Addis Maleda - አዲስ ማለዳ @addismaleda Channel on Telegram

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

@addismaleda


ዜና ከምንጩ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ (Amharic)

አዲስ ማለዳ ላይ የተገኘ በርካታ የኢትዮጵያ ዜና ከምንጩ እንዲደርስላችሁ እናመሰግናለን! አዲስ ማለዳ የሚሆነው ሰዎችን ስለ ዜናው የሚመልሳቸውን አስታወሱ። ዜና ከምንጩ የተገኙትን እናቅርብሽ የሚችሉትን ከቀይ ዜና በቀና አምልኮ ያዋለዋል። አዲስ ማለዳ፣ እንዴት በታዘዝከሃለው ቅንጅት ልዩነትን ከሚጠቀሙት አዜብ አንድ የፖዚሽን እቃዎች እንጂ ሩተውም ስለ ፈጣሪው ነው። ስለዚህ አዲስ ማለዳ በአርትቶ ውስጥ በየትኛውም ከነቂይና በፍጹም ደረጃ ሰውን የማሳዩዋ ምሳሌ እንዲሁም በአማርኛ የሚደረግበት በርካታ ዜናውን ዋጋ ያድርጉት ማወቅ የምንችልበት ምክር ነው። ከማኑኤል ሳናቹም ያለ ፖዚሽን ምስል፣ ከኖር፣ ከጆሮ ያለ ዜና ስትራዘፍ፥ የሚደክም እንደደም ስለኳችን ከአዲስ ማለዳ ዋጋ ያድርጉት በመሆኑ ሆኖም ካልተጫነሽ እምቢ እንቅስቃሴ አንድ የሚሳል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Feb, 10:31


ምክር ቤቱ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን ለአንድ ዓመት አራዘመ

ማክሰኞ የካቲት 11 ቀን 2017(#አዲስ_ማለዳ)

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን ለአንድ አመት አራዝሟል።

የኮሚሽኑን የስራ ዘመን ለማራዘም የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ፤ በሶስት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ በአብላጫ ጽምጽ ጸድቋል።

መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለተፈጠሩ ልዩነቶች “ወሳኝ ምክንያቶችን የመለየት” እና ውይይቶች የሚካሄዱባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች በመለየት “ምክክር እንዲደረግባቸው የማመቻቸት” ዓላማ ይዞ የተቋቋመው ኮሚሽኑ፤ በአዋጅ የተቀመጠለት የስራ ዘመን ሶስት ዓመት እንደነበር ይታወቃል።

ፓርላማው ኮሚሽኑ ለተጨማሪ አንድ ዓመት በስራ ላይ እንዲቆይ ውሳኔ ከማሳለፉ አስቀድሞ፤ የተቋሙን የሶስት ዓመታት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል።

ሪፖርቱን ለፓርላማ አባላት በንባብ ያቀረቡት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፤ ኮሚሽኑ በዚህ ጊዜ ውስጥ የምክክር፣ የአጀንዳ መለየት እና ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ስራዎችን በ10 ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።

አባላቱ ኮሚሽኑ በተሰጠው ተጨማሪ የስራ ዘመን ተጠባቂ ቀሪ ስራዎችን እንዲያጠናቅቅ ጠይቀዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Feb, 09:06


ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበት ቀንሷል ቢልም ተቃራኒ ሪፖርት መውጣቱ ተገለጸ

ማክሰኞ የካቲት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ባወጣው የእስታትስቲክስ ሪፖርት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ይህም በባለፈው አመት ጥር ወር ከነበረበት 29.4 በመቶ ወደ 15.5 በመቶ ዝቅ ያለ ሲሆን ይህም 13.9 በመቶ ማሽቆልቆሉን የሚያመለክት መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡

እንዲሁም የምግብ ግሽበት በ16.6 በመቶ እና በምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት በ10.2 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል።

ይሁን እንጂ ትሬዲን ኢኮኖሚክስ ተደረገ ባለው ጥናት ከብሄራዊ ባንክ ሪፖርት ጋር ተቃራኒ የሆነ ቁጥር መመዝገቡን ገልጿል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ አመታዊ የዋጋ ግሽፈት 17 በመቶ እንደሆነ ያስታወቀ ሲሆን የብሄራዊ ባንክ ካወጣው ቁጥር ጭማሪ የሚያሳይ ነው፡፡

ሁለቱም ሪፖርቶች የቁጥር ልዩነት ቢኖራቸውም የዋጋ ግሽበት እንደ አጠቃላይ ከነበረበት መቀነሱን አመላክተዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Feb, 08:30


ምክር ቤቱ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ አፈፃፀምን እያዳመጠ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ማክሰኞ የካቲት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ አፈፃፀምን አያዳመጠ ይገኛል።

የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የሀገራዊ የምክክክር ኮሚሽኑ ባለፉት ሶስት አመታት ያከናወናቸው ተግባራት እንደሚቀርቡ እና ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ አስረድተዋል።

ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ምክር ቤቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ በስፋት ተወያይቶ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን “የስራ ዘመን ያራዝማል” ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በታህሳስ 2014 ዓ.ም የጸደቀው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ፤ የኮሚሽኑ የስራ ዘመን ሶስት ዓመት እንደሆነ ይደነግጋል።

የኮሚሽኑ የስራ ዘመን የሚቆጠረው፤ በአዋጁ መሰረት የሚመረጡ ኮሚሽነሮች በፓርላማ ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ በድንጋጌው ላይ ሰፍሯል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በዕጩነት የቀረቡ 11 ኮሚሽነሮችን ሹመት ያጸደቀው የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ነበር።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Feb, 08:15


“የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዳናካሂድ መከልከላችን የገዢ ፓርቲውን አንባገነንነት ያሳያል” - ኢሕአፓ

ማክሰኞ የካቲት 11 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ የካቲት 9 እና 10 2017 ዓ.ም የማዕከላዊ ኮሚቴውን ስብሰባ በሆቴል ለማካሄድ የተያዘው ፕሮግራም በገዢው ፓርቲ ሹማማንት ተከልክሎብናል ብሏል፡፡ በመሆኑም በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት አዳራሽ ስብሰባውን ማስቀጠሉን የገለጸ ሲሆን የተወያየባቸውን የአቋም መግለጫ አስፍሯል፡፡

የኢሕአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የፓርቲው የ6 ወራት የሥራ ሪፖርት በማድመጥና በመወያየት፣ በተለያዩ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ፣ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በህብረትና በትብብር ለመስራት የሚያስችል ሰነድን መርምሮ በማፅደቅ፣ የተጓደሉ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በመምረጥ መጠናቀቁን ገልጿል።

ፓርቲው በአማራ፤ በኦሮሚያ ፤ በቤንሻጉል ጉሙዝ ፤ በጋምቤላ፣ በደቡብ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታየው የሰላም እጦት መቋጫ ሊበጅለት ይገባል ብሏል፡፡

በመግለጫው መንግሥት የህግ የበላይነትን የማክበር፣ የማስከበርና፣ የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ ፓርቲው በአጽንዖት አሳስቧል፡፡

“ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ምህዳሩ ከመጥበቡ የተነሳ እስር ፤ እንግልት፣ከስራ የመፈናቀል፣ ከፍ ሲልም ግድያ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ ሲገደዱ እያስተዋለ” መሆኑን ፓርቲው ኮንኗል፡፡

“ከዚህ አንጻር ገዢው ፓርቲ እጁን በማስረዘም የፓርቲዎችን እንቅስቃሴ በኃይል መጨፍለቁን እንዲያቆምና የተረጋጋ የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጠር ሕገመንግስታዊ ግዴታውን ይወጣ” ብሏል፡፡

“የገዢው ፓርቲ ሹማማንት የፓርቲዎችን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማኮላሸትና መሪዎቻቸውን ለማሸማቀቅ የሚያደርጉትን ጥረት አጥብቀን እናወግዛለን” ሲል ፓርቲው አስታውቋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Feb, 06:44


#አዲስ ማለዳ_ማስታወቂያ

ሶስት ቀን ብቻ ቀረ!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 9ኛው የጤና ኤግዚቢሽን እና ዓለምአቀፍ ኮንግረስ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ሊከፈት ሶስት ቀናት ብቻ ቀርተዋል፡፡ ከየካቲት 13 – 15 በሚደረገው ሁነት በጤና እና ህክምናው ዘርፍ ዓለም የደረሰችበትን ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሰራር ይመለከታሉ፣ የመድሃኒት አቅርቦት እና አሰራር የደረሰበትን ያያሉ፤ እርሶ ብቻ እንዳይቀሩ! ብዙ ነገር ይቀስማሉ፣ የንግድ እና የሥራ ግንኙነቶችን ለማዳበርም ሁነኛ አጋጣሚ ነው፡፡

ምን እሱ በብቻ!

አሉ የተባሉ የጤና እና ህክምና ባለሙያዎች በዘርፉ ያሉ አዳዲስ አሰራሮችን እና አገልግሎቶችን፣ እንደዚሁም የቴክኖሎጂ ግኝቶች እና ተሞክሮዎችን የሚያካፍሉበት እና ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተሳታፊዎች የሚሳተፉበት ዓለምአቀፍ ኮንግረስም ተዘጋጅቷል፡፡

ይምጡ!

• አዳዲስ የንግድ እድሎችን እና የሥራ ግንኙነቶችን መሥርተው ይሄዳሉ!
• ለህክምና ማዕከልዎ አስተማማኝ እና ደረጃቸውን የጠበቁ አቅራቢዎችን ይተዋወቃሉ!
• አዳዲስ እና ዘመናዊ አሰራሮች አይተው ተቋምዎትን ለማሳደግ ይጠቀሙበታል!
• የገበያ አድማስዎን ለማስፋት ሊከተሉት ስለሚገባ ስትራቴጂ እና ዘመናዊ አሰራር ተሞክሮ ይቀስሙበታል!

ይህ መልካም አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ ፈጥነው ይመዝገቡ! ይህን ሁሉ ሸምተው ምንም ክፍያ አይከፍሉም!

https://bit.ly/ethio-health-registration

ለበለጠ መረጃ
+251929 30 83 63/64
www.ethio-health.com

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Feb, 13:43


የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊዬነር አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የምዋዕለንዋይ ፍሰት በእጥፍ እንደሚያሳድጉ አስታወቁ

አዲስ ማለዳ - የካቲት 09፣ 2017 – የአፍሪካ ግንባር ቀደም ባለሃት ናይጄሪያዊው ቱጃር አሊኮ ዳንጎቴ፣ በኢትዮጵያ ያላቸው የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ ማስፋፊያ እንደሚሰሩ አስታወቁ። በማስፋፊያው በኦሮሚያ ክልል ሙገር የሚገኘው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ የማምረት አቅሙን በእጥፍ በማሳደግ በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ እንደሚያመርት ተነግሯል፡፡ በለሃብቱ በስኳር እና ማደባሪያ ዘርፍ ያካበቱትን ልምድ መሠረት በማድረግ በዘርፉ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንቶች ላይ እንደሚሳተፉም አስታውቀዋል፡፡

የዳንጎቴ ግሩፕ ሊቀመንበር እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አሊኮ ዳንጎቴ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ጋር በመሆን በሰጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ በሚኖረኝ ጉብኝት ሁሌም ደስተኛ ነኝ። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባደረግኩት ጉብኝት እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበረኝ ውይይት፣ በሃገሪቱ እየታዩ ያሉ ለውጦች ስላበረታቱኝ ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት ተነሳስቻለሁ ብለዋል።

“ውጣ ውረዶች ቢያጋጥመንም በሲሚንቶ ላይ ባደገነው ኢንቨስትመንት በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡” ፋብሪካውን ለመገንባት የተበደርነውን ብድር ሙሉ ለሙሉ የመለስን ከመሆኑም ባሻገር፣ ሰርተን ያተረፍነውን ትርፍም ሙሉ ለሙሉ በተሳካ ሁኔታ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡

አሊኮ ዳንጎቴ በአፍሪካ ውስጥ ካሉት ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውን ‘የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ’ን በሃገራቸው ሥራ ካስጀመሩ በኋላ ትልልቅ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለማቆም አቅደው ነበር። ሆኖም የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱ አመለከታቸውን እንደለወጠው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ የዳንጎቴ ግሩፕ ያቀዳቸውን የማስፋፊያ እና አዳዲስ እንቨስትመንቶችን በደስታ መቀበላቸውን ተናግረው ኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ እድገትን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡ “ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለኢንቨስትመንት እና ለስራ እድል ፈጠራ ቅድሚያ የሚሰጥ የኢኮኖሚ ለውጥ እያስመዘገበች ነው። ይህን ተከትሎ ዳንጎቴ ግሩፕ በሃገራችን አሻራውን ሲያሰፋ በማየታችን ተደስተናል፤ ይህ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ የንግድ ከባቢ ላይ የመተማመን ምልክት ሲሆን ለመሰረተ ልማት እና ለኢኮኖሚ እድገታችን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ይኖረዋል” ብለዋል።

ዳንጎቴ ግሩፕ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገሮች ግዙፍ አምራች ኢንዲስትሪዎችን በማስፋፋት ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያም 2.5 ሚሊዮን ቶን የሚያመርት የሲሚንቶ ፋብሪካ ከአስር አመት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያ ደሳለኝ አስመርቆ ሥራ ላይ ያዋለ ሲሆን በወቅቱ በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ገበያን ያረጋጋ ኢንቨስትመንት ነበር፡፡ ፋብሪካው በኦሮሚያ በተቀጣጠለው ግጭት ምክንያት በሥራው ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል የደረሰበት ከመሆን አልፎ ህንዳዊው የድርጅቱ አስኪያጅ እና ሁለት ሰራተኞቹም ግንቦት 2009 ከአማፂዎች በተተኮሰ ጥይት የተገደሉበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ያለው ትርፍ በውጭ ምንዛሬ ለማስወጣት ከገጠመው ችግር አንፃር የኩባንየው በኢትዮጵያ የሚኖረው ቆይታ ላይ አጠራጣሪ ሆኔታ ተፈጥሮ ነበር፡፡ እነዚህ ችግሮች ሁሉ አልፈው አሁን ላይ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ ባደረጉት ኢንቨስትመንት በጣም ደሥተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡

በተለይ በቅርቡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት እና አጠቃላይ የሃገሪቱ የኢንቨስትመንት ከባቢ ላይ ባዩት ተስፋ፣ ሙገር በሚገኘው የሲሚንቶ ፋብሪካቸው ላይ ከፍተኛ የማስፋፊያ ሥራ እንደሚያደርጉ እና የፋብሪካውን የማምረት አቅም በዕጥፍ በማሳደግ በአመት ወደ አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚኒቶ እንደሚያመርቱ ተናግረዋል። በተጨመሪም በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ ውስጥ አዳዲስ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው እና የኦሞ ኩራዝ ስኳር ኩባንያ እንደሚያለሙ ተነግሯል። የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዳው የሀገሪቱ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ከተፈጠረ በኋላ በኢትዮጵያ የዩሪያ ማምረቻ ፋብሪካ ለመትከልም እቅድ እንዳላቸው ተናግረወል።

ዳንጎቴ የአፍሪካን እድገት ለመምራት “የአፍሪካ የንግድ መሪዎች” ያላቸው ሚና ላይ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ “አፍሪካ የምትለማው በአፍሪካውያን ነው። የፖለቲካ መሪዎቻችን የአፍሪካ ህብረትን ለማጠናከር በሚሰሩበት ወቅት፣ እኛ ደግም የንግድ መሪዎች እንደመሆናችን በአህጉሪቱ ያለውን የንግድ ትስስራችንን በማጠናከር ጥረታቸውን መደገፍ አለብን” ብለዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Feb, 17:47


የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነው ተመረጡ

ቅዳሜ የካቲት 8 ቀን 2017 ( አዲስ ማለዳ) ጅቡቲን ለበርካታ ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ ቀጣዩ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነው ተመርጠዋል።

ኮሚሽኑን እንዲመሩ በሊቀመንበርነት የተመረጡት የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተካሔደውና ብርቱ ፉክክር በታየበት፣ እንዲኹም እስከ ሰባተኛ ዙር ድረስ በዘለቀ ምርጫ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ በማግኘት ነው።

ከሳምንት በፊት 60ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ያከበሩት ዩሱፍ፣ የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን በማሸነፍ ኮሚሽኑን በቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

አዲሱ የኅብረቱ ተመራጭ ከአውሮፓውያን 2005 ጀምሮ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ በአፍሪካ አህጉር ለረጅም ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የገለገሉም ናቸው።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Feb, 07:52


"ቦርዱ ከፌዴራል መንግስት ጋር የጀመርነውን ተከታታይ ውይይት ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን" - ህወሓት

ቅዳሜ የካቲት 08 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)  በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ( ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምርጫ ቦርድ ላስተላለፈበት እግድ ምላሽ የሰጠ ሲሆን "ቦርዱ ከፌዴራል መንግስት ጋር የጀመርነውን ተከታታይ ውይይት ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን" ብሏል።

ከተመሰረተ ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረ አንጋፋ ፓርቲ መሆኑን የገለፀው ህወሓት  በመግለጫው " ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካዋ የፕሪቶሪያ ከተማ የሰላም ውል ከተፈራረመ ጀምሮ ህጋዊነቴ የተመለሰ ነው " ብሏል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት ከነሃሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ህወሓትን በአዲስ ህግ እንደ አዲስ ፓርቲ " መዝግቤዋለሁ ማለቱን " አስገራሚ እና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ፓርቲው አስታውቋል፡፡

"የምርጫ ቦርድ አካሄድ በመሰረቱ ተቀባይነት የሌለው ፤ ህግን መሰረት ያላደረገ ፣ትርጉም አልባ ውሳኔ ነው" ብሎታል።

"ህወሓት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ተሰጥቶ የሰላም ውል የፈረመ ፓርቲ ነው " ያለው ህወሓት ፤ " ከኢፌዴሪ መንግስት ተከታታይ የፓለቲካ ውይይት በማካሄድ ላይ በመሆኑ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰላማዊ ውይይቱን ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ " ሲል አቋሙን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት 6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ ይጠበቅበት የነበር  ቢሆንም ይህንን ባለማድረጉ ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲታገድ ፤ በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Feb, 14:29


ምርጫ ቦርድ ሕ.ወ.ሓ.ትን አገደ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ምንም አይት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ እግድ ጣለ፡፡ በነዚህ የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንደሚሰረዝም አስታውቋል።

ሕ.ወ.ሓ.ት በሽብር እንቅስቃሴ ተሳትፏል በሚል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሸባሪነት ዝርዝርዝር ውስጥ ከተመዘገበ እና ህጋዊ ህልውናውን ካጣ በኋላ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት በልዩ ሁኔታ ነሃሴ 3 2016 ዓ.ም የተመዘገበ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ህጋዊ ሆኖ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት ሥድስት ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ ይጠበቅበት የነበረ ቢሆንም፣ ቦርዱ እውቅና የሰጠው እና በታዛቢነት የተሳተፈበት ጉባዔ ሳያደርግ ቀርቷል።

በመሆኑም ቦርዱ፥ ታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ የማድረጊያ ጊዜ ገደቡ ሊጠናቀቅ ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ አንደቀረው በመግለጽ በሕግ የተጣለበትን ግዴታ አንዲፈጽም ማሳሰቡን አስታውሷል።

ይህንን የሕግ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈጽም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሣኔ የሚሰጥ መሆኑን መግለጹንም አክሏል።

ይሁንና ፓርቲው የፓርቲው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ዐዋጁን ተከትሎ የወጣውን መመሪያ እና ደንጋጌዎች፣ እንደዚሁም የቦርዱን ውሣኔዎች በማክበር የጠቅላላ ጉባዔ ሳያካሄድ፣ መተዳደሪያ ደንቡን ሳያፀድቅ እና አመራሮቹን ሳይመርጥ በሕግ የተሰጠው የሥድስት ወር ጊዜ ተጠናቅቋል።

በዚህ መሠረት ቦርዱ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ የሕ.ወ.ሓ.ትን ጉዳይ መርምሮ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፦
1ኛ. ፓርቲው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ እና ዐዋጁን ተከትሎ የወጣውን መመሪያ ላይ የተመለከቱ ድንጋጌዎችን ባለማክበር ጉልህ ጥሠት በመፈጸሙ ይህ ውሣኔ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ለሦስት ወራት በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ እንዲታገድ ወሥኗል።

2ኛ. ፓርቲው ለእግዱ ምክንያት የሆነውን ጥሠት በማረም፤ ዐዋጁን፣ ዐዋጁን ተከትሎ የወጣውን መመሪያ፣ የቦርዱን ውሣኔዎችና ትዕዛዞች በማክበር ፖርቲው ሊያደርግ የሚገባውን ጠቅላለ ጉባዔ ለማድረግ የሚያስችለውን የጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለመሥራት ለቦርዱ በጽሑፍ ሲያሳውቅና ቦርዱ ይህንኑ ሲያረጋግጥ በመመሪያው መሠረት ቦርዱ ዕግዱን የሚያነሣ መሆኑን ወሥኗል።

3ኛ. ፖርቲው በተሰጠው የሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የተለየ አካሄድ ሳይከተል የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ወሥኗል።

ሃምሳኛ ዓመቱን የምሥረታ በዓል ለማክበር በተዘጋጀበት ዋዜማ ላይ የሚገኘው እና እንዲህ አይነት ውሳኔ የተላለፈበት ሕ.ወ.ሓ.ት ኢትዮጵያን ለ27 አመታት ያስተዳደረ እና በድርጅታዊ ጥንካሬው እንደዚሁም ጥብቅ የአባላት ሥነምግባር የሚታወቅ ሲሆን፣ የረጅም ጊዜ ሊቀመንበር ከሆኑት መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ የሚታወቅበትን ድርጅታዊ ማንነት እና ቁመና አጥቶ አንደሚገኝ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፓርቲው የገባበት ክፍፍል ዐቢይ ማሳያ ነው፡፡

ደም አፋሳሽ የነበረው የተግራይ ጦርነት አልፎ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በፕሪቶሪያ የሠላም ሥምምነት ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ህይወት የቀጠፈው ጦርነት የተቋጨ ቢሆንም፣ በፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ መካከል የተፈጠረው ፍጥጫ ፓርቲውን በታሪኩ አይቶ ወደማያውቀው ቀውስ እየወሰደው እንደሆነ ይታወቃል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Feb, 14:19


ሁሉንም የፋይዳ አገልግሎቶች አጠቃሎ የያዘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ፡፡

ሐሙስ የካቲት 06 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)፡ ሁሉንም የፋይዳ መታወቂያ አገልግሎቶች አጠቃሎ የያዘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ፡፡ መተግበሪያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት (ፋይዳ) አገልግት ውጤታማነት እና አግባብነትን በፍጥነት ለመከታተል ይረዳል ተብሏል።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የፕሮጀክቱ ዋና መስሪያ ቤት ይፋ የሆነው ይህ መተግበሪያ የምዝገባ መረጃን ለማረጋገጥ ያለኢንተርኔት ግንኙነት ጭምር ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ መተግበሪያ አጠቃሎ የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ የተያዘውን የዲጂታል መታወቂያ አሰጣጥ አገልግሎት ለማቀላጠፍ እና ለማስፋት ያስችላል ተብሏል።

ተጠቃሚዎች የጠፉ ወይም ያልታደሱ የፋይዳ መለያ ቁጥሮችን ማግኘት እና የዲጂታል መለያቸውን በቀጥታ በመተግበሪያው በኩል ለማውረድ መተግበሪያው ያስችላል ተብሏል። በተጨማሪም ነዋሪዎች የሕዝብ ቆጠራ ስህተቶችን ለማረም እንዲሁም እንደ አድራሻ ወይም ኢ-ሜይል ያሉ የግል መረጃዎችን በስልክ እንዲያሻሽሉ እድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።

በተጨማሪም ግለሰቦች ተመዝጋቢ ከሆኑ በኋላ የፋይዳ መታወቂያ ካርዳቸውን የታተመ ኮፒ መጠየቅ እንዲችሉ እና ለደንበኞች ምቹ የአስተያየት መስጫ አሰራሮችንም እንዳካተተ በመግለጫው ተነግሯል፡፡
ብዙ ተስፋ የተጣለበት የዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ እየተደረገለት የተጀመረ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ በመላ ሃገሪቱ 12,215,891 ዜጎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ የወንድ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከአጠቃላዩ 34.8% ሲሆን የሴቶች ደግሞ ከ65% በላይ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። ይሁን እንጂ በቀጣዩ ዓመት ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ወደ 90 ሚሊዮን ለማሳደግ እቅድ እንደተያዘ አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ በርካታ ጥቅሞች ይሰጣሉ፡፡ የወረቀት ሥራዎችንና የአስተዳደር ወጪዎችን በመቀነስ የሕዝብ አገልግሎቶችን ያቀለጣጥፋሉ። የማጭበርበር ድርጊትንና የማንነት ስርቆትን በመዋጋት የግል እና የጋራ ደህንነትን ያጎለብታል። የዲጂታል የገንዘብ አገልግሎቶችን ማግኘት በማስቻል የገንዘብ አጠቃቀም እንዲጨምር እንደሚያደርግ የተለያዩ ሃገሮች ተሞክሮ ያሳያል።

በተጨማሪም ዜጎች በተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎችን የሚፈጥርላቸው ከመሆኑም ባሻገር የንግድ ልውውጦችን ቀላል በማድረግ እና ኢንቨስትመንትን እና የፋይናንስ ተደራሽነትን በማስፋት እና በማቀለጣጠፍ አጠቃላይ ምጣኔ ሃብታዊ እድገትን ያፋጥናሉ ተብሎ በባለሙያዎች ይነገራል። ከዚህም በላይ መንግሥት እቅድ፣ ፖሊሲ እና በጀት ለማዘጋጀት የሚያስፈልገውን የተሟላ የዜጎች መረጃ በቀላሉ እንዲያገኝ ይረዳሉ ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Feb, 14:16


ኢትዮ ቴሌኮም ስድስት ወር ውስጥ ከ60 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘሁ አለ::

ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ በጀት ዓመቱ 61.9 ቢሊዮን ብር ገቢ በማስገኘት የእቅዱን 90.7በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ይህን ያስታወቀው የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አሰፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ከአለም አቀፍ አገልግሎት የተገኘ ገቢ 64.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማስገባት የእቅዱን 63.8በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል ፡፡

ባለፉት ስድስት ወራትም 3.24 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞች በማፍራት አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ብዛት 80.5 ሚሊዮን መድረሱን ገልፀው ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ5.9 ሚሊዮን እድገት ማሳየቱን ገልፀዋል።

በአገልግሎት አይነት ሲታይ የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 77.7 ሚሊዮን፣ የሞባይል ዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 43.5 ሚሊዮን አዲስ ማለዳ ከኢትዮ ቴሌኮም የሥራ ኃላፊዎች ሰምታለች።

ኢትዮ ቴሌኮም የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች እና የአቅርቦት እጥረት በስድስት ወር ውስጥ ያጋጠሙኝ ተግዳሮቶች ናቸው ሲል ገልጿል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Feb, 14:14


ከስልሳ በላይ አለማቀፍ የጤና ድርጅቶች የሚሳተፉበት አውደርዕይ ሊካሄድ ነው፡፡

በጤና እንክብካቤ በህክምና መገልገያዎችና መድሃኒት የእሴት ሰንሰለት እና የዲጂታል ኸልዝ ላይ ትኩረት የሚያደርገው 9ኛው ኢትዮ ኸልዝ አውደርዕይ እና ጉባኤ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው 4ኛው አለም አቀፉ የመድሃኒት አቅራቢዎች ጉባዔን ያካተተው ይህ አውደርዕይ ከየካቲት 13 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ የሁነቱ አዘጋጅ ፕራና ኤቨንትስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡
ይህ ልዩ ዓውደ ርዕይ እና ጉባኤ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አቅራቢዎችን በሃገር ውስጥ በማስተዋወቅ፣ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግርን በማምጣት ለዘርፉ ልማት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቁልፍ መድረክ ነው ተብሏል፡፡

በመሆኑም የህክምና አገልግሎት ፍላጎትን ለማሳካት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂ እና መፍትሄዎችን የሚያቀርቡ ከአስር በላይ ከውጭ ሀገራት የተውጣጡ በድምሩ ከስልሳ በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን ከ4 ሺህ በላይ ጎብኚዎችን እና ከ 2 ሺህ በላይ የኮንፍረንስ ተሳታፊዎችን ለማስተናገድ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከአዘጋጆቹ ሰምታለች።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Feb, 14:11


"ለባርነት ጨረታ" ቀርባ የነበረችው ኢትዮጵያዊት 700 ሺህ ብር ተከፍሎ ነጻ መውጣቷን ተናገረች::

ዓርብ ጥር 23 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሊቢያ "ለባርነት ጨረታ ቀርባ" የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ነሒማ ጀማል ለአጋቾቿ 700 ሺህ ብር ተከፍሎ ነጻ መውጣቷን ተናገረች።

በፎቶዎች እና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታይ የነበረችው ነሒማ በቤተሰቧ አማካይነት ገንዘብ ከኢትዮጵያ ተሰባስቦ ከተላከ በኋላ ከሁለት ቀናት በፊት አጋቾቿ ወደ ከተማ አምጥተው እንደለቀቋቸው አስረድታለች።

ታግታ ከነበረችበት ስፍራ እሷን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ቢኖሩም የተለቀቁት ገንዘብ የተከፈለላቸው "ውስን ሰዎች ነበሩ" ማለቷን ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ ገልጻለች፡፡

እንዱሁም በአሁኑ ወቅት በሊቢያ እንደምትገኛና "ከዚህ በኋላ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም" ስትል ጭንቀት ላይ እንደሆነች ተናግራለች።

ተማሪ የነበረችው ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ፣ በአዲስ አበባ በኩል ወደ በጎንደር በማምራት ከኢትዮጵያ በመውጣት ነበር ስራ አለ ተብላ ወደ ሊቢያ ያቀናችው።

አዲስ አበባ የተዋወቃቻቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን ወንዶች በሰሃራ በረሃ በውሃ ጥም ሕይወታቸው አልፏል ብላለች።

ለሌሎች ስደትን አማራጭ ለሚያደርጉ "አገራቸው ውስጥ ቢቀመጡ ይሻላቸዋል፣ መንገድ ላይ በሽታ አለ፣ ሞት አለ፤ ብዙ ጓደኞቼ መንገድ ላይ ሞተዋል" ስትል መክራለች።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

01 Feb, 06:52


አብን በቀጣዩ ምርጫ የመሳተፍ አቅም አይኖረውም-አባላቱ

ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) 300 የሚደርሱ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹ በሥራ ላይ ባለመኾናቸው በቀጣዩ ጠቅላላ ምርጫ የመሳተፍ አቅም አይኖረውም ሲሉ አንዳንድ አባላቶቹ ለዋዜማ ተናግረዋል።

ከፓርቲው አባላት የተወሰኑት መንግሥትን ለመግልበጥ ሙከራ አያደረጋችኋል ተብለው ለ6 ወራት ከታሠሩ በኋላ፣ ባለፈው ሳምንት እንደተፈቱም በዘገባው ተመላክቷል።

አብን መጋቢት 11 ቀን፣ 2014 ዓ፣ም በባሕርዳር ከተማ ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ በምርጫ ቦርድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ጉባኤው በድጋሚ እንዲካሄድ ቦርዱ ቢያዝም፣ እስካኹን ድረስ ፓርቲው ጉባኤውን ማካሄድ አልቻለም።

የፓርቲው አመራሮች ከምርጫ ቦርድ ጋር ያላቸው ንግግር በግልጽ የማይታወቅ መኾኑ፣ የፓርቲውን ሕልውና አሳሳቢ እንዳደረገው አባላቱ ገልጸዋል።

የአብን አባላት በፓርቲው ወቅታዊ ቁመና ዙሪያ ላነሱት ቅሬታ፣ የፓርቲው አመራሮች ምላሽ እንዲሠጡ ዋዜማ ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካም አስታውቋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Jan, 12:30


ብናልፍ አንዷለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው በመሾም ከፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ

ዓርብ ጥር 23 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የቀድሞው የሰላም ሚንስትር ብናልፍ አንዷለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለአምባሳደር ብናልፍ አንዷለም የሥራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት፤ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ግንኙነት የሚመጥን ትጋትና ቁርጠኝነት የተላበሰ አመራር መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንቱ "የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆኖ መሾም የኢትዮጵያን ሕዝብና መንግሥት ሃላፊነትና አደራ መጎናጸፍ ነው" ብለዋል።

ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የረጅም ዘመን ግንኙነትን የሚያጠናክር ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል።

በተጨማሪም አሜሪካ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙባት ሀገር በመሆኗ፤ በኢትዮጵያ ልማትና እድገት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አምባሳደሩ ጠንካራ ስራ ማከናወን እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።

በመሆኑም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም አሜሪካ ትልቅ እሳቤን የሚጠይቅ ዲፕሎማሲ የሚከናወንባት መሆኑን ታሳቢ ያደረገ አመራር እንዲሰጡም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ወዳጅን ማብዛት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ገልጸዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Jan, 07:57


"ለባርነት ጨረታ" ቀርባ የነበረችው ኢትዮጵያዊት 700 ሺህ ብር ተከፍሎ ነጻ መውጣቷን ተናገረች

ዓርብ ጥር 23 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሊቢያ "ለባርነት ጨረታ ቀርባ" የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ነሒማ ጀማል ለአጋቾቿ 700 ሺህ ብር ተከፍሎ ነጻ መውጣቷን ተናገረች።

በፎቶዎች እና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታይ የነበረችው ነሒማ በቤተሰቧ አማካይነት ገንዘብ ከኢትዮጵያ ተሰባስቦ ከተላከ በኋላ ከሁለት ቀናት በፊት አጋቾቿ ወደ ከተማ አምጥተው እንደለቀቋቸው አስረድታለች።

ታግታ ከነበረችበት ስፍራ እሷን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ቢኖሩም የተለቀቁት ገንዘብ የተከፈለላቸው "ውስን ሰዎች ነበሩ" ማለቷን ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ ገልጻለች፡፡

እንዱሁም በአሁኑ ወቅት በሊቢያ እንደምትገኛና "ከዚህ በኋላ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም" ስትል ጭንቀት ላይ እንደሆነች ተናግራለች።

ተማሪ የነበረችው ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ፣ በአዲስ አበባ በኩል ወደ በጎንደር በማምራት ከኢትዮጵያ በመውጣት ነበር ስራ አለ ተብላ ወደ ሊቢያ ያቀናችው።

አዲስ አበባ የተዋወቃቻቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን ወንዶች በሰሃራ በረሃ በውሃ ጥም ሕይወታቸው አልፏል ብላለች።

ለሌሎች ስደትን አማራጭ ለሚያደርጉ "አገራቸው ውስጥ ቢቀመጡ ይሻላቸዋል፣ መንገድ ላይ በሽታ አለ፣ ሞት አለ፤ ብዙ ጓደኞቼ መንገድ ላይ ሞተዋል" ስትል መክራለች።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

30 Jan, 09:45


ከቀጣይ አመት ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ የዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት ተገለጸ

ሐሙስ ጥር 22 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል፡፡

"መከላከያና መምህር የዚህ ሀገር ምሶሶዎች ናቸው" ያሉት ሚኒስትሩ ሰዎች ሙያውን ወደውት እና ዩኒቨርሲቲውን መርጠው እንዲገቡ የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።

እንዲሁም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲም እንደ አንድ አማራጭ እንደሚካተት ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርጋዲየር ጀኔራል ከበደ ረጋሣ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚመጥን በቂ ዕውቀት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Jan, 14:05


የትግራይ የፖለቲካ ልሂቃን ፍትጊያ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

ያመናቸው ከዱን የሚለው የአቶ ጌታቸው አስገራሚ ንግግርና የክልሉ አሁናዊ የፖለቲካ ቀውስን የተመለከተው ዝግጅታችንን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡ https://youtu.be/qTDvDmbU7Gk

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Jan, 11:59


የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች አዲስ አበባ ውስጥ መወያየታቸው ተገለፀ

ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የኤርትራ መንግሥትን ለመለወጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ትናንት ውይይት ያካሄዱ ሲሆን ውይይቱም በአዲስ አበባ መደረጉን ተሳታፊዎች መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡

ከሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑ ኤርትራዊያን በዚህ ውይይት መሳተፋቸው የተገለጸ ሲሆን  የተደረገውን ውይይት በተመለከተ “የኢትዮጵያ መንግሥት ዕውቅና ሳይኖረው አልሆነም” ሲሉ የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC) ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ የሱፍ አብደላ መናገራቸውን ዶችቬለ ዘግቧል።

ይህንን ውይይት አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ እድሉን እንዴት እንዳግፕኙ የተጠየቁት አቶ የሱፍ አብደላ ይህንን ለማድረግ "እድል ተገኝቷል፣ ያንን እድል ተጠቅመን ውይይቱን አድርገናል" በማለት ማብራሪያ አለመስጠታቸው ተጠቁሟል፡፡

የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ የተባለውና  የኤርትራን መንግሥት ለመለወጥ የሚንቀሳቀስ መሆኑን የሚገልፀው ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ የሱፍ አብደላ የፖለቲካ ትግላቸው ማጠንጠኛ የኤርትራ መንግሥት ኤርትራ ውስጥ በሚገኙ አፋሮች ላይ የሚፈጽመው ያሉትን "በደል" እና "ግፍ" ማስቀረት ነው ብለዋል፡፡

"መቼም  የኤርትራ መንግሥት ጓደኛ የለውም" ሲሉ የከሰሱት የኤርትራን መንግሥት የሚቃወመው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ሥራ አሥፈፃሚ አባል አቶ የሱፍ አብደላ፤ የኢሳያስ አፈወርቂን አስተዳደር "ዓለም ላይ ለጎረቤት ሀገሮች ችግር ነው፣ ለራሱ ሕዝብ ችግር የሆነ በአንድ ቡድን የሚመራ መንግሥት ስለሆነ ዛሬ ይህ እድል ተገኝቷል" ማለታቸውን ዘገባው አትቷል፡፡

ይህን ጉዳይ ተከትሎ የኤርትራ መንግሥትም እስካሁን ያለው ነገር እንደሌለ ተመላክቷል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Jan, 11:57


በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡

በክልሉ መንግስት የዘፈቀደ የጅምላ እስር መፈጸም ከተጀመረ ድፍን አራት ወራት ተቆጥረዋል ያሉት የድርጅቱ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታ በክልሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ ባለበት ሁኔታ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታ ከማሳፈርም በላይ ነው ሲሉ ኮንነዋል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የመብት ተሟጋቾች ጭምር በጅምላ ታፍሰው በግፍ የታሰሩት ሁሉ እንዲለቀቁ ተጽዕኗቸውን ተጠቅመው ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የህግ የበላይነት ተረግጦ ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ዓለም በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ አይቶ እንዳላየ ማለፉን ሊያቆም ይገባልም ተብሏል፡፡

መንግስት በዘፈቀደ እያፈሰ በጅምላ ያሰራቸውን ሊለቅ ካልሆነም ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባላቸው የተጠያቂነት የህግ መስፈርቶች ክስ ሊመሰርትና በህግ ሊጠይቃቸው እንደሚገባም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Jan, 08:20


ሀሙስ ደርሷል!! ፊንቴክስ ‹‹FINTEX›› የፈርኒቸር፣ የቤተ-ውበት እና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ቴክኖሎጂዎች ዓለም አቀፍ አውደ-ርዕይ ነገ ሃሙስ በድምቀት ይከፈታል። ዝግጁ?
በርካታ ታላላቅ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ አዳዲስ የገበያ አማራጮችን ለመፍጠርና የዘርፉን ዕድገቶች ለማሳየት ከጥር 22-25 በሚኒሊየም አዳራሽ እርስዎን ይጠብቃሉ!!
ፊንቴክስ በፈርኒቸር፣ በቤተ ውበት ዲዛይን እና በፊኒሺንግ ምርቶች ዘርፍ የሚያስደንቁ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ለማየት የሚችሉበት ትልቁ እድል ነው። በዚህ መደረክ በርካቶች ዘርፉን ለማሳደግ ይመክሩበታል። ይጎብኙት ብዙ ያተርፉበታል።
በነጻ ለመጎብኘት https://bit.ly/fintexregistration ይመዝገቡ ወይንም በ0913356709 ወይም 0929308364 አሁኑኑ ይደውሉ!!
ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ www.fintexaddis.com

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Jan, 12:16


አደገኛ የማጭበርበሪያ መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ መሆኑን ንግድ ባንክ አስታወቀ

ማክሰኞ ጥር 20 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)ደምበኞች በዋትስ አፕ እና በቴልግራም የሚሠራጭ Pharma+/CBE Vacancy መተግበሪያን እንዳይጭኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳስቧል።

ባንኩ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት፤ ባደረገው ምርመራ መሠረት አደገኛ መተግበሪያ ማግኘቱን ገልጿል።

ይህ Pharma+/CBE Vacancy የተሰኘ አሳሳች መተግበሪያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ መተግበሪያ በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወደ ደንበኞቹ እየደረሰ መሆኑን ጠቁሟል።

መተግበሪያው በስልክ ላይ ከተጫነ ያለ ፈቃድ ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችልም አሳውቋል።

ባንኩ ከዚህ አይነት የመጭበርበር አደጋ ለመጠበቅ ከቴሌግራም ወይም ከዋትስአፕ መተግበሪያዎችን አታውርዱ ብሏል።

ደንበኞች መሰል ተግባራት ሲገጥሟቸው በ951 ነጻ የስልክ መስመር ደውለው እንዲያሳውቁ አሳስቧል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Jan, 09:50


ብልጽግና ፓርቲ በ2ተኛ ጠቅላላ ጉባዔው የተለያዩ ሹምሽሮችን ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዚህ ሹምሽር ምን አዲስ ነገር ይመጣ ይሆን? ማንስ ተነስቶ ማን ይተካል? የሚሉና ተያያዥ ነጥቦች የተነሱበት አዲስ ማለዳ ትንታኔ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡ https://youtu.be/x25sO7ZzU4Q

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

27 Jan, 14:37


በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን የፋኖ ክንፍ የሚመሩት አቶ እስክንድር ነጋ ከመንግስት ጋር ልንደራደር ነው ማለታቸውን ተከትሎ የተለያ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡

ድርድሩ እንዴት ባለ መንገድ ይከናወናል? ሌሎቹ የፋኖ ሃይሎች ድርድሩን ይቀበሉታል ወይ አደራዳሪ ሆኖ የሚቀርበው ዋነኛ አካልስ ማን ነው?የሚሉና መሰል ስጋት ያዘሉ ጥያቄዎችም መነሳታቸውን ቀጥለዋል፡፡

ዝርዝር መረጃው ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/svIm5UY3XZw

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

27 Jan, 12:50


https://youtu.be/Pgz2Oza1li4

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

27 Jan, 11:30


“የማዳበሪያ አቅርቦት ከገበሬው የመሬት ዝግጅት አንጻር አይመጣጠንም ”- የፓርላማ አባላት

ሰኞ ጥር 19 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በተለያዩ ክልሎች የአፈር እና የማዳበሪያ አቅርቦት ከገበሬው የመሬት ዝግጅት አንጻር እንደማይመጣጠንና በገበሬው ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነሳ ጥያቄ መሆኑ መንግስት ምን አይነት የመፍትሄ ሀሳብ እንዳለው የምክር ቤት አባል ወርቅነሽ መሀመድ ጠይቀዋል፡፡

ይህም የተጠየቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው፡፡

በተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረቡት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ስንዴ አምራች ገበሬዎች ምርቶቻቸውን በመንግስት የዋጋ ተመን እንዲሸጡ የሚገደዱበት አግባብ ምክንያቱ ምን እንደሆነ እና በነጻ ገበያ እንዳይገበያዩ መሆኑ በውድ ዋጋ ማዳበሪያ እየገዛ የሚያመርተውን ገበሬ የሚያሳድርበትን ጫና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዴት እንደሚመለከተው ጠይቀል፡፡

በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ከዘመቻ ነት ወጥቶ ወደ ተቋማዊ የችግኝ ማልማት እና የተራቆቱ አካባቢዎችን የማልማት ስራ የሚካሄድበትን ጊዜ እንዲገለጽ አመላክተዋል፡፡

በአባላቱ ለተነሱ ሀሳብ እና ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር ግርማ አመንቴ 5.7 ሚሊዮን ማዳበሪያ ለመስኖ ወቅት እንደተዘጋጀ እና ስርጭቱ ላይ መስተጓጎሎች እንዳይኖሩም የመቆጣጠር ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታረሰው መሬት 43 ከመቶ የሚሆነው በአሲዳማ አፈር የተጠቃ መሆኑን እና 7 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው የአሲዳማ አፈር መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም መሬቱን ለግብርና ስራ ለማዋል በዓመት 6.2 ሚልየን ኩንታል ማዳበሪያ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን 70 ከመቶ የሚሆነው የአፈር ማዳበሪያ ይባክናል ተብሏል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

26 Jan, 15:40


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ያካሂዳል

እሁድ ጥር 18 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የግብርና ሚኒስቴርን የ2017 በጀት አመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያዳምጥ ሲሆን፤ ሁለት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።

የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

በተጨማሪም የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

አዲስ ማለዳ የምክር ቤቱን ስብሰባ በዩቲዩብ በቀጥታ ስርጭት የምታስተላልፍ መሆኑን እየገለጽን መሰል ጉዳዮችን ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን በመጫን አዲስ ማለዳን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Jan, 20:20


በትግራይ ክልል የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ስጋት መኖሩን ነዋሪዎቹ ተናገሩ

ቅዳሜ ጥር 17 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የትግራይ ወታደራዊ አመራር ሰሞኑን መፈንቅለ መንግስት የማድረግ ዕቅድ መኖሩን በመግለጫቸው ካሳወቁ በኋላ በትግራይ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ስጋት መፈጠሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በተለይም ውጥረቱን ተከትሎ በአካባቢው ግጭት ሊከሰት ይችላል በሚል ከወትሮው በተለየ መልኩ ገንዘብ ለማውጣት ባንኮች በሰልፍ ተጨናንቀዋል ሲሉ የአይን እማኞች ገልፀዋል።

በገበያ ማእከላት በተለይ የፍጅታ ሸቀጦች ላይ የፍላጎት መጠን በጣም ጨምሯል የሚሉት ነዋሪዎቹ ህዝቡ ጦርነት ይቀሰቀስ ይሆናል ብሎ የሰጋው ህዝብ ስጋት ላይ መውደቁን ይገልፃሉ።

ህዝቡ ስጋቱን ለመግለጽም የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ ጀምሯል።

በተለይም የመኾኒና የአካባቢው ህዝብ «መንግስትን የሚያፈርስ የትኛውንም አካል አንታገስም» የሚል መፈክር በማንገብ በትላንትናው አለት መግለጫ የሰጠውን እና የትግራይ ሀይል የበላይ ሀላፊ ነኝ ያለውን ቡድን ተቃውመዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Jan, 20:07


የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር የመንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ

ቅዳሜ ጥር 17 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ከመጪው የካቲት ወር ጀምሮ በኦንላይን ቦታ በማስያዝ የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚጀምር የአክሲዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ "ጥራት ያለዉና እና ቀልጣፋ የጉዞ አገልግሎት ለመስጠት ሲባል እንዲሁም ትክክለኛ የመንገደኛ መረጃን ለማረጋገጥ እና ከችግር የጸዳ ጉዞን ለማመቻቸት አስፈላጊ በመሆኑ ለሁሉም የሀገር ውስጥ ተሳፋሪዎቻችን ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) በመጠቀም ኦንላይን ቦታ ለመያዝም  ሆነ ለመጓዝ  መስፈርት መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን" ሲሉ አስታውቀዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

23 Jan, 10:32


ስመኝ ውቤ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕምባ ጠባቂ ሆነው ተሾሙ

ሐሙስ ጥር 15 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ዋና እንባጠባቂ ምክትል ዋና እንባ ጠባቂ እና የዘርፍ እንባ ጠባቂዎችን ሹመት ለማጽደቅ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በዚህም መሰረት ስመኝ ውቤ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕምባ ጠባቂ እንዲሁም የኔነህ ስመኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም ምክትል ዋና ዕምባ ጠባቂ እንዲሁም አባይነህ አዴቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም የዘርፍ ዕምባ ጠባቂ ሆነው ተሹመዋል።

አዲሷ ተሸሚ የቀድሞን የተቋሙን ዋና እንባ ጠባቂ የነበሩት እንዳለ ሃይሌን (ዶ/ር) በመተካትም ስራ የሚጀምሩ ይሆናል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

23 Jan, 09:26


የሰራተኞችን የክፍያ መጠን ለመወሰን እንደሀገር በቂ አቅም ላይ እንዳልተደረሰ ተገለጸ

ሐሙስ ጥር 15 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ስብሰባው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የ2017 በጀት አመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል፡፡

ለምክር ቤቱ አፈጻጸሙን ያቀረቡት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር መላኩ አለበል የሰራተኞችን የክፍያ መጠን በተመለከተ እንደ ሀገር ያለንን አቅም ማየት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የሰራተኞች ምርታማነት ሲጨምር የአገልግሎጽ ክፍያም እንደሚጨምር እና የክህሎት ግንባታን ማጠናከር የሰራተኞው ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ በዚህም አቅጣጫ እየተሄደ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ባንኮች ለአምራች ኢንዱስትሪው ፋይናንስ ከማቅረብ ይልቅ በተለመደው መንገድ የአጭር ጊዜ ትርፍ ወደ ሚያስገኝና ስጋታቸው ዝቅተኛ በሆኑ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው እንዳይቀጥሉ አሰራሩን መፈተሸ ያስፈለጋል ብለዋል፡፡

ባንኮች ስጋታቸው ዝቅተኛ እና የአጭር ጊዜ ትርፍ ወደሚያስገኙ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው እንዳይቀሩ ማድረግ የሚቻልበትን አሰራር ማየት ይገባናል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ለአምራች ዘርፉ ሲቀርብ የነበረው ከ13 በመቶ ያልበለጠው የብድር አቅርቦት ድርሻ ወደ 24 በመቶ እንዲያድግ የፖሊሲ አቅጣጫ ቢሰጥም እስካሁን የደረሰው ግን 16 በመቶ ነው ብለዋል፡፡

ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የስራ ማስኬጃ ብድር ባንኮች ካላቸው ካፒታል ከአንድ በመቶ ያልበለጠው ወደ 10.3 ከፍ እንዲል መደረጉን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

23 Jan, 06:33


https://www.youtube.com/live/ccjvgGe4aNI?si=br6nNitcMI41Y7eV

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Jan, 12:57


“ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ተከታታይ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ሆና ምንም አይነት ሀገራዊ ምክክር ማድረግ አትችልም”- ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

ጥር 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)ብሔራዊ መግባባት በሚል ርዕስ ዛሬ በተካሄደው 2ኛው የፓርላማ የዜጎች ፎርም ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ በርካታ ሀሳብ እና አስተያየት ተስተናግደዋል፡፡

ሀሳባቸውን የሰጡት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በበኩላቸው ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ተከታታይ የፖለቲካ ቀውስ እና አለመግባባት እንዲሁም ጦርነት ውስጥ ምን አይነት ሀገራዊ ምክክር ሊደረግ ይችላል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

እንዲሁም የሰላም እና የጸጥታ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ቢሆንም የውይይቱ ዋነኛ መወያያ ርዕስ አለመሆኑ ሊታሰብበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም “በትክክል አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ውጤታማ የሆነ ሀገራዊ መግባባት አካሂደን የሀገራችንን የወደፊት ተስፋ መቅረጽ በምንችልበት ቁመና ላይ ነው ያለነው” በማለት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠይቀዋል፡፡

ይህን ተከትሎ በአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ፕ/ር መስፍን አርአያ የተነሱት ጥጣቄዎች አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን ገልጸው ሀገራዊ ምክክር የሚደረገው በሶስት መንገድ ነው አንደኛውም በግጭት ውስጥም ተሆኖ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አንጻራዊ ሰላም እንደሚያስፈል እና ከመንግስትም ሆነ ከተቋዋሚ አካላት ከሁሉም ህዝቦች ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለውይይት የሚሆን አስቻይ ሁኔታዎችን ፍጠሩልን ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Jan, 12:34


https://youtu.be/xx9kUvj1qW8

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Jan, 11:18


“የትግራይ ሕዝብ አሳር ሊያበቃ ይገባል መፍትሄ ይሰጥ”- ኢሕአፓ

ጥር 14 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ነባራዊ የትግራይ ክልል ሁኔታን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ በበርካታ ችግሮች እየተጨቆነ ያለው የክልል ማህበረሰብ አሳር ሊያበቃ ይገባል ሲል ገልጻል፡፡

በቅርቡ አክሱም ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች፣ ሂጃብ በማድረጋቸው የተነሳ በተወሰኑ ርዕሰ- መምህራን የተናጠል ውሳኔ ለፈተና እንዳይ መዘገቡ መደረጋቸውን፣ይህንንህገ-ወጥ የዕምነት ነፃነት ነፈጋን፣ ከህግም ከሀገራዊ እሴቶች ያፈነገጠ በመሆኑ በአጽኖኦት እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡

እንዲሁም ፍርድ ቤት እንዲያርሙ የሰጠውን ትዕዛዝ ለማክበር ፈቃደኞች አለመሆናቸው ደግሞ ከፍተኛ ዕብሪትና ህገ-ወጥነት ስለሆነ በአፋጣኝ በሚመለከታቸው ክልላዊና የፌዴራል ባለሥልጣናት አስገዳጅ የርምት ርምጃ እንዲወስድባቸው ፓርቲው አሳስቧል፡፡

የትግራይ ህዝብ በአንዳድ የመገንጠል ዓላማ ባላቸው ፖለቲከኞች የተነሳ ከጎረቤቱ የአማራና የአፋር ክልል ህዝብ ጋር ሁሌም በጠላትነት እንዲተያይ የሚደረገው የአንዳንድ ፖለቲከኞች ሸር ማብቃት አለበትም ተብሏል፡፡

በመሆኑም ሁለቱም የህወሓት ቡድኖች በንግግርና በመቻቻል አስቸኳይ ሠላማዊ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲያበጁ እና በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን በማድረግ የህዝቡ ሁለንተናዊ ሠላም እንዲረጋገጥ መደረግ እንደሚገባው ኢሕአፓ አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም ምንም እንኳን የትግራይ ህዝብ እንደ ፌደሬሽን አባልነቱ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት 38 ወንበሮች ያሉት ቢሆንም ከጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ተወክሎ አያውቅም።

ይህም ሲባል ባለፉት 4 ዓመታት በፓርላማው እና በፌደሬሽን ምክርቤቶች የሚተላለፉ ውሳኔዎች የትግራይ ህዝብን ፍላጎቶች ያካተቱ አልነበሩም፤ ስለዚህ ለዚህም አስቸኳይ ምርጫ በማካሄድ የትግራይ ህዝብ ጉዳዮችን በእንደራሴዎቹ እንዲወስን በህዝብ ተወካዮች እንዲወከል እንዲደረግ ጠቁሟል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፣ በአክሱም ከተማ ትምህርት ቤቶች በሒጃብ ሳቢያ በሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ የተጣለው የትምህርት እገዳ አጀንዳ መኾን አይገባውም ነበር በማለት ገልጸዋል፡፡

ጌታቸው፣ ትናንት በመቀሌ በእገዳው ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሙስሊሞች ተወካዮችን ባነጋገሩበት ወቅት፣ ችግሩ "ኾን ተብሎ የተፈጠረ አጀንዳ" መኾኑን መጠቆማቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Jan, 11:15


በየመን አቅራቢያ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ ቢያንስ 20 ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ

ጥር 14 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) መነሻዋን ጅቡቲ ያደረገች መርከብ የመን አቅራቢያ በደረሰባት የመስጠም አደጋ ቢያንስ 20 ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው ማለፉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።

ከአደጋው 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የመናውያን የጀልባዋ ቀዛፊ እና ረዳቱ መትረፋቸውም ነው የተነገረው።

35 ስደተኞችን አሳፍራ ከጅቡቲ የተነሳችው ጀልባዋ ዱባብ አቅራቢያ ባጋጠማት ብርቱ ነፋስ ለአደጋው መጋለጧን ዓለም አቀፉ ድርጅት አመልክቷል።

በየመናዊ ካፒቴን እና ረዳቱ አማካኝነት ከጅቡቲ የባሕር ጠረፍ ጀልባዋ ስደተኞች አሳፍራ ቅዳሜ ዕለት በምሽት ጉዞ መጀመሯ ተነግሯል።

አደጋው በርካታ ስደተኞች የሚጋፈጡትን አሳዛኝ አደጋ እንደሚያሳይ የገለጸው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለሕገወጥ ስደት መንስኤ ለሆኑ ችግሮች መፍትኄ እንዲፈልጉ ጥሪውን አቅርቧል።

በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ፍለጋ በጅቡቲ በኩል ወደ የተለያዩ የአረብ ሃገራት እንደሚሰደዱ በተደጋጋሚ የሚነገር ሲሆን ባለፈው ጥቅምት ወርም በተመሳሳይ አደጋ ከጅቡቲ የተነሱ 45 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተሳፈሩበት ጀልባ በደረሰበት አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Jan, 14:37


የትግራይ ክልል በየጊዜው የሚካሄደው የሰላማዊ ሰልፍ እና የሰብዓዊ መብት ጥያቄ ጩኽት እንደቀጠለ ነው፤ የክልሉ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ ለብሳችሁ ትምህርት ቤት አትገቡም መባሉ ምላሽ ያላገኘ በመሆኑ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ቁጣን አስነስቷል፤ በዚህም መብታችን ይከበር ሲሉ ሰልፍ መውጣታቸውን እና ዝርዝር መረጃዎችን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ
https://youtu.be/AZxBJGBb_bg?si=UN1LaC_8SF_uBlqr

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Jan, 09:06


“የነዳጅ ምርት እጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰ በመምጣቱ ሽያጩ በኩፖን እንዲሆን ተወስኗል” የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል

ጥር 14 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በየጊዜው የነዳጅ እጥረት ከመሻሻል ይልቅ እየተባሰ በመምጣቱ ሽያጩ በኩፖን እንዲሆን ተወስኗል ሲል ያስታወቀውየደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ነው፡፡

በቢሮው በኩል ለሁሉም ዞን ንግድና ገቢያ ልማት መምሪያ ዛሬ ተጽፎ በተሰራጨው ሰልኩላር ደብዳቤ መሰረት ከጥር 30 ጀምሮ ሁሉም የነዳጅ ማደያ ያለባቸው ከተሞች ከጥር 30/2017 ጀምሮ ነዳጅ በኩፖን እንዲሸጥ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ቢሮው የነዳጅ ምርት እጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በተለይ የባለ ሁለት እግር ሞተሮች በየቀኑ ተመላልሶ መቅዳት ለኮንትሮባንድ ሽያጭ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ለችግሩ መባባስ ዋነኛ መንስኤዎች መሆናቸውን ከተደረገው ክትትል ለማረጋገጥ ተችሏል ብሏል።

በአንዳንድ የክልሉ ከተሞች የኩፖን ሥርዓት በመዘርጋቱ ሥርጭት ላይ ያለውን የቤንዚን ምርት በአግባቡ ማሰራጨት መቻሉንና ለክትትልም ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ማስተዋሉን ነው በደብዳቤው የጠቀሰው።

በመሆኑም የነዳጅ ማደያ ያለባቸው ከተሞች ከጥር 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ የትኛውም ተሽከርካሪ በኩፖን ብቻ እንዲስተናገድ እና ታርጋ የሌላቸው ተሽከርካሪዎች ሀጋዊ የተሽከርካሪ ሠሌዳ እስኪያወጡ ድረስ የግልም ሆነ የመንግስት ተሽከርካሪዎች እንዳይስተናገዱ ሲል በደብዳቤው ጠቅሷል።

ቢሮው አክሎም "ህገ-ወጥ የሆኑትን ማክሰም አስፈላጊ በመሆኑ ተግባራዊ እንዲደረግ እየገለጽን የነዳጅ ምርት ሽያጭም ቢሆን በኤሌክትሮኒክስ ቴሌ ብር እና ሲቢኢ ብር/ የመገበያያ መንገዶች ብቻ እንዲፈጸም በጥብቅ እናሳስባለን፡፡" ሲል በሰርኩላር ደብዳቤው አስታውቋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Jan, 08:47


በአፋር ክልል ከመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጋር  በተገናኘ  አርብቶ አደሮች ወደ ሌላ ቦታ ለመዘዋወር ፈቃደኞች አለመሆናቸው ተገለጸ

👉የአካባቢው ባለሥልጣናት ግን  በግዴታ ለማስለቀቅ አቅደዋል ተብሏል

ጥር 14 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአፋር ክልል ከመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጋር በተያያዘ ነዋሪዎች በተለይም ከብቶቻቸውና ንብረቶቻቸው አደጋ ውስጥ የገባባቸው አርብቶ አደሮች ወደሌላ ቦታ ለመዘዋወር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ተገልቷል፡፡
ይህን ያለው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) ነው፡፡
በአዋሽ እና ዱሌቻ ወረዳዎች ያሉ የተወሰኑ ነዋሪዎች በተለይም ከብቶቻቸው እና ንብረታቸው ላይ ስጋት ያላቸው የአርብቶ አድር ማህበረሰቦች ወደ ሌላ ቦታ ለመዘዋወር ፈቃደኞች አይደሉም" ሲል ነው ጽህፈት ቤቱ የገለጸው።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት መሠረት፤ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የህዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አደጋ ካለባቸው አካባቢዎች ለማስወጣት አስገዳጅ እርምጃዎችን ለመውሰድ እያሰበ ነው።

ከአያኤኤሲ ክላስተር አስተባባሪዎች እና አጋሮች ድጋፍ በተዘጋጀው አዲስ መረጃ  የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት፤ በኦሮሚያ ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰቱ ባሉበት አካባቢዎች የፀጥታ ስጋት እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Jan, 06:56


የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ

ጥር 13 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ በአክሱም አካባቢ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

ምክርቤቱ ለክልሉ መገናኛ ብዙሀን በላከው ደብዳቤ በአክሱም ከተማ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጀ ትምህርት ቤቶች ከጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የተፈፀመው ህገወጥ በሆነ የሂጃብ ክልከላ ምክንያት የእስልምና እምነት ተከታይ ሴት ተማሪዎች ለወራት ከትምህርት ገበታ እንዲገለሉ ማድረጉን አመላክቷል።

ምክርቤቱ አክሎም እስካሁን ድረስ ለተለያዩ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ያልናቸው አካላት በአካልና በፅሑፍ ጥያቄ ስናቀርብ ብንቆይም እስካሁን ድረስ ጉዳዩ መፍትሄ ሳያገኝ መጥቷል ብሏል።

እየተካሄደ ያለው ሰልፍም የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤትና ከክልሉ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዋና ፅህፈት ቤት መነሻውን አድርጎ በሮማናት አደባባይ ፍፃሜውን እንደሚያደርግ ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት የተገኘው መልእክት አመላክቷል።

በተመሳሳይ በአጠቃላይ አራት የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን እና እስካሁንም ድረስ የተደረሰ የጋራ መግባባት እንደሌለ እና ተማሪዎቹም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ እስማኤል አብድራህማን ገልጸው ነበር፡፡

እንዲሁም በአስተዳደር ደረጃ ማንም ሂጃብ አይልበሱ ብሎ የሚከራከር አመራርም ሆነ ግለሰብ ባይኖርም ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ የሰጠም አለመኖሩም መገለጹን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

20 Jan, 14:08


የኦነግ የፓርቲ ፖለቲካ፣ ከኦነግ ሸኔ እንዲሁም ከፋኖ የብረት ትግል እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከአቶ ወንድሙ ኢብሳ ጋር ያደረግነው ቆይታን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/jbIV-Ir3di0?si=0OQye_zV9r7yu439

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

20 Jan, 10:10


በአመራሮቹ መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ እየታየ ያለውን የሰላም ጭላንጭል የሚያጨልም ነው” - ብጹህ አቡነ ማትያስ

ሰኞ ጥር 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል የሚያጨልም ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀጻጻስ የሆኑት አቡነ ማትያስ ገልጸዋል፡፡

ብጹህነታቸው ይህን ያሉት ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል እና ለግዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በተናጠል በጻፉት ደብዳቤ ነው።

ፓትርያርኩ በደብዳቤያቸው ሁለቱን አመራሮች በአካል አግኝተው ለመወያየት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካላቸው በመጠቆም ደብዳቤውን ለመጻፈ መገደዳቸውን አስታውቀዋል።

“በእልክ እኔ እሻላለሁ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን፣ እኔ ብቻ ነኝ ለህዝብ የማስበው በሚል በተፈጠረው ውስብስብ ችግር የሚያዝን እንጂ የሚደሰት ህዝብ የለም” ሲሉ ጠቁመዋል።

“በአመራሩ መካከል የተፈጠረው መለያየት እንዳይበቃ በአንድነት ተስማምቶ ሲኖር በነበረው ህዝብ መካከልም ተጽእኖው እየወረደ ይገኛል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል::

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Jan, 14:27


በትላንትናው እለት በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ " ጎቱ ኦኖማ "በተራሮች ላይ የተነሳው ሰደድ እሳት ዛሬ መጥፋቱ ተሰምቷል

እሁድ ጥር 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)በትላንትናው እለት በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ " ጎቱ ኦኖማ " በተባለው አከባቢ በተራሮች ላይ የተነሳው ሰደድ እሳት ዛሬ መጥፋቱን የወረዳው መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Jan, 09:14


እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አጀረሳችሁ።

አዲስ ማለዳ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Jan, 06:15


ቲክቶክ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን እና አገልግሎት ማቆሙን ይፋ አደረገ

እሁድ ጥር 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ቲክቶክ በአሜሪካ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን እና አገልግሎት ማቆሙን ይፋ አደረግል።

ድርጅቱ ሰኞ ስራ ከሚጀምሩት አዲሱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር አብሮ በመስራት መፍትሄ ይገኛል ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል።

መተግበሪያው ገና እግዱ ተግባራዊ የሚሆንበት ሰዓት ሳይደርስ ቀደም ብሎ (ከሰዓታት በፊት) ነው የዘጋው።

በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ስክሪን ላይ ፥ " ቲክቶክን ለማገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል በዚህም አሁን ቲክቶክን መጠቀም አይችሉም " የሚል ፅሁፍ ነው የሚታየው።

ቲክቶክ ትራምፕ ስልጣናቸውን ተረክበው ወደ ቢሮ ሲገቡ መፍትሄ ለማበጀት አብረዋቸው እንደሚሰሩ እንደጠቆሟቸው በማመልከትም እስከዚያው ድረስ ተገልጋዮቹ እንዲጠባበቁት ጠይቋል።

ትራምፕ ቲክቶክ መተግበሪያ ካልተሸጠ እንዲታገድ የሚለው ህግ እንዲዘገይ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ከመታገድ ሊያድነቱ አልቻሉም።

ፕሬዜዳንታዊ ስልጣናቸውን ሲረከቡ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ? የሚለው በቀጣይ ይታያል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Jan, 20:56


በወንዶ ወረዳ "ጎቱ ኦኖማ" አካባቢ በተራሮች ላይ የሰደድ እሳት መነሳቱን የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን አስታወቀ

ቅዳሜ ጥር 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ "ጎቱ ኦኖማ" በተባለው አከባቢ ከሰዓት 10 ሰዓት ላይ በተራሮች ላይ የሰደድ እሳት መነሳቱን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

የሰደድ እሳቱ መከሰት መንስዔው በድርቅ ምክንያት የተከሰተ ስለመሆኑ ገልጿል።

ቢሮው የተከሰተውን ቃጠሎ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ለማጥፋት እየተሞከረ ነው ሲልም አስታውቋል።

ሆኖሞ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያው በ 'እሳተ ገሞራ' የተከሰተ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል።

በተራሮቹ ላይ የተከሰተው ሰደድ እሳት ከመስፋፋቱ እና ከፍተኛ ችግር ከማስከተሉ በፊት ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም ቢሮው ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Jan, 08:23


የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ባጸደቀው ብድር ዙሪያ ሁለተኛ ዙር ግምገማ አፀደቀ

ቅዳሜ ጥር 10 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ለኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ባጸደቀው የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ዙሪያ ሁለተኛውን ዙር ግምገማ ትናንት ማፅደቁን አስታውቋል።

የብድር ግምገማው መጽደቁን ተከትሎ፣ ድርጅቱ የ250 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱ የውጭ ዕዳ አስተማማኝ እንዲኾን ጥረቱን መቀጠሉንና በቡድን 20 አገራት ማዕቀፍ ሥር የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ ለመድረስ ከአበዳሪዎች ጋር የሚያደርገው ድርድር አበረታች መሆኑን ጠቅሷል።

የመንግሥትን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ ይፈጠራል ተብሎ የተሠጋው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አልተከሰተም ያለው ድርጅቱ፣ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችትም "በፍጥነት" እያደገ መኾኑን ገልጿል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Jan, 07:06


“አስከፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት የደረሰበት ዓመት ነው” ሂውማን ራይትስ ዎች

ቅዳሜ ጥር 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ሂውማን ራይትስ ዎች በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አስከፊ እንደነበር አለም አቀፉ የመብት ተሟች ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎች ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ ገልጧል።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39695

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

17 Jan, 14:27


የጥር ወር የማህፀን በር ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው::

እንደአለም አቀፉ የጤና ድርጅት መረጃ ይህንን ህመም የሚያመጣውን ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ( HPV) ለመከላከል ክትባት ወሳኝ ሚና አለው::

ይህ ቫይረስ ከ95% በላይ የሚሆኑት የማህፀን በር ካንሰሮች ለመፈጠራቸው ምክንያት ነው:: ክትባቱ ከ18 አመታት በላይ በጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም ከ9 አመት ጀምሮ ላሉ ልጃገረዶች እየተሰጠ መሆኑን በቅርብ የወጡ ዘገባዎች ይጠቁማሉ:: ክትባቱ እድሜያቸው እስከ45 አመት ድረስ ላሉ ሴቶችም ይሰጣል::

ከየጤና ወግ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የቀረበው ምስላዊ መረጃ ስለበሽታው የበለጠ ግንዛቤን ያስጨብጣል::

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

17 Jan, 13:58


ኢ-ተገማች የሆነው የአፍሪካ ቀንድ የሃይል አሰላለፍ መሽቶ በነጋ ቁጥር አዳዲስ ነገሮችን ማሳየቱን እንደቀጠለ ነው፡፡
ከሰሞኑ ከዋሽንግተን ቤተ-መንግስት የተሰማውና ከቀጠናው በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር የተገናኘው አንድ መረጃ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

ለመሆኑ በቅርቡ በአለ-ሲመታቸውን የሚፈጽሙት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራንፕ በቀጠናው ምን ሊወስኑ አስበዋል የሚሉና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ተመልክተነዋል፡፡

ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ

https://youtu.be/ZOwP1cbp0G0?si=Crj6VHHkW3O9M6wg

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

17 Jan, 10:01


መጪውን ሀገር አቀፍ ምርጫን የሚያሳልጥ ተቋም የሚመራበት አዋጅ ሊያሻሽል መሆኑን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

ዓርብ ጥር 9 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ከ1 ዓመት ያላነሰ ጊዜ የቀረ በመሆኑ ምርጫን የሚያሳልጥ ተቋም የሚመራበትን አዋጅ ሊያሻሽል መሆኑን ገልጿል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ምርጫ፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጁ ማሻሻያ ማድረግ ማሰቡን የገለጸ ሲሆን የሚያሻሽለዉ የአዋጁን አፈፃፀም እና አተገባበር ላይ የታዩ ክፍተቶችን እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ከግምት በማስገባት እና በተሰጠው ኃላፊነት መሆኑን አመላክቷል።

ማሻሻያዉን በዚህ ዓመት መጀመሩን የገለጹት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢሜላትወርቅ ሀይሉ፤ አዋጅን ለማሻሻል ያሉ ክፍተቶችን ላይ በርካታ ውይይት ከተካሄደበት በኃላ ክፍተቶችን ለመሙላት በማሰብ የተደረ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ቅሬታ ሲያነሱ የነበሩ ፖርቲዎችና ጉዳያቸውን ፍርድ ቤት ድረስ ያደረሱት ጋር ያለውን ክፍተት ለመመልከት የሚረዳ መሆኑንም ዋና ሰብሳቢዎ ተናግረዋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስት ዓመታትን የቆየውን አዋጅ ለመሻሻል ከፖርቲዎች በተጨማሪ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቀጣይ ውይይት እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Jan, 13:59


"የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ አይደለንም ሰብዓዊ መብታችን ይከበርልን" ፤ ወደ መኖሪያ ቀዬያችን መልሱን የሚሉትን ጥያቄዎች የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች አደባባይ ይዘው ቢወጡም፤ የክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ረስቶናል ሲሉ ድምጻችን ይሰማ ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በበኩሉ የተፈናቃዮችን ጥያቄ ለመመለስ የፌደራል መንግስቱም ሆነ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ቁርጠኛ ተባባሪ አልሆኑልኝም ብሏል፡፡

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የሰልፉ አስተባባሪ ለሶስት ቀን በቆየው የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ላይ የሰጡትን ማብራሪያ ያካተተ ዝግጅታችንን ማስፈንጠሪያውን በመጫን ይከታተሉ

https://youtu.be/zJgimf4LFZE

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Jan, 13:19


አሽከርካሪዎች በቀን እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ እንደሚከፍሉ በጥናት መረጋገጡ ተገለጸ

ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአዲስ አበባ ኮሪደሮች ላይ የሚጠየቀው የመኪና ማቆሚያ ዋጋ የሕብረተሰቡን አቅም ያላገናዘበ እንደሆነ ጥናት ማመላከቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም ጥናት በፓያሳ ፣ በቦሌ ፣ በአራት ኪሎ ያሉ አራት የኮሪደር መንገዶችን ላይ ባሉ የመኪና ማቆሚያዎች ላይ ትኩረት የተደረገ ሲሆን በቀን አሽከሪከዎች ከ41 እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ ወጪ እንደሚያደርጉ ተመላክቷል።

እንዲሁም አሽከርካሪዎቹ በቀን ለመኪና ማቆሚያ የማያወጡት ብር አቅማቸውን ያላገናዘበ እንደሆነ ተናግረዋል።

አንድ ወር የፈጀው ጥናት በእነዚህ ኮሪደር መንገዶች የእግረኛም ሆነ የመኪና ፍሰቱ ቀልጣፋ መሆኑን ከ400 የጥናቱ ተሳታፊዎች 65 በመቶ የሚሆኑት የገለጹ ቢሆንም የመንገድ የኮሪደር ልማቱ የእግረኛና የመኪና መጨናነቅን ቀንሷል ብሎ ቢያመላክትም ከንግድ ሱቆችና ከመኖሪያ ቤቶች መፍረስ እግረኛንም ሆነ የመኪናን ቁጥር ከመቀነሳቸው ጋር ያያያዘው ነገር የለም ተብሏል፡፡

ጥናቱን ያጠኑት ሻካ አናላይቲክስ ከ አለም አቀፍ የቢዝነስ ልማት ጋር በመተባበር ሲሆን የቢዝነስ ልማቱ በኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ አሰፋ " ጥናቱ ያተኮረባቸው ኮሪደሮች ከፒያሳ አራት ኪሎ ፣ ከአራት ኪሎ እንግሊዝ ኤንባሲ ፣ ከአራት ኪሎ ቦሌ ድልድይና ከሜክሲኮ ሳርቤት እንደሆነና አጠቃላይ ጥናቱ አንድ ወር ፈጅቷል" ማለታቸው ተገልጿል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Jan, 07:54


በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ።

“ከዚህ በኃላ የተሽከርካሪ አስመጪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ሳይተክሉ በሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም” የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር

ሀሙስ ጥር 8 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በመዲናዋ የሚገኙ የነዳጅ ማዲያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ የሃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት ተጀምሯል ያለው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ነው፡፡

የቢሮ ምክትል ኃላፊ ወርቁ ደስታ የኤሌክትሪክ ሃይል መሙያ ጣቢያዎችን ከከመስራት ባለፈም በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት በመኪና ማቆሚያዎች የኃይል መሙያ እየተሠራ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ዴዔታ በርኦ ሀሰን ደግሞ ከዚህ በኃላ የተሽከርካሪ አስመጪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ሳይተክሉ በሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም ብለዋል።

አሁን ላይ ከ400 በላይ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እያስመጡና እየገጣጠሙ ናቸው ያሉ ሲሆን ሁሉም የኃይል መሙያ አላቸው በማለትም ገልጸዋል።

አዲስ ማለዳ ከወራት በፊት በሰራችው ዘገባ የኤልክትሪክ መኪና ባለንብረቶች የሃይል መሙያ ጣቢያዎች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አለመኖሩ ለመንቀሳቀስ አዳጋች እያደረገባቸው እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

መንግስት በበኩሉ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ከቀረጥ ነጻ በማስገባት አስመጪዎችን እንደሚያበረታታ ቢናገርም ስለተሸከርካሪዎች የሃል መሙያ ጣቢያ ግን ያለው ነገር አልነበረም፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Jan, 14:04


የህግ ባለሙያው አቶ ወንድሙ ኢብሳ ከፓርቲ ፖለቲካ ለምን እንደተገለሉ፣ከብልጽግና ፓርቲ አግኝተውታል ስለተባለው ጥቅምና መሰል ጉዳዮች ላይ ከአዲስ ማለዳ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ተከታይ ክፍል ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ

https://youtu.be/kL_4vfG68kM

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Jan, 13:58


ቀሲስ በላይ መኮንን በተከሰሱበት የምዝበራ ሙከራ ወንጀል በሙሉ ድምጽ ጥፋተኛ ተባሉ

ዕረቡ ጥር 7 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ከአፍሪካ ህብረት ሂሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ለመመዝበር ሙከራ በማድረግ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ የቀረቡ የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን መርምሮ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መርምሮ በክሱ ዝርዝር የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን ተከሳሾቹ ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ በተገቢው ማስተባበል አለመቻላቸውን ጠቅሷል።

በዚህም በዛሬው ቀጠሮ 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙሉ ድምጽ የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባቸው ሲሆን፤ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት በአብላጫ ድምጽ ጥፋተኛ ተብለዋል።

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ለመወሰን ለጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጥሯል ተብሏል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Jan, 12:10


ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የመጀመሪያ የሆነውን ሱፐር አፕ ለአገልግሎት አቀረበ

ዕረቡ ጥር 7 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነውንና በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕቀፍ ያካተተ ዘመናዊ፣ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት ማቅረብ ያስችለኛል ያለውን መተግበሪያ አስመርቋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባደረጉት ንግግር ‘’ዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ በሁሉም የስራ ዘርፎች ለተሰማሩ ደንበኞቻችን ይበልጥ አሰተማማኝ፣ ጥራት ያለውና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት ደንበኛ-ተኮር አገልግሎት ለመስጠት ያስቀመጥነውን ራዕይ ይበልጥ ዕውን ለማድረግ ያስችለናል” ብለዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ሱፐርአፕ በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መተግበሪያ መሆኑን ጠቁመው ለአጠቃቀም ምቹና ለእይታም ማራኪ የሆነው መተግበሪው በግል ሂሳብ እና ለተለያዩ የቢዝነስ ተቋማት አገልግሎት መስጠት እንዲያስችል ሆኖ የቀረበ ነው።

ይህ ሱፐር አፕ በርካታ አገልግሎቶችን ያካተተ የደንበኞችን ማንነትና በህይወት መኖራቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ የነበረውን ክፍተት በማስቀረት ባንኩ የተረጋገጠ የደንበኞች መረጃ እንዲኖረው ያስችላል፡፡

ባነኩ የተለያዩ ፈር ቀዳጅ የባንክ ዘርፍ ቴክኖሎጂዎችን በተደጋጋሚ አስተዋውቂያለሁ ያለ ሲሆን አሁን ለአገልግሎት ያበቃው ዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ በርካታ አዳዲስ የአገልግሎት አማራጮችን ለባንክ ኢንዱስትሪው በማስተዋወቅ ይበልጥ ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት የምችልበት አማራጭ ይሆናል ብሏል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Jan, 10:46


“ለማስተባበር ብንሞክርም እስካሁን የጋራ መግባባት ላይ አልደረስንም” - የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ

ዕረቡ ጥር 7 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በትግራይ ክልል በአክሱም ወረዳ የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ መከልከሉ ይታወሳል፡፡

በአጠቃላይ አራት የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን እና እስካሁንም ድረስ የተደረሰ የጋራ መግባባት እንደሌለ እና ተማሪዎቹም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ እስማኤል አብድራህማን ገልጸዋል፡፡

“የወላጅ መምህር እና ተማሪ ህብረት ያወጣው መመሪያ ነው በማለት ማንኛውም ተማሪ ወጥ የሆነ የአለባበስ ህግ አውጥተናል ተግባራዊ መሆን አለበት በማለት” ክልከላን እንደጀመሩም ሀላፊው አስታውቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሀይማኖታዊ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈቀደ እና እስካሁንም ሲቀጥል የመጣ በመሆኑ ተማሪዎቹንም ስነልቦናዊ ጫና እንዳይደርስባቸው መግባባት ላይ ለመድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በአስተዳደር ደረጃ ማንም ሂጃብ አይልበሱ ብሌ የሚከራከር አመራርም ሆነ ግለሰብ ባይኖርም ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ የሰጠም አለመኖሩን ሀላፊው ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተፈቅዶላቸዋል ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል ሲባል የቆየው ሀሰት መሆኑን እና ማናቸውም ወደ ትምህርታቸው እንዳልተመለሱ ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የክስ አቤቱታውን ለአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን በዝርዝር ተመልክቶ ጊዜያዊ ውሳኔ ሰጥቶ ነበር፡፡

በውሳኔውም "የክስ ክርክሩ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ቢቆይ በተማሪዎቹ ላይ የማይቀለበስ የመብት ጥሰት ሊያስከትል ስለሚችል ተማሪዎቹን ለማገድ የተላለፈው አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲታገድ" ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።

በቤተልሄም ይታገሱ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

14 Jan, 15:02


ሰውዬው 30 ዓመታትን የተሻገረ የፖለቲካ ጉዞ አላቸው፡፡የፓርቲ ፖለቲካ ጥርሳቸውን የነቀሉበት ነው፡፡
ከመኢአድ እስከ ቅንጅት አልፎም እስከ ኢዴፓ ከተራ አባልነት እስከ ስራ አስፈጻሚነት የደረሰ የፖለቲካ ሽግግር ለማድረግ በቅተዋል፡፡

በአገረ አሜሪካ ሲኖሩ የነበሩት ጉምቱ ፖለቲከኛ ወደ አገር የመምጣታቸው ዜና ካሰሙ ቀን ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች እየረቡ ነው አስተያየቶቹና የፖለቲከኛው ውሳኔ ከምን የመነጨ ነው የሚለውን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ለመመልከት ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/MnmqcxZFBXw

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

14 Jan, 10:16


በቅርቡ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መሪዎች ግንኙነታቸውን አድሰዋል። ካይሮም የሶማሊያና የኤርትራን ሚንስትሮችን አስተናግዳለች።

በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያምና በጄኔራል መሐመድ ሲያድ ባሬ ዘመን የታየው የሁለቱ ሃገራት የወዳጅነት እና የጠላትነት አካሄድ ዛሬስ ከምን ያደርሳቸው ይሆን የሚለው በብዙዎች ዘንድ የሚጠበቅ ጉዳይ ነው፡፡
ሙሉ ትንታኔውን ከስር ባለው ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው እንዲከታተሉ ጋበዝን

https://youtu.be/AvgJhAcqDHY

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Jan, 14:04


ከሰሞኑ በወጣው የጀዋር መሃመድ “አልጸጸትም”መጽሃፍ ዙሪያ አነጋጋሪ አስተያያየትና ትችት ሲያቀርቡ የተደመጡት የህግ ባለሙያና ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

ጃዋርን ከግለሰባዊ ማንነቱ እስከ ተቋማዊ አስተዋጽኦ ድረስ አውቀዋለው የሚሉት አቶ ወንድሙ በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ ይህ ነው የተባለው አስቷትኦ አላበረከተም የሚል ሙግትን ያቀርባሉ፡፡

ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ

https://youtu.be/oHfN1PMw-gU

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Jan, 09:06


የ12ኛ ክፍል ተፈታዮች በተሰጠው የቀን ገደብ ምዝገባ ካላጠናቀቁ ለፈተና እንደማይቀመጡ ተገለጸ

ሰኞ ጥር 5 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የ2017 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ በመጪው ማክሰኞ ጥር 6ቀን2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።

በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ካሉ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እንዲመዘገቡ ያሳሰበው አገልግሎቱ፤ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ፈተናውን እንደማይፈተኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት አስጠንቅቋል።

የመደበኛ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን ከታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ሲሆን እስካሁን 499 ሺህ 200 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቆ ነበር፡፡

በተመሳሳይ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በመደበኛና በግል 750 ሺህ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡

ይሁን እንጂ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ከተፈተኑ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች መካከል የማለፊያ ነጥብ ያመጡት 5 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

11 Jan, 06:46


የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በይፋ ተጀመረ

ቅዳሜ ጥር 3 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን በትላንትናው እለት አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት ጽሑፍ ፣ ለኢኮኖሚና ፋይናንስ ምህዳራችን ታሪካዊ በሆነ እጥፋት የኢትዮጵያን የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውልናል ብለዋል።

ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ባላት፣ ለብልጽግና ሰፊ እምቅ አቅምና ምቹ መንገድ እየተነጠፈላት ባለችው ኢትዮጵያ ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

10 Jan, 12:44


“የፓርቲውን አባላት እና አመራሮች በማስፈራራትና በማሰር ትግሉን ማስቆም አይቻልም”- ኢሕአፓ

ጥር 2 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ባወጣው መገለጫ በሐረር ክልል የሚገኙት አባሎቻቸው እና አመራሮች ያለ በቂ ምክንያት በጸጥታ ሀይሎች መወሰዳቸውን አስታውቋል፡፡

በዚህም በክልሉ የሚገኘውን ኢሕአፓ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራር የጸጥታ ሀይሎች ከመኖሪያ ቤታቸው ወስደው እንዳሰሯቸው እና ወደ ፍርድ ቤትም እንዳላቀረቧቸው ገልጿል፡፡

እንዲሁም እንደታሠሩ ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት መጠየቅ ይቻል የነበረ ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በፊት ግን ከነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ አውጥተው ወዴት እንደወሰዷቸው አልታወቀም ተብሏል፡፡

በመሆኑም ሕገ መንግሥትን ማስከበር በሁሉም እርከን ላይ ከሚገኙ የመንግሥት ባለሥልጣኖች የሚጠበቅ ግዴታ ቢሆንም የብልጽግናው መንግሥት አገልጋዮች ሕጉን አላግባብ መጠቀማቸው እና ከስርዓት ውጪ መሆናቸው አሳፋሪ ነው ሲል ፓርቲው ኮንኗል፡፡

በተጨማሪም አባላቶቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እና በፓርቲው አባሎች ላይ የሚደረገው ማስፈራራት፣ ማፈንና ማሰር በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስቧል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

10 Jan, 08:59


ትላንት ምሽት በአርባምንጭና አካባቢው እንግዳ የሆነ ክስተት ተከስቶ ነበር፡፡

ይህ ያልተለመደ ክስተት ከሰማይ በእሳት የተቀጣጠለና ወደ ምድር ሲምዘገዘግ የተስተዋለ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎችም በዚህ ሳቢያ ፍርሃት ውስጥ እንደገቡ ገልጸዋል፡፡

ለመሆኑ ይህ እንግዳ የሆነ ክስተት ምን ይሆን? መነሻውስ ከየት ነው? የሚለውን አዲስ ማለዳ የአካባቢዉን ነዋሪዎች እና ባለሙያዎች አነጋግራለች ከስር ባለው መስፍንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተሉ

https://youtu.be/mAKsv6Slt4U

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

09 Jan, 12:17


ነዳጅን ከተመን በላይ የሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ እስከ ግማሽ ሚሊየን ብር ቅጣት የሚጥል አዋጅ ፀደቀ፡፡

ሀሙስ ጥር 01 2017 ( አዲስ ማለዳ) ነዳጅ ከተመን በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ ነው ቅጣቱ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው በዛሬው እለት በእንደራሴዎች ምክርቤት በጸደቀው የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ነው ፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39691

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

09 Jan, 11:07


https://youtu.be/0bku1TzeGeo

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

09 Jan, 09:35


በትግራይ ብሔራዊ ጉባኤ ተጠርቶ ግዜያዊ አስተዳደሩ እንደገና እንዲዋቀር ሳልሳዊ ወያኔ ጠየቀ

ሀሙስ ጥር 01 2017 ( አዲስ ማለዳ) በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ እና በምርጫ ቦርድ እውቅና ካገኙ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር በተግባር ፈርሷል ሲል ወቅሷል፡፡

በመሆኑም ብሔራዊ ጉባኤ ተጠርቶ ግዜያዊ አስተዳደሩ እንደገና እንዲዋቀር” ሲል ነው የጠየቀው።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39687

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

08 Jan, 06:05


ሰሞኑን በተደጋጋሚ የርእደ መሬት በኢትዮጵያ እየተከሰተ ይገኛል::

ርእደ መሬት ቢከሰት ምን ማድረግ እንዳለብዎት ይህን መረጃ በማንበብ መረዳት ይችላሉ::

ረቡዕ ታህሳስ 30 2017 ( አዲስ ማለዳ)

⚠️ርእደ መሬት ያለምንም ማስጠንቀቂያ ሊከሰት ይችላል፣ ይህም በህይወት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።

ዝግጁ መሆን ደህንነትን ለመጠበቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው—እራስዎን ይጠብቁ ፣ የአደጋ ጊዜ እቅድ ይኑርዎት፣ ርእደ መሬት በሚከሰትበት ጊዜ እና በኋላ ምን ማድረግ እንዳለቦት ይወቁ:-

👉 ባሉበት ዝቅ ይበሉ፣ በእጆችዎ እና ጉልበቶችዎ ይሂዱ። ይህ አካሄድ በሚወድቁ ነገሮች እና ፍርስራሾች ከመመታት እና መውደቅ ይከላከላል፣ ወደ ደህንነት ሳይጎዱ እንዲሄዱ ያስችላል🚨

👉 ጭንቅላትዎን እና አንገትዎን በእጅዎ ይሸፍኑ ፣ ጠንካራ ጠረጴዛ በአቅራቢያ ካለ ከሱ ስር ለጥበቃ በመግባት ይጠለሉ 🛡

👉 ምንም መጠለያ ከሌለ፣ ከመስኮቶች ይራቁ፣ ወደ የቤቱ/ህንጻ ውስጠኛው ግድግዳ ይሂዱ እና እራስዎን ከሚወድቁ ነገሮች ወይም ፍርስራሾች ለመከላከል ጎንበስ ይበሉ 🛡

❗️በጠረጴዛ ስር ከተጠለሉ በመንቀጥቀጡ ጊዜ ሊንቀሳቀስ ስለሚችሉ አጥብቀው ይያዙት።
❗️ጭንቅላትዎን እና አንገትዎን በእጅዎ ይሸፍኑ ፣ መጠለያ ከሌለ መንቀጥቀጡ እስኪቆም ድረስ በሁለቱም እጆችዎ ጭንቅላትዎን እና አንገትዎን በመሸፈን እራስዎን ይጠብቁ።

መረጃው ከየጤና ወግ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የቀረበ ነው:: https://yetenaweg.com/

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

07 Jan, 15:27


ቤንዚን በሊትር 101.47 ብር ሲገባ ናፍጣ በሊትር 98.98 ብር ሆኗል

ማክሰኞ ታሕሳስ 29 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ተደርጓል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ተወስኗል።

በዚሁ መሰረት ፦

አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር፣

አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር፣

አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር፣

የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር፣

አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ ተወስኗል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

06 Jan, 20:17


የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር  በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናንን በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል

ሰኞ ታሕሳስ 28 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)ለሁለተኛ ግዜ የተዘጋጀው የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር በቦሌ ደብረ ሳሌም መድሃኒዓለም ካቴድራል በድምቀት ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ እና ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ምእመናን ተገኝተዋል፡፡

የጃንደረባው ትውልድ ማኅበር ባዘጋጀው የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናንና ምዕመናት ተሳትፈዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

06 Jan, 07:46


አንጋፋው የፖለቲካና የምጣኔ ሀብት ምሁር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ሰኞ ታህሳስ 28 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ሥም የነበራቸው አንጋፋው የፖለቲካና የምጣኔ ሀብት ምሁሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39678

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

04 Jan, 15:16


ከመከላከያ ሚንስትሯ የሞቃዲሾ ጉዞ ጀርባ ያሉ ዲፕሎማሲ ስኬቶችና ቀጣይ ስጋቶች ምንድን ናቸው ?

በሞቃዲሾ ባለስልጣናት በኩልስ ምን እየተነገረ ነው የሚሉና ተያያዥ ጉዳዮችን ከዚህ በታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ

https://youtu.be/umZiqVlz0RI?si=bGpoYPezLcvygELG

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

04 Jan, 09:17


ትናንት ሌሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከዚህ በፊት ከተከሰቱት በመጠኑ ከፍተኛ መሆኑ ተገጸ

ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደቀጠለ ሲሆን ትናንት ሌሊት 9:52 ሰዓት ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍ ያለ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡም በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ መመዝገቡን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት 24 ሰዓታ ውስጥ በኢትዮጵያ ከ5 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች የተከሰቱ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ሶስቱ በሬከተር ስኬል ከ5 በላይ ሆነው ተምዝግበዋል።

ይህም እስካሁን በኢትዮጵያ ከተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ትልቁን የሬክተር መጠን የያዘ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ በአጠቃላይ ከ66 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች የተከሰቱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ስድስቱ በሬክተር ስኬል ከ5 በለይ ሆነው ተመዝግበዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

03 Jan, 11:23


የትግራይ ትምህርት ቢሮ ተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይማሩ ማደረጉ ልክ አለመሆኑን የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለጸ

ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ውጪ በሆነ ሁኔታ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ መግለጫ መስጠቱ ተገልጿል፡፡

በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ የተከለከሉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ 160 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ችግር እንዲፈታ ካለፈው ጥቅምት 2017 ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች እንዳደረገ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ በያዝነው ሳምንት የትግራይ ትምህርት ቢሮ አዲስ ህግ እና ደንብ ባልወጣበት ሁኔታ ተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸው እንዳይማሩ መደረጉ ልክ እንዳልሆነ አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ባለመቀበል ተማሪዎቹ በማስፈራራት እና በማሰር ከእውቀት ገበታ ውጭ እንዲሆኑ ማድረጉ ምክር ቤቱ አመላክቷል፡፡

በመግለጫውም የሂጃብ ክልከላው በህገ-መንግስት የተቀመጡ የጋራ እና የግል መብቶች የሚፃረር ፣ በትምህርት ሚንስቴር እና በክልሉ መከበር ያለባቸው ደንቦች የጣሰ ነው ብሏል፡፡

በመሆኑም በትምህርት ሚንስቴር ደንብ ቁጥር -6 ንኡስ ቁጥር -3 ሂጃብ መልበስ እንደሚፈቅድ በግልፅ የተደነገገ በመሆኑ እና ትግራይ አሁን ባለችበት ፓለቲካዊ ቀውስ በሃይማኖት ምክንያት ሌላ ቀውስ መጨመር ተገቢ ስላልሆነ ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመለስልን ሲል ምክር ቤቱ ጠይቋል፡፡

በተጨማሪም ጦርነቱ ምክንያት ከእውቀት መአድ ርቀው የነበሩ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንዲበረታቱ የሚገባቸው ሙስሊም ሴቶች ማበረታታት ሲገባ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከትምህርት ገበታ መከልከል ፍፁም ኢ-ህጋዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ተግባር መሆኑን አሳስቧል፡፡

በመጨረሻም ፍትሃዊ ጥያቄው በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልሉ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የሚወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

03 Jan, 08:52


በዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ

ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ተናግረዋል።

በዚሁ መሠረት " በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም በተደጋጋሚ መቀጠሉን ጠቅሰው " የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ዛሬ ተከስቷል፤ ንዝረቱም ከሰሞኑ ከፍያለ እና ጠንካራ ነበር " ብለዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Jan, 14:05


አግዋን ዘግታ ለቡግና ተረጂዎች ምግብ የላከችው፣የሰብአዊ መብት ጥሰት በመኖሩ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሹማምንት ደጄን እንዳይረግጡ ባለች ማግስት በፕሪቶሪያው ስምምነት ስለመደሰቷ ለመግለጽ ማንም ያልቀደማት አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት 100 ዓመታትን የተሸገረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በከፍታና በዝቅታ የታጀበ ሆኖ እዚህ ደርሷል፡፡

ከሰሞኑ የዶናልድ ትራንፕ አስተዳደር ወደ መንበሩ መውጣቱን ተከትሎ ቀጣይ የሁለቱ አገራት ግንኙነት በምን መንገድ ሊሄድ ይችላል የሚለውም የብዙዎች ጥያቄ ሆኖ ዘልቋል፡፡

በዚህ የዲፕሎማሲ ሂደት ውስጥ መጪውን የዋሽንግተንና አዲስ አበባ የግንኙነት መስመር ቀድመው የሚተነብዩና በተለያዩ ዘመናት የወጡ ደብዳቤዎችና መልእክቶችም የሰሞነኛው የሁለቱ አገራት የዲፕሎማሲ መዘወር በምን መልኩ እያሳዩ ነው የሚሉና ተያያዥ ጉዳዮችን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ልንቃኘው ወደድን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈኝጠሪያ በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/XcCu72t9VRE?si=QH-iJq00zDCcp8QE

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

01 Jan, 12:14


በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

ዕረቡ ታህሳስ 23 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ አስተዳደር ቢሮ አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱ ተጠቁሟል፡፡

በሰልፉ ላይ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተሾሙት የመቀሌ ከተማ ከንቲባ ስራቸዉን ይጀምሩ የሚል ጥያቄ ተነስቷል።

ለወራት ያለ ከንቲባ መቆየቷ አግባብነት የለውም፣ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ውሳኔዎች ይከበሩ፣ የህዝባችንን አንድነት ለመሸርሸር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አጥብቀን እንቃወማለን፣ መንግስትን ለመገልበጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ይቁሙ፣ መቐለ የሰላምና ልማት ከተማ እንጂ የሁከትና ዓመፅ ከተማ አይደለችም የሚሉ ድምፆች በሰልፉ ላይ መሰማታቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ መቀሌ በጊዜያዊ አስተዳደሩና በነ ደብረፅዮን ቡዱን የተሾሙ ሁለት ከንቲባዎች እንዳሏት ይታወቃል።

በከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል በተፈጠረ ልዩነት በትግራይ ክልል ረዥም ጊዜ ያስቆጠሩ የመልካም አስተዳደደር፣ የሰላምና ፀጥታ ጥያቄዎች ሲነሱ የቆዩ ቢሆንም የክልል ፀጥታ ቢሮ በየተኛውም ቦታ የድጋፍም ሆነ የተቃዉሞ ሰልፎች እንዳይደረጉ ባስተለለፈው ውሳኔ መሰረት ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ሰልፎች ሳይካሄዱ ቆይቶ ነበር፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

01 Jan, 12:04


https://youtu.be/HHdYsREjhig?si=Ab-udfgVtlYnFWAB

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

01 Jan, 08:12


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ አሳሰበ

ዕረቡ ታህሳስ 23 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር መሠረት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡ የሚታወስ ሲሆን ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ  ምርጫ ቦርድ አሳስቧል፡፡

ምንም እንኳን ፓርቲው በስድስት ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ የሚለውን ግዴታ ያለተጨማሪ ማሳሰቢያ መፈፀም እንዳለበት የሚታመን ቢሆንም ቦርዱ ለፓርቲው በተደጋጋሚ በፃፋቸው ደብዳቤዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማከናወን ጠቅላለ ጉባኤውን እንዲያደርግ ማስታወቁን ገልጻል፡፡

"ፓርቲው በልዩ ሁኔታ የተመዘገበው ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም በመሆኑ ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ ይጠበቃል " ያለው ምርጫ ቦርድ " ለዚሁ የጠቅላላ ጉባኤ ዝግጅት የሚያስፈልገውን የቅድመ ጉባኤ ዝግጅት የተመለከቱ ስራዎችን ቦርዱ መከታተል እንዲችል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ከማድረጉ 21 ቀናት በፊት ጉባኤው የሚደረግበትን ቀን ለቦርድ እንዲያሳውቅ ይጠበቃል" ብሏል።

ይሁን እንጂ ፓርቲው ከተመዘገበ ስድስት ወር ቢሆነውም ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ የሚያስችለውን እንቅስቃሴ እያደረገ አለመሆኑን አመላክቷል፡፡

ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ የሚገባው ወቅት ሊገባደድ ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ የቀረው በመሆኑ ፖርቲው ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በቀረው አጭር ጊዜ የጠቅላለ ጉባኤውን እንዲያደርግ ቦርዱ በጥበቅ አሳስቧል።

ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Dec, 14:09


የፖለቲከኛው ጃዋር መሃመድና  የተቀዋሚዎቹና የነቃፊዎቹ የቃላት ጦርነት እንደቀጠለ ነው፡፡

ከዲፕሎማት እስከ አክቲቪስት ከቴሌቭዥን ጣቢያ እስከ ጨፌ ኦሮሚያ ተቀማጭ ድረስ የትችት ካራቸውን ስለው የምላሳቸውን አፎት መዘው ከፖለቲከኛው ጋር የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል፡፡

ከመጽሃፉ መውጣት በኋላ ብዙ አስተያየቶች እየተነሱበት ያለው ፖለቲከኛው እሱን ከሚነቅፉና በመንግስት ሃላፊነት እያገለገሉ ካሉ ሰዎች የተሰሙ አስገራሚ አስተያየቶችና ምላሾች በአዲስ ማዳ ትንታኔአችን አዘጋጅተነዋል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/hm9ph-wEKLE

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Dec, 12:02


በወላይታ ዞን ሁምቦ እና አበሳ አባያ በተከፈተ ተኩስ የሰው ህይወት ማለፉ ተገለጸ

ማክሰኞ ታህሳስ 22 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) እናት ፓርቲ ደረሰኝ ባለው መረጃ በወላይታ ዞን፣ አበላ አባያ ወረዳ፣ አባያ ክላስተር በሚባል የእርሻ ልማት ከሲዳማ ክልል መጡ በተባሉ የልዩ ኃይል አባላት እንደተከፈተ በተገለጸ ተኩስ የሰው ሕይወት ማለፉን እና በርካታ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል እንደሚገኙ ገልጻል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39671

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Dec, 09:55


ከሰሞኑ በምስራቃዊው የኢትዮጵያ ክፍል ተደጋግሞ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ስጋቱና የንዝረት ስሜቱ ኪሎሜትሮችን አቋርጦ በአዲስ አበባ እየተሰማ ይገኛል፡፡

በተለይም በአፋር ክልል ፈንታሌ ወረዳ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ተደቅኖባቸዋል፤ ይህን ተከትሎ በአካባቢው ምን ስጋት አለ የተፈናቀሉ ነዋሪዎችስ ምን አይነት እርዳታ እያገኙ ነው እና ተያያዥ ጉዳዮችን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠርያ በመንካት ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ

https://youtu.be/x-UvnbwgflI

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

30 Dec, 14:21


የተራቡ ዜጎች በተለይም ህጻናት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መበራከት፣ግጭቶችና የኑሮ ውድነት ተዳምረው አገሪቱን አስከፊ ገጽታ ውስጥ እየከተታት ነው የሚሉ አስተያቶች መደመጣቸውን ቀጥለዋል፡፡

በሌላኛው ጫፍ ያሉ የመንግስት ተጠሪዎች ደግሞ የተራበ የለም ፣ምርቱም ሙሉ ነው የሚሉና ተያያዥነት ያላቸው አስተያየቶችን ሲሰጡ ይደመጣሉ፡፡

ለመሁኑ እየተፈጠሩ ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን ለማቅለል በእርግጥስ ስራ እየተሰራ ነው? ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቅርቡ አስደንጋጭና አነጋጋሪ መረጃ የወጣበት አካባቢና የመንግስት ባለስልጣኑን አነጋጋሪ ምላሽ አካተን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ተመልክተነዋል፡፡

ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ፡፡
https://youtu.be/Zc1W0T3icI8

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

30 Dec, 14:19


“የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ አገልግሎት መኖሩን የሚያውቁ ዜጎች ባለመኖራቸው ብዙ ጉዳት እየደረሰ ነው”- የኢንሹራንስ ባለሙያዎች

ሰኞ ታህሳስ 21 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣው የእሳት አደጋ በንብረት እና በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ችግር ከባድ እየሆነ መጥቷል፡፡

በንብረት ላይ በሚደርስ የእሳት አደጋ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ያላቸው ንብረቶች መውደማቸው በመርካቶ እና በተለያዩ አካባቢዎች የደረሱት የእሳት አደጋዎች የቅርብ ጊዜ ማሳያ ናቸው፡፡

ይህን ተከትሎ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የኢንሹራንስ ባለሙያዎች አብዛኛውን ባለንብረት ስለእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ይህ ነው የሚባል እውቀት የሌለው በመሆኑ ከንብረት መውደም በዘለለ ለማንሰራራት ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገቡ አስረድተዋል፡፡

“የኢንሹራንስ ኩባንያዎችም ስለ አገልግሎቱ መረጃዎችን በግልጽ ከማስረዳት እና ከማስተዋወቅ አንጻር ክፍተት እንዳለባቸው የሚያነሱት የኒያላ ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈጻሚና የኢንሹራንስ ባለሙያው ያሬድ ሞላ ይህ ደግሞ ከእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ጋር በተገናኘ እዚህ ግባ የሚባል ግንዛቤ በመድህን ሰጪዎቹ በኩልም ባለመኖሩ እንደሆነ ጠቁመዋል ፡፡

የእሳት አደጋ መድህን አገልግሎት በኢትዮጵያ የመድህን ዘርፍ እውቅና ከተሰጣቸው ውስጥ አንዱ ቢሆንም በተገቢው ሁኔታ አገልግሎት ስላለመስጠቱ ተደጋግሞ ይጠቀሳል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደ ስራ አስፈጻሚው ገለጻ “ብዙ ሰው እንደሚያውቀው የእሳት አደጋ ኢንሹንስ የሶስተኛ ወገን የመድህን አገልግሎት ግዴታ የሚያደርግ ህግ ቢጸድቅ የተሻለ ውጤት ሊመጣ እንደሚችልም አንስተዋል፡፡

የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ እንደማንኛውም የኢንሹራንስ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አንድ ግለሰብ ኢንሹራንስ በሚገባበት የንብረት መጠን የተለያየ የክፍያ ሂደት እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡

በቤተልሄም ይታገሱ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

30 Dec, 08:37


የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር በ100 አመታቸው ህይወታቸው አለፈ

ሰኞ ታህሳስ 21 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ከዲሞክራት ፓርቲ የወጡት ጂሚ ካርተር በ1976 አሜሪካ ምርጫ አሸንፈው ወደስልጣን መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

በነበራቸው አንድ የስልጣን ዘመን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እና በኢራን ታግተው የነበሩ አሜሪካውን ጉዳይ ለአስተዳደራቸው ፈተና ከነበሩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ባለ ሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበት ፣ የወለድ ምጣኔ ከ 20 በመቶ መሻገር እና የጋዝ ዋጋ ማሻቀብ እንዲሁም የኢራን የእገታ ቀውስ በአሜሪካ ላይ ውርደትን ያመጡ ቀውሶች ተብለው ይታሰቡ ነበር፡፡

በሌላ በኩል ለሰብአዊ መብት መከበር በነበራቸው ጠንካራ ሙግት እንዲሁም በ1978 በካምፕ ዴቪድ ስምምነት ግብጽ እና እስራኤል ሰላም እንዲፈጥሩ በማድረግ የኖቤል ሽልማትም አግኝተዋል፡፡

በወቅቱ በጦርነት ላይ የነበሩትን የሁለቱን ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ወደ ካምፕ ዴቪድ በመጥራት የሰላም ስምምነት እንዲፈጽሙ ካደረጉ በኋላ እስራኤል ከሲናይ በርሀ ወታደሮቿን እንድታስወጣ ሀገራቱም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጀምሩ አድርገዋል፡፡

በኢትዮጲያም የ1997 ዓ.ም ብሄራዊ ምርጫን በታዛቢነት እንዲሁም የኢትየ-ኤርትራ ጦርነትን በማስቆም ረገድ ሚና እንደነበራቸው አይዘነጋም፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

27 Dec, 13:07


7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት ኤክስፖ ተከፈተ

ዓርብ ታህሳስ 18 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በዛሬው እለት 7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ በሻራተን ሆቴል የመክፈቻ ዝግጅቱን ያደረገ ሲሆን እስከ እሁድ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የግሉ የቤት ልማት ዘርፍ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲረዳ ታስቦ መዘጋጀት የጀመረው ኢቲ ሪል ስቴት እና ሆም ኤክስፖ የሪል ስቴት አልሚዎችን ከገዥዎች፣ ከሻጮች፣ እና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ኤግዚቢሽን መሆኑ ተገልጿል።

በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ በተደረገው ውይይት ሪል ስቴቶች በታሰበው ፍጥነት እድገት እንዳያስመዘግቡ ተግዳሮቶች መኖራቸውን እና ከእነሱም ውስጥ የፋይናንስ እጥረት እና የረጅም ጊዜ የብድር አገልግሎት ህግ አለመኖር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም ለውጭ ሀገር ባንኮች ገበያው ክፍት መደረጉ መልካም ለውጥ ይዞ እንደሚመጣ እና ከውጪ ባንኮች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ እንደሚፈጠር ተስፋ መኖሩን የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡

የመኖሪያ ቤት የዋጋ ንረትን የሚያስከትለው ሌላኛው ነገር የጥሬ እቃ እና የግንባታ እቃዎች የዋጋ ውድነት እንደሆነ እና ሁሉንም የማህበረሰብ አቅም ያማከለ ንድፍና ዋጋ ለማቅረብ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል የተለያዩ በግንባታ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በአንድ ላይ መሰብሰብ ተጠቃሚው የተሻለ አማራጮችን እንዲያገኝ እንደሚያደርግ የካዝና ግሩፕ ሊቀመንበር አዲስ አለማየሁ ጠቁመዋል፡፡

ኤግዚቢሽኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለመቅረፍ ወሳኝ የሆኑ ዘላቂ የግንባታ አሰራሮችን፣ ተመጣጣኝ የቤት መፍትሄዎችን እና የፋይናንስ አማራጮችን የሚያጎላ ነው የተባለለት ሲሆን ከመንግስት ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት በኤግዚቢሽኑ ተገኝተዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

27 Dec, 09:51


የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ያለማስያዣ ማበደሩን አስታወቀ

ዓርብ ታሕሳስ 18 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በሚቹ መተግበሪያ አማካኝነት ያለማስያዣ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩን አስታውቋል።

ባንኩ ከ750 ሺህ በላይ ለሆኑ የሚቹ ደንበኞች ያለምንም ማስያዣ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር በመስጠት ከሁሉም ባንኮች ግንባር ቀደም መሆን መሆን መቻሉንም ይፋ አድርጓል።

የህብረት ስራ ባንኩ በሚቹ የፋይናንስ አቅርቦት አማካኝነት ለጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት የንግድ ፈቃድና የብድር ማስያዣ ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ የብድር አቅርቦት በማግኘት ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

ባንኩ ከዚህ ባለፈም ያለማስያዣ የሚሰጠውን ብድር ተበዳሪ ተቋማትና ግለሰቦች በቀላሉና በተያዘለት ጊዜ መሠረት በመክፈል ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 6ኛውን የህብረት ሥራ ማህበራት ቀን  "የኅብረት ሥራ ማህበራት፣ ለሁሉም  የተሻለ ነገ አቅኚዎች" በሚል መርህ በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ በደማቅ ስነስርዓት በማክበር ላይ ይገኛል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

26 Dec, 07:24


ሐሙስ ታህሳስ 17ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አንጋፋውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን ማገዱ ተገልጿል፡፡

ኢሰመጉ የታገደው ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አድርጓል በማለት ሲሆን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአመራሮቹና ሠራተኞቹ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጽሙ ለበርካታ ወራት ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

የኢሰመጉ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚሁ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ በቅርቡ መግለጹ ማስታወሱን እና በትናንትናው እለት መታገዱን ዋዜማ ዘግቧል፡፡

ባለሥልጣኑ በዲሞክራሲና መብቶች ዕድገት ማዕከል እና ጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኙት ሲቪል ማኅበራት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር በተመሳሳይ ምክንያት ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ፣ ድርጅቶች የተሰጧቸውን የማስተካከያ ርምጃዎቾ ተግባራዊ አላደረጉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ጥፋታቸውን ቀጥለውበታል በማለት በቅርቡ በድጋሚ እንዳገዳቸው አይዘነጋም።

በተመሳሳይ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ጨምሮ ሶስት የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች ላይ እገዳ ተጥሎ እንደነበር እና ቆይቶም እገዳው የተነሳ ቢሆንም በድጋሚ እገዳው ተጥሏል የሚል መረጃዎች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Dec, 17:37


https://youtu.be/-PuSwuyC90s

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Dec, 09:26


#ማስታወቂያ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

24 Dec, 09:48


https://youtu.be/RfkJhmHQt8M?si=AOu7DoOJmbXwlq5o

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

24 Dec, 08:04


#ማስታወቂያ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

23 Dec, 18:26


በፈንታሌ ተራራ ፍንዳታና ጭስ የታየበት በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ  የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

ሰኞ ታሕሳስ 14 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) እንዳሉት፥በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳና አካባቢው ከታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ነው፡፡

በዛሬው ዕለትም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛውና በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎም ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት ማሳየቱን ነው ያስረዱት፡፡

በአካባቢው የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው÷ነዋሪዎች ላይ ችግር እንዳያስከትል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

በአፋር ክልል የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ አቡበከር በኩላቸው÷ዛሬ ከሰዓት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የፍንዳታ ድምጽ ያስከተለ እና ጭስ የታየበት ነው ብለዋል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጡ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱ እና ጭስ መታየቱም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ድንጋጤ መፈጠሩን ማብራራታቸው ተገልጿል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

23 Dec, 14:16


ከአሰብ ወደብ፣ከቀጠናዊ ጉዳይ እንዲሁም ከቀይ ባህር አሰላለፍ ጋር በተያያዘ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጥብቅ ስብሰባ የተሰማው መረጃ አነጋጋሪ ሆኗል።

ከዚህ በታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ ።

https://youtu.be/S7_S1GOzBOo

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

23 Dec, 11:50


በእስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላቱ ክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው ህመማቸው ብሶባቸዋል ተባለ

ሰኞ ታህሳስ 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ለከፍተኛ ሕመም" መዳረጋቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡

የቅርብ ቤተሰብ እንደሆኑ የተገለጹት እስረኞቹ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ "የማያቋርጥ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው" ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ሁለቱ ፖለቲከኞች "በተደጋጋሚ አቤቱታ" ከሁለት ሳምንት በፊት ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል፡፡

ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሁለቱ ግለሰቦቹ በሆስፒታል ይቆዩ ቢባልም "ያንን እምቢ ብለው በሰዓታት ልዩነት በማይመች መኪና ጭነው ወደ ማረሚያ ቤት መልሰዋቸዋል" ሲሉ ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አንድ ክርስቲያን ታደለ የቅርብ ቤተሰብ "ቁስሉም አልደረቀም እና ደግሞ ደም እየፈሰሳቸው ነው ሐኪሞቹም ተናግረዋል፤ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም እንደሚችል እና ይህ ሲያጋጥምም እንድታመጧቸው ብለው ነበር ነገር ግን ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ወደ ሆስፒታል አለመወሰዳቸውን" ገልጸዋል፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ሰኞ ታህሳስ 7/ 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "ታራሚዎችን ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ ወደሚጠራው ማረሚያ ቤት እንደሚያዘዋውር አስታውቆ ነበር።

ይህን ተከትሎም "በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ" መሆኑን ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ በዚሁ መግለጫው ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ የተቋረጠው አገልግሎት ከዛሬ ታህሳስ 14 እንደገና እንደሚጀምር በመግለጫው ገልጾ ነበር።

ነገር ግን የአቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ ቤተሰቦች ዛሬም ምግብ ማስገባት እና እስረኞቹን መጠየቅ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Dec, 14:49


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ታውቀዋል፡፡

እሁድ ታሕሳስ 13 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)
በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጉባዔተኛው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
በእጩነት ከቀረቡት 14 ወንድ እና 12 ሴት ተመራጮች መሃል
1. አትሌት መሰረት ደፍር -18
2. ወ/ሮ ሳራ ሀሰን - 16
3. ወ/ሮ አበባ የሱፍ - 13
4. ዶ/ር ኤፍራህ መሀመድ -12
5.  አቶ ቢንያም ምሩፅ ይፍጠር- 10
6. አቶ አድማሱ ሳጅን - 10
7. ኢንጂነር ጌቱ ገረመው - 9
8. ዶ.ር ትዛዙ ሞሴ - 11
ድምጾችን በማግኘት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመርጠዋል።

በብሩክ ገነነ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Dec, 10:36


አትሌት ስለሺ ስህን አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን ተመርጠዋል።

እሁድ ታሕሳስ 13 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዛሬ ቀጥሎ በተካሄደው የሁለተኛ ቀን 28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አትሌት ስለሺ ስህን ለቀጣይ አራት አመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ አብላጫውን ድምፅ ማግኘታቸው ታውቋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Dec, 09:40


“የትግራይ ሰራዊት በዲዲአር ስም እንዲበተን እየተደረገ ነው” - በደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት

ቅዳሜ ታህሳስ 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ ታጣቂዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና በመልሶ ማዋሃድ ሥራ ስም፣ የትግራይ መሰረታዊ ጥያቄ ሳይመለስ የቀድሞ ተዋጊዎች እንዲበተኑ እየተደረገ ነው ሲል ክስ አሰምቷል።

የህወሓት አንዱ ክፋይ በመቐለ ከተማ፣ “የእምቢታ ዘመቻ” ብሎ የጠራው ስብሰባ ሲያጠናቅቅ፣ “ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲፈፅም የተሰጠው ሥራ ሙሉ በሙሉ ወድቋል” በማለትም ገልጿል።

በሌላ በኩል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለሦስት ቀናት ያካሔደውን ስብሰባ አስመልክቶ በአወጣው መግለጫ፣ “ክልሉን ወደ ግርግር እና የአመፅ ተግባር ለማስገባት የሚንቀሳቀሱ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አይታገስም” ብሏል።

የሁለቱ ቡድኖች ፖለቲካዊ ሽኩቻ  አሁንም ድረስ መፍትሄ ሳያገኝ እንደዘለቀ ነው፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

07 Dec, 12:51


https://youtu.be/bh6R0NR4fuc?si=vPhxXmHPuOFMdILi

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

06 Dec, 14:12


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው ሰሞነኛ ሪፖርት ብዙዎችን ያስደነገጠ ሆኗል፡፡

በአገሪቱ በተለይም በኦሮሚያ ክልል የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በየከተሞች ስለመከናወኑ፣የጸጥታ አካላት ስለጠየቋቸው በ100 ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብና መሰል ድራማዊና ፣አሳዛኝ መረጃ ከሌሎች ታሪካዊ ሁነት ጋር አገጣጥመን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ተመልክተነዋል፡፡

ከዚህ በታች ያለውን ማስፈኝተሪያ በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/OC0LZNBNLrs?si=rgwkdUKT46bDGk_T

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

06 Dec, 14:01


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው ሰሞነኛ ሪፖርት ብዙዎችን ያስደነገጠ ሆኗል፡፡

በአገሪቱ በተለይም በኦሮሚያ ክልል የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በየከተሞች ስለመከናወኑ፣የጸጥታ አካላት ስለጠየቋቸው በ100 ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብና መሰል ድራማዊና ፣አሳዛኝ መረጃ ከሌሎች ታሪካዊ ሁነት ጋር አገጣጥመን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ተመልክተነዋል፡፡

ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/FDq1Pjpz3l4?si=flHNTmYjkzASJyZm

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

06 Dec, 12:30


ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት የሚፎካከሩት ሦስት ዕጩዎች የምርጫ ክርክር ሊያደርጉ ነው።

ዓርብ ህዳር 27 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት የሚፎካከሩት ሦስት ዕጩዎች በቀጣዩ ሳምንት ታኅሳስ 4 በኅብረቱ አዳራሽ የምርጫ ክርክር እንደሚያደርጉ ኅብረቱ አስታውቋል።

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትርና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዱንጋ፣ የጅቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሞሐሙድ ዓሊ የሱፍ እና የማዳጋስካሩ የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ ናቸው የምረጡን ክርክር የሚያደርጉት።

እጩዎቹ ቀደም ሲል ወደየአባል ሃገራቱ እየዞሩ ድምፅ የማሰባስብ ተግባር እንደጀመሩ የሚታወቅ ነው።

የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ፤ የሥልጣን ጊዜያቸውን በመጭው ጥር ወር በሚያጠናቅቁት ሙሳ ፋኪ ምትክ ቀጣዩን የኮሚሽኑን ሊቀመንበር የሚመርጠው በየካቲት ወር እንደሆነ ይታወቃል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

05 Dec, 11:41


የኢዜማው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የብሄር ፖለቲካ፣የማህበረሰብ ስልጣኔን እንዲሁም አለም አቀፋ ርዕዮተዓለም አለምን በተመለከተ የሰጡትን ማብራሪያ ከዚህ በታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ ።

https://youtu.be/0gogR8VcWLU

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

05 Dec, 09:11


ከእስር ቤት በር ላይ የተወሰዱት አቶ ታዬ ደንድአ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸው ተገለጸ፡፡

ሀሙስ ህዳር 26 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ተወስኖላቸው ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመውጣት ላይ እያሉ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎት ከበር ላይ የተወሰዱት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳኣ ሜክሲኮ ወደሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ገልፀዋል።

ዛሬ ጠዋት ወደ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ አምርተው ከታዬ ደንዳኣን ጋር መገናኘታቸውን ነው ባለቤታቸው ያስታወቁት።

“ትናንት ከሰዓት 11 ሰዓት አካባቢ ከእስር ቤት ሊወጣ ሲል ከቤተሰብ ጋር ሳይገናኝ ትፈለጋለህ በለው ወስደውት ሄዱ። ከበላይ አካል የተጻፈ ያሉትን ደብዳቤ ይዘው ነበር። ምን እንደሆነ ግን አላነበብንም” ሲሉም የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል።

አቶ ታዬ ደንደአ ከቀናት በፊት የፌድራሉ ጠቅላይ ፍርድቤት በተከሰሱበት ወንጀል በዋስትና እንዲለቀቁ መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

04 Dec, 13:55


ሰላም ሚኒስቴር የተባለው መንግስታዊ ተቋም ሞፈረን በልጆቻቸው አንገት አስገብተው የሰላምን አስፈላጊነት ከተናገሩ፣በጋሞ እርጥብ ቄጤማ ይዘው የደም አቢዮትን ከተከላከሉ ሃገር ሽማግሌዎች በተለየ ምን ሰራ?

በአገሪቱ የሚፈጠሩ ቀውሶችን ለማስቆምስ ለምን አልቻለም?

ሚኒስትሮችን በመቀያየር ለውጥ ማምጣት ይቻላል ወይ የሚለው እሳቤስ መጨረሻው ወደ የት የሚወስድ ነው? የሚሉና ከተቋሙጋር

የተያያዙ ያልተሰሙ አስገራሚ ጥያቄዎችንና መረጃዎችን በአዲስ ማለዳ ትንታኔአችን ልንመለከተው ወደናል፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/veN8IQJMQZI

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

04 Dec, 13:49


በላሊበላ ከተማ በጸጥታ ችግር ምክንያት ሆቴሎች እና አስጎብኝዎች መስራት አለመቻላቸው ተገለጸ

ረዕቡ ህዳር 25 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በላሊበላ ከተማ 45 ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆማቸውን የላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በተመሳሳይ በጦርነቱ ምክንያት ወደ ስፍራው የሚመጡ ቱሪስቶችን ማጣቱን እና በዚህም 200 የሚደርሱ የላሊበላና አካባቢዉ አስጎብኝዎች ለከፋ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጋቸዉን የላሊበላ ከተማ አስጎብኝ ማኅበር ማስታወቁን ዶችቬለ ዘግቧል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39579

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

04 Dec, 12:04


የአቶ ጌታቸው ረዳን የፕሬዚዳንትነት ውክልና አንስቻለሁ’’ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት
ረቡዕ ኅዳር 25/2017 (አዲስ ማለዳ) በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ትላንት ምሽት ባወጣዉ መግለጫ ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረውን የፕሬዚዳንትነት ውክልና ማንሳቱን ገልጿል፡፡
በመሆኑም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንደሚተኩ ከፌደራል መንግስት ጋር እየተወያየበት እንደሚገኝ አስታዉቋል።
ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39575

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

04 Dec, 11:12


በአንድ አመት ውስጥ 28 ባንኮች 1.3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸው ተገለፀ

ረቡዕ ህዳር 25 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)ባለፈው ዓመት 28 ባንኮች በድምሩ 1.3 ቢሊዮን ብር እንደተጭበረበሩ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አመታዊ የፋይናንሺያል ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ባንኮቹ እንደተጭበረበሩ የገለጸ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ3መቶ ሚሊዮን ብር ብልጫ አለው ተብሏል።

በሪፖርቱ መሰረት በሀገሪቱ ከሚገኙ ሰላሳ አንድ ባንኮች ውስጥ 28ቱ የተጭበረበሩ እና ሀሰተኛ ምንዛሪ መጠቀምን ጨምሮ የተሰረቁ የኤቲኤም ማሽኖች፣ የውሸት ቼኮች፣ የተጭበረበሩ የስልክ መልዕክቶች እና ሌሎች ተዛማጅ መንገዶች እንደሚገኙ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ብድር ለመስጠት ከአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር የሚያደርጉት ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ከበይነመረብ ማጭበርበር ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለመጣው የገንዘብ ኪሳራ አስተዋፅዖ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

03 Dec, 14:10


በአገልግሎት አሰጣጥ ድክመት፣በሙስናና መሰል ህገወጥ የትቅም ትስስር በቀዳሚዎቹ የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ የሚመደበው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቢሮክራሲያዊም ሆነ ፖለቲካዊ መፍትሄ ርቆት እሱም ታሞ ህመሙን ለተገልጋዮቹ ያጋባ ድኩማን ድርጅት ሆኖ ዘልቋል፡፡

በምን ሂደት ነው የዚህ ተቋም ስርወ ችግር ከስሩ ተመንግሎ የሚነቀለው?

ከረቫት አድርጎና ፕሮቶኮሉን ጠብቆ ወደ ተቋሙ በእግርህ ብቻ ሳይሆን በእጅህም ግባ የሚል አመራር ቆርጦ መጣልስ ለምን የማይሆን ሆነ?

ተገልጋዮችስ አስገራሚ ነው የሚሉት የጸጥታ አካላት የወንጀል መረብ የማይታወቅ ወይስ እንደ ዶሚኖ ጨዋታ አንዱ ከተነካ ሁሉም የሚፈራርስ?

እነዚህን ቁልፍ ጥያቄዎች እና የህዝብ እሮሮዎች በአዲስ ማለዳ ትንታኔያችን ይቀርባል::

ሙሉ ዝግጅቱን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/cgVkO2aFTiU

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

03 Dec, 14:04


✍️ የአለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች  ቀን በየአመቱ December 3 ይከበራል።

✍️✍️ዘንድሮም ''የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጉላት አካታችና ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ!'' በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

👉 አካል ጉዳት ማለት የአእምሮ፣ የስሜት ህዋሳት እና የአካል መጎዳት ሲሆን ግለሠቡን በማህበረሰቡ ውስጥ እኩል ተሳትፎ እንዳያደርግ የሚገድብ ሁኔታ ነው፡፡

👉 አካል ጉዳተኝነት ማለት በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ ምክንያቶች ማየት ፣መናገር መስማት የማይችል ወይም በእግሩ ላይ ወይም በአእምሮ ዝግመት የሚሰቃይ ሰው ነው።

💥  አካል ጉዳተኞችን ማካተትን በሚመለከቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ድጋፍን ማሰባሰብ፣ ስለ አካል ጉዳተኞች ግንዛቤ የማሳደግ ስራን ማበረታታት እንዲሁም ትኩረትን ወደ ሁሉን አቀፍ እና ተደራሽ ማህበረሰብ ጥቅሞች ማዳረስ አስፈላጊ ነው።

@yetenaweg

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

03 Dec, 13:50


ምክንያት የለሽ የዋጋ ጭማሪ የህዝቡ ኑሮ እንዲመሰቃቃል አድርጎታል” _ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል

ማክሰኞ ህዳር 24 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ የኑሮ ውድነቱን እያጎላው ከመሆኑም በላይ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚደረገው ምክንያት የለሽ የዋጋ ጭማሪ የህዝቡ ኑሮ እንዲመሰቃቃል አድርጓል ሲሉ የፓርላማ አባሉ አበረ አዳሙ ተናግረዋል።

እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ገበያ ላይ እንደልብ አይገኑም፤ ቢገኙም ዋጋቸው እንደ ቀላል የሚቀመሱ አይደሉም ብለዋል፡፡

በተጨማሪም “ልጆቼን የማበላቸው አጣው የሚሉ አዛውንቶች እና ጋሽዬ ቁራሽ ዳቦ መግዣ ስጠኝ ራበኝ የሚሉ ህጻናትን ማየት የተለመደ እየሆነ መጥቷል” ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

ይህን የተናገሩትም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው ውይይት ላይ ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባቀረቤት ጥያቄ ነው፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

03 Dec, 09:13


የሲሚንቶ ዋጋ በሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች እንዲወሰን ተደረገ

ማክሰኞ ህዳር 24 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለሲሚንቶ ፋብሪካ ድርጅቶች በጻፈው ደብዳቤ ከጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ  ምርታቸውን በፍትሃዊ ዋጋ  እንዲያቀርቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የሲሚንቶ ምርት የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተወሰነ ለገበያ ሲሰራጭ የቆየ ቢሆንም በአዲሱ የአሰራር ሂደት ግን አምራች ፋብሪካዎች ሙሉ ሀላፊነቱን በመውሰድ በነጻነት ምርታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ እና ገበያውን እንዲያረጋጉ ሃላፊነት መስጠቱን ሚኒስቴሩ እውቁልኝ ብሏል፡፡

የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በተጠያቂነት ስሜት እና በፍትሃዊ የዋጋ ተመን ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉም መወሰኑን ገልጾ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ይውል የነበረውን መመሪያ 940/2015 ማንሳቱን ይፋ አድርጓል ፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

03 Dec, 08:54


ትግራይ አሁን ድረስ በዘለቀ የፖለቲካ ህመም እየተሰቃየች ነው፡፡

ድሎት፣ ምቾትና ስልጣንን ከህዝብ ጥያቄ ያስቀደሙት የክልሉ ልሂቃን በድህረ-ጦርነት ለሚማቅቀው ህዝብ መፍትሄን ማምጣት ተስኗቸዋል፡፡

ለመሆኑ ከድህረ ጦርነት በኋለ ህዝቡን ለዳግም ስጋትና የሰላም እጦት የዳረጉት የህወሃት አመራሮች ወዴት እየሄዱ ነው?

የጥይት ድምጽና የባሩድ ሽታ የሰለቸው የክልሉ ህዝብ መዳንን ከማን ይሆን የሚያገኘው?ከሰሞኑ የቀድሞ ፕሬዝዳንት የተባሉት ጌታቸው ረዳ በመቀለ በአንድ ስብሰባ ላይ ያሰሙትን የቁጣ ንግግር አንድምታና ተያያዥ ጉዳዮችን በአዲስ ማለዳ ትንታኔአችን ቃኝተነዋል

ሙሉ ዝግጅቱን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/H7HrdgKugic

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Dec, 14:42


አፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ትኩሳት ግፊቱ እየጨመረ ነው፡፡

ከአስመራ ሆነው ኢትዮጲያን ጨምሮ ስለቀጠናዊ ጉዳዮች አነጋሪ ነጥቦችን ያነሱት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ የፖለቲካ አሰላለፍን ስለመፍጠራቸው ማረጋገጫንም ሰጥተዋል፡፡

በቀንዱ እየታየ ያለው ውጥረትና የግጭት ድባብን አስጊ በሆነበት በዚህ ሰአት የፕሬዝዳንቱ ቃለ-ምልልስ ደግሞ ሌላ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል፡፡

ለመሆኑ የፕሬዝዳንቱ ቆይታ ያልተሰሙ ምን ምን አነጋጋሪ ጉዳዮች ተነሱበት የሚሉና? ከናይሮቢ የተሰማውን ተያያዥ ርእሰ ጉዳይ በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ተቃኝተዋል፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/A24puI9jCpg

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Dec, 14:04


በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግደያ ወንጀል የፈጸመ ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተፈረደበት

ሰኞ ህዳር 23 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል የመቀሌ ከተማ መካከለኛ ፍርድ ቤት በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸሙ ተከሳሾች ላይ የፍርድ ዉሳኔ ሰጥቷል።

የ16 አመት ታዳጊዋ ማህሌት ተክላይ መጋቢት 10 ቀን2016 ዓ.ም ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች በነበረችበት ወቅት ታግታ በመውሰድ ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ተገድላ መገኘቷ ይታወሳል።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39565

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Dec, 13:47


👉 እ.ኤ.አ. ከ1988 ጀምሮ በየዓመቱ December 1 ቀን አለም አቀፍ የHIV ቀን ታስቦ ይውላል።

✍️✍️የዘንድሮው ቀን ለ37ኛ ጊዜ ሲከበር ፣ ኤችአይቪ ኤድስን በመዋጋት ረገድ እኩልነትን እና የጤና መብትን ማስከበር አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥቷል.

👉ይህ ቀን በኤች አይ ቪ ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት የተከሰተውን የኤድስ ወረርሽኝ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና በበሽታው የሞቱ ሰዎችን ለማሰብ የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ ቀን ነው።

📊በ2023 መጨረሻ የተካሔደ ጥናት እንደሚጠቁመው  39.9 ሚሊዮን ሰዎች ከ HIV ጋር ይኖራሉ ።  እስከአሁንም የ 43.2 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። ይህም የበሽታውን አስከፊነት ያሳያል።

✍️በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ስርጭት ከ1980ዎቹ መገባደጃ ጀምሮ በ2000 ወደ 11 በመቶ ከፍ ብሏል፣ ከዚያ በኋላ በመጠኑ እየቀነሰ በ2024 ወደ 10 በመቶ ገደማ ደርሷል። በመቀነሱም ምክንያት መዘናጋት ታይቷል፣ጥንቃቄ ማድረጉ እየተተወ መቷል። ስለዚህም ግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት ግድ ይላል።

🩺 ግንዛቤን ያሳድጉ፡ ኤች አይ ቪን ስለ መከላከል፣ ምርመራ እና ህክምና በማህበረሰብዎ ውስጥ ይወያዩ።

✍️የሁሉንም ሰው የጤና መብት በመጠበቅ እና አዳዲስ ኢንፌክሽኖችን እንዳይፈጠሩ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ከኤድስ ነፃ የሆነ ትውልድ ማሳካት እና ለኤችአይቪ ኤድስ የሚደረገውን ምላሽ ዘላቂነት ማረጋገጥ እንችላለን።

@yetenaweg

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Dec, 12:47


የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደኣ በዋስትና እንዲለቀቁ ተወሰነ

ሰኞ ህዳር 23 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደኣ በዋስትና እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መወሰኑ ተገለጸ፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39561

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Dec, 12:41


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባልደረባ ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50ሺ ዶላር ለባለቤቱ አስረከቡ።

ሰኞ ህዳር 23፡2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጸጥታ ክፈል ባልደረባ ፍሬዘር በቀለ ህዳር 16 2024 ዐ.ም ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50 ሺህ ያሜሪካን ዶላር ለባለቤቱ ማስረከባቸውን አየርመንገዱ አስታውቋል ።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39557

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Dec, 11:12


የኦሮምያ ክልል መንግስት የሰላም ስምምነት የተፈራረመው በቡድኑ ቅቡልነት ከሌለው አመራር ጋር ነው” - የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት

ሰኞ ህዳር 23 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን  ባወጣው መግለጫ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጋር  የሰላም ስምምነት የተፈራረመው ጃልሰኚ ነጋሳ እንደማይወክለው ገልጿል፡፡

የተደረገው ስምምነት ከቡድኑ ጋር የተደረገ ስምምነት አድርጎ እንደማይወስደውም ነው ቡድኑ የጠቆመው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ትላንት ህዳር 22 ቀን የሰላም ስምምነት የፈረሙት ከወራት በፊት በስነምግባር ጉድለት ካባረርኳቸው አመራር ጋር ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አስታውቋል።

የኦሮምያ ክልል መንግስት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ዞን የቀድሞ አዛዥ ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል የሰላም ስምምነት ፈርመዋል ሲል መግለጹ ይታወቃል።

ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አፈንገጠው የወጡ ተደርጎ በመንግስት በኩል እየቀረበ ያለው መረጃ ፍጹም ሀሰት ነው ሲል የገለጸው መግለጫው የህዝቡን ስነልቦና ለመግዛት በሚል በመንግስት በኩል የቀረበ ማታለያ ነው ሲል ተችቷል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

01 Dec, 15:47


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ750 ቢሊየን ብር በላይ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

እሁድ ህዳር 22 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ5 ቢሊየን ፓውንድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።

ከአዲስ አበባ በ25 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ አቅራቢያ የሚገኘው ይህ የወደፊት አየር ማረፊያ በ2029 ሲጠናቀቅ እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን በዓመት የሚያስተናግድ ትልቅ ተርሚናል እና አራት ማኮብኮቢያዎችን ይይዛል ተብሏል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዳር አል ሀንዳሳ አማካሪዎች ጋር በመተባበር የሚመራው ይህ የ750 ቢሊየን ብር በላይ ፕሮጀክት፤ ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ዋና ተዋናይ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል።

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መጨናነቅ ቢያጋጥመውም "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ይህን ችግር በመቅረፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ያሳድጋልም ተብሎለታል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

01 Dec, 10:21


የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከጃል ሰኚ ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

እሁድ ህዳር 22 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት ስለመፈራረማቸው አዲስ ማለዳ ሰምታለች።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት ተብሏል፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ  ጁላ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት÷ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና ማቅረባቸው ተሰምቷል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

01 Dec, 10:17


"ለኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት መሻከር የውጪ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት አንደኛው ምክንያት ነው" ፕሬዚዳንት ኢሳያስ

እሁድ ህዳር 22 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)ለኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኘነት መሻከር የውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት አንዱ ምክንያት እንደሆነ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከአገራቸው መገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የድንበር ጦርነት ውስጥ የገቡትም ሆነ በባድሜ ለሁለት አስርት ዓመታት ሰፍኖ የቆየው ውጥረት "ለሁለቱ ሀገራት የድንበር ውዝግብና ጦርነት እንዲሁም አሁን ላለው የግንኙነት መቀዛቀዝ የውጭ ሃይሎች  ጣልቃገብነት  ዋነኛው አንደሆነ አብራርተዋል። 

አስመራ እና አዲስ አበባ ጦርነቱን በስምምነት ፣ከቋጩ በኋላም ሆነ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ የቀጠለው ግጭትና ጦርነት መነሻንም ከህገመንግስቱ ጋር አያይዘውታል።

"ህወሃት የሪፎርም አጀንዳዎችን ወደጎን በመተውና ጦርነት በመምረጥ ወደ ኤርትራ ከ70 በላይ ረጅም ርቀት ሮኬቶችን ተኩሷል ያሉት ፕሬዚዳንቱ ህወሃት ይህን ድርጊት እንዲያቆም ያቀረብነው ጥያቄ ሰሚ አላገኘም ነበር" ሲሉ ያወሳሉ።

ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ በአማራ ክልል አዲስ ግጭት መከሰቱን በመጥቀስም "ወደ ክሶችና ወቀሳዎች መግባት አንፈልግም፤ ዋናው ትኩረታችን ሁሌም ደም አፋሳሽ ጦርነትን መከላከል እና ማስወገድ ነው" ብለዋል።

መንግስታቸው ላይ የሚነሳውን ወቀሳ እንደማይቀበሉትም አክለዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

30 Nov, 13:59


በኢትዮጵያ የተፈጠሩና አሁንም ድረስ መቆሚያ ያጡ ችግሮች ለብዙሃን ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆነው ቀጥለዋል፡፡

ታዲያ ይህን ለማስቆም እንደ አንድ የፖለቲካ ተዋናይ የሚቆጠሩት ፓርቲዎች መግለጫ ከመስጠት በዘለለ ምን ፈየዱ?

ለግጭቶችስ መፍትሄ ላለማግኘትስ ዋነኛው ዳተኝነት ያለው ማን ጋር ነው የሚሉና መሰል ጉዳዮች በማንሳት ከፖለቲከኛው አቶ ጌትነት ወርቁ ጋር ቆታ ያደረግንበትን ሙሉ ዝግጅት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ

https://youtu.be/nxdaHSMJ4ww?si=6muGtsGn9AC9pC9r

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Nov, 14:48


የኢትዮጵያና የኤርትራ የቀደመ ግንኙነት መሻከር በብዙ አውዶች አየተገለጠ ነው።

ይህም የሁለቱ አገራት ፖለቲከኞች ጫፋ የደረሰ መተቻቸት ይህንን ገላጭ ሆኗል።

ለመሆኑ ላለፉት ሰባት አመታት የአገራቱ ግንኙነት ምን አጋጠመው ? ተከታዪ የአዲስ ማለዳ ትንታኔ ይህንን ጉዳይ በትንታኔ ተመልክቷል። ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ

https://youtu.be/OVBayWPYmSA

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Nov, 12:35


“በስንዴና ገብስ ምርቱ የሚታወቀው የአርሲ ምድር ደም ሲጠጣ የሚውል የሚያድር ከሆነ ሰነባብቷል”- እናት ፓርቲ

ዓርብ ህዳር 20 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) እናት ፓርቲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ፣ ሶሌ ፈረንቀሳና ሶሌ ጡጃ ቀበሌ በተፈጸመ ጥቃት በአንድ ቤተሰብ ዙሪያ ያሉ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡

ፓርቲው ግድያውን “የጫካው ሸኔ” መፈጸሙን ከአካባቢው ሰዎች አደረኩት ባለው ማጣራት ማወቁን ገልጿል፡፡

ባለፉት 5 ዓመታት በተለይ ማንነትና ሃይማኖት ተኮር ዘግናኝ ግድያዎች እንደሚፈጸሙ እና በስንዴና ገብስ ምርቱና በደግነቱ የሚታወቀው የአርሲ ምድር ዛሬ ዛሬ ደም ሲጠጣ የሚውል የሚያድር ከሆነ መሰነባበቱን ፓርቲው ከአካባቢው ነዋሪዎቹ ለማወቅ ችያለሁ ብሏል፡፡

እንዲሁም ከሰሞኑ በዚሁ አካባቢ 2 ሰዎች ተገድለው ሌሎች 8 ሰዎች ታግተው እንደተወሰዱ የአካባቢው ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን ታጋቾቹ የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸውም መናገራቸውን አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ‘መከላከያ ነን’ ያሉ ሀይሎች ከነዋሪው በግዳጅ መሣሪያ እየወሰዱ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎች ይህም በተለይ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ኃይል እጅግ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረለትና በቀላሉ መንደር ውስጥ ገብቶ ገድሎና ዘርፎ እንደሚወጣ ከሞላ ጎደል አካባቢውን ወደማስተዳደር እየሄደ መሆኑን በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ጥቃቱ በተፈጸመበት አካባቢም በግምት 3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን ጥቃት የተሰነዘረባቸውን ነዋሪዎች ለመታደግ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳላደረገና ለማትረፍ ጥረት እንዳልነበረ እናት ፓርቲ ገልጻል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Nov, 09:47


አቶ ብናልፍ አንዷለም ከሃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸው አቶ መሃመድ ተሾሙ

ዓርብ ህዳር 20 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) አቶ ብናልፍ አንዷለም ከሃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸው አቶ መሃመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል፡፡

በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቁዩት አቶ መሃመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

አቶ መሃመድ እድሪስ ከኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Nov, 08:47


የፖለቲካ ተንታኝ ቅጥር ማስታወቂያ

አዲስ ማለዳ ወቅታዊ የኢትዮጵያ እና አካባውን ፖለቲካዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን እየተከታተለ ሙያዊና ጥልቅ አስተያየት የሚሰጥ የፖለቲካ ተንታኝ ትፈልጋለች፡፡
ሥራው ካሉበት ቦታ ሆነው የሚሰሩት ሥራ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ተቋማት ውስጥ መደበኛ ሥራቸውን እየሰሩ ባላቸው ትርፍ ጊዜ የሚሰራ ሙያዊ ሥራም ጭምር ነው፡፡

አዲስ ማለዳ ህብረተሰብን ለማስተማር የሚጠበቅባትን አበርክቶ ለማሳደግ የተሻለ እውቀት እና ተሞክሮ ያላቸው ምሁራን ወደ ሚዲያው ቀረብ በማለት በርካታ ዝርዝር እና ጥልቀት ያላቸውን ውስብስብ የሃገራችን እና የቀጠናው ጉዳዮች ላይ ዕውቀትን መሠረት ያደረገ ትንታኔ በመሥጠት ሃገራችን ወደ ተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት በሂደት እንድታመራ ትሰራለች፡፡
ለዚህም የተጣሩ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን ለህዝብ የማድረስ ጥረቷን አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡

ይህን የአዲስ ማለዳ ጅምር ለማገዝ ፍላጎቱ ያላችሁ እና ከዚህ በታች የተቀመጠውን ዝርዝር መስፍርት የምታሟሉ ባለሙያዎች እና ምሁራን ከዚህ በታች ባለው አድራሻ ፍላጎታችሁን በመግለጽ፣ የሥራ እና ትምህርት ማሥረጃችሁን መላክ ትችላላችሁ፡፡ ዝርዝር መስፍርቶቹ ከስር ተያይዘዋል፡፡

አዲስ ማለዳ ለማኅበረሰብ ለውጥ ትተጋለች፡፡

[email protected] OR [email protected]
+251 937 026 664
+251 911 253 767

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Nov, 08:06


የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሬ ሂደት ተፈጻሚነት አሁንም ድረስ በእንጥልጥል እንዳለ ነው፤ በመሪር የድህነት ምድብ ውስጥ ናቸው የተባሉት የዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች ይሻሻላል የተባለው ደመወዛቸውም ወራትን ቢያስቆጥርም መንግስት ባለበት ቀን ተግባራዊ አለመደረጉ ተስፋ እንዳሳጣቸው ይናገራሉ፡፡

ድምጻችን ይሰማልን የሚሉት ሰራተኞች እኛን ወክሎ የሚጠይቅልን ማነው? መብታችንን ስንጠይቅ እስር እና እንግልት የህይወታቸን ስንክሳር ሆኗል የሚሉና መሰል አቤቱታዎችን በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡

ይህን የሰራተኞችን እሮሮ እና የመንግስት ሹማምንት አስገራሚ ምላሽ ያካተተውን ልዩ ዘገባችንን ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/ePJWC6L20H4

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Nov, 14:12


በኢትዮጵያ የተፈጠሩና አሁንም ድረስ መቆሚያ ያጡ ችግሮች ለብዙሃን ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆነው ቀጥለዋል፡፡

ታዲያ ይህን ለማስቆም እንደ አንድ የፖለቲካ ተዋናይ የሚቆጠሩት ፓርቲዎች መግለጫ ከመስጠት በዘለለ ምን ፈየዱ?

ለግጭቶችስ መፍትሄ ላለማግኘትስ ዋነኛው ዳተኝነት ያለው ማን ጋር ነው የሚሉና መሰል ጉዳዮች በማንሳት ከፖለቲከኛው አቶ ጌትነት ወርቁ ጋር ቆታ ያደረግንበትን ሙሉ ዝግጅት ከታች ያለው ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ

https://youtu.be/EaS0vnOt-UM

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Nov, 07:58


ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ 251 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ መስማማቱ ተገለጸ

ሐሙስ ህዳር 19 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ተቋሙ ብድሩን ለማጽደቅ የተስማማው፣ የድርጅቱ የባለሙያዎች ቡድን ከኅዳር 3 እስከ 17 በአዲስ አበባ ተገኝቶ ኹለተኛውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ግምገማ ማድረጉን ተከትሎ ነው።

የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፣ የብድር መልቀቅ ስምምነቱን በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ እንደሚያጸድቀውም ይጠበቀቃል ተብሏል

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቀረፈና በመደበኛውና በትይዩው ምንዛሬዎች መካከል ያለው ልዩነት ከ10 በመቶ በታች መውረዱን የጠቀሰው ድርጅቱ፣ መንግሥት ጥብቅ የገንዘብና ፊስካል ፖሊስ መከተሉን እንዲቀጥልም መክሯል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Nov, 07:35


የህውሃት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሰፋ ጌታቸው ረዳን “የቀድሞ ፕሬዜዳንት” ብለው መጥራታቸው ጥያቄ አስነሳ

ሐሙስ ህዳር 19 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ቡድን ውስጥ የሚገኙት አቶ አማኑኤል አሰፋ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ጌታቸው ረዳን የቀድሞ ፕሬዜዳንት ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ለመሆኑ አቶ ጌታቸው ረዳ ' የቀድሞው ' ከተባሉ ትግራይን ማነው እያስተዳደረ ያለው ሲሉ ጋዜጠኞቹ ጥያቃ አቅርበውላቸዋል፡፡

አቶ አማኑኤል ሲመልሱም " የፕሬዜዳንት ውክልና ሲነሳ እሱ በሌለበት በሌለበት ማን እንደሚሰራ ይታወቃል " ኃላፊ በሌለበት ጊዜ እሱን ተክቶ የሚሰራ እንዳለ ይታወቃል ምንም የስልጣን ክፍተት አይፈጠርም ሲሉ ገልጸዋል

እንዱሁም ህወሓት የወከላቸውን የተወሰኑ ሰዎች ውክልና አንስቷል ለዚህም ነው የቀድሞ ፕሬዜዳንት የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት " ሲሉ ለተነሳው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም "ፕሬዝዳንቱን የሚተካ ሰውን በሚመለከት ህወሓት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እየተነጋገር ነው" ያሉት አቶ አማኑኤል " ውጤቱ ይፋ ይደረጋል " ብለዋል።

ከየትኛው የፌዴራል አካል ጋር ንግግር እያደረጉ እንደሆነ በግልጽ ያልተናገሩ ሲሆን የፌዴራል መንግሥትም በህወሓት ክፍፍል ጉዳይ ምንም ቃል ሰጥቶ እንደማያውቅ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል ከቀናት በፊት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን ክፍፍልና ልዩነት ካልፈቱ የክልሉን አስተዳደር ፌዴራሉ መንግሥት ሊይዘው መናገራቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ነገር ግን ይህ ከእውነት የራቀ ነው በማለት "እዚህ ተስማምተን ካልተንቀሳቀስን 'የጊዜያዊ አስታዳደሩን ስልጣን ብልፅግና ይረከበዋል ተብሏል ' ተብሎ የተነገረው ፍጹም የተሳሳተ ነው እዛ ደረጃ አልደረስንም እንዲህ አይነት መልስም አልተሰጠም ሲሉ ኮንነዋል፡፡

አክለውም " ህወሓትንም ሆነ የመንግሥት ስልጣንን በተመለከተ ድርድር አይደረግም " ያሉ ሲሆን " በመቶ ሺህ የሚቆጠር አባል ያለው ፓርቲ ነው ያለን ከፓርቲው የወጡ ሰዎች መመለስ ከፈለጉ በአሰራሩ መሰረት የይቅርታ ደብዳቤ በማስገባት ነው መመለስ የሚችሉት " ሲሉ አሳስበዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የደብረፂዮን ቡድን አስተዳደሩ ስራ እንዳይሰራ እንቅፋት ከመሆን ባለፈ የወረዳ ምክር ቤቶችን በመጠቀም አስተዳዳሪዎችን ከቦታቸው እንዲነሱ እያደረገ ነው ይህ " መፈንቅለ መንግሥት ነው " ማለታቸውን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

27 Nov, 13:43


https://youtu.be/0kR-CMn_cAg

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

27 Nov, 12:49


አግባብ ያለው የጸረ ተዋህሲያን መድሃኒቶች አጠቃቀም

ይህ መረጃ ከየጤና ወግ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የቀረበ ነው

በ20ኛው ክፍለ ዘመን ላይ በህክምናው ዘርፍ ከተገኙት ትልልቅ ግኝቶች ውስጥ የፅረ-ተውሃስያን መድሃኒቶች ገበያ ላይ መዋል ለህክምናው ዘርፍ መጠነ ሰፊ አስተዎጾ በማበርከቱ ይታወቃል። ከዚህም ውስጥ የአሌክሳንደር ፍሌሚንግ በ1928 የነበረው የመጀመሪያው የአንቲባዮቲክ ግኝት(ፔንሲሊን)  በፈር-ቀዳጅነት ይጠቀሳል። በዚህ ምክንያት ለህክምና አና ለቀዶ ጥገና ዘርፎች ቀላል የማይባል አስተዋጾ በማበርከት ሚሊየኖችን ከበሽታ እና ከሞት መታደግ ተችሏል።

ይሁን እንጂ ከ1940`ቹ በኋላ አለም አቀፋዊ በሆነ መልኩ ቀደም ብለው በሽታ አምጪ ተህወሲያንን በመግደል ወይም እንዳይራቡ በማድረግ የተለያዩ በሽታዎችን ሲያክሙ የነበሩት መድሃኒቶች በጊዜ ሂደት ተህዋሲያኑ ባሳዩት መድሀኒትን የመላመድ ባህሪ ጥቅም አልባ ሲሆኑ ተስተውሏል። ይባስ ብሎ ደግሞ ከ1970`ቹ ጀምሮ አዲስ የሚገኙት የፀረ ተህዋሲያን መድሀኒት አይነቶች እየቀነሱ መምጣት ችግሩን የከፋ አድርጎታል።
@YetenaWeg

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39519

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

27 Nov, 12:35


በሰሜን ሸዋ ዞን ከወጣቱ ግድያ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች በማህበረሰቡ መካከል ቅራኔ የሚፈጥሩ ናቸው ሲል ኢሰመጉ አሳሰበ

ዕረቡ ህዳር 18 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የኢትዮጵያ ሰበዓዊ መብቶች ጉባኤ በግድያና ግጭት ቀስቃሽ በሆኑ ተግባራት ዙሪያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በየክልሉ እየተበራከተ የመጣው የፌደራል እና የክልል መንግስታት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ነው ሲል ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እየተስፋፋ የመጣው ግጭት መንግስት በሰላማዊ መንገድ እንዲያስቆም፤ ከነዚህ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች፣ እገታና አፍኖ የመሰወር ተግባር በአሳሳቢ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

በዚህም የሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ለማስቆም በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ባለማድረጋቸው እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶችን የማክበር፣ የማስከበር እና የማሟላት ኃላፊነታቸውን በሚጠበቀው ልክ ባለመወጣታቸው ችግሩ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መጥቷል ብሏል፡፡

እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭት ሊያስከትሉ የሚችሉ ድርጊቶችን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተበራከቱ መምጣታቸው ከፍተኛ ለሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚዳርግ መሆኑን መገንዘቡን ኢሰመጉ አመላክቷል፡፡

በመሆኑም በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ እና አካባቢው በታጣቂዎች እንደተፈጸመ እየተገለጸ ባለው የአንድ ወጣት ግድያ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ድህረገጾች ላይ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች በማህበረሰቡ መካከል ቅራኔ የሚፈጥርና ላልተገባ ተግባር የሚዳርግ መሆኑን አውግዟል፡፡

ኢሰመጉ የሚመለከተው የመንግስት አካል ለጉዳዩ በቂ ትኩረት በመስጠት እንዲከታተልና ግድያውን የፈጸሙ እና ተጨማሪ ግድያዎች እንዲከሰቱ ግጭት ቀስቃሽ ተግባራትን የሚፈጽሙ አካላትን በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

26 Nov, 16:04


https://youtu.be/VauGyJ6ZQbs?si=tTARr5TGzyisCnNm

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

26 Nov, 13:42


“አዋጆቹ ከህጋዊ ተፈጻሚነታቸው ይልቅ የፖለቲካ መሳሪያ የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው”

👉 አዋጆቹ የዜጎች ንብረት የማፍራትና ሰብአዊ መብት የሚጠብቁ ናቸው - ፍትህ ሚኒስቴር

ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ እርጎ የማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ተግባርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ ረቂቅ አዋጅ በፓርላማው ክርክርና ጥያቄ አስነስቷል፡፡

በረቂ አዋጁ ውስጥ የተካተቱ በሽብር የተጠረጠረን አካል ንብረት ማገድ፣የልዩ ምርመራ ሂደት እንዲሁም የመያዣ ትእዛዝን እስከ 3 ዓመት እንዲጸና የሚያስቀምጡ ድንጋጌዎችና ሌሎች ጉዳዮች ላይም የምክርቤቱ አባላት በጥያቄና በስጋት መልክ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡

በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ አካላትን ለመመርመር በልዩ ሁኔታ እስከ 120 ቀን ወይም 4 ወር የሚወስደው የምርመራ ሂደት ተራዛሚና ዜጎችም በፍትህ ስርአቱ ላይ ጥያቄ እንዲያስነሱ የሚያደርግ ነው ሲሉም ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

እንደዚህ አይነት አዋጆች ከህግ ተፈጻሚነታቸው ይልቅ የፖለቲካ መሳሪያ የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው ያሉት እንደራሴዎቹ ይህ ደግሞ የአዋጁ ተግባራዊነት ላይ ጥያቄ እንዲነሳ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አዋጁን የደገፉ የፓርላማ አባላት እንደዚህ አይነት አዋጆች ከዚህ ቀደም ንብረትን ለተፈለገ የወንጀል ተግባር የማዋል ሂደትን ይከላከላል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

የፍትህ ሚኒስትሯ ሃና አርዓያስላሴ አዋጆቹ የዜጎች ንብረት የማፍራትና ሰብአዊ መብት የሚጠብቁ ናቸው ሲሉ የአዋጆቹ አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በአዋጆቹ ላይ ውይይት ከተደረገም በኋላ ለዝርዝር እይታ ወደ ህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ተልከዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

26 Nov, 11:47


“የደሞዝተኛው ኑሮ እየከፋ ሂዷል” የምክር ቤት አባላት

👉 የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሺያው ሀገርን የታደገ ትልቅ እርምጃ ነው- ገንዘብ ሚኒስቴር

ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ የቀረበለትን የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት አጽድቋል፡፡

የተጨማሪ በጀት ረቂቁን በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ የቀረበ ሲሆን አዋጁን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ እና አስተያየት ተነስቷል።

ከተነሱት ሀሳቦች ውስጥም የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሬ ተግባራዊ ባለመሆኑ እና የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የደሞዝተኛውን ማህበረሰብ አኗኗር እንዳከበደው የተገለጸው ዋነኛው ነው፡፡

በተጨማሪም በነጋዴው ላይ ያለው የታክስ ክፍያ የንግድ ዘርፉን አለመረጋጋት ውስጥ ሊከት እንደሚችል ያለውም ስጋት ተነስቷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴም በጉዳዩ ላይ ከምክር ቤት አባላት በተነሱት ጥቄዎች ላይ በሰጡት ምላሽ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም ጊዜውን የጠበቀ መሆኑን እና ያለን ሀብት ለመጠቀም የሚረዳ ከመሆኑም በላይ ከማሻያው በፊት ባለው መቀጠል የሀገርን ኦኮኖሚ እያደሙ መቀጠል እና ወደ ለየለት የኢኮኖሚ ውድቀት የሚያመራ በመሆኑ ማስተካከያ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱም በተጨማሪ በጀቱ ላይ ከተወያየ በኋላ በሦስት ተቃውሞ እና በአምስት ድምጸ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ በጀቱን አጽድቆታል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ለፕላንና በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቷል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

26 Nov, 11:45


በሪል እስቴት ዘርፉ በወጡ ማእቀፎች ላይ መወያየትን ጨምሮ ሌሎች ዘርፉን የሚጠቅሙ ክንውኖችን ያቀፈ አመታዊ የሪል እስቴት እና የቤት አውደ-ርዕይ ሊካሄድ ነው

ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ይካሄዳል የተባለው ይህ አውደ-ርዕይ በኢትዮጵያ የቤት ልማት ዘርፍ የግሉ ዘርፍ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲረዳ ታስቦ መዘጋጀት የጀመረው ኢቲ ሪል ስቴት እና ሆም ኤክስፖ የሪል ስቴት አልሚዎችን ከቤት ባለቤቶች፣ ከገዥዎች፣ ከሻጮች፣ እና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ለማገናኘት ያለመ ዝግጅት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት ለመደገፍና የህዝብ አገልግሎቶችን በተለይም የመሰረተ ልማትን ጥራት ለማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነትን የሚያመቻች አዋጅ በቁጥር 1076/2018 ማፅድቋ የሚታወቅ ሲሆን ይህ አውደ-ራዕይ ለዚህ አላማ አጋዥ ግብእት እንደሚሆን ይጠበቃል ነው የተባለው።

ከፍተኛ አልሚዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትን፣ የቤት ገንቢዎችን እና የቤተ ውበት ባለሙያዎችን ጨምሮ በአንድ ላይ የሚያሰባስበው ይህ ዘርፍ ውስጥ ያሉ አዳዲስ እድገቶችን፣ ፈጠራዎችን እና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማሳየት ያለመ ሲሆን በኢንዱስትሪ መሪዎች መካከል ትስስር እና ትብብርን ይፈጥራል ተብሎም ይጠበቃል።

በዚህ ዓመታዊ ሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ ከኤግዚብሽኑ በተጨማሪ በኢንዱስትሪው ላይ ከሚገኙ ዋና ባለድርሻ አካላት የመገናኘት እድል እንደሚፈጥርም ተነግሯል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

26 Nov, 09:20


https://youtu.be/ShmXZ0inq5Q

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

26 Nov, 07:54


ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ጥፋተኛ በተባለችበት የኮምፒዩተር ወንጀል እስር ተፈረደባት

ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ከሦስት ሳምንት በፊት ጥፋተኛ በተባለችበት የኮምፒውተር ወንጀል ክስ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈርዶባታል።

ፍርድ ቤቱ በመስከረም ላይ የእስር ቅጣት ያሳለፈው በጣቢያዋ ባስተላለፈቻቸው ኹለት ፕሮግራሞች ፈጸመችው በተባለው በኮምፒውተር ተጠቅሞ በኅብረተሰቡ መካከል አመጽ፣ ኹከት እና ግጭት ለማነሳሳት የመሞከር ወንጀል ነው መሆኑም ተነግሯል።

ፍርድ ቤቱ የእስር ቅጣቱን ባስተላለፈበት ችሎት ላይ መስከረም በአካል እንዳልተገኘችም ነው የተነገረው።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Nov, 13:49


የትግራይ ክልል የፖለቲካ ችግር የክልሉ ብቻ ሳይሆን የአገረ-መንግስቱም ስጋት ነው የሚሉት የባይቶናው ሊቀ-መንበር ክብሮም በርኸ፤ እንደ አገር መታረቅ ዋነኛው ሊሰራበት የሚገባው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ያሉት አመራሮች ይህ ነው የሚባል ስራን እንዳልሰሩ የሚያነሱት ፖለቲከኛው የትግራይ ህዝብ ሁነኛ አዳኝ ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡

ፖለቲከኛው በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ ያደረጉበትን ቀጣይ ክፍል ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/dWrRgwBdq5U

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Nov, 13:24


ፒያሳ አገርፍቅር ቲያትር ቤት አካባባቢ የእሳት አደጋ ተከሰተ

ሰኞ ህዳር 16 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ፒያሳ ከሃገር ፍቅር ቲያትር ቤት ፊት ለፊት በተለምዶ 'ቻይና ግቢ' ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ዛሬ ከሰአት 9 ሰአት ገደማ ነው የእሳት አደጋው መከሰቱ የተነገረው፡፡

የእሳት አደጋው 'ጃንጉሲ ኮንስትራክሽን' በተባለ ድርጅት ውስጥ እንደተነሳም ታውቋል።

የእሳት በአደጋውን ለማጥፋት የእሳትና አደጋ ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ከስፋራው ያደረሱን የአይን እማኞች ያመለክታሉ፡፡

ከሰሞኑ በመርካቶ ሸማ ተራ በቀናቶች ውስጥ ሁለት የእሳት አደጋዎች መከሰታቸው አይዘነጋም፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

24 Nov, 20:22


"የትግራይ ፖለቲካ ወደባሰ ሁኔታ እየተጓዘ ነው" – ጌታቸው ረዳ

እሁድ ህዳር 15 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፤ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ከግምት ውስጥ ያላስገባ በወንበር ላይ የተመሰረተ ግጭትና ትርምስ እየተፈጠረ መሆኑን ገለፁ።

አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ "ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ የቆየው ሃይል" በማለት የጠቀሱትን ቡድን “ሁሉንም ነገር አፍኖ ወደ ስልጣን ለመመለስ እየሰራ ነው ብለዋል።

ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ወደጎን በማለት “ወንበራችን ተነጠቅን” የሚሉ አካላት “በጉልበት እንመልሳለን” ወደሚል እንቅስቃሴ መግባታቸውን ገልፀዋል።

"ጉባኤውን አከናውኛለሁ በማለት የሚንቀሳቀሰው ሃይል በጠላትነት ከፈረጀው ሀይል ጋር በመተባበርም ወንበር ለመያዝ ሌት ተቀን እየሞከረ ነው" ብለዋል አቶ ጌታቸው።

በመሆኑም የትግራይ ፖለቲካ ወደ ከፋ ሁኔታ እየተጓዘ መሆኑን ገልፀዋል።

“በዞኖችና ወረዳዎች ስርዓት የሌለው ህገወጥ አሰራር እየተሰራ ነው” ብለዋል።

"የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ እና የትግራይን ፀጥታ ከማረጋገጥ ይልቅ ወደ ሌላ የስልጣን ሽኩቻ እንድንገባ ተገድደናል" ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ እንዳሉት፤ የተካሄደው ጉባኤ በፓርቲው አሰራርም ሆነ የፌዴራል መንግስት ባወጣው መመሪያ ህገወጥ ነው ብለዋል።

ልዩነቶች በዕርቅና በድርድር ለመፍታት እርሳቸውና ጓቻቸው ዝግጁ መሆናቸውም በመግለጫቸው ተናግረዋል።

“እንደ ህወሐት መዳን ከፈለግን በራሳችን ውስጣዊ አቅማችን እንጂ በውጪ ሃይሎች መሆን የለበትም” ብለዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Nov, 14:00


በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ቀውስ እያስተናገዱ ያሉ ጦርነቶች አሁንም መፍትሄ እያገኙ አይደለም።

በክልሎቹ የሚፈጸሙ ከህግ፣ ከሞራልና ከሰብአዊነት የተፋቱ አያሌ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፤ የሚሊዮኖች ህይወት በሰቆቃ ውስጥ እንዲያልፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚህ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ የመንግስት ምላሽ እንዴት ይታያል? የፖለቲካ ሊህቃንስ ምን ይላሉ? የሚሉና መሰል ጉዳዮችን ያነሳንበት አዲስ ማለዳ የትንታኔ ፕሮግራማችንን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/-w_gklkCjZA

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Nov, 12:30


“ለነዳጅ ማስገቢያ የሚውል የውጭ ምንዛሬ የንግድ ባንኮችን እንዲሰጡ ማድረግ ከሌለ ሀብት ላይ እንደመውሰድ ይቆጠራል”- የፋይናስ ባለሙያ

👉 “ለነዳጅ ማስገቢያ የሚውል የውጭ ምንዛሬ የግል ባንኮች ላይ የሚያመጣው ምንም አይነት ተጽዕኖም ሆነ ጉዳት የለም” የምጣኔ ሃብት ባለሙያ

ሀሙስ ህዳር 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከህዳር ወር ጀምሮ የንግድ ባንኮች ለነዳጅ የሚወጣውን ወጪ ከፍተኛ ድርሻ መጋራት አለባቸው ሲል ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ኢትዮጵያ በአመት ከፍተኛ ወጪ ለነዳጅ ማስገቢያ ይወጣል በዚህም በባለፈው አመት የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአጠቃላይ ከ64ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ማውጣቱን ገልጾ እንደነበር እንዲሁ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም የዘርፉ ባለሙያዎች በርካታ ሀሳቦችን እየሰጡ ሲሆን ለባንኮች ከፍተኛ ጫና እንሚፈጥርባቸው እና በቂ ጥናት ሳይደረግ የተወሰነ ውሳኔ እንደሆነ የሚከራከሩ እንዳሉ ሁሉ ይህ ነው የሚባል ችግር አያመጣም የሚሉም አልጠፉም ፡፡

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የባንክ ባለሙያው ሙሀመድ አሰፋ እንደገለጹት በርካታ ባንኮች አሁን ያሉበት ሁኔታ ደንበኞቻቸውን እንኳን በበቂ ሁኔታ የሚያስተናግዱበት አቅም ላይ አይደለም ያሉት ይላሉ፡፡

“ባንኮች በበቂ ሁኔታ የተጣለባቸውን ውሳኔ ሊያሟሉ የሚችልበት አቅም ሳይጠና እና ምን ያህል ድርሻ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ እንደሚገባ ግልጽ ባልሆነበት መንገድ ውሳኔ ማስተላለፍ ባንኮች አሁን ካሉበት ሁኔታ ጋር ተመጣጣኝ ያልሆነ ውሳኔ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ወደ ውጪ የመላክ እና የውጭ ምንዛሬ የመሰብሰብ አቅም እየተዳከመ ያለበት ሁኔታ መሆኑ በተጨማሪም በየጊዜው የሚወጡ መመሪያዎች የባንኮችን እንቅስቃሴ የሚገድቡ መሆኑ ሁኔታውን እንደሚያባብሰው አስታውቀዋል፡፡

በእነዚህ ችግሮች እና ብዙ መስተካከል ባለባቸው ክፍተቶች ውስጥ ይህን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ እና ባንኮች ግዴታ ለነዳጅ ማስገቢያ የውጭ ምንዛሬ ለነዳጅ አስገቢዎች እንዲሰጡ ማድረግ ከሌለ ሀብት ላይ እንደመውሰድ ይቆጠራል በማለት ገልጸዋል፡፡

ውሳኔው ከፍተኛ የገቢ አቅም እና በኢኮኖሚ ልማት ውስጥ ሚና የሚሰጥ ቢሆንም ከውጭ ምንዛሬ ዋጋ ተለዋዋጭነት እና ከአሰራር ውስብስብነት ጋር የተያያዙ ስጋቶችንም እንደሚያስከትል ተጠቁሟል፡፡

በአንጻሩ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዮናታን ታደሰ የግል ባንኮች ለነዳጅ ማስገቢያ የውጭ ምንዛሬን ማዋጣታቸው ይህ ነው የሚባል ተጽዕኖም ሆነ ጉዳት የለውም ሲሉ ይሞግታሉ፡፡

“የግል ባንኮች ላይ ያለው የውጭ ምንዛሬ ፍሰት ምን አይነት እንደሆነ ሀገር የሚያውቀው ሚስጥር ነው፤ መንግስትም ይህን ስለሚረዳ ነው ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ እንዲሸፍኑ ሀላፊነት አልተጫነባቸውም እንዳላችሁ ሀብት እና አቅም አስተዋጽኦ አድርጉ ነው የተባሉት ይህ ሂደት ደግሞ ይበልጥ የሚሳተፉበትን መንገድ ስለሚያሰፋው በነጻነት እንዲሳተፉ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ባለሙያው አክለውም ውሳኔው ይተላለፍ እንጂ በምን መልኩ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ በግልጽ ባልተጠቀሰበት ሁኔታ ጫና ሊያሳድር ይችላል ብሎ መደምደም እንደማይቻል እና ለባንኮቹም በሚመች መልኩ የሚሳተፉበት ሁኔታ ሊቀርብ እንደሚችል ታሳቢ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም የአሰራር ችግር እንዳለ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሙሉ ለሙሉ የለም ማለት ሳይሆን እንደሚባለው የተጋነነ እንዳልሆነ እና ከሙስና በጠራና በትክክለኛ መንገድ መስራት ቢቻል ክፍተቱን መሙላት እንደሚቻል ባለሙያው ገልጸዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Nov, 12:22


"አንዳንድ ተቋማት ላይ ሰራተኞቻችን ወረፋ ሲይዙ በጥበቃ ሰራተኞች የተደበደቡበት፣ ተገፍትረው የተጣሉበት፣ የታሰሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል።" የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

ዓርብ ህዳር 13 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የአገልግሎት አሰራሩን ለመገምገም እንዲያመች በተሰራው ስራ የተቋማቸው ሰራተኞችን ጨምሮ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተለያዩ እንግልቶችን እንዳሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ገልቷል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ መኩሪያ ሃይሌ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና በስሩ የሚገኙ ቋሚ ተቋማትን የ2017 በጀት ዓመት፣ የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም በተገመገመበት ወቅት ነው ይህን ጉዳይ ያነሱት ።

ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ በክልሎች እና የመስሪያ ቤት አመራሮች ምንም አይነት መረጃ ሳይኖራቸው በሚንቀሳቀሱ ባለ ድርሻ አካላት፣ የኮሚሽኑ የአቃቤ ህግ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እና ሌሎችም መዋቅሮች በተካተቱበት በሁሉም ክልሎች ተገልጋይ ተኮር ጥናት መደረጉን ገልፀዋል።

በጥናቱም ጥልቅ ጉዳዮችን ለመረዳትና የበለጠ በማስረጃ የተደገፈ እና አንዳንድ ተቋማት ላይ የኮሚሽኑን ሰራተኞች ጨምሮ ወረፋ ሲይዙ በጥበቃ ሰራተኞች የተደበደቡበት፣ ተገፍትረው የተጣሉበት እና የታሰሩበት ሁኔታ መፈጠሩን አስታውቀዋል።

በበጀት ዓመቱ የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ወቅት የተገኙ በኢትዮጲያ ሲቫል ሰርቪስ ስር ከሚገኙ ተቋማት ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፣ በዋነኝነትም የመንግስት ሰራተኞች የክፍያ ማትጊያ እና ማበረታቻ ስርዓት ከመዘርጋት አኳያ ጥናት ለማካሄድ እና ማበረታቻ ሊያገኙ የሚችሉ ጉዳዮችን ለመለየት ታቅዶ ያልተተገበረበት ምክንያት ጥያቄ አስነስቷል።

ኮሚሽነሩም "በቅርቡ የገንዘብ ሚኒስትር ያሳወቀውን የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ በማስታወስ የተደረገው የደሞዝ ማስተካካያ ትልቅ እረፍት ይሰጠናል። ኢትዮጵያ የሚመጥናትን የመንግስት ሰራተኛ ሊኖራት ይገባል። ለዚህም ብቃት ወሳኝ ነው። በዚህ ሂደት ጠንክሮ የሚወጣ ይኖራል የሚንገዋለልም እንደሚኖር ታሳቢ ማድረግ ይኖርብናል። ይሁን እንጂ ከፊት ለፊታችን ትልቅ ፈተና እንዳለ መረዳት አለብን" ብለዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Nov, 12:20


#ማስታወቂያ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Nov, 11:43


የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ካርድ መታገዱ ተሰማ

ዓርብ ህዳር 13 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን አስታውቋል::

መንግስት ካገዳቸው የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ውስጥ “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን  ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አመላክቷል፡፡

ባለስልጣኑ ለእገዳው እንደምክንያት ያቀረበው  የመብት ተቋማቱ ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባቸው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራታቸውና  ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ካረጋገጠ በኋላ እግድ እንዳሳለፈ ዋዜማ ዘግቧል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Nov, 14:50


የተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የሳፋሪኮምን የስራ እንቅስቃሴ ገመገሙ

ሐሙስ ህዳር 12 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በዛሬው እለት የተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን አጠቃላይ የስራ ሂደት እና አፈጻጸም ገምግመዋል።

በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው በዚህ ፕረሮግራም ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄልፑት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመሆኑም ላለፋት ሶስት አመታት ከ6ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን እና በ9 የክልል ከተሞች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል።

እንዲሁም በኤም ፔሳ የሞባይል ግብይት ከበርካታ ባንኮች ጋር በጋራ በመስራት ላይ መሆኑን እና በተለያዩ አካባቢዎች ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የትምህርት መሳሪያ መስጠታቸውን ለምክርቤት አባላቱ ገልጸዋል።

በተጨማሪ ጉልህ የገበያ ሀይል ወይም አንድ የሳፋሪኮም ደንበኛ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚ ጋር ለመደወል ተጨማሪ ክፍያ እንዳይከፍል ለማስቻል እንዲሁም ለማስፋፊያ እና የግንባታ ፍቃድ ላይ ከምክር ቤቱ ድጋፍ ተጠይቋል።

የምክር ቤቱ አባላትም በቀረበው ሪፖርት ላይ ሀሳብ አስተያየት ካነሱ በኋላ ለተጠየቀው የድጋፍ እና የፍቃድ ጥያቄ ተወያይተው ምላሽ እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Nov, 12:55


በደራ ወረዳ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከ43 በላይ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ተገለጸ

ሀሙስ ህዳር 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ በታጣቂዎች ግጭት 43 ነዋሪዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡

በተደጋሚ የሰላ እጦት የሚያጋጥማት ወረዳዋ በተለይም የታጠቁ ሃይሎች በሚያደርሱት ዝርፊያና የንብረት ውድመት ምክንያትም ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደገባች ተደጋግሞ ይገለጻል፡፡

በተለይም ከ2015 በኋላ በመንግስት ሃይሎች፣ መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው አካል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተደረጉ ከፍተኛ ውጊያዎች ወረዳዋን ወደ አሳዛኝ የግጭት ማዕከልነት ቀይሯታል፤ በዚህም የበርካታ የአከባቢው ነዋሪዎች ህይወት ተቀጥፏል፣ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ቀውስ ዳርጓል።

ከሰሞኑም በወረዳዋ አንድ ወጣት በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደል የሚሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቶ በብዙዎች ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱ አይዘነጋም ፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Nov, 08:35


የትግራይ ክልል የፖለቲካ ውዝግብ ከሁለቱ ተፋላሚዎች ባለፈ የክልሉን ሊህቃን ለሁለት የከፈለ ሆኗል፡፡

የህዝቡን እሮሮ ለመስማት አለመፍቀድ ፣የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ መግባትና መሰል ሂደቶችን ማስተናገድ የክልሉ ነባራዊ ሃቅ ከሆነም ሰነባብቷል፤ የሚሉት አቶ ክብሮም በርኸ በክልሉ ያለው ቀውስና እያጋጠመ ያለውን ፖለቲካ ውድቀት በሚመለከት ከትዝብታቸው አጋርተዋል፡፡

ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ
https://youtu.be/pe-OjWSO2jk?si=1-aD15_hy2rYnrXr

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

20 Nov, 11:32


"የመንግስት ተቋማት ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ነው ቁጥጥር ያደረጉት” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የመንግስት ተቋማት ቁጥጥራቸውን ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ማድረጋቸውን እንደ ትልቅ ክፍተት አግኝተነዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ የበጀት ዓመቱን የሶስት ወራት የስራ አፈፃፀም በቀረበበት ወቅት ነው።

በጉባኤው በዋነኝነት ጥያቄ ካስነሱ ጉዳዮች መካከልም፣ በመርካቶ ገበያ ከሰሞኑ በደረሰኝ ከመገበያየት ጋር የተነሱ አለመግባባቶች ነበር።

ከንቲባዋ መርካቶን ዳግም ለማልማት ከመነሳታችን በፊት የተለያዩ ጥናቶች አከናውነናል ያሉ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ መርካቶ የሀገሪቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ከመሆኑ ጀርባ የህገ ወጥ ንግድ መሸሸጊያ ሆኖ በማግኘታችን ነው ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የመንግስት ተቋማት ቁጥጥራቸውን ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ማድረጋቸው እንደሆነ ነው የጠቆሙት።

" ሲነጋ ግብረ ሐይሎች እንዳያገኘን በሚል፣ በሌሊት ትልልቅ ተሸከርካሪዎች ተሰልፈው እቃ ጭነው ለመሄድ ጥረት ይደረጋል። ይህ ሀገርን ይጎዳል። ግብር መክፈል መርህ እስከሆነ፣ ችግሮቻችንን እያሳዩን እና የሚሰርቀውን ለእኛ አሳልፈው እየሰጡ እነርሱም ግድታቸውን መወጣት ነው ያለባቸው።" ሲሉ አስጠንቅቀዋል

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

20 Nov, 08:28


ሲቪል ሰርቪስ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር ነው መባሉን እና በፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ኢትዮጵያን የሚመስል የሰራተኞች ድልድል እንዲኖር በረቂቅ አዋጅ መቅረቡ ትክክል አይደለም ሲሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በፓርላማ ሰፊ ክርክር አድርገዋል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ጋር በፓርላማ ያደረጉትን ፍጥጫ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው በአዲስ ማለዳ ይከታተሉ

https://youtu.be/RzdONqXRWUE?si=QnxYL1re4_0Ah4Ik

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Nov, 18:05


https://youtu.be/Fe8TwYSxsWI?si=mAu8V6B86roWFDcM

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Nov, 14:50


https://youtu.be/3nV7utG2N6U

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Nov, 12:42


በትግራይ ክልል አለ የተባለው አለመረጋጋት ሰዎች ወደ ክልሉ እንዳይመጡ ሆን ተብሎ የሚደረግ ሴራ ነው ተባለ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር እና አለመረጋጋት መኖሩን በተለያዩ የማህበራዊ ድህረገጾች እና የዜና ምንጮች ሲነገር መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በተለይም በትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ባሳለፍነው እሁድ ማለትም ህዳር 08 ቀን 2017 ከአክሱም ወደ መቀሌ እየተጓዙ ባሉበት ወቅት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተኩስ እንደተከፈተባቸው መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

መኪናቸው ላይ ተኩስ እንደተከፍተባቸው የገለጹት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ከአክሱም ወደ መቐለ ሲመለሱ ማይቅነጣል ፈላፍል በተባለ ቦታ ሲደርሱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በተሽከርካሪ ውስጥ እሳቸውን ጨምሮ ሶስት ሰዎች እንደነበሩ እና በማንም ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ተኩሱን የከፈቱባቸው አካላት እነማን እንደሆኑ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንዲጣራላቸው ለክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ጥያቄ ማቅረባቸውን አሳውቀዋል፡፡

አስተዳዳሪው ከትግራይ ክልል አመራር መከፋፈል በኋላ በአቶ ጌታቸው ረዳ ከሚመራው 16 ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ ሆነው የቀጠሉ ናቸው፡፡

በአንጻሩ የመግደል ሙከራ ተቃጥቶባቸዋል የተባለው አካባቢን የሚያስተዳድሩት አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት በበኩላቸው “በማይ ቅነጣል ወረዳ ጉዳዩ አልተፈፀመም፤ መረጃው ከእውነት የራቀ ነው” ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ ያለው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ስትል አዲስ ማለዳ በአካባቢው ከሚኖሩ ምንጮች መረጃውን ለማጣራት የሞክራች ሲሆን እነዚህ ምንጮች በማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪዉ አቶ ሰለሞን መዓሾ መኪና ላይ ተኩስ መከፈቱን መስማታቸውን ጠቅሰዉ ከዚህ ውጪ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገጾች እንደሚናፈሰው በክልሉ ሁከትም ሆነ የተለየ ተኩስ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል በድምቀት የሚከበረውን አመታዊ የፂዮን ማርያም ሀይማኖታዊ ክብረ በዓልን ተከትሎ እና ከሰሞኑ በነበሩ ዝግጅቶች ምክንያት ከተለመደው በዛ ባለመንገድ የፖሊስ ሀይሎች በአካባቢው ላይ ከመታየታቸው ውጪ ምንም አይነት አዲስ ነገር እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም በዓሉን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከተለያዩ ክልሎች እና አካባቢዎች የሚመጡ ስለሆነ እና አንደኛው የቱሪስት መስህብ በመሆኑም ባልተረጋገጠ መረጃ ሆንተብሎ ሰዎችን ለማስቀረት የሚደረግ ሀሰተኛ መረጃ ስለመሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Nov, 11:44


https://youtu.be/Fe8TwYSxsWI?si=mAu8V6B86roWFDcM

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Nov, 08:38


“ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አመራሮች ከሃላፊነታቸው ሊነሱ ይገባል” ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አባላት ከሃላፊነት ሊነሱ ይገባል ሲል ከሰሞኑ ፍቃዱ የተሰረዘው ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ ከሷል፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ፍቃድ በመሰረዝ የሰላማዊ ትግል በርን እየዘጋ ነው ያለው ፓርቲው፣ ይህ ደግሞ ሆን ብሎ የሚከናወን ነው ሲል አብራርቷል፡፡

ከሰሞኑ ከታገዱ የ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጸው ምርጫ ቦርድ ህግን ባልጠበቀ መንገድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ፍቃድ በማገድና በመሰረዝ የፖለቲካ እንቅስቃሴን እየዘጋ ነው ያለ ሲሆን ፤ ይህም በተለይ በበህሄር የተደራጁ ፓርቲዎችን ሆን ብሎ ለማጥፋት ያለመ ነው ብሏል፡፡

የቦርዱ አመራሮች 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ፍቃድ በማገድ እና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ እንዳይገኙ በመከልከል የጋራ ምክር ቤቱን እንዲፈርስ ወይም ለሶስት ቦታ እንዲሰነጠቅ አድርገዋል በማለትም ፓርቲው ወቅሷል፡፡

ይህ ሂደት ከፓርቲ ስራ ባለፈ በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ተካተው ውይይት ሲያደርጉ የነበሩ ፓርቲዎችን ጭምር የጎዳ ነው በማለትም ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አመራሮች ከሃላፊነት መነሳት አለባቸው ሲልም ሃሳቡን ሰንዝሯል፡፡

አዲስ ማለዳ የፓርቲውን ክስ በሚመለከት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መልስ ለማገኘት በተደጋጋሚ ያደረገችው ጥረት ያልተሳካ ሲሆን በቀጣይ ቦርዱ ምላሽ በሚሰጥበት ወቅት የዘገባ ሽፋን የምንሰጥ ይሆናል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Nov, 08:22


በሶማሊላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ሙሴ ቢሂ በሰፊ ልዩነት ተሸነፉ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በሶማሊላንድ በፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ሙሴ ቢሂ በሰፊ ልዩነት ሲሸነፉ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " አሸነፈዋል።

የዋደኒ ፓርቲ እጩ ሆነው የቀረቡት አብዲራህማን ኢሮ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ አሳውቋል።

በምርጫው ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እንዲሁም ፋይሰል አሊ ዋርቤ ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

የኢሮ ፓርቲ ምርጫውን 63.92 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፈው። የተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ ፤ ኩልሚዬ ፓርቲ 34.81% ነው ያገኘው።

ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ተገንጥላ እራሷን እንደ ነጻ ሀገር የምትቆጥር ስትሆን ላለፉት በርካታ አመታት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላትም።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Nov, 07:57


በፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ የምክር ቤቱ አባል ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አንሥቷል።

በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት የምክር ቤቱ አባል ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን ያነሳ መሆኑን በምክር ቤቱ የሰላም፣ የፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ አስታውቋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሚኒስቴሩ የቀረበውን የሙስና ክስ በመመርመር የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።

ምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርትን በመመልከት አባሉ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Nov, 16:01


https://youtu.be/nLtW9l_JkFE

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Nov, 08:26


ሀብታቸውን በውጭ ባንኮች የሚያስቀምጡ ባለሐብቶች የሚቀጡት ቅጣት በቂ አይደለም ተባለ

ሰኞ ህዳር 09 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ሀብታቸውን ውጭ ባንኮች ውስጥ የሚያስቀምጡ ባለሀብቶች ሃገርን ከሚያሳጡት የውጭ ምንዛሬ አንጻር የሚቀጡት ቅጣት በቂ አይደለም ተብሏል

ከፍራንኮ ቫሉታ መከልከል ጋር ተያይዞ ቀድሞውንም የነዚህ ባለሃብቶች የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ህጋዊ አልነበረም ሲሉ ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ ያደረጉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

ባለሃብቶቹ የውጭ ምንዛሬ ምንጮቻቸውም ከጥቁር ገበያ እና በውጭ ባንኮች ያከማቹት ሀብታቸው ሊሆን ስለሚችል በሃገር ውስጥ ባንክ ማስቀመጥን አይፈልጉም ሲሉ አክለዋል፡፡

በተለይም ከፍራንኮ ቫሉታ መተግበር ቀደም ብሎም የውጭ ባንኮች ውስጥ ሀገር በቀል ባለሐብቶች ሀብታቸውን እንደሚያስቀምጡ ተገልቷል።

ነገር ግን እነዚህ ባለሀብቶች ሃገር ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ የሚተላለፍባቸው ቅጣት በቂ የሚባል አይደለም ያሉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ይህም ሊስተካከል ይገባል ብለዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Nov, 14:57


በትግራይ ክልል ለተፈጠረው የፖለቲካ ውድቀት ዋነኛ ምክንያት የህወሃት እንደ ድርጅት መሞት ነው፤ የሚሉት የድርጅቱ መስራችና የቀድሞ ስራአስፈጻሚ አባል አቶ ገብሩ አስራት ይህ ደግሞ የኤርትራ መንግስትን ጨምሮ በአካባቢው የተረጋጋ ፖለቲካ እንዳይኖር ለሚፈልጉ አካላት ሁለተኛ የጥፋት በር እየከፈተ ነው ብለዋል፡፡

አዲስ ማለዳ ከአቶ ገብሩ አስራት ጋር ያደረገችውን ቆይታ ክፍል ሁለት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/6V_Cjump0Lg?si=TUweDz_7Wkm889EV

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Nov, 09:59


ለኮሪደር ልማት ይፈርሳል የተባለው ሃይማኖታዊ ቦታ ቅሬታ አስነሳ


ቅዳሜ ህዳር 07 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጌዲዮ ዞን፣ ይርጋጨፌ ከተማ የሙስሊም መካነ መቃብር የተወሰነ ክፍሉ ለኮሪደር ልማት ይፈርሳል መባሉ ቅሬታ መፍጠሩን ነዋሪዎች ለቢቢሲ አስታውቀዋል፡፡

ቢላል የተባለው ይህ መካነ መቃብር የመንገድ ማስፋፊያን ጨምሮ ለሕዝብ መዝናኛ ግንባታ 15 ሜትሩ እንደሚፈልግ መነገሩም በተለይም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘነድ ቅሬታ መፍጠሩ ነው የተጠቆመው፡፡

መንገድ ዳር የሚገኘው ይህ መካነ መቃብር ላለፉት 50 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን የገለጹት ቅርታ አቅራቢዎቹ አሁን ላይ ይፈርሳል የተባለበት መንገድ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡


የይርጋጨፌ ከተማ ከንቲባ አቶ ታደለ ጥላሁን ለአምስት ጊዜ ያህል ስብሰባ አድርገው መቃብሩን ለማንሳት ስምምነት ተደርሶ እንደነበር ጠቅሰው፤ በ10 ቀናት ውስጥ አጽም ወደ ዘላቂ ማረፊያ እንዲዘዋወር መስማማታቸውን በማስታወስ አሁን እየተነሳ ያለው ቅሬታም ከምን የመጣ እንደሆነ እንደማያውቁ ገልጸዋል፡፡

የከተማው አስተዳደር እስከ እሁድ ኅዳር 8 ድረስ የመካነ መቃብር ቦታውን ለማፍረስ ዝግጅት ማጠናቀቁን መግለጹ ይታወሳል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Nov, 09:56


የአለም ጤና ድርጅት የኩፍኝ በሽታ አስጊ የጤና ችግር እየሆነ መጥቷል ሲል አስታወቀ

ዓርብ ህዳር 06 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኩፍኝ በሽታ የአለም የጤና ስጋት እየሆነ መጥቷል ሲል የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በኩፍኝ በሽታ የሚያዙ ዜጎች ምጣኔ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸርም የ20 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱን በመግለጽም ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ107 ሺህ በላይ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን እና አብዛኞቹ ሕጻናት መሆናቸውን አብራርቷል፡፡

በ57 ሀገራት ላይ በሽታው የጸና እንደነበር በማስታወስ ግማሽ ያህሉ በአፍሪካ መመዝገቡን ያመላከተው የጤና ተቋሙ ተላላፊ ከሆኑ በሽታዎች አንዱ የሆነው ኩፍኝ የጉንፋን ምልክቶች እና ትኩሳት ሊያሳይ የሚችል ሲሆን፥ ይህን እንደተመለከቱ በፍጥነት ወደሕክምና መሄድ እንደሚገባ ይመከራል ሲልም ገልቷል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Nov, 09:45


የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሚያካሂደዉ ጉባኤ ሕገ-ወጥ በመሆኑ አንሳተፍም ሲሉ 6 ፓርቲዎች ገለጹ

ቅዳሜ ህዳር 07 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)ን ጨምሮ ስድስት የሚሆኑ ፓርቲዎች ሕገ-ወጥ ያሉትን የኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ እንደማይሳተፉ መግለጻቸው ተጠቁሟል።

ፓርቲዎቹ የጋራ ምክር ቤቱ ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 7 እና እሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ለማድረግ የጠራውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሁም ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ሥራ አስፈፃሚ ለመመርጥ ማሰቡን በመቃወም በጉባኤው እንደማይሳተፉ ገልጸዋል::

ግዜው የተጠናቀቀው የጋራ ምክር ቤቱ ምርጫ እና ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ከዚህ ቀደም መጠየቃቸውን ያስታወሱት ፓርቲዎቹ፤ ስብሰባ መጥራት አይችልም ብለዋል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን)፣ ህብር ኢትዮጵያ እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ህብር- ኢትዮጵያ) ሕገ-ወጥ ነው ባሉት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ መገለጻቸውን አሀዱ ዘግቧል።

በጉባኤው የሚወሰኑ ማንኛውም ውሳኔዎችንም እንደማይቀበሉም ፓርቲዎቹ ያስታወቁ ሲሆን ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤውን ያለፈው ነሐሴ ማድረግ ቢኖርበትም፤ በበርካታ ተቃውሞ ዛሬ ቅዳሜ እና እሁድ ያደርጋል ተብሏል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Nov, 14:15


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ የከተተውን የ900 ቢሊዮን ብር ብድር መንግስት በልማት ድርጅቶቹ በኩል ለመክፈል ተስማምቶ ተረክቧል፡፡
ይህን ተከትሎ እንዴት ይከፈላል፣ በኢኮኖሚው ላይ እንዲሁም በማህበረሰቡ ላይስ ጫና ይኖረዋል ወይ ስትል አዲስ ማለዳ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችን አነጋግራለች፡፡
በኢኮኖሚው ላይ ጫና ሊኖረው ይችላል መንግስት ብድሩን ለመክፈል መስማማቱ ባንኩን ከማዳን አንጻር ተገቢ እርምጃ ቢሆንም በማህበረሰቡ ላይ ግን ጫና ማሳደር አይችልም፤ ይህን ተከትሎም የሚደረግ የግብር ጭማሬ መኖር የለበትም ሲሉ ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡
ሙሉ ማብራሪያውን ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው መከታተል ይችላሉ!
https://youtu.be/hlWbA6K-ncU

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Nov, 13:22


"የውጭ ባንኮች እንዲገቡ ቢፈቀድም፣ እንዲቆጣጠሩን አልተፈቀደም" ብሔራዊ ባንክ

ዓርብ ህዳር 06 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ገብተው እንዲቀሳቀሱ እንጂ የቁጥጥር ስራን እንዲሰሩ ፍቃድ እንዳልተሰጠ ተነግሯል፡፡

ይህ የተሰማው የህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የፕላን በጀት እና ፍይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ከተለያዩ የባንክ ባለ ድርሻ አካላት ይፋዊ የሆነ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

በዚህ ወቅት የብሔራዊ ባንክ ገዢው ማሞ ምህረቱ የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው በሚያመጣው እድል እና ስጋት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ " ክፍት ማድረግ ማለት ተጨማሪ ተዋናዮችን መጋበዝ ሲሆን፣ ይቆጣጠሩናል ማለት ከቁጥጥር ነፃ ማድረግ ነው። እኛ ከቁጥጥር ነፃ እናድርጋቸው እያልን ሳይሆን፣ እየተቆጣጠርን ዘርፉን ክፍት እናደርጋለን ነው ያልነው" ሲሉም መልሰዋል።

አክለውም የውጭ ባንኮች በመግባታቸው ለዘርፉ የተሻለ ተጠቃሚነትን የፍይናንስ ጤናማነት በተጠበቀ መልኩ ሲሆን ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ስለ ባንኮች ውህደት ለቀረበላቸው ጥያቄ እንደ መመሪያ ህግ ስርዓት ታስቦ የተቀመጠ እንጂ የፖሊሲ ውሳኔ አይደለም ሲሉም ነው ያብራሩት።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Nov, 12:38


https://youtu.be/W9ofHT8cUQE

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

15 Nov, 11:40


በመዲናዋ የስኳር በሽታ መድሀኒት እጥረት እንዳለ ተነገረ

ዓርብ ህዳር 06 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ በሚገኙ መድሃኒት ቤቶች የስኳር በሽታ መድሃኒት የሆነው  ኢንሱሊን እጥረት መኖሩን የመድሃኒት ቤት ባለቤቶችና  እና ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

እንደ ኢንሱሊን ያሉ መሰረታዊ የስኳር መድሃኒቶች እጥረት መኖር እንደማይገባው በመግለጽ አሁን ላይ እጥረት ከሚስተዋልባቸው መድሃኒቶች አንዱ መሆኑን የከነማ መድሃኒት ቤት ቁጥር አስራ አራት ተጠባባቂ ሃላፊ አቶ ታጠቅ ታደሰ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡

በብዛት ከሚሸጡ የስኳር መድሃኒት አይነቶች ዋነኛው የሆነው ኢንሱሊን ከተፈላጊነቱ አንጻር ቶሎ እንደሚያልቅ እና መድሃኒት ቤቶች ምርቱን ሲጠይቁ  በቶሎ እንደማይቀርብላቸው ይህ አይነቱ አሰራር ሊቀረፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በመርፌ የሚወሰዱት የበሽታው መድሃኒቶች ለውስን ሰአት በፍሪጅ የሚቀመጡ በመሆናቸው በተፈለገው ሰዓት ሁሉ በቂ አቅርቦት ሊኖርና በፍጥነትም አገልግሎት ላይ መዋል እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡

አንዳንዴም ምርቱ እያለ እጥረት ያጋጥማል ይህም የግዢ ሰንሰለቱ ጤናማ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በበኩላቸው አሁን ላይ ኢንሱሊንን ጨምሮ ሁሉም አይነት የስኳር መድሃኒት በበቂ ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል።

መንግስት የስኳር መድሃኒትን በከነማ መድሃኒት ቤቶች በበቂ ሁኔታ አቅርቧል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ነገር ግን የግል መድሃኒት አቅራቢዎችም ሆኑ መሸጫ መደብሮች በውድ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዳይቀርቡ ሲባል እንደማይሰራጭላቸው አስታውቀዋል።

የግል መደብሮች የአገልግሎት አቅራቢውን አርማ በመጠቀም በውድ የሚያቀርቡ እንዳሉና ይህን ባደረጉት ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጸዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

14 Nov, 13:17


በመንግስት የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሰላማዊ ዜጎችን ለህልፈት እየዳረገ ነው”- ኢሕአፓ

ሐሙስ ህዳር 05 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ “የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሃላፊነት ያለበት መንግሥት ቢሆንም በሚያሰማራቸው የጸጥታ ሃይሎችና የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጭምር የዜጎች ህይወት በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደቅጠል እያረገፈ ይገኛል” ብሏል፡፡

ኢሕአፓ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህገመንግሥቱን የመንግሥት አካላት ራሳቸው ካላከበሩት እንዴት ሊያስከብሩት ይችላሉ “በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደረጉት ግድያዎች ይቁሙ” ሲል አሳስቧል፡፡

እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከመዘገብ ቢቆጠቡም በውጪ የመገናኛ ብዙሀን ጭምር ጥቃቱ መፈጸሙን እየገለጹ መሆኑን እና ፓርቲውም አጣርቻለሁ ያለውን በየክልሉ የደረሱትን ጥቃቶች አስታውቋል፡፡

ፓርቲው አጣርቻለው ባለው መሰረት ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ጥቃቶች የሟቾችን ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን እና ጥቃት ከተፈጸመባቸው ውስጥም ነፍሰጡሮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ተማሪዎች እንደሚገኙበት አመላክቷል፡፡

በመሆኑም “ወደፊት ትውልድ እንዲከፍል በብድር በመጣ የጦር መሳሪያ ንጹሀን ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄድ አግባብነት የለውም”፤ መንግሥት ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ለማለት እንደዚህ ያለውን ሁኔታ በዝምታ ማስቀጠል አይችልም ሲል ኮንኗል፡፡

ኢሕአፓ መንግሥት በተለይ የጦርነት አውድማ በተደረጉት በአማራ፣በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝና በደቡብ ክልሎች ዉስጥ የሚደረገውን ህገመንግሥቱን እየጣሱ ያሉትን፣ መንግሥት መር የዜጎች ግድያዎችን በጥብቅ ማውገዙን እና ጦርነቶቹ አሁኑኑ ይቁሙ ሲልም አሳስቧል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

14 Nov, 11:21


የብዙዎች ስጋት እየሆነ የመጣው የስኳር ህመም

ይህ መረጃ ከየጤና ወግ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የቀረበ ነው

በኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አስጊነት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ህመሞች መካከልም የስኳር ህመም ይጠቀሳል፡፡ በሀገራችን ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር እንደሚኖሩ ሲገመት ከእነዚህም 50 በመቶ የሚሆኑት ህሙማን ምንም አይነት የስኳር ምርመራ ያላደረጉ በመሆናቸው የህክምና እርዳታ እያገኙ አይደለም፡፡በየአመቱ የሚከበረውን የአለም የስኳር ህመም ቀንን አስመልክቶም ከየጤና ወግ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የተለያዩ መረጃዎችን ወደእናንተ እናደርሳለን፡፡ በዚህ ጽሁፍ ስለስኳር ህመም ምንነት እና ከነርቭ ጤንነት ጋር በተያያዘ ሊደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ ተጽፏል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39464

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Nov, 14:21


የትግራይ ክልል ጉዞ እና የባለስልጣኖቹ ሽኩቻ ማብቂያው ምን ይሆን? በፖለቲከኛው ገብሩ አስራት እንዴት ይታያል?

በትግራይ ክልል ያለው ፖለቲካዊ መካረርን ለመፍታት በሁለቱም ቡድኖች መካከል ቁርጠኝነት የለም የሚሉት የህወሃት መስራችና የቀድሞ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ገብሩ አስራት በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና በጌታቸው ረዳ ቡድን መካከል ያለው ሽኩቻ ይጠባል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ያለው የድህረ-ጦርነት ምስቅልቅል፣የህወሃት የፖለቲካ ጉዞና መሰል ክልላዊና አገራዊ ጉዳዮችን በሚመለከት ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ሙሉ ዝግጅቱን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ!

https://youtu.be/Rc7oWjihPcc

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Nov, 13:01


https://youtu.be/7SAzb1qN35s

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Nov, 11:20


ፍራንኮ ቫሉታ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ተባለ

ዕረቡ ህዳር 04 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡

ነገር ግን ፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራው በመደበኛውና በትይዩ ገበያው መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ተቀራራቢ በማድረጉ የፍራንኮ ቫሉታ እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አክለውም መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉን እና በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም የንግድ ባንኮች ለመረሰታዊ ሸቀጦች የሚሆን በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዳላቸው ጠቅሰው በውሳኔው መሰረትም ከውጭ የሚመጡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ ብቻ እንዲገቡ መወሰኑንና ይህም ወደ ተግባር መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡

መንግስት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ የሚታወስ ነው፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Nov, 08:46


ወጋገን ባንክ ባለፈው ዓመት የተጣራ 1.6 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ
👉🏽ወጋገን ባንክ ከታክስ በኋላ በእያንዳንዱ አክሲዮን ያስገኘው ትርፍ 36 በመቶ በላይ መሆኑን አስታወቋል

ዕረቡ ህዳር 04 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ወጋገን ባንክ የ2016 የሒሳብ ዓመት አፈጻጸሙን ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት በበጀተ ዓመቱ በሁሉም የባንኩ አገልግሎት ዘርፍ አመርቂ ውጤት ማምጣቱን እና 9.8 ቢሊዮን ገቢ እንዳገኘ እና ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር የ40 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጻል፡፡

ባንኩ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ያስመለሰው የብድር መጠን 12.4 ቢሊዮን ብር መሆኑን እና በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ያበደራቸውን ብድሮች ማስመለስ አለመቻሉ ካጋጠሙት ችግሮች ውስጥ ቢሆንም ከፍተኛ ማሻሻል እና ለውጥ ማሳየቱን የወጋገን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን ገልጸዋል፡፡

አክለውም የባንኩ የተከፈለ ካፒታል የ27 በመቶ እድገት በማሳየት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 5.1 ቢሊዮን መድረሱን እና ይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የባንኮች አነስተኛ የካፒታል መስፈርት በላይ መሆኑን የቦርድ ሰብሳቢው አስታውቀዋል፡፡

እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ድረስ በመላው ኢትዮጵያ የከፈታቸው 436 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ፣ የሞባይል ባንኪንግ፣ የካርድ ባንኪንግና የወኪል ባንክ አገልግሎቶችን በ360 ኤቲኤም፣ 436 የክፍያ መፈጸሚያ ማሽኖች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Nov, 08:10


"ለአመታት ጥያቄ የነበረ ችግራችን ተቀርፏል "- የባቱ ከተማ አስተዳደር

👉 በቀጣይ በአካባቢው ያለውን የመሰረተ -ልማት ችግር ለመፋታት እንጥራለን- ቢጂአይ ኢትዮጵያ

ቢጂአይ ኢትዮጵያ በባቱ ከተማ ያስገነባውን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ባስተላለፈበት ወቅት ነው ይህ የተገለጸው ።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በአካባቢው ትምህርት ለማግኝት ለተቸገሩ ህጻናት መፋትሄ ሆኗል ያሉት የባቱ ከተማ ከንቲባ አህመዲን እስማኤል ይህ ተቋማት ማህበራዊ ሃላፊነት እንዴት መወጣት እንዳለባቸው ያሳየ ነው ብለዋል።

አባገዳ የሚል ስያሜ የተሰጠው ትምህርትቤቱ 9 ሚሊየን ብር እንደወጣበት የገለፁት የቢጂአይ ኢትዮጵያ ስራአስፈጻሚ ሄርቬ ሚልሃድ በከተማዋ ለጤና ፣ትምህርትና ለመሰል መሰረተ -ልማት ተቋማቸው ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ማውጣቱን ጠቁመዋል።

አዲስ የተገነባው ትምህርት ቤት 650 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት እድል መስጠቱ ተነግሯል ።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

13 Nov, 08:05


በአዲስ አበባ የሚገኙ አብዛኞቹ ህንፃዎች የመድህን ሽፋን የላቸውም ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ

ዕረቡ ህዳር 04 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በቅርቡ በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በተደጋጋሚ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በተለያዩ አካባቢዎች ንዝረት መሰማቱ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ንዝረት በመሰማቱ በከተማዋ ላይ ያሉ ህንጻዎችን ስጋት ላይ ጥሏቸዋል ተብሏል፡፡
ህንጻዎቹ የመድን ሽፋን ያላቸው ቢሆንም አብዛኞቹ የመድን ሽፋኑን እንደማይጠቀሙ ተጠቁሟል፡፡

የህብረት ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሠረት በዛብህ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት ምላሽም “በመዲናችን የሚገኙትን ግዙፍ ህንጻዎች ዓላማ ያደረጉ የተለያዩ ምርቶች ቢኖሩንም በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በአዲስ አበባ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ህንጻዎች የኢንሹራንስ ሽፋን የላቸውም" ሲሉ አስታውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ይህን የተናገሩት ህብረት ኢንሹራንስ የ30ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ ባዘጋጀው የጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው።

በተጨማሪም “ከዚህ ቀደም በከተማው ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች በርካታ ሕንፃዎች እንዲወድሙ ምክንያት ሆኗል፣ በወቅቱም መንግሥት ለባለሀብቶች ወጪውን ለመሸፈን ዕርምጃ የወሰደ ቢሆንም መንግሥት በቀጣይ ጊዜ ኃላፊነቱን እንደማይሸከም በግልጽ ተናግሯል" ሲሉ የህብረት ኢንሹራንስ ምክትል ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ደስታ ገልጸዋል፡፡

አክለውም "የመሬት መንቀጥቀጥ ኢንሹራንስ፣ የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ እና ሌሎች ወሳኝ ሽፋኖችን የሚያካትት የመድኋን ሽፋኖች ያሉ ቢሆንም አደጋው እየጨመረ ቢመጣም ብዙዎቹ እነዚህ አገልግሎቶች እንደተጠበቀው እየተጠቀሙ አይደለም" ሲሉ ጠቁመዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

12 Nov, 12:24


“የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን አዋጅ ማሻሻያውን ለማዘጋጀት የተሄደበት መንገድ ግልጽነት እና አሳታፊነት የጎደለው ነው”- የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና የጋዜጠኞች የሙያ ማህበር

ማክሰኞ ህዳር 03 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 19ቀን2017 በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ፣የኢትዮጵያ መገናኛ ብዘኃን አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ለይቶ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለዴሞክራሲ ጉዲዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎ ከጋዜጠኞች የሙያ ማህበር እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቾች በጋራ ባወጡት መግለጫ የአዋጁ ማሻሻያ አስፈላጊነት ላይ ገለልተኛ ጥናት ባልተደረገበት፣ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይት ባልተካተተበት ሁኔታ ረቂቁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ መቅረቡ እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም በአዋጁ ከለላ ተሰጥቷቸው የነበሩ የቁጥጥርና ሚዛን መጠበቂያዎች በረቂቅ አዋጁ ሊሻሩ የሚችሉ መሆናቸው አሳሳቢነቱን በእጅጉ እንደሚጨምር ገልጸዋል፡፡

አሁን በአስፈፃሚው አካል ተረቅቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ የቀረበው ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ በሥራ ላይ የሚገኘውን የመገናኛ ብዘኃን ሕግ በርካታ አንቀፆች ይዘትና መንፈስ የሚቀይር መሆኑን መገንዘባቸውን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ረቂቅ ማሻሻያው የአካሄድና የይዘት ግድፈቶች በስፋት የሚስተዋሉበት ሲሆን፣ በረቂቁ ማሻሻያ ላይ ምንም ዓይነት የሕዝብ ውይይቶች ባለመከናወናቸው የሲቪል ማኅበረሰቡን፣ የሚዲያ ሙያተኞችን እንዱሁም የሌሎች መብት ተሟጋቾችንና የማህበረሰብ ድምጾችን እንዳይሰሚ አድርጓል ተብሏል፡፡

እንዲሁም ማሻሻያውን ለማዘጋጀት የተሄደበት መንገድ ግልጽነትና አሳታፊነት የጎደለው ሲሆን የረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት በገለልተኛ አካል በተሰራ ጥናት ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተረድታለች፡፡

በተጨማሪም የረቂቅ አዋጁ የተለያዩ አንቀጾች በስራ ላይ የሚገኘው የመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ጥበቃ የሚሰጣቸውን ነጻነቶች የሚገድብ እና የሚዲያ ተቆጣጣሪውን አካል በአስፈጻሚው አካል ተፅዕኖ ውስጥ ይከተዋል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳለ ተገልጻል፡፡

የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ አስፈሊጊነት ላይ በጥናት የተደገፈ ማስረጃ እንዲቀርብ እና በባለድርሻ ወገኖች ሰፊ ውይይትና መግባባት እንዲደረስበት እና የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ በምክር ቤቱ ከመፅደቁ በፊት ትርጉም ያለውና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት እንዲከናወን በአጽንኦት ጠይቀዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

12 Nov, 11:51


"ከሶስት ትላልቅ የመድህን ሰጪ ተቋማት አንዱ መሆን ችለናል"-ህብረት ኢንሹራንስ

ሰኞ ህዳር 02 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ከሶስት አስርት አመታት በፊት የተቋቋመው ህብረት ኢንሹራንስ አሁን ላይ ጠቅላላ ሃብቱ 4.5 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሶስት መድህን ሰጪ ተቋማት አንድ ለመሆን እንደቻለ የገለፀው ኩባንያው በተጠናቀቀው የበጀት አመት ወደ 2 ቢሊዮን ብር አረቦን መሰብሰብ መቻሉም ተጠቁሟል ።

ኩባንያው በተጠናቀቀው የበጀት አመት ከብር 527 በላይ የትርፍ ድርሻ ማከፋፈሉን አስታውቆ ይህም ከኢንዱስትሪው ከፋተኛ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል።

ከዛሬ 30 አመት በፊት በ 87 ባለሀብቶች የተቋቋመው ህብረት ኢንሹራንስ አሁን ላይ የባለአክሲዮኖች ቁጥሩ 714 መድረሱን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ህብረት ኢንሹራንስ የፊታችን ሃሙስ ህዳር 5፣ 2017 ዓ.ም የኩባኒያው የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሸራተን አዲስ ሆቴል 30ኛ አመቱን በደማቅ ዝግጅቶች እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

11 Nov, 13:59


ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በእንደራሴዎች ምክርቤት ከተናገሩትና አሁንድረስ መነጋገሪያ ሆኖ የቀጠለው በብሄራዊ ቤተ-መንግስት ወቅት 400 ኪሎግራም ወርቅ መገኘቱን የገለጹበት ንግግራቸው ነበር፡፡
ታዲያ ይህን ተከትሎ ይህ የህዝብ ሃብት ነው ወደ ብሄራዊ ባንክ ሳይሆን ወደ ቅርስ ባለስልጣን ነው መግባት ያለበት የሚሉ አስተያቶች ጎላ ብለው ተደምጠዋል ከከከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ እናት ፓርቲ አንድ አነጋጋሪ መልዕክት አስተላልፏል ፡፡
ሙለ ዝግጅቱን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/CT39qEVEvYA

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

11 Nov, 11:17


በምእራብ ወለጋ የወርቅ ልማት ላይ ኢትዮጵያዊያን ኢንቬስተሮችን ለማሳተፍ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሰኞ ህዳር 02 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በከፊ ሚነራልስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚካሄደው የቱሉ ካፒ ወርቅ ልማት ፕሮጀክት ብቁ ለተባሉ ኢትዮጵያውያን ኢንቨስተሮች ከቀረበው የተወሰነ ድርሻ በተጨማሪ፣ በቅርቡ በሚከፈተው የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ሌሎች ዜጎች ተሳታፊ የሚሆኑበት መንገድ እየታሰበ እንደሆነ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ሃኒ አናግሮስታረስ በኩባንያው የኢትዮጵዮውያን የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖር ቁርጠኝነቱ መኖሩን ገልጸው ከአጠቃላይ የኩባንያው 500 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ውስጥ ስድስት በመቶ ወይም 30 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነውን ለኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች መቅረቡን አስታውቀዋል፡፡

አገሪቱ ካስቀመጠችው የኢኮኖሚ አካታችነት ራዕይ እንዲሁም ከኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ጋር ያለንን ቁርኝት ለማጠናከር እየጣርን ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው የኢንቪስተሮችን የፍላጎት ማሳወቂያ በመቀበል ቀሪውን ሒደት በአገሪቱ ሕግና አፈጻጸም አሠራር ለማከናወን ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ኩባንያው እ.ኤ.አ. በ2027 በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንደሚገባ ገልጾ ለዚህም አስፈላጊውን ስራ እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

11 Nov, 08:35


የንግድ ፖሊሲዎች ተደጋግመው መውጣታቸው እና መቀያየራቸው ለስራ አስጊ እየሆነብን ነው ሲሉ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን አሰሙ

ሰኞ ህዳር 02 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የንግድ ፖሊሲዎች ተደጋግሞ መውጣት የንግድ ዘርፉን ስጋት ውስጥ እየጣለው ነው ሲሉ በአስመጪና ላኪ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

በቅርቡ ክልከላ የተጣለበት የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያ እንኳን ብዙ ነጋዴዎችን እና ባለሀብቶችን ችግር ውስጥ እያስገባ ስለመሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ደጋግመው ሲገልጹ ይደመጣል፡፡

እንደነዚህ ያሉት ማሻሻያዎች ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ዓላማ ቢኖራቸውም ፣ ድንገተኛ ትግበራቸው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ መቀልበሳቸው ብዙውን ጊዜ የንግድ ሥራዎችን በአግባቡ እንዳይካሄዱ እየዳረገ ነው ሲሉም ነው ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ያሰሙት ።

ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ አንድ በቡና ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ እንዳሉት በተደጋጋሚ የፖሊሲ ለውጦችን በኢኮኖሚው ላይ መተግበራቸው ለንግድ ድርጅቶች ቀጣይ እርምጃ ከፍተኛ ጥርጣሬን እየፈጠረ ነው ብለዋል።

“ኢኮኖሚው ከመንግስት የፖሊሲ መረጋጋትን ይፈልጋል ምክንያቱም ብዙ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች መወሰን ሚቻለው ያኔ ነው” ያሉት ቅሬታ አቅራቢው ፖሊሲዎች ከመተግበራቸው በፊት በደንብ ሊጠኑ እንደሚገባ አስምረው መንግስትም ከሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት ጋር እንዲወያይ ጠይቀዋል፡

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አጥላው ዓለሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሚቀያየሩት ፖሊሲዎች የንግድ ባለቤቶች ረጅም ለማቀድ እንዳይችሉና ጥርጣሬ እንዲፈጥርባቸው እንደሚያደርጋቸው ጠቁመዋል፡፡

አክለውም ድርጅቶች በፖሊሲዎች ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦችን በመገመት አሳሳቢ ጉዳዮቻቸውን እና ስራዎቻቸውን በረጅም እቅድ ላይ ከማተኮር ይልቅ በአጭር ጊዜ እቅድና የንግድ እንስቃሴ እንዲገደቡ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የቢዝነስ ተቋማት ፈጣን የፖሊሲ ሽግሽግ የሚያስከትለውን መዘዝ ለመዳሰስ ፈታኝ እየሆነባቸው እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

10 Nov, 16:27


"የደብረፂዮን (ዶ/ር) ቡድን በአሁኑ ሰዓት የመንግስት የአመራር እርከን ከላይ እስከ ታች ለመቆጣጠር ጨርሰናል  የሚል የማደናገሪያ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው " ጊዜያዊ አስተዳደሩ

እሁድ ህዳር 01 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የደብረፂዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ቡድን ህዝብን እያደናገረ ነው ሲል በጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር ከሷል።

የቡድኑ ማደናገሪያ በአጉል ተስፋ ራስን ከማታለል የዘለለ ቅንጣት ሀቅ እንደሌለው መታወቅ አለበት " ያለው አስተዳደሩ " ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ መጥቷል " ሲል ገልጿል።

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በመቀለ ከተማ  ፣ በሰሜናዊ እና ማእከላዊ ዞኖች የታዩት የመንግስት ግልበጣና ስርዓት አልበኝነት ምልክቶች የቡድኑ ህግ አልበኝነት ማሳያ ናቸው ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስረድቷል።

ህዝቡም ይህንን የማደናገሪያ ሃሳብ እንዳይቀበልም ጊዜያዊ አስተዳደሩ አሳስቧል ።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

09 Nov, 13:24


ብሔርና ብሔርተኝነት በሽታ ነው የሚሉት አቶ ሰብስቤ ሀይሉ ከአዲስ ማለዳ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል።

ሙሉ ቃለምልልሱን ለመከታተል ከስር ያለውን መስፈንጠሪያ ይጫኑ።

https://youtu.be/Vp343lz74JE?si=TNOzwgm-Fti3DW2a

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

09 Nov, 07:34


የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ ባደረሰው የጎርፍ አደጋ በ3 ወረዳዎች ላይ ጉዳት አስከተለ

ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)በሱማሌ ክልል ስር በሚገኙት ቀላፎ ሙስታሄርና ፌርፌር ወረዳች ላይ ነው የጎርፍ አደጋው ውድመት ያስከተለው፡፡

አደጋውን ተከትሎም ጉዳት በደረሰባቸው አካባዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በአነስተኛ ጀልባች እንዲወጡ መደረጉም ነው የተገለጸው ፡፡

ከዚህ ቀደም በክልሉ ሸበሌ ዞን በደረሰ ተመሳይ አደጋ ከ6 ሺህ186 ሄክታር በላይ የሰብል መሬት ላይ ጉዳት ሲደርስ ከሁለት ሺ 827 በላይ አባወራዎች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

08 Nov, 14:15


በከተማዋ  አለ ስለተባለው ማጎሪያ ካንፕ ከከተማው ከንቲባ የተሰጠ አነጋጋሪ ምላሽ እንዲሁም ነብሰ-ጡር ሴትን ጨምሮ በርካቶችን ተገደሉበት ስለተባለው የአማራ ክልሉ ጥቃትን በሚመለከት አነጋሪ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን ከታቸ ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ


https://youtu.be/p7LmryBZ_IU

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

08 Nov, 13:32


''የክልሉ መንግስት የሚፈጽምብኝ በደል አብሮ ለመስራት የሚያስችል እየሆነ አይደለም'' ቦዴፓ

አርብ ጥቅምት 29 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) በሰኔ ወር አጋማሽ በክልሉ ከተደረገው ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ በኋላ በአባላቱ፣ በደጋፊዎቹ እና አመራሮቹ ላይ የሚደርስባቸው እስር፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ቀጥሏል ብሏል።

ከክልሉ መንግስት ጋር ችግሩን ለመፍታት ያለመ ውይይት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም በፓርቲው አባላት አና ደጋፊዎች ላይ የሚፈጸመው እስርና ወከባ ሊቆም አንዳልቻለ የፓርቲው የውጪና አለም ዓቀፍ ዘርፍ ኃላፊና የፓርላማ አባሉ መብራቱ አለሙ(ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ለበርካታ ጊዜያት እስር ላይ የነበሩ ወደ ሃያ የሚደርሱ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ጥቅምት 28/2017 መፈታታቸውንም አያይዘው ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በክልሉ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ጥሩ የሚባል እንዳልኾነ በመግለጽ ጉዳዩ አሳሳቢ ነው ብለዋል።

በዚህ ምክንያት ከመንግስት ጋር አብረን እንስራ ወይስ አንስራ የሚለውን ጉዳይ ለመወሰን የፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ ስብሰባ አድርጎ ውሳኔ አንደሚያሳልፍም መብራቱ (ዶ/ር) ጠቁመዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

08 Nov, 13:17


ገንዘብ ሚኒስቴር በፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ ምርቶች ላይ ክልከላ ጣለ

አርብ ጥቅምት 29 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዘይትን ጨምሮ ያለውጭ ምንዛሬ ፍቃድ በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ ምርቶች ላይ ሚኒስቴሩ ክልከላ እንዳደረገ ነው የገለጸው፡፡

በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሺያ ዘላቂ በሆነ መንገድ ውጤታማ እንዲሆን ከማስፈለጉ አንጻር ይህን ውሳኔ መወሰን የግድ ሆኖ መገኘቱም ነው የተገለጸው፡፡

በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈጸመባቸው እቃዎችም ከዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ጀምሮ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን የጉምሩክ መስፈርት በማሟላት እቃቸውን ማውጣት እንደሚገባቸው የገለጸው ገንዘብ ሚኒስቴር ይህን እንዲያስፈጽሙም ለጉምሩክ ኮሚሽንና ለብሄራዊ ባንክ ደብዳቤን ልኳል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤው በቀጣይ ዘይትን ጨምሮ በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ ምርቶች በምን አግባብ በአዲስ አሰራር ይቃኛሉ የሚለው ላይ ግን ግልጽ የሆነ ማብራሪያን አላስቀመጠም፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

08 Nov, 12:28


ሕብረት ኢንሹራንስ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማትረፉን አስታወቀ

አርብ ጥቅምት 29 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ሕብረት ኢንሹራንስ በ2016 በጀት ዓመት 525.27 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማትረፉን አስታውቋል፡፡

ኩባኒያው ያተረፈው ትርፍ ከተጠናቀቀው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከግማሽ በላይ ወይም የ60.62 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ሕብረት ኢንሹራንስ ይህንን ያስታወቀው ዓመታዊ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን በትላንትናው እለት ባካሄደበት ወቅት ነው።

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ከሁለቱም ከሕይወት እና ሕይወት ነክ ካልሆነው) የሰበሰበው አጠቃላይ አረቦን ገቢ ወደ 1.96 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ጠቅሷል።

ሕብረት ኢንሹራንስ ከሰበሰበው አጠቃላይ አረቦን መጠን ብር 1.7 ቢሊዮን ብር የተገኘው ሕይወት ነክ ካልሆነ የኢንሹራንስ ስራ መሆኑን በሪፖርቱ አመላክቷል።

የሕብረት ኢንሹራንስ የተከፈለ ካፒታል አንድ ቢሊዮን ብር መድረሱንና የኩባንያው ካፒታል ከባለፈው ዓመት በ2 መቶ 21 ሚሊዮን ብር እድገት አሳይቷል፡፡

የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ባለፈው አመት በአማካይ 23.72 በመቶ እድገት ማሳየቱን ኩባንያው ጠቅሶ በዚህም የሕብረት ኢንሹራንስ እድገት 30.19 በመቶ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ሕብረት ኢንሹራንስ አክሎም በ2016 በጀት ዓመት 6 መቶ 93 ሚሊዮን ብር ካሳ መክፈሉን በሪፖርቱ አመላክቷል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

08 Nov, 08:56


የአትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ለስራው እንቅፋት አንደሆነበት ገለጸ።

“በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ባለስልጣን ላይ ክስ መስርቻለሁ” ተቋሙ

አርብ ጥቅምት 29 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በትግራይ ክልል በተለይም በመቀለ ተንቀሳቅሶ ስራ መስራት እንዳልቻለ አስታውቋል

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ጸሃዬ እምባዬ ለአዲስ ማለዳ አንደተናገሩት፣በመቀሌ ከተማ የሚገኙ አንዳንድ የመንግስት አመራሮች የተቋሙን ስራ ሆነብለው ያደናቅፋሉ ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የመቀሌ ከተማ የሀድነት ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሀላፊ አቶ ብርሃነ ነጋሽ ላይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ክስ መመስረቱን ገልጸዋል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተገቢውን ምላሽ የማይሰጡ አስፈጻሚ አካላትን ጉዳይ ወደፍርድ ቤት መውሰዱን አንደሚቀጥልም አቶ ጸሃዬ አረጋግጠዋል።

በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለክልሉ ወግናችሁ በጦርነቱ ተሳትፎ አላደረጋችሁም በሚል ከስራቸው የተሰናበቱ የክልሉ ፖሊስ አባላት ጉዳይ ላይ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ምላሽ አንዲሰጥ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ጥቅምት 28/2017 ዓ/ም አንደተጠናቀቀም ተናግረዋል።

ጉዳዩ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ በቀጣይ ቀናት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ ክስ አንደሚከፍቱ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሃላፊ አመልክተዋል።

ለተቋሙ ከሚደርሱ ቅሬታዎች ውስጥ ከፍተኛውን (46.8 በመቶ) ድርሻ የሚይዙት ከስራ ስንብትና ዝውውር ጋር የተያያዙ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

08 Nov, 08:38


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያ ከወለድ ነጻ አገልግሎት ሰጪ ባንኮችን ያማከለ አይደለም ተባለ

አርብ ጥቅምት 29 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በአገር አቀፍ ደረጃ ባንኮች
የገንዘብ ፍሰታቸውን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ባንኮች እርስ በእርሳቸው መበዳደር የሚችሉበትን የብድር አማራጭ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በዚህም ተግባራዊ የሚሆነው አገልግሎትም የወለድ ተመን በብሔራዊ ባንኩ ፖሊሲ መሰረት የሚደረግ ሲሆን ብድሩን በአንድ ቀን ወይንም የሰባት ቀናት የመክፈያ ጊዜ መኖሩን አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ስርዓት ከወለድ ነጻ የባንክ ተቋማትን የሚያሳትፍ ግልጽ የሆነ መመሪያ አለመኖሩ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል የሚል ሀሳብ እየተዘዋወረ ይገኛል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ያወጣው ባለ ሁለት ገጽ መመሪያ የብድሩን ዋና ዋና ጉዳዮችን ማለትም የመመለሻ ቀናትን፣ የወለድ መጠንን ፣ለተበዳሪ የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች እና ሌሎች ጉዳዮችን የሚገልጽ ቢሆንም ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች በምን መልኩ እንደሚሳተፉ እና ከመመሪያው ጋር እንደሚዋሀዱ አይገልጽም፡፡

ይህ ክፍተት በብሔራዊ ባንክ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ እና በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ውይይት የፈጠረ ሲሆን በርካታ አስተያየት ሰጪዎች በቀረበው ጉድለት ቅር መሰኘታቸውን ገልጸዋል።

ቅሬታቸውን ካጋሩት መካከልም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኤሊያስ አደም “የአሁኑ መመሪያ የኢትዮጵያን ከወለድ ነፃ የሆኑ ባንኮችን ያገለለ ሲሆን ይህም በዚህ ወሳኝ የፋይናንስ ገበያ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚገድብ ነው” ብለዋል።

ከወለድ ነጻ ገበያ ኢስላማዊ መርሆዎችን በመከተል የሸሪዓን ህግ በጠበቀ መልኩ እና ለኢስላሚክ የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ አቅርቦትን በማቅረብ ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አስታውሰዋል።

በመሆኑም ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከወለድ ነፃ ባንኮች በገንዘብ ገበያ ላይ ውጤታማ ሥራ እንዲሠሩ የሚያስችል የቁጥጥር ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ብሔራዊ ባንክ ጥናቱን አጠናክሮ በመቀጠል ከወለድ ነፃ ባንኮች በገንዘብ ገበያ ውስጥ እና በተፈቀደው የባንኮች የእርስ በእርስ ብድር ላይ እንዲሳተፉ የሚያመቻች መመሪያ በማውጣት የበለጠ አሳታፊ የፋይናንስ ሁኔታን መፍጠር አለበት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ኢስላማዊ የገንዘብ ገበያ መመስረት በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እንዲያድግ ወሳኝ በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከወለድ ነፃ ባንኮች በወጣው መመሪያ ማለትም በባንኮች የእርስበእርስ የብድር አገልግሎት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንዲሳተፉ የሚያስችል መመሪያ ማውጣት አለበት ብለዋል፡፡

በቤተልሄም ይታገሱ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

07 Nov, 14:10


ብሄርና የብሄር ጥያቄ ቅዠት ነው በሚል አንድ ሰፋ ያለ መጽሃፍን ለአንባቢ ያበቁት አቶ ሰብስቤ አለምነህ ላለፉት 30 ዓመታት በበህሄር ፖለቲካ ውስጥ እየደዳከረች ያለችው ኢትዮጲያ አሁንም የፖለቲካ ችግሯ እየተባባሰ ነው ይላሉ፡፡
ይሁን እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ይህን ለማቆም እድል አለው ብለዋል እንዴት?
ሙሉ ዝግጅቱን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ

https://youtu.be/fgGr2_nUCdQ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

07 Nov, 14:10


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን በሞሮኮ በሚካሄደው የአፍሪካ ሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ በመሆናቸው ብቻ 150 ሺህ ዶላር ያገኛሉ፡፡
ካፍ በአጠቃላይ ለውድድሩ ተሳታፊዎች የ2 ሚሊዮን 350 ሺህ ዶላር ሽልማትን አዘጋጅቷል፡፡ ይህም ከበፊቱ አመት የ52% ጭማሪን አሳይቷል፡፡
በውድድሩ የሚሰጠው የገንዘብ መጠን

ለአሸናፊ 600,000 ዶላር

ሁለተኛ 400,000 ዶላር

ሶስተኛ 350,000 ዶላር

አራተኛ 300,000 ዶላር

በምድብ ሶስተኛ ሆኖ ለሚጨርሱ 200,000 ዶላር ለእያንዳንዳቸው

አራተኛ ሆነው ለሚጨርሱ 150 000 ዶላር ለእያንዳንዳቸው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምድብ ሁለት ከኤዶ ክዊንስ ፤ ማሜሎዲ ሰንዳውስ እና ማሳር ጋር ተደልድሏል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

07 Nov, 09:52


ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ገለጸ

ሐሙስ ጥቅምት 28 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ ከህዳር 22 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንደያደርጉ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አዲሱ መመሪያ ከጥሬ ገንዘብ ንክኪ ነጻ የሆነውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በኢትዮጵያ ለማጎልበት እየተሰራ ያለውን ስራ ለማጠናከር እንደሚያግዝ እና የዲጂታል ግብይትን እየለመደ ያለውን ማህበረሰብ በይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ይህ ኢት ኪውአር ኮድ (EthQR Code) የሚል ሥያሜ የሚኖረው አሠራር ዓለምአቀፍ የአሠራር ልምዶችን መሠረት ያደረገ፣ የክፍያም ሆነ የግብይት ተዋናያንን ሙሉ መረጃ የሚይዝ ነገር ግን ከተወሰኑ አስፈላጊ መረጃዎች በቀር ሌሎቹን በምሥጢር የሚጠብቅ ሥርዓት መሆኑ ተገልጿል።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የዲጂታል ክፍያ አገልግሎትና ግብይት የጥሬ ገንዘብን ዝውውር የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ፣ ሕብረተሰቡ ለሥርቆት፣ በእጁ ያለው ገንዘቡም ለእርጅና እንዳይጋለጥ፤ ከባንክ ውጭ የሚዘዋወር የገንዘብ መጠን እንዲቀንስ፣ ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ገንዘቡን ለማሳተም የሚወጣ ወጪን እንዳይጨምር ለማድረግ ይረዳል ብሏል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

07 Nov, 09:49


ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 163 ጋዜጠኞች ከሥራቸው ጋር በተያያዘ መገደላቸው ተገለጸ

ሀሙስ ጥቅምት 28 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአንድ ዓመት ብቻ 163 ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ ለህልፈት መዳረጋቸውን ዩኔስኮ ነው የገለጸው፡፡

ከተገደሉት ጋዜጠኞች በተጨማሪም ከሥራቸው ጋር በተያያዘ የሚታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥርም እምብዛም አለመቀነሱን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት የዛሬ አስር ዓመት 95 በመቶ የነበረው የተገደሉ ጋዜጠኞች ፍትህ ያለማግኘ ሁኔታ ከአስር ዓመት በኋላም ቢሆን በ10 በመቶ ብቻ ቀንሶ 85 በመቶ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ግድያዎች፣ እስሮች እና መንገላታቶች ባለሙያዎችን ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ደህንነት ሲሉ ከሙያው እራሳቸውን እንዲያገሉ እያደረገ መሆኑን የገለጸው ተቋሙ በዚህም ምክንያት ሙያው አስጊ ከሚባሉ የስራ መስኮች በቀዳሚነት የሚመደብ እንደሆነ አስታውቋል።

ዩኔስኮ እነዚህን ነጥቦች ያነሳው በመዲናችን አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው ጋዜጠኞች በግጭት ቦታዎች ላይ እየገጠማቸው ያለውን የደህንነት ችግር ለመፍታት በሚመክረው 10ኛው ጉባዔው ላይ ነው፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

07 Nov, 07:47


ኢሰመጉ በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ ዞን አረጋዊያንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ

👉”በወልቂጤ ከተማም ብሄርን መሰረት በማድረግ በርካታ ሰዎች ታስረዋል” ጉባዔው

ሀሙስ ጥቅምት 28 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ባወጣው መግለጫ ጥቅምት 17/2017 በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ ዞን አዲስ ቅዳም ከተማ የፋኖ ደጋፊ ናችኹ በሚል አረጋዊያንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መግደላቸውን ገልጿል።

በክልሉ በቀጠለው ግጭት በመንግስትና በፋኖ ታጣቂዎች በሚተኮሱ ጥይቶች የንጹሀን ሰዎች ህይወት አያለፈ አንደሚገኝ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ቦሩ ወረዳ እና ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ “በታጠቁ አካላት” በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የንጹሀን ሰዎች እንደተገደሉ አስታውቋል።

በማእከላዊ ኢትዮጵያ አና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በርካታ ሰዎች ያለፍርድ ቤት ተእዛዝ በቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ ማቆያ ጣቢያዎች እንደድሚገኙ ኢሰመጉ አመልክቷል።

በተለይም በወልቂጤ ከተማ የሚታየው የዜጎች እስር ብሄርን መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቁሟል።

የፌደራል አና የሚመለከታቸው የክልል መንግስታት አነዚህን የመብት ጥሰቶች እንዲያስቆሙ ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

06 Nov, 13:37


በአማራ ክልል ለአንድ ወር የዘለቀው የዘፈቀደ እስር እንዲቆም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ዕረቡ ጥቅምት 27 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) አምነስቲ ዛሬ ጥቅምት 27/2017 ባወጣው መግለጫ የፌዴራል መንግሥት እና የአማራ ክልል በተቀናጀ መልኩ በክልሉ በፈፀሙት የዘፈቀደ እስር ሺዎች ሰለባ መሆናቸውን ገልጿል።

ተቋሙ በክልሉ ከመስከረም 18/2017 ጀምሮ አደግሁት ባለው ጥናት በአራት ማቆያ ቦታዎች ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን እንዳረጋገጠ ገልጿል።

በኢትዮጵያ እንዲህ አይነቱ በርከት ያለ የዘፈቀደ እስር ባለፉት አመታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ከለላ በማድረግ የሀሳብ ልዩነቶችን ለማፈን ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ሲልም ወንጅሏል።

በእስር ላይ ቆይተው የተለቀቁ ሰዎች አነጋግሮ መረጃውን እንዳሰባሰበ የጠቀሰው አምነስቲ፤አሁን ካሉት እስረኛ ማቆያ ቦታዎች በተጨማሪ ሌሎች ማቆያዎች እየተገነቡ መሆናቸውን ጠቁሟል።

ምሁራንና የፍትህ አካላት በዘፈቀደ እስሩ ዋነኛ ኢላማ መደረጋቸውንም ሪፖርቱ አመልክቷል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

06 Nov, 13:35


በሴት የአእምሮ ሕሙማን ላይ ያተኮረ ጾታዊ ጥቃት አየተፈጸመ ነው ሲል ኢሰመኮ ገለጸ።

ዕረቡ ጥቅምት 27 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን 2ኛው የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ የተመለከተ ባለ 35 ገጽ የዘርፍ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ሪፖርቱ በትጥቅ ግጭቶች አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ለሞት፣ ለአካል ጉዳት እና ለንብረት ውድመት መዳረጋቸውን ያትታል።

የአረጋውያን እና አእምሮ ሕሙማን መንከባከቢያ ማእከላት ውስጥ የሚስተዋል እና በተለይም ሴት የአእምሮ ሕሙማን ላይ ያተኮረ ጾታዊ ጥቃት መኖሩን ሪፖርቱ ኣመልክቷል።

በ2016 ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባና በክልሎች እየተካሄዱ ባሉ የልማት ሥራዎች የሥራ ቦታዎቻቸው የፈረሰ አካል ጉዳተኞች አመቺ እና ተደራሽ ምትክ ቦታዎች ሳይሰጣቸው አንዲነሱ ተደርጓል ብሏል ኮሚሽኑ።

ይህም አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያንን ለከፍተኛ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ -ልቦናዊ ቀውሶች ማጋለጡን ገልጿል።

በረቂቅ ደረጃ የሚገኘው የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ ግልጽና አሳታፊ በሆነ መንገድ በፓርላማ ጸድቆ ወደ ሥራ ሊገባ የሚችልበትን ሁኔታ እንዲያመቻችም ኢሰመኮ በሪፖርቱ ጠይቋል

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

06 Nov, 10:53


የአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚወዛገቡባቸው አከባቢዎች ያለው ውጥረት ከመለዘብ ይልቅ ከሯል።

ውዝግቡ ከወሰንና ማንነት እስከ መሠረታዊው የትውልድ ዕጣ ወሳኝ ነገር -ትምህርት ድረስ ዘልቋል።

የውዝግቡ አካል የሆነችው የአላማጣ ከተማ የቀድሞና የአሁን ከንቲባዎችን የተቃርኖ መንገድ ቀጣዩን መስፈንጠሪያ ተጭነው ይመልከቱ
https://youtu.be/8EBF43g59-A

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

04 Nov, 14:06


አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ሌንጮ ለታ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር ፍቺ ስለፈጸሙበት ሁኔታ ፣ከ50 ዓመት በኋላም የፓርቲው ድርጅታዊ  ቁመና ላይ ያላቸውን ትዝብትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን  አጋርተዋል፡፡

እንዲሁም እሳቸው የመሰረቱት የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የት ነው ያለው? የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ እንዴትስ ቃኝቶታል? በሚሉና በሌሎች ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ  ከአዲስ ማለዳ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገዋል፡፡

ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/IbPtIQ_0i0Q?si=F6qHaNEUibNmejC8

አዲስ ማለዳን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

04 Nov, 09:55


"መንግስትም ሆነ ታጣቂ ቡድኖች እኛ ሰላም እንፈልጋለን ይላሉ ሰላምን ማጽናት የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኗባቸዋል"- ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

ሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የቀድሞ የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ታጣቂ ቡድኖች ሰላም እንደሚፈልጉና ተገደው ወደ ትጥቅ ግጭት እንደገቡ ደጋግመው እንደሚያነሱ ገልጸዋል፡፡

ትልቁ ጥያቄ መሆን ያለበት ሰላም እንዴት ይምጣ የሚለው ነው ያሉ ሲሆን መንግስትም ሲጠየቅ ሰላም እፈልጋለሁ፣ ሽማግሌ ልክያለሁ ሞክሬያለሁ፣ ሰላም አጥተናል ሰላም እንዲሆን እመኛለሁ ይላል  ታጣቂ ቡድኖችም ሲጠየቁ እኛም ሰላም እንፈልጋለን ተገደን ነው ወደዚህ ነገር ውስጥ የገባነው ማለታቸውን አንስተዋል።

በመሆኑም ሁለቱም ሰላምን እንፈልጋለን የሚሉ ወገኖች ናቸው ሰላምን እንዴት እናጸናለን የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኖብናል ሲሉ ዶ/ር ዳንኤል ገልጸዋል።

በተጨማሪም ይሄ የሰላም ጥያቄ ለመንግሥት እና ለተፋላሚ ወገኖች ብቻ የሚተው መሆን የለበትም ተመሳሳይ የሆነ የግጭት ዓውድ ውስጥ ባለፉ ሃገሮች ልምድ መሰረት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚከተሏቸው ስልታዊ እና ተቋማዊ ሂደቶች አሉ እነዚህም የሃገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትህ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ ሁለት መፍትሄዎች ቀደም ብለው ተጀምረው ተግባራዊ እየሆኑ መሆኑን ተናግረው የተዓማኒነት ጥያቄ ግን እየተነሳባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ሂደቱ በተቻለ መጠን ሁሉን አሳታፊና ተዓማኒ እንዲሆን ይፈለጋል፤ ነገር ግን በተዓማኒነታቸው ላይ ጥያቄ ምልክት ተነስቶባቸዋል። ይህ አይነቱ የተዓማኒነት ጥያቄ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የተነሳ ጥያቄ አይደለም ተመሳሳይ ሂደት በተከተሉ ሃገሮች በሙሉ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል ብለዋል።

በአማኑኤል ጀንበሩ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

04 Nov, 09:44


“የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሺያው የኩላሊት  ህመምተኞችን ሁኔታ ከባድ አድርጎታል” የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት

👉 “አንድ ድሃ ታማሚ በቀን ከ5 ሺህ ብር በላይ  ከፍሎ እንዴት ነው ሊታከም  የሚችለው”?

ሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ በተለያዩ የአገልግሎት መስጫ እና መገልገያ ተቋማት ላይ የተለያየ የዋጋ ልዩነት እና ጭማሬ እየተስተዋለ ነው፡፡

ይህን ተከትሎ በጤና ዘርፉ ላይ በተለይም የኩላሊት ታማሚዎች ለአንድ እጥበት 3ሺ500 ብርእንደሚያስፈልጋቸው እና ቀድሞ ከነበረው የአንድ ሺብር የዋጋ ጭማሬ ማሳየቱን የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

እጅግ እየጨመረ እና ከቀን ቀን እየከበደ የመጣው የህክምና ወጪ አንድ ታካሚ በሳምንት ሶስት ጊዜ ማድረግ ያለበትን የኩላሊት እጥበት ወደ ሁለት እና አንድ ዝቅ ለማድረግ እንዲገደድ ስለማድረጉም ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

አንድ ታካሚ በአግባቡ መንቀሳቀስ እንዲችል እና ንቅለ ተከላውን እስኪያካሂድ በህይወት ለማቆየት በሳምንት ሶስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት ማድረግ ያለበት ሲሆን በአሁን ሰአት በሳምንት ሶስት ጊዜ ለማድረግ በአጠቃላይ በአንድ ወር 42ሺህ ብር እንደሚያስፈልገው ተጠቁሟል፡፡

ይህም የገንዘብ መጠን መካከለኛ እና አነስተኛ የህክምና አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ላይ የሚጠየቅ እንደሆነ እና ከፍተኛ በሚባሉ ሆስፒታሎች አራት ሺ አምስት መቶ እና ከዛ በላይ ለአንድ የእጥበት አገልግሎት እንደሚጠየቅ አቶ ሰለሞን አመላክተዋል፡፡

እንዲሁም የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት በተለያዩ ድርጅቶች እና መስሪያ ቤቶች የእርዳታ ጥሪዎችን እንደሚያቀርብ ነገር ግን መልካም ምላሽ ማግኘት አለመቻሉ ከዋጋው ጭማሬጋር ሌላኛው ስጋት እንደሆነባቸው ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

በብዛት በበሽታው ተጠቂ ሆነው የህክምና ድጋፍ የሚፈልጉት ወጣቶች በመሆናቸው እንደሀገርም የስራ ሀይል ያለውን ዜጋ ማጣት ሊያሳዝን እና ሊያሳስብ ይገባል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ሁሉም ሰው ለታማሚዎቹ በተቻለ መጠን እርዳታ ለማድረግ ፍቃደኛ እንዲሆን እና ሁሉም ሰው በየእድሜ ክልሉ የኩላሊት ምርመራ በየጊዜው በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡

በቤተልሔም ይታገሱ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Nov, 11:34


የትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ ማድረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ

ቅዳሜ ጥቅምት 23 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደረጉ የመንገድ ግንባታዎችን ተከትሎ የተርሚናል ለውጥ መደረጉንም ቢሮው ተጠቁሟል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39406

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Nov, 09:19


በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት ባለስልጣንን ጨምሮ ከ45 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ

ቅዳሜ ጥቅምት 23 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ትናንት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ባለስልጣንን ጨምሮ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ተነግሯል፡፡

የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩን ጨምሮ ከ45 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ምንጮችን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ቢቢሲ አመራሩና በርካታ የጸጥታ ሃይሎች መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ሃይል ወደሚንቀሳቀስበት አካባቢ ሲያመሩ ግድያው መፈጸሙ ነው የተገለጸው።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39402

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Nov, 08:01


“የኦሮሞ ጥያቄ ከመገንጠል መለስ ምላሽ ማግኘት ይችላል” እንዲሁም የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ  ህብረ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑን ዲሞክራሲያዊ በማድረግ መመለስ ይቻላል በሚሉና በመሰል አስተያየታቸው የሚታወቁት  አቶ ሌንጮ ለታ  የብሄሩ የትግል ታሪክ መነሻና  መዳረሻ በመተንተን ይታወቃሉ፡፡

አሁናዊ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄስ እንዴት ይቃኛል? በሚሉና በሌሎች በርካታ ሀገራዊና ወቅታዊ ሁኔታን በሚመለከትም ከአዲስ ማለዳ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገዋል፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/kAdIRU2UQ7s

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

02 Nov, 06:41


በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአፋር ክልል መከሰቱ ተገለጸ

ቅዳሜ ጥቅምት 23 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)ትናንት ማምሻውን በአፋር ክልል የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ እንደሆነ ተገልጻል፡፡

ከዚህ ቀደም ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከበድ ያለ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱን ተጠቁሟል፡፡

እንደ አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ መረጃ ከአዋሽ በምዕራብ በኩል 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የመሬት መንቀጥቀጡ እንደተከሰተ የተገለጸው፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

01 Nov, 10:44


በቦሌ ቡልቡላ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Oct, 16:29


ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከ200 በላይ ስማርት ቅርንጫፎችን በመላ ሀገሪቱ በመክፈት ወደ ዲጂታል ባንክ መሸጋገሩን አስታወቀ፡፡

ዕረቡ ጥቅምት 20 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ባንኩ ያስተዋወቀው አዲሱ  አገልግሎት ደንበኞች ከወረቀት ንክኪ ነጻ በሆነ መንገድ ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጁ ታብሌቶችን በመጠቀም አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ነው።

በባንኩ ስማርት ቅርንጭፎች ወረቀት ላይ መሰረት ካደረገው ልማዳዊ አሠራር ወጣ ባለ አኳኋን፣ እንደ ገንዘብ ማስገባት፣ ማስወጣትና ማስተላለፍ ያሉ አገልግሎቶችን ደንበኞች ዲጂታል በሆነ መንገድ ማግኘት የሚችሉበትን አሠራር እንደሆነም ገልቷል፡፡

ከ 13 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት ባንኩ የዲጂታል አገልግሎቱን ለማሳደግና በዲጂታል ፈጠራ ልቆ ለመገኘት በርካታ በፈጠራ የታገዙ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለመድረግ በዲጂታሉ መስከ እየሰራ እንደሚገኝም ገልቷል፡፡

ባንኩ በሀገር ውስጥ በዲጂታል ወደፊት በመቅደም የደንበኞችን ተደራሽነትና እርካታ በመጨመር አካታች የፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓትን በመፍጠር ላይ እገኛለውም ብሏል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Oct, 11:15


የአብን አባልና የፓርላማ እንደራሴ ሆኑት ዶክተር አበባው ደሳለው በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ የንጹሃን ግድያ፣ ህጋወጥ ጅምላ እስር፣እገታ፣ ጾታዊ ጥቃት፣ መፈናቀል፣ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ፣ አግባብ ያልሆነ የቤቶች ፈረሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ ይህ መቼ ነው የሚያቆመው ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው "በሁለት ሳምንት መንግስትን አባርሬ 4 ኪሎ የአባቶቼን ርዕስት እወርሳለሁ " የሚል ገሃይል አለ አሁንም ቢሆን ግን ለሰላም ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን ከስር ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ

https://youtu.be/QVvqJgjafbU

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Oct, 10:07


"ኮሪደር የፈረሰውን ማፍረስ ነው ላስቲክ እና ጭቃ ፈረሰ ምትሉ ሰዎች መጀመሪያም አልነበረም" ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

👉"ኢትዮጵያ ውስጥ ሶስት ሾተላዮች ያሉብን ይመስለኛል"

ሐሙስ ጥቅምት 21ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) አንደኛው እያፈረሱ መስራት ነው ይህም ሲባል የኮሪደር ልማትን ማለት አይደለም ኮሪደር የፈረሰውን ማፍረስ ነው ላስቲክ እና ጭቃ ፈረሰ ምትሉ ሰዎች ከጅምሩም ያልነበረ ነው ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡

ሁለተኛው በእድል እና በጊዜ መቀለድ ነው ያሉ ሲሆን በተገኘው እድ መጠቀም እንጂ እድልን ማባከን እና ካለፈ በኋላ ጸጸት ዋጋ እንደሌለው ገልጸዋል፡፡

በሶስተኛነት ደግሞ ካለፈ በኳላ መቆዘም እንደሀገር የሚታይ ሾተላይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "አለም እያደነቀ ያለውን የኮሪደር ልማት መንቀፍ እኔ አላደረኩትም ከሚል እሳቤ የመጣ ነው" ብለዋል፡፡

እንደዚህ አይነት እሳቤ በብዙ እየጎዳን ስለሆነ አርቀን ወደ ፊት ብንሄድ ይሻላልም ብለዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Oct, 08:04


አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ጥናት ተደርጎ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አስታወቁ

ሐሙስ ጥቅምት 21ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እያካሄደ ነዉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይም ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 124 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ማዘዙን እና በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

በሌላ መልኩ ኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ማስመዝበቧን እና ባለፈው አመት 8 ነጥብ 4 የተመዘገበ ዕድገት መገኘቱን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ፤ በዚህም ዓመት ከዓምናው የተሻለ ዕድገት እንደሚመዘገበ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት 180 ቢሊየን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን መቶ በመቶ እቅዱን ያሳካ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ገቢ የተደረገውን ሪፎርም ተንተርሶ የተገኘ ገቢ መሆኑን እና በ2014 ዓመት በሶስት ወራት ውስጥ የነበረው ገቢ 70 ቢሊዮን ብር እንደነበረ አስታውሰው በ2015 ዓመት ደግሞ በሶስት ወራት ውስጥ 93 ቢሊዮን ብር መግባቱን በመግለጽ የልዩነት ስፋቱን አመላክተዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

31 Oct, 06:17


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ የሚሰጡትን ማብራሪያ በአዲስ ማለዳ ቀጥታ ስርጭት ለመከታተል ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተሉ።

https://www.youtube.com/live/tUHGU09UMPA?si=iAqAm47H5m3Avqee

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

30 Oct, 14:06


ካለፈው ታህሳስ አንስቶ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ውዝግብ ውስጥ የገቡት ኢትዮጵያና ሱማሊያ በመካከላቸው ያለው ችግር ከመፈታት ይልቅ ወደ ተወሳሰበ ጉዳይ እየሄደ ይመስላል፡፡

የቪላ ሶማሊያ ሰዎች ይህን የሁለቱን አገራት ጡዘት የሚያባብስ አደገኛ ውሳኔ በትናትናው እለት መወሰናቸው የተሰማ ሲሆን ይህም የቀጣናውን ፖለቲካዊ አሰላለፍ እንዲሁም የሃገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደለየለት መካረር የሚከተው ስለመሆኑ ብዙዎች ያነሳሉ፡፡

ለመሆኑ አዲሱ የሃሰን ሼህ መሃመድ መንግስት ውሳኔ አንድምታው ምንድን ነው? የሚለውን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/YFSCPY4phmk?si=xRpKPKyGbdOLQP3U

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

30 Oct, 12:21


‹‹በተወሰኑ ክልሎች ላይ የተከሰተው የወባ እና ኮሌራ ወረርሽኝ የጤና መብትን አሳሳቢ አድርጎታል›› ኢሰመኮ

ዕረቡ ጥቅምት 20 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው ሪፖርት የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሁኔታን መዳሰሱን አስታውቋል፡፡

ሪፖርቱ ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም ያለውን ጊዜ የሸፈነ ሲሆን የጤና ፖሊሲው ሰብአዊ መብቶች ተኮር በሆነ መልኩ መቀረጹ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ የተከራዮችን አቅም ባገናዘበና የመኖሪያ ቤት መብትን ለማረጋገጥ በሚያግዝ ሁኔታ ሥራ ላይ መዋሉ በሪፖርቱ ከተካተቱ ቁልፍ እመርታዎች መካከል መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ከነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ከተከሰተው የትጥቅ ግጭት እና በሌሎች ክልሎችም ከቀጠለው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ መኖሪያ ቤትና የመተዳደሪያ ንብረቶችን ጨምሮ በመሠረተ ልማቶችና የአገልግሎት ተቋማት ላይ ውድመት የደረሰ ሲሆን በተለይም በምግብ፣ በጤና፣ በንብረት፣ በትምህርት፣ በሥራና ተያያዥ መብቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጻል።

በተጨማሪም አፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎችን ጨምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ከግጭትና ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ከሚከሰት የምርት መቀዛቀዝ እንዲሁም የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ንረት ጋር ተዳምሮ በርካታ ሰዎችን ለምግብ እጥረት መዳረጉም ተጠቁሟል።

በተመሳሳይ በተወሰኑ ክልሎች የተከሰተው የወባ፣ ኮሌራና ኩፍኝ ወረርሽኝ የጤና መብት ሁኔታን አሳሳቢ ማድረጉ እና አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች በርካታ የንግድና መኖሪያ ቤቶች ሕጋዊ ሂደትን ባልተከተለ መልኩ እንዲፈርሱ መደረጋቸው እና የሠራተኞች ደመወዝ በወቅቱና በአግባቡ ባለመከፈሉ ምክንያት ሠራተኞች ለተለያዩ ችግሮች መዳረጋቸው በሪፖርቱ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡

በመሆኑም መንግስት በተነሱ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ በማጤን እና ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ውሳኔዎችና እርምጃዎች ሕጋዊ ሁኔታን በተከተለ መልኩ ከባለመብቶች ጋር ተገቢው ውይይት ተደርጎ እንዲወስን ኢሰመኮ አሳስቧል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Oct, 19:34


" ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ምሽት በተረጋገጠ የX ገጻቸው  ከደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር ንግግር ማድረጋቸውን በሚመለከት አጋርተዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም ለመቀራረቡ እኛ እንቀርባለን ብላችሁ እኛን ለማገናኘት በመጣር ላይ ያላችሁ ክብር ይስጣችሁ" ሲሉ አመስግነዋል።

አቶ ጌታቸው አክለውም "ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " ሲሉ ከደብረጽዮን (ዶ/ር) ጋር አብረው ከተነሱት ፎቶ ጋር ባጋሩት መልእክት።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጋራ የተነሱትን ፎቶ ብዙዎች በመጋራት አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አብዛኞቹ ምስሉ በአውንታ ተቀብለው ሲያስተጋቡ ፤ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ " ከአንገት በላይ " ያሉትን ፎቶና መልእክት ንቅፈው እየጻፉ ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ እና ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለበርካታ ሳምንታት በሚዲያ እና በፅሁፍ መግለጫ ብዙ ሲባባሉ እንደነበር አይዘነጋም።

ምንም እንኳን ዛሬ በምን ጉዳዮች ላይ እንደተነጋገሩ በዝርዝር ባይታወቅም አቶ ጌታቸው ረዳ ያጋሩት ፎቶ በክልሉ አመራሮች መካከል ያለውን ውጥረት ያረግበዋል ተብሎ ታምኖበታል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Oct, 09:58


‹‹የመምህራን ችግር ሳይፈታ የትምህርት ጥራት ይመጣል ተብሎ አይጠበቅም›› ዶ/ር አበባው ደሳለው

ማክሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የመምህራን አቅም ሳያድግ የትምህርት ጥራት ለማምጣት የሚሰራው ስራ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል የገለጹት የአብን አባልና የፓርላማ እንደራሴ የሆኑት ዶ/ር አበባው ደሳለው ናቸው፡፡

እንደራሴው ይህን ያሉት የአጠቃላይ የትምህርት አዋጅን መርምሮ ለቋሚ ኮሚቴ ለመላክ በተደረገ ውይይት ላይ ነው፡፡

የመምህራን የደሞዝ ጥያቄ ሳይስተካከል፤ደሞዝ ክፈሉኝ ያለ መምህር እየታሰረ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህረት ግብአቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ አዋጅ ማሻሻል ጥቅሙ እንብዛም ነው ያሉት ዶ/ር ደሳለው አዲስ የሚጸድቀው አዋጅ እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ይገባዋል ብለዋል፡፡

አዋጁ በጸጥታ ችግር ምክንያት በትምህርት ገበታቸው ያልተገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናትን ወደ ትምህርት ገበታቸው በመመለስ ረገድም ጉልህ ሚና ሊኖረው እንደሚገባ በማንሳትም አሁን ላይ አዋጁ ወደ ቋሚ ኮሚቴ ከመላኩ በፊት ዳግም ሊጠና ይገባል ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በምክር ቤቱ አባላት ከተነሱት ሀሳቦች መካከል የንግድ እና የመጠጥ ቤቶች በትምህር ተቋማት አካባቢ ላይ መበራከት እና የተማሪዎች አለባበስ እና የወላጅ ክትትልን በተመለከተ የሚያነሳው አዋጅ መታየት እንደሚገባው ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም የስራ እድል ሁኔታ ተማሪዎችን ለትምህርት ሊያነሳሳ የሚችል ነው የሚለውን መገምገም እና የየክልሉን የሰላም ሁኔታ ዘላቂ መፍትሄ የመፍጠር አቅጣጫ ሊቀመጥ እንደሚገባ በአባላቱ ተነስቷል፡፡

በተጨማሪም በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚሰጥ ትምህርት ገደብ እንዳይደረግበት እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጭምር ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ጎን ለጎን መሰጠት እንደሚገባም ከግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል ተብሏል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Oct, 09:13


ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በምክርቤቱ አዲሶቹን የሚኒስትሮች ሹመት በመቃወም ንግግር አድርገዋል፡፡

በተለይም ‹‹ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ብቁ አይደሉም›› ሲሉ የተደመጡ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪም ጠንከር ያለ ምላሽ ተሸጥቷቸዋል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ያደረጉትን የተቃውሞ ንግግር እና የተሰጣቸውን ምላሽ ከስር ባለው ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/R7yh_s78zv8

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Oct, 08:45


‹‹ባለንብረቱ በመሬቱ ጉዳይ አስከምን ድረስ ሊሄድ ይችላል የሚለውን በአዲሱ አዋጅ  ግልጽ በሆነ መንገድ ሊቀመጥ ይገባል››የም/ቤት አባላት 

ማክሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)  ባለንብረቱ በመሬቱ ጉዳይ አስከምን ድረስ ሊሄድ ይችላል የሚለውን ግልጽ በሆነ መንገድ ሊቀመጥ እንደሚገባ የምክር ቤት አባላት በዛሬው ውሏቸው ጥያቄን ካነሱበት ጉዳይ አንዱ ነበር፡፡

የከተማ መሬት ይዞታ እና ንብረት ምዝገባ አዋጅ ማሻሻያ እንዲደረግበት ጥያቄ በቀረበበት ወቅት ነው ይህ ሃሳብ በአባላቱ የተነሳው፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39407

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Oct, 08:15


‹‹ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ብቁ አይደሉም›› ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

👉🏿‹‹ዶ/ር ጌዲዮንን በጥቅሉ ብቁ አይደሉም ብሎ መፈረጅ ተገቢ አይደለም›› ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ

ማክሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በዛሬው እለት ሹመታቸው የጸደቀው የ5 ሚኒስትሮች የሹመት ሂደት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ዘንድ ቅሬታን አስነስቷል፡፡

የአካሄድ፤የስነስርአትና መሰል ህጋዊ አካሄዶች ተጥሰዋል በሚል በአንዳንድ የምክር ቤት አባላት ከተነሱ ቅሬታዎች ባላፈ የተሿሚዎች የግል አቅምን በማንሳት ተቋውሞ የቀረበበት ነበር፡፡

የአብን አባልና የፓርላማ እንደራሴ የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በተለይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስን በማንሳት ለቦታው ብቁ አይደሉም ሲሉ ሞግተዋል፡፡

ተቋማዊ ገለልተኝነትን አስጠብቆ ከመጓዝ አንጻር በፍትህ ሚኒስትር የሰሩት ስራ ጥያቄ የነበረበት ነበር ያሉት ዶ/ር ደሳለኝ አሁንም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ተሹመው ይህ ነው የሚባል ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አላስብም ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ እንዴት አዲስ የካቢኔ ሹመት ማግኘት አለባቸው የሚለው ሂደትም ተገቢ ግምገማ ሳይከናወንበት የተደረገ ነው የሚል እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

የመንግስት ተጠሪ ሚንስትር የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በተሸሙት ዶ/ር ጌዲዮን ላይ የተሰነዘረው አስተያየት ጥቅል ፍረጃ ያለበትና ተገቢው ምርመራ ያልተከናወነበት ነው ሲሉ ተከላክለዋል፡፡

ተሿሚን ብቁ አይደሉም በሚል የተሰጠው ጥቅል ፍረጃም ነባራዊውን ሁኔታ ያገናዘበ ነው ለማለት ይከብደኛል ሲሉም በዶ/ር ደሻለኝ ጫኔ የቀረበውን ቅሬታ አጣጥለውታል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

29 Oct, 08:00


አዲስ ማለዳ ከምክርቤቱ እያስተላለፈችዉ ያለውን ቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ https://www.youtube.com/live/RqHIXwqjYNM?si=0kJlPbOQHIcJXBye

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Oct, 18:39


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በነገው እለት በምክር ቤት ቀርበው የሚያደርጉትን ተጠባቂ ንግግር በአዲስ ማለዳ በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ!

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Oct, 14:14


“በኢትዮጵያ ታሪክ ከኦሮሞ ማህበረሰብ አንድ መሪ ወጥቶ ወደ ቤተመንግስት እና ወደ ፊት ሲመጣ ግርግር መፍጠር አዲስ አይደለም፡፡ ዘመነ መሳፍንትን የፈጠረው የኦሮሞ ቤተ መንግስት መግባት ነው፡፡ ኦሮሞን ተረኛ የሚሉት በጥላቻ ነው“
አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ያደረገችውን የመጨረሻ ክፍል ቃለ-ምልልስ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተሉ።

https://youtu.be/LQUJn733Jto?si=L7DmDjdZEA5rzf8W

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Oct, 13:50


‹‹በዘፈቀደ የሚሰጡ ሹመቶች ከባድ ቅጣትን ያስከትላሉ›› የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር

ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፍቃድና እውቅና ውጪ የሚደረጉ ሹምሽሮች እስከ በጀት መገደብ የሚደርስ ቅጣት ሊጣል ይችላል ሲል በጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር አስጠንቅቋል፡፡

ጊዚያዊ አስተዳደሩ በአቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ ተፈርሞ ባሰራጨው መመሪያ ፤ " የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች ማደናቀፍ እና በዘፈቀደ ህጋዊ ያልሆነ ሹመት መስጠትና መንሳት የበጀት ቅጣትና የህግ ተጠያቂነት ያስከትላል " ሲል ነው ማስጠንቀቂያ የሰጠው።

መንግስታዊ ስልጣን እና ሃላፊነት የሌለው ' ቡድን ' በማለት የተጠቀሰው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የሚሰጠው ሹመት የመሻርና ሹመት የመስጠት ተግባር ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

በመሆኑም ቡድኑ የሚያካሄዳቸውን ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት እንዲቆም ይህንን የጊዚያዊ መንግስቱ መመሪያ በመቀበል ፍርድ ቤት ጨምሮ የዞን እና የወረዳ የመንግስት መዋቅሮች ህጋዊ አሰራር እንዲከተሉና ህግ በሚጥስ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንዲሁም በክልሉ በየመዋቅሩ ያሉ ምክር ቤቶች ጊዚያቸው ያለፈ እና ህጋዊ መሰረታቸው ያበቃ መሆኑን በመቀበል ሹመት ከመስጠትና ከመሻር እንዲቆጠቡ ሲል ነው ያሳሰበው፡፡

ላለፉት ወራት የዘለቀው የህወሃት አመራሮች ፍትጊያ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን እኔ ብቻ ነኝ እውቅና ያለኝ የሚለው የሁለቱ ቡድኖች መካረርም ምንም አይነት መፍትሄ አላገኘም፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Oct, 13:21


‹‹በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙት 996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 86ቱ ብቻ ናቸው የተከፈቱት›› የዞኑ ትምህርት መምሪያ

ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ ከሚገኙ 996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 86ቱ ብቻ ትምህርት እየተሰተባቸው እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ በዘንድሮ ትምህርት ዘመን 710 ሺህ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ታቅዶ መመዝገብ የቻሉት 70 ሺህ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተከፍተው ሥራ የጀመሩት ትምህርት ቤቶችም ከችግሮች የጸዱ አይደሉም ያሉት አቶ ጌታሁን ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡ ሕጻናት በየመንገዱ “መጽሐፍና ደብተራቸው እየተቀደደባቸው እና እየተደበደቡ አልቅሰው ይመለሳሉ” ብለዋል።

ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እንደላኩ የተሰማባቸው ወላጆችም እስከ “15 ሺህ ብር ቅጣት፣ ድብደባን ጨምሮ እስከ ግድያ የደረሰ ግፍም እንደተፈጸመባቸው” የትምህርት መምሪያ ኃላፊው ለአሚኮ ተናግረዋል።

አቶ ጌታሁን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ቤት ሲውሉ በተለይም ሴት ልጆች “ያለዕድሜ ጋብቻ እየተፈጸመባቸው ነው” ሲሉ ገልጸው ወንዶቹም ቢኾኑ ዘመን በወለደው አጓጉል ቦታ እየዋሉ ለወላጆቻቸው የጭንቀት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Oct, 12:26


‹‹የኮሪደር ልማት ግንባታና የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ ለእንግልት እየዳረገን ነው›› ነዋሪዎች

‹‹የኮሪደር ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ብቻ ነው ችግሩ መፈታት የሚችለው›› መምሪያው


ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የኮሪደር ልማት ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል በመሆኑም በመንገድ ዳርቻዎች ላይ የሚካሄደው ግንባታ የትራፊክ ፍሰት መጨናነቁን መጨመሩ ተገልጻል፡፡

በአንደኛ እና ሁለተኛ ዙር የግንባታ ሂደት የቀጠለው የኮሪደር ልማት አስቀድሞ ከነበረው የመንገድ መጨናነቅ እና የትራፊክ ፍሰት እጅግ እንደጨመረ እና ተሸከርካሪዎችም ሆኑ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ካሰቡበት ቦታ ለመድረስ አማራጭ መንገዶችን ቢጠቀሙም ችግሩ እየባሰ እንጂ እየተፈታ እንዳልሄደ ይናገራሉ፡፡

በሰዓት ወደ ስራ ገበታ መግባትም ሆነ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ በመንገድ ላይ የሚያጋጥመው የትራፊክ መጨናነቅ ቀደም ብሎም ቢሆን ዋነኛ ችግር የነበረውን የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል ይላሉ፡፡

አማራጭ መንገዶች ለተሸከርካሪዎች ክፍት ቢደረጉም የመንገዱ እና የተሽከርካሪው ብዛት አለመመጣጠኑ መጨናነቁን ሊያስተካክል አለመቻሉም በምሬት የሚገልጹት እነዚሁ ቅሬታ አቅራቢዎች እኔ ነኝ የሚል ተጠሪ አካል ለጉዳዩ ትክክለኛና አፋጣን ምላሽ እየሰጠ አይደለም ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በዛየሚሉ አሽከርካሪዎች “አቋራጭ መንገድ ነው የምንጠቀመው በታሪፍ ዋጋ አያዋጣንም” በማለት የዋጋ ጭማሪ እያደርጉ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡
አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሙያ እና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን ለገሰ በአሁን ሰዓት በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኘው የከተማ ልማት ከተለመደው ውጪ የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅን አስከትሏል ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ መጨናነቁን እና አደጋውን ለመቀነስ እየተሰራ እንደሆነ እና አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ክፍት በማድረግ እንዲሁም ግንባታ በሚካሄድባቸው ቦታዎች በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የገለጹት ኢንስፔክተር ሰለሞን የኮሪደር ልማቱን በፍጥነት በመጨረስ ወደ መደበኛው የትራፊክ እንቅስቃሴ መግባት ዋነኛ መፍትሄ እንደሆነም ነው ያነሱት፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

26 Oct, 10:43


"የድጎማ ፖለቲካ ፖርቲዎችን መፍጠር ማቆም አለብን" ሲል ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በመንግሥት ድጎማ ላይ ተንጠልጥሎ ፖርቲ መመስረት መቆም አለበት ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

ቦርዱ ይህን ያለው በቅርቡ ያደረገዉን አገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡

"በኢትዮጵያ የመድብለ ፖርቲ ምስረታ ከተጀመረበት 1984 ዓ.ም በመንግሥት ድጋፍ ላይ ተንጠልጥሎ ቆይቷል" ያለው ቦርዱ በዚህም ፖርቲዎች በመንግሥት ድጎማ ላይ ተንጠልጥለዉ የቆዩ መሆናቸውን እና "የመንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ዓላማዉ ተጨማሪ ድጋፍ ሰጥቶ ፖርቲዎች ከፍ የሚሉበት እንጂ፤ የሥራ መፍጠሪያ አይደለም" ብሏል፡፡

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ውብሸት አየለ "የድጎማ ፖለቲከኛ አንድ ቦታ ላይ መቆም ይኖርበታል" ሲሉ አዲስ ለሚመጡ ፓርቲዎች አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጲያ ምርጫ ቦርድ አዲስ የሚመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት የሙሉ ዕዉቅና ለማግኘት ሲከፍሉ የነበረዉን 2 መቶ ብር ወደ 30 ሺሕ ከፍ ማድረጉን ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Oct, 13:48


ባለሃብቱ አቶ መቅደስ አክሊሉ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ዓርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ላለፉት ሶስት ቀናት በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው የነበሩበት ያልታወቀው ባለሀብቱ አቶ መቅደስ አክሊሉ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገልጧል፡፡

አቶ መቅደስ የአቢሲኒያ ባንክ ዋና ባለ ድርሻ ሲሆኑ ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የታወቀ ነገር አለመኖሩ የተነገረ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የ13 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንደተሰጠባቸውም ታውቋል::

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Oct, 11:33


በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ከ2ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የአልኮል መጠን ቅጣት መተላለፉ ተገለጸ

ዓርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ጠጥቶ ማሽከርከርን ለመቆጣጠር የሚያስችለው የአልኮል ትንፋሽ መመርመሪያ በተለያዩ ጊዜያት ተግባራዊ የተደረገ ቢሆንም መቀዛቀዞች እና ተግባራዊነቱ እየቀነሰ ነው የሚል ሀሳብ ሲዘዋወር ቆይቷል፡፡

የአልኮል ትንፋሽ መመርመሪያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል በመቆሙ ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር እንዳልተቻለ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመት ማሳወቁ ይታወሳል ቢሆንም ከበሽታው መረጋጋት ጋር ተያይዞ የተቋረጠው ምርመራ መቀጠሉ ተገልጻል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39405

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Oct, 08:14


አቶ ታዲዮስ ታንቱ የ6 ዓመት ከ3ወር ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተጣለባቸው

አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና ግጭት መቀስቀስ ወንጀል የተከሰሱትን አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የህገ-መንግስትና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ታዲዮስ ታንቱን በተከሰሱበትና ጥፋተኝነት በተባሉባቸው 3 ክሶች ነው የጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት የጣለባቸው።

አቶ ታዲዮስ ታንቱ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በፍትህ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አንደኛው ክስ ላይ እንዳመላክተው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/(1)ሀ እና አንቀጽ 257/ሀ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ግንቦት 11 ቀን እና በመጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም እና በተለያዩ የዩቲዩብ ቻናሎች ህዝባዊ አመጽ መቀስቀስ ወንጀል የሚል ነው።

በ2ኛ ክስ በተመለከተ ደግሞ የጥላቻ ንግግርንና ሀሰተኛ መረጃን ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁ 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7/4 በመተላለፍ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በአንድ የዩቲዩብ ቻናል ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል የሚል ክስ በዐቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

በ3ኛ ክስ ደግሞ የወንጀል ህግ ከንቀጽ 32 /1ሀ ና አንቀጽ 337 በመተላለፍ የመከላከያ ሰራዊትን እቅስቃሴን ለማሰናከልና የመከላከል አደጋ እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ ሀሰተኛ ወሬ በመንዛት ቅስቀሳ ማድረግ ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን በ4ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁ 958/2008 አንቀጽ 14 በመተላለፍ ህዝባዊ አመጽ እንዲፈጠር ቀስቃሽ መልዕክት በድምጽና በተቀሳቃሽ ምስል ተሰራጭቷል የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱም የ6 ልጆች አባት መሆናቸውንና የ70 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ሁለት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 24 መሰረት በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Oct, 07:41


ከታጣቂ ኃይሎች ጋር በውጭ ሀገራት ለመገናኘት ሀሳብ ማቅረቡን አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ

አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንዳሉት የታጠቁ ኃይሎች እና ራሳቸውን ከምክክሩ ያገለሉ ፓርቲዎችን እንዲሳተፉ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

"የታጠቁ ሀይሎችን እስካሁን ገጽ ለገጽ ወይም በቀጥታ አግኝተን አነጋግረናቸው አናውቅም ያሉት ኮሚሽነሩ የፖለቲካ ጥያቄ አቅርበው በምክክሩ እንዲሳተፉ በተለያየ መንገድ ጥሪ አድርገናል፤ ለድህንታቸው ሙሉ ዋስትና እንደምንሰጥ ከዛም አልፎ በውጭ ሀገራት ተገናኝተን ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፈቃደኛ መሆናችንን ገልጸናል ሲሉ ከዚህ በፊት የተደረገውን ጥረት አንስተዋል።

ከግጭት እና ጦርነት ያተረፍነው እንግልትና ስቃይ ነው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን እኛ የማደራደር ሀላፊነት ባይኖረንም ግጭቶች የሚፈቱበትን መንገድ የመቀየስ ስራ ግን እንሰራለን ብለዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

25 Oct, 03:48


“የኦሮሚኛ ቋንቋ ቤተመንግስት ለምን ገባ ብለው የሚከነክናቸው ሰዎች አሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዘመንን ሳስበው ከልጅ እያሱ ዘመን ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡” አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ያደረገችውን  ክፍል 2 ቃለምልልስ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተሉ።

https://youtu.be/gondkDP2tdc

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

24 Oct, 14:49


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

ሐሙስ ጥቅምት 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች አማራጭ ድረ-ገጾችን ተጠቅመው ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39397

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

24 Oct, 14:44


በጸጥታ ችግር ምክንያት ወደ ተለያዩ ክልሎች ደም ማድረስ አልቻልኩም ሲል የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎትአስታወቀ

አሁንም ብዙ ደም ፈላጊዎች እኛን እየተማጸኑ ነው-የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት

ሐሙስ ጥቅምት 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በተለያዩ ክልሎች እያጋጠመ ላለው የደም እጥረት የጸጥታ ጉዳይ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ሀላፊ ሲስተር ሀና ለገሰ አስታውቀዋል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39393

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

24 Oct, 14:38


‹‹አሁንም ድረስ በመሰረተ ልማት እጦት እየተሰቃየን ነው›› የኮሪደር ልማት ተነሺዎች

👉 ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተፈቷል ለማለት አንደፍርም- የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ

ሐሙስ ጥቅምት 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ በፒያሳ እና አራት ኪሎ አካባቢዎች ይኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች በኮሊደር ልማቱ ምክንያት ከቀድሞ የመኖሪያ መንደራቸው መነሳታቸው ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ተለዋጭ ቤቶች እና ቦታዎችን በእጣ በማቅረብ በወጣላቸው እጣ መሰረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ለልማት ተነሽዎቹ መኖሪያ ቦታን አስረክቧል፡፡

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39389

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

24 Oct, 14:30


“የኦሮሚኛ ቋንቋ ቤተመንግስት ለምን ገባ ብለው የሚከነክናቸው ሰዎች አሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዘመንን ሳስበው ከልጅ እያሱ ዘመን ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡” አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ያደረገችውን ክፍል 2 ቃለምልልስ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተሉ።

https://youtu.be/gondkDP2tdc

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

24 Oct, 06:49


በኮንሶ ዞን ሰገን ከተማ በተፈጸመ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገለጸ

ሐሙስ ጥቅምት 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ዞን ሰገን ዙርያ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ሰገን ከተማ ትናንት ጥቅሞት 12 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ወደ አካባቢው በመጡ ታጣቂዎች ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት የሁለት ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፁት፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡40 ሲሆን ከጉማይዴ አካባቢ በመጡ ታጣቂዎች መሆኑን ተናግረዋል።

በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡት በሹፍርና የሚተዳደሩት እሸቱ ጀማል እና ማዳቻ ኡዴሳ የተባሉ የሠገን ከተማ ነዋሪ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ደግሞ በፍቃዱ ማስረሻ እና አቶ ሀብታሙ ገነነ የተሰኙ ሲሆኑ፣ አቶ ሀብታሙ ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት ሲደርስባቸው አቶ በፍቃዱ ደግሞ እግራቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ በበኩላቸው በጥቃቱ የሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጸው በፍቃዱ ማስረሻ እና አቶ ሀብታሙ ገነነ የተባሉት ግለሰቦች በደቡብ ክልል ሶዶ ከተማ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

ድንበር ዘለል ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መጥተዋል ያሉት ነዋሪው በሰገን ዙሪያ የቀጠለው አለመረጋጋት እና የጸጥታ ችግር አርሶ አደሩ መሬቱን በአግባቡ እንዳያርስ እንቅፋት እንደሆነበት ጠቁመዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

23 Oct, 14:52


https://youtu.be/TLl1NiHupfg

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

23 Oct, 14:14


“መደበኛ ባልሆነ ማቆያ ቦታ ያሉበት ሳይገለጽ እንዲቆዩ እየተደረጉ የሚገኙ ተጎጂዎች እና የተጎጂዎች ቤተሰቦች ፍትህ ሊሰጣቸው ይገባል”- ኢሰመኮ

ዕረቡ ጥቅምት 13 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች የአስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁሙ በሚችሉ እና ያሉበት ሳይገለጽ በተራዘመ እስር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታ በተመለከተ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እና ፍትሕ ሊሰጣቸው ይገባል ሲል አስታወቀ፡፡

ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተወስደው ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ የቆዩ ከ52 በላይ የሆኑ ሰዎችን የተመለከቱ አቤቱታዎችን መርምሮ እስካሁን ድረስ 44 ሰዎች ከ1 ወር እስከ 9 ወር በተለያዩ መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸውን ማወቁን ገልጻል፡፡

በመሆኑም የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኃላፊዎችን እንዲሁም የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የዐይን ምስክሮችን እና የተለቀቁ ሰዎችን በማነጋገር መረጃዎችን እና ማስረጃዎችን ማሰባሰቡን ኢሰመኮ አስታውቋል፡፡

ተጎጂዎች በአብዛኛው ሰሌዳ በሌላቸው ተሽከርካሪዎችና በታጠቁ ሲቪል ወይም የደንብ ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት ተገቢውን የሕግ ሥነ ሥርዓት ባልተከተለ ሁኔታ በግዳጅ እንደሚያዙ ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም በእስር የቆዩበትን ቦታ የማያውቁ፣ በቂ ምግብና ውሃ የማይቀርብላቸው እና መሠረታዊ የመጸዳጃ፣ የመኝታ እና የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦቶች አለመኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡

የሚለቀቁትም በምሽት ዐይናቸው ተሸፍኖ በተሽከርካሪ ከተጫኑ በኋላ በተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች እንዲወርዱ ተደርገው እና “ለመጓጓዣ” በሚል ከ300 እስከ 1000 ብር ተሰጥቷቸው እንደሚለቀቁ ማስረዳታቸው ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

ኢሰመኮ ጉዳዩን በተመለከተ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምላሽ ለማግኘት የሚደረገው ጥረት ይህ መግለጫ እስከወጣበት ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች ያልተሳካ መሆኑን ገልጻል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Oct, 11:33


ቦርዱ በተለያዩ ምክንያቶች በ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሳኔ አሳለፈ

ማክሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባዔ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተያያዘ የዕግድ ደብዳቤ ይፋ አድርጓል፡፡

የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄና፣የአገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲን ጨምሮ 11 ፓርቲዎች ናቸው በቦርዱ እግድ የተጣለባቸው፡፡

ቦርዱ ፓርቲዎቹን ለምን እንዳገደ እስኪያሳውቅ ድረስም ፓርቲዎች ምንም አይነት ህጋዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይችሉም ነው ያስታወቀው፡፡

ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት  እግድ የተጣለባቸው ፓርቲዎች ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ክትትል እንዲያደርግም አሳስቧል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Oct, 10:37


ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የጡት ካንሰር ህመም

ይህ መረጃ ከየጤና ወግ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የቀረበ ነው

✍️✍️ በየአመቱ የጥቅምት ወር ለጡት ካንሰር ግንዛቤ በማስጨበጥ ታስቦ ይውላል።

💥 የጡት ካንሰር በአመት ከ 1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያጠቃል።

👉 የዘንድሮ የዓለም አቀፍ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር "ማንም ሰው የጡት ካንሰርን ብቻውን መጋፈጥ የለበትም''። በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

✍️ግንዛቤ ማስጨበጫው በራስ ላይ የሚደረግ የጡት ምርመራን አስፈላጊነትና በሽታው ከመሰራጨቱ በፊት ለመድረስና ለመዳን ያለውን ፍይዳ ይገልፃል።

✍️የጡት ካንሰር ምርመራ እንዴትና መቼ ይደረግ?

👉 የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድናቸው?

የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ካንሰሮች አንዱ ነው። በአለም አቀፍ ሁኔታ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር በ 1 ኛ ደረጃ ይቀመጣል። የጡት ሴሎች (ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ ይፈጠራል ። የጡት ካንሰር በአብዛኛው የሚከሰተው በሴቶች ቢሆንም በወንዶች ላይም ሊከሰት ይችላል።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39371

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Oct, 08:27


ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች የክፍያ ተመን ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አደረገ

ማክሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ለሀገር አቀፍና ለክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ ሰርተፊኬት ለማግኘት 100 ብር፤ ለሙሉ ዕውቅና ለሀገር አቀፍና ክልላዊ ፓርቲ 200 ብር እንዲሁም የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን በጉባኤ አሻሽለው ሲያቀርቡ 30 ብር ይከፍሉ እንደነበር ቦርዱ አስታውሷል።

እነዚህን የክፍያ ተመኖች ላይ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው መወሰኑን ያስታወቀው ቦርዱ አሁን ባደረገው ጭማሪም ጊዜያዊ ዕውቅና ክፍያ 15000 (አስራ አምስት ሺህ) ብር ፤ የሙሉ ዕውቅና ክፍያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር እና የሰነድ ማሻሻያ ክፍያ 5000 (አምስት ሺህ) ብር እንዲሆን መወሰኑን ቦርዱ አስታውቋል ።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 19:08


በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ እስከ አሁን መቆጣጠር ባለመቻሉ በሄሊኮፕተር እየተሞከረ መሆኑ ተገለጸ

👉 "በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ  እና ስጋት መከላከል እንዲሁም  ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ  ስለመሆኑ የገለጹት ከንቲባዋ አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት  አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ነው ብለዋል።

በመሆኑም የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን  ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል። 

ከንቲባዋ አክለውም ይህንን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጉ የሚገኙትን አካላት ሁሉ ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 17:05


በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ በዚህ ሰአት ተከስቷል

👉 እሳቱ ጠንከር ያለ ነው ፤ እስካሁን አልጠፋም ፤ ሰው ንብረት እያሸሸ ነው " - በስፍራው የሚገኙ ሰዎች

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

እሳቱ ከተነሳ በርከታ ደቂቃዎች ቢቆጠሩም እስካሁን መቆጣጠር እንዳልተቻለ በስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

የአይን እማኞቹ " እሳቱ ጠንከር ያለ ነው ፤ በስፍራው እሳት አደጋዎች ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ምንም ሊጠፋ አልቻለም።" ተብለዋል።

በስፍራው ላሉ የአደጋ ሰራተኞች ተጨማሪ ቦቴና እገዛ ያስፈልጋል ፤ በውሃ ብቻም የሚሆን አይደለም " ብለዋል።

" በአካባቢው ያሉ እሳቱ ያልደረሰባቸው ሰዎች ንብረታቸውን እያሸሹ ይገኛሉ " ተብሏል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 17:02


“የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ቀዳሚው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡

እኛ እንደ ኦነግ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስር መሆን አለባት ነው የምንለው! የፌደራሉ መንግስት መሬት የለውም፤ ከፈለገ ባህርዳርን ዋና ከተማው ማድረግ ይችላል፡፡”

አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተላሉ።

https://youtu.be/Y9o4949cJsQ?si=I-2AlP1dqLug6AYp

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 15:24


“እናት ፓርቲ ለሁለት ሊከፈል ነው” በሚል ሲናፈስ የቆየው መረጃ ሀሰት ነው ሲል ፓርቲው አስተባበለ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) እናት ፓርቲ ከሰሞኑ የላዕላይ ምክር ቤትና የስራ አስፈፃሚ አባላት ተፈርሞ ለምርጫ ቦርድ በገባ ደብዳቤ ላይ የፓርቲው የተወሰኑ የስራ አስፈፃሚ አባላት በስልጣን ፍላጎት እና በተለያዩ የአሰራር ጥሰቶች መክሰሳቸው ተቋሙን ለመከፋፈል የሚያደርስ አይደለም ሲል አስተባብሏል፡፡

ፓርቲው ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ እንደገለጸው በፓርቲው ላይ ክስ እና ውንጀላ ያቀረቡ አካላት ከሀገር ውጪ የሚገኙ እንዲሁም ከፓርቲው አባልነት የለቀቁ ከዚህ ቀደምም ከፓርቲው አካሄድ እና አስተሳሰብ ጋር የማይገናኝ ጥፋት ላይ ተገኝተው በማስጠንቀቂያ የታለፉ ናቸው ብሏል፡፡

በተጨማሪም ፓርቲው የውስጥ ችግሮች ሲፈጠሩ የቅሬታ አፈታት ሂደት በመተዳደሪያ ደንብ ላይ የተገለጸ ቢሆንም ቅሬታ አቅራቢዎቹ የፓርቲውን ደንብ ያልጠበቀ ክስ አቅርበዋል ሲል ኮንኗል፡፡

በመሆኑም ፓርቲው በጥቂት ሰዎች በተነሳ ቅሬታ አንድን ተቋም “ለሁለት ሊከፈል ነው” ከሚል አንጻር ሰው እንዲመለከተው ማድረግ አግባብነት የለውም ሲል አስታውቋል፡፡

የፓርቲውን መደበኛና ህጋዊ መዋቅር ወደ ጎን በመተው አዲስ አወቃቀር በመዘርጋት በፓርቲ ውስጥ “ጥያቄ የሚያነሱ” አባላትንና በማባረርና በማገድ አሁን ያለው አመራር የራሱን አዲስ አወቃቀር እየዘረጋ መሆኑንም የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ያሉበት ቅሬታ አቅራቢ ቡድን አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

እንዲሁም በፋይናንስ አሰራርና በሰራተኛ ቅጥር ዙሪያ ብልሹ አሰራር ሰፍኗል የሚለው ቅሬታ አቅራቢ ቡድን ምርጫ ቦርድ ጣልቃ ገብቶ የኦዲት ምርመራ እንዲያደርግ ጠይቆ ነበር፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 14:02


“የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ቀዳሚው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡

እኛ እንደ ኦነግ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስር መሆን አለባት ነው የምንለው! የፌደራሉ መንግስት መሬት የለውም፤ ከፈለገ ባህርዳርን ዋና ከተማው ማድረግ ይችላል፡፡”

አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተላሉ።

https://youtu.be/Y9o4949cJsQ?si=I-2AlP1dqLug6AYp

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 13:21


በጫሞ ሀይቅ ላይ በተከሰተው አደጋ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከአቡሎ አርፋጮ ወደ አርባምንጭ ከተማ 16 ሰዎችን እና ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ባሳለፍነው ሐሙስ 10 ሠዓት ከ20 ገደማ ጫሞ ሐይቅ ላይ ሰጥማ ነበር፡፡

የተለያዩ ስጋቶች በመኖራቸው እንዲሁም በጸጥታ ችግር ሳቢያ የትኛውም አይነት ጀልባ እንዳይጓዝ በተከለከለበት በጫሞ ሐይቅ ላይ 16 ሰዎችን እንዲሁም ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሰጥማ፤ ከተሳፈሩ 16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ በህይወት ተገኝተው የተቀሩትን 14 ሰዎች የመፈለጉ ሥራ ቀጥሎ መቆየቱን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

አሁን ላይ የሦስት ሰዎችን ሕይወት በፍለጋ ማዳን መቻሉን እና 13 ደግሞ ሕይወታቸው ማጣታቸውን እንዲሁም የሟቾች አስክሬን ከእልህ አስጨራሽ ፍለጋ በኋላ ሙሉ በሙሉ መገኘቱን እና ወደ ቤተሰቦቻቸው መላኩን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ኋላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ  መናገራቸው ተጠቁሟል፡፡

የአደጋው መንስኤ በተከለከለበት ቦታ መጓዛቸው ብቻ ሳይሆን ጀልባዋ ከመጫን አቅሟ በላይ በመጫኗ እና የጀልባዋ የመጫን አቅም 35 ኩንታል ቢሆንም በዕለቱ 70 ኩንታል ሙዝ እና 16 ሰዎችን መጫኗ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 12:14


የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ አለመሆኑን ማህበሩ አስታወቀ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን ማጠናቀቁን ገልጿል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ በስብሰባ ላይ የ2016 ዓ.ም የስራ አፈፃፀምና የኦዲት ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ ሰፊ ውይይት መደረጉን ማህበሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በውይይቱም መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ መከፈል፣ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ ችግሮት መነሳታቸው ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩ፣በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት እና የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች በተሳታፊዎች በአስተያየት እና በጥያቄ መልክ ተነስተዋል።

የትምህርት ሚንስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ  ጡሹነ ከመምህራን ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ እየታየ ያለው ጥያቄ የተጀመረው የትምህርት ሴክተር ሪፎርም ተጠናቆ ተግባራዊ ሲሆን ብዙ ጉዳዮች እንደሚፈቱ ገልፀዋል ።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 10:44


የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት በስልጠና ደረጃ 1 እና 2 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 እና ከዚያ በታች ፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 137 እና ከዚያ በታች እንደሆነ ተገልጻል፡፡

ለሴት ተማሪዎች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች ፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 134 እና ከዚያ በታች እንዲሁም ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት በስልጠና ደረጃ 1 እና 2 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 135 እና ከዚያ በታች ያለ ነጥብ ነው፡፡

ለሴቶች በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 124 እና ከዚያ በታች በተመሳሳይ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 07:35


የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ እራሱን ማግለሉን አስታወቀ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ድርጅት አሳታፊነትና ግልጸኝነት ስላላየሁበት ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳታፊነት እራሴን አግልያለሁ ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በሱማሌ ክልል የገዢው ፓርቲ መዋቅር ተሳታፊዎችን የሚለይበትና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድምጽ የሚያፍንበት ህገ-ወጥ አሰራር መዘርጋቱን የሚገልጸው ፓርቲው በዚህ ሂደት ውስጥ በምክክር መሳተፍ ረብ የለሽ ነው ሲልም ገልጾታል፡፡

ይህ አግላይ አሰራር አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተቋቋመበትን አላማ የሚጥስ ነው ሲልም በምክክር ኮሚሽኑ ሂደት ላይ ጥያቄ አንስቷል፡፡

ፓርቲው ከሱማሌ ክልል ውጪ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳሱ የታጠቁ ሃይሎች ባልተሳተፉበት ሁኔታ እንዴት የምክክር ሂደቱ ሊሳካ ይችላል ሲልም በጥያቄ መልስ አንስቷል፡፡

በቀጣይም ሁሉን አቀፍ የድርድር መድረክ እስካልተዘጋጀ ድረስ በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደማይችልም ጠቁሟል፡፡

ኦብነግ በ2010 ዓ.ም ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ለማድረግ ከፌዴራሉ መንግስት ጋር ስምምነት አድርጎ መግባቱ አይዘነጋም፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

20 Oct, 16:23


ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአምስተርዳም ማራቶን ድል  አድርገዋል

እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በሴቶች በተካሄደው ውድድር የአለምዘርፍ የኃላው የውድድሩን ክብረወሰን በማሻሻል በ2:16:52 አሸንፋለች::

ከሁለት አመት በፊት ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አልማዝ አያና የክብረወሰኑ ባለቤት እንደነበረች ይታወሳል::

የአለምዘርፍ ክብረወሰኑን በ28 ሰከንድ ነው ያሻሻለችው::ኢትዮጵያዊቷ ሄቨን ሀይሉ በ2:19:29 ሁለተኛ ጨርሳለች::

በወንዶች ውድድር ፀጋዬ ጌታቸው በ2:05:38 አንደኛ ጨርሷል:: ይህንንም በማሳካት ከሁለት አመት በፊት ያስመዘገውን ድል መድገም ችሏል:: 

የሀገሩ ልጅ ቦኪ አሰፋ በ2:05:40 ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል::

በብሩክ ገነነ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Oct, 16:24


ከኦሮሞ ጥያቄ እና ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ቆይታ አድርጋለች። ሙሉ ቃለምልልሱን በአዲስ ማለዳ ዩቲዩብ በቅርብ ቀን ይጠብቁን።

https://youtu.be/lDZ8nEA4Z1A?si=7rm1PUnoebYw9OQY

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Oct, 14:30


በአማራ ክልል በዳኞች ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘፈቀደ እስር በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል›› የክልሉ ዳኞች ማህበር

ዓርብ ጥቅምት 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የዳኞች አስር፣ ማዋከብና መሰል ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ካለፈው አንድ አመት ወዲህ ተባብሶ ቀጥሏል ያለው የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ድርጊቱን ባወጣው መግለጫ አውግዟል፡፡

የዳኞችን ነጻነት መጠበቅ ህገ-መንግስታዊ መብት ሆኖ የተደነገገ ቢሆንም ይህንን አክብሮ ከመንቀሳቀስ አኳያ መንግስት ዳተኝነት እየታየበት ነው ሲሉ የከሰሰው ማህበሩ ጉዳዩ አሳሳቢ ሆኗል ሲል አስታውቋል፡፡

ማንኛውም ጥፋት ያለበት ግለሰብ በህግ አግባብ ተይዞ የማጣራት ስራዎች ይከናወኑበታል የሚለውን መሰረታዊ የህግ ሂደት በጣሰ መልኩም ዳኞችን በአደባባይ ማፈን አስሮም ያለፍርድ ማቆየት በክልሉ ተባብሶ የቀጠለ ጉዳይ ነው ሲል ወቀሳ አቅርቧል፡፡

አሁን ላይም 8 ያህል ዳኞች ያለምንም የፍርድ ሂደት ታስረው ይገኛሉ ያለው ማህበሩ ይህ አካሄድ ፍትህን ለማረጋገጥ በሚሰራው ስራ ላይ ጥላ የሚያጠላ ስለመሆኑም ጠቁሟል፡፡

የሰው ልጅ ነጻነት እንዲከበር ፣ዘላቂ ሰላምና የኢኮኖሚ እድገት እንዲመጣ የዳኝነት ነጻነትን መጠበቅ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን በማንሳትም የታሰሩ አባላቶቼ በአፋጣኝ እንዲፈቱ ሲል አሳስቧል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Oct, 14:03


https://youtu.be/XPy6i139erg

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Oct, 14:02


ኢትዮጵያ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ በድህነት ውስጥ እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመላከተ
👉🏿ጥናቱ በኢትዮጵያ ከ86 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው ብሏል

ዓርብ ጥቅምት 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ባወጣው ሪፖርት በዓለም ከ1.1 ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በአስከፊ ድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት ሀገራት በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላቸው ሀገራት ሲል ኦክስፎርድ የድህነት እና የሰብአዊ ልማት ኢኒሼቲቭ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

ከተጠቀሱት አምስት ሀገራት ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ድሆች መካከል ግማሽ ያህሉን እንደሚሸፍኑ የአለም ሁለገብ የድህነት መረጃ ሪፖርት አመላክቷል።

ይህን ተከትሎ ከአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ 86 ሚሊዮን በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን በመያዝ ቀዳሚ ስትሆን ፣ናይጄሪያ 74 ሚሊዮን እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 66 ሚሊዮን ዜጎችን በመያዝ ይከተላሉ፡፡

በመሆኑም የድህነት መጠን በጦርነት ውስጥ ባሉ ሀገሮች በሦስት እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑን እና ሪፖርቱ የመኖሪያ ቤት እጥረት፣ የአካባቢ ጽዳት፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦት፣ የምግብ ማገዶ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የትምህርት ቤት ክትትልን የመሳሰሉትን መስፈርቶች እንደ ድህነት አመልካችነት መጠቀሙን አስታውቋል፡፡

በጥናቱ መሰረት 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ ዘርፈ ብዙ ድህነት ውስጥ እየኖረ ሲሆን፣ ከነዚህም 455 ሚሊዮን የሚሆኑት በግጭት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው ተብሏል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Oct, 09:55


https://youtu.be/3ApxRnCCBjk

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Oct, 08:12


ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ዓርብ ጥቅምት 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

በዚህም የፍህ ሚኒስትር የነበሩትን ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስን የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር አድረገው ሾመዋል፡፡

በተጨማሪም ቀደም ሲል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩትን ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳን የቱርዝም ሚንስቴር ሚንስትር አድርገው የሾሙ ሲሆን ፤ ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴን ደግሞ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር በማድረግ ሹመት ሰጥተዋል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Oct, 07:45


’’ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ሀገር ውስጥ የሚቆዩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ቅጣት እያስተላለፍኩ ነው’’ የኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ዓርብ ጥቅምት 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው አስቀድሞ ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ የተራዘመ ቆይታን በሚያደርጉ የውጭ ሐገር ዜጎች ላይ፤ ቅጣት እየጣለ እንደሚገኝ ማስታወቁ ተገልጻል፡፡

የውጭ ሀገር ዜጎቹ ከመጡበት ዓላማ ውጪ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ መኖራቸውን እና አስቀድሞ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ እንዲያከናውኑት ከተፈቀደላቸው ተግባር ውጪ ሲንቀሳቀሱ በተያዙትላይም እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

ይህ ተግባር ሲያደርጉ በተገኙ ዜጎች ላይ ከገንዘብ መቀጮ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ዳግም እንዳይመጡ ውሳኔ እስከማስተላለፍ የሚደርስ ቅጣት እየተደረገ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም ተቋሙ የሚሰጣቸውን የቪዛ ዓይነቶች የደህንነት መቆጣጠሪያ እንዲካተትባቸው ያደረገው መሰል ተግባራትን ለመከላከል እንዲያስችለው መሆኑ ተገልጻል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

17 Oct, 13:42


ከሰሞኑ የተከሰተው የጉንፋን ህመም የክረምት ወራት ማብቃቱን ተከትሎ የሚጠበቅ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሀሙስ ጥቅምት 07 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት “ወቅታዊ ጉንፋን እና ጉንፋን መሰል የመተፈንሻ አካላት ህመም” በተመለከተ በጋራ ባወጡት መግለጫ “የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው” ብለዋል፡፡

ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው ያለው መግለጫው ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ ብሏል።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39335

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

17 Oct, 10:17


ቀደም ባለው ድህረ ወሊድ ጊዜ: ምን ማወቅ አለብዎት

ድህረ ወሊድ

አንዲት እናት ልጅ ከወለደች በኋላ ያሉት ቀናት እና ሳምንታት የድህረ ወሊድ ጊዜ በመባል ይታወቃል።ይህም ልጅ ከተወለደ በኋላ ያለው ጊዜ በተለይም የመጀመሪያዎቹ ስድስት ሳምንታት ቀደምት የድህረ ወሊድ ጊዜ በመባል ይታወቃል። ቀደምት የድህረ ወሊድ ጊዜ በሴቶች ህይወት ውስጥ ከወሊድ በኋላ በአካል፣ በስሜታዊ እና በስነ ልቦና ለውጦች የሚታወቅ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።እነዚህን ለውጦች መረዳት እና እነሱን እንዴት ማስተዳደር እንደሚቻል ማወቅ ለአራስ እናቶች ደህንነት እና ምቾት ወሳኝ ናቸው። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ፣ ስለ መጀመሪያው የድህረ ወሊድ ጊዜ ቁልፍ ገጽታዎች ማለትም የአካል ማገገምን፣ ስሜታዊ ደህንነትን፣ አዲስ የተወለደ ሕፃን እንክብካቤን እና የድጋፍ ሥርዓቶችን የምናይ ይሆናል።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39330

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

17 Oct, 09:51


በአማራ ክልል የተፈጠረው ቀውስ ይህ ነው የሚባል አንድም የሰላም መፍትሄ ሳይበጅለት ሁለተኛ አመቱን ሊይዝ ወራቶች ቀርተውታል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ሁለቱ ተፋላሚ አካላት የራሳቸውን ፖለቲካዊ ትርፍ ከማስላት በዘለለ ተጨባጭ መፍትሄ እንዲመጣ እየሰሩ አይደለም የሚለው ድምጽ ጎላ ብሎ ይደመጣል፡፡ ለመሆኑ በመከራ ውስጥ ያለው የክልሉ ህዝብ ቀጣይ እጣፋንታው ምን ይሆን? የሚሉና ተያያዥ ጉዳዮችን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ልንመለከተው ወደናል፤ ሙሉ ትንታኔውን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/o1EMy7GcfB8

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

17 Oct, 03:43


መብላት ከብዶናል፣ ልጆቻችንን ምን እናድርጋቸው፤ ኢትዮጵያ የምትባለው ሃገርስ በዚህ ሁኔታ ወዴት እየሄደች ነው? በዝቅተኛም ሆነ በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙት ህዝቦቿስ በዚህ የኑሮ ውድነት ቀጣይ እጣፈንታቸው ምን ይሆን የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡

ሰሞነኛው የዋጋ ንረት፣ የመንግስታዊ ተቋማት የአገልግሎት ዋጋ ጭማሪ እና የነዳጅ በዚህ ልክ መጨመር ከታሪካዊ የኢትዮጵያ ክንውኖች ጋር አጣምረን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ልንመለከተው ወደናል፤ ሙሉ ትንታኔውን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/kdp5x49xwj4

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Oct, 16:06


የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻ ከዛሬ ጀምሮ በቴሌብር መተግበሪያ መግዛት እንደሚቻል ተገለጸ

ረቡዕ ጥቅምት 06 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻ ከዛሬ ጀምሮ በቴሌብር መተግበሪያ አማካኝነት መግዛት እንደሚቻል የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻ የድርሻ ሽያጩን በይፋ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያውያን ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን በመግዛት የኢትዮ ቴሌኮም ባለድርሻ እንዲሆኑ ጋብዘዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻ ከዛሬ ጀምሮ በቴሌብር መተግበሪያ መግዛት እንደሚቻል የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ አስታውቀዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም የሀብት መጠን 100 ቢሊየን ብር መሆኑን አስታውቀዋል።

ከዚህ ውስጥ ለሽያጭ የቀረበው 10 በመቶ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፣ ይህ በብር ሲተመንም 100 ሚሊየን ብር ነው ብለዋል።

ለሽያጭ የቀረበው የአንድ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር መሆኑን ያስታወቁት ስራ አስፈጻሚዋ፣ ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው ሼር 33 ሼር መሆኑን እና በብር ሲተመን 9 ሺህ 900 ብር እንደሆነም ገልጸዋል።

ከፍተኛ መግዛት የሚቻለው ሼር 3 ሺህ 333 ነው ያሉት ስራ አስፈጻሚዋ፣ በብር ሲተመን 999 ሺህ 900 ብር እንደሆነም አስታውቀዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች መግዛት እንደሚችሉ ያስታወቁት ወ/ት ፍሬህይወት፣ ተቋማት አክሲዮንን መግዛት አይችሉም ብለዋል።

የአክሲዮን ሽያጩ ዛሬ ጥቅምት 06 ቀን 2017 እንደሚጀምር እና ታህሳስ 25፣ 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አስታውቀዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Oct, 14:03


መብላት ከብዶናል፣ ልጆቻችንን ምን እናድርጋቸው፤ ኢትዮጵያ የምትባለው ሃገርስ በዚህ ሁኔታ ወዴት እየሄደች ነው? በዝቅተኛም ሆነ በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙት ህዝቦቿስ በዚህ የኑሮ ውድነት ቀጣይ እጣፈንታቸው ምን ይሆን የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡

ሰሞነኛው የዋጋ ንረት፣ የመንግስታዊ ተቋማት የአገልግሎት ዋጋ ጭማሪ እና የነዳጅ በዚህ ልክ መጨመር ከታሪካዊ የኢትዮጵያ ክንውኖች ጋር አጣምረን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ልንመለከተው ወደናል፤ ሙሉ ትንታኔውን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡
https://youtu.be/kdp5x49xwj4

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Oct, 12:39


ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው አውሮፕላን ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በውስጡ ጢስ ታይቶ እንደነበር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳወቀ

ረቡዕ ጥቅምት 06 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጢስ ታይቱ እንደነበር የኢትዩጲያ አየር መንገድ አሳውቋል፡፡

አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም በማረፍ መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡

አየር መንገዱ ጭሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ÷ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱ ይታወሳል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Oct, 12:27


የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አድርጎት የነበረውን ስምምነት በሚመለከት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

ረቡዕ ጥቅምት 06 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2018 ከፌዴራል መንግስቱ ጋር የተፈራረመውን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በሚመለከት ውይይት ለማድረግ ልዩ ስብሰባ ጠርቷል ፡፡

ነጻ አውጪ ግንባሩ የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ከፈረንጆቹ ጥቅምት 25-27 እንደሚያከናውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በስበሰባው በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለመወያየትና ግንባሩ ከዚሁ ጋር በተያያዘ መውሰድ ስላለበት አቋም በዝርዝር ለመወያየት ማቀዱም ታውቋል፡፡

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ከቅርብ ጊዚያት ወዲህም ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ያሰርኩት ስምምነት በተገቢው መንገድ እየተተገበረ አይደለም ሲል ተደጋጋሚ ወቀሳዎችን ሲያቀርብ ይደመጣል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Oct, 12:05


በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም እጦት ምክንያት የወረርሽኝ በሽታዎች እየተስፋፉ ነው ተባለ

ረቡዕ ጥቅምት 06 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት “ቀደም ሲል በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የጤና ችግሮች በወረርሽኝ መልክ እየመጡ ነው” ተባለ

ይህ የተገለጸው በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ባዘጋጀው ውይይት ወቅት ነው።

መንገዶች ይዘጋሉ፣ ወገኖች ያለ ስጋት ወደ ጤና ተቋማት ሄደው መታከም አይችሉም ተብሏል፤ የታጠቁ ወገኖችን የጤና አገልግሎቱን የሚጠብቁ ሕጎችን እንዲያከብሩ ተጠይቋል፡፡

ታመው መታከም የማይችሉ ወገኖች በርካቶች ናቸው፤ ስለ ምን ካሉ ሕሙማን በነጻነት ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ አይችሉም፣ የጤና ባለሙያዎችም በነጻነት ሕክምና አይሰጡምና ነው ማለታቸውም ተካቷል።

አሁን ባለው ችግር የጤና አገልግሎት ለመስጠት አስቸጋሪ መኾኑንም ተመላክቷል፡፡