SELAM TV @selamtvofficial Channel on Telegram

SELAM TV

@selamtvofficial


Aselamu aleykum werahmetulahi weberekatuh yh @Selamtvofficial yetesegnew channel yeteleyayu #nesheed #Da'wa
#Quran endihum be amargna trgum yekerebu ye wchi hager daiwoch muhadera yemikerbbet channel nw
Inbox @Don_abdi
@onlyaboutislambot

SELAM TV (Amharic)

ስለ SELAM TVnnSELAM TV እባክዎ ይህንን አገልግሎት ይመልከቱ: ምንም አልባ ላይ በተለያዩ ዜና እና የእስልምና በሽታ የሚሰጠውን ዜናዎች እና የድምፅ ቁርጥቆስዎች ይምረጡ፡ ከድምፃቸውን ለማግኘት ሲቅርብ የእኛን ቦታ አስተባባሪ አመልክቶ ነው።nnለበሽታ መረጃ ፍቶዎች ወይም ጥያቄዎች ለማሳየት በቁጥጥጥሽ የመንካት ቋንቋ ተጠቃሚ ይሆናል።nnህወሃት ከሚለየው የቁምፍ ውይም ከሚያገኙት የሚወዳጅ መረጃዎችን በማንበብ ተከትሎ ነፃነት ያሳያልnnየሶማት አላይምን ሊጠቀሙት ይከብሩ።nnለምሳሌ: @Don_abdin@onlyaboutislambot እንኳን ለማቀናበል ማከናወን የሚችል አለዎት።

SELAM TV

09 Jan, 14:05


The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 10 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

SELAM TV

22 Dec, 18:33


The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 28 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

SELAM TV

25 Aug, 04:44


ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ይላሉ፦
«ከምንም በላይ የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር፤ እድሜዬ ጨምሮ መልካም ሥራዬ ሳይጨምር ጀንበር የምትጠልቅበት ቀን ነው።»

[አል-ከላሙ-ጥ'ጦይባህ: 1322]

SELAM TV

25 Aug, 04:43


ሰዎች ተኝተው ሳለ ስገድ
===================
የአንዳንድ መልካም ነገሮችን እርካታ ለሌሎች ለማስረዳት ቃላት አይገልጹትም። ምናልባት ሰዎች ሲነግሩህም በትክክል ላትረዳቸው ትችላለህ። የዚያን ነገር እርካታ የምትረዳው Just ስትተገብረው ብቻ ነው። አለበለዚያ የፈለገ ቢያወሩህ እውነት አይመስልህም። ከእንዲህ አይነት ነገሮች አንዱ ሌሊት ተነስቶ የምር ከልብህ አላህን ፈርተኸው መስገድህ ነው። በቃ! ተግብርና ቅመሰው!
قيامُ الليل مفتاح الحلول وبوابة المعجزات
‏قال ابن القيم رحمه الله تعالى:

‏" قيام الليل:
‏ > مِن أنفع أسباب حِفظ الصِّحة
‏ > ومن أمنعِ الأمور لكثيرٍ مِن الأمراض المُزمِنة
‏ > ومِن أنشط شيءٍ لِلبدن والرُّوحِ والقلب ".

‏ [زاد المعاد(٤ / ٢٢٧)]..

SELAM TV

23 Aug, 05:44


ከፊሎቻችሁ በነሺዳው የምታውቁት ወንድማችን ሙሐመድ አወል ሳላሕ ወደማይቀረው አኺራ ሄዷል።
በቅርቡ ባደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ ህመም እንዳለበትና ወደ 10 ያክል መድሀኒቶች ይወስድ እንደነበር፣ በአሁኑ ወቅት ግን "አል-ሐምዱ ሊላህ ወደ አራት መድሀኒት ብቻ ነው የምወስደው!" ሲል ሰምቸው ነበር።
አብዛሃኛዎቹ ነሺዳዎቹ ራሱን በመውቀስና ከተውበት ጋር የተያያዙ እንደሆኑ ሲናገር ሰምቸው ነበር።

አላህ ይዘንለት! ወንጀሉንም ይማረው!
ለቤተሰቦቹና ወዳጆቹ አላህ ሶብሩን ይስጣቸው።

إنا لله وإنا إليه راجعون

ሞትን ግን አያችሁት ኣ ምን ያክል ቅርብ እንደሆነ?!
እኛ ለበርካታ አመታት ያቀድናቸው እልፍ አዕላፍ እቅዶች አሉን።
ግን ሞት ሳናስበው ድንገት ይመጣና ሲወስደን ሁሉም በአንድት ቅፅበት እንዳልነበሩ ይሆናሉ።
ሁልጊዜም ዝግጁ ከሆኑትና በቂ ስንቅ ከሰነቁት ባሮቹ አላህ ያድርገን።

SELAM TV

22 Aug, 14:14


ሐጂ የሱፍ አደም አረፉ።

በደሴ ከተማ ከ50 አመት በላይ የአረበኛ እውቀትን ሲያስተምሩ የኖሩት ሐጂ ዩሱፍ አደም ማረፋቸው ተሰምቷል።

ሐጂ ዩሱፍ አደም ለደሴ ህዝበ ሙስሊም የአረብኛ እውቀት አባት ነበሩ።

ወጣቱ የአረብኛ እውቀትን ሲማር ከእሳቸው እውቀት ያልተቋደሰ እንደሌለ ይነገራል።

ለደሴ ከተማ ወጣቶች ትልቅ የእውቀት ባለውለታ ፣ የእድሜ ባለፀጋ ፣ መካሪ እና አቃፊ አባት ነበሩ። አሏህ ጀነተል ፊርደውስ ይወፍቃችሁ!

SELAM TV

22 Aug, 06:32


ኢስቲግፋር ምህረትን፣ ሲሳይን፣ በረከትን፣ ደሰታን ያዘንባል።
በኢስቲግፋር መካከል የሚኖር ሰው አይቆሽሽም፣ አይጨቀይም።

የተዘጋ በር የሚከፈተው፣
የተሰበረ ህልም የሚጠገነው፣
የከሸፈ ጥረት የሚሳካው፣
በኢስቲግፋር ነው።

SELAM TV

31 Jul, 04:09


አላህ (ሱወ) ሰባት ነገሮችን ይወዳል

ተውበት ☆ “አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል” አል በቀራህ [2:222]
ጦሀራ ☆ “አላህ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡”አል በቀራህ [2:222]
ተቅዋ ☆ “አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡” አተ ተውባ[9:4]
ኢህሳን ☆ “አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡” አል ኢምራን[3:134]
ተወኩል ☆ “አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና” አል ኢምራን[3:159]
ዐድል ☆ “አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡”አል ማዒዳህ{5:42]
ሶብር ☆ “ ..”አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡”አል ኢምራን[3:146]

ሼር ይደረግ

SELAM TV

23 Jul, 15:28


የአላህ መልዕክተኛ ﷺ «አንድ የአላህ ባሪያ በአላህ መንገድ በሚጾመው በእያንዳንዱ ቀን አላህ ፊቱን የሰባ ዓመት ርቀት ያህል ከእሳት ያርቅለታል» በማለት ተናግረዋል።

(ቡኻሪና ሙስሊም)

SELAM TV

23 Jul, 15:28


ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ......
አብደላህ ኢብኑ አባስ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት......

"መልካም ነገርን ማበረታታት ;መጥፎ ተግባርን መከልከል ;የደካማ ሰዉን ሸክም ማንሳትና መንገድ ላይ የሚያጋጥምን እንቅፋት ማስወገድ
በአላህ (ሱ.ወ.) ዘንድ ተቀባይነትን
የሚያስገኙ መልካም ስራዎች ናቸው፡፡


በሰማነዉና ባነበብነው ምንጠቀም
አላህ ያድርገን...አሜንንንንንንን!!🤲

SELAM TV

23 Jul, 07:01


#ዑመቴ_ዑመቴ ብለው
ባለቀሱልን ነበይ ላይ
ሰለዋት እናውርድ
ሰሉ አላ ሀቢቡና ሙሀመድﷺ
#መልካም_ጁምዓ_ይሁንላችሁ

SELAM TV

19 Jul, 15:18


Before whatevert things i would like to say
Aselamualeykum werahmetulahi weberekatu and thanks for the supper force and owner of everythings in the world and out of the world (Allah)
Then i would like to say happy eid Al-Adha for all my muslim mothers ,fathers , brothers and sisters around the world.
Then after i wanna say eid mubarek for my dear and heart friends and also members of this channel😍
I wish happy festival for all musilms💎❤️


🌙Eid mubarek🌙
🌙Eid mubarek🌙
🌙Eid mubarek🌙
🌙Eid mubarek🌙



From the admin of this channel
@Don_abdi (ibn baba)

SELAM TV

19 Jul, 11:15


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ አላህን ፍሩ አላህን ፍሩ ኢተቂላህ ሙሉውን ካላነበቡ አይጀምሩት❗️❗️

አንድ ቀን ጂብሪል(ዐ.ሰ) ያለወትሮው ረሱል ሰዐወ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ መጣ።
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንት ጅብሪል ምነው ፊትህ እኮ ተቀየሯል?" አሉት። ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁበት ሰዐት አላህ(ሱ.ወ) የጀሀነም አቀጣጣዮችን እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት
ነው። ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣እሳትም እውነት መሆኗን ላወቀ፣የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣የአላህ ቅጣት ትልቅ መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለባትም" ብሎ መለሰላቸው።
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)፦"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም ንገረኝ" አሉት።
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ቀይ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ነጭ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ
አመታት አቀጣጠላት ጥቁር እስክትሆን ድረስ.....አሁን /ጀሀነም ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም።
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.... የመርፌ ቀዳዳ ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር።
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ....ከጀሀነም ሰዎች ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከል ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ ምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር።
ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ....አላህ ቁርአን ላይ የጠቀሰው የጀሀነም ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው መሬት ድረስ ይቀልጣል።
ያ በዕውነት በላከህ አላህ እምላለሁ....በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም ቢቀጣ ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር። ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ ነው። 7 በሮች አሏት።ለያንዳንዱ በር የተለያዩ በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም" ብሎ መለሰላቸው።
ረሱልም(ሰ.ዐ.ወ)፦"እኛ እንደምንጠቀመው አይነት በር ነው?"
ብለው ...ሲጠይቁት
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦" አይ አይደለም ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር
ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር ያለው ርቀት 70 አመት ያስኬዳል። እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል።የአላህ ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል። ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ ይታሰራል። እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል።ከዚያምሕ
በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ ይመቷቸዋል።ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎ መለሰላቸው።
ነቢያችንም(ሰ.ዐ.ወ)፦"በነዚህ በሮች የሚገቡት እነማን ናቸው?"ብለው ጠየቁት።
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦ "በታችኛው በር የሚገቡት
1፦ሙናፊቆች
2፦በዒሳ ዐሰ ማዕድ የካዱት
3፦"የፊርዐውን ቤተሰቦች...ሲሆኑ
የ አንደኛው በሩ ስም ሀዊያ ይባለል።
ሁለተኛው በር ስሙ ጀሂም ሲሆን በሱ የሚገቡት ሙሽሪኮች ናቸው።
ሶስተኛው በር ሳብያኖች ነው የሚገቡበት ስሙም ሰቀር ይባላል።
በአራተኛው በር ኢብሊስ እና ተከታዮቹ መጁሶችም ይገቡበታል ስሙም ለዟ ይባላል።
አምስተኛው በር የሁዶች የሚገቡበት ሲሆን ስሙም ሁጠማ ይባላል።
ስድስተኛው በር ስሙ ዐዚዝ ሲሆን የሚገቡበት ክርስቲያኖች ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት ያዘው።
ነቢያችንም(ሰ.ዐ.ወ)፦"ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?" ብለው ሲጠይቁት ጂብሪልም(ዐ.ሰ)፦"በሱ በር የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ የሞቱ ናቸው" ብሎ ሲመልስላቸው ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን ስተው ወደቁ። ከዚያም ጅብሪልም የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ)ጭንቅላት ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት ጀሀነም ሚገባ አለ እንዴ?" ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦" አዎን ካንተ ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣ የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ይሄን ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ።
😭😭😭😭/ፊዳከ አቢ ውኡሚ ያ ረሱለላህ/😭😭😭😭
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ይህኔ፦"ያጅብሪል አንተም ታለቅሳለክ?" አሉት ።
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ መጨረሻ በምን አውቃለሁ?
እብሊስ እኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

ያ አሏህ ያ ረህማን ሙስሊሞች አድርገህ እንደፈጠርከን ሙስሊሞች አድርገህ ውሰደን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

SELAM TV

19 Jul, 11:05


የኡዱሒያ ቅድመ መስፈርቶች የትኞቹ ናቸው?
★★★★★★★★★★★★★

ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል‐ዑስይሚን አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ብለዋል:‐

1⃣ የሚታረደው እንስሳ "በሂመት አል‐አንዓም" በመባል ከሚታወቁት ግመል፣ ላም ወይም በሬ እና በግ አልያም ፍየል መሆን አለበት።

2⃣ በሸሪዓ የተገደበለት የእድሜ ወሰን ላይ የደረሰ መሆን አለበት። ማለትም:‐

📌 በግ ከሆነ፥ ስድስት ወር የሞላው መሆን አለበት።

📌 ፍየል ከሆነ፥ አንድ አመት የሞላው መሆን አለበት።

📌 ላም ወይም በሬ ከሆነ፥ ሁለት አመት የሞላው መሆን አለበት።

📌 ግመል ከሆነ፥ አምስት አመት የሞላው መሆን አለበት።

3⃣ የሚታረደው እንስሳ በሸሪዓ የኡዱሒያን ብቁነት ለማረጋገጥ ከተጠቀሱት ጉድለቶች እና እንከኖች ነፃ መሆን አለበት። እነሱም:‐

📌 ግልፅ ከሆነ ሸውራራነት ነፃ መሆን አለበት።

📌 በግልፅ ከሚታወቅ በሽታ ነፃ መሆን አለበት።

📌 በጉልህ ከሚታይ አንካሳነት ነፃ መሆን አለበት።

📌 በከፍተኛ ሁኔታ ከመክሳት እና ከመድከሙ የተነሳ መቅኒ የሌለው ከመሆን ነፃ መሆን አለበት።

🔖የኡድሒያን ቆዳ መሸጥ ይቻላልን?

ኡድሒያ የሚታረደው ወደ አላህ ለመቃረብ ነው!
ስጋውን ለሶስት ከፍሎ፥ አንድ ሶስተኛውን ለቤት፣ አንድ ሶስተኛውን በስጦታ መልኩ ለዘመድ፤ለጎረቤትና ለጓደኛ፣ አንድ ሶስተኛውን ሳይበስል ለአቅመ-ደካሞች መስጠቱ የጠበቀ ሱና ነው

የኡድሒያውን ቆዳም ይሁን ሌላ ነገር ሽጦ ገንዘቡን መጠቀም ወይም በገንዘቡ ፋንታ ለሰራተኛ መስጠት አይቻልም!

ቆዳውን ሳይሸጡ ለራስ መጠቀም ወይም ለአቅመ ደካማ በነጻ-ሰደቃ- መስጠት ግን ይቻላል

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

ኡስታዝ ጣሀ አህመድ

SELAM TV

18 Jul, 17:34


🌀 #አደራ_የነገን_ቀን_እንጹም
______

በሂጅሪ-ይ'ያህ የዘመን ቀመር መሠረት ነገ ዕለተ ሰኞ ዙ-ል-ሒጃህ 09, 1442ኛው ነው።
በዚህ ዕለት ሑጃጆች (ሐጅ አድራጊዎች) በዐረፋህ ተራራ ላይ ስለሚቆሙ " የዐረፋህ ቀን" በመባል ይታወቃል።

በዐረፋህ ተራራ ላይ መቆም ደግሞ የሐጅ ስነ ስርዓት አስኳል (ዋና ክፍል) መሆኑን ውዱ ነቢይ ﷺ (الحجُّ عرفةَ) "ሐጅ ማለት ዐረፋህ ነው!" በማለት ተናግረዋል። [ነሳኢይ: 3016 ላይ አልባኒ ዘግበውታል።]

በርካታ ሂደቶች ያሉበት የሐጅ ተግባር በዚህ መልክ መገለጹ የዐረፋህን ታላቅነት ያሳያል።

የዚህን ቀን ትሩፋቶች በተመለከተ የተወሰኑ ነጥቦችን ለመጥቀስ ወደድኩ።
………………………
①ኛ) በሐጅ ስነ ስርዓት ላይ ያልሆነ ሰው ይህን ቀን መጾሙ ያለፈውን አመትና የመጪውን አመት ወንጀል እንዲማርለት ያደርጋል።
ውዱ_ነቢይ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
(صِيَامُ يَومِ عَرَفَةَ، أَحْتَسِبُ علَى اللهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتي قَبْلَهُ، وَالسَّنَةَ الَّتي بَعْدَهُ)
« የዐረፋህን ቀን መጾም ከርሱ በፊት ያለውን አመትና ከርሱ በኋላ ያለውን አመት ወንጀል እንደሚያስምር በአሏህ ላይ እተሳሰባለሁ።»
[ሙስሊም: 1162]

ተመሳሳይ_ይዘት ያለው መልዕከት [አሕመድ: 5/296 ላይ እና በሌሎችም የሐዲሥ መዛግብቶች ላይ ሰፍሮ ይገኛል።
…………………………………
ታዲያ_ማነው የሁለት አመት ወንጀሉ እንዲማርለት የማይፈልገው
የወንጀላችን_አይነትና ግዝፈት ቢለያይም ከኛ መካከል ወንጀል የሌለበት ይኖር ይሆን?!

በርግጠኝነት አይኖርም! ታዲያ በአንድት ቀን ጾም የሁለት አመታት ወንጀልን የሚያሰርይ (የሚያስምር) አጋጣሚ ሲገኝ፤ ማነው ይህን እድል የማይጠቀምበት⁉️

አዛኙ_ጌታችን አላህ ወንጀል እንዳንሠራ ከማስጠንቀቅ ባሻገር በአጋጣሚ ከሠራን እንኳ የሚማርልንን እድሎች በተለያዬ መልኩ ሰጥቶናል።
እውነተኛ_አዛኝ ጌታ የዚህ አዛኝ ጌታ ባሪያ መሆን ምንኛ ያስደስታል

②ኛ) በዚህ_ቀን አሏህ በርካታ ባሪያዎቹን ከእሳት ነፃ ያወጣቸዋል።

ውዱ_ነቢይ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
(ما مِن يومٍ أَكْثرَ من أن يُعْتِقَ اللَّهُ عزَّ وجلَّ فيهِ، عبدًا أو أمةً منَ النَّارِ، مِن يومِ عرفةَ)
« ከቀናት መካከል ከዐረፋህ ቀን የበለጠ፤ ልዑልና ከፍ ያለው አሏህ ወንድ ባሪያውን ወይም ሴት ባሪያውን ከእሳት በብዛት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም።»
[ሶሒሑ ነሳኢይ: 3003 ላይ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል። ሙስሊም: 1348]
°
3ኛ) ሸይጧን_የሚቆጭበት ቀን ነው።
(ما رُئِيَ الشَّيطانُ يَومًا هو فيه أصغَرُ، ولا أدحَرُ، ولا أحقَرُ، ولا أغيَظُ منه يَومَ عَرَفةَ، وما ذاك إلَّا لِمَا يَرى مِن تَنزُّلِ الرَّحمةِ، وتَجاوُزِ اللهِ عنِ الذُّنوبِ العِظامِ).
( የዐረፋህ ቀን የሆነውን ያክል ሸይጧን እጅግ በጣም ትንሽ፣ የተዋረደ፣ ያነሰ፣ የተቆጨ ሆኖ አልታየም። ይህንንም የሆነው የአላህ እዝነት ስለሚወርድና አላህ ከባሮቹ ታላላቅ ወንጀሎችን ይቅር ስለሚል ነው።»

④ኛ) ከዱዓዎች_ሁሉ_እጅግ በጣም በላጩ የዐረፋህ ቀን የሚደረግ ዱዓዐህ ነው።
ውዱ_ነቢይ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
(خيرُ الدُّعاءِ يومُ عرفةَ ، و خيرُ ما قلتُ أنا و النَّبيون من قبلي : لا إله إلا اللهُ وحده لا شريك له ، له الملكُ ، وله الحمدُ ، و هو على كلِّ شيءٍ قديرٌ)
« በላጩ_ዱዓእ የዐረፋህ ቀን (የሚደረገው) ነው። #እኔና_ከኔ በፊት የነበሩ ነቢያት በላጩ ያልነው "ከአላህ ውጭ በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም፤ ብቸኛ ነው፣ አጋር የለውም። ንግስና ሁሉ ለርሱ ነው፣ ምስጋናም ለርሱ የተገባ ነው፣ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው!" የሚለው ነው።»
[ሶሒሑ-ል-ጃሚዕ: 3274፣ ቲርሚዚይ።

⑤ኛ) አሏህ ዲኑን የሞላበትና ጸጋውን ያጎናጸፈበት ቀን ነው።
ከዑመር ኢብኑ-ል-ኸ-ጥ'ጧብ ተይዞ ቡኻሪይና ሙስሊም ላይ እንደተዘገበው " اليوم أكملت لكم دينكم وأتممت عليكم نعمتي ورضيت لكم الإسلام دينا " المائدة :3 .
ይህ አንቀፅ የወረደው ዕለተ ጁሙዓህ ነቢያችን በዐረፋህ ላይ ቆመው ሳለ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ይህን ቀን አሏህ የማለበት መሆኑንና ከአደም ዝርያ ቃል ኪዳን የያዘበት መሆኑን የሚያመላክቱ የሐዲሥ መዛግብቶች አሉ።

የሚገርመው_የነገውን ቀን መጾም ሌላ ከዚህ ተጨማሪ ምንዳ የሚያስገኝ መሆኑ ነው።
ይሄውም_ዕለቱ_ሰኞ ስለሆነ ሰኞ ቀን ደግሞ ሥራዎች ወደ አሏህ የሚቀርቡበት ዕለት ስለሆነ ቀኑን ጾመኛ ሆኖ ማሳለፍ እንደሚወደድ በሐዲሥ ተረጋግጧል።

በሉ_እንዳያልፋችሁ። ደግሞ ለአንድ ቀን! ሌሎች የአመቱን ግማሽ ወይም ሁልጊዜ ሰኞና ሐሙስን እየጾሙ፤ እኛን አንድትን ቀን መጾም ሊከብደን አይገባም።
በአጋጣሚ ሌሊት ላይ ሰሑር መብላት ቢያልፈን እንኳ፤ የቻልን ሰዎች ዝም ብለን እንጹም።
አሏህ ወንጀላችንን ትንሹንም ትልቁንም ይማርልን።
ከትክክለኛ_ባሮቹ ያድርገን።
እርሱን_በትክክል ለመገዛት የሚያስችል አቅምን ይስጠን።
በተውሒድና በኢኽላስ ከሚገዙት ባሮቹ መካከል ያድርገን ፤ የሰለፎችንም ግንዛቤ ይስጠን።።።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@kunuzil8jenah
@kunuzil8jenah
@kunuzil8jenah

SELAM TV

17 Jul, 18:31


የዱዓ ስርኣቶችና ቅደም ተከተል‼️
====================
ዱዓ ፈጣሪያችን አላህን (ሱብሃንሁ ወተኣላ) የምንማፀንበት፣ ሐጃችን አላህን በመጠየቅ የምንፈታበት የዕባዳ አይነት ነው፡፡
||
①) ጥሪት ያለች ዱዓ ማድረግ፣
②) አላህን በማመስገንና በማወደስ ከዛም በነቢያችን ሰለዋት በማውረድ ዱዓን መጀመር በዚሁም መጨረስ፣
③ ዱዓችን ተቀባይነት እንደሚያገኝ እርግጠኛ መሆን፣
④) በዱዓ ችክ ማለትና ለመልሱ ግን አለመቸኮል፣
⑤) በዱዓ ቀልብን መሰብሰብ፣
⑥) በሰራው ወንጀል አምኖ መሃርታ ይቅርታ መጠየቅ፤ አላህ የዋለለትን ፀጋ አምኖ ምስጋና ማድረስ፣
⑦) አላህን እንጂ ሌላን አካል ላይለምን፣
⑧) ድምፅን ዝቅ አድርጎ ዱዓ ማድረግ፣
⑨) ከዱዓ በፊት ውዱእ ማድረግ፣
10) ሶስት ጊዜ መደጋገም፣
11) ወደ ቅብላ አቅጣጫ መዞር ተወዳጅ ነው
12) ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸውን ሰዐቶችና ቦታዎች መምረጥ ሲሆን እነሱም ብዙ ናቸው፡፡

SELAM TV

14 Jul, 03:55


💢በምላስህ ጉዳይ አላህን ፍራ


ሱፍያን አስሰውርይ አላህ ይዘንለትና ለጓደኞቹ እንዲህ በማለት ገሰፃቸው።

🔹ሱፍያን አሰውርይ
🔺🔺🔺🔺🔺🔺⤵️⤵️
🔹አንድ ንጉስ ቢኖርና የምትናገሩት ነገር ሁሉ ወደንጉሱ የሚያደርስ ሰው ከናንተ ጋር ቢኖር ንጉሱን የሚያስቀጣና የማይወደው ንግግር ትናገራላችሁንአላቸው።

🔹ጓደኞቹም
🔺🔺🔺🔺⤵️⤵️
🔹ኧረ በጭራሽ አንናገርም ብለው መለሱ።

🔹ሱፍያን አስሰውርይ
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺⤵️⤵️
🔹ታዳ ከናንተ ጋር እኮ በግራና በቀኝ ተቀምጠው የምትናገሩትን ሁሉ ፅፈው ወደ አላህ የሚያደርሱ መላኢካዎች እኮ አሉ። ስለዚህ እሱን ከሚያስቆጣና ከማይወደው ንግግር ለምን አትቆጠቡም በማለት መከራቸው።
📚 التبصرة لابن الجوزي( 2/237 )

↪️አላህም በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል።

【إِذْ يَتَلَقَّى ٱلْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ ٱلْيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ قَعِيدٌ】
🔘ሁለቱ ቃል ተቀባዮች (መላእክት) ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡

【مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ】
🔘አንድ ሰው ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላኢካዎች) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡
📚 سورة "ق" (18-17)

SELAM TV

11 Jul, 16:31


🔻ተክቢራ🔻


በነዚህ አስር ቀናቶች ከሚፈፀሙ ኢባዳዎች ውስጥ አንዱ ተክቢራ ነው። ዙል ሂጃ ከገባበት ሰአት ጀምሮ እስከ ዙልሂጃ አስራ ሶስተኛው ቀን ድርስ ተክቢራ ማለት የተወደደ ተግባር ነው። ስንተኛ፣ ስንነሳ፣ ስራ ላይ ስንሆን በማንኛውም ሰአት ወንዶች ድምፃችን ከፍ ሴቶች ዝቅ በማድረግ ተክቢራ ልንል ይገባል።

الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
@hidaya_bemuslim
@hidaya_bemuslim

SELAM TV

11 Jul, 11:10


✔️አቢ ሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይቀበላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልክተኛ صلي الله عليه وسلم እንዲህ አሉ. ከናንተ አንድኛቹህ ረስቶ ቢበላ ወይም ቢጠጣ ፆሙን ይቀጥል ያበላው አላህ ነው። 📚ቡኻሪ ዘግበውታል

1,478

subscribers

41

photos

32

videos