EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት) @effrefe Channel on Telegram

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

@effrefe


This is official telegram chanel of Ethiopian football federation refereeing department.

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት) (Amharic)

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት (EFF Refereeing Departement) ከፋና ብቃት ጋር በትምህርትም በጣም በክለቦች እና በእግር ኳስ ሰልፍ ለማስራራት ከጊዜ ጋር የሚሆኑ ዳኞችን ከታብዩ ደንበኞች ጋር በመዘገብና በመዝገበ ዝግጅት እንዲሰጥ እና መረጃዎችን እንሰጥቷል። በአጭር ፈቃድ የሚታይ ሊሆናቸው ከፈቃዱ በፊት ያልፋል፡፡ ይህ ከታብዩ ለማስራራት የዳኞች ዲፖርትመንት በተናገርኳን መሪ ህዳሳ ጸሃፊ የመስረት ጉዳይ ከሆነ፣ በትክክለኛ የስራ ችግር የሚሰጥ ጥያቄዎችን አገናኝ የሚሆን መረጃዎች ያለው የስማቸው እና ያልሆኑ፣ ለመሆኑ ያበረከተ ጥያቄዎች እና መረጃዎች በመሞከረነት ከተሞላቸው ሊኖሩ ይችላሉ። በዚህ ቦታ በዚህበለይ መረጃዎች እና ጸሃፊ ይሁኑ።

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

20 Nov, 10:04


ለ20 ዓመት በታች የጨዋታ አመራሮች
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

ከላይ ስማችሁ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተ የጨዋታ አመራሮች የ2017 ዓ/ም የመጀመሪያው ዙር የአካል ብቃት ፈተና የሚሰጠው ማክሰኞ በ17/03/2017 ዓ/ም በመሆኑ ከጠዋቱ በ12፡00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የጤና የምርመራ ውጤት ይዛችሁ በመምጣት ለባለሙያዎች ማረጋገጥ እና በዚያው ቀን 2፡00 ጀምሮ የአካል ብቃት ፈተና በመውሰድ በዚሁ ቀን ከቀኑ 6:00 ጀምሮ ወደፊት በምናሳዉቀው ቦታ ውይይት እና የውድድር ዝግጅት ገለፃ  ይሰጣል። ስለሆነም በተገለፀው አግባብ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ
ስማችሁ በዝርዝሩ ከተጠቀሰው ውጭ የምትመጡ የጨዋታ አመራሮችን የማናስተናግድ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንሰራለን”

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

06 Nov, 13:42


ለሊግ አንድ የጨዋታ አመራሮች
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

ከላይ ስማችሁ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተ የጨዋታ አመራሮች የ2017 ዓ/ም የመጀመሪያው ዙር የአካል ብቃት ፈተና የሚሰጠው ሐሙስ በ05/03/2017 ዓ/ም በመሆኑ ከጠዋቱ በ12፡00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የጤና የምርመራ ውጤት ይዛችሁ በመምጣት ለባለሙያዎች ማረጋገጥ እና በዚያው ቀን 2፡00 ጀምሮ የአካል ብቃት ፈተና በመውሰድ በዚሁ ቀን ከቀኑ 6:00 ጀምሮ ወደፊት በምናሳዉቀው ቦታ ውይይት እና የውድድር ዝግጅት ገለፃ  ይሰጣል። ስለሆነም በተገለፀው አግባብ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ
ስማችሁ በዝርዝሩ ከተጠቀሰው ውጭ የምትመጡ የጨዋታ አመራሮችን የማናስተናግድ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንሰራለን”

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

28 Oct, 08:00


ለሴት የጨዋታ አመራሮች
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

የ2017 ዓ/ም የመጀመሪያው ዙር የአካል ብቃት ፈተና የሚሰጠው አርብ በ22/02/2017 ዓ/ም በመሆኑ ከጠዋቱ በ12፡00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የጤና የምርመራ ውጤት ይዛችሁ በመምጣት ለባለሙያዎች ማረጋገጥ እና በዚያው ቀን 2፡00 ጀምሮ የአካል ብቃት ፈተና በመውሰድ በዚሁ ቀን ከቀኑ 6:00 ጀምሮ ወደፊት በምናሳዉቀው ቦታ ውይይት እና የውድድር ዝግጅት ገለፃ  ይሰጣል። ስለሆነም በተገለፀው አግባብ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ
በየትኛውም አካባቢ የምትገኙ አዲስ ሴት ፌደራል የጨዋታ አመራሮች ፈተናውን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ወጫችሁን በግላችሁ የምትሸፍኑ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንሰራለን”

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

19 Oct, 10:30


ለከፍተኛ ሊግ የጨዋታ አመራሮች
የአካል ብቃት ፈተና ቀን መቀየሩን ስለማሳወቅ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ቀደምሲል የአካል ብቃት ፈተና በ14/02/2017 ዓ/ም እንደሚሰጥ ማሳወቃችን ይታወቃል። ነገር ግን ቀኑን መቀየር ስላስፈለገ አርብ 15/02/2017 ዓ/ም መቀየሩን እያሳወቅን ሙሉ ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት በተገለፀው አግባብ የሚካሄድ መሆኑን እንገልፃለን



ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንሰራለን

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

18 Oct, 13:16


በጤና ምርመራ ውጤት ከዝርዝር ለተቀነሳችሁ ኮሚሽነሮች
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ለ2016 ዓ/ም ለውውድር የቅድመ ዝግጅት ስናደርግ በኮሚሽነሮች ዙሪያ ይስተዋሉ ከነበሩ ችግሮች በመነሳት የጤና ምርመራ የተደረገ እና በዚህም የጤና ምርመራውን ማለፍ ያልቻላችሁ ኮሚሽነሮች በውድድር አመቱ የኮሚሽነሮች ዝርዝር ላይ አለመካተታችሁ የሚታወስ ነው። በዚህ መሰረት በተለያዩ ጊዜያት ቅሬታ እያቀረባችሁ የቆያችሁ አና አሁንም ቅሬታችሁን የምታቀርብ መኖራችሁ ይታወቃል። ይሁን እንጅ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በቀረቡት ቅሬታዎች ላይ በሰፊው የተወያየባቸው ሲሆን መሰል ምዘናዎችን በየ ዓመቱ ለማከናዎን ከተለያዩ ጉዳዮች አንጻር አዋጭ አለመሆኑን ስለታመነበት የምዘና ፕሮግራሙን በየ ሁለት ዓመቱ የምናካሂድ መሆኑ ተወስኗል። ስለሆነም በዚህ ዓመት ለ2016 ዓ/ም የውድድር ዓመት ተደርጎ የነበረው የምዘና ውጤትን መሰረት ተደርጎ የሚሰራ ሲሆን ለ2018 ዓ/ም የውድድር ዓመት ዝግጅት ሲደረግ ከጤና ምርመራው በተጨማሪ የጨዋታ ሕግ ፈተናን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ የምዘና አይነቶችን በመጨመር ምዘናው በድጋሚ ለሁሉም ኮሚሽነሮች ተጠናክሮ የሚሰጥ መሆኑን እና በዚህ መንገድ የሚሰራ መሆኑን እናሳውቃለን።


“አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንሰራለን”

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

18 Oct, 07:33


ለወንዶች ከፍተኛ ሊግ የጨዋታ አመራሮች
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

የከፍተኛ ሊግ ውድድር ከጥቅምት 16/2017 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚጀምር መገለፁ ይታወቃል። በመሆኑም ሀሙስ በ14/02/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ በ12፡00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የጤና የምርመራ ውጤት ይዛችሁ በመምጣት ለባለሙያዎች ማረጋገጥ እና በዚያው ቀን 2፡00 ጀምሮ የአካል ብቃት ፈተና በመውሰድ በዚሁ ቀን ከቀኑ 6:00 ጀምሮ ወደፊት በምናሳዉቀው ቦታ ውይይት እና የውድድር ዝግጅት ገለፃ  ይሰጣል። ስለሆነም በተገለፀው አግባብ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ
ከላይ ስማችሁ ከተዘረዘረ የጨዋታ አመራሮች ውጭ ለፈተናው የሚመጡትን የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንሰራለን”

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

14 Oct, 07:45


ለሁሉም የጨዋታ አመራሮች
ዝግጅት እንድታደርጉ ስለማሳሰብ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

የ2017 ዓ.ም የውድድር ዘመን ሊጎቻችን የሚጀምሩበት ቀናቶች ከዚህ በታች የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን ሁሉም የጨዋታ አመራሮች ሁለንተናዊ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በ16/02/2017
የኢትዮጵያ ሴቶች ኘሪሚየር ሊግ በ24/02/2017
የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ በ30/02/2017
ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ኘሪሚየር ሊግ በ10/3/2017
የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ በ14/3/2017 የሚጀምሩ መሆኑን እያሳወቅን የአካል ብቃት ፈተና ኘሮግራሞችን በየጊዜው ስለምናሳውቅ እየተዘጋጃችሁ እንድትጠብቁን እናሳውቃለን፡፡

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንጥራለን”

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

04 Oct, 16:17


ከላይ ስማችሁ የተዘረዘረ የጨዋታ አመራሮች ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመክፈት መጠይቁን እስከ ቅዳሜ 25/01/2017 ዓ/ም እስከ ሌሊቱ 6:00 ድረስ ብቻ እንድትሞሉ እናሳስባለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://forms.gle/WYH2C8c7BudZghui9

#ማሳሰቢያ
ስማችሁ በዝርዝሩ ውስጥ ያልተካተተ የጨዋታ አመራሮች ሊንኩን እንዳትከፍቱት ብሎም ምንም ነገር እንዳትሞሉ እናሳስባለን።


"ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንጥራለን"

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

17 Sep, 16:51


የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና ጎፈሬ የትጥቅ አምራች ኩባንያ በአይነቱ ልዩ የሆነ የዳኞች ትጥቅ አቅርቦት የአጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።

ዛሬ በኢሊሊ ሆቴል በተካሄደው ሥነ ስርዓት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የጎፈሬ መስራች እና ባለቤት አቶ ሳሙኤል መኮንን፣ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሸዋንግዛው ተባበል እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለሦስት ዓመታት በሚቆየው በዚህ የአጋርነት ስምምነት ጎፈሬ ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዳኞች አራት አይነት ትጥቆችን ጨምሮ የማሟሟቂያ ፣ የጉዞ እና ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ የሚጠቀሙባቸው ቲሸርቶች እና ቱታ በስፖንሰር መልክ የሚያቀርብ ሲሆን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር በሚካሄዱ ሌሎች ውድድሮች ደግሞ እንደ የደረጃቸው ቅናሽ የተደርገባቸው ትጥቆች የሚቀርቡ ይሆናል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ስለ ስምምነቱ ማብራርያ የተሰጠ ሲሆን የጨዋታ አመራሮቻችን የሚጠቀሙባቸው ትጥቆች ለእይታ ቀርበዋል።

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

16 Sep, 14:44


ለፕሪሚየር ሊግ ዳኞች
እያደገ የሚሄድ ዓመታዊ የአፈፃፀም መለኪያ መስፈርትን ስለማሳወቅ


ይህ መስፈርት ለፕሪሚየር ሊጉ መሆኑን እያሳወቅን የምስጉን ዳኛ ምርጫ በዚህ ሂደት የሚያልፍ መሆኑን እንገልፃለን። ለሌሎች ሊጎችም መጠነኛ ማሻሻያ እንደየሊጎቹ ሁኔታ በማድረግ የምናሳውቅ ይሆናል። ማንኛውም አስተያዬት ያለው ሰው ለዲፓርትመንቱ እንዲያቀርብ ይበረታታል።

#ማሳሰቢያ
ይህ የዓፈፃፀም መለኪያ ለፕሪሚየር ሊጉ የሚያገለግል የደረጃ መወሠኛ መሥፈርት ሲሆን በየጊዜው የሚደረጉ ልዩ ልዩ ምርጫዎች በተገኘው የደረጃ ቅደም ተከተል መሠረት ይሆናል።


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያለው የዳኝነት ሙያ በሀገራችን እንዲኖር እንሰራለን