አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙 @adinunnesiha Channel on Telegram

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

@adinunnesiha

በአዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM የሚተላለፉ ፕሮግራሞች።
የዕለቱ 3ቱ ሀዲሶች
✍️የዕለቱ ዉድ መልዕክት
✍️ማለዳ መልዕክት
✍️ሀዲስ
✍️ሶሂህ ቡኻሪ ሀዲሶች
✍️የተለያዩ የነብያት ታሪኮች
✍️ቁርአን
✍️ማለዳ live የቁርአን ግብዣ

ሀሳብ አስተያየታችሁን ለማድረስ 👇
@anwu6

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM (Amharic)

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM በከባቢያው በመሆን የሚተላለፉ ፕሮግራሞች። ይህ ፕሮግራሞች የዕለቱ 3ቱ ሀዲሶችን እና የዕለቱ መልዕክትን በመለየት እንዲሰጥና በሶሂህ ቡኻሪ ሀዲሶችን ከሰላም እና አዳዲስ መሰረት የተለያዩ የነብያት ታሪኮችን በበቀል ማለዳ መልዕክት በመጠቀም እንዲሰጣና ቁርአንን በመጠቀም ማለዳ live የቁርአን ግብዣ ለሆነ። በስልክ በመላክም እና በመልቀም ከሆነ ሀሳብ ተያይተናል፡፡ እዚህ t.me/anwu6 እና t.me/adinunnesihabot ላይ ይመልከቱ።

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

10 Jan, 08:01

➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች‼️
==============
ክፍል:-298
❶) «ከሱረተል ካህፍ መጀመሪያ አስር አንቀፆችን የሸመደደ ሰው ከደጃል ተጠበቀ»።
ﻣﻦ ﺣﻔِﻆ ﻋﺸﺮَ ﺁﻳﺎﺕٍ ﻣﻦ ﺃﻭﻝِ ﺳﻮﺭﺓِ ﺍﻟﻜﻬﻒ، ﻋُﺼِﻢَ ﻣﻦ ﺍﻟﺪَّﺟَّﺎﻝِ.
ምንጭ:-📒ሰሒሁ ሙስሊም (809)

❷) «ሱረተል ካህፍን ያነበበ ሰው እስከ ቂያማ እለት ድረስ ብርሀን ትሆንለታለች ካለበት ቦታ እስከ መካ ድረስ የሚደርስ ከመጨረሻዋ አስር አንቀፆችን ያነበበ ሰው ከዛም ደጃል ቢወጣ አይጎዳውም»።
ﻣﻦ ﻗﺮﺃ ﺳﻮﺭﺓَ ﺍﻟﻜﻬﻒِ ﻛﺎﻧﺖ ﻟﻪ ﻧﻮﺭًﺍ ﺇﻟﻰ ﻳﻮﻡِ ﺍﻟﻘﻴﺎﻣﺔِ ، ﻣﻦ ﻣﻘﺎﻣِﻪ ﺇﻟﻰ ﻣﻜﺔَ، ﻭﻣﻦ ﻗﺮﺃ ﻋﺸﺮَ ﺁﻳﺎﺕٍ ﻣﻦ ﺁﺧﺮِﻫﺎ ﺛﻢ ﺧﺮﺝ ﺍﻟﺪﺟﺎﻝُ ﻟﻢ ﻳﻀﺮُّﻩ،
📒ሰሒህ አት-ተርጊብ ላይ አልባኒ ሰሂህ ብሎታል (225)

➌) «ጁምአ ቀን ላይ ሱረተል ካህፍን ያነበበ ሰው በሁለቱ ጁምአዎች መሀከል ብርሀን ያበራለታል»።
ﻣﻦ ﻗﺮﺃ ﺳﻮﺭﺓَ ﺍﻟﻜﻬﻒِ ﻓﻲ ﻳﻮﻡِ ﺍﻟﺠﻤﻌﺔِ ﺃﺿﺎﺀ ﻟﻪ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﻮﺭِ ﻣﺎ ﺑﻴﻦ ﺍﻟﺠﻤُﻌَﺘَﻴﻦ
📒ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎﻣﻊ: (6470)
#ወሰላሙዓለይኩም
==============
#ሼር_አድርጉት‼️
https://t.me/adinunnesiha
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

10 Jan, 05:00

አሏሁ'መ ሶሊ ወሲሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሀመድ‼️
*
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.»
||
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/qurann_channel
https://t.me/qurann_channel

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

09 Jan, 18:30

Live stream finished (27 minutes)

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

09 Jan, 18:02

Live stream started

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

09 Jan, 17:52

ደርስ ከተወሰነ ደይቃ ብሀላ እንጀምራል

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

09 Jan, 14:55

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ኢንሻ አላህ ዛሬ ማታ 3:00 ሰአት ላይ ኪታባችንን ካቆምንበት እንቀጥልለን።

ሸር ሸር እያደረጋችሁ እንገናኝ

@Adinunnesiha
@Adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

08 Jan, 18:29

Live stream finished (31 minutes)

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

08 Jan, 17:58

Live stream started

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

08 Jan, 17:37

ኢንሻ አላህ ዛሬ ደርስ ይጀመራል 3 ሰዐት ላይ

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

07 Jan, 18:49

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

እንደተባለው ዛሬ በአላህ ፍቃድ ማታ ይሄ ኪታብ ይጀመራል የሚቀራው ከ3:00 እስከ 3:30 ነው በሳምንት ሁለት ቀን

የሚቀራበት ቻናል

https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

07 Jan, 14:09

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ዉድ እህት ወንድሞች አንድ ነገር ላስቸግራችሁ ሁላችንም የአቅማችንን እንተጋገዝ አንድ አባታችን የሚበሉት የሚጠጡት አጥተዉ ቤት ከተኙ ወራት ተቆጥረዋል ሀቂቃ ያሳዝናሉ ትልቅ አባት ናቸዉ አፍ አዉጥተዉ እራበኝ የምበላዉ አጣሁ እያሉ ነዉ ። ችግር ተወርቶ አያልቅ ብዙ ነዉ በረሀብ መሞት ደግሞ እኛ እያለን እማይሆን ነገር ነዉ
ትልቅ ሰዉ ናቸዉ ቤት ዉለዋል ረሃብ ህመም ጋር ተጨምሮ በጣም ያሳዝናሉ አንጀታቸዉ ታጥፎ ነዉ የሚዉለዉ ።

ለጊዜዉ የተወሰነ ነገር የአቅማችንን እንተጋገዝ እና እናድርግላቸዉ አቅም ያላችሁ በዉስጥ አናግሩኝ ።

#ያለንን_እንተጋገዝ_ግዴታ_ትልቅ_ነገር_መሆን_የለበትም_የሁላችንም_ሲደመር_ብዙ_ነገር_ያደርጋል

inbox :- @Anwu6

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

07 Jan, 14:09

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙 pinned «السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ደርሱ እስከሚጀመር ወደ ግሩፕ ሰው አድ እናድርግ ሐሙስ እንጀምራለን በአላህ ፍቃድ»

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

07 Jan, 13:32

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ደርሱ እስከሚጀመር ወደ ግሩፕ ሰው አድ እናድርግ ሐሙስ እንጀምራለን በአላህ ፍቃድ

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

07 Jan, 11:06

Share አቡ ሙሰየብ ሃምዛ حفظه الله's song

《የሴት ልጅ ሂጃብ እና ሓያዕ 》:

ይደመጥ
t.me/Adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

07 Jan, 08:14

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙 pinned «السلام عليكم ورحمة الله وبركاته በዚህ ቻናል ደርስ ሊጀመር ነው አላህ ካለ እሲኪ ሀሳብ አሳውቁን»

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

07 Jan, 08:14

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙 pinned «እሺ ኢንሻአላህ በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል አዱሩሱል ሙሂማ ይጀመራ ደርሱ የሚሰጠው በሳምንት 2 ቀን ይሆናል»

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

07 Jan, 04:34

እሺ ኢንሻአላህ በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል አዱሩሱል ሙሂማ ይጀመራ ደርሱ የሚሰጠው በሳምንት 2 ቀን ይሆናል

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

06 Jan, 12:21

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

በዚህ ቻናል ደርስ ሊጀመር ነው አላህ ካለ እሲኪ ሀሳብ አሳውቁን

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

04 Jan, 14:08

ያ አላህ መስጅደል ሀረም እንዴት ያምራል

ወደቤትህ ጥራን ሀጅ እና ኡምራ የምናደርግበት ልብና አቅም ስጠን ወደ ቤትህም ጥራን ያረብ

@Adinunnesiha
@Adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

31 Dec, 20:04

«በላጭ ስራ የሚባለው ፣ ውስጥን "ከጥላቻና ከምቀኝነት" ንፁህ ማድረግ ነው»።

ኢብኑ ረጀብ

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

30 Dec, 06:49

➩የቀኑ 3ቱ ሐዲሶች‼️
==============
ክፍል:-297
1) «መንገድ ለጠፋበት ሰው መንገዱን ማመላከት ሰደቃ ነው»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
📒ቲርሚዚ ዘግበውታል

2) «ከቤት ሁሉ ምርጥ ቤት ብሎ ማለት የቲሞች የሚስተናገዱበት ቤት ነው»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
📒ቡኻሪ ዘግበውታል

3) «እድለኛ ሰው ብሎ ማለት በላዕ ደርሶበት የታገሰ (ሶብር) ያደረገ ነው»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:-📒ሶሒሁል ጃሚዕ (1637)

||
ሼር‼️
ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ👇
https://t.me/adinunnesiha
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

26 Dec, 19:48

ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«በሰጋጅ ፊት ለፊት የሚያልፍ ሰው ከወንጀል በርሱ ላይ ያለበትን ቢያውቅ፤ በሰጋጁ ፊት ለፊት ከማለፍ 40 ቢቆም ለርሱ በተሻለው ነበር።»

ቡኻሪ (510)

@Adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

25 Dec, 07:04

➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል:- 296
1) ''ከአቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና)  እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ'' :–
[ አደራን ለሰጠህ ሰው መልስ ፣ የከዳህን ሰው አትክዳ።]
             📚ቲርሚዚ ዘግበውታል።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏:
      [ أَدِّ الأَمَانَةَ إِلَى مَنِ ائْتَمَنَكَ وَلاَ تَخُنْ مَنْ خَانَكَ]
      
2) ''ከአቢ-ደርዳእ (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)  እንዲህ  አሉ'':-
[በቂያማ ቀን በአማኙ ሚዛን ላይ ከመልካም ስነ-ምግባር የበለጠ የሚከብድ ነገር የለም። አላህም ፀያፍ ቃላትን የሚናገሩ፣ መጥፎ(የሚናገሩ እና የሚሰሩ) ሰዎችን ይጠላል።]
              📚ቲርሚዚ ዘግበውታል።
عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏:-
[ما من شيءٍ أثقلُ في ميزانِ المؤمنِ يومَ القيامةِ من خُلقٍ حسنٍ وإنَّ اللهَ يُبغضُ الفاحشَ البذيءَ]

3) ''ከዐብደላህ ቢን ዐባስ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው  እንዲህ አሉ'':-
"የአላህ መልእክተኛ ( ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሴቶችን የሚመሳሱሉ ወንዶችንና ወንዶችን የሚመሳሰሉ ሴቶችን ረግመዋል።"
             📚ቡኻሪ ዘግበውታል።
عن ابنِ عبَّاسٍ رضي اللَّه عَنْهُما قَالَ:-
"لَعَنَ رَسولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ المُتَشَبِّهِينَ مِنَ الرِّجَالِ بالنِّسَاءِ، والمُتَشَبِّهَاتِ مِنَ النِّسَاءِ بالرِّجَالِ"          
||
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

25 Dec, 03:42

ከትልቅ የሰደቃ አይነታዎች‼️

ነብዩ (ሶለሏሁ ​​ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
ليس صدقة أعظم أجرا من ماء.
«ውሃ ከማቅረብ የበለጠ ምንዳ ያለው ሶደቃ የለም።»

[ሶሒሕ አት-ተርጚብ (2/566)]

@Adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

22 Dec, 08:01

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ከዚህ ብሀላ በዚህ ግሩፕ በሳምንት 2 ቀን ደርስ ይኖራል አስከዛው አድ እያደረጋችሁ

https://t.me/qurann_group

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

22 Dec, 06:14

«ሙስሊሞችን የሚያስደስት ነገር ያላስደሰተው እንዲሁም እነርሱን የሚያስከፋ ነገር ያላስከፋው "ከነርሱ አይደለም»።

ኢብኑ ተይሚያ( ረሂመሁሏህ)

ምንጭ፦📚አል ፈታዋ (10-128)

@Adinunnesiha
@Adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

21 Dec, 19:01

«በሁሉም ነገር ላይ ሶብር (ትእግስት) ይኑርህ።»

ረሱል (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም)

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

20 Dec, 03:59

አል-ጁሙዓ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬
አሏሁ'መ ሶሊ ወሲሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሀመድ‼️
*
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.»

@Adinunnesiha
@Adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

15 Dec, 12:42

«ሰኞና ሀሙስ የጀነት በሮች ዘወትር ይከፈታሉ፣ በነዚህ ቀናቶች በአላህ ላይ ለማያጋሩ ሰወች ሁሉ ወንጀላቸው ይማርላቸዋል፣ ለተጣሉ ሰወች ሲቀር እነዚህ እስኪታረቁ ጠብቋቸው ይባላል»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
📒ሙስሊም ዘግበውታል

ሼር‼️
ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ👇
https://t.me/adinunnesiha
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

12 Dec, 13:44

💐💐ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💐💐

🔘ባለን ዕውቀት ወደ ዲን መጣራት በሚል ርዕስ፡

🔈በወንድም ኢብኑ ያሲን  [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።

ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00
🔜ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡

📱 https://t.me/tewhedandsuna

⭐️በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

09 Dec, 18:57

«የዲን መሰረቶች 2 ናቸው እነርሱም "በመልካም ነገር ማዘዝና ከመጥፎ ነገር መከልከል" ናቸው ፣ የመልካም ነገሮች ሁሉ ዋና ደግሞ ተውሒድ ሲሆን የመጥፎ ነገሮች ሁሉ ዋና ደግሞ ሽርክ ነው።
ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁሏህ)

ምንጭ:-📚አል ጀዋቡል ባሒር (327)

@Adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

06 Dec, 19:17

«ባሪያዬ! እየተራመደ ወደ'ኔ ሲመጣ፤ እኔ በፍጥነት እየገሰገስኩ ወደርሱ እጓዛለሁ።» ሶ/ጃሚዕ (8136)
ومن أتاني يمشي أتيته هرولة.
በማንኛውም ጊዜ ወደ አላህ ለመጓዝ ትግል አድርግ። በምታደርጋት ዚክር፣ በምትሰግዳት ሱና ሶላት ላይ፣ በምትሰጣት ሰደቃ፣ በምታደርጋት ዱዓ፣ በምታነባት ተጨማሪህ አንቀጽ፣ በምትሰራት ትንሽ መልካም ስራ ላይ፤ ወደ ጌታህ መቃረብህን ጨምር።
-
ተቀምጠህም ሆነ ቆማህ፣ ከሰዎችም ጋር ሆንክ ለብቻህ፣ ሁኔታህ ምንም ይሁን ምን፤ በምትችለው ዒባዳ ሁሉ ወደ አላህ ለመቅረብ ጥረት አድርግ።
ወደ ጌታህ መጓዝህን አታቋርጥ።

ምክንያቱም፦
ወደ ጌታው መቅረብን ያቋረጠ፣ ወደ አላህ መምጣት ያቆመ፤ አላህም ወደ እርሱ አልመጣለትምና። 

እርሱን በመቅረብ፣ እርሱን በማውሳት፣ እርሱን በመታዘዝ፤ ደስታ ሳይሆን ሀሴትን ያቀዳጃልና። 

አላህን የመፍራት ውበቱ ከይቀጣኛል ስጋት ሲያልፍ፤ ከይገ'ባዋል ባይነት ልብ ውስጥ ሲመነጭም ነውና።

አላህ ኸይራትን ኹሉ ገር ያ'ርግልን።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/adinunnesiha
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

06 Dec, 06:15

Telegram premium and stars big discount - 1month premium available.
ቴሌግራም ፕሪምየም እና ግፍት ስታር መግዛት ለምትፈልጉ ።

1month premium
3month premium
6month premium
12month premium

Buyers dm here   @anwu6

50stars
100star
500star
1000star

Buyers dm here @anwu6

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

04 Dec, 06:28

ነፍስ ከአካል የተዋሃደችውን ያህል ይህ የአላህ ኪዳን በልቦናዎች ማሕደር ውስጥ ቢሰርጽ፤ ልሳኖች ጌታቸውን ከማውሳት ባልተቆጠቡ ነበር። ሱብሓነ`ሏህ!
فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ
«አስታውሰኝ፤ አስታውሳችኋለሁ!»
ከጌታ ወደ ባሪያ የተጣለ ምን ውብ ያማረ ጥሪ ነው!?
-
ኢብኑል ቀይ'ዩም (ረሒመሁ-ሏህ) እንዲህ ይላሉ፦
«አላህን መዝከር በእርሱና በባሪያው መካከል ያለው ትልቁ የተከፈተ በር ነው። ባሪያው በመዘ'ናጋት ራሱ እስካልዘጋው ድረስ።»
‏قال الإمام ابن القيم رحمه الله تعالى:
الذكر هو باب الله الأعظم المفتوح بينه وبين عبده مالم يغلقه العبد بغفلته.
📚መዳሪጁ ሳሊኪን (2/4764)

@Adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

02 Dec, 07:13

የጀነት በሮች እና ትርጉማቸዉ

@adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

29 Nov, 19:07

اللهم صلي وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم تسليما كثيرا

اللهم صلي وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم تسليما كثيرا

اللهم صلي وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم تسليما كثيرا

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

27 Nov, 17:42

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

የዚህ ቻናል አላማ አንዳንድ ጠቃሚ ጠቃሚ ምክሮች የሚለቀቅበት ሲሆን

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የሰዉ ልጅ ዘንጊ ነዉ እና ስለ ድናችንም የምንተዋወስበት ቻናል ነዉ።

صلاة الله مع سلامه على خير خلقه محمد ابن عبد الله وعلى آله وأصحاه وكل من اهتدى بهديه

https://t.me/bin_muzemil_reshid

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

27 Nov, 12:43

ሁሉም ስለ ትዳር ያወራል ይመክራል ወሳኙ ነገር ማውራት ሳይሆን ማግባት ነው

አግባ አግባ ከምትሉኝ ዳሩኝ አለ አንዱ

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

27 Nov, 12:41

አንዳንድ ጊዜ ብቻህን ትሆን እና ታስባለህ ሁሉንም ነገር ማረግ የምችል ይመስለሀል:: ነገር ግን የሰው ልጅ ነህ ብዙ ቀዳዳ እና ጎደሎ አለብህ ያነገር ማድረግ ሳችል ስቀር በጣም ታዝናለህ ልብህ ይሰበራል ነገር ግን አስታውስ አላህ ለአንተ ኸይር የሆነውን ነገር ብቻ ነው የሚመርጥልህ:: ነብዩላህ አዩብ አለይሂ ሰላም 18 አመት ሲታመሙ ሰብርን ተምረዋል ስለዚህ ያ ነገር ኸይር ሆኖ ወደ አንተ እስኪመጣ ድረስ ሰብር አድርግ ሰብር የሙእሚን ትልቁ ጋሻ ነው::

📱ابن شيخ أحمد منور

https://t.me/Ibbn_Sheikh_Ahmed_Munawer

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

12 Nov, 17:22

➩የቀኑ 3ቱ ሐዲሶች‼️
==============
ክፍል:-297
1) «መንገድ ለጠፋበት ሰው መንገዱን ማመላከት ሰደቃ ነው»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
📒ቲርሚዚ ዘግበውታል

2) «ከቤት ሁሉ ምርጥ ቤት ብሎ ማለት የቲሞች የሚስተናገዱበት ቤት ነው»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
📒ቡኻሪ ዘግበውታል

3) «እድለኛ ሰው ብሎ ማለት በላዕ ደርሶበት የታገሰ (ሶብር) ያደረገ ነው»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:-📒ሶሒሁል ጃሚዕ (1637)

https://t.me/adinunnesiha
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

12 Nov, 17:19

أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ يُعَذِّبُ مَن يَشَاءُ وَيَغْفِرُ لِمَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ۝
የሰማያትና የምድር ንግሥና የሱ (የአላህ) ብቻ መኾኑን አላወቅክምን የሚሻውን ሰው ይቀጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ይምራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

📒አል-ማኢዳ'ህ (40)

@adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

11 Nov, 08:57

""የአላህ ራህመትና እዝነት ሼር ባደረገ ላይ ይሁን""

ይህ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ህጻን  ፊቱ ላይ በተለምዶ "ቁንጭር"የሚባል በሺታ ተከስቶበታል:: የሚያሳዝነዉ የሚያሳክም አለመገኘቱ ብቺ ሳይሆን እናቱም ሌላ ህፃን ልጅ በጀርባዋ ይዛለች  የሚገርመዉ  ነገር ልጁ ብቻ ሳይሆን እናቱም ትንሻ ህፃንም ተመሳሳይ የሆነ በሺታ ደርሶባቸዋል  የነሱ ግን ከንፈራቸዉ ላይ ብቻ በመሆኑ ለየት ያደርገዋል  3ቱንም ማሳከም ባንችል ልጁን እንደምንም ካሳከምን ለኛ ትልቅ ደስታ ነዉ በዛ ላይ የቲም ነዉ   እናቱ አይደለም ህክምና የሚበሉትና የሚጠጡት በጣም እንደተቸገሩ ነዉ የተነገረኝ  እናም እስኪ አምስትም አስርም ብለን በሺታዉ ሳይጎዳዉ በአላህ ይሁንብን እናሳክመዉ  "የመልካም ስራ ትንሽ የለዉም" የሚል በዉስጥ ያዉራኝ
0945719991
0965846673
👉  @Kedir_keta

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

08 Nov, 07:52

ሱረቱል ካህፍ

ረሱል እንዲህ ብለዋል፦

﴿من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَينِ﴾

“በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሀል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።”

ሶሂህ አልጃሚዕ=2470

https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

04 Nov, 09:16

ከአላህ ጋር ያለህ ግንኙነት ካማረ እና የአላህ ውዴታ ካገኝህ ሌላ ምን ትፈልጋለህ ወንድሜ!! ሁሉም ሰው ካልወደደኝ ወይ ሁሉም ሰው ካልተቀበለኝ ብለህ ችክ አትበል በጣም የሚወድህ እንዳለው ሁሉ ስላንተ ምንም ሳያቅ በዛው ልክ በጣም የሚጠላህ አለ:: አንተ በቻልከው መጠን ሰውን አትበድል የሰውን ሀቅ አትጋፋ ሌላው በቃ አለቀ የአላህን ውዴታ ለማግኘት ልፋ:: ስንት ወንድሞች አሉ ድሮ አበረሀቸው የነበርካቸው አሁን ላይ የተለያየሀቸው?

ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት መሞከር ግብ የሌለው አላማ ነው!!

💐 ኢማሙ ሻፊዒይ

📱 ابن شيخ أحمد منور

https://t.me/Ibbn_Sheikh_Ahmed_Munawer

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

31 Oct, 11:32

✔️ሶለዋት የምናወርደው እንዴት ነው⁉️
———
ከዕብ ቢን ዑጅረህ (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላል፦
إنَّ النبيَّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ خَرَجَ عَلَيْنَا،
فَقُلْنَا: يا رَسولَ اللَّهِ، قدْ عَلِمْنَا كيفَ نُسَلِّمُ عَلَيْكَ،
ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወደኛ መጡ። የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአንተ ላይ ሰላምታ እንዴት ማድረግ እንዳለብን አወቕን።
فَكيفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ؟
“ሶለዋት የምናወርደው'ስ እንዴት ነው?” ብለን ጠየቕናቸው።
قالَ: فَقُولوا
እንዲህ በማለትም አስተማሩን፦
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آل مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد.»
ምንጭ፦📒ሶሒሁል ቡኻሪ (6357)
“አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሐመድ”

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

30 Oct, 21:24

በሶላት ላይ የሚሳነፍ ሰው‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ሶላት በእስልምና ዋነኛው አላህ በባሮቹ ላይ የደነገገው ተግባር ነው። ውዱ ነቢያችን (ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙ ዓለይሂ) «የቂያማ ቀን የመጀመሪያው ሂሳብ ላይ የሚቀመጠው ሶላት ነው። ሶላቱ ጎደሎ የሆነ ስራው ሁሉ ይጎላል!» ብለዋል። ሶላት ዐቅል አስቦት፣ ዐይን አይቶት፣ ቀልብ ተመኝቶት የማያውቅ ፀጋ ያለበትን የጀነትን መንገድ ትመራለች።
-
ሶላት ላይ የሚሳነፍ ሰው ተከታዮቹን ዱዓዎች ያብዛ፦
رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ
➊) «ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ዱዓዬንም ተቀበለኝ።»
اللهم يامقلب القلوب ثبت قلبي على دينك.
➋) «ቀልብን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ! ቀልቤን ወደ ዲንህ ገልብጠው።»
اللهم إني أعُوذ بك من العجْز والكسل.
❸) «አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍና እና ከመታከት በአንተ እጠበቃለሁ።»
اللهم أعني على ذكرك و شكرك وحسن عبادتك.
❹) «አላህ ሆይ! አንተን በመዝከር፣ በማመስገን እና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።»
اللهم اجعل قرة عيني في الصلاة.
➎) «አላህ ሆይ! የዓይኔን ማረፊያ (እርካታዬን) በሶላት ውስጥ አድርግልኝ።»
||
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

28 Oct, 06:05

በቁርኣን እንተዎወስ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል፦295
የኣንድን ሰው ማንነት ከምንረዳበት ነገሮች መካከል ኣንዱ ነው። የኣረሕማን ባሪያ የመሆን ባሕሪ፣ የውብ ስብዕና መገለጫ፣ የማንነትና የዕሴት ነጸብራቅ፣ የስነ-ምግባር ሚዛን፤ መካከለኛ ኣረማመድ...

ወንድ ሲያወራ ድምፁን መቀነስ፤ ሴት ድምጿን ማስተካከልና መቀነስ ቁርኣናዊ ትዕዛዝ ነው። የወንድ ልጅ ኩራት ኣረማመዱ ላይ ሲሆን፤ የሴት ልጅ ከሩቕ ተጣሪ ክልክል-ውበት አነጋገሯና አረማመዷ ላይ ይንጠለጠላል።
√ አምላካችን አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፦
وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا ۖ إِنَّكَ لَن تَخْرِقَ الْأَرْضَ وَلَن تَبْلُغَ الْجِبَالَ طُولًا۝
«በምድርም ላይ የተንበጣረረክ ሆነህ፤ አትሂድ። አንተ ፈጽሞ ምድርን አትሰረጉድምና በርዝመትም ፈጽሞ ተራራዎችን አትደርስምና።»
📒ኢስራእ (37)
*
فَجَاءَتْهُ إِحْدَاهُمَا تَمْشِي عَلَى اسْتِحْيَاءٍ قَالَتْ إِنَّ أَبِي يَدْعُوكَ لِيَجْزِيَكَ أَجْرَ مَا سَقَيْتَ لَنَا ۚ ...
ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሓፍረት ጋር የምትኼድ ሆና መጣችው። «አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል» አለችው።
📒ቐሶስ (25)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

25 Oct, 18:38

ካስደነቁኝ አባባሎች

ተምረናል እንጂ አላወቅንም *

ተዋደናል እንጂ አልተፋቀርንም *

እናወራለን እንጂ አልተገበርንም *

እንሰብካለን እንጂ አልሰራንበትም *

እንሞክራለን እንጂ አልፈፀምንም *

እንስቃለን እንጂ አልተደሰትንም *

እናለቅሳለን እንጂ አላዘንም *

https://t.me/hajj_and_umrah_mosque

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

25 Oct, 09:13

ሶለዋት ➝ የአላህን እዝነት ያስገኛል‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ለአለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት በውዱ ነብያችን ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረድ በጁሙዓ ዕለት ከሚወደዱ ዒባዳዎች መካከል አንዱ ነው። ሶለዋት ሱና ብቻ ሳይሆን የአላህን ትእዛዝ መታዘዝ ብሎም፤ የቂያም ቀን የርሳቸውን አማልጅነት ማገኛም መንገድ ነው።
-
በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ የአላህን እዝነት ያስገኛል። አላህ ኸይር ነገር በርሳቸው ላይ አወረደ፤ እኛንም ከዚህ ኸይር ተጋሪዎች አደረገን። ኣንድ ሶለዋት ስናወርድ፤ አላህ በእኛ ላይ ዓስር ሶለዋት ያወርዳል። ከአላህ ዘንድ ለፍጥረታት የሚወ'ረድ ሶለዋት ደግሞ ከጨለማ ያወጣል። ብርሓንን ያስገኛል። የኣላህን እዝነትና ውዴታን ያጎናጽፋል።
*
በጁሙዓ ዕለት፣ ተሽሑድ ላይ፣ የርሳቸው ስም ሲነሳ፣ ኣዛን ሲባልና መስጅድ በምንገባበት ጊዜ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረዱ ይበልጥ ሙስተሓብ ከሚሆኑባቸው ወቅቶች ናቸው።

√ ሶለዋት አጭር ድካም ትልቅ ትርፍና የተነባበረ ፀጋ!
«በእኔ ላይ ኣንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ፤ አላህ በርሱ ላይ ዓስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:-📒ሙስሊም (384)
«مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلاَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا.»

√ ሶለዋት ከነብዩ ጋር በቀጥታ ሰላምታን ያስገኛል።
«ማንም ሰው ለእኔ ሰላምታ (ሶለዋት) ካደረገ፤ አላህ ሩሔን ይመልስና ሰላምታውን እመልስለታለሁ።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒ሶሒህ አቡ ዳውድ (2041)
«ما من أحدٍ يسلِّمُ عليَّ إلَّا ردَّ اللَّهُ عليَّ روحي حتَّى أردَّ عليْهِ السَّلامَ.»

√ በተቃራኒው ደግሞ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማድረግን የሰሰተ፤ በራሱ ላይ ኸይር ነገርን ከማግኘት ሰስቷል። በነፍሱ ላይ ነፍጓል።
ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦
«ስስታም ማለት ከርሱ ዘንድ እኔ እየተወሳሁ፤ በኔ ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነው።»
ምንጭ፦📒ሶሒሁ ቲርሚዚ (3546)
«البخيلُ الذي من ذُكِرْتُ عندَه فلم يُصَلِّ عليَّ.»

✔️ የሶለዋት ነገር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ አላህ ራሱ እኔ አወርዳለሁ፤ እናንተም ኣማኞች ሁሉ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርዱ የሚል ትዕዛዛዊ–መልክትን በቁርኣን ነግሯል።

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا۝
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
📒አል-ኣሕዛብ (56)
*
✔️ሶለዋት የምናወርደው እንዴት ነው⁉️
———
ከዕብ ቢን ዑጅረህ (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላል፦
إنَّ النبيَّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ خَرَجَ عَلَيْنَا،
فَقُلْنَا: يا رَسولَ اللَّهِ، قدْ عَلِمْنَا كيفَ نُسَلِّمُ عَلَيْكَ،
ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወደኛ መጡ። የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአንተ ላይ ሰላምታ እንዴት ማድረግ እንዳለብን አወቕን።
فَكيفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ؟
“ሶለዋት የምናወርደው'ስ እንዴት ነው?” ብለን ጠየቕናቸው።
قالَ: فَقُولوا
እንዲህ በማለትም አስተማሩን፦
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آل مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد.»
ምንጭ፦📒ሶሒሁል ቡኻሪ (6357)
“አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሐመድ”
||
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

21 Oct, 16:58

ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸው‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
በሐዲሥ የመጡ ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸው ሁነት፣ ቀንና ወቕቶች፦
①) ከውዱእ በኋላ፣
②) ሱጁድ ላይ፣
③) በእኩለ-ለሊት፣
④) የዓረፋ ቀን ላይ፣
⑤) ዝናብ ሲዘንብ፣
⑥) ፆመኛ ሲያፈጥር፣
⑦) ከፈርድ ሶላቶች በኋላ፣
⑧) ለሌሎች ዱዓ ስታደርጉ፣
⑨) የታመሙትን ሲትጎበኙ፣
⑩) በዩኑስ ዱዓ አላህን የለመነ፣
⑪) ከሓጅ ወይም ከዑምራ በኴላ፣
⑫) የዘምዘም ውሃ ከመጠጣት በፊት፣
⑬) በረመዷን በተለይ በለይለቱል ቀድር፣
⑭) በጁሙዓ ቀን ከዓስር ሶላት በኋላ፣
⑮) በአዛንና በኢቃም መካከል ባለው ጊዜ።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

20 Oct, 17:24

ሶላት ለሰው ልጅ ከአላህ በርሱ ወዴታና መሻት የተሰጠ ድንጋጌ ነው። ወደ አላህ ለሚደረግ ምስጋናም ሆነ ውዳሴ የማቅረብ ይዘት በሶላት ይካተታል። ሶላት የመጀመሪያው ሒሳብ፣ ብቸኛው የዝቅታ ከፍታ ነው። በተቃራኒው ችላ ባዩንም ያስጠይቃል።
-
ሶላት አላህን የመገናኛ መስመርም ነው። ወቅቶቹን ለጠበቀ የሁሉም መክፈቻ ቁልፍ። የስኬት ትልቁ መንገድ አላህን በብዙ ማስተውስ እንደሆነው፤ የኣንድ ሰው የውድቀት መጀመሪያው ደግሞ የአላህ ተጣሪ፣ እየተጣራ ሶላት ላይ መዘናጋቱ ነው።

ሶላት ረፍትም ነው። ልብ በሶላት ታርፋለች። በርሷ ውስጥ አላህን ሸክዋ ማድረግ አለ። ነፍስ በርሷ ትረጋ'ጋለች። ቀልብም ከዱንያ ድካም ታርፋለች።
ለዚያም أرحنا بها يا بلال «ቢላል! እስኪ አዛን በልና እንረፍ!» ይሉ ነበር። (ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም!)

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

15 Oct, 17:26

ኢብራሂም ኢብኑ አድሃም እንዲህ ይሉ ነበር
"ቤታችን ፊትለፊታችን ነው ህይወታችን ከሞት ቡሃላ ነው ወይ ወደ ጀነት ወይ ወደ እሳት"

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

30 Sep, 04:39

የነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ስሞች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«እኔ 5 ስሞች አሉኝ: እኔ ሙሐመድ ነኝ፣ እኔ አሕመድ ነኝ፣ እኔ ማሒ ነኝ አላህ እኔን በመላኩ ክህደትን የማስወግድ የማብስ፣ እኔ ሐሽር ነኝ ሰዎች ሁሉ ከእግሬ ስር የሚቀሰቀሱት፣ እኔ ዓቂብ ነኝ ከእኔ በኋላ ነቢይ የለም።»
«لِي خَمْسَةُ أسْماءٍ: أنا مُحَمَّدٌ، وأَحْمَدُ، وأنا الماحِي الذي يَمْحُو اللَّهُ بي الكُفْرَ، وأنا الحاشِرُ الذي يُحْشَرُ النَّاسُ علَى قَدَمِي، وأنا العاقِبُ الذي ليس بعده نبيٌّ.»

ምንጭ፦📒ሙስሊም (2354)

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

25 Sep, 19:27

قال ابن القيم رحمه الله تعالى

أعباد المسيح لنا سوال . . . نريد جوابه ممن وعاه
إذا مات الإله بصنع قوم . . . أماتوه فما هذا لإله
وهل بقي الوجود بلا إله . . . سميع يستجيب لمن دعاه
وكيف تخلت الأملاك عنه . . . بنصرهم وقد سمعوا بكاه
وكيف أطاقت الخشبات حمل . . .إله الحق مشدودا قفاه
وهل عاد المسيح إلى حياه . . . أم المحي له رب سواه
ويا عجبا لقبر ضم ربا . . . وأعجب منه بطن قد حواه
أقام هناك تسعا من شهور . . . لدى الظلمات من حيض غذاه
وشق الفرج مولودا صغيرا . . . ضعيفا فاتحا للثدي فاه
ويأكل ثم يشرب ثم يأتي . . . بلازم ذاك هل هذا إله
تعالى الله عن إفك النصارى . . . سيسأل كلهم عما افتراه

ኢብኑል ቀይም አላህይዘንላቸው እና እንዲህ ብለዋል

የመሲህ ባሮች ሆይ! አንድ ጥያቄ አለን . . . የተረዳው ካለ መልሱን እንሻለን
ጌታ ግፍ አቅቶት ሰዎች ከገደሉት . . . አለቀ አከተመ የታለ አምላክነት?
ፈጣሪዋን አታ አለም ስትዋትት . . . ሰው ወደ ማን ነበር የሚያስበው ፀሎት?
የሰማይ መላእክት ምነኛ ለጎሙ?! . . . እጁ ተቸንክሮ ዋይታውን ሲሰሙ?
እንጨቱም ተአምር ነው አቅሙ መቋቋሙ . . . የአምላክን ነገር ያክል ችሎ መሸከሙ
ኋላስ እራሱ ነቃ አንሰራራ? . . . ወይስ ጌታ አገኘ ሂወት የሚዘራ?
ጉድ በሉ ለቀብር ጌታ አቅፎ ለያዘ . . . የባሰም ሆድ አለ አምላክ ያረገዘ
ዘጠኝ ወር ሲኖር ገብቶ በጨለማ. . . ሀይድ እየተጋተ ደም እየተጠማ
ብልት ቀዶ ወጣ አብሻ ህፃኑ . . . አፉን ለጡት ከፍቶ አቤት ማሳዘኑ!
አስብ ይሄን አምላክ ሲጠጣ ሲበላ . . . ከዚያም ያስገባውን ሲያወጣ በሌላ
ጌታዬ ከፍ አለ ከነሷራ ቅጥፈት . . . ሁሉም ይጠየቃል በቀባጠረበት

https://t.me/Ibbn_Sheikh_Ahmed_Munawer

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

24 Sep, 11:14

ታላቅ ቅናሽ ‼️‼️

ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች በሙሉ ‼️

ቴሌግራም ስታር  (Star )
ቴሌግራም የፕሪሚየም 

መግዛት ለምትፈልጉ በታላቅ ቅናሽ መግዛት ትችላላችሁ

inbox:- @Anwu6

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

23 Sep, 18:49

የነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ስሞች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«እኔ 5 ስሞች አሉኝ: እኔ ሙሐመድ ነኝ፣ እኔ አሕመድ ነኝ፣ እኔ ማሒ ነኝ አላህ እኔን በመላኩ ክህደትን የማስወግድ የማብስ፣ እኔ ሐሽር ነኝ ሰዎች ሁሉ ከእግሬ ስር የሚቀሰቀሱት፣ እኔ ዓቂብ ነኝ ከእኔ በኋላ ነቢይ የለም።»
«لِي خَمْسَةُ أسْماءٍ: أنا مُحَمَّدٌ، وأَحْمَدُ، وأنا الماحِي الذي يَمْحُو اللَّهُ بي الكُفْرَ، وأنا الحاشِرُ الذي يُحْشَرُ النَّاسُ علَى قَدَمِي، وأنا العاقِبُ الذي ليس بعده نبيٌّ.»

ምንጭ፦📒ሙስሊም (2354)

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

22 Sep, 15:46

ከአላህ ደግ ባሮች መሀል አንዱ ሚስቱን መፍታት ፈለገና...
ምን ችግር ገጥሞህ ነው እሷን የምትፈታት? ተብለው
ተጠየቁ...
"አእምሮ ያለው ሰው የሚስቱን ገመና (አደባባይ)
አያወጣም!" አሉ።
ከተፋቱም በኋላ ለምንድነው የፈታሃት? ቢባሉ...
"ምን አገባኝና ስሌላሰው ሴት ሚስጥር ላውራ!"
ብለው መለሱላቸው።

https://t.me/Ibbn_Sheikh_Ahmed_Munawer

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

20 Sep, 07:49

ሶለዋት ➝ የአላህን እዝነት ያስገኛል‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ለአለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት በውዱ ነብያችን ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረድ በጁሙዓ ዕለት ከሚወደዱ ዒባዳዎች መካከል አንዱ ነው። ሶለዋት ሱና ብቻ ሳይሆን የአላህን ትእዛዝ መታዘዝ ብሎም፤ የቂያም ቀን የርሳቸውን አማልጅነት ማገኛም መንገድ ነው።
-
በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ የአላህን እዝነት ያስገኛል። አላህ ኸይር ነገር በርሳቸው ላይ አወረደ፤ እኛንም ከዚህ ኸይር ተጋሪዎች አደረገን። ኣንድ ሶለዋት ስናወርድ፤ አላህ በእኛ ላይ ዓስር ሶለዋት ያወርዳል። ከአላህ ዘንድ ለፍጥረታት የሚወ'ረድ ሶለዋት ደግሞ ከጨለማ ያወጣል። ብርሓንን ያስገኛል። የኣላህን እዝነትና ውዴታን ያጎናጽፋል።
*
በጁሙዓ ዕለት፣ ተሽሑድ ላይ፣ የርሳቸው ስም ሲነሳ፣ ኣዛን ሲባልና መስጅድ በምንገባበት ጊዜ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረዱ ይበልጥ ሙስተሓብ ከሚሆኑባቸው ወቅቶች ናቸው።

√ ሶለዋት አጭር ድካም ትልቅ ትርፍና የተነባበረ ፀጋ!
«በእኔ ላይ ኣንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ፤ አላህ በርሱ ላይ ዓስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:-📒ሙስሊም (384)
«مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلاَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا.»

√ ሶለዋት ከነብዩ ጋር በቀጥታ ሰላምታን ያስገኛል።
«ማንም ሰው ለእኔ ሰላምታ (ሶለዋት) ካደረገ፤ አላህ ሩሔን ይመልስና ሰላምታውን እመልስለታለሁ።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒ሶሒህ አቡ ዳውድ (2041)
«ما من أحدٍ يسلِّمُ عليَّ إلَّا ردَّ اللَّهُ عليَّ روحي حتَّى أردَّ عليْهِ السَّلامَ.»

√ በተቃራኒው ደግሞ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማድረግን የሰሰተ፤ በራሱ ላይ ኸይር ነገርን ከማግኘት ሰስቷል። በነፍሱ ላይ ነፍጓል።
ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦
«ስስታም ማለት ከርሱ ዘንድ እኔ እየተወሳሁ፤ በኔ ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነው።»
ምንጭ፦📒ሶሒሁ ቲርሚዚ (3546)
«البخيلُ الذي من ذُكِرْتُ عندَه فلم يُصَلِّ عليَّ.»

✔️ የሶለዋት ነገር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ አላህ ራሱ እኔ አወርዳለሁ፤ እናንተም ኣማኞች ሁሉ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርዱ የሚል ትዕዛዛዊ–መልክትን በቁርኣን ነግሯል።

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا۝
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
📒አል-ኣሕዛብ (56)
*
✔️ሶለዋት የምናወርደው እንዴት ነው⁉️
———
ከዕብ ቢን ዑጅረህ (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላል፦
إنَّ النبيَّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ خَرَجَ عَلَيْنَا،
فَقُلْنَا: يا رَسولَ اللَّهِ، قدْ عَلِمْنَا كيفَ نُسَلِّمُ عَلَيْكَ،
ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወደኛ መጡ። የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአንተ ላይ ሰላምታ እንዴት ማድረግ እንዳለብን አወቕን።
فَكيفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ؟
“ሶለዋት የምናወርደው'ስ እንዴት ነው?” ብለን ጠየቕናቸው።
قالَ: فَقُولوا
እንዲህ በማለትም አስተማሩን፦
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آل مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد.»
ምንጭ፦📒ሶሒሁል ቡኻሪ (6357)
“አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሐመድ”
||
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

16 Sep, 18:50

«ሓቀኛዉ ሞት፣ መራሩ እዉነት ሲጎበኘን እንዳንረሳው ይመስላል። በቅርቧ እንዳንፈዝ፣ እንዳንደነዝዝ፤ ብቅ እያለ ያስታውሳል። ሰርክ ላይ ያለች ነፍስን ይመክራል። ሆኖም ስለሞት ያልታሰበበት ቀን ኩሉ ያሞኛል። ኳስ በመሬት እያለ ያነሆልላል። ይህችን ዓለም ጥቂቶች ብቻ ኣስታዋሽ ሆነው፤ ሕይወትን እንደ መንገድ በድር`ብቡ ይገፏታል፡፡»

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

13 Sep, 08:26

ሱረቱል ካህፍ

ረሱል እንዲህ ብለዋል፦

﴿من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَينِ﴾

“በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሀል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።”

ሶሂህ አልጃሚዕ=2470

https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

10 Sep, 13:38

ሰው ሰራሽ አስተውሎት‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Ai) ሕይወትን ለሰው ልጅ ቀላል፣ ምቹና ቀልጣፋ ከማድረጉ ባሻገር፤ ከዚህ በፊት ይታሰቡ የማይመስሉ ስራዎችን ማከናወኑን ቀጥሏል።
ኤ.አይ ያልገባባቸው የሕይወት ዘርፎች የሉም ማለት ይቀላል። በተቃራኒው ደግሞ Ai የሰውን ልጅ የማጥፋት አቅም ይዞ እየመጣም ይመስላል።

Ai ይዞልን (ይዞብን) እየመጣ ያለው የሰው ልጅ ውስጣዊ ሃይልን ወደ ውጫዊ ማሽናዊ ሕልውናዎች የመተካት አዲስ ዓለም ነው። ከጥቅሙ ጉዳቱ ማመዘኑ ከግዜ ወደ ግዜ እየሰፋ ይገኛል። አሁን አሁን እየመጡ ያሉ የቴክኖሎጅ ውጤቶች ሰው ጠል ናቸው።
-
ለዚህም ምዕራቡ ዓለም ላይ በAi ብቻ የሚንቀሳቀሱ አውቶነመስ ተሽከርካሪዎችን መመለከት በቂ ነው።

የAI እድገት በዚሁ ከቀጠለ ፍፃሜው የሚሆነው፤ አሁን ላይ የሰው ልጅ ደረስኩበት ያለውን ስልጣኔ በሙሉ ኤ.አይ አጥፍቶ፣ ጠቅልሎ ይውጠዋል።

√ አላህ ስለ አውሮፓውያን ሲናገር እንዲህ አለ፦
يَعْلَمُونَ ظَاهِرًا مِّنَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَهُمْ عَنِ الْآخِرَةِ هُمْ غَافِلُونَ۝
«ከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ፡፡ እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም እነርሱ ዘንጊዎች ናቸው፡፡»
አር-ሩም (7)
*
✔️አምላካችን አላህ እውነትን ተናገረ። አውሮፓዊያን አላህ ግልፅ ያደረገላቸውን ስለቅርቧ ዓለም የተወሰነውን ያውቃሉ። ነገር ግን ለምን እንደተፈጠሩ፣ ለምን ወደዚህች ዓለም እንደመጡ አያውቁም።

https://t.me/adinunnesiha
https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

07 Sep, 03:53

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ

ለ 2ኛ ጊዜ የመጣ የስራ እድል ማስታወቂያ ደሴ እና ኮምቦልቻ ላላችሁ ሰዎች

ለሁሉም ሰው የሚሆን ስራ ስለሆነ እድሉን እንድትጠቀሙበት ጋብዛችኋለው

ስለስራው ሙሉ መረጃ ለማወቅ በአካል ቢሮ በመገኝት ማወቅ ትችላላችሁ

+251923352602
+251914600685 ይደውሉ ።

  Telegram :- @anush6

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

26 Aug, 18:33

እረስተውት ነው መሰለኝ አድራሻውን አላስቀመጡም እባካቹህ አድራሻውን የምታውቁ ካላቹህ? ክክክክ

https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

24 Aug, 11:55

አል'ሐምዱሊ'ላህ ከ ወይዘሮ ስህን ፖሊክቴክኒክ ኮሌጅ  ዛሬ ተመረቅኩ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ዛሬ ዕለተ ቅዳሜ ነሀሴ 18, 2016 E.C በ   Mrs. Sehn Polik Technical College በታሪኩ ለ__ኛ ጊዜ ካስመረቃቸው 362 ተማሪዎች ውስጥ አንዱ ነኝ።
||
Mrs. Sehn Polik Technical College ውስጥ ላለፉት ሶስት አመታት በመደበኛው መርሃር hardwar and networking service (HNS) ሳጠና(ስሰለጥን)  ቆይቻለሁ፣ በእርሱም ፍቃድ ለዚህ ቀን በቅቻለሁ።

አዎ! በዚህ ዘመንም ተመረቅኩ!....
በሶስት አመታታት ጉዞ ያሳለፍኳቸውን ፈተናዎችና መሰናክሎች እንዳልፍ ያገራልኝ፣ ሶብሩን የሰጠኝ፣ አዛኙ ጌታዬ አሏህ ምስጋና የተገባህ ነህ አል'ሐምዱ'ሊላህ‼️
:
በመቀጠልም የምወዳችሁ ቤተሰቦቼ ዉዷ  እናቴ ዉድ ሚስቴ በኔ መደደት ለተደሰታችሁ  እንኳን ደስ አላችሁ።
እማዬ የኔ ዉድ ኦናት ! አንቺ ተፈትነሽ እኔ ተመረቅሁ። እናቴ በምን ቃል እንደምገልፅሽ አላውቅም። ከጎኔ ሆነሽ ደስታየን ብታይ ደስ ባለኝ ነበር። በአንዳንድ ምክንያቶች አብራኝ ባለመገኘቷ አዝኛለሁ ደግሞ አላህ ከፊያ ያርግሽ ያሽርሽ አብራኝ ባለመሆኗ አዝኛለሁ።
እናቴ ተመርቄልሻለሁ፣ ባለሽበት እንኳን ደስ አለሽ፣ ዛሬ ከኔ ጋር በአካል መገኘት ባትችይም ባለሽበት ደስታዬና ምስጋናዬ ይድረስሽ።

*
መንገዱ ረጅም ቢሆንም እስከዚህ ቀን ድረስ ያለፍኳቸውን ሸካራ ጉዞዎችና መሰናክሎች ሳስብ ለኔ ይህ ቀን ታላቅ ስኬት ነው።

በትምህርት ቆይታዬ በተለያዬ መልኩ ትብብር ስታደርጉልኝ የነበራችሁ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ለነገሩ የለም መሰል ብቻ  ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይር።
:
በመጨረሻም አላህ ከየትኛውም ዓለማዊና አኼራዊ ፈተና ጠብቆ ለኢስላምና ሙስሊሞች፣ ለመላው የሰው ልጅ፣ ለራሴ፣ ለቤተሰቤ፣ ለወገኔና ለሃገሬ ጠቃሚ እሆን ዘንድ በመልካም ዱዓችሁ አስታውሱኝ።
:
ሰበብ ባገኘሁ ቁጥር ወደኋላ እንዳልመለስ በማይናወጥ አብሮነቱ እያጠነከረ አደናቃፊ እንቅፋቶችን ሁሉ በፀጋዉ እያሳለፈኝ «ቀጥል ሒድ አይዞህ እኔ አለሁልህ!» እያለ ይህን የሕይወቴን ሌላ ምዕራፍ እንዳጠናቅቅ የረዳኝ አላህ ነውና፤

ጌታዬ አላህ ሆይ! ሁሉም የአንተ፣ ከአንተ ነውና፤ ከምንም በላይ ለዚህ ቀን ያበቃከኝ አዛኙ ጌታዬ፤ ምስጋና የተገባህ ነህ።
አል'ሐምዱ'ሊላህ‼️
*
ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ ﺍﻟﻤﻨﺎﻥ، ﺫﻭ ﺍﻟﻔﻀﻞ ﻭﺍﻹﺣﺴﺎﻥ
ﺍﻟﺬﻱ ﺧﻠﻖ ﻓﻌﻠَّﻢ ﻭﺟَﻌَﻞَ ﺑﻌﺪ ﺍﻟﻌﺴﺮ ﻳﺴﺮًﺍ ﻭﺟﻌﻞ ﺍﻟﺼﺒﺮ ﻣﻔﺘﺎﺡ ﺍﻟﻔﺮﺝ ﻭﺍﻟﻨﺠﺎﺡ ﺛﻤﺮﺓ ﺍﻟﺠﺪ ﻭﺍﻟﻌﻤﻞ... ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﺍﻟﺬﻱ ﺑﻨﻌﻤﺘﻪ ﺗﺘﻢ ﺻﺎﻟﺤﺎﺕ رَﻓَﻊَ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﺍﻣﻨﻮ ﻭﺍﻟﺬﻳﻦ ﺍﺗﻞ ﻋﻠﻢ ﺩﺭﺟﺎﺕ ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﺍﻟﻘﺎﺋﻞ ﻭﻣﻦ ﺍﺣﻴﺎ ﻧﺎﺱ ﺟﻤﻴﻊ
الحمد الله!
ዕለተ ነሀሴ ሰኔ 18, 2016 E.C
August 24,2024 G.C

Mrs. Sehn Polik Technical College፣
dessie ኢትዮጵያ፣
||
አንዋር መሀመድ ይመር

https://t.me/Anush_tube
https://t.me/Anush_tube

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

22 Aug, 19:45

💙ዛሬ ማታ ጁምዓ ነው በሃቢባችን ሰለዋት ማብዛት ደግሞ ትልቅ አጅር አለው እስኪ ገብታቹ ሰለዋት አውርዱ🤍

اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا ونبينا وحبيبنا محمد ﷺ

https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

22 Aug, 19:33

እስኪ ወደ ሗላ መለስ እንበል እና የኢስላም የሴቶች አለባበስ እንዴት እንደነበረ እንመልከት ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት በቱኒዚያ በ19 ክፈለ ዘመን ሁሉም ሴቶች የሚለብሱት አለባበስ ነበር በጊዜው ሴቶች በጣም ቁጥብ እና እራሳቸውን የሚጠብቁ ለወንድ ልጅ የፊትና በር የማይከፍቱ እና እራሳቸውን ከፊትና የሚጠብቁ ነበሩ ስለዚህ እህቶች ከድሮ ዘመን መለስ ብለን እስኪ እናስተንትን እና አሁን ያለንበትን ሁኔታ እናስብ ተገላልጦ መውጣት የእርድና ምልክት አይደለም እርድና ማለት የነብዩን ሱና መከተል ነው በሰለፍች ጊዜ አንድ ሴት ስትናገር ወላሂ እኔ ከባሌ ከአባቴ እና ከልጄ በስተቀር ማንም አይቶኝ አያቅም ትል ነበር ስለዚህ እህቶች የአላህን መንገድ እያሰብን!!!!

https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

16 Aug, 19:22

አረ ወጣቶች አግብ እህቶቻችን የመህሩን ነገር ቀለል አርጉ ነብዩ እንዳሉት አንዳንዴም ሲዋክ እና ቁርአን መህር ጠይቁን ቀልባችን ይደሰት እስኪ ምን ታስባላችሁ ንገሩን በሀሳብ እንተጋገዝ እና አራት አራት እናግባ እህቶችም ለሌሎች እህቶች አስብ እንረዳዳ😊😊😂

https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

15 Aug, 11:29

በፊትና ዘመን ለአንድ ወጣት ከሐጅ ይልቅ ማግባት ይበልጣል ይላሉ አል-ኢማም አል-ቡኻሪይ። በርግጥ አቅሙ ለቻለ ሐጅ ዋጂብ'ኮ ነው። ግን ፊትና ካለና ከትዳር ውጭ መቋቋም የማይችለው ፊትና ከሆነ ማግባቱ የበለጠ ይወጅበበታል።

الزواج للشباب في زمن الفتن، أوجب مـن الحج!

إذا كان الرجل يحتاج إلى الزواج ، ويشق عليه تأخيره فإنه يقدم الزواج على الحج .
أما إذا كان لا يحتاج إلى الزواج فإنه يقدم الحج .
قال ابن قدامة رحمه الله في "المغني" (5/12) :
وَإِنْ احْتَاجَ إلَى النِّكَاحِ , وَخَافَ عَلَى نَفْسِهِ الْعَنَتَ ( أي المشقة ) , قَدَّمَ التَّزْوِيجَ , لأَنَّهُ وَاجِبٌ عَلَيْهِ , وَلا غِنَى بِهِ عَنْهُ , فَهُوَ كَنَفَقَتِهِ , وَإِنْ لَمْ يَخَفْ , قَدَّمَ الْحَجَّ ; لأَنَّ النِّكَاحَ تَطَوُّعٌ , فَلا يُقَدَّمُ عَلَى الْحَجَّ الْوَاجِبِ اهـ . وانظر أيضاً : "المجموع" (7/71) للنووي .
وسئل الشيخ ابن عثيمن رحمه الله :
هل يجوز تأجيل الحج إلى ما بعد الزواج للمستطيع ، وذلك لما يقابل الشباب في هذا الزمن من المغريات والفتن صغيرة كانت أم كبيرة ؟
فأجاب :
لا شك أن الزواج مع الشهوة والإلحاح أولى من الحج لأن الإنسان إذا كانت لديه شهوة ملحة فإن تزوجه حينئذٍ من ضروريات حياته ، فهو مثل الأكل والشرب ، ولهذا يجوز لمن احتاج إلى الزواج وليس عنده مال أن يدفع إليه من الزكاة ما يُزوج به ، كما يعطى الفقير ما يقتات به وما يلبسه ويستر به عورته من الزكاة .
وعلى هذا فنقول : إنه إذا كان محتاجاً إلى النكاح فإنه يقدم النكاح على الحج لأن الله سبحانه وتعالى اشترط في وجوب الحج الاستطاعة فقال : ( وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنْ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلا ) آل عمران / 97 .
أما من كان شاباً ولا يهمه أن يتزوج هذا العام أو الذي بعده فإنه يقدم الحج لأنه ليس في ضرورة إلى تقديم النكاح اهـ
فتاوى منار الإسلام (2/375) .

https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

10 Aug, 20:30

ሰው ለመኝታ ጋደም ሲል ከራሱ ጋር ይፋጠጣል። ከተጨባጩ ጋር እውነተኛ ሆኖ ይቀርባል።
ድክመቴን፣ ክፍተቴን፣ ድልጠቴን፣ ጥፋቴ፣ እንከኔን ...ላንተ ተናዝዤ ያልተኛሁባቸው ምሽቶች ሁሉ የኔ አይደሉም ጌታዬ።
ሰዎች ድምፃችንን ይሰማሉ፣ ውጫችንን ያያሉ።
አንተ ግን ልቦናችንን ትሰማለህ፣ ውስጣችንን ታያለህ።
ወንጀላችን ብዙ
ጥፋታችንን በርካታ ነውና።

በእዝነትህ እየን፣ በምህረትህ ጎብኘን የኔ ጌታ።

ቲስበሑ ዐላ ኸይር

https://t.me/adinunnesiha

አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

10 Aug, 19:49

አካዉን ለምትፈልጉ

1000270144784

4,682

subscribers

1,121

photos

177

videos