ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨) @fkr_eske_jenet Channel on Telegram

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

@fkr_eske_jenet


ሀላሌ ነሺ አሉ !!

ከወንዶቹ ሁሉ አይንሺ ለኔ አድልቶ
ልብሽ ከወደደኝ ሁሉን ነገር ትቶ
ወላጅም ከሰጠ ሽማግሌ መጥቶ
ኒካህ ከታሰረ ሁሉም ተመቻችቶ
ልቤም ይረጋጋል ያሰብኩት ተሞልቶ፡፡

📝 ወንድማችሁ ራማስ ኢብኑ በድሩ 🍃


ለአስታያየትዎ ☞ @fkr_eske_Jenet_Bot

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨) (Amharic)

የዚህ ቦታ ስለሆነ ከፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨) ተመሳሳይ መረጃ እንደሚለዋወጥ አስተያየቶችን እና መረጃዎቹን እንዲያስተካክሉ የቦታውን እይታይታ ገልብለዋል። ይህ ቦታ ግንባታ በኢትዮጵያ በጣም የሚገኙት አባላት በዚህ ቦታ ላይ የሚሾመውን ፍቅሩን እና ጀነቱን እንደሚያዝናቸዋሻል። እንደጨዋፍ በሽቆት ሊያጉርጉር ላይ የምንችልበት ስለሆነ በምክንያቱ ለመናገር የቦታውን ማስተማር ይችላሉ። ለእነሱ ራሱ መረጃዎችን መነሻ እና ማከብከብ ማየት እንችላለን። እና በግለሰብ ተዘጋጅቷል። እንዲሁም ለአስታያየትዎ የቦታውን ይቅርታ አድርጉ። በመስራት ከፍቅሩ እስከ ጀነት የመሰረታዊ ስልጣን በማድረግ ይህ ቦታ መነሻ የሚያድርጉትን ጥሪቶች እና መረጃዎችን እንድናከብክ በሚመልከቱ ስፖርቶች ላይ ይህንን ቀረብ በቁምፊ ቀልቦት ይሞክሩ። ወደ ቦታው ተጨማሪ ይምረጡ።

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

11 Jan, 18:59


አንድ ከእናንተ ሂወት መማር ያለብኝን ነገር ከታች ባለው ቦት ፃፉልኝ ። 👇

@fkr_eske_Jenet_Bot

👆

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

10 Jan, 04:08


በህልማችንና በምኞታችን መካከል እንዲሁም በቀደርና በእድል መካከል አላህ ከፃፈልን ነገር በስተቀር የሚሆን ነገር የለም !!!

━━━━✦🌹🌹✦━━━
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

08 Jan, 05:25


😋
📣የዳዕዋህ ፕሮግራም

😓የፕሮግራሙ አቅራቢ፦
1️⃣ኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አልባጂ
ርዕስ፦ስለ ተቅዋህ
2️⃣ኡስታዝ አቡ ሒበቲላህ
ርዕስ፦ስለ ሞት
3️⃣ኡስታዝ ኑረዲን አል ዐረቢይ
ርዕስ፦ስለ ሶብር


✈️መድረክ መሪ፦ወንድም አቡ ሑዘይፋህ

0️⃣0️⃣0️⃣የሚተላለፍበት ቻናል፦
📥📥📥📥📥📥
t.me/tdarna_islam

😮ዛሬ እሮብ ከምሽቱ 3:30😓

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

07 Jan, 11:20


እየሱስን አምላኪዎች ‼️

የእየሱስ ባሮች ሆይ አንድ ጥያቄ አለን
የተረዳ ካለ መልሱን እንሻለን ?

ጌታ ግፍ አቅቶት ሰወች ከገደሉት
አለቀ አከተመ የታል አምላክነት ?!
ሰወቺ የሰሩትን በሱ ላይ ሲያደርሱ
ጌታ ግብራቸውን ፈቅዶ ነው በርሱ
ባደረሱት ሁሉ አልፎ ከተከፋ
አንግድህ ምን ይባል
ሀይሉ ከኮሰሰ ሀይላቸው ከሰፋ ?

ግን እንጠይቃለን ለመልስ አትንፈጉ
ማለባበስ ይቅር ይመለስ በወጉ
ፈጣሪዋን አጥታ ዐለም ስትዋትት
ሰው ወደ ማን ነበረ የሚያስበው ፀሎት?
ፋጡር ፈጣሪውን ሲያደበየው
ሰባቱን ሰማያት ማ ነበር ያቆየው ?


ምስማር ተቸንክሮ ሲያሸልብ ፈጣሪ
አለም ቀርታ ነበር ያለ አስተናባሪ?
የሰማይ መልአክት ምንኛ ለገሙ ?!
እጁ ተሰንክሮ ዋይታውን ሲሰሙ፡፡
እንጨቱም ታምር ነው አቅሙ መቋቋሙ
አምላክ ያክል ነገር ችሎ መሸከሙ
ስለቱ ጭካኔው ብረቱ ምስማሩ
አካሉን ሠንጥቆ ስቃይ ማሳደሩ
ጉድ በሉ ይሄ ጌታ በአይሁድ የሚረታ
ማጅራቱን ታንቆ ታስሮ የሚመታ


ኀላስ ራሱ ነቃ ከሞት አንሰራራ
ወይስ ጌታ አገኝ ህይወት የሚዘራ?!
ጉድ በሉ ለቀብር ጌታ አቅፎ ለያዘ
የባሠም ሆድ አለ እምላክ ያረገዘ
ዘጠኝ ወር ታሺጎ ሲኖር በጨለማ
ሀይድ እየተጋተ ደም እየተጠማ
ብልት ቀዶ ወጣ አቡሹ ህዓኑ
አፉን ለጡት ከፋቶ አቤት ማሳዘኑ!


አስቡት ይሄን አምላክ ሲጠጣ ሲበላ
ከዚያም ያስገባውን ሲያስወጣ በሌላ
ጌታየ ከፋ አለ ከክርስቲያን ቅጥፈት
ሁሉም ይጠየቃል ለቀባጠረበት
የመስቀል ባሮቺ ሆይ ግራ ገባኝ አኔ
ያሽቀነጠረው ስው ፅድቅ ነው ኩነኔ
ማቃጠል ሰባብሮ ፈቃጁን ጨሞሮ
ህሊና ከዚህ ውጭ ይፈርዳል አዕምሮ
አምላክ አቅም አንሶት ለተፈጠረበት
ሰብሮ እንደማቃጠል ጭራሽኑ አምልኮት?!


እውነትም እርጉም ነው ለምንስ ይዘንጋ
በመሳለም ሳይሆን በእግር ይሰጥ ዋጋ?!
ለተዋረደበት ጌታህ ከነነፍሱ
አንተ ካመለከው የሱ ነህ የነሱ

ጌታህ ስለ ዛለ ከሆነ አክብሮቱ
አስተዋሽ ቅርፃ ቅርፅ ቢሆንጂ አንጨቱ
መስቀሉ ከጠፋ ሺ ስንት አመታቱ?!


እንዲያ ከሆነ ሂሳቡ ቀመሩ
ለመስገድ አትቧዝን በየ መቃብሩ
ያስተውሳልና ነገረ ስርአቱ
ጌታህ ከአፈር በታች ለነበረበቱ
የክርስቶስ ባሪያ ሆይ ንቃ ተረጋጋ
ይህ ነው እውነታው ከአልፋ እስከ ኦሜጋ፡፡

ይገነዘቡት ዘንድ ሼር አድርጉት ።
●▬▬▬▬๑۩🌹۩๑▬▬▬▬
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

06 Jan, 04:03


ውዴታ እኮ ማለት  አቡበክር የሆነ ሰሀባ ምን ያስለቅስሀል የአባ በክር ብሎ ሲጠይቃቸው ...? የአላህ መልዕክተኛ  ﷺ ሲያለቅሱ አይቼ አለቀስኩ ማለታቸው ነው ።

ውዴታ ማለት  የአላህ መልዕክተኛ ﷺ
"በአዒሻ አትጉዱኝ " እንዳሉት ነው ።

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ለእናታችን አዒሻ የኔ ውዴታ ላንቺ ገመድ ላይ የተቋጠረ ቋጠሮ ነው ማንም የማይፈታው ማለታቸው ነው። 

እናታችን አዒሻም እየሳቀች አልፎ አልፎ ቋጠሮው እንዴት ነው ብላ ትጠይቃቸው ነበር ረሱል ( ﷺ ) እንደዛው ነው ይሏት ነበር ።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Jan, 19:47


የገንዘብ ባሮች !!!!

ሃገራት በገንዘብ ተሽጠዋል። ክብር በገንዘብ ተቀይሯል። ቤተሰብ በገንዘብ ተበትኗል፤ ጓደኛሞች ለገንዘብ ሲሉ ተለያይተዋል። የሰው ነብስ ለገንዘብ ሲል እንዲሁ መና ቀርቷል።

በጥቅሉ ሰዎች ለገንዘብ ሲሉ ያደሩ ባሮች ሆነዋል !!!

አላህ አንዲህ አለ ፡-

وَتُحِبُّونَ الْمَالَ حُبًّا جَمًّا

ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡

ለገንዘብ ያለን ውዴታ በልኩ ይሁን ፡ አንዳዱ ለብር ሲል ነፍሱ ልቶጣ ይደርሳልኮ ሱብሀንሏህ !!!


@FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Jan, 19:37


አሏህ ለሁላችንም የተለያየ ችሎታ ሰቶናል እራሳችንን እንሁን ማንነታችንን እንቀበል ምክንያቱም ስለታሙ ምላጭ ዛፍ መቁረጥ እንደማይችለው ሀሉ ጠንካራው መጥረቢያም ፀጉር መላጨት አይችልም። 
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅ 🍃
➢t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Jan, 19:33


ለሀሰት ከመኖር ትክክለኛ ለሆነው ነገር መሞት ይሻላል ።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Jan, 05:43


👑          ⭐️             ⚡️
ٰ    • ○ ° 🌹🌹🌹• ○ °• ○ °• ○ °
 • ○    🌹🌹🌹🌹    • ○ °  👈አበባውን
• ○ °🌹🌹🌹🌹🌹           በመንካት• ○ °
  • 🌹🌹🌹🌹🌹🌹    ብቻ ምርጥ
○ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹    የሱና 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡  ° :.
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹         ያገኛሉ📡
 • 🌹🌹🌹🌹🌹      ° :.   * • ○       
• ○  🌿🌹🌹🌿      
  • ○ °   🌿🌿            👈
     •        🌿   • ○ °        🌿🌿
 • ○ °        🌿     • ○ ° 🌿🌿🌿
   • ○ °         🌿       🌿🌿🌿🌿
    • ○ °          🌿  🌿🌿🌿🌿🌿
        • ○ °       🌿   🌿🌿🌿🌿
      • ○ °         🌿  🌿🌿🌿
          • ○ °     🌿  🌿° :. * • ○
         °• ○ °      🌿° :.   * • ○
                    🌿° . °☆  . * ● ¸
.    ★  🌿° :.   * • ○ °
        ° .     🌿. * ● ¸
                  🌿       በቀላሉ ይቀላቀላሉ ።
☆  . * ● ¸ .
★ ° . *   ° . °☆  . * ● ¸
.    ★  ° :.   * • ○
🅰️🅰️🅰️⭐️🔗🔡🔡🔡
ለተጨማሪ ሀሳብ አስተያየት  ጥቆማ
@twhidfirst1 ⭐️🔗🔡🔡🔡

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

04 Jan, 03:39


የአላህ ዉዴታ ያሳሰበው አንድ ደረሴ

❝ ሸይኻችን ሆይ አላህ ከሚወዳቸው መካከል መሆኔን እንዴት ላውቅ እችላለሁ?❞  አላቸው።

❝ ልጄ ባይወድህማ ኖሮ ስለ ዉዴታው አያሳስብህም ነበር።❞ አሉት።
 
አላህ ከወደዳቸው ባሮቹ ያድርገን 🤲

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Jan, 10:49


🗡

ሁሉም አብረው ቢሰሩ ቢተባበሩ ወንድማቸውን በቀላሉ መርዳት እና ማዳን ይችሉ ነበር፣ ነገር ግን ወንድማቸው ሲበላ ቆመው በማየታቸው ሁሌ እንደተጠቁ ይኖራሉ።

አሁን ያለው የአለም ሙስሊሞች መዘናጋትም ከዚህ የተለየ አይደለም !!!

አሏህ ለተጎዳ የሚያዝን እና መርዳትን የሚወድ ልብ ያድለን!

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Jan, 04:08


እንዴት ይሆን ?

#ሙአዝ ኢብን ጀበልን ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም "አንተ ሙአዝ ወላሂ እወድሃለሁ "ያሉት ቀን እንዴት እንቅልፍ ወስደው!?

#አልይ ኢብን አቢ ጣሊብስ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አንተኮ ለኔ ለ ሙሳ ሃሩንን እንደማለት ነክ ያሉት ቀን እንዴት እንቅልፍ ወሰደው!?

#አስሩ ሰሀቦችስ በ ጀነት የተበሰሩ ቀን እንዴት ተኙ!?

#ዘይድ ቢን ሀሪስስ አላህ ቁርአን ላይ ስሙን እንዳወሳው የ ነገሩት ቀን እንዴት ተኛ!?

#ውዱ የ ሀበሻዉ ቢላልስ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም "ጀነት ዉስጥ ኮቴህ ይሰማኛል "ያሉት ቀን እንዴት ተኛ!?

የኛ ዉድ ነቢይ ሰላትና ሰላም በአንቱ ላይ ይሁን ﷺ

══ •⊰✿ 🌹 ✿⊱• ═
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Jan, 03:56


🍃ሁሉንም ነገራቶች የምንፅፋቸውና የምንናገራቸው ቢሆንም በልብ ላይ የሚቀሩ ከንግግር በላይ የሆኑ ነገራቶች አሉ።🍃

  ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

02 Jan, 12:37


🍃   ራሀቱል ቀልብ  🍃
https://t.me/Rahetulqelb

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

01 Jan, 11:46


የሰውን ልጅ ሀዘኑን እንደ መደበቅ የሚያሰቃየው ነገር የለም።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

01 Jan, 11:42


🎁ታላቅ የሙሓደራ   ፕሮግራም📱


በ ግሩፕ  ላይ  የዳዕዋ  ፕሮግራም  አዘጋጅተን  እየጠበቅናችሁ  እንገኛለን።

ተጋባዥ

⭐️ኡስታዝ ኸድር አህመድ
⭐️ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ አል-ባጂ
⭐️ኡስታዝ ዶ.ሰዒድ ሙሳ
⭐️ኡስታዝ አቡ ሱፊያን
⭐️ኡስታዝ አቡ ሙአዝ
⭐️ኡስታዝ አቡ ዐብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
⭐️ሼህ አውል አል_ከሚሴ(አቡ አማር)

መድረኩን የሚመሩልን ወንድሞች
አቡ ኹዘይፋ ሰኢድ
አቡ ሂበቲላህ ሁሴን
አቡ ፈዉዛን አብዱ ሽኩር
በእለቱም ታላቅ የምስራች ይኖረናል ሁላችሁም በጉጉት እንድትጠብቁን እናሳስባለን።

❄️የፊታችን ጁማዓ✈️

ሰአት ⭐️ ከምሽቱ 3⃣:0⃣0⃣ጀምሮ

  ሙሓደራው  የሚካሄድበት  ግሩፕ
መርከዝ አቡ ፈውዛን
    👇👇👇

t.me/merkez_abu_fewzan
t.me/merkez_abu_fewzan

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

01 Jan, 07:35


የምታውቁት ሰው ሲጠላችሁ፤ በማታውቁት ሰው አሏህ ይክሳችኋል።

ነብዩሏህ ዩሱፍን የሚያውቁት ወንድሞቹ ሸጡት የማያውቁት ግብፆች አነገሱት።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

01 Jan, 05:59


#ወቅታዊ_መረጃ

📌ትናንት 18 ጊዜ ዛሬ 21ጊዜ በአጠቃላይ  በ48 ሰዓታት ውስጥ 39 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሟል።

📌ትናንት ምሽት 4:117// 4:18,// 4:20 ሰዓት ገደማ በሬክተር ስኬል 5.0 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ መከሰቱን ተከትሎ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ንዝረቱ መሰማቱ ተገልጿል።በምስሉ የሚታየው የመኖሪያ ቤት ጉዳት አፋር ክልል ፈንታሌ አካባቢ ያጋጠመ ነው።
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
➢ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

07 Dec, 09:31


አዳምጠኝ ወዳጄ !

ለእነርሱ በቂ የሆነው ምክንያት አንተ ስትሰማው ሊቀየር አይችልምና ካልነገሩህ ለምን ብለህ አትጠይቃቸው፤ ካላካተቱህ እንዴት ብለህ ግራ አትጋባ፤ ካልጋበዙህ በፍፁም አትሒድ፤ ካገለሉህ እንዴት ብለህ አትጠይቃቸው። በህይወታቸው ቦታ እንዳለህ የምታውቀው አንተ ጠይቀህ ሳይሆን እነርሱ የሚያደርጉትን አይተህ ነው። ጊዜ አላፊና አላቂ ነው፤ አቅም የሚባክንና የሚሸረሸር ነው፤ ስሜት የሚዋዠቅና የሚወድቅ ነው። ያለአግባብ፣ ያለምክንያት በማይሆን ሰው፣ በማይሆን ስፍራ የሚባክን ነገር ደግሞ ያማል፤ አንጀት ይበላል፤ ያሳዝናል፤ ይቆጫል። እናም ካላጠበከው ሰው ያልጠበከው ነገር ቢገጥምህ እንኳን ብዙ አትገረም፣ ብዙ አትደነቅ፤ ግራ አትጋባ፤ ይልቅ እውነተኛውን ቦታህን ለማወቅ ተጠቀመው።

አዎ! ጀግናዬ..! በሰዎች ህይወት ውስጥ ያለህ ስፍራህ የምትጠይቀው ሳይሆን የሚሰጥህ ነው። ምናልባት ካልጠየክ የማታገኘው ስፍራ ሊኖር ይችላል አንተን የፈለገ፣ እገዛህን የሚሻ ሰው ግን ጥያቄህን አይፈልግም፤ አይጠብቅም። ሰው ፈልጎ ሊረሳህ ይችላል፤ አውቆ ሊዘነጋህ ይችላል፤ አስቦበት ሊያስቀርህ፣ ከህብረቱም ሊያስወጣህ ይችላል። ሁን ተብሎ በተፈፀመብህ ተግባር በእራስህ ላይ ጥያቄ አታዝንብ፤ ማናቸውም ያድርጉት ማናቸው ሃሳባቸውን ተቀብለህ ማንነትህን አሳይ፤ አንተን ባለማካተታቸው እራሳቸውን እንዲወቅሱ አድርግ፤ መዳብ የመሰለ እንቁ እንዳጡ አሳያቸው፤ ክብርህን ጠብቀህ እራስህን አስከብር። መግፋታቸው እሾህ ሆኖ እስኪወጋቸው በእራስህ ማማ መታየትህን አታቁም። ተሽለህ ተገኝ፤ ደምቀህ ታያቸው። መሪ መሆን በነበረብህ ቦታ ውስጥ ለምን ረዳት እንኳን አልሆንኩም በማለት አተከራ ውስጥ አትግባ፤ ጊዜህን አታባክን። ቦታህን እወቅ፤ ክብርህን ጠብቅ። ታግለህ የምታገኘው የሰው ትኩረት፣ በግዴታ የምትገዛው የሰው ልቦና እንደሌለ እወቅ።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
➳ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

07 Dec, 04:33


🌹እሱ ነው ምኞቴ 🌹

ኢማኑ የሞላ ያማረ በሱና
ቀጥ ብሎ የያዘ የአላህን ጓደና
ለአኼራው ሚሰራ ዱንያን ያለወደደ
እሱ ነው ምኞቴ አላህ ከፈቀደ
ባለዉ የተብቃቃ እዉነትን የያዘ
ከሀራም የራቀ ለአላህ የታዘዘ
ቢድአን አርቆ ሽርክን ተጠንቅቆ
ከብሬን የሚጠብቅ ክብሩን አስጠብቆ
የወደፌት ህልሜ የሀሳቤ ተጋሪ
አሡን ነዉ ምኞቴ ቢልልኝ ፈጣሪ

እሱ ነው !

@FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

06 Dec, 04:27


የሠው ልጅ  አዳማጭ እንጂ መፍትሔ ሰጭ አይደለም ሰለዚህ ችግርሽን ለሠው ሣይሆን ለፈጣሪሽ ንገሪው ያረብ በይና ለምኝው መፍትሔ ይሰጥሻል ኢንሻ አላህ !! 🍃

➳ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

06 Dec, 03:52


🍃   ራሀቱል ቀልብ  🍃
https://t.me/Rahetulqelb

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Dec, 20:50


__

ሁሉም ሠው ፊቱን ሲያዞርብኝ እሷ ግን
በእኔ ፍፁም እምነት ነበራት” ይላሉ ረሱል (ﷺ)


ረሱል (ﷺ) ስለ ባለቤታቸው ኸዲጃ ምርጥነት ሲመሰክሩ አየሽ እህቴ !

መልካም ሚስት ቤተሰቦቿም ሆኑ የእሱ ቤተሰቦች እንዲሁም በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች በባሏ ላይ ቢነሱና መልካምነቱን ቢያገድፉ ቢያስተባብሉ እሷ ከባሏ ጎን ሁና ታበረታታዋለች አይዞህ ትለዋለች
ምክኒያቱም ከእሷ የበለጠ ሰለ ባለቤቷ መልካምነት ማንም አያውቅምና ለዛ የመጣውን ሁሉ ከሱጋ ትጋፈጣለች እንጂ እጅ አትሰጥም የመልካም ሴት መገለጫውም አንዱ ለባሏ ታማኝና ታዛዥ ሚስት መሆን ነው።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
➳ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Dec, 03:52


ትላንት አልፏል ፤
ነገ ሚስጥር ነው፤
ዛሬ ስጦታ ነው። 🌱 🌹

መልካም ቀን ጀግናየ🤚

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
➳ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Dec, 03:47


የሰዉ ልጅ

የሰው ልጅ ትንሽ ስህተት ከሰራህ
ያሳለፍካቸውን ውብ ነገሮችን እንዳለ
እንዳልሰራህ አድርገው ያፈርሱታል‥

አላህ (ሱብሀነ ወተአላ) እዝነት ስፋት ደግሞ አንዴ ባደረግካት እውነተኛ ተውባ ሰበብ ያሳለፍካቸውን መጥፎ ወንጀሎችህን ሁሉ እንዳልነበሩ ያብሳቸዋል/ወደ መልካምም
ይቀይራቸዋል።

አልሃምዱሊላህ የኛ ጌታ ! 🍃
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
➳ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Dec, 03:35


🍃   ራሀቱል ቀልብ  🍃
https://t.me/Rahetulqelb

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Dec, 17:38


🌹ጉዳዩን ሁሉ ለአላህ የተወ አላህ እሱ ከተመኘው በላይ ይሰጠዋል!!
                     
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

➳ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Dec, 16:06


#ጥቆማ

ማንኛውም አይነት ከሸሪዓ ጋር የማይጋጩ የስራ ማስታወቂያዎችን በአንድ ፕላትፎርም ላይ ማግኘት ከፈለጉ Halal Jobsን ይቀላቀሉ!

አዲስ ስራ ለሚፈልጉ፣ ስራ መቀየር ላሰቡና የተሻለ የስራ አማራጭ ለሚፈልጉ ሐላል ጆብስ ቤታቸው ነው። እንዲሁም ቀጣሪዎች የስራ ማስታወቂያቸውን በነፃ እንዲለቁበት በማሰብ የተዘጋጀ ፕላትፎርም ነው!

ይወዳጁን! ይከታተሉን! ወዳጅዎንም ይጋብዙ! ያተርፉበታል!

ቻናል👉 
t.me/HalalJobsEth

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

26 Nov, 17:55


ስትሞት የሌላ ሰው ህይወት አይቆምም።
ሁሉም ሰው በተለመደው ህይወቱን ይኖራል፣ ቤተሰቡን ይመራል። አንተ ግን ትረሳለህ። አፈር አልብሰውህ ከተመለሱ በኋላ ርዕስ ተቀይሯል።
ከሞት በኋላ ላለው ህይወትህ ከመልካም ሥራህ በስተቀር ማንም አይጠቅምህም።
              
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
~
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

24 Nov, 19:55


በክህደት አትሰበሩ!

እምነቱን የበላ ሰው ፍርዱ ከምድር ሳይሆን ከአሏህ ነው፣ አልታየውም ብሎ በድብቅ በወዳጁ ላይ ሸፍጥ የሚሰራ ሰው ቅጣቱ ከሰው ሳይሆን ከአሏህ ነው። ከእናንተ የሚጠበቀው ማመን ነው፣ አምናችሁም ሁሉ ነገሩን ለፈጣሪ ስጡት። አምናችሁት፣ ልባችሁን ከፍታችሁለት፣ ራሳችሁን ሰጥታችሁት፣ በራሳችሁ ላይ ሾማችሁት ሳለ እርሱ ግን እምነታችሁን በልቶ፣ የሰጣችሁትን ሀላፊነት ሽሮ፣ የክህደትን ካባ ቢያከናንባችሁ በቅድሚያ ሰውነቱን አስታውሱ፣ በቀጣይነት ምክንያቱን አስተውሉ፣ በመጨረሻም ለራሳችሁ ደህንነትና ውስጣዊ ጤንነት ብላችሁ ለፈጣሪ አሳልፋችሁ ስጡት። ክህደት ትልቅ የልብ ስብራትን ያመጣል፣ ክህደት ያለፈውንም የሚመጣውንም ህይወት ጥላሸት ይቀባዋል፣ ክህደት በቀላሉ ለማይሽር ጠባሳ ይዳርጋል። የሰው ልጅ ለምን የገዛ ወዳጁን፣ ብዙ ክፉና ደግ አብሮ ያሳለፈውን፣ አንድ ሰሞን "የልቤ ነው።" የሚለውን ሰው እንደሚከዳ ቢመረመር ምናልባትም ይሔን ያህል ሚዛን የሚደፋና የሚያሳምን ምክንያት ላይገኝ ይችላል። የክህደት ገፈት ቀማሾች እናንተ ብቻ አይደላችሁም። ክህደት ትናንተ የነበረ፣ ዛሬም ያለ፣ ነገም እንዲሁ የሚኖር ክፉ ተግባር ነው።

አዎ! በክህደት አትሸበሩ፤ አንድ ያመናችሁት ሰው ቃሉን ስላጠፈ ራሳችሁን አትውቀሱ፣ በሌላው ጥፋት ራሳችሁን አትቅጡ። ቢዘገይ እንጂ ማንም ሰው የእጁን ማግኘቱ አይቀርም። ማንም ቃላችሁን በልቶ፣ ልባችሁን አድምቶ፣ ተስፋችሁን አጨልሞ፣ ህይወታችሁን አመሰቃቅሎ አይቀርም። የስራውን የምትሰጡት እናንተ ሳትሆኑ የእናንተንም የእርሱንም ልብ የሚያውቀው ፈጣሪ ነው። እናንተ ምንም ብታደርጉ አንዴ የተሰበረ ልባችሁን ልትጠግኑት አትችሉም። መፍትሔያችሁ አንድና አንድ ነው። እርሱም ራሳችሁን ብርታትና ፅናቱን እንዲሰጣችሁ ለአሏህ መስጠት፣ የከዳችሁን ሰውም እንዲሁ ለአሏህ አሳልፎ መስጠት። እናንተ ምን በወጣችሁ  በሰው ጥፋት ራሳችሁን ትቀጣላችሁ? እናንተ ምን ለማግኘት ያሳመማችሁን ሰው በልባችሁ አዝላችሁ ትኖራላችሁ? ጥፋት ሳታጠፉ የማንንም በደል አትቀበሉ፣ በሰው መበደላችሁ ሳያንስ ዳግም ራሳችሁን አትበድሉ። በወቅቱ ሁኔታውን መቀቡል ከባድ ቢሆንም ስራው ያውጣው የማለት ብርታት ይኑራችሁ። ያመናትን ሰው የከዳች ነፍስ መቼም ረፍት እንደማታገኝ አስታውሱ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሰውን ማመንህ ሞኝነት አይደለም፣ ራስህን አሳልፈህ መስጠትህ ጥፋት አይደለም። ምናልባትም ጥፋት ሊሆን የሚችለው ሁሉም ሰው ልክ እንዳንተው ታማኝና ቃሉን የሚጠብቅ እንደሆነ ማሰብህ ሊሆን ይችላል። አንዳንዴ ያንተ ታማኝ መሆን ከመከዳት ላያድንህ ይችላል፣ ያንተ ጥሩና ሩህሩህ ሰው መሆን ከመገፋት ላያድንህ ይችላል። ህይወት እንዲህ እንደዚህ ነች። አንተ ከልብህ ታማኝ የልቤ የምትለው ሰው ግን ከዳተኛ፣ አንተ መልካም ሰው የእኔ ብቻ የምትለው ሰው ግን አስመሳይ መሰሪ ሊሆን ይችላል። እውነታውን ከመቀበል ውጪ ምንም አማራጭ የለህም። የሰው መጫወቻ መሆንህ ሳያንስ በገዛ ራስህ አትጫወት። አንዴ የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም፣ አንዴ የተሰበረ ልብህም እንደቀድሞ ሊሆን አይችልም። እውነታውን ለማድበስበስ አትሞክር፣ የሆነብህን አምነህ ተቀበል። ዓለም ከጥቂት ከሃዲዎች በላይ ልክ እንዳንተ ባሉ ብዙ ታማኞች የተሞላች እንደሆነች እወቅ። ሰው ያቆሰለውን ልብህን አሏህ በሰው ዳግም እንደሚያክመው እመን።

~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

24 Nov, 19:42


ሐሰን አል-በስሪይ

☞በጣም ምቹ የሆነ ስፍራ ላይ መጠን ያለፈ ኩራት ወይም ደስታ አይሰማችሁ አደም (ዐለይሂ ሰላም) ካጣጣሙት ጀነት የተሻለ ሥፍራ የለምና !

▪️ብዙ ኢባዳ ስለምታዘወትሩ ትልቅ ኩራት አይሰማችሁ ያን ሁሉ ኢባዳ ያከናወነውን ኢብሊስ መጨረሻ አስታውሱ!
            
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

23 Nov, 19:36


ሀቢብቲ

ብትስቂ ብታለቅሽ ህይወት መንገዷን   አታቆምም...ነፍስሽን ጭንቀት አታሸክሚያት ከጭንቀትሽ ምንም አታተርፊም !

ከሌሎች ሰዎች የተሻልሽ ለመሆን አታስቢ ነገር ግን መጀመርያ ከነበርሽበት ማንነትሽ የተሻለች ለመሆን ጣሪ !!!

~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

23 Nov, 07:11


አሏህ ሀጃችሁን ሁሉ ይሙላላችሁ !!!

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

23 Nov, 03:42


የሱፍን መግደል ፈለጉ ተረፈ ፤ የአባቱ ውዴታ እንዲጠፍ አራቁት የአባቱ ፍቅር ይባስ ጨመረ ፡፡ ባሪያ እንዲሆን ሸጡት ባለ ስልጣን ሆነ። ወዳጄ የሰው ልጂ ሴራ ምንም ያክል ቢገዝፍ የአላህ ወሳኔ ከሁሉም የበላይ ነው፡፡

@Fkr_eske_jenet

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

22 Nov, 19:02


«ባል ሆይ»

ባለቤትህ የሚያስፈልጋት ማረፊያና አስቤዛ ብቻ አይደለም!
ከምንም ነገር በላይ...

እልህን የሚያጠፋ መልካም ንግግርን፣
ልቦናን የሚገራ እዝነትና ቅንነትን፣
ልፋቷን የሚያስረሳ ርህራሄን፣
ትፈልጋለችና ተንከባከባት።


= t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

22 Nov, 18:52


የዓለም ምኞቶች እንደ ባህር ውሃ ናቸው ከእነሱ ብዙ ስንጠጣ ይበልጥ እንጠማለን፤

ዱንያ እንዲናት በቃ መቼም አትጠግብም የሰው ልጅን አፍ አፈር እንጂ አይሞላውም


~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

22 Nov, 18:44


በምድር ላይ ለወንዶች ከተሰጡ ጸጋዎች ሁሉ ላቅ ያለና ማራኪ ስጦታ ቢኖር  ሚስት ነች። ሚስት ልዩ ቦታ የሚሰጣትና ትልቋ የዱንያ ኒዕማ ባትሆን ኖሮ ጌታችን በጀነት  ለወንድ አማኞች ስላዘጋጀው አጓጊ መስተንግዶ ሲነግረን  ሁረል ዒንን በቀዳሚነትና በተደጋጋሚ ባልጠቀሰልን ነበር።

@FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

21 Nov, 05:19


አንዳንዴ ወደ ሂወታችን ዝም ብለው ባጋጣሚ የገቡና እኛጋ ቦታ የሌላቸው የነበሩ ሰዎች ለእኛ በጣም አስፈላጊ ሰዎች ሆነው ይገኛሉ።

@FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

21 Nov, 03:37


ዛሬ በምታገኘው ተስፋ እንጂ
ትላት ባጣሀው ነገር በፀፀት አትኑር

ዛሬ ሌላ አዲስ ቀን ስለሰጠን
አልፍ አልሀምዱሊሏህ !!!

~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

20 Nov, 18:59


ኢማሙ አህመድ ስለሚስታቸው ጥሩነት ምስክር ሲሰጡ እንዲህ አሉ፡-

"ሚስቴን አሏህ ይዘንላትና 20 አመት አብረን ስንኖር አንድም ቀን በአንዲት ቃል እንኳን ተጋጭተን አናውቅም ነበር"።

(ረህመቱላህ አለይሁም)

ምንጭ:-አስ~ሲየር [333/11]

አላህ ምንኛ ደረጃዋን ከፍ አደረገው! አንደዚህ ያሉ ሚስቶችን ያብዛልን! በባላቸው የጥሩነት ምስክር የሚያገኙ ሴቶች ደረጃቸው ትልቅ ነው ፡፡

ሚስት ሆይ ነቃ በይ !!!

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

19 Nov, 19:06


~~~
ለጉዳይህ ስትል ሰላትህን በጥድፌያ አትስገድ ፡ ምክንያቱም የቆምከው የቸኮልክበትን ጉዳይ ጨምሮ ዱንያ ሁሉ ያያዘው ጌታህ ፊት ነው ፡፡

= t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

19 Nov, 14:07


ትዕዛዝ ተረስቶ

አፈር ለሚበላው ለዚ ፈራሽ ገላ
ተሠባብሮ ለሚቀር ልክ እንደ ሸክላ
ያበጃጀው ጌታ ትዕዛዝ ተረስቶ
ሁሉም ይጨፍራል ሚዲያ ላይ ተወጥቶ

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

18 Nov, 18:40


በአሏህ ላይ
የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው ።
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

18 Nov, 18:29


የቀኑ ብርሃን ምን ይጠቅማሀል? ጨለማው በልብህ ውስጥ ከሆነ!!
 
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

18 Nov, 18:03


ኢማም ሻፊዒይ ሰዎችን ሁሉ ማስደሰት አትችልም ይላሉ!

በአንተና በአላህ መካከል ያለውንም ጉዳዮችህን ሁሉ አስተካክል። በአንተና በሰዎች መሀል ያለውን አላህ ያስተካክለዋል።


 ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

18 Nov, 09:06


ٰ            🌹🌹🌹
         🌹🌹🌹🌹        👈አበባውን
      🌹🌹🌹🌹🌹            በመንካት
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹           ጠቃሚ
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹       ነገር ያግኙ
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹        
      🌹🌹🌹🌹🌹            
         🌿🌹🌹🌿      
              🌿🌿            👈
                 🌿                     🌿
                  🌿               🌿🌿
                 🌿           🌿🌿🌿
                🌿      🌿🌿🌿🌿
               🌿    🌿🌿🌿🌿
              🌿 🌿🌿🌿🌿
               🌿 🌿🌿🌿
                 🌿              .
                  🌿               .
                   🌿                  .
                    🌿                    .
                    🌿
                  🌿       በቀላሉ ይቀላቀላሉ ።
🔤🔤🔤🔤🔤🎁

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

18 Nov, 05:31


☪️አዲስ የሙሀደራ ፕሮግራም 🕌

💡በትዳር እና ኢስላም ቻናል 🌙

1️⃣ኡስታዝ አብዱረዛቅ አልባጂ
ርዕስ🔴
🟡أنواع العلوم
🔢የእወቀት አይነቶች


2️⃣🔴ኑረዲን አል አረቢ 
ርዕስ 
🟤ሰላት

ቀን ዛሬ ሰኞ 🔈

ሰአት ከምሽቱ3⃣:30 ጀምሮ

💬የፕሮግራም መሪ አቡ ሱፊያን⤴️

✈️✍️
የሚተላለፍበት ቻናል🔂

t.me/tdarna_islam
t.me/tdarna_islam

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

17 Nov, 17:50


ንግስቴ 🍃

ስላንች ማማር ስላንች ቁንጅና
ግጥም ልፅፍልሽ እንደረደርና
ቃላትን ስፈልግ ከኔ ይደበቃሉ
ላንች እንደማይመጥኑ እነሱም
         ያውቃሉ።
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
~ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

17 Nov, 17:14


ማፍቀር በሽታ ነው ያፈቀሩትን ማግባት ደግሞ መድሀኒቱ ነው ።

ኢብኑ ቀይም 


@FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

16 Nov, 19:05


ያኢላሂ ፍፃሜው ያማረ ደስታን ፤ ደርሶ የማይጨልም የማንጠፋበት አንተን ለመገዛት የሚያግዘን ከልባችን የሆነ ኢማን እና ፍቅር ስጠን 🤲

@FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

16 Nov, 08:37


ፈፅሞ በማይቻልና በሚቻል ጉዳዮች መሃል፤የአሏህ ውሳኔ ብቻ ነው ያለው ።
ቀጠሮው ሲደርስ #ኩን ቃሉ በቂ ነው !

@FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

15 Nov, 19:22


የሆነ ግዜ በጣም የምንቀርባቸው በተለያየ የሂወት አጋጣሚ ፤ በቦታ መራራቅ ይሁን ስልክ በመጥፍት የተለያየን ወንድምና እህቶች አለን።  ብዙ የጠፉ ወዳጆች አሉኝ ! የት ይኑሩ ? በምን ሆኔታ ላይ ይሁኑ አላውቅም ! ብቻ ብዙ ወዳጆች ነበሩኝ ። እናም  የጠፉችሁኝ ወዳጆቼ ካለችሁ እስኪ አስታውሱኝ የት ነው ያላችሁት?

ከታች  ባለው ቦት  ኑ  እስኪ  👇

@fkr_eske_Jenet_Bot

☝️(k.B)

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

15 Nov, 07:05


🍃

ተስፋ ከመቁረጥህ የተነሳ መክፈቻ የሌለው የመሰልህን በር አላህ ይከፍተዋል።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
= t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

08 Nov, 03:59


ምናልባት ህልሞችህ ነብዩላህ ዩሱፍ የወደቁበት ጉድጎድ ውስጥ ወድቀው ይሆናል። ነገር ግን የነጋዴወቹ ቅፍለት በአላህ ትዕዛዝ እንደሚመጣ እርግጠኛ ሁን.. ..አትሰብ አትፍራ

እሷ ዱንያ እንጂ ጀነት አይደለችም
አላህ ላንተ እንደፃፋት ተዋት
ምናልባት እንደተመኛሀት ሁና ወይም ከተመኝኸው የተሻለ ሁና ልትመጣ ስለምትችል አብሽር!  🤚
        
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
~ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

07 Nov, 20:03


ከጸጋዎች መሀል አንዱ በመከራ ወቅት «አብሽር ምንም አንሆንም» ሲል የሚያጽናናህ ጓደኛ ማግኘት ነው!

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

07 Nov, 14:09


ወጣትነት !

ወጣትነት በሁለት ድክመቶች መሀል የሚገኝ ብርታት በመሆኑ ለብዙ ፈተናዎች የተጋለጠ እርከን ነው። ለማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ጌጥ እና ውበት ብሎም የጥንካሬው ሚስጥር ነው። በማንኛውም ህብረተሰብ ወጣቱ የአፍላ ጉልበት ፤ የብሩህ አእምሮና እምቅ ሀይል ባለቤት ነው። ስለሆነም ለወጣቱ ትኩረት የማይሰጥ ስርአት የወደፊት ህልውናው ለአደጋ የተጋለጠ ነው።
 
 ኢስላም የህይወት መንገድ ነው። ለአማኝ ሰዎች ምቹ እና የመንፈስ መርጊያ ጭምር ነው። ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ይህንን ዲን ለማስተማር እና ለማስፋፋት ከአላህ እርዳታ በመቀጠል የወጣቱ ሚና የጎላ እንደነበር በሀዲሳቸው ነግረውናል። ሁለንተናዊ ባህሪና ይዘት ያለው ኢስላም በወጣቶች ትከሻ ላይ በመሆን የምድርን ገላ ከእድፍ አጸዳው።

 አሊይ ኢብኑ ጧሊብ፣ዘይድ ኢብኑ ሳቢት፣ሙአዝ ኢብኑ ጀበል፣ ሙስአብ ኢብኑ ኡመይር፣ ሰአድ ኢብኑ አቢ ወቃስ፣ዙበይር ኢብኑል አዋም፣ ጦልሀ ኢብኑ ዑበይዲላህ ረዲየላሁ አንሁም አጅመዒን እና ሌሎችም በርካታ ሰሀባዎች ከ 10 - 20 ባለው የእድሜ ክልላቸው እስልምናን በመቀበልና ለእስልምና እድገት ታላቅ ተጋድሎ የፈጸሙ ብርቅዬ ወጣት ሰሀቦች ነበሩ።

📌  ወጣትነት ላይ አእምሮ በፍጥነት የሰጡትን ይቀበላል፤ ያስተነትናል።ልብ ደም ይረጫል ፤ ደም ይዘዋወራል ፤ አይኖች በሚገባ ያያሉ፤ ጆሮ ሁሉን ይሰማል፤ አግሮችና እጆች ሁሉን ይፈጽማሉ። እርጅና ለይ ግን አዕምሮን በቀላሉ መግራት ይከብዳል። አስቀድሞ የያዘውን ሙጥኝ ይላል። አዲስ ሀሳብን ተቀበል ቢሉት ወኔው ብዙም የለውም። ስለሆነም እርጅናህ ከመምጣቱ በፊት ወጣትነትህን አላህ በሚፈልገው መልኩ ተጠቀምበት።

📌  ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ምክር ይለግሱናል፦
 
"ከአምስት ነገሮች በፊት አምስት ነገሮችን ተጠቀም ወጣትነትህን ከእርጅናህ በፊት፤ ጤናህን ከህመምህ በፊት፤ ሰፊ ግዜህን ከውጥረትህ በፊት፤ ሀብትህን ከድህነትህ በፊት እና ህይወትህን ከሞትህ በፊት።"

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
= t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

07 Nov, 03:53


ለአንድ የአረብ ዘላን: አንተኮ ሟች ነህ አሉት…

አርሱም አለ: ከዚያስ ወዴት እሄዳለሁ?
ወደ አሏህ አሉት እርሱም: ኸይርን ከአሏህ እንጂ አግኝተን አናውቅ…

ታዲያ ከርሱ ጋር መገናኘትን እንፈራለን እንዴ! አለ

በአላህ መልካምን ማሰብ ምንኛ ያማረ ነው!! ሁሌም ቀናችንን ከአላህ የሚመጣ መልካም ነገር እንዳለ በማመን በርሱ ላይ በመመካት እንጀምር ብሩህ ቀን ይኖረናል!!

መልካም ቀን 🤚

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Nov, 18:17


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Nov, 18:04


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ሰላት የማይሰግድ ሰውን አትመን ልክ ጌታውን እንደተወ አንተንም ይተውሀል።
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

05 Nov, 17:59


⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ባለቤቶች

የሱና ቻናል ተደራሽነት ይበልጥ ይሰፋ ዘንድ
የቻናል ሊንክ መላክ ትችላላችሁ  ⚡️

✍️መስፈርት 1/ :- የሱና ቻናል ሊሆን ስለማጣራ⚫️
✍️መስፈርት2/ ከ1k member በላይ 🔤 ከዛበታች
✍️መስፈርት 3/:-  ቻናሉን አይቼ አሳውቃቹኋለሁ

🚫ግሩፕ አልቀበልም

⭐️ @twhidfirst1
🌟 @twhidfirst1

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

04 Nov, 19:02


በህይወት ውስጥ ፈተና ስበዛብህ አትዘን ታገስ...የጨረቃ ውበት የሚጨምረው ጨለማ በዙሪያዋ በጨመረ ቁጥር ነውና።
ራህማኑም " ታጋሾችን አበስራቸው " ይላል


አብሽር!!

=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Nov, 19:09


ውድ እህቶቼ

አሏህ መልካሙን አባታችሁን
የሚተካ ባል ይስጣችሁ! !!

@FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Nov, 19:06


ስናማርር ውለን፣
ሰናማርር መሸ፣
ለሩቁ ስንቋምጥ፣
የሰጠኸን ሸሸ!
ደሞ አዲስ ቀን ሆነ፣
ላልተሰጠን ሁሉ፣ልናማርር ነጋ፣
የሰው ልጂ አይደለን?
በቃኝ ን የማናውቅ ባለን የማንረጋ፤
ተኝቶ መነሳት አይመስለንም ፀጋ !!!

አልሃምዱሊላህ !!!
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Nov, 18:37


🔤🔤🔤🔤🔠🔠🔠🔠🔤🔠

🔤 الأربعون النبوية في السعادة الزوجية

🎤ኡስታዝ ኢብራሂም ኸይረዲን

🌹
   
🌹
       
🌹
            
🌹
                
🌹
ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም ተከታተሉ


🔗🔡🔡🔡
https://t.me/tdarna_islam?livestream
https://t.me/tdarna_islam?livestream

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Nov, 17:34


አሏህ...በልቤ ውስጥ ያለውን ሁሉ እንደሚያውቅ ማወቄ በራሱ እረፍት ይሰጠኛል !

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

03 Nov, 17:25


አሏህ መጠጊያዬ 🤲

“አንዳንዴ  ወደ አላህ የምታደርገው መንገድ የሚጀምረው…  ልብህን በሚሰብር ሰው፣ እንደጠበቅከው በማይሆንልህ ጓደኛና በሚበድልህ ጉዳይ ፈፃሚ ምክንያት ነው። ከዚያም ሰዎች ዘንድ ካለው ነገር ተስፋ ትቆርጥና ወደ አላህ ብቻ ትጠጋለህ። እርሱም ከዓለም ያብቃቃሃል።”

ኢማሙ ሻፊኢ

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

02 Nov, 20:11


በህልማችንና በምኞታችን መካከል እንዲሁም በቀደርና በእድል መካከል አሏህ ከፃፈልን ነገር በስተቀር የሚሆን ነገር የለም !!!

━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

02 Nov, 19:58


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ከመጥፎዎች ጋር ጨለማው አይነጋም
ከመልካሞች ጋር ፅልመት አያሰጋም ።
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

02 Nov, 19:39


አትዋሽ !

እምነት ከክብር ጋር የተያያዘ ነው እምነትህን ማጉደል ስትጀምር ፤ ክብርህን ታጣዋለህ !

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

02 Nov, 10:31


ሁሌም ለምትወዱት ብርሀን ሁኑ !

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

31 Oct, 17:57


ልዩ ናት 🌹

መስፈርቱን አሟልታ አደቡን ጠብቃ
የለበሰች ግዜ ግዴታዋን አውቃ
እንደ ሰማይ ኮከብ  እንደ ዉብ ጨረቃ
ኒቃቢስቷ እህቴ ትታያለች ደምቃ።

አሏህ ይጠብቅሽ !!

=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

31 Oct, 13:01


የዳዕዋና የኒያ ፕሮግራም

የፊታችን ጁመዓ በሱና ኡስታዞቻችን ደማቅ የዳዕዋና የኒያ ፕሮግራም አዘጋጅተን አየጠበቅናችሁ እንገኛለን።  ስለሆነም ሁላችሁ የዚህ ፕሮግራም ተካፋይ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

     ተጋባዥ ኡስታዞች

1 ሳዲቅ ኢብኑ ኸይሩ
2 ኡስታዝ አብዱሰመድ ሙሐመድ ኑር
3
ወንድም ኑረዲን አል-ዐረቢ


ሰአት   ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ

አድራሻ ➡️
t.me/nikab_jilbab_group

🔄Share

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

31 Oct, 09:34


የሚገርማችሁ ከኛ ከሙስሊሙ ራሱ ኒቃብ የሚጠላ ሰው እንዳለ ታውቃለችሁ ???

1,ሂጃብ ብቻ የምትለብሰውን እህት ጂልባብ ጨምሪበት ብሎ መምከር እየቻለ።
2ኛ, ጂልባብ የምትለብሰውን እህት ኒቃብ ጨምሪበት ማሻአሏህ ይሆናል ማለት ሲችል።

ኒቃብ አድርገው አይናቸው ሰለሚያሳይ ብቻ ተቆጥቶ ይሄ ከሚሆን ጭራሽ ባትለብሽ ይሻላል ይላል¡

አይ አለማወቅ የለበሽው ጥሩ ነው ነገር ግን ይሄን ብጨምሪበት አላህ ይዘንልሽና ብትል ምን ይጎልብሀል ።
የለበሱትን ለማስወለቅ ከምትንደረደር ጨምሩበት ይህ ልክ አይደለም ብትል አይሻልም ተረጋግተህ ።

በተረጋጋ መንፈስ መመካከር እየተቻለ የሚቆጣ ሰው አለ አዋቂ መስሎ ባዶ የሆነ ሰው !!

ድሮም ሸንበቆ ቀርቅሀ ይመስላል ግና ውስጡ ባዶ ነው ።👌

https://t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

31 Oct, 04:01


ኒቃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች !

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

30 Oct, 03:31


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ የሰው ልጂ ትልቁ የህይወት ስኬቱ ለጌታው ምርጥ ባሪያ መሆን ነው ።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

29 Oct, 18:53


ለሀሰት ከመኖር ትክክለኛ ለሆነው ነገር መሞት ይሻላል ።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

28 Oct, 17:43


   📖🌙🌙

🌹🌹🌹
         🌹🌹🌹🌹        👈አበባውን🔻
      🌹🌹🌹🌹🌹            በመንካት 🔻
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹           ጠቃሚ 🔻
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹       ነገር ያግኙ🎁
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹         🔻
      🌹🌹🌹🌹🌹             🔻
         🌿🌹🌹🌿       🔻
              🌿🌿            🔻
                 🌿                     🌿🔻
                  🌿               🌿🌿🔻
                 🌿           🌿🌿🌿🔻
                🌿      🌿🌿🌿🌿🔻
               🌿    🌿🌿🌿🌿🔻
              🌿 🌿🌿🌿🌿🔻
               🌿 🌿🌿🌿🔻
                 🌿              .🔻
                  🌿               .🔻
                   🌿                  .🔻
                    🌿                    .🔻
                    🌿
                  🌿       🌿

⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️📡💡🌙

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

28 Oct, 03:47


🍃

ሙሉ የሆነች ሚስት የሚፈልግ
#ወንድ እና ሙሉ የሆነን ባል የምትፈልግ #ሴት ሙሉ እድሜያቸውን ላጤ ሆነው ይኖራሉ፡፡

አንዱ አንዱን እንዲሞላ እንጂ ሙሉ ሆነው አልተፈጠሩምና፡፡

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

28 Oct, 03:42


"ዱኒያ ላይ ባለ ነገር አትዘን ምክንያቱም በዚች ምድር ላይ እኛ እንግዳዎች ነንና"

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄ 
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

27 Oct, 04:38


#ጥቆማ

ማንኛውም አይነት ከሸሪዓ ጋር የማይጋጩ የስራ ማስታወቂያዎችን በአንድ ፕላትፎርም ላይ ማግኘት ከፈለጉ Halal Jobsን ይቀላቀሉ!

አዲስ ስራ ለሚፈልጉ፣ ስራ መቀየር ላሰቡና የተሻለ የስራ አማራጭ ለሚፈልጉ ሐላል ጆብስ ቤታቸው ነው። እንዲሁም ቀጣሪዎች የስራ ማስታወቂያቸውን በነፃ እንዲለቁበት በማሰብ የተዘጋጀ ፕላትፎርም ነው!

ይወዳጁን! ይከታተሉን! ወዳጅዎንም ይጋብዙ! ያተርፉበታል!

ቻናል👉 
t.me/HalalJobsEth

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

26 Oct, 20:18


"መልካም #ጓደኛ የበረሀ ጥላ ነው"

እንደሚባለው ሁሉ በህይወትህ ውስጥ አንድ ጥሩ ጉዋደኛ ማፍራትህን አትርሳ፡፡
አንተም ጥሩ ጉዋደኛ ሁን፡፡ በተደሰትክ ሰዓት ብቻ ሳይሆን በተጨነክ እና ባዘንክ ሰዓት ጭምር ከጎንህ ሚሆንልህ እውነተኛ ጉዋደኛህ ነውና አጥብቀህ ያዘው፡፡"

@FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

26 Oct, 19:57


የእብደት ትርጓሜ❗️

“አንድ ጊዜ ከተሸነፍክ ለራስህ ተመልሰህ እንደምትመጣ ንገረው፤ ሆኖም ከዚህ ቀደም በመጣህበት መንገድ ከተመለስክ አሁንም ትርፉ ድካም እና መታመም ይሆንብሃል!”

የእብደት ትርጓሜ አንድን ነገር በተመሳሳይ ሁኔታ ደጋግመህ እየፈጸምክ መጨረሻው የተለየ እንዲሆን መጠበቅ ነው። እንዲህም ሆኖ አብዛኛው ሰው ይህንን ያደርጋል።

ለራሳቸውም እንዲህ ይሉታል፡- ዛሬ ላይ አልበሳጭም። ዛሬ ላይ ራሴን ገደል ውስጥ አልከተውም።

ሆኖም አዋዋላችን የተለየ አይደለም፤ ተመሳሳይ ተግባራት፣ ተመሳሳይ ቀናቶች እየዋሉ አዲስ ውጤት እንዲመጣ ተስፋ ያደርጋሉ።

ተስፋ ብቻውን መፍትሄ አይሆንም!

መወሰን ካልቻልን በሕይወታችን ላይ ውድቀቶች ይከሰቱብናል።

በሌላ በኩል ከስህተቶቻችን የመማር ምርጫ አለን።

ለመማር መምረጥ እንችላለን። አስበን እና አቅደን ነገሮችን በተለየ መንገድ መፈጸም እንችላለን - መንገዳችንን ስንለውጥ እና ስንቀይርም የምንፈልገውን ውጤት በሕይወታችን ላይ እናገኛለን። ይህን ማድረግ ከባድ ነውን?

ስኬታማ ባልሆንበት መንገድ ደጋግሞ መጓዝ ቀላል ነው። ምንም አይነት ኃይልም ሆነ ተጨማሪ ፍላጎት ሊኖረንም ግድ አይሆንም። ለዛም ነው ብዙ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት።

= t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

26 Oct, 19:46


ሰለመች

ከላይ ነው ሚሠጠው
ከላይ ነው ማማሩ
ከላይ ነው ስጦታው
ከዚያው ነው መቸሩ
1 እና 3 ነው ከሚለው ድንግር
ፈጣሪ ተወልዷል ከሚል መደናበር
ማንነቱ ልዩ ምንነቱ እኮ አንድ
ማስረጃ ከሌለው ከከንቱ ንግግር
ፍጡርን አምልከው ከሚያልቁት መንደር
ማርያም የአምላክ እናት ከሚሉበት ሰፈር
ገብርዔል ባለክንፉ ከሚለመንበት
የ አላህ አንድነት ከሚኮሰስበት
ከዚያ ማዶ ካሉት ካልነቁትም መንደር
እዛ ቀዬ ሆነው ካላወቁት ሀገር
እሷ ተጠርታለች አቤት የ አላህ ነገር
እኔ የተላኩት ለጠፉት በጎች ነው
መገኛዬም ከቶ ከአምላክ ዘንዳ ነው
እያለ እየሱስ ቢያቀነቅንም
አረ ማን ሊሠማው ግግም አምላክ ነው!
በ ዮሀንስ ወንጌል በማርቆስ በሉቃስ
አሳይቶን ሳለ የሱን ትንሽነት
መፀለይ መብላቱን ማልቀስም መፍራቱን
አምላክ ነው ይሉናል እንዴት አርገው ይሆን
ከዚህ ሁሉ ጣጣ ከዚህ ሁሉ ኮተት
መጣችልኝ እሷ መመራትን ሰጣት
በሂዳያ ብርሀን በቁርዐን አስዋባት
በደሏን ሰርዞ እስልምናን ቤዣት
ሰለመች እህቴ አላህ መረጠላት
ዱዐ አርጉላት እስኪ አላህ እንዲያፀናት::
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
   ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
= t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

23 Oct, 19:10


በጣም እንደምትወዳቸው ንገራቸው
ነገን ማንም አያውቅም፣ ማን እንደሚቆይ፣ማን እንደሚሄድ አናውቅም።ዛሬ ከአጠጋባችን ያሉ ሰዎች ነገ ይኖራሉ ማለት አይቻልም።
ህይወት አጭር ናት
!

እናም ውዶችየ እንደምወዳችሁ ስነግራችሁ በደስታ ነው !!! ሰላም ለእናንተ !

📝 ወንድማችሁ ራማስ

┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
https://t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

22 Oct, 20:19


ጀግና አባት

➧አንድ ወጣት የታላቁን ታቢዒይ ልጅ "የሱፍያን ኢብኑ ዑየይናን ልጅ ለትዳር ሊጠይቅ ይመጣል" ፡

ይህ ወጣት የራሱ የሱፍያን ኢብኑ ዑየይና የወንድሙ ልጅ ነው፡

▸ወጣቱ ለሱፍያን እንዲህ አለው፡ አጎቴ ሆይ ! ሴት ልጅህን ለትዳር ፈልጌያት ነበርና እርሷን እንድትድረኝ ልጠይቅህ ነው የመጣሁት ፡ አለ

ሱፍያን እንዲህ አሉት፡ ጥሩ ደስ ይለኛል

➧ከዛም ሱፍያን እንዲህ አሉት ፡ አስር ሀዲሶችን አንብብልኝ ?

▸ወጣቱ ማንበብ አልቻለም !

▸ከዛም ፡ እሺ አስር የቁርአን አንቀጾችን ቅራ አሉት

▸አሁንም መቅራት አልቻለም

▸ሁለቱንም ሳይችል ሲቀር ሱፍያን እንዲህ አሉት:-

ልጄ ሆይ ቁርአን ማንበብ አልቻልክ ወይንም ሀዲስ ማንበብ አልቻልክ  ታዲያ ውድ ሴት ልጄን ካንተ ጋ እንዴት እንድትኖር ላደርጋት እችላለሁ ??!!

▸ከዛም ሳይድሩት ተመለሰ

↝ምንጭ፦ ቡስታኑል አሪፊን (377)

┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

22 Oct, 19:36


ውበት የበለጠ ጎልቶ የሚታየው በሚመለከተው አይን ሳይሆን ሊያየው በሚናፍቀው ልብ ውስጥ ነው።

@Fkr_eske_jenet

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

22 Oct, 17:21


ሁሉም ነገር ከአሏህ ነው ፤ ከእሱ እንጂ ከሰው አንጠብቅም ።
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

21 Oct, 17:46


ፍቅር ጊዜያዊ ስሜት ሳይሆን በበጎነት የምንኖርበት ቋሚ ቃልኪዳን ነው።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

21 Oct, 17:36


❝ጀነት ስንገባ አንድም ሰው ከመካከላችን እንዲጎድል አንፈልግም..በሉ ተነሱ ልጆቼ❞ እያለች ልጆቿን ለሱብሒ ሶላት የምትቀሰቅስ አንዲት እናት ነበረች።

አሏህ ለልጆቻችሁ ምርጥ ዓርዐያ የምትሆኑ ያድርጋችሁ !!! 🤲


╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

21 Oct, 17:26


ያለማድረግ ጸጸት

በጣም ብዙ ግዜ የሚታየው ፣ አድርገን ከተሳሳትነው ነገር ይልቅ ማድረግ ሲገባን ሳናደርገው የቀረነው ነገር ከእኛ ጋር እስከወዲያኛው የሚቆይን ጸጸት ይሰጠናል፡፡

በሌላ አገላለጽ፣ “ምነው ባለደረኩት ኖሮ” ከምንለው ይልቅ፣ “ምነው ባደረኩት ኖሮ” የሚለው ጸጸት እኛን የመጉዳትና እስከወዲያኛው አብሮነ የመቆየት አቅም አለው፡፡

ምንም ሳትንቀሳቀሱ እና ሳትሰሩ በኋላ ከምትጸጸቱ፣ ትክክል ነው ብላችሁ ባመናችሁበት አቅጣጫ ተንቀሳቀስሳችሁና አንድ ነገር አድርጋችሁ ብትሳሳቱ እንኳን በኋላ ከሁኔታው ብትማሩ ይሻላችኋል፡፡

መሳሳትን ፍራቻ አዳዲስ ነገርን ከመጀመር መገታት ማለት ቀድሞውኑ ያለመንቀሳቀስን ስህተት መስራት ማለት ነው፡፡

ዓላማችሁን እወቁ፣ አስቡ፣ አቅዱ፣ ግብ አውጡና ተንቀሳቀሱ!

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

20 Oct, 18:55


ሪዝቅ ሰጪው አላህ ነው!!!

አሏህ የከፈተልህን በር ማንም አይዘጋብህም ። የዘጋብህን ደሞ ማንም አይከፍትልህም።

ላንተ ከወሰነው የትም አይሄድም እናም አትስጋ ላንተ ካላለው ደሞ ምንም ብትለፋ አታገኘውም ። ልፋትህን ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋው።
              
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

20 Oct, 10:01


ናፍቆት
""""""''"

ታዛ ማይጠልለው ፣
ሀሩር ማይነጥለው ፣
ከሀሳቤ እኩል ከእኔጋ የሚጓዝ ፣
ዘለው የማያልፉት የናፍቆትሽ ጉዝጓዝ ።

በሁካታ መሀል ፣
በፀጥታ መሀል ፣
የሚሰማኝ ድምፀት የሚሰማኝ ቅኔ ፣
ልፈታው አልቻልኩም ያንችን ናፍቆት እኔ ።

➻ t.me/FKR_ESKE_JENET

ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)

20 Oct, 09:43


ሰላም ለእነዛ !

መናገር ፈልገው ለስሜታቸው መግለጫ ቃል አጥተው ዝምታን ለመረጡ ሁሉ !!

@FKR_ESKE_JENET

19,268

subscribers

1,074

photos

135

videos