"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 @orthodoxtewahdoc Channel on Telegram

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

@orthodoxtewahdoc


🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ። https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን

የእመ ብርሃን ልጅ🤗

ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 (Amharic)

ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 የኦርቶዶክስ ጠዋትና የእምባቶች አገልግሎች ስለሚሆኑ የቅዱሳንን ታሪክ እና ዕውቀት የምንገባውን ዝግጅት በተከታታና በመረጃዎት ሊያዩት ያሰባሰባል። ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 የተለያዩ አስተማሪ ታሪካዊ መረጃዎችን እና ጽሁፎችን በዚህ መንገድ ለማግኘት እንዲሁም በሚገኙት ሰዎችን ዝግጁት እና አስፈላጊ መረጃዎችን ለመረጃው እና ለመከታተል ያለንን አገልግሎት እንዳታገኙ እንሰማለን።

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

08 Dec, 02:31


አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ። በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል። እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።

መዝ 3፥3-5
----------

🌷መልካም እለተ ሰንበት
🤲

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 20:55


መልክአ ኢየሱስ 📗

ቅዱስ ባለ ወልድ በቀኝ ያሳድረን  ያዉለን ክፉውን ያርቅልን ደጉን ያቅርብልን🤲 በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ ባለ ወልድ አባቴ አለው ይበላችሁ።

🌷መልካም እለተ ሰንበት🌸

🥰🙏🥰

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 20:53


Audio from Sara

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 19:05


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር ፳፱/29//

ቃላት  ባነጠፍኩ ባጎደልኩ በአፈ መላእክት ይርመኝ  ይሙላልን ከቅዱሳን በረከት እረድኤት ይክፈለን በጸሎታቸው ይማረን አሜን 🌹

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
ጓደኞችዎን ይጋብዙ ቤተሰብ ያድርጉ🌹🥀

🌹መልካም ሌሊት🌹🕊

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 18:18


ልጆቼ "ዛሬ የሚታየው ነገ ይሰወራል፤ የማይታየው የእግዚኣብሔር ተሰፋ ግን እየገዘፈ ይመጣል። ቢጨልምም በእሱ ዘንድ ግን ብርሃን ነው"ክብር ምስጋና ለድንግል ማርያም ልጅ ለቸሩ ለመድኃኔዓለም ይኹን🙏🙏🙏

የያዕቆብ ሌሊት ይኹንልን🌷

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 15:25


«ስለ ፍቅርህ ጥልቀት ልጽፍ ብዕሬን ሳነሳ ብዕርህን ስበራት ስበራት ይለኛል መልክህን ማየት ተለል ተለል ያደርገኛል ፍቅርህም ያዝለኛል አንተን መዘከር ያቃጥለኛል ሁልጊዜ ሥራ ለመሥራት ያነቃቃኛል አቤቱ #ፍቅርህ_በልቦናዬ_ፈጥኖ አደረ በሰውነቴ ተሰራጨ ሕዋሳቴን ጸጥ አደረጋቸው ከዚህ ዓለም ግብር መለየቴም ጌትነትህን ለማየት ወደ መግባት ያፋጥነኛል፡፡»

(አረጋዊ መንፈሳዊ)

🌸ፍቅሩን አንድነቱን ያድለን🌸

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 12:20


❇️ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

ንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠   
/(ማቴ ፫:፫/)

እንኳን አደረሰን!!


ባርከኒ አባ እንሣእ በረከተከ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተክለሐዋርያት አባ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ።

❇️"ብጹእ አንተ ወሰናይ ለከ ብእሴ እግዚአብሔር መርቆሬዎስ ሰማዕት ሰላመ ጸሊ ለሩኅቃን ወዳኂና ለቅሩባን ሰአል ወጸሊ በእንቲያነ::"❇️

❇️ማኅደረ ሰላምነ ቅድስት ደብተራ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት ንዑ ንስግድ ኵልነ ኀበ ማርያም እምነ።❇️

❇️ሰላም ለክሙ እንጦንስ ወመቃርስ፤
አቢብ ሲኖዳ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፤
ለባርኮትነ ንዑ ውስተ ጽርሐ ዛቲ መቅደስ፤
ተክለሃይማኖት አኖሬዎስ ኤዎስጣቴዎስ፤
ሳሙኤል ተክለ አልፋ በብኑዳ ኪሮስ፡፡
❇️

❇️ነብያት ወሐዋርያት ጻድቃን ወሰማዕት ደናግል ወመነኮሳት አዕሩግ ወሕጻናት ገዳማውያን ወሊቃውንት ሰአሉ ለነ ኩልክሙ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት።❇️

" ❇️ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::❇️
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር
https://t.me/zikirekdusn

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 12:20


💖💖💖#ቅዱስ ባለ ወልድ🌹🌹🌹

📗•••የባለወልድ{ በዓለ ወልድ }ትርጉም ወር በገባ በ29 ቀን የሚከበር 📌 ጌታችን በድንግል ማርያም ማሕፀን ተፀንሶ መወለዱንና ሙቶ መነሳቱን የሚያሳስብ በዓል ነው።ቀደም ሲል የነበሩ አበው ነቢያት ሲጸልዮ{ እግዚእነ አምላክነ ንጉስነ } እያሉ ይጸልዮ ነበር፡፡ ይህም ከግብረ ዲያብሎስ ለዲያብሎስ ከመገዛት እንዳልዳኑ ለማጠየቅ ነው፡፡እኛን ግን ከግብርናተ ዲያብሎስ ነጻ አውጥቻችኋለሁ ሲል አባታችን ሆይ ብላችሁ ጸልዮ ብሎ አስተማረን፡፡ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን እግዚአብሔር አባ አባቴ ብላችሁ የምትጠሩትን የልጁን መንፈስ በልባችሁ አሳደረ።{ ገላ 4፥6 }፣{ሮሜ 8፥15 }አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር አባትነቱን በሁለት ነገር ከምድራዊ አባት ለይቶታል ፡፡በመውለድና በመግቦት ከምድራዊ አባት ይለያል፡፡ምድራዊ አባት በዘር በሩካቤ ይወልዳል፡፡በማር፣በወተት፣በፍትፍት ያሳድጋል፤ኃላም በሞት ሲያልፍ የምታልፍ ርስትን ያወርሳል፡፡ እርሱ አምላካችን ግን ሲወልደን በርቀት ሲያሳድገንም በሥጋውና በaደሙ ነው፡፡ከስጋ የተወለደ ስጋ ነው ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው።{ ዮሐ 3፥6 }ኃላም የማታልፍ ርስት መንግስተ ሰማያትን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን
{ ኤፌ 1፥11 }፣{ 1ኛጴጥ 3፥5 }።
ቅዱስ ባለወልድ የአምላኮች አምላክ የጌቶች ጌታ የንጉሦች ንጉሥ አንተ ነህ የቅዱሳን አምላክ የድንግል ማርያም ልጅ በመንገዳችሁ ሁሉ ይቅደም በያላችሁበት ሰላማቹን ያብዛው የእለት እንጀራችንን ይስጠን።ቅዱስ ባለወልድ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን ቸርነቱ ምሕረቱ ረድኤት በረከቱ አይለየን ቤተክርስቲያንና ሃገራችን ኢትዮጵያን ከፈተና ይጠብቅልን ብርታቱንም በመላው ሕዝበ ክርስቲያን አድሮ ይኑር አሜን።
☞በአበው ነቢያት ሐዋርያትን በሐዋርያትም እኛን አቅርቦ አባታችን ሆይ ብለን እንድናመሰግነው ለፈቀደልን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ኃይልና ምስጋና ይድረሰው ለዘለዓለሙ አሜን።
የቅዱስ ባዓለ ወልድ ይቅርታው ቸርነቱ ረድኤት በረከቱ አይለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላድቱ ድንግል ማርያም
ወለ መስቀሉ ክቡር
አሜን ።አሜን ። አሜን።
ይቆየን

https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 12:19


🌹#ቅዱስ አባታችን አባ አፍፄ ማለት

☞ወር በገባ በ 29 የአባ አፍጼ ወርሐዊ መቲሰቢያው ነው፡✞ አባ አፍጼ ከተሰዐቱ ቅደሳን አንዱ ናቸው፡፡
☞አባቱ አቡድራስ እናቱ አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ በሕፃንነቱ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን ተምሮ በ15 ዓመቱ ዲቁና ከተቀበለ በኃላ ወደ ግብጽ በመኼዶ ገዳመ አስቄጠስ ገብቶ ሥርዐተ ምንኩስናን ተቀብሏል፡፡

☞ከሌሎች 8 ቅዱሳን ጎደኞቹ በመኾን ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል፡፡
☞በአክሱም ተቀምጦ በቤተ ቀጢን የሀገሪቱን ባሕል እና ቋንቋ አጥንቷል፡፡
☞ገዳማዊ ኑሮን ለመመሥረት በእየራሳቸው ሲበታተኑ ከአክሱም 8 ኪሎ ሜትር
ራቅ ብሎ ወደ ሚገኝ የሐ ወደ፡ተባለው ጥንታዊ ከተማ በመኺድ ጣዖት
አምላኪውን ሕዝብ አስተምሮ ወደ ክርስትና መልሷል፡፡
☞ቀጥሎም ሳባውያን ከደቡብ ዐረብ በመፍለስ ቀይ ባሕር ተሻግረው የሐ
ውስጥ እንደ ሰፈሩ የሠሩትን የጣዖት ማምለኬያ መቅደስ ባርኮ ወደ ቤተ
ክርስቲያን በመለወጥ ለክርስቲያኖች መገልገያ አድርጎታል፡፡
☞ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን የፀሐይ ጮራ የሆነ ተአምራትና ድንቆችን
የሚያደርግ የማር አቡነ አፍጼ ተአምር ይህ ነው ጸሎቱ በረከቱ ከህዝበ
ክርስቲያኑ ጋር ይሁን፡፡
☞ልጅ የሌለው ልጅ በማጣቱም ምክንያት ሲያዝን የሚኖር አንድ ሰው ከሩቅ
ሀገር ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን ወደ ሆነ ተአምራትና ድንቆችን ወደ ሚያደርግ
ማር አቡነ አፍጼ ቤተ ክርስቲያን መጣ በአቡነ አፍጼም በዓል ቀን አባቴ ሆይ
በእግዚአብሔር ዘንድ በከበረች በምትስማም ጸሎትህ የተሰገነ እግዚአብሔር
ደስ የሚያሠኝ ፈጽሞ የተባረከ ትእዛዙ መንፈሳዊት የሰውንም ፍጠረት ሁሉ
የሚያረጋጋ ፈቃድን የሚፈጽም ልጅ ትሰጠኝ እማፀናለሁ ብሎ ለመነ፡፡
☞በበዓሉ ቀን ማምሻ ንዑድ ክብር የዓለም ብርሃን የፀሐይ ጮራ የሆነ
ተአምራትና ድንቆችን የሚያደረግ የማር አቡነ አፍጼ በግልጥ ታየው ሰውየውንም
ወዳጄ ሆይ ልጅ በማጣት ምክንያት አትዘን እንሆ ሚስትህ እግዚአብሔር ደስ
የሚያሠኝ ትእዛዙንም አብዝቶ የሚፈጽም በጎና የተባረከ ልጅ ትወልዳለች አለው፤
ይህንንም ብሎ ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን የፀሐይ ጮራ የሆነ ተአምራትን
ድንቆችን የሚያደርግ ማር አቡነ አፍጼ ከእሱ ተሠወረ፡፡
☞ሰውየውም ይህንን ነገር ሰምቶ ፈጽሞ ደስ አለው፤ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን
ከሆነ ከማር አቡነ አፍጼ ግርማ ሞገስና ከጸዳሉ የተነሣ ይህን ሁሉ ቸርነት
ያደረገለትን ፈጽሞ እግዚአብሔር አመሰገነ፡፡
☞ከዚያ በኃላ ወደ ሀገሩ ተመለሰ ወደቤቱም ገብቶ ይህን ሁሉ ነገር
ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን የፀሐይ
ጮራ የሆነ ማር አቡነ አፍጼ እንደተገለጠለትም ለሚስቱ ነገራት፡፡የአቡነ አፍጼ
የገድሉና መጽሐፍ የተነበበትን የአባታችንን ጠበል ረጫት አጠጣትም፡፡
☞ከዚያ በኃላ ሚስቱን በግብር ዐወቃት ያንጊዜም ፀነሰች፡፡ የፅንሱ ጊዜ
ሲፈጸምም መልከ መልካም ልጅ ወለደችለት፡፡ አሦስት ዓመት ፍጻሜ በኃላ ይህ
ሰው ለዓለም ብርሃን አቡነ አፍጼ ቤተ ክርስቲያን እጅ መንሻ ይሰጥ ዘንድ ቡዙ
ገንዘብ ይዞ ሄደ፡፡
☞ያንም ገንዘብ ለካህናት ሰጣቸው በረከትም ተቀበለ፡፡
☞የንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን የፀሐይ ጮራ ተአምራትንና ድንቆችን
የሚያደርግ የማር አቡነ አፍጼን ደግነቱን ትሩፋቱን ተአምሮቹንና ድንቆችን
እየመሰከረ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡
☞ጸሎቱና በረከቱ የክርስቲያን ወገኖች ከምንሆን ከእኛ ከሁላችን ከሀገራችን
ከኢትዮጵያ ጋር ትሁን ለዘለዓለሙ ይሁን፡፡
☞(ገድለ አፍጼ)
☞አባታችነ አቡነ አፍጼ የእኛንም ጎዶሏችንም ይሙሉልን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 12:19


☞ወር በገባ በ 29 የአባታችን የአቡነ ዕጨጌ ዮሐንስ ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡
፡☞የተውልድ ቦታቸው እየሩሳሌም ነው፡፡
☞አባታቸው ድላሶር እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡
☞መስቀል ከሰማይ የወረዳላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡
☞መስቀሉ ሁሊም ተአምር ይሰራል በተለይ በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን
መስቀሉ ከገዳሙ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ጸበሉ ሲወርድ ከየት እንደ መጣ
ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ
አብሮ ወደ ጸበሉ ይወርዳል፡፡እዛው ቆይቶ መስቀሉ ሲመለስ አብሮ አጅቦ
ይመለስና መስቀሉ ወደ ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ
ሳይታወቅ ይጠፋል፡፡ ይህ ታምር በዚህ ዘመን ጭምር እየታየ ያለ ታአምር ነው፡፡
☞ጻድቁ ደመና ፤ጨረቃንና ፀሀይን በእጃቸው ይዘው ጸልየዋል፡፡
☞ጻድቁ አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ በጠገሮ ፤በፍርኩታ ፤በአዘሎ፤በሳፍጅ
በሌሎች ታላላቅ ቦታወች ላይ በእያንዳንዱ 50 በጸሎት ኖረዋል፡፡
☞በዘመኑ የሀገሩ ተወላጆች ጻድቁን እያሙ ስላስቸገሯቸው እረግመዋቸዋው
ተነስተው ወደ ደቡብ ጎንደር እስቴ ሄደው በዚያ ተቀምጠዋል፡፡ወንጌልን
እየተዘዋወሩ ካስተማሩ በኃላ ሐምሌ 29 ቀን ዐርፈዋል በጎንድ ተክለ ሃይማኖት
ተቀብረዋል፡፡
☞ጻድቁ ካረፍ በኃላ በእርግማናቸው መሠረት በመንዝ እና ድርቁ ሰለበዛባቸው
አንድ የበቁ አባት ከበአታቸው ወጥተው በሐሜታቸው ምክንያት አቡነ እጪጌ
ዮሐንስ ሰለረገሟቸው የእሳቸውን አጽም ካለመጣችሁ ብርዱ ውርጩ ድርቁም
አይጠፋላችሁም አሏቸው፡፡ ሕዝቡም በቅዱሳን እየተመሩ ሄደው በሌሊት ግማሽ
ዐፅማቸውን አምጥተው በሀገራቸው ስላስቀመጡ ብርዱና ውርጩ በመንዝ
እየቀነሰላቸው መጥቷል፡፡
☞ዛሬ ላይ በሀገሩ ብርዱና ውርጭ ሲበዛ የጻድቁን ታቦት ሲያወጡ ውርጩ
ይጠፋል፡፡
☞አፅማቸው በፊት ከተቀበሩበት ፈልሶ መንዝ ከአርባ ሐራ መድሀኒአለም
አጠገብ ፍርኩታ ኪዳነ ምህረት ገዳም ውስጥ ይገኛል፡፡
☞የጻድቁ ጥበቃ አማላጅነት እንዲሁም ረዲኤት በረከት አይለያችሁ፡፡
☞ከትምህርታቸው ትንሽ ልጥቀስ ስላችሁ፡፡
☞(ሰውነትህ ከማንጻት ይልቅ ልቡናህን ከቂም በቀል አንጻ ፡፡ልቦናህ ከበቀልና
ክፍትን ከማሰብ ካልነጻ ነፍስም አትነጻም፡፡
☞ከውዳሴ ከንቱ በቀር ለእግዚአብሂር ልዮ ጠላት የለውም፡፡
☞ነፋስ የወሰደው ትቢያ እና ውዳሴ ከንቱ አንድ ናቸው፡፡
☞በሰው ዘንድ ከመመስገን መቀበር ይሻላል፡፡
☞የአባቶችን እርስት ከምትወርስ የእግዚአብሄር ረስት መንግሰተ ሰማያትን
ብትወርስ ይሻልሀል፡፡)
☞ከአባታችን ከአቡነ እጨጌ አሰተምሮ በትንሹ ይሄን ይመስላል ፡፡
☞ለበለጠ መረጃ ገድለ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ይመለከቱ፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞28-7-2014

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 12:19


#ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ🌹

☞ወር በገባ በ29 ታስባ የምትውለው እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ያደረገችው ታዕምር ይህ ነው ፡እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶሰ የተወለደችው በጎንደር ክፍለ ሀገር በደራፎገራ አንበሳ መዳ ነው፡፡

☞የተወለደችው ክርስቶስ በተወለደበት ቀን ታኅሣሥ 29ቀን በመልአከ አብሳሪነት ተወለደች፡፡ ☞በተወለደችም ጊዜ በእግሯ ቆማ ከጨለማ ወደ ብርሐን ላወጣህኝ ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅድስ ምስጋና ይገባል ብላ አመሰግናለች፡፡

☞እርሷ በነበረችበት ዘመን ንጉስ ሱስንዮስ "ሁለት ባሕርይ"የሚለውን የረከሰ የሮማውያንን ሃይማኖት ሕዝቡ ሁሉ እንዲያምን በማወጁ ምክንያት በሀገራችን
ከፈተኛ የሆነ የሃይማኖት ግጭት ሰለተነሣ ከ8ሺ በላይ ክርስቲያኖች በግፍ ተጨፍጭፈው ሲየልቁ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከእነ አቡነ ስምዖን እና ከሌሎችም ቅድሳን ጋር ተሰልፋ ሰማዕትነት ዐርፋ ሰባት አክሊልን ወርዶላታል፡፡
☞ቅድስት እናታችን አምላኳን እሰከ ሐጨረሻው በድንግልና መገልገል ብትፈልግም ዕድሜዋ ለ ከፍ ሲል ቤተሰቦቿ ዘርዓ ክርስቶስ ከሚባል አገረ ገዥ ጋር አጋባት፡፡ እርሷም ግን በጫጉላ ቤት እያሉ በእኩ ሌሊት ቧሏን ወንድሜ ሆይ
እግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ ነገር ድንግልናችንን እጠብቅ አለችው እርሱም እሺ አላት ይህን ተመካክረው በጸሎት ሲተጉ አደሩ፡፡ በሌሊትም ወደ ባሕር ውስጥ እየገቡ ጸሎት ያደርጉ ጀመር፡፡

☞በመጨረሻም እርሷ በጳጳሱ በአባ ማርቆስ እጅ ስትመነኩስ ቧሏም ድንግልናውን እንደጠበቀ በሰማዕትነት አንገቱን ተሰይፎ ዐርፏል፡፡

☞ - - - - መልአኩም ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መልሶ ወደ ኢትዮጵያ ካመጣት በኃላ ዛሬ ገዳሟ ካለበት ቦታ ሴትደርስ ከቦታዋ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ በቀሰተ ደመና ተከቦ አይታ ይህቺ ቦታ ምንታምር ብላ ጠራቻት፡፡ በቦታውም ላይ በመድኃኔ ዓለም ትእዛዝ የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በአንዲት ቀን ብቻ ሠርታለች፡፡

☞እናታችን ቅድስ ፍቅርተ ክርስቶስ የሠራቻት በሰሚዝ(በሰንሰል)እንጨት በአይጥ ሐረግ፤ በነጠላ ማገር አድርጋ የግድግዳ ቤተ መቅደስ በአንዲት ቀን ብቻ ሠርታ በታህሳስ 16ቀን በዕለተ እሁድ አሰቀድሳለች፡፡

☞ቅዱስ ሩፉኤልም መሲፋይልም በክንፋቸው አፈር ከእየሩሳሌም አምጥተው በቦታዋ ላይ ቀላቅለውበታል፡፡
፼ጌታችንም ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ተገልጦላት ቦታዋን ባርኮላታል፡፡ ☞ቤተ ክርስቲያኗ አስከ እለተ ምጽአት እንደማትፈርስ ቃል ገብቶላታል፡፡

☞ይቺ ቤተክርስቲያን ጌታችን ለቅድስ ፍቅርተ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሊሰጣት ሲመጣ ሰግዳለች፡፡ዛሬም በአራቱ አቅጣጫ ሲመለከቱት ዘንበል ብሎ ይታያል፡፡

☞የእናታችን የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ያደረገችው ታዕምር ይህ ነው፡፡
☞በሀገሯ አቅራቢያ የሚኖሮ አንድ አይነ ስውር ነበር፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን እጅ ይነሣ ዘንድ በዛው በአይኖ መታወር ሁሌ ያዝ ነበር እና እንድታማልደው እናታችን ቅድስት ፍቅርቶስን ለመለመን ሄደ፡፡
☞በዚየም ቆሞ ሲጸልይ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ እንባዋን እንደ ውሃ እረጨችው፡፡ በዚያን ጊዜ አይኖቹ በሩለት እና እየ በፊቷም ሰገደ፡፡
☞እስከለተ ሞቴ ድረስ ለሰው አትንገር አለችው ይህን ብላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ተሰወረች፡፡
☞የእናታችን የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የጸሎቷ በረከት አይለየን፡፡
☞የእናታችን የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አማላጅነት አይለያችሁ፡፡ የዕረፍቷም
መታሰቢያ የካቲት 29 ቀን ነው፡፡ የዛ ሰው ትበለን፡፡
☞(ገድለ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 12:18


ተቆጥሮለታል::

ቅዱሱ ሐዋርያ እንዲህ ሲመላለስ ኖሮ በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በጠራብሎስ እጅ ወደቀ:: ንጉሡም "ክርስትናን አስተምረሃል" በሚል ብዙ አሰቃይቶ: ከትልቅ ድንጋይ ጋር አስሮ ባሕር ውስጥ አስጥሞታል:: በዚህም ዐርፏል::

ሁሌ ግን በዓመት በዓመት ባሕሩ እየተከፈለላቸው: ምዕመናን እየገቡ ከቅዱስ አካሉ ይባረካሉ:: ቅዱሱን ብዙ ጊዜ "ቀሌምንጦስ ዘሮም" የምንለው "ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ" የሚባል መናፍቅ ስላለ ከእርሱ ለመለየት ነው::
የቅዱሱ ክብር በእውነት ታላቅ ነው!

††† አምላከ ሐዋርያት ወሰማዕት በመከራቸው ከመከራ ይሰውረን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

††† ኅዳር 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን ሰማዕታተ ክርስቶስ (ሁሉም)
2.ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
3.ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ (ዘሮም)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት
2.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
3.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮጵያዊት
4.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
5.ቅድስት አርሴማ ድንግል

††† "አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ::
የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ::
ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት::
የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች አደረጉ::
የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት::
ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ::
የሚቀብራቸውም አጡ::" †††
(መዝ. ፸፰፥፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

https://t.me/zikirekdusn

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

07 Dec, 12:18


††† እንኳን ለአእላፍ ሰማዕታት: ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱሳን ሰማዕታት †††

††† ቤተ ክርስቲያን ዛሬ (ኅዳር 29) የሁሉንም ሰማዕታት በዓል ታከብራለች:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቅዱሱ ሊቅ) በመጽሐፈ ሰዓታት ሰማዕታትን:-
"መስተጋድላን ከዋክብት ብሩሃን::
ማኅትዊሃ ለቤተ ክርስቲያን::" ይላቸዋል::

በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የሮም መንግስት ዓለምን የሚያስተዳድረው በሁለት ከተሞች: ማለትም በራሷ በሮምና በአንጾኪያ ነበር:: የወቅቱ ንጉሥ ኑማርያኖስ ሲሆን የቤተ መንግስቱ ልዑላንና የጦር አለቆች ቅዱሳኑ:- *ፋሲለደስ: *ገላውዴዎስ: *ፊቅጦር: *መቃርስ: *አባዲር: *ቴዎድሮስ (ሦስቱም): *አውሳብዮስ: *ዮስጦስ: *አቦሊ: ሌሎቹም ነበሩ::

ሴቶቹ ደግሞ ቅዱሳቱ:- *ማርታ: *ሶፍያ: *ኢራኢ: *ታኡክልያ: ሌሎቹም ነበሩ:: ለእነዚህ ሁሉ የበላይ ደግሞ ቅዱስ ፋሲለደስ ነበር:: ወቅቱ ከፋርስ: ከቁዝና ከበርበር ጦርነት የሚበዛበት ነበርና ባጋጣሚ ንጉሡ ኑማርያኖስ በሰልፍ መካከል ተመትቶ ወደቀ (ሞተ)::

የሮም መንግስትም ባዶ ሆነች:: ዙፋኑን መያዝ ለቅዱስ ፋሲለደስም ሆነ ለሌሎቹ ቅዱሳን ቀላል ነበር:: ግን እነሱ ዝም ብለው ጠላትን ለመዋጋት ወጡ::

በዘመኑ ደግሞ በግብጽ የፍየል እረኛ የነበረና ከልጅነቱ ሰይጣን የሚያናግረው አንድ አግሪጳዳ የሚሉት ጉልበተኛ ሰው ነበር:: ንጉሡ ከወለዳቸው ልጆች ሁለቱ ሴቶች ክፉዎች ነበሩና ትንሿ አግሪጳዳን ማንም በሌለበት አንግሣ ጠበቀቻቸው:: ስሙንም ዲዮቅልጢያኖስ አለችው::

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም:: የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው:: ትልቋ ደግሞ የትንሿን አይታ መክስምያኖስ የሚባል አውሬ አግብታ አነገሠችው:: ዓለምም በእነዚህ ጨካኝ ሰዎች እጅ ወደቀች::

ሠራዊቱ ሁሉ በሚሊየን ይቆጠራሉ:: የተደረገውን ሲያዩ ተበሳጩ:: ይህንን የተመለከተው ቅዱሱ ፋሲለደስ ግን ልዑላኑንና አለቆችን ሰብስቦ:- "ይህ ዓለም ከነ ክብሩ ጠፊ ነው:: ስለዚህ የተሻለውን የክርስቶስን መንግስት እንምረጥ" አላቸው:: ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ ደስ ተሰኝተው ምድራዊ ክብራቸውን ሊተው ወሰኑ::

ቀጥለውም በአንድ ቤት ተሰብስበው ይጾሙ: ይጸልዩ ገቡ:: ወደ ውጪ የሚወጡት ለምጽዋት ብቻ ነበር:: ከሃዲውም ይህንን ሲያይ የልብ ልብ ተሰማው:: ከድሮ ያሰበውንና ክርስቲያኖችን የማጥፋቱን እቅድ ሊፈጽም ምክንያት አገኘ::

አባ አጋግዮስ በሚባል መነኩሴ ምክንያት "አብያተ ክርስቲያናት ይትዐጸዋ: አብያተ ጣዖታት ይትረኀዋ - ቤተ ክርስቲያኖች ይዘጉ: ቤተ ጣዖቶችም ይከፈቱ" አለ:: አጵሎን: አርዳሚስ የሚባሉ ጣዖቶችንም አቆመ::

በዚህ አዋጅ ምክንያትም የክርስቲያኖች ሰቆቃ ጀመረ::
*ምድር በደም ታጠበች::
*ቅዱሳኑ ቀባሪ አጡ::
*እኩሉ ተገደለ:: እኩሉ ተቃጠለ:: እኩሉ ታሠረ:: እኩሉም ተሰደደ::

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተጻፈው በብራናና በብዕር አይደለም:: ይልቁኑ እንደ ቀለም የሰማዕታት ደማቸው: እንደ ብዕር አጥንታቸው: ቆዳቸው እንደ ብራና ሆኖ ተጽፏል እንጂ:: ሰማዕታት ለሃይማኖታቸው የከፈሉት ዋጋ እጅግ ታላቅ ነው::

ስለዚህም "ተጋዳዮች: የሚያበሩ ኮከቦች: የቤተ ክርስቲያን ሻማዎች" ተብለው: እነሱ እየቀለጡ አብርተዋል:: ሰማዕትነት በብሉይ ኪዳን የጀመረና እስከ ዳግም ምጽዐተ ክርስቶስም የሚቀጥል ቢሆንም "ዘመነ ሰማዕታት" የሚባለው ከ150 እስከ 312 ዓ/ም ድረስ ያለው ዘመን ነው::

በተለይ ግን ከ270ዎቹ እስከ 312 ዓ/ም ድረስ ያሉ ዓመታት እጅግ የከፉ ነበሩና: የአርባ ሰባት ሚሊየን (47,000,000) ክርስቲያኖች ደም በምድር ላይ ፈሷል:: የሰማዕታት ምሥጢራቸው ቃለ ወንጌል: የጌታ ስብከትና ሕይወት እንጂ ሌላ አይደለም:: (ማቴ. 10:16, ማር. 13:9, ሉቃ. 12:4, ዮሐ. 16:1, ሮሜ. 8:35, ራዕይ. 2:9)

የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳሳት ነው::

††† ቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕት †††

††† ይህ ቅዱስ የሚታወቀው "ተፍጻሜተ ሰማዕት (የሰማዕታት መጨረሻ)" በሚለው ስሙ ነው::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት:: ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ 5 ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ጴጥሮስ" አለችው::

ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ጳጳሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ:: ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ጴጥሮስን የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::

ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር:: ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ14 ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ::

አርዮስን (ተማሪው ነበር) አውግዞ ለየው:: ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ጵጵስናው ላይ አልተቀመጠም:: በኋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ::

ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ጴጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ:: በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ:: ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ:: ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::

††† ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም †††

††† የዚህ ቅዱስ ሐዋርያ ስሙ እንደ ምን ያምር! እንደ ምንስ ይከብር! ለቤተ ክርስቲያን ትልቁ ድልድዩዋ ነውና:: ቅዱስ ቀሌምንጦስ የቅዱስ ቀውስጦስና የቅድስት አክሮስያ ልጅ ሲሆን ወንድምም ነበረው::

አባትና እናቱም የሮም መሳፍንት: በስብከተ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ያመኑ: ገንዘባቸውን በምጽዋት የጨረሱ የመጀመሪያዎቹ የሮም ክርስቲያኖች ናቸው:: ልጆቻቸው (ቀሌምንጦስና ወንድሙ) በመርዝ ቢሞቱባቸው በአምላከ ጴጥሮስ ተማጽነው ተነስተውላቸዋል::

አንድ ጊዜ ቀውስጦስ በሌለበት አንድ ሰው አክሮስያን ስላስቸገራት ልጆቿን ይዛ ተሰዳለች:: በመንገድም መርከባቸው ተሰብሮ ቅዱስ ቀሌምንጦስ በስባሪው ግብጽ ደርሷል:: በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስን አግኝቶት የሊቀ ሐዋርያት ደቀ መዝሙሩ ሆኗል::

ቅዱስ ጴጥሮስንም ተከትሎ ለአገልግሎት ብዙ አሕጉራትን ዙሯል:: ብዙ ምሥጢራትንም ተካፍሏል:: የቅዱሳን ሐዋርያትን ዜናም ከቅዱስ ሉቃስ (ግብረ ሐዋርያት) ቀጥሎ የጻፈ እርሱ ነው::

ቅዱሳን ሐዋርያት ሙሉ ቀኖናቸውን ለቅዱስ ቀሌምንጦስ ሲሰጡት ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ሰብአ ሰገል ለክርስቶስ ያመጡትን ወርቅ: እጣን: ከርቤውን አስረክቦታል:: በተለይ ሁሉም ሐዋርያት ባረፉ ጊዜ እርሱ ቤተ ክርስቲያንን ተረከበ:: በሮም ሁለተኛው ፓትርያርክ ሆነ::በጊዜው መጽሐፈ ቅዳሴ ባለ መደራጀቱ ሥጋውን ደሙን ሲፈትቱ ፈጣሪ እንዳመለከታቸው ይጸልዩ ነበር:: ቅዱሱ ግን የጌታንና የሐዋርያትን ቅዳሴ ዛሬ በምናየው መንገድ አደራጅቶ ጽፎታል:: በስሙ የሚጠራና "ቀሌምንጦስ" የሚባል መጽሐፉም (8 ክፍሎች አሉት) ከ81ዱ (አሥራው) መጻሕፍት

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

18 Nov, 06:15


ልጆቼ ወጣቶች ናችሁን?
               
የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም  ዓመታት ሳይደርሱ፤
ወጣት በመሆንህ ገና ብዙ ዘመን አለኝ ብለህ እድሜዬ ገና ነው ብለህ አትተማመን ።ተለክቶ የምትላቸውምየታወቀ ቀሪ ጊዜ ያለነገ አድርገህ አታስብ።
<<የጌታ ቀን ድንገት
#እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና። >> 1ኛ ተሰ.5÷2 ስለዚህም ምክንያት የእድሜአችንን መጨረሻ አስቀድመን እንዳናውቀው አደረገ። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አትዘግይ ከዛሬ ነገ እመለሳለሁ እያልክ አትቁጠር። ሲራ 5÷8 ዛሬ ነገ እመለሳለሁ ስትል አንድ ቀን ባቋራጭ እንዳትወሰድ #ንስሀ ግባ።ሰላምና ደህንነት ነው ሲሉ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል። 1ኛ ተሰሎ 5÷3 የዚህ ዓለም ነገሮች ሁሉ ተለዋዋጮች ናቸው።እኛ በራሳችን የወደፊት ህይወትና ሁኔት ላይ ማዘዝ የምንችል አይደለንም ነገር ግን በፅድቅ ሥራ ላይ የሰለጠንን እንሁን ቸሩ መድኃኔዓለም ይለመነን።

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

18 Nov, 02:29


አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በእለተ ቀናቸው ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰዉሩን መንገዳችን የቀና ህይወታችን የበራ ያድርጉልን በቀኝ ያውለን መልካም ቀን።🤲🌷💗

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 20:57


🌷መልክአ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ📗

የሞቱትን ነፍስ የምታስምሩ ፃድቁ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ በአካለ ነፍስ የሌሉ የህዝበ ክርስቲያን ነፍስ ይልቁንም የወላጆቼን የገብረ ማርያምን የወለተ ማርያም የወለተ ማርያምን ነፍስ ያስምሩልን አሜን በእውነት🤲😔

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 19:03


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር ፱/9/

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 16:06


💒ኦርቶዶክሳዊ ውበት
         🌷💗🌷


🌷ሳየው ነፍሴ ደስ የምትሰኝበት ምስልእናት ዓለም እምዬ ተዋህዶ🥰

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 14:28


"ወር በገባ በ 9 ፃድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ናቸው።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቁን🙏💙

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 13:28


††† እንኳን ለአበው ቅዱሳን "318ቱ ሊቃውንት" ዓመታዊ የጉባኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ጉባኤ ኒቅያ †††

††† በዚህች ዕለት (ኅዳር 9 ቀን) በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተሰብስበዋል::

የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት መስከረም 21 ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች "ሊቃውንት" ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው::

እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: እስኪ እናውቃቸው ዘንድ የጥቂቶችን ማንነት በስምና በመገለጫ እንመልከት:-
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው)
2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው)
3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው)
4.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው)
5.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው)
6.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕጻንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው)
7.ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው)
8.ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ:
ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው)
9.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው)

ለአብነት እንዲሆኑን እነዚህን አነሳን እንጂ 318ቱም ሊቃውንት ስለ ቤተ ክርስቲያን ተግተው የተጋደሉ: ብዙ ዋጋም የከፈሉ አባቶች ናቸው::

በወቅቱ ታዲያ ቤተ ክርስቲያንን የበጠበጡ ብዙ መናፍቃን ቢኖሩም የአርዮስ ግን ከመጠኑ አለፈ:: የእርሱ ኑፋቄ (ፈጣሪያችንን ፍጡር ነው ማለቱ) መነሻው ከእርሱ በፊት ነው:: መናፍቃን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኩ መኖራቸው ግልጽ ነው::

በተለይ ደግሞ ቢጽ ሐሳውያንና ግኖስቲኮች የወለዷቸው እሾሆች አባቶቻችንን እንቅልፍ ነስተው ነበር:: የሚገርመኝ በዘመኑ እንደ ነበሩ መናፍቃን ኃይለኝነት የእኞቹ ከዋክብት ሊቃውንት ባይኖሩ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያሳስብ ነበር::

ግን እግዚአብሔር ለሁሉ እንደሚገባ ያዘጋጃልና አበው ብርቱ መናፍቃንን በብርቱ መንፈሳዊ ክንድ እያደቀቁ ከጐዳና አስወገዷቸው:: የዛሬውን ደካማ ትውልድ ደግሞ የአርዮስ ልጆች 2 (3) ጥቅስ ይዘው ሲያደናብሩት ይውላሉ::

ሐረገ መናፍቃን በርጉም ሳምሳጢ ጳውሎስ: በመርቅያንና በማኒ ይጀምራል:: በእርግጥ አርጌንስ እና የግብጹ ቀሌምንጦስም ተቀላቅለዋቸዋል:: ርጉም ሳምሳጢ ድያድርስን በኑፋቄ ወልዶታል:: ድያድርስ ሉቅያኖስን: ሉቅያኖስ ደግሞ አርዮስን ወልደዋል::

ይህ አርዮስ እጅግ ተንኮለኛ በመሆኑ ልክ እንደ ዘመኑ መሰሎቹ ግጥምና ዜማ እየጻፈ በየመንገዱ እያደለ: በየቤቱ እየሰበከ ብዙዎችን በኑፋቄው በከለ:: በመጀመሪያ ተፍጻሜተ ሰማዕት
ቅዱስ ጴጥሮስ (አስተማሪው) መከረው:: ባይሰማው ከአንዴም ሁለት ጊዜ አወገዘው::

ቆይቶ ሰነፉ ጳጳስ አኪላስ ቢፈታውም ሊቁ ቅዱስ
እለእስክንድሮስ እንደ ገና አወገዘው:: እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው::

ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ (ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5) አርዮስና የዛሬ መሰሎቹ አንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል::

በወቅቱም በመወገዙ "ተበደልኩ" ብሎ የጮኸው አርዮስ ከ2ቱ አውሳብዮሶች ባልንጀሮቹ (ዘቂሣርያና ዘኒቆምድያ) ጋር ሆኖ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውነት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ::

ከሚያዝያ 21 እስከ መስከረም 21 ተጠቃለው ገቡ:: በ325 ዓ/ም (በእኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ጴጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::

በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት:: በጉባኤው መጨረሻም:-
1.አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ::
2.ጸሎተ ሃይማኖትን "ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም" እስከሚለው ድረስ ተናገሩ::
3.ፍትሐ ነገሥትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብለው አዘጋጁ::
4.ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ::
5.በስማቸው የሚጠራ አንድ ቅዳሴን ደረሱ::

ይህ ሁሉ ሲሆን መድኃኒታችን ክርስቶስ 319ኛ ሆኖና ገሊላዊ ጳጳስን መስሎ ሁሉን አከናውኖላቸዋል:: አባቶችም ሥራቸውን
ከጨረሱ በኋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል::

††† በየዘመኑም ዐርፈው ለክብረ መንግስተ ሰማያት በቅተዋል:: እኛም እነሆ "አባቶቻችን:
መምሕሮቻችን:
መሠረቶቻችን:
ብርሃኖቻችን:
ምሰሶዎቻችን" እያልን እናከብራቸዋለን::

††† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ኅዳር 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን 318ቱ ሊቃውንት
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
4.አባ ይስሐቅ ሊቀ ጳጳሳት
5.ሊቁ አካለ ወልድ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
3.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
4.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
5.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ

††† "እውነት እላቹሃለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል:: ደግሞ እላቹሃለሁ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል:: ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና::" †††
(ማቴ. ፲፰፥፲፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 13:28


📕#አቡነ_ብፁእ አምላክ ያደረጉት ተአምር🌹📘

📘•••ወር በገባ በ9 ታስበው የሚውሉ የአባታችን የአቡነ ብፁዐ አምላክ ታአምር ይህ ነው፡ ልመናውና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ከአቡነ ዮሐንስ በኃላ በተሾመው በአባ ሠረቀ ብርሃን ዘመን ወደ ደብረ ቢዘን ከአባቱና ከወንድሞቹ ጋር በገባ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምረው ዘንድ ለአባ ጴጥሮስ ተሰጠ፡፡

☞የትምህርት ቤት ለጆች ወንድሞቹ ቀኑበት፡፡ ለምን ከእኛ ጋራ እየተማረ እንደ
እኛ አይፈጭም አሉ፡፡ አባ ጴጥሮስም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ብፁዐ አምላክ ሆይ
እዳያዝኑብህ እንደ ወንድሞችህ የምትፈጨውን ውሰድ አለው፡፡
☞የዋህ የሆነ ብፁዐ አምላክም እሺ አምላክህ በጸሎትህ ያስችለኝ አለ፡፡
የሚፈጨውንም ወሰዶ ተኛ በነቃም ጊዜ ተፈጭቶ አገኘው እግዚአብሔር
አመሰገነ ለሰውም አልተናገረም፡፡
☞ለብዙ ጊዜ እንዲህ በሆነበት ጊዜ ጓደኞቹ የተማሪዎች አለቃ ከፈጩት ዱቄት
የሚሰጠው አለ ብለው ተጠራጠሩ፡፡ እስኪ መጣም ሦስት ሦስት ሁነን እንጠብቅ
ከመካከላችን ነቅቶ እህል ወስዶ ዱቄትን የሚሰጠው አለ አሉ፡፡ ሦስት ሦስት
ሁነው ሲጠብቁ የፈጭታዎች
መንቂ ደረሰ፡፡
☞የእየራሳቸውንም ሊፈጩ እሳትን አበሩ፡፡ የብፁ አምላኮ እህል ግን ተፈጭቶ
አገኙት፡፡ ተደንቀውም አትናገሩ፡፡ ሁለትኛ ሦስተኛ እንዲህ የሚሆን እንደሆነ እንይ
አሉ፡፡ እንዲህም ሆነ፡፡ በምሽት በየተራቸው ለብፁ አምላክ የተከፈለውን እህል
ያስቀምጣሉ፡፡
☞ ሦስት ሦስት ሁነውም ይጠብቃሉ፡፡ በነቁም ጊዜ ተፈጭቶ ያገኙታል፡፡ ከዘህ
በኃላ ለመምህሮቻቸው ተናገሩ፡፡
☞እነሱም እንደ ልጆች አድርገው ሦስት ሦስት ሆነው ጠበቁትና ሥራውን
እንግለጥበት አሉ፡፡ ግን ሥራውን አስትተን የቤተ ክርስቲያን ተልኮና መጻሕፍትን
ማንበብ እናዝዘው አሉ፡፡
☞እሱም ጌቶቼ በመፍጨቴ ካልተደስታችሁ ምግብ ማብሰል ወይም ሌላ ሥራ
የወደዳችሁን በቤተ ክርስቲያን ምልከታ ላይ እና መጻሕፍትን ማንበብን እዘዙኝ
አላቸው፡፡
☞ውሃ መቅዳትን አዘዙት፡፡ አባታችንም ብፁዐ አምላክ ቀድቶ ሊሸከም ባነሣው
ጊዜ ውሃው ከራሱ ላይ አንድ ክንድ ከፍ ከፍ አለ ይህን አይተው አደነቁ፡፡
☞ዳግመኛ ዕንጨትም ሊለቅም ሄደ፡፡ በጸሎት ሰዓት ሊጸልይ ሲቆም ዕንጨቶች
የሚበቃውን ያህል ይሰበሰቡለታል፤ ሊሸከምም ሲያስር አንድ ክንድ ከራሱ ላይ
ከፍ ከፍ አለ፡፡
]ወደ ኀላ ባለጊዜም ሊጠብቁት ወንድሞቹ ተመለሱ፡፡ ይህንንም አይተው አደነቁ
መክረንም እስክናዝዝህ ድረስ ታገስ አሉት፡፡ ብሩክ ሁን መንፈስ ቅዱስ
እንደሰየመህ ብፁዕ ሁን አሉት፡፡
]☞የብጹ አቡነ አምላክ ወዳጆቹን እግዚአብሔር በጸሎቱ ይቅር ይበላቸው
ለዘላለሙ አሜን፡፡
☞(ገድለ አቡነ ብፁዐ አምላክ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ


https://t.me/Orthodoxtewahdoc ቤተሰብ ይሁኑ

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 13:28


"ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በኒቅያ ጉባኤ ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው ድንቅ አባት ነው በእውነት  አንክሮ ይገባል!!)::"
     <<<ከበረከቱ ይክፈለን።>>>

https://t.me/zikirekdusn

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 13:28


#ወር በገባ በ9 አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ💖
አባታችን አቡነእስትንፋሰ ክርስቶስ ያደረጉት ታዕምር ይህ ነው፡፡
#ኮሬብ በሚባል አገር ብዙ ዘመን ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ የሚኖር አንድ ሰው
ነበር፡፡ ለዘመዶቹ ወደ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ገዳም ውሰዱኝ ያለ
እሱ የሚፈውሰኜ
ኝ የለም በፍጹም ልቡናው አምኖ ይህን በተናገረ ጊዜ ተሸክመው አምጥተው
ከአባታችን መቃብር ላይ አስቀመጡት ያም ታማሚ ሰው አባታችንን ከደጅህ
ወደቅሁ በጸሎትህና ተማጸንኩ የተአምራትህን ኃይል በእኔ ላይ ግለጽ ኃጢአተኛ
የምሆን የእኔን የባሪያህን ልመና ቸል አትበል አለ ይህን ብሎ ከአባታችን
እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አጠገብ የምትፈሰ ጠበል ተጠምቆ ተኛ ሲነሳ
በአባታች በአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በጸሎቱ ኃይል ዳነ፡፡
#እጆቹና እግሮቹ ቀንተውለት በእግሩ ቆመ ጉልበቱም እን ጎልማሳ ሆነ ሕዝቡም
የተደረገውን ተአምር አይተው እጅግ እግዚአብሔርን አመሰገኑና ይህ ጻድቅ
ተአምራቱን አሳየን እኛም በጸሎቱ ኃይል ተማጽነናል እያሉ አባታችን እስትንፋሰ
ክርስቶስን አደነቁ፡፡
#እኛንም አባታችን አብነ አስትንፋሰ ክርስቶስ በጸሎቱ ሀይል ከክፋ ዕለት እና
ከጥፋት ሠዓት በሚመጣው ዓለም ከገሐነም እሳት ታድኑን ዘንድ እንማጸናለን፡፡
#(ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ)

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 13:28


📌#ቅዱስ_ዞሲማስ_ጻድቅ_ማን ነው

🌹ወር በገባ በ9 የቅዱስ ዞሲማስ ወርኀዊ በዓሉ ነው📕
❖ይህም ጻድቅ ከፍልስጥዔም ሰዎች ወገን ነው፤ ወላጆቹም ደጋጎች ክርስቲያኖች ናቸው ይህንን ጻድቅ በወለዱት ጊዜ አምስት ዓመት አሳደጉት፤ ከዚያም የቤተክርስቲያን ትምህርትን የሃይማኖትንም ምሥጢር ሕግና ሥርዓትንም እያስተማረ እንዲያሳድገው ለአንድ ሽማግሌ መምህር ሰጡት።

❖ ያ ሽማግሌም ተቀበሎ ልጁ አደረገው ትምህርቱንም ሁሉ አምላካዊ ጥበብ ሃይማኖትንም አስተምሮ አመነኰሰው ዲቁናም አሾመው በበጎ ሥራም አደገ ትሩፋት መሥራትንም አበዛ እግዚአብሔርንም ሁል ጊዜ ያመሰግነዋል በቀንና በሌሊትም መጻሕፍትን ያነባል፤ ሥራ ሲሠራ ሲበላም ቢሆን ሁል ጊዜ ከአፉ ምስጋናዎችን አያቋርጥም፤ በዚያ ገዳም አርባ አምስት ዓመት በተፈጸመለት ጊዜ ቅስና ተሾመ ተጋድሎውንም ጨመረ።

❖ ከዚህ በኋላም እየተጋደለና አገልግሎት በመጨመር በቅስና ሹመት ዓሥራ ሦስት ዓመት ሲሆነው በዘመኑ ካሉ ተጋዳዮች ሁሉ እርሱ በገድሉ ከፍ ከፍ እንዳለ ተቃራኒ ጠላት ዲያብሎስ በልቡ ክፉ ሀሳብ አሳደረበት በልቡም ከበጎ ሥራ እኔ ያልሠራሁት የቀረኝ አለን ይል ጀመር፤ ነገር ግን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልተወውም መልአኩን ልኮ በዮርዳኖስ ወንዝ አቅራቢያ ወደ አለ ገዳም ይሔድ ዘንድ እንጂ፤ ያን ጊዜም ተነሥቶ ሔዶ ወደዚያ ገዳም ደረሰ በገድላቸው ፍጹማን የሆኑ ዕውነተኞች አገራውያንን አገኘ እርሱ ከእርሳቸው እንደሚያንስ አወቀ እርሱ በዓለም ውስጥ ነው የኖረውና ስለዚህ ከእርሱ ይሻላሉ።

❖ በዚያ ገዳም ከሳቸው ጋር ኖረ ብዙ ዘመናትም አብሮአቸው ሲጋደል ኖረ፤ ለዚያ ገዳም መነኰሳትም ልማድ አላቸው ታላቁ ጾም በደረሰ ጊዜ የመጀመሪያውን አንድ ሱባዔ በአንድነት ይጾማሉ በቅድስት እሑድ ሥጋውንና ደሙን ይቀበላሉ በማግሥቱም ሰኞ ጥዋት ሃያ ስድስተኛ መዝሙር እግዚአብሔር ብርሃነ ረድኤቱን ሰጥቶ ያድነኛል የሚያስፈራኝ ምንድነው የሚለውን እሰከ መጨረሻው እየዘመሩ ይወጣሉ በሚወጡም ጊዜ ወደ በሩ ተሰብስበው በአንድነት ጸልየው እርስ በርሳቸው ሰላምታ ይሰጣጣሉ የገደሙ አበ ምኔትም ይባርካቸዋል።

❖ ከዚህም በኋላ እየአንዳንዱ ወደ በረሃ ይበተናሉ አንዱም አንዱ ባልንጀራውን ያየ እንደሆነ እንዳያየው ወደ ሌላ ቦታ ይሔዳል፤ ቅዱስ ዘሲማስም በየዓመቱ ከሳቸው ጋራ ወጥቶ በበረሀው ውስጥ ይዘዋወራል የሚጽናናበትንም ይገልጥለት ዘንድ እግዚአብሔርን ይለምነው ነበር፤ ሲዘዋወርም በበረሀ የምትኖር ግብጻዊት ማርያምን አገኘ ከእርሷም በልጅነቷ ወራት በእርሷ ላይ እንዴት እንደሆነና በበረሃም የሆነውን ኑሮዋን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተረዳ።

❖ ከዚህ በኋላም በሁለተኛው ዓመት ሥጋውንና ደሙን ያመጣላት ዘንድ ፈለገች እንዳለችውም አደረገላት፤ ለዚህም ጻድቅ ብሔረ ብፁዓን ይገባ ዘንድ ተገባው እርሱም ገድላቸውን ጻፈ ሥራቸውንና ጽድቃቸውን ገለጠ፤ ዘጠና ሦስት የሚሆን መላ ዕድሜው በተፈጸመለት ጊዜ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።

አርኬ
✍️ ሰላም ለዞሲማሰ ሶበ ጸለየ ወአበተብቍዐ። መጠነ ዓመታት አርብዓ። ብሔረ ብፁዓን በዊአ አምሳለ ማቴዎስ ቦአ። ኵሎ በሀየ እንተ ነጸረ ወሰምዐ። በውስተ ዓለም ከመ ይስብክ ወጽአ። https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

17 Nov, 09:38


አንቅዕተ ማኅሌት አንቅዕተ ውዳሴ
ምግባቸው ምስጋና ልብሳቸው ቅዳሴ
ዘወትር ይቀኛሉ ለቅድስት ሥላሴ /፪/

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 18:40


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር /፫/3

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 14:30


ነገ ኅዳር ፫/3 ቅድስት እናታችን በዓታ ለማርያም ናት።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ትሰውረን ።🙏

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 12:15


🌹#ወር በገባ በ3 ቅዱስ ፋኑኤል #መልከአ ቅዱስ ፋኑኤል📕

📗ለተፈጥሮከ📗
#በልዑል እግዚአብሔር እጅ ከቅዱሳን መላዕክት ጋራ በአንድነት ለተከናወነ ተፈጥሮህ ሰላምታ የሚገባህ ከሰዎች ላይ ዘወትር ሰይጣናትን የምታሳድድ ሊቀ መላዕክት _ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ_ ርኩሳን አጋንትን ወደ እኔ እንዳይቀርብ ገስጸህ ታስወግዳቸው ዘንድ እለምንሃለሁ።

በመለኮተ አብ_

በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን አንደበቴ የአጋእዝተዓለም ሥላሴ ባለሟል የሆነ የሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤልን_* ምስጋና እነሆ ጀመረ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ ምንም አንደበቴ ጎልዳፋ ቢሆንም ስምህን ስጠራ ፈጥነህ ምስጢርን በመግለጽ ትረዳኝ ዘንድ ድረስልኝ።

*_ለሲመትከ_*

በወረኃ ታኅሣሥ ሦስተኛይቱ ዕለት ነገስታት ከንጉሠ ነገሥት *_እግዚአብሔር_* ለተቀበልከው ሹመትህ ሰላምታ የሚገባህ ቅዱስ መንፈስም የተመላህ *_ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ_* በዚህ አዲስ ምስጋናህ ከስንፍና ለይተህ አንቃኝ። በሥጋና በነፍስም እርዳኝ ።

*_ለዝክረ ስምከ_*

ገናንነቱ ለሚያስደንቅ ዳግመኛም ከሰዎች ስም ይልቅ እጅግ ደስ ለሚያሰኝ ስምህ ሰላምታ የሚገባህ *_ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ ከአንተ ጋር እንደተፈጠሩ መላዕክት ለሰዎች ሁሉ አማላጅ ትሆን ዘንድ ፈጣሪዎችህ አጋእዝተ ዓለም *_ቅድስት ሥላሴ_* አንተን ሾሙ።

*_ለሥዕርተ ርእስከ_*

ደስ የሚያሰኝ የረድኤተ ዕጣን መዓዛን የተመላህ ለራስ ጸጉርህና ፍጹም ብርሃንን ለተሸከመ ራስህ ርእየተ ዐይንን ለሚያንፀባርቅ የከበረ መብረቅ ገጽህም ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ በርጉም ጠላቴ ሰይጣን ላይ ሰይፍህን ምዘዝ። የሚያስደንቅ የፊትህ ግርማም ለፊቴ ሞገስ ይኹነኝ።

*_ለቀራንብቲከ_*

ከብርሃናት የሚልቅ ፍጹም ብርሃንን ከአዩ ጊዜ ጀምሮ ለአላንቀላፋ ቅንድብህ ሰላምታ የሚገባህ የቅዱሳን አርባዐቱ እንስሳ ኪሩቤል ወገን ኃያል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ እንደ አንበሳ በመንገዴ ኹሉ ከሚሸምቅብኝ ጠላት በአማላጅነትህ ሥጋዬን አድን። ነፍሴንም ከጽኑዕ አበሳ አንጻት።

*_ለአዕዛኒከ_*

በምስጋና ቃል ዘወትር መለኮትን የምታመሰግን ለቅዱሳት ጆሮችህና ጒንጮች መልካም መዓዛ ስብሐትን ለሚያሸቱ አፍንጫዎችህም ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ መከራ በደረሰብኝ ጊዜ በረድኤትህ ጠብቀኝ እንጂ ከአንተ አታርቀኝ።

*_ለከናፍሪከ_*

የንጉሠ ነገሥት እግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነቱን ለሚያመሰግኑ አፍህና ከንፈሮችህ ሰላምታ የሚገባህ ክፉ የሰው ልማድ የሌለብህ ዐመፃንም የምትጠላ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ ይኸን ምስጋናህን አቃልሎ የሚዘብት ክፉ ሰው ይኖር ዘንድ በውኑ ተገቢ ነውን።

*_ለአስናንከ_*

እግዚአብሔር አምላክ ከእሳትና ነፋስ ለፈጠራቸው ለተቀደሱ አንደበትህና ጥርሶችህ ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ_* እባክህ! ተገለጽልኝ በወዳጅ ቃል አነጋግረኝ ጧትና ማታም በዕየለቱም እየጎበኝህ ከሀዘንና ከጭንቀት አውጣኝ።

*_ለቃልከ_*

ልዑል እግዚአብሔርን በእውነት የምታገለግል እንደ ነጎድጓድም ለሚያስተጋባ ቃልህና የተራቆቱትን ለሚያሞቅ እስትንፋስህ ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ ቅዱሳን መላዕክት ሁላችሁ በተፈጠራችሁ ግዜ የተጠራጠሩ መላዕክትማ ከማዕረገ ክብራቸው ፈጥነው ወደቁ።

*_ለጉርዔከ_*

በእግዚአብሔር ምስጋና የተመላች አንዲት ቅድስት ጎንህና አንገትህ ለትከሻዎችህም ሰላምታ የሚገባህ የመስሀቲ ዲያብሎስ ሐሳብም በልብህ ያልጎበኘህ ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ የመዋቲ አዳም የበደል መጠጥን ትጠጣ ዘንድ አልተመኝህምና ምስጋና ይገባሀል።

*_ለአክናፊከ_*

እሳተ ነበልባልን ለሚጎናጸፉ ክንፎችህ ከእሳትና ነፋስም ለተፈጠረ ጀግባህ ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት _*ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ*_ የሚያበራ ፊትህን አሳየኝ ወደ መንግስተ ሰማይ ትመራኝ ዘንድ በክንፎችህ እቀፈኝ።

*_ለእንግድዓከ_*

ለቅዱሳት ደረትህና የመባረቅት ብረሃንን ለተሸከመ ሕጽንህ ሰላምታ የሚገባህ መጋቤ ድንግል ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ_* ሰማያዊ የሕይወት ጽዋንና ሰማያዊ መናን *_ለእመቤታችን ድንግል ማርያም_* እንደመገብካት ለእኔም ምግብን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ።

*_ለአእዳዊከ_*

ሰማያዊ የብርሃን ሰይፍን ለሚይዙ እጆችህና ዳግመኛም የሰውን ልጅ ደግፈው ለሚያሳርፉ ክንዶችህ ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *_ፋኑኤል ሆይ_* ጠላቶቼ ገፍተው እንዳያጠፉ ዘወትር ከሚቃኙኝ አጋንት በክንፎችህ ጋርደህ ጠብቀኝ።

*_ለኩርናዓቲከ_*

ኃይላቸው ለጸናና አንድ ለሆኑ ቅዱሳን መከንጃዎች ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ በተሰበሰቡ ማኅበር ፊት ሁሉ ከፍ ከፍ አድርገኝ ። በሕይወቴ ህልፈት ግዜም ለነፍሴ ከአማላጅነትህ የተገኘ ድህነትን አድላት።

*_ለእራኅከ_*

ሰማያውያን መናና መጠጥን ለሚይዝ መሀል እጅህና እንደ ፀሐይ ለሚያበሩ ጣቶችህ ሰላምታ የሚገባህ ድንቅ ተዐምራትን የምታደርግ መልዐከ አድኅኖ ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ_* ከሰው ዘንድ ሁሉ አጋንትን ታሳድዳቸው ዘንድ ከቅዱሳን ሊቃነ መላዕክት ጋር አንተም በታላቅ ግርማ የተሾምህ ገናና መልዐክ ነህ።

*_ለአጽፋረ እዴከ_*

ብረሃን ተመልተው ለተፈጠሩ ጥፍሮችህና የምስጋና መብረቅን ለተሸለመ ጎንህ ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *_ፋኑኤል_* ሆይ ልቤ አንተን ወዷልና በገሃድ ተገልጸህ አይህ ዘንድ ፍቀድልኝ።

*_ለከርሥከ_*

የተወደደ ምስጋና መገኛ ለሆነ ሆድህና ከኮከብና ከፀሐክ ይልቅ ለሚያበራ ልብህ ሰላምታ የሚገባህ ቅዱሳንን የምትረዳቸው ለተገፋውም የምታዝን ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *_ፋኑኤል_* ሆይ ያዘነውንና የተከዘውን ሰው ሁሉ በአማላጅነትህ ይርዳው ዘንድ እለምንሃለሁ ።

*_ለኩልያቲከ_*

እንደ እሳት የሚያቃጥል ሰማያዊ ብረሃንን ለተጎናጸፈ ኩላሊትህና ለለመኑት ሁሉ ስለሚያዝን ሕሊናህ ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *_ፋኑኤል_* ሆይ ረዳቴ ስለሆንህ አዘውትሬ ስምህን ስጠራ ሳትዘገይ ፈጥነህ ድረስልኝ

*_ለአማዑቲከ_*

በአማላጅነትህ ይድኑ ዘንድ ፍጥረት ሁሉ ወደ አንተ አንጋጠው የሚማጸኑህ ለተቀደሱ አንጀቶችህና በሆድህ ውስጥ ለአሉ ንዋያተ ውስጥህ ሁሉ ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ በረድኤትህ ከላይኛው መልዐከ ሞት አመልጣለሁ።

*_ለኅንብርትከ_*

ከአምላክህ እግዚአብሔር ጽኑዕ ኃይል የተሰጠህ ከሥጋዊ ኅንብርት በላይ ለከበረ ኅንብርትህና በምስጋና መብረቅ ለተመላ ጭንህ ሰላምታ የሚገባህ ክብርህም ከፍ ያለ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *_ፋኑኤል_* ሆይ ክፉዎች አጋንትን ከእኔ አርቃቸው

*_ለአቀያጺከ_*

ዕሩያን በሆነ አጋእዝተ ዓለም *_ቅድስት ሥላሴ_* ለተፈጠሩ ቅዱሳን ጉልበቶችህና ጭኖችህ ሰላምታ ይገባሀል። የልዑል እግዚአብሔር ወዳጅ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *_ፋኑኤል_* ሆይ ዐሥሩ ቃላተ ወንጌልን ለመፈጸም እችል ዘንድ አጽናኝ ። ከአጠገቤም የሚጠሉኝን ሁሉ አርቅልኝ።

*_ለአእጋሪከ_*

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 12:15


ለአምላክ ምስጋናን የምታቀርብ ፆፉ ራማ ያለ ምንም ድካም በነዲድ እሳት ላይ ለሚቆሙ እግሮችህና ተረከዝህ ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ ከዘማይቱ ባቢሎን ወገን በተገኘ በደለኛ ጠላቴ ፊት እንዳላፍር በአማላጅነትህ ሞገስህን አጎናጽፈኝ።

*_ለመከየድከ_*

መጫሚያቸው እሳት ለሆነላቸው የእግርህ መረገጫና በቅድስና ለተመሉ ጣቶችህ ሰላምታ የሚገባህ ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ_* ከተመረጡ ቅዱሳን ጋር ወደ መንግስተ ሰማያት እገባ ዘንድ እኔ ኅጥእ ወዳጅህ ........እኅተ መስቀልን..... በእጅህ እየመራህ የፈጣሪዬ *_እግዚአብሔር_* ወልድ ማደሪያ መንግስተ ሰማያትን አሳየኝ ።

*_ለአጽፋረ እግርከ_*

ተፈጥሮአቸው ለተዋበ በዐሥሩ ጣቶችህ ላይ ለተሸለሙ ቅዱሳን ጥፍሮችህ ሰላምታ የሚገባህ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋይ ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ ቅዱስ *_ሚካኤል_* እስራኤል እንደ መገባቸው ከሰማይ መናን አውርደህ ትመግበኝ ዘንድ እለምንሃለሁ

*_ለቆምከ_*

ዝክርህ ከቀናንሞስ ይልቅ የጣፈጠ የተቀደሰ አካለ ቁመትህን ሁሉ ሰላም እያልኩ ክብርና ምስጋና ለቅዱስ መልክዕህ ሁሉ የማቀርብልህ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *_ፋኑኤል_* ሆይ በደል በሽታ ከላዬ ይወገድ ዘንድ ሥጋ መለኮትን በጉጠትህ ስጠኝ

*_እዌድስ_*

*_መጋቤ ድንግል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል_* አንተን አባትና እናት አድርጌሀለሁና ምን ብዬ አመሰግንህ ዘንድ ይቻለኝ ይሆን?? ስለዚህም ምግባርን በአማላጅነትህ ታሰጠኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ።

*_አዕርክተ ንጉሥ_*

*_ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ የምድራዊ ንጉስ ወዳጆች ስንኳ ለሚወዷቸው ሁሉ የሚገባ ሹመትና ክብርን ከንጉሣቸው ይለምናሉ አንተም ወዳጅህ ሰማያዊው ንጉስ እግዚአብሔር ፈጣሪህ በችግሬ ግዜ ሁሉ እንዲረዳኝ ከዚህ አለም በተለይሁም ግዜ ይቅር ይለኝ ዘንድ ለምንልኝ ።

*_እምፈለገ ኤፍራጥስ_*

የትጉሃን መላዕክት አለቃ ርህሩህ ካህን ሊቀ መላዕክት *ቅዱስ ፋኑኤል* ሆይ ከኤፍራጥስና ከግዮን ከኤፌሶንና ከጤግሮስም ወንዞች ይልቅ የኃጢአቴ ጉርፍ እጅግ በዝቷልና ካህን የህዝብን በደል ይቅር እንደሚያሰኝ በደሌን ታስተሠረይ ዘንድ በይቅርታ ቃል እኔ ኅዘንተኛ ልጅህን አጽናናኝ።

*_ክንፍህ_*

በአምላክ እግዚአብሔር ፊት የምስጋና መለከትን የምታሰማ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ አስጨናቂ የዓመጻ ጨለማ ገዢ ዲያቢሎስ ርነሆ ሊውጡኝ ያጋሳልና ክንፍህ ከወጥመዱ እንዲ ሠውረኝ እርዳኝ ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ ዐንበሪ ሆድ ተሰውሮ ከሞት እንደዳነም አድነኝ ።

*_ሀገሪተ ብርሃን_*

ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ ጠላቶቼ አጋንትን አንዲት ስንዝር ስንኳ ለማለፍ ከልክለውኛልና የሚያስፈራ የበደል ማልዕበል እንዳያሰጥመኝ የሚፈላ የእሳት ነዳድም እንዳይውጠኝ ክንፍህን ዘርጋልኝ ። ከሁሉም በከበረች አሜላጅነትህም መንግስተ ሰማይን እወርስ ዘንድ ወደምታበራ ቅድስት ሀገር ገነት ምራኝ።

*_ኢይፈቅድ_*

ሊቀ መላዕክት *_ቅዱስ ፋኑኤል_* ሆይ ፈጣራህ ልዑል እግዚአብሔር የኃጢአተኛ መመለስን እንጂ ጥፋቱን አይሻምና በዚህ አለም የተገፉ ቅዱሳን መንግስተ ሰማይን በሚወርሱ ግዜ እኔንም ከእነሱ ጋር ይደምረኝ ዘንድ ሲሠለስ ሲቀደስ ከሚኖር ፈጣሪ ልዑል እግዚአብሔር ምሕረትህን ለምንልኝ።

*_ነአ ኅቤየ_*

ልብህ የርኅራኄ ውኃ መፍሰሻ የሆነ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ በአስጨናቂ ቁር የሚመሰል ሰይጣን ወደ ልቤ እንዳይገባ ጧትና ማታም የከበረ ኑሮዬን ትጎበኝ ዘንድ ከወዳጅህ ነብይ ኄኖክ ጋራ ናልኝ ።

*_ነአ ኅቤየ_*

የእሳት መጎናጸፊያን የምትጎናጽፍ ካህን ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *ፋኑኤል* ሆይ የሚጠትን ነገር ይነግረው ዘንድ ወደ ነቢይ ዳንኤል ከተላከ ቅዱስ ሚካኤል ጋራ ወደ እኔ ና ። በረዶ በደጋ ተራሮች ላይ እንደ ሚወርድ በልቤ መሠዊያ ላይ የጥበብ ጸጋን ተአወርድ ዘንድ ፈጥነህ ድረስልኝ ።

*_ነአ ኅቤየ_*

ሊቀ *መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ* ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የምሥራችን በአበሠራት ግዜ እውነትን ከተናገረ በወርቅ ዘንጉም ነደ እሳትን ከአጠፋ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ጋር መጥተህ የሰላም ብሥራትን አሰማኝ።

*_ነአ ኅቤየ_*

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ ከተባረከ ጦቢት ቤት ክፉ ጋኔንን ለማውጣት ከተገለጸ ቅዱስ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል ጋር መጥተህ በጠላቴ ፊት ጋሻ ሁንልኝ ። በሚያንፀባርቅ ሰማያዊ ባህር ላይም ከአንተ ጋር ቆሜ ምስጋናን ለእግዚአብሔር አቀርብ ዘንድ ርዳኝ ።

*_ነአ ኅቤየ_*

እሳተ ነበልባልን የተጎናጸፍህ የከበርክ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ በጨረቃና ፀሐይ ላይ ያዝዝ ዘንድ ከተመረጠ ከሊቀ መላዕክት ቅዱስ *ራጉኤል* ጋር መጥተህ ከግብጽ ኃጢአት ተለይቼ መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ እኔ ወዳጅህን የንስሐ ጠለ ፍቅር እንዲያለመልመኝ እማፀንሀለሁ።

*_ነአ ኅቤየ_*

ደስ በሚያሰኝ ድምፅህ ምስጋናን ለአምላክህ እግዚአብሔር የምትሰዋ ካህን ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ ስለ ሕዝቡ ትንቢትን ለተናገረ ነቢይ ዕዝራ በበረኅ የሕልምን ምስጢር ከተረጎመለት ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *ዑራኤል* ጋራ ና የተወደደ የሕይወት መንፈስ ያድነኝ ዘንድም እኔ ሀዘንተኛ ወዳጅህን ዛሬ ሰላምህ ይጎብኘኝ።

*_ነአ ኅቤየ_*

መታሰቢያህ ከቀናንሞ ዛፍ ይልቅ ለዘላለም የሚለመልም ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ ለሰው ልጆች ሁሉ ምሕረትን ከሚል ምን ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *ሳቁኤል* ጋራ ናልኝ እንደ ሊቀ ካህናት ዔሊ መሥዋዕትን ልመናዬ ከንቱ እንዳይሆን የኃጢአትን ፍሬ በኡማላጅነትህ ከእኔ ዘንድ አስወግድ።

*_ነአ ኅቤየ_*

በአማላጅነትህ ብዛት ዘመንን የምታሰጥ ዓቃቤ ሕይወት ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ ከፈጣሪው ተልዕኮ መርከብን ይሠራ ዘንድ ለጻድቁ ኖህ ጥበብን ከገለጸለት ሁሉን ከሚያረጋጋ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ *ሱርያል* ጋራ በዓለም ሁሉ መርዙን የሚረጭ የጨለማ አበጋዝ ሰይጣን ሥልጣንም በላዬ እንዳይሰለጥንብኝ ጠብቀኝ።

*_ነአ ኅቤየ_*

የመብረቅ ነፀብራቅ መዞሪያ በሆነው ምዕላደ ሰማይ የተሾምህ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ እንደ ነጎድጓድ የሚላስገመግምና የሚያረጋጋ ግሩም ድምጽህን በምታስፈራ አደባባይ እሰማ ዘንድ እንደ በረዶ የነጣ ብረሃናዊ መንበር በሰማይ ተሸክመው እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን *አርባዕቱ እንስሳ ኪሩቤል* ጋራ ና

*_ነው ኅቤየ_*

ማኅበረ ሰይጣናትን የምታሳድድ ነዲድ እሳታዊ መላዕክት ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ ለዘላለም እውነትን እንድከተል እርዳኝ። በአማላጅነትህም ኃጢአት ከሚያመጣው በደል አንጻኝ። ሸማቂ ጠላት ሰይጣንም ወደ ልቤ እንዳይገባ የልቤን እምነት ቁልፍ አጽናልኝ።

*_ዐስበ ማኅሌት_*

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ ሦስት የመልክህን ምስጋናዎች በማስከተል ዐርባ ያህል የመልክህን መግለጫ ምስጋናዎች እነሆ ፈጸምኩ። አንተም ይህንን ምስጋናዬን ተቀብለህ አንዲቷን ኅምሳ መቶ በእየመቶውም ዕጥፍ አድርገህ ለእኔ ለወዳጅህ በጎ ዋጋን ከፈጣሪ ታሰጠኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ።

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 12:15


በአንተ ለሚያምኑ ሁሉ ምሕረትን ይለምን ዘንድ በሥልጣናት ላይ አለቃ አድርገህ መጋቤ ድንግል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤልብ የሾምከው የቅዱስ ፋኑኤል አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ እኔ ባሪያህን ........እኅተ መስቀልን....ስለ ወዳጅህ መጋቤ ድንግል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ብለህ ከሥጋና ነፍስ መከራ ሁሉ ሠውረኝ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን ወአሜን.......
*አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር.....*

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 12:15


" 3 በዓታ ለማርያም ማለት

✞ እመቤታችን የብጸሐት ልጅ ናት ( የስለት ልጅ) 3 ዓመት ሲሆናት አፍዋ እህል ሳይለምድ ሆድዋ ስው ሳይውድ ብለው እናት አባትዋ ውስደው ለቤተ እግዚአብሔር ስጡዋት ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ይባላል ✞ የእመቤታችን መልኳ እንደ ፅሀይ ሲያበራ አይቶ ይእችን የመስለች ውብ ብላቴና ተረክቤ እንደምን አድርጌ አኖራታለው ብሉ ደውል አስምቶ ካህናትን ስብስቦ የምግቧን ነግር ሲማከሩ መልአኩ ቅዱስ ፋኖኤል ዕብስት ስማያዊ ጸዋ ስማያዊ ይዞ ከላይ እርቦ ታየ
ሊቀ ካህናቱ ዛሬ ሀብቴን ክብሬን በስው መካከል
ሊገልጥልኝ መስለኝ ብሎ ሊቀበል ቀርበ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀበት
+ ካህናቱም ሊቀበሉ ቀርቡ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው
+ እህሩገ እስራኤልም ቀርቡ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው
+ ሐና እያቄምም ሊቀበሉ ቀርቡመልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው
ሐና ምን አልባት ለዚህች ብላቴና የውርደ መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን አይቀርምና እስኪ ትተሻት ጥቂት እልፍ በይ አሏት ትታት ትንሽ እልፍ ብትል መልአኩ ውርዶ ግራክንፉን አንጥፋ ቀኝ ክንፈን አጉናጸፏ በቆመ ብዕሲ አድርጉ መግቧት አርጓል
"ምግቧ ሰማያዊ ነው ሲል ነው "
የምግቧ ነግር ከተያዘልን ይህችን ውብ ብላቴ ከስው ጋራ ምን ያጋፈታል ኖሮዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን ብለው ከቤተመቅደስ አግብተው አኖርዋት ሄደዋል
እመቤታችንም መላእክት ሊቃነ መላዕክት አያጫውትዋት እያርጋጓት 12ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀምጠች ከእናት አባትዋቤት 3ዓመት በአጠቃላይ 15ዓመት ሲሆናት

🌿💖 አይሁዶች መቼም ለምቀኝነት አያርፉምና ይእች ብላቴና ለአቅመ ሔዋን ደርሳለች እሷን ያለ ጉልማሳ በቤተ መቅደሳችን አስገብተን ቤተ መቅደስሳችንን ታርክስብናለች እንዲያውም ጠረጠረናት ትውጣልን የጠየቀችሁን አድርግላት አሉት

🌿💖 ሊቀ ካህናቱም ዘካርያስ ከእመቤታችን ሄዶ ልጄ እንደምን ብለሽ መኖር ትውጃለሽ አላት
እመቤታችንም ፍፃምተ ፈቃድ ፤ ትሁት ናትና እንግዲህ ከእግዚአብሔር በታች ያለከኝ አባት አንተ ነህ ውደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ አለችሁ

🌿💖 ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት ጌታ ስራውን ያለ ምክንያት አይስራውምና ከነገደ ይሁዳ ሚስቱ የሞተችበትን በትር ስብስበ በቀዳማይ ሰዓታት ሌሊት ይዘህ ገብተ ስትፀልይበት እደር ከዚያ ምልክት አሳይካለው ለዕዚያ ስው ስጣት አለው

🌿💖 ሊቀ ካህናቱም በትር ቢስበስብ 9መቶ 1985 በትር ሆነ ያንን በቀዳማይ ስዓት ሌሊት ይዙ ገብቶ ሲጸልይበት ቢያድር
+ በዮሴፍ በትር ላይ የሎሚ ቅጠል አብባ አፍርታ ታየች
+ እርግብም በዮሴፍ እራስ ላይ አርፈለች
+ እጣም ቢጥሉ ለዮሴፍ ደርስው በሦስት ምስክር ለዮሴፍ ደርስች
ሱባዬ ገብተን የስጠንክን ሱባዬ ገብተን እስክንቀበልክ ድርስ ጠብቃት ተንከባከባት አሉት የዮሴፍም ይዟት ውደ ቤቱ ሄደ።
ከቤቱ አኑሯት ዘመኑ የንግድ ውቅት ነበርና ወደ ንግድ ለመሄድ ዕለቱን ተሸኝቶ አድሯል ዮሴፍ ከ3ወር በሀላ ተመለስ ዮሐንስ የሚባል ፍላስፍ ወዳጅ ነበርው ሊጠይቀው መጣ ጥቂት ተጨዋወተው ሊሄድ ተነሳ ሊሽኘው ውጣ
ዮሴፍ ይህች ብላቴና ፀንሳለች ከአንተ ነው ወይስ ከሌላ አለው በምን አውቀው ቢሉ በፈልስፈና የጌታስ ፀንስ በፈልስፈና አይታውቅም ብሎ
ሴቶች ሲፀንሱ ከቀደመው ይልቅ መልካቸው ያምራል ጡታቸው ይጦቅራል ከንፈራቸው ይደርቃል በዚያ አውቆ።

🌿💖 ዮሴፍም አር እኔ እንኳን ግቢር ቀርቶ ሐልኦም አልውቅባትም አለው እንግዲያውስ ስስነች ተብላ እንዳትውገርብህ ገብተህ ጠይቀ ተረዳ አለው።
ዮሴፍም ውደ ቤት ተመልሶ ድንግል ማርያምን
የፀነሽው ከማን ነው ብሎ ጠየቃት
ድንግልም ከመንፈስ ቅዱስ ነው አለችሁ ከዚህ በፈት እንዲህ ተደርጉ አያውቅም እና ነገሩ እርቀቀበት ቢርቀው ከደጅ ወድቆ ይኖር የነበር ደርቅ ግንድ አለ ይሀንን አለምልማ አብባ አፈርታ አሳይታዋለች

🌿💖 በዚያውስ ላይ ዐፁቅ በባህሪያቸው እንዲያብቡ ንቦችን እንዲራቡ የሚያደርግ ጌታ እኔንስ በእቱም ድንግልና ፀንሼ በህቱም ድንግልና እንድውልድ ቢያደርገኝ ይሳነዋል ትላለክ???
ብላ ነገሩን እንደዚህ አስርድታዋለች

🌿💖 ይህም አልቀርም ውድያው ለባህል የሚውጡበት ጊዜ ደርስ የሴፍም ትቺያት ብሄድ ያደርገውን አውቆ ትቷት መጣ ይሎኛል
ይዥትም ብሄድ ሴስነች ብለው በድንጋይ ወግርወ በእሳት አቃጥለው ይገድሉብኛል ምን ይሻለኛል እያለ ይህን ሲያውጣ ሲያውርድ መላከ እግዚአብሔር በህልም ታየው ተነጋገርው
ዮሴፍ ከእርሷ የሚወለደው የአብ አካለዊ ቃል በግብር መንፈስ ቅዱስ ነውና አይዞህ አትፈሪ ይዘሀት ውጣ አለው ይዝዋት ውጥቷል ነገሩም አልቀርም

" 🌿💖 ማየ ዘለፈአጠጧት " ይህ በኦሪቱ ልማድ ነው ባልየው መንፍሳዊ ቅናት ተነሳስቶ ከሌላ ውንድ ደርሳለች ብሎ ሚስቱን የጠርጠራት እንደሆነ
" አሪፀ ስግምን ውሃ በገንቦ አሲዞ እራሷን አከናንቦ ወደ ቤተ መቅደስ ይዟት ይሄዳል ሊቀ ካህናቱ ከምህዋሩ ለይ ሆኖ ክንብንብሽን ግለጭው ይላታ እንዲህ ይግለጥብኝ በይ ሲያስኛት ነው

🌿💖 ከኦሪቱ የሚደገም የሚነበብ የሚጸለይ አንዳንድ አለ
ሊቀ ካህናቱ ያንን ደግሞ ህራር እጣኑን አመደ ምስዋቶን በጥብጦ ባልሽ የጠርጠርሽን አድርገሽ ስውርሽ እንደሆነ
ስውነትሽ ይበጥ ፣ ጉንሽ ይላጥ ፣ አጥንትሽ ይርገፍ
አላደርግሽው እንደሆነ
በውንድ ልጅ ይታርቅሽ ብሎ ይስጣታል
እርሷም አሜን ውአሜን ብላ ተቀብላ ትጠጣዋለች ።

🌿💖 እርግማኑ ይደርግብኝ ምርቃኑ ይደርግልኝ ስትል ነው ባልዋ የጠርጠራትን አድርጋ ስውራ እንደሆነ ውድያው ስውነቷ ያብጣል ፣ጉንዋ ይላጣል ፣አጥንቷም ይርግፈል
ያላደርገችው እንደሆነ በውንድ ልጅ ይታርቃታል
በዚያ ልማድ ነው

🌿💖 ለእመቤታችንም ቢያጠጥዋት ፈትዋ ከፀሐይ ስባት እጅ አብርቶ ተገኘ ታየ ከዚያ የተስበስ ህዝቡ ይህችን ብላቴ ባላደርገችው ነገር በከንቱ አምተናታል ብለው
የተናገሩት ለእርሷ ስጥቶ ውይትፀርይ ብሉ ተናገር።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች እንዲህ ብላ ተናገርች መላኩ ቅዱስ ገብርኤል ከነገርኝ ነገር ቃል በቀር ሌላ እንደማላውቅ እግዚአብሔር ያውቃል ብላ ተናገርች ።

✞ ንፅህት ድንግል ማርያም አምላክን ለመውለድ የታመነች ናት
✞ አምላክን ለመውለድ የታመነች ድንግል ማርያም ብቻ ናት
✞ የስውን ልጅ ለማማለድ ድንግል ማርያም የታመነች ናት

🌿💖 ድንግል ሆይ !!! የማይውስነውን ውስንሽ
የማይቻለውንን ቻልሽ ምንም ምንም ሊችለው የሌለውን ቻልሽ
ምልዕተ ፀጋ ምልዕተ ክብር እመቤታችን የአብ አካላዊ ቃል ማደሪያው ድንግል እመቤታችን
የማህፀኗ ፈሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለሙን ሁሉ አዳነ
ከእኛ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን አጠፈ

🌿💖 እመቤቴ ማርያም ሆይ
ዘር ያልወደቀባት ገበሬ ያልጣረባት የቅዱስ ቁርባንን አዝመራ ያፈራሽ ገራህት ሆይ፤ ከትጉሃን መላእክት ጋር ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡

🌿💖 ድንግል እመቤቴ ሆይ
ብልህ አዋቂ የሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ያፈቅራል፤ ሰነፍ ልበ ቢስ ግን በከንቱ ይጠላሻል፤ ዳሩ ግን በመከረው የተንኮል ምክር ወጥመድ እሱ ራሱ ይጠመድ፡፡

🌿💖 እመቤታችን ድንግል ማርያም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
ድንግል ሆይ ከልጅሽ ከውዳጅሽ ከኢየሱስ ከክርስቶስ ለምኝልን ከሀጥያታችንን ያስተስርይልን ዘንድ አሜን!!!
ወስብሓት ለእግዚአብሔርው
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 12:15


=>+"+ እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን "አቡነ መድኃኒነ እግዚእ" : "ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል" እና "ቅዱስ ኪርያቆስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" አቡነ መድኃኒነ እግዚእ "*+

=>መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጭ ኢትዮጽያውያን አባቶች ትልቁን ሥፍራ እኒህ አባት ይወስዳሉ:: የማር ወለላን በሚያስንቅ ጣዕመ ሕይወታቸው ሃገራችንን ያጣፈጡ: ብርሃን ሆነው ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው::

+አባ መድኃኒነ እግዚእ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ትግራይ (አዲግራት) ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸውም ቀሲስ ሰንበትና ሒሩተ ማርያም ይባላሉ:: በደግነትም እጅግ የታወቁ እንደ ነበሩ ገድላቸው ይናገራል:: "መድኃኒነ እግዚእ" ማለት "ጌታ መድኃኒታችን ነው" ማለት ነው::

+ብዙ ጊዜም "ዘደብረ በንኮል - ሙራደ ቃል" እየተባሉ ይጠራሉ:: "ደብረ በንኮል" ማለት ትግራይ ውስጥ የሚገኝና ጻድቁ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ያነጹት ገዳም ነው:: "ሙራደ ቃል" ደግሞ "የቃል (የምሥጢር) መውረጃ" እንደ ማለት ሲሆን በቦታው ሱባኤ የያዘ ሰው ልክ እንደ ቅዱስ ያሬድ ምሥጢር እንደሚገጥለት የሚጠቁም ስም ነው::

+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በልጅነታቸው ከሊቁ ካህን አባታቸውና ከሌሎችም መምሕራን ተምረው: ምናኔን መርጠው ገዳም ገብተዋል:: በጾም: በጸሎትና በስግደት ተግተው ጸጋ እግዚአብሔር ሲሰጣቸው ወደ ደብረ በንኮል ሒደው ገዳም መሠረቱ::

+በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን (በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
*ክርስትና ያበበበት::
*መጻሕፍት የተደረሱበት::
*ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
*ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::

+ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ:-
¤አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤አባ ሰላማ ካልዕ::
¤አቡነ ያዕቆብ::
¤ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::

+በተጨማሪም:-
¤12ቱ ንቡራነ ዕድ::
¤7ቱ ከዋክብት::
¤47ቱ ከዋክብት::
¤5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::

+ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም (ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ የገዘቱ አባት ናቸው) የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ ይባላል::

+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በተትረፈረፈ የቅድስና ሕይወታቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: አራዊትን ገዝተዋል: በአንበሳ ጀርባ ላይ እቃ ጭነዋል:: ከረዥም የተጋድሎ ሕይወት በሁዋላም ኅዳር 3 ቀን ዐርፈዋል:: እድሜአቸውም 180 ነው::

¤" መድኃኒነ እግዚእ አቡነ መስተጋድል::
ምንኩስናሁ ምዑዝ ከመ ኮል::
በመንፈሰ ጸጋ ክሉል::" (መጽሐፈ ሰዓታት)

¤" ተአምረ ኃይልከ አባ መድኃኒነ እግዚእ አቡነ::
እም አፈ ዜናዊ ሰማዕነ:: ወበዓይነ ሥጋ ርኢነ::
መንክርኬ አእላፈ ቤትከ ንሕነ::
ባሕቱ በዝ ተአምሪከ ርድአነ::
ለሰይፈ አርዕድ ንጉሥ ዘወሀብኮ ኪዳነ::
ከመ ረድኤቱ ታፍጥን ጊዜ ጸብዕ ኮነ::" (አርኬ)

+"+ ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል +"+

=>የዚህ ቅዱስ ኢትዮዽያዊ ዜና ሕይወት ለሁላችንም ትልቅ ትምርትነት ያለው ነው:: በተለይ በምክንያት ከቅድስና ሕይወት እንዳንርቅ ያግዘናል ብየም ተስፋ አደርጋለሁ:: የቅዱሱ ወላጆች ገላውዴዎስና ኤልሳቤጥ ሲባሉ በምድረ ሽዋ በበጐ ምጽዋታቸው የተመሰከረላቸው ነበሩ::

+ፈጣሪ ሰጥቷቸው ኅዳር 8 ቀን (በበዓለ አርባዕቱ እንስሳ) ወልደውታልና "ዓምደ ሚካኤል - የሚካኤል ምሰሶ" ሲሉ ሰይመውታል:: ገና በልጅነቱ ብዙዎችን ያስገርም የነበረው ቅዱሱ አንዴ በ3 ዓመቱ ከቅዳሴ መልስ ጠፋቸው::

+ወላጆቹ እያለቀሱ በሁሉ ቦታ ፈለጉት:: ግን ሊገኝ አልቻለም:: በ3ኛው ቀን የሞቱን መታሠቢያ ሊያደርጉ ካህናትና ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ግን ባዩት ነገር ተገረሙ:: ሕጻኑ ዓምደ ሚካኤል ከቤተ መቅደሱ መሃል: ከታቦቱ በታች ካለው መንበር (ከርሠ ሐመር ይሉታል) ቁጭ ብሎ ይጫወታል::

+ያየ ሁሉ "ዕጹብ ዕጹብ" ሲልም አደነቀ:: ምክንያቱም በተፈጥሮ ሥርዓት ሕጻን ልጅ ያለ ምግብ 3 ቀን መቆየት ስለማይችልና ሕጻኑ በዚያ የቅድስና ሥፍራ ላይ ምንም ሳይጸዳዳ በመገኘቱ ነው::

+ብጹዕ ዓምደ ሚካኤል ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እየተማረ: በጾምና በጸሎት አደገ:: በ15ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ላይ ንጉሥ የነበረው ጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ቅዱሱን የሠራዊት አለቃ (ራስ ቢትወደድ): ወይም በዘመኑ አገላለጽ የጦር ሚኒስትር አድርጐ ሾመው::

+መቼም እዚህ ቦታ ላይ ተቀምጦ መልካምን መሥራት ልዩ ነገርን ይጠይቃል:: በተለይ ደግሞ በዙሪያው የሚከቡትን ተንኮለኞች ድል መንሳቱ ቀላል አልነበረም:: ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ግን በዘመነ ሲመቱ እነዚህን ሠራ:-

1.በጠዋት ተነስቶ ነዳያንን ይሰበስብና ቁርስ: ምሳ ያበላቸዋል:: ይሕም ዕለት ዕለት የማይቁዋረጥ በመሆኑ ሃብቱ አልቆ ደሃ ሆነ::

2.ከቀትር በሁዋላ ዘወትር ቆሞ ያስቀድስና ጸበል ተጠምቆ ይጠጣል:: ማታ ብቻ እህልን ይቀምሳል::

3.ሽፍታ ተነሳ ሲባል ወደ ዱር ወርዶ: ጸልዮ: ሽፍታውን አሳምኖት ይመጣል እንጂ አይጐዳውም::

4.ጦርነት በሚመጣ ጊዜ ክተት ሠራዊት ብሎ ይወርዳል:: ግን ለምኖ: ጸልዮ: ታርቆ ይመጣል እንጂ ጥይት እንዲተኮስ አይፈቅድም ነበር::

+በዚህ መንገድ በ3ቱ ነገሥታት (በዘርዐ ያዕቆብ: በዕደ ማርያምና እስክንድር) ዘመን ሁሉ አካባቢውን ሰላም አደረገው:: ዓለም ግን ዓመጸኛ ናትና በአፄ እስክንድር ዘመን (በ1470ዎቹ) በሃሰት ተከሶ ስደት ተፈረደበትና ወደ በርሃ ተጋዘ::

+በዚያም ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መናን እየመገበው: ሥጋ ወደሙን እያቀበለው ኖረ:: ትንሽ ቆይቶ ግን የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በንጉሡ አደባባይ ተገደለ:: ለ30 ቀናትም በመቃብሩ ላይ የብርሃን ምሰሶ ወረደ በዚህም ንጉሡ በእጅጉ ተጸጸተ::

+"+ ቅዱስ ኪርያቆስ +"+

=>ሊቅነትን ከገዳማዊ ሕይወት የደረበው ቅዱስ ኪርያቆስ የቆረንቶስ ሰው ሲሆን አበው "ጥዑመ ቃል - አንደበቱ የሚጣፍጥ" ይሉታል:: ገና በልጅነቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲያነብ ከአንደበቱ ማማር: ከነገሩ መሥመር የተነሳ ከዻዻሱ እስከ ሕዝቡ ድረስ ተደመው ያደምጡት ነበር::

+በወጣትነቱ ጣዕመ ዓለምን ንቆ ከቆረንቶስ ኢየሩሳሌም ገብቷል:: ቀጥሎም ወደ ፍልስጥኤም ተጉዞ የታላቁ አባ ሮማኖስ ደቀ መዝሙር ሁኖ መንኩሷል:: በገዳሙ ለበርካታ ዘመናት ሲኖርም እጅግ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል::+በ381 ዓ/ም መቅዶንዮስ: አቡሊናርዮስና ሰባልዮስ በካዱ ጊዜም ለጉባኤው ወደ ቁስጥንጥንያ ከሔዱ ሊቃውንት አንዱ ይሔው ቅዱስ ኪርያቆስ ነው:: ወደ ጉባኤው የሔዱትም ከታላቁ ሊቅና የኢየሩሳሌም ሊቀ ዻዻሳት ቅዱስ ቄርሎስ መንፈሳዊ ጋር ነው::+ሁለቱ እጅግ ወዳጆች ነበሩና:: በጉባኤውም ከሀዲያንን ረትተው: ሃይማኖትን አጽንተው: ሥርዓትን ሠርተው ተመልሰዋል:: ቅዱስ ኪርያቆስም በተረፈ ዘመኑ በቅድስና ኑሮ በዚህች ቀን

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 12:15


ዐርፏል::=>አምላከ አበው የወዳጆቹን የቅድስና ምሥጢር ለእኛም ይግለጽልን:: በረከታቸውንም አትረፍርፎ ይስጠን::

=>ኅዳር 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ጻድቅ (ዘደብረ በንኮል)
2.ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ጻድቅ (የሠራዊት አለቃ)
3.ቅዱስ ኪርያቆስ ሊቅ
4.ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ንጉሥ (ልደቱ)
5.ቅዱሳን አትናቴዎስና እህቱ ኢራኢ (ሰማዕታት)
6.አቡነ ፍሬ ካህን

=>ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)

=>+"+ በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል:: +"+ (ምሳሌ 10:6)

<< <ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>>

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 12:15


🌹#ተአምረ_አባ_ሊባኖስ📗

☞ወር በገባ በ3 ታስበው የሚውሉት አባታችን አባ ሊባኖስ ያደረጉት ተአምር ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር ይኑር ለዘአለዓለሙ አሜን፡፡
☞ከንጉስ ጭፍራዎች የታመመ ትከሻውም ከጉልበቱ ጋር እስከሚገናኝ የጎበጠአንድ ወታደር ነበር፡፡

☞ወደ አባታችን ወደ አባ ሊባኖስም ቦታ በፈረስ ጭነው አምጥተው አባታችን
አባ ሊባኖስ በመስቀል ባርኮ ባፈለቀው በሕይወት ውሃ አጠመቁትና በክብር
አባታችን በአባ ሊባኖስ መቃብር ውስጥ አስቀመጡት፡፡
☞ከዕለታት በአንድ ቀን ካህናቱ በማህሌት እያመሰገኑ ሳለ የዚያ በሽተኛ
አጥንቶቹ ሲንቋቁ ከቤተክርስቲያን እንጨት የተሰበረ መስሏቸው ወደ
ቤተክርሲቲያኑ ጠፈር ይመለክቱ ጀመር፡፡
☞ዳግመኛም ወደዚያ በሽተኛ ሮጠው ቢሄዱ ሁለተናዉ ተቃንቶ ድኖ አገኙት፡፡
ከተኛበትም አነሱትና እግሩና ወገቡ ፀንቶለት ተቃንቶ በእግሩ ሄደ፡፡
☞አንድ ካህንም ወንድሜ ሆይ እንደምን ሆነህ ዳንክ ብሎ ጠየቀው እሱም ተኝቼ
ሳለ አንድ ሰው በመነኩሴ ተመስሎ ወደ እኔ መጣና በመስቀል ምልክት በላዬ
ላይአማተበ አጥንቼ ሁሉ እየተንቋቁ ጮኹ ይኸው ዛሬ እንደምታየኝ ተቃንቼ ድኜ
አለሁ አለ፡፡
☞ያየና የሰማ ሁሉ እግዚአብሔር አመሰገኑ፡፡ለቅዱስ ለአባ ሊባኖስ ፈጽሞ
ተገዙለት፡፡
☞ያም በሽተኛ አባታችን አባ ሊባኖስ በፀሉቱ ከአፈለቀው ከፀበሉ ይዞ ወደ ንጉሱ
ወደ ሰይፈ አርዕድ ሄደ፡፡
☞በዚህ ምክንያት ንጉሱ ሰይፈ አርዕድ ወደደው ያን በሽተኛ ያየውም ሰው ሁሉ
አደነቀ፡፡
☞ያም በሽተኛ ብዙ ገንዘብ ሁሉ ለአባ ሊባኖስ ቤተክርስቲያን አወረሰ፡፡ስሙም
መጣዕ መሐሮ ተባለ፡፡
☞የአባታችን የአባ ሊባኖስ ጸሎት በረከታቸው ከሁላችን ከተዋህዶ ልጆች ጋር
ይሁን፡፡
☞ገድለ አቡነ ሊባኖስ
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

https://t.me/Orthodoxtewahdoc ቤተሰብ ይሁኑ

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 08:53


ድንግልን በዚህ መዝሙር እንዲህ እንበላት 🥹🙏

ለምኚ ድንግል ለምኚ

ለምኚ ድንግል ለምኚ /2/ 
ለኃጥአን /3/ አኮ ለጻድቃን                

ለምኚ  ታላቅ ስጦታዬ               
ለምኚ  አዛኝ ሩህሩህ ነሽ            
ለምኚ  የጌታዬ እናት                 
ለምኚ  ጸጋን የተሞላሽ     
ለምኚ  የአምላክ ማደሪያ        
ለምኚ  ለምነሽ አስምሪኝ        
ለምኚ  አማናዊት ጽዮን          
ለምኚ  ከእኔ አትለዪኝ     
          አዝ======
ለምኚ ሐዘንሽ ሐዘኔ              
ለምኚ ለኔ ይሁን ድንግል        
ለምኚ የተንከራተትሽው               
ለምኚ በሃገረ እስራኤል 
ለምኚ ትዕግስትሽን ሳየው 
ለምኚ ልቤ ይመሰጣል 
ለምኚ የሐዘን እንባ ጎርፍ 
   ለምኚ ዓይኔን ይላዋል 
           አዝ======
ለምኚ በቀራንዮ አንባ 
ለምኚ በዚያ የፍቅር ቦታ 
ለምኚ በእግረ መስቀሉ ስር 
ለምኚ ከክርስቶስ ጌታ 
ለምኚ ለእኛ ተሰጥተሸል 
ለምኚ እናት እንድትሆኚ 
ለምኚ ልጆችሽ ነንና 
ለምኚ ምልጃሽ አይለየን 
          አዝ======
ለምኚ  አንደበቴን ጌታ 
ለምኚ  በምስጋና ሙላው 
ለምኚ  ደስ ይበልሽ ብዬ 
ለምኚ  እኔም ላመስግናት 
ለምኚ  አንደበቴን ጌታ 
ለምኚ  በምስጋና ሙላው 
ለምኚ  ደስ ይበልሽ ብዬ 
ለምኚ  እኔም ላመስገግናት 

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 06:10


የማህተመ ጋንዲ እሳቤዎች.....✍️

1. ‹‹ እኔ ሃይማኖተኛ ነው የምለው የሌሎችን ስቃይ የሚረዳ ሠውን ነው፡፡ ››

2. ‹‹ በዓለም ላይ እውነተኛው ሠላም እንዲሠፍን ከፈለግን ልጆችን ስለሠላም ማስተማር መጀመር አለብን፡፡ ››

3. ‹‹ ዓለም ላይ ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ሁን፡፡ ››

4. ‹‹ መንፈሳዊ ጥንካሬ ከማይበገር ውስጣዊ ፈቃድ እንጂ ጡንቻን በማሳበጥ አይመጣም፡፡ ››

5. ‹‹ ነፃነት የመሳሳት ነፃነትን ካላካተተ በራሱ ዋጋ የለውም፡፡ ››

6. ‹‹ ማንም ሠው እኔን ከራሴ ፈቃድ ውጪ ሊጎዳኝ አይችልም፡፡ ››

7. ‹‹ ፀሎት ጧቱን መክፈቻ ቁልፍና እና ማታውን ማጥበቂያ ብሎን ነው፡፡ ››

8. ‹‹ ራስህን ለማግኘት ምርጡ መንገድ በአንተ ውስጥ ያለውን የሌሎች ማንነት መጣል ነው፡፡ ››
9. ‹‹ እንዴት ማሠብ እንዳለባቸው የሚያውቁ ሠዎች መምህር አያስፈልጋቸውም፡፡ ››

10. ‹‹ለመሞት ተዘጋጅቻለሁ፣ ለመግደል ግን የምዘጋጅበት ምንም ምክንያት የለም።››

11. ‹‹ መልካም ሠው ሕይወት ላላቸው ነገሮች ሁሉ ወዳጅ ነው፡፡ ››

12. ‹‹ ዓይንን በዓይን የሚለው ህግ መጨረሻው ዓለምን በሙሉ አይነስውር ማድረግ ነው፡፡ ››

13. ‹‹ ደስታ ማለት የምታስበውን ነገር፣ የምትናገረውን ነገርና የምታደርገውን ነገር ከሌሎች ጋር በመስማማትና በመዋሃድ የምታመጣው ሲሆን ነው፡፡ ››

14. ‹‹ ደካሞች ይቅር አይሉም፡፡ ይቅር ማለት ወይም ይቅርታ ማድረግ የጠንካሮች መገለጫ ነው፡፡ ››

15. ‹‹ ራስህን ስለሆንክና ትክክል ስለሆንክ ብዙ ሠዎች በተለይም አላዋቂ የሆኑ ሠዎች ሊቀጡህ ወይም ሊጠሉህ ይፈልጋሉ፡፡ ለትክክለኛነትህ ይቅርታ አታድርግለት፡፡ ትክክል ከሆንክና ትክክል መሆንህን ካወቅክ ለአዕምሮህ ንገረው፡፡ ምንም እንኳን ከታናናሾቹ አንዱ ብትሆንም እውነት አሁንም እውነት ነው፡፡ ››

16. ‹‹ አንድ ግራም ተግባር ከብዙ ቶን ስብከት በላይ ዋጋ አለው፡፡ ››

17. ‹‹በዓለም ላይ የሰውን ስግብግብነት ለማሟላት ሳይሆን ለሰው ልጅ ፍላጎት የሚበቃ በቂ ነገር አለ።››

18. ‹‹ ሠው ማለት የአስተሳሰቦቹ ብዜት ነው፡፡ የሚያስበውን ነውና የሚሆነው፡፡››

19. ‹‹ ያለአንዳች ተግባር የትም መድረስ አትችልም፡፡ ››

20. ‹‹እውነተኛ ሀብት የሆነው የወርቅና የብር ቁርጥራጭ ሳይሆን ጤና ነው።››

የትኞቹን አባባሎች ወደዳችኋቸው? የትኞችስ ከእናነተ እሳቤ ጋር ይዛመዳሉ#comment አድርጉልኝ።

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን🙏እግዚአብሔር ብርኃኔና መድኃኒቴ ነው።

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

11 Nov, 02:19


"ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር፡፡"

ሰቆቃወ ድንግል


🧎‍♀ቅድስት ሆይ ለምኝልን🤲

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

10 Nov, 06:20


የጽጌረዳ ወራት ባለፈ ጊዜ በስዕልሽ ፊት የማያልቅ ምስጋናሽን እያመሰገንኩ መቆምን አላፍርም አላቋርጥም።

      እንኳን አደረሳችሁ


🌹 ተፈጸመ ማኅሌተ  ጽ🌹

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

10 Nov, 02:19


ሱላማጢስ ተመየጢ ሰለማዊት ተመለሽ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ
እመቤቴ ሆይ ከስደትሽ ተመለሽ

ስትመለሽ እኛን ከሰላም የተሰደዱ ልጆችሽን አብረሽ መልሽን
እኛን ከሕይወት የተሰድዱ ልጆችሽን አብርሽ መልሽን
ከብዙ ነገሮች ተሰደናል መልሽን

ያኔ ከስደት ስትመለሽ ኢትዮጵያን ቃል ኪዳን ተቀብለሽ ይዘሻት ተመለሽ ዛሬም ይዘሻት ተመለሽ
ሱላማጢስ ተመየጢ ተመየጢ።

ተፈፀመ ናሁ ማህሌተ ፅጌ ስሙር🌹

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

10 Nov, 00:10


"በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ እናቴ  ልደታ ለማርያም አለው ትበላችሁ"።

🥰🙏🥰

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 20:59


🌷መልክአ ቅድስት ልደታ📗

እመቤቴ ማርያም ሆይ እኔ ኃጢዓተኛ ልጅሽን ወለተ ሥላሴን ለመንግሥተ ሰማያት እንድታበቂኝ በዚህ ዓለምም ከክፉ ነገር ኹሉ እንድትሰውሪኝ ዕለተ ልደትሽ ተስፋና አለኝታ አድርጌ እማፀንሻለሁና በፊት በኋላዬ ከእኔ ሳትለዪ ጠብቂኝ ዛሬም ነገም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።🤲

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 19:08


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር ፩/1/

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 18:01


ተፈጸመ ማህሌተ ጽጌ.. ✝️👏❤️💒

ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ማህሌተ ጽጌ ስሙር ተፈጸመ ናሁ አክሊል አክሊል ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግስቱ!

እነሆ በእመቤታችን ስም ተሰባስበን አበባ ይዘን ልጅዋን በአበባ እርስዋን በጽጌረዳ እየመሰልን የምንዘምርበት ያ የተወደደው የምስጋና የዝማሬ ወር አለፈ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ የጊዮርጊስ የክብር ዘውድ ነሽ! እያሉ በተመስጦ እንደ ቅዱስ ያሬድ የቅዱስ ያሬድ ልጆች ሊቃውንቱ እናታቸውን ሲያመሰግኑ የሚያሳይ ግሩም (ማህሌተ ጽጌ)

እመቤታችን ዘውድነቷ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን ውዳሴዋን ቅዳሴዋን እየደገመ ስሟን እየጠራ ለሚማጸን በአማላጅነቷ በቃል ኪዳኗ ለሚያምን ሁሉ ዘውድ ናት!

ምዕመናንም ትምክህተ ዘመድነ! እያሉ ይዘምሩላታል፤ ያመስግኗታል! ድንግል ሆይ የባህርያችን መመኪያ ነሽ! ተስፋችን ነሽ! የድህነታችን ምልክታችን ነሽ! እያሉ በእናትነቷ ጥላ ስር ያሉ ምዕመናን ይዘምሩላታል! እርስዋም እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ትባርካቸዋለች! ሁላችንም እናታችን ትባርከን!

ለእኛም ለልጆችሽ ሞገስ ሁኝን አማላጅነትሽ ቃልኪዳንሽ አይለየን!!✝️👏💒❤️

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 16:31


ሰዓሊ ለነ ቅድስት /፫/
ሰዓሊ ለነ ቅድስት /፫/
ሰዓሊ ለነ ቅድስት /፫/

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 14:29


"እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን በቸርነቱ ወርኀ ጥቅምት ተፈፀመ ወርኅ ኅዳርን ይቀድስልን የበረከት ወር ያድረግልን ቅድስት ቤተክርስቲያን ስላሟን ይመልስልን አሜን🙏

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 13:42


🌹"ነገ ኅዳር1 ልደታ ለማሪያም እናታችን ናት በዕለተ ቀኗ ከክፉ ሁሉ ትሰውረን ረድኤት በረከቷ አይለየን🙏

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 13:41


<<< በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። >>>

"" ኅዳር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ""

+" ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ "+

+ሃገራችን ኢትዮዽያ በሁሉም ዘርፍ ቅድስና ያላቸው ቅዱሳን ባለቤት ናት:: በዘመኑ ያለን ወጣቶችም ሆነ ጐልማሶች ከቤተ ክርስቲያንና ከቅድስና ሕይወት ለምን እንደራቅን ስንጠየቅ ከምንደረድራቸው ምክንያቶች አንዱ ሥራችን ነው::

+ነገር ግን ሥራው በራሱ ኃጢአት እስካልሆነ ድረስ በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ቢሆን ቅድስናን ማስጠበቅ እንደሚቻል አበው አሳይተውናል:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም ከእነዚህ ቅዱሳን አንዱ ነው::

*እርሱ ንጉሥ ነው: ግን ገዳማዊ ሕይወትን በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያሳየ ጻድቅ ነው::
*ሁሉ በእጁ ነው: እርሱ ግን ንጹሕና ድንግል ነው::
*እርሱ የጦር መሪ ነው: ግን በእጁ ደም አልፈሰሰም::

*እርሱን 'ወደድንህ: ሞትንልህ' የሚሉ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ነበሩት:: ለእርሱ ግን ፍቅር ማለት ክርስቶስ ነበር::
*የሃገር መሪ: የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት እንደ መሆኑ እጅግ ባተሌ (busy) ነው:: ግን ደግሞ ለክርስትናው ጊዜ ያጣ ሰው አልነበረም::

+እኛ ቤተ ክርስቲያንን "በሐኪ" ለማለት (ለመሳለም) እንኳ 'ጊዜ የለኝም' ስንል እርሱ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ይፈለፍል: ያንጽ: በክህነቱ ያገለግል: ማዕጠንት ያጥን: ለረጅም ሰዓትም ይጸልይ ነበር::

+እኛ 'ሥራ ውያለሁና ደክሞኛል' ብለን ከስግደት ስንርቅ እርሱ ግን ንጉሥ ሆኖ ሳለ: ጦር በፊት: በኋላ: በቀኝና በግራ ተክሎ ይሰግድ ስለ ነበር ደሙ እንደ ውሃ በምድር ላይ ፈሷል:: ይህንን ሁሉ ያደረገው ቅዱሱ የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ነአኩቶ ለአብ ነው::

"ለመሆኑ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ማን ነው?"

#‎ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በዛግዌ ሥርወ መንግስት ከነገሡ 11 ነገሥታት አንዱ ሲሆን ከመጨረሻውም 2ኛ ነው:: እርሱን በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን የወለዱት ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ (ገብረ ማርያም) እና መርኬዛ ናት:: ዘመኑ ቅድስና በላስታ ዙሪያ የመላበት በመሆኑ ቅዱስ ሐርቤ ከመነኑ በፊት ነበር ነአኩቶ ለአብን የወለደው::

+እናቱ መርኬዛ እርሱን ልትወልድ ምጥ ተይዛ ሳለ ጀሮዋ ቅዳሴን ይሰማ ነበር:: ቅዳሴው ሲጀመር የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ (ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ) ተፈታላትና ልጇን ተገላገለች:: ሕጻኑን አንስታ ስትታቀፈው ዲያቆኑ ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ" እያለ ሲዞር ሰማችው::

+እዚያው ላይም 'ነአኩቶ ለአብ' (አብን እናመስግነው) ስትል ስም አወጣችለት:: ወዲያው ግን አባቱ ቅዱስ ሐርቤ መንግስቱን ለቅዱስ ላሊበላ ሰጥቶ በርሃ በመግባቱ ቅዱሱ ሕጻን ወደ አጐቱ ላሊበላ ቤተ መንግስት ውስጥ ገባ::

+የቅዱስ ላሊበላ ቤት ደግሞ በቅድስና ያጌጠ ነውና ከርሱና ከሚስቱ (ቅድስት መስቀል ክብራ) ሕጻኑ ነአኩቶ ለአብ ምናኔና ፍቅረ ክርስቶስን ተማረ:: በዘመኑ ብዙ ሊቃውንት ስለ ነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን በደንብ አጠና:: ክህነት ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግልም እድሜው 30 ደረሰ::

+በወቅቱ ቅዱስ ላሊበላና ባለቤቱ መስቀል ክብራ ልጃቸው ይትባረክ እያለ ንግሥናቸውን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አወረሱ:: ቅዱሱ ነአኩቶ ለአብም ምን እንደሚሠራ ሲያስብ አንድ ነገር ተገለጠለት:: ቤተ መንግስቱን እንደሚገባ ካደራጀ በኋላ በቤት ውስጥ አንድ ጉድጓድን በቁመቱ ልክ አስቆፈረ::

+በውስጡም በ4 አቅጣጫ ጦሮችን ተከለባቸው:: ድንግል ካህን ነበረና ቀን ቀን ሃገር ሲያስተዳድር: ቅዳሴ ሲቀድስ: በጾም ይውላል:: ሌሊት ደግሞ ወዳስቆፈረው ቦታ ገብቶ ያለማቁዋረጥ እየጸለየ ይሰግዳል::

+ወደ ምድር ሲሰግድ በፊቱ ያለው ጦር ይወጋዋል:: ቀና ሲል ደግሞ የጀርባው ይቀበለዋል:: እንዲህ እያለ የፈጣሪውን ሕማማት ይካፈላል:: በተለይ ዐርብ ዐርብ ሲሆን ደሙ: እንባውና ላበቱ ተቀላቅሎ ይፈስ ነበር:: እርሱ መስቀሉን ተሸክሞ ጌታውን ይከተል ዘንድ መርጧልና::

+ከተጋድሎው ጐን ለጐን ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አብያተ ክርስቲያናትንም ያንጽ ነበር:: በተለይ በ1211 አካባቢ ያነጻት አሸተን ማርያም ልዩ ናት:: እርሷን ካነጸ በኋላ ከቤተ መንግስቱ በደመና ሠረገላ ተጭኖ እየሔደ ያጥናት: ይቀድስባትም ነበር::

+ታዲያ አንድ ቀን አጥኖ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ብዙ ሥውራን ቅዱሳን መቅደሱን ከበው ተመለከተ:: እርሱም "ወገኖቼ! ከወዴት መወጣችሁ?" ቢላቸው "መዐዛ እጣንህን አሽተን መጣን" ሲሉ መለሱለት:: በዚህ ምክንያትም እስከ ዛሬ ድረስ "አሽተን (አሸተን) ማርያም" ስትባል ትኖራለች::

+ዛሬ ታቦቱ ያለበት ገዳሙም በእርሱ የታነጸ ሲሆን እጅግ ተአምረኛ ቦታ ነው:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የነገሠ በ30 ዓመቱ ነው:: ለ40 ዓመታት በእንዲህ ያለ ቅድስና ኑሮ 70 ዓመት ሞላው:: በዚህ ጊዜም ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ሰላምታንም ሰጠው::

+"ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ! አንተ ስለ እኔ ፍቅር ለ40 ዓመታት መከራን ተቀብለሃልና ሞት አያገኝህም:: ከፍልህ ከነ ኤልያስ ጋር ነውና:: የሚያከብርህን አከብረዋለሁ:: ደጅህን የሳመውን: ይህ ቢያቅተው በሩቁ ሆኖ በአድናቆት የተመኘህን: መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው::

+ቀጥሎም "ይሕች ቤት አንተ ስትደማ እንደኖርክባት እርሷም እስከ ምጽዓት ድረስ ለመታሰቢያህ ስትደማ ትኑር" አለው:: እነሆ ዛሬም ድረስ ከመቅደሱ ጸበል ይንጠበጠባል:: ለዚህም ደግሞ እኛ ኃጥአን ምስክሮች ነን:: ሳይገባን የቅዱሱን ደጅ ተመልክተናልና::

+ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም የዚህን ዓለም ተጋድሎውን ፈጽሞ ወደ ብሔረ ሕያዋን መላእክት ወስደውታል:: የተሰወረበትን ዕለት ስንክሳር ሕዳር 1 ሲያደርገው አንዳንድ መዛግብት ደግሞ በ3 ነው ይላሉ:: በዙፋኑም ላይ የአጐቱ የላሊበላ ልጅ አፄ ይትባረክ ተተክቷል::

+አምላከ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከበረከቱም አትረፍርፎ ይስጠኝ::

+ኅዳር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱሳን መክሲሞስና ባልንጀሮቹ (ሰማዕታት)

ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር


++"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን:: +"+ (ሮሜ. 6:5)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 13:41


📒#ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት †††🌹

†††••ወር በገባ በ1 የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ራጉኤል ወርሐዊ መታሰቢያው ነው፡፡ጸሎቱ በረከቱ ለዘአለሙ ይደርብንና ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ራጉኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡፡

☞በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቀራንዮ በሚባል ቦታ በሰቀሉት ጊዜ
☞ለንጊኖስ የተባለ አንድ ጭፍራ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሣለ ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፡፡

☞በዚያም ጊዜ መልአኩ ዑራኤል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደሙን
ይቀዳ ዘንድ በእጁ የብርሃን ጽዋ ይዞ ቀረበ፡፡
☞እንደዚሁ መልአኩ ዑራኤል የክርስቶስን ደም በሚቀዳበት ጊዜ ለአይሁድ
አልተገለጸላቸውም ነበር ይህም የመላእክት አለቃ ዑራኤል የጌታችን የኢየሱስ
ክርስቶስን ደም በምድር ላይ ከጽንፍ ረጨው፡፡
☞በዚያን ጊዜም በመላአከ ብርሃናት ራጉኤል እጅ ፀሀይ ጨለመ ጨረቃም ደም
መሰለ ከዋክብትም ረገፋ እሱ ራጉኤል መልአክ በፀሐይና በጨረቃ በከዋክብትና
በሌሎችም ብርሃናት ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጥቶታልና፡፡
☞ከብርሃናት አለቃ ከራጉኤል በቀር ፀሐይና ጨረቃን ከዋክብትንም
የሚያዠዛቸዉም የለም፡፡ ፀሐይን በጠፈረ ሰማይ ላይ በቀን ያበራ ዘንድ
አሠለጠነው፡፡ ጨረቃንም ብርሃኑን በሊት ይሰጥ ዘንድ አሠለጠነው፡፡ከዋክብትም
እንዲሁ ለሰማይ የፈረጥ ጌት ናቸው፡፡
☞ዳግመኛም መልአከ ብርሃናት ራጉኤል በከዋክብት ላይ ሰባት አለቆችን ሾመ፡፡
☞የኒህ የብርሃናት አለቆች የመላእክት ሰማቸው ነቢዮ፤ኢሳይያስ እንደስማቸው
ሸረህ መሽተሪህ አጣርድ ዝኁራ፤ዙኃል፤ቀመር ይባላል፡፡
☞እነዚህ የከዋክብት አለቆች ታዛዥነታቸው ለመላእክት አለቃ ለራጉኤል ነው፡፡
እሱ በብርሃናት ሁሉ ላይ የሠለጠኀ ነውና፡፡
☞ልመናው አማላጅነቱ ለሁላችን ይደረግልን፡፡
☞የጽሑፍ ምንጭ (ድርሳነ ራጉኤል)
☞ቅዱስ ራጉኤል ህይወት ለጨለማችሁ ሁሉ ብርሃን ይሆናችሁ፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 09:14


እልልልልልልልል🌸👏🌸🌷👏🌷🌸🌷👏🌷👏🌷👏🌷

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 06:04


መብል መጠጥ የሆነ ሙሽራ!

''በሠርጉ ጊዜ ሥጋውን የሚሠዋና ፈጽሞ መብል የሚሆን ሙሽራ ያየ ማነው? የእግዚአብሔር ልጅ ዓለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ከእርሱ በቀር ሌላ ያደረገው የሌለ አዲስ ሥርዓት ሠራ፥ በሠርጉ ጊዜ በሐዋርያት ፊት ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ማዕድ አድርጎ ሠራ። ከእርሱ ይበሉ ዘንድ፥ ያመኑበት ይድኑበት ዘንድ። በሠርጉ ጊዜ መብል መጠጥ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሰጠን አምላካችን ብሩክ ነው፥ ለኃጢአት ማስተሰርያ ሊሆን ለዘለዓለም እንድንበት ዘንድ። ለርሱ ምስጋና ይግባው ለዘለዓለሙ አሜን።''

(መጽሐፈ ቅዳሴ፥ 2:9-10)።

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

09 Nov, 02:41


"ብቻህን አይደለህም፤ ሕይወትን ብቻህን አትኖርም ነገር ግን ትኖራለህ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይኖራል። እግዚአብሔር ለአንድ አፍታ ወይም ለዐይን ጥቅሻ አይተውህም ።"

አቡነ ሺኖዳ

🌷እንደምን አደራችሁ ቤተሰብ🤲

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

06 Nov, 06:06


መድሃኒአለም ሆይ ፦ አንተ ቸር ስትሆን ንፉግ የሆንኩት እኔ አንተን ጌታዬ ማለቴ እንዴት ደፋር ብሆን ነው? በሽተኛ የሆንኩ እኔ መድሃኒት አንተን የገፋሁ ምንኛ ብኩን ነኝ? እንግዲህስ አባቴም ብዬ እንዳልጠራህ የአባትነት ክብርን አልሰጠሁህም ፡ ጌታዬ ብዬም እንዳልጠራህ አንተን መፍራቴ አልፀናም ፡ ነገር ግን ልጅ ምንም በአመፃ ቢኖር ደግ አባት የልጁን መመለስ ይናፍቃልና አንተ እኔን እንደምትወደኝ አውቃለሁ ስለእኔ መልካም ግብር ያይደለ ስለአንተ የፍቅርህ ብዛት ልጄ ትለኛለህና አመሰግንሃለሁ።
ደሃን የሚያቀርብ ማነው? ክፉ ደሃንስ ማን ያቀርባል? ፀባዩ የከፋ ደሃንስ ማን ወደቤቱ ይጋብዛል? የሚሰርቅ ሌባ ችግረኛንስ ማን ባልንጀራ ያደርጋል? እኔ እንዲሁ ነኝና፦ ምንም የሌለኝ ደሃ ሃጢአትን የማደርግ ደሃ ፡ ፍቅር የሌለኝ ደሃ ፡ በሃጢአት አንተን የማሳዝን ችግረኛ እኔ ነኝና ፡ እንግዲህ እንዲህ ላለ ሰው ወዳጁ ማነው? ለተናቀ ፡ ለተጠላ ፡ ለደከመ ደጉ ሳምራዊ የሚሆነው ማነው? ከአንተ በቀር ፡ አንተ የሁሉን መመለስ ትወዳለህና ፡ አንተ የሁሉን መዳን ትወዳለህና ስለፍቅርህ ተስፋ ይቆይልኛል፡፡ ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን፡፡ አሜን፡፡"
"አቤቱ ፥ ስለስምህ ህያው አድርገኝ ፤ ስለፅድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት "። መዝ 142(143)÷11

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

06 Nov, 02:05


"የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

አባቱ ሞቶ የማያለቅስ ማን ነው?? አባቱ በሞተበትስ ሰሞን ዘፈንና ተደላ ደስታን የማይተዋት ማን ነው?? ክርሰቶስ ስለ እኛ ሲል ሁሉንም ተወ፦ መንግሥቱን መላእክቱን ክብሩን ሁሉንም ትቶ ስለ እኛ ስለሰው ልጆች ሰው ሆነ። በምላሹ አኛ አንድስ በደል እንኳን ስለስሙ መተው አቃተን። ዘፈን ዝሙትን ስንፍናን ስለስሙ እንተው። እርሱ ከተወልን እኛ የተውንለት አይበልጥምና ስለ ፍጹም ፍቅሩ ከኃጢአት እንራቅ።

"የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"[ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ]

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 20:59


🌷መልክአ ቸሩ መድኃኔዓለም📗

በሕይወታችን በኑሯችን የጎደለውን ኹሉ የዓለሙ ቤዛ ቸሩ መድኃኔዓለም ይሙላልን አሜን በእውነት🤲

@Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 19:04


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት ፳፯/27/

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 17:09


📗"ሳይኖረን በክብር የሚያኖረን ቸሩ መድኃኔዓለም ነው ቸሩ መድኃኔዓለም ጥበቃው አይለየን


🌹በቀኙ ያቁመን የዓለሙ ቤዛ🙏

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 15:25


✞እንኳን አደረሳችሁ!

"መድኃኔ ዓለም ኀቤከ እገይሥ ለለጌሠሙ፤
እስመ ሰማዕኩ ኂሩተከ በከመ ትቤ ቀዲሙ፤
በላዕለ መስቀል አባ ስረይ ሎሙ!"
(መልክአ መድኃኔ ዓለም)

"ያንተን መሐሪነት፥ ያባትህን ልዕልና፤
የሁሉ ፈጣሪ፥ ያለህ በዕሪና፤
'ይቅር በል' ማለትህን፥ ሰምቻለሁና፤
ቸሩ መድኃኔዓለም፥ እገሠግሳለሁ፥ በእግረ ልቡና!"

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 15:23


ንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠   
/(ማቴ ፫:፫/)

እንኳን አደረሰን!!


ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም
ለወልድ ሰላም
ወለ መንፈስ ቅዱስ ሰላም
ለማርያም ሰላም
ወለመላእክት ሰላም
ሰላም ለነብያት
ወለሐዋርያት ሰላም
ለሰማዕታት ሰላም
ወለጻድቃን ሰላም


ማኅደረ ሰላምነ ቅድስት ደብተራ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት ንዑ ንስግድ ኵልነ ኀበ ማርያም እምነ።


ሰላም ለክሙ እንጦንስ ወመቃርስ፤
አቢብ ሲኖዳ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፤
ለባርኮትነ ንዑ ውስተ ጽርሐ ዛቲ መቅደስ፤
ተክለሃይማኖት አኖሬዎስ ኤዎስጣቴዎስ፤
ሳሙኤል ተክለ አልፋ በብኑዳ ኪሮስ፡፡


ነብያት ወሐዋርያት ጻድቃን ወሰማዕት ደናግል ወመነኮሳት አዕሩግ ወሕጻናት ገዳማውያን ወሊቃውንት ሰአሉ ለነ ኩልክሙ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት።


❇️ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)❇️

" ❇️ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::❇️
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/


ንስሃ አባት የሌላችሁ👉https://t.me/+sGJzhNXvJPw2NWQ0

https://t.me/zikirekdusn

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 15:23


📕#አባታችን_አባ_ጽጌ_ድንግል 🌹

☞•••ወር በገባ በ 27 የማህሌተ ጽጌ ደራሲ የአባ ጽጌ ድንግል ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡ሀገራቸው ወሎ ቦረና ሲሆን ደራሲና ማኅሌታዊ ናቸው ጻድቁ ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ጀምሮ አስከ 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን
የነበሩ ሲሆን የመጀመሪያ ስማቸው አባ ዮሐኒ ይባል ነበር፡፡

☞አባ ጽጌ ድንግል በመጀመሪያ ታሪካቸው ከቤተ እስራኤላውያን ወገን የሆኑና
የኦሪትን ሃይማንት ብቻ የሚከተሉ ነበሩ፡፡
☞እመቤታችን በተአምር ተገልጣለቸዎ የሐዲስ ኪዳን ሕግ ከአቡነ ዜና ማርቆስ
እንዲማሩ አድርጋቸዋለች፡፡
☞ጻድቁ ለኦሪት ሕግ ቀናኢ ሆነው ሲኖሩ አንድ ቀን ከጓደኞቻቸው ጋር መንገድ
ሲሄዱ የእመቤታችንን ሥዕል አድኅኖ በጽጌሬዳ አበባ መሐል ያገኛሉ፡፡
☞አባ ጽጌ ድንግልም በዚያች ሥዕል ፊት ላይ አንዳች ክፋ ነገር አደርጋለሁ
ብለው ከኦሪታዊ ጓደኛቸው ጋር ተፎካክረው ሥዕሏን ለመምታት ሲያመሩ
እመቤታችን በተአምራት እዛው ባሉበት ደንዠዘውና በአንዳች ኃይል ተይዘው
ቆመው እንዲቆዩ ታደርጋቸዋለች፡፡
☞ወዲያው እመቤታችን ለአቡነ ዜና ማርቆስ ተገልጣ እንዲህ ዓይነት ቦታ ላይ
ወዳጄና አገልጋዬ ሊሆን የተገባው አንድ የኦሪት ሰው አለና ሄደህ ከእስራቱ ፈተህ
ሃይማኖትን አስተምረው ብላ ነግራቸዋለች፡፡
☞አቡነ ዜና ማርቆስም ወደተነገራቸው ቦታ ቢሄዱ አባ ጽጌ ድንግል በተአምራት
ታስረው በፊት ለፊት ካለቸው የእመቤታችን ሥዕል ጋር እየተያዩ አገኟቸው፡፡
☞ከዚህም በኃላ አቡነ ዜና ማርቆስ ከፈወሷቸው በኃላ የሐዲስ ኪዳኑን ክርስትና
በደንብ አሰተምው ካጠመቋቸው በኃላ አመንኩሰው ስማቸውን ጽጌ ብርሃን /ጽጌ
ድንግል አሏቸው፡፡
☞አባ ጽጌ ድንግል እንደ ቅዱስ ጳውሎስ የኦሪት ምሁር ስለነበሩ ሐዲስ ኪዳንን
ከተማሩ በኃላ ብሉይን ከሐዲስ እያስማሙ በማስተማርና በመጻፍ ከአቡነ ዜና
ማርቆስ ጋር ለአገልግሎት ተዘዋውረዋል፡፡ አብረው ብዙ ዘመን ተቀምጠዋል፡፡
☞አባ ጽጌ ድንግል በደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም አበ ምኔት
ተደርገው ተሹመው ነበር፡፡
☞ከዚኽም በኃላ አባ ጽጌ ድንግል ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስለነበራቸው
ምስጋናዋን ይናፍቁ ነበር በጾም በጸሎት ይጠይቋት ነበር፡፡
☞እመቤታችን እንደ ቅዱስ ያሬድ ምሥጢርን ገልጣላቸው ማኅሌተ ጽጌ
ወሰቆቃወ ድንግልን ደረሰዋል፡፡
☞አባ ጼጌ ድንግል ከዕሴይ ሥር የምትገኘውን እመቤታችንን በበትር ከእርሷ
የሚገኘውን መድኃኒ ዓለምን በጽጌና በፍሬ በመመሰል እመቤታችን ልጇን ይዛ
በግብፅ በረሃ መከራ መቀበሏን የቅዱሳን መጻሕፍትን ሐተታ በመውሰድ
ምሥጢር አዘል ታሪኮችን ተግሣጽንና ተማጽኖን የያዘ ኃይለ ቃላት በስነ ግጥም
መጠን ተለክቶና ተመጥኖ የተዘጋጀ እንደ መዝሙረ ዳዊት መቶ ሃምሳ ጸሎት
አድርገው ማኅሌተ ጽጌን ደርሰውታል፡፡
☞የላመ የጣፈጠ ከመብላት ተቆጠበው ጥሬ ቆርጥመው 9 ዓመት በታላቅ
ተጋድሎ ከኖሩ በኀላ የእመቤታችንን ስደት በጣም በጥልቀት
የሚናገረውን"ማኅሌት ጽጌ"የተሰኘውን ድርሰት የደረሱ ታላቅ አባት ናቸው፡፡
☞ውኃም በሦስት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ ነበር የሚጠጡት፡፡ አቡነ ጽጌ ድንግል
ከደብረ ሐንታው ከአቡነ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ
ቃል ተናጋሪ ሆነው እመቤታችንንና ፈጣሪዋን ልጇን በጎ መዓዛ ባለቸው አበባዎች
ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ድርሰታቸውን በመዝሙረ ዳዊት መጠን
150 አድርገው ደረሰዋል፡፡
☞አቡነ ገብረ ማርያምና አቡነ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌን በጥምረት ሊደርሱት
የቻሉት አቡነ ገብረ ማርያም በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ልዩ ስሙ
ደብረ ሐንታ በሚባለው ገዳም የሕግ መምሕር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ነው፡፡
☞አንድ ዓመት አቡነ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ
በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥተው ደብረ ብሥራት አቡነ ጽጌ
ድንግል ገዳም ገብተው ከመስከረም 25-ኅዳር 5ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40
ቀን አገልግሎት ከአቡነ ጽጌ ድንግል ጋር ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብራቸው
ደብረ ሐንታ ይመለሳሉ፡፡
☞እነዚህ ሁለት ታላላቅ ቅዱሳን እንዲህ እያደረጉ በየተራ አንደኛው ወደ
አንደኛው ገዳም እየሄዱ አስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍጹም ፍቅርና በትሕትና
አብረው እመቤታችን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡
☞የጻድቁ ቅዱስ ዐፅማቸው ታቦታቸውና የደረሷቸው በርካታ ድርሰቶች
በገዳማቸው ደብረ ጸጌ በክብር ተጠብቀው ይገኛል፡፡
☞አባ ጽጌ ድንግል በዚህ ገዳማቸው በጣም በርካታ ተማሪዎችን
አስተምረዋል፡፡ በተለይም(ወተት ሜዳ)በተባለው ቦታ ቃለ እግዚአብሔርን
በሰፊው ለትውልድ አስተላልፈዋል፡፡
☞አምሃራ ሳይንት ቦረና ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም የ5 ሰዓት የእግር
መንገድ ከተሄደ በኃላ የሚገኘው (ደብረ ጽጌ)ከአንድ ወጥ ዓለት ተፈልፍሎ
የተሠራው ሲሆን አሠራሩም እጅግ ድንቅና ውብ ነው፡፡
☞የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ጋር የሚያገናኘው
የእግዜር ድልድይ የተባለ አስገራሚ ታሪክ ያለው ድልድይ አለው፡፡
☞የጻድቁ አባታችን ወርሐዊ መታሰቢያቸው ወር በገባ በ27 ነው፡፡
☞የእመቤታችን ወዳጅ የአባታችን የአባ ጽጌ ድንግል የጸሎታቸው በረከት
አይለየን፡፡
☞የጽሑፍ ምንጭ☞(መዝገበ ቅዱሳን፡መጽሐፍ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ


ቤተሰብ ይሁኑ. https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 15:22


ሲመነኩሱም "ጽጌ ብርሃን" ተብለዋል:: ቀጥለውም
በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ
ምሥጢር ተገለጠላቸው::+የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም
ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ
የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን 150 ዓርኬ አድርገው
ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን
በገዳማቸው (ወለቃ አካባቢ የሚገኝ) ሲያመሰግኑ
ኑረዋል:: በዚህች ቀንም ዐርፈዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን በአማኑኤል ስሙ: በማርያም እሙ:
በፈሰሰ ደሙ: በተወጋ ጐኑ: በንጹሐን ቅዱሳኑ ይማረን::
ከመስቀሉና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::

=>ጥቅምት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
2.ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ
3.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
4.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
3.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
5.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

=>+"+ በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ:: ሕማማችንንም
ተሸክሟል:: እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ
ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው:: እርሱ ግን ስለ
መተላለፋችን ቈሰለ:: ስለ በደላችንም ደቀቀ::
የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ:: በእርሱም
ቁስል እኛ ተፈወስን:: +"+ (ኢሳ. 53:4)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 15:22


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞ ጥቅምት ፳፯ (27) ✞

✞✞✞ እንኩዋን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ "*+

=>ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው
የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ
ውስጥ ያዙት::
¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ
ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

+ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት::
¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት::
¤ራሱንም በዘንግ መቱት::
¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::

+በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ
6,666 ገረፉት::

¤ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው
ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::
¤6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው
ሰቀሉት::

+7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
¤ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን
ተናገረ::
¤ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን
ከቅዱስ ሥጋው ለየ::

+በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ
ፈታ::

¤11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና
ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::
በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ::
ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት
አንስት በዋይታ ዋሉ::

+ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27
ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት
አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት
27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ
በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::

+ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ
አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን
እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ
ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::

+በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት
27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ
ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም
17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::

+"+ ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ +"+

=>በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው:: "ታላቁ
መቃርዮስ": "መቃርስ እስክንድርያዊ": "መቃርስ
ባሕታዊ"ን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል:: ይህኛው
ቅዱስ ደግሞ "መቃርስ ኤዺስ ቆዾስ: መቃርስ ብጹዓዊ:
መቃርስ ዘሃገረ ቃው" ይባላል:: ሁሉም መጠሪያዎቹ
ናቸው::

+ቅዱሱ የ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ሲሆን የቅዱስ
ቄርሎስና የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ተከታይ ነው:: ከሕይወቱ
ማማርና ከቅድስናው መሥመር የተነሳ አበው
አመስግነውት አይይጠግቡም:: ልበ አምላክ ቅዱስ
ዳዊት "ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል" እንዳለው:: (መዝ. 91)

+ዳግመኛ "ወይከውን ከመ ዕጽ እንተ ትክልት ኀበ
ሙሐዘ ማይ" (መዝ. 1:3) እንዳለው ቅዱስ መቃርስ
እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን አፍርቷል:: ከሁሉ አስቀድሞ
በበርሃ ኗሪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ስለ ጌታ ፍቅር እንባው
እንደ ዥረት እየፈሰሰ:: ራሱን በብረት ዘንግ ይመታ ነበር::

+"ቃው" በምትባል ሃገር ዻዻስ ሆኖ በተሾመ ጊዜም
ተጋድሎውን አልቀነሰም:: ዻዻስ ቢሆንም የሚለብሰው
የበርሃዋን ደበሎ ነው:: ከብቅዓቱ የተነሳ የሕዝቡ
ኃጢአት በግንባራቸው ላይ ተጽፎ እየታየው ስለ ወገኖቹ
ያለቅስ ነበረ:: በቤተ መቅደስ ውስጥ ቆሞ አንጀቱ ቅጥል
እስኪል ድረስም ያለቅስ ነበር::

+ሁልጊዜ ሲቀድስ ጌታችንን ከመላእክቱ ጋር ያየው
ነበር:: አንድ ቀንም ጌታ ቅዱስ መቃርስን "ዻዻሱ ሆይ
ሕዝቡን ገስጻቸው:: ብትገስጻቸውና ባይሰሙህ እዳው
በእነርሱ ላይ ነው" አለው:: ቅዱስ መቃርስም ሕዝቡ
ከኃጢአታቸው ይመለሱ ዘንድ ይመክራቸው:
ይለምንላቸውም ነበር::

+ከዚህ ሁሉ በሁዋላ በጉባኤ ኬልቄዶን (ጉባኤ አብዳን)
636 ዻዻሳት ንጉሡን ፈርተው ሃይማኖታቸውን ሲክዱ
ቅዱሳኑ ዲዮስቆሮስና መቃርስ "ተዋሐዶን አንክድም"
በማለታቸው ዘበቱባቸው:: ብዙ አሰቃይተውም ወደ ጋግራ
ደሴት አሳደዷቸው::

+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ውስጥ ሲሞት ቅዱስ
መቃርስ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ሕዝቡን ሲመክር
ያዙት:: ከመሬት ላይ ጥለውም እየደጋገሙ ኩላሊቱን
ረገጡት:: ከመከራው ብዛትም በዚህች ቀን ነፍሱን
አሳልፎ ሰጠ:: ቅዱሱ ሙታንን ማስነሳትን ጨምሮ ብዙ
ተአምራትን ሠርቷል::

+አበውም ስለ ቅዱስ መቃርስ ብሎ ጌታ እንዲምራቸው
እንዲህ ይጸልዩ ነበር:-
"ሰላም ሰላም ለፈያታዊ ዘቀደሶ::
ሃገረ ጽጌ የአኀዝ ምስለ ጻድቃን በተዋርሶ::
ተዘከረኒ ክርስቶስ አመ ትመጽእ ለተዋቅሶ::
በእንተ መቃርስ ጻድቅ እንተ መጠወ ነፍሶ::
ወበበትረ መስቀል ዘይዘብጥ ርዕሶ::" (አርኬ ዘጥቅምት 27)

+*" አቡነ መብዓ ጽዮን "*+

=>ሃገራችን ኢትዮዽያ እጅግ በርካታ ቅዱሳንን ስታፈራ
አንዳንዶቹ ደግሞ የተለዩ ናቸው:: ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮን
በ15ኛው መቶ ክ/ዘመን በሽዋ (ሻሞ) አካባቢ የተነሱ
ጻድቅ ናቸው:: ገና ከልጅነታቸው የእመቤታችንና የጌታችን
ፍቅር የሞላባቸው ነበሩ::

+በ3 ዓመታቸው ከእንግዳ የወሰዷት ስዕለ አድኅኖ
ተለይታቸው አታውቅም ነበር:: በወጣትነታቸው ጊዜም
ብሉያት ሐዲሳትን: ቅኔንም ጨምሮ ተምረው:
ከቤተሰባቸው አስፈቅደው በምናኔ ገዳም ገቡ::

ከዚያ በሁዋላ ያለውን ገድላቸውን ማን ችሎ
ይዘረዝረዋል!

+በተለይ ዐርብ ዐርብ የጌታን 13 ሕማማት ለማዘከር
ሲቀበሉት የኖሩት መከራ እጅግ ብዙ ነው:: ድንጋይ
ተሸክመው እንባና ላበታቸው እየተንጠፈጠፈ ይሰግዳሉ::
በድንጋይ ደረትና ጀርባቸውን ይደቃሉ:: ራሳቸውን
ይገርፋሉ:: በዋንጫ ሐሞት (ኮሶ) ሞልተው ይጠጣሉ::

+ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ወር በገባ በ27 ስለ መድኃኔ
ዓለም ጠላ ጠምቀው: ንፍሮ ነክረው ወደ ገበያ ይወጡና
ይዘክሩ ነበር:: ከዝክሩ የነካ ሁሉ ይፈወስ ነበር:: ከእንባ
ብዛት ዓይናቸው ቢጠፋ ድንግል ማርያም መጥታ
ብርሃናዊ ዓይንን ሰጠቻቸው:: ስለዚህም "ተክለ ማርያም
(በትረ ማርያም)" ይባላሉ::

+ጌታችንም ስለ ፍቅራቸው በአምሳለ ሕጻን
ይገለጽላቸው: እርሳቸውም አቅፈው ይስሙት ነበር::
ጻድቁ ተናግረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ ተጋድለው ጌታ
በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡበት ስልጣንን
ሰጣቸው:: አባታችን ቅዱሱና ጻድቁ መብዓ ጽዮን ከብዙ
ትሩፋት በሁዋላ ዐርፈዋል::

+"+ አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ +"+

=>ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን
የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም
ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ
ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ
ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::

+የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም
"ክርስቶስ አልተወለደም:: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ
ነው::" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ
ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር
ተገናኙ::

+ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ::
አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው
(ሲያጠምቁዋቸው) "ጽጌ ድንግል" አሏቸው::

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 15:07


መድኃኔዓለም

💠«መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት  ማለት ነው።ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።ምን ዓይነት ፍቅር ነው????? ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለእኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው።ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን።ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው። በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት።እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር። ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር።ታድያ እኛ ደግሞ ራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን። በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ።አንተም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግህ ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።

መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።

ቤተሰብ ይሁና https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 15:07


❖ ዳግመኛም ‹‹እነሆ የተመኘኸውን ታገኘዋለህና፣ ጊዜው ቀርቧልና ጽና በርታ እኔንና ልጄን የለመንከንን ነገር አስብ›› ብላቸው ተሰወረች፡፡
❖ አባታችን በተደጋጋሚ እመቤታችንንና ጌታችንን ስለ ስሙ ብለው ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ ይለምኑ ስለነበረ ነው እመቤታችን ይህንን የነገረቻው፡፡
❖ ከዚህም በኋላ የንጉሡ የዐፀ ዘርዐ ያዕቆብ ባለቤት አባታችንን ‹‹ስለ ክርስቶስ ብለሁ መጥተው አስትምሩን ምከሩን›› ብላ ለመነቻቸውና አባታችን ሄደው መከሯት፤ ልጃቸውን ገላውዴዎስን አስተምረው ባረኩት፤ ለንጉሡ ዐፀ ዘርዐ ያዕቆብም ብዙ ምሥጢርን ነገሩት፡፡
❖ ንጉሡም በአቅራቢያው የእመቤታችን ታቦት ካለችበት ቦታ ሦስት ወር ከእርሱ እንዲቀመጡ ለመናቸው፤ እሳቸውም በዚያ ሲቆዩ የንጉሡ ወታደሮች በፈረስ ግልቢያና በድብደባ እየተገዳደሉ አይተው አዘኑ፤ ‹‹ይህ የአረመኔዎች ሥራ ነው›› ብለው ሕግንና ሥርዓትን ሊያስተማሯቸው አስበው ወደ ንጉሡ ዐፀ ዘርዐ ያዕቆብ እንዲያናግራቸው መልእክተኛ ላኩበት፡፡
❖ ንጉሡም ‹‹ዛሬ አይመቸኝም›› አላቸው፤ አባታችንም መልአክተኛውን ስለ ሰዎቹ በከንቱ መሞትና ሌላንም መልእክቶችን ላኩለት፤ መልእክተኛውም የመዘምራን አለቃ ደብተራ ስለነበር አባታችንን ‹‹እኔ እያለሁ ለአንተ ነቢይነትን ማን ሰጠህ›› ብሎ በክፉ ቃል ተናገራቸውና ሄዶ ከንጉሡ ጋር በክፉ ወሬ አጣላቸው፤ ወደ ንጉሡ ገብቶ ‹‹ንጉሥ ሆይ ይህ መነኩሴ ጻድቅ ነኝ ይላል፣ አንተን ግን ይሰድብሃል ባንተ ላይም ብዙ ዘለፋ ይናገራል…›› አለው፡፡
❖ ንጉሡም በጣም ተቆጥቶ አባተችን አስመጥቶ ‹‹ለምን ይዘልፉኛል›› አላቸው፤ አባታችንም ዘለፋ ሳይሆን ሊሆን የማይገባውን ነገር ሁሉ ነገሩት፤ ይልቁንም ስለሴቶቸና ስለፍርድና መሥራት ስለማይገባው ነገር ሁሉ ሲናገሩት ንጉሡም ደፍረው ስለተናገሩት በኃይል ይደበድቧቸው ዘንድ አዘዘ፤ ከአፍና አፍንጫቸውም ደም እንደውኃ እስኪርድ ድረስ ደበደቧቸውና አሠሯቸው፡፡
❖ ዳግመኛም ንጉሡ ቢያስመጣቸው ደግመው ስለጥፋቱ ገሠጹት፤ አሁንም ጽኑ ድብደባን አደረሱባቸውና አሠሯቸው፤ በዚያም ብዙ አሠቃዩአቸው፡፡
❖ በዚህም ጊዜ እመቤታችን ለአባታችን ለተልጣላቸው ‹‹እነሆ የልጄን ትእዛዝ ፈጸምህ የተመኘኸውን አገኘህ፣ ነገር ግን ሁለት የትዕግስት በር ይቀርሃል እርሱን ከፈጸምክ ልጄ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ያሳርፍሃል›› አለቻቸው።
❖ ከዚህም በኋላ የንጉሡ ጭፍሮች አባታችንን በጠጠር ጎዳና ላይ እየጎተቷቸው ብዙ አሠቃዩአቸው፡፡
❖ የንጉሡ ስምንት ጭፍሮች በመቀጣጠብ ‹‹ንጉሡ መቼ እሞታለሁ›› ብሎሃል እያሉ በመሾፍ አባታችንን ወደ ዱር ወስደው በአቅማቸውን ያህል በኃይል ደበደቧቸው፡፡
❖ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ባያጸናቸው ኖሮ በአንደኛው ሰው ዱላ ብቻ ነፍሳቸው በወጣች ነበር፤ በእሥርም 8 ወር ከተቀመጡ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት የሚያርፉበት ጊዜ ስለደረሰ ቅዱሳን መላእክት ከእሥር ቤት ነጥቀው ወስደው ወደ ሰማይ አሰረጓቸውና በሥሉስ ቅዱስ ፊት አቆሟቸው፡፡
❖ በዚያም ለሦስት ሳምንት ቆዩ፤ ጌታችንም ለአባታችን ብዙ የሕይወትን ምሥጢር ነገራቸው፤ እንደጸሐይ የምታበራዋን የምድርን ማዕዘነ ዓለም የምታክል ሰማያዊት ሀገር ርስት አድርጎ ሰጣቸው ‹‹ስምህን ከሚጠሩ ልጆችህ፣ የገድልህን መጽሐፍ ከጻፉ ካጻፉ ከሰሙ፣ ዝክርን ካዘከሩ በጸሎትህ ከተማኑ ልጆችህ ጋር የምትኖርባት ዕድል ፈንታህ ናት›› አላቸው፡፡
❖ አባታችንም ጌታችንን ‹‹አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ ይህን ቃልኪዳን የሰጠኸኝ አንተን የሚያስደስት ምን ነገር አደረኩልህ በቸርነትህ ነው እንጂ›› አሉት፡፡
❖ ጌታችንም ‹‹ዕድል ፈንታህ ጽዋ ተርታህ እውነተኛ የእኔ ምስክር ከሚሆን ጊዮርጊስና ወዳጄ ከሚሆን ከዮሐንስ ጋራ ይሁን›› አላቸው፡፡
❖ ዳግመኛም ጌታችን ሰባት አክሊትን አቀዳጃቸውና ‹‹አንዱ ስለ ድንግልናህ ነው፣ አንዱ ሃይማኖትህን ለማስተማር ከአንዱ ሀገር ወደ አንዱ አገር ስለሄድክ ነው፣ አንዱ ቅዱሳንን ለመጎብኘት እየተዘዋወርክ ከቅዱሳን ጋራ ስለተነጋገርክበት ነው፣ አንዱ ስለየዋህነትህ ኃላፊ ዓለምን ስለመናቅህ ነው፣ አንዱ ስለተወደደ ክህነትህ ነው፣ አንዱ ታግሰህ ስለመጋደልህ ነው፣ አንዱም ደምህን ስለማፍሰስህ ነው›› አላቸው፤ ጌታችን ይህን ቃልኪዳንና ክብር ከሰጣቸው በኋለ ‹‹ከዚህ ከሚጠፋው ዓለም አሳርፍሃለሁ›› አላቸው፡፡
❖ ከዚህም በኋላ ከተነጠቁበት ከሦስት ሳምንት በኋላ ተመልሰው ከእሥር ቤቱ ሆነው ያዩትን ሁሉ ለአንድ ወዳጃቸው ለሆነ ቄስ ተክለ ኢየሱስ ነገሩት፡፡
❖ ዳግመኛምም አባታችን በእሥር ቤት ሳሉ በመላአክት እጅ ተነጥቀው ወደ ሰማይ ከተወሰዱና ከጌታችን ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን እንዳነጋገረቻቸው ተናገሩ ‹‹እመቤታችን ማርያም ‹ዘርዐ ያዕቆብን ይቅር በልልኝ፣ ኃጢአቱንም ተውለት፣ በልጄ ፊት ቀርበህ ‹ግፌን ተመልከትልኝ› አትበል እርሱ ዘወትር ስሜን ይጠራልና፣ ስለ ድንግልናዬም የሚያስተምር ነውና› አለኝ፡፡
❖ እኔም የእመ ብርሃንን ርኅራኄ አደነቅሁና ‹እመቤቴ ሆይ አንቺ እያዘዝሽኝ ወድጄ ነውን የምመረው እኔ ኃጢአተኛ ለምን ይቅር አልልም ይቅር እላለሁ እንጂ ነገር ግን የአንቺ ጸሎት ሁላችንንም ይማረን› አልኋት›
❖ አቡነ ተክለ ሐዋርያት በመጨረሻ ዘመናቸው በንጉሡ አደባባይ ኅዳር 27 ቀን ሲያርፉ ቅዱሳን መላእክት መጥተው ገንዘው ቀብረዋቸዋል፤ በመካነ መቃብራቸውም ላይ ብርሃን ተተክሎ ታይቷል፡፡
❖ ንጉሡ ዘርዐ ያዕቆብም በመካነ መቃብራቸው ላይ ብርሃን መውረዱንና ብዙ ተአምራት ማድረጉን በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ፤ ብዙ ምልክትም አገኘ፤ አባታችን ሰማዕትነትን ይቀበሉ ዘንድ ተመኝተው ራሳቸው ለምነዋልና መደብደብ መሠቃየታቸው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡
❖ ንጉሡም መነኮሳት ልጆቻቸውንም ጠርቶ የአባታችንን ሥጋ በክብር እንዲያፈልሱ ነገራቸው፤ ርስት ጉልት የሚሆን መሬት ሰጣቸው፤ ነገር ግን ዐፅማቸው ከመፍለሱ በፊት ንጉሡ በሞት ስላረፈ ልጁ በእደ ማርያም በአባቱ ትእዛዝ መሠረት የአባታችንን ዐፅም ከ13 ዓመት በኋላ ወደ ደብረ ጽሞና በክብር አፍልሶታል፤ ታቦታቸው ደብረ ሊባኖስ አውራጃ አጋት መድኃኔዓለም ይገኛል።
የአቡነ ተክለ ሐዋርያት ረድኤት በረከታቸው ይደረርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን

አርኬ
✍️ሰላም እብል ለተክለ ሐዋርያት በተአምኆ። ወለተአምሪከ እሴብሖ። ለምሳሐ ሰንበት ሶበ ፈቀደ ይጥብሖ። ተማሕፀንኩ በጸሎትከ እንዘ ይብል ከሊሖ። በልሳነ ሰብእ ነበበ ነቃዊ ዶርሖ።

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

05 Nov, 15:06


💦አቡነ ተክለ ሐዋርያ ማለት📒

📕#ወር በገባ በ27 የአቡነ ተክለ ሐዋርያ መታሰቢ ነው🌹

❖ አባታቸው የእናርዕት አገረ ገዥ የነበሩት እንድርያስ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ እሌኒ ይባላሉ፤ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ሲሆን በዚሁ የምትገኘውን ታላቋን የደብረ ጽሙናን ገዳም የመሠረቱ ሲሆን በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የነበሩ ታላቅ አባት ናቸው፤ ገና በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ አጋንንትን እያቃጠሉ ያጠፏቸው ነበር፡፡

❖ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምረው ከጨረሱ በኋላ ገና በድቁና እያገለገሉ ሳለ 40 ቀን በማክፈል ይጾሙና ይጸልዩ ነበር፡፡
❖ አባታችን የመነኮሱትና ብዙ ተጋድሎአቸን ፈጽመው ወደ ሰማይ ተነጥቀው ሥላሴን እስከማየት የደረሱት በደብረ ሊባኖስ ነው፤ ያመነኮሷቸውም ሁሉን በስውር ያለውን የሚውቁት አቡነ ዮሐንስ ከማ ናቸው፡፡

❖ አባታችን ማታ ማታ ከባሕር ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ እያደሩ በቀን 30 ፍሬ አተር ብቻ እየተመገቡ ይጾሙ ነበር፤ ስውራን የሆኑ ቅዱሳን አባታችም እየተገለጡላቸው ምሥጢራትን ይነግሯቸዋል፤ ከስግደታቸውም ብዛት የተነሣ የአባታችን ሁለት የእጆቻቸው አጥንቶች ተሰበሩ፤ ከቁመታቸውም ብዛት የተነሣ እግሮቻቸው አበጡ፡፡

❖ ስምንት ስለታም ጦሮችን ያሉበትን የብረት ሰንሰለት በወገባቸው ታጥቀው ሁለት ሁለቱን በፊት በኋላ በቀኝ በግራ አድርገው ታጠቁ፡፡

❖ እነዚህም ጦሮች ከልደት፣ ከጥምቀትና ከትነሣኤ በዓል በቀር ከወገባቸው ላይ አያወጧቸውም ነበር፤ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ሲቀመጡ፣ ሲነሡና ሲሰግዱ ጦሮቹ ሰውነታቸውን ሲወጓቸው በዚያን ጊዜ የጌታችንን በጦር መወጋቱንና መከራውን ያስባሉ፤ በታመሙም ጊዜ ‹‹ኃጢአተኛ ሰውነቴ ሆይ ስለአንቺ የተቀበለውን የክርስቶስን መከራ አስቢ›› እያሉ ሰውነታቸውን ይጎስማሉ፡፡

❖ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወስዶ ከገነት ዕፅ አምጥቶ አባታችንን ካሸታቸው በኋላ ግን ርሃብና ጥም የሚባል ነገር ጠፍቶላቸዋልና ምድራዊውን ነገር ለመቅመስ የሚጸየፉ ሆኑ፡፡
❖ ጻድቁ ቅስና እንዲሾሙ የገዳሙ አበምኔት ግድ ቢሏቸውም አባታችን ግን እምቢ ስላሉ ‹‹ለጳጳሱ መልእክት አድርስልኝ›› ብለው በዘዴ ልከዋቸው ጳጳሱም በመንፈስ ተረድተው ቅስና ሾመዋቸዋል፡፡

❖ ጻድቁ በአቡነ አትናቴዎስ መቃብር ላይ ሄደው አጥብቀው ይጸልዩ በነበረበት ወቅት ብርሃን ይወርድላቸው እንደነበር እግዚእ ክብራ የተባለች አንዲት ትልቅ ጻድቅ እናት ትመለከት ነበር፡፡
❖ አባታችን ሁልጊዜ ‹‹ሦስት ነገሮችን እፈልጋለሁ እነርሱም ከሐሜት ስለመራቅ፣ ክፉ ነገርን ከማየት ስለመራቅና ከንቱ ነገርን ከመስማት ስለመራቅ ናቸው›› እያሉ ይናገሩ ነበር፡፡

❖ አቡነ ተክለ ሐዋርያት የታላቁን አባት የአቡነ አትናቴዎስን መቃብር ለማየት በሄዱ ጊዜ ቆመው ሲጸልዩ ከእግራቸው በታች ጸበል ፈልቆ በጽዋ ውኃ ሲፈስ አገኙት፤ ውኃውንም ወስደው ቦታውን ላሳየቻቸው ለእግዚእ ክብራ ሰጧት፤ እርሷም መካን ለነበረችው ገረዷ ሰጠቻትና ገረዷም በጻድቁ ጸሎት የፈለቀውን ውኃ ጠጥታ ልጅ ወለደች፤ ይህ አባታችን ያፈለቁት ጸበል ዛሬም ድረስ ሲፈስና ሕሙማንን ሲፈውስ ይገኛል፡፡

❖ ባሕር ውስጥ በሚገኝ ዋሻ ውስጥም ገብተው ብዙ ዘመን በጸሎት ኖረዋል፤ ሰዎች የአባታችንን የእግራቸውን እጣቢ ሕመምተኞች ላይ በረጩት ጊዜ በላያቸው ላይ ያደረባቸው ርኩስ መንፈስ እየጮኸ ይወጣል፡፡

❖ ቅዱሳን መላእክት ዘወትር እየመጡ አባታችንን ይጎበነኟቸዋል፤ እመቤታችን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትላ እየመጣች ትጎበኛቸዋለች፤ ብዙ ተጋድሎ ባደረጉበት ዋሻ ውስጥም ሳሉ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ተገልጦላቸው በቦታው ላይ ታላቅ ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡

❖ መላእክትም ወደ ሰማይ አሳርገዋቸው በሥሉስ ቅዱስ መንበር ፊት አቁመዋቸው ታላቅ ምሥጢርን አይተዋል፡፡
❖ አቡነ ተክለ ሐዋርያት ለመድኃኔዓለም ሥጋና ደም ትልቅ ክብር ያላቸው አባት ናቸው፤ አንድ በከባድ በሽታ ይሠቃይ የነበረ ሰው ‹‹ነፍሴ ከሥጋዬ ሳትለይ ፈጥናችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውሰዱኝና የጌታችንን ሥጋና ደም ልቀበል›› ብሎ ቤተሰቦቹን ለመነ፡፡
❖ ቤተሰቦቹም ወደ ቤተ ክርስቲያን ወስደውት ሥጋ ወደሙን ከተቀበለ በኋላ ከሆዱ ውስጥ ዥንጉርጉር ደምና ሐሞት ከመግል ጋር ወጣ፡፡
❖ በዚህም ጊዜ ካህናቱ ስለ ሥጋ ወደሙ ክብር ብለው በዕቃ ተቀበሉት፤ ሽታው ግን ቤተ ክርስቲያኑን አናወጸው፡፡
❖ በዚህም ጊዜ አባታችን ተክለ ሐዋርያት መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለእኛ ብሎ በዕለተ ዐርብ መራራ ሐሞትና ከርቤ መጠጣቱን አስበው ከሰውየው ሆድ ውስጥ የወጣውን ደም የተቀላቀለበትን መግልና ሐሞት ስለ ሥጋ ወደሙ ክብር ብለው በቤተ ክርስቲያኑ በተሰበሰቡት ሰዎች ፊት አንሥተው ጠጡት፡፡
❖ ይህም የሆነበት ዕለት እሁድ ነበርና አባታችን እዚያው ቤተ ክርስቲያኑ ዋሉ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስም አባታችን ወዳሉበት መጥቶ ‹‹ወዳጄ ተክለ ሐዋርያት ሆይ ሰላምታ ይገባሃል፡፡
❖ በሰው ሁሉ ፊት እንዳከበርከኝ እኔም በምድራውያንና በሰማያውያን መላእክት ሁሉ ፊት አከብርሃለሁ›› ካላቸው በኋላ ሌላም ብዙ ቃልኪዳን ገባላቸው፡፡
❖ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደተለያዩ የሀገራችን ገዳማት በመሄድ ከቅዱሳን በረከትን ከተቀበሉ በኋላ በየሄዱባቸው ገዳማት 40 ቀንና 40 ሌሊት ይጾማሉ፤ ከሰንበት በቀርም ምንም ምንመ አይቀምሱም፤ ሰንበትም በሆነ ጊዜ የዕንጨቶችን ፍሬ ብቻ ይመገባሉ፡፡
❖ አባታችን ከዋልድባ ገዳም ወጥተው ወደ ደባብ ገዳም በመሄድ በዚያ አርባዋን ቀን ከጾሙ በኋላ ጌታችን ተገለጠላቸውና ‹‹ተነሥተህ ወደአልተጠመቁ አሕዛብ አገር ሂድ በዚያ በአንተ እጅ የሚጠመቁና የሚድኑ ብዙ አሕዛብ አሉና በስሜ አስተምር›› አላቸው፡፡
❖ አባታችንም ተነሥተው ‹‹ሀገረ ጽልመት›› ወደሚባል ወዳልተጠመቁ አሕዛብ አገር ሄደው የአገሪቱን ንጉሥና ሕዝቡንም በጠቅላላ አስተምረው በተአምራቶቻቸው አሳምነው አጥምቀዋቸዋል፡፡
❖ በዚያም ሀገር ለአሕዛብ እየጠነቆለ የሚኖር አንድ መሠርይ ነበርና አባታችንን አግኝተውት አስተምረው በላዩ ያለበትን ርኩስ መንፈስ አውጥተውለት አጥምቀውታል፡፡
❖ አባታችን የእግዚአብሔርን ወዳጅ የሊቀ ነቢያትን መቃብር ያሳቸው ዘንድ ጌታችንን በለመኑት ጊዜ ጌታችን በሌሊት ተገልጦላቸው ወስዶ የሙሴን መቃብር አሳይቷቸዋል፡፡
❖ በጌታችን የጥምቀት በዓል ቀን አባታችን ተክለ ሐዋርያት ጸሎት በማድረግ ሰዎችን ሲያጠምቁ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሳቸው ላይ ይታይ ነበር፤ በቆሙበትም ቦታ የብርሃን ምሰሶም እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶ ተተክሎ ታይቷል፡፡
❖ አባታችን ቅዱሳት ገዳማትን ለመሳለም ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ የሚዘዋወሩት በብርሃን ሰረገላ ነበር፤ በደመናም ተጭነው ሲሄዱ ያዩአቸው ቅዱሳን አሉ፡፡
❖ የመኮትን ቃል ወንጌልን ሲጸልዩ ቅዱሳን መላእክት መጥተው በክንፋቸው ይጋርዷቸው ነበር፡፡ የአቡቀለምሲስን ራእይ በጸለዩ ጊዜ ራሱ ዮሐንስ ወንጌላዊው መጥቶ በአጠገባቸው ይቆም ነበር፡፡
❖ አባታችን የዕረፍታቸው ጊዜ በደረሰ ሰዓት የብርሃን እናቱ እመቤታችን ሚካኤልንና ገብርኤልን ሰማዕቱን ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትላ መጥታ ‹‹የጳውሎስ አበባ የጴጥሮስ ፍሬ የልጄ ተክል ወዳጄ ተክለ ሐዋርያት ሆይ ሰላምታ ይገባሃል›› አለቻቸው፡፡

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 20:59


🌷መልክአ ቅዱስ መርቆሬዎስ📗

የቅዱስ መርቆሬዎስ አምላክ ሆይ የገብረ ማርያም ነፍስ ማርልኝ /፫/

የገብረ ማርያምን ነፍስ ማርልኝ
የገብረ ማርያምን ነፍስ ማርልኝ
የገብረ ማርያምን ነፍስ ማርልኝ

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 19:02


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት ፳፭/25/

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 16:52


በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ መርቆሬዎስ አለው ይበላችሁ።

🥰🙏🥰

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 15:00


ነገ ጥቅምት ❷❺ ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ነው።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን።🙏

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 15:00


🌿#ቅዱስ መርቆሪዎስ🌿🔴

📌•••ወር በገባ በ25 ታላቁ ሰማእት ቅዱስ መርቆርዮስ መታሰቢያ በዓሉ ነው እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ቅዱስ መርቆርዮስ የቀድሞ ስሙ ፒሎፓደር ሲሆን ትርጉሙም #የአብ ወዳጅ የወልድ አገልጋይ ማለት ነዉ፡፡ በወጣትነቱ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም ብሎ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ፤በመጨረሻም ህዳር 25 ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ። ንጉሱ በዚያዉ ዘመን ክርስቲያኖችን በጣም ያሰቃይ ነበር፡፡ቅዱስ ባስልዮስም ይገስጸዉ ነበር በዚህም ምክንያት ንጉሱ ቅዱስ ባስልዮስን አሰረዉ፡፡ጳጳሱ በታሰረበት እስር ቤት የቅዱስ መርቆርዮስ ሥዕል ነበር፡፡ቅዱስ ባስልዮስም ከሥዕሉ ስር በመሆን ጸለየ ሥዕሉም ከቦታዉ ታጣ ያ ሥዕል ወደ ዑልያኖስ ቤት ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለዉ፡፡በስዕሉ ላይ ያለዉ ጦር ጫፉ ደም ይንጠባጠብ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሀዲ ዑልያኖስን ቅዱስ መርቆርዮስ በሥዕሉ አማካኝነት እንደገደለዉ አዉቆ እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ ይህ ሰማዕት በአገራችን በስሙ በርካታ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት አሉት በተለይም ቅዱስ ላሊበላ ካነጻቸው 11 ውቅር አብያተክርስቲያናት አንዱን ቤተ መርቆሪዎስ ብሎ ሰይሞለታል፤ በዚህ በሰሜን ሸዋ ደግሞ የሚገርም ገዳም አለው፤ ካህናት በማህሌት ወረብ ሲያቀርቡ ስዕሉ ያሸበሽባል ይዘላል፤ ይህንንም አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል፤ በመዲናችን አዲስ አበባ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ታቦቱ አለ:: መርቆሪዎስ ከሞተ በኃላ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል፤ በኃላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት፤ እኛስ እስመ አልቦ ነገር ዘይሳኣኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን፤ ዘኁልቁ 22፤28 ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አለ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነብዩን እብድነት አገደ ይላል 2ጴጥ 2፤16። ከሰማዕቱ በረከት ያሳትፈን።
<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>
አሜን አሜን አሜን+++

https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 14:59


☞ ወር በገባ በ 25 የጻድቁ አባታችን አቡነ ሕፃነ ሞዓ ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡ ☞የአቡነ ህፃን ሞዓ ቤተሰቦቻቸው ልጅ ባለ መውለዳቸው እድሜያቸው በጣም አርጅተው ሰለነበር ፈጣሪያቸውን ዘወትር ይማፀኑ ነበር፡፡
☞ለጻድቁ አባታችን ለህፃን ሞዓ አባት ለሆኑ አርኬሌዲስ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ
ገብርኤል ተገልጾ ለሰማይ ለምድር የበቃ ልጅ እንደሚወልዱ አበሰራቸው፡፡
☞ለጻድቁ እናታቸውም ትቤፅዮን ታላቁ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ እንዲሁ
የበቃ የነቃ የልጅ ፍሬ እንዳለቸው ነገሯቸው፡፡
☞በዚህም መሠረት አባታችን በግንቦት 25 ቀን ተፀንሰው በብርሃን ክርታስ
ተጠቅልለው በጥር 25 ቀን ተወለዱ፡፡
☞አባታችን አብነ ሕጻን ሞኣ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመድ
ናቸው፡፡
☞አቡነ ህፃን ሞዓ ሌላኛው ስማቸው ህፃን ዘደብረ በግዕ ተብለው ይጠራሉ፡፡
ይኸውም የደብረ በግዑ ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ሰለሆኑ ነው፡፡
☞ጻድቁ አባታችን ወይንዬ ተክለ ሐይማኖት (ከደብረ ብርሃን) በቅርበት ከሚገኝ
ቦታ አንድ ሀብታም ገበሬ ጋር በጉልበታቸው ተቀጥረው እያገለገለገሉ ሳለ፡፡
☞ከእለታት በአንድ ቀን ያ ገበሬ እርሻ ለመሄድ እተሰናዳ ሳለ በጠዋት አንደኛው
ገበሬ ይሰወራል ገበሬውም ዛሬ እርሻ ከመሄድ አልቀርም ብሎ ለግዜው በጠፋው
በሬ ተተክተው አባታችን አቡነ ሕጻን እንዲያርሱ ያደርጋቸዋል፡፡
☞በዚያም ሲያርሱ የጎተቱበት ፈሩ(መስመሩ) ከዛም በጣም ደክሟቸው ሰለነበር
ከሰውዬው ሽሽት እየሮጡ ከትልቅ ተራራ አናት ሲደርሱ ሰውነታቸው ተብረብርኮ
በእግራቸው ወደ፡ታች ስርጉድ ያለች ድንጋይ ከሩጫቸው የተነሣ በቆሙበት ቦታ
ሆነው እጅጉን ደክሟቸው በሐይል የተነፈሱበት ምድር ዛሬም የተነፈሱበትን
ለማሰብ እፍ እፍ የሚል ትንፋሽ ልክ እንደ ሰው የሚሞቅ ትንፍሽ ታወጣለች፡፡
☞ያም በፃድቁ እስትፋስ የተመሰለው ይህ ከመሬት ውስጥ የሚወጣ እስትንፋስ
ለአስም በሽታ መድሐኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወሰ ይገኛል፡፡
☞ይህ የጻድቁ የአብነ ሕጻን ገዳም ከደብረ ብርሃን በቅርብ ርቀት ከወይንዬ
ተክለሐይማኖ
ወረድ ብሎ ይገኛል በዚህ በተጸነሱበት በግንቦት 25 ቀን በደማቅ ሁኔታ
ይከበራል፡፡
☞ጌታች መድኃኒታች እየሱስ ክርስቶስ የሰጣቸው ቃል ኪዳን፡፡
☞ወር በገባ በ25 ቀን ሰምህን የሚጠራ፤ ዝክርህን ያዘከረውን፤ገድልህን
ያነበበውን ያስነበበውን የሰማውን ለቤተክርስቲያን መገልገያ ጧፍ እጣን
የሰጠውን፤ገዳማቸውን የረገጠውን እሰከ 12ትውልድ እምርሃለሁ የሚል ቃል
ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡
☞እኛንም የቃልኪዳናቸው ተካፋይ ያድርጉን፡፡
☞ጻድቁ አባታችን አቡነ ሕፃን ሞኣ ገዳማትን ከቀኑ ሀይማኖት ካስተማሩ በኃላ
በሐምሌ 25 ቀን እረፍታቸው ሆነ፡፡
☞የጻድቁ አባታችን አቡነ ህፃን ሞዓ ረድኤትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
☞የጻድቁ አባታችን የአቡነ ህፃን ሞዓ በዓለ እረፍታቸው ሐምሌ 25 ነው፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 14:59


🌹ወር በገባ በ 25/ታስባ የምትውለው ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት የሕሙማን እናት የተባለችው ሐምሌ 25 ያረፈችው በብዙ ሊቃውንት የተወደሰችው የቅድስት ቴክላ ድንቅ ታሪክ +

❖ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረችው ብዙዎች አበው በድርሳናቸው የመሰከሩላትን በድንግልናዋ ጸንታ የኖረችውን ቅድስት ቴክላ ናት፤ ይኽቺ ቅድስት ሴት፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ከተከተሉት ቅዱሳን ሴቶች አንዷ ስትኾን እጅግ ውብ፣ ሀብታምና የተማረች ነበረች ፤ በዚኽም ከልዑላኑ ታሚሪስ የሚባል ወጣት ሰው አጭቷት ነበር፤ ቅዱስ ጳውሎስ በ45 ዓ.ም. ከአንጾኪያ ከተማ ወደ ኒቆምድያ ከተማ ኼዶ ወንጌልን ሲሰብክ በተመስጦ ኾና ትምህርቱን ትከታተል እንደነበር ከሊቃውንት ቅዱስ አምብሮስና ቅዱስ አውግስጢኖስ ጽፈዋል።

❖ በሐዋርያውም ትምህርት ልቧ በመነካቱ የድንግልና ሕይወትን በመምረጥ ለእናቷ የታሚሪስ እጮኝነቷን ማፍረሷንና ክርስቲያን እንደምትኾን ነገረች፤ ወላጆቿ ግን ርሱን እንዳትሰማ ቢያግባቧትም ርሷ ግን እነርሱን አልሰማቻቸውም፤ በዚኽ ምክንያት አባቷ ዲማኖስና ርምጋኖስ ከሚባሉ ዳኞች ኺዶ ከሰሳት፤ እነርሱም ሊያስገድዷ ቢሞክሩም አልቻሉም፤ ከዚያም የቀደመ ልብሷንና ጌጦቿን ኹሉ ትታ ከቅዱስ ጳውሎስ ጉባኤ ተቀመጠች፡፡

❖ በዚኽ ተበሳጭተው በመኰንኑ ዘንድ እንደገና ከሰዋት፤ ርሱም ሌሎቹ ፈርተው ወደ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳይኼዱ በእሳት እንዲያቃጥሏት አዘዘ፤ ርሷ ግን በሚያቃጥሏት ጊዜ ልቧን አጽንታ ቅዱስ ጳውሎስን ተመለከተችው፤ ያን ጊዜ ሐዋርያው በመስቀል ምልክት ባማተበ ጊዜ ወደ እሳቱ ምድጃ ተወረወረች፡፡

✍️ “ፈነወ እግዚአብሔር ዝናመ ብዙኀ ወበረደ ወመብረቀ ወኮነ ዕቶነ እሳት ከመ ጠል ቈሪር ወሮጸት ቴክላ ወበጽሐት ኀበ ቅዱስ ጳውሎስ ኀበ ኀሎ መካነ ኅቡአ” ይላል፤
❖ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ብዙ ዝናብን፣ በረድን፣ መብረቅን ላከ፤ የእሳቱም ምድጃ እንደ ቀዝቃዛ ጠል ኾነ፤ ቴክላም ሩጣ ቅዱስ ጳውሎስ ተሰዉሮ ወደ አለበት ቦታ በመድረስ፤ ወንጌልን ለመማር በኼደበት ኹሉ ትከተለው ዘንድ ለመነችው፡፡

❖ ከዚያም ከርሱ ጋር አንጾኪያ ከተማ በመኼድ ለዐዲስ አማኞች የእግዚአብሔርን ቃል ትነግራቸው ነበር፤ ከመልኳ ውበትም የተነሣ ከመኳንንቶቹ አንዱ ሊአገባት ፈለገ፤ ርሷ ግን ዘለፈችው፤ ከዚያም ለአንበሶች እንድትጣል ቢደረግም ልክ እንደ ነቢዩ ዳንኤል አንበሶቹ ሳይነኳት በነርሱ መኻከል ኹለት ቀናት ቆየች፤ ከዚኽም በኋላ በኹለት በሬዎች መኻከል አስረው በከተማው ውስጥ አስጐተቷት፤ ነገር ግን ምንም ክፉ ነገር አልደረሰባትም፤ ከዚያም በኋላ ለቀቁዋት፡፡

❖ ርሷም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ኼደች ርሱም አጽንቶና አረጋግቶ የሰማችውን እንድትመሰክር አዘዛት፡፡ ርሷም ወደ ወላጆቿ ሀገር በመኼድ ስለ ክርስቶስ መሰከረች፤ አባትና እናቷም አምነው ክርስቲያን ኾኑ፤ ሀብተ ፈውስም ተሰጥቷት ብዙዎችን ትፈውሳቸው ነበር በዚኽም “የሕሙማን እናት” በመባል ትታወቃለች፤ በመጨረሻም ተጋድሎዋን ፈጽማ ሐምሌ 25 ዐረፈች፤ መስከረም 27 ትታሰባለች፤ ሥጋዋም በግብጽ ደቡብ ሰንጋር በሚባል ቦታ ተቀመጠ፤ በዚያም ከሥጋዋ የተነሣ ብዙ ድንቅ ተአምር ተገልጧል፡፡

❖ በርካቶች ቅዱሳን አበው በየድርሳናቸው የቅድስት ቴክላን ቅድስናና ተጋድሎ ጽፈውላታል፤ በተለይ ቅዱስ ሜቶዲየስ ቅድስት ቴክላ ከቅዱስ ጳውሎስ በተማረችው ትምህርት ምን ያኽል ጠንካራ እንደነበረች፤ በጊዜው ከነበሩት የደናግል ኅብረት ከፍ ከፍ ያለች፤ ድንግልናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ በዝማሬም ትመራቸው እንደነበር ይገልጣል ፡፡

❖ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም ስለ ርሷ ክብር ሲጽፍላት የተባረከች ድንግል ቴክላ ንጽሕናዋን ሰማዕትነቷን ለልዑል እግዚአብሔር በማቅረብ በአንድ እጇ በሥጋው በደማዊ ፈቃድ ላይ የድል ዘውድን ስትይዝ፤ በሌላኛው እጇ በአደገኛ ሥቃይና መከራ ላይ የክብር አክሊሏን እንደያዘች ዐውቃለኊ ብሏል፡፡

❖ ቅዱስ ጀሮምም በደብዳቤው ላይ “የጌታ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም የደናግልን ማኅበር አስከትላ እናንተን ለመገናኘት የምትመጣባት የዚያቺ ቀን ክብር እንደምን ያለ ነው!... ያን ጊዜ ቴክላ እናንተን ለማቀፍ በደስታ ትበርራለች ብሏል፡፡
❖ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያም የድንግልና ሕይወቷን አብነት እንዲያደርጉ ሲያስተምር
✍️“የንጽሕና አምሳል ከምትኾን ወደር ከሌላት ከአምላክ እናት በመቀጠል ከሴቶች አስቀድማ ሰማዕት የኾነች ቴክላን ምሳሌ አድርጌ አነሣለኊ፤ እናንተም የርሷን መንፈሳዊ ውበት ተላብሳችኊ ሰማያዊ ጸጋን ለማግኘት ነፍሳኹን በተለያዩ መንፈሳዊ መልካሞች ሥራዎች ታስጌጧት ዘንድ ይገባል” በማለት አስተምሯል፡፡

❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም ተጋድሎዋን በማዘከር
✍️“ሰላም እብል ለሐዋርያዊት ቴክላ እግዚአብሔር ዘአኀየላ ኢያቊስልዋ አናብስት ወእሳተ ዕቶን ኢያሕልላ እስመ አምነት ትምህርተ ጽድቅ ከመ ጳውሎስ ይቤላ እስከኀደገት አበዊሃ ወገደፈት ብዕላ”
👉አንበሶች እንዳያቈስሏት የእሳት ምድጃም እንዳያቃጥላት እግዚአብሔር ያበረታት ሐዋርያዊት ለኾነች ለቴክላ ሰላምታ ይገባል፤ አባቶቿን እስክትተውና ሀብቷን እስክትጥል ድረስ ደርሳ ጳውሎስ እንዳላት የእውነት ትምህርትን አምናለችና እያለ የተቀደሰ ሕይወቷን በአድናቆት ጽፎላታል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ
✍️“ሰላም ለጤቅላ (ቴክላ) ዘሞአቶ ለተኲላ በገድል ንጽሕት ድንግል”
👉ንጽሕት ድንግል በገድል ተኲላውን ያሸነፈችው ለኾነች ለጤቅላ ሰላምታ ይገባል)እያለ ያወድሳታል።

የቅድስት ቴክላ በረከት ረድኤት ይደርብን
https://t.me/zikirekdusn
ምንጭ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ አቡየ

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 14:59


ለሁነኛ ሰው ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን ለነዳያን አካፈለ::

+ቀጥሎም ቤተሰቦቹንና አገልጋዮቹን ጨምሮ ወደ ሃገረ ገምኑዲ ሔደ:: በመኮንኑ ፊት የክርስቶስን አምላክነት ቢመሰክር ፈጽመው አሰቃዩት:: በማግስቱም ወታደሮቹ ለጣዖት ካልሰገድክ ሲሉት "ቆዩማ ላሳያችሁ" ብሎ በጸሎቱ ጣዖታትን ከነ ካህናቶቻቸው ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው አደረገ:: በተአምሩም መኮንኑና ሠራዊቱ አምነው ተከተሉት::

+በፍጻሜውም በሌላ ሃገር መኮንኑ ቅዱስ ዮልዮስን ከቤተሰቡና ከ1,500 ያህል ተከታዮቹ ጋር: 2ቱን የሃገረ ገዥዎች ጨምሮ አንገታቸውን አሰይፏቸዋል::

=>አምላከ ጻድቃን ወሰማዕት በቃል ኪዳናቸው እንዲምረን ቸርነቱ ይርዳን:: በረከታቸውንም አትርፎ ይስጠን::

=>ጥቅምት 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
2.አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
3.ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4.ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ
5.ቅዱሳን አሞኒና ሙስያ (የታላቁ ዕብሎ ወላጆች)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.ቅዱስ አቡፋና ጻድቅ
6.ታላቁ አባ ቢጻርዮን

=>+"+ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: +"+ (ማቴ. 16:24)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 14:58


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

=>+"+ እንኩዋን ለታላቁ "ጻድቅና ሰማዕት አቡነ አቢብ": "አባ ዕብሎይ" እና "ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" አቡነ አቢብ (አባ ቡላ) "*+

=>ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን!

¤እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን: ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል!

¤ቅዱሱ አባታችን:- "ቡላ - የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን::

¤ዳግመኛም "አቢብ - የብዙኃን አባት" ብለን እንጠራሃለን::

¤እርሱ ቅሉ አባትነትህ አንተን ለመሰሉ ቅዱሳን ቢሆንም እኛን ኃጥአንን ቸል እንደማትለንም እናውቃለን::

¤አባ! ማነው እንዳንተ የክርስቶስን ሕማማት የተሳተፈ!

¤ማን ነው እንዳንተ በፈጣሪው ፍቅር ብዙ መከራዎችን የተቀበለ!

¤ማንስ ነው እንዳንተ በአንዲት ጉርሻ አማልዶ ርስትን የሚያወርስ!

¤የፍጡራንን እንተወውና በፈጣሪ አንደበት ተመስግነሃልና ቅዱሱ አባታችን ላንተ ክብር: ምስጋናና ስግደት በጸጋ ይገባሃል እንላለን::

+"+ ልደት +"+

=>አባታችን አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ ሮሜ ናት:: ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ እጅግ ጽኑ ክርስቲያኖች ነበሩ:: ልጅ ግን አልነበራቸውም:: ዘመነ ሰማዕታት ደርሶ ስደት በሆነ ጊዜ እነርሱም በርሃ ገቡ::

+በዚያም ሳሉ በቅዱስ መልአክ ብሥራት ሐሪክ ጸንሳ ብሩሕ የሆነ ልጅ ወለደች:: ቅዱሱ ሕጻን ሲጸነስ ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ እንዲህ የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል::
"ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን"

+"+ ጥምቀት +"+

=>ቅዱሱ ሕጻን ከተወለደ በሁዋላ ሳይጠመቅ ለ 1 ዓመት ቆየ::
ምክንያቱም ዘመኑ የጭንቅ ነውና ካህናትን እንኩዋን በዱር በከተማም ማግኘት አይቻልም ነበር:: እመቤታችን ግን ወደ ሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ሒዳ "አጥምቀው" አለችው::

+ወደ በርሐ ወርዶ ሊያጠምቀው ሲል ሕጻኑ ተነስቶ: እጆቹንም ዘርግቶ:- "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕጻኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ::

+"+ ሰማዕትነት +"+

=>የቅዱሱ ቡላ ወላጆች ለ10 ዓመታት አሳድገውት ድንገት ሕዳር 7 ቀን ተከታትለው ዐረፉ:: ሕጻኑን የማሳደግ ኃላፊነትን የአካባቢው ሰዎች ሆነ:: ሕጻኑ ቡላ ምንም የ10 ዓመት ሕጻን ቢሆንም ያለ ማቁዋረጥ ሲጾም: ሲጸልይ ክፉ መኮንን "ለጣዖት ስገዱ" እያለ መጣ::

+በዚህ ጊዜ በሕጻን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት:: በጅራፍ ገረፉት: በዘንግ ደበደቡት: ቆዳውን ገፈፉት: በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት:: ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና 2 ጊዜ ከሞት ተነሳ:: በመጨረሻ ግን ሚያዝያ 18 ቀን ተከልሎ ሰማዕት ሆኗል::

+"+ ገዳማዊ ሕይወት +"+

=>ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በሁዋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ::

+ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል::
ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኮሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው::

+"+ ተጋድሎ +"+

=>አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል::

+በጭንቅላቱ ተተክሎ ለብዙ ጊዜ ጸልዮ ጭንቅላቱ ይፈሳል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ስለ ጌታ ፍቅርም ምንም ነገር ሳይቀምስ ለ42 ዓመታት ጹሟል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር::

+የሚታየውም እንደ ተወለደ: እንደ ተጠመቀ: እንደ ተሰቀለ: እንደ ተነሳ: እንዳረገ እየሆነ ነበር:: አንድ ቀንም ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! እንዳንተ ስለ እኔ ስም መከራ የተቀበለ ሰው የለም:: አንተም የብዙዎች አባት ነሕና ስምህ አቢብ (ሃቢብ) ይሁን" አለው::

"እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ:
ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ:
ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ" እንዲል::

+" ዕረፍት "+

=>አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ::

+ጌታም ከድንግል እናቱ ጋር መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! ስምህን የጠራውን: መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ:: አቅም ቢያጣ "አምላከ አቢብ ማረኝ" ብሎ 3 ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን: በስምሕ እንኩዋ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" ብሎት ነፍሱን በክብር አሳረገ: በሰማይም ዕልልታ ተደረገ::

+"+ ታላቁ አባ ዕብሎይ +"+

=>ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት "ርዕሰ ገዳማውያን" ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ በመሆኑ በዕለተ ዕረፍቱ (የካቲት 3 ቀን) እንመለከተዋለንና የዚያ ሰው ይበለን::

+"+ ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት +"+

=>ከሁሉ አስቀደሞ ስለ ሰማዕታት ዜና ሲሰማ ለዚህ ቅዱስ አንክሮ (አድናቆት): ክብርና የጸጋ ውዳሴ ይገባዋል:: ምክንያቱም ገድለ ሰማዕታትን የጻፈልን እርሱ ነውና:: ነገር ግን መጻፍ ሲባል: ነገሮች እንዲህ እንደ እኛው ዘመን ቀላል እንዳይመስሏችሁ:: ቅዱሱ ዜና ሰማዕታትን ለማዘጋጀት ሃብቱን: ንብረቱን: ቤተሰቦቹንና ሕይወቱንም ሰውቷል::

+ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በመጨረሻው ዘመነ ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ ክ/ዘ) ዓለም በደመ ሰማዕታት ስትሞላ እንኩዋን የሰማዕታቱን ዜና የሚጽፍ: ሥጋቸውን እንኩዋ የሚቀብር አልተገኘም:: "ወኃጥኡ ዘይቀብሮሙ - የሚቀብራቸውም አጡ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: (መዝ. 78:3)

+እግዚአብሔር ግን ስለ ወዳጆቹ ሰማዕታት ይህንን ቅዱስ አስነሳ:: ቅዱስ ዮልዮስ በዘመኑ ደግ ክርስቲያን: ትዳርና ልጆች ያሉት: እጅግ ባለ ጸጋና 300 አገልጋዮች ያሉት: ምጽዋትንም የሚወድ ሰው ነበር::

+በወቅቱ የክርስቲያኖች በየመንገዱ ወድቀው መታየታቸው ዕረፍት ቢነሳው ከቤተሰቦቹ ጋር መክሮ መልካም ግን ደግሞ ከባድ ውሳኔን አስተላለፈ:: ውሳኔውንም ታጥቆ ይተገብረው ጀመር::በእውነት ድንቅ ሰው ነው:: በምን እንመስለዋለን! እርሱን የፈጠረውን ጌታ "ዕጹብ ዕጹብ" ብለን ከማድነቅ በቀር::+ሰማዕታቱም ስለ ደግነቱ የሚመልሱለት ቢያጡ ዝም ብለው ይመርቁት ነበር::+እንዲህ: እንዲህ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ሊፈጸም ወራት ቀሩት:: በዚህ ጊዜ ለሰማዕትነት ከመነሳሳቱ የተነሳ ጌታችንን ተማጸነ:: ጌታችንም ተገልጾለት "ሒድና ሰማዕት ሁን: ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: እርሱም ደስ እያለው ዜና ሰማዕታቱን

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 10:35


አረሳት ኢትዮጵያ በእርፈ መስቀል
አባ ተክለሃይማኖት ሰባኬ ውንጌል
የእግዚአብሔር ሰዉ ነዉ ተወዳጅ በሰማይ
የተረማመደ በጽድቅ አደባባይ

......አዝ.....

ፈውሱ ና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠር ከተማ
ይኢቲሳው ኮከብ የደብረ አሰቦቱ
ለውንጌል ተዋጋች ንጽህት ሕይወቱ

......አዝ......

ፋናው እስከ ዛሬ ሲያበራ የኖረ
የኢቲሳው አባት ፍስሃጽዮን
የእግዚሓርያ እናቱ ማህጸነ ብሩክ
ወለደች ኮከብን ሲዖልን የሚያውክ

......አዝ.....

ዲያብሎስ እስካሁን ስሙ ስጠራበት
ሲረገጥ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋና ቆላዉን በመስቀል ባረካት

......አዝ......

ምንጩና ፏፏቴዉ ተራራዉ ቅዱስ ነዉ
የአባታችን መስቀል ጸሎት ስለነካዉ
የተራመደበት የዳሰሰዉ ሁሉ
ዲዊ ይፈዉሳል ሳርና ቅጠሉ

/ዘማሪ ይልማ ኃይሉ/

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

03 Nov, 09:20


🌼 ምስለ ወልድኪ ዐማኑኤል
በሰላም ንኢ ማርያም 🌹🤍

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

30 Oct, 13:04


በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ እመ ብርሃን አለው ትበላችሁ።

ሰዓሊ ለነ ቅድስት

🥰🙏🥰

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

30 Oct, 12:16


"ነገ ጥቅምት 21 እናታችን እመቤታችን ቅድስተ ድንግል ማርያም ናት።🙏

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ትሰውረን።🙏

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

30 Oct, 12:15


«#ወር በገባ በ21 #እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት»🌹

🌹=>የአምላክ እናቱ እመ-ብርሃን ድንግል ማርያም:-
🌹=»በ3 ወገን (በሥጋ: በነፍስ: በልቡና) ድንግል
🌹=»በ3 ወገን (ከኀልዮ: ከነቢብ: ከገቢር) ንጽሕት
🌹=»ሳትጸንስ: በጸነሰች ጊዜና ከጸነሰች በሗላ ድንግል
🌹=»ጌታን ሳትወልድ : በወለደችው ጊዜና ከወለደችው በሗላ ድንግል ስትሆን እናትም ድንግልም መሆኗን አምነን እንመሰክራለን::

💖+እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ በላይ ክብርትና ንዕድ ናት:: ሊቃውንት አበው እንዳስተማሩን በዚህ ዕለት እንዲህ ብለን እንጸልያለን::
"ረስዪ ፍና ትሕትና አእጋርየ ይሑሩ:
ትዕቢትሰ ለአምላክ ጸሩ"
(እመቤቴ ሆይ ትዕቢትን አምላክ ይጠላልና እግሮቻችን በትሕትና እንዲሔዱ አድርጊ) አሜን ፫🙏

https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

30 Oct, 12:15


#አቡነ ቀውስጦስ ማለት

🌹☞•••ወር በገባ በ21 የሚታሰቡ በእመቤታችን ልደት ግንቦት 1የተወለዱ በእመቤታችን የዕረፍት ቀን ጥር 21 ያረፉ የእመቤታችን ወዳጅ የአቡነ ቀውስጦስ  ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡
☞ጻዱቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ የተወለዱት በሸዋ ክፍለ ሀገር በውግዳና ቡልጋ ውስጥ ሲሆን አባታቸው ገላውዴዎስ እናታቸው እምነጽዮን ይባላሉ፡፡
☞የጻድቁ የአቡነ ተክለሃይማኖት እናት እግዚኃሪያ አምነጽን ታናሽና ታላቅ
እህትማማቾች ናቸው፡፡
☞ገላውዴዎስ እና አምነጽዮን እግዚአብሔር የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ለዓመታት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰዕል ፊት ሲጸልዮና ሲለምኑ እመቤታችንም በስዕሏ ላይ አድራ አናገረቻቸው እንዲህም አለቻቸው፡

☞አንድ ልጅም ትወልዳላችሁ የሚወለደውም እኔ በተወለድኩበት ግንቦት 1 ቀን ሲሆኖ እረፍቱም በእኔ የዕረፍት ቀን ጥር 21 ቀን ነው እሱም የሰማያዊ ንጉሥ ጭፍራ ይሆናል አለቻቸው፡፡ በቃሉ መሠረትም ግንቦት 1 ቀን ጻድቁ አቡነ
ቀውስጦስ ተወለዱ፡፡

☞ጻድቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ የዚህን ዓለም ተድላ፤ደስታና ጣዕም ንቀው
ፈለገ ሐዋርያትን ተከትለው በሸዋ በከፋና በጅማ ዞረው የጌታችን መድኃኒታችን
የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በማስተማር በአረማውያን ነገስታት የሚደርስባቸውን መከራ በመታገስ በተጋድሎ ጸንተው ብዙ ሕዝብ ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከኃጥያት ወደ ጽድቅ መልሰዋል፡፡

☞በተለይም በሸዋ ክፍለ ሀገር ፈንታሌ ላይ ሠሪቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያስቃዩ(አራት መቶ ሰባ ሦስት መቶ) አጋንንትን እንደ ነብዩ ኤልያስ በጸሎታቸው ከሰማይ እሳት አውርደው ተራራውን ደምሰስው አጋንንቱን አቃጥለዋል፡፡ ሕዝቡንም ለጣዖት ለጠንቋይ ከመገዛት አድነውታል፡፡

☞ጻድቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ በብዙ ተጋድሎ ሲኖሩ በሰማዕትነት ያርፋ
ዘንድ ሰለ እግዚአብሔር መንግሥትና ዘላላማዊ ሕይወት የሚተጉ እንጂ የዚህ
ዓለም መንግሥት ሀብትና ሥልጣን የማይሹ እውነተኛ መናኝ ነበሩ፡፡

☞የታናሽ ወንድማቸው የአፄ ይኩኖ አምላክ ልጅ አፄ አምደ ጽዮን የአባቱን
እቁባት በማግባቱ ይህንን ልታደርግ አይገባህም ብለው እንደ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ቢገስጹት 11አሸከሮቹን በሌሊቱ ልኮ ከበዩ ወደ አንሣሮ ሀገር
ከወሰዳቸው በኃላ ኮሶ አረህ ከሚባል አፋፍ ላይ በእኩለ ሌሊት በጦር ጎናቸውን አሰወግቶ ደማቸውን አስፈሰሰ፡፡

☞ደማቸውም አስከታላቁ ወንዝ ጀማ ድረስ ሆነ፡፡
☞የፈሰሰው ደማቸውም ቀይ ብርሃን ሲሆን የሌሊቱ ጨለማ ከፀሐይ ሰባት እጅ የሚበልጥ ብርሃን በአውራጆቹ ሁሉ ታየ፡፡ በዘህ የተነሣ እሰከ ዛሬ ድረስ ሀገሩ ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡

☞ነፍሳቸው ከስጋቸው ስትለይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ
ከቅዱስ ድንግል ማርያም ጋር መጣና እንዲህ አላቸው፡፡
☞በዘመንህ ሰላሰለፍከው ክርስቲያናዊ ፍፁም ተጋድሎህ (7) የብርሃን አክሊል (ዘውጆች)ያዘጋጀውልህ ሲሆን

☞2 ለቱ እንደ ነብዩ ኤልያስና ነብዩ ሳሙኤል ለሆነው ንፅህናህ፡፡
☞2ለቱ እን አነ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ለሆነ የወንጌል ሰብከትህ፡፡
☞2ለቱ እንደ አነ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ፊቅጦር በትዕግሥት ሰለተጋደልክ፡፡
☞አንዱ(1) ሰለ ልብህ ርህራሄ ናት ብሎ አጎናጽፈኩህ፡፡
☞እንዲሁም ሰለ እኔ ምስክርነት የሞትከባት ምድር እንደ ዳዊት ሀገር እንደ
እየሩሳሌም ትሁንልህ፡፡ ወደ እርሷ የሆደውም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ
መቃብሬ ጎለጎታ እንደሄደ እቆጥርለታለሁ፡፡
☞ቡዙ ኃጢያት የሠራ ሰው ንሰሐ ገብቶ በዚያች ሀገር በስምህ ጥቂት ምጽዋት ቢሰጥ እኔ ኃጥአቱን አደመሰሰለታለሁ፡፡ ጠበልህንም ቢጠመቅ በደሉን አጠፋለታለሁ፡፡

☞በእረፍትህ ዕለት ለቤተክርስቲያን ለቅዱስ ቁርባን ሰንዴ፤ ወይንና ዕጣን
ያቀረበ ሰለ ኃጢአቱ ንሰሀ የገባ ሰው ቅዱስ ሥጋውንና ከቡር ደሙን ደሙን
እንደተቀበለ ንጹህ ሰው አደርገዋለሁ፡፡

☞ለስምህ መታሰቢያ በታነጸው ቤተ መቅደስ በንጽህና ቅዱስ ሰጋውንና ከብር
ደሙን የሚቀበል ሰው ራሱን ቤተሰቡን ባልንጀሮቹን ያድናል፡፡
☞ጌታችን ለጻድቁ አቡነ ቀውስጦስ ይህንን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው አረገ፡ ቅዱሳን መላእክትም ነፍሳቸውን ከስጋቸው በክብር ለዩ፡፡

☞እመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያምም በሰማይ መካከል ነፍሳቸውን
በፈገግታ ተቀበለች፡፡

☞የእረፍታቸውም ዕለት እመቤታችን ድንግል ማርያም ባረፈችበት ጥር 21
በመሆኑ እመቤታችንም መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ በልጄ በረከት
እባርካቸዋለሁ ብላ ቃል ኪዳን ገባችላቸው፡፡

☞የጽሁፍ ምንጭ ☞(ገድለ አቡነ ቀውስጦስ)
☞የጻድቁ አቡነ ቀውስጦስ በረከታቸው አማላጅነታቸው አይለየን፡፡
የቃልኪዳናቸው ተካፋ ያድርገን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህ ልጅ

☞https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

30 Oct, 12:14


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ጥቅምት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ እግዝእትነ ማርያም ✞✞✞

+እመቤታችን ድንግል ማርያም የወልደ እግዚአብሔር
እናቱ ናትና ሁሉን ትችላለች:: እርሱን ከሃሊ (ሁሉን ቻይ)
ካልን እርሷን "ከሃሊት" ልንላት ይገባል:: ልክ ልጇ ሁሉን
ማድረግ ሲችል በትእግስት ዝም እንደሚለው እመ
ብርሃንም ስንት ነገር እየተደረገ: በእርሷ ላይም አንዳንዶቹ
ስንት ነገርን ሲናገሩ እንደማትሰማ ዝም ትላለች::

+እኛ ኃጥአን ንስሃ እስክንገባ ድረስም "ልጄ! የዛሬን
ታገሣቸው?" እያለች ትለምንልናለች:: ቸሩ ልጇም ሊምረን
እንጂ ሊያጠፋን አይሻምና "እሺ እናቴ!" እያለ ይኼው
በዚህ ሁሉ ክፋታችን እስከ ዛሬ ድረስ አላጠፋንም::
*ቸር ነው
*መሐሪ ነው
*ይቅር ባይ ነው
*ታጋሽ ነው
*ርሕሩሕ ነው
*ቂምም የለውም:: በንስሃ ካልተመለስን ግን አንድ ቀን
መፍረዱ አይቀርምና ወገኖቼ ንስሃ እንግባ: ወደ እርሱም
እንቅረብ::

+ይህቺ ዕለት ለእመቤታችን እሥረኞችን የምትፈታባት
ናት:: የሰው ልጅ በ3 ወገን እሥረኛ ሊሆን ይችላል::
በሥጋዊው:- አጥፍቶም ሆነ ሳያጠፋ ሊታሠር ይችላል::
በመንፈሳዊው ግን ሰው በኃጢአት ማሠሪያ የሚታሠረው
በጥፋቱ ብቻ ነው::

+ሌላኛው ማሠሪያ ደግሞ ማዕሠረ ደዌ (በደዌ ዳኝነት)
መታሠር ነው:: መታመም የኃጢአተኛነት መገለጫ
አይደለም:: ምክንያቱም ከቅዱሳን ወገን ከ80 %
(ፐርሰንቱ) በላይ ድውያን ነበሩና::

+ታዲያ በዚህች ዕለት እመ በርሃን 3ቱንም ማሠሪያዎች
እንደምትፈታ እናምናለን:: በእሥር ቤትም: በኃጢአትም
ሆነ በደዌ ማሠሪያ የታሠርን ሁላችን በዚሁ ዕለት
እንድትፈታን የአምላክ እናትን እንለምናት::

+በ3ቱም ማሠሪያዎች የታሠሩ ወገኖቻችንንም እያሰብን
"ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሐን-የእሥረኞች ጩኸት
ወደ አንተ ይድረስ" እያልን (መዝ. 78:11) ልንጸልይ
ይገባል::

+እመ ብርሃንንም እንደ ሊቃውንቱ:-
"እማእሠረ ጌጋይ ፍትሕኒ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክ:
እምነ ሙቃሔ ጽኑዕ ወእማዕሠር ድሩክ:
ከመ ፈታሕኪዮ ዮም ለማትያስ ላዕክ::" እንበላት::

+" ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ "+

+ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ
ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው
ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት
ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት
ቆጥሯቸዋል::

+በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ
አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ
የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው
እንጂ::

+ቅዱስ መጽሐፍ እንደነገረን ጌታችን በነአልዓዛር ቤት
በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ
ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ
ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::

+ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ
ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል::
(ዮሐ.11)

ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በኋላ ሊያስነሳው
ይመጣል::

+ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው
ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር
ተቀበለችው::

+'አዳም ወዴት ነህ' ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ
'አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት' አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ
ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::

+ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር" ብሎ
አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ
ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ
እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው)

+ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በኋላ በበዓለ ሃምሳ
መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት
ነውና): ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ74 ዓ/ም
አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::

+" ፍልሠት "+

+ይህቺ ዕለት ለቅዱሱ ሐዋርያ በዓለ ፍልሠቱ ስትሆን ይህ
የተደረገውም በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ቅዱሱ
ያረፈው ቆዽሮስ ውስጥ ነው:: ግን ባልታወቀ ጊዜና
ምክንያት ወደ ኢየሩሳሌም ሒዷል::

+አንድ ቀንም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ኢየሩሳሌም
ውስጥ ሲቆፍሩ አንድ አንድ ሳጥን አገኙ:: በላዩ ላይ
ደግሞ "ይህ የጌታ ወዳጅ የአልዓዛር ሥጋ ነው" የሚል
ጽሑፍ አግኝተው ደስ ተሰኝተዋል:: በታላቅ ዝማሬና
ፍስሐም ከኢየሩሳሌም ወደ ቁስጥንጥንያ አፍልሠውታል::
+የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::

+" አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም "+

+እኒህ ጻድቅ ሰው ግብጻዊ ሲሆኑ በሰፊው የሚታወቁት
በኢትዮዽያና በኢየሩሳሌም ነበር:: ገና በወጣትነት
የጀመሩትን የተጋድሎ ሕይወት ገፍተው በበርሃ ሲኖሩ
የወቅቱ የግብጽ ሲኖዶስ ከበርሃ ጠርቶ የኢየሩሳሌም
ዻዻስ እንዳደረጋቸው ይነገራል::

+በቅድስት ሃገርም በንጽሕናና በመንኖ ጥሪት ወንጌልን
እየሰበኩ ኑረዋል:: አባ ዮሐንስ የነበሩበት ዘመን 14ኛው
መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የወቅቱ የኢትዮዽያ ንጉሥ ደጉ አፄ
ዳዊት ነበሩ::

+ንጉሡ የግብጽ ክርስቲያኖችን ደም ለመበቀል (በወቅቱ
ከሊፋዎች ያሰቃዩዋቸው ነበር) እስከ ላይኛው ግብጽ
ወርደዋል::
በሃገር ውስጥ ያሉ ተንባላት አባሪዎቻቸውንም ቀጥተዋል::
በዚህ የተደናገጠው የግብጹ ሡልጣን 'አስታርቁኝ' ብሎ
ስለ ለመነ ለእርቅ የተመረጡ አባ ዮሐንስና አባ ሳዊሮስ
ዘምሥር ናቸው::

+እነዚህ አባቶች በ1390ዎቹ አካባቢ ወደ ኢትዮዽያ
ከመጡ በኋላ አልተመለሱም:: ምክንያቱም ደጉ አፄ
ዳዊት እጅግ ስለ ወደዷቸው 'አትሔዱም' ብለው
ስላስቀሯቸው ነው:: እንዲያውም ለግማደ መስቀሉ
መምጣት ትልቁን አስተዋጽኦ ያደረጉት አባ ዮሐንስ
ሳይሆኑ አይቀሩም:: ዛሬ የጻድቁ ዕረፍታቸው ነው::

+አምላከ ቅዱሳን ስለ ድንግል እናቱ ብሎ ከኃጢአት ሁሉ
ማሠሪያ ይፍታን:: የወዳጆቹን በረከትም አያርቅብን::

+ጥቅምት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እግዝእትነ ማርያም
2.ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ
3.አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
4.ቅዱስ ኢዩኤል ነቢይ
5.ቅዱስ ማትያስ ረድእ

በ 21 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ

+" ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር
እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት... ይሕንም ብሎ በታላቅ
ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ::
የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ::
ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም
'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው::" (ዮሐ. 11:40-44)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/zikirekdusn

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

30 Oct, 06:06


ነጭና ቀይ አበባ - ኢየሱስ ክርስቶስ!

ያለነው በዘመነ ጽጌ ነው። በማኅሌተ ጽጌ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው ምስጋናዎች "እንዘ ተሐቀፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀአዳ ወቀይሕ..." የሚለው ክፍል ይጠቀሳል። ይሄውም ቅድስት ድንግል ማርያም ነጭና ቀይ አበባ ከተባለ ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ፥ ደስ ከተሰኘ ከቅዱስ ገብርኤልና እንደርሷ ሩህሩህ ከሆነ ከቅዱስ ሚካኤል ጋር በመሆን ከሐዘን ታረጋጋን ዘንድ በረድኤት ወደኛ እንድትመጣ የምንማጸንበት ነው።

በዚህ ክፍል ልጇ መድኃኒታችንን "ጽጌ ፀአዳ ወቀይሕ - ነጭና ቀይ አበባ" ይለዋል። ጠቢቡ ሰሎሞን ነገረ ቤተክርስቲያንና ነገረ ክርስቶስን በገለጠበት "መኃልየ መኃልይ" በተባለ ከመዝሙራት በሚበልጥ መዝሙሩ ጌታችንን "ውዴ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።" እንዳለ(መኃልየ መኃልይ 5:10)።

"ነጭ" ያለው ፀአዳ መለኮቱን ሲገልጥ ነው። ይህም የንጽሐ ባሕርይው ምስክር ነው። ቅዱስ ዮሐንስም በራዕይ ያየው በርግጥ ፀአዳ መለኮቱ የተገለጠ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።  "ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ።" እንዳለ(ራእይ 1:14)። "ቀይ" ያለውም ደግሞ መሥዋዕት መሆኑን ሲያወሳ ነው። ይህም ስለ እኛ ደሙን ማፍሰሱን የሚያስረዳ ነው። ጌታችን ስለ እኛ በመገረፉና ደሙን በማፍሰሱ መላ አካላቱ በደም ተሸፍነው ነበር። ነቢይ እሳይያስ "ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጕልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው?" ያለው ይህ ልብሱ በደም የቀላ መድኃኒት በርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው(ኢሳ 63:1)።

ስለ ፀአዳ መለኮቱ ነጭ፥ ደሙን ስለማፍሰሱ ቀይ የሚባል አበባ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን።
ከእናቱ በረከት እንዲያሳትፈን ፈቃዱ ይሁንልን።

ጥቅምት 2016 ዓ.ም
ዲ.ን አምደመስቀል ሙሉጌታ

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

30 Oct, 04:46


''እናቴ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ልጅሽ ሲታገሰኝ ልቤ የደነደነብኝ እኔን በምልጃሽ አስቢኝ''🙏

🙏ቅድስት ሆይ ለምኝልን

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

30 Oct, 02:48


"ወር በገባ በ 20 ሕንፀታ ለማርያም   እንዲሁም አባ በብኑዳ ናቸው ዛሬ ጥቅምት 20 አቡነ ዮሐንስ ሀፂር ዓመታዉ በዓላቸው ነው በእውነት በዓመቱም ይሁን በወሩ ታስበው ከሚዉሉት ቅዱሳን በረከት ረድኤታቸው ይክፈለን ፀጋቸው ጸሎታቸው ይደርብን አሜን🙏

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

29 Oct, 18:44


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት ፳/20/

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

29 Oct, 16:20


"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እግዚአብሔር ይመስገን

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

29 Oct, 14:35


🌹#ቅዱስ_በብኑዳ ሰማዕት🌹

📌 ወር በገባ በ20 የቅዱስ በብኑዳ መታሰቢያ ነው ይህ ቅዱስ ለብቻው የሚኖር ዕውነተኛ ተጋዳይ ነው የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጦለት የመቀደሻ ልብስ ለብሰህ ወርደህ ለመኰንኑ ተገለጥለት አለው።

❖ በዚያን ጊዜ መኰንኑ አርያኖስ ከመርከብ ወርዶ ወደዚያች አገር ወደብ መድረሻው ጊዜ ነበር፤ ይህንንም ባሕታዊ ፈልጎት አላገኘውም ነበር፤ እነሆ ቅዱስ በብኑዳም በፈቃዱ መጥቶ ወደ መኰንኑ ሔዶ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን በግልጥ እኔ ክርስቲያን ነኝ ብሎ በታላቅ ቃል ጮኸ።

❖ መኰንኑም ፈልጎ ያጣው የታወቀ ባሕታዊ መሆኑን በአወቀ ጊዜ እንዲአሠቃዩት በእግር ብረትም አሥረው ከጨለማ ቤት እንዲጥሉት አዘዘ፤ በዚያን ጊዜም ብርሃን ወጣ የእግዚአብሔር መልአክም ከሕማሙ ፈወሰው አበረታው አጽናናውም።
❖ በዚያችም አገር ስሙ ቄርሎስ የሚባል ምእመን ሰው ነበረ ከእርሱ ጋራም ሚስቱና ዐሥራ ሁለት ጐልማሶች ልጆቹ አሉ፤ እነዚህን ሁሉንም የከበረ በብኑዳ አስተማራቸው አጽናንቷቸውም ራሶቻቸውን ቆርጠዋቸው በሰማዕትነት ሙተው አክሊልን ተቀበሉ።

❖ አርያኖስም ተቆጥቶ በቅዱሱ አንገት ከባድ ደንጊያ ሰቅለው ወደ ባሕር ይጥሉት ዘንድ አዘዘ በእግዚአብሔር ኃይልም ከድንጋዩ ጋራ ዋኘ ደግሞ ከሰሌን ዛፍ ላይ ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ ያቺም ሰሌን ዐሥራ ሁለት ዘለላን አፍርታ ለመጪው ትውልድም መታሰቢያ ሆነች፤ ከዚህም በኋላ የከበረች ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

                      አርኬ
✍️ሰላም ዕብል ለበብኑዳ ሰማዕት። እንተ አግሀደ ብርሃነ በቤተ ጽልመት። ወአመ ሰቀልዎ ሎቱ መልዕልተ በቀልት። አውጽአት ፍሬ በይእቲ ሰዓት። እስከ ጉቡአን አንከሩ እምዛቲ ትእምርት።
✍️ሰላም ለክሙ ማኅበረ በብኑዳ በሕቁ። ዐሠርተ ወክልኤቱ እለ ትትኌለቁ። ወሰላም ካዕበ ለዘተለውዋ ለጽድቁ። ቄርሎስ ወብእሲቱ ወዓዲ ደቂቁ። እስከ በደሞሙ ኅቡረ ተጠምቁ።

🌹ጆይን እያላችሁ ተቀላቀሉ🌹https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 18:54


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት ፲፮/17

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 18:05


✞መዳፍሽ ካይኔ መቼ ዞርይላል እንባየ ሲያፈስ ያድራል ይውላል መአዛሽ አለ ሁኖኝ ትዝታ የእናት ነትሽ ፍቅር ውለታ 🌹🌹🌹

ቅድስት ኪዳነ ምህረት ትጠብቀን

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 14:02


ይህች ዕለት ጥቅምት 17 ለቅዱስ እስጢፋኖስ በዓለ ሲመቱ ናት:: ቅዱሱ መጽሐፍ እንደሚል "ምሉዓ ጸጋ ወሞገስ-ሞገስና ጸጋ የሞላለት" (ሐዋ. 6:5, ቅዳሴ ማርያም) ነውና የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበር መሪ ሆኖ ተመርጦ እንደሚገባ አገልግሏል:: በሰማይ ባለችው መቅደስም የሚያገለግለው በዚሁ ማዕረጉ ነው::

በቅንነት ቴሌግራም ይቀላቀሉ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 13:54


🌹አባ ገሪማ (ይስሐቅ )ማለት🌹

«#ወር በገባ በ17 የአባ ገሪማ ዘመደራ ወርኀዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ🌹
📌•••አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ::

+እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን #ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ : መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል::

+አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው #አባ_ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር::

+ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን #ቅዱስ_ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው::

+እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ #ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር::

+አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም:: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ተጠራርጎ ሸሸ::

+ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ" (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "#አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ::

+አቡነ ገሪማ ወደ #መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል:: ይህም የተደረገው በዚህች ቀን (መስከረም 30) ነው::

+ጻድቁ ወንጌልን : ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:-

1.ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::
"ነግሃ ይዘርዕ ኪነቶ:: ወሠርከ የዓርር ገራኅቶ::" እንዲል::

2.ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::

3.አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ::

4.ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች::

5.አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ (ወንጌለ ዮሐንስን ሲጽፉ) ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል::

+ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በሁዋላ #ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ : መታሰቢያህን ያደረገ : እስከ 12 ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ #ብሔረ_ሕያዋን አድርሰዋቸዋል::

=>ቸሩ አምላካችን ከታላቁ ቅዱስ ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::

=>+"+ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ::
ግርማው በእሥራኤል ላይ : ኃይሉም በደመናት ላይ ነው::
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው::
የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን : ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል::
እግዚአብሔርም ይመስገን:: +"+ (መዝ. 67:34)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Join እያላችሁ ተቀላቀሉን  >>>https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 13:54


#ወለተ_ጴጥሮስ_ማን_ናት🌹
         ━⊱✿⊰━

📒☞ወር በገባ በ17 የእናታችን የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ወርሀዊ መታሰቢያዋ ነው፡፡ይቺ ደገኛ ሴት አባቷ ባሕር ሰገድ እናቷ ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡ ☞የትውልድ ሀገሯ ጎንደር ደዋሮና ነው፡፡ ይቺ የተቀደሰች እናታችን ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ በሕግ በሥርዓት በሊቀ ጳጳስ ትዕዛዝ የንጉሥ ሱስንዮስን የአማካሪዎች አለቃ የሆነው መላክአ ክርስቶስን አግብታ ሦስት ልጆችን ወልዳለች፡፡ ባሏም ታላቅና እጅግ ባለጸጋ ነበርና ከልጆች ጋር በተድላ በደስታ መኖር እንደጀመረች፡፡ አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ እነዚህ ሦስት ልጆቼ አንተን የሚያስደስቱ ከሆነ በሞት ውሰዳቸው፡፡ ብላ ከጸለየችበኃላ እንደፋላጎቷ ሦስት ልጆቿ በሞት ተወስደውላታል፡፡

☞ባለቤቷ እጅግ እየወደዳት እርሷ ግን ይህን ዓለም እንደ ጤዛ ያልፋል፡፡ ብላ
ከሞላ ሀብቷ ከሞቀ ቤቷ ተለይታ ወጥታ በመመነን ጣና ገባች፡፡ በዚያም
በተጋድሎ ስትኖር ባሏ አበምኔቱን ለምን ገዳም አሰገበሀት ብሎ ከሰሳቸውና
ከገዳሙ አስወጣት፡፡ እርሷ ግን ተደብቃ አክሱም ሄዳ ደብረ በንኮል ገዳም
ገባች፡፡ ተመልሳም መጥታ በጣና ባሕር ላይ ቆማ መጸለይ ጀመረች፡፡
በዘመኗ የነበረው ገዢ ጨካኝ ለጣዎት የሚሰግድ ሰለነበረ በትልቅ ገደል
ወረውረው እንዲጥሏት አደረጋት፡፡ ነገር ግን መልአኩ ቅድስ ሚካኤል
ከእግዚአብሔር ተልኮ መጥቶ በክንፋ ተቀብሏት ወስዶ ብሔረ ብፁዓን አሳይቶ
መልሶ አምጥቶ ዋልድባ አደረሳት፡፡

☞ቅድስት እናታችን ወለተ ጴጥሮስ ወደ ጉምዝ ሀገርም ተስዳ ሳለ በነደደ አሳትውስጥ ቢጨምሯት ምንም ሳያቃጥላት ወጥታለች፡፡ ተመልሳም በጣና ባሕርላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ነበር፡፡ ቧላም እምነቱን ቀይሮ
ከካቶሊኮች ጋር ሰለተዛመደ ቅድስ እናታችን ካቶሊኮቶችንና ባሏን አጥበቃ
ሰለተቃወመች በገመድ አሰረዋት በጎንንደር ከተማ ጎዳና ላይ ጎትተው አሠቃያት፡

☞ቅድስ ወለተ ጴጥሮስ ሰባት ገዳማትን ያቀናች ሲሆን ከ700በላይ በሚሆኑ
ወንዶች መነኮሳትና ሴቶች መነኮሳት ላይ እመ ምኔት ሆና ተሹማ
አገልግላለች፡፡
☞ከመነነችበት ጊዜ ጀምሮ ምግቧም የመረረ ቅጠል፤ኮሶና አመድ ነበር፡፡
ቅድስት እናታችን ታላቁን የራማ መድሀኒአለም ቤተ ክርስቲያን ሠርታ ሙታንን
እያነሳች ድውያንን እየፈወሰች በታላቅ ተጋድሎ እያገለገለች ሳለ ኅዳር 17ቀን
በታላቅ ከብር ዐርፋለች፡፡ ወርሐዊ የመታሰቢያ ዕለቷ ወር በገባ በ17 ነው፡፡
በዕረፍቷም ጊዜ የብርሃን ምስሶ ከምድር ሰማይ ተተክሎ ታይቷል፡፡

☞የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዐፅሟ በራሷ በመሠረተችው በሬማ መድኃኔአለም
አንድነት ገዳም ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል ፡፡በዚህ ገዳም ውስጥ በቅድስ ሥላሴ ምሳሌ የተሠሩ ሦስት የተለያዩ ድምፆችን የሚያወጡ ደወሎች ይገኛሉ፡፡ ሦስቱም ደውሎች የሚያወጡት ድምጽ ፍጽም የተለያየ ነው፡፡

☞የእናታችን የወለተ ጵጥሮስ አማላጅነት አይለያችሁ፡፡
☞የጽሁፍ ምንጭ☞መዝገበ ቅዱሳን
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

ቤተሰብ ይሁኑን ብዙ የቅዱሳንን ታሪክ እናቀርብለወታለን https://t.me/Orthodoxtewahdoc

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 13:54


=>+"+ እንኩዋን ለቅዱስ "እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት": ለቅዱስ "ፊልያስ" እና ለቅድስት "ሐና ነቢይት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት "*+

=>በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5:33 ላይ ተጠቅሷል::

+በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን: ዻውሎስን: ናትናኤልን: ኒቆዲሞስን . . .) አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::

+በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ6 ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ::

+ለ6 ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ::
በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::

+"ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: (ሉቃ. 7:18) በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም ተገዙለት:: (ሉቃ. 10:17)

+ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ:: ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በሁዋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኩዋል::

+በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን (ዽዽስናን) ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት: ምሥጢርም የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ::

+በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7 ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ6ቱ ዲያቆናት አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ) ሆኗል::

+8ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው:: አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለድኅነት ማብቃት እንኩዋ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ እንደሚል ግን "መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ እግዚአብሔር" ነውና ለእርሱ ተቻለው:: (ሐዋ. 6:5)

+አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ "ሊቀ ዲያቆናት" ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው:: ዲቁናው ለእርሱ "በራት ላይ ዳረጐት" ነው እንጂ እንዲሁ ዲያቆን ብቻ አይደለም::

+ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በሁዋላ ለ 1 ዓመት ያህል 8ሺውን ማሕበር እየመራ: ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት "እጠፋ እጠፋ": ወንጌል ደግሞ "እሰፋ እሰፋ" አለች:: በዚህ ጊዜ "ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው" ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ ገደሉት::

+እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::

+ይህች ዕለት ለቅዱስ እስጢፋኖስ በዓለ ሲመቱ ናት:: ቅዱሱ መጽሐፍ እንደሚል "ምሉዓ ጸጋ ወሞገስ-ሞገስና ጸጋ የሞላለት" (ሐዋ. 6:5, ቅዳሴ ማርያም) ነውና የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበር መሪ ሆኖ ተመርጦ እንደሚገባ አገልግሏል:: በሰማይ ባለችው መቅደስም የሚያገለግለው በዚሁ ማዕረጉ ነው::

+"+ ቅዱስ ፊልያስ ሰማዕት +"+

=>ሰማዕቱ የነበረበት ዘመን 3ኛው መቶ ክ/ዘ (ዘመነ ሰማዕታት) ሲሆን ቀምስ ለምትባል የግብጽ አውራጃም ዻዻስ ነበር:: ቅዱሱ እጅግ ጻድቅ በዚያውም ላይ ክቡርና ተወዳጅ ሰው ነበር:: የመከራው ዘመን ሲመጣ በቃሉ ያስተማራቸውን እንደ በጐ እረኝነቱ በተግባር ይገልጠው ዘንድ ወደ መኮንኑ ሔደ::

+ሕዝቡ በአንድነት ተሰብስበው ሳለ መኮንኑ ቁልቁልያኖስ ቅዱስ ፊልያስን 4 ጥያቄዎችን ጠየቀው:: ምላሾቹ ለእኛ ሕይወትነት ያላቸው ናቸውና እንመልከታቸው::

1."የእናንተ እግዚአብሔር ምን ዓይነት መስዋዕትን ይሻል?" ቢለው "ልበ ትሑተ: ወመንፈሰ የዋሃ: ወነገረ ሕልወ: ወኩነኔ ጽድቅ: ዘከመዝ መስዋዕት ያሠምሮ ለእግዚአብሔር-እግዚአብሔርን ትሑት ልቦና: የዋህ ሰብእና: የቀና ፍርድና ቁም ነገር ደስ ያሰኘዋል" ሲል መለሰለት::

2."የምትወዳቸው ሚስትና ልጆች የሉህም?" ሲለው ደግሞ "እምኩሉ የአቢ ፍቅረ እግዚአብሔር - ከሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል" አለው::

3."ለነፍስህ ትጋደላለህ ወይስ ለሥጋህ?" ቢለው "ለ2ቱም እጋደላለሁ:: አምላክ በአንድነት ፈጥሯቸዋልና:: በትንሳኤ ዘጉባኤም ይዋሐዳሉና" ብሎታል::

4."አምላካችሁ የሠራው ምን በጐ ነገር አለ?" ብሎትም ነበር:: ቅዱስ ፊልያስ መልሶ: "አስቀድሞ ፍጥረታትን በጥንተ ተፈጥሮ ፈጠረ:: በሁዋላም በሐዲስ ተፈጥሮ ያከብረን ዘንድ ወርዶ ሞተልን: ተነሣ: ዐረገ" ቢለው መኮንኑ "እንዴት አምላክ ሞተ ትላለህ!" ብሎ ተቆጣ:: ቅዱሱም "አዎ! በለበሰው ሥጋ ስለ እኛ ሙቷል" ብሎ እቅጩን ነገረው::

+ወዲያውም "እስከ አሁን የታገስኩህ በዘመድ የከበርክ ስለሆንክ ነው" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "ክብሬ ክርስቶስ ነው:: መልካምን ካሰብክልኝ ቶሎ ግደለኝ" አለው:: በዚያን ጊዜ የሃገሩ ሰዎች "አትሙትብን! እባክህን ለመኮንኑ ታዘዘው?" ሲሉ ለመኑት::

+ቅዱስ ፊልያስ "እናንተ የነፍሴ ጠላቶች ዘወር በሉ ከፊቴ! እኔ ወደ ክርስቶስ ልሔድ እናፍቃለሁና" ብሎ ገሰጻቸው:: መኮንኑም ወስዶ ከብዙ ስቃይ ጋር ገድሎታል::

+"+ ቅድስት ሐና ነቢይት +"+

=>"ሐና" ማለት "የእግዚአብሔር ስጦታ" ማለት ነው:: እጅግ ከሚታወቁ ሴት ነቢያት አንዷ የሆነችው ቅድስት ሐና ከክርስቶስ ልደት 1,100 ዓመታት በፊት በዚህች ቀን እንደ ተወለደች ይታመናል:: ቅድስቲቱ ልጅ በማጣት ተቸግራ: ከጐረቤት እስከ ሊቀ ካህናቱ ኤሊ ድረስ ሽሙጥና ስድብን ታግሣ ታላቁን ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤልን ወልዳለች::

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 13:54


+በሐረገ ትንቢቷም:-
"ኢይጻእ ዐቢይ ነገር እምአፉክሙ: እስመ እግዚአብሔር አምላክ ማዕምር ውዕቱ - እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ አምላክ ነውና ከአንደበታችሁ (ጽኑዕ) ነገርን አታውጡ" ስትል ተናግራለች:: (ሳሙ. 2:3)
=>አምላከ ቅዱሳን የእስጢፋኖስን ጸጋ: የፊልያስን ማስተዋልና የሐናን በጐነት ያሳድርብን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::=>ጥቅምት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ወቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ፊልያስ ሰማዕት
3.ቅድስት ሐና ነቢይት
4.ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
5.የደብረ ሊባኖስ ሰማዕታት (ካቶሊካውያን የገደሏቸው)
6.ቅዱሳን ሔራን ሰማዕታት
7.አባ ዲዮስቆሮስ ካልዕ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
2.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
3.አባ ገሪማ ዘመደራ
4.አባ ዸላሞን ፈላሢ
5.አባ ለትጹን የዋህ
6.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)

=>+"+ እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ ተነስተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት:: +"+ (ሐዋ. 6:8-15)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 10:08


እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት

ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
ራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
#አዝ
ለዘላለም ንፅሕት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ሕያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሐዘኔን አልፌ
አፅናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
#አዝ
ከጥፋት ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
#አዝ
በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእግሬ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
#አዝ
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
ራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 06:01


"ኹሌም በሄድኩበት የምናገረው አንድ ነገር አለኝ"!

"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣
ምልኩስና እና
ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር፣ በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ "እንዴት?" ካልን፦
የተከበረ ትዳር የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል።
የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል።
ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ!
ተምረን ማግባትና፣ ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

26 Oct, 02:03


፲፮❤️ እናቴ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሆይ በዕለተ ቀንሽ ከክፉ ሁሉ ሰውሪን ሀገራችንን ሰላም አድርጊልን ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ  ሰውሪን።

🌷አሜን በእውነት።🙏

"ላመነባት ለተማፀናት ኪዳነ ምህረት አምባ መጠጊያ ናት🙏

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

25 Oct, 20:58


🌷መልክአ ቅድስት ኪዳነ ምህረት

ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሆይ በክፉ ሰዎች እጅ ከመውደቅ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ካልታሰበ አደጋ ሰውሪን።🤲

23,450

subscribers

11,702

photos

59

videos