𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 @abusufiyan_albenan Channel on Telegram

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

@abusufiyan_albenan


➜ ከዚህ ቻናል አንብባችሁ በተጠቀማችሁ ቁጥር፤ይህን ደካማ እና ስህተቱ ብዙ የሆነውን ወንድማችሁን በመልካም ዱዓችሁ አስታውሱት!
||
ወንድማችሁ አቡ ሱፍያን―
@Benan65

አቡ ሱፍያን~ቻናል (Amharic)

ይህ ቻናል አንብባችሁ በተጠቀማችሁ ቁጥር፤ በመልካም ዱዓችሁ አስታውሱት፣ እና ስህተቱ ብዙ የሆነውን ወንድማችሁን ደካማ እና ስህተቱን በብቻ ማከሚያዎች እና የሚያሳውቁትን መልእክተኛ ቅንብሮች ተመልከቱ። አቡ ሱፍያን ተሰምተናል፣ እርምጃዎችን ለመቀበል ደካማ እና ስህተቱን በብቻ ተልኩ።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

11 Jan, 19:51


بِذكر الإلهِ تطيبُ الحياة

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

11 Jan, 15:02


ራስህን ሰብሰብ አድርገህ ተሸከም። ታሪክህን ለመስማት የሚጓጓ እንጂ ችግርህን ለመፍታት አብሮህ የሚጨነቅ የለም።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

11 Jan, 08:04


🎁ታላቅ የሙሓደራ   ፕሮግራም📱
በጌቶ ወረዳ ሙስሊም ወጣቶች ጀማዐ ግሩፕ

በእለቱ ተጋባዥ እንግዳ እና ርዕስ

ኡስታዝ አብድራህማን አባስ

ርዕስ  የአብሬት መውሊድ ቢደዐ ነውን
በጉራግኛ  ቋንቋ

❄️ቀን  ዛሬ ቅዳሜ ✈️

ሰአት ⭐️ ከምሽቱ 3⃣:0⃣0⃣ጀምሮ

  ሙሓደራው  የሚካሄድበት  ግሩፕ
የጌቶ  ወረዳ ሙስሊም  ወጣቶች  ጀማዐ
🔤✈️🔤

⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
➡️   https://t.me/+05iEttbAV91lMWE0

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

10 Jan, 18:23


«አንቱ ሰው ጌታዎን ምን ብለው እያመሰገኑት ነው?»
«ልቦችን የምታገለባብጠው አንተ ስለሆንክ ምስጋና ይገባህ እያልኩ ነው።»
«አልገባኝም?»
« የኔ ልጅ ልባችንን እርሱ ዘንድ የሆነውን ጌታችንን እያመፅነው፣ የልባችንን እድፍ እየተመለከተ ነው የሚያዝንልን! የኔ ልጅ ልብን ያህል የምስጢር ውቅያኖስ ሰዎች የሚዘውሩት ቢሆን እንዴት እንሆን ነበር? ልባችንን ማዘዝ ሳይችሉ ሰዎች የከበዱን ልባችንን ማዘዝ የሚችሉ ቢሆን ምን ይውጠን ነበር? የኔ ልጅ የልብህን ምስጢር ጌታህ ብቻ ስለሚያውቀው አመስግነው! »
«አንቱ ሰው እወዶታለሁ! »

ልባችሁን በሰዎች ላይ ከማንጠልጠል የልቤ ጌታ ይጠብቃችሁ!
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

10 Jan, 18:03


ሰው እየበሰለ ሲሄድ የማስመሰሉን ባህሪ ይቀንሳል፣ ይደክመዋል፣ በሂደትም ይተዋል። ለዚህም ነው ከፍ እያልን ስንሄድ የጓደኞቻችን ቁጥር የሚቀንሰው።

መሰለኝ ...

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

10 Jan, 11:42


~አባት በወጣትነቱ ወንድ ልጅ ሲያገኝ ይደሰታል፣ ሴት ልጅ ስትወለድለት ደግሞ ይበሳጫል። በስተርጅና ማምሻ ዕድሜው ላይ ግን ብዙ ጊዜ የምትጠይቀዉና ከታመመም አስታማሚው ሴት ልጁ ናት።

የመጀመሪያ ልጅ ሴት መሆን በረከት ነው ይላሉ። ክብር ለሴት ልጅ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

09 Jan, 17:20


ብዙ የመስጂድ ኢማሞች ይህን ቢድዓ ሲፈፅሙት ይስተዋላል!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

09 Jan, 14:30


አፈርኩ...

~ ከሚገባኝ በላይ ሲሰጠኝ አፈርኩ፣
~ የማይገብባኝን ሁሉ ሲደርብልኝ አፈርኩ፣
~ ለማመስገን በሰነፍኩ ጊዜ አፈርኩ፣
~ ጥፋቴን ሁሉ እያየ ሲያልፈኝ አፈርኩ፣
~ ውርደቴን ሲደብቅልኝ አፈርኩ፣
~ ተውባዬን ባስተዋልኩ ጊዜ አፈርኩ፣
~ ፀጋውን መሸከም አቃተኝና አፈርኩ፣
~ እኔ እየሸሸሁት እሱ ሲከተለኝ አፈርኩ፣
~ ተኝቼም ነቅቼም ሲጠብቀኝ ባየሁ ጊዜ አፈርኩ፣

ወላሂ አፈርኩ...
اللهم لك الحمد كما ينبغي لجلال وجهك وعظيم سلطانك…
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

08 Jan, 18:40


~በችግርህና ለችግርህ መፍትሄ ማግኘት መካከል ያለው ርቀት በግንባርህና በመሬት መካከል ያለው ርቀት ብቻ ነው ፡፡ ሱጁድ በመውረድ ለአምላክህ ችግርህን ነገርከው ማለት ችግርህ ተፈታ ማለት ነው ፡፡
ይኸው ነው።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

08 Jan, 07:47


http://t.me/tdarna_islam

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

07 Jan, 17:54


📚ዛሬ ሁላችንም ልንከታተለው የሚገባ አንድ ምርጥ ኪታብ በ ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ ይጀመራል!

▶️ትምህርት የሚሰጠው በዚህ ቻናል ሊንክ ነው👇
https://t.me/fewaidabdurazaq
https://t.me/fewaidabdurazaq

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

07 Jan, 17:08


~ለሰው ሊነገሩ የማይችሉ ቁስሎች አሉ። በቃላት ቢገለፁ ህመሙን ከማስታወስ በቀር ፋይዳ የሌላቸው ህመሞች አሉ። በስድ አፅናኞች «ያልፋል!» ተብለው ቀለል የሚደረጉ የሚያደሙ ስቃዮች አሉ። የልባችሁን ሰላም ጀባሩ ይመልስላችሁ። ልቦችን በፍቅር የሚዳብሱ ልባሞች አላህ ማስገኘቱን አላበቃም። ወደሱ ገስግሱ፣ የልባችሁን ጉዳይ ከእርሱ በቀር የሚረዳው የለም። አብሽሩ!
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

07 Jan, 11:17


~ከፊትለፊታችን ያሉ ቀናት ምን እንደያዙልን አናውቅም ። ግና አምላካችን ሩህሩህና አዛኝ እንደሆኑ እናውቃለን። ተስፋችን ሁሌም አንተው ነህ። ከጠየቅንህ በላይ አደረግክልን። ከለመንንህ በላይ ሠጠኸን።አምላካችን ሆይ! አንተ ከራቅከን እኛ ምንም ነን። በዲንህ ላይ አጽናን። ከመስመርህ ከሚያስወጣ፣ ነሻጣችንን ከሚያበርድ፣ ሩሓችንን ከሚሰርቅ ነገር ሁሉ ጠብቀን።
=t.me/Benan68

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

06 Jan, 06:54


አስቸኳይ  የእርዳታ  ጥሪ !!

አሰላሙ  አለይኩም  ወራህመቱለሂ  ወበረካቱህ 
ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወንድማችን ሚስባህ ተማም መሀመድ  ይባላል  ኑሮውን በአዲስ አበባ  ያደረገ ሲሆን እድሜው 28  ነው:: ላለፉት 4 ዓመታት በከባድ  የኩላሊት ህመም እየተሰቃየ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በሳምንት ለሁለት ጊዜ  7,000 (ሰባት ሺ ብር )  በመክፈል  የኩላሊት እጥበት  በሆስፒታል  በማድረግ ላይ ይገኛል። በተጨማሪም ለረጅም ጊዜ ደረቱ አካባቢ በሚገኝ  ትቦ በኩል ትጥበት በማድረጉ  የደም ትቦ  መጥበብም አጓጥሞታል፡፡ ለትጥበቱ  ወጪ  የቤተሰብ  ቋሚ ንብረት ጀምሮ እጁ ላይ ያለውን ቅሪት ሙሉ ሽጦ ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ከመጅሊስ የድጋፍ ደብዳቤ በመውሰድ በአራት መስጂዶች ላይ የገቢ ማሰባሰብ በማድረግ 450,000 (አራት መቶ ሃምሳ ሺ ብር) ያገኘ ቢሆንም  ሕይወቱን ለማስቀጠል  ዘላቂ  መፍትሔ  ሊሆን አልቻለም፡፡ ስለሆነም  ወደ ውጭ  ሐገር  በመሄድ የተዘጋ የደም ትቦ በማስከፈትና  የኩላሊት ንቅለ–ተከላ ሕክምና በማድረግ ሕይወቱን ማትረፍ እንደሚችል የጥቁር አንበሳ  የሐኪሞች ቦርድ ተወያይቶ ባቀረበው ምክረ–ሐሳብ  መሰረት በሕንድ ሀገር ህክምና ማድረግ እንደሚችል የተገለጸለት ሲሆን  የሕክምና ወጪውም  ለደም ትቦ ማስፋት  1,400,000 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ  ሺህ) ብር እንዲሁም ለኩላሊት ንቅለ ተከላ 2,500,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ  ሺህ) በአጠቃላይ 3,900,000 (ሶስት  ሚሊዮን  ዘጠኝ  መቶ  ሺህ)    እንደሚያስፈልግ  የተገለፀ ሲሆን ይህ ብር  ለእርሱም ሆነ ለቤተሰቦቹ ከአቅም በላይ  በመሆኑ ከአላህ ቀጥሎ የሁሉም ሙስሊም እርዳታ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት  ሁላችሁም  የአላህን ምንዳ  ጀነቱን ለማግኘት ስትሉ  የወንድማችንን  ሕይወቱን  ለመታደግ  ሰበብ ሁኑልን ስንል በአላህ ስም እንማፀናለን። 

ለበለጠ መረጃ  በስልክ ቁጥር 0910666736
እንዲሁም በአካል አለም ባንክ የተከራየው ቤት በመሄድ ታካሚውንም ሆነ ቤተሰቦቹን ማግኘት እንደሚችሉ በትህትና እንገልፃለን።
ነፍስን ህያው ከማድረግ በላይ የአንድ ሰው ገንዘብ ምን ተኣምር ሊሰራ ይችላል!?
የአቅሞትን ከታች በተዘረዘሩት የባንክ አካውንቶች ያስገቡ
የአካውንቶቹ ስም ሙስባህ ተማም መሀመድ
ዘምዘም ባንክ፡- 0025936320101/259363
ንግድ ባንክ፡-1000549483082
ዳሽን ባንክ፡-2939216121321
አቢሲኒያ ባንክ፡-193025595
ንብ ባንክ፡-4130
አዋሽ ባንክ፡-01425927730500

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

05 Jan, 18:56


• ዓላማችን ተከታይ ማብዛት አይደለም
ለመወደስና ለመሞገስም አይደለም!

የፈጠረንን አንድ አምላክ ለፍጥረታት ሁሉ ማስታወስ፣ በሕይወት እያለን ሞት ሳይቀድመን፣ መቃብር ወርደን አፈር ሳንሆን፤

ከመለኮታዊው ዓለም የመጣልንን ሐቅ ማድረስ፣ በአላህ ፈቃድ ወደ ጀነት አብሮ መፍሰስ።

ባንተ ምክንያት አንድ ሰው ተስተካከለ ማለት፤ እሱ የሚያገኘውን ምንዳ ሁሉ ተጋራህ ማለት ነው።
= t.me/Benan68

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

05 Jan, 17:07


እናንተ ግን እዚህኛው ቤታችሁ እየገባችሁ ሰወችን አድ አታደርጉምዴ¡¿ ካልሆን ጓዜን ጠቅልሌ ወደሱ እንዳልሄድ¡👇
https://t.me/Benan68
https://t.me/Benan68

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

05 Jan, 16:02


መስጂድ ውስጥ መቀመጥ ያለው ደረጃ―
⚡️ወንድም አቡ ሱፍያን
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

05 Jan, 04:40


إِذَا زُلْزِلَتِ الْأَرْضُ زِلْزَالَهَا
ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤
وَأَخْرَجَتِ الْأَرْضُ أَثْقَالَهَا
ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤
وَقَالَ الْإِنسَانُ مَا لَهَا
ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤
يَوْمَئِذٍ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا
በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡

بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا
ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

04 Jan, 19:28


~ጌታዬ  ሆይ! የቂያም ቀን ደርሶ ከማልቀሴ በፊት ዛሬ ባንተ ፍራቻ የምታለቅስ ዐይን ስጠኝ፤
• ያ ቀን ተከስቶ ከመቆጨቴ በፊት ዛሬ አስተዋይ ልቦና አውርሠኝ፤
• የቂያም ቀን እውን ሆኖ ከመባነኔ በፊት ዛሬ ተዘናግቼ ካለሁበት ሁኔታ ቀስቅሰኝ።

• አምላካችን ሆይ! ንፁሃንን ብቻ እንጂ የማትቀበል ከሆነ ለእኛስ ለቆሸሹት ማን አለልን!፤
• አሳማሪዎችን እንጂ የሚያበላሹትን የማትሰማ ከሆነ ለኛስ አጥፊዎቹስ ማን ይድረስልን!።
• ጌታችን ሆይ! ጥፋት ብንፈጽምም አንተን መታዘዝ እንወዳለን። 
• የተለያዩ በርካታ  ወንጀሎችን ብንፈጽምም ባንተ ማመፅን እንጠላለን።
• ወደ ጀነት ሊያስገባን የሚችል በቂ የሆነ መልካም ስራ ባይኖረንም ጀነትን ስጠን።
• እንደ ክፉ ሥራችን ብዛት የሚገባን ቦታ ጀሀነም ቢሆንም ከጀሀነም ጠብቀን፡ አርቀን።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

04 Jan, 13:56


ማስታዎሻ!
• ይህን የ ሸይኽ አብዱ ረዛቅ አል-በድር ድንቅ ኪታብ ነገ እሁድ ከ ዓሱር ብኃላ በ ሰላም መስጂድ እንጀምራለን።―ኢንሻ አላህ―
📚من وصايا السلف للشباب
«ከቀደምቶች ምክር ለወጣቶች!»
መልዕክቱን ላልሰሙት አድርሱላቸው!

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

04 Jan, 07:17


በኢትዮጵያ እስከዛሬ ከተመዘገበው መጠን ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

ሌሊት 9፡52 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ ተምዝግቧል። በሳምንቱ 66 የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፤ 6ቱ በሬክተር ስኬል ከ5 በለይ ተመዝግዋል።

አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

04 Jan, 04:39


~ዛሬ ሌሊት ከስከዛሬው በተለየ መልኩ ነበር መሬት የተንቀጠቀጠው። እኔ በህልሜ ነው ብየ ነበር።: ከእንቅልፌ ስነቃ ለካስ ጎረቤት ሁሉ ስለ እሱ ነው የሚያወራው።

አላህ ይድረስልን! በዚህ ሳምንት በተከታያይ በሚባል መልኩ ነው መንቀጥቀጥ የያዘችው መሬት።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

03 Jan, 12:11


⚡️ ቲክ-ቶክ ላይ መመላለሱ መልካም ነገር ባይኖረውም፤ነገር ግን አላህ ግዜውን በረካ ላደረገለት ሰው እና ፊትናውን አውቆ ለሚገባ ሰው አንዳንድ መልዕክቶችን በዚያ ቢያስተላልፍ ትልቅ ስራን መስራት ይችላል!

ሰሞኑን ብዙ ሰለፍያ ወንድሞቻችን ወደዚያው ጎራ እያሉ ነው!―
فأسأل الله جل وعلا بأسمائه الحسنى وصفاته العليا أن يوفقنا وإياكم لما يرضيه وأن يصلح قلوبنا وأعمالنا جميعا

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

03 Jan, 12:03


አዲሱ የቲክቶክ ፔጃችንን follow በማድረግ ይቀላቀሉ👇
https://vm.tiktok.com/ZMkDPSCBS/

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

02 Jan, 19:39


ሸህ አህመድ ደግ አደረጉ¡ ማብራት ከለለ መደርደሪያ ማድረጉ ነው ሚሻለው¡
= t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

02 Jan, 14:53


ወደ ኃላ…

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

02 Jan, 14:47


እንድህ እያጠነጠነ ያዳመጠ¡

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

02 Jan, 09:26


መዝሪያችን አሁን ነው!

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

01 Jan, 18:41


እጅ ወደ ላይ አንስታችሁ ረጅም ዱዓ ማድረግ ቢያቅታችሁ እንኳ «ያ ረብ!» ካላችሁ በቂ ነው። እሱ ያላችሁበትን ሁኔታ ሁሉ ያውቃል።
📱 t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

01 Jan, 16:46


~በረጀብ ወር ዑምራ ማድረግ ይበረታታል። ኢብኑ አቢ ሸይባ በትክክለኛ ሰነድ እንደዘገበው ዑመር፣ ዑስማን፣ ዐኢሻ፣ ኢብኑ ዑመርና ሌሎችም ሶሃባዎች በረጀብ ዑምራ አድርገዋል። ኢብኑ ረጀብ እንደገለፁት ዑመር ቢን ኸጧብ በረጀብ ዑምራ ማድረግን ይወድ ነበር። ኢብኑ ሲሪንም ሰለፎች በረጀብ ወር ዑምራ ያደርጉ ነበር ብሎ አስተላልፏል።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

01 Jan, 06:37


🎁ታላቅ የሙሓደራ   ፕሮግራም📱


🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️
🔤🔤🔠🔤🔤🔤🔤🅰️🔤  ግሩፕ  ላይ  የዳዕዋ  ፕሮግራም  አዘጋጅተን  እየጠበቅናችሁ  እንገኛለን።

ተጋባዥ 🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠

⭐️ኡስታዝ ኸድር አህመድ
⭐️ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ አል-ባጂ
⭐️ኡስታዝ ዶ/ር ሰዒድ ሙሳ
⭐️ኡስታዝ አቡ ሱፍያን
⭐️ኡስታዝ አቡ ሙአዝ
⭐️ኡስታዝ አቡ ዐብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
⭐️ሼህ አውል አል_ከሚሴ(አቡ አማር)

🔢መድረኩን የሚመሩልን ወንድሞች
አቡ ሑዘይፋ ሰኢድ
አቡ ሂበቲላህ ሁሴን
አቡ ፈዉዛን አብዱ ሽኩር

በእለቱም ታላቅ የምስራች ይኖረናል ሁላችሁም በጉጉት እንድትጠብቁን እናሳስባለን

❄️የፊታችን ጁማዓ✈️

ሰአት ⭐️ ከምሽቱ 3⃣:0⃣0⃣ጀምሮ

  ሙሓደራው  የሚካሄድበት  ግሩፕ
መርከዝ አቡ ፈውዛን🔤✈️🔤
    👇👇👇

t.me/merkez_abu_fewzan
t.me/merkez_abu_fewzan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

01 Jan, 05:17


የ ረጀብ ወር ገብቷል!

ረመዷን🌀

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

31 Dec, 15:03


~በቃ ምንም ብታፈቅሪው ምንም ያክል ብታምኚው..…ሰው ነው ብለሽ አስቢ… እንዳሰብሽው ባይሆን እና ስህተት ቢሰራ ህመምሽን ምትቋቋሚበት ትንሽ ጥንካሬ ለራስሽ አስቀምጪ። ለሱ ካለሽ ፍቅር እና እምነት ትንሽ ለራስሽም አስቀሪ።ሰው ነው ብለሽ አስቢ.... በፍቅርሽ እና በእምነትሽ ልክ ፍፁም አታድርጊው ጥንካሬ እንዲሆንሽ ለራስሽም የመፅናኛ ቃል አስቀምጪ ሰው ነው ብለሽ አስቢ .....

«ሰው ነው»
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

31 Dec, 09:08


ይህም ቤታችሁ ነው!👇
https://t.me/Benan68
https://t.me/Benan68

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

31 Dec, 09:05


• ምን ያመጣል? ምን ታመጣለች?ብላችሁ…የትከሻዋን መሳሳት፣ ሁነኛ ዘመድ እንደሌለው አስልታችሁ በግፍና በጭካኔ የሰበራችሁት ልብ ከአላህ ጋር ያለው ትስስር ጠንካራ ቢሆንስ ምን ሊውጣችሁ? በጥሩ ሁኔታ መለያየትም እኮ አንድ ጥሩነት ነው።
فإمساك بمعروف أو تسريح بإحسان
እንዲል ቁርአኑ…በደልን ተጠንቀቁ!
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

31 Dec, 07:34


~የ͟ተ͟ከ͟በ͟ሩ͟ ወ͟ራ͟ት͟ (አ͟ሽ͟ሁ͟ሩ͟ል͟‐ሑ͟ሩ͟ም͟)

አላህ እንዲህ ብሏል፦
"إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ"
«የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»

የተከበሩ ወራት አራት ናቸው:
• ዙል‐ቀዕዳ (ቂዕዳ አትበሉ)
• ዙል‐ሒጃ
• ሙሐር‐ረም
• ረጀብ
ሦስቱ ተከታታይ ወራት ናቸው። አንዱ ብቸኛ ነው። እርሱም ረጀብ ነው። በሂጅራ አቆጣጠር ሰባተኛው ወር ነው።

ኢማም አል‐ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»
(ከላይ የጠቀስነው አያ ውስጥ)ኃጢኣት በመፈፀም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ ማለት ነው። ምክንያቱም የመልካም ሥራዎች ምንዳ እንደሚነባበረው ሁሉ በዚህ ጊዜ የሚፈፀም ኃጢኣትም ቅጣቱ ይነባበራል። 
ቀታዳ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በተከበሩት ወራት የሚፈፀም በደል በሌላ ጊዜ ከሚፈፀመው እጅግ የከፋ ወንጀል ነው።»

ለነፍሳችን መዳን የምንመርጠው ጊዜ ላይ አለንና እናስብበት!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

30 Dec, 17:28


አምስቱ የተውበት መስፈርቶች

🎙ሸይኽ ሙሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ (ረሂመሁላህ)
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

30 Dec, 12:15


አላህ በተሻለ ነገር ይተካችሁ!

• ሌላ አማራጭ መከተል ስትችሉ የምትወዷቸውን ቤተሰቦቻችሁን መርዳት ስላለባችሁ ብቻ የማትፈልጉትን ስራ ለምትሰሩ፣

• ትዳር ይዛችሁ የግል ሕይወታችሁን መኖር ስትችሉ እናንተ ከሄዳችሁ ደጋፊ ለሌላቸው ሰዎች ስትሉ እቅዳችሁን ይቆይልኝ ላላችሁ፣

• ሌላ ስፍራ ሄዳችሁ መኖር ስትችሉ የእናንተ በአካባቢው መገኘት ለሕልውናቸው ወሳኝ ለሆነላቸው ሰዎች ስትሉ እግራችሁን ለሰበሰባችሁ፣

• ሌላ ሕይወት መጀመር ስትችሉ ለልጆችሁ ስትሉ ለጊዜውም ቢሆን የብቸኝነትን ኑሮ ይዛችሁ ለምትታገሉ ብቸኛ ወላጆች፣

• ለተደረገባችሁ ክፉ ነገር አጸፋ ብትመልሱ ለብዙ አመታት የተገነባ ነገር እንዳይፈርስ በማለት ብዙ ነገር በትእግስትና በዝምታ ለተሸከማችሁ፣

ለእናንተና መሰሎቻችሁ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት አለኝ!

ጀሊሉ ያግዛችሁ! ይካሳችሁ! ለሌላው ብላችሁ ለእናንተ የሚበጀውን በተዋችሁት ሁሉ በብዙ እጥፍ ይስጣችሁ!
ሁሌም አድናቂያችሁ ነኝ!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

30 Dec, 06:09


ነውሯን ሲከታተሉ ከረሙ። ለጀሀነም አጭተዋት ሰርክ ነውሯን በማውሳት ተጠመዱ። የልቧን እናውቃለን ብለው አምላክ ለመሆን ቃጣቸው።በረቀቀ መንገድ በጌታዋ ላይ አሻረኩ። ያ ልቦችን የሚያገለባብጠው አላህ ተውበትን ለባርያው አደላት። በተውበት ቀደመቻቸው። እነሱ ግን አሁንም የሰዎችን ነውር በመከታተል የሚገኝ ቅድስና እንዳለ ነገር ከተግባራቸው አልተቆጠቡም። ይባሱኑ ያወገዙትን ነውር እራሳቸው መፈፀም ጀመሩት።

እርሷ ግን አሁን የምስጋና እንባ እያነባች ነው። እንኳን የሰዎችን ነውር ልትከታተል ቀርቶ ያኔ ነውሯን ሲከታተሉ ለነበሩት እርሷ ያገኘችውን ሰላም ያገኙ ዘንድ ትመኛለች።መገን አላህ ልቦችን ሲያገለባብጥ!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

29 Dec, 19:06


مَنْ سَوْفَ تَحذُو حَذْوَهَا؟!
تَمْضِي كَمَا أَسْلَافُهَا!!


📖-كَتَبَتْهُ: حَسَّانَةُ بِنْتُ مُحَمَّدٍ نَاصِرِ الأَلْبَانِي
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

29 Dec, 11:32


~ሰዎች ገፍተው ገፍተው ምርር አድርገውት ወደ አላህ እንደሄደ ሰው የታደለ ማን አለ?
በደላቸው ወደ አላህ እንድንጠጋ ባደረገን ሰዎች ላይ የአላህ እዝነት ይስፈን!አላህን ካገኙ ወዲህ የሚታጣ ምናለ? (ምንም)
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

28 Dec, 18:42


~እከሌ እጅግ ደስተኛ ነው ብለን ልንናገርለት የምንችለው ሰው ለማግኘት እንቸገራለን። እከሌን ግን እጅጉን ከፍቶታል ወይም ከፍቷታል ብለን የምንጠቅሰው ግን አናጣም።ብዙ ልቦች ደስታን ተርበው በጥርሳቸው ያገጣሉ። ውስጣቸው ተዝረክርኮ ይዘንጣሉ።

አንቺስ የደበቅሽውን ማን ያውቃል? ስትስቂ ሳቅሽ ሲቃሽን ሲያሰማኝ ውስጤን ይዘገንነዋል። አንተስ ትግልህን ማን አወቀልህ? መደመጥ፣ መታቀፍ፣ አይዞህ መባል መታገዝ እንደራበህ ሲታየኝ ምንም ላደርግ ስላልቻልኩ አዝናለሁ።
እኔንስ ማን ያውቀኛል? ሁሌም አንድ አይነት አይደል ባህሪዬ።ሁሉም ሳይታወቅለት እየታገለ ነውና ማንም ላይ ዘራፍ አትበሉ። ፍትህ የምታሰፍኑ ይመስል አትፍረዱ። ጀነት ላይ የምትጥሉ ይመስል አትገፋተሩ!
ብቻ አብሽሩ!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

28 Dec, 07:40


~ነገሮች ሁሉ በተወሳሰቡበት በዚህ ዘመን አንዳንድ ጊዜ ጥግ መያዝን የመሠለ ነገር ይሆን?!

ከአብዛኛው ሰው ዉሎ መራቅ፣ መገለል።
ጥግ ይዘህ ራስህን መገምገም።ስለ ጥፋትህ፣ ስለ ጉድለትህ፣ ስለ ድክመትህ ከአላህ ጋር ማውራት፣ ማንሾካሾክ።ነገሮችን ቁጭ ብለን ስናስባቸው ይደክማል ። ከአላህ ጋር ስናንሾካሹክ ቀለል ይላል።

አምላካችን ሆይ! አትተወን፣ አታርቀን፣ አትጥላን።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

27 Dec, 19:32


ከአላህ የራቅክ እንኳን ብትሆን ስለርሱ ለሰዎች ተናገር፣ፃፍ ምናልባት ንግግርህ አስተጋብቶ በውስጥህ ሲመላለስ ይመልስህ ይሆናል…
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

27 Dec, 13:29


https://vm.tiktok.com/ZMkk9vkmW/

የወንድማችሁ የtiktok page ነዉ ።
اللهم اجعلنا
مفاتيح للـخير
مغالـيق للـشر
نساعد و ننصح
من نعرف ومن لا نعرف
ونعوذ بك من آفة الغرور
ونسألك التواضع وحسن الخاتمة

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

26 Dec, 20:11


ኢላሂ!
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

26 Dec, 12:08


~በነገራችን ላይ…ዑምራም አድርግ ሐጅ፣ ፁምም ስገድም፤ መጽዉትም ደግ ነገርም አብዝተህ  ሥራ፣ የቱን ያህል አምልኮ ብታበዛ.... በነኚህ ተግባራት ጋጋታና ብዛት የሰው  ሐቅ ካንተ አይወርድም፤ ይቅር አይባልም። በደል አይሠረዝም። በደል የሚሠረዘዉና ይቅር የሚባለው ተበዳዩ ይቅር ያለ እንደሆነ ብቻ ነው።

ገንዘብ በመከልከል፣ በመምታት፣ በመሳደብ ይሁን ሥም በማጥፋት የሰው ዕዳ ያለበት ሰው ጉዳዩን እንደ ቀላል አይመልከተው። ምን ያመጣል አይበል። ሰዉን አይናቅ።

ከዚያ ይልቅ ገንዘቡን በመመለስ፣ ይቅር በማስባልም ይሁን በሌላ መንገድ ዛሬዉኑ በደሉን ይካስ።
ካልሆነ ፊትለፊታችን "ቂያማ" የሚባል ትልቅ የፍርድ ቀን አለ። የቂያማ ቀን ለተበዳይ የሚክሰው አላህ ነው። ከበዳይ ለተበዳይ በደሉን የሚበቀለው ኃያሉ ጌታ ነው። በዚያ ቀን ደግሞ ካሳ የሚከፈለው በገንዘብ አይደለም። ገንዘብ ዋጋ አይኖረዉም። ከበዳይ መልካም ሥራ እየተወሰደ ለተበዳይ ይሰጣል። መልካም ሥራ የሌለው እንደሆነ ደግሞ ከተበዳይ መጥፎ ሥራ ተቀንሶ በበዳይ ላይ ይጫናል።

የአላህ ባሮች ሆይ! ከዚያ ቀን በፊት ዛሬዉኑ ነገሮችን አስተካክሉ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

25 Dec, 16:00


~የትኛውም ዳዒ፣ ታዋቂ፣ አዋቂ(?) የምትሉት ሰው ለሚወዳቸው ሰዎችና እጅግ ለቀረባቸው ሰዎች ካልሆነ በቀር የማይገልጣቸው ቀሽም ባህሪዎች ይኖሩታል። በአደባባይ በቃላቱ፣ በንግግሩ፣ በፅሁፉ መልካም መልካሙን የሚያስታውስ ሁሉ የግላችሁ ብታደርጉት ልባችሁን ደስተኛ የሚያደርገው አይምሰላችሁ። ሰው የሚመስለውን ብቻ ሳይሆን የማይመስለውንም ይመስላል።
ግዴለሽም መልካም ብለሽ ካሰብሸው ሰው ላይ የሚገጥሙሽን ቀሽም ባህሪዎች ለመረዳት ሞክሪ። ግዴለህም ከጠበቅካት ውጪ  የማትገምተው ባህሪ ይኖራታልና ስትገልጠው አትሸበር፣ ሰው ነች። ልብ በሉ ሰው በወደደው በኩል ለመሰበር  እጅጉን ቅርብ ነው። ሰው በሚወደው በኩል እራሱን የሚጠብቅበት ድንበር ልል ነው። ሰው በሚወደው በኩል ጥንካሬው ሊከዳው እጅጉን ቅርብ ነው።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

25 Dec, 14:18


«ያንተ አይን ፀጉሬን ማየት ስላልቻለ እንጂ እኔ  መላጣ አይደለሁም።»አለ አንዱ መላጣ።

ወገን አንዳንድ ሰዎች ያልፈለጉትን ላለማመን ምክንያት አያጡም። እየተከራከራችኋቸው አትቃጠሉ። በቃ አንዳንዴ እውነትም ካይኔ ነው ችግሩ ብላችሁ ጤናችሁን ጠብቁ። ግዴላችሁም እየኖራችሁ ኃይላችሁን አታባክኑ!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

25 Dec, 08:02


ሐዘንን ጆሮ አትስጡት አባርሩት። ከሰማችሁት፣ ካዳመጣችሁትና ከተንከባከባችሁትማ መቼም ቢሆን አይፋታችሁም።

ደስታችሁ ብዝት ይበል!
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

24 Dec, 18:58


~የጀመራችሁት በጎ ሥራ ካለ ጨርሱ፤
ያቋረጣችሁት ጥሩ ነገር ካለ ቀጥሉ፤
ያልጀመራትሁት መልካም ነገር ካለ ጀምሩ፤
የያዛችሁትን ከዳር አድርሱ እንደገና ጀምሩ ቀጥሉ ጨርሱ ሕይወት መጀመር፣ መቀጠል፣ መጨረስ ናት ዕድሜ ማለት መወለድ፣ መኖር፣ መሞት ነውና።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

07 Dec, 14:52


ቢዚ ሆኜ፣ ሀሳብ ጠፍቶኝ፣ ወይ አሞኝ፣ ወይ ጥሩ ስሜት ላይ ሳልሆን ቀርቼ ወይም ደግሞ እንዲሁ ተዘናግቼ እዚህ አካባቢ ፖስት ሳላረግ ስለቆየሁባችሁ ጊዜያት ሁሉ  እናንተን ተከታዮቼን ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

07 Dec, 12:13


~ዛሬ ላይ …የዘመን ባቡር እንደ ጉድ ይከንፋል፣ቀኑ በብርሃን ፍጥነት የሚምዘገዘግ ይመስላል፤ በመሸ በነጋ ልክ የሆነ ቁጥር በዕድሜያችን ላይ ይጨምራል፤ ዕድሜያችን ይህን ያህል ብለን ለመናገር ፈራን እኮ ወዳጆቼ፡፡

ወዳጆቼ!ዱንያን የኖንርባት ሳይመስለን አሯሩጣ እዚህ አደረሰችን፡፡ የሄድንበትን መንገድ መለስ ብለን ስናስተዉለው የተረፈን ነገር ቢኖር  የተሸበሸበ ፊት፣ የነጣ ፀጉር፣ የገረጣ ቆዳ፣ የደከመ ሰዉነት ነው …፡፡ በመጨረሻም አንድ ቀን ምንም ብናደርግ ልንከላከለው በማንችለው ሞት ፊት እንቆማለን፡፡

ወዳጄ…አንተ በዚህች ምድር ላይ ሕይወት እስካለህ ድረስ የዱንያ ላይ መብራት መሆንህን እወቅ፡፡ ዕድሜህ እንደ ሻማ ነው፣ ሰዓት ባለፈ ቁጥር ይቀልጣል፡፡ ጨለማን ለማብራት፣ መሃይምነትን ለመግፈፍ፣ መልካም ቃል ለማስተላለፍ፣ የከፋዉን ለማጽናናት፣ መሰናክልን ለማስወገድ ተናገር፣ ቅለጥ፣ፃፍ … አደራ፡፡ ባትችል እንኳ መልካም የሚፅፉትንና የሚናገሩትን አግዝ፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

22 Nov, 18:33


~አንድ ሰው ነበረ…መልካም ባይሆንም ለመልካም ነገር ሰበብ ለመሆን የሚሞክር፣ የረባ እውቀት ሳይኖረው የሚያውቃትን ለማስታወስ የሚጥር፣ የምናውቀውን የሚደግምልን ሰው ነበር ብላችሁ ያንን ሰው አስታውሱት። ያንን ሰው እንደ በፊቱ አታገኙት እንደሆነ፣ የሄደ ጊዜ እሱም እንደ ሰው የልቡ ጉዳይ ይኖረው ይሆናል፣ጌታው እንዳሳካለት የሚለፋለት ነገር ኑሮት ይሆናል ብላችሁ ይሞክር የነበረውን ጌታው እንዲቀበለው ዱዓ አድርጉለት። በእርግጥ ከሄደም ይሂድ የት አባቱ።ይመለስም አይመለስ እንዲያ አስታዉሱት። በዱዓችሁ ባታስታውሱትም፣ ትረሱትም እንደሆነ ሰላም ለልባችሁ ይሁን!
―𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥―

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

22 Nov, 17:05


~ግማሹ ኩራተኛ ነው ይልሃል፡፡ሌላው እንደርሱ ያለ ትሁት ሰው ገጥሞኝ አያውቅም ይላል፡፡ አንዳንዱ ገና ስምህ ሲነሳ በርግጎ ይጠፋል፤ ሌላው ስላንተ አውርቶ አይጠግብም፡፡ ከፊሉ ያንተን መገኛ ሲያስስ ይውላል፤ ሌላው አንተ ያለህበት ምቾት አይሠጠዉም ይሸሻል፡፡

በአንድ አቋምህ ብቻ አንቅረው የተፉህ እንዳሉ ሁሉ፤ በአንድ አቋምህ የተነሳ ከልባቸው ሊያወጡህ የተቸገሩ አሉ፡፡ አንዳንዱ ለትችትህ ሲሽቀዳደም ሌላው ሲያድንቅህ ዉሎ ቢያድር አይደክመዉም፡፡ አንዱ እሱ ጥሩ ሰው ነው ሲልህ፤ ሌላው በጣም መጥፎ ነው ብሎ ይሞግታል፡፡ አውቀዋለሁ መልካም ሰው ነው የሚል እንዳለ ሁሉ አታውቁትም መሰሪ ሰው ነው ብሎ የሚከራከርም አለ፡፡ ያለምክንያት እንደሚጠሉህ ያሉ ሁሉ ያለምክንያት የሚወዱህም ብዙ ናቸው፡፡

ይህ ሁሉ እንግዲህ አንድ አንተው ብቻ ነህ። አንተ አንድ ነህ፤ ሰዎች ላንተ ያላቸው እይታ ግን ብዙ ነው። የተለያየ መልክን ስብእና ይዘህ በሰዎች ልብ ዉስጥ ትኖራለህ፡፡ ሁላችንም እንደዚያው ነን፡፡

አይግረመን፡፡ ብቻ ትክክል ለመሆን እንጣር፣ እውነትን ይዘን እንኑር፣ ከአላህ አንጻር እንሥራ፡፡ ለአላህ ስንሠራ የሰዎችን ጉዳይ የሚያስተካክልልን እሱ ነው፡፡  ይገርማል የአላህ ሥራ፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

21 Nov, 16:46


~የሰዎችን መጥፎ ጎን ብቻ ለማስታወስ ከተቀመጥክ ለማንም ውዴታ አይኖርህም። ፍፁም ንፁህ ስለማይኖር ቅርብ ሰዎችህን እንኳን ባልተለመደ መልኩ በጥቁር ዓይን መመልከት ትጀምራለህ። ከዚያ ቀንህም አያፈካህም፣ ሌሊትህም አያሳርፍህም። አንዳንዴ መጥፎ ጎናቸው ጋር  ስትደርስ አይንህን ስበር፣ አይቶ እንዳላየና ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍንም ተለማመድ።አንዳንዴ «መርሳት»ን እንደ ትራስ ተደገፈው። አንተም አጠገብህ ያሉትም ሰላም እንዲሆኑ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

21 Nov, 10:40


رضَا النّاس غَاية لَا تُدرَكُ ..
~ሰዎችን ለማስደሰት አትልፋ!

• ሰዎች ዘንድ ለመወደድ ስትለፋ ጌታህ ዘንድ እንዳትጠላ ተጠንቀቅ።

•ለምትወዳቸው ሰወች ክብር ስታበዛ የጌታህን ክብር እንዳትነካ ተጠንቀቅ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

21 Nov, 06:19


~እንግዳ የሚበዛበት ቤት አላህ የሚወደው ቤት ነው ይላሉ።ለትንሽ ትልቁ ልድሃ ሀብታም ሚከፈትን ቤት የሰዉም ሆነ  የመላኢካ ዱዓ አይለየዉም። የአላህ ችሮታም አይጎድልበትም።እንግዳ እቤት ሲገባ በረከትና የአላህ እዝነት አብሮት ይገባል።እንግዳው ብዙ ችሮታዎችን ይዞ ይመጣል፣ ወንጀልም አጥቦ ይሄዳል።«በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳዉን  ያክብር።» ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ﷺ―
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

20 Nov, 19:21


እንደ ነቢዩ ሱለይማን ሥልጣን ቢሠጠኝ ኖሮ የተወሰኑ ጅኖችን ልኬ ነበር የምወስድሽ አላት።

ጉረኛ! እስቲ የጅኑን ነገር እርሳና የተወሰኑ ሸማግሌዎችን ብቻ ልከህ ውሰደኝ።
አለችው።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

19 Nov, 18:06


~ላንተ የተለየ ጊዜ የሚሰጥህ ሰው… ሌላ የሚሰራው ስራ ሳይኖር ቀርቶ አይደለም…  ላንተ ተደጋጋሚ እድል የሚሰጥህ ሰው…  ሌላ እድሉን የሚፈልግ አጥቶም  አይምሰልህ… ውስጡ ላንተ ያለው ፍቅርና ክብር እንጂ… ግን የመጨረሻው እድል መች እንደሆነ አታውቅም… የቀለሙ መድረቂያን የመዝገቡ መዝጊያ እለትም አልተነገረህም… ግንኙነትህን አሳምር!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

17 Nov, 18:58


ወዳጅ የማይፀናበት፣ መሠለቻቸት የበዛበት ዘመን ነዉና አንዳንድ ጊዜ ብቸኝነትንም አስቀድማችሁ ተለማመዱት።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

17 Nov, 14:47


ርብርብ ለጋራ ግብ
~
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

በዚህ የብዙ ሴቶች አለባበስ በተበላሸበት ዘመን ጂልባብ እና ኒቃብ መልበስ እየፈለጉ በችግር ምክንያት ያን ማድረግ ካቃታቸው እህቶች ጎን መቆም ድንቅ ስራ ነው።
ችግሩን ለመቅረፍ የበኩላችንን እንወጣ ዘንድ ይመለከተኛል የሚልን በሙሉ አካታች የሆነ ሰፊ ሀሳብ ይዘንላችሁ መጥተናል። ይህም የጂልባብ እና የኒቃብ ባንክ መክፈት ነው። ስራዉን በሚሰሩ ወይም በሚመለከታቸዉ እህቶች ስም የባንክ አካውንት የተከፈተ ሲሆን  
1. ገንዘብ በማሰባሰብ ኒቃብና ጅልባብ መግዛት፣
2. ቅያሪ ኒቃብና ጅልባብ ኖሯቸዉ መስጠት ለሚፈልጉ እህቶች ያሉበት ሰፈር ድረስ ሄዶ በመቀበል ለተቸገሩ እህቶቻችን ማድረስ ናቸው።

የድርሻችንን እንወጣ። በችግር ምክንያት መልበስ ላልቻሉ እህቶቻችን እንድረስላቸው።

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ➛ 1000588690486
Hikma and/or Ahlam and/or Muhiba

ለየትኛውም ሀሳብ፣ አስተያየት፣ ጥቆማና ጥያቄ እነዚህን አማራጮች መጠቀም ትችላላቹ።

እህቶች በዚህ👇
@AhluYeWereilua
@nikab_new_wbetea 

ወንድሞች በዚህ👇
@FuadBezu
@red_one1212

ስልክ 0913666695
         0903939033

የቴሌግራም  ቻናላችን👇
t.me/NikabJilbab

የቴሌግራም  ግሩፓችን 👇
t.me/nikab_jilbab_group

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

17 Nov, 14:37


لأبكين على نفسي .. كلمات مؤثرات ..

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

17 Nov, 13:40


☪️አዲስ የሙሀደራ ፕሮግራም 🕌

💡በትዳር እና ኢስላም ቻናል 🌙

1️⃣ኡስታዝ አብዱረዛቅ አልባጂ
ርዕስ🔴
🟡أنواع العلوم
🔢የእወቀት አይነቶች


2️⃣🔴ኑረዲን አል አረቢ 
ርዕስ 
🟤ሰላት
ቀን ነገ ሰኞ
ሰአት ከምሽቱ3⃣:30 ጀምሮ

💬የፕሮግራም መሪ አቡ ሱፊያን⤴️

✈️✍️
የሚተላለፍበት ቻናል🔂

t.me/tdarna_islam
t.me/tdarna_islam

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

17 Nov, 09:30


عشر فوائد تعينك على حفـظ القرآن. «الشَّيخ صَالِح العُصَيمِي»
° ቁርኣንን ለመሀፈዝ የሚረዱ አስር ፈዋኢዶች―

🎙ሸይኽ ሷልህ አል-ዑሰይሚ―ሐፊዞሁሏህ―
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

17 Nov, 06:35


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ኢማራት ያላችሁ በተለይ አል ላኢን
በቅርብ ሀገር የምትገቡ ወይንም ተመላላሽ ነጋደ የምታቁ
@umuteymiyah በዚህ አናግሩኝ

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

16 Nov, 16:45


ለብቻ ማደርን እስልምና ለምን ጠላው!?

~ ለብቻ በሚያድር ሰው ላይ ፈተናው ብዙ ነው፡፡በተለይ ለላጤና ለላጢት። የሸይጧንም የነፍሲያም ነፃ የመጫወቻ ሜዳ ነው፡፡ ሲቃዥ የሚያድርም ብዙ ነው።የሸይጧን ዉትወታው የሚበረታው ብቸኛዉን በሚያድር ሰው ላይ ነው፡፡ ሰው ብቻዉን ሲሆን ነው ለአላህ ያለው ፍራቻ ምን ያህል እንደሆነ የሚለካው። አላህን ካልፈራ የፈለገዉን ነገር ዘና ብሎ መሥራት ይችላል፤ በተለይ በዚህ በቴክኖሎጂ ዘመን፡፡ ስልክ አጠገቡ ነው፣ ኢንተርኔት ቅርቡ ነው፡፡ ዋትሳፑ፣ ቪዲዮ ኮሉ፣ ኢሞው፣ ቻቱ … ሁሉም ሲጀመሩ ጥሩ ነገር ይመስላሉ፣ ደስ የሚል ስሜት ይሠጣሉ፣ እንጂ መጨረሻቸው አያምርም፡፡ ለባለቤቱም መልካም ነገር ይዘው አይመጡም፡፡

ብቸኝነት ሲደመር ነፃ መሆን ለሸይጣን ዱላ ያጋልጣል፤ መከላከሉም ይከብዳል። በተቻላችሁ መጠን ብቻችሁን አትደሩ፡፡ሰው ብቻዉን ሲሆን ደካማ ነው፤ ሶላት መስገድ እንኳን ሊከብደው ይችላል፡፡ ከወንድም/እህቱ ጋር ሲሆን ግን ብርቱ ነው፡፡ በዚህ ዘመን ላይ ና መስጊድ እንሂድ፣ ተነስ ሱንና እንስገድ፣ ና የሆነ ኸይር ሥራ አለ፣ አረ እሱ ነገር ይብቃህ! የሚለን ሰው ሁላችንም ያስፈልገናል፡፡

ብቻችሁን አትተኙ ለማለት ነው።
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

16 Nov, 05:34


~ከረፈደ እና ምናልባት ካጣነው በኋላ ከምናውቀው ፍቅር ውስጥ ግንባር ቀደሙ የአባት ፍቅር ነው።እጅግ ጠንካራ፣ በመስወዓትነትና በድርጊት የታጀበ ፍቅር ሆኖ ሳለ ለመረዳት የሚቸግረን ፍቅር ውስጥ የአባት ፍቅር ነው። አባቶቻችን ድንቅ አፍቃሪና ፍቅርን አዋቂ ናቸው። ግና በይበልጥ ለቃላት የተገሩ ስላልሆኑ እንደሚወዱን እንኳ ላለማመን አቅም እናገኛለን። እመኑኝ አባቶቻችሁ ፍቅርን ያውቃሉ። ያፈቅሯችኋል። አባት ለልጆቹ ፍቅሩን ለመግለፅ እየታተረ ነው የሚያልፈው። ፍቅሩ ግን ጥልቅ ነው።  የሕይወት መስወዓትነት ለሚከፍልላችሁ አፍቃሪያችሁ ለሆነው አባታችሁ ውዴታችሁን ነግራችሁት ታውቁ ይሆን?
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

16 Nov, 05:00


~አላህ በድንገተኛ አጋጣሚዎች እንዳይፈትናችሁ ዱዓ አድርጉ። ድንገተኛ ነገሮች በሁሉም መልኩ ህመማቸው ከባድ ነው። ድንገተኛ ሞት፣ ድንገተኛ ማጣት፣ ድንገተኛ የሪዝቅ መቋረጥ፣ ድንገተኛ ሀዘን፣ ድንገተኛ መለያየት… በአጠቃላይ ድንገተኛ የነገሮች ለውጥ ፅኑ የውስጥ ህመም ያሳርፋሉ። ከነብዩ ዱዓዎች መሀል«ጌታዪ ሆይ! ከድንገተኛ ቅጣትህ በአንተ እጠበቃለሁ።» የሚል ነበር። ከድንገት በጌታችሁ ተጠበቁ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

15 Nov, 18:44


የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ደርሶች

1) ሹሩጡ ሶላት
2) ሪያዱ ሷሊሒን
3) ኪታቡ ተውሒድ
4) ኪታቡ ተውሒድ
5) ሒስኑል ሙስሊም
6) ላሚየቱ ብኒ ተይሚያ
7) አልአርበዑነ ነወዊያህ
8) አልቀዋዒዱል አርበዕ
9) ሓኢየቱ ብኒ አቢ ዳውድ
10) ዶላሉ ጀመዐቲል አሕባሽ
11) ሸርሑ ሱንና ሊል በርበሃሪ

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

15 Nov, 07:12


«የወንድምህን ቀልብ ከመስበር ጌታዬ ይጠብቅህ!» ብለው ዱዓ አደረጉለት።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

15 Nov, 05:17


- مَن أكثَـر مِن الإستغفَار جَـعل الله
لهُ مِن كُل هَم فَرجاً ..

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

14 Nov, 18:43


👈             [نواقض الإسلام]
                 [የእስልምና አፍራሾች]

                           ትርጉም
              አቡል`ቡኻሪ ሰዒድ ሙሳ
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/AbulBukhariSeid

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

14 Nov, 14:46


|«ልጄ ሆይ…» አሉ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አዛውንት። ወደ ሕይወት ትግል ገና እየተቀላቀለ የሚገኝ ጎረምሳ ወጣትን እየተመለከቱ።

•ልጄ ሆይ… መጠበቅህን አደብ አሲዘው። የመጠበቅ ልጓምህን ተቆጣጠረው።
የኔ ልጅ ሰዎች መጥፎ ነገር በማድረግ ብቻ አይጎዱህም። ልብህን በአጉል ተስፋ አንጠልጥለው ከጌታህ ጋር ሊያጣሉህ ይችላሉና ተጠንቀቅ።

• ልጄ ሆይ… ሕይወት እንደ እናትህ ልብ አይደለችም። አትራራልህም። እንደ አባትህም እቅፍ አይደለችም። እንዳይበርድህ ሙቀት አታቀብልህም። ሕይወት የወቅት ዘመድ ነች። የአሁን ሁኔታ ነች።»

• ልጄ ሆይ ወደ ልብህ የዘለቀን አክብር። የተለየህን አትጥላ።
• ልጄ ሆይ… ሰዎች በመጥፎ ምግባር ላይ ስላየሀቸው ብቻ አትፍረድባቸው። በምታውቀው እኩይ ምግባር ላይ ስለተገኙ አትጠየፋቸው። ይህን ልብ አድርግ አላህ ምርጥ ነብያቶቹን በእጅጉ ቆሽሸው ለነበሩ ሰዎች ልኮ የቆሸሹትን አፅድቶ እንዳስከበራቸው።
• ልጄ ሆይ!  ወንድሞችህ ከፊርዓውን የባሱ አይሆኑምና ከፊርዓውን ያነሰ ክብር ሰጥተህ አታዋርዳቸው። የአላህ ነብይ ሙሳ ፊርዓውንን በለዘብታ ቃል እንዲያናግረው መታዘዙን ዘንግተህ በወንድሞችህ ላይ አጉል አትጩህ!

ልጄ ሆይ…!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

14 Nov, 10:26


የድብቅ ወንጀሎች ...

🎙ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ حفظه الله ورعاه

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

13 Nov, 17:28


~ከመሀከላችን ያልተቀየረው ማን ነው?…  ክስተቶች ይቀይሩናል፣ ከጓደኞቻችን ጋር መለያየት ይቀይረናል፣ ብቸኝነት ይቀይረናል፣ ሀላፊነት መሸከም ይቀይረናል፣ የድካም ጊዜዎቻችን ራሱ ይቀይሩናልኮ። ባደግን ቁጥር… ሃለታችንን፣ ዱንያንና ሰዎችን እየተረዳን እንመጣለን። በየጊዜው ቅድሚያ የምንሰጣቸው ጉዳዮች ይለዋወጣሉ።   እንደነበረ የቆየ ማን አለ?…   መቀየራችንን ለጥሩ ያድርግልን እንጂ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

13 Nov, 11:57


ይህችን ልጅ አፋልጉን

የምትጠራው በእንጀራ አባቷ ነው ሞሚና ሀሰን ባቡ ትባላለች። ከ ሀገር ከወጣች 12 አመቷ ሀገር ሂዳ አታውቅም።እናቷ በሂወት ካለች ንገሩኝ እያለች ነው ሁሌ እንዳለቀሰች ናት።

የምትኖረው ሪያድ ከተማ ነበር

ከተወሰነ ወራት በፊ እያናገረችን ነበር።ግን አሁን ላይ ስልኳም አይሰራም ብሯንም የ4 አምት  ብቻ ነው የተቀበለችው ሌላው አልሰጧትም አድራሻዋን የሚያውቅ ሰው ካለ 0550845152 አናግሩኝ።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

13 Nov, 06:01


ይህ ቻናል በሀገር ውስጥ ያሉ ስራ አጥ
            ወንድም እህቶች
በአላህ ፍቃድ  የስራ ማግኛ ሰበብይሆን ዘንድ
ታስቦ የተከፈተና የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲስ ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው 

🔗ተቀላቀሉ
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

12 Nov, 19:20


~በጊዜ ለመነሳት ደግሞ በጊዜ ተኙ። ዕድሜያችሁን ለርካሽ ነገር አታዉሉ። ቲክቶክ ይቅርባችሁ ። ቻትም እንደው ዝምብሎ መድከም እኮ ነው። እኔ ትናንሽ ንግድ አልሠራም እንደሚለው ኩሩ ነጋዴ ከፍ ከፍ ያሉ በጎ ሥራዎችን መርጣችሁ ሥሩ።

ዉዱእ አድርጉና፣ ሱናችሁን ስገዱና፣ ዚክራችሁን አድርጉና ነፍሳችሁን ለፈጠራችሁ ጌታ አስረክቡና፣ የአላህን ጥበቃ እመኑና ጥቅልል ብላችሁ ተኙ። ያኔ ሌሊታችሁ ያምራል ፤ ህልማችሁም ጥሩ ይሆናል። ኢንሻአላህ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

11 Nov, 18:54


https://youtu.be/tevqCpbGNBo?si=uOtmcRXO3UbhDp1z

የዩትዩብ ቻናሉን ሰፕስክራይብ አድርጉ ባረከሏሁ ፊኩም

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

11 Nov, 18:27


وكيف يلذّ العيش

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

11 Nov, 04:47


ዘወር ብላችሁ ስትሄዱ ይገባቸዋል…

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

10 Nov, 19:20


በ እግር በሚጓዙበት ግዜ ፈጠን ፈጠን እያሉ መጓዝ ሱና ነው።

ሐድሱ ላይ አል-ነሰላን―የሚለው ቃል በፍጥነት መሄድ ወይም መራመድ ማለት ነው።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

10 Nov, 17:55


~ካገቡ በኋላ እንዲህ አግቡ እያለ የሚመክር እንጂ ትዳር ውስጥ ጭቅጭቅ ብቻ እንዳለ አድርጎ የሚያስፈራራ አንፈልግም። የአንዱ ጭቅጭቅ ቢሆን የሌላው አይሆንም። ባይሆን ምንም ነገር የሌለ አስመስሎ በውሸት የሚተውንም አንፈልግም። እንዳውም እንዲህ አይነቱ ጉዳቱ ከባድ ነው። የሆነ አለመግባባት በተከሰተ ቁጥር "3ቱንም ፈታሁሽ!" የሚል ወንድ ይፈጥራል።

ሁለቱንም ጠርዞች ሚዛናዊ ባደረገ መልኩ ትዳር ውስጥ ፍቅርም አለ፤ ፀብም «ሊኖር ይችላል» ብሎ ተዘጋጅቶ መግባቱ ነው የሚሻለው።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

10 Nov, 14:53


አንዳንዴ…ገንዘብ ወሣኝ ነው፡፡ ዲናችንም ቢሆን ድህነትንና ደካማነትን አይመክርም፡፡ ዛሬ ላይ በተለይ ኢማን ተዳክሞ ቁሳዊ ነገሮች ትልልቅ ዋጋ ባገኙበት ሰዓት ይዞ መገኘት መልካም ነገር ነው፡፡ ኢማን በሌላቸው ሰዎች ዘንድ፤ ያለዉና የሌለው ሰው በእኩል ዐይን እየታየ አይደለም፡፡ ቁሳዊነት በነገሰባት ዓለም፤ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ ቦታ አላቸው፡፡ ገንዘብ ከሌለህ በድሮ ጓደኞችህ ጭምር ትገፋለህ፡፡ - ስልክህ ቶሎ አይነሳም፤ ንግግርህ ለጆሮ አይስብም፣ ወሬህ ዉሃ አይነሳም፣ ቀጠሮህ አይከበርም፣ ሽምግልናህ አይደመጥም፡፡

~አንዳንዴ…ራስህን ለማስከበርና  ለእልህም ስትል ገንዘብ ያስፈልግሃል፡፡ ከአንዳንድ ስስታሞች ለመብቃቃት ስትል ገንዘብ ያስፈልግሃል፡፡ በደወልክላቸው ቁጥር ገንዘብ ፈልጎ ነው ብለው ለሚደነግጡና ኒያቸዉን ለሚያበላሹት ስትል ገንዘብ ያስፈልግሃል፡፡ በግብዣቸው ሁሉ ለሚመፀደቁብህ ስትል ገንዘብ ያስፈልግሃል፡፡ እኔ ነኝ የረዳሁትና ለዚህ ደረጃ ያበቃሁት ብለው ለሚያስወሩብህ ጉረኞች ስትል ገንዘብ ያስፈልግሃል፡፡ ትንሽ ሆነው ትልቅነታቸዉን፣ መሃይም ሆነው አዋቂነታቸዉን ባንተ ላይ ለማሳየት ከሚፈልጉት ለመዳን ስትል ገንዘብ ያስፈልግሃል፡፡

~ዉዳችን ረሱሉ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)ከሚያስረሳ ድህነት እንዲጠብቃቸው አላህን ተማፅነዋል፡፡ አሁን ላይ ዱዓቸው አስፈላጊነቱ ጎልቶ ይታያል፡፡ ገንዘብ ከሌለህ ስለመኖርህ እንኳን የሚረሳበት አጋጣሚ አለ፡፡ ወዛም ብትሆንም ደብዛዛ ነህ፡፡ የገረጣህ ነህ፡፡ በሰዎች መካከል ሆነህ ብትንጠራራም አትታይም፡፡ ረጅም ብትሆንም አጭር ነህ፡፡ ቆንጆ ብትሆንም አስቀያሚ ነህ፡፡
ገንዘብ ማጣት እንኳን ሰዉን ራስህንም አምላክህንም ያስረሳሃል ወዳጄ፡፡

~ጥሩ ገንዘብ ጥሩ ነው ወዳጄ፡፡ ነጭ ሳንቲምም ለጥቁር ቀን ወዳጅ ናት። ከሰው እጅ  ትጠብቃለች። ከመከጀል ታድናለች።
በጥሩ ገንዘብ ...የአላህንም ሆነ የሰዎችን ዉዴታ ታተርፍበታለህ፡፡ በመሰደቅና በአላህ መንገድ በመበተን ጀነትንም ትገዛበታለህ፡፡ ፍቅርንም፣ ዱዓንም፣ ከበሬታንም ትገዛበታለህ፡፡

አንዳንድ የተረሱ ሸሆች ላስታወሳቸው አላህን ይለምናሉ፡፡ አንዳንድ ወላጆች ገንዘብ ያለዉን ልጃቸዉን ይወዳሉ፤ አንዳንድ እናቶች ገንዘብ ላላት ልጃቸው አብዝተው ዱዓ ያደርጋሉ፡፡ አንዳንድ ዘመዶች የእገሌ ልጅ እንዲህ እንዲህ አደረገልን ይላል፡፡ አንዳንድ ወንድም የልጅነት ጓደኛዬ አልረሳኝም ረዳኝ ብለው ለዚህም ለዚያም በደስታ ያወራሉ፡፡

ገንዘብ ወሣኝ ነው ወዳጄ፡፡ ብዙ ዓሊሞች ድምፃቸው ያልተሰማው፣ ብዙ አዋቂዎች ሀሳባቸው ያልተዳረሰው፣ ብዙ ፀሐፊዎች ብርሃናቸው ያልወጣው በገንዘብ ማጣት እኮ ነው፡፡

•ለገንዘብ ባርያ የማያደርግ፣ የማያስገበግብ፣ ዲንን የማያስረሳ፣ ቤተሰብን፣ ሶላትንና ዚክርን የማያስዘነጋ ገንዘብ ወሣኝ ነው ወዳጄ፡፡ እንደዚያ ነው ሀሳቤ፡፡ አላህን በረሳ በገንዘብ  ባርያማ ማን ይቀናል ወዳጆቼ።!
አላህ ከገንዘብ ፈተና ይጠብቀን፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

10 Nov, 14:04


ቀደምቶች እነዚህ ናቸዉ አንቺስ...ነፍሴ!?

🎙አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን

t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
t.me/abu_fewzan_abdu_shikur

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

10 Nov, 13:49


•እና  ከሁሉ ነገር በኋላ…ዱዓ የሌለበት ዓለም ከንቱ እንደሆነ ይገባሃል። በመጨረሻ…  ስኬትም ስክነትም እዚህ መተናነስ ውስጥ እንደነበረ ትረዳለህ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

09 Nov, 17:19


~ንግግርህን ገምግም፣ ዉሎህን ፈትሽ፣ የሰደድከዉን መልዕክት መልሰህ እይ፣ ከአንደበትህ የወጣው ንግግር ምን እንደነበር አስታውስ፣ በቅድሙ ቻት ልክ ነህ ወይ፣ የፖሰትከው ነገርስ ካንተ ይጠበቃል፣ ሞባይልህ ውስጥ ምን አለ? ጥሪውስ ምን ይላል? ሴቭ ያረግካቸው ነገሮች ምንድነው ጥቅማቸው? ቪዲዮና ፎቶዎችስ ትክክል ናቸው ወይ? ከሚያሳፍር ነገር የፀዳ ነውን? እነኚህን ጥያቄዎች መልሰህ እይ፣ አሁኑኑ ራስህን ገምግም…

ሞባይልህ አሁን ባንተ እጅ ሊኖር ይችላል፡፡ በማን እጅ ሆኖ እንደሚነጋ ግን አታውቅም፡፡  

ካመሸህ አነጋለሁ ብለህ በርግጠኝነት አትጠብቅ፤ካነጋህም አመሻለሁ ብለህ እርግጠኛ አትሁን፡፡በንጋትና ምሽት፣ በምሽትና ንጋት መካከል ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

09 Nov, 09:05


√ ዱባይ ሻርጃ አከባቢ የምትኖር አንድት እህታችን ለረዥም ግዜ ስራ አጥታ ተቀምጣላች እና ስራ የሰማችሁ በዚህ አድራሻ አሳውቋት!👇
00971581957815

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

09 Nov, 08:11


ምንኛ ደስ የሚያሰኝ ርብርብ ነው! ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የሚችለውን እያደረገ ነው። በዚህ የመስጂድ ግንባታ ላይ የሶደቀቱን ጃሪያ ድርሻ እንዲኖረው የሚሻ ያቅሙን በማገዝ ለኣኺራው ስንቅ ያስቀምጥ።
መስጅደል ፉርቃን በወረባቦ ወረዳ ዋና ከተማ ቢስቲማ ላይ እየተሰራ ያለ መስጂድ ነው። መስጂዱ ለከተማው ድምቀት ነው። ከዚያ በላይ ግን ለከተማውም በዙሪያው ላሉ ቀበሌዎችም ጥሩ የደዕዋ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፣ ኢንሻአላህ።

መርዳት ለምትፈልጉ ከታች በተለጠፈው አካውንት ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።
#ወረባቦ ፉርቃን መስጂድ
ንግድ ባንክ - 1000401221957
አቢሲኒያ - 64828638
ዳሽን - 2935824167011

መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩን። ምናልባት በናንተ በኩል ተሳትፎ የሚያደርግ ቢኖር ከአጅሩ ተካፋይ ትሆናላችሁ።
{ مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ }
"ሌሎችን ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የተገበረውን ሰው አምሳያ ምንዳ ይኖረዋል።"
=
ቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

09 Nov, 06:49


السلام عليكم ورحمةالله وبركاته

𒊹አድስ ብስራት መርከዝ አል—ቡርሃን ትምህርት ቤት

᯾ውድና የተከበራችሁ ወንድም እህቶች እንደት ናችሁ

እነሆ መርከዝ አል—ቡርሃን ሁለተኛ ዙር መዝገባ ጀምሯል እናም በያላችሁበት ሁናችሁ በኦላይን ቂርአት መቅራት የምፈልጉ ራሳችሁንና ቤተሠባችሁን መቀየር  የምትፈልጉ መመዝገብ ትችላላችሁ

𖣘በመርከዙ የሚሰጠው ትምህርቶች

   ✫ቁርዓን ሂፍዝ
     ✫ቁርዓን ነዞር
      ✫ቃኢደቱል ኑራንያ
       ✫ተጥቢቅ
        ✫የተጅዊይድ ኪታቦች ናቸው

መመዝገብ የምትፈልጉ ከታች ባለው ዩዘርኔም ተመዝገቡ

𒊹 @Selefya_Menhaji4822
     
      𒊹 @Onlinmedresa

      

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

08 Nov, 18:59


~በነገራችን ላይ…ብር አልያም ዕቃ ስትሰርቀው የያዘህ ወይም ያወቀብህ ብቻ የሚከስህ እንዳይመስልህ ከቁስ ውጪ የሆነን ምናልባት ከዛም በላይ የሆነን ነገር የሰረቅከው ወይም ሀቁን የቀማኸው ነገ አላህ ፊት እንደሚጠይቅህ እርግጠኛ ሁን። ሁሉም ስርቆቶች ዱንያ ላይ አይዳኙም። 
አንዳንድ ሰዎች አላህ ፊት ብቻ ሊጠይቁህ ፈልገው ምንም ስትወስድባቸው አውቆ እንዳላወቀ፣ አይቶ እንዳላየ ያልፉሀል። ነገ ከጌታህ ፊት ሀቁን የቀማኸው፣ እያወቅክ የነፈግከው ደግሶልሀል። ስርቆት በቁስ ብቻ የተገደበ አይደለም። ምናልባት የቁስ ስርቆት እጅጉን ትንሽ ሊሆን ይችላል። ከቁስ ውጪ የሚሰረቁ መዓት ነገሮች አሉ። በተለይም ደሞ የሰውን ልብ መስረቅ…
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

08 Nov, 16:07


• ሕይወት በሕይወት እስካለህ ድረስ መረበሿን አትተውም፤ ጫና ማሳደሯን አታቆምም። አንተው ተረጋግተህ ያዛት እንጂ።

ማናት ሕይወት በለኝ ደግሞ¡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

07 Nov, 18:10


𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 pinned «t.me/Muhibu_Shier t.me/Muhibu_Shier 👆👆 ☞ይህ ቻናል ከሀገር ውጭም ሆነ በሀገራችን የሚገኙ ወንድሞችን በማሳተፍ የዓረብኛ ግጥሞችን በድምፅ የምናቀርብበት ልዩ ቻናል ነው።👇👇 https://t.me/Muhibu_Shier https://t.me/Muhibu_Shier»

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

07 Nov, 17:37


t.me/Muhibu_Shier
t.me/Muhibu_Shier
👆👆
☞ይህ ቻናል ከሀገር ውጭም ሆነ በሀገራችን የሚገኙ ወንድሞችን በማሳተፍ የዓረብኛ ግጥሞችን በድምፅ የምናቀርብበት ልዩ ቻናል ነው።👇👇
https://t.me/Muhibu_Shier
https://t.me/Muhibu_Shier

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

06 Nov, 19:18


•በድምፅ የተቀዱ የ አረብኛ ግጥሞችን ብቻ የምለቅበት አዲስ የቴሌ ግራም  ቻናል ለመክፈት አስቢያለሁ…በዚህ ሐሳብ ላይ የ እናንተ ላይክ 👍ከ 200 በላይ ከደረሰ እከፍታለሁ ኢንሻ አላህ።

አላችሁ?

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

06 Nov, 18:39


•በሰው ቀልብ እየተጫወቱ አላህ ጌታ ሆይ ቀልቤን አረጋጋልኝ ብለው ይለምናሉ።
አይታሰብም።አላህ ሥራችሁን አይመዘግብም መሰላችሁ እንዴ!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

06 Nov, 05:27


ደስተኛ ሆነህ ለመኖር ራስህን ዉደድ።
ራስህን ዉደድ ስልህ ደሞ ምን መሰለህ…

~ በሰው ለመወደድ አትልፋ፣ እንዲህ ለማለት ፈልጌ ነው ብለህ ለማሳመን አትድከም፣ ከግትር ሰው አትከራከር፣ስለ መጪው ጊዜ አትጨነቅ፣ጥለዉህ ስለሄዱት አታስብ፣ ሥምህን ያጠፉትን እርሳ፣ለመታወቅ አትፍጨርጨር፣መጥፎ ጥርጣሬን ራቅ፣ሰው ስለኔ ምን አለ አትበል፣የሰዉን ነዉር አትከተል፣
መጥፎ ስብስብ አትቀላቀል፣ብቸኝነትን አዘውትር፣ጊዜህ በአግባቡ ተጠቀም…።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

05 Nov, 18:09


~ውበት ዋስትና አይደለም ውበት ተከትላችሁ ትዳርን አትጀምሩ። ውበት ሲያረጅ ፍቅራችሁ እንዳይቀንስ ውበትን አትከተሉ።ትዳር መከባበር ከሌለው ሀቁ ይጓደላል። በማትከበሩበት ቦታ ፍቅራችሁ አይፀዳም። ለማታከብሩትም ሰው ንፁህ ፍቅር መስጠት አይቻላችሁም። ንቀት ባለበት ፍቅር አይዘልቅም። ስትፈቃቀሩ፣ በደንብ ስትተዋወቁ መከባበርን አትርሱ። ማክበር፣ መከባበር ፍቅር ነው። በእርግጥ በክብር የሚያፈቅሯቸውን ያገኙ ታደሉ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

05 Nov, 04:54


~በዕድሜ ከፍ ባልን ቁጥር ያ በዲን ጠንካራ የነበርንበት የድሮ እኛነታችን ይናፍቀናል፡፡ ብዙ ሰው በዲኑ ጠንካራ የሚሆነው በወጣትነት ዘመኑ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ወጣቶች ሆይ ዘመናችሁን በሚገባ ተጠቀሙበት፡፡ 
አሁንማ ዲን ዉስጥ ቆየንና ተላመድነው መሰለኝ ደከምን፣ ደረቅን፣ ወረድን፡፡ አላህ ይዘንልን፡፡

አሁንማ ነገሮች ሁሉ ተቀላቅለው ግራ ገባን፡፡ ሐራም ነገርን ትልቁም ትንሹም፤ ዓሊሙም ጃሂሉም ስለሚዳፈረው ድንበሩ የቱ ጋ እንደሆነ ለተራው ሰው መለየት ቸገረ፡፡ተራው ሰው ዲንን ዲን ካልሆነው መለየት ከበደው፡፡ ዲን ማለት ሰው ይመስለዋላ። መጥፎ ነገር በርግጥም መጥፎ ስለመሆኑና እርካታም እንደሌለው መጥፎ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ጭምር ይነግሩሃል፡፡ እነርሱ እንደተበላሹት ሁሉ መልካም ሰዎች እንዳይበላሹ ሲሚመክሩ አታይም እንዴ!፡፡ 

«አንተ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነህ፤ እኛን አትቀላቀል፣ እዚያው ባለህበት ፅና፣ ይህ ሥራና ሰፈር ላንተ የሚሆን አይደለም፣እኛ እንደተነጀስነው አትነጀስ… የሚሉህ ለምን ይመስልሃል?፡፡

አይነግሩህም እንጂ መጥፎ ሰዎች በጥሩነትህ/ሽ እንደሚቀኑ አትርሳ፡፡ እንደሱ/ሷ ጠንካራ በሆንን እንደሚሉ አትዘንጋ።መረጋጋትህን እንደሚወዱት አትጠራጠር፡፡ «አቤት ታድሎ/ላ!»ብለው በሌለህበት ሥምህን እንደሚያወሱ አይጥፋህ፡፡ አለመቃምህ፣ አለመጠጣትህ፣ ቁጥብነትህ፣ ከሱስ ነፃ መሆንህ ... ያስቀናቸዋል፣ መጥፎ ሰፈር አለመታየትሽ፣ አለመቅበጥሽ ያስከብርሻል፡፡ሆ ወንጀል እሣት እኮ ነው። መቼ ሰላም ይሠጥና፡፡ ኃጢኣት መቼ ያረጋጋና!፡፡ ስለሆነም ነው ኃጢኣት በሚሠሩ ሰዎች አትቅና፣ መጥፎ ሠርተው ሀብታም በሆኑት አትቁለጭለጭ ያልኩህ፡፡

እና ምን መሰለህ/ሽ … እነርሱ ወዳንተ/ቺ ይምጡ አንተ/ቺ ወደነርሱ አታስብ፡፡ ሰው ሐራም ስለሠራ አትሥራ፣ ሰው ዲንን ሰው ስለተወ አትተው፡፡ ጥሩ ሱንና ተከታይ ከሆንክ ለመልቀቅ አትነይት፣ በሒጃብሽ የበለጠ ለመጽናት እንጂ ለማውለቅ ከራስሽ ጋር አታውሪ፣ ሌሎች አምታተው በሐራም እንደታወቁት ለመታወቅ አትጎምጅ፡፡
እዚያው በነበርክበት ፅና፡፡ በያዝከው መስመር ላይ ተራመድ፣ በቅናቻው ጎዳና ተጓዝ፡፡ የሀብት ብዛት ባይኖርህ በረካዉና እርካታው ይኖርሃል፡፡ ኃጢአተኞች ግን በረከትም እርካታም የላቸዉም ነው የምልህ፡፡በሐራም ትዳርም ሆነ በሐራም ከስብ መቅናት ትልቅ ኪሣራ ነው።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

04 Nov, 16:56


~ቀልብህ ላይ የሆነ ነገር ተጠራቅሞ ምንም ነገር መሥራት የሚያቅትህ ደረጃ የደረስክ እንደሆነ ከሰዎች ተገለል፡፡ ከአላህ ጋር ሁን፡፡ ልብህን ሰብስብና ከርሱ ጋር ተቀማመጥ፤ እርሱ ሁሉን ነገር እንደሚስተካክልልህ እርግጠኛ ሁን።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

04 Nov, 11:58


ለምንወዳቸው ሰዎች እነርሱ ሳያውቁ በሩቅ ዱዓ ከማድረግ በላይ ምን ከባድ ዉለታ ልንዉላቸው እንችላለን?ምንም ወላሂ።

ጌታዬ የሁሉንም ሕይወት አሁን ካሉበት የተሻለ አድርግ። የጎደላቸዉን ሙላላቸው። ያሳሰባቸዉን ፍታላቸው። የቸገራቸዉን ስጣቸዉ። የከበዳቸዉን አግራላቸው።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

02 Nov, 15:58


~ሁሌም ካንተ ጋር ነኝ፣ ፈፅሞ አልለይህም ለሚሏችሁ ...ሁሌም ከኛ ጋር የሚሆነው አላህ ብቻ ነው በሏቸው።

በዚህች አጭር የዱንያ ላይ ዕድሜያችን ከስንቱ ጋር ወዳጅነት ጀምረን፤ ስንትና ስንት ሰው ወደኋላ ጥለን እዚህ ደርሰናል።ሰው ይረሳል። ይረሳና ሁሉንም ነገር ይረሳል።

ቢሆንም በሂደትም ቢሆን መርሳት የማትፈልጉት ሰው በሕይወታችሁ ውስጥ ይኖራል።ሆነብላችሁ ሳይሆን እረስታችሁ እንዳታጡት አልፎ አልፎ «እባክህን አለህ ወይ» በሉት።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

02 Nov, 13:56


📖- يَـا ابنَ آدَم!
إِذا افنيتَ عُمركَ فِي طَلب الدّنيا، فمَـتى تطلُب الآخرة؟

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

02 Nov, 13:32


~ከባድ ነው ብለን የምናስበው ነገር ለአላህ ቀላል ነው፤ ትልቅ ነው ብለን የምሰጋው ለአላህ ትንሽ ነው፤ እሩቅ ነው ብለን የምንፈራው ለአላህ ቅርብ ነው፤ ዉስብስብ ነው ብለን የምንሸሸው ለአላህ ገር ነው፤

ኦ! ይሔማ አይታሰብም ብለን የተውነው ለአላህ ምንም ነው፤ወላሂ ምንም ነው፡፡ብቻ ጉዳይህን ለርሱ ስጥ…ለአላህ የሠጡት ነገር ሁሉ መላ አለው፡፡
الحمد لله!

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

21 Oct, 14:47


«ዱዓ አርግልኝ» አልኩት።«ምን ሆንክ?» አለኝ።«ምንም ካልሆንኩ ዱዓ አታደርግልኝም?» ማለት ነው ? አልኩት።
«እሺ በቃ»አለኝ።

አዎ ምንም ሳይሆኑም ዱዓ ይደረጋል፣ያስፈልጋልም።

እንዲህም ሆኖ…ምንም እንኳ እንደ ጉዳዩ ባለቤት ጉዳዩን ለአምላኩ የሚናገር የሌለ መሆኑን ባውቅም፤ ከራሴ እጅ ይልቅ በሌሎች እጅ የሚደረግልኝን ዱዓ እመርጣለሁ ።

እጄ በእጅጉ ቆሽሿል።ወንድም እህቶች ሆይ ይህን ደካማ ባርያ በዱዓችሁ አስታውሱት።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

21 Oct, 04:37


ينادي فؤادي بليل السكون..

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

21 Oct, 04:19


•አላህ የወደደዉን በመውደድ ዉስጥ ትልቅ እርካታ አለ። ከቻልክ ዉደድ። ካልሆነ ታገስ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

20 Oct, 06:19


ታልቅስ አትከልክሏት!

~ማልቀስ ድክመት አይደለም። አንዳንዴ ዘግታችሁ አልቅሱ። የተጠራቀመ ብሶታችሁን በእንባ ተንፍሱ። እንባ እንጂ ሌላ ነገር መፍትሄው ያልሆነ ችግር አለ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

20 Oct, 04:08


إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

وَمَن تَابَ وَعَمِلَ صَالِحًا فَإِنَّهُ يَتُوبُ إِلَى اللَّهِ مَتَابًا
ተጸጽቶ የተመለሰም ሰው መልካምንም የሠራ እርሱ የተወደደን መመለስ ወደ አላህ ይመለሳል፡፡
{سورة الفرقان}
= t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

19 Oct, 17:21


«ደህና እደሩ» ብሉ የተኛ ሁሉ በርግጥ የተኛ ይመስላችኋልን?! ዉሸት ነው።ዱንያ ስንቱን አድክማለች መሰላችሁ።

አንዳንዱ ዓፊያ ርቆት ይገላበጣል፣ሌላዉን ትዝታ ወስዶት ያንገላተዋል፣አንዳንዱን ናፍቆት ወጥሮ ትያስከንፈዋል፣ሌላው ብቸኝነት ወስዶ ያስባንነዋል፣ትራስ ላይ ያረፈ ጭንቅላት ሁሉ አይተኛም፣ያረፈ ገላ ሁሉ አያርፍም፣የነገ ዉሎው የሚያሳስበው አለ፣የወደፊት ዕጣወ የሚያስጨንቀው ብዙ ነው፣የሁኔታዉን መጨረሻ የሚያሰላስል በርካታ ነው፣የዕዳ መዓት የሚያስተክዘው መዓት ነው፣የተጋደመ ሁሉ አይተኛም።

ጨለማ ብርድልብስ ነው። በዉስጡም  የሚወራ ነገር ጉድ ነው።ምሽት ፀጥታ ነው፣ የናፍቆት ጓዙ በርካታ ነው።

ወዳጄ ሁሉን ነገር ነፍስህን ለፈጠራት ጌታ አስረክበህ ተኛ።ከተሸከምነው ይከብደናል፣ ለሱ ስንሰጥ ግን ይቀለናል።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

19 Oct, 03:51


• هذا من حكمة الشيخ بارك الله فيه  فإن أهل أندونيسيا مذهبهم شافعي، ويجهرون بالبسملة، فهو قرأ على ما اعتاد عليه أهل البلد‌
ولذلك قال شيخ الإسلام ابن تيمية – رحمه الله – ومع هذا : فالصواب : أن ما لا يُجهر به ، قد يشرع الجهر به لمصلحة راجحة ، فيشرع للإمام – أحيانا – لمثل تعليم المأمومين ، ويسوغ للمصلين أن يجهروا بالكلمات اليسيرة أحيانا ، ويسوغ أيضا أن يترك الإنسان الأفضل لتأليف القلوب واجتماع الكلمة ، خوفاً من التنفير عما يصلح ،

📚 ”مجموع الفتاوى”
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

18 Oct, 17:19


📌ሰይጣንን እና ወንጀሎቻችንን ለማሸነፍ የሚረዱን አምስት ምልከታዎች!

①ኛ―አትዘውትር!

ማለትም ወንጀልን ልማድህ አታድርግ።በየዕለቱ የምታደርገው ነገር አይሁን።
   •• አላህ እንዲህ ይላል፡-
إِنَّ الَّذِينَ اتَّقَوْا إِذَا مَسَّهُمْ طَائِفٌ مِّنَ الشَّيْطَانِ تَذَكَّرُوا فَإِذَا هُم مُّبْصِرُونَ
እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ፡፡ ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ፡፡

አወ! የሕይዎትህን መሰረት ኢስቲቃማ አድርግ።ስህተት መስራትን ደሞ ከመንገድ(እንደመውጣት አድርግ) ልክ እንደተበላሸ መኪና። መኪናህ ሲበላሽ ትቆማለህ፣ ትጠግነዋለህ ከዛም መንገድህን ትቀጥላለህ።

ስለዚህ ወንጀል ስትሠራ ተመልሰህ ወደ ነበርክበት መንገድ ተመለስ። ምክኒያቱም አንድ ሰው ከመንገድ ወጥቶ እየሄደ ጉዞውን ከቀጠለ በመጨረሻ ወዴት እንደሚደርስ አያውቅምና።

ለዚህም ነው አብደሏህ ኢብኑ ዓባስ እንዳሉት፦
"لا صغيرة مع الإصرار"
«(ወንጀል ላይ) ከመዘውተር ጋር ትንሽ የሚባል ወንጀል የለም።» ይላሉ።

ማለትም…አንድ ሰው ትንሽም ወንጀል ቢሆን እዛ ላይ ከዘወተረ ትንሹ ወንጀል እንኳን ትልቅ ይሆናል ማለታቸው ነው።

②ኛ ወንጀልን በይፋ አታድርገው!

አደራህን የሰይጣን ድርጅት ውስጥ ሰራተኛ ከመሆን ተጠንቀቅ።ሰይጣን ሰዎችን ለመበከልና ለማጥመም እራሱን ዳዒ ያደረገ፤ ብዙ ሰዎችንም በድርጅቱ ውስጥ ቀጥሮ ወደ ወንጀል በመጣራት ወይም በግልፅ ወንጀልን በመፈፀም ላይ ተጣሪ አድረጓቸዋል።

ለዛም ሲባል ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- «የኔ ኡመት ሁላቸውም ይቅር ይባላሉ።(ወንጀልን)በ ግልጽ የሰሩትን ሲቀር!» ስለዚህ ወንጀልህን በግልፅ ከመፈፀም ተጠንቀቅ።

ወንጀልን በይፋ የሚሠሩ ሰዎች የሰይጣን አጋር ናቸው። ምክንያቱም ሌሎችንም ወደ ወንጀል ስለሚጋብዙ።

③ኛ ወንጀልን አታብዛ!

ሰይጣን ወንጀልን እንዳትተወው ቢያሸንፍህ እንኳ፤በተቻለህ መጠን ለመቀነስ ሞክር።
ከ ወንጀል መላቀቅ የማትችል ከሆነ ቢያንስ የምትሰራውን ወንጀልን ለመቀነስ ሞክር።

④ኛ― ተውበት እና ኢስቲጝፋር አድርግ!

ወንጀል ላይ ከወደቅክ ቶሎ ብለህ በተውባ እና በ ኢስቱግፋር አጥፋው።የሥራ መዝገቦቻችን እንደ ነጭ ሰሌዳ ነው። ወንጀሎቻቸን ደግሞ በላዩ ላይ በጥቁር ቀለም እንደተፃፉ ፁሁፍ ናቸው።ስለዚህ በሥራ መዝገብህ ላይ በ ወንጀል ጥቁር ቀለም ስትጽፍ እና በኃጢአት ስትበክል ወዲያውኑ በተውበት እና በኢስቲጝፋር አጥፋው። በየጊዜው ወንጀል ስትሠራ ወዳው ተውበትን ማድረግ ተለማመድ።

⑤ኛ― መጥፎውን በመልካም ተካ!

ወንጀልን መተው አለመቻልህ፣በተደጋጋሚ ወንጀል ላይ መውደቅህ ተስፋ እንዳያስቆርጥህ። አንተም በተደጋጋሚ መልካምን ስራ ስራበት። ምክንያቱም መልካም ስራዎች መጥፎ ስራዎችን ያጠፋሉና!

ስለዚህ ወንጀል በሰራህ ቁጥር ከሱ ብኃላ መልካም ስራዎችን አስከትል።ለሰዎች መልካምን መዋል፣ ቁርአን መቅራት፣ዚክር ማድረግ፣ ሰደቃ መስጠት፣የሱና ሶላቶችን መስገድ…መሰል ዒባዳዎችን ፈፅም።

📑ከሸይኽ ሃመደል-ዓቲቅ የቴሌ ግራም ቻናል ተወስዶ ከትንሽ ቃላት ቅያሬ ጋር ወደ አማርኛ የተመለሰ―
=t.me/Sle_qelbachn1

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

18 Oct, 05:09


~አንዱ ወጣት ትልቅ ሴትን በመውደዱ ምክንያት ሰዎች ክፉኛ ሲተቹት ዑመር ቢን  አቢ ረቢዐ የገጠማትን ግጥም ትዝ አለችኝ፦
تعشقتها  شمطاء شاب ولدها  
وللناس فيما يعشقون مذاهب
የግጥሟ ጥቅል መልእክትም―ሰዎች  ሲያፈቅሩ የሚከተሉት የራሳቸው የሆነ  መዝሀብ አላቸው የሚል ነው።በሀገራችንም እኔ ከወደድኳት ዝንጀሮም  ትሁን የሚል ሀሳብ ያለው ግጥም አለ።

ኢስማዒል ቢን ጃሚዕ ከሂጃዝ አካባቢ  መርየም የተባለችን ጥቁር እንድሁም  የሰዎች  አገልጋይ የሆነችን ልጅ ያገባል።ከዕለታት አንድ ቀን  ረሺድ ወደተባለው ንጉስ ዘንድ ጉዞ ይጀምራል። ከረሺድ አካባቢ ሲደርስ ያቺ መልከ ጥፉዋ መርየም ትናፍቀዋለች።ከእሷ ጋር የሚጨወቱበትን ቦታ ፣የሚዝናኑበትን አካባቢ እየጠቃቀሰ መርየም ማለት እንደ ዐንበር የምትሸት፣እንደ ሀር ልብስ  የምትለሰልስ፣እንደ አበባ የፈካች ምርጥና ቆንጆ ሚስት ነች እያለ በተጋነነ መልኩ  በግጥም አወዳደሳት።ረሺድም በኢስማዒል ግጥም ተደመሞ  ነበርና ለመሆኑ ይች ሁረል ዐይንን አስመስለህ የገለፅካት መርየም ማን ነች ብሎ ሰፊ ማብራርያን ይጠይቀዋል።የኔማ ሚስት ብሎ ጀምሮ በግጥም ከገለፃት በበለጠ መልኩ እንዳደነቃት ተነግሯል፡፡

ከተዋደዳችሁ ምን አገባኝ ለማለት ነው¡¡
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

17 Oct, 18:48


وَلَا تُخْزِنِي يَوْمَ يُبْعَثُونَ
በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡

يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ
ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡

إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»

[سورة الشعراء]
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

17 Oct, 10:05


«ስጦታ ተሠጣጡ ትዋደዳላችህ!»
የሚለውን የነቢያችን ﷺ ሐዲሥ የምናውቅ ስንቶቻችን እንሆን!።ይህ ሐዲሥ ስጦታ በሰዎች ላይ ተፅእኖው ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ያመለክተናል።

~ስጦታ አንዱ ሰው ለሌላው ያለውን ከፍ ያለ ግምት ከሚገልፅበት ነገሮች መካከል አንዱ ነው። ቆም ብሎ ለማሠብ እድል ይሠጣል። ሀሣብን ያስቀይራል ።ቅሬታንም ያስወግዳል። በተለያዩ አጋጣሚዎች በምክኒያትም ሆነ ያለምክኒያት ሥጦታ መለዋወጥ መልካም ነገር ነው።

በተለይ በባለ ትዳሮች መካከል ጠንካራ ግንኙነትን ለመፍጠር ያግዛል።ይልመድባችሁ¡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

17 Oct, 06:02


سلسلة تعنى بجمع أقوال العلماء الربانين من سلف هذه الأمة الذين كان لهم دورهم في الدعوة إلى الله وكان لأساليبهم ومواعظهم دورها الفعال في تربية المسلمين .
صدر منها :
مواعظ الإمام الحسن البصري
مواعظ الإمام سفيان الثوري .
مواعظ الإمام عمر بن عبد العزيز
مواعظ الإمام مالك بن دينار
مواعظ الإمام إبراهيم بن أدهم
مواعظ الإمام عبد الله بن المبارك
مواعظ الإمام الفضيل بن عياض
مواعظ الإمام الشافعي
مواعظ الإمام أبو سفيان الدراني
مواعظ الإمام الحارث المحاسبي
مواعظ الشيخ عبد القادر الجيلاني
مواعظ الإمام ابن الجوزي
مواعظ شيخ الإسلام ابن تيمية
مواعظ الإمام ابن القيم الجوزية
مواعظ الإمام زين العابدين
مواعظ الإمام الجنيد
مواعظ الإمام أحمد بن حنبل
مواعظ الأمام الأوزاعي

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

16 Oct, 14:52


قَالَتْ يَا وَيْلَتَىٰ أَأَلِدُ وَأَنَا عَجُوزٌ وَهَٰذَا بَعْلِي شَيْخًا ۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيْءٌ عَجِيبٌ
(እርሷም) ዋልኝ! እኔ አሮጊት ይህም ባሌ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው አለች፡፡

قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ
«ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

16 Oct, 13:20


ጁዳ እና አከባቢያዋ ያላችሁ ጥራት የለው ንፁህ ማር በጂምላም በችርቻሮችም ከፈለጋችሁ ከእኛ ጋር ያገኛሉ!
ይደውሉ!👇
0550845152

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

16 Oct, 10:14


ተቀባይነትን ለማጣት ቀላሉ መንገድ!

~በማንኛውም መስክ በሚኖራችሁ የሰው-ለሰው ግንኙነት ውስጥ ቀስ በቀስ ተቀባይነትን፣ ተከባሪነትን፣ ተፈላጊነትንና የሰዎችን አብሮነት ማጣት ከፈለጋችሁ የሚከተሉትን አጓጉል ባህሪያት ግለፁ፡፡

1.ብዙ ማውራት፡- ብዙ ማውራት የእውቀትና የተግባር ማጣት ምልክት ነው፡፡ ለሌላው ሰው ሃሳብ ጊዜ ባለመስጠት ሁል ጊዜ እሱ ብቻ ከሚያወራ ሰው አካባቢ መሆን የሚፈልግ ሰው የለም፡፡  

2.በሆነ ባልሆነው መነጫነጭ፡- መነጫነጭ የአቅመ-ቢስነት ምልክት ነው፡፡ የሚነጫነጭ ሰው አቅም የሌለው ሰው ከመሆኑም በላይ የሰሚውንም አቅም ስለሚጨርስ ሰዎችን ያርቃል፡፡

3.ተቃዋሚነት፡- ተቃዋሚነት የቅንአትና የመበለጥ ስሜት ምልክት ነው፡፡ ሁል ጊዜ ሰዎችን የመቃወምን ሃሳብ ከሚሰነዝር ሰው አካባቢ መክረም የሚፈልግ ሰው የለም፡፡   

4.ግትርነት፡- ግትርነት የጠባብነት ምልክት ነው፡፡ ግትር ሰዎች አመለካከታቸው ጠባብ ስለሆነና ከእነሱ ሃሳብና አቋም ውጪ መቀበልን ስለማይፈለጉ ሰዎችን ያርቃሉ፡፡

«ሰዎች ትንሽ ቀርበውኝ ይሸሹኛል…ከሰዎች ጋር ያለኝ ግንኙት አይቆይም… ሁሉም ሰው ትንሽ ካወቀኝ በኋላ ይርቀኛል…»እና የመሳሰሉት ስሜቶች ካሏችሁ የተጠቀሱትንና መሰል አጉል ባህሪያቶቻችሁን ለማጤንና ለማስተካከል ሞክሩ፡፡ ከዚህ በላይ ወናው እና ትልቁ ደሞ ከ አላህ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ፈትሹ።በ አንተ እና በአላህ መካከል ያለውን ስታስተካክል፤አላህ ደሞ በ አንተ እና በባሮቹ መካከል ያለውን ጉዳይ ያስተካክልልሃልና!።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

15 Oct, 12:03


~ከፍቅር ጋር ዘላለማዊ ፀብ ውስጥ ያለህ ይመሰል አንዳንዴ የማይወድህን ሰው ትወዳለህ፤ወይ ደግሞ አንተ ሳትወደው የሚወድህን ሰው ታገኛለህ። አላህ ብሎልህ አንተም እሱም የምትዋደዱ ሆናቹ ስተገናኙ ደግሞ ህይወት ትለያያቹሃለች።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

14 Oct, 14:01


የቂን…

የቂን ማለት ዙርያህ ሁሉ በተስፋ አስቆራጭና ድቅድቅ ጨለማ የተሞላ ቢሆንም አላህ ያሰብኩትን ሁሉ ያሳካልኛል ብሎ ማሰብ ነው።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

14 Oct, 12:06


~ወንጀል ላይ በወደቅክ ቁጥር ሁሌ ወደ አላህ የምትመለስ ከሆነ፤ይህ አላህ በ አንተ ላይ ከዋለልህ ፀጋ ውስጥ ነው!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

13 Oct, 15:22


يا من هواه أعزّه وأذلّني..

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

13 Oct, 14:01


~ሰዎች ችግር ሲያጋጥማቸው ወደ አንተ መቅረባቸው አላህ ከሰጠህ ፀጋዎች ውስጥ አንዱ ነው።«እሱ ሲቸግረው ነው የሚያውቀኝ!» ከምትል ይልቅ«ወደኔ የመጣው የተሻልኩ ሆኜ በመገኘቴ ነውና ጌታዬ የበዛ ምስጋና ይገባሀል!» እያልክ ልታወድሰው ይገባል።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

12 Oct, 16:52


አንተን ማጣት ምንም የማይመስለውን ሰው
እየተንከባከብክ ነፍሰህን አትጣት።

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

12 Oct, 05:19


~በራሳችን ሁኔታ የተነሳ አንዳንድ ጊዜ ለብቻ ከራሳችን ጋር የምናወራበት ሁኔታ ይኖራል፡፡

በአላህ መንገድ ላይ ወጥ በሆነ አቋም ፀንተን የምንኖረው መቼ ይሆን?የመሆን ፍላጎቱን እንጂ ጉልበቱን አጣን…ያቦካነው ሁሉ አልደርስ እያለ ተቸገርን…የያዝነውን ኢማን ይዘን መዝለቅ አቃተን…ሙከራዎቻችን ሁሉ ሊለውጡን አልቻሉም…ተውባችን ሁሉ ታጥቦ ጭቃ ሆነ።

ታዲያ ለማን ትተወናለህ የኔ ጌታ!
ወዳንተ መምጣት እየፈለግን የዱኒያ ጣጣዎች መንገድ ላይ አስቀሩን…ካንተ  ለመድረስ አስበን በተነሳን ቁጥር ነፍሲያና ሸይጣን ከጉዞአችን አገቱን።

ቁጣህ አይኑርብን እንጂ ሌላው ሁሉ ምንም ነው!!
አንተው በጀን ያ ረብ…
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

11 Oct, 05:21


~ጁሙዓ ሲነሳ ሐቢባችን ﷺ ፊታችን ይደቀናሉ፤ በሀሳባችን ይጣዳሉ፤ ይደርሠኛልና ሶለዋታችሁን አድርሱኝ ብለዋልና ከሌላው ጊዜ በበለጠ ትዝ ይሉናል፡፡ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም―
t.me/AbuSufiyan_Albenan

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

10 Oct, 16:40


~እስልምና ሥራን ያወድሳል፤ጥረትን ያበረታታል። ምድር ላይ ዝምብሎ አላህ! አላህ! እያሉ መቀመጥ የለም። ለሥራና ለዒባዳ እንጂ ለዚክር እና ዱዓ ብቻ የተላከ የሰው ልጅም የለም።ካልሠራን  ሰማይ ወርቅ አትዘንብም፤  ምድር ብር አታበቅልም።በኑሮህ ዉስጥ ሁሉ አላህን ታወራዋለህ፣ ታማክረዋለህ፣ ትለምነዋለህ።ሳትሞክር፣ ሳትሰራ፣ ተኝተህ ... አላህ በደለኝ፣ ከለከለኝ አትበል።

~ባይሆን ባይሆን ትሞክርና አልቻልኩም ትለዋለህ፤ ትጥርና ደግፈኝ ትለዋለህ፣ ትሸሽና አድነኝ ትለዋለህ፣ ታጠራቅምና ሙላልኝ ጎድሎኛል ... ብለህ ትለምናለህ፣ ትበረታና ምራኝ አቅናኝ ትለዋለህ ...እሱ ያለምንም መነሻ ነገሮችን ማድረግ ቢችልም ግና የሚጥሩትን ታታሪዎች ይወዳል።
~t.me/AbuSufiyan_Albenan

22,170

subscribers

627

photos

477

videos