ወርቃማ ንግግሮች @golden_speech Channel on Telegram

ወርቃማ ንግግሮች

@golden_speech


ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።

አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot

🍂

ወርቃማ ንግግሮች (Amharic)

እንዴት ነው ወርቃማ ንግግሮች እና የቴሌግራም እርስዎኛ ይዘቴ ስለነበር? ወርቃማ ንግግሮች ላይ አሉታዊ እንቅስቃሴዎችን እና ኮምፒዋችን እንዲሁም ሌሎች ታዳጊ አረፋላቸው። እናስከረካቸው ከሆነ በሳምንቱና መረጃቸው፣ እንቅስቃሴ ጋር አማካይ እንደሚያስተምሩበት እና በሳምንት የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን ይሰራል። ወርቃማ ንግግሮችን ከአንደኛው አስተዋጽኦ እና እንድናደርግ በመባል ለራስን ላይ ይተዋላል። እሱንም ለ@Golden_SpeechBot ይዘቱ እናመሰከርናል። ከዚህ በፊት መረጃዎችን መካከል ለመከተል እና ለመቀየር የቴሌግራም የአዳግ ዜና ለእስከ መረጃ እንደዚህ ከተጣራ የእገዛ ቀን እንዳደረገ የአዳግ ዜና ለተቀናመረ እና መረጃዎች የቴሌግራምን ለእነሱ ለማክበር ይችላሉ።

ወርቃማ ንግግሮች

20 Nov, 09:16


የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲሱ  ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው 
በሀገር ውስጥም ይሁን ካሀገር ውጪ ያላችሁ
የሱና ወንድም እና እህቶቻችን 
ይህ ቻናል ይጠቅማችኋል ተቀላቀሉ
👇
join request የሚለውን በመጫን✅️
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0

ወርቃማ ንግግሮች

20 Nov, 02:29


"አንዲት ቅጠል አትወድቅም አላህ ቢያቅ እንጂ"

እንዴት ታዲያ ይሁ ሁሉ መልካም ነገር በልብህ የያዝከውስ?

ለሰወች የያዝከው ይህ ሁሉ ውዴታስ..?
የሰወች ስኬት የራስህ ስኬት ያህል የምትደሰተው ደስታህስ!
የሰወች ህመም ህመሜ ብለህ የምትታመመውስ ?
ወዳጄ :- አላህ እኛን ከላይ ያለንን አይመለከተንም ። አላህ የሚመለከተው ውስጣችንን ነው ።

ንጉሱ የሚመለከተውን ክፍል አሳምረው
በአካል ውስጥ አንዲት ስጋ አለች እሷ ከተስተካከለች ሙሉ አካላችን ተስተካከለ እሷ ከተበላሸችም ሙሉ አካላችን ተበላሸ
እሷም ልብ ነች!

ወርቃማ ንግግሮች

19 Nov, 17:21


✍️ማእከላዊ የፌደራሎች ካምፕ ደረስን። ሻንጣ አይገባም በፌስታል አድርግ ልብስህን ተባልኩና አንዳንድ ደግ ወታደሮች ፌስታል ገዝተውልኝ ልብሴን በፌስታል ይዠ ወደ አድስአበባ ፓሊስ ኮሚሽን አመራሁ። ሰዓቱ የኢሻ አዛን እየወጣ ነበር።
ፌደራሎቹ ለአድስአበባ ፖሊስ አስረክበው ከጨረሱ በሗላ ቻው ብለውኝ ሔዱ።

✍️የአድስአበባ ፖሊስ ጋ ፍጥጫ ተጀመረ። ቅዳሜ ምሳ የበላሁ ነኝና ብርዱም ረሓቡም በጣም አድክሞኛል። ፖሊሶቹ ልብሴን ፈተሹ የጀለቢያ አላባሽ ቱታዎቸን ገመዶቻቸውን መንጥረው መዘው አወጡ።ስም ሲመዘግቡ ክልል ሲሉኝ አማرا ስል በግልምጫ ኮስተር አሉ ዞን ሲሉ ወሎ ስል ትንሽ ሞተር አቀዘቀዙ። እርቦኛል የሚበላ ስጡኝ ስል ክፉ ቃል ተናገሩኝ ትንሽ ባሰኝና የድካም እንባ መጣ

✍️ኬዙ ከባድ ነው ልዩ ጥበቃ አድርጉ ጨለማ ቤት አስገቡት የሚል የስልክ ትእዛዝ ተሰጣቸውና መብራት እያለው ግን ጨለማ የሆነ የሚጨንቅ 4ማእዘን ላይ ካሜራ የተገጠመለት ግራውንድ ክላስ አስገብተው ወረወሩኝ።

✍️መግሪብና ኢሻን ቂብላውን ሳላውቅ በብርድና በረሓብ በደከመ ሰውነት በደመ ነፍስ ሰገድኳቸውና ብርድ ልብሴን ደርቤ ጎኔን አሳረፍኩ።ምንም እንኳ በጣም የረሓብ ስሜት ቢሰማኝም ብርዱ ሰውነቴን ስላደነዘዘው እንቅልፍ ወሰደኝ።የሆነ ሰዓት ላይ ነቃሁኝና ረጅም ሰዓት የተኛሁ ስለመሰለኝ ፈጅር ይደርሳል እስካሁን ብዬ ተየሙም አድርጌ ሰገድኩኝ።ትንሽ አዝካር ለማለት ሞከርኩና ግርግዳውን ተደግፌ ቁጭ አልኩኝ።እንደምንም ነጋና ጧት ፍርድ ቤት ሊያቀርቡኝ ስሜ ይጠራል በሩ ስለተቆለፈ ብሰማም ምንም ማድረግ አልቻልኩምና ዝም አልኩኝ። የተወሰነ ሰዓት በጥሪ ከደከሙ በሗላ ማታ ጨለማ ቤት ያስገባነው አድሱ እስረኛ ነው ብለው አስታውሰው መጡና ከፈቱልኝ ስምህ ሲጠራ አትሰማምዴ ብለው ጮሁብኝ ብሰማስ ምን አደርጋለሁ የተቆለፈ ክላስ ተቀምጨ አልኳቸው። በል አሁን መፀዳጃ ከፈለክ ግባና ተጣጠብና ውጣ ወደ ፍርድ ቤት ልትሄድ ነው አሉኝ።
✍️በተያዝኩ በሳምንቱ ሰኞ አድስአበባ አራዳ ፍርድ ቤት ቀረብኩ።መርማሪ ፖሊስ ተብየ ወረቀት ተሸክሟል። ስሜ ተጠራና ችሎት ቆምኩ መርማሪ ፖሊስ በዛ ወጥቶ በዚህ ወርዶ ወወወ የሚል እጅግ ብዙ ነገር አነበበ በቃ ቢላደንን የያዙ አስመሰሉት በዛ ሒዶ ወጣት እየመለመለ እንትና ከተማ ሴል እያዘጋጀ ከእንትን አለም አቀፍ የሽብር ቡድን ጋ ጥብቅ ትስስር በመፍጠር ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ወዘተ በቃ ኡፍፍፍ።ዳኛው ምን ትላለህ አለኝ ስለምኑ ነው የምናገረው አልኩት ስለተነበበው ክስ አለኝ ይህ ክስ ለእኔ ነው ስለው ቆጣ ብሎ የምትናገረው ካለህ ተናገር አለኝ።እኔ ስለተነበበው ነገር የማውቀው ታሪክ የለም ከዚህ ነገር የጠራሁ ንፁህ ሰው ነኝ።ሒወቴን አታበላሹት የሐሰት ክስ ፅፋችሁ ወዘተ ብዬ ለፈለፍኩ የሚሰሙኝ መስሎኝ።
✍️መርማሪ ፖሊስ ተብየው 28ቀን የምርመራ ጊዜ ይሰጠን ብሎ ጠየቀ ተሰጠውና ከችሎት ወጣን።
✍️ሌሎች ታሳሪዎች ጋ በሰርቪስ ስንመለስ የት ነህ መች ገብተህ ነው ብለው ሲጠይቁኝ ጨለማ ቤት ነኝ ማታ ነው ያመጡኝ ብዬ ነገርኳቸው። አይዞህ ምን እንላክልህ ሲሉኝ ረሓብ ክፉ ነውና መሶበር አልቻልኩም
👉የሚበላ ነገር ካለ 😥ላኩልኝ አይኔ እየደከመብኝ ነው አልኳቸው።
✍️በዚህ መልኩ እዛች ጨለማ ቤት ተመለስኩ ወቅቱ ሐጂ ሰዒድ ያሲን የታሰረበት ጊዜ ነበርና ፍርድቤት ያገኙኝ ልጆች ሐጅ እረ አንድ የወሎ ልጅ ጨለማ ቤት አለ ምግብ ይፈልጋል ሲሉት ከምግብ መርጠው ምርጡን ከውሓ ጋ ላኩልኝ። ሰኞ ከሰዓት ምግብ ቀምስኩና ጌታዬን አመሰገንኩ። ይቀጥላል

ደህና እደሩ

ወርቃማ ንግግሮች

19 Nov, 17:20


የፖሊስ ጣቢያው ኮማንደር አሳልፌ አልሰጣችሁም ልጁን የምናውቀው በመልካም ነው ሲላቸው እርስበርስ ተጣሉና ሳይሳካ ቀረ።
✍️ሐሙስ ከሰዓት ከላይ ለኮማንደሩ ቀጭን ትእዛዝ ተሰጠው መሰል ጁሙዓ ጧት ፌደራሎቹ መጡና ውጣ አሉኝ።ልብሴን ሸክፌ ወጣሁ።

✍️👉ፌደራሎቹም በፕሌን ነው የምንወስደው ለሒወታችን መንገድ ላይ እንሰጋለን አሉ።ትኬት ተቆርጧል😂
የሆነች ጀግኖች የሚበዙባትን ከተማ ፈርተው ነውኮ ።
✍️ጁሙዓ ጧት ፖሊስ ጣቢያው በወዳጆቸ ተጥለቅልቋል በፌደራል የታጀቡ ፓትሮሎች ቀርበዋል እጄ በካቴና ታሰረና ፓትሮሉ ላይ ተጫንኩኝ። ወዳጆቸ ወደ ቀብር የሚሸኙኝ ይመስላል መሪር ሐዘን አለቀሱ። ይች ወቅት ትንሽ ለሕሊና ትከብዳለች
እኔው ተሽዬ ፓትሮሉ ላይ ሆኘ አብሽሩ አታልቅሱ አላህ በቂያችን ነው በማለት ለማፅናናት ሞከርኩ ግን የወዳጆቸ እንባ ከባድ ነበር።ራሳቸውን ስተው የወደቁ ሷሒቦች ነበሩ። አላህ ሐያታቸውን በደስታ የተሞላ ያድርግላቸው።አሚን

✍️ፓትሮሎ ተነስቶ ወደ ኤርፖርት ተጓዘ ሕዳር ወቅቱ ዝናባማ ነውና እዛ ስንደርስ በረራ ላይኖር ይችላል ተባለ።በቃ እጄ በካቴና እንደተጠረነፈ ብርድ ላይ ተወዳጇን ጁሙዓ ኤርፖርት አሳለፍኩት።10ሰዓት ሲሆን የበረራው ነገር እንዳልተሳካ ከበላይ አካል ሲነገራቸው ፌደራሎቹ ይዘውኝ ሌላ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱኝ።

✍️ጣባያ ከጣባያ ለምንድን ነው የምታንከራትቱኝ አለመሄዴን ለወዳጆቸ ልናገር ስልክ ልደውል ብዬ ስጨቃጨቅ ከየት እንደመታኝ የማላውቀው ጥፊ ጆሮዬን ሕው አደረገው አላህ ይምታህ አቦ ብየ ዝም አልኩ።እንደማንም ሰው ሰምቶ ቅዳሜ አለሁበት ጣቢያ ቁርስ ምሳ ወዘተ አመጡልኝ ።

✍️አሁንም ቅዳሜን ከዘያሪዎቸ ጋ አሳለፍኩት። ሌላ ቦታ ሆኖ ሚድያ ላይ ፎቶየን ያየ ወንድም ለእናቴ ደውሎ ኸበሩን ሲነግራት ቀኑ ጨለማ ሆነባት። ለቤተዘመዱ ስትናገር ሁሉም በድንጋጤና በፍርሓት ተጨንቋል ግን ይህን ሓይማኖት ማጠባበቅ ተው ብለነዋል አልሰማ ብሎ ነው ወዘተ ወሬ ተጀመረ።ነባሮቹ ዝም ያሉትን እርሱ ከቀሳውስት ቤት ተወልዶ አጉል ቃልቻ ነኝ አለ ተብያለሁም 😂

✍️ቅዳሜ ለይሏን ለእሁድ ልታስረክብ በቀረበችበት ለይል 10ሰዓት የታሰርኩበት ክላስ ተንኳኳና ተነሳሁ። ምንድን ነው ስል ውጣ የሚል ድምፅ ሰማሁ አልወጣም በዚህ ሰዓት መግደል ከፈለጋችሁ እዚሁ ግደሉኝ በማለት ጭቅጭቅ ተፈጠረና ፈጅር ደረሰ።
ወደ አድስአበባ ማእከላዊ ሊወስደኝ የመጣው የፓትሮሉ ሹፌር እና ዋና ክትትሉ ሶላት ይሰግዳሉና ፈጅር ሰግደን እንጓዝ ለአንተም ይሻልሓል ከፓትሮል ላይ ተጭነህ ከዚህ አድስአበባ መንገዱ ከባድ ነውና በጧት እንጓዝ መሄድህ ላይቀር አሉኝ።ፕሌኑ በቃ ቀረ 😂 ከአየር ላይ ሳይጥሉኝ ሆ

✍️እሁድ ጧት ከፓትሮል ወንበር ጋ እጄ ወደሗላ ተጥርንፎ ጉዞው ተጀመረ። እናቴ በዚሁ ቀን ከኩታበር ሰው ተከትሏት ከተማው ደርሳ ስትጠይቅ ልጄን ስትል የተረገሙ ፖሊsoች ለሊት ነው የወሰዱት ብለው ሲያረዷት እጅግ በጣም ደነገጠች።😥

✍️የለበስኩት ጀለቢያ ነው ብርዱ የሌለ ነው ይባስ ብሎ ደብረሲናን እንዳለፍን መንገድ ተበላሽቶ ለ5ሰዓታት ያክል ቆምን።ብርዱ አጥንቴ ሲደርስ ይታወቀኛል። እንደምንም ሰንዳፋ ነው መሰለኝ ሹፌሩ ሶላት እንስገድ ብሎ ካቴናው ተፈታልኝና ውረድ ተባልኩ
😥ግን ሰውነቴ በረድ ሆኗልና አልታዘዘኝ አለ እግሬ ደርቋል መዘርጋት አልቻልኩም። ይህንን ሲያይ ሹፌሩ በጣም አዘነና እቅፍ አድርጎ አወረደኝና ትከሻውን ይዠ ሰውነቴን እንዳፍታታ አገዘኝ። አገር ስንጠያየቅ የአንድ ወረዳ ልጆች ሆንና በጣም ተሰማው በጣም ጀግና ኮማንደር ሹፌር ነበር።
✍️ዝሁርንና አስርን ሰግደን የማላውቃት አዲስአበባ ገባን። ይቀጥላል 😂

ወርቃማ ንግግሮች

19 Nov, 17:19


☔️ወደሗላ

✍️ከተማ ላይ የታየው እኔን አንድ ፍሬ ልጅ ለመያዝና ቤት ፍተሻው የትዕንቱን አስፈሪነት ሕብረተሰቡ ትልቅ ጭንቀት ስለፈጠረበት
፨ወላጆች ልጆቻቸው ጋ እየደወሉ ከቤት እንዳትወጡ ከተማ ረብሻ አለ በማለት ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፈዋል። እኔኮ ያኔ 64ኪሎ ነው ብሆን ብዙም አረብሽም አልከብድምም ነበር😂😂

✍️ሰኞ ሕዳር 8/2012 ስራ ቦታ ከያዙኝና ቤት ፍተሻው ተጠናቆ በይነል መግሪብ ወል ኢሻእ በሆነ ወቅት"حسبي الله ونعم الوكيل" እያልኩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘውኝ ገቡና ከፌደራል ፓሊስ ለኮቻ ከተማ ፓሊስ ጣቢያ የአደራ እስረኛ ተብዬ ወደ እስረኛ ክፍል አስገብተው በሩን ከረቸሙብኝ። አንዳንድ ደፋር ሰዎች መጥተው ራት አምጥተንለታል ፍራሽም ይግባለት ብለው ሞገቱ በእርግጥ ፖሊስ ጣቢያው ያሉ ፖሊሶች ብዙወቹ ያውቁኛልና ደግሞ እሱ ምን አጠፋህ ተብሎ ነው ምናምን ብለው ለእኔ ለመወገን ሞከሩ።
✍️በስንት ጭቅጭቅ ራት እና ፍራሽ ወዘተ ገባልኝ ክላሱ ጨለማ ነው እኔም ንደት ብስጭት እየጀማመረኝ መጣ ክላሷ ውስጥ ያለው አንድ ሌላ ታሳሪ አብሽር ብሎ ሊያረጋጋኝ ሞከረ።

✍️በሩ ተከርችሞ ተቆልፏል።መብራቷ ቢልጭ ነው የምትለው በዚህ ሓል ማን ራት ይበላል ብዬ ሶላቴን ሰግጀ ለመተኛት ሞከርኩ። ልክ ለይል 7ሰዓት የተጣሉ ሰከራm እስረኞች መጡና በቃ በጣም እረበሹ ለእኔ የመጣውን ራት አገኙና ጥርግ አድርገው ከበሉ በሗላ ሰላም እንቅልፍ ተኙ።

✍️ለይሉ ነጋና ቀኑ ማክሰኞ ሆነ በሩ ተከፈተና እዛችው ጠባቧ ግቢ እግሬን ማፍታታት ጀመርኩ ። ማታውኑ ወንድማችን ፉላን ታስረ ወዘተ የሚል ኸበር በfb የከተማዋ ሙስሊሞች ፔጅ ተለቆ ስለነበር ሙሉ ሰው ሰምቷል። አስፈሪ ነው የተያዘው እንድህ እንድህ ነው የሚል ወሬ ስለተሰራጨ የሚቀርቡኝ አብረውኝ የሚውሉት ሳይቀር ጣቢያ መጥተው ለመጠየቅ ተቸግረው ነበር። አንዳንድ ደፋር ወንድሞችና እህቶች ቁርስ ይዘው መጡ እንዴት አደርክ ሲሉኝ አይኔ ፈጦ ነው ያደረው አልኳቸው😂 ሁሏንም ለመፃፍ ይከብዳል

✍️ማክሰኞ ረፋዱ 3ሰዓት አካባቢ አንድ መልከመልካም ጀመዓ ላይ የማውቀው ከመስጅድ የማይጠፋ ፖሊስ ካቴና ይዞ ወደ እኔ መጣና ወንድሜ ትእዛዝ ነው ይቅርታ አድርግልኝ በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ እጄ በካቴና ተጠረነፈ። ወደየት ልትወስዱኝ ነው ስለው የስራ ቦታው ይፈተሽ ተብሏል አለኝና ከጣቢያው ይዞኝ ወጥቶ ፓትሮል ላይ ተጭኘ ዳይ ወደ መሓል ከተማ ስራ ቦታ አላህ አላህ
የስራ ቦታ ደረስንና ተከፍቶ ፈታተሹ ምንም ነገር የለምና ማታ ነበር ይህንንም መፈተሽ የነበረብን ልጁ እጁ ረጅም ነው አዳር አሸሽቶት ነው በማለት በንዴት ዐይን እርስበርስ ተያዩ።

✍️የስራ ቦታ አካባቢ ሰው የሱቁን በር ገርበብ አድርገው ይመለከታሉ እኔም በካቴና የታሰረውን ሁለቱንም እጄን ከፍ አድርጌ አሰላሙ ዐለይኩም አብሽሩ ደህና ነኝ ስል ሁሉም ከሱቁ ብቅ ብቅ የማለቱን ድፍረት አገኙና አብሽር አይዞህ አሉኝ።

✍️ታዳ የስራ ቦታ ተፈትሾ ከወጣን በሗላ ፓትሮላ ላይ ሆኘ አንድ ትራፊክ ጠጋ አለና ሸሁ ደግሞ ምን አጥፍተው ነው
በዚህ የለውጥ ጊዜ ደግሞ የሚረብሽ አለዴ በማለት ነገር ለማቀሳሰር ሞከር እኔም ገለማመጥኩትና ወደጣቢያችን አመራን።
✍️ጣቢያ ስደርስ ግቢው በሰው ተሞልቷል የጓደኞቸ እናቶች እህቶች እረ በቃ ጥልቅልቅ ብሏል ሐዘን ቤት መስሏል ግቢው እረ የሰው ሆድ ማባባት ብዬ ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ።

✍️ማክሰኞ እዛው ጣቢያ ዋልኩ አደርኩ እሮብም እንድሁ ከዘያሪዎቸ ጋ አሳለፍኩት።

✍️ሐሙስ ፌደራል ከመራያቸው ጋ መጡና ልብስ አምጡለት በሻንጣ ፌደራል ልንወስደው ነው አሉ ግን ወረቀት አልያዙም ነበር።ይቀጥላል

ወርቃማ ንግግሮች

19 Nov, 17:19


✍️ሰዎች ምንድን ነው ለማለት ለመጠየቅ መድፈር ተሳናቸው ድባቡ ትንሽ ያስፈራ ነበርና።ነሷራ አምናያዎቹ እሳት የሆነ ግልምጫቸውን መወርወር ጀመሩ እኔም ሓስቢየላህ ወኒዕመል ወኪል እያልኩ ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ። አሁንም ባለሱፉ ከፌደራሎቹ ጋ ጠጋ ብሎ እንደማስጨነቅ አይነት መንገድ ተጠቅሞ ወደ ቤትህ ምራ በማለት ሲያንባርቅብኝ እኔም ኮስተር ብዬ ቤት የለኝም አልኩኝ
ሃሃሃሃ ቤት የለህም ጎዳና ነው ወይስ ጫካ የምት ኖረው በማለት አሾፉና ያችን ጥቁር ዱላ አስተካከሉ
✍️ኣሃ ሊወግሩኝ ነዋ ብዬ ተመትቸም ቤትም መርቸ ኣይይ ይሄማ አይሆንም ወዳጆቹ እንዲያዝኑ ጠላቶቸ ደስ እንድላቸው አላደርግም ብዬ ከውስጤ ጋ ተስማማሁና ወደ ቤት መምራቱን መረጥኩ ምክናያቱም ተመትቸም ቤትም በግድ መምራቴ አይቀርምና።

✍️ና ብለው ገፍተር ለማድረግ እየሞከሩ ፓትሮል ላይ ጫኑኝና በሒወቴ ጠባሳው የማይለቀኝን ስራ ሊሰሩ ወደ ሰፈር ቤት ፍተሻ ጉዞ ጀመርን።
✍️አንድ ባለሐብት ወንድም ስቴሽነሪ ሱቅ ላይ ተቀጥሬ እሰራ ስለነበር ከተማሪ እስከ የመንግስት ሰራተኛው በርካታው የከተማ ሕዝብ ያውቁኛልና በፓትሮል ተጭኘ ባዩ ጊዜ በድንጋጤ ራሱን የያዘ የሚያለቅስም መንገድ ዳር ቆሞ ሁኔታውንም የሚመለከት ሰው ሞልቷል።

✍️ፓትሮሉ ሰፈር በደረሰ ጊዜ የወታደሩን ድባብ ያዩ የሰፈር ሰወች ህፃናቶች ዋይታቸውን ለቀቁት።
፨ውሓ እየረጨሁ የማጫውታቸው በዚህ ጨዋታ ሱስ የሆነባቸው ከስራ ወደሰፈር መምጣቴን የሚጠባበቁት ህፃናቶች በዛች ቀን ግን ጨለማ የሆነባቸው መሳሪያ የደቀኑና የሰፈሩን ዋና ቦታዎች አቀባብለው በሚጠባበቁ ወታደሮች ተከብቤ ባዩኝ ጊዜ
😥ሰው የሚታሰረው ሰው ጋ ተጣልቶ መሆኑን ብቻ እሱኮ አይጣላም በማለት ከወላጆቻቸው ጋ ይዳረቃሉ።

✍️በዚህ መልኩ ግቢውን አቀባብለው የሚጠብቁ ወታደሮች ተመድበው የተወሰኑት እኔን ይዘው ወደ ቤት ውስጥ ገባን።
✍️እንደ እኔ ቤት ፍተሻ የሚባል ነገር በጣም አሳማሚ ከሕሊና የማይጠፋ ድርጊት ነው።

✍️ኪታቤን ከወጥ ጋ እያዳፉ ዘግናኙ የቤት ፍተሻ ተጀመረ ልብስን በጫማ እየረገጡና ውሓውንም እየደፉ ያጣድፉኝ ጀመር።
✍️አንዱ ፓስፓርት አገኘሁ ሲል ሌላኛው የስላቅ እየሳቀ ሶማሊያ ነው ሶሪያ የምትሄደው ይላል።
✍️ሌላው ፍላሾች አገኘሁ ሲል ኮርስ የሚሰጥበት ነው ይባባላሉ።የባንክ ደብተር አገኘሁ ሲለው ከአረብ አገር የሚቀበልበት ነዋ ይባባላሉ።

✍️ይሄ ሁሉ ኪታብ ምንድን ነው በማለት ከጫፍ ሲነካው ከመደርደሪያ ሙሉ ወረደ በጫማው ረገጠው እኔ ግን አሁን ደንዝዣለሁ

✍️ሰዓቱ እየመሸ ነው መግሪብ ደረሰ ያገኙትን ይዘው ከቤት ወጡና መሳሪያ አለህ አውጣ በማለት ያፋጥጡኝ ጀመር።እኔም እረ የለኝም አልኩ አንዱ ደብተራ አምንያ ማተቡን በእጁ ይዞ አንተ እኛን ልትገድል ነው በማለት በጥፊ ሊማታ ሲንደረደር አንድ ፌደራልና ፖሊስ እረፍ በሕግ ጥላ ስር ነው በማለት አስቆሙልኝ።
መሳሪያውን አውጣ እያሉ የተወሰነ ካስጨነቁኝ በሗላ ቀጥታ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ፓትሮል ላይ ጭነው ይዘውኝ ሄዱ።

✍️የመጀመሪያዋ የእስርቤት አዳር ......

ወርቃማ ንግግሮች

17 Nov, 16:00


☔️ወደ ሗላ ህዳር 8/3/2012 እና እኔ☔️

✍️ቀኑ ሰኞ ነው እንደ አገራችን ሳምንታዊ ቀን አቆጣጠር ሰኞ የመጀመሪያ ቀን የስራ ቀን ነው። እኔም ከሷሒቤ ጋ ከጀመርናት ስራ ላይ ተጥጃለሁ ነገር ግን ብዙ ጊዜ የማያቸው ሕልሞች ውለው ሳያድሩ በዟሒሩ ከች ይላሉና ጁሙዓ ለቅዳሜ ለይል አንድ ሕልም አይቸ ስለነበር በስጋትና በተበታተነ ሐሳብ ውስጥ ነኝ።ለሷሒቤ ሕልሜን ስለነገርኩት እሱም ስጋት ይዞታል ነገር ግን ያ ቀን ሰኞ ድባቡ ደስ ይላል ዝሁር ድረስ ቆየንና ወደየሰፈራችን አመራን።ምሳ በልተን ድጋሜ ወደ ስራ ገብተን ተፍ ተፍ ማለትን ጀመርን አስር ሶላት ደረሰና ሰግጀ ልቤ ጥሩ ስሜት ሲያጣብኝ ወደ እናቴ ደወልኩና ዘለግ ያለ ወሬ አወራ ምነው ድምፅህ አሞሓል እንዴ አለች እናቴ እኔም እረ ደህና ነኝ አልኩ ግራ በተጋባ ስሜት ከዛም በቃ ሰላም አምሹ ተባብለን ስልኩ ተዘጋ።
✍️ከ10ሰዓት ከ30በሗላ ነው የመንግስት ሰራተኛው የሚወጣበት ተማሪውም ከትምህርት የሚለቀቅበት ወቅት ደርሷል ወደ ከተማ ጎራ ብለው አስቤዛ የሚያደርጉ ሰዎች ከተማዋ ላይ የሚርመሰመሱበት ሰዓት ነው።በዚህ ሰዓት ከተማዋ ጭንቅ ጥብብ ብሏታል ፌደራሎች ፣ፖሊሶች ፣ልዩ ሚሽን ፈፃሚ ፖሊሶች ወዘተ አባላት ከተማዋ ዋና ዋና ቦታቸውን ይዘዋል።ከምሰራበት ሕንፃ ፊትለፊት ያለው ሕንፃ ላይ ስናይፐሮች ቦታቸውን ይዘዋል የተሽከርካሪዎች ሐረካ ተቀንሷል ።እኔ ግን ስራ ቦታዬ ውስጥ ነኝና ውጭ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ አላወኩም።
✍️ሁኔታውን የሚያዩ ሰዎች ምን አይነት ባለስልጣን ከተማችን መጥቶ ነው ወይስ ምን ምን አይነት ፀጉረ ልውጥ ገብቶ ነው የሚል የስጋት ወሬ ጫጫታ ተያይዟል።

✍️በዚህ ጊዜ ክትትል ክፍሉና የተመረጡ ፌደራሎች ከአጋዥ GPs ጋ በመሆን ከባንክ ባወጡት ፎቶዬ ተመርተው ሱራው ተመሳስሎባቸው አንድ ወንድማችን ሱቅ ጋ በመድረስ ይይዙታል በእርግጥ GpS እሱ አይደለም እያላቸው ነበር እነርሱ ግን መረጋጋት አልቻሉምና
✍️ሱራውን እያሳዩ ይህ አንተ ነህ አሉት ወንድማችንን በድንጋጤ እየተንተባተበ እረ እኔ አይደለሁም ሲላቸው በጣም መደነገጡን እንደ አድቫንቴጅ ተጠቅመው እሽ ይህንን ባለፎቶ ታውቀዋለህ ሲሉት የደነገጠ ሰው ችግር ነውና አወ አውቀዋለሁ አለ።
✍️አወ አውቀዋለሁ ካልክ ጉዳዩ ሲልሲላ አለውና ምራ የሚል ጥያቄ ይከተላል። እናም የት ነው ምራ ሲሉት እሽ በማለት ቀጥታ ወደ እኔ ስራ ቦታ ይዟቸው መጣ።

✍️ልክ ፎቁን ወጥተው ሱቅ በር ላይ ሲደርሱ ወንድማችን ጣቱን ወደ እኔ በመቀሰር 👉ይህ ነው አላቸው። እኔም ምንድን ነው ሸይኽ ፉላን ስል እንባው አይኑን ሲሞላው ተመለከትኩ ኣሓ ያ እጄ በካቴና ውስጥ ሲገባ ያየሁት ሕልም ዛሬም ግልፅ ሆኖ መጣ ማለት ነው ብዬ የያዝኩትን ትልቅ የጨርቅ መቀስ ይዠ ቀጥ ብዬ ቆምኩ።

፨ከተማዋ ውስጥ አይቸው የማላውቀው ሱፉን ደቅ አድርጎ የለበሰ ሰው ወደ ፊት ቀደም ብሎ ፉላን ማለት አንተ ነህ አለኝ ስልኩ ላይ ያለውን ከባንክ የወጣ ፎቶ እያሳየኝ።
እኔን ይመስላል እስኪ ስልኩን አምጣው ብዬ ጠጋ እንደማለት ስል በቅፅበት ረጃጅሞቹ ፌደራሎች ከቀኝም ከግራም እጄን ጠምዘዝ በማድረግ ጠፍንገው ያዙኝና የያዝኩትን መቀስ ቀምተው አስቀመጡ።

✍️ሱቁ ውስጥ ጓደኞቸ ደንግጠው እንደ እንጨት ደርቀዋል እኔ ቀድሞ ኢሻራው ስለመጣ ብዙም አልደነገጥኩም።ያው እጅ ሰጠሁ ማለት ነው ብዬ ለራሴ ነገርኩና ፀጥ አልኩ።

✍️ከሕንፃው በፍጥነት ይዘውኝ ወረዱና የሆነች ቅያስ አለች ወደሷ ገለል አድርገው በከበባ አስቀመጡኝ።በመገናኛ የሚያወሩት ቀውጢ ሆኗል። ሰዎች እንዴ እሱን ለመያዝ ነው ይህ ሁሉ ጋጋታና ወታደር ደህናውን ልጅ ይላሉ......

~ ከአቡ ሃላል… ከፌስቡክ መንደር የተገለበጠ ነው።

ወርቃማ ንግግሮች

17 Nov, 12:24


አስቡት በቀን ክፍለ ጊዜ ውስጥ የሆነ የተገደበ ሰዐት ብቻ ነው ወደ አላህ መመለስ ሚቻለው ብንባል

ማለትም ለ ምሳሌ ከ ጥዋት 4:00 ሰዐት እስከ ዕኩለ ቀን 6 ሰዐት ድረስ ብቻ ነው ላጠፋቹት ለወነጀላቹት ወንጀል ተውበት ማድረግ የምትችሉት ከዛ በተቀረ ሰዐት ተውበት ማድረግ አትችሉም ብንባል ወንጀል ሰርተን ተመሳሳይ ሰዐት እስከሚደርስ ምን ያህል መጠበቅ እንዳለብን
በመሀል ምን እንደምንሆን አናውቅም ተፀፅተንም no ያቺን ሰዐት መድረስ አለብህ ማን ወንጀል ስራ አለህ የለም ተቀባይነት ብንባል ? አስቡት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ

ጌታችን ግን አዛኝ ነው ለኛ
ባሮቼ በየትኛውም ሰዐት ተፀፀቱ በየትኛውም ጊዜ ተመለሱ ምድረበዳ ለይ ግመሉ ጠፍታበት ሊሞት ሲል ምግቡን ይዛለት ስትመጣ ከሚደሰተው ባርያ በላይ እኔ በናንተ ወደኔ መምጣት እደሰታለው ከሰማይ እስከምድር በሚሞላ ወንጀል ብትመጡኝ እና ብትፀፀቱ እኔ ከሰማይ እስከምድር በሚሞላ ምህረት እመጣቹዋለው ምን አይነት ጌታ ነው ?
እኛስ ምን አይነት ደረቅ ባሮች ነን ይህን ያህል 😥

አሁንም ይነግረናል ባርያዬ የ ስንዝር ያህል ብትቀርበኝ የክንድ ያህል እቀርበሀው የ ክንድ ያህል ብትቀርበኝ የ እርምጃ ሚያህል እቀርበሀለው እየተራመድክ ብትቀርበኝ በመሮጥ ያህል ፍጥነት እቀርበሀለው ......ምን ያህል የ ላቀ ነው ጌታችን ?
እኛስ ምን ያህል ደረቅ ባሮች ነን 😥

ስለ ጌታችን ማውራት ብንቀጥል አያበቃም የሱ ምህረት ዕዝነት ቃላት አይጨርሱትም የኛን ድርቅናስ ምን ይገልፀው ይሆን ?😥

ዉደደኝ ቅረበኝ የሚል ልዉደድህ ልቅረብህ የሚል ጌታን ጀርባ ሰጥቶ መኖር ልማርህ ያጠፋሀው ጥፋት ለኔ ምንም ነው አንድ እንባ ሁሉንም ያብሰዋል አንተ ብቻ ተመለስኩ በለኝ የሚል ጌታን ምን ይሆን መልሳችን ? 😥

ይህ ግን ሁሌም አይቆይም ሩሀችን ከነፍሳችን በወጣችበት ቅፅበት ነገሩ ይቀየራል እያንዳንዱዋ ከጌታችን ርቀን ያሳለፍነው ሰዐት መሪር ፀፀት ነው ሚሆንብን የቀብር ቅጣት ከ እሳት ቅጣት በላይ ይህን ፍቅር የሚለግሰንን ጌታ ሙሉ ለሙሉ እናጣዋለን 😥

ሰዎች ጊዜ አለን እንመለስ ተውውው ወላሂ ፀፀቱን አንችለውም ነገሩ ቀልድ የሚገባው አይደለም !!

ወርቃማ ንግግሮች

17 Nov, 01:22


~ የንግሥና ባለቤት የሆይከው ጌታዮ ሆይ ፣ ፍላጎቶቼን ለአንተ ሰጥቻችኋለሁ ፣ ጥሩ ከሆነ አሳካልኝ መጥፎ ከሆነ በጥሩ ቀይርልኝ።


ውሎዮን ከአንተ መስመር ያልወጣሁ ሆኜ አውለኝ ፣ በሥራዬም የሕይወትን በሮች የሚከፍትልኝን ብስራት አብሥረኝ ፣…

ይህን ዱዓ በማለት ቀንህን ጀምር። የደስታ በሮች ለልባችሁ ..

~ እንደምን አደራችሁ
~ ሰብሃል ከይር

https://whatsapp.com/channel/0029VawofIrJP20yVRgdBb0D

ወርቃማ ንግግሮች

17 Nov, 01:08


በዋትስ አፕ ቻናል ከፍተናል ተጎራበቱን!!!

https://whatsapp.com/channel/0029VawofIrJP20yVRgdBb0D

ወርቃማ ንግግሮች

15 Nov, 09:40


አንዳንዱ ነገር በኛ ልፋት ብቻ አይወሰንምና ጀሊሉን መለመን ቀደሩን መቀበል ግድ ነው።

ልጅህ ጠማማ ቢሆን ያሳዝናል። እስከለፋህ ድረስ በልጁ ሁኔታ ራስህን አትውቀስ። ነብይ አሳድጎት የሚከፍ*"ርም ልጅ አለ።

ልጆችህ ባይስማሙ ቀልብ ይሰብራል። አንዱ ባንዱ ሲነሳ ያሳዝናል። ሆኖም ራስህን አዛ አታድርግ። ነቢላህ የእቁብ (አሰ) ያሳደጋቸው ልጆች በዩሱፍ ላይ ያደረጉትን አትርሳ።

ሚስቴ ጥሩ ባህሪ ለምን የላትም ብለህ አትገረም። የጠናው ቀደር የገጠመ እለት እንደ ሉጥ (አሰ) ሚስትህ በአመጸኞች ባህሪ ስር አድራ አላህ ካጠፋቸው ሰዎች ትሆናለች።

ባሌ ሀይለኛ ነው አመጸኛ ሆነ ብለሽ ራስሽን አትጉጂ። እስከሆነ ትኖሪያለሽ። ጀሊሉ በሂክማው አስያን በፊርአውን ስር ያሳቀፈ ጌታ ነው። እንደው በደፈናው አግራው እያሉ መኖር ነው።

ሰርቼ ለፍቼ ለምን ሀብታም አልሆንኩም ተብሎ ማማረር አያስፈልግም። መስራቱ እንጂ ሀብታም መሆን እጣህ ላይሆን ይችላል። እንደው የተሳሳተ ትርጓሜ እንጂ ለፍቶ ከሚኖር በላይ ሀብታም ማን አለ?

አላህ በቸርነቱ ዚክርን ተውባን ሰለዋትን ሀምድን ለሁሉም አድሏል። ያለከልካይ የፈለገ ከገኒማው እንዲዝቅ እና በሰኪና ባህር በዚህች አለም እንዲነግስባት ለሁሉም አድሏል። የኖሩት እንደነገሩን በዚህ ባብ ሲኖር ታዲያ ከ physical dimension ወጣ ብለው በሌላ ደረጃ ይኖራሉ። ከዛም ኢማን ይጣፍጣቸዋል።

ኢማን ስኳር ስኳር ወይም ማርማር አይልም። የራሱ ኢማን ኢማን የሚል ጣእም አለው። ረሱል እንዳሉት " 3 ነገሮችን በውስጡ የተገኘበት ሰው የኢማንን ሀላዋ ጣእም ቀምሷል አሉ 1) አላህና መልክተኛው ከነሱ ውጭ ካለ ሁሉ ይበልጥ የወደደ 2) ሰውን ሲወድ ምክንያቱ ለአላህ ብቻ ከሆነ 3) ወደ ኩፍ*ር መመለስን እሳት ላይ ከመጣል እኩል የሚጠላ ከሆነ።

መልካም ጁምአ

☞ Kha Abate 👦

ወርቃማ ንግግሮች

13 Nov, 17:14


ሳኡዲ ያላችሁ ከስልካችሁ ወደ ኢትዮጵያ ካርድ ለቤተሰብ  ከመላክ ከዛዉ ቢገዙ ይሻላል። መላክ ግዴታ ከሆነባችሁ ግን ባላችሁበት ሆናችሁ
➡️ የሳኡዲ ሰዋ ካርድ ባለ 23 ብልኩ
የኢትዮጵያ የ 400 ብር ካርድ
➡️ ባለ 20 ከላካችሁ የ 350 ብር ካርድ  የቤተሰብዎ ቁጥር ላይ በቀጥታ እናስገባለን! ወይም የኢትዮጵያን ካርድ በፎቶ እናስረክባለን እነሱ ቀጥታ እንዲደዉሉላችሁ ደዉለን እናሳዉቃለን
መገኛችን_✍️✍️⤵️
➽ቀጥታ ,ዋትሳብ ,ኢሞ እንዲሁም ቴሌግራም
   ➼ 05 06 32 50 65 ሳቢረት ሰኢድ 📞
መለያችን ፍጥነታችን


☞በቴሌግራም :- @Sabi2425

ወርቃማ ንግግሮች

13 Nov, 04:25


ይህ ቻናል በሀገር ውስጥ ያሉ ስራ አጥ
            ወንድም እህቶች
በአላህ ፍቃድ  የስራ ማግኛ ሰበብይሆን ዘንድ
ታስቦ የተከፈተና የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲስ ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው 

🔗ተቀላቀሉ
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0

ወርቃማ ንግግሮች

12 Nov, 17:43


ሚስትህን
ብቻችሁን ስትሆኑ ውቀሳት
በቤተሰቦችህ ፊት አመስግናት
በልጆችህ ፊት አሞግሳት
ስታገባ ግን ደብቀህ አግባባት😊

(መንቁል)

ወርቃማ ንግግሮች

08 Nov, 21:40


📍በቀን ክፈለ ጊዜ ላይ የሚተኙ ሶስት የእንቅልፍ አይነቶች አሉ እነሱም
(ሀይሉላ ፣ ቀይሉላ እና ዐይሉላ) ይባላሉ።

1 ሀይሉላ / حيلولة
ጠዋት ከፈጅር ቦሃላ የሚተኛ እንቅልፍ ነዉ ።
الحيلولة : هي النوم بعد صلاة الفجر وهي تحول بينك وبين رزقك.
📌 በሰዉዬዉ እና በርዝቁ መሀል መጋረጃ/ግርዶሽ ትሆናለች ፣ ዱኒያዊም ሆነ አኺራዊ ብዙ ማግኘት እና ማትረፍ የሚችል ነገር ታስመልጠዋለች ።
📌ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂወሰለም) አላህ ለህዝባቸዉ የጠዋት ክፍለ ጊዜ ዉስጥ በረካ እንዲያደርግላቸዉ ዱዓ አድርገዋል ፣ ሁሌ በዚህ ሰዓት የሚተኛ ሰዉ ይሄ ዱዓም እንዳመለጠዉ ነዉ።

2 ቀይሉላ / قيلولة
ከዱሃ ሶላት ቦሃላ ወይም ከ ዙህር ሶላት ቦሃላ ለተወሰነ ደቂቃ ጋደም የምትባል እንቅልፍ ናት።

القيلولة : هي النوم بعد صلاة الضحى او بعد صلاة الظهر لمدة 30 دقيقه وهي مفيدة للصحة الجسم للتقوية على العبادة.
📌ለአካል ጤና እጅግ በጣም ጣቃሚ ነዉ።
📌ኢባዳ ላይ ኢንዲያጠናክረዉ ነይቶ የተኛ ሰዉ አጅር ያገኝበታል ።
📌ሶሃባዎች እና በርካታ አኢማዎች ይተኟት ነበረ።

3 ዐይሉላ /عيلولة
ከ አሱር ሶላት ቦሃላ የሚተኛ እንቅልፍ ነዉ።
العيلولة: هي النوم بعد صلاة العصر وهي تسبب علة للجسم والنفس وضيق لصدر.
📌በዚህ ጊዜ መተኛት የተከለከለ መሆኑ እና እጅግ በጣም የጠላ መሆኑን በሰሂህ ሀዲስ ተዘግበዋል ፣ የሚያስተኛዉ በቂ የሆነ ምክንያት/ዑዝር ከሌለዉ በቀር ።
📌በጤናችንም ላይ ለበሽታ ሰዉን ያጋልጣል
📌ለጭንቀት እና የሀሳብ ጥበት ላይ ሰዉን ይጥላል።


እናንተስ በዬትኛዉ ሰዐት ላይ የመተኛት ልምድ ነዉ ያላችሁ? ምን ምንስ ታዝባቹሃል?

ወርቃማ ንግግሮች

08 Nov, 21:36


ልዩ ኸበር - የጥንቱን ፍለጋ፡ ከአንደሉስ እስከ መካ

ከሠላሳ አራት ዓመታት በፊት ነው - እ.አ.አ በ1990፡፡ ስፔናዊው ራፋኤል ፈርናንዴዝ ከእስልምና ጋር ተዋወቀ፡፡ መምሕሩና የጂኦግራፊ አጥኚው ሰው አላህ ልቡን ወደ እውነት ስለመራው ደስታው ወደር አልነበረውም፡፡ ደስታው በትኩሱ ሳለ ለጌታው የገባው ቃል እንዲህ የሚል ነበር - “ሐጅ የማደርገው በፈረስ ተጉዤ ነው”፡፡ ይህ ለወቅቱ ጉልበታም ወጣት በአንድ ጊዜ የሚቻል አልነበረም፡፡ ጉልበት ብቻ አይደለም፣ ጊዜ እና ገንዘብ የሚጠይቅ ቃል ኪዳን ነበር፡፡ ጉልበት፣ ጊዜ እና ገንዘብ ቢሟላም ጽናት የሚጠይቅም ነበር፡፡ ስለዚህ መታገስ ነበረበት፡፡

ከ35 ዓመታት በኋላ የዚያን ጊዜው ወጣት ራፋኤል ፈርናንዴዝ፤ በእስልምና ሥሙ ዓብደላህ ተብሎ የሚጠራ ሆኗል፡፡ አብዱላህ በዩኒቨርሲቲ ባጠናው ጂኦግራፊ፣ በዲግሪ ላይ ሌላ ዲግሪ እየደረበ የዶክትሬት ማዕረግ ላይ ደርሷል፡፡ በትምሕርት ረዥም ርቀት በመጓዝ ብቻ ሳይወሰን ወጣት ሳለ ቃል ኪዳን ገብቶ ያልፈጸመውን ሐጅን በፈረስ ጀርባ ተንጠላጥሎ ወደ ቅዱሳኑ ሥፍራዎች የመድረስ ውጥን ለማሟላት ዝግጁ ሆኗል፡፡

ዓብደላህ በዚህ መልኩ ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ሲነሳ አርዓያ ያደረገው ከ500 ዓመታት በፊት በአንደሉስ ምድር የነበሩ በጀግንነት የሚያወድሳቸውን አያት ቅድመ አያቶቹን ነው፡፡ በርግጥ የፈረስ ግልቢያ መውደዱ፣ ከዚያም ሲያልፍ በአንዳንድ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ማሸነፉ ይህን መንገድ እንዲመርጥ አስችሎታል፡፡ በጉዞው አያት ቅድመ አያቶቹንም አብሮ ያስታውሳል፡፡ ዓብዱላህ የቅድመ አያቶች አንደሉስ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ሥፍራዋ ከፍ ያለ መሆኑንም ያውቃል፡፡ እነርሱ ያን ጊዜ የጌታን ትእዛዝ ለመሙላት ፀሐይ እና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ሀገራትን አቋርጠው ከ8 ሺሕ ኪሎ ሜትር በኋላ ሳዑዲ ዐረቢያ እንደሚደርሱም ከድርሳናት አንብቧል፡፡

ዓብዱላህ ፌርናንዴዝ ያለፉት ዓመታት ይህን ገድል ለመድገም የተጋበት ነበር፡፡ የጉዞ እቅድ ነደፈ፣ ራሱን የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ በማድረግ ይህን ፅናት የሚጠይቅ ጉዞ በማድረግ በርትተው የሚያበረቱን ባልንጀሮች መፈለግ ጀመረና የሕልሙን ተጋሪዎች አገኘ፡፡ እነዚህ የሕልም ተጋሪዎቹ ሙሐመድ ሚስባሂ፣ እስማኢል ጎንዛሌዝ፣ ዑመር ከሪም፣ ሙጃሂድ ኤስፒኖ፣ ዑመር ሚላኒሮ እና ዓብዱልቃድር ሃርካሲ ሆኑ፡፡ ዓብዱላህ ሕልሙን የሚጋሩትን ሰዎች ከማግኘት ውጪ ሌሎች መሟላት የሚኖርባቸው ሎጂስቲክሶችን ለማግኘት እንቅስቃሴውን ቀጠለ፡፡ ሰዎቹን 8 ሺሕ ኪሎ ሜትር አቆራርጠው ሳዑዲ ዐረቢያ ምድር ላይ የሚያደርሱ ብርቱ ፈረሶችን መፈለግ ተጀመረ፡፡ የትኞቹ ዝርያዎች የተሻለ ብርታት፣ ቅልጥፍና እና ጉልበት አላቸው ብሎ መምረጥ ስለነበረበትም በማፈላለግ የዐረቢያ ዝርያ ያላቸው ፈረሶችን ለጉዞው ተስማሚ ሆኖ አገኛቸው፡፡ ፈረሶቹን ማሠልጠንና ምግባቸውን እየመረጡ ጡንቻቸው እንዲፈረጥም ማድረግ የእለት ተእለት ሥራው ሆነ፡፡ ብርታት የሚጨምሩ ተግባራት ሲደረጉ የነበሩት ለፈረሶቹ ብቻ ግን አልነበረም፡፡ የጉዞው ተሳታፊዎችም ይህንኑ ሲከውኑ ቆዩ፡፡ በዚህ ሒደት የሕክምና ባለሞያዎች የሚያስፈልገውን እገዛ እያደረጉ ቆይተዋል፡፡

ቀጣዩ ሒደት የነበረው የፈረሶቹን ጉልበት መለካት ነበር፡፡ እነ ዓብዱላህም ወደፊት የሚጠብቃቸውን ብርታት የሚጠይቅ ጉዞ የሚሞክሩበት ቀን ተቆረጠ፡፡ ለሙከራው የተመረጠው የሰሜናዊ ስፔን ክፍል ነበር፡፡ 2021 ክረምት የመጀመሪያው የፈረስ ጉዞ ተጀመረ፡፡ ዓብዱላህ እና የሕልም ተጋሪዎቹ ለአስራ ስድስት ቀናት ባደረጉት የፈረስ ላይ ጉዞ 700 ከሎ ሜትር መሸፈን ቻሉ፡፡ የፈረሱም የሰውም ጉልበት ተፈተሸ፡፡ ስለ ጉዞው እነ ዓብዱላህ ሲናገሩ “ፈታኝ ቢሆንም ስኬታማ ነበር” ይላሉ፡፡ ጉልበት ከሚፈትሸውና ከሌላው ሁሉ “ጠንካራ ወዳጅነት እንዲኖረን አድርጎናል” ብለዋል፡፡ ይህ ሲጠናቀቅ ሌላ አንድ ዓመት ጠብቀው ሁለተኛው ጉዞ ማድረግ ነበረባቸው፤ አደረጉት፡፡ በአጎራባች ፖርቹጋል በኩል ከሰሜን ወደ ደቡብ የተደረገው የፈረስ ላይ ጉዞ በ2022 የተደረገ ነበር፡፡ ይህ ጉዞ እንደቀደመው ጊዜ 16 ቀናት ሲፈጅ፤ የሸፈኑት 600 ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ይህ ቁጥር ቀድሞ ከተመዘገበው ያነሰ ነው፡፡ እነ ዓብዱላህ ለዚህ ሰበብ የሆነው የአየር ሁኔታው በጣም ደረቅ መሆኑ እንዲሁም “በማናውቀው ሀገር እና ቋንቋ ጉዞውን ማድረጋችን ነው” ሲል ያስታውሳሉ፡፡ ይህ ቢሆንም ለቀጣይ ጉዞ በርካታ ስንቅ የተያዘበት ነበር ይላል፡፡

አሁንም ይህ ብርታት የሚጠይቅ ልምምድ እንደቀጠለ ነው፡፡ ከወራት በፊት ከአንደሉስያ ምእራባዊ አካባቢ የተነሱት እነ ዓብዱላህ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ከረር ባለ ፀሐይ ውስጥ ትግላቸውን ቀጥለዋል፡፡ ቀኑ ከረር ያለ ፀሐይ ቢያስተናግድም ሌሊቱ እጅግ በጣም ቀዝቃዛ የሚባል ስለነበር ከሁለቱ የልምምድ ጉዞዎች ለየት ያለ አጋጣሚ ማስተናገድ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ በዚህ የአየር ጠባይ 420 ኪሎ ሜትር ሸፍነው ተመለሱ፡፡ በተለይ በምሽት በደረሱበት እሳት እያቀጣጠሉ መሞቅ ግድ ነበር፡፡ በፈረስ ላይ ከአንደሉስ ምእራብ አቅጣጫ ወደ ምሥራቅ ተጉዘው ግራናዳ ሲደርሱ የተወሰኑ ሰዎች አቀባበል አደረጉላቸው፡፡

አሁን ልምምዱ አበቃ፡፡ የፈረስ ላይ የሐጅ ተጓዦቹ ቀድመው እቅድ ሲያወጡ አላህ ቢፈቅድ መድረስ የሚፈልጉት በዚህ ዓመት በሚከናወነው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ነው፡፡ ሆኖም ከፊታቸው ስምንት ሺሕ ኪሎ ሜትር መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከደቡባዊ ስፔን ተነስተው፣ ዐስር ሀገራትን ያቆራርጣሉ፡፡ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ስሎቬንያ፣ ክሮሽያ፣ ቦስንያ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ኮሶቮ፣ ሰሜን ሜቄዶንያ፣ ቡልጋሪያ፣ ቱርክ ደርሰው ቀይ ባህርን በጀልባ ተሳፍረው ግብጽ መድረስ ይኖርባቸዋል፡፡ ከግብጽ ደግሞ ቅዱሳኑን ሥፍራዎች ወደያዘችው ሳዑዲ ዐረቢያ መጓዝም አለ፡፡

ይህ 35 ዓመት ያስቆጠረን ቃል ኪዳን ለመሙላት የሚደረገው ጉዞ ከ23 ቀናት በፊት ተጀመረ፡፡ ዶክተር ዐብዱላህ ፌርናንዴዝ ዝግጅቱን ሲጀምሩ ከስድስት ሰዎች ጋር የነበረ ቢሆንም እንደ አለመታደል አሁን የጉዞው ተሳታፊዎች አራት ቀርተዋል፡፡ የእንስሳት ሐኪም፣ ነርስ፣ ምግብ አብሳይ እና ሌሎች ጉዳዮችን የሚያስፈጽሙ ሰዎችም በመኪና ይከተሏቸዋል፡፡ ሕልም የሚመስለው ለአላህ የተገባን ቃል ኪዳን የመሙላት ጉዞ እነ ዓብዱላህ ጥንት አያት ቅድመ አያታቻቸው እንዳደረጉት መነሻውን በአንደሉስ ውስጥ በሚገኘው አልሞናስቴር መስጂድ አድርጓል፡፡ ተጓዦቹ የእለቱ የት እንደደረሱ ኢንስታግራም እና ፌስቡክን በመሳሰሉ ማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ያጋራሉ፡፡ እስከ ትላንት ሐሙሰ ድረስም 935 ኪሎ ሜትር መጓዝ የቻሉት እነ ዓብዱላህ፤ ቀሪ ከ7 ሺሕ በላይ ኪሎ ሜትሮችን ለቃል በመታመን እና ቅዱሳኑን ሥፍራዎች በመናፈቅ ቀጥለዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9384

ወርቃማ ንግግሮች

08 Nov, 20:55


~•

እውነትን የያዙ ሰዎች ሐሰተኞችን ከመቃወም ዝም ሲሉ ሐሰትን የያዙ ሰዎች በእውነት ላይ እንዳሉ ይሰማቸዋል።

[ዐሊ ኢብን አቢ ጣሊብ]

ወርቃማ ንግግሮች

03 Nov, 14:21


አብዛኛዉ ሰዉ ቁርዓን እየቀራ ሱጁድ ያለበት አንቀፅ ላይ ሲደርስ በሱጁድ ላይ ምን እንደሚባል አያዉቅም።

ይሀዉላችሁ የሱጁድ ዱዓዉ/ ዝክሩ

اللهم لك سجدت و بك آمنت ولك أسلمت سجد وجهي للذي خلقه وصوره وشق سمعه وبصره تبارك الله أحسن الخالقين

አለሁማ ለከ ሰጀድቱ ወቢከ ዓመንቱ ወለካ አስለምቱ ፣ ሰጀደ ወጅሂ ሊለዚ ኸለቀሁ ወሰወረሁ ወሸቀ ሰምዐሁ ወበሰረሁ ፣ ተባረከላሁ አህሰነል ኻሊቂን።

👌ቢሸመደድ ይወደዳል።

ወርቃማ ንግግሮች

31 Oct, 02:27


ደስ የሚለው የአኺራ ጉዞ ላይ የቀደመ የውድቀት ታሪክህ መጪውን ስኬት አይወስንም። ዛሬ አንድ ብለህ መጀመር ትችላለህ!
የፊርዐውን ድግምተኞች ምስክር ናቸው። "በሙሳ እና በሃሩን ጌታ አመንን" ባሉ ጊዜ የልቅና በር ወዲያው ተከፈተላቸው! የተዋረዱት ድግምተኞች ታላላቅ ወልዮች ሆኑ!
#በተውበት
#በኒያ
#በትጋት
ነገህ የተሻለ እንደሚሆን አትጠራጠር👌

16,634

subscribers

1,125

photos

213

videos