አርከለዲስ | Arkeledis Media @arkeledis_21 Channel on Telegram

አርከለዲስ | Arkeledis Media

@arkeledis_21


√ ይህ የደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካውንት ነው። 1000057909769 ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ እያላችሁ የቻላችሁትን አበርክቱ።

🔗 https://www.youtube.com/@Arkeledis_21
🔗 https://www.facebook.com/Arkeledis21

@Arkeledis_21

አርከለዲስ | Arkeledis Media (Amharic)

Arkeledis Media የይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካውንት ነው። ይህ አካውንት ደብረ ይድራስ ሽማጎዊን እና መንገድዎን ለአንተ እንደክፈለን፣ ቅዱስ ጊዮርጊስን በማቅረብ እና መልካም መረጃዎን በቴም ለቀማንበሉ። በተጨማሪም ይህ አካውንት በኢትዮጵያ እየለዩ ይሆናል። በቀላሉ እንስራት ስለመተንተንት ስለ ጌታ አገልጋዮች፣ የግል ቤተክርስቲያን ስራውን ይቀዩና፣ በመስራት እና በመከላከል የትኞቹን መረጃዎችን በዚህ ቦታ ተመልከቱ። ከእነሱም ጋር እጅግ በመፈለግ በሚሰሩበት ጊዮልታሶችና ፍርዶች እጅግ በሚሰሩበት ተጨባጭ እና የቴም ቦታዎን ለተጠቁመ ተመልከቱ። Follow @Arkeledis_21 በቴም ያግኙ።

አርከለዲስ | Arkeledis Media

01 Jul, 13:49


እንኳን ደስ አላችሁሁሁ! 💥💥💥

አርከለዲስ | Arkeledis Media

01 Jul, 13:49


https://youtu.be/AWfmyAbi5_A?feature=shared

አርከለዲስ | Arkeledis Media

13 Jun, 13:00


# *ዕርገት*
# *በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ*

የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡

ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡    

እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡

ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር  የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡

ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡

ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡

(ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

አርከለዲስ | Arkeledis Media

12 Jun, 08:48


፨፨፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚችም ዕለት የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም አመታዊ የበዓሏ መታሰቢያ ነው፨፨፨

ቅድስት ዜና ማርያም

፨ በ11መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት ግንቦት 30 ቀን በጎጃም ክፍለ ሀገር ተወለደች። የአባቷ ስም ገብረ ክርስቶስ የእናቷ ስም አመተ ማርያም ይባላሉ። እጅግ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፡ ቅዲስ ጋብቻቸውን በንጽሕና የሚጠብቁ፡ ለሰው የሚራሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ። እንዲህ ባለ መልካም ግብር ከኖሩ በኀላ በፈቃደ እግዚአብሔር 3 ወንዶች ልጆች እናት አንዲት ሴት ልጅ ወለዱ። ይህችም ሴት ልጅ ተወዳጇ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ናት።

፨ ቅድስት ዜና ማርያም እናት እና አባቷን እያገለገለች፡ ፈርሐ እግዚአብሔን፡ በጎ ምግባርን ከወለጆቿ እየተማረች አደገች። ለአቅመ ሔዋንም በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ ወጣት አጯት። ታላቅ ግብዣ ተደረጎ በተክሊል ተዳረች። በዚያው ወራት ግን የዜና ማርያም እናት አመተ ማርያም አምስተኛ ልጅ ወልዳ ተኝታ ሳለች በአካባቢው ሕማመ ብድብድ (ተላላፊ በሽታ) በመነሳቱ የዜና ማርያም እናት ታማ ነበር፡ በመጨረሻም ከዚህ ኃላፊ ዓለም አረፈች።

፨ ከዚህ በኋላ የታመመውን ወንድሟንና ሌሎቹንም በመያዝ ከተላላፊው በሽታ ለመትረፍ ሲሉ አካባቢውን ለቀው ወደ በረሃ ወጡ። በዚያም ሌሊት የዱር አራዊት መጥተው ከበቧቸው ሁሉንም ሊበሏቸው ሞከሩ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ስመ እግዚአብሔርን ስትጠራ አራዊቱ ወደኋላ በመሸሽ ከአካባቢው ራቁ። እርሷም ከክፉ ሁሉ የጠበቃቸውን፡ ከአራዊት መበላት የሰወራቸውን እግዚአብሔርን አመሰገነች። በነጋም ጊዜ የታመመውን ወንድሟን እና ሌሎችን በመያዝ መንገድን ቀጠሉ አንዲት ባዶ ቤት አግኝተው ከእርሷ ተጠጉ። በፀሐዩ ንዳድና ታናሽ ወንድሟን በማዘል እጅግ ስለደከመች ከባድ እንቅልፍ ጣላት። ጠዋት ስትነሳ ግን የታመመው ወንድሟ ከአጠገቧ አላገኘችውም ሌሊት የዱር አራዊት በልተውታልና። አጅም አዘነች የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብላ አራሷን አፅናናች የወንድሟን ተረፈ ሥጋ አጠራቅሟ ቀበረች። በመቀጠልም በአካባቢው ካለ ገዳም ሔዳ ምንኩስናን ተቀበለች።

፨ ከዚህ በኋላ ባሏ አባቷን ሚስቴን አምጣ እያለ ስለጨቀጨቀው ከብዙ ልፋት እና ድካም ፈልጎ አገኛት ወደ ሀገሯም ወሰዳት። በዚያም ወደ ጉባኤ ቀርባ ለምን ወደ ገዳመ እንደሄደች እና ባሏን አንደከዳች ተጠየቀች። እርሷም እግዚአብሔር ከብዙ መከራ አድኖኛል እና እራሴን ለእግዚአብሔር ሰጥቻለሁ አለች። የጉባኤው ተሰብሳቢ በሏ ሀብቷን ወርሶ እንዲያሰናብታት ፈረዱ። እርሷም በዚህ ነገር በመስማማት የነበራትን ላም እና በሮች አስረከበች።
፨ ከዚህ በኋላ በአባቷ ቤት ለአንድ ዓመት ያህል በመቀመጥ የእናቷን ተዝካር አውጥታ ወደ ገዳሙ ተመለሰች በዛም ለጥቂት አመታት የተለያዩ ገድላትን ስትፈጽም ከቆየች በኋሏ ከነፍስ አባቷ ባሕታዊ አባ ገብረ መስቀል ጋር ወደ ጎንደር ሀገረ ስብከት ልዩ ስሙ እንፍራንዝ (ጣራ ገዳም) አካባቢ ዋሻ እንድርያስ በተባለው ለ25 ዓመት በብሕትውና ኖረች። አሁንም ድረስ በዚያ ዋሻ እናታችን ዜና ማርያም በፀሎት ጊዜዋ እንቅልፍ እንዳይጥላት ስትጠቀምበት የነበረ ዘንግ ፣ የምተቆምበት ዙሪያውን በገመድ የታሰረ የተቦረቦረ ግንድ አሁንም ድረስ ተአምር እየሰሩ ይገኛሉ። ከዚህም በመቀጠል ዛሬ ዜና ማርያም ተብሎ ወደ ሚጠራው ዋሻ ሔደች በዚያም በጾምና በጸሎት በልዩ ልዩ ተጋድሎ እስከ እለተ እረፍቷ ድረስ በዚያ ኖራለች።

+++ የገድል ዓይነቶች +++

፨ በየሰዓቱ ከ 100-300 ትሰግድ ነበር
፨ ሁለት ቀን እየፆመች በሶስተኛ ቀን ጥቂት ጥሬ ቀምሳ ሳምንቱን ታሳልፈው ነበር
፨ 150ን መዝሙረ ዳዊት እና ወንጌል በየቀኑ ትጸልይ ነበር
፨ በብሕትውና ወራት ማር፣ ቅቤን፣ ወተትን ፈጽሞ አትቀምስም ነበር
፨ የጌታችን መከራ መስቀል እና ስትየ ሐሞት በማሰብ በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ ኮሶ የሚባል ቅጠል እየበጠበጠች ከቅል ውስጥ ከሚገኘው መራራ ፍሬ ጋር በማዋሐድ ትጠጣ ነበር
፨ ከጸሎት እና ከስግደት በምታርፍበት ጊዜ አትክልት በመትከል እና በመኮትኮት ጊዜዋን ታሳልፍ ነበር
፨ የጌታችንን ግርፋቱን በማሰብ 100 ጊዜ ጀርባዋን ስለምትገረፍ እና ደም ስለሚፈሳት ጀርባዋ ይቆስል እና ይተላ ነበር።

+++ተአምራት+++

፨ ዓይናቸውን በተለያየ በሽታ የታመሙ ሰውዎች ሁሉ ከህመማቸው ተፈውሰዋል
፨ የራስ በሽታ ( የራስ ፍልጠት፣ ጭንቀት፣ ማዞር) የታመሙ ጸበሉን በመቀባት ድነዋል፡፡

፨ ጸበሉን በመጠመቅ፤ የጻድቋን ተአምር በማዘል፤ ስዕለት በመሳል መካኖች ወላድ ሆነዋል። ሌሎች በየቀኑ ብዙ ተአምራትን እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ታደርጋለች።

+++ቃል ኪዳን+++

ቅድስት ዜና ማርያም ከዚህ ዓለም የምታርፍበት ጊዜ እንደደረሰ በመንፈስ ቅዱስ በአወቀች ጊዜ ከታላቅ ዛፍ ወጥታ ስትፀልይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክት ጋር፣ ከነቢያት፣ ከሐዋርያት፣ ከሰማዕታት፣ ከጻድቃን፣ ከደናግል መነኮሳት ጋር በመሆን ተገልጾ ከአረጋጋት በኋላ ቃል ኪዳንን ሰጧታል።
፨ በፀሎትሽ ያመነውን ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ
፨ በስምሽ የተራበውን ያበላ በመንግስተ ሰማያት ኅብስተ ሕይወት አበላዋለሁ፤ የተጠማውን ያጠጣ ጽዋዓ ሕይወትን አጠጣዋለሁ
፨ መጽሐፈ ገድልሽን የጻፈውን፡ ያጻፈውን፡ የሰማውን፡ ያሰማውን ስሙን በዓምደ ወርቅ እጽፈዋለሁ
፨ ከሕፃንነትሽ እስከ አሁን ድረስ ስለ እኔ ብለሽ ብዙ መከራ ተቀብለሻል፦ ደጅሽን የረገጠ የሦስት ጭነት ጤፍ ያህል ነፍሳትን እንደሚምርላት፡ እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት ጌታችን በማይታበል ቃሉ ቃልኪዳን ገብቶላታል። እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት፡፡

+++ ገዳሟ እና መገኛው+++

፨ የቅድስት ዜና ማርያም መካነ መቃብሯ ( ጸበሏ) በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ከም ከም ወረዳ ይገኛል ቦታውም አዲስ ዘመን ከተማ 20 ኪ.ሜ ርቆ የሚገኝ ሲሆን ከከተማው በስተሰሜን በኩል "ደሪጣ" ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ይገኛል።

"ደሪጣ"

ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜው ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ (ገዳም) ተብሎ እስከ አሁን ድረስ እየተጠራ ይገኛል፡፡ ይህን ስያሜ ያገኘውም በቅድስት ዜና ማርያም ገድል ውስጥ " ወትሰቲ ሲካር (ኮሶ) ደሪፃ" የሚል ቃል ይገኛል። ይህም ማለት ኮሶ የተባለውን እንጨት (ቅጠል) ቀጥቅጣ (አልማ) ከቅል ውስጥ ከሚገኘው ፍሬ ጋር በማደባለቅ ትጠጣለች ማለት ነው። ስለዚህ ቦታው "ደሪፃ" ተብሎ ተሰየመ በማለት በአካባቢው የሚገኙ አባቶች ይናገራሉ። በመጨረሻም ተጋድሎዋን በመፈጸም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን ከዚህ አለም ድካም ዐርፋለች። የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም በረከቷ ቸርነቷ ይደርብን። አሜንን!!

+++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎታ፡፡ ወበረከታ ለቅድስት ዜና ማርያም የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን

አርከለዲስ | Arkeledis Media

12 Jun, 08:47


ፎቶ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

12 Jun, 08:47


*<<ዕንባ>>*

_በቅዱስ *ዮሐንስ አፈወርቅ*_

በአትሕቶ ርእስ የሚኖሩ ሰዎች፥ ልብሰ ንግሥናውን ለብሶ በጭንቀቴ ደክሜአለሁ፤ ሌሊቱን ኹሉ አልጋዬን አጥባለሁ፤ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ” እያለ ንስሐ የገባውን ንጉሥ ዳዊትን ያድምጡት (መዝ.6፡6)፡፡ እኛም እንደዚሁ እናድምጥ፤ አድምጠንም እንገሠጽ፡፡ ንጉሥ ዳዊት የተጨነቀ ብቻ አይደለም፤ በመቃተትም ደከመ እንጂ፡፡ እንዲሁ ያነባ ብቻ አይደለም፤ አልጋውንም በዕንባ አራሰ እንጂ፡፡ ለአንድ፣ ወይም ለኹለት፣ ወይም ለሦስት ቀናት ብቻ አይደለም፤ ሌሊቱን ኹሉ ያነባ ነበር እንጂ፡፡ በሌላ አገላለፅ ዕንባውን አንድ ጊዜ ብቻ አፍስሶ ከዚያ በኋላ አላረፈም፤ በሕይወት ዘመኑ ኹሉ ዕንባውን ሲያፈስስ ኖረ እንጂ፡፡ ብዙውን ጊዜ ለአንድ ቀን፥ ከአንድ ቀንም ለሽርፍራፊ ሰዓታት ዕንባችንን አፍስሰን ከዚያ በኋላም ይህን አቁመን ተድላ ደስታ እንደምናደርገው እንደ እኛ አይደለም፡፡ ንጉሥ ዳዊት እንደዚህ አላደረገም፤ ለዘወትር ዕንባውን እያፈሰሰ ያለቅስ ነበር እንጂ፡፡

እኛም ይህን (እንደዚህ ያለውን) ኑዛዜ አብነት እናድርገው፡፡ በዚህ ዓለም እያለን ዕንባችንን ለማፍሰስ ካልፈቀድን፥ በወዲያኛው ዓለም ከማልቀስና ከመቃተት በቀር ሌላ ዕጣ የለንምና፡፡ በወዲያኛው ዓለም ዕንባችንን ብናፈስስ ለምንም ለምን አይጠቅመንም፤ ገና በዚህ ዓለም እያለን ዕንባችንን ብናፈስስ ግን ረብ ጥቅሙ ብዙ ነው፡፡ በወዲያኛው ዓለም ዕንባችንን ብናፈስስ የሐፍረት ዕንባ ነው፤ በዚህ ዓለም ዕንባችንን ብናፈስስ ግን ለጥቅም ነው፡፡
በዚህ ዓለም አልጋውን በዕንባ የሚያጥብ ሰው ክፋትን ወይም ጥፋትን ኹሉ ያርቃል፡፡ በዚህ ዓለም መኝታውን በዕንባ የሚያርስ ሰው ሕሊናውን ከፀሐይ ይልቅ ጽሩይ በማድረግ ነፍሱን ከማንኛውም ዓይነት ማሰሪያ ነጻ ያደርጋል እንጂ ምድራዊ ለኾኑ ነገሮች ከፍ ያለ ዋጋ አይሰጥም፡፡ 
እየተናገርሁ ያለሁት ለመነኰሳት እንደ ኾነ አድረገህ አታስብ፡፡ በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎችም ጭምር ነው እንጂ፡፡ ይህ ትምህርት ለመነኰሳት ከሚሰጣቸው ረብሕ በላይ በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ይረባቸዋልና፡፡ ንስሐ የሚያሻቸው እነዚህ ናቸውና፡፡

እንደዚህ ዕንባውን እያፈሰሰ ሌሊት ሌሊት የሚቃትት ሰው ሕሊናው ከደመናት በላይ ይነጠቃል፡፡ እንደዚህ ያለ ሰው በመንፈሳዊ ሐሴት ተሞልቶም በእምነት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ይቀርባል፡፡ ከባልጀሮቹ ጋር በደስታ ይነጋገራል እንጂ አይቈጣም፤ በፍትወት አይቃጠልም፤ ፍቅረ ንዋይ አይሠለጥንበትም፤ አይቀናም፤ እንደዚህ ባለ በሌላ ነገር አይያዝም፡፡ እነዚህ ኹሉ ስሜቶች እንደ አራዊተ ገዳም በውስጡ ቢያገሡም እንኳን፥ የሚቃትትና ዕንባውን የሚያፈስስ ሰው እንደ ለማዳ እንስሳ ይገዛቸዋል፡፡

ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

09 Jun, 16:17


*ኃጢአትህን_ኹሉ_በዲያብሎስ_ላይ_አታሳብብ*

በንስሐ ተስፋ ከቆረጥክ ዲያብሎስ ይወድሃል፡፡ ግን እርሱ እንዲረካ አታድርግ፡፡ ለድኅነት ቀንም ሁሌም ዝግጁ ሁን፡፡

እነዚህን ኹሉ የተናገርኩት ዲያብሎስን ከነቀፋ ነፃ ለማውጣት ሳይሆን እናንተን ከስንፍና ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ ኃጢአታችንን ኹሉ በእርሱ እንዳናሳብብ በእውነት ይስፈልጋል፤ ለሁሉም ክፋታችን ሰይጣንን ተጠያቂ የምናደርግ ከሆነም የራሳችንን ቅጣት እንጨምራለን፤ ጉዳዩን ኹሉ ወደ እርሱ ስላስተላለፍንም ይቅርታ አናገኝም - ልክ ሄዋን ይቅርታን እንዳላገኘች ሁሉ፡፡

ግን ይህን አናድርግ፡፡ እራሳችንን እንወቅ፡፡ ቁስላችንን እንወቅ። ከዚያም መድኃኒቶቹን ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን፤ ደዌውን የማያውቅ ሰው፣ ድካሙን አይፈውስምና፡፡

ብዙ ኃጢአት ሠርተናል፤ ይህን በሚገባ አውቃለሁ፡፡ ሁላችንም ቅጣት ይገባናል፡፡ እኛ ግን ያለ ይቅርታ አይደለንም፣ ከንስሐ አንቀርም፤ አሁንም በአደባባይ ቆመናል፤ በንስሐም ተጋድሎ ውስጥ ነን፡

አርጅተኻል እና በመጨረሻው የሕይወት ደረጃ ላይ ነህ? አሁን እንኳን ከንስሐ እንደወደቅክ አታስብ፡፡ በራስህ መዳን ተስፋ አትቁረጥ፤ በመስቀል ላይ ነፃ የወጣውን ዘራፊ አስብ፡፡ እርሱ ዘውድ ከተቀዳጀበት ጊዜ የበለጠ ምን አጭር ነገር አለ? ያም ሆኖ ይህ ለእርሱ መዳን በቂ ነበር፡

ወጣት ነህ? በወጣትነትህ አትተማመን፣ ከፊትህ ረዥም ጊዜም እንዳለ አታስብ “የእግዚአብሔር ቀን እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና" (፩ኛ ተሰ. ፭፣፪) ለዚህም ነው ፍጻሜያችንን የማይታይ ያደረገው፣ ተግተን እንድንጸና።

ማንም ኃጢያተኛ ሊያደርግህ አይችልም ይላል አቡነ ቴዎድሮስ - ዲያብሎስም ቢሆን፡፡ ለኃጢአት የመስማማት ወይም የመቃወም ኃይል ያለው በአንተ ውስጥ ብቻ ነው፡፡

አሁን እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ክፋት እንዲሆን የፈቀደ እንደሆነ አልያም በሌላ ምክንያት እንደሆነ እንመርምር።

በስንፍና በልቡም ምኞት ወደ ራሱ ኃጢአትን ከሚያስገባ ሰው በቀር፣ ኃጢአት በማንም ላይ ሊጫን አይችልም፡፡ ፈቃደኛ ባልሆነው እና ኃጢአትን በሚቃወመው ሰው ላይ ዲያብሎስ ኃይል የለውምና፡፡

ዲያብሎስ በኢዮብ ላይ ይህን የኃጢአት ክፋት ለመጫን የክፋት ዘዴውን ኹሉ ከተጠቀመ በኋላ ዓለማዊ ንብረቱን ኹሉ ገፍፎት፣ በሞት ሰባቱን ልጆቹን ነጥቆት፣ ከጭንቅላቱ ፀጉር እስከ እግሩ ጥፍር ድረስ የሚያስፈሩ ቁስሎችን፣ የማያባሩ ስቃዮችን ከሰጠው በኋላ የኃጢአት እድፍ በኢዮብ ላይ እንዲጣበቅ ለማድረግ በከንቱ ሞከረ፤ ኢዮብ በዚህ ኹሉ ጸንቶአልና፤ ከቶ አምላኩን ለመሳደብ ፍቃደኛ አልነበረም።

(የነፍስ ምግብ - #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው ገጽ 80-82 #በፍሉይ_ዓለም የተተረጎመ)

አርከለዲስ | Arkeledis Media

07 Jun, 04:37


https://youtu.be/ER7HCwTrSaM?feature=shared

አርከለዲስ | Arkeledis Media

06 Jun, 19:57


† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

† ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፴ †

† አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት †

=>አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሠላሳ በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ሚካኤል አረፈ። ይህም አባት የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ስለ ተማረ አዋቂ ነበር። በልቡም አጠናቸው በቃሉም አጠናቸው።

ከዚህም በኋላ ንጽሕት ሰውነቱ ከአምላክ በተገኘ የምንኵስና መንገድ በመጋደል ክብር ይግባውና የክርስቶስ ጭፍራ ልትሆን ወደደች። ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በውስጡ ብዙ ዓመታት ኖረ ቅስናም ተሾመ።

ከዚህም በኋላ በግብጽ አገር ወደ አለ ወደ ሠንጋር ወጣ በዚያም በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አድርጎ አርባ ዓመት ኖረ ከዚያም የሚበዛ ኖረ በዚያም ዋሻ ውስጥ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ።

የትሩፋቱ የጽድቁና የዕውቀቱ ወሬ በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ኤጲስቆጶሳት ተስማው ወዲያውኑ ይዘው በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

በተሾመም ጊዜ በጎ አካሔድን ሔደ የዚህን ዓለም ጥሪት ሁሉ ንቆ ተወ። ከሚገባው ከሚአመጡለት ገጸ በረከት አንድ ዲናር ወይም አላድ ጥሪት አድርጎ አላኖረም። ከእርሱ በየጥቂት እየተመገበ የቀረውን ለድኃና ለጦም አዳሪ ይሰጣል ለአብያተ ክርስቲያናትም ለንዋየ ቅድሳትና ለቅዱሳት መጻሕፍት መግዣ ያደርገዋል።

ሕዝቡንም ያስተምራቸውና ይገሥጻቸው ይመክራቸውም ነበር። አንድ ጊዜ ከመጻሕፍት አንድ ጊዜም ከቃሉ። መልካም አገልገሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ከዚህ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው የሕይወትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ሊሰጠው ወዶ የአንዲት ቀንና የአንዲት ሌሊት ሕመም በላዩ አመጣ።

ከቶ አልተናገረም በሚሞትበትም ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን አመሰገነው ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ። ነፍሱንም ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ መላ ዕድሜውም ዘጠና ዓመት ከስምንት ወር ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለሚካኤል እግዚአብሔር ዘንዕዶ። ሶበ አሥመሮ ፈድፋደ እንዘ ይጸመዶ። በመጽሐፍ ወቃል ልበ ምእመናን ምዒዶ። አዕረፈ ዮም ቅድመ እለ ይቀውሙ ዐውዶ። በአርአያ መስቀል ቅዱስ እንዘ ይሰፍሕ እዶ።
፨፨፨

=>በዚችም ዕለት ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሐዋርያ ቆሮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ጌታችን በሚያስተምርበት ወራት ሦስት ዓመት አገልግሎታል ከዕርገቱ በኋላም ሐዋርያትን አገልግሏቸዋል ከእሳቸውም ጋራ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ።

ከዚህም በኋላ ከሐዋርያ ጳውሎስ ጋራ በመሆን መልእክቶቹንም ወደ ብዙ አገሮች ተሸክሞ በመውሰድ አገለገለው። ከአይሁድና ከአሕዛብም ብዙዎቹን አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።

ከዚህ በኋላም በምሥራቅ ወዳሉ አገሮች ሔደ ከመኵራቦችም ብዙ መከራ ደርሶበት አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለቆሮስ ለወልደ ማርያም ዘተልእኮ። መጠነ ፫ቱ ዓመት በኢያውክኮ። ወእምድኅረዝ ዐርገ ካዕበ ምስለ ጳውሎስ ተወሲኮ። እምነ ሥቃይ ዘረከቦ ወእምንዳቤ ዘሆኮ። አመ ፍጻሜ ወርኅ አዕረፈ በሠናይ አምልኮ።
፨፨፨

=>በዚችም ዕለት ተጋዳይ የሆነች ፍትወተ ሥጋን ድል ያደረገች በበጎ ሥራዋም እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘች ቅድስት አርዋ አረፈች። በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለአርዋ እንበለ ትግበር ጌጋየ። በስምዐ ሐሰት ተቀቲላ እንተ ተንሥአት ጥዑየ። ምስሌሃ ለሰኪብ አመ ብእሲ ሐለየ። እግዚአብሔር መሠጣ ኀበ ትረክብ ናህየ። ከመ በጸሎት ትቤ ተመጠው ነፍስየ።
፨፨፨

=>በዚህችም ዕለት የሰማዕት ዲማዲስ መታሰቢያው ነው በረከቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘላለሙ አሜን።
የግንቦት ወር ንባብ ተፈጸመ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ለመንግሥተ ሰማያት የተዘጋጀን ያድርገን ለዘላለሙ አሜን።

=>ግንቦት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አርዋ እናታችን
2.ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ዲማዲስ ሰማዕት
4.አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ
3.አባ ሣሉሲ ክቡር
4.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
5.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

=>+"+ መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ:: ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው::
እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥረዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት:: +"+ (ምሳሌ. 31፥29)

፨፨፨፨
ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።
ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
፨፨፨፨

( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

የግንቦት ወር ስንክሳር ተፈፀመ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

06 Jun, 10:06


ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

04 Jun, 20:31


ወንድማችን እንኳን ደሕና መጣሕ ምን ሖኑ አባታችን 🥲🥲🥲 ኑእስኪ ተወዳጆች ሊንኩን ነክተን እንግባ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

04 Jun, 14:54


https://youtu.be/Rhbcf4MOGjo?feature=shared

አርከለዲስ | Arkeledis Media

03 Jun, 14:36


*አቡነ_ሀብተ_ማርያም* ፡- አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ዮስቴና የሚባሉ በሕገ እግዚአብሔር፣ በሃይማኖት፣ በትሩፋትና በምግባር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፣ ልደታቸው ግንቦት 26፣ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡
አቡነ ሀብተማርያም ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነሱም፡-

*1/ መብረቅ፣*
*2/ ቸነፈር፣*
*3/ ረሃብ፣*
*4/ ወረርሽኝ፣*
*5/ የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡*

አቡነ ሀብተ ማርያምን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ‹‹አምስት መቅሰፍታት እንዲጠፉ በደጄ በደብረ ሊባኖስ ተቀበርልኝ›› ብለው የለመኗቸው ታላቅ አባት ናቸው ይህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለነበር ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በጻድቁ መቃብር ቅዱስ አጽማቸው አርፏል፡፡

የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከተ ረድኤት ምልጃቸው ከሁላችን ጋር ይሁን።

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

03 Jun, 14:31


ፎቶ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

02 Jun, 09:47


ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

01 Jun, 19:23


📌 ያልተሰጠህን አትሻ

❖ የተሰጠህን ጸጋ እንዳታጣ ያልተሰጠህን አትሻ፤ ወደ ጸጋ ወደ ክብር ለመድረስ እግዚአብሔር ቢያበቃህ ያሳየህን እይ ያላሰየህን አያለሁ አትበል፤ አንድም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፣ በተሰጠህ ጸጋ ለእግዚአብሔር ተገዛ፤ ማር አብዝቶ መመገብ እንዳይመች እንደዚህም ሁሉ ያልተሰጠውን መሻት አይገባም አያስመስግንም፡፡

❖ ነፍስ ያልተሰጣትን ጸጋ በመሻት እንዳትደክም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፤ የምታየው ማየት ቢኖር እውነተኛውን ምትሐት ሆኖ ታየዋለህ ፤ ሕሊና ያልሰጡትን ጸጋ በመሻት በማውጣት፣ በማውረድ የተሰጠውን ያጣል፡፡

❖ ሰሎሞን መልካም ነገር ተናገረ ‹‹በሰጡት ጸጋ የማይኖር ሰው ቅጽር የሌላትን አገር ይመስላል›› ብሎ ያን ማንም እየገባ እንዲዘረፈው እሱም የተሰጠውን ጸጋ ያጣል ፤ አንተ ብሩህ አእምሮ ሰውነትህን ያልተሰጣትን ጸጋ እንዳትሻ ከልክላት፡፡

❖ ከቁመተ ሥጋ የወጣ አብዝቶ መገበርን ከአንተ አርቅ ያልተሰጠህን መሻት ከአንተ አርቅ፤ ባልተሰጠህና በተሰጠህ ጸጋ መካከል ትሕትናህን፣ ንጽሕናህን መጋረጃ አርጋቸው፤ አንድም በተሰጠህ ጸጋ ላይ ያልተሰጠህን ጋርደው በንጽሕና፣ በትሕትና፣ በልቡናህ የምታስበውን መንፈሳዊ ክብር ታገኛለህ።

📌ምንጭ
📚ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

01 Jun, 06:52


*ጻድቁ አባታችን ተክልዬ*

✝️ ‹ *ተክል› ማለት ፍሬያማ ዕንጨት፣ ዛፍ፣ ቅመም፣ ቅጠላ ቅጠል፣ የሚበላ፣ የሚሸተት፣ ገነታዊ ዕፅ፣ እንዲሁም ሕግ ሥርዓት ማለት ነው /* ማቴ.፲፭፥፲፫/፡፡

✝️‹ *ሃይማኖት› ማለት ደግሞ በሀልዎተ እግዚአብሔር፣ እግዚአብሔር የዅሉ አስገኚ መኾኑን፣ በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት፣ በቅዱሳን ተራዳኢነት ማመን አምኖም መመስከር ማለት ሲኾን ተክለ ሃይማኖት የሚለው ሐረግም የሃይማኖት ተክል፣ ይኸውም የጽድቅ ፍሬን ያፈራ፣ ከኃጢአት ሐሩር ማምለጫ ዛፍ፣ ምእመናንን በቃለ ወንጌል ያጣፈጠ ቅመም፣ መዓዛ ሕይወቱ የሚማርክ፣ ቢመገቡት ረኃበ ነፍስን የሚያስወግድ ቅጠል፣ የጻድቃን መጠለያ ዕፅ የሚል ትርጕም አለው፡፡*

✝️ *ገድለ ተክለ ሃይማኖትም ‹‹ተክለ ሃይማኖት ማለት የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ተክል ማለት ነው›› ሲል የጻድቁን ስም ይተረጕመዋል፡*
  ✝️ *ጻድቁ አባታችን ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው፣ ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና በመኖራቸው፤ እርሳቸው በአሚነ ሥላሴ ጸንተው ሌሎችንም እንዲጸኑና እንዲያምኑ በማድረጋቸው፤ እንደዚሁም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ በመስበክ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሰባኬ ወንጌል በመኾናቸው ‹‹ተክለ ሃይማኖት›› ተብለው ይጠራሉ።*

✝️ *ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ከፍጹም ቅድስናቸው የተነሳ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ጋር በአንድ ቆመው መንበረ ሥላሴን አጥነዋል ቅድስት ሥላሴን አመስግነዋል። ገድላቸው ይህን ድንቅ ሥራ እንዲህ ይመሰክራል። ከዚህ በኋላ መልአኩ ወደ ሰማይ አውጥቶ ከመጋረጃው ውስጥ አስገብቶ ከሥላሴ ዙፋን ፊት አቆመኝና ሰገድኩለት፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በማላውቀው በሌላ ምስጋና አመሰገንኩት፡፡ ‹ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከ24ቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን› የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ፡፡*

✝️ *የወርቅ ጽናም አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር አንድነት አጠንሁ፡፡ ምስጋናዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደልብሳቸው ሆነ፡፡ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት፡፡*

✝️ *በጸሎትህ የሚታመን ሰው ሁሉ ስለአንተ ይድናል አለኝ…..›› (ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገጽ 216-223)**

✝️ *እንደዚህ ባለ ቅድስና የኖሩ አባታችን ጻድቁ ተክለሃይማኖትን ዛሬም በዕለተ ቀናቸው ወደ ቅድስት ሥላሴ እንዲለምኑልን እንዲያማልዱን አጥብቀን ልንማጸናቸው ይገባል። ይልቁንም እንዲህ ባለ  በመታሰቢያቸው ዕለት ስማቸውን ጠርቶ፣ በስማቸው መጽውቶ፣ በመቅደሳቸው ተገኝቶ፤ አባባ ተክለሃይማኖት ከቅድስት ሥላሴ አማልዱኝ ብሎ መማጸን የሚያስገኘው ዋጋ ታላቅ መሆኑን በመረዳት ልንተጋ ይገባል።*
 
✝️ *የጻድቁ አባታችን የተክለ ሃይማኖት እና የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በረከት በየቤታችን ይግባ።*

     ✝️ *ብሩህ ቀን* ✝️

አርከለዲስ | Arkeledis Media

30 May, 17:51


ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

30 May, 10:45


ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ

አርከለዲስ | Arkeledis Media

29 May, 07:07


ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ

1,288

subscribers

292

photos

13

videos