ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀 @hanunmedia Channel on Telegram

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

@hanunmedia


በአይነቱ ከ ሁሉም ቻናሎች
ለየት ያለ ቻናል
ይቀላቀሉ

ሀሳብ እና አስተያየት ካለ



💌 @hanun7 💌

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈ᗩ (Amharic)

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈ᗩ is a vibrant and engaging Telegram channel that brings together all types of content for your entertainment. Whether you are looking for news, stories, or just a place to connect with like-minded individuals, this channel has it all. With a focus on creativity and innovation, ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈ᗩ promises to bring you the latest and most interesting content to keep you engaged. Join the community and be a part of the fun today! For more information and updates, follow @hanun7 on Telegram. ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈ᗩ - where creativity meets entertainment.

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Feb, 07:16


....<< አንዴ ሰፈራችን ያለች አንዲት ሙተነቂባህ ለትዳር አሰብኳትና ቀጠሮ አስይዘን ከእናቴ ጋር ልናያት ሄድን
ይላል አንዱ ጓደኛዬ ያው ሸሪዐዊ እይታ ማለት ነው >> ።

" ከቤታቸው ገብተን እንደተሰየምን
መጣችና ከፊት ለፊታችን ትንሽ ተቀመጠች " ።

" ከደቂቃዎች በኋላ ተነስታ ሄደች።
እናቴም ጨርሰናል እንሂድ!😐 አለችኝ።

እኔም፦ 😳እንዴ ኡሚ ኒቃቧን ተገልጣ
ሳላያት?! አልኳት .......?

አይ .... ልጁን አይቼው ካማረኝ ነው የምገለጥለት ብላ ነበር አለችኝ .....🥹

ለማየት ስንሄድ መታየትም አለ ብሏችኋል😁

Share to your friends 🙏

@hanunmedia
https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

15 Feb, 05:54


ፅሁፉ ትንሽ ረዘም ቢልም አንብቡት 😇

ኔግሮ የሚባል ፍሬንድ ነበረኝ ፀባይኛ ነው፣ ሌባ ነው፥ እናቱን ይወዳታል፥ ትምህርት አይገባውም፤ ተንኮል፣ ኳስ ፣ጆተኒ ፣ ትረባ ጎበዝ ነበር።

በአንድ ሴሚስተር መቶ እና ሁለት መቶ መፅሃፍ ይሰርቃል መቼ? ...እንዴት?...ከማን?... አላውቅም!

መጨረሻ ላይ ውጤቱን እየሳቀ ይነግረኛል።
አንድ ቀን እንኳን ሲሰርቅ ተይዞ አያውቅም !

የሰረቀውን መፅሐፍ ሲሸጥ አብሬው ሄጄ አውቃለሁ። ከሚገዙት ጋር ደምበኛ እንደሆነ ሰላምታ አለዋወጣቸው ያስታውቃል። አሻሻጡ የሰረቀ ፣ ሳይለፋበት ያመጣ አይመስልም፤ በቸልታ አይደለም። በርጋታ እንደትልቅ ሰው... "አይሆንም...፣ ይቅር...፣በቃ፣ ጨምር " እያለ ነው ።

እናቱን "ሸቅዬ... እዛ ማዶ ያሉት ሃብታም ሰዎች፤ ለእናትህ ስጣት ብለው ብር ሰጡኝ" እያለ እንደሚሰጣት ነገሮኝ ያውቃል ።

ሰባተኛ ክፍል ፣ ስምንተኛ ክፍል እያለን እናቱን ያግዛት ነበር ። ይወዳታል፤ አወዳደዱ እንደትልቅ ሰው ነው። "ማሚዋ ደብሯታል ...አሟታል. . . ገበያ ቀዝቅዞባታል" እያለ ያስብላታል።

ከጓደኛው አይሰርቅም። ለጓደኛው ለኔ ለሚለው ሰው ይሳሳል።

አይኖቹ ትናንሽ ናቸው፣ አካባቢውን በትኩረት ያያል፣ ከወሬ ሁኔታን ያያል። ሌባ መሆኑን ብዙ የሩቅ ሰዎች አያውቁም።

ኔግሮ ቁርንጫጭ ፀጉር ያለው፣ ድቅቅ ያለ ገላ ያለው፣ ሲስቅ ቀጭን ድምፅ የሚያወጣ ልጅ ነበር ።

አንዳንድ ቀን ይፎርፍና ሜዳ ጥግ ውኃ ልኩ ጋር ብቻውን ይሆናል ። ዝም ይላል ኳስ አይጫወትም። ቀጭን ድምፅ እያወጣ የሚስቃት ሳቅ አትኖርም። ለመኮረጅ ብዙ አይሰቃይም።

...ጨዋታ ያበዛል...።

ስለ አባቱ አላውቅም፤ እናቱ ግን ትምህርት ቤታችን በር ጎን ላይ ቃርያ ፣ ቲማቲም፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ድምብላል፣ ኮሰረት፣ ስኳር ድንች ...ምናምን ይሸጣሉ። ብዙ ደንበኛ ያላቸው አይመስለኝም። ስንወጣ ስንገባ የደራ ገበያ አንድም ቀን አይቼ አላውቅም ።

ኔግሮ የትምርት ቤት ስሙ መቆያ ነው። እኛ ነን ኔግሮ የምንለው።

እኛ ትምህርት ቤት የሚማሩ የሰፈሩ ልጆች ሲጠሩት ሰምተን መሰለኝ መቆያን ትተን ኔግሮ የምንለው።

መቆያ የሚባለው ክላስ ስም ሲጠራ ብቻ ነው። ኔግሮ ሲባል ነው እሱም ደስ የሚለው።

የሆነ ቀን ሃይሚ ግርማ መፅሃፍ ጠፍቶብኝ ኔግሮ ሰጠኝ አለችኝ። ጠየኩት "ከራሷ ቦክመህ ለራሷ ገጫሃት ኣ?" ስለው ፤ ሲስቅ የሚያወጣትን ቀጭን ድምፅ አውጥቶ ሳቀ "ባክህ እኔ እንደኔ ችስታ እናት ካለው ቤተሰብ አልሰርቅም "አለ ።

ከስምንት ወደ ዘጠኝ ስንዘዋወር ኔግሮ ታስሯል አሉን። ስሰማ "ዕድሜው ለእስር ደርሷል ወይ?" ብዬ ያኔ አልጠየኩም።

የመንግስት ትምህርት ቤት ስለተማርን ለብዙ ነገር ከዕድሜያችን በላይ ነበርን። የሚታሰሩት በግሩፕ የሚጣሉ ልጆች ስለነበሩ ብዙ አልገረመኝም።

መስከረም አስራ ሰባት ቀን ኔግሮ ሞተ አሉን። እናቱን ስናያቸው ጥቁር ለብሰዋል፥ ጉስቁልናው ብሶባቸዋል። ጉሊት የደረደሩት ከዚህ ቀደም ለመሸጥ ከሚደረድሩት በዐይነትም በመጠንም ቀንሶ አየሁ ።

ሞትን ያኔ ነበር በቅርብ ያወኩት ....በቅርብ የማውቀው፣ ሲያወራ የሰማሁት፣ አብሬው የተጫወትኩት ጓደኛዬ ሞተ ሲባል። ያኔ ነው ለመጀመሪያ ግዜ ያመንኩት።

የታሰሩበት ክፍል የነበረው ካቦ መቶት ነው ይላሉ፤ አንዴ ፖሊስ መቶት ነው ይላሉ፤ አንዴ ታሞ ነው ይላሉ ....
ኔግሮ ሞተ። እውነት ነበር!

"ልጅ ይሞታል እንዴ?!" አልኩኝ
ለምን መቆያ አሉት ግን እናቱ??
በዛ ዕድሜው እንዴት በዛ ልክ አሰበላቸው??
በምን ይሆን የሚፅናኑት??
ለምን ሌባ ሆኖ ለጓደኞቹ ታመነ??

እንዴት የሰረቀውን እንደትልቅ ሰው አስቦ ተከራክሮ ሸጠ?? ላለፋበት ነገር እንዴት ዋጋ ሰጠ?? ለምን ምንም ከሌላቸው ሰዎች አልሰርቅም አለ??

በዛ ዕድሜው እንዴት አረጀ ?
እሺ ይሁን መርህ እና ሌብነት እንዴት አብሮ ሄደለት!!

እኔንጃ ኔግሮ ግን ሞተ አሉ !!!
© Adhanom ምትኩ


ዉስጣችሁ ላይ የሆነ ስሜት አልፈጠረባችሁም 🥺🥺

@hanunmedia
https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

14 Feb, 12:31


''የ Bank accountሽን ላኪልኝ''

የበሰለ ሰው ንግግር 😉 😘

@hanunmedia @hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

13 Feb, 17:43


......ሆስፒታል ሄጄ ዶክተሩ ሁለት መድኃኒቶችን አዘዘልኝ። ሁለተኛውን መድሃኒት ወዲያውኑ አገኘሁት። መጀመሪያ ላይ የተጻፈውን አንደኛውን መድኃኒት ግን 13 ፋርማሲዎች ዞሬ አጣሁት።

ድራጊስቶቹ ያሉኝን ልንገርህ፣

አንዱ "መድኃኒቱ ዛሬ የለም። ነገ ላምጣልህ" አለኝ፣🥲

ሌላው "ይህንን መድኃኒት የሚያመርተው ካምፓኒ ተዘግቷል። ሌላ ካምፓኒ ያመረተውን ተመሳሳዩን ልስጥህ?" አለኝ፣🙂‍↔️

ሌላው ደግሞ "ይሄንን መድኃኒት ብዙ ሰው ይፈልገዋል። አሁን ከተማ ውስጥ አይገኝም። በብላክ ላምጣልህ?" ብሎ አስደነገጠኝ።😖

አንዱ ግን "ይሄ መድኃኒት ለካንሠር ህሙማን የሚሰጥ መድኃኒት ነው። ካንሠር የያዘው ቤተሰብ አለህ?" ሲለኝ በጀርባዬ ልወድቅ ስል ግድግዳውን ተደግፌ ተረፍኩ።😖

በመጨረሻም ያዘዘልኝ ዶክተር ጋ ሄጄ  "መጀመሪያ ላይ የጻፍከው መድኃኒት የምን መድኃኒት ነው? ፈልጌ አጣሁት" ስለው፣ ወረቀቱን ተቀበለኝና እንዲህ አለኝ

"ይሄ እኮ የመድኃኒት ስም አይደለም።😳  እስክሪብቶዬ አዲስ ስለሆነ እንዲጽፍልኝ የሞከርኩበት ነው" ብሎ ወረቀቱን ቀዶ ጣለው።

ባልተጻፈ ህግ ሰው በሚሞትበት አገር በተጻፈ ወረቀት ብትሞት እንዳይደንቅህ።


ፋርማሲስቶቻችን ለዘላለም ይኑሩ!!!😁

ተመልሻለው 🤭🫡
@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Feb, 14:49


...አንገቷን ደፍታ የምትኖር ሴት ከፈለክ በሁሉም ነገር አንተ ላይ ጥገኛ መሆኗን መቀበል እና የጠየቀችውን ብቻ ሳይሆን ያልነገረችህንም ነገር እያሟላህላት አለምንም ጉድለት ልትይዛት ይገባል

ቆንጆዋን ሴት ከፈለክ ከአላፊ አግዳሚው ጋር እየታገልክ እንደምትኖር መቀበል ይገባሀል

ስራ የምትውል ሴትን ፈልገህ ከወደድክ እቤት ውስጥ የማትኖርባቸው ጊዜያቶች እንዳሉ ልትቀበል ይገባል

ሀብታም ሴት ከፈለክ ጉልበተኛ፣ ግትር፣ ሀይለኛ እንደሆነች የእሷን አሳብ ተቀብለህ መኖር እንደሚገባህ ማወቅ አለብህ

በራሷ የምትተማመን እና ራሷን የቻለች ሴት ከሆነች ልብህ ያበጠባት ጊዜ ትታህ ለመሄድ እንደማትፈራ ማወቅ ይገባሃል

መዝናናት እና ጭፈራ የምታበዛን ሴት ከወደድክ መቼም ምንም ብታደርግ ደስታዋን ሙሉ እንደማታደርግላት ማመን ይገባሃል

አላህን የምትፈራ ሴት ከፈለክ ሳትቆጭ ትኖራለህ

የሀብታም ልጅ ከፈለክ ከእሷ በላይ ቤተሰቦቿ እንዲወዱህ ፀልይ

የድሀ ልጅ ከፈለክ ቤተሰቦቿን መርዳት ተቀዳሚ ሀላፊነትህ እንደሆነ ተረዳ

በዘር እና በብሄር በተከፋፈለ አገር ውስጥ ከብሄርህ ውጪ የሆነች ሴት ከፈለክ ያንተ ብሄር ሰዎች በእሷ ላይ በምንም ምክንያት ጥያቄ ቢያነሱ ከእሷ ጎን መቆም እንደምትችል እርግጠኛ ሁን

ከሌላ ወንድ ልጅ ያላትን ሴት ከወደድክ፤ ልጇን (ልጆችዋን) ውደድላት .... እንዴት እንደምትወድህ ለመንገር ቃላት ያጥረኛል

© Abby Junior

ከ ፌስቡክ ነው መንትፌ ያመጣሁት 🫣

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Feb, 04:48


Sebahal kheyr🍓

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

04 Feb, 16:38


ኧረ በ አላህ የ አይጥ መቀለጃ ሆንን እኮ ዶርማችን የ አይጥ መራቢያ ከመሆኑ በፊት... ሆነ እንጂ 😭የሆነ ነገር በሉኝ መተኛት አልቻልንም 😭😭😭

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

03 Feb, 04:16


ሰባሃል ወርድ ☀️🌸
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

01 Feb, 10:04


#ሼር
እባካችሁን_ልጄን_አድኑልኝ😭😭😭" አባት

ይህች ውብ የዘጠኝ ወርዓ ህፃን ሷድ_ዩሱፍ ትባላለች! ከተወለደች ጀምሮ በተደጋጋሚ ስትታመም እናትና አባት ጤናጣቢያ ቢወስዷትም ቶንሲል ነው እየተባሉ  መርፌ እየታዘዘላት ደህና ትሆናለች በሚል ተስፋ ቢጠብቁም ልትድንላቸው አልቻለችም!!

አንጀት የምትበላው ትንሿ ሷድ  ከጊዜ ወደ ጊዜ የባሰ እያመማት ጡት አልጠባም ብላ ስታስቸግርና ላብና ለቅሶዋ ሲያስጨንቃቸው ለተሻለ ህክምና ሌላ ሆስፒታል ወስደዋት"እረ ልጃችን በጣም ታመመችብን ምን ሆናብን ይሆን?እዩልን"ብለው በፍርሀት ጠየቁ!

ጨቅላዋ  ሷድ በሚያሳዝን ሁኔታ ከፍተኛ የልብ ህመም እንዳለባት ለወራት በተለያየ ጊዜ የወሰደችው መድሀኒት ህመሟን እንዳባሰባት በአስቸኳይ ወደ ውጪ ሄዳ ካልታከመችም ለህይወቷ አስጊ እንደሆነ ተነገራቸው!!

ቤት ኪራይ መክፈል ሲከብዳቸው ወደ እናታቸው ቤት የተመለሱት ባልና ሚስት ይህ መርዶ አስደነገጣቸው!ከ3,000,000(3ሚሊዮንብር) በላይ ለሚያስፈልገው የህክምና ወጪ ምንም ማድረግ እንደማይችሉና ልጃቸውን እያዩአት ሊያጧት እንደሆነ ሲያስቡ በጣም ጨነቃቸው!እርዱን ብለው ሰውን መለመንና ሰው ፊት መቅረብ በጣም ከበዳቸው😭

ሀዘንና ስብራታቸውን የተመለከቱ ጓደኞቻቸው ግን
እባካችሁን ሰው አስቸግረን እንሞክርና ሷድን እናድናት ብለው እገዛችሁን ፈልገው መጥተዋል! #እንድረስላቸው🙏ምንም ማድረግ ካልቻልን #ዱአ እነድርግ ለብዙ ደጋጎች እንዲደርስ
#ሼር እናድርግላቸው🙏

#አካውንት
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000304310937 የሱፍ ሀምደላ

  "ለመልካም ስራ ረፍዶ አየውቅም💔🙏
ስቁ 0713172605

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

30 Jan, 16:34


ለምን እንደዛ አልሽ ለምሳሌ እዛ እኔን የሚያፅናና ምን አለ ካልከኝ.......

ነፍስ ያላወቁ ሕፃናቶች በ ህመም ሲሰቃዩ እናቶቻቸው በ ጭንቀት የሚያደርጉትን ሲያሳጣቸው.....ልጆቻቸውን አንዴ ሲያቅፉ አንዴ ሲያዝሉ አንዴ ሲቆሙ አንዴ ሲቀመጡ.... በ ጭንቀት ሲባዝኑ......አባቶች የ ሕክምና ወረቀት ይዘው በየቢሮው ሲንከራተቱ ተጨንቀው ከላይ ከታች ሲሉ የ እድሜ ባለ ፀጋዎች በ ሰው ድጋፍ ከ አንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ራሳቸውን ችለው መፀዳዳት ስለማይችሉ የ ሰው እርዳታ ሲያስፈልጋቸው ... ያለ አስታማሚ ከ ህመማቸው ጋ እየታገሉ የራሳቸውን ጉዳይ የሚያስጨርሱ.... ድንገተኛ አደጋ ደርሶባቸው ደማቸውን እየፈሰሰ ወደ emergency ክፍል ሲያጣድፉአቸው ሩሀቸው ስላለ ብቻ በማይድን በሽታ ተይዘው ለመሞት ቀናቸውን የሚጠባበቁ... ለ አንዱ ጠያቂ በዝቶበት ሙሉ ክፍሉን እያጨናነቀው ለ ሰላምታ እንኩአ ዞር ብሎ የሚያየው የሌለው......ብቻ ብዙ ብዙ ልብ ሰባሪ ነገር
አለ.... እና ምን ልልህ ነው

1.ሙሉ ጤነኛ ነህ 100 %

2.በራስህ መብላት መጠጣት መፀዳዳት ትችላለህ::

3. በ ህመም ላይ ሆነህ ሞትህን እየጠባበክ አይደለም

4. መድሃኒት ከ እንደ ምግብ እየወሰድክ አይደለም::

5 በ አጭሩ ከላይ የተዘረዘሩት መሃል አይደለህም

6ልጅህ ሚስትህ ቤተሰብህ እዚ ስቃይ ዉስጥ የሉበትም ::

እና ምን ሆንኩ ብለህ ነው የምታማረው እእ እንዴት እንዴት ነው ሚያደርግህ ባክህ ዝም ብለህ ሲደብርህ ሼም አይዝህም አላህስ አይታዘብህም ሰው በዛ ስቃይ ዉስጥ ሆኖ እንኩአ አላህን ያመሰግናል በል አሁኑኑ አልሃምዱሊላህ በል እንደ ጤና ያለ ጣፋጭ ነገር የለም

አልሃምዱሊላህ ተመስገን ለሰጠከኝ ጤና አልሃምዱሊላህ ላደረክልኝ ነገር ሁሉ

አልፍ አልፍ ሹክር ያረብ 🤲

አፊያውን ላጣ አላህ አፊያውን ይመልስለት
አሚን ያረበል አለሚን

@hanunmedia @hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

29 Jan, 18:29


ከጨነቀህ ምንም ጥቅም የሌለው ሰው አንደሆንክ ከተሰማህ ደብሮህ ተኝተህ ስለ ሕይወት እያማረክ ከሆነ ዝም ብለህ ወደ ሆስፒታል ሂድ ከዛ አላህን የምታመሰግንበት 1000ምክንያት ይዘህ ትመለሳለህ trust me

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

26 Jan, 17:18


የ ግቢ ላይ አዝናኝ ማስታወቂያ (ማስጠንቀቂያ )😂

part 1 😂😂

ካልተነበበባችሁ comment ላይ አለላችሁ

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

26 Jan, 06:01


Word :- ኪሳራ

Definition :- target audience ስቶሪያችሁን ሳያይ expired ሲያደርግ 😢💔

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

24 Jan, 14:45


በዛ በጭንቅ ሰአት የሰሀቦች ማረፊያ በነበረችው ሀገራችን በነጃሺ፣በኡሙ አይመን እና በቢላል ምድር ላይ መመሪያችን የሆነው የአላህ ሱብሀነ ወተአላ ቃል ከፍ ብሎ በአደባባይ ሊቀራ ከአለም ከተውጣጡ ሁፋዞች ሀገራችን ልትደምቅ በአዛን ድምፅ ልታሸበርቅ እነሆ ቀናት ቀናትን እየተኩ ወደፊት አስጉዘውን መዳረሻው ላይ እንገኛለን

እርሶም ትኬቱን በእጅዎ አስገብተው ታሪካዊ አሻራዎትን በዚህ ታሪካዊ ቀን ያኑሩ

ጥር 25 ኢትዮያጲችን በአላህ ቃል እና በአዛን ትደምቃለች

ትኬቱን በ Awash Bank፣Coop፣Hijra bank፣Tele Birr Event በማለት ማግኘት ይችላሉ

ጥር 25 በአዲስ አበባ እስቴዲየም እንገናኝ
እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

23 Jan, 17:15


<<  የ አንድን ሰው ሕይወት በ ዉሸት እና ባልተገቡ ቃል ኪዳንኞች ስታበላሽ... ብድር አድርገህ ቁጠረው እስከነ ወለዱ ትከፍላታለህ::  >>

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

22 Jan, 03:57


ሀራም relation መጀመርያው ይጣፍጣል ሲባል ጉዳት ያለው ጣዕም ነው ልብ ብላቹ አይታቹ ከሆነ በጣም ብዙ የ ሀራም ትስስሮች ከባድ የሆኑ ጥርጣሬዎች አሉት ይወደኝ ይሆን ይተወኝ ይሁን ለጊዝያዊ ፍላጎቱ ሊጠቀመኝ ይሁን......ወዘተ

ወንድ ጋርም በተመሳሳይ ከኔ የተሻለ ከመጣ ትተወኝ ይሁን ባትፈልገኝስ እወድሀለው ምትለኝ መጠባበቂያ አርጋኝ ቢሆንስ....ወዘተ የሚል ጥርጣሬ አለ

እንዴት አይጠራጠሩ ትስስሩ በምንም አልቆመም prove ሚያደርጉበት ምንም አይነት መንገድ የለም በጣም ሚገርመው ይህ ሁላ ጥርጣሬ ሚኖረው ለየብቻቸው ሲሆኑ ነው አብረው ሲሆኑማ ይረሳል እንዴት አይረሳ ሸይጧን 3ተኛቸው ሆኖ

ሀላል ኒካህ እኮ መህር ያለው ሻሂድ ያለው ወሊይ ያለው ከ ቤተሰብ ወጥታ እሱን ብላ ወደሱ ቤት መግባት ያለው ለሰዎች ማሳወቅ ያለው ....እና ወዘተ እንደፈለጋት እና እንደፈለገችው ማረጋገጫ ነው !

ሀራም ትስስር ማለት ከላይ ምስሉ ለይ እንዳለው ነው አብረህ ስትሆን ይጣፍጣል ስትለያይ ይቆርጠሀል
[ጥርጣሬው፣ጭንቀቱ፣ፀፀቱ፣ቤተሰብ ፣ወንጀል የመስራት ፣የማጥፋት፣ክብርን የማጣት፣ፍቅር የያዘንን ሰውን የማጣት ፍርሀት....ወዘተ ] ያቆስላል ይጨንቃል ያስለቅሳል ይደክማል ለዚህ ነው ጌታዬ በ ቃሉ እንዲህ ያለው

[ ولا تقربوا الزنا انه كان فاحشة وساء سبيلا ]

https://t.me/hanunmedia
https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

20 Jan, 17:19


ሁሉም ሰው የሚያየው ሕልም 😂😂

ሲነጋ እጅህ ላይ ስታጣው ያለው ስሜት ግን የትም የለም 🥹😅

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

19 Jan, 17:47


ደጋግመው ያገኙት ቶሎ ይሰለቻል
መላልሰው ያሰቡት ዋጋው ይቀንሳል

አንቱዬ ልጠይቅ ምንድን ነው ምስጢሩ
ባወሳሆት ቁጥር ውዳሴው ማማሩ

ቀልቤም አልሰለቸ አልዛም ምላሴ
ይበልጥ ስታወሳ ስላንቱ ሰትዘክር ትርሳለች ነፍሴ።

ሰሉ አለ ነቢ

አላሁመሶሊ አላ ሙሀመድ

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

17 Jan, 12:48


ተናፋቂው የረመዳን ወር ለመገባት ➍➋ ቀናት ብቻ ቀርተውታል..😱🙈
ይሄን የተከበረ ወር ደርሰው ከሚፆሙትአላህ ያድርገን አሚን🤲

"ያለፈው ረመዳን ቀዳ ያለባቹሁ ቀዳቹሁን መፆም አትርሱ"
#Share!

@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

17 Jan, 10:25


ጁመአ 🌹😊

الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Jan, 17:17


አንድ ሰዉ:- «ሶላትን እንዴት ቀጥ አድርገህ ልትሰግድ ቻልክ?» ብለዉ ጠየቁት።

እሱም:- «አንድ ሼይኽ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ:- "አንተ ሶላት የተዉክ ሆይ! መከራህ ከኢብሊስ መከራ ይበልጣል። ምክንያቱም ኢብሊስ ለአደም ነዉ አልሰግድም ያለዉ፤ አንተ ግን ለአደም ጌታ ለሆነዉ አላህ ነዉ አልሰግድም ያልከዉ። ታዲያ በአንተና በአላህ መካከል ምን ተፈጥሮ ነዉ። እሱን መገናኘት እንድትጠላ ያደረገህ? ሲሉ ሰማሁ" አለ።

አላህ ሆይ! በሶላት ላይ ተገደን ሳይሆን ወደን የምንፅና አድርገን። ከዱንያና በዉስጧም ካሉ ነገሮች ሁሉ ለኛ የበለጠ የተወደደች አድርጋት።

https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Jan, 18:02


ሲጀመር.....ወይኔ ጨጓራዬ 😔😞

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Jan, 18:00


ሲጀመር አርሰናል አያበላኝ አያጠጣኝ

ጥናቴን ትቼ ያየውት ለዚ ነው ወይ uuuuu😭😭

ግቢውን እየቀወጡት ነው 😭

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Jan, 17:44


ዛሬ የ ዉበታችን ቀን ነው እስኪ አንዳንዴ አስተማሪ የሆነ ነገር ለ ባለ ትዳር እህቶቼ 🥰

ጀናባ ትጥበት🛁

ይህ ትጥበት እጅግ በጣም ቀላል እና ግዜ የማይፈጅ ኢባዳ ነው።
ሁለት አይነት አስተጣጠብ አለ የመጀመሪያው በሱና መሰረት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ያብቃቃል የሚባለው ነው።
የመጀመሪያውን ዘርዘር አድርገን ስናየው፦
ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለጀናባ ትጥበት ከ 2-3ደቂቃ🕒 ብቻ እንደሚወስድባቸው እና በ3-4litter🚰 ውሃ እንደሚታጠቡ ዘገባዎች ያስረዳሉ(ወፍራም እና ረጅም ፀጉር እንደነበራቸው እንዳትረሱ)

➡️ስንታጠብ በሱናው መሰረትም ይሁን በኖርማል አስተጣጠብም ይሁን ውሃ የግድ መንካት ያለባቸው ቦታዎች፦

↪️አፍን መጉመጥመጥ
↪️አፍንጫ ውስጥ ውሃ አስገብቶ ማስወጣት(ይህ ብዙ ግዜ ይረሳል ግን የትጥበቱ አካል ነው)
↪️ከራስ እስከ እግር ያለው ሙሉ የሰውነት አካል ውሃ መንካት አለበት

ሱናው ይህን ይመስላል፦ሰሂህ ቡሃሪ መፅሃፍ 1 ቁጥር 273

0⃣ኒያ ማድረግ እና ቢስሚላህ ብሎ መጀመር
1⃣እጅን 3ግዜ መታጠብ
2⃣እስቲንጃ ማድረግ
3⃣አሁንም እጅን በደንብ መታጠብ
4⃣ውዱእ ማድረግ(እግራችንን ታጥበን ስንጨርስ እንታጠባለን)
5⃣በሁለት እጃችን🤲 ውሃ ሞልተን 3ግዜ(1ግዜም ይቻላል ሱናው ግን 3ነው) ራሳችን ላይ ማፍሰስ እና የፀጉራችንን ስር በጣቶቻችን እያሸን ማዳረስ(ርዝመቱ ላይ ሳይሆን ስሩን ማዳረስ ነው ዋናው)
6⃣ከዚያ ሙሉ ሰውነታችን ላይ ከላይ እስከታች ውሃ ማፍሰስ
7⃣መጨረሻ ላይ እግራችንን ታጥበን እንጨርሳለን

ያብቃቃል የሚባለው አስተጣጠብ ደግሞ፦
0⃣ኒያ
1⃣አፍ እና አፍንጫ ውስጥ ውሃ አስገብቶ ማስወጣት
2⃣ከራስ ጀምሮ ሙሉ አካል ላይ ውሃ ማፍሰስ ....አለቀ....

ይህን ኢባዳ አድካሚ እና አሰልቺ እንዳይሆን፦

ሁሌም በውሃ ብቻ መታጠብ ሳሙና እና ሻምፖ አለመጠቀም ልክ ውዱእ ስናደርግ ሳሙና እንደማንጠቀመው።

በኖርማል ሻወር የምንወስድበትን እና ፀጉራችንን በደንብ የምንታጠብበትን ጊዜ ከዚህ ትጥበት ጋር አለማድረግ/መለየት

ፀጉራችንን እስከጫፍ ድረስ ውሃ ውስጥ አለመንከር(ዋናው የፀጉራችን ስርን ማዳረስ ነው)

አነስ ባለ ውሃ መጠቀም (ሱና ነው እንዲሁም ማባከን ደግሞ ኢስራፍም ስለሆነ)

በተቻለ መጠን በትንሽ ደቂቃ ውስጥ ታጥቦ መጨረስ

በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ለማትወዱ መብራት ሲጠፋ መጠባበቂ ሚሆን ትንሽዬ ሲሊንደር መግዛት😜😜

@hanunmedia
@hanunmedia

👍Like &#share ↗️

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

11 Jan, 15:29


ይህ መርፌ..

ልጄን ለማውጣት ሲባል በሚስቴ ጀርባ የገባ #_መርፌ!
.
.
ነርቯን ለማግኘት ሲባል የጀርባዋ ማለቂያ ላይ ተሰካ። ግማሸ ሰውነቷ በደነላቸው። ቁልቁል እንዳታይ ከአንገቷ በታች መጋረጃ ተዘርግቷል!
.
ቀዶ ጥገናውን ተጀመረ። "አህ" አለች።
"እንዴ! ትቅሚያለሸንዴ?" አሏት።
ፈርታለች እንጂ የኔ ሚስት
"የታለ? ወይም መቼ?" ነበረ የምትለው😁
.
በአፏ በኩል ደገሟት።
.
.
አካሏ ከቀዶ ጥገና ክፍል እየተገፋ ወጣ። አንሶላ ብቻ ጣል ተደርጎባታል። ብቻዬን የማየው ይሔ ገላ ኮሪደር ለኮሪደር እንደ ስጋ ተገፋ።
ከአይን እና ጥቂት የአንገት እንቅስቃሴ በስተቀር ሚስቴ የለችም። በአንሶላ ወጥረን አነሳናት። ባል ነኝና አስደበረኝ ይሔም። ባል "በኔ ብቻ የመጣ አይደለም" እያለ ልቡን ይደግፍ።
.
እያሾፍኩ መሆኑ የገባኝ ቆይቶ ነው።
.
ከተቀደደችበት ቦታ ይልቅ አድባ እንድትቀደድ የረዳት ያ መርፌ ለካ አሻራው ቀላል አይደለም። ቁስሉ ደርቆ ተንቀሳቀሽ ሲሏት የስለት ዣንጥላ ይመስል ታጥፋ ተነሳች። ሚስቴም እንደ ልጄ አንገቷን በራሷ መደገፍ የተሳናት ሆነች።
.
የማስታገሻ አይነት ዋጠች ማስታገሻው ያደረሰውን ጉዳት ልታስታግስ። ራስምታቱ ደሞ ሌላ ነው። በዛ ላይ ደሙ እንዲወርድ እያሉ ሆዷን እንደምለዋ ያሹታል። ቆጣ ያለ ዶክተር መጥቶ "ተነስተሽ ወክ አድርጊ" ይላል።
.
ጌታዬ ሆይ!🥺

እኔስ በዛ ግዜ ምን እያደረግኩ ነው?...
ከየአቅጣጫው #እንኳን_ደስ_አለህ እየወረደብኝ። "ታድለህ ሴትናትንዴ" ታድለህ እየተባልኩ።
.
አሁን እኔም ወላጅ ነኝ አ? ወንድ አስወላጅ እንጂ ወላጅ ሊባል አይገባውም አልኩ ግራ ቀኙን ሳልገላመጥ። ለደስታዬ በረ*ሁት እሷ ዘጠኝ ወር ቋቅ አላት። ወልዳም አታርፍ።
.
አዳም የሔዋን ባል በለስ ስላበላችው "አሳች" ብሏት ነበረ። ልጅ ስትወልድስ? #ሒወቴ_ነሽ አላት። #የህያዋን_ሁሉ_እናት_ነሽ ሲል ሔዋን አለ።
.
እንደ አዳም ሰራኝ። ለሰርጋችን እህቶቿ ፊት ፎቶ አንሺው ሳም ሲለኝ ያፈርኩ ሰውዬ እናቷ ፊት አይዞሽ እያልኩ ሳምኳት።
.
ለዘጠኝ ወር በጀርባና በሆዷ መተኛት ሲያምራት እየተገላበጥኩ ተኝቻለሁ ጎኗ። "ኧረ በቀኝ ጥሩ አይደለም" ሲሏት ጎድኗ እስኪያብጥ በአንድ በኩል ተሰየፈች። ከወለደች በሗላ ደሞ በግራና ቀኝ አይቻልም በጀርባሽ ያለትራስ ብለዋታል🥺
.
ሴት በመውለድ ትድናለች እንዲል ይህ መድሀኒት ይሁንልሸ!
.
የወለዳችሁ ሴቶች ለናንተ ትልቅ ክብር አለኝ🙏

ሲል አንድ ወንድማችን የፃፈውን አጋራዋቹ...

ሱብሃንአላህ እንዲ አይነት ባልም አለ አስብሎኛል

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

10 Jan, 14:08


በመጨረሻም
..
..
..... የፈረድንባቸውን ሰወች እየሆንን ነው 🥺💔

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

09 Jan, 18:10


በ ዉስጥ መታችሁ ምን ሆነሽ ነው ፖስት የማታደርጊው ላላችሁኝ ስለደበረኝ ነው ፖስት ሳደርግ like አታደርጉም ከዛ ደሞ ብዙ ሰው leav አያለ ስለሆነ እያስጠላኝ ነው 🥺🥹 እስኪ አበረታቱኝ 😥

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

08 Jan, 18:13


ጠዋት ስትነሱ ያለው smet😡😭

አጋጥሞት የሚያቅ...🥹
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

07 Jan, 11:31


የ ጉልበት ህመም የሚያሰቃያችሁ ሰወች አላችሁ......? እስኪ አለን በሉኝ እኔ ሰርቼ ለውጥ ያየሁበትን ስፖርት ላሳያችሁ

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

06 Jan, 07:31


የኑሮ ድራማ
አይቆይም ተከፍቶ አንድ ቀን ይዘጋል
አንድ ቀን ቢመሽም እንድ ቀን ይነጋል

ብቻ ምን አለፋሽ ተዋናይ ነሽ አንቺ
አምላክ ነው ደራሲው

እራሱ ነው መሪው
የተፃፈልሽን ዝምብለሽ ኑሪው
muba...

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Jan, 18:29


የምትበሉትን ጣፋጭ ነገር ግን እያስተዋላችሁ በአላህ
ተመልከቱ ይሄን 😢 እንዳለ ስኳር እና ዘይት ነው ያ ሰላም

አስቡበት ❗️
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Jan, 12:46


የመጀመሪያዉን አግኝታችሁታል 👏👏

አሁን ደሞ ድመቷን ፈልጉ 😇
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Jan, 11:39


እናንተ ደሞ እየቀለድኩ እኮ ነው አረ አትሸልሙኝም ተሳተፉ 🙄🙄

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Jan, 11:04


ይገምቱ ይሸልሙ



ከዚያ ምስል ልዩ የሆነውን ፈልጎ ያሳየኝ ሰው ካርድ ይሸልመኛል ፍጠኑ......
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

04 Jan, 18:09


ትንሿ እህቴ ሕልም ምን አንደሆነ ስለማታቅ በ ስልክ እያወራሁአት ምን ብትለኝ ጥሩ ነው
.
.
.
.
ነገ ማታ እንቅልፌን ተኝቼ በ አይኔ ዉስጥ አየውሽ

😂 ወይ hilal
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

03 Jan, 17:44


..ሲጀመር ለ ሕፃናት ልብስ እና ጫማ መወደድ ዋና ተጠያቂዎቹ አጫጭሮች መሆናችሁ የ አደባባይ ሚስጥር መሆኑን ይታወቃል 🙄😌...

ደሞ አጭር መሆን አያኮራም እኛም እኮ አጭር የመሆንን ስሜት እናቀዋለን.... አ ን ሰ ካ ከ ሳ...ምክንያቱም እኛ በቅለን አይደለም አጭርም ሆነን ረጅምም ሆነን እናቃለን 😅

Where are my loga people 😶🌫

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

03 Jan, 17:15


በ አላህ ሥራ እየገባሁ አይደለም
.
.
.
.
.
ግን...... እኔ እንደዚ ተንቀዋልዬ አጫጭር ወንዶችን ሳይ ሚሰማኝ ስሜት 💔

" ከኔ ትከሻ የማይደርሱ እንዳሉ ሳስብ "🥹

" ቀና ብለው የሚያዩኝ እንዳሉ ትዝ ሲለኝ "😭
ኡፍፍፍፍ🥹😁

"ሴት ምንም ብትረዝም ከ ወንድ ጋ ስትቆም እኩል ናት ከኔጋ አይሰራም!

🥹🥹..አጭር አግብቼ እንዳላርፈው ብቻ
አስተግፊሩላህ 🤲🤧 ደሞ ለ ጨዋታ ነው እሺ

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

03 Jan, 16:55


<<.. አስበሽዋል, ረጅም ሆነሽ ብልጥም ስትሆኚ 😋 >>

@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

02 Jan, 14:24


እናት እና አባቱ በ ሂወት እያሉ ከ አያቱ ጋ እንዳደገ ሰው እድለኛ ሰው ግን አለ በ አላህ 🙈.....ለምን ቤተሰቦቹ እያሉ አልሽ ካላችሁኝ ከ ዉስጣቸው ባለ ፍቅር ና ፍላጎት ሲያሳድጓችሁ እና ግዴታ ማሳደግ ስላለባቸው የሚያሳድጓችሁ አስተዳደግ አንድ አይደለም በዛ ላይ ደሞ ለ ቤቱ የ መጀመሪያ ልጅ ስትሆኑ ስሜቱ ይለያያል ነው የምላችሁ ..... ረጅም እድሜ እና ጤና ለ አያቶቻችን... የ አያት ልጅ ቀበጦች አላችሁ 🥰🤌

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

01 Jan, 05:37


ስሚኝማ ሀቢብቲ.... 🥰

<<....ከ ወደዱሽ ከ ፈለጉሽ እነሱ ይምጡ
ወደዱኝ ብለሽ በ ፍፁም አንቺ ተከትለሽ እንዳትሄጂ ሰምተሻል... አዎ እንዳትሄጂ እነሱ ይምጡ ::🤗

በ ክብር ካልተጠራሽበት ካልተጋበዝሽበት ቦታም አትሂጂ ::
ነገር ግን ነይ ባሉሽ ሁሉ የምትገኝከሆነ ደሞ ዋጋሽ ይወርዳል አንዳንዴ አውቀሽ ዛሬ አልችልም በያቸው አስቢበት

ምንም ቢሆን ከ ፈለግሽ ነይ የተባልሽበት ቦታ እንዳትሄጂ እሺ ብለሽ ቅሪ... እሺ በይ ላንቺ ብዬ ነው.... ምክንያቱም አትምጪ ማለት ደብሯቸው ነው ::💯

So...ከነዚ አይነት ሰወች ጋ የሚያስተሳስርሽ እጣ ፋንታ የለም ከ ፊታቸው ዞር በይ አላህ ሞልቶታል እሱ ::

ሌላው ደሞ ሰወችን ፈልገሻቸው በተደጋጋሚ አይመቸኝም ካሉሽ መጀመሪያ ኡዝር ስጭ ከዛ በኋላም ድጋሚ ካልተመቻቸው ....አምልጭ🏃‍♀🏃‍♀‍➡️ የኔ ቆንጆ ምንም አይጠቅሙሽም አለመፈለጋቸውን እያሳዩሽ ነው 👎

አይደለም ደጋግመሽ ልትለምኝ ይቅርና ደግመሽ ልታያቸው ማይገቡ ሰወች ናቸው ::😎

ዙሪያሽን አስተዉይ.... >> 😊

@hanunmedia
@hanunmedia

https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

31 Dec, 17:11


" ለቤት አከራዬ 1000 ብር ደመወዝ ተጨመረልኝ ብየ ስነግራቸው "
እልልል እሰይ እሰይ ብለው አቅፈው እየሳሙኝ ነው........እንደዚህ በሰው ደስታ የሚደሰት አከራይ ከየት ይገኛል 🥺 ይለኛል አንዱ ደውሎ 😂😂😂 ምስኪን ነፈር 😅

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

30 Dec, 09:49


Me: እርሜን አንድ ቀን ስጋ በልቼ ስገባ

የ ዶርም ልጆች በያይነት እየበሉ ሳገኛቸው be like 😂😂😂

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

30 Dec, 07:50


እኔ ብቻ ነኝ እንደዚ አይነት እቃዎች የምወደው 🥰

ደስ አይሉም በ ረቢ 🙈🤌🤌🥹🥹

@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

29 Dec, 14:56


እርጎ በ ቡና መቀባት እንዳትረሱ girl's 😘

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

26 Dec, 04:49


ማንኛውንም ነገር ላደርግ እችላለሁ ግን በ ፍፁም የማላደርገው ነገር ቢኖር 💀😎

@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

25 Dec, 05:56


የጥንቃቄ መልዕክት ❗️❗️ ሼር ሼር ሼር

ይህች በምስሉ ያለቸውን ግለሰብ ምስል በመጠቀም ስልክ ቁጥሮቻችነን ከየግሩፖች ወይም ከሚያውቁን ግለሰቦች በመውሰድ እንድሁም በፌስቡክ ሜሴንጀር ከራሳችን ጠይቀው በመውሰድ በቴሌግራም እና በዋትሳፕ ራሷ ግለሰቧን መስለው እንደሚከተለው ያዋሯችኋል።

“ ስሟ ሜሪ እንደምትባል አሜሪካዊት እንደሆነች ባሏ ወታደር እንደነበር እና ኢራቅ ሄዶ እንደተሰዋ ከዛ ለርሷ ደግሞ በስሟ 2 ሚልየን ዶላር በስሟ እና በአካውንቷ እንዳስቀመጠላት : እርሷም ምንም አይነት ዘመድም ሆነ ቤተሰብ እንደሌላት እና አሁን ላይ የካንሰር ታማሚ ሆና ከፍተኛ ክትትል ውስጥ እንዳለች ታጫውታችኋለች። ከዚያም ከዶክተሮቹ ለመኖር የቀረሽ ቀን 8 ቀን ነውና ሳልሞት ይህን ገንዘብ ወደ እርሰዎ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ አደራ ይህን ገንዘብ ለሚስኪኖች 70% አድርሱልኝ 30% ደግሞ ለራሳችሁ አድርጉ ብላ ትደሰኩራለች ::

ይህ መጨረሻ ላይ ያለውን ምስል በመላክ ገንዘቡን ድፕሎማቶች ስለሆኑ የሚያመጡት ዶላሩም ሳይፈተሽ እንድገባ ለፈታሾች እና ለጉምሩክ ሰራተኛ የሚከፈል እስከ 50000 ብር አስገባ ተብለህ ትጠየቃለህ ። ያው እንደ ሀገሩ ነው ሳኡዲ ወይም ዱባይ ከሆናችሁ በሪያል እና በድርሀም አስገባ ትባላለህ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆንክ ይህ ከታች ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ይላክልሀል
1000519613879 ፈርሀን አህመድ ሰይድ የሚል

እናም በዚ መልኩ እያጭበረበሩ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ

መረጃው እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ ሼር አድርጉት

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

25 Dec, 05:27


👉ለወንዶች🙋‍♂️

ወንድሜ ሆይ ወንድነት ወይም አራድነት ማለት ቆንጆ የተባለች ሴትን ሁሉ እያሳደዱ የውሸት ተረት እየነገሩ በማሳመን ለጊዜያዊ ስሜት ተጠቅሞ እንደ ርካሽ እቃ መጣል አይደለም።

ሲጀምር ሴት ልጅ እራሷን አሳልፋ የምትሰጥህ አምናህ ነው መታመን ደግሞ ትልቅ ሀላፊነት ነው መወጣት የማትችለውን ሀላፊነት ደግሞ አትውሰድ።
ላንተ ቀላል ሊመስልህ ይችላል ለእሷ ግን በጣም ከባድ ነው የአእምሮ የስነልቦና ቀውስ ተስፋ መቁረጥ ያልሆነ ማንነት ውስጥ መግባት የበታችነት ስሜት ክብር ማጣት ብዙ ብዙ ነገር ይካተታል አንተስ ከዛ ምን ተጠቀምክ? አንተ ያደረከውን ሌላው እህትህ ላይ ቢያደርገውስ?

እህት ባይኖርህ ነገ ሴት ልጅህ ላይ እንደማይደርስ በምን እርግጠኛ ነህ?? ሁሉም የዘራውን ማጨዱ አይቀርም ይልቅ ጊዜህን አታጥፋ ካሉት ከዋክብቶች መሃል አስተውለህ ጨረቃህን ምረጥ።

በእጅህ ያለችውን አርክሰህ ከምትተዋት አንግሰህ ተንከባከባት። አባት ስትሆን ደግሞ ለወንድ ልጅህ አርአያ ለሴት ልጅህ ደግሞ የምንግዜም ንጉስ ወደ ፊት ለሚያጋጥሟት ወንዶች መለኪያ ትሆናታለህ።

አይደል እንዴ....? Share

@hanunmedia
@hanunmedia
@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

24 Dec, 09:32


አላህ አይጎድልበትምና

በሌሎች ደስታ የሚያዝኑትንና በሌሎች ማግኘት ውስጥ ያጡ ያህል የሚሰማቸውን ሀሲዳምና ሳሂሮችን አላህ በራሳቸው ሃጃ ቢዚ አድርጎ የሚሹትንም ጀብቶ ከመንገዶቻቹና ከመንገዶቻችን ሁሉ ያርቅልን በሲህር ምክንያት እየተሰቃዩና እየታመሙ ያሉትንም ያሽርልን የህይወታቸውንና የህይወታቹን አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ያሰባቹትን በሙሉ አዛኙ ሁሉን አድራጊውና የማይጎድልበት አሏህ መርሃባ ይበላቹ ደስታም እንጂ ስብራት አያግኛቹ አያግኘን🤲 አሚን

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

24 Dec, 05:56


Its literally Me

always 😭😭

@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

23 Dec, 08:25


ወዳጄ ምንም መልካም ሰሪ ብትሆን ባንተ ጉዳይ የሚጠመዱ ሰዎች አይጠፉም። ይህን ግሩም አንቀጽ ተመልከት

﴿وَقَالُوا مَا لَنَا لَا نَرَىٰ رِجَالًا كُنَّا نَعُدُّهُم مِّنَ الْأَشْرَارِ﴾

ዱንያ ላይ በመጥፎ የምናያቸው የእሳት እንደሆኑ የምንቆጥራቸው ሰዎች የት ጠፉ? ይላሉ።

እጅግ አቃጣይ በሆነው እሳት ውስጥ፣ በዛ ከባድ ህመም ውስጥ ሆነው እንኳን ስለ ሌሎቹ የህመም ደረጃ ለማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። የራሳቸው ህመም ስለሌሎቹ ለማወቅ ከመፈልግ አላገዳቸውም።

እሳት ውስጥ እንዲ ካሉ፣ በዱንያስ?

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

23 Dec, 04:38


የ ሌላ ሰው ዶርም ውስጥ ያገኘውት ጥቅስ👇
.
.
.
.
" ዝቅ ብለህ ተማር , ቀና ብለህ ኮርጅ!"😂

ተማሪዎች ብቻ መልካም ቀን እና class የማይኖርበት ይሁንልን

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

22 Dec, 13:58


ዛሬ ደግሞ ስለ ፀጉር እንክብካቤ ልናወራ ነው🪮🧴

መጀመሪያ አንድ ነገር ላስታውሳችሁ

ከሃይድ እና ከጀናባ ቡሃላ ሹሩባ ተሰርተን ከሆነ ለመታጠብ መፍታት አለብን

መልስ፦የለብንም❗️ ከሃይድም ሆነ ከጀናባ ቡሃላ በጣም ጠብቆ የተሰራ እና ውሃ የማያስገባ እስካልሆነ ድረስ ፀጉር መፍታት ግዴታ አይደለም።

አንዳንድ ኡለሞች ከሃይድ ቡሃላ ከሆነ ፀጉር መፈታት አለበት ምክኒያቱም ሃይድ እንደ ጀናባ ቶሎ ቶሎ አይሆንም በወር አንድ ግዜ የሚመጣ ስለሆነ ፀጉሯን ፈትታ መታጠብ አለባት ይላሉ።
አብዛኞች ግን ለሁለቱም ትጥበት ሹሩባው ውሃ ሚያስገባ እስከሆነ ድረስ መፍታቱ ግዴታ እንዳልሆነ አስቀምጠዋል።

➡️ለፀጉራችን ጤንነት፦

ፀጉራችንን በሳምንት አንድ ግዜ በደንብ በሻምፖ እና ኮንድሽነር/ትሪትመንት መታጠብ በቂ ነው!
ከታጠብን ቡሃላ ከፀጉራችን ላይ ውሃውን በእጃችን ጨምቀን በደንብ ማውጣት

ኤሌክትሪክ ማድረቂያዎችን በተቻለ መጠን አለመጠቀም! የፀጉር ፎጣ መጠቀም በደንብ ነው የሚያደርቀው

እርጥበቱ እንዳለ ጭቃ ቅባት የፀጉሩን ዘለላ መቀባት እና በወፍራሙ ሁለት/አራት ቦታ መስራት፥ሹሩባ ምንሰራ ከሆነም በማግስቱ መሰራት

ለቆዳችን የሚስማማንን ፈሳሽ ቅባት ቢያንስ በሳምንት 2ግዜ መቀባት እና በደንብ ማሳጅ ማድረግ💆‍♀

ለዘለላው ደግሞ ጭቃ ቅባት መጠቀም

ፀጉር ስናበጥር ብዙ ከሆነ አራት ቦታ ከፋፍለን ለየብቻ ማበጠር፥ፀጉራችን እንዳይያያዝ እና ሁሉንም የፀጉራችንን ክፍል በማበጠሪያ እንድናገኘው
ያግዘናል

🪮ማበጠሪያ ሰፋፊ ጥርስ ያለውን መጠቀም።እንዲሁም ፀጉራችን በጣም ደረቅ ከሆነ ውሃ እየረጨን አለስልሰን ማበጠር።በደረቁ ሲበጠር ይሰባበራል፣ያማልም

በየግዜው የፀጉርን ጫፍ አለመቆረጥ✂️💇‍♀፥መቆረጥ ፀጉርን አያሳድግም።ጫፉ መንታ ሚያወጣው ስለተጎዳ ነው ስለዚህ መፍትሄም ጫፉን መንከባከብ ነው።

ብዙ ግዜ ቅባት ስንቀባ ትኩረት ምናደርገው ቆዳችን ላይ ነው ነገር ግን በጣም ትኩረት ማድረግ ያለብን የፀጉራችን ዘለላ እና ጫፍ ላይ ነው፥ምክኒያቱም ፀጉራችን ሲያድግ ቆዳችን ጋር ያለው አዲስ/ህፃን ፀጉር ነው ጫፍ ላይ ያለው ደግሞ የቆየ/ያረጀ ፀጉር ነው ስለዚህ እንክብካቤ ካልተደረገለት በቀላሉ የመሰባበር፣መንታ የማውጣት፣የመያያዝ ባህሪ ያመጣል ስለዚህ ፀጉራችን ከስር ቢያድግም ጫፉ ስለሚሰባበር እድገቱን አናየውም።

ከታጠብን ቡሃላ ፀጉራችን በጣም ስብስብ
ለሚልም መፍትሄው በእርጥበቱ እንዳለ የፀጉሩን ዘለላ ጭቃ ቅባት በደንብ ቀብቶ በወፍራሙ መስራት እና በማግስቱ ፈቶ  ማበጠር

ከተቻለ በ15ቀን አንድ ግዜ የሚስማማንን የተፈጥሮ ማስክ መጠቀም(አቮካዶ፣ተልባ፣ካሮት፣ሬት....)

ሹሩባ ካልተሰራን ልንተኛ ስንል 2/3ቦታ ሰርተነው መተኛት፥አሲዘነው ምንተኛ ከሆነ ፀጉራችን በጣም ይሰባበራል።

ስንተኛ ሲልክ የሆነ የፀጉር መሸፈኛ መጠቀም
ምንተኛበት ትራስ ጨርቅ ከተቻለ ሲልክ(ለስላሳ የሚሸራተተው ጨርቅ)ቢሆን ይመረጣል፦cotton ትራስ ጨርቆች የፊትንም ይሁን የፀጉርን ቅባት የመምጠጥ እና የማድረቅ ባህሪ አላቸው።

እንዲሁም ቶሎ ቶሎ ማንቀይራቸው ከሆነ የፊት
ቡጉር እንዲወጣ መንስዔ ይሆናሉ።

በየቀኑ ወይም በሳምንት 3/4ግዜ በሻምፖ🧴 ፀጉራችንን አለመታጠብ፥ ፀጉራችን ወዙን እንዲያጣ፣ እንዲደርቅ እና እንዲሰባበር ከሚያደርጉ ምክኒያቶች ዋነኛው ተደጋጋሚ ግዜ ሻምፖ መጠቀም ነው።

በውሃ ብቻ ስንታጠብ ፀጉራችን ወዙን እንደጠበቀ እንዲቆይ እንዲሁም እንዲፋፋ ያደርግልናል።

ውሃ አንድ እና አንድ ጉዳቱ እርጥበቱን ሳናደርቅ ምናፍነው ከሆነ የተለያየ ፈንገስ እንዲፈጠር ምክኒያት ይሆናል❗️

Like እና share ስለምታደርጉ ሁሌም አመሰግናለሁ

ብዙ አዲስ ሃሳቦች ይኖራሉ ፖስቱን ለ አዳዲስ ሰዎች ሼር በማድረግ ጋብዙልኝ ፀዴ እሁድ 💋😘

@Hanunmedia
https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

22 Dec, 10:17


ዛሬ እሁድ ነው የ ዉበት ቀናችን ነው
.
.
.
.
ሴቶችዬ አላቹአ.....👋

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

21 Dec, 17:30


እስኪ ጣፋጭ ነገር እና ስኳር በመጠቀም ብቻ የስኳር በሽታ የሚይዛችሁ ለሚመስላችሁ ሰወች አንዳንድ መረጃ ልንገራችሁ

የስኳር በሽታ | Diabetes mellitus

የስኳር በሽታ የደም የስኳር ወይም ግሉኮስ መጠን ረዘም ላለ ጊዜ  ከሚፈለገው በላይ ጨምሮ  ሲቆይ የሚፈጠር የጤና ችግር ነዉ

🐚ቆሽት በውስጧ ኢንሱሊንን የሚያመነጩ ቤታሴል |beta cells  የሚባሉ ህዋሳት  ያሏት ሲሆን ኢንሱሊን የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን የደም ስኳር መጠን ከልክ በላይ እንዳይጨምር የሚያደርግ ብቸኛው ሆርሞን ነው::

🧮ቆሽት ኢንሱሊንን በበቂ ሁኔታ ማመንጨት ሲያቅታት የሚከሰተውን አይነት 1 የስኳር በሽታ| type 1  diabetes በመባል የሚታወቅ ሲሆን ኢንሱሊን ተግባሩን ማከናወን ባለመቻሉ ምክንያት የሚከሰተው ደግሞ አይነት 2| type 2 diabetes ይባላል::

🧮የስኳር በሽታ መንስኤዎች

አይነት 1 የስኳር በሽታ በዋነኝነት የሚከሰተው የሰውነታችን በሽታ መከላከያ ህወሳት |Antibodies የቆሽት ቤታ ሴልን በሚያጠቁበት ጊዜ ነው ይህም Autoimmune disease በመባል ይታወቃል

🔥አይነት 2  የስኳር በሽታ የሚከሰተው በዚህ ምክንያት ነው ብሎ ማረጋገጥ ባይቻልም  ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ብዙ
ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል።
ከነዚህም መካከል
  
ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት መጨመር
    
💯የስኳር በሽታ ታሪክ ካላቸው ቤተሰቦች መወለድ
  
🏃‍♀🏃በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ                                                            
 እድሜ እየገፋ ሲሄድ

የተቀነባበሩ ወይም የተጣሩ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ
    
የተቀነባበሩ የአትክልት ቅቤወችንና ዘይቶችን መጠቀም

የስኳር በሽታ ምልክቶች

     ❄️ከፍተኛ  የውሀ ጥም
     ❄️ቶሎ ቶሎ መሽናት
     ❄️የረሀብ ስሜት
     ❄️የድካም ስሜትና እና ሌሎችም ይገኙበታል ::

ከሚታዩት ምልክቶች በተጨማሪ በደምና ሽንት ውስጥ የሚገኝን የግሉኮስ መጠንን በመለካት የሚረጋገጥ ይሆናል

🔥 ለአይነት 2 የስኳርን በሽታ የተለያዩ የመድኀኒት ህክምና አማራጮች ቢኖሩም በመድኀኒት ብቻ የስኳር በሽታን መቆጣጠርና ማከም እንዳልተቻለ ብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች ያሳያሉ::

🔥በአንጻሩ ጤነኛ የአኗኗር ዘየን በመከተል በተለይም የአመጋገብ ስርአት ላይ ማሻሻያ ማድረግና መደበኛ አካላዊ እንቅስቃሴን በመተግበር የአይነት ሁለት የስኳር በሽታን የመድኀኒት ህክምና ውጤታማ እንዲሆን ከማሰቻሉም በላይ ችግሩን ከስር መሰረቱ ለማሰወገድ ይረዳል::

⛔️የስኳር በሽታን ለመከላከልና ለመቀልበስ ከሚረዱን ምግቦች

🍎ዝቅተኛ ግላይኬሚክ ኢንዴክስ |low glycemic index እና ከፍተኛ የአሰር|fiber ይዘት ያላቸውን ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ

🧀🍳በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ

ጤናማና ተፈጥሯዊ የቅባት ምንጮችን መጠቀም 🥑

✿ እንደ ለውዝ፣ የዱባ ፍሬ፣ ስፒናችና የመሳሰሉትን በ Mg2+ የበለፀጉ ምግቦችን አዘውትሮ መጠቀም
 
✿ እንደ እርድና ቀረፋ ያሉ ብግነትን ለመቀነስ የሚረዱ ምግቦችን መመገብ 
                                                                   
ጤናማ የምግብ አዘገጃጀት ዘዴዎችን መከተልና የመሳሰሉትን  ተግባራት በማከናወን የስኳርን በሽታን መቆጣጠርና ማከም                                                                           
📌የስኳር በሽታ በጊዜው ካልታከመና እየተባባሰ ከሄደ የተወሳሰቡ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል                              

ከነዚህም መካከል
  
    ⚡️የእይታ መቀነስ
      ⚡️ስትሮክ
      ⚡️ የኩላሊት ስንፈት
      ⚡️የእጅና እግር መቁስል
      ⚡️የደም ግፊት መጨመር
      ከዛም ሲያለልፍ ሞትን ሊያስከትል ይችላል

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

20 Dec, 14:22


..ሀበይ በወገሬት መጣሙ 🤗

@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

20 Dec, 09:52


🌸 اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد🌸
      
الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 

@hanunmedia

@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

19 Dec, 17:08


ለሰው አደገኛ ተስፋ አትስጡ!

ላትኖሩ አለውልህ አትበሉት።
ላታዳምጡት ንገረኝ አትበሉት። መሸከም ማትችሉትን እንሸከማለን አትበሉት። የማንንም ህመም የመታመምም ሆነ የማስታመም ግዴታ የለባችሁም።

ከማስመሰል ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ሰውን ያተርፋል። ለሰው ያልፋል ብቻ ሳይሆን ላያልፍም ይችላል ባያልፍም ግን መኖር ትችላለህ በሉት።

ለደከማቸው እውነቱን ንገሯቸው። አንዳዴ ማንም ላይሰማህ ይችላል አንዳዴ ደግሞ የሰሚ ጆሮ ራሱ ይዝላል። በጣም የቅርብ ጓደኛህ ቀርቶ እናትህ እንኳን ስላንተ ግድ ላይሰጣት ይችላል።

በቃ እንደዚህም ከባድ ይሆናል ህይወት። ይህንንም ችሎ መኖር ነው ሁሉም ነገር ደግሞ በንግግር አይፈታም አንዳንዱ ችግር አንተ ጋር ብቻ የሚቀር ነው ።

በቃ ለሰው ማውራት እንኳን 'ማትችለው ይሆናል። እናትህ፣አባትህ፣ወንድምህ፣ጓደኛህ የማይራመዱልህ መንገዶች ብዙ ናቸው። ሁሉም በራሱ ዓለም ውስጥ የተጠመደ ነው። ለራስህ 'ራስህ ብቻ አዳኝ ሆነህ ምትቀርበት ጊዜ አለ።

ሳቅህን ከሰው ጋር አድርገው ለቅሶህን ግን አስብበት ወዳጄ።
ካነበብኩት 📖

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

18 Dec, 06:31


.. << አንድ በቅርቡ ያገባች ጉአደኛዬን ከባሏ ጋ ለምን አንደተጣላች ጠየኩአት....አንደሚከተለው መለሰችልኝ >>
.
.
.
.
.
ሱብሂ ሰግዶ ከ መስጅድ ሲመለስ ሁለት አንቁላል ገዝቶ መጣ :: 🙄

" ከዚያም አንዱን አንድጠብስ አንዱን አንድቀቅል ነግሮኝ ሳሎን ገብቶ ተቀመጠ::
እኔም እሺ ብዬ አንዳዘዘኝ አድርጌ ሰርቼ አቀረብኩለትና ሻይ ለማፍላት ተመልሼ ወደ ኪችን ገባሁ :: "

"ባለቤቴ በቁጣ ሀያት ብሎ ጮሆ ጠራኝ😡 "::

"እኔ ደሞ ምን ሆነ ብዬ ደንግጬ አቤት አልኩት 😨"::

" ነይ አለኝ በ ቁጣ ድምፅ "

"እኔም እሺ ብዬ ሄድኩና ምነው ምን ሆንክ አልኩት 😳"

" ሁለት እንቁላል ሰጥቼሽ አንዱን ጥበሽልኝ፣ አንዱን ቀቀይልኝ ስልሽ ጥበሽልኝ ያልኩሽን ቀቀልሸው፣ ቀቀይልኝ ያልኩሽን ጠበሽው አንቺ የኔን ትዕዛዝ ስለማታከብሪ ከዚ በኋላ ላይሽ አልፈልግም!!!
ብሎ ያቀረብኩለትን ሳይበላ ጥሎኝ ሄደ 😅 አለችኝ

ልሳቅ ወይስ ላልቅስ 😂 🥺

የነሱ ታሪክ አያልቅም p2 ይቀጥል የምትሉ 🥰
Like&share🥰

https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

17 Dec, 14:52


ኑሮ ውድነቱ በዚ ከቀጠለ አፈር ብላ😡

#ግብዣ እንጂ ስድብ አይሆንም😳🤦‍♂
.
.
.
😂😁😁😁😁
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Dec, 16:58


<<...ስታዝን ከ ጎንህ ነኝ

ሳዝን ነው ከ አንተ የምርቀው...>> 🥺

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Dec, 05:03


... <<ሙሉ ቀን Class የለም ከሚል ንግግር የበለጠ ለ አንድ ተማሪ አስደሳች ዜና የለም ">> !.. አራት ነጥብ 😎

.... ካደኩ ቡሃላ እሁድን ማጣጣም አንዳልችል ሆኛለው :: ምክንያቱም እሁድ ከሆነ ነገ ሰኞ ነው ሚሆነው ይሄን የማስበው ቅዳሜ ላይ ሆኘ ነው :: elementary እያለው መች ሰኞ ደርሶልኝ ጉአደኞቼን አግኝቻቸው ነበር ጭንቀቴ ::

አሁን ላይ ግን ዛሬ እሁድ ነው ነገ ሰኞ ነው ስለዚህ ነገ እረፍት የለም ወይ class ወይ ሥራ ነው ሚሆነው በሚል እሳቤ ሳልፈልግ depression ዉስጥ አገባለው በዚ ምክንያት ሰኞ ቀንን እጠላለሁ: ጠዋት class ያላቸውን አስተማሪወች በ ዉስጤ እራገማለሁ : ደጋግሜ እጠላቸዋለሁ ከዛ ስነጫነጭ እውላለሁ አማርራለሁ: ማክሰኞ ቀንን አንደ ሰኞ ሀ ብዬ በ ሰላም እጀምራለው aposto 😌

እና ዛሬ class የለኝም በ ደስተኝነት ደስተኛ ሆኘ አዉላለሁ ማለት ነው 😊💃 yupiii

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

15 Dec, 18:38


የ ማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች

Be like:-😂😂😂😂

@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

15 Dec, 15:11


ሀኑ er ፊትሽ በየቀኑ ነጭ እየሆነ ነው 😮

የ ምግብ እጥረት ነው🙄

ምን እየተቀባሽ ነው🤔 (ሴቶቹ) 😅

ፀሐይ ነክቶሽ ያቃል ግን eee ከ ዶርም አትወጭማ...?

ይሄን ሁሉ ጥያቄ የሚጠይቁኝ ግቢ ዉስጥ ያሉ ልጆች እና classmateቶቼ ናቸው ወላሂ sax አይደለም እና ለምን እንደዚ አሉሽ ካላችሁኝ
በምጠቀማቸው ተፈጥሯዊ የ ፊት maskኦች ነው
እውነት ለመናገር በተፈጥሮ በጣም ቀይ ነኝ ቢሆንም ብጉር በጣም ያስቸግረኝ ነበር ምናምን እና ፊቴም በጣም ወዛም ነበር ::

መፍትሄውን ከማወቄ በፊት

ይሄን ሁሉ የምነግራችሁ ተጠቅሜ ለውጥ ያየሁባቸውን እና የሞከርኩአቸው መሆናቸውን አንድታቁ ብዬ ነው ያ በናት 😘
ከብዙ በ ጥቂቱ እነሆ

#1

1ማንኪያ ከ ግማሽ የ በቆሎ ዱቄት (ታሽጎ ሚሸጠው )

1ማንኪያ ማር

ካነሳችሁ ከ ሁለቱም እየጨመራችሁ ፊት ለመቀባት አመቺ እስከሚሆን አስተካክሉት then መቀባት ከ 15-20 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ ከዛ ፊታችሁ empuuaa 💋 ነው ሚሆነው lets try it wela🤌

#2

የ 1 እንቁላል ነጩ part
1 የ ሾርባ ማንኪያ የ ቡና ዱቄት

ሁለቱንም አንድ ላይ በ ደምብ ማቀላቀል
የ ሜካፕ ብሩሽ ካላችሁ አሪፍ ከሌላችሁ ችግር የለውም ለመቀባት እንዲመቻችሁ ነው....አንድ ዙር ፊታችሁን ከተቀባችሁ ቡሃላ የማይበነውን ሶፍት በ ስሱ ፊታችሁ ላይ መለጠፍ ከዛ ድጋሚ መቀባት...
Horror ነው የምትመስሉት 😂 ቻሉት

ከዛ softu ሲደርክ ቀስ አያደረግሽ መላጥ ከዚያም መታጠብ አለቀ 😘

ከ ሁለት አንዱ ቤት ዉስጥ ያለውን ተጠቀሚ

Save አድርጊው ይጠቅምሻል
ይሄን ፖስት ለ ጉአደኛሽ share አድርጊ

የሚቀጥለው ሳምንት ደሞ ሌላ tip አነግራችሃለው byy🥰

@hanunmedia
@hanunmedia

https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

06 Dec, 04:21


🍂🌹የጁምአ ቀን🌹🍂
~~~~

🍂ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ .ወሰለም )እንዲህ ብለዋል ፡-🍂
አርብ(ጁመዓ) ቀን፡ ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ፡ቅባትና ሽቶ ከተቀባ በሗላ ጁመአ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ ፡በመሔድ ሌሎች ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሺ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ
፡ከዚያም የቻለውን ያህል (ነፍል) ከሰገደ በሗላ በፀጥታ ኹጥባን(የኢማሙን ንግግር )ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመዓ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሐጢያቱን አላህ ይተውለታል፡፡

ነብዩ{ሰ,ዐ,ወ} ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ኑጉስ ነው እነዚህ አምስት ነገሮች በጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል።

እነሱም
🍃1, አላህ አደምን የፈጠረው በጁመአ ቀን ነው፣
🍃2, አደም ከጀነት የወጡት በጁምአ ቀን ነው፣
🍃3, አደም የሞተውም በጁመአ ቀን ነው፣
🍃4, ቂያማ የምትቆመውም በጁመአ ቀን ነው፣
🍃5, በጁምአ ቀን የሆነች ሠአት አለች።አንድ የአላህ ባሪያ የጠየቀውን ነገር ይሠጠዋል፣ያቺን ሠአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልሆነ ድረስ አላህ ይቀበለዋል።

በሌላ የሀድስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሠማ ጁማአውን ከሰገደ አላህ ካለፈው ጁምአ እሥከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል።

በሌላ የሀድስ ዘገባ የጁምአ እለት በመጀመሪያ ሠአት ወደ መስጅድ የገባ ግመል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታላ። ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘግቡት መላኢኮች የኢማሙን ኹጥባ ለመስማት መስጂድ ይገባሉ።

የአላህ መላእክተኛ(ሰ,ዐ,ወ) እንድህ ብለዋል፦

🍂🌱የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላወትን ማውረድ አብዙ፣ማንኛውም ሠው የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላዋት አያወርድም ሠላዋቱ ቢቀርብልኝ እንጅ።🌱

{አልባኒ ሶሂህ ብለውታል} ‌"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ።" ‌ "ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ። ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡" ((62:910)

[የጁመአ ቀን ሱናወች] ~‌
~ገላን መታጠብ
~ ጥሩ ልብስ መልበስ
~ሽቶ መቀባት ለወንዶች
~ ሲዋክ
~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ
~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰ፣ዐ፣ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ።

  اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد
      
الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Dec, 16:42


ሴት ❤️....... ወንድ 👍

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Dec, 16:41


እንዴት አመሻችሁ,,,,,👋👋👋

አንዴ ላስቸግራችሁ 🙏

እስኪ አንዳንድ ነገሮችን ፖስት ለማድረግ እንዲያግዘን ከታች ያለው ድምፅ መስጫ በመጠቀም ብዛታችሁን አሳውቁን

ሴቶች ❤️ ወንዶች ደግሞ 👍 የሚለውን reaction ተጠቀሙ


👇👇

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Dec, 05:53


ስሚኝማ.....🤫
.
.
.......ደካማ ጎንሽን ለወንድ ልጅ መንገር እና ከ ፓሊስ ጋር ማውራት አንድ ነው ያወራሽውን ወሬ መልሰው አንቺን ለመጉዳት ይጠቀሙበታል ::

በደስታ ቀን አብረሽው ለተነሳሽው ፎቶ እንኩአን ለክፉ ቀን ማስፈራሪያ ያደርገዋል ጥንቁቅ ሁኝ ልክ ይኑርሽ💋

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

04 Dec, 21:43


እሷ🧕፦ሀቢቢ ተነስ መስጂድ ሂደህ ስገድ
እሱ👳፦እዚሁ ቤት እሰግዳለሁ ሁቢ
እሷ🧕፦ግን እኮ ውዴ ሀዲሱ መስጂድ🕌 ሄዳችሁ ስገዱ ነው የሚለው
እሱ👳፦እንደዛ ካልሽማ ሀዲሱ 4 ሚስት ማግባት ትችላላችሁ ይላል እኮ ውዴ😍
እሷ🧕፦የኔ ውድ ና እሺ እዚሁ በጀመዓ እንስገድ ተነስ

😂😂
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

04 Dec, 07:57


ቴሌግራም premium የምተጠቀሙ ሃብታም ሰወች ብቻ ደና ዋሉልኝ 💋 አስኪ
1..አንድ star ስጡኝ habaybi 🥺🤧

⭐️ 🌟
ስጡኝ እንጂ አንጀቴን በላችሁት 🫣

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

04 Dec, 04:47


ጥቅም የሌለኝ ፍጥረት ነኝ ብዬ አስብና
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
EBS ቅዳሜ ከሰአት ፕሮግራም ላይ ከጀርባ ሚቀመጡ ሰዎችን ሳይ እፅናናለሁ 😞🙄
Alhamdulilah 🫣

@hanunmedia @hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

03 Dec, 04:23


....ከ " ብላልኝ " ቡሃላ "በላብኝ" እንዳይመጣ "ብላ" ብለው ያቀረቡልህ ማዕድ ላይ በጎረስከው ልክ ማጉረስ እንዳትረሳ ፣ በጥጋብ የተከፈተ ደግነት እርሃብን አብዝቶ ይፈታተነዋልና . . . . .

( ካሊድ አቅሉ)

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

02 Dec, 14:31


<<.....በዚች ምድር ላይ ከአስከፊ በሽታዎች ሁሉ የላቀ ህመም ፤ ቁርጡን ሳያውቁ ዝም ብሎ በተስፋ መቀመጥ ነው ።

አገኘው ይሆን ፡ አጣው ይሆን ...? ፣ የኔ ይሁን ወይስ የሌላ እያሉ ቀን ከለሊት ያለ እረፍት ማሰብና መጨነቅ የህመሞች ሁሉ አስከፊው ህመም ነው ።

በሚያሳዝን ሁኔታ አብዛሃኞቻችን የዚው በሽታ ተጠቂዎች ነን 😔💔

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

02 Dec, 05:22


Like ለምታደርጉ active members ብቻ መርጥየ ቀን..... 💋🥰🥰🥰

.
.
.
.
.
ከዛ ዉጭ ያላችሁትን ደሞ 😅😅😅👇

First comment 🫣

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

01 Dec, 13:22


✍️ #earphone (የጆሮ ማዳመጫ) #እና #ጤናችን
*****
ውድ የ ሃኑን media ተከታታዮች በዛሬው ጽሁፋችን ይዘንላችሁ የቀረብነው አብዛኞቻችን ስለምንጠቀምበት የቴክኖሎጂ ውጤት ስለሆነው ኢርፎን ወይም የጆሮ ማዳመጫ እና ከጤናችን ጋር ተያያዥነት ስላለው ሁኔታ ነው ተከታተሉን፡፡ ማንኛችንም ብንሆን ኢርፎን ለነሺዳ ፣ ለፊልም ወይም ድምጾችን ለመስማት እንጠቀምበት ይሆናል ነገር ግን አንዳንዶች እንደሱስ የሚሆንባቸውም አሉ ግን የሚያስከትለውን የጤና ጠንቅ የተገነዘቡት አይመስልም፡፡ ሆኖም ግን አዘውትሮ መጠቀሙ እነዚህን ችግሮች ስለሚያስካትል የአጠቃቀም ሁኔታችንን ቆም ብለን ልናስተውል ይገባል፡፡

📌 የመስማት አቅም መዳከም
📌 ያልተለመዱ ድምጾችን መስማት
📌 የጆሮ ኢንፌክሽን
📌 የጆሮ ኩክ መብዛት
📌 የጆሮ ህመም
📌 የራስ ማዞር
📌 የአእምሮ ሴሎች መዳከም
📌 ለልብ ችግር መጋለጥ
📌 የራስ ምታት

አጅግ ጉዳት ስላለው በቻላችሁት አቅም ለተወሰነ ጊዜ ለማቆም ሞክሩ 🤗

Share###
@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

01 Dec, 08:26


የምወደው ልጅ ነበር ።

እርጋታው ህልሙ መልኩ ሁኔታውን እወደዋለሁ ስህተቱን ድክመቱን ሳይቀር ነበር የምታገሰው ።

ብጥር ...ብጥር... ከኔ ጋ ማቆየት አልቻልኩም ።

ጊዜ ሄደ ...

እኔም ሄድኩኝ

ሌላ መስመር ሌላ ኑሮ ሌላ ጠዓም አየሁኝ እሱ
ዘግይቶ ወደ ምፈልገው መንገድ መጣ

ዳር ዳር አለ እንዳልገባኝ ሆንኩኝ እብረን እንድንሆን ጠየቀኝ ......ዋጋሽ ገብቶኛል ወድጄሻለሁ አለኝ ።

አልታበይኩም አልጎረርኩም ሰነፍ ነው ቀድሞ ደርሶ ባረፈደ የሚያሾፈው ።

ብስለት የሚለካው የሆነልን ሲመስለን በያዝነው አቋም እና ሁኔታ ነው ።

በትህትና አልችልም አልኩት ።

Timing is every thing ፀሎቴ ውስጥ ህልሜ ውስጥ ቅዠቴ ውስጥ ማሳካት የምፈለገው ውስጥ እምይዘው አቋም ውስጥ እሱ ነበር ።

ጊዜ ሁኔታ አጋጣሚ ተደራረበ እና አንዱም ውስጥ ጠፋ !!

ግዜ ልቤ ውስጥ የተወለደውን ፍቅር አደብዝዞት ነበር ።

ልቤ ውስጥ የተከማቸውን ፍቅር ስላልወደደው ፍቅሬን ፊት ነስቼው በግዜ ብዛት ተነነ ።

ብቻ መወደድ ከብዶኝ ስለነበር ሳስታውሰው እረፍት አይሰማኝም ነበር ።

እረፍት የሌለው ፍቅር ምኑን ፍቅር ነው ??

ናፍቆኝ ጓጉቼ ሳገኘው አይኑ ለኔ ስሜት አልባ እንደሆነ ስለሚነግረኝ ናፍቆቴ ወደ ድብርት ይቀየራል ።

የሚለኝን ያደረገውን የሆነውን ሁኔታውን ትርጉም አየሰጠው ስቀምር የማድር እንደነበርኩ እኔን ካልሆነ አይገባውም !!

ዛሬ ሁኔታሽ አንቺነትሽ ሁሉ ትርጉም ሰጠኝ አብረን እንሁን አለኝ ።

ዘግይቶ ነበር Timing is every thing

እንደማይሆን እያወኩ ፍላጎት እንዳለኝ ምልክት ሰጥቼ አልበድለውም !!

" አልችልም" አልኩት

ቁርጣችንን አልነግር እያሉ እንደሚበድሉን መሆን አልፈለኩም ተፈላጊ የመሆኔን እርሃብ ለማስታገስ ወለም ዘለም እያልኩ አልበድለውም

በትህትና " አልችልም ሌላ የህወት መንገድ ላይ ነኝ " አልኩት ። እየመከርኩ አልተመፃደኩም ። መልካሙን ሁሉ እንዲገጥመው ግን በልቤ ተመኝቼለታለሁ ።

ትክክለኛ ነገር ትክክለኛ የሚያደርገው timing
ነው !

timing is every thing እንዲሉ አበው!!

መልካም ቀን
@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

30 Nov, 08:17


<<…..# በተለያየ ምክንያት አጠገባችን የነበሩ ሰዎች ሲርቁ  መጥፋት ሲጀምሩ  የሆነ ነገራቸው ሲቀየር ማስተዋል እና በቴክስት ወይም ደውለን ቼክ ማድረግ ይኖርብናል ምክንያቱም ከባድ ችግር ውስጥ ሊሆኑ ይችላላሉ.....>> ::

<<... እኛስ በተመሳሳይ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ የሚጠይቀን ሰው አጠገባችን አለ ?

እንዴት ነሽ/ህ ? የት ጠፋሽ/ህ ? እንዴት
ናችሁ የሚሉን?.....>>

<<....እንደዚህ አይነት ሰዎች ሊኖሩን ይገባል ::
እስኪ ከደወለላችሁ የቆየ ሰው ጋ ደውላችሁ ጠፋሽ/ጠፋህ በሉት 😘....>>

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

29 Nov, 07:23


ዛሬ ጁመአ ስለሆነ ሁላችሁም መልካም ቀን
🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗

የ ጁመአ ሱናወችን የምተገብሩበት....ሰለዋት የምታወርዱበት.... ፍ..ክ..ት ያለ ቀን ይሁንላችሁ
‏اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى سيدنا محمد

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

28 Nov, 14:11


ስሚኝማ....


ይሄን ሳልነግርሽ ባድር ግን ሼም ነው አ...!🙈 እርጎ እና ቡና tekebche እና ሰወቹ እያዩኝ 🫣 ሲደነግጡ ሲያስቁ 😂 ግን ቁም ነገሩን ልንገርሽ ወላሂ ፊቴ በ አንዴ ነው ጥርት ያለው ያበራው :: ለውጡን ወዲያው ታይዋለሽ በ እርግጠኛነት ነው የምነግርሽ አሁኑኑ ሞክሩት

ቢያንስ 3ማንኪያ እርጎ

2 ማንኪያ የ ቡና ዱቄት (ቡናው ካነሰ ጨምሪበት)
ከዚያ መቀባት ለ 20ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ ::

ከንፈርሽን ደሞ ትንሽ Colgate ተቀብተሽ ከ 2ደቂቃ ቡሃላ በ whips ወይም ሶፍት ዉሃ አስነክተሽ ጥረጊው ከንፈርሽም በ አንዴ fuaa ይላል trust me 🥰

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

28 Nov, 09:13


<<"በጣም ቀይ ሴቶች ብቻ ደና ዋሉ" >>😘
መልካም ቀን •~•

ደሞ
😌🌝 ያለ sunscreen አትውጭ እሺ ቆንጂዬ 💋

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

28 Nov, 04:22


በጫወታችን መሀል..."ባል ፈልግልኝ"..... አለችኝ

ምን አይነት?.....አልኳት

"ጥሩ ጸባይ ካለው ይበቃኛል።"

የምሯን እንደሆነ ሁለ ነገሯ ይናገራል.....ጉጉቷ እንጀቴን በላው።

ፍ*ረኛ ኖሮሽ ያውቃል? አልኳት።

ጥያቄውን ለማለስለስ ስታገል::

"ነበረኝ"

"ዛሬ ነገ እያለ ሕልሙ ላይ ተመስጦ ድክመቴን እያጎላ፣ እያሳጣ... ከዛሬ ነገ እንጋባለን እያለ ቀኔን እድሜዬን በልቶ ተልካሻ ምክንያቶችን ጠቃቅሶ ተለየኝ። አሁን ሌላ ከእኔ በአስር አመት የምታንስ ጉብል አግብቶ ይኖራል"

ምናለ.....

ካልወደድካት፣ ካላገባሃት ብትተዋት፣ ቀኗን ባታኝከው!! ውበቷ ሳይደበዝዝ፣ የከጀለችውን አማርጣ በጊዜዋ ታግባ። ጊዜ ለሴት ልጅ ከወንድ ልጅ የበለጠ ትርጉም አለው።

ለዛ ነው relationship ሃራም የሆነው የማታገባትን ሴት አታዋራ ተስፋም አትስጣት ዛሬዋን ትጠቀምበት ሴትጋ ነገ ሚባል ጊዜ የለም ጊዜዋ ያልፍባታልና🙏

አትስማሙም እንዴ 🙊😢

📖አዎ! እሱ ጋ ያመኛል ! 📖
©adhanom mtku


@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

27 Nov, 07:48


...<<"ረጅም ሴቶች ብቻ ደና ዋሉ ">>😘

😌🙈

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

26 Nov, 17:39


....ወደ አንዲት ተበዳሪዬ እና ባለትዳ የሆነች ሴት ጋር ደወልኩላት።

ዕዳ አለባት ፣ ግን ስልኬን አታነሳም
10 ጊዜ ደወልኩ፣ አሁንም መልስ የለም።

ባሏ እቤት ውስጥ አለመኖሩን ስላወቅኩ ይህን መልእክት ልልክላት ወሰንኩ።

"ጤና ይስጥልኝ ለገንዘቡ አይደለም የደወልኩት ። ዛሬ ከተማ ውስጥ 2 ሴቶች በባልሽ ምክንያት እየተጣሉ እንደሆነ ልነግርሽ ፈልጌ ነበር፣ በጣም ትልቅ ጠብ ነበር እና እሱም እዚያ ነበር::

አንዷ ሴት አሸንፋ አብረው በመኪናው ሄዱ እርሱን ልነግርሽ ነበር የደወልኩልሽ...

ከደቂቃዎች በኋላ ደወለችኝ ግን ችላ አልኳት። መደወል ቀጠለች እና 21 ጊዜ ደወለች

በመቀጠል የሚከተለውን መልእክት አገኘሁ።

...." የት ነበር የጠጣሉት ?"....

......"የት ሄዱ?"........

...."እነዚያን ሴቶች አስተውለሃቸዋል?"......

"እባክህ ንገረኝ....?"

ዝም ብዬ አንብቤ አልመለስኩም።

ድጋሚ 5 ጊዜ ደወለች አልመለስኩም ከዛ ሌላ መልእክት ላከችልኝ

"አሁኑኑ ገንዘብህን ልስጥህ እባክህ መገናኘት እንችላለን፣ ስለዚህ የበለጠ ንገረኝ?"

ከዛም “እሺ በባንክ አካውንቴ መላክ ትችያለሽ ነዳጅ ለመሙላት በመሙያ ጣቢያው በኩል ስለማልፍ በኋላ አንቺን ይዥሽ ወደ ልጅቷ ቤት እነዳለሁ ምክንያቱም ስለማውቃቸው ነው አልኳት::

ከ 2 ደቂቃዎች በኋላ, ሒሳቤን አካውንቴ ውስጥ መግባቱን አረጋገጥኩ, ገንዘቤ ሙሉ በሙሉ ተመልሷል እፎይ... 😊
ከዚያ እግር ኳስ ለማየት ስልኬን አጠፋሁ።😌

የተበደራችሁትን ገንዘብ ሳትጠየቁ መልሱ ለማለት
ያክል ነው..🥰🥰
@Hanunmedia
@hanunmedia ❤️ 👍

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

26 Nov, 07:43


የ ቻናሌ active meምበሮች ብቻ ደና ዋሉ 😌😌🤭 መልካም ቀን

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

24 Nov, 16:44


No words 🥹

ይሄን ስሜት ሚጋራ ሰው የለም....??

@Hanunmedia

ሀኑን 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

24 Nov, 06:58


ዛሬ እሁድ ነው እስኪ ፊታችንን ጥርት አንዲል የሚያግዙ ነገሮችን ልንገርሽ 🎁

መፍትሄዎችን ከመዘርዘሬ በፊት ግን🖐

ላስታውሳችሁ ምፈልገው ነገር እራሳችንን ከማንም ጋር ማወዳደር እንደሌለብን ነው በተለይ ደሞ ሶሻል ሚዲያ ላይ  ካሉ ሰዎች ጋር አብዛሃኛው እውነት አደለም ሜካፕ ወይም ፊልተር ነው

እራስሽን እንዳለሽ እንድትቀበይ አና እንድትወጂ እመክራለሁ 🥰🙏

1. ፊትን በቀን ሁለቴ መታጠብ
ሳሳ ያለ ማሻ በመጠቀም በስሱ ማሽት በጣም በማሸት እንዳይቆስልብሽ ጥንቃቄ  አድርጊ የማይስማማሽ ሳሙና ካለ ለይ

የመግዛት አቅም ካለሽ ደሞ በ ፊትሽ type cleanser ገዝተሽ ተጠቀሚ

🎀ያ ማለት ሱብሂ ላይ እና መግሪብ ዉዱእ
ስታደርጊ በ ሳሙና or cleanser መታጠብ

2. ፊታችንን ከታጠብን ቡሀላ ሞይስቸራይዘር (የ ፊት ማለስለሻ )መቀባት

   ሞይስቸራይዘር መግዛት ማትችይ ከሆነ እሬት መቀባት ትቺያለሽ

   Toner መግዛት ከቻልሽ ከሞይስቸራይዘር በፊት በትቀቢ አሪፍ ነው... እንደ ሃሳብ 😊

3. ብዙ ውሃ መጠጣት
   የውሃ ማነስ ፊታችን ላይ በጣም ተፅኖ አለው
   ውሃ ስጠጭ ግን ሽንት በመያዝ የኩላሊት ችግር እንዳያስከትልብሽ ጥንቃቄ አድርጊ ❗️


4. ሜካፕ ምትጠቀሚ ከሆነ በፍፁም ሳታስለቅቂ እንዳተኚ በፍጹም!! 🙅‍♀🙅‍♀ሜካፑን በዋይፕስ ብታስለቅቂ ይመረጣል ደሞ ፊትሽን በጣም አንዳትፈትጊ 🙅‍♀


5. ብዙዎቻችን ኢትዮጵያ ውስጥ ማንጠቀመው ነገር ቢኖር sunscreen ነው ፅሐይ ለቆዳችን ብዙ ጉዳት አለው ቆዳችንን ማድረቅ: ቶሎ ማስረጀት እና ሌሎችም

እና በቻልሽው አቅም Sunscreen መጠቀም አንዳትረሺ... ፊትሽ አንዲጠራ እና እንዲቀላ ያግዝሻል 🌝

6. በቂ እንቅልፍ :እንቅስቃሴ ማድረግ: የተመጣጠነ ምግብ መመገብ :ጭንቀት መቀነስ

በስተመጨረሻ እራስሽን ከማንም ጋር አታወዳድሪ 💋

Save ላይ አስቀምጭው ይጠቅምሻል 😘

ሌላ አንደዚህ አይነት tipኦች አንዲደርሳችሁ
Like&share 🫡🫡

@hanunmedia

https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

22 Nov, 18:39


➥. መውሊድ በዓለም ላይ ብዙ ሚሊየን ሙስሊሞች ያከብሩታል። አንዳንዶቹ አይቻልም ይላሉ።

➲. ስለ  መውሊድ ብዙ ኺላፎች አሉ እናንተ ከየትኛው ናችሁ

👍 አክባሪ ነኝ ❗️

👎 አላከብርም
ስለ መውሊድ ሙሉ መረጃ ለማግኝት

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

22 Nov, 18:09


ተጀመረ ተጀመረ ተጀመረ❤️🥳🥳🥳

እነሆ የሙስሊም ሴት ሰሃብዮች የጀግንነት ታሪክ ተጀምሯል

ለማንበብ አሁኑኑ JOIN የሚለውን ይጫኑ👇

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

22 Nov, 09:40


🫴እንከን አልባው ትዳር


በአረቦች ውስጥ " ሞዴል ባለ ትዳር" ተብሎ የሚታሰበውን ግለሰብ እንዲህ ብለው ጠየቁት : -
.

ሚስትህ ጋር በትዳር ዓለም ለአርባ ዓመት ያክል ያለ አንዳች እንከን እንዴት ልትቆዩ ቻላችሁ ??
.

ባልየው እንዲህ ብሎ መለሰ :-
.

በሰርጋችን የመጀመሪያዋ ሌሊት የሚከተለውን ስምምነት አደረግን: -

"እኔ ስናደድ ባለቤቴ ወደ ማእድ ቤት ልትገባ፤ ቁጣየ ሲበርድ ልትመለስ። እርሷም በበኩሏ ስትበሳጭ ወደ በረንዳ ልወጣ። ቁጣዋ ሰከን ሲል ወደቤት ልመለስ" በማለት ተስማማን። ስምምነቱን ልናከብር ቃል ኪዳን ገባን።
.
.
ይኸው አልሐምዱ ሊላህ ትዳራችን ለዚህ የበቃው ለአርባ ዓመት ያክል በረንዳ ላይ ሆኜ ነው🥹

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

21 Nov, 17:21


🍄🫙🫧
..…"እነሱን ለማስደሰት እስካልጀመርከው ድረስ… እንሱን ለማስደሰት ብለህ እንዳታቆም"..…🫧🫙🍄

ያደገን እና ያማረን የሚጠላ የለም....
keep shining 💋🤌

@hanunmedia 🥰

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

21 Nov, 05:17


من طرائف رأفة النبي ﷺ ﷺ ﷺ
ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ
ለኡመቴ የሚደርሰውን ፈተና ግማሹን እኔ ተፈትኘዋለሁ ከመካከላችሁ አንዳችሁ ፈተና በደረሰባችሁ ግዜ የኔን ፈተና አስታውሱ የኔ ትልቅ ፈተና ነው እና
ይህን ታላቅ ሰው እንየው እስኪ ለኡመቱ ሲል ምን አሳለፈ??
ከእለታት አንድ ቀን በመካ ዙሪያ እያሉ ኡቅበቱ ኢብኑ አቢ ሙአይጥ የተባለ የካፊሮች ባለ አባት በሁዋላቸው መጥቶ ትከሻቸውን ይዞ አንገታቸውን በጨርቅ በጣም አነቃቸው ማንን???😰😰😰
ለኛ ሲሉ የሚንሰፈሰፉትን ታላቅ ነብይ 😭
በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳሉ አቡ በክር አሲዲቅ ይደርሱና የኡቅባን ትከሻውን ይዘው ይገፈትሩታል
ያ አሏህ!!!!  ምን ይሰማቸው ይሆን አቡ በክር እኛስ ይህን ክስተት ብናይ ምን እንል ነበር
አቡ በክርም ቃላቸው ይህ ነበር
ጌታየ አንድ አሏህ ነው ስላለ ልትገድሉት ነው እንዴ?????
እስኪ ለኛ ብለው ለደሙት ነብይ ሶለዋት እናውርድ
ያ ሀቢቢ ያ ረሱለሏህ❤️❤️❤️ ﷺ  ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ

ሰባሀል ኸይር ☀️☀️

JOIN 👉 @hanunmedia
......... @hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

20 Nov, 03:58


መገን ረሱለሏህ💛

ዓጂብ ነው የዚህ ሰው ነገር
  ቂሳው መካ ውስጥ ነው፣ አንዲት አሮግት ሴትዮ እንጨት ለቀማ ወጥታ የቻለችውን ያህል ሰብስባ በወገቧ ተሸክማ ወደ ቤቷ እየተመለሰች አንድ ሰው ከሩቁ አያት፣ ፈጠን ብሎ መጣና:- እማማ አምጡትማ ይስጡኝ እኔ ልሸከምልዎ! እርሶ መንገዱን ብቻ ይምሩኝ ብሎ ከወገቧ ላይ አውርዶ ተሸክሞ መጓዝ ጀመሩ።
  መንገዱ እጅግ አስቸጋሪ፣ዳገት ቁልቁለታማ ነው፣የጸሀዩም ቃጠሎ ጉድ የሚያሰኝ ነበር። ከረ ጉዞና ድካም በኋላ እቤቷ ደረሰና እንጨቱን አስቀመጠላት።

  ሴትይቱም ዘወር አሉና:- ልጄ ሆይ! ለውለታህ የምከፍልህ አንዳችም ነገር የለኝም፣ ነገር ግን አንዲት ምክር ልስጥህ ትጠቅመሀለች አለችው።
ሰውየውም:- እሺ ይንገሩኝ አላቸው
ሴትይቱም:- መካ ወደ ህዝቦችህ ስትመለስ አንድ #ሙሀመድ የተባለ ነብይ ነኝ ባይ ሰው አለ ካገኘኸው ራቀው አትስማው አታዳምጠው እንዳትከተለውም አደራ፣ አለችው።

ሰውየውም:- ለምን!!? ሲል ጠየቃት!!
ሴትይቱም :- ምክንያቱም ባህሪውም ስነ-ምግባሩም መጥፎ የሆነ ሰው ነው አለች።

ሰውየውም:-ያ ሰው እኔው ሙሀመድ ነኝ  ሲሏት:- አንተ ከሆንክማ
{አሽሀዱ_አን_ላ_ኢላሀ_ኢለሏህ_ወአነከ_ሙሀመድ_ረሱሉሏህ} አለችና ወዲያው ሰለመች❤️❤️

ታዲያ ለዚህ ነቢ ሰለዋት አይገባቸውምን !!!!?


اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

19 Nov, 16:51


"ቃል ያደክማል..."....ብልህስ....

""ማለት..."

"በቃ ያደክማላ...."

"እኮ እንዴት...."

"ዛሬ ያበረታህ ቃል ነገ አንድ አንድ እያለ ይሸራርፍሀል....ብርጭቆ ቢሰበር ስብርባሪውን አይተህ መርጠህ ትረግጥና ከመድማት ትድናለህ...ቃል ሲሰበር ግን እግርህን እየተከተለ ይቆራርጥሀል..."


"ለዚህ ነው ቃልህን እያሰብክበት የምልህ....."

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

17 Nov, 20:09


🗯ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም🗯

2⃣4⃣ ሰዐት ኢስላማዊ ሀዲሶች፣ቁርዐን እና ኢስላሚክ ፕሮፋይል ፒክቸሮች የሚያገኙበት ተወዳጅ ቻናል ተጋበዙልኝ🙂‍↕️🤚

🚨 ሙስሊም አይዋሽም❗️❗️❗️🚨

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

17 Nov, 19:50


#እምባዬ 😭 የተሰኘ አሳዛኝ ተከታታይ ታሪክ ተጀመረ 🥳

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

17 Nov, 19:31


#ትንሿ_አፍቃሪ🧕ገራሚ የፍቅር ታሪክ ተዘጋጅቶ ወደናንተ መቅረብ ጀመረ🥳

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

17 Nov, 18:21


😍😍ገብተህ ማትወጣበት ቻናል ላሳይህ ናና ከስር ያለውን ንካው🙋‍♂/ንኪው🙋‍♀🤩🤩🤩

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

17 Nov, 17:28


👒የልጅነት ጊዜ ጨዋታ
እስከምን ጊዜም የማይጠፋ❤️

ጨርሱት አላቹ ቤተሰብ ዛሬ አንድ ለየት ያለ ቻናል ይዘን መተናል ቻናሉ ልጅነታችንን የሚያስታውሱ ማንኛውም ነገሮች የሚለቀቁበት ነው እና ቶሎ ተቀላቀሉ❤️‍🔥

join የሚለውን በመንካት ተቀላቀሉ
👇👇👇👇

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Nov, 19:48


#እምባዬ 😭 የተሰኘ አሳዛኝ ተከታታይ ታሪክ ተጀመረ 🥳

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Nov, 18:38


👉 የጀናዛ ብልት ውስጥ እጇ አልወጣ ያለች ሴት!

  .........መዲና ውስጥ አንዲት ሴትዮ  ትሞትና ጀናዛዋ መታጠብ ይጀምራል በድንገት የአጣቢዋ ሴት  እጅ ከጀናዛው ብልት ጋር ተጣብቆ አልላቀቅም አለ መዲና ውስጥ ያሉ ኡለማዎች የአጣቢዋ እጅ ይቆረጥ ወይስ የጀናዛው ብልት በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገ ቡ  በዚህ ጊዜ ነበር ለእንግድነት ለመጡት ኢማሙ ማሊክ ይህ  ጥያቄ የቀረበው እሳቸውም ወደ አጣቢዋ በመዞር
.....see more

ውሸት አደለም ገብተዉ ሙሉውን ያንብቡት

    👇👇👇👇👇👇
       ሙሉውን ለማንበብ
     👆👆👆👆👆👆

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Nov, 18:05


🔞🔞🔞🔞🔞❗️😳
   ሙስሊም ሆናችሁ እስከ አሁን ይሄ ቻናል ሳይኖራችሁ ቴሌግራም እየተጠቀማችሁ ነው?😳😳

ሊያመልጣችሁ የማይገባ ሁሌም ሊኖራችሁ የሚገባ ቻናል ነው።

😳ገብታችሁ እዩት በ ቻናሉ ትገረማላችሁ

አሁኑኑ JOIN በሉ በፍጥነት👇👇👇

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Nov, 17:27


ተጀመረ ተጀመረ ተጀመረ❤️🥳🥳🥳

እነሆ የሙስሊም ሴት ሰሃብዮች የጀግንነት ታሪክ ተጀምሯል

ለማንበብ አሁኑኑ JOIN የሚለውን ይጫኑ👇

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Nov, 11:45


🧣"ሩቅ መጓዝ ከፈለክ እልህ የሚያሲዝ ምክንያት ያስፈልግሀል፤ ከአልጋ አስነስቶ በሚገርም ንቃት እና ጉልበት እንድትሰራ ለህይወት እንትታገል የሚያደርግ ምክንያት ያስፈልግሀል። ምክንያት ሳይኖርህ የምትሰራቸው ነገሮች ጓጉተህ ብትጀምራቸውም አትጨርሳቸውም! "


 @hanunmedia
@hanunmedia
@Hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

15 Nov, 05:42


🔰አንቱ ትልቁ ሰዉ(1)  

መሀባዉ በረካን ሹመት እሚያለብሰዉ
በሹመት ትልቁ ኸልቁ የማይደርሰዉ
ጌታችን በፍቅር ጠርቶ ያወደሰዉ
በፅልመቱ ጌዜ ለአለም የደረሰዉ
የጌታ መሀባ በርሱ የፈሰሰዉ
የጅህልናን ቀንበር ደርሶ ያፋለሰዉ
የተዉሂድን ፍሬ ኸልቁን ያጎረሰዉ
የታመመን እሩህ ሁቡ ሚፈዉሰዉ
ህመሙ ይሽራል እጁ የዳበሰዉ

አንቱ ትልቁ ሰዉ

አንጀቱ ሚሳሳ ለወንድም ለሴቱ
ለእንስሳ ታይቀር የማይችል አንጀቱ
ፍራንክ አያከማች ተካዝናዉ እቤቱ
መሷደቅ ነዉ ስራዉ ያለዉን ተቤቱ

ዘዉዱ የገነነ ሹመቱ ማረጉ
አምሳያ የላቸዉ ወደ አላህ ሲጠጉ
አንጀተ ልስላሳ ሆዱ የማይችለዉ
የጠላቱን እምባ ጠርጎ ሚያባብለዉ
ከሸርቅ እስከ ገርባ ሹመቱ የከለለዉ
ጌታችን ሲኸልቀዉ ሁሉንም አደለዉ

በጀሊሉ ቁጣ ኸልቁ ሲርበደበድ
ጠሀይቷ ቀርባ አካልን ስታነድ
ጠፍቶት መላ ኸልቁ ሲወናበድ
ወዳንቱ አደል ወይ በቶሎ ሚራመድ
በስምሁ ልቅና ባንቱ እንዲማለድ
መጃለስን ሽቶ ከኻሊቁ ሷመድ
ሁሉም ይፈረጃል በውዱ ሙሐመድ
የጌታችን ቁጣ ይልልናል በረድ

አንቱ ትልቁ ሰው..

የተጥለፈለፈዉ ችግርም መከራዉ
ቋጠሮዉ ይፈታል ስምሁን ስንጠራዉ
በርሱ ሰበብ አደል ቁጣዉ እሚያባራዉ
በመኽሉቁ ሸምጋይ ተአርሹ በተጠራዉ

ባንቱ መኖር አደል ጀነት መሸብረቋ
ማማሯ ማጌጧ ሌላዉን ማስናቋ
ለአማኞች ተብላ በፉርቃን መፅደቋ
ነፍስ መቋመጧ በፍቅር መዉደቋ
ተፀጋዎች ሁሉ በርሱ መፈንደቋ

ሶለዋቱ ረቢ ዐለይሂ ሰላሙ!

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

15 Nov, 05:03


Malkes yshalal😅😅🥹🥹

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

15 Nov, 04:47


ምላስን የመጠበቅ አስፈላጊነትና ትሩፋቶቹ》

🚩አሏህ ሱብሀነ ወተዓላ በተከበረው ቁርኣኑ እንዲህ ብሏል

{ ما يلفظ من قول إلا لديه رقيب عتيد }
[የሰው ልጅ አንዲትንም ቃል አይናገርም ከቀኝና ከግራው ረቂብና ዐቲድ የሚባሉ ስራውን የሚመዘግቡ መላኢካዎች ያሉበት ቢሆኑ እንጂ]
ሱረቱ ቃፍ :18
🔸ረቂብ ማለት ተጠባባቂና ተቆጣጣሪ ማለት ሲሆን፣ ዐቲድ ማለት ደግሞ ካጠገቡ የማይጠፋ ማለት ነው
🔹ከላይ የተጠቀሰውን የቁርኣን ኣያ አስመልክተው ሲናገሩ ታላቁ ታቢዒይ ሀሰን አል በስሪ እንዲህ ብለዋል
"ረቂብ እና ዐቲድ የሰው ልጆችን ሁሉንም ንግግራቸውን ይፅፋሉ"
ኢክሪማህ የሚባሉትም ታቢዒይ ይህንኑ አስመልክተው የሚከተለውን ብለዋል
"ረቂብ እና ዐቲድ ጥሩ እና መጥፎ ንግግሮችን ማለትም ለሰውየው ምንዳ የሚያስገኝ የሆነውን መልካም ንግግርም ይሁን ሰውየውን የሚያስቀጣው የሆነን መጥፎ ንግግሩን ብቻ  የሚፅፉ ናቸው ብለዋል"
👌የምላስን አደገኝነት እርሱንም ከመጥፎ የመጠበቅ አስፈላጊነትና ትሩፋቱን አስመልክተው ረሱል ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ብዙ ሐዲሶችን ተናግረዋል
ከነዚህም ውስጥ
📎ኢማም አልቡኻሪይ ከሰህል ኢብኑ ሰዕድ  እንደዘገቡት   የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
["በሁለት ከንፈሮቹ መካከል ያለውን (ምላሱን) እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያለውን (ብልቱን) ለመጠበቅ ቃል የሚገባልኝ ሰው እኔ እሱ ጀነት እንደሚገባ ሀላፊ እሆነዋለሁ"]
📎ኢብኑ በጧል የተባሉት ታላቁ የሐዲስ ምሁር ከላይ የተጠቀሰውን ሀዲስ አስመልክተው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል
🔸"የሰውን ልጅ ከአደጋ ሊያጋልጡት ከሚችሉ ነገሮች ሁሉ ከባዱ ምላሱ እና ብልቱ መሆኑን ሀዲሱ ያመለክታል። የነዚህን የሁለቱን አደጋ የዳነ ሰውም የአደጋዎችን ሁሉ አደጋ ድኗል"

📎በሌላም አቡ ሁረይራህ አሏህ ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ የአሏህ መልዕክተኛ የሚከተለውን ብለዋል
🔸"አንድ ሰው አሏህን የሚያስቆጣ እሱ ግን ምንም አይነት ቦታ የማይሰጠው የሆነን ወይም ምንነቱን ያላረጋገጠውን ንግግር ይናገራል በዚህም ንግግሩ ምክኒያት ጀሀነም ውስጥ ይምዘገዘጋል (ይጣላል)
ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የበለጠ ርቀት ያለው የእሳት ጉድጓድ ውስጥ ይጣላል- "
ሐዲሱን ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል
🔹ኢዝ ኢብኑ አብዲስሰላም የሚባሉት ዓሊም ረሒመሁላህ ከላይ የተጠቀሰውን ሀዲስ በተመለከተ እንዲህ ብለዋል "ይህቺ ንግግር ( ተናጋሪዋን ጀሀነም ላይ እንዲጣል የምታደርገዋ ንግግር) ተናጋሪው መልካምነቷንና መጥፎነቷን (አደጋዋን) ለይቶ ሳያውቅና ሳያጣራ የሚናገራት ንግግር ናት" ካሉ በኋላ
አስከትለውም "የሰው ልጅ  መልካምነቱን እና መጥፎነቱን (አደጋውን) ለይቶ የማያውቀውን ንግግር መናገር ክልክል ይሆንበታል" ብለዋል

🔹ኢማም አንነወዊይም ይህንኑ ከላይ የተጠቀሰውን ሀዲስ አስመልክተው የሚከተለውን ብለዋል
"ሀዲሱ ማንኛውም ሰው ምላሱን መጠበቅ እንዳለበት  ይገፋፋል በመሆኑም አንድን ንግግር መናገር የፈለገ ሰው ከመናገሩ በፊት ሊናገር ያሰበውን ንግግሩን ያስተንትነው ከዚያም ይህንን ንግግር በመናገሩ ለሱ መልካምነቱ ከታየው (ግልፅ) ከሆነለት ይናገር ካልሆነ ግን ይታቀብ" ብለዋል
🔸አቡ ጁህፈህ የተባሉት ሰሀቢይ ባስተላለፉት ሀዲስም የአሏህ መልዕክተኛ
["አሏህ ዘንድ ተወዳጅ ስራ ብሎ ማለት ምላስን መጠበቅ ነው"] ብለዋል ኢማም
አል በይሀቂይ ዘግበውታል
🔹በሌላም ኢማም አትቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ ሱፍያን ኢብኑ አብዲላህ አሏህ ስራቸውን ይውደድላቸውና ለመልዕክተኛው
"አንቱ የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ከሚያስፈሩ ነገሮች ሁሉ ለኔ በጣም የሚፈሩልኝ ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቃቸው እሳቸውም ምላሳቸውን እየያዙ ይሄን ነው የምፈራልህ አሉት
🔸እንደዚሁ ኢማም አቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ ዑቅበት ኢብኑ ዓሚር አሏህ ስራቸውን ይውደድላቸውና የአሏህን መልዕክተኛ እንዴት ነው መዳን የሚቻለው ብሎ ጠየቃቸው ነቢዩም "ምላስህን አቅብ (ጠብቅ)" ብለውታል

🔹ኢማም አሕመድና ኢብኑ ሒባን በዘገቡት ሌላ ሐዲስ ደግሞ ["ከኸይር ነገር እንጂ ምላስህን አቅበው-ጠብቀው-"] ብለዋል
🔸በሌላም ኢማም አል ቡኻሪይ በዘገቡት ሐዲስ የአሏህ መልዕክተኛ ["ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱ እና ከዕጁ አደጋና ክፋት የዳኑ (ሰላም የሆኑ) ሰው ነው"] ብለዋል
🔹ኢማም አሕመድና ሌሎችም ከሙዓዝ ኢብኑ ጀበል በዘገቡት ሌላ ሐዲስ  ነቢዩ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም የሚከተለውን ብለዋል
["የሰው ልጆችን እሳት ውስጥ በፊቶቻቸው እንዲደፉ የሚያደርጋቸው ምላሶቻቸው ያጨዱት ነገር አይደለም እንዴ?!"] ብለዋል

🔹እንደዚሁ ኢማም አጥጦበራኒ ከሙዐዝ በዘገቡት ሀዲስ ["ዝም እስካልክ ድረስ ሰላም ከመሆን ወደሗላ አትልም በተናገርክ ጊዜ ግን ላንተ ይፃፍልሀል ወይም ደግሞ ባንተ ላይ ይፃፍብሀል"] ብለዋል
🔸በሌላም ሐዲስ
["አንድ ግለሰብ ከእስልምናው ማማርና መስተካከል ምልክቶች መካከል አንዱ የማይመለከተውን  ነገር መተው ነው"] ብለዋል
ኢማም አጥጦበራኒ ዘግበውታል

🔸እንደዚሁ ኢማም አትቲርሚዚይ ከአብዱሏህ ኢብኑ ኡመር በዘገቡት ሐዲስ መልዕክተኛው ["ዝም ያለ ዳነ"] ብለዋል ፈትሁ አልባሪ ገፅ 4583 4ተኛውን ሙጀለድ ይመልከቱ
📌እነሆ በስተመጨረሻም ሊታወቅ የሚገባ ነገር ቢኖር፥ አሏህን ሱብሓነሁ ወተዓላን ማስታወስ (ዚክርን) ማብዛት ከዝምታ የተሻለ ነው፣
ዝምታ ደግሞ ምንም አይነት ጥቅም የሌለውን ንግግር ከመናገር የተሻለ ነው
📌እንዲሁም ሀቅን ከመናገር ዝም የሚል ድዳ የሆነ (መናገር የማይችል) ሸይጧን ነው በተቃራኒው ደግሞ ባጢል (ውድቅ) የሆኑ ንግግሮችን የሚናገር ደግሞ ተናጋሪ ሸይጧን ነው!
ዉድ የአላህ ባሮች ሆይ፥
ትልቅ የአላህ ጸጋ በሆነው ምላሳችሁ አላህንም ይሁን ሰዎችን ከማስቀየም ጥንቃቄ
አድርጉ!
የሰው ልጅ በምላሱ ሊከፍርና ሽርክ ላይም ሊወድቅ ይችላል
በዚህም ዱኒያውም አኬራውም ይበላሽበታል
እንደዚሁ በምላሱ የአላህን ባሪያዎች ቀልብ ሊሰብርና ስማቸውን ሊያጠፋ ይችላል።

ለዚህም ነው
"ምላስ አጥንት አይደለም ግን አጥንት ይሰብራል"
" በዚህ ምድር ላይ እንደ ምላስ መታሰር የሚያስፈልገው ነገር ምንም  የለም"
" አንተ ሰው ሆይ ምላስህን ጠብቅ እርሱ እባብ ነውና እንዳይነድፍህ"
የተባለው
አሏህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ለኔም ለናንተንም መልካም ንግግርን ከመልካም ስራ ጋር   ያግራልን ከስህተትም ይጠብቀን!

ወላሁ አዕለም።
https://t.me/hanunmedia
https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

14 Nov, 05:35


በ ልጁ ሃሳብ ⬆️በጣም እስማማለሁ የኔ ሃሳብ ደሞ ⬇️

"..ዱንያ is too shout.. የማያስፈልጉ ሰወችን ከ ሂወታችሁ አስወጡ ያኔ ሰላማችሁን ታገኛላችሁ ወላሂ::.."
ዛሬ ነገ ሳትሉ አዛ የሆኑ ሰወችን ከ ሂወታችሁ አስወጡ.. ያለው ሰላም 🥰ሞክሩት ታመሰግኑኛላችሁ😇

""ሁሉንም ነገር ብቻችሁን ለማድረግ ሞክሩ ከዛ ራሳችሁን መሆን ትጀምራላችሁ.. ወደሁአላ የሚጎትታችሁ አይኖርም...ማንም አንደፈለገ አያሽከረክራችሁም... So ብቸኝነትን ጠበቅ!😋 "...

"እናንተን ሊጎዳችሁ የማይችለው እራሳቹ ብቻ ነው እራሳቹን ልባችሁን እየጠበቃችሁ eee በ ሰላማችሁ አንዳትደራደሩ ☑️"

ከተመቻችሁ like 👍❤️🔥

መልካም ቀን

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

13 Nov, 08:05


የውመል ቂያማ ሲደርስ ድንገተኛ ሞት ይበዛል። አላህ ከድንገተኛ ሞት እንዲጠብቃቹህ! ለምኑት።
اللهم قنا من فجأة الموت!
إنا لله وإنا إليه راجعون
ዱአ አድርጉ 😭😭

@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

13 Nov, 07:09


ልክ ከሁለት አመታት በኋላ ሳየው በጣም ደነገጥኩኝ ግን ደስ ነው ያለኝ🥹💔
.
.
.
.
መፅሐፍ ውስጥ ያስቀመጥኩትትን 200 ብሬን😉😉😂

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Nov, 20:34


💡ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም💡

ይህ ምርጥ ኢስላማዊ ቻናል በቅርብ ጊዜ ተከፍቶ ተወዳጅነት አትርፏል ለናንተም ጀባ አልኳችሁ😊

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Nov, 20:12


🚨ቁርዐን      🚨አስገራሚ ታሪኮች😱
🚨ሐዲሶች👌    🚨አዝናኝ ኢስላማዊ ቂሳዎች😂

☺️የያዙ ምርጥ ቻናሎች ተጋበዙልኝ ☺️

⭕️ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም⭕️


🗂ADD FOLDER
👉contact🌟@Muslims_Waver

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Nov, 19:35


#እምባዬ 😭 የተሰኘ አሳዛኝ ተከታታይ ታሪክ ተጀመረ 🥳

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Nov, 17:37


ይሄንን ምስል ወይም ቪዲዮ እዩ ከእናንተ መልስ እፈልጋለሁ ይቻላል #ኢማሙ የሚሰረው ስራ ትክክል ነው ወይ...??

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Nov, 17:31


👌ለዩንቨርሲቲ ና  ለ ሃይስኩል  ተማሪዎች   ብቻ የተከፈተ የኢትዮጲያ  ቻናሎች ❤️❤️

⚠️ ከ 10 ደቂ ቡሃላ ስለማታገኙት ፈጥነዉ ይቀላቀሉ!👇👇👇

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Nov, 05:48


በእጄ የያዝኩት ውሀ…

⚡️...."በእጄ የያዝኩት ውሀ እንደሆነ አላስተዋልኩም ነበር ፥ እስካሁንም ያቆየሁት እንዴት ጎበዝ ብሆን ነው ብዬ ገርሞኛል ፤ እውነቱን ለመናገር መቼ እና በየት በኩል መፍሰስ እንደጀመረ አላወኩም ፥ በቻልኩት አቅም ግጥም አድርጌ ለመያዝ እየታገልኩ ነበር ፤ በዚህ በኩል መፍሰሱን ሳይ በሚፈሰው በኩል ለማጥበቅ እሞክራለሁ : ከዛ ደሞ በሌላ በኩል መፍሰስ ይጀምራል ፥ መጀመሪያ ላይ እኮ ጥሩ ይዤው ነበር ፤ ጠብ እንኳ ሳይልብኝ...

ግን እየደከመኝ ሲመጣ ነገሩ ፈታኝ እንደሆነ ገባኝ። በቃ መፍሰስ ጀመረ ፥ ፍጥነትም ጨምሯል። እያየሁት ነው! ውሀው ሸፍኖት የነበረው እጄ እየተጋለጠ መጣ ፥ እጄን አጠብቃለሁ ግን በፍፁም አልቻልኩም አይኔ እያየ ውሀው ፈሶ አለቀ በቃ ፣ እኔም እጄን ለቀቅኩ….

ባዶ እጄን ቀረሁ…”💔💔

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

10 Nov, 18:23


ጥቁር ልብ(እውነተኛ ታሪክ)

ክፍል 11

ቆማ አንድ ቀን ጠይቋት ማያቀው ህዝብ ተሰበሰበ እኔ የሞተች መስሎኝ መጮህ ማልቀስ ጀመርኩ ።
ያጎቴ ሚስት ህፃኗን አቅፋ እንዳትሞት ትጣጣራለች ።
አንዳንዶች ደሞ  አንዳንድ ልጅኮ ገፊ ነው ናቸው ይኸው አሷን ስትወልድ ሞተች ህፃኗም አትተርፍም እናትየውም ሞታለች የሚያሳዝነው ወንዱ ልጅ ነው እያሉ ያንሾካሹካሉ።

አንድ ሰው ከጎንህ ይኑርህ ብሎ ፈጣሪ የሰጠኝ አጎቴ ደሞ ከሁላችንም ተሽሎ ለመገኘት እና መፍትሄው ላይ ለማተኮር እየሞከረ ነበር ።

በመሀል የት እንደገባ ሳይታወቅ ድራሹ ጠፋብን ባለቤቴ እንዳትገነዝ ትንፋሹ ተቆራርጦ ይወጣል እንዳንተዋት የሆነ ሰአት ላይ ትንፋሿ ሙሉ በሙሉ ይጠፋል።

በቃ ሙሉ በሙሉ እስክታርፍ እንጠብቅ ፈጣሪ እስኪወስዳት ብለው ሞቷን መጠባበቅ ጀመሩ ግማሾቹ በቃ ሲጮህ እንመጣለን ወደቤታችን እንሂድ እያሉ ወደቤታቸው ሄዱ።

ከሁለት ሰአታት ቆይታ ቡሀላ አጎቴ ልጄን ያዳነውን ሰውዬ ይዞ መጣ ።
ዞር በሉለት ይያት እሱ እጁ መዳኒት ነው ያድናታል ያድናታል እያለ ሰውዬውን ይዞት ገባ።

ሰውዬውም መጀመሪያ ሰውነቷን ሲያየው ደነገጠ ልትፈነዳኮ ነው እንደዚህ እስኪያብጥ የት ነበራችሁ አውቃችሁ እየገደላችኋት ነው እንዴ አንተስ ባል ተብዬው እንዴት ሚስትህን ማስተዋል ያቅትሀል ብሎ አንባረቀብኝ ።
እኔ ከመጀመሪያው ማስተዋሌን ተቀምቼ የለ ልትወልድ አካባቢ ሰውነቷ በጣም ሞልቶና ጨምሮ ነበር እኔ ግን አልታየኝም ነበር እርጉዝ ስለሆነች ነው ሰውነቷ የሞላው ብዬ አስቤ ነበር።

ሰውዬው እዛው ግቢ ውስጥ ያለ አጥር ላይ የሚገኝ ቅጠል ፍለጋውን ተያያዘው በመጨረሻም ከዛው ከግቢው ቆርጦ አሸና ሙሉ ሰውነቷን ቀደምኩህ ቀደምኩህ እያለ ቀባላት ቀብቶላት ሲጨርስ ሁላችሁም ከቤት ውጡ ብርድ ልብስ አልብሷትና ካጠገቧ ዞር በሉ ይሄ በላብ ነው ሚወጣላት ሌሎቻችሁ ወደቤታችሁ ሂዱ ልጅቷ ምንም አልሆነችም አታሟርቱባት አለና ተቆጣ እኔ አይኔ ፍም እስኪመስል ማልቀሴን አቆምኩ በልጄ ስላየሁት ተስፋ አድርጌ ነበር እንደምትድን።

ለሰላሳ ደቂቃ ከቤት ወጥተን ቁጭ አልን ያጎቴ ሚስት ብቻ አራሷን ይዛ እዛው ቁጭ ብላ ነበር።

ከሰላሳ ደቂቃ ቡሀላ ያጎቴ ሚስት ኑ እባካችሁ የሆነ ነገር እያለች ነው ኑ ግቡ ብላ ጮኸች እውነትም እንዳለችው እያቃሰተች ልጄን አሳዩኝ ልጄ ሞተች ልጄን እያለች እያወራች ነበር አጎቴ ዘሎ ገብቶ የለበሰቸውን ብርድ ልብስ ገለጣት ያ ሊፈነዳ የደረሰዎ ቁስል የለም ጡቷኗ ሆዷ አይለይም ነበር ባንዴ ሙሽሽሽ ብሎ ጠፍቷል የተኛችበት ቁርበት (አልጋ ላይ የሚነጠፈው የሚተኛበት ነገር ቁርበት ይባላል ከከብት ቆዳ ነው ሚሰራው)
የተኛችበት ቁርበት እንዳለ መዋኛ ቦታ መስሏል ማንም ሰው ያንን አይቶ ከሰው ልጅ ላይ የወረደ ላብ ነው ብሎ አያምንም ውሀ ተደፍቶባት  ነው ይላል እንጂ።

አጎቴና ሰውዬው አረጋጓትና ከአልጋ ላይ ሰውነቷን በነጠላ ጨርቅ ደግፈው አወረዷትና ቁርበቱ ላይ የነበረውን ላብ ወደመሬት አፈሰስነው የፈሰሳት ደምም ተቀላቅሎ ነበር ያጎቴ ሚስት ሁሉንም አፀዳዳችና ሌላ ልብስ ቀየረችላት የለበሰችው ብርድ ልብስ እንዲታጠብ ተብሎ ለብቻው ተቀመጠ እና ከነሱ ቤት ሌላ ብርድ ልብስ ይዘውላት መጡ ከበሽታዋ እስክታገግም ድረስ ያጎቴ ሚስት እየተመላለሰች አረሰቻት ቢያንስ አስራ አምስት ቀን ከሞላት ቡሀላ ግን ወገቧን እያሰረች እራሷን በራሷ ማረስ ጀመረች።

በቃ ሴቷ ልጄ ከተወለደች ቡሀላ መትረፍረፍን ይዛልን መጣች እህል ከወትሮው በተለየ ብዙ ነበር የወቃነው ቤታችን በእህል ተሞልቶ ነበር።
እንደሌሎች ህፃናት አትረብሽ አታለቅስ አታስቸግር በቃ ዝምም ነው ወንዱ ልጄም ጡት ስላላቆም ወንዱ በቀኝ ሴቷ በግራ ሁለቱም ነበር ሚጠቡት ። እሷ ከተወለደች ቡሀላ ሆኖ ማያቀውን ገንዘብ እጃችን ላይ መቆየት ጀመረ ።

አጎቴ ግማሹን እህል ሸጠን አነስ ያለ በሬ እንድንገዛና የተወሰነ ብር እሱ እንደሚሞላልን  ነገረኝና አደረግን አይገርምም እኛም ደጃችን ላይ አምቧ ሚል በሬ ኖረን ።

ሴቷ ልጄም አንድ አመት ሞላት ባለቤቴ ውሀ ልትቀዳ ስትሄድ ልጆቿን ምታስቀምጥበት ጎረቤት  ስላልነበራት ሰውጋ ለማስቀመጥም ለልጆቿ ካላት ፍቅር የተነሳ  ስለማታምናቸው እንስራውን በጀርባዋ ወንዱን ልጅ እሽኮ ሴቷን በሆዷ ይዛ ነበር ውሀ ምትቀዳው አንድም ቀን አንቺ አረፍ በይ እኔ አለሁ ብያት አላቅም ።

ህይወት መስመሯን ያዘች ብዬ ሳልጨርስ አጎቴ በድንገት አረፈ እና ለሱ ለቅሶ እናቴ መጣች።

ይቀጥላል....... like አድርጉ 😘🙏

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

10 Nov, 17:19


ጥቁር ልብ ክፍል 11

.
.
.
.
.
.
.
.





ይለቀቅ........ ዝግጁ.... አስኪ በ like አሳዩን 🥰🙏👍😘❤️

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

10 Nov, 07:20


❄️🌟 አላህ አንድም ቀን እንዳላዘንክ
አድርጎ ያስደስትሃል‥ ተስፋ አትቁረጥ......❄️🌟

     @hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

09 Nov, 11:55


🎁 የአላህ ስጦታ ስጦታ ሲሆን
ክልከላውም ስጦታ ነው ።
🎁

@hanunmedia

@hanunmedia @hanunmedia

@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

08 Nov, 16:24


እንደዚህ አይነት ዘመናዊነት መበረታታ አለበት !

ይሄ ፀዴ ተግባር ነው። አሪፍ ጀማሮ ነው። በሌላ ቦታዎችም ሆነ በሌሎች ዘርፎች ሊቀጥል የሚገባው መልካምነት ነው። ቦታው ሳር ቤት አካባቢ ነው አሉ። የፋርማሲው ስም በሃልተን ይሰኛል። የሆኑ አቅም ያላቸው ሰዎች ለራሳቸው መድሃኒቱ ሲገዙ ፣ መድሀኒት መግዛት ለማይችሉ ሰዎች በማሰብ እንዲሁ ለሌላ ተጨማሪ መድሃኒት ከፍለው ይሄዳሉ። ከዛ አቅም የሌላቸው ሰዎች መጥተው ፣ የሚፈለጉትን መድሃኒት ካገኙ እነዛን ሰዎች አመስግነው ብቻ በነፃ ይውስዳሉ !

ታዲያ ይሄ አይገርምም ? አያስደስትም ወይ ?

ይሄን ሃሳብ ካመጡት ጀምሮ ፣ ላላዩት'ና ለማያውቁት ታማሚ መድሃኒት ገዝተው ለሚሄዱ መልካም ሰዎች በሙሉ ምስጋና ይገባል።

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

08 Nov, 05:42


🤌 አላህን ስታምፀው ሁሉም ነገር
አንተን ሲወቅስህ ታገኘዋለህ‥

๏ መልእክት ሁሉ ላንተ የተላኩ ይመስልሃል

๏ ሁሉም የቁርአን አንቀፆች አንተ ላይ
የሚነበቡ ይመስልሃል‥

๏ የሆነ ነገር ሲከሰት ስታይ ትፈራለህ
ይህ ሁሉ ስሜት አላህ ከእርሱ ሸሽተህ
ወዴትም እንዳትሄድ ብሎ ነው ።

@hanunmedia
@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

07 Nov, 04:17


🪞🧡 ልክ እንደ አፍቃሪ አቀራረብ
አላህን ስትቀርበው ሀዘንህ የቱንም ያህል
ቢሆንም በእዝነቱና በፍቅሩ አብቃቅቶህ
ያስደስትሃል :: 🧡🪞

ለአላህ ሁን ህይወት ለአንተ ትሆናለች ።

         @hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

06 Nov, 05:24



#በሕይወትህ #ዘመን #ይህን #አስብ!"

#ደስታና #መከራ ባገኘህ ጊዜ ሁለቱም በመጠንና በእርጋታ ተቀበላቸው እንጂ በደስታ ጊዜ ፈንጠዝያ በመከራ ጊዜ ደግሞ መጨነቅ አታብዛ።

⭐️ #ደስተኛ #ሆነህ መኖር ከፈለግክ ልብህን ከጥላቻ እንዲሁም አእምሮህን ከጭንቀት ነፃ አድርግ።

#ኑሮ #እንድታለቅስ #መቶ ምክንያቶችን ከሰጠችህ፤ አንተ ደግሞ ፈገግ ለማለት ሺህ ምክንያቶችን ደርድርላት።

⭐️ #በዚህ #ዓለም ጥድፊያና ሁካታ ሳትበገር በእርጋታ ኑር፤ ከፀጥታ ሰላምና እረፍት የሚገኝ መሆኑን አትዘንጋ።

#አሁን #እያለፍክበት #ያለው #ፈተና እና የኑሮ ጦርነት እድልህን እንድታማርር እያደረገህ ይሆናል፤

☞ነገ የሚመጣውን ግን አታውቅም፤

☞የአንተ ችሎታና ጥበብ መሆን ያለበት ሁሉንም እንደአመጣጡ መቀበል እና ነገን ለአላህ መተዉ ነው።

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

05 Nov, 05:14


⚡️አምስት መቶ ዓመት!!⚡️

ይህ አጭር ታሪክ ጂብሪል ለነብዩ ሙሐመድ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም የነገራቸው የአንድ ሰው ታሪክ ነው። ሰውየው ለአምስት መቶ ዓመታት ያለማቋረጥ አለህን ሲገዛ ኖሯል። የሚኖረው ተራራ አናት ለይ በተሠራ ቤት ውስጥ ይኖር ነበር። ተራራው ታዲያ ጨዋማ በሆነ ውሃ የተከበበ ነበር። ነገር ግን አለህ (ሰ.ወ) ለሰውየው ሲል ከተራራው ውስጥ  ጣፋጭ ውሃ እንዲመነጭ አድርግለት። ይህ ሰው ከዚህ ውሃ ይጠጣል። ለዉዱእ እና ለሌሎች አስፈለጊ ነገሮችም ውሃውን ይጠቀማል።

@hanunmedia

አለህ (ሱ.ወ) ከምንጩ ውሃ አጠገብ ደግሞ እጅግ ጣፋጭ ፍሬ ያለውን ዛፍ አብቅሏለታል። ሰውዬው ከዚህ የዛፍ ፍሬ ይመገባል።

በዚህ ሁኔታ የሚኖረው ይህ ሰው ከዕለታት አንድ ቀን ዱዓ ያደርጋል። ሶላት እየሰገድኩ በሱጁድ ላይ እያለው ነፍሴን እንዲወስዳት አለህን ይለምናል። አለህም ዱዓውን ይቀበለዋል።
በመጨረሻው የፍርድ ቀን ይህንን ሰው አላህ (ሰ.ወ) በራሕመቱ ወደ ጀነት እንዲገባ ለመላኢካዎቹ ትዕዛዝ ያስተላልፋል። ነገር ግን ሰውየው ጀነት የምገባው አምስት መቶ ዓመታት በሠራሁት መልካም  ተግባር ነው በማለት ይከራከራል። በምድር ላይ ሲኖር  አላህ ከሰጠው መልካም ምንዳዎች ጋር እንዲያወዳድሩ  ለመለኢካዎቹ እንዲያስረዱት ትእዛዝ ያስተላልፋል። መላኢካዎቹም ሰውየው ለአምስት መቶ ዓመታት በተከታታይ የሠራቸው መልካም ሥራዎች አላህ ከሰጠው ዓይኑ ጋር እንኳ ሊመጣጠን አለመቻሉን ያስረዳሉ። በመጨረሻም ወደ ጀሀነም ይዘውት እንዲሄዱ በአላህ (ሱ.ወ) ይነግራቸዋል።
ለአንዲት ደቂቃ እንኳ ያለሰበው ነገር የገጠመው ሰውየው ግን በዚህ ጊዜ አለህን ይማጸናል፤ "ጥፋተኛ ነኝ! እባክህ በአንተ ራሕመት ብቻ ወደ ጀነት አስገባኝ፤" በማለት አላህን ይለምናል።

  ይህንን ተከትሎም በአላህ (ሱ.ወ) እና በሰውየው መካከል የሚከተለው ንግግር ይካሄዳል ፦

አላህ ፦ አንተ ባሪያዬ ሆይ! የፈጠረህ ማን ነው?
ሰውየው ፦ የፈጠርከኝማ አንተ ነህ!
አላህ ፦ ለአምስት መቶ ዓመታት ፈጣሪህን እንድትገዛ አቅም የሰጠህ ማን ነው?
ሰውየው ፦ የታላቆች ሁሉ ታላቅ የሆንከው ጌታዬ ሆይ! ይህንን አቅም ሁሉ የሰጠኸኝ አንተ ነህ።

አላህ ፦ በውሃ በተከበበው ተራራ ላይ መኖሪያህን በማድረግ ከእርሱም የሚጠጣ ንጹሕ ጣፋጭ ውሃን ከጨዋማው ውሃ ያፈለቀልህስ ማን ነው? ማንስ ነው ሁል ቀን የምትመገበውን ጣፋጭ ፍሬ ዛፍ ያበቀለልህ? በሱጁድ ላይ ሆነህ እንድትሞት ያደረገህስ ማን ነው?
ሰውየው ፦ ዓለምን በሙሉ የምትቆጣጣረው አምላኬ ሆይ! ይህን ሁሉ ማግኘት የቻልኩት በአንተ ራሕመት ነው።

በመጨረሻም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ ፦  ይህ ሁሉ የሆነው በእኔ ራሕመት ነው፤ ጀነት የምትገባውም በእኔ ራሕመት ይሆናል።

ጌታችን በራህመትህ  ጀነት አስገባን🤲🤲

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

04 Nov, 18:04


👉 የጀናዛ ብልት ውስጥ እጇ አልወጣ ያለች ሴት!

  .........መዲና ውስጥ አንዲት ሴትዮ  ትሞትና ጀናዛዋ መታጠብ ይጀምራል በድንገት የአጣቢዋ ሴት  እጅ ከጀናዛው ብልት ጋር ተጣብቆ አልላቀቅም አለ መዲና ውስጥ ያሉ ኡለማዎች የአጣቢዋ እጅ ይቆረጥ ወይስ የጀናዛው ብልት በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገ ቡ  በዚህ ጊዜ ነበር ለእንግድነት ለመጡት ኢማሙ ማሊክ ይህ  ጥያቄ የቀረበው እሳቸውም ወደ አጣቢዋ በመዞር
.....see more

ውሸት አደለም ገብተዉ ሙሉውን ያንብቡት

    👇👇👇👇👇👇
       ሙሉውን ለማንበብ
     👆👆👆👆👆👆

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

03 Nov, 16:48


#ለአላህ #ብሎ #የመዋደድ #ጥቅም

የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል:-

#ከአላህ ባሪያዎች ዉስጥ ነቢይም ሸሂድም ያልሆኑ ሠዎች አሉ ሆኖም
የፍርዱ ቀን ከአላህ ጋር ባላቸዉ ቦታ ነቢዮችም ሸሂዶችም የሚቀኑባቸዉ አሉ::

ሠሃቦችም እንዲህ ብለዉ ጠየቁዋቸዉ::" #የአላህ #መልክተኛ ሆይ!
እነማን እንደሆኑ ግለፁልን! መልክተኛዉም እንዲህ አሉ:-

☞"የዝምድናና
የንግድ ግንኙነት ሳይኖራቸዉ ለአላህ ብለዉ የተዋደዱ ሰዎች ናቸዉ::

#በአላህ #ይሁንብኝ! ፊታቸዉ ብርሃን ነዉ በብርሃንም ላይ ይጓዛሉ ሌሎች
ሲፈሩና ሲያዝኑ እነሱ ግን አይፈሩምም አያዝኑም::

" #ከዚያም ነቢዩ
(ሰ.ዐ.ወ)የሚከተለዉን የቁርአን አያ አነበቡ:-

("አዋጅ! የአላህ ወዳጆች
ፍርሃትም ሀዘንም የለባቸዉም::")....
(በአቡ ዳዉድ የተዘገበ)

የፍርዱ ቀን አላህ በሚከተለዉ ተወዳጅ በሆነ ጥሪ ይጠራቸዋል::

" #የታሉ በኔ
ክብር ለኔ ብለዉ የተዋደዱ? ዛሬ የኔ ጥላ እንጂ ሌላ በሌለበት ቀን::
ከጥላዬ ጥላን እሠጣቸዋለሁ::".....

(በሙስሊም የተዘገበ)

እኔ ለአላህ ብየ እወዳችሁአለሁ🫶
አላህ ይውደዳችሁ 🥰

መልካም ምሽት 💋

  t.me/hanunmedia
t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

03 Nov, 09:04


አንድ የክፍላገር ሰው ነው ሀጅ ለማድረግ ወደ መካ ሄዶ ካእባን መዞር ጀመረ ዱአ እያደረገ በሚዞርበት ሰአት ፀሀይ በጣም መቶት ነበር እና እራሱን ስቶ ይወድቃል::

ይዘውት ወደ ሀኪም ቤት ይሄዳሉ:: ከ ሰአታቶች ቡሀላ ነቅቶ ግራ ቀኙን ሲያይ ክፍሉ ነጭ በ ነጭ ነው:: የተኛበትንም አልጋ ሲመለከት ትልቅና ሚያምር ነው::
.
.
ጀነት የገባ መሰለው!" አላሁ አክበር ጀነት ገባሁ እያለ ሙጮህ ጀመረ:: ወደ ቀኝ ዞር ሲል 5 ነጫጭ ልብስ የለበሱ ፊሊፒናዊ ሴት ነርሶችን ተመለከተ::
.
.
"አላሁ አክበር ሁረል አይኖች ሁረል አይኖች "እያለ መጮህ ጀመረ:: ነርሶችም የሚለው ስላልገባቸው ሊይዙት ጠጋ ሲሉ
.
.
.
.
.
"ቆይ እንጂ ተራ በተራ ይሁና" 😂😂😂

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

02 Nov, 18:50


ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን
ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል፡፡
አለቃውም 'መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ
ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም'
በማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡ ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡
ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን
አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል ፤
አለቃውም 'ይሞታል ብዬህ አልነበረም?
ለሚሞት ሠው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤' በማለት
ይወቅሰዋል፡፡
ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር ፡፡
አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም
ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር ፣
አለቃውም 'ምን አለህ?' ሲለው
ወታደሩም #እንደምትመጣ_እርግጠኛ_ነበርኩ ፡፡

እውነተኛ ጓደኛ ማለት ሁሉም ሠው ሲሸሽህ እሱ ግን የሚፈልግህ ነው!

ከወደዱት😍ለዘመድ ጓደኛዎ #ሼር/ #SHARE ያድርጉ።

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

01 Nov, 04:20


❤️‍🔥 የፍቅርን ጌታ ማፍቀር
አፍቃሪው መቼም የማይደክምበትና
እድለቢስ የማይሆንበት ፍቅር ነው ።

@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

31 Oct, 04:07


ወላሂ እጅግ በጣም ቀናሁ. . . .

☞ሰብር አድርጋችሁ አንብቡት ትጠቀማላችሁ ኢንሻ አላሁ ተዓላ !
✿መጪው ዘመን የሚል አንድ ደብዳቤ ላይ አንድ የአረብ ሀገሮች
የመኪና ፍጥነት የሚቆጣጠር ትራፊክ ይህንን ታሪክ ዘግቦታል. . .
>ለናንተ ላካፍላችሁ! ትራፊኩ እንዲህ ሲል ታሪኩን ጀመረ:- "
አንዴ የተለመደውን ስራዬን ቆሜ እየሠራሁ እንዳለ አንድ መኪና
እንዲሁ ረጋ ብሎ ሲሄድ ነበር ይህ ሰው መኪናው ተበላሸበትና
ከመኪናው ወቶ ወርዶ ለማስተካከል ልክ እንደወረደ ከሁዋላ
መጣችና አንዲት መኪና ወጣችበት ወደቀ ተገጨ
ይህ ሰው ከባድ የሆነ አወዳደቅን ወደቀ እኛም ሩጠን አነሳነውና
መኪና ላይ ሰቀልነው ይሄን ሰው ይህ ሰው ስናየው ገና ለጋ
~ወጣት ነበር ይህ ልጅ የአላህ ባሪያ መሆኑ ፊቱ ላይ ያስታውቃል
``ፂሙ ፊቱ ያበራል የኢማን ኑር ይታይበት ነበር ልክ አንቡላንስ
>መኪና ላይ ስንጭነው ይህን ወጣት አብረነው ስንሳፈር የኾነ
ቃል ይናገር ነበር የሚለውን ግን መረዳት አልቻልንም ነበር ነገር
ግን መኪና ውስጥ አድርገነው ከጎን እኔና ጉዋደኛዬ ትራፊክ
አብረን ከጎን ሁነን መሄድ ስንጀምር ለየት ያለ የሚያምር ድምፅ
መስማት ጀመርን አላሁ አክበር!!!
❀ይህ ወጣት ቁርዓን እየቀራ ነበር ይህ ወጣት በሚያምር ድምፅ
ቁርዓን እየቀራ ነበር ሱብሀንአላህ! በጣም ይገርማል እንደው
የተመታ እንደዚያ አይመስልህም ደም ልብሱን እንዳለ አካላቱን
አልብሶታል አጥንቱ ደቆ ተሰባብሮዋል ልክ ወጣቱን ስታየው ሞት
አፋፍ ላይ ያለ ነው የሚመስልህ ነገር ግን ይህ ወጣት
በሚያምር ድምፅ ቁርዓንን ይቀራ ነበር ሞት አፋፍ ላይ ያለ
ወጣት! አላሁ አክበር!
ተገርመን በጣም ማየት ጀመርን ትንሽ እንደቆየ ፀጥ አለ!ወደ
ሁዋላ ዞር ብዬ ስመለከተው እጁን ወደ ላይ አድርጎ ሸሀዳ እያለ
ነበር :- " አሽሀዱ አላ ኢላሀ ኢለላህ ወአሽሀዱ አነ ሙሀመደን
ረሱሉላህ" ያ አላህ! ሱሀነክ! ;-( ;-( ;-( ከዛም ፀጥ አለብን
ይህ ወጣት እጁን ሂጄ ነካሁት ደረቱን ዳሰስኩት ምንም
የሚንቀሳቀስ ነገር የለም ይህ ወጣት ዱንያን ለቆ ወጥቶ ነበር
ሱብሀነላህ!
ብዙ አተኩሬ ይህን ወጣት ተመለከትኩት ከአይኔ እንባ መርገፍ
ጀመረ ጉዋደኛዬ እንደው መቆም አልቻለም ለቀቀው ማልቀስ
ጀመረ እንዲህ ብሎ ቁርዓን እየቀራ ሲሞት ሆስፒታልም
እንደደረስን ስለዚህ ወጣት ሁኔታ ያገኘነውን ሰው ሁሉ ስለ
ወጣቱ ነገርናቸው አብዛኛዎቹ በጣም ልባቸው ተነካ እንባቸው
መውረድ ጀመረ አንደኛው ታሪኩን እንደሰማ በጣም ተገረመና
ይሄን የአላህ ባሪያ ሄጄ ግንባሩን ነው የምስመው ብሎ ሳመው
አብዛኛዎቹ በቃ ከዚህ ከአላህ ባሪያ ላይ ሶላተል ጀናዛ
ሳንሰግድበት አንሄድም አሉ::
`
ከዛም ከሆስፒታሉ ሰራተኞች ውስጥ አንዱ ወደ ቤተሰቡ ደወለና
ወንድሙ መጣ:- ወንድሙ ነው ይሄን የሚቀጥለውን ታሪክ
የሚናገረው:- "ወንድሜ ሁሌ ሰኞ ሰኞ አንዲት ገጠር አካባቢ
አያቱ አለች እሷን ሊዘይራት ይመላለስ ነበር:: እዛች አገር
ውስጥ ያሉ ሚስኪኖችን የቲሞችን ባል የሞተባቸውን ሴቶችን
እየሄደ ይረዳቸው ነበር:: ያቺ ከተማ ወንድሜን ታውቀው ነበር::
ለዛች አገር ሰዎች ሁሌ ሰኞ ሰኞ ካሴቶች መፅሐፎችን እየወሰደ
እሱ ነበር የሚሰጣቸው::
ሁሌም ወደዛች ሀገር ሲሄድ መኪናው ውስጥ ሩዝ ስኩዋር
ምናምን ሞልቶ ነበር የሚሄደው ለችግረኞች እዛ ሊበትንላቸው
ማለት ነው:: ከረሜላ እንኩዋን ለዛች ሀገር ሕፃናቶች አይረሳም
ነበር:: ሁሌም ታዲያ ሰዎቹ አንተ የዚህን ያህል ጉዞ
ትመላለሳለህ እንዴ! ብለው ለሚተቹትና ሀሳብ ለሚሰጡት
ሰዎች እንዲህ ብሎ ይመልስላቸው ነበር:- " እኔኮ ወደዝች
ሀገር በመመላለሴ በረጅሙ ጉዞዬ ውስጥ ቁርዓንን ለመሐፈዝና
ቁርዓንን ሙራጃ ለማድረግ ለማስታወስ እጠቀምበታለሁ
የሚጠቅም ሸሪጦችን ሙሀደራ እሰማበታለሁ እንደኛ ሙዚቃ
ከፍቶ አይደለም የሚሄደው ይሄ ሁሉ ጎማዬ የሚሽከረከረው
መሽከርከር ከአላህ ዘንድ አጅር አኝበታለሁ ብዬ አምለናለሁ
ይለን ነበር::
እያለ ወንድምየው ነገረን:: ሱብሀን አላህ!!! ትራፊኩ ምን
ይላል:- ሀያቴ ልክ በማዕበል እንደምትናጥ መርከብ እዛ እዚ
እየዋተትኩ ነበር መዋለል ከሁሉ አቅጣጫ ወሮኝ ነበር አላህ
(ሱ.ወ) ን ከራቁት ውስጥ ነበርኩ ወጣቱን ቀብር ላይ ከተነው
በሰገድንበት ጊዜ እሱ የአኼራን የመጀመሪያን ቀን ሲገናኝ እኔ
የዱንያን የመጀመሪያዬን ቀን ተገናኘሁ ወደ አላሁ (ሱ.ወ)
ተመለስኩ አላሁ (ሱ.ወ) ያሳለፍኩትን ይምረኝ ዘንድ ይህንን
ወጣት አሟሟቱ እንዳሳመረው ሁሉ በኸይር ይወስደኝ ዘንድ
አላሁ(ሱ.ወ) እየተማፀንኩ ቶብቼ ተጸጽቼ የዱንያን
የመጀመሪያዬን ቀን ጀመርኩ ይላል::
" መጪው ዘመን በሚል ርዕስ ላይ ይህ ትራፊክ ነው ታሪኩን
የዘገበው እናቶቼ አባቶቼ እህቶቼ ወንድሞቼ ወላሂ የመጨረሻን
ሸሀዳ ማግኘት ከባድ ነው አሁን ምላሳችን ዚክር ያለመደ ከኾነ
ከቁርዓን ጋር ያልኖርን ከሆነ ያኔ ጣዕረሞት ላይ አይመጣልንም
ወላሂ !!! የቁሉላሁ (ተባረከ ወተዓላ) ፊ ሙህከሚ ተንዚሊህ:
- "አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ
ልፋትን ለፊ ነህ! ተገናኚውም ነህ!" ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ 6
ያ አላህ!!! ያ አረሕማን!!! ያ ዘልጅላሊ ወል ኢክራም!!! ያ
አርሀሙ ራሒሚን!!! አሟሟታችንን አሳምርልን!!! ኑሮአችንን
በኢባዳ ሞታችንን በሸሀዳ አድርግልን!!! አሚን!!! አላሁመ
አሚን!!!
ሼር ያድርጉ ለሌላውም ያስተላልፉ

Join 👇👇👇👇
t.me/hanunmedia
t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

30 Oct, 11:35


Enezin konjo konjo lip gloss ena lip mask mifelg inbox 💋 @Li34B

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

29 Oct, 14:15


የገባሁበት ታክሲ ሊሞላ የኋለኛው ወንበር ብቻ እንደቀረው አንዲት ልጅ ያዘለች ወጣትና ልትሸኛት የተከተለቻት ሌላ ሴት አብረው መጡ።ባለ ልጇ ጠጋ ብላ የኋላ ወንበር መሆኑን አይታ ተመለሰች።ወደኔ ዞር ብላ "ትቀይሪኛለሽ?"ስትለኝ፣ወደኋላ እየጠቆምኩ "እዛ ጋርኮ ቦታ አለ" አልኳት።ቆጣ ብላ "ልጅ ይዤ እንዴት ነው እዛ 'ምቀመጠው?አይታይሽም?...ለነገሩ ተሸፍነሻል እንዴት ይታይሻል?¡"አለችና ወደኋላ አለች።(ሶስተኛ ሰው ቢደርቡ ላይመቻት ይችላል፣ይበልጥ የሚሻላትም ያ ነው ብዬ ነበር እንደዛ ማለቴ)።ንግግሯ ሰውነቴን ቢነዝረኝም ፊቴን ከሷ አዞሬ የታክሲውን መሙላት ተጠባበቅኩ።ግን አላስቻለኝም።ምክንያቴን ሳልነግራት ባልፍ፣ከጥላቻዋ ሌላ ኒቃብ ያደረጉ እህቶችን በሙሉ ለሰው ባለማዘን ጎራ መመደቧ ነው ብዬ ወረድኩና ተጠጋኋት።...(ፋይዳ ላይኖረው ነገር!)
.
ገና ስታዬኝ<<ይኼው መውረድሽ ላልቀረው ነገር...እኔን አልቀይርም ብለሽ ይኼው ሌላ ሰው ገባ!ምን ዓይነቷ ናት?>>ድምጿን በእጅጉ ከፍ አድርጋ ተንጨረጨረች።

<<አልሰማሽኝም መሰለኝ እኔኮ ከኋላ ቦታ አለ ያልኩሽ...>>


<<ከኋላ!ከኋላ ይሄን ልጅ ይዤ እቀመጣለሁ?አታስቢም!ለነገሩ ስለተሸፈንሽ ነው!>>ደገመችው።ብዙ አወራች።

<<መጀመሪያ ይሄንን አስተሳሰብሽን አስተካክይ!ይሄንን መልበስ ሰውነትን እንጅ አዕምሮን አይጋርድም፤ማሰቢያን አይደፍንም።ራቅ ስላልሽ ድምፄ አልተሰማሽ ይሆናል እንጅ፣እኔ ያልኩሽ..>>አላስጨረሰችኝም።

<<እንደሚሸፍን፣እንደሚደፍንኮ አሳየሽኝ!አይደፍንም ትላለች...ይች...ኧረ ምኗ ናት!>>
.
ምንም ብላት ትርጉም አልባ መሆኑ ገባኝ።ላወራ አፌን ሳንቀሳቅስ በስድብ ትቀድመኛለች፣እኩል ባወራም ድምጿ ድምፄን ይውጠዋል።ትዕግስቴ ሲሟጠጥ

<<ይሄውልሽ እየሰማሽኝ አይደለም...በቅድሚያ ጥላቻሽን አስወግጅ፣ልብሱን ከሆነ አንቺ ዕድሜውን ይስጥሽ እንጅ መንገዱ ሁሉ እሱን በለበሱ ሰዎች ሚሞላበት ጊዜ ሩቅ አይደለም!>>ጮክ ብላ እጇን ወዲያና ወዲህ እያወናጨፈች ደጋግማ አማተበች።

<<ጭራሽ??!>>ደነፋች።ብዙ ጮኸች።

<<አዕምሮ ለመጋረዱ ደግሞ አሁንም ዕድሜውን ይስጥሽ እንጅ ተምረው የሚያክሙሽን፣ሀገርን...>> አሁንም አቋረጠችኝ።

<<ጭራሽ ሀገርንም?...የሚመሩሽን ልትይ ነው??>>ታቦቶቿን ጠራች።(መምራት ልል አልነበረም)።ከዚህ በላይ አንድ ቃል ማውጣት ጊዜዬን ማቃጠል ነው።ትቻት ሄድኩና ቀጣይ ታክሲ ውስጥ ገባሁ።
.
በሚያሳዝን ሁኔታ መንገዳችን አንድ ስለሆነ ጥቂት ቆይታ ገባችና ተቀመጠች።

<<የኛ የሀገር መሪም እዚህ ተቀምጣልኛለች¡>>

<<ሀገር በማሸረጥ የሚመመራ መሰላት?ሀገር በጭንቅላትና በጸሎት ነው ሚመራው>>
.
<<አወልቅላት ነበር ብትጠጋኝ!ከላይዋ ላይ እገፍላት ነበር>>
.
ድምጿን ከፍ አድርጋ እኔን ለጎሪጥ እያየች፣ሲላትም የታቦቶቿን ስም እየጠራች ስድቧን ቀጠለች።እኔ ግን ምንም ማለት አልፈለኩምና ዝምታን መረጥኩ።
.
<<ስላሸረጠች ሀገር ልትመራ?...አንሰማው ጉድ የለ!...ትኋናም!...በመሸፈን መሰላት?>>ሰው ሁሉ እየዞረ ያያታል(እንደጤነኛ አይመስለኝም ግን)
.
<<ተከራይ ብዬ ባኖረው፣ባለቤት ሊሆን አማረው አሉ¡ሃ...ሃ...ሃ>>
.
እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ።በጥላቻዋ ውስጥ እልፍ ጥላቻዎች፣በንቀቷ ውስጥ እልፍ መደፈሮች ታዩኝ።...ባለፈው አንዱ ሎንችን ውስጥ ልገባ "ወንበር አለ?"ብዬ መጠየቄን ሰምቶ "ወንበር ለተማረ ነው" ያለኝ ትዝ አለኝ።...ለወንድሜ ጉዳይ ትምህርት ቤት ሄጄ ጥበቃውን አቅጣጫ ስጠይቀው "ማንበብ ከቻልሽ የመምህራን ማረፊያ የሚል ተፅፎበታል" ያለኝም ታወሰኝ።
.
እንዲሁ እንደጮኸች መውረጃዬ ደርሶ ልወርድ ስነሳ፣
<<የኛ ሀገር መሪ ልትወርድ ነው። ደረሰች። ሀገር መሪያችን¡>> አለችኝ።
.
<<ሰላም!>>አልኳትና ወረድኩ።ሰማችኝና ለአፍታ ፀጥ አለች።እንባዬን ጠረኩና ጉዞዬን ቀጠልኩ።ድምጿ ግን ተከተለኝ...የዒምራን ሱራ ውስጥ ያለች አንዲት አያም በራሴው ድምፅ ትሰማኝ ጀመር።

***
لَتُبْلَوُنَّ فِي أَمْوَالِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ وَلَتَسْمَعُنَّ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ وَمِنَ الَّذِينَ أَشْرَكُوا أَذًى كَثِيرًا ۚ وَإِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ

በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ በእርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከእነዚያም ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትና ከእነዚያም ከአጋሩት ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፡፡ ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው፡፡
***
ከ ሌላ ቻናል የተኮረጀ

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

28 Oct, 18:17


ጥቁር ልብ🖤(እውነተኛ ታሪክ)

  
         ክፍል 10

ሌላኛው ቆጣ ብሎ አይ እንግዲ ስርአት ያዝ አሁን እንደዚህ ጠዋትና ምሽቱ ተምታቶባት ስትንከራተት እያየህ ስሜትህ እራሱ ይታዘዝልሀል ብሎ ይቆጣውና ከባለቤቴ አጠገብ ያሸሸዋል።

እሷም የሰዎቹ አጥር ስር ተደግፋ ስታለቅስ አድራ ሌሊት ዶሮ ሲጮህ ተነስታ ጉዞ ትጀምራለች።
እኔ እሷ ያንን ሁሉ ስታሳልፍ ቤት ተኝቼ ልጁ አለቀሰ እያልኩ ስበሳጭ ነበር ።
በገጠር ጡጦ የለ አልሰጠው እንዲህ እንዳለቀሰ ነጋለት ጠዋት ላይ እንቅልፍ ወሰደው እሷም ክሷን ጨርሳ ለሷ ተፈርዶላት በፀሀይ ያንን ተራራ ስትሮጥ ትወርዳለች።
እንደገባች ደሞ እኔ ለምን ልጁን ትተሽ ሄድሽ ሰዎቹ ልጅ እንዳለሽ ካወቁ ላንቺ አይፈርዱልሽም አንቺን አይፈልጉሽም አደል ብዬ ቁጣ ጀመርኩ ማታ ወጥታ ያጋጠማትን ስትነግረኝ ግን በራሴ አፍሬ አንገቴን ደፍቼ ከቤት ወጣሁ።

እኔ እንደሴት ቤት ተኝቼ እሷ እንደወንድ ስትሆን ሞራሌ ተነካ ሆድ ባሰኝ ።

ብቻ ህይወት ቀጠለ ልጃችንም አንድ አመት ሆነው መቼስ ቁንጅናው ማማሩ የገጠር ልጅ አይመስልም ነበር እኔ በልጅነቴ የነበረኝን መልክ የሚያስንቅ ነበር የሱ ደሞ።

በየመንገዱ ያገኘኝ ሰው ሁሉ ልጁ ግን ያንተ ነው ካንዱ ከተሜ ዲቃላ ወልዳ ባንተ አሳባ እንዳይሆን እሷ እንደሆነ ጎዳና ስታድር መስጠቱን ለምዳዋለች ይሉኝ ጀመር።
ሞኝ እንደመከሩት ሆኖቦኝ የምር እሷን መጠራጠር ጀመርኩ በሰበብ ባስባቡ እየተነሳሁ ልጁ የኔ አደለም ማለቱን ተያያዝኩት ጭራሽ ከቤት እየወጣሁ እመቤትጋ ማደር ጀመርኩ ።

እሷ ግን ከለቅሶ ውጪ ምቴድበትም ስላልነበራት ዝም ብላ ተቀመጠች።

እኔ ጭራሽ ይባስ ብዬ አዲስ አበባ እሄዳለሁ እዛ ቀን ስራ እየሰራሁ እኖራለሁ አልኩኝ እሷ በየሄድኩበት እየመጣች እባክህ መሬታችንን እያረስን ልጃችንን እናሳድግ አለች እኔ አሻፈረኝ አልኩ።

በእናትና አባቴ ተስፋ ስለቆረጥኩ አዲስ አበባ መጥቼስ ማንጋ አርፋለሁ ሴት አደለሁ ሰው ቤት አልገባ ብዬ ጨነቀኝ አባቴንም ካሁን ቡሀላ አልፈልገውም አንድ ቀን ልጄ ምን ላይ ወደክ ብሎኝ ሳያውቅ ዛሬ እሱን ፍለጋ አልንከራተትም እኔ እሱን ለማግኘት እንደሚከብደኝ ያውቃል እሱ ግን እኔን ማገኘት ከፈለገ ገጠር መምጣት ብቻ ነበር ሚጠበቅበት በቃኝ አልኩኝ።

በዚህ ጭንቀት ውስጥ እያለሁ ልጄ ታመመ አንገቱ መተነፍስ እስኪያቅተው አበጠ።
ሌሊቱንም መተንፈስ ይቸገራል አይተኛም አፉን ለደቂቃ መግጠም አይችልም ከገጠመው ታፍኖ ይሞታል።
ያንን ስሰማ እንደ እብድ አደረገኝ የማደርገው ጠፋኝ ወደ ህክምና ወሰድንው መፍትሄ የለውም ጎረቤት ሁሉም ተስፋ ቆረጠ የተለያየ ባህላዊ መድሀኒት ተሞከረ ሁሉም ሳይሆነ ቀረ ተስፋ ቆርጠን በቃ ሞተ አለ ሁሉም ሰው።

ሌሊትና ቀኑ እስኪምታታብን ድረስ ከጎኑ ቁጭ አልን ከዛ ግን  አጎቴ በጣም ጨንቆት ሌላ ሀገር ሄዶ የሚያቅ ሰው ይዞ መጣ ። በፈጣሪ እርዳታ የልጄ በሽታ ታወቀ አልቅት የምትባል ነገር አለች ጉሮሮ ላይ ተለጥፋ የምትቀር አታስተነፍስ አታስበላ አታስጠጣ ትክክለኛ መዳኒቷን ካላገኘች ከጉሮሮ አትንቀሳቀስም ተለጥፋ በየቀኑ እየገዘፈች እየገዘፈች ትሄዳለች።

ያ ሰውዬው ግን መዳኒቷን ያውቅ ነበርና አደረገለት ባንዴ ከጉሮሮው ተመንጭቃ ወጣች በጣም ትልቅ ናት በሱ እድሜ ይሄንን መቋቋሙ ሁሉም ሰው ተገረመ።

በዛ መሀል ሚስቴም ሰውነቷ ደካከመ አመመኝ አመመኝ አበዛች የገጠር ሰው በጣም ዝንጉ ስለሆነ ማርገዟን እራሱ አላወቀችም ነበር ።
ለካ ሁለተኛ ልጃችንን ካረገዘች በጣም ቆይታለች ጥርጣሬ ነበራት ግን ምታወራው ሰው አጥታ ነው ዝም ያለችኝ እንኳንም ጥያት አሌድኩ ብዬ ፈጣሪን አመሰገንኩ።

በድጋሜ  የእርሻ ወራት መጣ ያው የፈረደበትን አጎቴን ቦሮች ለምኜ እያረስኩኝ የባለቤቴ እንጀራ አባት መጥቶ አስቆመኝ መቼስ አንዴ ሀገሬው ላይ ፈሪ ተብሎ ስሙ የተነሳ ሰው በሁሉም የተናቀ ነው ።
ስንት አመት ስገብርበት የኖሮኩትን መሬት እናንተ አታርሱትም ፍታ ብሎ ከብቶቹን አስፈታኝ እሺ ብዬ እንደሴት ወደቤቴ ተመለስኩ ነገርኳት እያበደች ከቤት ወጥታ ሄዳ አስፈራራችው እሷ ወንድ እኔ ሴት ሆነን እኔ ፈርቼ ቤቴ ስመጣ እሷ ሄዳ ተጋፈጠችው።

እሱ እናንተ አታርሱትም እናትሽ ብትሞትም እኔም መብት አለኝ አለ።

እንደለመደችው ወደ ፍርድ ቤት ሄደች እርጉዝ ሆና ያንን ተራራ ተራራ ሳይመስላት ወጣችው ።
ከሰሰችው  ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት ተንከራተተች በድጋሜ እሱንም እረታችውና ለሷ ተፈረደላት እንደውም እስከዛሬ እሷ ጎዳና ላይ እየኖረች እሱ የሷን መሬት ለተጠቀመበት ካሳ እንዲከፍላት ተፈረደበት ባለቤቴ የሱን ምንም ነገር አልፈልግም አለች።

ከዛን ቡሀላ የሀገሬው ሰው በጀግንነቷ አደነቃት አንዳንዶች ክስ ሊካሰሱ ሲመጡ እሷን መጠየቅ ጀመሩ እናቷን,አጎቷን,እንጀራ አባቷን በክስ አሸንፋለችና ከሷ ብዙ ነገር እንማራለን ብለው ነበር አጠያየቃቸው ።

ብቻ ወንዱ ልጃችንን በማሳደግ ክንዷ ሳይጠነክር ሁለተኛ ልጃችንን ወለደች ምጧ ቀኑ ቀድሞ ይሁን ወይ ተራራው አድክሟት ተጎድታ አይታወቅም ግን ታመመች።
ልክ ልጃችን እንደተወለደች አሷ አልጋ ላይ ተዘረረች በደቂቃዎች ውስጥ ሰውነቷ እንዳለ ተነረተ በቃ ሞተች ተብሎ ሊጥ ተቦካ ሰወ ተሰበሰበ ህፃኗ ታለቅሳለች እንዲሁ እስክትሞት እየተባለ ከንፈሯ ላይ ቅቤ ያደርጉላት በገጠር እናት ጡቷ ካልፈነዳ ለህፃኗ ቅቤ እየተደረገ በህይወት እንድትቆይ ትደረጋለች ...

ይቀጥላል .... Like አንዳይረሳ 🥰

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

28 Oct, 04:56


#ኒቃብዋንም_ትለብሳለች።
ትምህርትዋንም_ ትማራለች።

~ኒቃብ ፊትን እንጂ አእምሮን አይሸፍንም !!.

#ኒቃብዋንም_ትለብሳለች።
ትምህርትዋንም_ ትማራለች።

ቻሌንጁን ተቀላቀሉ 🙏 share

@hanunmedia
@hanunmedia

https://t.me/hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

27 Oct, 16:44


የ ጥቁር ልብ like በጣም እየቀነሰ ነው.. እና ምን ማድረግ ይሻላል ማልቀስ ይሻላል ... 🙄ወይስ ማስነበቡን እናቁም እንዴ like እና share ሲደረግ ተቀባይነት እንዳገኘ እና እንደተመቻችሁ ነው የማስበው ሆ like ማድረግ ምኑ ነው ሚከብደው በ ረቢ 🫤

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

26 Oct, 19:29


ጥቁር ልብ🖤(እውነተኛ ታሪክ)

ክፍል 9

እንደምንም ደፈር ብዬ ፊቷን ለማየት ሞከርኩ ግን አቃተኝ።

ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ የአጎቴ ሚስት ምሳና ትንሽ አጥሚት ትንሽ ገንፎ እህል ይዛላት መጣች።

ከዛን ቀን ቡሀላም አንዳንድ ሰዎች ድግስ ሲኖራቸው የማርያም አራስ እያሉ ምግብ እየላኩላት እሱን ትቀምሳለች።

አንዳንዴ ከሷጋ ቁጭ ብዬ በረሀብ አንጀቴ ሲታጠፍ ሳይ እኔ ወንዱ ልጅ እንደዚህ ያቃተኝ የልጅ እናቷ ባለቤቴስ እንዴት ትሆን ይሆን እረሀቡን እንዴት ቻለችው ለዛውም እያጠባች እልና ተነስቼ እሄድና አልቅሼ እመለሳለሁ ።


ከግዝያት ቡሀላ እህል ሚሰበሰብበት ወቅት ደረሰ ተመስገን እንደሰው የራሳችንን እህል ዘርተን አጭደን ወቅተን ለመብላት በቃን ብለን ተደሰትን።

ያመርትነውን እህል ግማሹን አስቀምጠን ግማሹን ሸጥነውና በብሩ ጎጆ ቤት ሰራንበት ባለቤቴ ጉብዝናዋ ወደር አልነበረውም በገጠር ግርግይ የሚባል ነገር አለ በአዲስ አበባ እቃ መደርደሪያ ቡፌ እንደማለት ነው ቤታችንን በግርግይ ታስጌጠው ነበር ።
ቀስ በቀስስ ሰው ወደመሆን ጉዞ ጀመርን እሷም እንደሰው ልብስ መልበስ ከሰውጋ መግባባት ጀመረች ። እንደሰው ዘግተን ወጥተን ከፍተን ምንገባበት ቤት አገኘን።

ግን በዛ አልቆመም ነበር የኛ ስቃይ ድንገት ያባተበ ወንድም ተነሳና የያዝሽው መሬቱ የወንድሜ ነው ልቀቂ አላት እንግዲህ ጎዳና እያደረች በቀዳዳ ልብሷ ባልጠነከረ ጉልበቷ ተራራ እየወጣች ተካሳ ከናቷ ስትቀበል ዝም አሉና ልክ እሷ እህል አግኝታ ከመሬቱ መጠቀም ስትጀምር እሷን ከሰው መሬቷን ለመውሰድ መታገል ጀመሩ።

ይሄን ሁሉ የሚያደርጊት ለኔ ካላቸው ንቀት ነው ምክንያቱም በገጠር ወንድ ልጅ ሲከበር ሲፈራ አደለም ሚስቱን አደለም ልጆቹን የበሩን አጥር እንኳን ማንም አይነካበትም እኔን ግን አንዴ ፈሪ ነው ምንም አያረገንም ብለው ስላሰቡ እሷን ፍርድ ቤት ገተሯት ባለቤቴ የሴት ወንድ ስለሆነች ወገቧን አስራ በድጋሜ ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት መንከራተት ጀመረች።

ከኛ ቤት ፍርድ ቤት እስክትደርስ በእግራ የሶስት ሰአት መንገድ እየተጓዘች ነው ምትካሰሰው ።

በዛ መሀል የሷ አጎት(የሚከሳት ሰውዬ) ከኔጋ በጣም ለመቀራረብ ሞከረ እንደጓደኛ ሲያወራኝ ሲያሳስቀኝ በፈገግታ ተቀበልኩት እንጠጣ ሲለኝ አብሬው መጠጣት ማምሸት ጀመርኩ።

ከባለቤቴጋ ተካሰው ተካሰው የመጨረሻ የፍርዱ ቀን እንደነገ ሆኖ እንደዛሬ ጠራኝና አብረን መሸታ ቤት አመሸን ባለቤትህኮ ለመካሰስ ሳይሆን ፍርድ ቤት ካሉ ከተሜዎችጋ ለመጋደም ነው ምትሄደው አሉኝ።

ሞኝነቴ መገለጫዬ ሳይሆን አልቀረምና ቤት ገብቼ ነገ እግርሽን ወደፍርድ ቤት ብታነሺ ሰባብሬ ነው ምጥልሽ አልኳት ዛትኩባት አስፈራራኋት አንድ ቀን እንኳን የፍርድ ቤቱ በር በየቱጋ እንደሆነ ሳላቀው አንድ ቀን እንደወንድ ልከተልሽ ሳልላት በ16 አመቷ የሴት ወንድ ሆና ልጅ እያዘለች በተንከራተተች በምላሹ እሷን መጠርጠር ጀመርኩ።

እሷ ግን ሞቼ እገኛለሁ እንጂ በፍርዱ ቀን አልቀርም አለችኝ።
እኔ ደሞ አስቲ ትሄጃለሽ ብዬ ዝቼባት ተኛን ።
ለካ እሷ ልቧ እንደተሰቀለ ነበርና ትንሽ እንቅልፍ ወስዷት ሸለብ እንዳደረጋት በዛው የነጋባት መስሏት እኔ ሳልነሳም ቶሎ ለመውጣት አስባ ልጄን ካጠገቤ አስተኝታው ከቤት ወጥታ ትሄዳለች።


በዛ በጨረቃ በሌሊት ለመድረስ እያለች በጥድፊያ እየተራመደች ቀስ በቀስ ከመንደሩ ትርቃለች ባጋጣሚ ከዳገቱ በታች የሚኖሩ ማለትም ወደ ተራራው መውጣት ከመጀመሯ በፊት ትንሽዬ መንደር ነበረችና እሷጋ ስትደርስ ምንም ድምፅ ታጣለች።

እየፈራችም ቢሆን ወደፊት መራመዷን አላቆመችም ነበር።

አጋጣሚ ሆኖ እሷ እየተራመደች ሁለት ሽፍቶች ከፊት ለፊቷ ይመጣሉ ።
መጀመሪያ ማን እንደሆነች አስኪያውቁ ድረስ መሳሪያ ያነጣጥሩባታል እኔ ነኝ እኔ እያለች ስሟን እየጠራች ስትጮህ መሳሪያቸውን አውርደው ወደሷ ይቀርቡና በዛ ሰአት እዛ ምን እያደረገች እንደሆነ ይጠይቋታል የፍርድ ቤት ክስ እንዳለባትና በጠዋት ለመድረስ እንደፈለገች ትነግራቸዋለች።

አንድኛው በጣም እየተቆጣና እየጮኸ ታዲያ እንዴት በዚህ ሰአት ትወጫለሽ ይሄኮ የጅብና የሽፍታ ሰአት ነው ገናኮ ማታ ነው ምንስ ሰአት ምታይበት ባይኖርሽ ዶሮ እስኪጮህ አጠብቂም ብሎ ይቆጣታል። የነጋ መስሎኝኮ ነው ትላቸዋለች።

ለማንኛውም ወደቤትሽ ተመልሰሽ ዶሮ ሲጮህ ውጭ አሁን ገና ከምሽቱ አምስት ሰአት አካባቢ ነው ጨረቃዋ እንዳትሸውድሽ ብለው እነሱ ወደቤተሰቦቻቸው ቤት ለመግባት ይሰናዳሉ።( ሽፍታ በቀን አይሄድም በሌሊት ነው ቤተሰቦቹንና ልጆቹን ጠይቆ ወደጫካ ሚመለሰው)።

እሷ ግን ወደቤት ከተመለሰች እኔ አትሄጂም ብዬ እንደማስቀራት ስለምታውቅ እዛው መንደር ውስጥ አንዱን አጥር ደገፍ ብላ ለመተኛት ታስብና ጥጓን ትይዛለች ጎዳና ለሷ ብርቋ አደለም አደል።

ከዛ ግን አንድኛው ለምን አንደፍራትም እኛ እንደሆንን አንዴ ሸፍተናል ማን ይናገረናል በራችን ድረስ የመጣችልን ሲሳይኮ ናት ለምን ታልፈናለች ይለዋል...

ይቀጥላል ቻናሉን share እያደረጋችሁ

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

25 Oct, 18:07


👉 የጀናዛ ብልት ውስጥ እጇ አልወጣ ያለች ሴት!

  .........መዲና ውስጥ አንዲት ሴትዮ  ትሞትና ጀናዛዋ መታጠብ ይጀምራል በድንገት የአጣቢዋ ሴት  እጅ ከጀናዛው ብልት ጋር ተጣብቆ አልላቀቅም አለ መዲና ውስጥ ያሉ ኡለማዎች የአጣቢዋ እጅ ይቆረጥ ወይስ የጀናዛው ብልት በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገ ቡ  በዚህ ጊዜ ነበር ለእንግድነት ለመጡት ኢማሙ ማሊክ ይህ  ጥያቄ የቀረበው እሳቸውም ወደ አጣቢዋ በመዞር
.....see more

ውሸት አደለም ገብተዉ ሙሉውን ያንብቡት

    👇👇👇👇👇👇
       ሙሉውን ለማንበብ
     👆👆👆👆👆👆

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

25 Oct, 17:51


ጥቁር ልብ🖤(እውነተኛ ታሪክ)

ክፍል 8

ከሷ ማርገዝ በላይ ትልቁ አሳሳቢ ጉዳይ የእህል መሰብሰቢያ ወቅት እስኪደርስ ድረስ አርሰን ምንበላው በራሱ አለመኖሩ ነው።

እንዳረገዘችም ያወቅነው ቢያንስ አራት ወሯ ላይ ነበር።

አጨዳ የለ እርሻ የለ ተጨነቅን እኔ መልሼ መነገድ ጀመርኩ ባለቤቴ እኔ በሌለሁበት አዲስ አበባ መጥታ ሰው ቤት ገባች ሰውነቷ ሞላ ያለ ስለነበር ጭራሽ እርጉዝ እንደሆነች አታስታውቅም ነበር በወር 14 ብር ተቀጥራ ገባች ።
እኔ ከንግዱ ቦታ ስመለስ መሬት ብገባ ሰማይ ብወጣ ድራሿ ጠፋብኝ።

ከመሄዷ በፊት ግን ለእመቤት ነግራት ስለነበር እሷ የተፈጠረውን አጫወተችኝ ከዛሬ ነገ ትመጣለች እያልኩ ጠበኳት እንደቀልድ ሁለት ወር ሆናት ስልክ የለ አንደዋወል ።

ብቻ ከሁለት ወር ቡሀላ አለቃዋ አወቀችባት በዛ እድሜዋ ማርገዟ አስደንግጧት ከደሞዟ ላይ ሁለት ብር ጨምራ ሰላሳ ብር ሰጥታ ሸኘቻት።

ተመልሳ ወደገጠር መጣች ደስ አለኝ በሰራቸው ገንዘብ ለተወሰነ ጊዜ የሚያቆየንን ምግብ ሸማምታ ነበር ።

እሷ ለመውለድ እየተቃረበች እንደዛ ምታደርጋት እናቷ ታማ ሚያስታምማት አጥታ አልጋ ስር ሞታ ተገኘች ።
እናቷን ቀበረች። በዳይ ከመሬት በታች ተበዳይ ከመሬት በላይ ሆኑ።

እናቷ ከሞተች ቡሀላ መሬቱም ሚታረስበት ወቅት ነበር።

መሬቱ ሲገኝ እኛ ግን ምናርስበት በሬና ምንዘራው እህል እራሱ አልነበርንም አጎቴ እግር ላይ ወደኩና እባክህን ሰው እንድሆን አግዘኝ ከብቶችህን አበድረኝ አልኩት ምን ቸግሮኝ አንተ ምታርሰው ካገኘህ አለኝ አረስኩኝ ከዛ ደሞ እህሉ እስኪደርስ ሌላ መከራ።

በድጋሜ
ስትወልድ የምትበላው ይቸግራታል ብዬ ለመነገድ እራቅ ወዳለ አገር ሄድኩኝ።

(ሁሌም ቢሆን ከኛ ሀገር እራቅ ወዳለ ቦታ ሄደን ነው ምንሸምተው)

እኔ እንደሄድኩኝ ባለቤቴ ለካ ባዶ ቤት ሞትሽ ወይ ዳንሽ ወይ የሚላት ሰው በሌለበት ሀምሌ 22 ከቀኑ ሰባት ሰአት አካባቢ  ሳያማት ድንገት ምጧ ይመጣል
ወገቧን ቆረጥ ሲያደርጋት መደብ ላይ ጠጋ ትልና አረፍ ትላለች አረፍ ባለችበት ቅፅበት ልጁ ከሆዷ ለመውጣት ያጣድፋታል መቼስ ፈጣሪ ደግ አደል አንዲት ሴትዮ በኛ ቤት ጀርባ እያለፈች ወይኔ ብላ ስትጮህ ትሰማትና እሮጣ ትገባለች።

ስታያት ምጧ መጥቷል ሴትዮዋ ወደቤት በገባችበት ቅፅበት ባለቤቴ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ ዱብ ታደርጋለች የዛኔ እሷ 15 አመቷ ነበር።

ሴትዮዋም ከ ፈጣሪ ነውና የተላከችው የልጁን እትብት ቆርጣ ደሙን ጠርጋ መሬት ላይ ጨርቅ ደልድላ አንጥፋ ታስተኛትና ሰው ትጠራለች ።

በዛን ሰአት እመቤት ነበረች አብራት ያደረችው ።
ያላትን ከልጆቿ አፍ እየገመሰች አምጥታ እህል ያቀመሰቻትም እሷ ነበረች።

አጎቶቿ ዘመዶቿ ሞልተው በፈሰሱበት ሀገር ላይ አንዴ እናቷ ስትንቃትና ጎዳና ለጎዳና ስትንከራተት ስላዩ ብቻ ናቋት አንቋሸሿት ልጅ ነው ወይስ አውሬ የወለድሽው እንይልሽ ሳይሏት ቀሩ። በአራተኛው ቀን ሀገር አማን ብዬ ወደ ቤቴ ስመለስ ባለቤቴ ወልዳ ባዶ ቤት ተኝታ አገኘኋት።

አጎቴጋ ሄድኩኝ ባለቤቱን ሚስቴ እንደወለደችና ለአራስ የሚሆነኝነ ምግብ እንድታዘጋጅልኝ ለመንኳት በልውጫው እኔ ሸምቼ ከመጣሁት እህል እንደምሰጣት ነገርኳች እሺ አለችኝ።

በአጋጣሚ በነጋታው ደሞ የእመቤት ሴት ልጅ ታገባ ነበርና እሷጋ ሰርግ ቤት ሄድኩኝ ቀድሜ ምግብ ቋጥሬ ለባለቤቴ አምጥቼ ከሰጠኋት ቡሀላ እየተጣደፍኩ አራሷን ሚስቴን ትቼ ወደ ሰርጉጋ ሄድኩኝ እዛው ስጠጣ ሳስተናግድ ከሰዎችጋ ስሳሳቅ ጊዜ ምስኪኗን ሚስቴን እረሳኋት እዛው ሰክሬ ባዶ ቤት ትቻት አደርኩ ።

ስተቴ ሚጀምረው ከዛን ሌሊት አንስቶ ነው። ያደርኩት ከሌላ ሴትጋ ነበር ።

በነጋታው ከስካሬ ስነቃ ባለቤቴና ልጄ ትዝ አሉኝ እየተጣደፍኩ ወደ ጎጇችን አመራሁ።

አየኋት በአራስነቷ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች አገኘኋት ለልጁ ምታጠባው ጡት እራሱ ደርቆ ነበር።

ገና እንደገባሁ እየተንሰቀሰቀች ማታ በሌሊት ውሀ ጠምቷት እንደምንም ተነስታ ግቢ ውስጥ መሬት ላይ ከተጠራቀመው የዝናብ ውሀ ቀድታ እንደጠጣች ነገረችኝ።

ሳስበው ዘገነነኝ በር በሌለው ቤት መብራት በማያውቀው ከተማ አራስ ልጅ ይዛ ትን ቢላት ምትቀምሰው ውሀ ሳይኖር ትቻት ውጪ  ማደሬን ሳስብ ጭንቅላቴ በትክክል ስለመስራቱም ተጠራጠርኩ


ይቀጥላል.......

ታሪኩ በየቀኑ ይለቀቅ ወይስ አንድ ቀን አልፎ አንድ ቀን...? ሃሳብ ስጡኝ

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

25 Oct, 13:30


"የበደለሽን ተናገሪ ይላሉ "
የቅርቤ የሚላቸው ሰዎች ተሰብስበው...

አውቃለሁ!

"..ለማስታረቅ አይደለም ነውሩን ለመስማት
ጓጉተው እንጂ..."


ዝም........!


ተጣላን ብዬማ ከጠላቶቹጋ አላብርም ❤️‍🩹🥺

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

25 Oct, 04:56


እፈራዋለሁ‼️

ካደግንበት የጅህልና ማህበረሰብ ጋ ስንኖር ከነበረው ጊዜ እስካሁኗ ሰአት ድረስ ያለውን ስራየን አስታውስና የተቀደረልኝ ቢሆንም ሰበብ አድራሽ ነበርኩና ፍረሀት ውርር ያደርገኛለ

ان نفس لامارة بسوء
ነፍስ በመጥፎ አዛዥ ናት እንዳልከን በቃልህ ነፍሴ በአዘዘችኝ መጥፎ ነገር ተገፋፍቸ ላለፍኳቸው ሁዱዱክ ዋ የበርዘህ ህይወቴ እንደት ይሆን እላለሁ ግን እንደት ይሆን⁉️

እነዚያ ከጀነት ፍራፍሬ እየመጣላቸው ከሚመገቡት እሆን ወይስ ጧት ማታ ጀሀነም ከምትቀርብባቸው እልና እፈራለሁ😢

ግን እኮ እወድሀለሁ አላህየ የምር እወድሀለሁ

ኪታብህን ገልጨ ተፍሲር በቀራሁ ሰአት ስለጀሀነምህ ስቀራ ዋ እኔን ይቅር አልልም ብለህ ታስገባኝ ይሆን ብየ እጨነቅና

ስለ አዛኝነትህና ለቶበቱ ሰወች ይቅር ባይ እናም ጀነትህን እንዳዘጋጀህላቸው የነገርከንን ሳነብ እውነት አዝነህ ጀነትህ ታስገባኝ ይሆን ⁉️ እላለሁ
ወደ አንተ እንደተመለስኩና ፀፀቴም ጧት ማታ እንደሚያቃጥለኝ ታውቀዋለህ

ልክ በደለኛነቴን ረስቸ ጭንቅ ሲለኝ ከለሊቱ ፅልመት ውስጥ ከችግሬ እንድታወጣኝ ልነግርህ መጥቸ እልቅስ ስልብህ አውጣኝ ብየ የለመንኩህ እኔ ስታወጣኝ ጊዜ እኔ ነፍሷን የበደለች አንዷ ከንቱ ሰው ሁኘ ሳለ ዱአየን ሰማኸኝ እንደ እልሀለሁ ⁉️
ዱአየን ሰማኸኝ ወይ ብየ በመገረም በጥርጣሬ ብጠይቅም መልሸ አውጣኝ ብየ ሳለቅስብህ እንደምታወጣኝ እርግጠኛ ነበርኩ‼️

ምን ባደርግ ቁስሌ ይዳን ምን ባደርግ ጌታየ ምን ባደርግ

ምን ባደርግ ለተላለፈረኳቸው ድንበሮችህ መካሻ አገኝ ይሆን ምን ባደርግ⁉️

ድንበሬን አልፋለች ብለህ አልተውከኝም ደግመህ ደጋግመህ ሸፈንከኝ ምን ያክል አዛኝ እንደሆንክ አሳየኸኝ

ግን እየወደድኩህ የአሄራየን ጉዳይ እፈራዋለሁ አወ እፈራዋለሁ 😭

@hanunmedia
@Hanunmedia

https://t.me/+kmoHm6kd-wA5MTJk

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

24 Oct, 14:20


ምደባ ይፋ ሆነ‼️

የ2017 ዓ. ም የዪኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

🙅‍♂️የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር አያስተናግድም‼️


የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች👇

WEBSITE:
https://placement.ethernet.edu.et

TELEGRAM
https://t.me/moestudentbot


እምቢ ያላችሁ ልጆች የ service መጨናነቅ ስለሆነ ተረጋግታችሁ ሞክሩት
 
           

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

21 Oct, 18:12


Part 2

አባቴና ጓደኛዉ አብዱ ነበሩ። አርጅተዋል። አባቴ ዘሎ አቀፈኝ። ሳምኩት። አፉ በለኝ በስህተት ነዉ አለኝ።ቢልቂስ ዕዉነቱን አዉጥታለች።በጣም ታማ ሞት አፉፍ ላይ ነች። አጥፍቻለሁ ብሎ እግሬ ላይ ሊወድቅ ሲል ያዝኩት።አባዬ አይሆንም
ሁለታቹህንም አፉ ያልኩት ወዲያውኑ ነው። ግን አሁን ሌባ ልጅ እንደሌለህ በማወቅህ ደስ ብሎኛል አልኩት።
በሳምንቱ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተባቦሮን ሊሴፖሴ ሰቶኝ ከ25 ዓመታት በሃላ ካሳንችስን ለማየት በቅቻለሁ። በጣም ተለዉጣለች።
እናቴ ቢልቂስ ቀና ብላ ልታየኝ አልቻለችም። ዶክተሮች የወራት እድሜ ብቻ ነዉ ያላት ብለዋል። ሳምኳት። እቅፍ አድርጌ። አይዞሽ አባቴ ነግሮኛል ፡ ቂም አልያዝኩብሽም ፡ ምክንያቱንም ለማወቅ አልሻም አልካት።
በወራት ዉስጥ ትሞታለች የተባለችዉ አሁን 3 ዓመት አልፏታል፡ በህይወት አለች። እኔዉ ነኝ ከሰራተኛ ጋር የምካድማት።
አንድ ቀን ጥዋት ዱዓ አደረገችልኝና አንድ ነገር ልጠይቅህ አለችኝ። ጠይቂኝ አልኳት፤
እንዲህ በደዬህ ህይወትህ ምስቅልቅሉ ወጥቶ እንዴት ቻልከዉ አለችኝ።
አልሐምዱ ሊላህ እናቴ የፈለገዉ ነገር ቢደርስ ሰላትህን እንዳትተዉ ስላለችኝ፡ አባቴ ባባረኝ ማግስት አባኮራን ሰፈር ከጋደኛቼ ጋር አድረን አዉቶቢስ ከመሳፈራችን በፊት የሱብህ ሰላትን አንዋር መስጊድ ሰገድኩና ሼክ መሐመድ የሚባሉ ዓሊም ስለ ቀደር ከሰላት በኋላ አስተማሩ። ለ10 ደቂቃ ያህል ብቻ ሰምቼ ወጠሁ። ትምህርታቸውን ማሰላሰል ጀመርኩ። የደረሰብኝ የአላህ ትዕዛዝ መሆኑን ተቀበልኩ። ጌታዬ ፍትሐዊ ነህና ተቃውሞ የለኝም ብዬ ህይወቴን ቀጠልኩ። ከቁጣዬ ባነንኩ። ጡሩ ዒባዳ ሆኖልኛል። ለ25 ዓመታት ሳልቸገር ኖሬያለሁ። እከሌ በሞት ተለየኝ፡ የምወዳትን አጣሁ ፡ ትዳሬን በተኑት፡ ወዘተ ብለን ሀዘን ማብዛት ፡ቀደርን አለመቀበልን ያሳያል። አልሐምዱ ሊላህ ተቀብያለሁ።በመቀበሌም ነፃነት ይሰማኛል። የቁጣ እስረኛ አይደለሁም።
አስጠግዬ አብደልከሪም ከልጆቹ ሳይለየኝ ምንም ሳይጎልብኝ የቁጣና የተበዳይነት ሸክም ሳይጫነኝ ለዚህ በቅቻለሁ፡ አልሐምዱ ሊላህ አልኳት።
ከጋደኛዬ መሰለ ከኔ ተለይቶ አያዉቅም ስሙንም ከመሰለ ወደ ማህሙድ ለዉጧል። ወደአገር ከተመለሰ ሰንብቷል። አግብቷል በመባሉን ሰምቻለሁ። አድራሻቸውን እያፈላለኩ ነው።
አደፍርስ ወደ መጠጥና ሀሺሽ ዓለም ዝዉ ብሎ ገባ። መታሰር መታመም ሆነ ስራው። በሁለት ዓመት እድሜ ዉስጥ ዱንያን ለዘላለም በቁጣ ተወጥሮ ተለያት።
እኔ አልሐምዱ ሊላህ ወደቤተሰቤ ተመልሼ፡ አሁን እናቴ ቢልቂስ የጋሽ ዓብዱን የመጨረሻ ልጅ ካልዳርኩህ ሞቼ እገኛለሁ እያለች ነዉ።ልጅቷ ቆንጅዬ ነች።
ለማንኛዉም አልሐምዱ ሊላህ ።እናንተም አንባብያን አልሐምዱ ሊላህ በሉ፡ የአላህ ፀጋ ተቆጥሮ ኣያልቅምና። ከተሳሳትኩ ምከሩኝ።
ብሎናል ወንድማችን 🙏

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

20 Oct, 10:53


Part 1

አባቴ ከቤት አባረረኝ .....እናቴ አቻ የሌላት ሴት ነበረች።
ከአባቴ ጋር የነበራት ግንኙነት በጣም ጠንካራ ነዉ።
ምንም ነገር ሊለያያቸዉ አይችልም። ግን ምን ያደርጋል ሞት ለየን።

አባቴ ካለሷ መልበስ አያዉቅም። የትኛውን ከለር ከየትኛዉ ጫማና ከረቫት ሸሜዝ ጋር እንደሚሄድ የምትመርጥለት እሷ ነበረች።

ባጭሩ ዓይኑ ናት። ምን ማለት እንዳለበት እንኳን ስትመክረዉ ሰምቻለሁ።

ለናት አባቴ አንድ ብቸኛ ልጅ ስለነበርኩ አሞላቀዉ ነው ያሳደጉኝ።
የሷ መሞት በህይወታችን ላይ ከፍተኛ ክፍተት ፈጥሯል። ሁለታችንም በጣም ነዉ ከፍተኛ ቀዉስ ዉስጥ የገባነዉ።
ነገርግን የማይረሳ የለምና ቀስ በቀሰ ሀዘናችን እየቀዘቀዘ መጠ።
እኔን ለማጽናናት ላለማግባት ወስኗል። አገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም ያንሸራሽረኛል።ብዙ ቦታና የተለያዩ አገራት ሄደናል።
አብዛኛውን ግዜ ከኔ ጋር ነዉ የሚያሳልፈዉ።በዚህ ሁኔታ 3 ዓመታት አለፉ። ትዝ ይለኛል ያኔ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ነበርኩ።
ከቅርብ ጓደኛዉ ከጋሽ ዓብዱ ጋር ቁጭ ብዬ መከርኩ።

አባቴ ለኔ ብሎ በዚህ ሁኔታ በሀዘን ተዉጦ ህይወቱን ማሳለፍ የለበትም አልኩት። ሃሳቤን ተቀበለ።
አንድ ቀን አብረን አባቴን ከብዙ ጭቅጨቃ በኋላ አሳመንነዉ።

አንተ በደንብ አጥንተህ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከገባህ አገባለሁ አለኝ።
በደንብ ሌት ከቀን አጥንቼ እንቅልፍ አጥቼ የፈለገዉንና የተመኘዉን ዲፓርትመንት ባይሆንም የኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንትመትን ተቀላቀልኩ።

ሊያረሳሳኝ ሞከረ። ጓደኛዉን ጋሽ ዓብዱን ጠርቼ፡ የጠየከዉን ፈፅሟል ቃልህን መጠበቅ አለብህ አለዉ።

እሺ ማግባት ካለብኝ የማገባዉ እህትህን ቢልቂስን ነዉ። ከሰጠሀኝ ሲለዉ የጓደኛዉ  ፊት በፈገጋታ ተዋጠ።

እናቴ ቢልቂስ አግብታ የፈታች ሴት ናት። የ30 ዓመት ልጅ ነበረች።
በሳምንቱ በኒካህ ብቻ ቤተሰባችንን ተቀላቀለች።

አራት አመት የዱንያ ህይወት ሳይሆን የጀነት ኑሮ አሳለፍን። ሁለታችንም በጣም ወደድናት። ቀስ በቀስ ሙሉ በሙሉ የናቴን ቦታ ያዘች። ይገባታል።

አባቴ ለኔ የነበረው ፍቅር ጨመረ። የማይረሳ ህይወት ነበር።
እኔ ተመርቄ ስራ አጥቼ ለአንድ አመት ከጓደኞቼ ጋር መዋል ጀመርኩ።

ጫት እንቅማለን። አልፎ አልፎም በርጫ ላይ ከነሱ ጋር አመሻለሁ።
አንድ ቀን ጥዋት አባቴ ሰአቴን አላየህም ወይ ብሎ ጠየቀኝ።

ሌላ ቀን 3000 ብር ጠፋብኝ ብሎ ጮሀብኝ። በጣም ነዉ የገረመኝ። ምክንያቱም ከዚህ በላይ ገንዘብ ይሰጠኝ ነበር።

አንድ ቀን ጠዋት እናቴ ቢልቂስ ወርቄን ያስቀመጥኩበት ቦታ አጣሁት ስትለዉ ሰማኋት።

ብዙ ወርቅ ነበር ተንደርድሮ መጣ። አፋጠጠኝ አላየሁም አልኩት  መቃሜን ግን አመንኩኝ።
የዛን ቀን ከቤቴ ዉጣ አለኝ። ወጣሁ። አልተመለስኩም።
ሌባ መባል አልፈለኩም። አዲስ አበባን ከመሰል ጓደኞቼ፡ ከመሰለ እና ከአደፍርስ ጋር ከአገር ተሰደደን።
ሳምንት አልፈጀብኝም፡ እናቴን ቢልቂስንና አባቴን መሐመድ ይቅር ካልኳቸዉ። አፉ ካልኳቸዉ።

አሁን ከቤት ከተባረርኩ 25 አመታት አልፈዋል። ሱዳናዊው አስጠጊዬ በስም የሚፈልጉህ ሰዎች አሉ ብሎ ወደ ሱቁ አስጠራኝ።

ይቀጥላል.....

Like and share @hanunmedia
     
          @hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

17 Oct, 17:52


ጥቁር ልብ🖤( እውነተኛ ታሪክ)


ክፍል 7

አንድ ቀን ቆላ ውዬ እየተመለስኩ እናቷን አገኘኋት ና እስቲ አንተ ያቺ ዘረ ቢስ ልጅ እናንተጋ ናት አሉ ያቺ እመቤት ተብዬዋ ሴተኛ አዳሪ የማንንም ዲቃላ እየሰበሰበች ታኖራለች አደል ላንተ አልበቃ ብሎ ጭራሽ እሷንም ቀላቀለች ቆይ ግዴለም ዋጋችሁን ነው ምሰጣችሁ ብላ ዛተችብኝ።

መልስ ለመመለስ እራሱ አቃተኝ አውጥተሽ የጣልሻትን ልጅ መኖሪያ በሰጠቻት እንደዚህ መሳደብሽ ልክ ነው እናት አደለሽ እንዴ አንጀትሽ ከምንድነው የተሰራው አልኳት።

አይ እንግዲ እኔ እንደሷ አይነት ልጅ አልወለድኩም እናቷን ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት ምታንከራትት ልጅ ልጅ ትባላለች እንዴ ይቺ ሴጣን ስንቱን ሲወስድ ለሷ ቦታ አጥቶ ነው እስካሁን ያልገደላት አለችኝ።

አነጋገሯ አስገረመኝ ለኔ እናት ስገረም ጭራሽ የባሰም አለ እንዴ ብዬ አልፊያት ሄድኩ ቤት ስገባ መደብ ላይ ጭብጥ ብላ ተኝታ አየኋት ውስጤ ልውስ አለ አቃተኝ።

አጨዳ በቀን 5 ብር ነበር ምውለው ማሳው ታጭዶ እስኪያልቅ ድረስ 50 ብር ሞላልኝ 20 ብር  ለእመቤት ሰጠኋት በዛ ሰአት 20 ብር በጣም ብዙ ብር ነበር የቀረኝን ብር ይዤ ወደገበያ ወጣሁና ለልጅቷ ሜትር 12 ብር ነበር
2 ሜትር በ24 ብር ቀሚስ አሰፋሁላት ስታየው አበደች በደስታ ዘለለች ፍርድ ቤት ይሄንን የተቀዳደ ልብስ ለብሰሽ ስትሄጂ ይኑቅሻል ሀሳብሽንም አይሰሙሽም ቢያንስ ግን የተቀደደ ልብስ ካለበሽ ምን እንደምታወሪ ይሰሙሻል ያዝኑልሻል አልኳት አመሰገነችኝ ስትስቅ የፊቷ ብርሀን ያንፀባርቃል ።

ከዛን ቀን ቡሀላ ፍርድ ቤት ከእናቷጋ ልትካሰስ ስትወጣ እኔ እስከፍርድ ቤት  ማውጣት ጀመርኩ ።

በዛ ምክንያት እናቷ  ጥምድ አድርጋ ያዘችኝ በየጊዜው አንተንና እሷን አንድ ቀን አስደፋችኋለሁ እያለች ትዝትብኝ ጀመር።

ቀስ በቀስ እኔ እየወደድኳት መጣሁ ለምን እኔ አላገባሽም ቤት ባይኖረንም አንድ ቀን ይኖረን ይሆናል ብዬ ጠየኳት እንቢ አለችኝ

ቆይታ ስታስበው ግን ቢያንስ ብቸኝነቷን መርሳት ፈልጋ ነበርና እሺ አለችኝ።

ከዛ ለእመቤት ነገርናት እዛው ግቢዋ ውስጥ እቃ ምናምን ምታስቀምጥበት በር የሌለው ቤት ነበር እና እሷ ውስጥ መኖር ትችላላችሁ አለችን።

እሺ ብለን ባዶ እጃችንን እሷ ውስጥ ገባን እንጨት ሰብስቤ መጣሁና ለበሩ እንደመዝጊያ ሚሆነን ማታ ማታ ምናቆመው ጠዋት ጠዋት ደሞ አንስተን ወደጎን አድርገን ምናስቀምጠው በር ሰራሁለትና እመቤት ቡና አፍልታ አስገባችን የዛን ቀን አብረን አደርን ጎዳና ላይ ስታድር ብዙ ወንዶች ሊደፍሯት እና ትንሽ ትንሽ ገንዘብ እየሰጡ አብረዋት እንድታድር ይጠይቋት እንደነበር በምግብ ሁላ ካልደለልንሽ እንደሚሏት እሰማ ነበር ቢሆንም ግን እሷ እንቢ ባይ ነበረችና ከነ ክብረ ንፅህናዋ አገኘኋት።

የሀገሬው ሰው እንደተጋባን ሲሰማ መሳቂያ መሳለቂያ ቡና መጠጫ አደረጉን ለራሱ ሰው ቤት እየለመነ ጎኑን እያሳረፈ ጭራሽ ሌላ ዲቃላ ይጨምራል እንዴ እያሉ ያወሩብን ጀመር አጎቴ ይሄን ሲሰማ ተበሳጨ እንዴት ለራስህ ሳትሆን ሌላ ሸክም ትጨምራለህ ልጅ ይመጣል በምናችሁ ልታሳድጉት ነው አለኝ።

ችግር የለም እሱን አልኩት።

ምግብ ምንሰራበት እቃ እንኳን ስለሌለን ምንበላው ምንጠጣው እመቤትጋ ነው።

በዛ መሀል ባለቤቴ እንደዛ እየተንከራተተች ከናቷጋና ከእንጀራ ካባቷጋ እየተካሰሰች እያወቀ ሚፈርድላት ዳኛው አብረሽኝ እደሪና ነገውኑ ላንቺ ላስፈርድልሽ አላት ሚስቴ ሞቼ እገኛለሁ ብላ እንቢ አለች።

ከዛ በቃኝ ሳትል የበላዩጋ ሄዳ ከሰሰችው ፈጣሪ ከሷጋ ነበርና ተሳካላት።

አባቷ ሲሞት ያለውን መሬት እንዳለ በሷ ስም አስደርጎት ነበር እድሜዋ ስላልደረሰ እናቷ መሬቱን የማስተዳደር መብት ስለተሰጣት  ለካ በዛ ልክ ምታሳድዳትና ምትጠላት ስታድግ መሬቱን ከምትቀማኝ ቶሎ ሞታ በተገላገልኩ ብላ ኖሯል  ።

ያው ግን ፈጣሪ ከሷጋ ሆነና 4 የእርሻ መሬት 1 የጌሾ እርሻ እና አባቷ በህይወት እያለ ከቤታቸው ጀርባ በቆሎ እየዘራ ሚጠቀምበትን መሬት ሰጧት እናቷ እዛ መሬት ላይ ከረገጠች እንደምትታሰር አስጠነቀቋት ።

ከዛን ቡሀላ ከእመቤት ቤት ወጣንና በቆሎ ሚዘራበት የነበረው እርሻ ላይ በጨርቅ ጋርደን ቤት ሰራን አጎንብሰን እንገባለን አጎንብሰን እንወጣለን ።

ከእመቤት ቤት ጉልቻ ከአጎቴ ቤት ድስት ና ምጣድ ተሰጠን ግን እኛ ምንሰራው ሁላ አልነበረንም።

በዛ ሁላ መሀል ለካ እኛ ሳናውቅ ሚስቴ እርጉዝ ነበረች ።

Yketlal......

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

16 Oct, 03:54


«የተፈታች ሴት ምን አልባት እጅግ መልካምና ጥሩ ሚስት ሆና ሳለ በማይሆን ወንድ እጅ ወድቃ ይሆናልና ለ ተፈቱ እህቶቻችን ያለንን አመለካካከት ልናስተካከል ይገባል።»

አስቡበት 🙄 ደና ዋሉ 😊🫡
@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

15 Oct, 08:05


ጊዜው የውበት ነው ! እናንተን ለማስዋብ ደግሞ ለኛ ሀላፊነት ተሰጥቶናል። በዚህ በውበት አለም አምሮ ደምቆ ለመታየት እኛን ምርጫዎ ያድርጉ። የተለያዪ የመዋቢያ(ኮስሞቲክስ) እቃዎች ኦሪጅናል ሲፈልጉ እኛ ጋር ይገኛሉ።
☎️ 0923156651 ይደውሉ።
አድራሻ ፒያሳ ዳውን ታውን ህንፃ። በDelivery ያሉበት እናደርሳለን። contact @Abudibudi

Join the group

👇👇👇👇

https://t.me/+LaOKhMD2qCo4MzNk

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

15 Oct, 05:51


አንድ ሀብታም ሰው በመስኮቱ በኩል ሲመለከት አንድ ድሃ ሰው ከቆሻሻ ማስቀመጫው ውስጥ አንድ ነገር ሲመርጥ አየ ...
ኻሊቁ ይመስገን እኔ ድሃ አይደለሁም አለ።

ድሃው ሰው ዞር ብሎ ሲመለከት እርቃኑን ሰው በመንገድ ላይ ሲሄድ አየ ...
ጀሊሉ አመሰግናለሁ አላበድኩም አለ።

እብዱ ሰው ወደ ፊት ተመለከተና አንድ አምቡላንስ አንድ ታካሚ ይዞ  ሲሄድ ተመለከተ፡
ረቢዬ  ይመስገን አልታመምኩም አለ።

ከዚያ በሆስፒታል ውስጥ የታመመው ሰው የሞተ አስከሬን ወደ አስከሬኑ ማቆያ ሲወስዱት አየ...
አልሞትኩም አላህን አመሰግናለሁ አለ።

አላህን ማመስገን የማይችለው የሞተ ሰው ብቻ ነው

ስለ በረከቶችዎ ሁሉ እና ስለ ሕይወት ስጦታ ዛሬ አላህን አመስግኑ🙏

ሕይወት ምንድን ነው?
ህይወትን በተሻለ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብዎት

1. ሆስፒታል
2. እስር ቤት
3. የመቃብር ቦታ

በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና የበለጠ የሚያምር ነገር እንደሌለ ይረዳሉ።

በእስር ቤቱ ውስጥ ነፃነት በጣም ውድ ነገር መሆኑን ያያሉ።

በመቃብር ስፍራ ሕይወት ምንም ዋጋ እንደሌላት ትገነዘባለህ። ዛሬ የምንራመደው መሬት ነገ ጣራችን ይሆናል።

እውነት;

ሁላችንም ከምንም ጋር እንመጣለን እና ምንም ይዘን አንሄድም ... ስለዚህ እኛ ትሑት ሆነን ሁል ጊዜ ስለሁሉም ነገር አላህን አመስጋኝ እና አመስጋኝ እንሁን።


ስለ ሁሉም ነገር  አልሃምዱሊላህ ልንል  ይገባል
መልካም ቀን 🥰
@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

14 Oct, 13:13


I miss that day 🥺🤭😂

@Hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

14 Oct, 04:05


ልጃገረዶችን ያበላሻሉ ከዚያ ሷሊህ (ጥሩ) ሚስት
ይፈልጋሉ ሁለተኛዋ ላይ የምታገኛት ሚስትህ
የአንተው አይነት ስነ-ምግባር ያላት ነው የምትሆነው።

👌 #አብዛኛው #ወጣት ገርል ፍሬንድ ብሎ የያዛትን የዝሙት ጓደኛ በፍጹም አላገባም ይላል፣
👌 #የምልህ #ነገር ቢኖር የዝሙት ጓደኛህን ባታገባትም አንተ የምታገባት ሚስትህ የሌላ ሰው የዝሙት ጓደኛ እንደነበረች ቅንጣት ያህል አትጠራጠር፣

⭐️ #ከፈለግክ ይህንን የአሏህን ተባረከ ወተዐላ ቃል አንብብ"
{መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎቹ ወንዶች መጥፎዎቹም ወንዶች ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው"}

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

13 Oct, 16:12


.....አይናችን ለ ቅንድባችን ከሚቀርበው
በላይ ነፍሳችን ለ ሞት ቅርብ ናት 💔......
Sad Truth 😔😔

ኩሉ ነፍሲን ዛኢቀቱል መውት

@hanunmedia
@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

12 Oct, 18:22


ጥቁር ልብ🖤(እውነተኛ ታሪክ)


ክፍል 6

አንገቴና ሰውነት የተለያዩ መስሎኝ ነበር ወዲያው ከድገሱጋ ሚወጡ ሰዎች ሳቃስት ሰምተውኝ መጡና አፋፍሰው አነሱኝ ።

ያው ገጠር መኪና አንፖላንስ የሚባል ነገር ስሌለ በቃሬዛ ተሸክመው ወደ ሀኪም ቤት ወሰዱኝ በፈጣሪ ተአምር እንደምንም ተረፍኩኝ ያ ሰው ሁሉ ሚቀናበት ፁጉሬ ተላጨ ።

ከስንት ቀን የሆስፒታል ቆይታ ቡሀላ ወደ ቤት ተመለስኩ እሱም ከዛ ሀገር ጠፋ የህክምናውን ወጪ እንዳለ አጎቴ ነበር የሸፈነልኝ።

ወደ ቤት ከተመለስኩ ቡሀላም  እንደልቤ መንቀሳቀስ አልቻልኩም የጭንቅላቴ ቁስል አፉን እንደከፈተ ነበር።
እሱ እስኪሻለኝ ታማሚ ሆኜ እቤት መተኛት ነበረብኝ በዛን ሰአት ሃይ አጎቴ ወደራሱ ቤት ወስዶ አስታመመኝ ሚስቱ እንደልጇ ትኩስ ትኩሱን እያበላች እያጠጣች እስኪሻለኝ ድረስ ተንከባከበችኝ።

ትንሽ ሲሻለኝ ደሞ መልሶ ከአጎቴ ቤት ወጣሁና ወደ ምኖርባት ሴትዮ ቤት ተመለስኩ ።
እሷጋ እየኖርኩ የጠፋው ጓደኛዬ ተመልሶ መጥቶ ካልጨረስኩት እያለ እንደሆነ ሰማሁ ይገኝበታል ያልኩት ቧታ ሁሉ እየሄድኩ ፈለኩት ግን ላገኘው አልቻልኩም።

የሆነ ቀን ማታ ላይ  ቤት ቁጭ ብለን  ድንገት ከጓደኛውጋ ቤቱን ብርግድ አድርገው ገቡ ሴትዮዋ ልጆቼን ጨረሱብኝ አረ የሰው ያለህ ብላ ጮኸች
አፍሽን ዝጊ ብሎ በጥፊ ጣላት እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ የመጣ ፍርሀት ቢኖርብኝ የመኖር ያን ያህል ጉጉት ስላልነበረኝ ከፊት ለፊቱ ቆምክና እንደወንድ ልጅ ፊትለፊቶ ቆመህ መልስልኝ ሰዎችን ከመግደልህ በፊት ምክንያትህን ተናገር አልኩት ሳይመልስልኝ ገድሎኝ እንደሚሄድ መጠርጠሬ አልቀረም

አፍህን ዝጋ አንተ ዲቃላ ሰው ባደረኩህ ሁሉም ሲንቁህ ሲያገሉህ ካጠገቤ ባስጠጋህ ጭራሽ ላገባት የማስበውን ሴት ውሽሜዬ ካልሆንሽ እያልክ መውጫ መግበመያ ታሳጣታለህ ብሎ መሳሪያውን አቀባበለ።

እኔን አንዴ ገለኸኛል ግን ልንገርህ እኔ ላይ እጅህን ከመጠቆምህ በፊት ያንተ ሚስት ሴቷ ይሁዳ መሆኗን እወቅ።

እኔ አሁን ምልልሀለሁ

ፍም የመሰለው ፊቱ ትንሽ በረድ አለለት ማለት እና ፈጥራ ነው የነገረችህ እያልከኝ ነው አለ።

ልማልልህ አልኩት ቅደም አለኝ ቀደምኩኝ ማልኩለት ።

ወይኔ ጓዴ ምንም በማታቀው ነው ህይወትህን ላሳጣህ የነበረው ጓዴ ይቅር በለኝ ብሎ መሳሪያውን እንደያዘ እየሮጠ ሄደ።

በነጋታው አገሬው ለቅሶ ለመድረስ ይጠራራል ምንድነው ብዬ ጠየኳቸው።
ሞተችኮ ጓደኛህ እጮኛውን ገደላት አሉኝ
አብሬ እንደሰው ለቅሶ ላይ ዋልኩኝ ቀበረናት።

እሱም ከዛ ሀገር ጠፍቶ ወደሌላ ቦታ ተደበቀ አባቷ ወንድሟ ለመግደል እየፈለጉት ነበር።


ብቻ እኔም በደንብ ከህመሜ ሳገግም በድጋሜ እየዞርኩ መነገድ ጀመርኩ።

እዛ እኛ ከምንኖርበት ብዙም ሳይርቅ ቤተክርስቲያን ደጅ ላይ የምታድር አንድ ልጅ ነበረች በስሟ ቤት, ቦታ, መሬት, እያላት አባቷ ስለሞተ እነሱ ቀምተዋት እየኖሩበት እሷ ግን ጎዳና ላይ ነበር ምትኖረው።
ክስ ጀምራ ክሱን እስክታሸንፍ ድረስ ዘመድ አላስጠጋ ብሏት ቀን ለብሳ የዋለችውን ቀሚስ ማታ እንደብርድ ልብስ እየለበሰች ዛፍ ስር ነበር ምታድረው።

ሁሌ አያትና ታሳዝነኛለቸሰ ደሞኮ ቆንጆና ምታሳሳ ልጅ ናት ።

እኔ ስነግድ ሰንብቼ ስመለስ ባጋጣሚ እኛ ቤት ቡና ተሰብስበው እየጠጡ እሷም ጥጓን ይዛ ቁጭ ብላ ነበር ።

ለሁሉም ሰላምታ አቀረብኩላቸውና ያመጣሁላቸውን ሸንኮራ ሰጠኋቸው ስለምታሳዝነኝ ለሷ በዛ አደረኩላት።

እመቤት(የምኖርባት ሴትዮ) እርቧትኮ እራሷን ልትስት ደርሳ መንገድ ላይ ተቀምጣ ሳያት አሳዝናኝ ነው ወደቤት ይዣት የመጣሁት ይገርምሀል አባቷ ምን የመሰለ የተከበረ ሰው ነበር መሰለህ የዚህን አውራጃ ሚያስተዳድረው የሷ አባት ነበር ትንሸ ትልቁ ጎንበስ ቀና ሚልለት ሰው ነበር።

እሷንም አይቶ አይጠግባትም በጣም ነበር ሚወዳት ግን ሞት ክፉ ነው በክፉ ቀን ሞት ቀደመው ያቺ የተረገመች እናቷም ጎዳና ላይ አውጥታ ጣለቻት ይቺ ጨካኝ አለችኝ።


ከራሴ ህይወትጋ ተመሳሰለችብኝ አሳዝናኝ ዝም ብዬ አየኋት ተመልሳ ከዛፍ ስር ለማደር ሲመሻሽ ከቤት ወጣች ተከትያት ወጣሁና እኛጋ እደሪ ምንም አትልሽም እኔ አናግርልሻለሁ አልኳት።

እሺ ብላኝ ተመልሳ ገባች
ለእመቤት ታሳዝናለችኮ እኛጋ ትደር ስላት ሆዷን ከቻልክ እኔ አብራን ብትኖርስ ምን ቸገረኝ አለችኝ።

እሺ ችግር የለውም እኔ ከየትም ከየትም ብዬ ለሆዳችን መሆን አያቅተንም አልኳትና እኛጋ አደረች።

በቃ ከዛን ቀን ጀምሮ እኛጋ መኖር ጀመረች እኔ ለሰዎች እርሻ እያረስኩ እህል እያጨድኩ ገንዘብ ማገኘት ጀመርኩ።

ይቀጥላል.....

@hanunmedia

ሀኑን 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐌𝐄𝐃𝐈𝐀

10 Oct, 06:13


በተለይ ጉአደኞቼ ተጠንቀቁ አንዳትታፈሱ 😂😂😂

@hanunmedia