Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር @ethiopiannationaltheatre Channel on Telegram

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

@ethiopiannationaltheatre


Weekly Programs

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር (Amharic)

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የቴሌግራም ቢሮዎችን አካባቢ ማስከበረት ይሆናል። በዚህ ቦታ በየአካባቢ ውስጥ ለአንዲነክ እና ሌሎች ወንጌላዌች የሚገኙ ቴሌግራም ቢሮዎችን ለማስከበር ዋጋ ስለሚችሉ መረጃዎችን ስናስተናግዷ እንዳለን። በቴሌግራም አራት የቴሌግራም ቢሮዎች እርምጃ ወይም እርምጃ ተደጋጋሚ አክሽን አካባቢዎች እና ተጠቃሚ አዳዲስ ቅንብሮችን በማግኘት ማስከበር ይችላል። ከዚህም ፕሮግራማችን በከተሞች ምላሽ አገልግላ።

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

26 Dec, 05:00


የፕሮግራም ለውጥ

ዛሬ ታህሳስ 17/2017 ምሽት 11:30 "ጎዶን ጥበቃ" ቴአትር የማይቀርብ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር እየገለጽን "የቅርብ ሩቅ" በተጠቀሰው ሰዓት እንደሚቀርብ በአክብሮት እናሳውቃለን።

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

08 Nov, 07:30


የፕሮግራም ማስተካከያ
ለክቡራን የኪነጥበብ ቤተሰቦች ዛሬ አርብ 11፡30 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሚቀርበው ‹‹ የሕይወት ታሪክ›› የተሰኘ አዲስ ቴአትር መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡


ደራሲና አዘጋጅ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕሮፌሰር) እና ቢኒያም ወርቁ
ፕሮዲውሰርና ረ/አዘጋጅ ቢኒያም እሸቱ

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

30 Oct, 08:49


🎭 የቅርብ ሩቅ 🎭

አዲስ ቴአትር
🕙 ዛሬ ረቡዕ ከምሽቱ በ11፡30

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

25 Oct, 05:17


በልዩ ፕሮግራም ዛሬ

ለክቡራን የኪነጥበብ ወዳጆች በሙሉ ዛሬ ጥቅምት 15ቀን 2017 ዕለተ አርብ ምሽት 11፡30 ‹‹እምዬ ብረቷ›› ቴአትር በልዩ ፕሮግራም ለተመልካቾች ይቀርባል፡፡

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

22 Oct, 10:56


🎭 የቅርብ ሩቅ 🎭

አዲስ ቴአትር
ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ/ም
ሰዓት 11፡30

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

16 Oct, 05:00


በቅርቡ ‹‹የቅርብ ሩቅ›› ቴአትር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፡ከጥቅምት 13 ጀምሮ
ዘወትር ረቡዕ በ11 ፡30

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

14 Sep, 05:23


በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባል።

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:30

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:30

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

05 Aug, 07:21


አዲስ ቴአትር በአፋን ኦሮሞ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
🎭🎭🎭

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለመጀመሪያ ጊዜ በአፋን ኦሮሞ የቀረበው ቴአትር በ1991 ዓ/ም ሲሆን የተውኔቱ ርዕስ "Dukkanaan Duuba" "ከጨለማው ጀርባ" ይሰኛል። ከዚያ በኋላ ጥቂት በአፋን ኦሮሞ የተጻፉ ቴአትሮች በቴአትር ቤቱ መድረክ ላይ የመታየት እድል አግኝተዋል፡፡

እነሆ ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ‹‹ወላቡ››የተሰኘ በአፋን ኦሮሞ የተዘጋጀ ቴአትር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይቀርብላችኋል፡፡ ሁላችሁም ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በቦታው ተገኝታችሁ እንድትመለከቱ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል።

ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ኑ ሁላችንም አብረን እንሰብሰብ!


በነገራችን ላይ በቅርቡ ከከንባታ ጠንባሮ ዞን ጋር በመተባበር በሀድይኛ ቋንቋ ‹‹ ኡቱፕያ ወጋ ››የተሰኘ እንዲሁም በሙርሲ ቋንቋ የተጻፈ‹‹ቲራኒያ_ኮ_ኮይሳ" ወይም "ዳኛው"...የተሰኙ ትውፊታዊ ቴአትሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መቅረባቸው ይታወሳል፡፡

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

01 Aug, 12:47


ዕለተ አርብ ከምሽቱ 11፡30

ከታላቁ ደራሲ ሎሪት ጸጋዬ ገ/መድሕን ሕያው ሥራ ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንገኛለን፡፡

እናንተስ?

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

01 Aug, 07:32


🎭 🎭 🎭
አዲስ ቴአትር በቅርብ ቀን

Ethiopian National Theatre የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

21 Jul, 07:07


ዛሬ እሁድ
8፡30 ‹‹ሸምጋይ››
11፡30 ‹‹እምዬ ብረቷ›› ኑ በጋራ እንመልከት፡፡

‹‹ሸምጋይ›› ቴአትር 8፡30 መታየቱ በጊዜ ቴአትር አይቶ በጊዜ ወደቤት ለመመለስ አጋጣሚው ጥሩ ነው፡፡
ብዙዎች ‹‹የሰአት ለውጥ ይደረግ ፤ምሽት ይመሻል ፤ትራንስፖርት አይገኝም ፤ቤታችን እሩቅ ነው፡፡››ላላችሁን ይህ ኣጋጣሚ ጥሩ ስለሆነ በቀትር‹‹ሸምጋይ›› ላይ እንገናኝ፡፡

‹‹ሸምጋይ›› ደራሲው ታደለ አያሌው ሲሆን አዘጋጁ ሁለገቡ አርቲስት ሳሙኤል ተስፋዬ. ነው። ይህ ታሪክ ቀመስ ትውፊታዊ ቴአትር በሰምና ወርቅ ንግግራቸው በበርካቶች ከሚታወቁትና ከሚደነቁት ከዘመን አይሽሬው ፈላስፋ ከአለቃ ገብረሃና ጋር ፊትለፊት ያገናኝዎታል።

ዛሬ ሳይመሽ በቀትር አለቃ ገብረሃናን ትኩር ብሎ ማየት ነው፡፡ እሳቸው አያልቅባቸው፡፡ ምን ይሉን ይሆን?

🎭የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር🎭