elam @elam12 Channel on Telegram

elam

@elam12


የየሰንበቱ መዝሙር፣ ምስባክና ወንጌል

Elamaba.org

ኢላም - መዝሙር፣ ምስባክና ወንጌል (Amharic)

ኢላም በአማርኛ በእንዴት ባለሙያዎቹን መስማማትን እና ማንም በግል ለውጥ ያለንዎቹን የሆነበት ንግግር ፍፁምን ማሳየቱ በእርስዎ መረጃዎ ተሰምቷል። አብዛኞቹ ሰዎች፣ መዝሙርና የእውነት መዝሙር መነሻ እና መቸገሪያዎች ወንጌልን እንዲጠቀሙ አቅሩ። ከእድሜ በኋላ ገላጭን የሚያከናውኑ ዜጎች እና መዝሙሮችን ለማየት ማቅረብ ይኖራል። ስለሆነ በስልክ ላይ ግል እንስኪውና ቄምለኛ መረጃዎ ወደ @elam12 ብሄሩ። ከታች በች የሚሆኑ እና በመሣሪያዎ የሚታዩ ሁሉ አይነቁም።

elam

13 Oct, 20:45


Live stream finished (34 seconds)

elam

13 Oct, 20:44


Live stream started

elam

13 Oct, 20:43


Live stream finished (2 minutes)

elam

13 Oct, 20:40


Live stream started

elam

08 Oct, 02:04


https://youtu.be/tHtcpbCRdmo

elam

08 Oct, 02:01


https://youtu.be/IzhhtZ9TpLo

elam

30 Sep, 18:58


https://youtu.be/QqOGLhLeMQc

elam

30 Sep, 17:09


https://youtu.be/T3oBc8dVMa4

elam

16 Dec, 03:32


https://youtu.be/VN8E0Qqhlgg

elam

03 Oct, 18:38


https://youtu.be/SP4r0ecio2Q

elam

03 Oct, 16:31


https://youtu.be/gBD-BdDhek0?si=Vqtf6opGI4s56yHy

elam

15 Sep, 23:33


https://docs.google.com/forms/d/1IFEJWVhBnFxLXmpm6Q25NCYFYKPVWnDPzeuObRsLlBg/edit

elam

13 Sep, 15:36


https://docs.google.com/forms/d/1jmdfJn4ZOPSOQcv0D7uIDA9PjLzOgS_7fbkPiB0KTD0/edit

elam

12 Sep, 17:19


ሁላችሁንም እንኩዋን ለዘመነ ዮሐንስ አደረሳችሁ ትምህርታችን የሚሆነው በዙም ነው መልእክቱን ለሚፈልጉ ሁሉ ብታጋሩት ድንቅ ነው

elam

08 Sep, 00:32


መዝሙር ዘወርኃ ጳጉሜን ከመ እንተ መብረቅ

(በ፪) ከመ እንተ መብረቅ ዘይወጽእ እምጽባሕ ወያስተርኢ እስከ ዓረብ ከማሁ ምጽአቱ ለወልደ እግዚአብሔር ምስለ ኃይለ ሰማያት በንጥረ መባርቅት (ከ) ምስለ አእላፍ መላእክት ወኵሎሙ ሊቃነ መላእክት (ከ) አክሊለ አክሊላት ዲበ ርእሶሙ ለካህናት።

ትርጕም፦

መብረቅ (ፀሐይ) ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንዲታይ የሰው ልጅም አመጣጡ እንዲሁ ነው። ከሰማይ ኃይላት ጋር በመባርቅት ብልጭታ። ከአእላፍ መላእክትና ከሊቃነ መላእክት ሁሉ ጋር። የአክሊላት አክሊል በካህናት ራስ ላይ አለ።

የዕለቱ ምንባባት 

፩ቆሮ ፩፥፩ - ፲፤
፪ጴጥ ፫፥፲ - ፍጻሜ፤
ግብ ፱፥፩ – ፲፤
ወንጌል፦ ሉቃ ፲፯፥፳፪ - ፍጻሜ፤ 
ከቁጥር ዐሥራ አንድ እስከ ሃያ ሰባት የሚያዝ ግጻዌም አለ። 
ቅዳሴ፦ ያዕቆብ ዘሥሩግ (ተንሥኡ)

የዕለቱ ምስባክ፦

እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ፤
ወአምላክነሂ ኢያረምም፤
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ። መዝ ፵፱፥፫፤

ትርጒም፦

እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፤
አምላካችን ዝም አይልም፤
እሳት በፊቱ ይነዳል።

ምሥጢር፦

እግዚአብሔር በሰባ ዘመን በረድኤት ተገልጦ ይመጣል፤
መጥቶም ዝም አይልም በበጎዎቹ አድሮ ይፈርዳል አንድም በበጎዎቹ ካህናት አድሮ ክፉዎችን ካህናት ይዘልፋል፤
እሳት በፊቱ ይነዳል ማለት ክፉዎች የሚጠፉበትን መቅሠፍት መናገር ነው፤
አንድም እግዚአብሔር አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም በሥጋ ማርያም ይገለጣል፤
መጥቶ ዝም አይልም ወንጌልን ያስተምራል አንድም አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን - ጻፎችና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ እያለ ይዘልፋል
አይሁድ የሚጠፉበት መቅሠፍት በፊቱ ነው፤
አንድም በዕለተ ምጽአት የተወጋበትን ኲናት/ጦር የተቸነከረበትን ቀኖት አስይዞ ይመጣል፤
ጻድቃንን ንዑ ኀቤየ ብሎ ይጠራል ኃጥአንን ሑሩ እምኔየ ብሎ ያሰናብታል፤
ጻድቃን የሚድኑበት ሕይወት ኃጥአን የሚቀጡበት መቅሠፍት በፊቱ አለ።

መልእክት፦

እግዚአብሔር በግልጥ በሚመጣ ጊዜ እያንዳንዱ እንደሥራው ፍዳውን ይቀበል ዘንድ በእግዚአብሔር እሳታዊ ዙፋን ፊት ይቆማል። የጸና ሃይማኖትና የቀና በጎ ምግባር ያለው በቀኝ ቆሞ የምስጋና ቃላትን ሰምቶ ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀለትን መንግሥተ እግዚአብሔር ይወርስ ዘንድ ሥልጣን ሲሰጠው በዚህ ተቃራኒ ያለ ሁሉ ለሰይጣንና ለሠራዊቱ ወደተዘጋጀ ዘለዓለማዊ እሳት ይጣል ዘንድ ጽኑዕ የሆነ አምላካዊ ትእዛዝ ይሰማል።
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በቅዳሴው አሜሃ መሐረነ መሀከነ ወተሣሃለነ - ያን ጊዜ ማረን ራራልን ይቅርም በለን እንዳለ ዛሬም በቤተ መቅደሱ ተሰብስበን ማረን ይቅር በለን እንበለው። በተለያየ ምክንያት የሸፈተውንና የሻከረውን ልባችንን በቃሉ እየመለስንና እያነጻን በንስሐ ሕይወት እየተመላለስን መንፈሳዊ ቤት ለመሆን እንሠራ። መተርጉማን ሊቃውንት በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ የሚለውን ሲያብራሩ በደላችንን የምታርቅልን እንደ ይቅርታህ እንደ ቸርነትህ ብዛት ነው እንጂ እንደ በደላችን አይደለም እንደ በደላችን ቢሆን በዝቶ በተደረገብን ነበር አንድም ሥጋህን ደምህን የምትሰጠን እንደ ይቅርታህ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይደለም እንደ በደላችን ቢሆን ባልተገባን ነበር እያሉ ነው። እኛም ይህንን ግሩም ምሥጢር ከልባችን ብንረዳውና አንደበታችንንም ልባችንንም አንድ አድርገን ድምጻችን እስከ ሰማይ ድረስ እንደራሄል ድምጽ እንዲሰማ አድርገን ብንጮህ ለችግሮቻን ሁሉ መፍትሔ በመጣልን ነበር።
የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል እንደተባለ እልከኛ በሆነ ልብ መጓዛችን ለእኛው እንዲብስብን ማድረግ መሆኑን መገንዘብ አለመቻላችንና በየራሳችን መንገድና ፍላጎት ብቻ መሄዳችን የዓመታት ለውጥ ብቻ እንጂ የምንፈልገውንና የሚጠቅመንን ለውጥ ማምጣትና ማግኘት አላስቻለንም። ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤል በክፉ መንገድ መሄዱን እስካላቆመ ድረስ የሚገጥመውን ሲናገር እንዲህ ብሏል። "እግዚአብሔር በዕብደት በዕውርነት በድንጋጤም ይመታሃል በቀትርም ጊዜ ዕውር በጨለማ እንደሚርመሰመስ ትርመሰመሳለህ መንገድህም የቀና አይሆንም በዘመንህም ሁሉ የተጨነቅህ የተዘረፍህም ትሆናለህ የሚያድንህም የለም" ዘዳ ፳፰፥፳፰
ሊሆን የሚገባውን አንደበታችን ይናገረዋል ስሕተት ሠሩ የምንላቸውን ሁሉ እንተቻለን እናወግዛለን ግን እኛው ደግሞ ያንኑ ስሕተት አሻሽለን እንደግመዋለን "በዘመንህም ሁሉ የተጨነቅህ የተዘረፍህም ትሆናለህ" ማለት ይሄ ይሆን? እንጨነቃለን መፍትሔ ግን የለም እንጮሃለን መልስ ግን የለም እንዘምራለን በረከት ግን ከቀን ወደቀን እየራቀን ነው...። ብፁዕ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ነገን ሲያጠነቅቀን እንዲህ አለ። "መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና" ፪ቆሮ ፭፥፲
በዘወትር ጸሎታችን "አመ ዳግም ምጽአቱ ኢያስተሐፍረነ - በዳግም ምጽአቱ ጊዜ እንዳያሳፍረን/አያሳፍረን" እያልን የምንጸልየውን ጸሎት ሰምቶ እንዳያሳፍረን ማለትም አላውቃችሁም እንዳይለን ይልቁንም ንዑ ኀቤየ ቡሩካኑ ለአቡየ እንዲለን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

elam

01 Sep, 20:57


መዝሙር ሰንበት ተዐቢ ነሐሴ ፳፯ እና ፳፰

(በ፭) ሰንበት ተዐቢ እምኵሉ ዕለት ሰንበት ተዐቢ እምኵሉ ዕለት ወሰብእ ይከብር እምኵሉ ፍጥረት (ሰ) አዕበያ ኖኅ በውስተ ታቦት አብርሃም አክበራ በውስተ ምሥዋዕ (ሰ) አዘዞሙ ሙሴ ለሕዝብ ያክብሩ ሰንበተ በጽድቅ (ሰ) አዝዞሙ እግዚኦ ለደመናት ያውርዱ ዝናመ ዲበ ምድር ሰንበት ተዐቢ እምኵሉ ዕለት ወሰብእ ይከብር እምኵሉ ፍጥረት።

ትጕም፦

ከዕለት ሁሉ ሰንበት ትከብራለች ከፍጥረት ሁሉ ሰው ይከብራል ኖኅ በመርከብ ውስጥ አገነናት አብርሃም በመሥዋዕት አከበራት ሙሴ ሰንበትን ያከብሩ ዘንድ ጉባኤውን አዘዛቸው አቤቱ በምድር ላይ ዝናምን ያዘሙ ዘንድ ደመናትን እዘዛቸው ከዕለት ሁሉ ሰንበት ትከብራለች ከፍጥረት ሁሉ ሰው ይከብራል።

የዕለቱ ምንባባት፦

ዕብ ፯፥፭ - ፍ፤
ያዕ ፪፥፲፬ - ፍ፤
ግብ ፯፥፩ - ፱፤
ወንጌል፦ ሉቃ ፲፪፥፲፮ - ፳፯፤
ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ

የዕለቱ ምስባክ፦

ወሐመልማለ ለቅኔ እጓለ እመሕያው፤
ዘይሁቦሙ ሲሳዮሙ ለእንስሳ፤
ወለእጕለ ቋዓት እለ ይጼውዕዎ። መዝ ፻፵፮፥፱፤

ትርጕም፦

ልምላሜውን ለሰው ልጆች አገልግሎት የሚያበቅል፤
ለእንስሳትና ለሚጠሩት ቍራዎች ምግባቸውን የሚሰጣቸው እሱ ነው።

ምሥጢር፦

እህሉን ተክሉን የሚያበቅል እሱ ነው ያንን እየተመገበ በሥጋ በነፍስ ለእግዚአብሔር እንዲገዛ፤ አንድም ለሰው ለሚገዛ ለእንስሳ ልምላሜውን የሚያበቅል እሱ ነው፤
ለእንስሳት ምግባቸውን የሚሰጣቸው እሱ ነው በእንስሳ ሁሉን መናገር ነው፤
ለሚለምኑት ለዕጕለ ቋዓት - ለቍራዎች ልጆች ምግባቸውን የሚሰጣቸው እሱ ነው፤ እሱ ባወቀ ይለምኑታልና እንዲህ አለ፤ አንድም ለእለ ኢይጼውዕዎ ይላል ለማይለምኑት ለዕጕለ ቋዓት ምግባቸውን የሚሰጣቸው እሱ ነው። ቋዕ/አሞራ ሲወለድ ፍህም መስሎ ይወለዳል እናት አባቱ ምን ጉድ ተወለደብን ብለው ጥለዉት ይሄዳሉ ሲርበው ጧ ጧ እያደረገ አፉን ይከፍተዋል ተሐዋስያን ርጥበት ሲሹ ይገባሉ ግጥም አድርጎ ይዞ ይመገባቸዋል። አንድም ተሐዋስያን ሲያልፉ በእስትንፋሱ እየሳበ እስከ አርባ ቀን ድረስ ይመገባቸዋል ከአርባ ቀን በኋላ ጸጕር ያበቅላል በመልክ ይመስላቸዋል ተመልሰው መጥተው ያሳድጉታልና እንዲህ አለ።

elam

03 Aug, 17:15


https://www.youtube.com/watch?v=F2yLdyQN8vI

elam

03 Aug, 01:44


ይህ ጎፈንድሚ ለደብራችን በደብራችን ጽ/ቤት የተከፈተ ነው እግዚአብሔር ቢፈቅድ ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ለማግኘት አስበናል አምላከ ቅዱስ ገብርኤል እንዲጨመርበት እየጸለያችሁ ለምታውቋቸው ሁሉ በማጋራት ካሰብነው ለመድረስ ሁላችንም የምንችለውን እናደርግ ዘንድ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ስም ከልብ እናሳስባለን።

1,478

subscribers

23

photos

2

videos