Commercial Bank of Ethiopia - Official @combankethofficial Channel on Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

@combankethofficial


Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1,940 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Promotional Article for Commercial Bank of Ethiopia - Official Telegram Channel (English)

The Commercial Bank of Ethiopia - Official Telegram channel, with the username @combankethofficial, is your go-to source for all things related to the leading bank in Ethiopia. Established in 1942, Commercial Bank of Ethiopia has been a pioneer in introducing modern banking services to the country. With over 1,940 branches spread across Ethiopia, this bank is dedicated to providing top-notch financial services to its customers.

By joining the Commercial Bank of Ethiopia - Official Telegram channel, you will gain access to exclusive updates, news, and information about the bank's services, promotions, and events. Whether you are a customer of the bank or simply interested in the banking industry in Ethiopia, this channel is the perfect platform to stay informed and engaged.

In addition to Telegram, you can also connect with Commercial Bank of Ethiopia on other social media platforms such as Facebook (www.facebook.com/combanketh) and Twitter (www.twitter.com/combankethiopia). These channels offer a more interactive experience and give you the opportunity to engage with the bank and other followers.

Don't miss out on the opportunity to stay connected with the leading bank in Ethiopia. Join the Commercial Bank of Ethiopia - Official Telegram channel today and be part of a thriving community of individuals who are passionate about modern banking and financial services in Ethiopia.

Commercial Bank of Ethiopia - Official

07 Dec, 09:24


በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖንሰርነት ከታላቁ ሩጫ ጋር በመተባበር በእንጦጦ ፓርክ በዛሬው ዕለት የተካሄደው የ5 ሺ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተጠናቋል
ENTOTO PARK CBE RUN

Commercial Bank of Ethiopia - Official

30 Nov, 08:59


ዛሬ ቅዳሜም አይደል?
ሸመታዎን በፖስ!
====
በግብይት እና በአገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳይጠበቅብዎ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የክፍያ መፈፀሚያ ማሽኖች (ፖስ) በመጠቀም
በካርድዎ በቀን እስከ 500 ሺ ብር ግብይት መፈፀም ይችላሉ፡፡

ነካ ከፈል፣ ኑሮዎን ቀለል!
****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #digitalbanking #pos #banking #ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

30 Nov, 08:36


National Competitive #Bid
==========

Commercial Bank of Ethiopia invites interested and qualified bidders/suppliers for the purchase of the following goods/service:

1. Construction Of CSOC Monitoring Room Facilities (Bid No. 96/2024/25).
Interested bidders can get the full information on our website using the following link:

https://combanketh.et/cbeapi/uploads/CSOC_file_7a493d0119.pdf

Commercial Bank of Ethiopia - Official

30 Nov, 06:11


እንዴት ያለካርድ ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ?

አይደንግጡ!
********
የኤቲኤም ካርድዎን ባይዙም አያሳስብም!
በሲቢኢ ብር አገልግሎት ከኤቲኤም ያለ ካርድ ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ፡፡
*******
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ለመጫን/ለማዘመን የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
ለአይፎን ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

Commercial Bank of Ethiopia - Official

30 Nov, 05:17


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Saturday, 30 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

29 Nov, 13:57


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሸናፊነቱ ቀጥሏል፡፡
**********

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ኢትዮ ኤሌክትሪክን የገጠመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ብርቱካን ገብረክርስቶስ (27') የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አሳርፋለች፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በውድድር አመቱ ያደረጋቸውን ሁለቱንም ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ እመቤት አዲሱ የጨዋታው ኮኮብ ሆና ተመርጣለች፡፡

Commercial Bank of Ethiopia - Official

29 Nov, 13:08


ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

29 Nov, 07:26


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የረጅም ግዜ አጋርነት እውቅና ሰጠ::
*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከባንኩ ጋር ለነበረው የረጅም ጊዜ ግንኙነት የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡

ባንኩ በቅርቡ ዩኒቨርሲቲውን ለመምራት በትምህርት ሚኒስቴር ለተመደቡት ተ/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ የመልካም ምኞት መግለጫም አቅርቧል::

የባንኩ ሀዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ወየሣ ጥላሁንና የዲስትሪክቱ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ተገኝተው እውቅናና መልካም ምኞታቸውን አቅርበዋል፡፡

በዚሁ ጊዜ አቶ ጥላሁን እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ለረጅም ግዜ በትብብር እየሰራ መቆየቱንና በተለይም የኢንተርኔት ባንኪንግ በመጠቀም ፈር ቀዳጅ ተቋም መሆኑን አስረድተዋል::

ባንኩ በቀጣይም ከዩኒቨርሲቲው ጋር የቆየውን ትብብር አጠናክሮ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ለተደረገላቸው የመልካም ምኞት መግለጫና ለዩኒቨርሲቲው ለተሰጠው እውቅና አመስግነው ባንኩ ወደፊትም በበርካታ የፋይናንስ አገልግሎቶች ዩኒቨርሲቲውን እንደሚያግዝ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል::

ፕሬዝዳንቱ በተለይም ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስገዝነት እያደረገ ባለው የሽግግር ሂደት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጠንካራ አጋር አድርጎ ለጋራ ተጠቃሚነት በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል::

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
https://twitter.com/combankethiopia
https://www.tiktok.com/@combankethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

29 Nov, 06:35


አሁንም ጉርሻ አለ!
*****

በኢትዮ ዳይሬክት (#EthioDirect) እና ካሽ ጎ (#CashGo) ከባህር ማዶ ገንዘብ ሲላክልዎ
ከዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን በተጨማሪ ጉርሻ ያገኛሉ!

#cbe #gift #moneytransfer #banking #ethiopia #forex #EthioDirect #CashGo
************
- የ EthioDirect መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• IOS፡ https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491

- የ CashGo መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US
• IOS: https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306

Commercial Bank of Ethiopia - Official

29 Nov, 04:51


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Friday, 29 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

28 Nov, 15:00


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያይቷል፡፡
*******

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት መርሀ ግብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን እና በኢትዮጵያ መድን መካከል የተደረገው ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል፡፡

አዲስ ግደይ (52'፣ ፍ) ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ረመዳን የሱፍ (12') ለኢትዮጵያ መድን ጎል ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

Commercial Bank of Ethiopia - Official

28 Nov, 09:38


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ግሬት ራን ጋር በመተባበር በእንጦጦ ፓርክ የሚደረገውን ወርሃዊ የሩጫ ውድድርን (ENTOTO PARK CBE RUN) ስፖንሰር አደረገ፡፡
• የመሮጫ ትኬቱ በሲቢኢ ብር ይቆረጣል።

******************
ባንካችን በስፓርቱ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ በማጠናከር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባደረገው ድጋፍ እና ታይትል ስፖንሰርነት በእንጦጦ ፓርክ የሚደረገው ወርሃዊ የሩጫ ውድድር ተተኪ ስፓርተኞችን እና ምርታማ ዜጋን ለማፍራት እንደሚያስችል ተገልጿል።

ጉዳዩን በማስመልከት ዛሬ በባንካችን ዋና መስሪያ ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አቶ ደረጄ ፉፋ እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች አንዱ የስፖርቱን ዘርፍ መደገፍ ነው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ባንካችን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ታላቁን ሩጫ ስፖንሰር ማድረግ እንደጀመረ አቶ ደረጄ ገልፀው፣ የዚሁ የታላቁ ሩጫ አካል የሆነው “እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ” ስፖንሰር ሲያደርግ በደስታ መሆኑን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) በበኩላቸው የዚህ ዓይነት ስፖርታዊ ውድድር ለነዋሪው መገናኛ መድረክ ለመፍጠር እና ጤናን ለመጠበቅ እንደሚረዳ ገልፀዋል፡፡

ውድድሩ በወር አንድ ጊዜ ሳይሆን በየሳምንቱ ቢደረግ ውጤታማነቱ የጎላ እንደሚሆን የገለፁት ዶ/ር ሂሩት፣ የአካባቢውን ቅርስነት ለማቆየት፣ ለከተማው ውበት እና የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ነው የተናገሩት።

ዶ/ር ሂሩት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ “ንቁ ፣ብቁ እና የይቻላል መንፈስን የያዘ ትውልድ” ለመፍጠር የያዘውን ርዕይ ለማሳካት እንደዚህ ዓይነት ውድድሮች በጣም ጠቀሜታ እንዳላቸው አክለው ገልፀዋል።

በእንጦጦ ፓርክ የሚካሄደው ይህ የሩጫ ውድድር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ወር በገባ የመጀመሪያው ቅዳሜ የሚደረግ የ5 ኪሜ ውድድር ሲሆን፣ በሚቀጥለው ቅዳሜ ኅዳር 28 ቀን 2017 የሚጀምር ሲሆን፣የመሳተፊያ ትኬት በሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ማግኘት እንሚቻል ታውቋል።

Commercial Bank of Ethiopia - Official

27 Nov, 08:41


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2024/25 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዐውደ ነዋይ መፅሔት ይፋ ሆኗል።
***************

👉🏾ከሞባይል መኒ እስከ አጠቃላዩ የዲጂታል ባንኪንግ ሥራዎች፤
👉🏾ከአበይት የባንካችን ክንውኖች እስከ ድል አድራጊው የስፖርት ማህበራችን ውጤቶችና
👉🏾ሌሎች ማህበራዊ ሃላፊነታችንን የተመለከቱ ስራዎቻችን
📖በዜና መፅሄት፣
📖 በአምድ ፅሁፍ እንዲሁም
📷 በምስል ተዳሰዋል።
ባንካችን በሩብ ዓመቱ ስላከናወናቸው አንኳር ጉዳዮች ለማወቅ ዲጂታል መፅሄታችን ጠቃሚ መረጃዎችን ታካፍላችኋለች።

ሊንኩን በመጫን ዲጂታል መፅሄታችንን ያግኛሉ።
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/First_Quarter_00bf4e4734.pdf

መልካም ንባብ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
https://twitter.com/combankethiopia
https://www.tiktok.com/@combankethiopia
https://www.facebook.com/combanketh

Commercial Bank of Ethiopia - Official

27 Nov, 06:35


ከወዲሁ ይዘጋጁ!
******

ትዳር አስበዋል?
መማርስ?
በአልዎን ድምቅ አድርገው ማሳለፍስ ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ ከወዲሁ ይዘጋጁ!
ውጥንዎን ለማሳካት በሚረዱና ባንካችን በሚሰጣቸው የቁጠባ አገልግሎቶች ይጠቀሙ!
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #ethiopia #banking #savings

Commercial Bank of Ethiopia - Official

27 Nov, 05:06


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Wednesday, 27 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

26 Nov, 12:43


እርስዎ ይበርቱ፣ እኛ እንሸልምዎታለን!
******

የሲቢኢ ብር ዋና ወኪል ወይም ወኪል ከሆኑ
የሲቢኢ ብር አገልግሎትዎን በማቀላጠፍ
መኪናን ጨምሮ የበርካታ አጓጊ ሽልማቶች ዕድለኛ ይሆናሉ!
******
የሽልማት መስፈርቱን እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Agent_and_Super_Agent_Reward_Criteria_53533f2f0a.pdf
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #cbebirr #agent #prize #banking #ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

26 Nov, 05:43


ማጂክ ፔይ!
አጠገብዎ ላለ ሰው በቀላሉ ገንዘብ መላክ ይችላሉ፡፡
ሲቢኢ ብር ፕላስ (CBEBirr Plus)
**
በማጂክ ፔይ አጠግብዎ ላለ ሰው ገንዘብ ለመላክ፡

• የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያዎ ላይ የሚገኘውን ማጂክ ፔይ (Magic Pay) ከፍተው ‘ላክ’ ‘Send’ የሚለውን ይምረጡ፣
• የገንዘብ መጠን አስገብተው ‘ማጂክ ኮድ ይፍጠሩ’ ‘Generate Magic Code’ የሚለውን ይጫኑና የሚስጥር ቁጥር ያስገቡ፣ የQR ኮድ ይመጣልዎታል፣
• ገንዘብ ተቀባዩ የራሱ ስልክ ላይ ወደ ማጂክ ፔይ በመግባት ‘ተቀበል’ ‘Receive’ የሚለውን መርጦ ላኪው ስልክ ላይ ያለውን የQR ኮድ ስካን ሲያደርግ ገንዘቡ ይደርሰዋል፡፡ አለቀ፡፡
***
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ይጫኑ/ያዘምኑ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#cbe #cbebirr #ethiopia #digitalbanking #banking #business

Commercial Bank of Ethiopia - Official

26 Nov, 04:56


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Tuesday, 26 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

25 Nov, 11:45


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያ ጨዋታውን ድል አድርጓል፡፡
**********

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ዛሬ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን 4፡00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ ንግስት በቀለ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ እና ታሪኳ ዴቢሶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ጎሎች አስቆጥረዋል።

የአምና ሻምፒዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጣይ በ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር የሚጫወት ይሆናል።

Commercial Bank of Ethiopia - Official

25 Nov, 11:10


አፍሪካን ይወቁ !
*********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘አልፋቤቲክ አፍሪካን ታይምላይን’ (Alphabetic African Timeline) ከተሰኘው ድርጅት ጋር የበይነ መረብ (online) የመጽሐፍት ግብይት ክፍያን በማቀላጠፍ አብሮ እየሠራ ይገኛል፡፡

አልፋቤቲክ አፍሪካን ታይምላይን https://africacomplete.org/ በተሰኘ ድረ-ገፅ በአፍሪካ ሀገራት ታሪክ፣ ባህል፣ ጥበብ፣ እምነት፣ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ላይ የሚያጠነጥኑ ፅሁፎችን በበይነ መረብ ለግብይት የሚያቀርብ ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱ እ.ኤ.አ በ2024 ድረ-ገፁ ላይ በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረግ ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ነጋዴዎች ፣ዲፕሎማቶች ስለ አፍሪካ የተጻፉ የምርምር ሥራ ጽሁፎችን በቀላሉ እንዲያገኙ ማድረግ ችሏል፡፡

በተጨማሪም "A to Z of AFRICA - General Information of African Nation States" የተሰኘ የኤሌክትሮኒክስ ካርታ በማዘጋጀትም ስለ አፍሪካ አጠቃላይ መረጃ ያቀርባል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከአልፋቤቲክ አፍሪካን ታይምላይን ጋር በገባው ስምምነት መሠረት የፅሁፎቹን ተደራሽነት ለመጨመር የኦንላይን ክፍያ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በድረ-ገፁ የሚገኙትን ፅሁፎች የማስተር ካርድ ወይም የቪዛ ካርድን ተጠቅሞ ክፍያ በመፈፀም መግዛት እንደሚቻል እንገልፃለን፡፡

አልፋቤቲክ አፍሪካን ታይም ላይን በዋነኛነት የአፍሪካ አሀጉርን ለማስተዋወቅ እየሠራ የሚገኝ የሚዲያ ተቋም ሲሆን፤ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተቋም የሙያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው እና ከልዩ ልዩ መንግስታዊ ተቋማት ፈቃድና እውቅና ያገኘ ነው፡፡
Alphabetic African Timeline (https://africacomplete.org/)

Commercial Bank of Ethiopia - Official

25 Nov, 06:36


በጭማሪ ይንበሽበሹ!
*******

ከባህር ማዶ በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ ከባንካችን ሲቀበሉ፣ በኢትዮ ዳይሬክት (#EthioDirect) እና ካሽ ጎ (#CashGo) ገንዘብ ሲላክልዎ በጭማሪ ይንበሸበሻሉ!
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #moneytransfer #banking #ethiopia #forex #gift #EthioDirect #CashGo

Commercial Bank of Ethiopia - Official

25 Nov, 04:58


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Monday, 25 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

23 Nov, 09:46


ለክቡራን የባንካችን ደንበኞች
*****
ባንካችን የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ በሚያደርግበት ወቅት ለክቡራን ደንበኞቹ ቀደም ብሎ እንደሚያሳውቅ ይታወቃል።

በዚህ መሠረት ባንካችን በሚሰጣቸው የብድር፣ የቅርንጫፍ እና የዲጂታል፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች ላይ በቅርቡ የብድር ወለድ እና የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ የሚያደርግ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን እናሳውቃለን።
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

23 Nov, 08:53


የሰው ልጅ ጨረቃን ሳይረግጥ
*********

ቀደምት ነን...........
ፈር ቀዳጅ
ዓለም የደርሰበትን በማስተዋወቅ
በከፍታ ላይ ከፍታን ደርበን
ጊዜ ሳይገድበን በመሪነት የምንጓዝ
የወገን አለኝታ
በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገት አሻራችን ጉልህ
********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #pioneer #banking #ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

23 Nov, 06:43


ነገን ዛሬ ይሥሩ!
ዛሬ ሲቆጥቡ፣ ነገ የተሻለ ይሆናል!
****
ዕቅድዎን ለማሳካት የሚረዱ በርካታ የቁጠባ አማራጮች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኛሉ!
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #ethiopia #banking #savings

Commercial Bank of Ethiopia - Official

23 Nov, 05:25


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Saturday, 23 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

22 Nov, 13:47


https://t.me/combankethofficial/6785
ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ በአግባቡ ሊተገብሯቸው የሚገቡ
የጥንቃቄ እርምጃዎች፡፡
=========

ደንበኞች እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ኤቲኤም፣ ፖስ፣ ሲቢኢ ብር የመሳሰሉ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚከተሉትን የደህንንት መጠበቂያ ተግባራት ሊተገብሩ ይገባል፡

• የሚስጢር ቁጥርዎን በስልክዎ ውስጥ አለማስቀመጥ፣ በወረቀት ወይም በማስታወሻ ደብተር ላይ አለመፃፍ እና በአጠቃላይ ለሌላ ሰው አለማሳየት ወይም በቀላሉ በሚታይበት ቦታ ላይ አያስቀምጡ፤
• የተንቀሳቃሽ ስልክዎን በተቻለ መጠን ለሌላ ሰው አይስጡ (አያውሱ)፡፡ ነገር ግን ለሌላ ሰው የሚሰጡ ወይም የሚቀይሩ ከሆነ ግን ስልኩ ላይ ያለውን የየዲጂታል ባንክ አገልግሎት መጠቀሚያ መተግበሪያ እና ሌሎች የግል መረጃዎን የያዙ ጽሑፎችንና ኢሜሎችን ያጥፉ፤
• የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ በሚያደርጉት ነገር ላይ ብቻ ያተኩሩ፤ ትኩረትዎን የሚያስተጓጉሉ እንደ ሞባይል ስልክ እና መሰል ነገሮቸን አይጠቀሙ፤
• የኤቲኤም ማሽን ላይ ሲጠቀሙ የሚስጢር ቁጥርዎ እንዳይታይ፤ የኤቲኤም ቁልፍ ሰሌዳውን ሰውነትዎን ተጠቅመው በመሸፈን በቅርብ የቆሙ ሰዎች እንይመለከቱ ይከላከሉ፣ ከግብይት በኋላ ካርዱን መቀበሎን ያረጋግጡ፤
• የተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ የሚጭኗቸውን መተግበሪያዎች ሲያወርዱ አፕስቶር እና ፕሌይስቶርን ብቻ ይጠቀሙ፤
• ደኅንነቱ ያልተረጋገጠ ድረ-ገጽ እና የማኅበራ ሚዲያ ገፆችን አይጠቀሙ፣ አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን (links) አይክፈቱ፤
• ግብይትዎን በሚያካሂዱበት ጊዜ ችግር ቢያጋጥምዎ ከሚመለከታችው የባንኩ ሠራተኞች ውጪ የማንንም እገዛ አይጠይቁ፤
• የሚስጢር ቁጥርዎን በየጊዜው ይቀያይሩ፤
• ተከታታይ የሆኑ ወይም የስልክ ቁጥርዎን የመጨረሻ ዲጂቶች፣ ማንኛውም የግል መረጃ ለምሳሌ የልደት ቀን የሚስጥር ቁጥር አድርገው አይጠቀሙ፤
• በስልክ ምንም አይነት የባንክ መረጃዎን አይስጡ፣
• ሞባይል ሲጠፋብዎ ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እንዲቋረጥ ያስደርጉ፤
• የሚጠቀሙበት ኮምፒዩተር ሁሌም የቫይረስ መከላከያ እንዳለው ያረጋግጡ፤
• ሂሳብዎ ላይ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲኖር ለባንኩ ወዲያውኑ ያሳውቁ፤
• የባንክ አገልግሎት በሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮች እና ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የማይታወቁ መተግበሪያዎችን አይጫኑ፤
• አገልግሎት ካገኙ በኋላ አስፈላጊውን ቅደም ተከተል በመከተል ዘግተው ይውጡ፡፡

Commercial Bank of Ethiopia - Official

22 Nov, 13:24


#ዜና
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቼሻየር ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠውን ድጋፍ እያገዘ ነው፡፡
• የባንኩ ሠራተኞች ቼሻየር ኢትዮጵያን ለ46ኛ ጊዜ ባደረገው የእግር ጉዞ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
https://youtu.be/WCBInUhOsu8

Commercial Bank of Ethiopia - Official

22 Nov, 11:32


ኃላፊነትዎን በሲቢኢ ብር ፕላስ ያቅሉ!
******

ክፍያ ሲሆን ጉዳይዎ
ኃላፊነቱን ለሲቢኢ ብር ፕላስ ይስጡ....
ባሉበት ምቾትዎ ተጠብቆ፣ እንዳይረሱ አስታውሶ
ፍጥነት በማጂክ ፔይ፣ ካለቀም ከባንክ ሂሳብ
ክፍያ በሲቢኢ ብር ፕላስ፣ ቅልል ዝምን ብሏል!
******
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎን ያዘምኑ/ ይጫኑ!

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

Commercial Bank of Ethiopia - Official

22 Nov, 06:31


እየቆጠቡ ንያዎትን ያሳኩ!
======

ሐጅ / ኡምራ የማድረግ ንያዎትን በለበይክ የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት
በመቆጠብ እውን ያድርጉ!

እንደምርጫዎ በለበይክ ወዲዓህ የቁጠባ ሂሳብ፣ ወይም
ከትርፍ ላይ 70 በመቶ በሚያጋራው ሙዷራባህ ለበይክ
የቁጠባ ሂሳብ መጠቀም ይችላሉ፡፡
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#CBE #cbenoor #interestfree #saving #mudarabah #wadiah #lebbeyk

Commercial Bank of Ethiopia - Official

22 Nov, 05:04


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Friday, 22 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

21 Nov, 15:02


#ዜና
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን የሥራ ፈጠራ ሀሳቦችን መደገፉን እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ፡፡
• ባንኩ የነጋድራስ የንግድ ሥራ ፈጠራ ውድድር የቴሌቪዥን ፕሮግራምን በገንዘብ ለማገዝ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት አድርጓል፡፡
https://youtu.be/Pf5Kg2ovU28

Commercial Bank of Ethiopia - Official

21 Nov, 11:15


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለፋና ብሮደካስቲንግ ኮርፖሬት 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ፡፡
***
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኃላፊዎችንና ሠራተኞችን እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልዕክታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው አስረክበዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አቶ አልሰን አሰፋ ፋና ራዲዮ ከሰላሳ ዓመት በፊት በ1987 ዓመተ ምህረት አዲስና ማራኪ አቀራረብ ይዞ ስራ መጀመሩን፣ የፕሮግራም ይዘቱን እያሻሻለና እያዘመነ በመምጣቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅና ተመራጭ ሚዲያ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

አቶ አልሰን አክለዉም የኢትየጵያ ንግድ ባንክ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ማስታወቂያ ከማስነገር ባለፈ ስትራቴጅክ አጋር ሆኖ እየሰራ እንደሚገኝና የሥራ ግንኙነትና አጋርነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ባንኩ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው በበኩላቸዉ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላስተላለፈዉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አመስግነዉ፤ "በኢትዮጵያ የባንክ ኢንደስትሪ ቀዳሚ ከሆነዉ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ስንሰራ ቆይተናል፤ ወደፊትም አጠናክረን አብሬን እንሰራለን" ብለዋል፡፡
ተቋማቸዉ ወደፊት በአዳዲስ ይዘቶችና አቀራረብ ከባንኩ ጋር በስፋት እንደሚሰራም ዋና ሥራ አስፈፃሚው አረጋግጠዋል፡፡

https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
https://www.linkedin.com/company/commercialbankofethiopia
https://twitter.com/combankethiopia
https://www.tiktok.com/@combankethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

21 Nov, 08:11


ይቀበሉ፤ ተጨማሪ ያግኙ!!
*******

ከባህር ማዶ በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ ከባንካችን ሲቀበሉ
ከዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን የበለጠ ያገኛሉ!
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #moneytransfer #banking #ethiopia #forex

Commercial Bank of Ethiopia - Official

21 Nov, 05:25


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Thursday, 21 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

20 Nov, 11:18


የይለፍ ቃልዎን ያጠናክሩ!
*******

እስከ አስር አሀዝ በመጠቀም
የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የይለፍ ቃልዎን ያጠናክሩ!
#cbe #mobilebanking #digitalbanking #banking #ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

20 Nov, 05:40


በስልክዎ ዕቁብ ይጣሉ!
==========
ውጥንዎን ለማሳካት ዕቁብ መጣል ሲሹ ሳይወጡ ሳይወርዱ በዲጂታል ዕቁብ (Digital Equb) በሚፈልጉት አማራጭ በስልክዎ ዕቁብ መጣል ይችላሉ፡፡

የዲጂታል ዕቁብ መተግበሪያን በሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ሚኒ አፕስ ላይ ያገኙታል፡፡

በቀላሉ ተመዝግበው የመረጡትን የዕቁብ አማራጭ ይቀላቀሉ፡፡
#CBE #cbebirr #apps #digitalbanking #digitalequb
*************
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት ሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ያውርዱ
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

Commercial Bank of Ethiopia - Official

20 Nov, 04:52


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Wednesday, 20 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

19 Nov, 15:05


#ዜና
በኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥ ምርት እድገት የዲጂታል ኢኮኖሚው ከፈተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገለጸ፡፡
**********
#GSM የተባለ ተቋም የተንቀሳቃሰ የእጅ ስልኮች በዲጂታል የገንዘብ እንቅስቃሴ ላይ ሊኖራቸው የሚችለውን ሚና መሰረት አድርጓ ባደረገው ጥናት እንደገለፀው፣ በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2028 የዲጂታል ኢኮኖሚው ለሀገር ውስጥ ምርት እድገት የ1.3 ትሪሊየን ብር አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
https://youtu.be/6VjCNAB-bJ0

Commercial Bank of Ethiopia - Official

19 Nov, 05:28


ለሽልማት እየተዘጋጁ ነው?
******

የሲቢኢ ብር ዋና ወኪል ወይም ወኪል ከሆኑ
የሲቢኢ ብር አገልግሎትዎን በማቀላጠፍ
መኪናን ጨምሮ የበርካታ አጓጊ ሽልማቶች ዕድለኛ ይሆናሉ!
******
የሽልማት መስፈርቱን እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Agent_and_Super_Agent_Reward_Criteria_53533f2f0a.pdf
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #cbebirr #agent #prize #banking #ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

19 Nov, 04:44


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Tuesday, 19 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

18 Nov, 10:01


የቁጠባ መዳረሻ ስኬት ነው!
******

ዕቅድዎን ለማሳካት የሚረዱ በርካታ የቁጠባ አማራጮች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኛሉ!
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #ethiopia #banking #savings

Commercial Bank of Ethiopia - Official

18 Nov, 08:20


የሳይበር ደህንነት ወርን በማስመልከት የተደረገ ቆይታ
**********

5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት አንድ እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ወሩን በልዩ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች አክብሯል፡፡

ከሳይበር ደህንነት ወር ጋር በተያያዘ የባንካችን ቴሌቪዥን ዝግጅት ክፍል ከባንኩ የመረጃ ሥርዓት ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ስዩም ዳምጠው ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

በቆይታው ፡

• የመረጃ ሥርዓት ደህንነት ምን ማለት ነው?
• ባንካችን የደንበኞችን መረጃ እንዲሁም የዲጂታል አገልግሎቶቹን ደህንነት የተጠበቀ ለማድረግ ምን በመሥራት ላይ ይገኛል?
• ከዲጂታል አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ መጭበርበሮችን ለመከላከል ከደንበኞች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል?
የሚሉ እና ሌሎች ጉዳዮችም ተዳሰውበታል፡፡ እንዲከታተሉት ጋብዘናል፡፡
https://youtu.be/Lyyj1IFG_1Y

Commercial Bank of Ethiopia - Official

18 Nov, 06:13


የኮንዶሚኒየም ክፍያዎን በሲቢኢ ብር ፕላስ ይፈፅሙ!
****

የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ የኮንዶሚኒየም ክፍያዎን በቀላሉ መፈፀም የሚያስችል የአገልግሎት አማራጭ ይዟል፡፡
****
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ይጫኑ/ያዘምኑ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች : https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች : https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#cbe #cbebirr #ethiopia #digitalbanking #banking #business #fuel #payment

Commercial Bank of Ethiopia - Official

18 Nov, 05:01


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Monday, 18 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

16 Nov, 09:01


ነዳጅዎን በሲቢኢ ብር ፕላስ በቀላሉ ቀድተው
በሰላም ይጓዙ!
****
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ተጠቅመው
ከሲቢኢ ብር ሂሳብዎ ወይም ከባንክ ሂሳብዎ ጋር በማገናኘት በቀላሉ የነዳጅ ክፍያዎን መፈፀም ይችላሉ፡፡
****
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ይጫኑ/ያዘምኑ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች : https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች : https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#cbe #cbebirr #ethiopia #digitalbanking #banking #business #fuel #payment

Commercial Bank of Ethiopia - Official

16 Nov, 06:51


ጉብኝት በዓቢይ ቅርንጫፍ
ክፍል 3

******
በዛሬው የዓቢይ ቅርንጫፍ ጉብኝታችን ቅርንጫፉ ከያዛቸው ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ ቴክኖሎጂዎች መካከል አንዱ የሆነውን ገንዘብ ገቢና ወጪ ማድረጊያ ኤቲኤም ማሺን (Cash Recycler ATM) እንመለከታለን::

ዓቢይ ቅርንጫፍ በባንካችን አዲሱ የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ሥር ይገኛል፡፡ ይገልገሉበት!
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #commercialbankofethiopia #facts #MainBranch #banking #Ethiopia

https://youtu.be/3m2VpNejaGs

Commercial Bank of Ethiopia - Official

16 Nov, 05:52


ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ !
*****

በኢትዮ ዳይሬክት (#EthioDirect) እና ካሽ ጎ (#CashGo) ከባህር ማዶ ገንዘብ ሲላክልዎ
ከዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን በተጨማሪ ጉርሻ ያገኛሉ!

#cbe #gift #moneytransfer #banking #ethiopia #forex #EthioDirect #CashGo
************
- የ EthioDirect መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• IOS፡ https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491

- የ CashGo መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US
• IOS: https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306

Commercial Bank of Ethiopia - Official

16 Nov, 05:00


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Saturday, 16 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

15 Nov, 10:01


ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ አዲስ አገልግሎት መቅረብ ጀምሯል!
ምስሉን በማጫወት ስለአገልግሎቱ ይረዱ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
https://www.linkedin.com/company/commercialbankofethiopia
https://twitter.com/combankethiopia
https://www.tiktok.com/@combankethiopia
https://www.facebook.com/combanketh

Commercial Bank of Ethiopia - Official

15 Nov, 06:00


የኤቲኤም ካርድዎን ረስተው ቢወጡና ገንዘብ ለአስቸኳይ ጉዳይ ቢያስፈልግዎ ምን ያደርጋሉ?
******

መፍትሄ አለው!
የሲቢኢ ብር አገልግሎትን በመጠቀም
ያለካርድ ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ!
=======
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ለመጫን/ለማዘመን የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
ለአይፎን ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

Commercial Bank of Ethiopia - Official

15 Nov, 04:47


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Friday, 15 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

14 Nov, 13:10


ጉብኝት በዓቢይ ቅርንጫፍ
ክፍል 2
******

እጅግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና አሠራር የተደራጀውን ዓቢይ ቅርንጫፍ እያስጎበኘናችሁ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በክፍል 1 ጉብኝታችን የዓቢይ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ስለቅርንጫፉ የሰጡትን አጠቃላይ ገለፃ ተከታትለናል፡፡

ዛሬ ቅርንጫፉን ዘመናዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ካስቻሉት ዲጂታል የአገልግሎት መስጫ ሥርዓቶች መካከል አንዱን እንመለከታለን፡፡

ይህ የቅርንጫፉ ቨርቹዋል ማኔጅመንት ሲስተም (Virtual Management System) ደንበኞች ወደ ቅርንጫፉ ሲመጡ ምንም አይነት የወረቀት ንክኪ ሳያስፈልጋቸው ሲስተሙ ላይ የሚፈልጉትን አገልግሎት (ወጪ፣ ገቢ፣ ገንዘብ ማስተላልፍ፣ የቼክ አገልግሎት ሌሎችንም) በመሙላት የአገልግሎት ተራ ቁጥር ይዘው የሚሰተናገዱበት ነው፡፡

የአገልግሎቱን አጠቃቀም በተመለከተ ድጋፍ ለሚሹ ደንበኞች እገዛ የሚያደርጉ የባንካችን ሠራተኞች በቅርንጫፉ አሉ፡፡

የበለጠውን ከቪዲዮው እንመልከት፡፡
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!


#cbe #commercialbankofethiopia #facts #MainBranch #banking #Ethiopia
https://youtu.be/092VsatDYiQ

Commercial Bank of Ethiopia - Official

14 Nov, 11:01


ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማኅበራዊ ገጾች በመከተል ቤተሰብ ይሁኑ!
***

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስም፣ አርማ እና ቀለም በመጠቀም ሀሰተኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆችን የሚከፍቱ አጭበርባሪዎች ተበራክተዋል፡፡ ክቡራን ደንበኞቻችን የባንካችንን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ፣ ከአጭበርባሪዎች ራስዎን ይጠብቁ፡፡ የባንካችን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች፡
• Facebook (https://www.facebook.com/combanketh)
• Telegram (https://t.me/combankethofficial)
• Facebook Afan Oromo (https://www.facebook.com/BaankiiDaldalaItiyoophiyaa)
• Facebook CBE NOOR (https://www.facebook.com/cbenoor)
• Facebook Tigrigna (https://www.facebook.com/profile.php?id=100063784606106)
• YouTube (https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia)
• LinkedIn (https://www.linkedin.com/company/commercialbankofethiopia)
• Twitter (https://twitter.com/combankethiopia)
• Telegram CBE NOOR (https://t.me/combankcbenoorofficial)
• Telegram Afan Oromo (https://t.me/baankii_daldala_itiyoophiyaa)
• Instagram (https://www.instagram.com/commercialbankofethiopia/)
• Tiktok (https://www.tiktok.com/@combankethiopia)

Commercial Bank of Ethiopia - Official

14 Nov, 07:41


በመኾኒ ከተማ ከሲቢኢ ኑር ደንበኞች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መርኃግብር ተካሄደ።
*************************************
መርኃግብሩ በዋናነት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ጋር ተያይዞ ከደንበኞች የሚነሱ ፍላጎቶችንና አስተያየቶችን ተቀብሎ አገልግሎቱን የበለጠ ለማሻሻል እና በሲቢኢ ኑር ስለሚሰጡ አገልግሎቶች ግንዛቤ ለማስፋት አላማ ያደረገ ነው፡፡ በዕለቱም የባንካችን የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ አባል ፕሮፊሰር መሐመድ ሀቢብ፣የሰሜን ምስራቅ ሪጅን የባንክ አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ሽመልስ ፣የዋናው መስሪያ ቤት የወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አንዋር አብደላ እና የመቐለ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ልሳነወርቅ ከመኾኒ ከተማ ደንበኞች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ባንኩ ይህንን የውይይት መድረክ በማዘጋጀቱ ደንበኞች ደስታ እንደተሰማቸው በመግለጽ ከባንኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡ እንዲሁም ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የባንካችን የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ አባል እና የስራ ሃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ባንካችን እየሰጠ የሚገኘውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ላይ የሚነሱ ጉድለቶችን በመለየት የደንበኛን ፍላጎት ያከበረ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በዲስትሪክት፣ በሪጅንና በባንክ ደረጃ በፍጥነት እንዲፈቱ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

Commercial Bank of Ethiopia - Official

13 Nov, 13:52


የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ለ4ኛ ጊዜ በካዛብላንካ ሞሮኮ ያዘጋጀውን የ2024 የካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ እግር ኳስ ክለብ ውድድር ዛሬ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን እና በደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ /Mamelodi Sundowns/ መካከል ይካሄዳል ፤ ጨዋታውን በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል ትከታተሉ ዘንድ እንጋብዛለን፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ፡፡

Commercial Bank of Ethiopia - Official

13 Nov, 11:49


ወደ ዓቢይ ቅርንጫፍ ጎራ ብለው ያውቃሉ?
************

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ሥር የሚገኘው እና ነሀሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ የጀመረው ዓቢይ ቅርንጫፍ እጅግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና አሠራር የተደራጀ ነው፡፡

ይህ 2586 ስኩዌር ሜትር ስፋት ያለው የሀገራችን ትልቁ ቅርንጫፍ የተገልጋዮችን ምቾት በሚጠብቁ የቢሮ መገለገያዎች የተሟላ ሲሆን፣ ለአገልግሎት ብቻ ሳይሆን ለጉብኝት የሚመጡበት ውብ ስፍራ ነው፡፡

እስካሁን ወደ ዓቢይ ቅርንጫፍ ጎራ ካላላችሁ መጥታችሁ በአገልግሎቱ እንድትጠቀሙ እየጋበዝን፡፡ በክፍል አንድ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ ስለቅርንጫፉ የሚሰጡትን አጠቃላይ ገለፃ እንመለከታለን፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

#cbe #commercialbankofethiopia #facts #MainBranch #banking #Ethiopia
https://youtu.be/inCNxd219Ck

Commercial Bank of Ethiopia - Official

13 Nov, 10:22


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደኅንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለደንበኞቹ በመስጠት ራሱን ከጊዜው ጋር እያዘመነ ነው፡፡
በጥቅምት ወር በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የሳይበር ደኅንነት ወር በማስመልከት ፤በባንኩ የመረጃ ሥርዓት አስተዳደር ክፍል የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሂዷል::
ከሳይበር ጥቃት ነፃ የሆነ ሀገርም ይሁን ተቋም ስለማይኖር፤ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ተጠቁሟል፡፡
https://youtu.be/3N0dFEnGkYw

Commercial Bank of Ethiopia - Official

13 Nov, 07:06


ስልክዎ ላይ ቅርንጫፍ ከፍተናል!
************

ወዲህ ወዲያ ሳይሉ ባሉበት ፍላጎትዎን ልናሟላ
ስልክዎ ላይ ቅርንጫፍ ከፍተናል!

በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ
ህይወትዎን ቀላል ያድርጉ!

#cbe #digitalbanking #mobilebanking #banking #ethiopia
************
የሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን ለማግኘት፡

• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.mobilebanking
• IOS: https://apps.apple.com/us/app/cbe-mobile-banking-new/id1534203410#?platform=iphone

Commercial Bank of Ethiopia - Official

13 Nov, 05:07


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Wednesday, 13 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

12 Nov, 14:12


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአዋሽ ባንክ 30ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ የባንኩን ባለድርሻዎች፣ ኃላፊዎችንና ሠራተኞችን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የፕሬዚደንቱን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት የባንካችን የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሠን አሰፋ ለአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሺፈራው አስረክበዋል፡፡

አቶ አቤ ባስተላለፉት መልዕክት ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ላስመዘገባችሁት የስኬት ጉዞ እንኳን ደስ ያላችሁ፤ መልካም 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ይሁንላችሁ ብለዋል፡፡

‹‹ባንኩ ለደረሰበት ደረጃ በመብቃቱ ደስተኞች ነን፡፡ ለአገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት የጋራ ርዕይ ሰንቀን እንደምንሰራም አረጋግጥላችኃለሁ" ብለዋል፡፡   

የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሺፈራው በበኩላቸው ‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአዋሽ ምስረታ ትልቅ ባለውለታና እንደ ታላቅ ወንድማችን የምናየው ባንካችን ነው፡፡ ትልቅ አክብሮትና ፍቅር ለባንኩ አለን›› ብለዋል፡፡

አዋሽ ባንክ በተመሠረተበት ወቅት የነበረውን የሰው ኃይል ችግር ለመቅረፍ ባንኩ የላቀ አስተዋጽኦ ነበረው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ የአሰራር እና መሰል መመሪያዎችን ለማዘጋጀት የባንኩ ፈቃደኝነት ባይኖር ኖሮ ዛሬ ላይ ለመድረስ አዳጋች ነበር ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት ባስተላለፉልን የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት በጣም ደስ ብሎናል ያሉት አቶ ፀሐይ መልዕክቱ የባንኩ ዘርፍ በመተባበርና በመደጋገፍ የምንሰራበት መሆኑን ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አዋሽ ባንክ የብሔራዊ ባንክን ፈቃድ አግኝቶ የመጀመሪያው የግል ባንክ ሆኖ የተመሰረተው ሕዳር 03 ቀን 1987 ዓ.ም. ነበር።

Commercial Bank of Ethiopia - Official

12 Nov, 11:00


ነፃ!
በሲቢኢ ብር ፕላስ
ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ እና ወደ ባንክ ሂሳብ ገንዘብ በነፃ ያስተላልፉ!
#cbe #cbebirr #cbebirrplus #ethiopia #digitalbanking #banking #business

Commercial Bank of Ethiopia - Official

12 Nov, 06:03


ለተሻለ ነገ...
የትምህርት ቁጠባ ሂሳብ
=====
የርስዎንም ሆነ የልጆችዎን የከፍተኛ ትምህርት ወጪ ለመሸፈን
የትምህርት ቁጠባ ሒሳብ ተጠቃሚ ይሁኑ!
#CBE #education #saving

Commercial Bank of Ethiopia - Official

12 Nov, 05:05


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Tuesday, 12 November 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia - Official

11 Nov, 13:57


ካርድዎ በቂ ነው!
====
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የክፍያ መፈፀሚያ ማሽኖች (ፖስ) በመጠቀም
በካርድዎ በቀን እስከ 500 ሺ ብር ግብይት መፈፀም ይችላሉ፡፡

ነካ ከፈል፣ ኑሮዎን ቀለል!
#cbe #digitalbanking #pos #banking #ethiopia