችን የማገልገል ጉዳይ ሆኖ ቀርቧል የሚለውን ነጥብ ይፈትሻሉ፡፡ ከዚህ ያፈነገጠ ሪፖርት፣ ዕቅድ፣ ውሳኔና አቋም ሁሉ ብፁዓን አባቶች የሚመሯትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንደማይመለከት በግልጽ ያሳያሉ፡፡ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሪፖርትም ለዚህ በአደራ የተሰጣቸውን ከባድ ኃላፊነት መወጣት የሚያስችል ምላሽ የሚሰጥ መሆን ይገባዋል፡፡ በዚህ ጉባኤ ከሚገኙት የሪፖርት ምላሽ ተነስተው አባቶቻችን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን አጀንዳ ይቀርጻሉ፡፡

አገልጋዮች ለአገልግሎታቸው ምን ዓይነት ማነቆዎች አጋጠሟቸው? የትኞቹስ ቀኖናዊ መፍትሔ የሚፈልጉ ናቸው? የትኞቹ በጸሎት የሚፈቱ ናቸው? የትኞቹ በምክርና ተግሣጽ የሚፈቱ ናቸው? …ወዘተ ብሎ በዓይነትና በመልክ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡
• #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ጭንቀት ክፍል_ ፩ "በሚል ርእስ መጋቤ ሐዲስ #አእምሮ ደምሴ #የኳታር ጸርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ መ/ር ደግሞ ሥጋዊ ጭንቀት፦ከልብ የሚመነጭ በሕሊና የሚወጣና የሚወርድ ፣በረቂቁ አእምሯችን የሚመላለስ ፣ በሐሳብ መሥመር የሚንቀሳቀስ፣ በሕሊና ቦይ የሚፈስ፣ ለጉዳት የሚያጋልጥ ነው። ጭንቀት፦ ክብደቱና ቅለቱ ይለያያል እንጂ በሁሉም ሰው ላይ የሚታይና የሚገለጽ ነው።ጭነቀትት ፦ መጠኑ ከሚገባው በላይ እየጨመረ ከሄደ ሰውነትን የሚያዛባ፣ አእምሮን የሚያቀውስ፣ ሕሊናን የሚያዘነጋ፣ ራስን እስከመጣል የሚያደርስ፣ ከቤተሰብ፣ ከትዳር፣ ከጓደኛ፣ ከጎረቤት፣ ከማኀበራዊ ኑሮ የሚለይ ፣ በብቸኝነት መኖርን እንዲመርጡ የሚያደርግ፣ ከፍ ሲልም ተስፋ እስከ መቁረጥ የሚያደርስ አደገኛ እንደሆነ በጹሑፋቸው ይጠቁማሉ። ስማችን፣ አለባበሳችን፣ ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ ነገር ግን ከኦርቶዶክሳዊነት ውጭ በሆነ እሳቤ ብዙ ጉድለቶች እንዳሉብን ያሳያሉ ።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የምሥራቅ አፍሪካ ፈርጥ #ናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን " በሚል ርእስ በኬንያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረቱ ምክንያቶችና የአመሠራረት ሁኔታውን ፣የናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ፣ በአብነት ትምህርት ፣ የደብሯን የሰበካ ጉባኤ የልማት እንቅስቃሴ ፤በሰንበት ትምህርት ቤት እና በየዘመናቱ የነበሩ ተግዳሮቶች ፣ወቅታዊጉዳዩች፣ የናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ልዩ የሚያደርጉት ጉዳዮችን ፣-በደብሩ የሚገኙት የሰበካ ጉባኤ አባላት ፣የሰንበት ት/ቤት አባላትና በማኀበረ ቅዱሳን የኬንያ ማእከል አባላት በፍጹም አንድነት ያለ ምንም ልዩነት አገልግሎት የሚሰጥበት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፣ የናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መልካም አጋጣሚዎችን ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር "ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ሚና _ክፍል ፪ " በሚል ስብከተ ወንጌላችን ተደራሽ እንዲሆን ምን መደረግ እንዳለበት የተወሰኑ ነጥቦችን ያነሳል ።ተልዕኮ ተኮር የስብከት ዘዴን መከተል ፤የቋንቋ እንቅፋትን ማስወገድ፣ በቦታ ያልተገደደበ አገልግሎት መስጠት ይገባናል ።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "# ትንሣኤ_፪ "በሚል ታስነብባለች ።
• # በጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምዳችን “ወርኃ ጽጌን ክፍል -፩ ” በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ ይሰጡን ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል የሆኑትን መጋቤ ሐዲስ #ተስፋ ሚካኤል ታከለ ጋር የተደረገውን ምልልስ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፲ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ!!
#subscribe eotcmk telegram channel
@mahbere_kidusan

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

09 Oct, 12:35


https://youtu.be/BQ_bngvtS_U

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

09 Oct, 12:35


https://youtu.be/LXouaEUcx38

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

06 Oct, 19:37


"ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር፡፡"

ሰቆቃወ ድንግል

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

04 Oct, 08:18


አደራ አለብኝ!

ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

የ2017 ዓ.ም 1 ኛ ዙር ቨርቹዋል ጉባኤ

ቀን፡ መስከረም 26/2017 ዓ.ም

ሰዓት፡ ምሽት 2፡00-3፡00

ሁሌም በየወሩ በግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ዓለም አቀፍ ኅብረት የቴሌግራም ቻናል

https://t.me/gibigubayat_mirukan_hibret

ማህበረ ቅዱሳን Mhbere kidusan

01 Oct, 09:44


ዜና
https://youtu.be/kWmTBOgtv6g?si=24WYvATqjNw8R9bi

10,096

subscribers

1,248

photos

62

videos