General Wingate Students Channel @gwstudent Channel on Telegram

General Wingate Students Channel

@gwstudent


ይህ የጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተማሪ ቻናል ነው። @Gw2016bot
This is the Student Channel of General Wingate Polytechnic College.

General Wingate Students Channel (Amharic)

ወደ ጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ኮሌጁን ቻናል የተመዝገቡትን ቴክኒክ ኮለጠር እንዴት ያወቁን ማንኛውንም ዝግጅት፣ ትምህርት ወደጆንል ለመማር እና ለማስተዋወቅ እባኮችን ማሳየት ብለን የጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዲስ አማርኛ ቴክኒክ ቻናል ተጠቃሚው በማየት ከሚሆነው ቴክን ተምሳሌ። @Gw2016bot

General Wingate Students Channel

21 Nov, 17:54


ማስታወሻ
Aladi's Collection ከ General Wingate Polytechnic College Student Council ጋር በጋራ በመተባበር ለተከታታይ ሁለት ቀን ማንኛውንም አይነት የፈለጋችሁትን መፃሀፍቶች በኮሌጁ ላይብረሪ በመምጣት መቀየር እንደምትችሉ ገልፀን ነበር ፤ሆኖም በእነዚህ ሁለት ቀን መጥታችሁ መቀየር ያልቻላችሁ ነገ አርብ 13/03/2017 ዓ.ም በኮሌጁ ላይብረሪ በመገኘት የምትፈልጉትን አይነት መፅሀፍት መለወጥ እንደምትችሉ ለመግለፅ እንወዳለን።
ቦታ - የኮሌጁ ቤተ መፅሀፍት
ሰዓት - ከ3:00 -11:00 ድረስ

General Wingate Students Channel

19 Nov, 18:29


ለመፅሃፍት አንባቢያን በሙሉ

Aladi's Collection ከ General Wingate Polytechnic College Student Council ጋር በመተባበር ለመፅሀፍ አንባቢ ወዳጆች አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል ። ከነገ ዕሮብ ህዳር 11 /2017ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን እስከ አርብ 13/2017ዓ.ም ድረስ ከ3:00 ጀምሮ ያነበባችሁት እጃችሁ ላይ ያሉትን መፅሀፎች ይዛችሁ በመምጣት በምትኩ ማንበብ የፈለጋችሁትን ማንኛውንም መፅሀፍ መቀየር እንደምትችሉ ስንገልፅ በደስታ ነው።

👉 ከእናንተ የሚጠበቀው የምትቀይሩት መፅሀፍ የፊት ገፁ ያልተቀደደ እንዲሁም በውስጡ ያሉት ገፆች ያልጎደሉ ሙሉ መሆን አለባቸው።
👉 ከ ፖለቲካ ሀይማኖት እንዲሁም የትምህርት መፅሀፎች በስተቀር ሁሉንም አይነት የመፅሀፍ ዘውጎች ያካተተ ስለሆነ በፈለጋችሁት አይነት መቀየር ትችላላችሁ ።
📍ቦታ የኮሌጁ ላይብረሪ ውስጥ ከ 3:00 ጀምሮ

©️GWPTC Student Council

General Wingate Students Channel

19 Nov, 18:17


ICT night class.pdf

General Wingate Students Channel

18 Nov, 09:58


Do you like reading books? 📚📖📙

We invite you to bring your gently used books and exchange them for any books from Aladi's collection. This is a wonderful opportunity to refresh your personal library while sharing reading materials with others.
@addisamcenter                           register to attend: https://forms.gle/oDvSbGcESg6Jo61d8

General Wingate Students Channel

15 Nov, 15:02


ለሁሉም የቀን አዲስ ገቢ ሰልጣኞች

ከ16/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ የስልጠና ልብስ(ጋወንና ቱታ) ሳይለብሱ ወደ ግቢም ሆነ ወደ ስልጠና ክፍል መግባት የማይቻል መሆኑን አውቃችሁ ከላይ በተገለፀው መሰረት አዘጋጅታችሁ በመልበስ የምትመጡ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ እናሳውቃለን።

ኮሌጁ

General Wingate Students Channel

12 Nov, 10:13


የቀን ስልጠና ሚጀምረው

ረቡዕ 04/03/2017 ዓ.ም ጠዋት 2:45
መቅረት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

ኮሌጁ

General Wingate Students Channel

10 Nov, 10:09


ማስታወሻ
ነገ ማለትም ሰኞ 02/03/2017 ጋቢ Day ስለሚከበር ሁላችሁም ጋቢ ይዛችሁ በመምጣት የፕሮግራሙ ተሳታፊ መሆን ትችላላችሁ ።
ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በዕለቱ ዲኖች የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የ2017ዓ.ም አዲስ ገቢ ሰልጣኞች ይገኙበታል።

General Wingate Students Channel

07 Nov, 09:54


📍Postponed
ነገ ሊካሄድ የነበረው የጋቢ ደይ በተለያዩ ምክኒያቶች ወደ ሰኞ ህዳር 2 / 2017 ዓ.ም ተዘዋውሯል።

General Wingate Students Channel

04 Nov, 17:21


    ከ3ሺ 300 በላይ አዳዲስ ሰልጣኞች በ2 ሳምንት ተመዘገቡ!!👏🏼👏🏼

ኮሌጁ የ2017 ዓ.ም አዳዲስ ሰልጣኞችን  ከጥቅም 15 ቀን 2017 ዓ∙ም ጀምሮ በበየነ መረብ /online/  እና በሀርድ ኮፒ ለ2 ሳምንታት የመዘገበ ሲሆን በዚህም 3365 የሚሆኑ አዳዲስ ሰልጣኞችን መዝግቧል።

ኮሌጁ አሁን ላይ በISO 9001:2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ መሆኑ፤ የስልጠና ጥራቱን ለማሳደግ ከግዙፍ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራቱ  እና ባለው ተቋማዊ ዘርፈ ብዙ ፋሲሊቲዎች ለስልጠና ጥራቱ ትኩረት መስጠቱ ተመራጭነቱን ይበልጥ ስላሰፋው ከፍተኛ ተመዝጋቢ ካላቸው የመዲናችን ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ተርታ ይሰለፋል።

ውድ አዳዲስ ተመዝጋቢዎች! በመሉ እምነት እኛን ተማምናችሁ መርጣችሁን ስለመጣችሁ እናመሰግናለን።

የምዝገባ ቀናትን በተመከለተ ምንም እንኳን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ቢታቀድም በተለያየ ምክኒያት ምዝገባቸውን ላላጠናቀቁ አመልካቾች ተጨማሪ 4 ቀናት ዕድል ተመቻችቷል።                                                    
ስለሆነም እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ባሉበት ሆነው በበየነ መረብ /online/ ወይም በኮሌጁ በአካል በመገኘት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ስናበስርዎት በታላቅ ደስታ ነው።      

የሙያ ምርጫን በተመለከተ በማታና በቅዳሜና እሁድ ለምትሰለጥኑ በፍላጎታችሁ የምትስተናገዱ ሲሆን ለቀን አመልካቾች ደግሞ ከቢዝነስ፣ ከአይሲቲ፣ ከአውቶሞቲቭ እና ከፉሽን ዲዛይን ዲፓርትመንቶች ውጪ ባሉ ሙያዎች እንደ ምርጫችሁ ትስተናገዳላችሁ።  

ስለሆነም በተቀመጡበት ቀሪ ቀናት ፈጥነው እንዲመዘገቡ እየሞከርን ከዚያ በኋላ የመመዝገቢያ ሰንደቁ /ሊንኩ/ የሚዘጋ መሆኑን እንገልፃለን።

   "በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

General Wingate Students Channel

04 Nov, 12:41


ልዩ የትምህርት  ድጋፍ እድል ከፋዌ ኢትዮጵያ !

ፋዌ ኢትዮጵያ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር እድሚያቸው ከ 15 እስክ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴት እና የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ኮርሶች ነው፡፡

ምዝገባው የሚካሄደው በአዲስ አበባ  ከተማ  በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣  ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን አመልካቾች በ2014፣2015 ወይም 2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ እና የ2017ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ መግቢያ ውጤት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

የማመልከቻ ቀናት ከጥቅምት 22-29/2017 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡ 
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0911330024 / 0902662688
አዳማ  በ 0911383055
ባህርዳር በ 0913042043
ሀዋሳ በ 0965679139 በመደወል ወይም በድረ፟ገጻችንwww.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ሴቶችን ማስተማር ህብረተሰብን ማስተማር ነው!

ምዝግባዉም ሆነ የመረጣው ሂደተ ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃልን