Federal Justice and Law Institute @jlrtinet Channel on Telegram

Federal Justice and Law Institute

@jlrtinet


Federal Justice and Law Institute (English)

Welcome to the Federal Justice and Law Institute, a Telegram channel dedicated to providing valuable insights and updates on the legal system. Whether you are a law student, legal professional, or simply interested in learning more about justice and law, this channel is the perfect place for you! The Federal Justice and Law Institute covers a wide range of topics, including the latest legal news, case studies, and analysis of important court decisions. Run by a team of experienced legal experts, the channel aims to educate and inform its members on all aspects of the legal field. From discussions on landmark cases to tips on navigating the legal system, you will find everything you need to stay informed and up-to-date on the world of law. As a member of the Federal Justice and Law Institute, you will have access to exclusive content, webinars, and resources that will enhance your understanding of the legal system. Whether you are looking to expand your knowledge, network with other legal professionals, or simply stay informed on current legal issues, this channel has something for everyone. Join us today and become a part of a vibrant community of individuals who share a passion for justice and law. Follow @jlrtinet for daily updates and engaging discussions on all things legal. Don't miss out on this valuable opportunity to connect with like-minded individuals and stay informed on the latest developments in the legal field. We look forward to having you as part of our community at the Federal Justice and Law Institute!

Federal Justice and Law Institute

14 Nov, 15:22


የማስማማትና የግልግል ዳኝነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሥልጠና እየተሰጠ ነው

Federal Justice and Law Institute

14 Nov, 15:21


የማስማማትና የግልግል ዳኝነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሥልጠና እየተሰጠ ነው
(ሕዳር 05/03/2017 ዓ.ም) የፌዴራል ጠቅላይ ፍረድ ቤት ከፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የማስማማትና የግልግል ዳኝነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደሩት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚኒስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው የግልግል ዳኝነትን ፍርድ ቤት መር አድርጎ ከመዘርጋትና የወጣውን መመሪያና አሰራር አበጅቶ አደራዳሪዎች ተጠያቂነትና ሃላፊነትን እንዲሸከሙ መደረጉ መልካም ነው ያሉ ሲሆን ይህ መሆኑ ደግሞ የፍትሕ ሥርዓቱን ያጎለብታል፤ የባለ ጉዳዮች የጊዜና የገንዘብ ወጪን ይቀንሳል፤ ፍርድ ቤቶች ላይ የፋይል መጨናነቅ እንዳይኖር ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ባለጉዳዮች በራሳቸው ፍቃድ ወደዚህ ሥርዓት እንዲመጡ ማድረግ ይበጃል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህ መሆኑ ደግሞ ተበደልኩ ባለው ከሳሽም ሆነ በተከሳሹ ዘንድ የአሸናፊነት እና የተሸናፊነት አስተሳሰብ እንዳይኖር ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ድሪባ ፈየራ በበኩላቸው የማስማማትና የግልግል ዳኝነት በህግና መመሪያ መደገፉ ብቻ የታለመለትን ዓላማ እና ግብ ስለማያስገኝ ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ለተግባራዊነቱ መትጋት አለባቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ሥልጠናው የፍርድ ቤት መር አስማሚነት፣ የአስማሚዎች ሚና እና የአስማሚነት ክህሎት፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሂደቶች እና የቤተሰብ አስማሚነት ተግባራዊ ተሞክሮ ዳሰሳ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰጥ ሲሆን፤ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተወጣጡ 50 ረዳት ዳኞች የሚሳተፉበትና ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚሰጥ ሥልጠና ነው፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!

Federal Justice and Law Institute

11 Nov, 12:14


ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል
ክፍት የስራ መደብ
ለስራ ፈላጊዎች
ሸር ላይክ በማድረግ ለህግ ተመራቂዎች አድርሡ!
@federal justice and law institute

Federal Justice and Law Institute

09 Nov, 17:07


የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና ሕግ ቋሚ ኮሜቴ አባላት በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በመገኘት የመስክ ምልከታ ጉብኝት አደረጉ
(ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም) የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና ሕግ ቋሚ ኮሜቴ አባላት በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አያት ጨፌ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት የመስክ ምልከታ ጉብኝት አደረጉ፡፡
በጉብኝታቸው የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለአገልግሎት የሚጠቀምባቸውን የስልጠና ክፍሎች፣ የቤተ መጽሃፍት፣ የኢ-ላይበራሪ፣ የመረጃ ማዕከል፣ የሰልጣኞች መኝታ ክፍልና መሰል ነገሮችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከኢንስቲትዩቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚህም የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች ተቋሙ ከተሰጠው ሃላፊነት አኳያ የሚሰራቸውን ሥራዎች በማብራራት እስካሁን ያጋጠሙ ችግሮችንና የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማንሳት ለሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ አባላት አብራርተዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴ አበላት በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ለሕግና ፍትሕ ዘርፉ የሚሰጠው ግልጋሎት ጉልህ መሆኑን በማንሳት የፍትሕ ዘርፉ ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን ተቋሙ የሚሰጣቸውን ተግባርና ሃላፊነቶች በማጠናከር ፣ ገለልተኛ የሆነ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲሆንና የሚጠበቅበትን ያህል እንዲሰራ የበኩላቸውን ሃላፊነት እንደሚወጡ የምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡
መረጃው፡- የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!

Federal Justice and Law Institute

09 Nov, 17:04


የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና ሕግ ቋሚ ኮሜቴ አባላት በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በመገኘት የመስክ ምልከታ ጉብኝት አደረጉ

Federal Justice and Law Institute

08 Nov, 15:00


ክፍት የስራ መደብ
ለስራ ፈላጊዎች
ሸር ላይክ በማድረግ ለህግ ተመራቂዎች አድርሡ

Federal Justice and Law Institute

05 Nov, 13:57


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ጉዳዮችን መርምሮ አጸደቀ
(ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የተለያዩ ጉዳዮችን መርምሮ አጸድቋል።
ምክር ቤቱ በውሎው የፌዴራል የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን፤ ዳኞችና ዐቃቢያነ ህጎች በአግባቡ ስልጠና ወስደው የፍትህ ሰርአቱ ለመዘመን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንድሰጡ ለማስቻል እና ተቋማትን በምርምር ለመደገፍ የሚያግዝ መሆኑን ለምክር ቤቱ አስገንዝበዋል፡፡
የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ የህግ ኢንስቲትዩት ከስራ አስፈጻው ነፃና ገለልተኛ ሆኖ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚመራለት ቋሚ ኮሚቴ በዝርዝር ሊያየው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የፌዴራል የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ፤ ለዝርዝር እይታ አዋጅ ቁጥር 11/2017 አድርጎ ለህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቷል፡፡

Federal Justice and Law Institute

05 Nov, 08:48


Best News !

Federal Justice and Law Institute

04 Nov, 15:58


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል‼️

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የፌዴራል የፍትህ እና የሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት ሌላኛው የስብስባ አጀንዳ መሆኑም ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Federal Justice and Law Institute

02 Nov, 15:49


የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ
(ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ በመገኘት የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚንስትር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ የህግ ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ የፍትሕና ሕግ ዘርፉ ቅሬታ የማይቀርብበት፣ የህብረተሰቡም የፍትሕ ጥያቄ የሚመለስበት እንዲሆን መሰል ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ሃላፊነታችንን እንወጣለን ፤ ነገር ግን ሥልጠና በራሱ ደግሞ ውጤት አይደለምና ሥልጠናውን የሚያገኙ አካላት የሰለጠኑትን ሥልጠና በተግባር ማዋል አለባቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና ደግሞ የወደፊት አሰልጣኞችን የምናፈራበትና የሃገር አደራ የምንሰጥበት የስልጠና አይነት እንደመሆኑ መጠን በዚህ ሥልጠና ላይ ለመሳተፍ እድል ያገኛችሁ ሲኒየር የህግ ባለሙያዎች በሙሉ የሰለጠናቹህትን ሥልጠና ለሌሎች በማድረስና ታናናሾቻቹህን በማብቃት ረገድ ትልቅ ሃላፊነት እንዳለባቹህ ልታውቁት ይገባል ሲሉ ሚኒስቴር ዴዔታው መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ሰልጣኞች በበኩላቸው ከአሁን በፊት የወሰዷቸው ስልጠናዎች ቢኖሩም የአሁኑ ስልጠና ግን ከእስካሁኑ የተለዬ እና ለወደፊት ሥራቸውም ግብዓት የሚሆን ሥንቅ እንደያዙበት ተናግረዋል፡፡
ይህ የአሰልጣኞች ሥልጠና የሕግ ባለሙያዎች በሚያሰለጥኑበት ወቅት እንዴት አይነት የስልጠና መንገድ መከተል እንዳለባቸው ግብዓት የሚገኙበት የስልጠና አይነት ሲሆን ከጥቅምት 19/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆዬ ነው፡፡
ሁለተኛው ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ከህዳር 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!

Federal Justice and Law Institute

02 Nov, 15:49


የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ

Federal Justice and Law Institute

02 Nov, 15:48


የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ

Federal Justice and Law Institute

29 Oct, 08:59


የአሰልጣኞች ሥልጠና ተሳታፊዎች የሥልጠና ፍላጎት ዳሰሳ (need assessment) ምን ማለት ነው የሚለው ላይ የቡድን ውይይት ሲደረግ በከፊል

Federal Justice and Law Institute

29 Oct, 07:40


የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ
(ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የአሰልጣኞች ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ መስጠት ጀመረ
በስልጠናው ማስጀመሪያ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የዳኝነትና ፍትሕ አካላት ሥልጠና መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ሰናይት አንዳርጌ ስለ ኢንስቲትዩቱ ተግባርና ሃላፊነት ለሰልጣኞች በማጋራት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን የዛሬው ስልጠና በዋናነት የወደፊት አሰልጣኞችን ለማፍራት ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በዋናነት በሃገሪቱ ያሉ የሕግ ባለሙያዎችን በማብቃት ረገድ ትልቅ ሥራ ይሰራል ያሉት ወ/ሮ ሰናይት የአሰልጣኞች ሥልጠና፣ የቅድመ ሥራ ሥልጠና፣ የስራ ላይ ሥልጠና እና የሕግ አመራሮች ሥልጠና እንደሚሰጥ ጭምር አብራርተዋል፡፡
የአሰልጣኞች ስልጠና በዋናነት የአሰለጣጠን ዘዴ ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ሥልጠና ላይም ከጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ እና ከፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዪት የተወጣጡ 33 የህግ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ይህ ሥልጠና የአሰለጣጠን ፍላጎት ዳሰሳ፣ የስልጠና መንገዶች፣ ሰልጣኞችን ማበረታታትና የስልጠና ግምገማ ላይ ትኩረት በማድረግ ሰልጣኞችን እንዴት መያዝ እንዳለብን፣ እና ከስልጠናው በኋላ የምናገኘውን ውጤት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰጥ ሥልጠና ነው፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!

Federal Justice and Law Institute

18 Oct, 12:02


ለስራ ፈላጊዎች
እንካቹህ ጉርሻ!

Federal Justice and Law Institute

14 Oct, 07:54


17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከበረ

(ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም) 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በመላ ሀገሪቱ ተከብሮ እንደሚውል ይታወቃል፡፡ ይህንንም ምክንያት በማድረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ባለሙያዎች በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ አክብረውታል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሰኞ የሚከበር ሲሆን የዘንድሮው ዕለት “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ በዛሬው ዕለት ተከብሮ ይውላል።
በዚሁ መሰረት ይህ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመላ ሃገሪቱ ያሉ የመንግስት ተቋማት፣ በመከላከያ ሠራዊት ካምፖች ፣ በኢትዮጵያ ኢምባሲዎችና ሚሲዮኖች ይከበራል።
መረጃው፡- የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!

Federal Justice and Law Institute

13 Oct, 18:39


በሃገራችን ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው የሰንደቅ አላማ ቀን ነገ ጥቅምት ፬ ቀን 2017 ዓ.ም የተለያዩ ሁነቶች በመታጀብ የሚከበር ይሆናል!
መልካም የሰንደቅ ዓላማ ቀን!!

Federal Justice and Law Institute

11 Oct, 14:52


የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩትበፍርድ ቤት ችሎት ዘገባ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ

Federal Justice and Law Institute

10 Oct, 14:14


#የፌዴራል_የፍትሕና_ሕግ_ኢንስቲትዩት_በፍርድ_ቤት_ችሎት_ዘገባ_ላይ_ያተኮረ_ስልጠና_ሰጠ
(መስከረም 30/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለተወጣጡ ባለሙያዎች በፍርድ ቤት ችሎት ዘገባ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ፡፡
በስልጠናው ላይ የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ምትኩ ማዳ በንግግራቸው ዝግጅቱ አጭርና ውይይታዊ የስልጠና መርሃ ግብር መሆኑን በመጥቀስ፣ በመሆኑም ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ወደ ፊት በምናደርጋቸው የፍርድ ችሎት ዘገባዎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
የዕለቱ የክብር እንግዳና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው መገናኛ ብዙሃን የተጣለባቸው ተግባርና ሃላፊነቶችን ከመወጣት ረገድ በአግባቡ መስራት ይጠበቅባቸዋል ያሉ ሲሆን በዚህም ማህበረሰቡ ሊያውቃቸው የሚገቡ መረጃዎችን የህዝብ አይንና ጀሮ በመሆን የፍርድ ቤት ጉዳዮችን በመዘገብ ትክክለኛ እና የተሟላ መረጃ ለህዝብ ማቅረብ፣ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሕዝቡን የሕግ ግንዛቤ ማዳበር፣ አስቀድሞ በማስተማር ወንጀል እንዳይሰራ መከላከል፣ በፍርድ ቤቶች አሰራር፣ ነጻነትና የሕግ የበላይነት ላይ ሊኖር የሚገባን እምነት ማጎልበትና በህገ መንግስቱ የተደነገጉ የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች በሙሉ በነጻነት ይሰጣሉ ማለት ሳይሆን የተለያዩ የሕግ እገዳዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የጠቀሱት አምባሳደሩ ከእነዚህም መካከል የተከራካሪዎችን የግል ህይወት ፣ የሕዝብን ሞራልና የሃገርን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ገደቦች ሊደረጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ይህ ስልጠና ከክልል መገናኛ ብዙሃን የተወጣጡ ባለሙያዎች፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ባለሙዎችና ከተለያዩ የፍትሕ አካላት የተወጣጡ የሕግ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ስልጠና ነው፡፡
መረጃው፡- የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!

Federal Justice and Law Institute

10 Oct, 14:14


የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩትበፍርድ ቤት ችሎት ዘገባ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ

Federal Justice and Law Institute

10 Oct, 04:29


የሕግ መዝገበ ቃላቱን በሚመለከት የኢቢኤስ (EBS) ዘገባ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://youtu.be/cweW23EYjew?si=VUNL2SEqhpnUfZLd

Federal Justice and Law Institute

08 Oct, 17:47


በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ታትሞ ለምረቃ በቃ!!
(መስከረም 28/2017 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ታትሞ ዛሬ ተመረቀ፡፡
የፌዴራል የፍትህና የሕግ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ እና ከጄስቲስ ፎር ኦል ፒ.ኤፍ. ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ምረቃ ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች ምሁራን እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተመርቋል፡፡
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ እና የጀስትስ ፎር ኦል ፒ.ኤፍ. ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ የሕግ መዝገበ ቃላቱን በሚመለከት ንግግር ያደረጉ ሲሆን ይህንን ተንተርሶም የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
ይህ የህግ መዝገበ ቃላት ከ4500 በላይ ቃላቶችን የያዘ ሲሆን ዘጠኝ የሕግ ምሁራንና ስድስት የሥነ-ልሳን ምሁራንን በማካተት የተዘጋጀ ነው፡፡
የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት እስካሁን ከ20 በላይ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን እንዳደረገ የተናገሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በእነዚህ ጥናቶች ውስጥ የፍትሕና ሕግ አካላት ወጥና አንድ የሚደርግ የሕግ አተረጓጎም ችግር ይስተዋል እንደነበረ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ይህ የሕግ መዝገበ ቃላት መዘጋጀቱ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ያሉ የፍትሕ ዘርፉ ተዋናዮች ወጥ የሆ አረዳድ እንዲኖራቸው ያግዛል ያሉት ክቡር አምባሳደር በተመሳሳይ የኦሮምኛ የሕግ መዝገበ ቃላትም በሶስትዮሽ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቅም በፈቀደ መልኩ ከኦሮማኛው የህግ መዝገበ ቃላት በኋላ በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎችም ለመስራት ታቅዷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በአማርኛው የህግ መዝገበ ቃላት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች ምስጋናቸውን በመቸር ንግግራቸውን አጠናቀዋል፡፡
በዕለቱ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን የዕውቅና እና የሽልማት መርሃ ግብር በማድረግ ዝግጅቱ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!

Federal Justice and Law Institute

08 Oct, 17:47


በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ታትሞ ለምረቃ በቃ!!

4,555

subscribers

2,631

photos

13

videos