ተከሳሽ የኔው ብርሀኑ የእንጅባራ ከተማ አሰተዳደር ነዋሪ ሲሆን በጥቅምት 19/ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6.30 ሰዓት ከቢዳ ጀጎላ ት/ቤት የሚማረውን ወንድሙን ስልክ በመደወል የእናታችንን ልብስ ውሰድ ብሎ ከት/ቤት ከአሰወጣ በኋላ የ14 ዓመት ወንድሙን በማገት ከወላጅ ቤተሰቦቹ 1,000,000/አንድ ሚሊዮን ብር/ መጠየቁን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
በሁኔታው የተደናገጡት የታጋች ቤተሰቦች ወዲያውኑ ለእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ በሰጡት ጥቆማ በተደረገ ብርቱ ክትትልና ቁጥጥር በሶስተኛው ቀን ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ሲሆን ከተደበቀበት ቢዳጀጎላ ቀበሌ ልዩ ስፍራ አማያስቲ ጎጥ ላይ እጅ ከፍንጅ ተይዟል።
ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል የላከ ሲሆን መዝገቡ የቀረበለት የአዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ የኔው ብርሃኑ በ7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዋና ክፍል የተገኘው መረጃ ያሳያል።
አዩዘሀበሻ
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
http://t.me/ayuzehabeshanews
http://t.me/ayuzehabeshanews