Fuad kheyredin @fuadkheyr Channel on Telegram

Fuad kheyredin

@fuadkheyr


የልብ ንግግር… የሀሳብ ዓለም…

ለሀሳብ @Fukheyredin

ፉዓድ ከይረይዲን (Amharic)

ፉዓድ ከይረይዲን በአማርኛ የልብ ንግግር እና የሀሳብ ዓለምን ለመቀነስ፣ ለትምህርትና ለነጻ መሰረት ላይ መረጃ በሚገኝ በቴሌግራም ዜናዎችን እና መረጃዎችን በትክክል እንዲያክል ይዘው ይጠቀሙ። የልብ ንግግር ላለው መዝናኛውና በቴሌግራም በሚገኘው @Fukheyredin በማድረግ ለጥንቃቄ እና አስከብርናቸው እንደአዟል። የፉዓድ ከይረይዲን ቴሌግራም አዘጋጅ ማለት እና ከምኞታችን በኃላ የመጣው ጌታ የሚሆነውን መልእክት ለማድረግ እና ሕዝብንም ለመቆጠር እናስታዋለን።

Fuad kheyredin

20 Aug, 17:25


አላህ አያረፍድም። ዩሱፍ ላይ እንዳላረፈደው።
👆👆
"አዳምጡት"

Fuad kheyredin

20 Aug, 17:23


https://vm.tiktok.com/ZMrWkY3QB/

Fuad kheyredin

17 Aug, 04:26


መካሪ ሁሉ ጨዋ አይደለም። በምክሩ ውስጥ አብዝቶ ስለፅድቅና የሚነግርህ ሰው ፃድቅ ነኝ እያለም አይደለም። በተሸወደበትና በወደቀበት ነገር ውስጥ የከፈለውን ዋጋ እየነገረህ ሊሆን ይችላል። ነፍሱን ማሰር በተሳነው ጉዳይ ላይ "ይህ ነው ክፈተቴ አንተ ግን በዚህ በኩል ነፍስህን አሸንፋት" ይሆናል የሀሳቡ ውጥን።
@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

15 Aug, 14:14


“ሰዎችን የመንገዱ አጋማሽ ላይ አትተው። መንገዱን በናንተ ምክንያት ብቻ ጀምረውት ሊሆን ይችላል።” የሚል የዐረብኛ ጥቅስ አነበብኩና እውነት ነው አልኩኝ።

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ስንት እህቶች ከአንዳንድ ወንዶች በተሰጣቸው አጉል የይሆናል ተስፋ መሀል መንገድ ላይ ቀርተዋል? የማያውቁትን መንገድ ጀምረው። በስራ ምክንያት እኛ እናውቀዋለን ብለው መሀል መንገድ ላይ በሚጠፉ ሰዎች ስንት ነጋዴዎች ከሰሩ? ስንት ወጣቶች በጓደኞቻቸው ውትወታ ጀምረውት… መመለስም ማለፍም የተሳናቸው የሱስ አዘቅት ውስጥ ገብተዋል። አይደል? እስኪ ሀሳብ ስጡበት።

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

10 Jul, 16:47


በመጨረሻም ዱንያ ከቤተሰብህ የበለጠ ውድ ነገር ልትሰጥህ አትችልም። ዱንያን በሙሉ ብትዞራት ከነርሱ የበለጠ ዋጋ ያለውን ነገር አታገኝም። ደስታን ከነርሱ ጋርና በነርሱ ውስጥ አብዝተህ ታሸተዋለህ፣ ትኖረዋለህ። ቤተሰብ ከዚያም ቤተሰብ ከዚያም ቤተሰብ።

@Fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

08 Jul, 17:00


ከጊዜ ጋር… የእድሜያችንን እኩሌታ ስናልፍ… ወደ አመሻሽ ላይ እንደድሮው ሁሉንም ነገራችንን ለሰው አንናገርም። መጥፎ የሆኑ ስሜቶቻችንን የመደበቅ ትልቅ ችሎታ ከወዴት እንደመጣ ሳናውቀው ይቆጣጠረናል። እንደጉድ እንችላለን። በጣም ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ምንም ያልሆንን ፅኑ መስሎ መታየት እንዴት እንደሆነ እንማራለን። አይገርምም? ወላጆቻችን የራሳቸውን ችግር ሲነግሩን እንኳን በአስተውሎት እናደምጣለን። የኛን ጉዳይ ሳንተነፍስላቸው። እንድናለቅስ የሚያስገድዱን ነገሮች ተፈጥረው እንኳን ፈገግታ ለመላበስ እንውተረተራለን። ፈገግታ የሚያሸነፈው የማይደረመስ የእንባ ግድብ ከየት መጣ? አቤት የአመሻሽ ውበት…

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

06 Jul, 07:55


"ዱዓዬ እጣፈንታዬን ለመቀየር በቂ አልነበረም ማለት ነው?" የሚሉ ከርታታ ልቦች አሉ። በህይወት ልዩ መልኮች እንቅፋት የተመቱ ልቦች። በህመም፣ በእዳ፣ በትዳር አለመሳካት፣ በሁኔታዎች መዘበራረቅና ግራመጋባት የሚዋኙ ስሜቶችም እንዲሁ። ምን ያህል ጌትዬን ተለማምጠናል? … ከአለሙ ሁሉ እስኪያስቀድመን፣ ከጠያቂዎች ሁሉ እስኪመርጠን። እርሱ የሚለማመጡትን ይወዳል። የሚወደውን ደግሞ ይመርጣል።
@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

05 Jul, 17:47


የተሸፈነ ነገር አይገለጥም። በተለይ አንድ ባርያ በርሱና በጌታው መካከል ስላጠፋው ጥፋት ለሰዎች እንዲታያቸው የምንገልጠው መጋረጃ አይኖርም። ደብቀንለት ለመምከር ካልሆነ በቀር ጌታው ጋር ይጨርስ ዘንድ መተው የደጋጎች መገለጫ ነው። ሁሉም ሰው ከራሱ ጋር እንኳን የሚተፋፈርበት መጥፎ ጎን ይኖረዋል። ለራሳችን እንኳን ደግመን ለመንገር የሚቀፈን ስንት ኃጥያት አለን? በቃ ሰዎች አክብረውን እንኳ ጥሩ ጎናቸውን ካሳዩን ይበቃናል። የጥፋት መዝገባቸውን ሙሉ ለሙሉ ብናውቅ እንኳን ከጌታቸው ዘንድ ያወሩ ዘንድ እድል እንሰጣለን እንጂ ለሰው ምላስ አሳልፈን አንሰጥም። እየተሸፋፈንን የምንመካከርበት ሜዳ ናት… ዱንያ።

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

05 Jun, 19:19


አለመፍረድ። ትንሽ በእድሜ ከፍ ስንል፣ ትንሽ በሚፈትኑ የህይወት ተሞክሮዎች ስናልፍ፣ ትንሽ በኢማን መጨመርና መቀነስ ውስጥ ስንመላለስ… የምንረዳው እውነታ ነው። በቃ… "ምናልባት" ብለን ማሰብ እንድንችል የሚያደርገን የብስለት ደረጃ ነው።

በሆነ መልኩ ዱንያ ያንገላታቻቸውን ሰዎች ስታይ … "ገንዘብ እንዴት እንደሚሰራ ማያውቁ ሞኝ ድሆች" ብለህ ጭራሽ እንዳታስብ። ጭራሽ። ትዳር ዓለም ያልዘለቀላቸውን ሰዎች ስታይ "የባህሪ ደካሞች፣ ጥሬዎች" ብለህ እንዳትፈርድ። እነርሱ ብቻ የሚያውቁት ብዙ ማታውቀው ነገር አለ። "ምናልባት" የሚያስብልህ።

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

24 May, 19:17


በጣም መንገብገብ፣ በጣም ክፍት መሆን፣ በጣም ራስን መስጠት ብዙ ጊዜ በጣም ያዋርዳል። ሁለተኛ ሰው ወይም አማራጭ የሚታይበት ሰው ያስደርጋል። ሁሉንም ነገር ሰጥቶ አንድ ነገር እንዲሰጡት የሚለምን አይነት ሰው ያስደርጋል። ሰዎች ያልተዘጋጁበትና ያላሰቡት ዓይነት ቦታ ስትመጣላቸው ይኮራሉ። በእጅ ያለወርቅ እንደመዳብ የሚሉትን ዓይነት እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን… በራሳችን እጅ። አንዳንዴ "አይመቸኝም" ያስፈልጋል። አንዳንዴ "ፈልገው ይደውሉ" ብሎ መተውም ያስፈልጋል። … ሲመስለኝ።

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

19 May, 07:04


ግብፃዊው ፀሓፊና ፈላስፋ አኒስ መንሱር “የሰዎችን ውስጣዊ ዓለም እንዴት ነው ማወቅ የምንችለው?" የሚል ጥያቄ ተጠይቆ ነበር። እንዲህ ሲል መለሰ፦
“ባል ሚስቱ በታመመች ጊዜ ይታወቃል። ሚስት ደግሞ ባሏ በደኸየ ጊዜ ትታወቃለች። በመከራ(ችግር) ወቅት የእውነት ጓደኛ ይበጠራል። ልጆች ወላጆቻቸው ሲሸመግሉ ይታወቃሉ። ወንድምና እህቶች የውርስ ጊዜ ይታወቃሉ። ዘመድአዝማድ በብቸኝነት ውስጥ እንግዳ ሆነህ ሲያገኙህ ታውቃቸዋለህ። የእውነት ፍቅር ደግሞ ጥቅም ሲያበቃ ይታወቃል። አማኝ በፈተና ወቅት ይለያል።”

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

06 May, 09:52


ውስብስብ ጉዳዮቹን ለአላህ አደራ የሰጠ ሰው አይከስርም፣ አይፀፀትም።

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

24 Mar, 08:09


አቡበከር የቢላልን ያህል ድብደባ አላስተናገደም።  ድህነትም እንደአቡዘር አልፈተነችውም። ሰይፎች የኻሊድን ያህል ታዘውት በካሃዲያን አንገት ላይ አላሳረፈም። ግን  ከሁሉም የሚበልጥ ሰሓባ ነበር። ለነብዩ ልቡን ሰጥቷል። እንዳሻዎት ያድርጉኝ ብሏል። የልብ ሰው!!

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

22 Mar, 10:18


በዙሪያህ ያለውን ሁሉንም ነገር ለመረዳት አትሞክር። አንዳንድ ጉዳዮችን አለመረዳት ነው የሚሻለው። አንዳንዴ ነገሩን በመረዳትህ የሚመጣብህ የልቦና ቀውስና አንደበትህ ላይ የሰዎች ስም መመላለስ ብቻ ነው። …  በቃ ምናገባኝ ማለት አስፈላጊ ነው። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ!

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

12 Mar, 16:51


ሰዎችም እድል ናቸው። በሆነ አጋጣሚ የምናገኛቸው ወይንም የምናጣቸው። ሁል ጊዜ በነበረበት የምናገኘው አይኖርም። ምናልባት ዛሬ ለኛ የተገባ ሰው… ነገ ላይሆን ይችላል።

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

11 Mar, 17:05


"አንዲት ሴት ለቤተሰቦቿ ምግብ ማዘጋጀቷ  ፆመኞችን የማስፈጠር አጅር ውስጥ ይካተታል።"
ሸይኽ ኻሊድ መስለህ
@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

10 Mar, 18:50


“ጌታዬ ሆይ! ባምፅህም እወድሃለሁ።”
ታላቁ ሰሓባ ዐምር ቢን ዓስ

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

11 Feb, 17:23


ድንገት አልነበረም። የቀደር መስመር ላይ ነው የተገናኛችሁት። በህይወትህ ላይ የሆኑ ትምህርቶችን ሰጥተውህ ያለፉት ሁሉ(ምናልባትም ክፉዎች)፣ ከዋክብቶች ሲሸሹህ ሰማይህን ሊያበሩልህ የመጡት ምርጥ ሰዎችህ ሁሉ… ለነርሱ የተወሰነላቸው የህይወት ዓለም ከተወሰነልህ የህይወት ዓለም ጋር እንዲነካካ ተፅፏል። ሌላ አይደለም።

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

10 Feb, 19:21


እና ከሁሉ ነገር በኋላ… ዱዓ የሌለበት ዓለም ከንቱ እንደሆነ ይገባሃል። በመጨረሻ… ስኬትም ስክነትም እዚህ መተናነስ ውስጥ እንደነበረ ትረዳለህ። አልሏሁመ!!

@fuadkheyr
@fuadkheyr

Fuad kheyredin

10 Feb, 19:03


አንዳንድ ሰዎች አይንህን ብትሰጣቸው "ከነቅንድቡ አልሰጠንም" ብለው ያወራሉ።  እነዚህ ምንም ብታደርግላቸው መልካም ጎንህን ለመመልከት የሚከብዳቸው ሰዎች ናቸው።

@Fuadkheyr
@fuadkheyr

2,133

subscribers

21

photos

4

videos