ብርሃን ለ ኢትዮጵያ ብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበር @birhan_le_ethiopia Channel on Telegram

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ ብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበር

@birhan_le_ethiopia


እያበርን እንሠራለን እየሠራን እናበራለን...
እኛን ለማግኘት ከታች ያለውን ስልክ ቁጥር ይጠቀሙ
ለማንኛውም አስተትያየት👇
@Birhan_Le_Ethiopia_Bot

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇 (Amharic)

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር የኢትዮጵያውያን ለማቅረብ አገልግሎት የሚጀመርበትን የብርሃን ማህበር ምስጋና ያሳውቃል። ይህ ብርሃን ከታች የእያንዳንዱን ፕሮፌሰንሶሽን ቁጥር እና ስም የሚጠቀሙን አስተትያየትን ይምከር። እስኪቁሙ እና መረጃውን ትክክለኛ ያሰብኩ፣ ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር ተጨማሪ እና ማህበር ስለ እኛን መልእክት አያሸንፉ።

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ ብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበር

15 Nov, 12:49


ጉዳዩ:- ብድር በአግባቡ ለማትመልሱ እና ደረሰኝ መጥታችሁ ማወራረድ ላልቻላችሁ አባላት በሙሉ:-

ከተቋሙ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ሆናችሁ ነገር ግን እዳችሁን በአግባቡ ለማትመልሱ አባላት እና የገቢ ደረሰኝ  ይዛችሁ በመምጣት

ማወራረድ ያልቻላችሁ አባላት፣ተቋሙ በተደጋጋሚ በስልክ እና በዕሑፍ መጥታችሁ እንድትከፍሉ እጃችሁ ላይ ያለ ደረሰኝ ይዛችሁ
በመምጣት እንድታወራርዱ መልዕክት መላካችን ይታወሳል ።

ስለዚህ ከዚህ በኋላ ተቋሙ ጉዳዩን ወደ ህግ ስለሚወስድ ፤ከህግ ሂደት ጋር ተያይዞ ለሚፈጠር ማንኛውም ጉዳይ ሙሉ ኃላፊነቱን የምትወስዱ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን !!

👉Telegram
https://t.me/BIRHAN_LE_ETHIOPIA
https://t.me/BIRHAN_LE_ETHIOPIA

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ ብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበር

31 Oct, 04:18


Channel name was changed to «ብርሃን ለ ኢትዮጵያ ብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበር»

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ ብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበር

31 Oct, 04:17


ብርሃን ለ ኢትዮጵያ ብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበር pinned «ብርሃን ለኢትዮጵያ የገ/ቁ/ብ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማ የተከበራችሁ የብርሃን ለኢትዬጵያ የሕብረት ስራ ማህበር አባላቶቻችን በሙሉ ፤ ባለፈዉ መስከረም 19/2017 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ መደረጉ እና አዳዲስ የቦርድ አመራሮች ከአባላቶች መካከል ተመርጠው ወደ ስራ መግባታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በቀድሞው አመራር ተቋሙ አጋጥሞት የነበረውን የአሰራር ችግር ለመፍታትና ለመቅረፍ ጥረትና እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡…»

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ ብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበር

31 Oct, 04:17


ብርሃን ለኢትዮጵያ የገ/ቁ/ብ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማ

የተከበራችሁ የብርሃን ለኢትዬጵያ የሕብረት ስራ ማህበር አባላቶቻችን በሙሉ ፤ ባለፈዉ መስከረም 19/2017 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ መደረጉ እና አዳዲስ የቦርድ አመራሮች ከአባላቶች መካከል ተመርጠው ወደ ስራ መግባታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በቀድሞው አመራር ተቋሙ አጋጥሞት የነበረውን የአሰራር ችግር ለመፍታትና ለመቅረፍ ጥረትና እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በተቋሙ ውስጥ እስካሁን በገጠማችሁ መጉላላት ፥ አባላቶቻችንን በሙሉ ከልብ ይቅርታ እየጠየቅን ተቋማችን ወደ ቀደመ የአሰራር ሂደቱ እስኪመለስ በትዕግስት እንድጠባበቁ እየጠየቅን በተለይ ከተቋሙ የብድር አገልግሎት ወስዳቹ እዳችሁን በአግባቡ የማትከፍሉ እና ውዝፍ ያለባችሁ አባላት በሙሉ ፡በተደጋጋሚ ያለባቹን ዉዝፍ እዳ እንድትከፍሉ ቢጠየቅም የህዝብን ገንዘብ ባለመክፈል የማህበሩን አባላት እና የስራ አመራሩ ስራውን በአግባቡ እንዳይሰራ እንቅፋት መሆናችሁን ተገንዝባችሁ በአስቸኳይ ክፍያችሁን እንድትፈፅሙ ስንል እናሳስባለን፡፡ የማትከፍሉ ከሆነ ግን በህግ ከሰን ከነ ኪሳራውና ከነወለዱ ለማስከፈል የምንገደድ መሆኑን እናስታውቃለን::

ቀን፡ 21/2/2017ዓ.ም
ለበለጠ መረጃ +2519-09-42-05-64/ 09-09-42-05-81

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇

08 Aug, 13:13


👉 ከብርሃን ለኢትዮጵያ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ሆናችሁ እዳችሁን በተገቢው እየከፈላችሁ ላልሆናችሁ አባላት በሙሉ:-

እንሆ ከብርሃን ለኢትዮጵያ
የገ/ቁ/ብ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ሆናችሁ እዳችሁን በተገቢው እየከፈላችሁ ላልሆናችሁ አባላት በተደጋጋሚ እዳችሁን ከነ ቅጣቱ እንድትከፍሉ እና እንድታወራርዱ ማሳሰቢያ የሰጠን ቢሆንም በዚህ መሰረት እዳችሁን ለመክፍል እና በተቋሙ ተገኝታችሁ ምላሽ መስጠት ያልቻላችሁ አባላቶች ላይ ህጋዊ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመራችንን እናሳውቃለን ።

02/12/2016 ዓ.ም

ብርሃን ለኢትዮጵያ
የገ/ቁ/ብ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማ

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇

21 May, 13:28


👉 ከብርሃን ለኢትዮጵያ የብድር ከአገልግሎት ተጠቃሚ ስለሆናችሁ ሁሉ:-

ብድር ተመላሽ 6 ወር እና ከዚያም በላይ እስከ ቅዳሜ 17/09/16 ዓ.ም ተመላሽ ለሚያደርጉ አባላት 15% ተቀናሽ ፣ከ19/09/16 እስከ 24/09/16 ዓ.ም ለሚመልሱ አባላት 10%ቅናሽ ያደረግን መሆኑን እየገልጽን ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ በመገኘት ሙሉ መረጃ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን!

ብርሃን ለኢትዮጵያ
የገ/ቁ/ብ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማ

ለበለጠ መረጃ:- +2519-09420581
                        +2519-09420578 ደውለው       መረጃ ይውሰዱ !

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇

07 Feb, 11:45


VACANCY ANNOUNCEMENT
Our Company is looking to the recruit qualified employ's for the following vacant positions.therefore , we would like to remind u that those who meet required criteria can come the company (Ble) &apply.

We encourage working h's!

contract :- +2519-74-25-18-30
*or+2519-09-42-05-64
To our pages
Telegeram channel 🔗
https://t.me/BIRHAN_LE_ETHIOPIA

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100083378105731
#BLE #saving #credit #financial institutions #loanservice #creditservice #cooperative #microfinance #Ethiopia #Ethiopian #Addisababa #Torhayelocharea

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇

29 Dec, 08:20


የብርሃን ለኢትዮጵያ የገ/ቁ/ብ/ኅ/ህ/ስ/ማህበር አባላት እሁድ በ21/4/16 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤ ስለምናካሂድ የአባልነት ደብተሮን ይዘው ቤቴል በሚገኘው ኮ/ቀ/ክ/ከ እዳራሽ በ 7፤00ሰዓት እንዲገኙ እናሳስባለን።

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇

21 Jul, 09:51


ሰላም ውድ ደንበኞቻችን በድርጅታችን ስም የተለያዩ ማጭበርበሮች እየተፈፀሙ መሆኑን መረጃ ደርሶናል  እኛም ጉዳዩን ወደህግ ወስደነው ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል ስለሆነው አዲስ የተቀየረ መረጃ ስለሌለ ከነዝ አጭበርባሪዊች እራስዎን እንዲጠብቁ በድርጅቱ ስም  በተከፈተ አካውንት ብቻ ገንዘብዎን ገቢ እንዲያደርጉ እንዲሁም ምዝገባ ባካል በመምጣት እንዲመዘገቡ ጥያቄ ወይም ጥቆማ ካለ በነዝህ ብቻ ስልኮች  ይደውሉ 

+251909420564        +251974251830   +251988749301        +251983124330

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇

16 May, 08:17


ብርሃን ላኢትዮጵያ የገ/ቁ/ብ/ኋ/የተ/ህ/ስ/ማህበር በመተባበር፤ በመተሳሰብና በመረዳዳት መንፈስ ላይ ተመሥርቶ የቁጠባ፤ የብድር እና ብድርን መሠረት ያደረገ አነስተኛ የብድር መድን አገልግሎት ለመስጠት በሰዎች ነፃ ፍላጎትና ፈቃደኝነት የተቋቋመ የፋይናንስ ነው፡፡

ማህበሩ ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ገንዘብንም ሆነ ንብረትን በሥርዓት መጠቀም፤ ብኩንነትን ማስወገድ፣ ከገቢ በመቀነስ ለወደፊት ጥሪት ማካበት፣ ፍላጎትን ስርዓት ባለው መንገድ ማስተናገድ፣ ከእለት ፍጆታ ቀንሶ ለወደፊት ፍጆታ ማስቀመጥ፣ነገውን በህልሙ ስኬት ውጤታም ያደርጋል ብሎ ያምናል ፡፡ ስለሆነም የተለያዩ የቁጠባና የብድር አማራጮችን ይዞ መቷል ፣ ስለዚህ ወደኛ ይምጡ አባል ይሁኑ ለህልሞ መሳካት አብረን እንስራ ፡፡
ለበለጠ መእጃ ፤፟ ከታቸ በተቀመጥው የስልክ ቁጥሮች ይድውልሉ
+2519 09 42 05 64
+2519 74 25 18 30
+2519 88 74 93 01
+2519 09 42 05 78
+2519 09 42 05 81
አድራሻ ጦር ኋይሎች ቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌ ቤተ ክርስቲYአን ጀርባ ማክዳ ህንጻ 2 ፍሎር ላይ

https://t.me/BIRHAN_LE_ETHIOPIA
https://vm.tiktok.com/ZM2efjb8J/
https://www.facebook.com/profile.php?id=100083378105731&mibextid=ZbWKwL

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇

14 May, 05:32


መልካም የእናቶች ቀን‼️

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇

30 Apr, 12:37


የቁጠባ ምንነት
አሁን ባለንበት ዘመን ማንኛውም ሰው ለፍቶ ያገኘውን ገንዘብ በአግባቡ ተጠቅሞ ደስተኛ ሕይወት መምራት ይፈልጋል፡፡ ይህ ማለት ግን የተገኘውን ገንዘብ እንዲሁ በረባ ባረባው መርጨት አይደለም፡፡ በገቢያችን ልክም ወጪ ማውጣት አለብን ማለትም አይደለም፡፡ ገንዘቡ እሴት ለሚጨምሩ ጉዳዮች መዋል እንዳለበት ግን እንረዳለን፡፡ በመሆኑም ከገቢያችን የተወሰነውን ለአንዳንድ ወጪዎች ስንጠቀምበት የተቀረውን ደግሞ እንቆጥበዋልን፡፡ ነገን በእርግጠኝነት መናገር ስለማይቻልም በሕይወት ጉዟችን የሚያጋጥሙን ያልጠበቅናቸውን ነገሮች ዋጋ ሊያስከፍሉን ስለሚችሉ ችግሩን መጋፈጥ የምንችለው ለነገ ብለን ያስቀመጥነው ጥሪት ሲኖረን ባቻ ነው፡፡   በመሆኑም ዛሬ ሰርተን ያገኘነውን ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ መጠቀም ብልሀት የጐደለው ውሳኔ ነው፡፡ ስለዚህ የተወሰነው ለነገ በማለት መቆጠብ ተገቢ ይሆናል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ቁጠባ ምንድን ነው የሚለውን ጉዳይ በጥልቀት እንመለከታለን፡፡
ቁጠባ ማለት ለነገ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ገንዘብ ከዛሬ ገቢያችን ለፍጆታ ከተጠቀምንት በኋላ የሚተርፍን ገንዘብን ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ የቁጠባ መጠኑን የሚኖረን ገቢ እና ፍጆታችን የሚወስኑት ቢሆንም ከየትኛውም የገቢ መጠን ቁጠባ መቆጠብ እንደሚቻል መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ የቀን፣የሳምንት፣ አልያም የወር ገቢያችን ምንም ይሁን ምን ቁጠባ የግድ ነው፡፡ ሆኖም ግን የገቢ መጠናችን ሲያድግ የመቆጠብ አቅማችን ይጨምራል፡፡ እንዲሁም ብዙ ወጪ ካወጣን የመቆጠብ አቅማችን ይቀንሳል፡፡ በመሆኑም የገቢ መጠናችንን በማሳደግና ወጪ በመቀነስ የተሻለ መቆጠብ እንችላለን፡፡
ቁጠባ  የረጅም ጊዜ ወይንም በተወሰነ ግዜ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንንም የምንቆጥብበት አላማ ይወስነዋል፡፡ የምንቆጥበው በእርጅና ዘመን መጦሪያዬ፣ ብታመም መታከሚያየ፣ንግድ ላማስፋፋት፣ እና ያልታሰበ ችግር ቢገጥመኝ ለችግሬ መፍትሔ ይሆናል ብለን የምናስብ ከሆነ ቁጠባም ረጅም ጊዜ የሚወስድና በተከታታይ የሚከናወን ተግባር ይሆናል፡፡ ነገር ግን የምንቆጥበው የቤት እቃ ለመግዛት፣ የንግድ ሥራን ለማስፋት ከሆነ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ተግባር ይሆናል፡፡
ገንዘብን ለመቆጠብ ጥሩ ምክንያት ከሚባሉት ውስጥ፡-
ድንገት ለሚያጋጥሙ ክስተቶች ማለትም ሰው ቢታመም፣ መኪና ቢበላሽ፣ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሠራሽ አደጋ ቢደርስ ዝግጁ ሆኖ ለመጠበቅ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የቤት ቁሳቁስ ለመግዛት፣ በበዓላት ጊዜ አስፈላጊውን ወጪ ለመሸፈን፡፡
ለጡረታ ጊዜ እቅድ ለማውጣት፤ በጡረታ አበል ብቻ ኑሮን መግፋት ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ የተወሰነ ተቀማጭ ገንዘብ ቢኖረን ግን በጡረታችን ጊዜ ሳንጨነቅ የጡረታ ጊዜያችንን እንደናሳልፍ ይረዳናል፡፡
ኢንቨስትመንት ላይ ለመሣተፍ፡- በአሁኑ ሰዓት ለኢንቨስትመንት በቂ ገንዘብ ላይኖረን ይችላል፡፡ ነገር ግን ከላይ በተጠቀሰው አኳኋን መቆጠብ ከጀመርን ለወደፊቱ ኢንቨስት ለማድረግ በቂ ገንዘብ ሊኖረን ይችላል፡፡ ኢንቨስትመንት ስንል የባንክ እና ኢንሹራንስ ድርጅቶች አክሲዮን መግዛትን ያጠቃልላል፡፡ የአጭር ጊዜ እቅድ ወደ ረጅም ጊዜ ስኬት ሊቀየር ይችላል፡፡
ቁጠባ አንድን ነገር ለመግዛት ስንፈልግ የምናቅድበት መንገድ ነዉ፡፡ በአደጋ ጊዜ፣ያልታለቡ ወጪዎች ሲኖሩን ወይም ሳንበደር አንድን ነገር ለመግዛት ስንፈልግ ቁጠባ አይነተኛ አማራጭ ነዉ፡፡
ቁጠባ ከማጥፋት ያግዶታል፤የቆጠቡትን ገንዘብ መቼም የማይጠቀሙበት አድርገዉ አይዉሰዱት፡፡ ቁጠባ ማለት አሁን የሚያጠራቅሙት ወደፊት ግን የሚጠቀሙበት ነዉ፡፡
ቁጠባ ጥበቃ ይሰጥዎታል፤ገንዘብዎን ትራስ ዉስጥ ማስቀመጥ አደገኛ ነዉ፡፡ በአንፃሩ ግን ባንክ ዉስጥ የሚቀመጥ ገንዘብ ኢንሹራንስ ስለሚሸፍነዉ ሁሌም አስተማማኝ ነዉ፡፡
በምናስተዳድራቸው የንግድ ተቌማትም ሆነ በግል ኑሯችን ገንዘብ አንዱ ዋነኛ ግብዓት ነው፡፡ የገንዘብ ሀብት በየትኛውም ድርጅት፣ግለሰብ፣ እንዲሁም ሀገር በቂና የተትረፈረፈ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ የገንዘብ ሀብታችን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ይህንን ለማድረግ ከሚያስችሉ ዘዴዎች አንዱ ደግሞ ቁጠባ ነው፡፡ የወደፊት እቅዳችን ምንም ይሁን ምን ቁጠባ እቅዳችንን በማሳካት ይረዳናል፡፡ ምንም እንኳን ቁጠባ መጀመር ፈታኝ ቢሆንም መቆጠብ መልካም ነው፡፡
➭ የመረጃ ምንጭ:- ማህበራዊ ድህረገጽ
https://t.me/BIRHAN_LE_ETHIOPIA
https://t.me/BIRHAN_LE_ETHIOPIA

ብርሃን ለ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር👇

15 Apr, 11:20


ውድ የብርሃን ለኢትዮጵያ የገ/ቁ/ብ/ኅ/ስ/ማህበር አባሎቻችን እንኳን አደረሳችሁ! በዓሉ የጤና ፣የፍቅርናየሰላም ይሁንላችሁ !ይሁንልን !
መልካም በዓል !

3,632

subscribers

40

photos

1

videos